ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በለውጡ ዓመታት የመንግስት አገልግሎት ተደራሽነትን ያረጋገጡ ተግባራት ተከናውነዋል
May 23, 2026 123
አገና፤ ግንቦት 15/2018 (ኢዜአ)፦ በለውጡ ዓመታት የህዝብ ተጠቃሚነት እና የመንግስት አገልግሎት ተደራሽነትን ያረጋገጡ የአሰራር ስርዓቶች በመዘርጋታቸው ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸውን የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ሃይሌ (ዶ/ር) ገለጹ። በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ አገና ከተማ፣ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተመዘገቡ የልማት ስኬቶችን የሚደግፍ ሰልፍ ተካሂዷል። በወቅቱ ኮሚሽነር መኩሪያ ሃይሌ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት ሳይፈቱ የቆዩ የልማትና የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቅረፍ የተደረጉ ጥረቶች ተጨባጭ ውጤት አስመዝግበዋል። በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሰረታዊ ማሻሻያ በመጣቱ በጤና፣ በትምህርት እንዲሁም በከተማና ገጠር ልማት ሁለተናዊ ብልፅግናን የሚያረጋግጡ ውጤቶች ታይተዋል ብለዋል። በተለይም በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን በተቀናጀና በዘላቂነት ለመፍታት የተከናወኑ ተግባራትን ጠቅሰዋል። ለአብነትም የ"መሶብ" የአንድ ማዕከል አገልግሎት በተለያዩ ከተሞች ወደ ስራ የገባው ይህ አሰራር፣ በርካታ ተቋማትን በአንድ ስፍራ በማቀፍ የተገልጋዩን ጊዜና ጉልበት የቆጠበ ከመሆኑም በላይ ቀደም ሲል ያጋጥም የነበረውን እንግልት በከፍተኛ ደረጃ አስቀርቷል ብለዋል። ኮሚሽነሩ አክለውም፣ መንግስት የህዳሴ ግድብን ባሳካው ልክ የባህር በር ለማግኘት የሚያስችሉ የዲፕሎማቲክ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህንን ታላቅ እቅድ በላቀ ተነሳሽነት ለማሳካት ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ርብርብ እንዲያደርግ አሳስበዋል። በብልፅግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይግለጡ አብዛ በበኩላቸው፤ በለውጡ ዓመታት በሁሉም ዘርፎች ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። የመደመር መንግስት ለውጤት እንዲበቃ በማድረግ በኩል ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን በወቅቱ ጀምሮ በማጠናቀቅ ረገድ ተምሳሌት መሆን ችሏል ነው ያሉት። በክልሉ በገጠርና በከተማ የተከናወነው የኮሪደር ልማት ስኬታማ በመሆኑ የህዝቡን የአኗኗር ዘይቤ በመቀየር ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን ማጎልበት እንደተቻለም አስረድተዋል። የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በበኩላቸው፤ በበጀት ዓመቱ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውና የህዝብን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ለውጤት መብቃታቸውን ገልጸዋል። ይህም አገሪቱ ከተረጂነት ለመውጣት ለምታደርገው ጥረት ጠንካራ መሰረት የሚጥል መሆኑን ጠቁመዋል። የሰልፉ ተሳታፊ የነበሩት አቶ መክብብ ገብረፃዲቅ በሰጡት አስተያየት፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በውጤታማነት የመለሱ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል። ህብረተሰቡ በአንድነትና በመተባበር መለወጥ እንደሚቻል ያሳየ በመሆኑ ልማቱ እንዲቀጥል የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ
May 23, 2026 97
ወላይታ ሶዶ ፤ ግንቦት 15/2018 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ተናገሩ። በወላይታ ዞን የበሌ አዋሳ አጠቃላይ ሆስፒታል የደረጃ ማሻሻያ ዕውቅና እና የማህበረሰብ መድኃኒት ቤት ምረቃ መርሃ ግብር በበሌ አዋሳ ከተማ ተካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት አቶ ገብረመስቀል ጫላ እንደገለጹት፤ የክልሉ መንግስት የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን በማስፋት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ይገኛል። በየመዋቅሩ የጤና ተቋማትን በመገንባትና ባለሙያዎችን በመመደብ፣ ዜጎች የጤና አገልግሎትና መድኃኒት በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። የበሌ አዋሳ ከተማ አጠቃላይ ሆስፒታል ደረጃ ማሻሻልና የማህበረሰብ መድኃኒት ቤት ምረቃ ለዚህ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰው፣ እነዚህን አገልግሎቶች የማስፋት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አክለዋል። አካባቢው ለወባ በሽታ ተጋላጭ መሆኑን ጠቅሰው፣ የሆስፒታሉ ደረጃ መሻሻልና የማህበረሰብ መድኃኒት ቤቱ መመረቅ የህዝቡን የዘመናት ችግር በዘላቂነት እንደሚቀርፍም ተናግረዋል። የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ በበኩላቸው፤ የክልሉ መንግስት የጤና ተቋማትን ደረጃ በማሻሻልና የአገልግሎት አሰጣጥን የማሻሻል ስራዎችን ተግባራዊ በማድረጉ ውጤት እየተገኘ መሆኑን ገልጸዋል። የበሌ አዋሳ ሆስፒታል መደበኛ ህክምና፣ ድንገተኛ ህክምና እና የመድኃኒት አቅርቦትን ጨምሮ ሌሎችንም የአገልግሎት ዘርፎች ያሟላ ሲሆን፣ ለ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች አገልግሎት መስጠት ይችላል ብለዋል። ከለውጡ ወዲህ በክልሉ ከ70 በላይ የማህበረሰብ መድኃኒት ቤቶች ተገንብተው አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ሲሆን፣ ይህም ዜጎች መድኃኒትን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ አስችሏል ነው ያሉት። የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሳሙኤል ተሰማ (ረዳት ፕሮፌሰር) በበኩላቸው፣ አስተዳደሩ በሁሉም መዋቅሮች የጤና አገልግሎትን ለማሻሻል ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑንና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የበሌ አዋሳ ከተማ ከንቲባ አባይነህ አጫ (ዶ/ር) በከተማው የጤና ተቋማት አቅም ማጎልበትን ጨምሮ በ75 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት የተለያዩ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል። የማህበረሰብ መድኃኒት ቤትና የሆስፒታሉ ደረጃ ማሻሻል ከእነዚህ መካከል አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፣ ልማቱን ለማስቀጠል ከከተማው ነዋሪዎች ጋር የተጀመረው ቅንጅት እንደሚቀጥል ተናግረዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች የሆኑት ወይዘሮ ርብቃ ጎዳና እና አቶ አስፋው አስራት በሰጡት አስተያየት፤ ከዚህ ቀደም የጤና አገልግሎት ለማግኘት ወደ ወላይታ ሶዶ እና ሌሎች ቦታዎች በመጓዝ ለከፍተኛ ወጪና እንግልት ይዳረጉ እንደነበር አስታውሰዋል። የአሁኑ የሆስፒታሉ ደረጃ መሻሻል እንግልታቸውን እንዳስቀረላቸውና የማህበረሰብ መድኃኒት ቤቱ ደግሞ ደህንነቱ የተረጋገጠ መድኃኒት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ የተሻለ አማራጭ በመፍጠሩ መንግስትን አመስግነዋል። በዚሁ የምረቃ መርሃ ግብር ላይ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር የመንግስት ስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ በሽታዎችን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች ውጤት እስያገኘ ነው
May 23, 2026 179
ጂንካ፤ ግንቦት 15/2018(ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እ.ኤ.አ በ2030 ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ በሽታዎችን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለው የተቀናጀ ጥረት አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። የክልሉ ጤና ቢሮ ከካርተር ሴንተር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ በሽታዎች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በጂንካ ከተማ አካሂዷል። የቢሮው ኃላፊ ተወካይ አቶ ታምራት አሰፋ በምክክር መድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ በክልሉ ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ በሽታዎችን ለመቆጣጠር እና ለማጥፋት ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል። የሕብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ እና መከላከያ መድኃኒቶችን ተደራሽ በማድረግ የበሽታዎቹን ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ መቻሉን ነው የገለጹት። በዚህም ትኩረት የሚሹ የሀሩራማ በሽታዎች ተብለው ከተለዩት መካከል ትራኮማ፣ ወባ፣ ተላላፊ የዝሆኔ በሽታ እና የጊኒ ዎርም በዋናነት ተጠቃሽ መሆናቸውን ጠቁመው፤ የጊኒ ዎርም በሽታን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር የተቻለ ሲሆን፥ ባለፉት 15 ዓመታት በክልሉ ምንም ዓይነት የጊኒ ዎርም በሽታ አለመከሰቱን አረጋግጠዋል። የዛሬው የምክክር መድረክ በቀጣይ በክልሉ የሀሩራማ በሽታዎችን ጨርሶ ለማጥፋት ለሚደረገው ርብርብ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብለዋል። የካርተር ሴንተር ኢትዮጵያ ምክትል ተጠሪ አቶ የማነ ቀጀላ በበኩላቸው፤ በጤና ሚኒስቴር አማካኝነት በሀገሪቱ የሀሩራማ በሽታዎችን ለመቆጣጠር እና ለማጥፋት የተያዘውን ብሔራዊ ግብ ለማሳካት ድርጅታቸው የበኩሉን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ድርጅቱ በተለይም ኦንኮሰርኪያስስ፣ ተላላፊ የዝሆኔ በሽታ እና የጊኒ ዎርም በሽታዎችን ለመከላከል የሚያስችል የሕክምና እና የመድኃኒት ድጋፍ በሀገሪቱ በሚገኙ ሰባት ክልሎች ተደራሽ እያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል። በካርተር ሴንተር የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ዳንኤል ታምራት በበኩላቸው፥ በክልሉ የኦንኮሰርኪያስስ እና የዝሆኔ በሽታን ለመከላከል መንስኤዎችን ከመለየት ጀምሮ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ረገድ ድርጅቱ እገዛ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በክልሉ ከ974 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች የዝሆኔ እና የኦንኮሰርኪያስስ በሽታዎችን ጨምሮ ሌሎች 11 የአንጀት ጥገኛ ትላትሎችን መከላከል የሚያስችሉ መድኃኒቶች ተሰጥተዋል ብለዋል። ለዚህም ተግባር የሚውል ከ5 ሚሊዮን በላይ የመድኃኒት እንክብል ለማኅበረሰቡ መሰራጨቱን አስተባባሪው ጠቁመዋል።
ብልፅግና ፓርቲ ዜጎችን ከድህነት በማውጣት የሀገርን እድገትና ማንሰራራት እውን የማድረግ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል - ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)
May 23, 2026 160
ጅማ፤ ግንቦት 15/2018 (ኢዜአ)፦ ብልፅግና ፓርቲ ዜጎችን ከድህነት በማውጣት የሀገርን እድገትና ማንሰራራት እውን ለማድረግ የጀመራቸውን ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ገለጹ። ብልፅግና ፓርቲ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) በሚወዳደሩበት ኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ሸቤ ሶምቦ ወረዳ የምርጫ ቅስቀሳ አካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)፤ በለውጡ ዓመታት ብልፅግና ፓርቲ የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ለማድረግና ሀገርን ከድህነት ለማውጣት ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን ማከናወኑን ገልጸዋል። በግብርና ልማት በተለይም በመስኖ ስንዴ ልማት አስደናቂ ውጤት መገኘቱን አንስተው በሌሎችም መስኮች ተጨባጭ ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል። በመሆኑም ብልፅግና ፓርቲ ዜጎችን ከድህነት በማውጣት የሀገርን እድገትና ማንሰራራት እውን ለማድረግ የጀመራቸውን ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል። የሸቤ ሶምቦ ወረዳ አስተዳዳሪ መሀመድሳኒ አባኦሊ፤ ብልፅግና ፓርቲ በለውጡ ዓመታት ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን በማከናወን የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ማድረግ ችሏል ብለዋል። በተለይም በግብርና ዘርፍ ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጅነት ለመውጣት የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል። የሸቤ ሶምቦ ወረዳ በሩዝ ምርት የሚታወቅ መሆኑን አስታውሰው፤ ባለፉት ጥቂት አመታት ምርቱ በእጥፍ እንዲያድግ የተደረገበትን ስኬት ለአብነት አንስተዋል።
መንግስት በነዳጅ አቅርቦት ላይ የወሰደው እርምጃ በከተማዋ የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭትን በማሳለጥ በኩል ከፍተኛ ለውጥ አስገኝቷል
May 23, 2026 149
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 15/2018(ኢዜአ)፦ መንግስት በነዳጅ አቅርቦት ላይ የወሰደው እርምጃ በከተማዋ የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭትን በማሳለጥ በኩል ከፍተኛ ለውጥ ማስገኘቱን ኢዜአ ያነጋገራቸው አሽከርካሪዎች እና የነዳጅ ማደያዎች ገለጹ፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ ተከስቶ የነበረውን ችግር ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ በነዳጅ ምርት አቅርቦት ላይ የተፈጠረው ክፍተት፣ በሀገር ውስጥም የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል አስከትሎ የነበረ ቢሆንም፤ መንግሥት አቅርቦቱ ከጦርነቱ በፊት ወደነበረበት ደረጃ እንዲመለስ አድርጓል። መንግሥት በነዳጅ አቅርቦት ላይ የወሰደው እርምጃ የነበረውን ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ተቋቁሞ ለማለፍ ያስቻለ ሲሆን፣ አሁን ላይ በተለያዩ ከተሞች የተረጋጋ፣ ቀልጣፋ የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት እንዲኖር አስችሏል። የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በወቅታዊ የዓለም የነዳጅ ሁኔታን በማስመልከት በሰጡት ማብራሪያ፣ የናፍጣ ነዳጅ አቅርቦት ከመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በፊት ወደነበረበት እንዲመለስ መደረጉን መጥቀሳቸው ይታወቃል፡፡ ኢዜአ በመዲናዋ ያነጋገራቸው አሽከርካሪዎችና የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች፤ መንግሥት በነዳጅ አቅርቦት ላይ የወሰደውን የማሻሻያ እርምጃ ተከትሎ በአቅርቦቱና በስርጭቱ ላይ ከፍተኛ አዎንታዊ ለውጥ መታየቱን ገልጸዋል። አስተያየት ከሰጡ አሽከርካሪዎች መካከል አባይነህ ይሁኔ፤ ቀደም ሲል ከዓለም አቀፉ የነዳጅ እጥረት ጋር ተያይዞ በነበረው መስተጓጎል በእለት ተእለት እንቅስቃሴያቸው ላይ ከፍተኛ ችግር ገጥሟቸው እንደነበር አስታውሰዋል። አሁን ላይ ግን የነበረው ችግር ሙሉ በሙሉ ተፈትቶ ሁኔታው ወደ ቀድሞው በመመለሱ፣ በሁሉም ማደያዎች የሚፈልጉትን ያህል ነዳጅ ያለምንም እንግልት እያገኙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ሌላኛው አሽከርካሪ ከድር ሁሴን በበኩላቸው፤ ቀደም ሲል ነዳጅ ለማግኘት እስከ አንድ ሳምንት ይወስድባቸው የነበረው አስቸጋሪ ሁኔታ በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ መፈታቱንና ያለምንም እንግልት ነዳጅ እያገኙ ማኅበረሰቡን በሚገባ እያገለገሉ መሆናቸውን አስረድተዋል። በተመሳሳይ አሽከርካሪ ተፈሪ ዓለሙ እና ረታ ጂቢቲ እንደገለጹት፤ ቀደም ሲል ተከስቶ የነበረው የነዳጅ እጥረትና የረጅም ሰዓት ወረፋ በመንግሥት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት በመቀረፉ፣ በአሁኑ ወቅት ያለምንም መስተጓጎል እየተስተናገዱ ይገኛሉ። በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ላይ የነበረው ችግር በመወገዱ በአሁኑ ወቅት የተረጋጋ ሁኔታ መፈጠሩንና መደበኛ ሥራቸውን በተሻለና ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መልኩ እያከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል። የነዳጅ ማደያ ሱፐርቫይዘሮች በበኩላቸው ቀደም ሲል በዓለም አቀፍ የነዳጅ ቀውስ ምክንያት ይፈጠር የነበረው የአቅርቦት ችግር በመቀረፉ ደንበኞቻቸውን ያለምንም እንግልት እያስተናገዱ መሆኑን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት በአቅርቦትና በስርጭት ላይ ችግር አለመኖሩን ጠቁመው ለማኅበረሰቡ ጥሩ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ጠቁመዋል። በቡልጋሪያ አካባቢ የቶታል ማደያ ሱፐርቫይዘር ሰለሞን ገብረሕይወት እና በአሮጌው ቄራ አካባቢ ቶታል ማደያ ሱፐርቫይዘር ይርጋ ኪዳነ ማርያም ቀደም ሲል በነበረው እጥረት ምክንያት ተሽከርካሪዎች ነዳጅ ለማግኘት እስከ አምስት ቀናት የሚደርስ ረጅም ሰልፍ ይጠብቁ እንደነበር አስታውሰው፤ አሁን ላይ ችግሩ ሙሉ በሙሉ መቀረፉን አረጋግጠዋል። በተመሳሳይ የሜክሲኮ አካባቢ የካምፖ አስመራ ነዳጅ ማደያ ሱፐርቫይዘር ጥበቡ በቀለ በበኩላቸው፤ መንግሥት ዓለም አቀፉን የነዳጅ አቅርቦት ቀውስ ለማስተካከል የወሰደውን ቁርጠኛ እርምጃና የመጣውን ፈጣን አዎንታዊ ለውጥ አድንቀዋል። በአሁኑ ወቅት ነዳጅ ለማደያቸው በአግባቡና በወቅቱ እየቀረበ መሆኑን ገልጸው እያገኙት ያለውን ምርትም ለተጠቃሚ አሽከርካሪዎች እያቀረቡ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።
ፖለቲካ

በምርጫው በንቃት በመሳተፍ ተጠቃሚነታችንን ይበልጥ የሚያሳድግ ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል
May 23, 2026 153
ወልቂጤ ፤ ግንቦት 15/2018 (ኢዜአ)፦ በምርጫው በንቃት በመሳተፍ ተጠቃሚነታችንን ይበልጥ የሚያሳድግ ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ሲሉ በጉራጌ ዞን አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ አካል ጉዳተኞች ተናገሩ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት፣ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መጪው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳ። በዘንድሮው የመራጮች ምዝገባ ከ50 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የመራጭነት ካርድ ወስደው ቀኑን እየተጠባበቁ ሲሆን፣ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ፖሊሲና ፕሮግራሞቻቸውን በምርጫ ቅስቀሳና በሚዲያ አማራጮች እያስተዋወቁ ነው። ኢዜአ በጉራጌ ዞን ያነጋገራቸው አካል ጉዳተኞች እንደገለጹት፤ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለአካል ጉዳተኞች የተሰጠውን ትኩረትና ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ተጠቃሚነታቸውን የሚያሳድግ የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል። በዞኑ የአካል ጉዳተኞች ማህበራት ህብረት ፕሬዝዳንት አቶ ዓብይ ጀማል በሰጡት አስተያየት፤ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለአካል ጉዳተኞች ልዩ ትኩረት በመሰጠቱ ከምዝገባ ሒደት ጀምሮ በተለያዩ ተግባራት ላይ በንቃት እየተሳተፉ መሆኑን ገልጸዋል። ባለፉት የምርጫ ዓመታት የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚያደርጓቸው ክርክሮች ላይ ለአካል ጉዳተኞች የሚሰጡት ትኩረት አናሳ ነበር፤ በዚህ ዙር ግን ምርጫውን አካታች ለማድረግ የሚደረጉ አበረታች ጥረቶችን ታዝበናል ብለዋል። በዞኑ በምርጫው ቅድመ ዝግጅት ወቅት የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎ የተሻለ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ዓብይ፤ ከ23 ሺህ በላይ አካል ጉዳተኞች ካርድ መውሰዳቸውንና 54 ታዛቢዎች ስልጠና መውሰዳቸውን ጠቁመዋል። በመሆኑም የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በአግባቡ በመጠቀም ምርጫው ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑን አረጋግጠዋል። ሌላው አስተያየት ሰጪ ወጣት ነፃነት ፍቅሬ በበኩሉ፤ የምርጫ ጣቢያዎች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ አድርገው መደራጀታቸው ተሳትፏቸውን በእጅጉ እንዳሳደገው ገልጿል። የተፈጠረውን ምቹ መደላድል በመጠቀም በምርጫው ዕለት ድምጻቸውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን አክሏል። የፖለቲካ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙኃን በሚያደርጉት የ"ይምረጡኝ" ክርክር ቅስቀሳ እና የማኒፌስቶ ማስተዋወቅ ላይ አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ ዕቅዶች ሲንጸባረቁ መመልከታቸው እንዳስደሰታቸው የገለጹት ደግሞ አቶ ፈቀደ ባደታ ናቸው። ምርጫው የሀገር ሰላምና የዜጎችን ደህንነት የሚያረጋግጥ እንዲሆን እንደሚመኙ ጠቅሰው፤ ለአካል ጉዳተኞች መብትና ተጠቃሚነት የሚቆረቆር ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። በዘንድሮው የምርጫ ሂደት ለአካል ጉዳተኞች የተሰጠው ትኩረት እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣት ፈይሰል ሙደርም፤ የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅና የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት የሚሰራን ፓርቲ ለመምረጥ ዝጁ መሆኑን አረጋግጧል።
ለምርጫው በስኬት መጠናቀቅ የበኩላችንን እየተወጣን ነው - ተፎካካሪ ፓርቲዎች
May 23, 2026 177
ባህር ዳር፤ ግንቦት 15/2018(ኢዜአ)፦ ሰባተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ በስኬት መጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ እንደሚገኙ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ገለጹ። በምርጫው ለመወዳደር የተመዘገቡ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ምርጫው ለሀገር አንድነትና ለሕግ የበላይነት መረጋገጥ ያለውን ፋይዳ በመገንዘብ ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ እስካሁን ተሳትፏቸውን እያጠናከሩ መጥተዋል። መራጩ ሕዝብ በድምፁ የሚፈልገውን ፓርቲ ወደ ሥልጣን ለማምጣት የወሰደውን የምርጫ ካርድ በአግባቡ ይዞ፣ በምርጫው ዕለት በአግባቡ እንዲጠቀምበትም ፓርቲዎቹ መልእክት አስተላልፈዋል። የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴሃን) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ገብረመስቀል አደመ እንደገለጹት፤ ፓርቲያቸው የምርጫው ሂደት ፍትሃዊና አሳታፊ እንዲሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል። ፓርቲያቸው እስካሁን ለአባላቱና ለደጋፊዎቹ የምርጫ ሕጉንና የፓርቲውን ማኒፌስቶ መሠረት በማድረግ ግንዛቤ መፍጠሩን አውስተዋል። የሰለጠነ የፖለቲካ ትግል መገለጫው የሚፈልጉትን ፓርቲ በካርድ ወደ ሥልጣን ማምጣት መሆኑን መራጩ ሕዝብ መገንዘብ እንዳለበትም ገልጸዋል። በዚህም መራጩ ሕዝብ ያወጣውን የምርጫ ካርድ በአግባቡ በመያዝ፣ በዕለቱ ሀገርና ሕዝብን ያሻግራል ብሎ ያመነበትን ፓርቲ እንዲመርጥ መልእክት አስተላልፈዋል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የሰሜን ኢትዮጵያ አስተባባሪና የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ ሃይለማሪያም ብርሃኑ በበኩላቸው፤ በሕዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያለው መንግሥት ለመመስረት ምርጫ ዋናው መሣሪያ መሆኑን ገልጸዋል።
ካርዳችንን በጥንቃቄ በመያዝ የምንፈልገውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል -የገንዳ ውሃ ከተማና የጋዚግብላ ወረዳ ነዋሪዎች
May 23, 2026 150
ሰቆጣና ገንዳውኃ፤ ግንቦት 15/2018 (ኢዜአ)፦ በጠቅላላ ምርጫው ለመሳተፍ የወሰድነውን ካርድ በጥንቃቄ በመያዝ ለሁሉም የሚጠቅም ፖሊሲ ያለውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ሲሉ በአማራ ክልል የገንዳ ውሃ ከተማና የጋዚግብላ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ። ነዋሪዎቹ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ በወሰድነው ካርድ ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ተጠቅመን ለህዝብና ለሀገር ይበጃል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተዋል። በጠቅላላ ምርጫው ለመሳተፍ የወሰድነውን ካርድ በጥንቃቄ በመያዝ ለሁሉም የሚጠቅም ፖሊሲ ያለውን ፓርቲ እንመርጥበታለን ብለዋል። ከገንዳ ውሃ ከተማ ነዋሪዎች መካከል አቶ ዮሴፍ አየነው የመምረጥ መብቴን ተጠቅሜ የዜግነት ግዴታዬን ለመወጣት ተዘጋጅቻለሁ ሲሉ ተናግረዋል። ያወጣሁትን ካርድም ለህዝብ ተጠያቂ የሚሆንና ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ይገነባል ብዬ ለማምነው ፓርቲ ድምጽ በመስጠት ለጠንካራ ሀገረ መንግስት እውን መሆን የድርሻዬን እወጣለሁ ብለዋል። ሌላኛዋ የከተማዋ ነዋሪ ወይዘሮ ቤዛ አለሙ በበኩላቸው ሰላምና ዴሞክራሲን ለሚያሰፍን ፓርቲ ድምጻቸውን እንደሚሰጡ ተናግረዋል። "ካርዴን በወቅቱ ወስጃለሁ፤ በምርጫው ቀን በጠዋት ተገኝቼ ድምፄን በመስጠት ኃላፊነቴን እወጣለሁ" ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በዋግ ኽምራ ዞን የጋዝጊብላ ወረዳ ነዋሪው አርሶ አደር ምስጋናው መኮነን ያወጡትን ካርድ አርሶ አደሩን የሚጠቅም ፖሊሲ ያለውን ፓርቲ ለመምረጥ እንደሚጠቀሙበት ተናግረዋል። "የምንፈልገውን ፓርቲ ለመምረጥ ሰላም ወሳኝ ነው" ያሉት አርሶ አደሩ የአካባቢያቸውን ሰላም በንቃት በመጠበቅና የመኸር እርሻ ዝግጅታቸውንም እያከናወኑ መሆናቸውን ገልፀዋል። "የፖለቲካ ፓርቲዎች እያደረጉት ያለው ቅስቀሳ የሚበጀንን ፓርቲ ለመለየት አግዞናል" ያሉት ደግሞ ሌላው የወረዳው ነዋሪ አርሶ አደር ሞገስ ደባሽ ናቸው። ምርጫው ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ የአካባቢያቸውን ሰላም አፅንተው እየጠበቁ መሆኑን ጠቁመው በድምፅ መስጫው ቀን ማልደው በመነሳት ድምፅ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
ለጠቅላላ ምርጫው በስኬት መጠናቀቅ የበኩላችንን እየተወጣን ነው
May 23, 2026 202
ግንቦት፤ ግንቦት 15/2018(ኢዜአ)፦ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት መጠናቀቅ ህብረተሰቡን በማስተማርና ግንዛቤ በመፍጠር የበኩላቸውን እየተወጡ መሆናቸውን ኢዜአ ያነጋገራቸው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ገለጹ። አስተያየት ሰጪዎቹ አክለውም ምርጫ የህዝብ የስልጣን ባለቤትነት የሚረጋገጥበት በመሆኑ፣ በስኬት እንዲጠናቀቅ የድርሻቸውን በመወጣት ላይ እንደሚገኙ አመልክተዋል። በባሌ ዞን የሮቤ ከተማ የሀገር ሽማግሌዎቹ አቶ ኡመር ገመዳ እና አቶ በሺር በከር ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ የሀገር ሽማግሌዎች ግንባር ቀደም ኃላፊነት አለብን ብለዋል። ለምርጫው ስኬታማነት ከተለያዩ አካላት ጋር በትብብር እየሰሩ እንደሚገኙና ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል። የሃይማኖት አባት የሆኑት አባ ጥበቡ ቁምላቸው ህብረተሰቡ በጠቅላላ ምርጫው በንቃት እንዲሳተፍ የማንቃትና ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እየሰሩ መሆናቸውን አመልክተዋል። በኢሉባቦር ዞን ሀሉ ወረዳ የሀገር ሽማግሌዎች በበኩላቸው፣ በምርጫ ካርዳችን የምንሰጠው ድምፅ የሀገራችንንና የልጆቻችንን የነገ እጣ ፈንታ የሚወስን ነው ብለዋል። አቶ ሳህለ ጉተማ እና አቶ ኃይሉ መኮንን በወሰዱት የመራጭነት ካርድ የሀገርንና የልጆቻቸውን የወደፊት እጣ ፈንታ ለመወሰን መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። ምርጫ ዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በነፃነት የሚጠቀሙበት ሀገራዊ ሁነት በመሆኑ፣ በመራጭነት የሚሳተፉ ዜጎች የድምፃቸውን ዋጋ ለሀገራቸው መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል። በተመሳሳይ በምዕራብ ሀረርጌ ዞን የጭሮ ከተማ ወጣቶች ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ወጣት ኦብሳ መሐመድ እና ወጣት ቡርቃ አሊዪ ምርጫ የሀገር የወደፊት ተስፋ የሚወሰንበት በመሆኑ እንደ አንድ ወጣት ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን ገልጿል። ምርጫው የወጣቶችን የልማት ተጠቃሚነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ወሳኝ ስለመሆኑ በቂ ግንዛቤ ማግኘታቸውንና ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚያበረክቱ ተናግረዋል። የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ወጣቶች ማህበር ሰብሳቢ ወጣት ሙርቴሳ መሐመድ በበኩሉ፤ በዞኑ ለሚገኙ 70 ሺህ ወጣቶች አስፈላጊው ቅስቀሳና የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መሰጠቱን አስታውቋል። ማህበሩ ወጣቶች በምርጫው በንቃት እንዲሳተፉ ከማድረግ ባለፈ 2 ሺህ 756 የምርጫ ታዛቢዎችን መመደቡንም አመልክቷል።
በብልፅግና ፓርቲ መሪነት በክልሉ ባለፉት አምስት ዓመታት በሁሉም ዘርፎች ስኬቶች ተመዝግበዋል - አቶ ጌቱ ወዬሳ
May 23, 2026 180
አዲስ አበባ ፤ ግንቦት 15/2018 (ኢዜአ) ፦ በሀረሪ ክልል ባለፉት አምስት ዓመታት በብልፅግና ፓርቲ መሪነት በሁሉም ዘርፎች ስኬታማ አፈፃፀም መመዝገቡን የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ገለጸ። የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ይሄንን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ባለፉት አምስት አመታት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በሌሎችም የልማት መስኮች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። ፓርቲው ወንድማማችነትና አብሮነትን በማጠናከር እውነተኛ ሕብረ-ብሔራዊነትን በተግባር በማረጋገጥ ቋንቋ እና የጋራ ማንነትን ለኢትዮጵያ ብልፅግና ምሶሶ እንዲሆኑ ማድረግ መቻሉን አመልክተዋል። ባለፉት አምስት ዓመታት ፓርቲው ለህዝብ የገባውን ቃል ዕውን በማድረግ ተጨባጭ ስኬቶች መመዝገቡንም ገልጸዋል። በፖለቲካ ረገድ ከፓርቲው ምስረታ በኋላ በክልሉ ከሴራ ፖለቲካ ወደ መርህ ፖለቲካ፣ ከመገፋፋትና ከጥላቻ ወደ ሰላምና አብሮነት እንድንሸጋገር አድርጎናል ብለዋል። ፓርቲው ከልዩነት አንድነትን፣ ካለፈ ጥላቻና ቁርሾ የነገ ተስፋን፣ ትብብርና ኅብረትን መሰረት ያደረጉ ተግባራትን በማከናወን ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገቡንም ገልጸዋል። በኢኮኖሚ ረገድም በግብርና እና በቱሪዝም ልማት የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ውጤቶች መገኘታቸውን ገልጸዋል። በማህበራዊ ልማት ዘርፍም የትምህርት ጥራትን ከማጎልበትና የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን ከማረጋገጥ አንጻር የተለያዩ ስራዎች መከናወናቸውን አመልክተዋል። ከዚህ በተጨማሪም በጁገል ዓለም አቀፍ ቅርስ እና በከተማው በተሰራው የኮሪደር ልማት፣ በከተማ እና በገጠር የመሰረተ ልማት ተደራሽነት ከፍተኛ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። ኃላፊው አክለውም ፓርቲው ለሰው ተኮር ስራዎች የሰጠው ትኩረት የዜጎችን ችግር በማቃለል ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡ የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ፍትሀዊ ፤ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የዜጎችን እርካታ ማሳደግ መቻሉንም አስረድተዋል። በቀጣይም በሁሉም ዘርፎች የተመዘገቡ አበረታች ስኬቶችን በውጤት አጅቦ ለማስቀጠል ግንቦት 24 ቀን በሚካሄደው 7ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ የፓርቲው አባላት፣ ደጋፊዎችና የክልሉ ነዋሪዎች ብልፅግና ፓርቲን እንዲመርጡ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ወጣቶች በሀገራዊ ብልፅግና ተጠቃሚ የማድረግ ስራዎች እየተከናወኑ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
May 23, 2026 233
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 15/2018 (ኢዜአ)፦ መንግስት ወጣቶችን በሀገራዊ ብልፅግና ተጠቃሚ የማድረግ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመልዕክታቸው፤ ዛሬ "ወጣት ይምረጥ ኢትዮጵያ ትጽና” በሚል መሪ ቃል የብልጽግና አሻራ በተቀመጠበት ገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ከመላ ከተማዋ ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር የድጋፍ ሰልፍና የምርጫ ቅስቀሳ ፕሮግራም መካሄዱን አመልክተዋል። ስለ ወጣቱ ተጠቃሚነት ችግርን እያወራን ሳይሆን ቀንና ሌሊት እየሰራን ለችግሩ ተግባራዊ ምላሽ ከሰጠንባቸው እና ተጠቃሚነቱን ካረጋገጥንባቸው ስፍራዎች አንዱ በሆነው በገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ70 ሺህ በላይ ከሆኑ የከተማችን ወጣቶች ጋር በስፖርታዊ እንቅስቃሴ የምርጫ ቅስቀሳ አድርገናል ሲሉ ገልጸዋል። ባለፉት 5 ዓመታት የሰራናቸው የልማት አሻራዎች የኢትዮጵያን ብልፅግና አይቀሬነት የሚመሰክሩ መሆናቸውንም አስታውቀዋል። ከማንም በላይ ሀገር እየተገነባች ያለችው ለወጣቶቻችን በመሆኑ የብልፅግናዋ ተጠቃሚዎች ይሆናሉ ብለዋል። የከተማችን ወጣቶች የፓርቲውን ራዕይና የወደፊት አሻራ ሁለንተናዊ እድገት ሰንቃችሁ፥ ተስፋ ተጋርታችሁ ማልዳችሁ ከአራቱም አቅጣጫዎች በመትመም ድጋፋቸውን በመግለጻቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል። መንገዳችን መደመር፤ መዳረሻችን ብልፅግና ነው፤ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት አገር በማለት ከንቲባዋ መልዕክታቸውን አጠቃለዋል።

ማህበራዊ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ
May 23, 2026 97
ወላይታ ሶዶ ፤ ግንቦት 15/2018 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ተናገሩ። በወላይታ ዞን የበሌ አዋሳ አጠቃላይ ሆስፒታል የደረጃ ማሻሻያ ዕውቅና እና የማህበረሰብ መድኃኒት ቤት ምረቃ መርሃ ግብር በበሌ አዋሳ ከተማ ተካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት አቶ ገብረመስቀል ጫላ እንደገለጹት፤ የክልሉ መንግስት የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን በማስፋት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ይገኛል። በየመዋቅሩ የጤና ተቋማትን በመገንባትና ባለሙያዎችን በመመደብ፣ ዜጎች የጤና አገልግሎትና መድኃኒት በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። የበሌ አዋሳ ከተማ አጠቃላይ ሆስፒታል ደረጃ ማሻሻልና የማህበረሰብ መድኃኒት ቤት ምረቃ ለዚህ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰው፣ እነዚህን አገልግሎቶች የማስፋት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አክለዋል። አካባቢው ለወባ በሽታ ተጋላጭ መሆኑን ጠቅሰው፣ የሆስፒታሉ ደረጃ መሻሻልና የማህበረሰብ መድኃኒት ቤቱ መመረቅ የህዝቡን የዘመናት ችግር በዘላቂነት እንደሚቀርፍም ተናግረዋል። የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ በበኩላቸው፤ የክልሉ መንግስት የጤና ተቋማትን ደረጃ በማሻሻልና የአገልግሎት አሰጣጥን የማሻሻል ስራዎችን ተግባራዊ በማድረጉ ውጤት እየተገኘ መሆኑን ገልጸዋል። የበሌ አዋሳ ሆስፒታል መደበኛ ህክምና፣ ድንገተኛ ህክምና እና የመድኃኒት አቅርቦትን ጨምሮ ሌሎችንም የአገልግሎት ዘርፎች ያሟላ ሲሆን፣ ለ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች አገልግሎት መስጠት ይችላል ብለዋል። ከለውጡ ወዲህ በክልሉ ከ70 በላይ የማህበረሰብ መድኃኒት ቤቶች ተገንብተው አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ሲሆን፣ ይህም ዜጎች መድኃኒትን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ አስችሏል ነው ያሉት። የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሳሙኤል ተሰማ (ረዳት ፕሮፌሰር) በበኩላቸው፣ አስተዳደሩ በሁሉም መዋቅሮች የጤና አገልግሎትን ለማሻሻል ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑንና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የበሌ አዋሳ ከተማ ከንቲባ አባይነህ አጫ (ዶ/ር) በከተማው የጤና ተቋማት አቅም ማጎልበትን ጨምሮ በ75 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት የተለያዩ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል። የማህበረሰብ መድኃኒት ቤትና የሆስፒታሉ ደረጃ ማሻሻል ከእነዚህ መካከል አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፣ ልማቱን ለማስቀጠል ከከተማው ነዋሪዎች ጋር የተጀመረው ቅንጅት እንደሚቀጥል ተናግረዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች የሆኑት ወይዘሮ ርብቃ ጎዳና እና አቶ አስፋው አስራት በሰጡት አስተያየት፤ ከዚህ ቀደም የጤና አገልግሎት ለማግኘት ወደ ወላይታ ሶዶ እና ሌሎች ቦታዎች በመጓዝ ለከፍተኛ ወጪና እንግልት ይዳረጉ እንደነበር አስታውሰዋል። የአሁኑ የሆስፒታሉ ደረጃ መሻሻል እንግልታቸውን እንዳስቀረላቸውና የማህበረሰብ መድኃኒት ቤቱ ደግሞ ደህንነቱ የተረጋገጠ መድኃኒት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ የተሻለ አማራጭ በመፍጠሩ መንግስትን አመስግነዋል። በዚሁ የምረቃ መርሃ ግብር ላይ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር የመንግስት ስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ በሽታዎችን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች ውጤት እስያገኘ ነው
May 23, 2026 179
ጂንካ፤ ግንቦት 15/2018(ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እ.ኤ.አ በ2030 ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ በሽታዎችን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለው የተቀናጀ ጥረት አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። የክልሉ ጤና ቢሮ ከካርተር ሴንተር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ በሽታዎች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በጂንካ ከተማ አካሂዷል። የቢሮው ኃላፊ ተወካይ አቶ ታምራት አሰፋ በምክክር መድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ በክልሉ ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ በሽታዎችን ለመቆጣጠር እና ለማጥፋት ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል። የሕብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ እና መከላከያ መድኃኒቶችን ተደራሽ በማድረግ የበሽታዎቹን ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ መቻሉን ነው የገለጹት። በዚህም ትኩረት የሚሹ የሀሩራማ በሽታዎች ተብለው ከተለዩት መካከል ትራኮማ፣ ወባ፣ ተላላፊ የዝሆኔ በሽታ እና የጊኒ ዎርም በዋናነት ተጠቃሽ መሆናቸውን ጠቁመው፤ የጊኒ ዎርም በሽታን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር የተቻለ ሲሆን፥ ባለፉት 15 ዓመታት በክልሉ ምንም ዓይነት የጊኒ ዎርም በሽታ አለመከሰቱን አረጋግጠዋል። የዛሬው የምክክር መድረክ በቀጣይ በክልሉ የሀሩራማ በሽታዎችን ጨርሶ ለማጥፋት ለሚደረገው ርብርብ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብለዋል። የካርተር ሴንተር ኢትዮጵያ ምክትል ተጠሪ አቶ የማነ ቀጀላ በበኩላቸው፤ በጤና ሚኒስቴር አማካኝነት በሀገሪቱ የሀሩራማ በሽታዎችን ለመቆጣጠር እና ለማጥፋት የተያዘውን ብሔራዊ ግብ ለማሳካት ድርጅታቸው የበኩሉን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ድርጅቱ በተለይም ኦንኮሰርኪያስስ፣ ተላላፊ የዝሆኔ በሽታ እና የጊኒ ዎርም በሽታዎችን ለመከላከል የሚያስችል የሕክምና እና የመድኃኒት ድጋፍ በሀገሪቱ በሚገኙ ሰባት ክልሎች ተደራሽ እያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል። በካርተር ሴንተር የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ዳንኤል ታምራት በበኩላቸው፥ በክልሉ የኦንኮሰርኪያስስ እና የዝሆኔ በሽታን ለመከላከል መንስኤዎችን ከመለየት ጀምሮ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ረገድ ድርጅቱ እገዛ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በክልሉ ከ974 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች የዝሆኔ እና የኦንኮሰርኪያስስ በሽታዎችን ጨምሮ ሌሎች 11 የአንጀት ጥገኛ ትላትሎችን መከላከል የሚያስችሉ መድኃኒቶች ተሰጥተዋል ብለዋል። ለዚህም ተግባር የሚውል ከ5 ሚሊዮን በላይ የመድኃኒት እንክብል ለማኅበረሰቡ መሰራጨቱን አስተባባሪው ጠቁመዋል።
ለአንጀት ካንሰር አጋላጭ ምክንያቶች በውል ይታወቃሉ? ቀድሞስ መከላከል ይቻላል?
May 22, 2026 495
የጤና ነገር እንደ ዘርፉ የሕክምና ባለሙያዎች ገለጻ፤ በአጠቃላይ የካንሰር ህመም ማለት የኅዋሶች (ሴሎች) ከተፈጥሯዊና ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ሁኔታ መራባት ማለት ነው። የካንሰር ሕክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ቢንያም ተፈራ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ከአንጀት ካንሰር ጋር በተያያዘ አጋላጭ ሁኔታዎቹንና መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ አብራርተዋል። መንስዔ (አጋላጭ ምክንያቶች) እንደ ዶክተር ቢንያም ገለጻ፤ የአንጀት ካንሰር በዋናነት በትልቁ አንጀት ላይ የሚነሳ የካንሰር ዓይነት ነው። የካንሰር ህመም መንስዔ በአብዛኛው ይህ ነው ተብሎ የሚጠቀስ እንዳልሆነ ጠቁመው፤ በአብዛኛው አጋላጭ ምክንቶችን ነው የምናነሳው ይላሉ። መፍትሔውም አንድ ወጥ እንዳልሆነና እንደ አጋላጭ ሁኔታዎቹ የሚሰጥ መሆኑን በማስገንዘብ። የአንጀት ካንሰር ሊያመጡ የሚችሉ አጋላጭ ምክንያቶችም፤ ዕድሜ፣ ዘረመል እና የአኗኗር ዘይቤ በሚል በሦስት ተከፍለው እንደሚታዩ ያስረዳሉ። ዕድሜ፡- ዕድሜ እየገፋ ሲሄድ የአንጀት ካንሰር የመከሰት ዕድል እየጨመረ እንደሚሄድ በመግለጽ፤ በተለይም ከ50 ዓመት በላይ ሲሆን የመከሰት ዕድሉ እንደሚጨምር አመላክተዋል። ዘረመል፡- የዘረመል ተጋላጭነት ከቤተሰብ የሚወረስ ወይም ከአካባቢ የሚገኝ አጋላጭ የዘረመል ለውጦች ካሉ ከ50 ዓመት ቀደም ብሎም ሊከሰት የሚችል የካንሰር ዓይነት ነው ይላሉ። የአኗኗር ዘይቤ፡- በዋናነት የአንጀት ካንሰርን የሚያባብሱ ነገሮች ደግሞ የአኗኗር ዘይቤዎች መሆናቸውን ነው ያስገነዘቡት። በተለይም ከአመጋገብ አንጻር የፋይበር ይዘታቸው ዝቅተኛ የሆኑ ምግቦችን መመገብ፣ ቀይ ሥጋ እና በፋብሪካ የተቀነባበር (ፕሮሰስ የሆነ) ምግብ አብዝቶ መመገብ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ያነሰው የአመጋገብ ዘዴና ሌሎችም ሊነሱ ይችላሉ ብለዋል። በተጨማሪም አልኮል፣ ሲጋራ፣ ከልክ ያለፈ ውፍረት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ (ስፖርታዊ እንቅስቃሴ) አለማድረግ እና ተያያዥ ሁኔታዎች ለአንጀት ካንሰር ሊያጋልጡ እንደሚችሉ አንስተዋል። ምልክቶች የአንጀት የሥራ ሂደት መስተጓጎል፣ በአብዛኛው ቶሎ የማይሄድ ወይም እየተለዋወጠ የሚመጣ ድርቀት፣ ተቅማጥ፣ ደም የቀላቀለ ሰገራ መኖር፣ በሰገራ ወቅት የተለየ ማስማጥ፣ መንስዔው በውል ያልታወቀ ክብደት መቀነስ፣ መንስዔው ያልታወቀ ከፍተኛ ድካም የአንጀት ካንሰር ምልክቶች ከሚባሉት መካከል መሆናቸውን አብራርተዋል። በሌላ በኩል በርካቶች ምንም ዓይነት ምልክት ሳይታይባቸው በህመሙ ሊጠቁ እንደሚችሉም ባለሙያው ጠቁመዋል። በአብዛኛው እነማንን ያጠቃል? ዶክተር ቢንያም እንዳሉት፤ የአንጀት ካንሰር ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍል የሚያጠቃ ቢሆንም በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲታይ በአብዛኛው በወንዶች ላይ ይከሰታል። በኢትዮጵያ ደግሞ ተቀራራቢ በሆነ ሁኔታ በሁለቱም ጾታዎች ላይ ይከሰታል። በተለየ ሁኔታ የአንጀት ካንሰር ሊከሰትባቸው የሚችሉ ሰዎች የዘረመል አጋላጭ ምክንያቶች ያሉባቸው መሆናቸውንም አንስተዋል። በተለይም ከቤተሰብ የሚወረስ የዘር መለወጥ ያላቸው ሰዎች ከ50 ዓመት ቀደም ብሎ የአንጀት ካንሰር የመያዝ ዕድል እንዳላቸውም ይገልጻሉ። የአሳሳቢነት ደረጃ የአንጀት ካንሰር በሕጻናት ላይ አይከሰትም ማለት ባይቻልም አልፎ አልፎ በጣም ጥቂት የመከሰት ዕድል ሊኖረው እንደሚችል ጠቁመው፤ በአጠቃላይ ግን የአንጀት ካንሰር ለሕጻናትና አዳጊዎች ያን ያህል በአስጊ ደረጃ እንደማይጠቀስ ያነሳሉ። በዓለም አቀፍ ደረጃ ከጡትና ማኅጸን ካንሰር በመቀጠል በ3ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝና በኢትዮጵያም ወንድንም ሴትንም ደምረን ካየነው በ3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ብለዋል። ወንዶችን ለብቻ ነጥለን ካየነው ደግሞ 1ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ የካንሰር ዓይነት ነው ያሉት ዶክተር ቢንያም፤ እስከ 6 ሺህ ገደማ የሚሆኑ ሰዎች በዚህ ካንሰር በየዓመቱ ይያዛሉ፤ ከ4ሺህ 500 የሚልቁት ደግሞ በየዓመቱ በዚሁ ካንሰር ይሞታሉ ሲሉ አብራርተዋል። የሕክምና ሁኔታ እንደ ዶክተር ቢንያም ገለጻ፤ የአንጀት ካንሰር በወቅቱ ሲደረስበት ታክሞ የመዳን ተስፋው በጣም ጥሩ ነው። ይህን የሚወስነው ግን በዋናነት በሽታው የተገኘበት ደረጃ መሆኑን በአጽንኦት ተናግረዋል። ስለዚህ ቶሎ የተገኘ የአንጀት ካንሰር እንደሚታከም ገልጸዋል። በተለይም በደረጃ 1 እና 2 ላይ የሚገኝ የካንሰር ዓይነት የመዳን ዕድሉ እጅግ በጣም ሰፊ መሆኑን አስረድተዋል። ደረጃው እያደገ በሚሄድበት ጊዜ ግን ሕክምናውም እየተወሳሰበና አስቸጋሪ እየሆነ እንደሚሄድ አንስተዋል። የመዳን ዕድሉም በዚያው መጠን እያስቸገረ መሄዱ አይቀርም ይላሉ። አንጀት በጣም ረጅም በመሆኑ ሕክምናው ካንሰሩ እንደተገኘበት ደረጃ እና እንደተከሰተበት ቦታ እንደሚወሰንም አንስተዋል። በአጠቃላይ ግን ላልተሠራጨ ካንሰር ቀዶጥገና (ኦፕሬሽን) ዋነኛ የሕክምና አማራጭ ነመሆኑን አስታውቀዋል። በተጨማሪነት ኬሞቴራፒና የጨረር ሕክምና የሕክምናው አካል መሆናቸውን ገልጸዋል። በዋናነት ሦስቱ የሕክምና አማራጮች እንደሚሰጡ ገልጸው፤ እንደ ካንሰሩ ደረጃ የወሰን ሆኖ ሚኖ ቴራፒ እና ታርጌትድ ቴራፒ የሚባሉ ተጨማሪ የሕክምና አማራጮ ስለመኖራቸውም ጠቁመዋል። ምክረ ሐሳብ የአንጀት ካንሰርን ልንከላከለው የምንችለው የካንሰር ዓይነት ነው ብለዋል ዶክተር ቢንያም። በተለይም የአኗኗር ዘይቤን በማስተካከል፣ በመአጋገብ ሁኔታ ላይም በፋብሪካ የተቀነባበሩ (ፕሮሰስ የሆኑ) ምግቦችን (ቀይ ሥጋን ጨምሮ) አብዝቶ ባለመመገብ፣ በፋይበር የበለጸጉ ምግቦችን አዘውትሮ በመመገብ፣ አትክልትና ፍራፍሬን በማዘውተር፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ የአንጀት ካንሰርን ቀድሞ መከላከል እንደሚቻል አስረድተዋል። በተለይም ማንኛውም ከ50 ዓመት በላይ የሆነው ሰው የአንጀት ካንሰር ምርመራ ቢያደርግ እንደሚመከርም ገልጸዋል። በሌላ በኩል በቤተሰብ የአንጀት ካንሰር ተጠቂ ካለ ከ50 ዓመት በታች የሆኑም ምርመራ እንዲያደርጉ ይጠበቃል ብለዋል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ነጻ የልብ ቀዶ ህክምና እየሰጠ ነው
May 22, 2026 266
ጎንደር ፤ ግንቦት 14/2018 (ኢዜአ)፦የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት የልብ ህክምና ማግኘት ላልቻሉ ወገኖች ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ነጻ የልብ ቀዶ ህክምና እየሰጠ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ሆስፒታሉ ከግንቦት 13 እስከ 15 ቀን 2018 ዓ.ም እየሰጠ በሚገኘው ህክምና ለ14 ህጻናት ህክምናውን መስጠት መቻሉም ተገልጿል። በዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጤና ትምህርትና ህክምና አገልግሎት ኮርፖሬት ዳይሬክተር አቶ ደምስ ሙላቱ እንደተናገሩት፤ በአመት እስከ 500 የሚደርሱ የልብ ጤና ችግር ያለባቸው ህጻናት ለህክምና እርዳታ ወደ ሆስፒታሉ ይመጣሉ። የህጻናቱ ቤተሰቦች የልብ ህክምናውን ለማግኘት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ሀገር ከፍለው የማሳከም ከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይህንን ችግር ለማቃለልም ከጣሊያን ሀገር ከመጡ ከፍተኛ የህክምና ባለሙያዎች ጋር በመተባበር እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡ የህክምና ባለሙያዎቹ፣ በአፈጣጠር ምክንያት የልብ ጤና ችግር ለገጠማቸውና እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት ህክምናውን እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ህክምናው የህጻናቱን ጤና ከመመለስ ባሻገር በቴክኖሎጂና በእውቀት ሽግግር ረገድ ፋይዳው የጎላ መሆኑንና ይህም ሆስፒታሉ በቀጣይ ራሱን ችሎ የልብ ቀዶ ህክምና አገልግሎት እንዲሰጥ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር አቶ ደምስ ጠቁመዋል። የልኡካን ቡድኑ አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ ተድላ በበኩላቸው፤ የህክምና ቡድኑ በኢትዮጵያ በሚኖረው የ45 ቀናት ቆይታ በጎንደር፣ በአዲስ አበባና በሌሎችም የሀገሪቱ ክፍሎች ለ175 ህጻናት ነጻ የልብ ቀዶ ህክምና ለመስጠት ማቀዱን ተናግረዋል፡፡ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እስከ 24 ለሚደርሱ ህጻናት የልብ ቀዶ ህክምና ለመስጠት እቅድ ተይዞ፣ በሁለት ቀናት ውስጥ ለ14 ህጻናት ህክምናውን መስጠት መቻሉን አስረድተዋል፡፡ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በተደረሰ ስምምነትና በአጋር የጤና ተቋማት ድጋፍ እየተሰጠ የሚገኘው ይህ ነጻ የልብ ቀዶ ህክምና በክፍያ ቢሆን ኖሮ፣ ለአንድ ህጻን የህክምና ወጪ ብቻ እስከ ሁለት ሚሊዮን ብር ይጠይቅ እንደነበር አስታውቀዋል። ይህ የነጻ የልብ ቀዶ ህክምና በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ልጆቻቸውን ከፍለው ማሳከም ሳይችሉ ለቆዩ ወላጆች ትልቅ እፎይታ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ደብሬ የኋላ ናቸው፡፡ ሰብአዊነትን በመላበስ አህጉር አቆራርጦ በመምጣት ህክምናውን እየሰጠ ለሚገኘው የልኡካን ቡድን ምስጋና በማቅረብ፣ የከተማ አስተዳደሩ ያዘጋጀውን የባህል አልባሳትና ወካይ ቅርሶች በስጦታ አበርክተዋል፡፡ በጎንደርና በአካባቢው የልብ ቀዶ ህክምና አገልግሎት የሚሰጥ የጤና ተቋም ባለመኖሩ ልጃቸውን ማሳከም ሳይችሉ ቆይተው እንደነበር የጠቀሱት ደግሞ ለ9 ወር ልጃቸው ነጻ የልብ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ያገኙት ወይዘሮ ሀረገወይን ደሴ ናቸው። በገንዘብ ማጣት የልጃቸውን ህመምና ስቃይ ከመመልከት የታደጋቸው ይህ የነጻ ህክምና አገልግሎት ለሌሎችም ችግረኛ ወገኖች እንዲደርስ ጠይቀዋል።
ኢኮኖሚ
መንግስት በነዳጅ አቅርቦት ላይ የወሰደው እርምጃ በከተማዋ የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭትን በማሳለጥ በኩል ከፍተኛ ለውጥ አስገኝቷል
May 23, 2026 149
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 15/2018(ኢዜአ)፦ መንግስት በነዳጅ አቅርቦት ላይ የወሰደው እርምጃ በከተማዋ የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭትን በማሳለጥ በኩል ከፍተኛ ለውጥ ማስገኘቱን ኢዜአ ያነጋገራቸው አሽከርካሪዎች እና የነዳጅ ማደያዎች ገለጹ፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ ተከስቶ የነበረውን ችግር ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ በነዳጅ ምርት አቅርቦት ላይ የተፈጠረው ክፍተት፣ በሀገር ውስጥም የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል አስከትሎ የነበረ ቢሆንም፤ መንግሥት አቅርቦቱ ከጦርነቱ በፊት ወደነበረበት ደረጃ እንዲመለስ አድርጓል። መንግሥት በነዳጅ አቅርቦት ላይ የወሰደው እርምጃ የነበረውን ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ተቋቁሞ ለማለፍ ያስቻለ ሲሆን፣ አሁን ላይ በተለያዩ ከተሞች የተረጋጋ፣ ቀልጣፋ የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት እንዲኖር አስችሏል። የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በወቅታዊ የዓለም የነዳጅ ሁኔታን በማስመልከት በሰጡት ማብራሪያ፣ የናፍጣ ነዳጅ አቅርቦት ከመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በፊት ወደነበረበት እንዲመለስ መደረጉን መጥቀሳቸው ይታወቃል፡፡ ኢዜአ በመዲናዋ ያነጋገራቸው አሽከርካሪዎችና የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች፤ መንግሥት በነዳጅ አቅርቦት ላይ የወሰደውን የማሻሻያ እርምጃ ተከትሎ በአቅርቦቱና በስርጭቱ ላይ ከፍተኛ አዎንታዊ ለውጥ መታየቱን ገልጸዋል። አስተያየት ከሰጡ አሽከርካሪዎች መካከል አባይነህ ይሁኔ፤ ቀደም ሲል ከዓለም አቀፉ የነዳጅ እጥረት ጋር ተያይዞ በነበረው መስተጓጎል በእለት ተእለት እንቅስቃሴያቸው ላይ ከፍተኛ ችግር ገጥሟቸው እንደነበር አስታውሰዋል። አሁን ላይ ግን የነበረው ችግር ሙሉ በሙሉ ተፈትቶ ሁኔታው ወደ ቀድሞው በመመለሱ፣ በሁሉም ማደያዎች የሚፈልጉትን ያህል ነዳጅ ያለምንም እንግልት እያገኙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ሌላኛው አሽከርካሪ ከድር ሁሴን በበኩላቸው፤ ቀደም ሲል ነዳጅ ለማግኘት እስከ አንድ ሳምንት ይወስድባቸው የነበረው አስቸጋሪ ሁኔታ በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ መፈታቱንና ያለምንም እንግልት ነዳጅ እያገኙ ማኅበረሰቡን በሚገባ እያገለገሉ መሆናቸውን አስረድተዋል። በተመሳሳይ አሽከርካሪ ተፈሪ ዓለሙ እና ረታ ጂቢቲ እንደገለጹት፤ ቀደም ሲል ተከስቶ የነበረው የነዳጅ እጥረትና የረጅም ሰዓት ወረፋ በመንግሥት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት በመቀረፉ፣ በአሁኑ ወቅት ያለምንም መስተጓጎል እየተስተናገዱ ይገኛሉ። በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ላይ የነበረው ችግር በመወገዱ በአሁኑ ወቅት የተረጋጋ ሁኔታ መፈጠሩንና መደበኛ ሥራቸውን በተሻለና ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መልኩ እያከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል። የነዳጅ ማደያ ሱፐርቫይዘሮች በበኩላቸው ቀደም ሲል በዓለም አቀፍ የነዳጅ ቀውስ ምክንያት ይፈጠር የነበረው የአቅርቦት ችግር በመቀረፉ ደንበኞቻቸውን ያለምንም እንግልት እያስተናገዱ መሆኑን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት በአቅርቦትና በስርጭት ላይ ችግር አለመኖሩን ጠቁመው ለማኅበረሰቡ ጥሩ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ጠቁመዋል። በቡልጋሪያ አካባቢ የቶታል ማደያ ሱፐርቫይዘር ሰለሞን ገብረሕይወት እና በአሮጌው ቄራ አካባቢ ቶታል ማደያ ሱፐርቫይዘር ይርጋ ኪዳነ ማርያም ቀደም ሲል በነበረው እጥረት ምክንያት ተሽከርካሪዎች ነዳጅ ለማግኘት እስከ አምስት ቀናት የሚደርስ ረጅም ሰልፍ ይጠብቁ እንደነበር አስታውሰው፤ አሁን ላይ ችግሩ ሙሉ በሙሉ መቀረፉን አረጋግጠዋል። በተመሳሳይ የሜክሲኮ አካባቢ የካምፖ አስመራ ነዳጅ ማደያ ሱፐርቫይዘር ጥበቡ በቀለ በበኩላቸው፤ መንግሥት ዓለም አቀፉን የነዳጅ አቅርቦት ቀውስ ለማስተካከል የወሰደውን ቁርጠኛ እርምጃና የመጣውን ፈጣን አዎንታዊ ለውጥ አድንቀዋል። በአሁኑ ወቅት ነዳጅ ለማደያቸው በአግባቡና በወቅቱ እየቀረበ መሆኑን ገልጸው እያገኙት ያለውን ምርትም ለተጠቃሚ አሽከርካሪዎች እያቀረቡ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።
የአካባቢ ጸጋዎችን መሰረት ያደረጉ የሥራ ዕድል ፈጠራ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገቡ ነው
May 23, 2026 116
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 15/2018(ኢዜአ)፦ በየአካባቢው የሚገኙ የፈጠራና የተፈጥሮ ጸጋዎችን በመለየትና የሥራ ዕድሎችን በማስፋፋት ተጨባጭ ውጤቶች እየተገኙ መሆኑን የተለያዩ ክልሎች የሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች ገለጹ። በኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማሳደግ፣ የግል ዘርፉን ለማበረታታትና የሥራ አጥነት ቁጥርን ለመቀነስ በርካታ መዋቅራዊና ሕጋዊ ሪፎርሞች ተከናውነዋል። ለአብነትም የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ማስፋፋት፣ ለሥራ ዕድል ቅድሚያ የሚሰጥ ስትራቴጂ ትግበራ፣ ተቋማዊ ሪፎርም እንዲሁም የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትን ማመቻቸት በዋናነት የሚጠቀሱ ተግባራት ናቸው። የተለያዩ ክልሎች የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊዎች ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የአካባቢ ጸጋዎችን በጥናት በመለየት የሥራ ዕድልን ለማስፋፋት የተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶችን አስገኝተዋል። የአካባቢውን ጸጋ ተጠቅመው ዜጎች በማኅበረሰብና በቤተሰብ የንግድ ሥራዎች ላይ እንዲሰማሩ ምቹ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን አመልክተው፤ የሥልጠና፣ የብድር እና የሌሎች ተያያዥ ድጋፎችን በማድረግ የዜጎች ውጤታማነት ይበልጥ እየጎለበተ መምጣቱን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት አማካኝነት የሥራ ፈላጊዎች ምዝገባና የሥራ ዕድል ፈጠራ መረጃዎችን በዘመናዊ መልኩ በማደራጀት፣ ቀልጣፋ፣ ግልጽና ተደራሽ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ኃላፊዎቹ ጠቁመዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ተመስገን ኃይሌ፤ በክልሉ የሀገር ውስጥ የሥራ ዕድሎችን ለማሳደግ የአካባቢ ጸጋዎችን በመለየት ዜጎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በተያዘው በጀት ዓመትም ለዜጎች የክህሎት፣ የአቅም ግንባታና ሌሎች ድጋፎችን በማመቻቸት እና የሥራ ዕድል ፈጠራው ክህሎት መር በማድረግ እስካሁን ለ280 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፈጠሩን ጠቁመዋል፡፡ በሲዳማ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ከፍያለው ከበደ በበኩላቸው፤ በክልሉ በስፋት የሚገኙ ምርቶችን በመለየት የማኅበረሰብና የቤተሰብ የንግድ ሥራዎችን ከሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር ጋር በማስተሳሰር ውጤታማ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ስምሪትና ገበያ ልማት ዘርፍ ኃላፊ ዘውዱ ሳሙኤል፤ በክልሉ የሥራ ዕድል ፈጠራ ትኩረት ያደረገው በአካባቢ ጸጋዎችና አቅሞች ላይ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም ዜጎች ተደራጅተው በአካባቢው በሚገኙ ጸጋዎች ላይ እሴት በመጨመር በስፋት እንዲያመርቱና ወደ ገበያ እንዲያስገቡ በማድረግ በኩል ስኬታማ ሥራዎች መከናወናቸውን አስገንዝበዋል።
በምስራቅ ወለጋ ዞን በመጪው ክረምት በ39 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የቡና ችግኝ ይተከላል
May 23, 2026 110
ነቀምቴ፤ ግንቦት 15/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን በመጪው ክረምት በ39 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የቡና ችግኝ እንደሚተከል የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ። በጽህፈት ቤቱ የቡና ምርት ቡድን መሪ አሰፋ መኮንን እንደገለጹት፤ በዞኑ የቡና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተተገበረ ባለው ኢኒሼቲቭ የአርሶ አደሩ ተጠቃሚነት እያደገ መጥቷል። በተያዘው ዓመት ክረምትም በ39 ሺህ 983 ሄክታር መሬት ላይ በአጭር ጊዜ ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ 279 ሺህ 632 የቡና ችግኝ ለመትከል ታቅዶ ወደ ስራ ተገብቷል ብለዋል። ችግኞቹም በመንግስት፣ በማህበራትና በአርሶ አደሮች የችግኝ ጣቢያዎች እንዲባዙ ተደርጎ በአሁኑ ወቅት ለተከላ ዝግጁ መደረጉን ገልጸዋል። ከችግኝ ዝግጅትና ተከላ ጋር ተያይዘው የሚታዩ ክፍተቶችን ለማረምም የባለሙያዎች የአቅም ግንባታና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እየተሰጠ ነው። የቡና ምርትና ምርታማነትን በተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ያረጀና ምርት የማይሰጥ የቡና ተክል ጉንደላ ሲከናወን መቆየቱን ጠቅሰው የተጎነደሉ ተክሎች በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ መልሰው ምርት የሚሰጡ መሆኑንም ተናግረዋል። በዞኑ የጉቶ ጊዳ ወረዳ አርሶ አደር ሹምዬ ባይሳ እና አርሶ አደር ገመቹ ደረጄ በሰጡት አስተያየት፤ ቀደም ሲል በባህላዊ መንገድ ያመርቱ ስለነበር በሚፈለገው ልክ መጠቀም እንዳልቻሉ ገልጸዋል።
በአማራ ክልል የከተማ ነዋሪዎችን የቤት ባለቤት ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው
May 23, 2026 92
ጎንደር፤ ግንቦት 15/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የከተማ ነዋሪዎችን የቤት ባለቤት ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት በትኩረት እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሞላ መልካሙ (ዶ/ር) ገለጹ። የጎንደር ከተማ አስተዳደር በ550 የመኖሪያ ቤት ሕብረት ሥራ ማኅበራት ለተደራጁ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የቤት መስሪያ ቦታ፣ የሳይትና የብሎክ ርክክብ መርሃ ግብር አካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የቢሮው ኃላፊ ሞላ መልካሙ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፤ የክልሉ መንግሥት የቤት ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂውን ወደ ተግባር በማውረድ፣ በመካከለኛና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በተለያዩ አመራጮች የቤት ባለቤት ለማድረግ እየሠራ ነው። መንግሥት የሕዝቡን አቅም በማስተባበርና ዘመናዊ አሠራር በመዘርጋት የቤት አቅርቦት ችግርን ለመፍታት የተቀናጀ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። መሬት ውድና ውስን ሀብት በመሆኑ ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ትኩረት በመስጠት፣ ለኑሮ ምቹና ውብ የሆኑ ዘመናዊ ከተሞችን ለማስፋፋት የቤት ልማት ፖሊሲውን መሠረት ያደረጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም ገልጸዋል። የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው በበኩላቸው፤ በማኅበራት የተደራጁ ነዋሪዎች ፈጥነው ወደ ግንባታ መግባት እንዲችሉ ከተማ አስተዳደሩ መሠረተ ልማቶችን በፍጥነት እንደሚያሟላ ገልጸዋል። ማኅበራቱ በገቡት ውል መሠረት ግንባታቸውን በፍጥነት መጀመር እንዳለባቸው ያሳሰቡት ምክትል ከንቲባው፤ መሬት አጥረው ለረጅም ዓመታት በሚያቆዩ ማኅበራት ላይ ጥብቅ ክትትል በማድረግ ከተማ አስተዳደሩ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቀዋል። የከተማ አስተዳደሩ የመሬት መምሪያ ኃላፊ አቶ ታዛዙ በጽሐ፤ በዛሬው ዕለት የቅየሳና የብሎክ ሥራ ተሠርቶላቸው የመኖሪያ ቤት ግንባታ ቦታ ተጠቃሚ የሆኑት ከ13 ሺህ በላይ አባላትን ያቀፉ 550 የቤት ሥራ ማኅበራት መሆናቸውን አስታውቀዋል። ለእያንዳንዱ የማኅበር አባል 150 ካሬ ሜትር የግንባታ ቦታ መዘጋጀቱን የጠቆሙት ኃላፊው፤ ከተጠቃሚዎቹ መካከል የመንግሥት ሠራተኞች፣ መምህራንና የጤና ባለሙያዎች፣ ሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች፣ በክብር የተመለሱ የሠራዊት አባላት፣ እንዲሁም ከስደት ተመላሾች እንደሚገኙበት አስረድተዋል። የቤት መስሪያ ቦታ ተጠቃሚ ከሆኑት ነዋሪዎች መካከል አቶ ታደለ በላይ በሰጠው አስተያየት፤ ለረጅም ዓመታት በግለሰብ ቤት ኪራይ አስቸጋሪ ሕይወት ሲመራ መቆየቱን ገልጾ፣ አሁን ቦታውን በማግኘቱ ፈጥኖ በመገንባት የቤት ባለቤት ለመሆን መወሰናቸውን ተናግረዋል። ወጣት አማኑኤል ምሕረቱ በበኩሉ፤ የቤት መስሪያ ቦታ ዕድለኛ በመሆኑ የተሰማውን ከፍተኛ ደስታ ገልጿል። በዚሁ የርክክብ ሥነ-ሥርዓት ላይ የክልሉና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በቤት ሥራ ማኅበራት የተደራጁ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የአምስት ሚሊየን ኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና በክህሎት የበለፀገ የሰው ኃይል በማፍራት የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን እያሳለጠ ነው
May 23, 2026 144
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 15/2018 (ኢዜአ)፦ የአምስት ሚሊየን ኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና በክህሎት የበለፀገ የሰው ኃይል በማፍራት የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን እያሳለጠ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ በኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና መርሃ ግብር እስከ አሁን ከ4 ነጥብ 85 ሚሊየን በላይ ሰዎች ስልጠና በመውሰድ የሰርተፍኬት ባለቤት እየሆኑ እንደሚገኝም አስታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአምስት ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ስልጠናን ሐምሌ 2016 ዓ.ም በይፋ ማስጀመራቸው የሚታወስ ነው። የአምስት ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ተነሳሽነት ወጣቶች ላይ ትልቅ ለውጥ ለማምጣት ያለመ የዲጂታል ክህሎት ማልሚያ መርሃ ግብር ሆኖ እያገለገለ ሲሆን በዚህም ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገብ ጀምሯል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች መንግሥት ጋር በመተባበር ያስጀመረው የኢትዮ-የኮደርስ ስልጠናም ሀገራዊ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን በማፋጠን ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው። ስልጠናውም ዜጎች በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ዳታ አናሊሲስ፣ በአንድሮይድና በፕሮግራሚንግ ዴቨሎፕመንት ዋና ዋና ዘርፎች ስልጠና የሚያገኙበትን ምኅዳር ፈጥሯል። ስልጠናው በኦላይን ሥርዓት በነፃ የሚሰጥና ዜጎች ያለ ዕድሜ ገደብ መሠረታዊ የዲጂታል ስልጠና ወሰደው ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው ሰርተፍኬት ያገኙበታል። የዲጂታል ኢኮኖሚ ሥርዓትን በመገንባት ሂደትም በርካታ ዜጎችን የቴክኖሎጂ ክህሎት በማስታጠቅ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል። ይህም የኢትዮጵያን የግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና አይሲቲ ብዝኅ የኢኮኖሚ ጉዞ የሚያሳልጥ ሀገር በቀል የዲጂታል ክህሎት የታጠቀ ትውልድ በማፍራት እያስቻለ ነው። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ስዩም መንገሻ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዲጂታል ኢኮኖሚን መገንባት የሚያስችል ሥነ-ምኅዳር ተፈጥሯል። ለአብነትም የአምስት ሚሊየን የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና በርካታ ዜጎች የዲጂታል ዕውቀትና ክህሎት የሚታጠቁበትን አስቻይ የአሰራር ሁኔታ መፍጠሩን አስታውቀዋል። የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና ከተጀመረ አንስቶም እስካሁን ከ4 ነጥብ 85 ሚሊየን በላይ ዜጎች የስልጠናው አካል በመሆን የተለያዩ የዓለም አቀፍ ሰርተፊኬት ባለቤት እየሆኑ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ለፈጠራና ቴክኖሎጂ ልማት የተሰጠው ትኩረትም የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ የሚያሳልጥ የሰው ሃይል ማፍራት እያስቻለ መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠናም የዲጂታል ዕውቀትና ክህሎት የታጠቀ ብቁ የሰው ሃይል በማፍራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ አንስተዋል። የስልጠና መርሃ ግብሩም ዜጎች ባሉበት ቦታ ሆነው በኦላይን ሥርዓት ዕውቀት የሚሸምቱበትን ዕድል መፍጠሩን ጠቅሰዋል። በቀሪ የሥልጠናው ጊዜያትም ዜጎች የዕድሉ ተጠቃሚ በመሆን የዲጂታል ዕውቀትና ክህሎት ማዳበር እንደሚችሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያን የዲጂታል ሉዓላዊነት በማረጋገጥ የሳይበር ደኅንነት ስጋትን የሚቀለብስ የሰው ሃይል ማፍራት እየተቻለ ነው
May 21, 2026 711
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 13/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የዲጂታል ሉዓላዊነት በማረጋገጥ የሳይበር ደኅንነት ስጋትን የሚቀለብስ የሰው ሃይል ማፍራት እየተቻለ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ገለጸ። አስተዳደሩ በዘንድሮው ክረምት ለ5ኛ ጊዜ የሚያካሂደውን የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ (Cyber Talent Summer Camp) ዝግጅት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። የአስተዳደሩ የሳይበር ልህቀት ማዕከል ዳይሬክተር ቢሻው በየነ በመግለጫቸው፤ መርሃ ግብሩ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች በማሰልጠን የሳይበር ደኅንነትና የቴክኖሎጂ ሙያተኞችን ለማፍራት ያለመ ነው ብለዋል። የስልጠና መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያን የሳይበር ደኅንነትና ሉዓላዊነት የማስጠበቅ አቅምን የበለጠ ለማጠናከር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል። የመርሃ ግብሩ ዋና ዓላማ ኢትዮጵያ በዘርፉ ሀገራቸውን ከሳይበር ጥቃት የሚከላከልና ብቁ የሳይበር ሠራዊት ማፍራት መሆኑን አብራርተዋል። እንደ እስራኤል፣ እንግሊዝ እና አሜሪካ ያሉ ሀገራት ተሞክሮ መርሀግብሩ ታዳጊዎችን ለማፍራት ያለውን ወሳኝነት እንደሚያሳይ ገልጸዋል። ይህ ካምፕ የ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ስትራቴጂን ስኬታማ ለማድረግና የኢትዮጵያን ዲጂታል ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል። የዘንድሮው የስልጠና ካምፕ በክልል ደረጃ በስድስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲካሄድ የተወሰነ ሲሆን ይህም ታዳጊዎች በቅርበት ስልጠናውን እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ብለዋል። በእስካሁኑ ሂደትም ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ ከ4 ሺህ በላይ ታዳጊዎችና ወጣቶች መመዝገባቸውን ገልፀዋል። ምዝገባውም ግንቦት 17/2018 ዓ.ም የሚጠናቀቅ በመሆኑ በሳይበር ደህንነትና ቴክኖሎጂ ልዩ ተሰጥኦና ፍላጎት ያላቸው ታዳጊዎችና ወጣቶች በኦንላይን እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል።
የምርት ጥራት ደረጃ ማረጋገጫ መተግበሪያው የኢትዮጵያን የንግድ ስርዓት ወደ ላቀ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ነው
May 21, 2026 393
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 13/2018(ኢዜአ)፦ የምርት ጥራት ደረጃ ማረጋገጫ መተግበሪያው የኢትዮጵያን የንግድ ስርዓት አፈጻጸም ወደ ላቀ ምዕራፍ የሚያሸጋግር መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት በዛሬው ዕለት የምርት ጥራት ደረጃን በኦንላይን ማረጋገጥ የሚያስችል መተግበሪያ አስመርቆ ወደ ስራ አስገብቷል። በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር መሠረት በቀለ (ዶ/ር) ተገኝተዋል፡፡ ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ሪፎርሙ በንግድ ስርዓቱ ላይ ትልቅ እመርታ እንዲመዘገብ አድርጓል ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከ46 በላይ አገልግሎቶች በኦንላይን እየተሰጡ እንደሚገኙ ጠቅሰው፥ ይህም የንግድ ሥርዓቱን በማዘመን የምርት ጥራት አፈፃጸም ላይ የላቀ ውጤት እንዲመዘገብ ማስቻሉን ገልጸዋል። በ2018 በጀት ዓመት አስር ወራት ብቻ ከወጪ ንግድ ከ8 ነጥብ 7 ቢሊየን በላይ የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱንም ነው የተናገሩት፡፡ ዛሬ የተመረቀው የኦንላይን መተግበሪያ አገልግሎቶችንና የምርት ጥራትን በላቀ አፈፃጸም መምራት የሚያስችል መሆኑንና የኢትዮጵያን የንግድ ስርዓት አፈፃጸም ውጤታማነት ለማላቅ አይነተኛ ሚና ያበረክታል ብለዋል። የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር መሠረት በቀለ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ተስፋ ሰጭ የለውጥ ጉዞ እያስመዘገበች ትገኛለች ብለዋል። ኢንስቲትዩቱ የለውጥ ጉዞውን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የሕግና ተቋማዊ ማሻሻያዎችን እንዳደረገ በመግለጽ፡፡ የዚህ ጥረት አካል የሆነው የኦንላይን የምርት ጥራት ማረጋገጫ መተግበሪያ የኢትዮጵያ ምርቶችን በዓለም አቀፍ ገበያ በዋጋና በጥራት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑንም አክለዋል፡፡ መተግበሪያው የኢንስቲትዩቱን የማስፈጸም አቅም ሀገሪቱ ከደረሰችበት የዕድገት ደረጃ ጋር እንዲጣጣም አጋዥ ስለመሆኑም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ በምርት ጥራት ላይ እያከናወነቻቸው ያሉ ተግባራት ለአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ እንደሚሆኑ የተናገሩት ደግሞ የአፍሪካ የደረጃዎች ተቋማት የማዕከላዊ ኮሚቴ ጸሐፊ ሬዩበን ጊሶር ናቸው፡፡ ኢንስቲትዩቱ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ያከናወናቸውን አጠቃላይ ተቋማዊ የሪፎርም ስራዎችን አስመርቋል።
የሕክምና ሙከራዎች ፈቃድ የመስጠትና የቁጥጥር ሥርዓቱን ዲጂታላይዝ ለማድረግ የሚያስችል ሥርዓት ተዘርግቷል
May 21, 2026 413
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 13/2018 (ኢዜአ)፦አዳዲስ የሕክምና ሙከራዎች ወደ ሥራ እንዲገቡ ፈቃድ የመስጠትና የቁጥጥር ሥርዓቱን ዲጂታላይዝ ለማድረግ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋቱን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ። የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የሕክምና ሙከራ የቁጥጥር አሠራር የምክክር መድረክ ላይ አዲስ የተገነባውን የሕክምና ሙከራ የኦንላይን ማመልከቻ ሥርዓት (Online Application System) ማስጀምሪያ መርሃ ግብር አካሄዷል። የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬሕይወት አበበ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት፤ ደህንነታቸውና ፈዋሽነታቸው የተረጋገጡ አዳዲስና በሙከራ ላይ የሚገኙ የሕክምና መሣሪያዎች፣ መድኃኒቶችና ሌሎች ግብዓቶች በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገቡ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው። አዳዲስ የሕክምና ሙከራዎች ወደ ሥራ እንዲገቡ ፈቃድ የመስጠትና የቁጥጥር ሥርዓቱን ዲጂታላይዝ ለማድረግ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋቱን ተናግረው፤ ይህም ለሕብረተሰቡ ጤናና ደህንነት መጠበቅ ጉልህ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል። ዛሬ ይፋ የተደረገው የኦንላይን የቁጥጥር ስርዓትም የሕክምና ሙከራዎች ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር አገልግሎትን ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ የሚያደርግ መሆኑን አብራርተዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ለኢትዮጵያ የሚቀርቡ የሕክምና ሙከራ ፈቃድ አገልግሎት ጥያቄዎች እየጨመሩ መሆኑን ጠቅሰው፤ መተግበሪያው ሀገሪቱ የምታደርጋቸውን ዓለም አቀፍ ትብብሮች ይበልጥ ያጠናክራል ብለዋል። የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ በበኩላቸው፤ አዳዲስ የሕክምና ሙከራዎች የሕብረተሰቡን ጤናና ደህንነት ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል። የሕክምና ሙከራዎች ፈቃድና ቁጥጥርን በዓለም አቀፍ መስፈርቶች መሠረት ዲጂታላይዝ ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት ውጤቶች መገኘታቸውን ተናግረዋል። ለአብነትም የማርበርግ ቫይረስ ሕክምናን ወደ ተግባር ለማስገባት ፈጣን ምላሽና ቀልጣፋ አገልግሎት በመሰጠቱ የቫይረሱን ስርጭት መግታት መቻሉን አንስተዋል። ኢትዮጵያ በሕክምና ሙከራ አገልግሎት ዘርፍ ከአፍሪካ ተመራጭ ሀገር ለመሆን በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑንም አክለው ገልጸዋል።
ስፖርት
የዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ትኬትን ለመቁረጥ 90 ደቂቃዎች የቀራቸው ቀይ ቀበሮዎቹ
May 23, 2026 277
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 15/2018 (ኢዜአ)፦ በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው 16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። 16 ሀገራት በአራት ምድቦች ተከፍለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። ከየምድቡ አንደኛ እና ሁለተኛ የወጡ ስምንት ሀገራት በኳታር ለሚካሄደው 20ኛው ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ አልፈዋል። በተጨማሪም ከየምድቡ ሶስተኛ የወጡ አራት ሀገራት የመለያ ጨዋታ አድርገው ቀሪ አላፊ ብሔራዊ ቡድኖች ይለያሉ። በውድድሩ ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንም በምድብ አንድ በአራት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ወደ መለያ ጨዋታው ተሸጋግሯል። ብሔራዊ ቡድኑ በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ቱኒዚያን 1 ለ 0 መርታቱ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ አሸጋግሮታል። ቀይ ቀበሮዎቹ ለዓለም ዋንጫው ለማለፍ ከሞዛምቢክ ጋር ዛሬ ከምሽቱ አንድ ሰዓት በመሐመድ ስድስተኛ ኮምፕሌክስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። በምድብ ሶስት ተደልድሎ ጨዋታውን ያደረገው የሞዛምቢክ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በአራት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወቃል። የሞዛምቢክ ቡድን በመጨረሻ የምድብ ጨዋታው አንጎላን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለመለያ ጨዋታ ደርሷል። በአሜሪካዊው አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር የሚመራው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ሞዛምቢክን ማሸነፍ ከቻለ በኳታር አስተናጋጅነት ለሚከናወነው 20ኛው ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ያልፋል። ቡድኑ ለዓለም ዋንጫ ካለፈ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ይሆናል። ቀይ ቀበሮዎቹ ለጨዋታው የመጨረሻ ልምምዳቸውን ትናንት ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ሁሉም ተጫዋቾች በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙም አመልክቷል። አጥቂው ዳዊት ካሳው በውድድሩ ላይ በተመለከታቸው ሁለት ቢጫ ካርዶች ምክንያት በዛሬው ጨዋታ ላይ አይሰለፍም። አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር ከጨዋታው በፊት በሰጡት አስተያየት ለኢትዮጵያ ህዝብ በእግር ኳስ ደስታ መስጠት እንፈልጋለን ሲሉ ገልጸዋል። የቡድኑ ተጫዋቾችን ኢትዮጵያ ለዓለም ዋንጫ እንድታልፍ ቁርጠኛ ናቸው፤ ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንገባለን ብለዋል። በሌላኛው የመለያ መርሐ ግብር ጋና ከዩጋንዳ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። አዘጋጇ ሞሮኮ፣ ግብጽ፣ ኮትዲቯር፣ ካሜሮን፣ ታንዛንያ፣ ማሊ፣ ሴኔጋል እና አልጄሪያ በቀጥታ ወደ ዓለም ዋንጫ ያለፉ ሀገራት ናቸው። 16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ እስከ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል። በአፍሪካ ዋንጫው እየተሳተፉ ካሉ 16 ሀገራት መካከል 10ሩ በጥቅምት እና ህዳር ወር 2019 ዓ.ም በኳታር ለሚካሄደው 20ኛው የፊፋ ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ያልፋሉ። በዓለም ዋንጫው 48 ሀገራት ይሳተፋሉ።
ማይክል ካሪክ የማንቸስተር ዩናይትድ ቋሚ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ
May 22, 2026 352
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 14/2018 (ኢዜአ)፦ ማንቸስተር ዩናይትድ የቀድሞ ተጫዋቹን ማይክል ካሪክን የሁለት ዓመት ውል በመስጠት የክለቡ ቋሚ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን አስታወቀ። የ44 ዓመቱ ማይክል ካሪክ ክለቡን በቋሚነት እንዲመራ የተመረጠው፣ የቀድሞው አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ ጥር ወር ከኃላፊነታቸው መሰናበታቸውን ተከትሎ በጊዜያዊ አሰልጣኝነት በነበረው አጭር ቆይታ ያስመዘገበውን መልካም ውጤት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው። ካሪክ ቡድኑን ከተረከበ በኋላ ባሳየው ተከታታይ የውጤት መሻሻል ክለቡ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መሳተፍ የሚችልበትን ደረጃ ማረጋገጥ መቻሉን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል። ማንቸስተር ዩናይትድ ባለፈው እሁድ ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ማሸነፉን ተከትሎ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ ሦስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁን አረጋግጧል። አሰልጣኙ ቡድኑን በጊዜያዊነት መምራት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ካደረጋቸው 16 ጨዋታዎች መካከል በ11ዱ ድል ቀንቶታል። ማንቸስተር ዩናይትድ ካሪክ በጥር 13 ቀን 2026 (እ.ኤ.አ) ከተሾመበት ጊዜ ጀምሮ 36 ነጥቦችን የሰበሰበ ሲሆን፣ ይህም በሊጉ ካሉ ክለቦች ሁሉ በወቅቱ ከፍተኛው የተሰበሰበ ነጥብ ሆኖ ተመዝግቧል። ይህንን ተከትሎም ካሪክ ለፕሪሚየር ሊጉ የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ሽልማት ከታጩት ስድስት እጩዎች ዝርዝር ውስጥ ተካቷል። ማይክል ካሪክ ሹመቱን አስመልክቶ በሰጠው አስተያየት፣ ከ20 ዓመታት በፊት ወደ ኦልድ ትራፎርድ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ የክለቡን ታላቅነት እንደሚረዳ ገልጾ፣ ይህንን ልዩ ክለብ በቋሚነት የመምራት ኃላፊነት በመስጠቱ ታላቅ ኩራት እንደተሰማው ተናግሯል። ባለፉት አምስት ወራት የተጫዋቾች ስብስብ ያሳየው የአንድነትና የጽናት መንፈስ የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሶ፣ ወደፊት ክለቡን ወደ ቀድሞ ታላቅነቱ ለመመለስና ለትላልቅ ዋንጫዎች ለመፎካከር በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አስታውቋል። የቀድሞው አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በክለቡ በነበራቸው የ14 ወራት ቆይታ ማብቂያ ላይ በተመዘገቡ ደካማ ውጤቶች እና በታክቲክ ምርጫዎች ዙሪያ ከክለቡ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በነበራቸው አለመግባባት ሳቢያ ከኃላፊነታቸው መሰናበታቸው ይታወሳል። ማይክል ካሪክ እ.ኤ.አ በ2021 የቀድሞው አሰልጣኝ ኦሌ ጉናር ሶልሻየር ከተሰናበቱ በኋላም ቡድኑን ለሦስት ጨዋታዎች በጊዜያዊነት መምራቱ የሚታወስ ሲሆን፣ በአሁኑ ቆይታው በሜዳ ላይና ከሜዳ ውጪ ባሳየው አመራር የክለቡን ባለሥልጣናትና ደጋፊዎች አድናቆት አትርፏል። አዲሱ ቋሚ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ በማንቸስተር ዩናይትድ በነበረው የ12 ዓመታት የተጫዋችነት ዘመን አምስት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን፣ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ እና ኤፍኤ ካፕ ማሸነፍ የቻለ የክለቡ ስኬታማ ተጫዋች እንደነበር ቢቢሲ በዘገባው አውስቷል።
ፔፕ ጋርዲዮላ ከ10 ዓመታት በኋላ ማንችስተር ሲቲን እንደሚለቅ ተረጋገጠ
May 22, 2026 306
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 14/2018 (ኢዜአ)፦ የማንቸስተር ሲቲ ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከእሁዱ የአስቶንቪላ የሊጉ የመጨረሻ ጨዋታ በኋላ ክለቡን እንደሚለቅ ይፋ ሆኗል። ማንቸስተር ሲቲ የአሰልጣኙን መልቀቅ አረጋግጧል። ስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ባለፉት 10 የፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመናት ክለቡን በመምራት ስድስት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን ጨምሮ 17 ዋና ዋና ክብሮችን ማሳካት መቻሉን ቢቢሲ ዘግቧል። የ55 ዓመቱ አሰልጣኝ የመጨረሻ ጨዋታውን እሁድ በኢትሃድ ስታዲየም ከአስቶንቪላ ጋር እንደሚያደርግ ተገልጿል። ማንቸስተር ሲቲ የአሰልጣኙ ውል ከመጠናቀቁ አንድ ዓመት ቀደም ብሎ ለስንብቱ ዝግጅት እያደረገ እንደነበር ቢቢሲ ስፖርት በዘገባው አስታውሷል። አሰልጣኝ ጋርዲዮላ ስለ ስንብቱ በሰጠው አስተያየት "የምለቅበትን ምክንያት አትጠይቁኝ፤ ምንም አይነት የተለየ ምክንያት ባይኖርም የመልቀቂያዬ ጊዜ መድረሱን ግን በውስጤ አውቀዋለሁ" ብሏል። አክሎም "በዚህ ዓለም ላይ ዘላለማዊ የሚሆን ምንም ነገር የለም፤ ቢኖር ኖሮ እዚሁ እቆይ ነበር። ዘላለማዊ ሆኖ የሚቀረው ግን ስሜቱ፣ ሰዎቹ፣ ትዝታዎቹ እና ለክለቡ ያለኝ ፍቅር ብቻ ነው" ሲል ስሜቱን ገልጿል። አሰልጣኙ ከሳምንት በፊት ከሲቲ የመጨረሻ ዋንጫውን በኤፍኤ ካፑ አንስቷል። የ55 ዓመቱን ፔፕ ጋርዲዮላ ለመተካት ቀደም ሲል በማንቸስተር ሲቲ በረዳትነት የሰራውና የቀድሞው የቼልሲ አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ቀዳሚው እጩ መሆኑ ተጠቁሟል። የጋርዲዮላ ከክለቡ የመልቀቅ ዜና ይፋ የሆነው ማንቸስተር ሲቲ የ2025-26 የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን በአርሰናል ከተቀማ ከሶስት ቀናት በኋላ ነው። ማንቸስተር ሲቲ ማክሰኞ ከቦርንማውዝ ጋር አቻ መለያየቱን ተከትሎ አርሰናል ከ22 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን መሆን መቻሉ ይታወሳል።
ነገሌ አርሲ እና ምድረ ገነት ሽሬ ነጥብ ተጋሩ
May 21, 2026 667
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 13/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 33ኛ ሳምንት ነገሌ አርሲ እና ምድረ ገነት ሽሬ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተካሄዷል። ጨዋታውን ተከትሎ ነገሌ አርሲ በ52 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። ነገሌ አርሲ የሁለተኝነት ደረጃን ከመቻል የመረከብ እና ከሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት የማጥበብ እድል አልተቀመበትም። ምድረ ገነት ሽሬ በ37 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ዛሬ አስቀድመው በተደረጉ የ33ኛ ሳምንት ጨዋታዎች የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና አርባምንጭ ከተማን 3 ለ 0 ሲረታ አዳማ ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል። ጨዋታዎቹን ተከትሎ 33ኛ ሳምንት ተጠናቋል። የ34ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች በኋላ ከግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳል።
አካባቢ ጥበቃ
በሚቀጥሉት አሥር ቀናት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎችን ጨምሮ የደቡብ ምዕራብ እና የምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ
May 22, 2026 497
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 14/2018 (ኢዜአ)፦በሚቀጥሉት አስር ቀናት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎችን ጨምሮ የደቡብ ምዕራብ እና የምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች በርካታ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በሚቀጥሉት አስር ቀናት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ ስፍራዎች ላይ ለዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች አንጻራዊ ጥንካሬ ይኖራቸዋል። ከእርጥበት አዘል የአየር ሁኔታው ጋር ተያይዞም የተሻለ የዝናብ ስርጭት እንደሚኖር ገልጿል። በዚህም በደቡብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ ምስራቅ፣ በምስራቅ እንዲሁም በስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች የተሻለ የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚኖር አመልክቷል። በሚቀጥሉት ቀናት ከሚኖሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በመነሳት፤ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎችን ጨምሮ የደቡብ ምዕራብ እና የምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ብዙ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ብሏል። አልፎ አልፎ በውኃ አካላትና በአካባቢ አየር ውስጥ ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በመነሳት፤ በጥቂት የደቡብ፣ የደቡብ ምዕራብ እና የምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች መጠቆማቸውን ገልጿል። ይህም ለግብርና ሥራ በቂ የአፈር ውስጥ እርጥበት እንዲኖር በማድረግ ለሰብሎች፣ ለግጦሽ ሳርና ለመጠጥ ውኃ አቅርቦት አዎንታዊ ተፅዕኖ እንዳለው አስታውቋል። ከተፈጥሮና ሰው ሠራሽ የውኃ ማጠራቀሚያዎችን አቅም ለማሳደግ እንዲሁም ለቋሚ ተክሎችም አዎንታዊ ሚና እንዳለው ገልጿል። በተጨማሪም ለመኸር ሰብሎች የማሳ ዝግጅትና ዘር ለመዝራት፣ ፍሬ በማፍራትና በተለያየ የእድገት ደረጃ ላይ ለሚገኙ የበልግ ሰብሎች የውኃ ፍላጎት መሟላት፣ ለአረንጓዴ ዕፅዋት ልምላሜ፣ ለመጠጥ ውኃና ለግጦሽ ሳር አቅርቦት መሻሻል የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው ተጠቁሟል። በተፋሰሶች ላይ ያለውን የእርጥበት ሁኔታ በተመለከተም ባሮ አኮቦ፣ መካከለኛና ታችኛው አባይ፣ በአብዛኛው ኦሞ ጊቤ፣ በላይኛውና መካከለኛው ስምጥ ሸለቆ ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ የገጸ ምድር ውኃ ፍሰት ይኖራቸዋል ብሏል። በላይኛው ገናሌ ዳዋ፣ ኦጋዴን፣ ታችኛው ተከዜ እንዲሁም በላይኛውና መካከለኛው ዋቤ ሸበሌ ደግሞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው የገጸ ምድር ውኃ ፍሰት እንደሚያገኙ ይጠበቃል ብሏል። በተጨማሪም ደረቅ የገጸ ምድር ውኃ ፍሰት የሚኖራቸው በአብዛኛው አፋር ደናኪል፣ አይሻ፣ መካከለኛና ታችኛው አዋሽ እንዲሁም በታችኛው ገናሌ ዳዋ መሆኑን የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ ሲል ገልጿል። በሌላ በኩል በበልግ ወቅት የሚኖረው የሙቀት መጠን መጨመርና በሌሊት ደግሞ የሚታየው ወበቅ አንዱ የዚህ ወቅት ክስተት መሆኑን ጠቁሟል። ከሚኖረው ከፍተኛ የፀሐይ ኃይል ጋር ተያይዞም በተለይም በጋምቤላ፣ በአፋር፣ በሶማሌ፣ በቤንሻንጉል-ጉሙዝና በምዕራብ አማራ አካባቢዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት ከ32 እስከ 41 ዲግሪ ሴልሺየስ እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ ብሏል።
በክልሉ ከ261 ሺህ ሔክታር መሬት ላይ ችግኞችን ለመትከል የ ጉድጓድ ቁፋሮ ስራ ተጀምሯል
May 20, 2026 829
ባህርዳር ፤ግንቦት 12/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ከ261 ሺህ ሔክታር በላይ በሆነ መሬት ላይ ችግኞችን ለመትከል የጉድጓድ ቁፋሮ ስራ መጀመሩን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። በቢሮው የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር እስመለዓለም ምህረት ለኢዜአ እንደገለፁት የክልሉን የደን ሽፋን ቀድሞ ወደ ነበረበት ለመመለስ በትኩረት እየተሰራ ነው። በመጭው ክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ1 ነጥብ 7 ቢሊዮን በላይ የዋንዛ፣ ወይራ ፣ ዝግባ ፣ ፅድ ፣ አኬሺያ ዲከረንስ፣ ባህር ዛፍ፣ የፍራፍሬና ሌሎች ችግኞችን ለመትከል እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የችግኝ ተከላውን በስኬት ለማከናወን እስካሁን 401 ሚሊዮን በላይ ጉድጓዶችን በማስቆፈር ለተከላ ዝግጁ ማድረግ መቻሉን አረጋግጠዋል። በቀጣይም የአረንጓዴ አሻራ ግብን ለማሳካት ተጨማሪ የችግኝ መትከያ ጉድጓዶችን የማስቆፈር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል። ባጠቃላይ በክረምቱ ለሚካሄደው ችግኝ ተከላ 261 ሺህ 297 ሄክታር መሬት ከወዲሁ ተለይቶ የጉድጓድ መቆፈር ስራው እየተካሄደ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። በምዕራብ ጎጃም ዞን የሰከላ ወረዳ አርሶ አደር መኮነን ልንገር እንደገለጹት ፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር መጀመሩ ተራቁተው የነበሩ አካባቢዎችን መልሰው በደን እንዲሸፈኑ ለማድረግ አስችሏል። መርሃ ግብሩ ለመኖ ፣ በንብ ማነብና እንስሳት እርባታ እያስገኝ ያለውን ተጠቃሚነት ለማስፋት በመጭው ክረምት በሚካሔደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በግልና በወል ቦታዎች ችግኝ ለመትከል ጉድጓዶችን እያዘጋጀን ነው ብለዋል። የሚተከሉት ችግኞች አያስገኙ ያለውን ጠቀሜታ በመረዳት በየዓመቱ ችግኞችን እያለማሁ ነው ያሉት ደግሞ በደቡብ ጎንደር ዞን የደራ ወረዳ አርሶ አደር ካሴ መንግስት ናቸው። በመጭው ክረምት የሚተከሉ ችግኞች ተንከባክበን በማሳደግ ለውጤት ለማብቃት ከወዲሁ ዝግጅት ጀምረናል ነው ያሉት። ባለፈው ክረምት በነቃ የህዝብ ተሳትፎ ከተተከለው ከአንድ ነጥብ አራት ቢሊዮን በላይ ችግኞች ውስጥ 80 በመቶ የሚሆነው መጽደቁን ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በአፍሪካ የሚያጋጥሙ አደጋዎችን ለመከላከል ሀገራት ቅንጅታቸውን ሊያጠናክሩ ይገባል
May 19, 2026 876
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በአፍሪካ የሚያጋጥሙ አደጋዎችን ለመከላከል ሀገራት ቅንጅታዊ አሰራራቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለጸ። የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ከምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የአየር ፀባይ ትንበያ ማዕከል ጋር በመተባበር ለሁለት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየውን 73ኛውን የምስራቅ አፍሪካ የአየር ፀባይ አዝማሚያ ትንተናና ትንበያ ፎረም ተጠናቋል። በፎረሙ የቀጣናው ሀገራት ተወካዮች፣ የዘርፉ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ ዓለም አቀፍ አጋር ድርጅት ተወካዮች እና ሌሎች አካላት ተገኝተዋል። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተርና በዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዚዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ባለፉት ሁለት ቀናት በአፍሪካ ቀንድ ዙርያ ያሉ የኢጋድ አባል ሀገራት ያለፈው የበልግና መጪው ክረምት ወቅት የሚጠበቀውን የአየር ጠባይ ትንበያን አስመልክቶ ተወያይተዋል። በዚህም ሁሉም ሀገራት ከራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት የራሳቸውን የሜቲዎሮሎጂ መረጃዎችንና ከአካባቢያቸው አየር ሁኔታ በማገናዘብ ትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቅያ የሚሰጡበት ሁኔታ ላይ መነጋገራቸው አንስተዋል። ከአየር ትንበያው በመነሳትም የሚኖረው የአየር ሁኔታ በግብርና፣በውሃ፣በጤና ላይ ሊያደርሰ የሚችለው አሉታዊና አዎንታዊ ተፅእኖ በመገምገም ለቀጣይ ዝግጅት የሚደረግበት መሆኑ ተናግረዋል። እንዲሁም በህይወትና በንብረት ላይ ሊደርስ የሚችለውን የአደጋ ተጋላጭነትን ከመቀነስ አንፃር ጉልህ ድርሻ ያለው በመሆኑ መሰል መድረክ መዘጋጀቱ ጠቀሜታው የላቀ ነው ብለዋል። በአፍሪካ ቀንድ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚያጋጥሙ አደጋዎች በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ አደጋ እያደረሰ እንደሚገኝ ጠቁመው፤ ይህን ለመከላከል ሀገራት በቅንጅት መስራት አለባቸው ብለዋል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የአየር ንብረት ትንበያ እና የመተግበሪያ ማዕከል(ICPAC) ዋና ዳይሬክተር አብዲ ፊዳር (ዶ/ር) በአፍሪካ ቀንድ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የኢጋድ አባላት ሀገራት መረጃን መሰረት ያደረገ መረጃ በመለዋወጥ በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ አሳሰበዋል።
ለዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ እስካሁን ከ8 ነጥብ 6 ቢሊዮን በላይ ችግኝ ተዘጋጅቷል-ግብርና ሚኒስቴር
May 19, 2026 794
አዲስ አበባ፤ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ለዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እስካሁን ከ8 ነጥብ 6 ቢሊዮን በላይ ችግኝ የማዘጋጀት ስራ መከናወኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የአየር ንብረት ተፅዕኖን በመቀነስና የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ረገድ ዘርፈ-ብዙ ፋይዳዎችን እያስገኘ ይገኛል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በ2011 ዓ.ም የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የሀገር በቀል እጽዋቶችንና የተፈጥሮ ሀብቶችን ከመጠበቅ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተፅእኖ ለመከላከልና የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ መንግስት የተለያዩ ተግባራትን ከማከናወን አንጻር ግንባር ቀደም ለውጥ አስገኝቷል፡፡ ባለፉት ሰባት ዓመታት በተሰሩት ስራዎች አበረታች ውጤት የተመዘገበ ሲሆን፤ በመርሃ-ግብሩ 48 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል የሀገሪቱን አረንጓዴ ሽፋን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ተችሏል። የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ ልማት ከተፈጥሮ ኃብት ጥበቃ ባለፈ ዘርፈ-ብዙ ጥቅሞችን የሰነቀ ሲሆን የአየር ንብረት ተጽዕኖን በመቀነስ ለኢትዮጵያ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ መስኮች ዘርፈ-ብዙ ፋይዳ እያስገኘ ይገኛል፡፡ ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ ለሚካሔደው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ ሰፊ ዝግጅት በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡ የግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሀብት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፋኖሴ መኮንን ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ ባለፉት ሰባት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ ላይ የተከናወኑ ሥራዎችና የተመዘገቡት አበረታች ውጤቶች ትልቅ ምስክር ናቸው፡፡ የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የሁለተኛው ምዕራፍ ማጠናቀቂያ መሆኑን የገለጹት መሪ ሥራ አስፈጻሚው፤ ቀደም ሲል ከነበሩ የአረንጓዴ አሻራ አፈጻጸሞች የተወሰዱ ተሞክሮዎችን መነሻ በማድረግ የዘንድሮው ዕቅድ በቁጥር ደረጃ ከፍ ያለ መሆኑን አብራርተዋል። በዚህም መሠረት 8 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ ተይዞ ሰፊ ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውንና አሁን ላይ ለተከላው የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ ጠቁመው የስነ-ምህዳር ሁኔታን መሠረት ያደረገ የችግኝ ዝርያዎች መረጣ መከናወኑንም ጠቅሰዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ችግኝ የሚተከሉባቸው ጉድጓዶችን የማዘጋጀት ሥራ በስፋት እየተከናወነ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አሁን ላይ በበርካታ ዜጎች ዘንድ ባህል እየሆነ መምጣቱንና የተሳታፊዎች ቁጥርም ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን ገልጸዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አንድነት በተግባር የሚረጋገጥበት ትልቅ አገራዊ ኩነት በመሆኑ፣ መላው ሕዝብ በኃላፊነት ስሜትና በቀዳሚነት እየተሳተፈበት ይገኛል ብለዋል። ለዘንድሮው የችግኝ ዝግጅት ከተከናወኑ ሥራዎች መካከል 40 በመቶው ሀገር በቀል የደን ዛፎች ላይ ትኩረት ማድረጉን ጠቅሰው፣ 60 በመቶው ደግሞ ለምግብ ዋስትናና ለሌሎች ዘርፈ-ብዙ ጥቅሞች የሚውሉ የፍራፍሬና የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች መሆናቸውን አስረድተዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ ነው
May 13, 2026 2146
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ በጸጥታ፣ በዘላቂ ልማት እና በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ተቋማዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፈርመውታል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በዚሁ ወቅት በሰጡት መግለጫ፣ የአፍሪካ ህብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል። አጋርነታቸውን ይበልጥ ተቋማዊ የሚያደርገው ይህ ስምምነት በቁልፍ ዘርፎች ላይ የተመዘገቡ ስኬቶችንና የወደፊት ዕቅዶችን መነሻ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ በቋሚ አባልነት አለመካተቷን ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነት ነው ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ ይህም የምክር ቤቱን ተቀባይነትና ውጤታማነት እንደሚጎዳው አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ሊስተካከል እንደሚገባ ጠቅሰው አፍሪካ ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወጥታ ለአረንጓዴ ኢነርጂ ሽግግር የማምረቻና የማጣሪያ ማዕከል መሆን እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው፣ የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ እና የተባበሩት መንግሥታት የ2030 አጀንዳ የተጣጣሙ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ፈተናዎችን ለመፍታት በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ማሻሻያ ተደርጎ የአፍሪካ ሀብቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በናይሮቢ የተካሄደው የ"አፍሪካ ፎርዋርድ" (Africa Forward) ጉባኤ ውጤቶች ክትትል እንዲደረግባቸው አሳስበዋል፡፡ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብትን ጨምሮ ቋሚ መቀመጫና ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራት የሚለውን የአህጉሪቱን ጥያቄ በድጋሚ አረጋግጠዋል። ይህ ስምምነት በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለውን ስልታዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል። 10ኛው የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወቃል፡፡
አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ነው
May 13, 2026 1259
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ተግባር መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት እየተካሄደ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የመንግስታቱ ድርጅት በሁሉም ዘርፎች ቀዳሚ ተግባር አፍሪካን የማድረግ የፖለቲካም ሆነ የሞራል ግዴታ አለበት። አፍሪካ አህጉራዊ ግጭቶችን በማርገብ፣ አህጉራዊ ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናና ሌሎች የሰላምና ጸጥታ ኢኒሼቲቮች አስደናቂ መሆናቸውን ገልጸዋል። አፍሪካ በዓለም ሁለንተናዊ እንቅስቀሴ ላይ ያላት ሚና የጎላ መሆኑን እንገነዘባለን ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ በታሪክና በዓለም ኢ-ፍትሐዊ አሰራር የደረሰባትን በደል ለመቀልበስ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት ባልወጡበት ወቅት የተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት አህጉሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረጋቸው ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ ባልተሳተፈችበት የተቋቋሙ የዓለም አቀፍ ተቋማት ኢ-ፍትሐዊነት አፍሪካን ብዙ አሳጥቷታል ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካ ለመፍታት የተጀመሩ ኢንሼቲቮችን መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት አፍሪካዊ ግጭቶች በአፍሪካ ማዕቀፍ እንዲፈቱ በመሪነት ከመሳተፍ ባለፈ የአፍሪካ ሕብረትን ጥረት እንደሚደግፍ ጠቁመዋል። አፍሪካ በወሳኝ ማዕድናትና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም እንዳላት ገልጸው፤ ሀብቷን እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ የምታቀርብበትን መንገድ መቀየስ ይገባል ብለዋል።
አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም ለማቋቋም ወሰነች
May 13, 2026 1181
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የተዛባውን የዓለም የፋይናንስ ስርዓት የሚያጣጥም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (African Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እየተካሄደ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መድረኩ በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ፣ ዘላቂ ልማት፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አስተዳደርና በተለዋዋጭ ዓለም የአፍሪካ ፈተናዎች ዙሪያ የሚያተኩር ነው። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትን ጨምሮ የዓለም ነባራዊ ሁኔታ በአሕጉሪቱ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚደረግ ጥረት ቢኖርም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሰቃዩበትና የሚሰደዱበት አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል። ይሄውም በአፍሪካ አስተማማኝና ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን በመጥቀስ፣ ከጸጥታ ባለፈ በመልካም አስተዳደር፣ በልማትና የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት አስቻይ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል። በአፍሪካ የልማት ፋይናንስ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን የገለጹት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር፤ ዓለም አቀፉ የፋይናንስ አስተዳደር የአጀንዳ 2063 እና 2030 ግቦችን ለማሳካት እንቅፋት ፈጥሯል ብለዋል። በተለይም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተቋቋሙና አሁንም ያለው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት ለአፍሪካ ፍላጎትና እውነታ ምላሽ የማይሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል። በመሆኑም አፍሪካን ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ስርዓት ጋር ለማጣጣም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (Africa Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን ገልጸዋል። ይሄውም የአፍሪካ ሕብረት በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ሲሰራ ቆይቶ እ.አ.አ በመጪው ሰኔ ወር 2026 በሞሪሼስ በይፋ እንደሚጀመር አስታውቀዋል። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በአፍሪካ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ገልጸው፤ በብዙ ሀገራት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ንሯል፤ በአንዳንድ ሀገራት የነዳጅ ዋጋ ከ100 እስከ 150 በመቶ ጨምሯል ነው ያሉት። የአፍሪካ ሕብረት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በትብብር ሲሰራ መቆየቱን በመጥቀስ፣ የእርስ በርስ ትብብሩን ለማጠናከር በቅርበት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ተቋማት አጋርነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው በመግለጽ፤ በተቋማቱ መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ትብብር ወደፊት ማሻገር ያስፈልጋል ብለዋል።
የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት በአዲስ አበባ ይካሄዳል
May 13, 2026 1223
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ 10ኛው የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት በሕብረቱ ዋና መቀመጫ ዛሬ በአዲስ አበባ ይደረጋል። በውይይቱ ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እንደሚገኙ ይጠበቃል። ውይይቱ በሁለቱ ወገኖች መካከል በአፍሪካ ልማት እና በዓለም አቀፍ አስተዳደር ዙሪያ ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማጠናከርን ያለመ ነው። በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለውን ቅንጅት፣ የጋራ ተጠያቂነት እና ትብብርን በልማት፣ በአስተዳደር፣ በሰብአዊ ድጋፍ እና በሰላም ግንባታ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ያላቸውን ትስስር ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ይካሄዳል። በዚህ የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ላይ በርካታ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች የሚዳሰሱ ሲሆን፣ በተለይም የአጀንዳ 2063 እና የሁለተኛው የአስር ዓመት ምዕራፍ የትግበራ ዕቅድ አፈፃፀምን ማፋጠን እንዲሁም አፍሪካን በዓለም አቀፍ ፖሊሲ እና አስተዳደር ውስጥ ያላትን ማዕከላዊ ሚና መጠበቅ በሚሉ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት ያደርጋል። በተጨማሪም "ከጥገኝነት ወደ ሉዓላዊነት" የተሸጋገረ የልማት ፋይናንስ፣ የ2026 የአፍሪካ ሕብረት የዓመቱ መሪ ቃል የሆነው ዘላቂ የውሃ አቅርቦት እና የንጽህና አጠባበቅ፣ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ተቋማት ሪፎርም እና አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ያላትን ውክልና የተመለከቱ ጉዳዮች ውይይት ይደረግባቸዋል። መድረኩ ለአህጉራዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔዎችን ማምጣት፣ የአገር ውስጥ ሀብት ማሰባሰብን ማሳደግ፣ የወጣቶች እና የሴቶች ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንዲሁም በአህጉራዊ እና በዓለም አቀፍ የልማት የቅድሚያ ትኩረቶች መካከል ያለውን ትስስር ማጠናከር ወሳኝ መሆኑ አጽንኦት የሚሰጥበት እንደሆነ ተመላክቷል። ከውይይቱ ከሚጠበቁ ውጤቶች መካከል የተሻለ ስትራቴጂካዊ ቅንጅት፣ ፍትሐዊ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ለውጥ፣ በአፍሪካ ህብረት የዓመቱ መሪ ቃል ዙሪያ ጠንካራ ቅንጅት መፍጠር እና በተባበሩት መንግሥታት ሥርዓት ውስጥ ፍትሐዊ የአፍሪካ ውክልና እንዲኖር የቀረቡ ጥሪዎችን ማጠናከር እንደሚገኙበት ህብረቱ ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የውይይቱን ውጤቶች አስመልክቶ የጋራ መግለጫ ይሰጣሉ።
ሐተታዎች
የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር
May 17, 2026 1461
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፦ የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በሀገራችን ሁሉም ክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን። 👉የግንቦት - ታላቁ ሁነት የምርጫ ጉዳይ ወቅታዊና ሀገራዊ አጀንዳ ሆኖ በሁሉም አካባቢዎች የዜጎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ተጠናክሮ የቀጠለበት ሳምንት ነው። መራጮች ካርዳችንን ለሀገርና ለህዝብ ይበጃል የምንለውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ብለዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎችም በተመቻቸላቸው ነፃ የአየር ሰዓትና የጋዜጣ ዓምድ የፖሊሲ አማራጮቻቸውንና ማኒፌስቷቸውን እያስተዋወቁ ቀጥለዋል። የተለያዩ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችም ዜጎች የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የግንዛቤ ማጎልበቻ ትምህርት በመስጠት ሙያዊና ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ። ለዘንደሮው ጠቅላላ ምርጫ በመራጮች ትምህርት ላይ ለሚሰማሩ 169 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዕውቅና መስጠቱ ይታወቃል። 👉የመጠጥ ውሃ ችግሮችን የመፍታት ጥረት ማሳያዎች በሳምንቱ በወላይታ ዞን ከ150 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የሆቢቻ ወረዳ ብዝሃ ቀበሌ የንጹህ መጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል። ፕሮጀክቶቹን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ (ዶ/ር) መርቀዋል። የፕሮጀክቶቹ ተመርቀው ለአገልግሎት መብቃት ለአካባቢው ማህበረሰብ ተጠቃሚነት የላቀ ትርጉም እንዳለው ተነስቷል። በተመሳሳይ የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ በቀብሪደሃር ከተማ በ407 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚካሄድ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ አስጀምረዋል። ከለውጡ በኋላ በክልሉ ከ370 በላይ የጥልቅ ውሃ ጉድጓዶች ተቆፍረው ለአገልግሎት መብቃታቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። በዚህም የመጠጥ ውሃ ሽፋኑ ከ19 ወደ 52 በመቶ ማሳደግ መቻሉ ታውቋል። በምስራቅ ሐረርጌ ዞንም የደደር ከተማንና የአካባቢውን ማህበረሰብ የመጠጥ ውሃ ችግር ለመፍታት ታስቦ የተገነባው ፕሮጀክትም ተጠናቆ ለአገልግሎት የበቃው በዚሁ ሳምንት ነበር። የፕሮጀክቱ ምረቃ ላይ የኦሮሚያ ክልል መሬት ቢሮ ሃላፊ መሰረት አሰፋ፣ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር እና ሌሎችም የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል። የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ ደደር ከተማን ጨምሮ ሌሎች በወረዳው ሶስት ቀበሌዎች የሚገኙ ከ100 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ታውቋል። 👉የጤና ጉዳይ የጤና ሚኒስቴር የተቀናጀ የህክምና እና የምርመራ ዘመቻ ከግንቦት 3 እስከ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በስምንት ክልሎች በሚገኙ 154 ወረዳዎች የሚያካሄድ መሆኑ የተገለጸውም በዚሁ ሳምንት ነበር። ይሄው መርሃ ግብር የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በይፋ ተጀምሯል። መርሃ ግብሩ በተለይም ትምህርት ቤቶችን ማዕከል በማድረግ የሚከናወን ሲሆን ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል አላማ ያደረገ መሆኑም ተገልጿል። 👉ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና በግብርና ሚኒስቴር ትብብር "ከተረጂነት ወደ ምርታማነት" በሚል መሪ ሃሳብ በሐዋሳ ከተማ የተካሄደው የውይይት መድረክም የሳምንቱ አበይት ጉዳይ ነበር። በመድረኩ ላይ የተገኙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቴ አለነ፣ ሀገራዊ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጂነት የመውጣት ጥረት ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል። በግብርና ልማት በተለይም የስንዴ ምርታማነትን በማሳደግ ከራስ አልፎ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የተመዘገበውን የላቀ ስኬት ለአብነት ጠቅሰዋል። በሌሎች የተለያዩ የግብርና የልማት ስራዎችንም በተጠናከረ መልኩ በማከናወን ምርታማነትን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ተችሏል ብለዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)፤ ከተረጂነት የመውጣት ጉዳይ የብሔራዊ ጥቅም አካል ሆኖ የመንግስት ስትራቴጂክ አጀንዳ ተደርጎ በፖሊሲ አቅጣጫ እየተመራ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም ምርታማነትን በማሳደግ የሀገርን ብልጽግና እውን በማድረግ የኢትዮጵያን የድህነት ታሪክ መቀየር ይኖርብናል ብለዋል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ዋና ስራ አስፈፃሚ ሠይፈ ደርቤ በበኩላቸው፤ እንደ ሀገር በምግብ ራስን ለመቻል የተጀመረው ግብ እንዲሳካ በቂ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል። ለዚህም ሚዲያ የማይተካ ሚና ያለው መሆኑን ገልጸው ኢዜአ ይህንን ሀገራዊ ትልም ለማሳካት የይዘት ስራዎችን በስፋት ተደራሽ የማድረግ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። 👉የምግብ ስርዓት ሽግግር በጋምቤላ ክልል ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚተገበረው የምግብ ስርዓት ሽግግር እና የኒውትሪሽን ፍኖተ-ካርታ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በጋምቤላ ከተማ በይፋ የተካሄደውም በዚሁ ሳምንት ነው። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን(ዶ/ር)፤ በክልሉ የተሟላ ስርዓተ ምግብን በማረጋገጥ ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልፀዋል። 👉ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በአሶሳ በአሶሳ ከተማ ሞዴል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ የተጀመረው በዚሁ ሳምንት ነው። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፤ የትምህርት ቤቱን ግንባታ አስጀምረዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ እስካሁን 34 ሞዴል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተገነቡ መሆኑን ያስታወሱት የትምህርት ሚኒስትሩ፤ በአሶሳ ከተማ የሚገነባው ትምህርት ቤትም በአንድ ዓመት ተጠናቆ ለአገልግሎት ይበቃል ብለዋል። 👉የሰላምና አብሮነት እሴት ግንባታ የሐረሪ ክልል፣ የኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞንና የማያ ከተማ አስተዳደር "የህዝቦች ሰላምና አብሮነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ የህዝብ ለህዝብ የሰላምና አብሮነት ኮንፍረንስ የተካሄደውም በዚሁ ሳምንት ነው። የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፤ የሐረርጌ ህዝቦች ትስስር በሀገሪቱ የታሪክ ማህደር ውስጥ ልዩ ስፍራ የሚሰጠውና ለታላቅ ማህበራዊ ውህደት ተምሳሌት እንደሚሆን ገልጸዋል። የኮንፈረንሱም ዓላማ የሰላም እሴት ግንባታና የልማት ትስስርን ይበልጥ ማጠናከር ስለመሆኑ አንስተዋል። 👉የግብርና ልማትና ምርታማነት በአማራ ክልል ለዘንድሮው የመኸር እርሻ ከ81 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ የተፈጥሮ የአፈር ማዳበሪያ በማዘጋጀት ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ያስታወቀው በዚሁ ሳምንት ነው። የአፈር ለምነትን በዘላቂነት ለማሻሻል ለተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ከ76 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለማዘጋጀት ታቅዶ እስካሁን ከ81 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ ኮምፖስት መዘጋጀቱ ታውቋል። 👉በኦሮሚያ ክልልም ለዘንደሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አካል የሆነው ከ10 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በአቮካዶ ተክል እንደሚሸፈን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል። በቢሮው የአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ ኃላፊ ሙሐመድሳኒ አሚን፤ በመጪው ክረምት ለሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም አቮካዶን ጨምሮ አስር አይነት የተለያዩ የፍራፍሬ ችግኞች ስለመዘጋጀታቸውም ተናግረዋል። በተለይም አቮካዶ፣ ሙዝ፣ ዘይቱን፣ ፓፓያ፣ ግሽጣ፣ ብርቱካን፣ አፕል፣ ሎሚና ሌሎች የፍራፍሬ ችግኞች በስፋት መዘጋጀታቸውን ጨምረው ገልፀዋል። በክልሉ የአቮካዶ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሻሻሉና ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ ዝርያዎችን በማዳቀል የችግኝ ዝግጅት ላይ በስፋት እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት። በክልሉ እስካሁን ከ80 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመደበኛና በተሻሻሉ የአቮካዶ ችግኞች መሸፈኑንም ገልጸዋል። 👉የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፤ በክልሉ ሎካ አባያና ደራራ ወረዳዎች በበልግ ወቅት በኩታ ገጠም እየለማ ያለውን የበቆሎ ማሳ በመስክ የተመለከቱትም በዚሁ ሳምንት ነው። ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንደገለጹት በክልሉ የሰብል ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ገበያን የሚያረጋጋ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተደረጉ ባሉ ጥረቶች ውጤት እየተገኘ ነው። በዚህም በበልግ ወቅትም ፆም የሚያድር መሬት እንዳይኖር በማድረግና ግብአቶችን በወቅቱ በማቅረብ እየተከናወነ ባለው የእርሻ ስራ የምርት ቁመናው ተስፋ ሰጪ መሆኑን ጠቅሰዋል። በበልጉ ያለውን አመቺ የዝናብ ስርጭት እንዲሁም የቴክኖሎጂ አቅርቦት በመጠቀም የተሻለ ምርት ለማግኘት የተያዘውን እቅድ ለማሳካት አሁን ላይ ለማሳ እንክብካቤ ስራ ትኩረት መሰጠቱን አመልክተዋል። 👉የኢንዱስትሪ ከተማዋ ኮምቦልቻ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ በኮምቦልቻ ከተማ ተገኝተው የመረቋቸው የምግብ ዘይት እና የቆርቆሮ ማምረቻ ፋብሪካዎች ሥራ የጀመሩትም በዚሁ ሳምንት ነው። የከተማ አስተዳደሩ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሁሴን ሙሄ፤ በኮምቦልቻ የኢንዱስትሪ ልማት ይበልጥ እያንሰራራ ስለመሆኑ አንስተዋል። በኢንዱስትሪ ከተማዋ ኮምቦልቻ በድምሩ 69 አምራች ኢንዱስትሪዎች መኖራቸውን ገልጸው ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን በማምረትና ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡትን በመተካት ከፍተኛ የሃብት ምንጭ እየሆኑ ነው ብለዋል።
የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር
May 10, 2026 1800
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 2/2018 (ኢዜአ)፡- በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በሀገራችን ሁሉም ክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን? የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምልከታ- በሱሉልታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሳምንቱ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ በ2 ሺህ 150 ሄክታር መሬት ላይ የለማ የስንዴ ሰብል ጎብኝተዋል። መንግሥት በግብርናው ዘርፍ በወሰዳቸው ስትራቴጂካዊ እርምጃዎች እየተገኙ ያሉ ውጤቶች አመርቂና ለቀጣይ ሥራዎች ስንቅ መሆናቸውን በጉብኝታቸው ወቅት ተናግረዋል። መሬት ጦም ማደር የለበትም በሚል ጽኑ እምነት የተጀመረው የበጋ ስንዴ ልማት አስደማሚ ውጤት እያስመዘገበ ስለመሆኑም አንስተዋል። ከልመና ራሳችንን መገላገል አለብን፤ ሊታረስና ሊለማ የሚችል መሬት መታረስ አለበት በሚል ጽኑ እምነት የበጋ ስንዴ ልማት መጀመሩን አስታውሰው፤ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አሁን ላይ አስደማሚ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል። የቱሪዝም ልማት የወፍ በረር ጉዟችን የቀጠለ ሲሆን ከሱሉልታ ቀጥታ ወደ አማራ ክልል ባህር ዳር አምርተናል። የባህር ዳር መዳረሻችን በጣና ሐይቅ ደቡባዊ ዳርቻ ላይ በ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት ይሆናል። የሪዞርቱ ግንባታ ተጠናቆ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ ባሳምንቱ ተመርቆ በይፋ ስራ ጀምሯል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "ገበታ ለሀገር" እቅድ መሰረት በሐይቁ ሌላኛው አቅጣጫ ከሚገኘው የጎርጎራ ብርሃን (ጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት) ጋር በመቀናጀት የጣናን የቱሪዝም ቀጣና ለማነቃቃት አላማ በማድረግ ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት መገንባቱ ተመላክቷል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በባህርዳር ከተማ ቆይታቸው በ3 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የሚገነባውን ፎር ፖይንትስ ባይ ሸራተን ጣና የሆቴል ፕሮጀክት ግንባታም አስጀምረዋል። በሚድሮክ ኢንቨስትመንት የሚገነባው ይህ ዓለም አቀፍ ሆቴልም በ18 ወራት ውስጥ ተገንብቶ የሚጠናቀቅ መሆኑ ታውቋል። የመልካ ቁንጡሬ ሁነት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ከኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር የአፍሪካ ዓለም አቀፍ የቅርስ ቀንን በዩኔስኮ በተመዘገበው በመልካ ቁንጡሬ–ባልጩት አርኪዮሎጂና ፓሊዮንቶሎጂ መካነ ቅርስ ስፍራ በሳምንቱ በተለያዩ ዝግጅቶች አክብሯል። የአፍሪካ ዓለም አቀፍ የቅርስ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ10ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ4ኛ ጊዜ በመልካ ቁንጡሬ–ባልጩት አርኪዮሎጂና ፓሊዮንቶሎጂ መካነ ቅርስ ስፍራ ተከብሯል። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ህይወት ኃይሉ፤ ባህላዊና የተፈጥሮ ቅርሶች ለሀገር ገጽታ ግንባታና ለኢኮኖሚ ዕድገት ያላቸውን አስተዋጽኦ ለማጎልበት የሚያስችሉ ተግባራት ይቀጥላሉ ብለዋል። ሀዋሳ ሀይቅ ዳርቻ የሀዋሳ ሀይቅ ዳርቻ ልማት የዲዛይን ሥራ ተጠናቅቆ ለህዝብ ይፋ የተደረገውም በዚሁ ሳምንት ነው። የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በወቅቱ እንደገለጹት ከተማዋን ለኑሮ፣ ለስራ፣ ለቱሪዝምና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ለማድረግ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ውጤት እያስገኙ ነው። የልማት ስራዎቹ ከተማዋ ሀገር አቀፍ ስብሰባዎችን¸፣ ስፖርታዊ ውድድሮችና ሌሎች ኩነቶችን በማስተናገድ ተመራጭ እየሆነች እንድትመጣ አድርገዋታል ብለዋል። የሀይቅ ዳርቻ ልማቱ ለከተማዋ ተጨማሪ ውበትና የተወዳዳሪነት አቅም ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ጠቁመው ለተግባራዊነቱ በትብብር እንደሚሰራ አመላክተዋል። የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥሉ ብለዋል። የሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻን በማልማትና ከአካባቢው መስህቦች ጋር በማስተሳሳር ሀይቁን የቱሪዝም ማዕከል የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም ተናግረዋል። ጅማ ዞን ጎማ ሁለት በጅማ አጠር ያለ ቆይታችን ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጅማ ዞን ጎማ ሁለት የምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው መቅረባቸውን በማስተዋወቅ የቅስቀሳ መርሃ ግብር ተካሂዷል። በዚህ የቅስቀሳ ስነ ስርአት ላይ የፓርቲው አባላትና አመራሮች እንዲሁም ደጋፊዎች በመውጣት የተሳተፉበት መሆኑን ለማየት ችለናል። በመርሃ ግብሩ ላይ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ነመራ ቡሊ፤ በፓርቲው አመራር ሰጪነት ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች እድገት እያስመዘገበች መሆኑን ገልጸው በመደመር እሳቤ የኢትዮጵያን እድገትና ማንሰራራት ለማስቀጠል ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል። በተመሳሳይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ርዕሰ መስተዳድሩ በሚወዳደሩበት ምስራቅ ጉራጌ ዞን ደቡብ ሶዶ ወረዳ የምርጫ ቅስቀሳና እጩ የማስተዋወቅ መርሐ ግብር የተካሄደውም በዚሁ ሳምንት ነበር። ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንዳሉት ብልፅግና ፓርቲ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችንን ሲያከናውን ቆይቷል። በባለፉት የለውጥ ዓመታት የሀገርን እድገትና የህዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን በመተግበር ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገቡን ተናግረዋል። የሽንሌ እመርታ በሳምንቱ በሶማሌ ክልል ሽንሌ ወረዳ የተገነባው የ10 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የኮንክሪት አስፋልት መንገድና በሽንሌ ጠቅላላ ሆስፒታል የተገነባው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በክልሉ ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ተመርቋል። በሽንሌ ወረዳ የመርማርሳ ከተማን ከድሬዳዋ ጋር የሚያስተሳስር የ3 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታንም አስጀምረዋል። የተገነቡት የልማት ስራዎች በተለይም ለወረዳው እመርታ መሆኑን የገለጹት አመራሮቹ በክልሉ ያለውን እምቅ ሃብት የማልማትና የዜጎችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራዎች ይቀጥላሉ ብለዋል። ሳተላይት በሐረር የሳተላይት የመገኛ መረጃ መቀቢያ ጣቢያ ተከላ ስራ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በተገኙበት በዚሁ ሳምንት ተጀምሯል። የሳተላይት የመገኛ መረጃ መቀበያ ጣቢያው በክልሉ ለሚከናወኑ የልማት ስራዎች ከፍተኛ እገዛ የሚያደርግ ሲሆን የመረጃ ግብዓት ከመሆን አኳያም ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተመላክቷል። የመንገድ ዲዛይን፣ አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ስራ ለሚያከናውኑ፣ የመሬት አጠቃቀምን በጥንቃቄ ለመቆጣጠር፣ ለይዞታ መረጋገጫና ሌሎችም የተሟላ መረጃ ለመስጠት የሚጠቅም መሆኑ ታውቋል።
የአፍሪካዊው የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣረ ዎዴ ማያ - በአዲስ አበባ
May 6, 2026 1624
ፐልስ ኦፍ አፍሪካ (Pulse of Africa-POA) ከኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ (AGA-Tech) ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁት ጉባኤ በአዲስ አበባ፣ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል። ይህ ጉባኤ ከሚያዚያ 29 እስከ 30 ቀን 2018 ዓ.ም "ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለተሻለች አፍሪካ" በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄድ አህጉራዊ መድረክ ነው። የአህጉሪቷ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ዳያስፖራዎች እና የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች የረጅም ጊዜ ትብብር የሚፈጥሩበት ይህ መድረክ፤ የአፍሪካን ትክክለኛ ትርክት ለዓለም ለማስተዋወቅ አልሟል። ታዋቂው የአፍሪካዊ ዲጂታል ታሪክ ተራኪ ጋናዊው በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) ጨምሮ የአህጉሪቷ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል። በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) በዲጂታል መገናኛ ብዙኅን የአፍሪካን ትክክለኛ ትርክትና ገፅታ ለዓለም የሚያስተዋውቅ ዓለም አቀፍ አንቱታን ያተረፈ የአህጉሪቷ የዘርፉ ፈርጥ ነው። ለኢትዮጵያ ጥልቅ ፍቅር ያለው ጋናዊው ታዋቂ ዩቲዩበርና የዲጂታል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) አዲስ አበባ ገብቷል። በጉባኤው ላይ የበርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) መገኘትም የአፍሪካን የዲጂታል ገፅታ መቀየር የሚያስችል የአህጉራዊ ይዘት ፈጠራ ትብብርን ለመፍጠር ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ይጠበቃል። የአየር በረራ መሐንዲስ ስልጡኑ በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) የዲጂታል ታሪክ ተራኪነት ጉዞ በሀገረ ቻይና ትምህርቱን በሚከታተልበት ወቅት ነበር የዩቱዩብ ይዘት ፈጠራን መሞከር የጀመረው። የመጀመሪያዎቹ የዲጂታል ይዘት ፈጠራ ሥራዎቹም አስቂኝ የነበሩ ቢሆንም ወላጅ አባቱ የአፍሪካን በጎ ገፅታ ለዓለም ማስተዋወቅ እንዳለበት የሰጡትን ምክር ተከትሎ ጉዞውን ቀይሯል። ባህላዊ ግንኙነትን ለማጠናከር የቻይንኛ ቋንቋ ቪዲዮዎችን ያዘጋጅ የነበረው ዎዴ ማያ፤ ወደ ጋና ተመልሶ በሰራቸው የመጀመሪያ ምዕራፍ ሥራዎቹ የሚፈለገውን ያህል ዕውቅና አላስገኙለትም ነበር። መነሻውን በአዲስ አበባ በማድረግ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ጉዞ በማድረግ አህጉሪቷን ለማስተዋወቅ ከሰራቸው ይዘቶች ውስጥ በሩዋንዳ የሰራው ቪዲዮ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ዕውቅናው እንዲናኝ አድርጎታል። ኢትዮጵያ በእርሱ አተራረክ ማዕከላዊ ስፍራ እንዳላት የሚናገረው ዎዴ ማያ፤ የአፍሪካን ያልተነገሩ ስኬቶችና የአፍሪካዊያን ፅናት በተከታታይ ለዓለም ማስተዋወቁን ተያይዞታል። አሁን ላይ የአፍሪካን ለውጥ፣ ተስፋና ዕድሎች ለዓለም ማህበረሰብ የሚያስተዋውቁ ዘጋቢ ፊልሞችን በመስራት የአህጉሪቷን ስሁት ትርክት በመቀየር ረገድ ጉልህ ስፍራ ከሚሰጣቸው ሰዎች አንዱ ሆኗል። በሚሊዮን የሚቆጠር ዕይታ ያላቸውን ዘጋቢ ፊልሞቹና የጉዞ ታሪኮችም ጊዜ ያለፈባቸው ስሁት ትርክቶችን በመሞገት የአፍሪካን ተስፋና ዕድሎች ለዓለም በመግለጥ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የኢትዮጵያን ዕድገትና ተስፋ ደጋግሞ የተረከው ዎዴ ማያ፤ በአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS) ወደ አዲስ አበባ መምጣቱም መድረኩን ተምሳሌታዊና ስልታዊ ያደርገዋል። ይህም የበርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) የግል ጉዞ ከመሆኑም በላይ፤ ኢትዮጵያ የአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ መድረክ ፈጠራና የታሪክ አተራረክ ለውጦች ማዕከላዊ ሚና በተግባር ያስመሰክራል። በዚህ ጉባኤ፤ እንደ ዎዴ ማያ ያሉ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች መሰባሰብ የአፍሪካን የዲጂታል ሥነ-ምኅዳር በማጠናከር ይዘት ፈጣሪዎች የአህጉራቸውን ትክክለኛ ገፅታ ለዓለም ለማስተዋወቅ ጉልህ ፋይዳ አለው። ለኢትዮጵያም የዎዴ ማያ መገኘት ሀገሪቱ ለአፍሪካ ዲጂታልና ባህላዊ ሕዳሴ ያላትን ቁርጠኝነት የበለጠ በማሳደግ አዲስ አበባን የአፍሪካ የዲጂታል ገፅታ ግንባታ ሃሳቦች መነሻነት በተግባር ያረጋግጣል።
የቴክኖሎጂ እምርታ -ሌላው የኢትዮጵያ ከፍታ ጉዞ አመላካች
May 3, 2026 1689
የቴክኖሎጂ እምርታ -ሌላው የኢትዮጵያ ከፍታ ጉዞ አመላካች በሙሴ መለሰ በኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የታየው የቴክኖሎጂ ለውጥ ወደ ዘመናዊው የዲጂታል ምህዳር እያሸጋገራት ይገኛል።የፖሊሲ ማሻሻያዎች፣ የመሰረተ ልማት እና የተቋማት ግንባታ ስራዎች ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በምታደርገው ጉዞ ውስጥ የሚጠቀሱ ዋንኛ ስራዎች ናቸው። ለውጡን ተከትሎ መንግስት "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" የተሰኘውን ስትራቴጂ በመቅረጽ የዲጂታላይዜሽን ስራውን የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ምሰሶ አድርጎታል። የለውጡ መንግስት ስልጣን ከያዘ በኋላ ቴክኖሎጂን እንደ አንድ የኢኮኖሚ ምሰሶ በመቁጠር "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" የተሰኘውን አጠቃላይ ስትራቴጂ ነድፎ ወደ ተግባር ገባ።ይህ ስትራቴጂ የሀገሪቱን የዲጂታል ጉዞ ከመሰረቱ የለወጠ ሲሆን፣የመጀመሪያው ትልቅ እርምጃም የቴሌኮም ዘርፉን ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት ማድረግ ነበር። የቴሌኮም ዘርፉ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት መደረጉ የሳፋሪኮም ወደ ኢትዮጵያ መግባትና የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶችን የማዘመን ስራ የኢንተርኔት ተደራሽነት እንዲሰፋ ምክንያት ሆኗል።በተለይም የአምስተኛ ትውልድ (5G) ቴክኖሎጂ አገልግሎት መጀመር ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንድትሆን አስችሏታል። የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ለውጡ የፋይናንስ ዘርፉ ላይ ውጤት አምጥቷል።እንደ ቴሌብር (telebirr) ያሉ የዲጂታል ክፍያ አማራጮች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ያለ ምንም የባንክ ሂሳብ በስልካቸው ብቻ ግብይት እንዲፈጽሙ በማድረግ፣ ሀገሪቱ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ እንድትሸጋገር ትልቅ መደላድል ፈጥረዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ረገድ የተመዘገቡት ስኬቶችም የኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ አድማስ ይበልጥ አስፍተውታል። የኢትዮጵያ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት መቋቋም ሀገሪቱ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያላትን ራዕይ ለዓለም ያሳየችበት አጋጣሚ ነው።ኢንስቲትዩቱ በአሁኑ ወቅት በጤናው ዘርፍ የካንሰር ህመምንና የሳምባ በሽታዎችን ቀድሞ መለየት የሚያስችሉ የኤአይ ውጤቶችን አበልጽጓል። በግብርናውም ረገድ የአፈርን ለምነትና የሰብል በሽታን በቴክኖሎጂ የመለየት ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን፣ ይህም በምግብ ዋስትና ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ሌላው ትልቅ ስኬት የሀገር በቀል ቋንቋዎችን በዲጂታል ዓለም ውስጥ ተወዳዳሪ ለማድረግ የተሰሩ የቋንቋ ፕሮሰሲንግ (NLP) ስራዎች ናቸው። ይህም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ውስጥ እንዲካተቱና ለተጠቃሚው ምቹ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። የፋይዳ (Fayda) ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮጀክት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን መረጃ በአንድ ማዕከል በመሰብሰብ፣ ለባንክ፣ ለጤናና ለሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች አስተማማኝ መሠረት ጥሏል። በአሁኑ ወቅት ዜጎች እንደ ፓስፖርት ማደስ፣ የንግድ ፈቃድ ማውጣትና ግብር መክፈል ያሉ አገልግሎቶችን ከቤታቸው ሆነው በኢንተርኔት ማከናወን መቻላቸው የለውጡ ፍሬያማነት ማሳያ ነው።የሳይንስ ሙዚየምም የወጣቶችን የፈጠራ አቅም የሚያሳይና የሀገሪቱን ቴክኖሎጂ የሚደግፍ ትልቅ አቅም ሆኗል።የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በቅርቡ መጠናቀቁ ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2025 ስትራቴጂው መጠናቀቁን ተከትሎ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ታህሳስ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ማስጀመራቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት ተደራሽነትን ማስፋት፣ ለዜጎች እኩል እድል መፍጠር እንዲሁም በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ደግሞ የስትራቴጂው ቁልፍ መሰረታዊ ትልሞች መሆናቸውን ገልጸዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ም ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት በማድረግ መዘጋጀቱን አንስተዋል።ትልሞቹ እንዲሳኩም በተለይ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ስራ እንደሚከናወን ጠቁመው፤ ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ እንዲያሻሽል ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል። በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ስራዎች የመደመር መንግስት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እንዲሳካም ሁሉም በትብብር መስራት እንዳለበት ነው ጥሪ ያቀረቡት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዲጂታል 2030ን ይፋ ሲያደርጉ የነበረው ትልቁ መልዕክት ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዓለም ተመልካች ሳይሆን ተሳታፊና መሪ ትሆናለች የሚል ነው። ስትራቴጂው በዋናነት"የፋይዳ" ዲጂታል መታወቂያን ከሁሉም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ጋር በማቀናጀት፣ ለዜጎች ቀልጣፋ አሰራርን መፍጠር፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዲጂታል ስራ እድሎችን ለወጣቶች ማመቻቸት እና ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ማዕከል (Innovation Hub) አድርጎ መገንባትን እንደ ዋነኛ ግብ አስቀምጧል። ይህም ሁሉን አቀፍ የኢንተርኔት ተደራሽነትን በማረጋገጥ፣ የመንግስት አገልግሎቶችን መቶ በመቶ ወረቀት አልባ በማድረግ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI) በግብርና፣ በጤናና በኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ በስፋት በመተግበር የምርታማነት አብዮት መፍጠርን ያለመ ነው። በዚህ ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው መሾማቸው ኢትዮጵያ በዘርፉ የጀመረችው ስራ በአህጉራዊ ደረጃ ያለውን ተቀባይነትና የተሰጣትን ትልቅ ኃላፊነት የሚያሳይ ነው።ኢትዮጵያ አሁን ላይ የደረሰችበት የቴክኖሎጂ ከፍታ፣ ሀገሪቱን በአፍሪካ የቴክኖሎጂ ተፎካካሪ ብቻ ሳይሆን የፈጠራ ምንጭ እንድትሆንም እያደረጋት ይገኛል። በዚህ ረገድም የቀጣዩ ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ስኬትም ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባና በቴክኖሎጂ የበለጸገች ሀገር የማድረግ ራዕይን ለማሳካት እና ለሀገራዊ ብልጽግና እንደ ቁልፍ ሞተር ሆኖ ያገለግላል።
ትንታኔዎች
እንግልትንና ብልሹ አሠራርን መቅረፊያ ብልኀት - መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት
May 17, 2026 3797
በኢዜአ ዐይን …! በዮሐንስ ደርበው እንግልትንና ብልሹ አሠራርን መቅረፊያ ብልኀት - መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ለእንግልትና ብልሹ አሠራር አጋላጭ ሁኔታዎች ይስተካከሉን የሚሉ እሮሮዎች በተለያዩ ሕዝባዊ ውይይቶች ሲነሱ ቆይተዋል። በተለይም በአንዳንድ ተቋማት መንግሥታዊ አገልግሎት ለማግኘት እዚያም እዚህም መንከራተት፤ደግሞም ወረፋ በመጠበቅ መጉላላት ብሎም ለጊዜና ገንዘብ ወጪ መዳረግ ይስተዋላል የሚሉ ሐሳቦች ተስተጋብተዋል። ሾተላይ ምንድነው? እንዴትስ ይከሰታል? ቀድሞ መከላከልስ ይቻላል? ባሳለፍነው ሳምንት … መንግሥትም የተነሱ ቅሬታዎችን ማረቅ የሚያስችል አሠራር በመንደፍ ሚያዝያ 18 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አንድ ብሎ አስጀመረ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ማዕከሉ አገልግሎት ባስጀመሩበት ወቅትም ዜጎቻችን ላይ ምሬት የሚፈጥሩ አሠራሮችን ፈትሾ ማስተካከል ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው ብለው ነበር። አሁን ላይም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሁን በተለያዩ ከተሞች እየተስፋፋ ነው።መስፋፋቱም በማዕከላት ብዛት፣በአገልግሎት መስጫ መስኮቶች ቁጥር እና በአገልግሎት ዐይነቶች እየተገለጠ ነው። በዚህም በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 2 ሺህ 260 አገልግሎቶች በአንድ ቋት የተደራጁ ሲሆን ይህ አሃዝም ለዘርፉ የተሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት እና ያለውን ፈጣን እድገት ያመላክታል። ጉዳዩ የዜጎችን የአገልግሎት አሰጣጥ ማላቅ፤ ብልሹ አሠራርንም መቅረፍ ነውና መንግሥት በልዩ ትኩረት ይዞታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድሬዳዋ አሥተዳደርና በሐረሪ ክልል ጉብኝት ባደረጉበት ወቅትም፤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን የምልከታቸው አካል ማድረጋቸው ለጉዳዩ የተሰጠውን ከፍያለ ትኩረት ያሳያል። በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሶብ የሞባይል አገልግሎትን በመረቁበት ወቅት ደግሞ፤ ካቀድናቸው አምስት የልማት ምሰሶዎች መካከል ቴክኖሎጂን ለአገልግሎት ዘርፉ እንደ ዋነኛ መሣሪያ በመጠቀም፣ የአገልግሎት ቅልጥፍናንና ተደራሽነትን ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሠራን ነው ብለዋል። አክለውም፤በመሶብ አገልግሎቶች የታየው ከፍተኛ የደንበኞች ዕርካታ የዚህን የሥራ ሞዴል ውጤታማነት በግልጽ አረጋግጧል፤ ይህም አሠራሩን ይበልጥ ማስፋፋት አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል። ዜጎቻችን ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙና ትርጉም ያለው የጊዜ ቁጠባ እንዲያገኙ ለማስቻል፤ እነዚህን የተቀናጁ አገልግሎቶች ይበልጥ ተደራሽ የማድረግ ሥራችንን እንቀጥላለን ሲሉም አረጋግጠዋል። በተመሳሳይ በዚሁ ጉዳይ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባጋራው መረጃ መሶብ ተንቀሳቃሽ የአውቶቡስ አገልግሎት፤ አስፈላጊ የሆኑ የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀጥታ ወደ ማኅበረሰቡ ለማድረስ የተወሰደ ትልቅ እርምጃ ነው ብሏል። የስምንት ተቋማትን አገልግሎት በአንድ ላይ በማቀናጀት፣ ዜጎች ረጅም ርቀት ሳይጓዙ ወይም የተለያዩ ቢሮዎችን ማንኳኳት ሳያስፈልጋቸው ምቹ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ መፍትሔ ይሰጣል ማለቱም ይታወቃል። የፌዴራል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል አንተነህ ማሞ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ደግሞ፤ ዘመናዊና ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት ምኅዳር በመፍጠር የተገልጋዮችን እርካታ ማረጋገጥ ያስቻለ ስኬት ተገኝቷል ብለዋል። በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሚሰጡ የመንግሥት አገልግሎቶችም ዜጋ ተኮር፣ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍልና የተገልጋዮችን ፍላጎት ማዕከል ያደረጉ መሆናቸውን አብራርተዋል። በዲጂታል 2030 የአገልግሎት አሰጣጥ አመላካች ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚጠቀሱ 50 ሀገራት መካከል አንዷ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል። ዜጎች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በኦንላይን በየትኛውም ቦታ ሁሉንም አገልግሎቶች እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሠራ ስለመሆኑም እንዲሁ። አገልገሎቱን ያገኙ አስተያየት ሰጭዎች ለኢዜአ እንዳሉት፤ እንግልትን ያስቀረ፣ ጊዜና ወጭን የቀነሰ ነውና ይስፋፋ፤ ተጠናክሮም ይቀጥል። #መሶብ_የአንድ_ማዕከል_አገልግሎት #የዜጎችን_እንግልትና_ብልሹአሠራርን_መቅረፍ #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #በኢዜአ_ዐይን
ባሳለፍነው ሳምንት …
May 17, 2026 1901
በዮሐንስ ደርበው ከግንቦት 2 እስከ ግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … · ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ጋር መምከራቸው ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ዋና ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂየቫ ጋር መክረዋል። በዚሁ ወቅትም በኢኮኖሚያዊ እድገት፣ በአጋርነት እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል። ለነበረን ጠቃሚ የሐሳብ ልውውጥና ቀጣይነት ላለው አጋርነትም ምስጋናዬ የላቀ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። · ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባዔ በኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ እና በፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በጋራ አዘጋጅነት በናይሮቢ በተካሄደው የአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባዔ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን ተሞክሮ አካፍለዋል። በዚሁ ወቅትም በተለይም የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማት እና የኃይል ሽግግርን በተመለከተው ውይይት ላይ ከተሞክሯችን የተቀዱ ከፍ ያሉ ሐሳቦች ተነስተዋል ብለዋል። አክለውም፤ ኢትዮጵያ በተነሱት ሁለት ዘርፎች የጀመረችውን ሥራ በማጠናከር የላቀ ሚና መጫወቷን ትቀጥላለች ሲሉ አረጋግጠዋል። · የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሳምንት የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንኳን ደህና መጡ ስል ሁልጊዜም በልዩ ኩራትና ደስታ ነው ሲሉ ተቀብለዋቸዋል። ከአቀባበሉ በኋላም፤ መሪዎች በጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። በዚህም መሠረት፤ በታዳሽ፣ የተቀናጀ እና ዘላቂ ኃይል እንዲሁም የዲጂታላይዜሽን ፕሮግራምን ለመተግበር የሚውል የ54 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ ብድርን ጨምሮ የ150 ሜጋ ዋት የጂኦተርማል የመንግሥትና የግል አጋርነት አዲስ የማዕቀፍ እና የፍኖተ ካርታ ስምምነት ተፈርሟል። · ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የስምንት አስርት ዓመታት ጉዞ ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የስምንት አስርት ዓመታት ጉዞን ምክንያት በማድረግ፣ "በሰላም አብሮ ለመኖር" በሚል መሪ ቃል ልዩ የመታሰቢያ ቴምብር ስብስብ ማውጣቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ አድርገዋል። እነዚህ አራት ቴምብሮች እ.ኤ.አ. በ1945 በሳን ፍራንሲስኮ የተባበሩት መንግሥታት ቻርተርን ከመፈረም ጀምሮ፤ በኮንጎ የሰላም አስከባሪ ኃይሎችን እስከማሰማራት እና በአፍሪካ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደውን የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ እስከ ማስተናገድ ያለውን የጋራ ታሪካችንን የሚተርኩ ናቸው ብለዋል። በዓለም የፖስታ ኅብረት በኩል ለ192 ሀገራት የተሰራጩት እነዚህ ቴምብሮች፤ ለአንድ ወቅት ብቻ ሳይሆን ለትውልድ ሁሉ የሚተርፍ የታሪክ ዐሻራ ማሳያ መሆናቸውንም አስታውቀዋል። በተያያያዘም፤ ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እና ለቡድናቸው፣ በዘመናዊው ታሪክ ውስጥ እጅግ ፈታኝ በሆነ ወቅት ላይ ሰላምን፣ ልማትን እና ሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር እያሳዩት ላለው ጽኑ አመራር ጥልቅ አድናቆታችንን እንገልጻለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። የተባበሩት መንግሥታት የጸናው ሀገራት ከመከፋፈል ይልቅ ውይይትን ስለመረጡ መሆኑን አስገንዝበው፤ ኢትዮጵያም ይህንኑ የሁልጊዜ ምርጫዋን ታጸናለች ሲሉ አረጋግጠዋል። · የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የአፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የአፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ባሳለፍነው ሳምንት ተካሂዷል። በዚሁ ወቅትም የምክክር ባህል እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበው፤ ጠንካራ የሲቪክ ማኅበረሰብ ባህል ግንባታ ደግሞ ያላሰለሰ የመነጋገር ልምምድ እና የሰከነ የወል መደማመጥን ግድ ይላል ብለዋል። የእስካሁን ሂደቱም በማኅበረሰባችን በየደረጃው የመደማመጥን ከፍ ያለ ጠቀሜታ አሳይቷል ሲሉም ገልጸዋል። ሂደቱ በሀገራችን ሁሉም ማዕዘናት የሚገኙ ከ90 በመቶ በላይ ኢትዮጵያውያንን አመለካከቶች እና የውይይት ውጤቶች ያንፀባረቀ ሆኗልም ነው ያሉት። ለሀገር ወሳኝ ፋይዳ የያዘው የምክክሩ ምዕራፍ ተጨባጭ ውጤት ወደሚያስገኘው ቀጣይ ምዕራፍ በሚሸጋገርበት በዚህ ወቅት፤ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለሀገራችን ሰላም፣ አንድነት እና ዘላቂ መረጋጋትን የሚያረጋግጥ የጋራ ፅኑ አቋም እና ገንቢ በሆነ መንገድ አስተዋፅኦ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል። · የገላን ኢንዱስትሪ ፓርክ መመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክን በመረቁበት ወቅት፤ ፓርኩ አስተማማኝ እና ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት በጀመርነው የብልጽግና ጉዞ ተደማሪ እመርታ ነው ብለዋል። ለመካከለኛ እና ከፍተኛ ኢንተርፕራይዞች ምቹ የንግድ ከባቢ ከመፍጠር ባሻገር በሺዎች ለሚቆጠሩ ወጣቶቻችን የሥራ ዕድል ይከፍታል ሲሉም ገልፀዋል። ፓርኩ የሀገራችን አምራቾች አቅማቸውን በማጎልበት፣ ምርታማነታቸውን ማሳደግና ተወዳዳሪነታቸውን በመጨመር ለከተማችን፣ ለሀገራችንና ለቀጣናው የሚተርፉበት ታላቅ እድልን ይዟል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ተኪ ምርቶችን በማምረት በአምራቾችና በሸማቾች መካከል ቀጥተኛና ቀልጣፋ የንግድ ትስስር ይፈጥራል፤ ምርቶችን ደግሞ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የሀገራችንን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግ ጉልህ ሚና ይጫወታል ሲሉ አስረድተዋል። · ዓለም አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ጉባዔ መጀመር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባሳለፍነው ሳምንት ዓለም አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ጉባዔን ባስጀመሩበት ወቅት፤ ኢትዮጵያ ለልማት በምታደርገው ቆራጥ ጥረት ውስጥ የሰው ተኮር የልማት አቅጣጫ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ዋና ጉዳዮች አንዱ መሆኑን አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት መንግሥት መጪው ትውልድ ጤናማ፣ ብቁ እና ውጤታማ እንዲሆን የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራምን ማዕከል በማድረግ ሁሉን አቀፍ ሥራ እየተገበረ እንደሚገኝም ተናግረዋል። በመላ ሀገሪቱ ከ35 ሺህ በላይ የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በማስፋፋት የነጻና አስገዳጅ ትምህርት ተደራሽ እንዲሆን እያደረግን ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ልጆች ላይ መሥራት በነገ ሀገር ላይ መሥራት በመሆኑ ተባብረን፣ በጊዜ የለንም መንፈስና በትጋት እንሥራ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። · የፖሊሲ ቀን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት፤ ባሳላፍነው ሳምንት በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያው የፖሊሲ ቀን ተከብሯል። በዚሁ ወቅትም፤ ውጤታማ ፖሊሲ ለሀገራዊ ዕድገት የጀርባ አጥንት መሆኑን አስገንዝበው፤ መንግሥት በግልፅ፣ ተተግባሪና ጥራት ባላቸው ፖሊሲዎቹ ለሕዝብ የገባውን ቃል እየተገበረ ስኬትም እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል። ሀገራችን ወሳኝ ምዕራፍ ላይ በምትገኝበት በዚህ ወቅት ብሔራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ በጂኦ-ፖለቲካዊና በቴክኖሎጂ ለውጦች ላይ ቀድሞ ምላሽ የሚሰጡ ጥናቶች ያስፈልጋሉ ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግሥት በዕውቀት ላይ ኢንቨስት በማድረግ እና ለማስረጃዎች ዋጋ በመስጠት፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆነ የፖሊሲ ሥነ-ምኅዳር ለመገንባት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። ለዚህ ስኬት ሁላችንም በጋራ እንሥራ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
የጤና ነገር
May 15, 2026 1723
በዮሐንስ ደርበው ሾተላይ ምንድነው? እንዴትስ ይከሰታል? ቀድሞ መከላከልስ ይቻላል? ሾተላይ የሚከሰተው RH-Negative የሆነች እናት RH-Positive የሆነ ፅንስ በምታረግዝበት ወቅት የእናትየው በሽታ የመከላከል ሥርዓት የፅንሱን ደም እንደ ባዕድ ነገር በመቁጠር በሚያመነጨው ንጥረ-ነገር (Antibodies) አማካኝነት መሆኑን የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። የጽንስና ማህጸን ስፔሻሊስት ዶክተር ዳንኤል ኃብተማርያም ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ከወሊድ ጋር በተያያዘው አር ኤች ኔጌቲቭ (RH-) ወይም ሾተላይ እየተባለ በሚጠራው በጽንስ ላይ የሚያጋጥም ችግር ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ሾተላይ ወይም አር ኤች ኔጌቲቭ (RH-) ምንድን ነው? እንደ ዶክተር ዳንኤል ማብራሪያ፤ ሰዎች ከሚታወቁበት አራቱ የደም ዓይነቶች ምደባ (ኤ፣ ቢ፣ ኤቢ እና ኦ) በተጨማሪ በቀይ ደም ኅዋስ ሰርፌስ ላይ በፕሮቲን መኖርና አለመኖር ይለያሉ። በዚህም መሠረት አር ኤች ፖዘቲቭ (RH+) እና አር ኤች ኔጌቲቭ (RH-) ተብለው እንደሚከፈሉ ያስረዳሉ። በዚህ ምደባ መሠረት ከአጠቃላይ ሕዝቡ 85 በመቶው አር ኤች ፋክተር ፖዘቲቭ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም ማለት በቀይ ደም ኅዋሳቸው ሰርፌስ ላይ ፕሮቲን አላቸው ማለት ነው ይላሉ። 15 በመቶው ደግሞ አር ኤች ኔጌቲቭ ወይም በቀይ የደም ኅዋሳቸው ሰርፌስ ላይ ፕሮቲን የሌላቸው ናቸው ሲሉ አብራርተዋል። አክለውም አር ኤች ኔጌቲቭ ወይም ፖዘቲቭ መሆን በሽታ እንዳልሆነ በአጽንኦት ገልጸው፤ ከወላጆች የሚወረስ መሆኑን አስገንዝበዋል። ስለዚህ አንድ ልጅ ሲወለድ እንደ ወላጆቹ አር ኤች ፋክተር መሠረት አር ኤች ፖዘቲቭ ወይም አር ኤች ኔጌቲቭ ይሆናል ሲሉ ይገልጻሉ። ይህን በምሳሌ ሲያስረዱም፤ አንዲት ሴት አር ኤች ፋክተሯ ኔጌቲቭ ሆኖ ጽንሷ ደግሞ አር ኤች ፖዘቲቭ ቢሆን ተገቢው የሕክምና ክትትል ካልተደረገ ብሎም የእናትና ልጅ ደም ንክኪ ከተፈጠረ የበሽታ መከላከል ሥርዓቷ የሚያመነጨው አንቲ ቦዲ ጽንሱን እንደ ባዕድ ነገር ስለሚቆጥረው ጉዳት (ሾተላይ) ያስከትላል ይላሉ። የአንቲ ቦዲ ሥራ ሴቷ ለአር ኤች ፖዘቲቭ የምትጋለጥበት ሁኔታ ከተፈጠረ ጽንሱን (አር ኤች ፋክተሩ ከእሷ ተቃራኒ ሲሆን) እንደ ባዕድ ነገር ቆጥሮ ሴትዮዋን ለመከላከል በጽንሱ ላይ ጥቃት ማድረስ መሆኑንም አመላክተዋል። መፍትሔው ምንድን ነው? ለማንኛውም ጤናማ የእርግዝና ሂደት የሕክምና ክትትል ማድረግ ቀዳሚ መፍትሔ መሆኑን መክረዋል። ከሾተላይ ጋር በተያያዘ ደግሞ በእርግዝና ወቅት የሚስትና ባልን አር ኤች ፋክተር መለየት ተገቢ መሆኑን አስገንዝበዋል። ይህን ተከትሎም አር ኤች ፋክተራቸው ተመሳሳይ ከሆነ ጽንሱም ከእነሱ ጋር ስለሚመሳሰል ጤናማ እንደሚሆን ገልጸዋል። በአንጻሩ ግን፤ አር ኤች ፋክተሯ ኔጌቲቭ የሆነች ሴት የባለቤቷ አር ኤች ፋክተር ፖዘቲቭ ከሆነ ወይም ለአር ኤች ፖዘቲቭ ተጋልጣ ሰውነቷ መከላከያ አምርቷል ወይስ አላመረተም የሚለው በሕክምና ምርመራ እንደሚታወቅ አስረድተዋል። ይህ ምርመራ ሲሠራ ውጤቱ ኔጌቲቭ ከሆነ ወይም ለአር ኤች ፖዘቲቭ ተጋልጣ ሰውነቷ መከላከያ አላመረተም የሚል ከሆነ በዚህኛው እርግዝናም ለአር ኤች ፖዘቲቭ ተጋልጣ፣ የእናትና የጽንስ ደም ንክኪ ኖሮ መከላከያ እንዳታመርት የሚሰጥ ሕክምና እንዳለ አረጋግጠዋል። ይህ ሕክምናም 28ኛ ሳምንት ላይ በመርፌ ለመጀመሪያ ጊዜ ይሰጣል ብለዋል። ከወለደች በኋላ ደግሞ የተወለደው ልጅ አር ኤች ፋክተር ታይቶ እንደእናቱ ከሆነ ተጨማሪ መድኃኒት እንደማያስፈልግና ከአባቱ ጋር ከተመሳሰለ ግን (አር ኤች ፖዘቲቭ ከሆነ) በመርፌ ተጨማሪ መድኃኒት በወለደች በ72 ሠዓት ውስጥ በመስጠት ለቀጣይ እርግዝናዎች ሰውነቷ መከላከያ እንዳያመነጭ ማድረግ እንደሚቻል አብራርተዋል። በሌላ በኩል ከሾተላይ ጋር በተያያዘ የሚደረጉ ሳይንሳዊ ያልሆኑ ልማዳዊ ድርጊቶችን ኮንነው፤ ትክክለኛው መፍትሔ ያለው የሕክምና ክትትል በማድረግ መሆኑን አስረድተዋል። እንዲሁም፤ በተለይም የጎንዮሽ ህመም ያለባቸው ሴቶች (የኩላሊት፣ የደም ግፊት፣ ስኳር እና ሌሎችም) ቀድመው ሐኪም አማክረው ወደ እርግዝና ቢገቡ እንደሚመከር ገልጸው፤ የቅድመ እርግዝና ክትትል ማድረግ ካልተቻለ እንኳን በእርግዝና ወቅት በአግባቡ ክትትል ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል። ለመከላከያ ትልቅ ትኩረት መስጠት ችግሩ ተፈጥሮ ከመታከም የተሻለና ተመራጭ መፍትሔ መሆኑንም ነው ያስገነዘቡት። #የጤና_ነገር #ኢዜአ #Ethiopian_News_Agency #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት
ለተቃና ነገ የኢትዮጵያ ትጋት አንዱ መገለጫ
May 11, 2026 2372
በዮሐንስ ደርበው ኢትዮጵያ ከምትከውናቸው ዐበይት ጉዳዮች መካከል ሰው ተኮር ተግባራት ቀዳሚው ነው። በአዲስ አበባ በተካሄደው ዓለምአቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ጉባዔ፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ኢትዮጵያ ለልማት በምታደርገው ጥረት ሰው ተኮር የልማት አቅጣጫ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ ነው ብለዋል። መንግሥት መጪው ትውልድ ጤናማ፣ ብቁ እና ውጤታማ እንዲሆን የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራምን ማዕከል አድርጎ ሁሉን አቀፍ ሥራ እየተገበረ ስለመሆኑም አስረድተዋል። በዚህም መሠረት፤ የልጆች ትምህርት ቤቶችን ማስፋፋት፣ የምገባ ሥርዓትን ማሳደግ፣ የሕጻናት መጫወቻ ሥፍራዎች ግንባታ ላይ ተጨባጭ ውጤቶች መምጣታቸውንም ነበር የጠቀሱት። ሀገር አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ልማትና ትምህርት ፖሊሲ የዘላቂ ብልጽግና መንገዳችን ከሆነው የመደመር ዕሳቤ ጋር በተናበበ መልኩ እየተተገበረ በስኬት ቀጥሏልም ብለዋል። ኢትዮጵያ ለነገ የተዘጋጀ ትውልድ ለመገንባት በሕግና በፖሊሲ የተደገፉ የቀዳማይ ልጅነት ኢኒሼቲቮችን እየተገበረች እንደምትገኝም አስታውቀዋል። ለአብነትም፤ በ2015 ተሻሽሎ የፀደቀው ሀገር አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ልማት እና ትምህርት የፖሊሲ ማዕቀፍ እንዲሁም በ2017 የፀደቀውን አጠቃላይ የትምህርት አዋጅ መሠረት በማድረግ ከ35ሺህ በላይ የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመላው ሀገሪቱ እየተተገበረ መሆኑን አንስተዋል። በመንግሥት ተቋማት የሕጻናት ማቆያ ማዕከላት ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን በመጠቆምም፤ ኢትዮጵያ የሕጻናትን ደኅንነት ማሻሻል የሚያስችል ጉልኅ ብሔራዊ መርሐ-ግብር መጀመሯን አንስተዋል። በሰቆጣ ቃል ኪዳን አማካኝነት የ15 ዓመት ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ ከሁለት ዓመት በታች በሆኑ ሕጻናት ላይ የሚደርሰውን መቀንጨር በ2022ዓ.ም ዜሮ ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም ነው ያስገነዘቡት። የሌማት ትሩፋትና የአልሚ ምግቦች ምርታማነት የሕጻናትን ጉዳት ለመቀነስና የልጆችን ጤናማነት መጨመር እያስቻሉ እንደሚገኙም ነው የተናገሩት። ኢትዮጵያ ለዘላቂ የልማት ግቦችና ለሕጻናት መብቶች ጥበቃ የገባቻቸውን ቃል ኪዳኖች ወደ ተግባር እየለወጠች መሆኑን በማንሳት፤ ይህንንም አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል። መንግሥት ብልጽግናን ለማረጋገጥ የተቀናጀ የቀዳማይ ልጅነት ልማትን በመላ ሀገሪቱ ለማስፋት ሙሉ ቁርጠኛ መሆኑንም አመላክተዋል። በዚህም መሠረት፤ በጀት በመመደብ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል፣ የተማሪዎችን ምገባ በማስፋፋት ውጤት ማምጣቱን ነው የሚያብራሩት። ልጆች በአካልና በመንፈስ የሚጎለብቱባቸው የስፖርትና የመዝናኛ ቦታዎች በየአካባቢው በመገንባት፣ በኮሪደር ልማት ለልጆች ምቹ ሥፍራ እየተፈጠረ መሆኑንም በመጥቀስ። ልጆች ላይ መሥራት በነገ ሀገር፣ አኅጉር እና ዓለም ላይ መሥራት በመሆኑ በትጋት ማስቀጠል እንደሚገባም በአጽንኦት ይናገራሉ። አፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ተግዳሮቶችን ለመፍታት የራሷን መፍትሔዎች በማፍለቅ፣ በብሔራዊ የልማት አጀንዳዋ እያካተተች መሆኑን የሚገልጹት ደግሞ የአፍሪካ ቀዳማይ ልጅነት ልማት ማዕከል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ከበደ ወርቁ ናቸው። በሕጻናት ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ማንኛውም ሀገር በመጪው ትውልድ ላይ ሊያደርጋቸው ከሚችላቸው እጅግ አስፈላጊ ኢንቨስትመንቶች አንዱ መሆኑንም ያነሳሉ። አፍሪካ በቀዳማይ ልጅነት ልማት ላይ ያሉባትን ተግዳሮቶች ከመጋፈጥ ባለፈ፤ የራሷን መፍትሔዎች እያመነጨች መሆኑንና ጉዳዩን የብሔራዊ ልማት አጀንዳዋ አካል እያደረገችው እንደምትገኝም ገልጸዋል። አዲስ አበባ ይህን ዓለምአቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ጉባዔ እንድታስተናግድ የተመረጠችበት ዋና ምክንያትም፤ በዘርፉ እያከናወነች ያለው ተግባር አርዓያነት ያለው በመሆኑ ነው ብለዋል። ከተማዋ የጤና እና የሥርዓተ-ምግብ አገልግሎቶችን ያካተተ የተቀናጀ ዘርፈ-ብዙ አሠራር መዘርጋቷን ጠቅሰው፤ የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት እና የቀን የሕጻናት እንክብካቤ ማዕከላትን በከተማ አቀፍ ስትራቴጂ ተግባራዊ እያደረገች እንደምትገኝም ጠቁመዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው፤ መዲናዋ በቀዳማይ ልጅነት ያመጣችው ተጨባጭ ውጤት በአርዓያነት እንድትጠቀስ እንዳደረጋት አንስተዋል። በሕጻናት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ዓመታት የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች፤ በትምህርት፣ በሰው ሃብት ልማትና በኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ረጅም ጊዜ የሚቆይ ፋይዳ እንዳለውም አስረድተዋል። በዚህም በአዲስ አበባ ፍትሐዊና አካታች የቀዳማይ ልጅነት ልማት መርሐ-ግብርን ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ የትውልድ ግንባታ ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል። "ሕጻናት የአዲስ አበባ የነገ ተስፋዎች" የሚል ፍኖተ ካርታ በመቅረጽ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ለሚሆኑ ከስድስት ዓመት በታች ሕጻናት ሁለንተናዊ ዕድገት መረጋገጥ እየተሠራ እንደሚገኝም ተናግረዋል። በትምህርት ቤት ምገባ መርሐ-ግብርም ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ፣ ዩኒፎርምና በቀን ሁለት ጊዜ ምግብ በማቅረብ በሕጻናት ክብካቤ ተጨባጭ ለውጥ መጥቷል ነው ያሉት። የሕጻናት ማቆያና መጫወቻ የመሠረተ-ልማት ግንባታ፤ ሕጻናት ነፃ የሕክምና፣ የምገባና የሥነ-ልቦና አገልግሎት የሚያገኙበትን ዕድል መፍጠሩን አስረድተዋል። የቀዳማይ ልጅነት መርሐ-ግብር በ2015 ዓ.ም ሲጀመር በዕድገት ወደ ኋላ የቀሩ የሕጻናት መጠን ከነበሩበት 13 በመቶ አሁን ላይ ወደ 10 በመቶ ዝቅ ማድረግ መቻሉን ከንቲባዋ አመላክተዋል። አክለውም፤ የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዝግጁነታቸው ከነበረበት 49 በመቶ አሁን ወደ 90 በመቶ ማደጉንም ተናግረዋል። ሀገር በሁሉም ዘርፍ የበቃ መጪ ትውልድ እንዲኖራት መንግስት የያዘው ጥረት በሚፈለገው መጠን ለውጤት እንዲበቃ የሁሉንም ትኩረትና ተሳትፎ ይሻል። ለነገ በሁሉም ዘርፍ የዳበረ ትውልድና የበለጸገች ኢትዮጵያ እውን መሆን ዛሬ ላይ እየተደረገ ያለው ርብርብ የሀገራችንን መፃኢ ብሩህ ተስፋ ይበልጥ የሚያለመልም ነውና ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 7009
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 4257
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 10046
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 8525
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
የከተማ ግብርናን ከጤና ሙያው ጋር ያጣመረው ወጣት
May 14, 2026 1715
በቀደሰ ተክሌ (ከሚዛን አማን) የሰው ልጅ የሕይወት ኡደት በጊዜ የታጠረ ነው። የሰውነት ሚዛን ተለክቶ ውብ ሆኖ የሚገኘው ደግሞ በዚህ የጊዜ ምጣኔ ውስጥ ስኬታማ ሥራ ሰርቶ ተገቢው ቦታ ላይ ሲገኙ ብቻ ነው። ጠንካራ ሰዎች በዕድሜ ዘመናቸው የተሰጣቸውን ጊዜ በአግባቡ ተጠቅመው ስኬት ላይ ይደርሳሉ። ለጊዜ ብዙም ትርጉምና ዋጋ የማይሰጡ ሰዎች ደግሞ እንቅስቃሴያቸውን በጊዜ ስለማይገደብና በዚያው ልክ ተሯሩጠው ስለማይሰሩ ስኬታማ ሳይሆኑ ዘመናቸውን በችግር ያሳልፋሉ። ሰው ሲፈጠር ይህን በማመዛዘን የተሻለውን መንገድ ይጠቀም ዘንድ ደግሞ አዕምሮ ተሰጥቶታል። ማንም ሰው በኑሮ ከመመራት ይልቅ ራሱ ኑሮን መምራት የሚችለው ጠንክሮ ሲሰራ ነው። የአንድ ጠንካራ የሥራ ሰው አንዱ መለኪያ ደግሞ የጊዜ አጠቃቀሙ ነው። ጊዜውን በማብቃቃት ካለው ሥራ ተጨማሪ ሥራ ፈጥሮ የሚሰራና ለበለጠ የሚተጋ ስኬታማ ሕይወትን መምራት ይችላል። በሚዛን አማን ከተማ ኢዜአ ያነጋገርው ወጣት ይህን በተግባር በማረጋገጥ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ነው። ወጣት ዳዊት ባይቴንስ ይባላል። ከተሰማራበት የጤና ዘርፍ ጎን ለጎን ባለው ትርፍ ጊዜ በከተማ ግብርና ሥራ ተሰማርቶ ተጠቃሚነቱን እያሳደገ ይገኛል። ሰርቶ ለመለወጥ ካላው ፍላጎትና ቁርጠኝነት የተነሳ በሕይወቱ ምንም አይነት ጊዜ እንዲባክንበት አይፈልግም። እያንዳንዷን ሰዓትና ደቂቃ ትርጉም ባለው መልኩ ለሥራ ያውላል። ይህ የመነጨው ደግሞ ከሥራ ወዳድነቱ ነው። ሲሰራ ውሎ ሲሰራ ቢያድር ደከመኝና ሰለቸኝን አያውቅም። ለእዚህ ባህሪው እርሾ የሆነው ደግሞ በልጅነቱ ወላጆቹን በግብርና ሥራ እያገዘ ማደጉ ነው። በትምህርቱም ወደ ኋላ ሳይል ጠንክሮ በመማር ስኬታማነቱን አስመስክሯል። የኮሌጅ ትምህርቱን በፋርማሲ የተመረቀው ወጣቱ በአሁን ወቅት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል በጤና ባለሙያነት እየሠራ ይገኛል። የጤና ተቋም ሥራው ቀንና ማታ በፈረቃ የሚሰራ በመሆኑ ከሆስፒታል ሥራው ውጪ ሲሆን ከተማ ወጥቶ በመዝናናት አሊያም በዋዛ ፈዛዛ የሚያሳልፈው ጊዜ የለውም። ከጤና ሥራው ጎን ለጎን በቤቱ ዙሪያ ያለውን ባዶ መሬት እያለማ ይገኛል። የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮችን ተከትሎ በተለይ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ ይህን የግብርና ልማት ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። የግብርና ሥራውን የጀመረው በጤና ሙያ ሥራው በወር ከሚያገኘው ደመወዝ ባሻገር ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ለማግኘት አስቦ ነው። "የግብርና ምርቱ ለቤት ውስጥ ፍጆታ ባውለው እንኳ ወጪዬን ይቀንሳል" የሚለውም ሌላው መነሻ ምክንያቱ ነበረ። በዚህም ባለው ጠባብ መሬት ላይ ቆስጣ፣ ጥቅል ጎመን፣ ካሮትና መሰል የጓሮ አትክልቶችን አልምቶ በመጠቀም "ምግቤን ከጓሮዬ" የሚለውንም ንቅናቄ በተግባር አሳይቷል። በጓሮ ያለማቸውን ምርቶች ለቤተሰብ ፍጆታ ማዋሉም ከወጪ እንደታደገው ነው የገለጸው። የአካባቢው መሬት ያለስስት ከሚያበቅላቸው ፍራፍሬዎች መካከል ሙዝ በቀዳሚነት ይጠቀሳል። ወጣት ዳዊትም በጓሮ አትክልት የጀመረውን ሥራ በማስፋት በቤቱ ዙሪያ የሙዝ ልማት ስራውን አጠናክሯል። የሙዝ ምርቱም ከቤት ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለገበያም እያቀረበ ነው። ዛፉም ጥላ ሆኖ እያገለገለው ነው። ሁሌም ለተጨማሪ ሥራ የሚተጋው ይህ ባለ ራዕይው ወጣት ምርጥ የቡና ዘር ከግብርና ባለሙያዎች በመውሰድ ችግኝ አዘጋጅቶ ለአርሶ አደሮች ያሰራጫል። አምና የቡና ችግኝ ተከላ ወቅት ከ15 ሺህ በላይ የቡና ችግኞችን በጓሮው አዘጋጅቶ በመሸጥ ተጠቃሚ ሆኗል። ከጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ባሻገር በቆሎ በማልማትም ተጠቃሚነቱን እያሳደገ ነው። ወጣት ዳዊት ባለው ጠባብ የከተማ ማሳ ላይ እነዚህን ልማቶች እያከናወነ ያለው በአንድ ጊዜ አይደለም። እንደ የአዝመራው ተስማሚነት አፈራርቆ የማልማት ጥበብንም ተክኗል። በቆሎ ደርሶ የተነሳበት ማሳ ላይ ሌሎች አትክልቶችን ያለማል። በሌላ በኩል ደግሞ ጥምር የእርሻ ሥርዓትን በመከተል በሙዝና ሌሎች ፍራፍሬዎች ስር ባለ ክፍት ቦታ ላይ ቡና ያለማል፤ የአትክልት ችግኞችንም ያዘጋጃል። ይህ ብልህነት የተሞላው የከተማ ግብርና ልማት ሥራው የከተማ ቤቱን የገጠር ሞዴል አርሶ አደር ማሳ አስመስሎታል። ወደፊት የተቀናጀ የግብርና ልማት ጣቢያን የመፍጠር ዓላማ እንዳለው የገለጸው ወጣቱ፣ በቅርቡም በንብ ማነብ ሥራ ውስጥ ለመሰማራት እየተዘጋጀ መሆኑን ነው የተናገረው። ለዚህም የቀፎ ግዥና የቀፎ ማስቀመጫ ቦታ ዝግጅት ሥራ ላይ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት በገበያ እየታየ ያለውን የዋጋ ንረት መቋቋም የሚቻለው ሰርቶ ውጤታማ ሲኮንና ገቢን ማሳደግ ሲቻል ነው የሚል እምነት አለው። ወጣቱ እንደሚለው ምርት የሚያመርት ሰው እየበዛ ሲመጣ ገበያው ይረጋጋል። በመሆኑም ሰዎች ሁሉንም ነገር ከገበያ ከመግዛት ይልቅ ባላቸው ትንሽ መሬት ላይ የተወሰነ ምርት በማምረት ለቤት ውስጥ ፍጆታ እንዲጠቀሙ ይመክራል። ከመደበኛ የመንግሥት ሥራው ጎን ለጎን የተሰማራበት የከተማ ግብርና ልማት ሥራ ወጪውን ከመቆጠብ አልፎ ተጨማሪ ገቢ እያስገኘለት በመሆኑ በቀጣይም ልማቱን ለማጠናከር ሞራል እንደሆነው ተናግሯል። እሱ እንደሚለው ከሆነ በአካባቢው በርካታ ወጣቶች የቤተሰቦቻቸውን ማሳ ትተው በከተማ ያለ ሥራ ጊዜያቸውን ሲያሳልፉ ማየት የተለመደ ነው። ነገር ግን ነገን የተሻለ ለማድረግ ዛሬ የወጣትነት ጊዜን ጠንክረን ልንሰራ ይገባል ይላል። ወጣቶችም ያላቸውን ጉልበትና ጊዜ በመጠቀም ሀብት ማፍራት የሚያስችላቸውን ሥራ መሥራት እንዳለባቸው ይመክራል። በተለይ የእርሻ መሬት ያላቸው ወጣቶች በግብርና ሥራ ራሳቸውን መለወጥ፣ ቤተሰቦቻቸውን መመገብ፣ ገበያ ማረጋጋትና በሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ውስጥ አሻራቸውን ማሳረፍ እንዳለባቸው ነው የገለጸው። የሚዛን አማን ከተማ ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ኅብረት ሥራ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን መንግሥቱ የወጣት ዳዊት ታታሪነት ለብዙዎች ተሞክሮ እንደሚሆን ነው የገለጹት። በተለይ የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮችን መሠረት በማድረግ ያከናወናቸው ተግባራት በትንሽ መሬት መስራት ከተቻለ ገበያን ማረጋጋት እንደሚቻል በተግባር ያሳየ ነው ብለዋል። ጽህፈት ቤቱ ወጣቱንና የእሱን ፈለግ ተከትለው የሚሠሩ ወጣቶችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። ኃላፊው እንዳሉት በአሁኑ ወቅትም በሌማት ትሩፋት የሥራ ዘርፎች ወጣቶች በብዛት እንዲሰማሩ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው። በራስ ተነሳሽነት ያላቸውን ጊዜ አብቃቅተው ወደልማት የገቡ እንደ ወጣት ዳዊት ያሉ ወጣቶች ቢበራከቱ ለግብርናው ዘርፍ ኢኮኖሚ የሚኖራቸው አዎንታዊ ሚናም የጎላ ነው። ማንም ሰው ኑሮን አሸንፎ ወጤታማ ለመሆን እንደ ወጣት ዳዊት በሥራ መትጋት ይኖርበታል። ወቅቱ ያለን ጊዜ አብቃቅቶ ተጨማሪ ሥራዎች መስራት የግድ የሚልበት ወቅት ነው። ለብዙዎች በቅጥር ሰርቶ በሚገኝ ገቢ ብቻ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት አስቸጋሪ በመሆኑ አማራጮችን መጠቀም ያስፈልጋል። ለእዚህም እንደወጣት ዳዊት በዙሪያችን ምን ሀብት አለ በሚል ለይቶ ጥቅም ላይ ማዋል ያስፈልጋል። ጊዜን ከጉልበት ጋር አጣምሮ መጠቀምም እንዲሁ ትኩረት ልንሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። የሰው ልጅ በሕጻንነትና በእርጅናው ዕድሜ የፈለገውን ማድረግ፣ ወጥቶና ወርዶ ሀብት ማፍራት አይችልም። ይህ የሚሆነው በወጣትነትና በጎልማሳነት ዕድሜ ብቻ ነው። በመሆኑም ለነገ ያለምነውን በጊዜው ማሳካት የምንችለው ዛሬ ጠንክረን ስንሰራ ነው። ስለዚህ የወጣትነት ዕድሜያችንን በውጤት ለማጀብ ጠንክረን ልንሠራበት ይገባል። ሥራ ክቡር ከመሆን በላይ ጠንክሮ የሰራውንም ያስከብራል፤ ይለውጣል፤ ሰላም !
አዲስ ምዕራፍ- ከዜጎች ደጃፍ እስከ እጅ ስልክ
Apr 25, 2026 2350
አዲስ ምዕራፍ- ከዜጎች ደጃፍ እስከ እጅ ስልክ በቁምልኝ አያሌው በአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ውስጥ የመንግሥት አገልግሎት ጥራት ከሰው ልጅ የደም ዝውውር ጋር ይመሰላል። በሌላ በኩልም፣ የአገልግሎት አሰጣጥ የዜጎች የሞራልና የፍትሕ ልዕልና መለኪያ ተደርጎ ይወሰዳል። መንግሥት ለዜጎቹ የሚያቀርባቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ጥራት፣ ፍጥነትና ፍትሐዊነትም የሀገርን ፖለቲካዊ መረጋጋትና የኢኮኖሚ አቅጣጫ የሚበይኑ መጋቢዎች ናቸው። ታዋቂው የፖለቲካል ኢኮኖሚ ምሁር ፍራንሲስ ፉኩያማ እንደሚሉት፤ "የመንግሥት ተቋማት ብቃት (State Capacity) ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለዴሞክራሲ መረጋጋት መሠረት ነው።" መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ሥርዓት የሕዝብ አመኔታን በመጨመርና ማህበራዊ እኩልነትን በማስፈን ለዘላቂ ሰላም የማይተካ ሚና ይጫወታል። ይህም ሀገርን በኢኮኖሚ ለማሳደግና ለማበልጸግ በሚደረገው ርብርብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ሌላኛው የኢኮኖሚክስ ምሁር ጆሴፍ ስቲግሊዝ በበኩላቸው፤ "ውጤታማ መንግሥት ማለት ዜጎቹን በግልጽነትና በተጠያቂነት የሚያገለግል፣ በሂደቱም የህዝብ አመኔታን መገንባት የሚችል ነው" ሲሉ አጽንኦት ይሰጣሉ። በአንፃሩ፤ የአገልግሎት ክፍተትና የአስተዳደር ጉድለት ለሀብት ብክነት፣ ለሙስና እና ብልሹ አሰራር በር በመክፈት ዜጎችን ለከፍተኛ ምሬት በማጋለጥ አመኔታን ያሳጣል። ይህንን እንግልት ለማቃለል ሀገራት አገልግሎትን የሚያዘምን ፈጣንና ቀልጣፋ የዲጂታል ሥርዓት እየዘረጉ ይገኛል። ኢትዮጵያም ይህንን መርህ በመከተል ዘገምተኛ አሰራር ከወለደው የ"እጅ መንሻ" (ሙስና) ልምምድ በመላቀቅ ዘመናዊና ግልጽ የዲጂታል ሽግግርን በማፋጠን ላይ ትገኛለች። ይህም ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባትና ሉዓላዊነትን የሚያጎናጽፍ ወሳኝ የልማት ምኅዳር እየፈጠረ ነው። የመደመር መንግሥት ዕሳቤ፤ በተቋማት ግንባታና አገልግሎት ጥራት!! በመደመር ፍልስፍና ውስጥ የመንግሥት ተቋማት ግንባታ የሀገር ግንባታ የጀርባ አጥንት ተደርገው ይወሰዳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው ገፅ-129 እንዳሰፈሩት፤ ''የመደመር መንግሥት ከውስብስብ ቢሮክራሲ ተላቀው የመደመር ለውጥ የሚያመጡ ተቋማት ውቅር ነው። በመሆኑም ተቋማት ከተለመደ ''የሥራ ሂደት መር'' አካሄድ መላቀቅ ይጠበቅባቸዋል። አደረጃጀታቸውንም ለሚያገለግሉት ሕዝብ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲያገኙ ወደሚረዳቸው አደረጃጀት መሸጋገር አለባቸው። ለመደመር መንግሥት ሕዝቡን ማገልገል ከቢሮክራሲ በላይ ነው'' በሚል አስገንዝበዋል። ለዚህም ነው ተቋማት የሰውን ልጅ አቅምና ዕውቀት አቀናጅተው ለጋራ ዓላማ የሚያውሉ ሕያው መዋቅሮች ናቸው የሚባለው። በመደመር ዕሳቤ ጠንካራ ተቋማት ማለት በግለሰቦች ፍላጎትና ስሜት ላይ ያልተመሰረቱ ይልቁንም በሕግና በሥርዓት የሚመሩ መሆን አለባቸው። በመደመር መንግሥት መፅሐፍ ገፅ-130 እንደሰፈረው፤ ''በየተቋማት ያሉ የመንግስት ሠራተኞች ሕዝቡን ከቢሮክራሲው በላይ የሚመለከቱ እንዲሆኑ ይጠበቃል። አገልጋይነትን የተላበሱ መሆን ይጠበቅባቸዋል።'' መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ይህንን ዕሳቤ በተግባር የሚተረጉም ነው። ግለሰባዊ ንክኪን በመቀነስና አሰራርን በቴክኖሎጂ በመተካት ተቋማት ከግለሰቦች መልካም ፈቃድ ይልቅ በሥርዓት ወደሚመራ ተቋማዊ ብቃት መሸጋገርን ያሳያል። የአገልግሎት ጥራትና የዜጎች ክብር በመደመር መንግሥት ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ሰው ተኮር የልማት ነጥብ ነው። ''ለሕዝቡ ቅድሚያ የማይሰጥ አመራርም ሆነ ሠራተኛ የመደመር መንግሥት ወገን አይደለም። እንዲህ ዓይነቱን ግለሰብም ሆነ አይቶ እንዳላየ በማለፍ የማይታገል ሰው በመደመር መንግሥት ውስጥ ዕድል ፈንታ የለውም'' በሚል በመደመር መንግሥት መፅሐፍ የሰፈረው ግልፅ መልዕክትም መንግሥት የአገልጋይነት እንጂ የገዥነት መንፈስ ሊኖረው እንደማይገባ በጉልህ ያመላክታል። የአገልግሎት ጥራት መሻሻልም ዜጎች በሀገራቸው ተቋማት ክብራቸውና መብታቸው ተጠብቆ ያለ እንግልት የሚገለገሉበትን ምኅዳር ይፈጥራል። በተቋማት አገልግሎት የዜጋ እርካታ (Citizen Satisfaction) ዋነኛ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ዕድገት ምንጭ ተደርጎ ይወሰዳል። በመደመር መንግስት ዕይታ የብልሹ አሰራር መታገያ ስትራቴጂ በጩኸትና በቅጣት ብቻ የሚመጣ ሳይሆን አሰራርን በማዘመን ጭምር ነው። የመሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ሌብነትን የማይጋብዝ ሥርዓት የፈጠረ (Systemic Prevention) ስትራቴጂክ አቅጣጫ ሆኗል። የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማትና የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመደመር መንግሥት መሠረታዊ የተቋማት ሪፎርም ትግበራን (Institutional Reform) የሚያሳዩ ናቸው። ይህም ተቋማትን ከመዋቅራዊ ሽግግርና ለውጥ ባለፈ የተቋማት ሠራተኞችን ከመንግሥት ሠራተኛነት ወደ ሕዝብ አገልጋይነት የአስተሳሰብ ለውጥ (Paradigm Shift)፣ ኋላ ቀር አሰራርን በዲጂታል የቴክኖሎጂ አማራጭ የሚተካ (Technology Integration)፣ አገልግሎትን ለሁሉም ዜጋ በእኩልነት፣ በቅርበትና ፍትሐዊነት የማዳረስ ፅንሰ ሃሳባዊ ግብን በተግባር ያረጋገጠ ሆኗል። ይህ ታላቅ ተግባርም ኢትዮጵያ በመደመር ዕሳቤ የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ የሚያፋጥንና ዜጎች በመንግሥታቸው ላይ ያላቸውን አመኔታ በጽኑ መሠረት ላይ የሚገነባ መሠረት ነው። የዲጂታል ኢትዮጵያ ርዕይና ስትራቴጂክ ሽግግር!! ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ለግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና አይሲቲ ዘርፎች ወሳኝ የልማት ዕድሎችን ፈጥሯል። በዚህ ሰፊ መርሃ ግብር ውስጥ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እንደ ዋነኛ የብልፅግና ምሰሶ ተወስዷል። በ"ዲጂታል ኢትዮጵያ-2025" ስትራቴጂ የተጀመረውና በስኬት የተጠናቀቀው ጉዞ ዛሬ ላይ ሀገሪቷን ወደ "ዲጂታል ኢትዮጵያ-2030" አሸጋግሯታል። ይህ ስትራቴጂ ዜጎች ካሉበት ቦታ ሆነው አገልግሎት የሚያገኙበትን ምኅዳር በመፍጠር በሰው ንክኪ የሚፈጠሩ ብልሹ አሰራሮችንና የአገልግሎት እንግልትን በማስቀረት ረገድ ታሪክ ቀያሪ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የልማትና ዕድገት ምሁሩ አማርትያ ሴን፤ "ልማት የሰው ልጅ ምርጫና የመገልገያ አቅሙን ማስፋፊያ መሣሪያ ነው" በማለት የሚገልጹት ስለልማት ከፍ ያለ ትርጉም ይሰጠናል። የኢትዮጵያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ዜጎች የሚያጋጥሟቸውን እንግልቶች በማስወገድ ትኩረታቸውን በልማት ላይ እንዲያደርጉ በማስቻሉ፣ ይህንን የልማት ፅንሰ-ሃሳብ በተግባር እየተረጎመ ይገኛል። የአንድ ጣሪያ በረከትና የቅልጥፍና ተምሳሌት - መሶብ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዚያ 18/2017 ዓ.ም የተመረቀው የፌዴራል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ ለተቋማዊ ሽግግር መነሻ ሆኗል። ቁልፍ የመንግሥት አገልግሎቶች በአንድ ጣሪያ ስር መሰባሰባቸው የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ አሸጋግሮታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ይህ ማዕከል ዜጎች ጊዜያቸውንና ሀብታቸውን በመቆጠብ ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ለዘመናት የቆየውን ምሬት የሚቀለብስ የሪፎርም እርምጃ ነው። በወቅቱ ሲጀመር 12 የነበሩት ፌዴራል ተቋማት፤ አሁን ላይ 23 በመሻገር አገልግሎታቸውን እየሰጡ ይገኛል። ይህም የዜጎች እንግልት በማስቀረት ታላቅ እፎይታን ፈጥሯል። እነዚህ ተቋማት፦ የብሔራዊ መታወቂያ፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት፣ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ስልጠና ባለስልጣን፣ ኢትዮ ፖስታ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን፣ የኢትጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የፍትሕ ሚኒስቴር፣ ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች አገልግሎት ናቸው። መነሻውን አዲስ አበባ ከተማ የፌዴራል ተቋማት በአንድ በማሰባሰብ የጀመረው ይህ አገልግሎት አሁን ላይ በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ተደራሽ እየሆነ ነው። ይህም የመልካም አስተዳደር እጦትን የሚያቃልል ታሪክ ቀያሪ መደላድል ፈጥሯል። አዲስ መሶብ - የተንቀሳቃሽ አገልግሎት ተስፋ!! በመዲናችን ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎት፣ "መንግሥት ወደ ዜጋው ይሄዳል" (Citizen-Centric Governance) የሚለውን የዘመናዊ አስተዳደር ፍልስፍና በተግባር ያሳየ ነው። በፀሐይ ኃይልና በፈጣን ኔትወርክ የታገዘው ይህ ተንቀሳቃሽ አገልግሎት የስምንት ተቋማትን 36 ዓይነት አገልግሎቶች ወደ ህዝቡ ደጃፍ በማምጣት ረገድ ተምሳሌት ሆኗል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ከተማዋ ለዘመናት ስር በሰደደ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ተተብትባ ብትቆይም፣ የመሶብ ዲጂታል አገልግሎት ግን ለተገልጋዩ እውነተኛ እፎይታን ይዞ መጥቷል። የቀጣዩ ዘመን ግብ - አገልግሎትን በእጅ ስልክ!! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀጣይ አገልግሎቱን ወደ ዜጎች የእጅ ስልክ የማሸጋገር ግብ መኖሩን አረጋግጠዋል። ይህ ሽግግር ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዲሆን የዲጂታል መታወቂያ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ዜጎችን በዲጂታል መታወቂያ መለየት መቻሉ የአሰራር ግልጽነትን ከመጨመሩም በላይ መንግሥት አገልግሎቱን ለማን እየሰጠ እንደሆነ በትክክል እንዲያውቅ ያስችለዋል። ተገልጋይን አክብሮ፣ ስርቆትና "እጅ መንሻን" አስቀርቶ አገልግሎት መስጠት የባህል ለውጥ ይጠይቃል። ለዚህም ሲቪል ሰርቪሱን በማዘመን፣ ቴክኖሎጂንና የባህል ለውጥን በማቀናጀት የእጅ መንሻን ባህል የሚያስቀር መሠረት እየተጣለ ይገኛል። ለዚህ ለውጥ ስኬት እያንዳንዱ ዜጋና ተቋም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማት መርሃ ግብርና የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሙስናን በማድረቅ ፍቱን መፍትሔ እየሰጡ ይገኛሉ። ይህም ሀገሪቷን ከቆየችበት የ"እጅ መንሻ" አዙሪት አውጥቶ፣ ተቋማት ለዜጎች ክብር ወደሚያሳዩበት አዲስ ምዕራፍ አሸጋግሯታል። ይህ ጉዞ እመርታ ነው፤ ግልጽነትን በማንገስና የህዝብን እርካታ በመጨመር የብልጽግና ጉዞውን የሚያፋጥን ነው።