ብልፅግና ፓርቲ ዜጎችን ከድህነት በማውጣት የሀገርን እድገትና ማንሰራራት እውን የማድረግ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል - ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
ብልፅግና ፓርቲ ዜጎችን ከድህነት በማውጣት የሀገርን እድገትና ማንሰራራት እውን የማድረግ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል - ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)
ጅማ፤ ግንቦት 15/2018 (ኢዜአ)፦ ብልፅግና ፓርቲ ዜጎችን ከድህነት በማውጣት የሀገርን እድገትና ማንሰራራት እውን ለማድረግ የጀመራቸውን ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ገለጹ።
ብልፅግና ፓርቲ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) በሚወዳደሩበት ኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ሸቤ ሶምቦ ወረዳ የምርጫ ቅስቀሳ አካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)፤ በለውጡ ዓመታት ብልፅግና ፓርቲ የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ለማድረግና ሀገርን ከድህነት ለማውጣት ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን ማከናወኑን ገልጸዋል።
በግብርና ልማት በተለይም በመስኖ ስንዴ ልማት አስደናቂ ውጤት መገኘቱን አንስተው በሌሎችም መስኮች ተጨባጭ ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል።
በመሆኑም ብልፅግና ፓርቲ ዜጎችን ከድህነት በማውጣት የሀገርን እድገትና ማንሰራራት እውን ለማድረግ የጀመራቸውን ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።
የሸቤ ሶምቦ ወረዳ አስተዳዳሪ መሀመድሳኒ አባኦሊ፤ ብልፅግና ፓርቲ በለውጡ ዓመታት ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን በማከናወን የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ማድረግ ችሏል ብለዋል።
በተለይም በግብርና ዘርፍ ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጅነት ለመውጣት የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።
የሸቤ ሶምቦ ወረዳ በሩዝ ምርት የሚታወቅ መሆኑን አስታውሰው፤ ባለፉት ጥቂት አመታት ምርቱ በእጥፍ እንዲያድግ የተደረገበትን ስኬት ለአብነት አንስተዋል።