አርእስተ ዜና
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የክህሎት ውድድር እየተሳተፈች ነው
Sep 11, 2024 63
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2017 (ኢዜአ):-ኢትዮጵያ በፈረንሳይ ሊዮን እየተካሄደ ባለው 47ኛው የዓለም አቀፉ የክህሎት ውድድር እየተሳተፈች ትገኛለች። የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን “የክህሎት ኦሊምፒክ” የሚል ስያሜ ያገኘውን ውድድር ትናንት በይፋ አስጀምረዋል።   ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታዎች በሶስት ክህሎት ዘርፎች (ICT and Networking, CNC Machine, Furniture Making ) ተወክላ ውድድሩ ላይ እየተሳተፈች እንደምትገኝ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በውድድሩ ላይ ተሳታፊ የሆነችው በ2016 በጀት አመት የዓለም ክህሎት ማህበረሰብ (World Skills Member ) አባል መሆኗን ተከትሎ እንደሆነ አመልክተዋል። ዓለም አቀፉ የክህሎት ውድድር እስከ መስከረም 5 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል። በውድድሩ ላይ ከ70 አገራት የወጣጡ 1 ሺህ 400 ወጣቶች ይሳተፋሉ። ወጣቶቹ የተለያዩ የክህሎትና የፈጠራ ስራዎቻቸውን በማቅረብ ውድድራቸውን ያደርጋሉ። የውድድሩ አላማ በየጊዜው እየተለወጠች ባለው ዓለም የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ያላቸውን ወሳኝ ሚና ማሳየት መሆኑ ተገልጿል።
የልማት ስራዎች የሁሉንም ተሳትፎና ተጠቃሚነት መሰረት በማድረግ ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Sep 11, 2024 66
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2017(ኢዜአ):- የልማት ስራዎች የሁሉንም ተሳትፎና ተጠቃሚነት መሰረት በማድረግ ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባዋን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በመዲናዋ 21ኛው የምገባ ማእከል በይፋ ስራ አስጀምረዋል።   የምገባ ማእከሉ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አየር ጤና አካባቢ በበረከት ወርቁ (በበረከት ገበሬዋ) ድጋፍ የተገነባ ነው፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር፤ በአዲስ አበባ የተገነቡ የምገባ ማእከላት በቀን አንድ ጊዜ በራሳቸው መመገብ የማይችሉ ወገኖችን የሚመግቡ ናቸው ብለዋል። ለማእከላቱ እውን መሆንም የተለያዩ የግል ተቋማትና ባለሃብቶች እያደረጉት ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የምገባ ማዕከላቱ ወገኖችን ከመመገብም ባለፈ ለብዙዎች የስራ እድል እየፈጠሩ ስለመሆኑም ገልጸዋል። ከበረከት ወርቁ ጋር በመተባበር አየር ጤና አካባቢ የተገነባው 21ኛው የተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከልም በዛሬው እለት ለአገልግሎት በቅቷል ብለዋል። የማእከሉን ግንባታ አጠናቀው ያስረከበችው ባለሃብቷ በረከት ወረቁ፤ ለዜጎች የሚጠቅም በጎ ተግባር መፈፀም ከምንም በላይ የላቀ ደስታ የሚፈጥር መሆኑን ተናግራለች። የተገነባው የምገባ ማዕከል በራሱ ገቢ እንዲተዳደር የግብርና ምርቶች የሚሸጡበት ሱቆች የተካተቱበት ስለመሆኑ ጠቅሳለች። ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር በቀጣይም 22ኛውን የተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከል ለመገንባት ዝግጁ መሆኗን ባለሃብቷ አረጋግጣለች።
ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመትን በሚኖሩባቸው አገራት አከበሩ
Sep 11, 2024 76
አዲስ አበባ፤መስከረም 1/2017 (ኢዜአ):- በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን የአዲስ ዓመት በዓልን አክብረዋል። በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አዲስ ዓመትን ኢትዮጵያውያን፣ የኢትዮጵያ ወዳጆች፣ የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ሌሎች ተቋማት አመራሮች እንዲሁም ተቀማጭነታቸውን ኬንያ ያደረጉ ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ በተገኙበት ተከብሯል። በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ የኢትዮጵያ አዲስ አመት እንደ አገር አንድነታችን የምንጠናክርበትና የወደፊት የጋራ እድሎቻችንን በጋራ የምንቀበልበት ልዩ ቀን ነው ብለዋል። የዘንድሮውን አዲስ ዓመት ስናከብር ኢትዮጵያና ኬንያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበት 60ኛውን ዓመት ጭምር በማክበር እንደሆነ ገልጸዋል።   የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዴኒስ ምቡሩ ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈዋል። በሕንድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በአገሪቷ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን አዲስ ዓመትን አክብሯል።   የኤምባሲው ምክትል ሚሲዮን መሪ አምባሳደር ብዙነሽ መሰረት ኢትዮጵያ የ13 ወራት የዘመን አቆጣጠር ያላት አገር መሆኗንና ይህም በአገር ውስጥና በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመትን በጋራ እንዲያከብሩ የሚያደርግ ልዩ አጋጣሚ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት በተለያዩ መስኮች ስኬት ማስመዘገቧንና ይህንንም በአዲሱ ዓመት ዘላቂ ልማትን እውን በማድረግ አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ከሕንድ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጎልበት እንደምትሰራም ገልጸዋል። በበዓሉ አከባበር ላይ ኢትዮጵያውያን፣ የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ የንግዱ ማህበረሰብና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።   በተመሳሳይ የአዲስ ዓመት በዓል በጣልያን ሮም ተከብሯል። በጣልያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ አዲሱ አመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነትና የምንበለጽግበት ጊዜ እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። አዲሱ ዓመት የተሻለች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስረከብ ተግተን የምንሰራበት፣ እጅ ለእጅ ተያይዘን ልማትን ለማረጋገጥ ጠንካራ ርብርብ የሚደረግበትና በጋራ የምንቆምበት ዓመት ነው ብለዋል:: የዳያስፖራ ተወካዮችም በበኩላቸው ኤምባሲው ዳያስፖራው ከአገሩ ጋር ያለውን ትስስር እንዲያጠናከር እያከናወነ ያለውን ስራ አመስግነው በአዲሱ ዓመት ለተሻለ ውጤት እንደሚተጉ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ የ2017 አዲስ ዓመት አንካራ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተከብሯል።   በተርኪዬ የኢትዮጵያ አምባሳደር አደም መሐመድ አዲስ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ እና የስኬት ዘመን እንዲሆን ተመኝተዋል። የኤምባሲው ዲፕሎማቶችና ሰራተኞች በአዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያ ልማት፣ሰላምና ዲሞክራሲ ግንባታ ስራ የበለጠ አስተዋጽኦ በሚያበረክት መልኩ የዲፕሎማሲ ስራዎችን በተቀናጀና በላቀ ሁኔታ እንዲያከናውኑ አሳስበዋል። ጀርመን፣ኩዌትና ዩናይትድ ኪንግደም በዓሉ ከተከበረባቸው አገራት መካከል ይገኙበታል።
በቀን አንዴ መመገብ ለማይችሉ ወገኖቻችን 21ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል የአዲስ ዓመት ስጦታ አድርገን እነሆ ብለናል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Sep 11, 2024 113
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2017(ኢዜአ):- በቀን አንዴ እንኳን መመገብ ለማይችሉ ወገኖቻችን 21ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል የአዲስ ዓመት ስጦታችን አድርገን እነሆ ብለናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። በአዲስ ዓመት በቀን 1 ሺህ ሰዎችን የሚመግበውን 21ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አየር ጤና አካባቢ መርቀን በቀን አንዴ እንኳን መመገብ ለሚቸገሩ ወገኖቻችን መልካም አዲስ ዓመት ብለን ምገባ አስጀምረናል ብለዋል።   ከተማችንን ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት ለማድረግ ከጀመርናቸው ስራዎች አንዱ በቀን አንዴ እንኳን መመገብ የሚቸገሩ ወገኖቻችንን መመገብ ሲሆን 21ኛውን የምገባ ማዕከል በረከት ገበሬዋ ገንብታ አስረክባናለች ሲሉም ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል። በቀጣይም ሙሉ ወጪውን ችላ 22ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ገንብታ ለወገኖቿ ለማስረከብ ቃል መግባቷንም ጠቁመዋል። ለበጎነቷ በተጠቃሚ ነዋሪዎቹ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ላመሰግናት እወዳለሁ ሲሉም አክለዋል በመልዕክታቸው።
የሚታይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች ማእድ አጋሩ
Sep 11, 2024 123
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2017(ኢዜአ):- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች ማእድ አጋሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ማዕድ ያጋሩት ከአዲስ አበባ ከተለያዩ አካባቢዎች ለመጡ አቅመ ደካማ ወገኖች ነው። በማዕድ ማጋራት መርሃ ግብሩ ላይ ያነጋገርናቸው አረጋውያንና አቅመ ደካሞች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያከናወኑት በጎ ተግባር በሁሉም ዘንድ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።   አቶ ሙሉጌታ ዱኬሳ ከዚህ ቀደም መሪዎች የበዓል ወቅትን ከአረጋዊያን ጋር ሲያሳልፉ ማየት ያልተለመደ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ ከዚህ አኳያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በዓሉን ከአረጋዊያንና አቅመ ደካማ ወገኖች ጋር ማሳለፋቸው ልዩ የደስታ ስሜት እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።   አቶ ከሳዬ ህሉፍ በበኩላቸው ለ30 ዓመታት ኢትዮጵያን በውትድርና ሞያ ማገልገላቸውን አንስተዋል። በመሆኑም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገር ባለውለታ የነበሩ አረጋዊያንን በማገዝ እያከናወኑ ያለውን በጎ ተግባራ አድንቀዋል፡፡   ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝቅ ብለው አረጋዊያንን ማገዛቸው በተለይ ለወጣቶች አርአያነት ያለው ተግባር መሆኑን የተናገሩት ደግሞ ሻምበል አማን አብዱልሽኩር ናቸው፡፡   በተመሳሳይ ወይዘሮ ጸሀይ ከበደ እና ወይዘሮ ፈለጉሽ አምሳሉ የዘንድሮውን አዲስ ዓመት በተለየ የደስታ ስሜት ማሳለፋቸውን ተናግረዋል፡፡   ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ላጋሯቸው ማእድ ምስጋና አቅርበዋል።    
በክልሉ የዘመን መለወጫ በዓል ያለ ምንም ፀጥታ ችግር እንዲከበር  ዝግጅት ተደርጓል-ፖሊስ
Sep 10, 2024 104
ሆሳዕና ፤ ጳጉሜ 5/2016 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የዘመን መለወጫ በዓል ያለ ምንም ፀጥታ ችግር እንዲከበር አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። በኮሚሽኑ የወንጀል መካላከልና ትራፊክ ቁጥጥር ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አብርሐም ቲርካሶ ለኢዜአ እንዳሉት የዘመን መለወጫ በዓልን ለማክበር ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ ክልሉ በርካታ እንግዶች እየገቡ ናቸው። ከዚሁ እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችለውን ወንጀል ለመከላከል የሚያስችል እቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱን ጠቁመዋል። "በተለይ በአሉን ለማክበር ወደ ወዳጅ ዘመድ በሚንቀሳቀሱ ሰዎች ላይ ያልተገባ የትራንስፖርት ዋጋ ጭማሪ እንዳይደረግ የተቀናጀ ቁጥጥር እየተደረገ ነው" ብለዋል። ለዚህም ስኬት ማህበረሰቡን ያሳተፈ የወንጀል መከላከል ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል። ማህበረሰቡ የተለያዩ የወንጀል እንቅስቃሴዎችን በሚመለከትበት ወቅት አስፈላጊውን መረጃ ለፖሊስ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ አሳስበዋል። በሀዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ የሞተረኛ ትራፊክ ቲም አስተባባሪ ኢንስፔክተር አድማሱ አወቀ በዓሉ ያለ ምንም የትራፊክ አደጋ በሰላማዊ መንገድ ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ስራ ተገብቷል። "ትርፍ በሚጭኑ የትራንስፖርት አሽከርካሪዎች ላይ ክትትል በማድረግ ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል" ብለዋል። ዜጎችን ያለ አንዳች እንግልት እንዲንቀሳቀሱ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው ማህበረሰቡም በትራንስፖርት እንቅስቃሴ ወቅት ችግር ሲገጥመው ለጸጥታ አካላት እንዲያሳውቅ አሳስበዋል።  
ፖለቲካ
በክልሉ ለመጪው ጊዜ ተስፋ የሆኑ ተግባራት ተከናውነዋል- ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ
Sep 10, 2024 104
ባህር ዳር፤ ጳጉሜ 5/2016 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በችግር ውስጥ ቢታለፍም ለመጪው ጊዜ ተስፋ የሆኑ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተግባራት መከናወናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ገለፁ። የ2017 ዓ.ም አዲስ ዓመት መግቢያ ዋዜማ "አዲስ ዓመት፣ አዲስ እይታና አዲስ መገለጥ" በሚል መሪ ሃሳብ በድምቀት እየተከበረ ነው። ርዕሰ መስተዳድሩ በስነ ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት፤ የ2016 ዓ.ም በክልሉ ችግሮች ያጋጠሙበት ቢሆንም በዚያ ውስጥም በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል። በክልሉ ውስጥ ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት ከተደረጉ ጥረቶች ጎን ለጎን በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሌሎች ልማቶች የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት መከናወናቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውቀዋል። በተጨማሪም አብሮነትን የሚያሳድጉ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቅሰው፤ በዚህም ለአዲሱ በጀት ዓመትና ለመጪው ጊዜ አሻጋሪና ተስፋ የሆኑ ስራዎች በቅንጅት ማከናወን መቻሉን ተናግረዋል። አዲሱ ዓመትም ባለፈው ዓመት በተከሰቱ ችግሮች ያጋጠሙ መጥፎና እኩይ ተግባራት ተወግደው "የደስታ፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የተስፋ ዓመት እንዲሆን ከህዝባችን ጋር በጋር የምንሰራበት ነው" ብለዋል። ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ አዲሱ ዓመት የተስፋ፣ የፍቅርና የሰላም እንዲሆን በመመኘት ለመላው የአማራና የኢትዮጵያ ህዝብ "እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ" የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።   የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ መልካሙ ፀጋየ በበኩላቸው፤ "የአገራችን የአዲስ ዓመት በዓል የአባቶቻችን የስነ ፈለግ፣ የሂሳብ ቀመርና ጥበብ ውጤት ነው" ብለዋል። በዚህም የዘንድሮው አዲስ ዓመት የበረከትና ጥጋብ ዓመት እንዲሆን የምንተጋበት ዓመትመሆኑን ገልጸዋል። "አዲስ ዓመት፣ አዲስ እይታና አዲስ መገለጥ" በሚል መሪ ሃሳብ በባህር ዳር ከተማ እየተከበረ ባለው የበዓል ዋዜማ በየደረጃው ያሉ አመራሮች፣ የመከላከያ ሠራዊት አባላትና ባልድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።
የወል ትርክቶችን በማጎልበት ሁለተናዊ ብልጽግናን በጋራ ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለጸ
Sep 10, 2024 104
ደሴና ደብረ ብርሃን ጳጉሜ 5/2016 (ኢዜአ):- የወል ትርክቶችን በማጎልበትና ትውልድ የሚሻገር የልማት ስራ በማከናወን ሁለተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚገባ የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ ገለጹ። የደቡብ ወሎ ዞንና የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደሮች የጳጉሜ 5 የነገው ቀንን በሐይቅ ከተማ አክብረዋል። የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አሊ ይማም በዚሁ ወቅት እንዳሉት ፤ ለነገው ትውልድ የሚተርፍና የኢትዮጵያን ብልጽግና የሚያረጋግጡ ትላልቅ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ነው። ከተረጅነት ተላቀን ክብራችንን ለማስጠበቅ እየተደረገ ባለው ጥረት የስንዴ ምርታማነት አበረታች ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን አንስተው የተጀመሩ ተግባራትን ማጠናከር ይገባናል ብለዋል። የሐይቅ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር መሀመድ በበኩላቸው የከተማውን ሰላም በማስጠበቅ ለነገው ትውልድ የሚተርፉ ሰፋፊ የልማት ስራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል። በገበታ ለትውልድ የሚለማውን የሎጎ ሐይቅ ፕሮጀክት ጨምሮ ሌሎችም ግዙፍ ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተከናወኑ መሆኑን ለአብነት ጠቅሰዋል። የወልና የጋራ ትርክቶችን በማጎልበት ለትውልድ ምቹ፣ ጠንካራ፣ የበለፀገችና ሉዓላዊነቷ የተጠበቀ አገር ለማስረከብ መስራት እንደሚገባ አመልክተዋል። የሐይቅ ከተማ ነዋሪ አቶ ጀማል አህመድ ትውልድ ተሻጋሪ የልማት ስራ ለማከናወን የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ገልጸዋል።   በተመሳሳይ በሰሜን ሸዋ ዞን የጳጉሜ 5 የነገው ቀን ''የዛሬ ትጋት ለነገው ትሩፋት” በሚል መሪ ሃሳብ በደብረ ብርሃን ከተማ ተከብሯል። የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ተክለየስ በለጠ የቀደሙ አባቶቻችን ዋጋ ከፍለው ያስረከቡን አገር ለትውልድ የተሻለ ኑሮ እንዲያሳልፍ ዛሬ ላይ ተግተን መስራት አለብን ብለዋል። ከአሁናዊ አስተሳሰብ ወጥተን ነገን አሻግሮ የሚመለከት ትውልድ መገንባት ላይ ሁሉም ሊባረብ እንደሚገባ አመልክተዋል። የሰሜን ሸዋ ዞን ሴቶች ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ የሮምነሽ ጋሻውጠና በበኩላቸው ዕለቱ ስናከብር ጥላቻን በመንቀል ፍቅርን በመትከል ለመደመር ትውልድ ቃል ኪዳን የምንገባበት ነው" ብለዋል። የዞኑ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ብርቃብርቅ ተሾመ በተያዘው በጀት ዓመት ከተሞችን በማዘመን ለኑሮና ለኢኮኖሚ ምቹ እንዲሆን እየተሰራ ነው ብለዋል።  
በአማራ ክልል በአዲሱ ዓመት ሰላሙ የተረጋጋ ክልል ለመፍጠርና ብልፅግናን ለማረጋገጥ በላቀ ትጋት ይሰራል -አቶ ይርጋ ሲሳይ
Sep 10, 2024 105
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 5/2016(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በአዲሱ ዓመት የተረጋጋ ሰላም በመፍጠር ኢኮኖሚያዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት በላቀ ትጋት እንደሚከናወኑ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የርዕሰ መስተዳደሩ የህዝብ ተሳትፎና አደረጃጀት አማካሪ አቶ ይርጋ ሲሳይ ገለፁ። "የዛሬ ትጋት፤ የነገ ትሩፋት" በሚል መሪ ሃሳብ 'የነገ ቀን' በባህር ዳር ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ውሏል። አቶ ይርጋ ሲሳይ እንዳሉት፤ በክልሉ በአዲሱ ዓመት የተገኘውን ሰላም አፅንቶ ለማዝለቅና ብልፅግናን ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል። ''በአዲሱ ዓመት በአዲስ ተነሳሽነትና ጉልበት ሁላችንም ነገን አስበንና አቅደን መጪውን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ የልማት ስራዎችን ማከናወን ይገባል'' ብለዋል። ''ለዚህም ያሉንን መልካም ባህሎች፣ እሴቶች፣ ታሪኮችና ቅርሶችን በመጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስረከብ ከእኛ የሚጠበቅ ተግባር ነው'' ሲሉም ገልፀዋል። በአዲሱ ዓመት ሰላሙ የተረጋጋ ክልል ከመፍጠር ባሻገር ኢኮኖሚያዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በየደረጃው ያለው አመራር፣ ባለሙያና መላ ህዝቡ በትጋት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል። እንዲሁም ትምህርት ቤቶችን ለመማር ማስተማር ምቹ በማድረግ ለፈጠራና ቴክኖሎጂ ቅርብ የሆነ፣ በምክንያት የሚያምን ትውልድ በመገንባት ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራም አስገንዝበዋል።   የክልሉ ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ብርቱካን ሲሳይ በበኩላቸው፤ ''በአዲሱ ዓመት ዋዜማ ላይ ሆነን የነገን ቀን ስናከብር የኢትዮጵያን ብሩህ ነገ ቅርብ መሆኑን በማስገንዘብ ነው'' ብለዋል። በተለይ ሴቶች፣ ህፃናትና አካል ጉዳተኞች ለችግር እንዳይጋለጡ ሁሉም በጋራ መረባረብ እንዳለበትም አመልክተዋል። ''በአዲሱ ዓመት ወጣቶች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን በንቃት እንዲያከናውኑ በማስቻል መሆን አለብት'' ያሉት ደግሞ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ዶክተር ዘሪሁን ፍቅሩ ናቸው።   በክልሉ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የሀይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች የድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑንም አስታውሰዋል። "የዛሬ ትጋት፤ የነገ ትሩፋት" በሚል መሪ ሃሳብ የነገ ቀን በባህር ዳር ከተማ የክልሉና የከተማ አስተዳደር አመራር አባላት፣ ወጣቶች፣ ሴቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተከብሮ ውሏል።    
ብልፅግና ፓርቲ በአዲሱ ዓመት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግናና የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት ይሰራል- አቶ አደም ፋራህ
Sep 10, 2024 101
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2016(ኢዜአ)፦ ብልፅግና ፓርቲ በ2017 የኢትዮጵያውያንን ሁለንተናዊ ብልፅግናና የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ገለጹ። አቶ አደም ለመላው ኢትዮጵያውያን ባስተላለፉት የአዲስ ዓመት መልዕክት 2017 ዓ.ም የሰላም፣ የደስታ የፍቅር፣ የጤናና የብልፅግና እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። የተጠናቀቀው 2016 ዓ.ም በአገር በቀል እሳቤዎች በመመራት ቃልን በተግባር ማረጋገጥ ያስቻሉ ዘርፈ ብዙ ስኬቶች የተመዘገቡበት መሆኑን ተናግረዋል። ለአብነትም በደም የተከበረውን ነጻነት በላብ ለማጽናት የሚያስችሉ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርትና ምርታማነት በከፍተኛ ደረጃ የማሳደግ ሥራዎች መከናናቸውን አመልክተዋል። በተጠናቀቀው ዓመት በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ገልጸው፤ ሰው ተኮር በተለይም ድሃ ተኮር የሆኑ ውጤታማ ሥራዎች ተከናውነዋል ነው ያሉት። ኢትዮጵያን ተወዳዳሪ የሚያደርጉ ደረጃቸውን የጠበቁ የቱሪዝም መዳረሻዎችና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የከተማ ልማቶች መተግበራቸውንም አንስተዋል። አዲስ አበባን ለኢትዮጵያም ሆነ ለአፍሪካ መዲናነት የምትመጥን እንድትሆን የሚያስችሉ ሰፋፊ ሥራዎች መሠራታቸውንም ጠቁመዋል። ልማትን በሚያሳልጥና አገልግሎት አሰጣጥን በሚያዘመን መልኩ አገራዊ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም መሻሻሉንም ነው ያነሱት። እንዲሁም ነጻ፣ ገለልተኛና ብቃት ያላቸው ተቋማት በውጤታማነት መገንባታቸውንም ጠቁመዋል። የ2017 ዓ.ም ባለፉት ዓመታት ያስመዘገብናቸውን እምርታዎች፣ የህዝቡን የላቀ ተጠቃሚነት በሚያረጋገጥ አኳኋን ይበልጥ አስፍተን የምንሄድበት ዓመት ይሆናል ብለዋል። አዲሱ ዓመት በሁሉም አካባቢዎች ሰላምን ለማፅናት፣ የአገልግሎት ቅልጥፍናና ውጤታማነትን በማረጋገጥ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን እንዲሁም የአገራችንን ብሔራዊ ጥቅም በተሻለ ለማስከበር በትጋት የሚሰራበት ዓመት መሆኑን ገልጸዋል። ብልፅግና ፓርቲ በአዲሱ ዓመት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ውጤታማ ሥራዎችን ከመላው ሕዝብ ጋር በመሆን በከፍተኛ ቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። ሕዝቡም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ያቀረቡት አቶ አደም አዲሱ ዓመት በተስፋ፣ በአዲስ መንፈስ፣ የልብ መሻታችንን እውን የሚሆንበትና የስኬት ዓመት እንዲሆንም ተመኝተዋል።          
ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የአዲስ አመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
Sep 10, 2024 106
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2016(ኢዜአ):- የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የአዲስ አመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። የመግለጫው ሙሉ ቃል ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል:- ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ከአመት አመት አሸጋገራችሁ እንኳን ለአዲሱ 2017 አመት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! አዲሱ አመት የሰላም የብልጽግና የመተሳሰብ እና በህብረት የማደግ አመት እንዲሆንልን መልካም ምኞቴን በቅድሚያ እገልጻለሁ፡፡ ጊዜ ከፈጣሪ ለሁላችንም የተሰጠን ታላቅ ሀብታችን ነው፡፡ ጊዜ ህይወታችን ነው፤ ዕድሜያችን የጊዚያት ድምር ውጤት ነው፡፡ የተቸረንን ዕድሜያችን በአመታት ተከፋፍለው በህይወት ዘመናችን ራሳችንንና ሌሎችን የሚጠቅሙ ቁምነገሮችን እንድንሰራ ይጠበቃል፡፡ እነሆ እንደኛ እንደ ኢትዮጵያውን አቆጣጠር 2016 አመትን ሸኝተን 2017 አዲሱ አመትን በአዲስ ተስፋ በአዲስ መነሳሳት አርሂብ ብለን በክብር ተቀብለናል፡፡ ከአመት አመት መድረስ በፈጣሪ የሚሰጥ ችሮታ ነውና ለአምላካችን ታላቅ ምስጋናን በማቅረብ አዲሱን አመት እንዲባርክልን እንለምነዋለን፡፡ 2016 አመት ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የብልጽግና ማማ ከፍ ለማድረግ እንደ ክልላችንም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ ህብረ ብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ላይ የተመሠረተ ሀገረ መንግስት ግንባታ፤ በወንድማማችነት እሴት ላይ የቆመ ህረ ብሄራዊ አንድነት ግንባታ፤ ብዝሀ ልሳን የሆነ የፖለቲካ ማህረሰብ ግንባታ፤ ብሄራዊ መግባባት እና እርቅን በመጠቀም ዘላቂ ሰላም ግንባታ ረገድ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል። ከምግብ ዋስትና ጥያቄ የተሻገረ የዜጎች የምርጫ አድማስ የሚያሰፋ የበለጸገ ኢኮኖሚ መገንባት፤ የዜጎች የስራ ዕድልና ተጠቃሚነት መብት ማረጋገጥ፤ የኑሮ ውድነት ማረጋጋትና መቆጣጠር፤ አካታችና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚያረጋግጥ የብብሀ ዘር ኢኮኖሚ ልማት ስትራቴጂ መከተል፤የአረንጓዴ አሻራ ስራን በማጠናር አረንጓዴ ኢኮኖሚ መገንባት፤ ጥራቱን የጠበቀ ፍትሀዊ የመሰረተ ልማት ስርጭት ማረጋጥ፤ ፍትሀዊና ጥራት ያላቸው መሰረተ ልማት መዘርጋት፤ ለቀጣዩ ትውልድ ዕዳን የማያወርስ ዘላቂ የልማት ፋይናንስ ማረጋገጥ፤ የህዝባችንን ፍላጎት የሚያሟላ ፍትሐዊ የማበህራዊ አገልግሎት ስርዓት መዘርጋት እና ተያያዥ ጉዳዮችም ተከናውነዋል። በአዲሱ 2017 አመትም የተሻለ ስራ ለመስራት እንደ መንግስት በፖለቲካዊ፤ ማህበራዊና ኢኮኖሚ ዘርፎች ኢላማዎች ተቀምጠው ለተፈጻሚነቱ ርብርብ የሚደረግ ይሆናል፡፡ ሁሌም ቢሆን ዕድገትና ብልጽግና ሁለንተናዊ መሆን ስለሚገባው በሁሉም አካባቢዎችና ዘርፎች የሚጠበቀውን ውጤት ለማስመዝገብ እጅ ለእጅ ተያይዘን አዲሱ አመትን ለነገው ትውልድ አሻራ አስቀምጠን ማለፍ የምንችልበት እንዲሆን ጥሪዬን አቀርባለሁ። ለሁሉም ነገር መሰረቱ ከአእምሯችንና ከውስጣችን የሚጀምር በመሆኑ ሁላችንም ራሳችንን ለለውጥና ለእድገት ዝግጁ በማድረግ ለሀገሬ ምን አደረግኩ? ብለን በመጠየቅ ለቀጣይ ትውልድ ማውረስ የምንችለውን ግዴታ በመወጣት ሀላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል። በአዲሱ አመት በአዲስ መንፈስ በአዲስ መነሳሳት ለኢትዮጵያችን ከፍታና ለብልጽግናችን የራሳችንን አሻራ እንድናኖር ጥሪዬን እያቀረብኩኝ በድጋሜ እንኳን አደረሳቹህ አደረሰን እላለሁ።
መልካም ስራዎችን ለነገ ማስቀጠል እና ለተተኪው ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ ተጠቆመ
Sep 10, 2024 99
ደብረ ማርቆስ/ ወልዲያ ጳጉሜን 5/2016 (ኢዜአ)፡- ነገ ከዛሬ የተሻለና ያማረ እንዲሆን መልካም ስራዎችን በላቀ ስኬት ለተተኪው ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ገለፀ። ጳጉሜን 5 ''የዛሬ ትጋት ለነገ ትሩፍት'' በሚል መሪ ሃሳብ በደብረ ማርቆስ እና ወልዲያ ከተሞች በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ውሏል። የከተማ አስተዳደሩ ተወካይ ከንቲባ መኮንን ሙሉአዳም እንዳሉት፤ ነገ የተሻለ እና ያማረ እንዲሆን የተከናወኑ ስራዎች ማሳየት ቀጣይ እንዲደገሙ እና እንዲጠናከሩ የሚያስችል ነው። ትናንት በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የተሰሩ ስህተቶችና ዋጋ ያስከፈሉ ችግሮችን በማረም ለነገ እንዳይሻገሩ ማድረግ እንደሚገባም ተናግረዋል። በተለይ ህጻናት ነገን የሚረከቡ የአገር ባለተስፋዎች በመሆናቸው በጎ ተግባራትን፣ ልማቶችን እና እሴቶቻችን ባህል አድርገው እንዲቀበሉ ማድረግ የግድ እንደሚል ገልጸዋል።   የከተማ አስተዳደሩ ከተማ እና መሰረተ ልማት መምሪያ ምክትል ስራ አስኪያጅ ዲያቆን ሰለሞን ይግረም በበኩላቸው እንደገለጹት፤ ተቋማቸው በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የህብረተሰቡን የመሰረተ ልማት ፍላጎት እና ጥያቄ ለመመለስ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። በተለይ ከተማዋን በማዘመን ለነዋሪዎቿ ሳቢ እና ማራኪ ከማድረግ አኳያ በርካታ ስራዎች እና የኮሪደር ልማቶች እየተከናወኑ መሆኑን አብራርተዋል። ለነገ መልካም ትሩፋት ደግም አሰራሮችን በቴክኖሎጅ በማስደገፍ ፈጣን እና የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት የተዘጋጅ መሆኑን ጠቅሰው፤ የተጀመሩ ልማቶችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። በተመሳሳይ "ነገን ስኬታማ የምናደርገው ዛሬ ላይ ሆነን ትርጉም ያለው ተግባር ስናከናውን ነው" ያሉት ደግሞ የወልዲያ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዱባለ አብራሬ ናቸው። አዲሱን ዓመት ስንቀበልና ነገን ስናስብ ከምንም በላይ የዘርፈ ብዙ ስራችን ስኬት ለሆነው "ሠላም" ልዩ ትኩረት በመስጠት ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል። ስለ ሰላም እየተጋን፣ ችግረኞችን እየፈታን፣ ያለፈውን ዓመት ቁርሾ በፍጹም ቅን ልቦና በመተው ለአዲሱ ዓመት ልንዘጋጅ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። የወልዲያ ከተማ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አስራት በሪሁን በበኩላቸው፤ ለአዲሱ የትምህርት ዘመን 4 ሺህ 200 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል። ይህም በቀጣይ በትምህርት ቁሳቁስ አቅርቦት እጥረት ምክንያት አንድም ተማሪ ከትምህርት ገበታ ውጪ እንዳይሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ ድጋፉም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። "የተደረገልኝ ድጋፍ ጠንክሬ እንድማርና የተሻለ ውጤት እንዳስመዘግብ መነሳሳት ፈጥሮብኛል" ያለችው በእቴጌ ጣይቱ ብጡል አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ወይንሸት ተገኘ ናት። በአማራ ክልል የጳጉሜን 5 የነገ ቀን በተለያዩ አካባቢዎች በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።
በአዲሱ አመት  ለአዳዲስ ውጤቶች ለመብቃት በትጋት እንሰራለን -ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው 
Sep 10, 2024 100
ሆሳዕና ፤ ጳጉሜ 5/2016 (ኢዜአ)፦ በአዲሱ አመት ለአዳዲስ ውጤቶች ለመብቃት ብርታታችንን፣ ፅናታችንንና ትጋታችንን ከፍ በማድረግ እንሰራለን ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው አስታወቁ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው አዲሱን አመት አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት በአዲሱ ዓመት አዲስ ተስፋ ሰንቀን፣ አዳዲስ ዕቅዶችን ይዘን ፣ ለአዳዲስ ውጤቶች ለመብቃት ብርታታችንን፣ ፅናታችንን ፣ ትጋታችንን ከፍ በማድረግ እንሰራለን ። "እንዲሁም አዲሱ ዓመት እምቅ አቅሞቻችንን እና ፀጋዎቻችንን አስተባብረን በማንቀሳቀስ አዳዲስ ውጤቶችን እውን ለማድረግ በጋራ የምንተጋበት ዓመት ነው" ብለዋል። ለዚህም መላው የክልሉ ሕዝቦች የበኩላችውን አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው አመልክተዋል፡፡ "አዲሱ ዓመት በክልላችን በሁሉም መስኮች እመርታ የምናሳይበት፣ በሀሳብና በተግባር ተዋህደን ጠንካራ አንድነት በመፍጠር አዳዲስ ስኬቶችን የምናስመዘግብበት እንዲሆን እመኛለሁ" ሲሉ ገልፀዋል ። ለአዲሱ ዓመት ለ2017 ዓመተ ምህረት፣ የዘመን መለወጫ በዓል እንኳን በሠላም አደረሰን! አደረሳችሁ! በማለት ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ለክልሉ ህዝብ መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የአብሮነት፣ የስኬትና የሐሴት እንዲሆንም ተመኝተዋል ።  
ለነገው ትውልድ የበለፀገች ኢትዮጵያን ለማስረከብ ዛሬ ላይ ተግተን ልንሰራ ይገባል
Sep 10, 2024 105
ሶዶ፣ ጳጉሜ 5/2016 (ኢዜአ)፦ ለነገው ትውልድ የበለፀገች ኢትዮጵያን ለማስረከብ ዛሬ ላይ በትጋት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጳጉሜ 5 "የነገ ቀን" "የዛሬ ትጋት፤ ለነገ ትሩፋት" በሚል መሪ ቃል በወላይታ ሶዶ ከተማ በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል። የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጋቱ ዳንሳ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት "ለነገው ትውልድ የበለፀገች ኢትዮጵያን ለማስረከብ ዛሬ ላይ ተግተን ልንሰራ ይገባል" ብለዋል። የነገው ትውልድ በሀገሩ የሚኮራና በጠንካራ አንድነት የሚያምን እንዲሆን ማስቻል ዛሬ የኛ ኃላፊነት ነው ሲሉ ተናግረዋል። የነገው ትውልድ የነገ አገር ተረካቢ በመሆኑ ዛሬ ላይ በመልካም እሴትና ስነምግባር በማነፅ ለአገሩ የሚጠቅም ዜጋ መፍጠር እንደሚገባ ተናግረዋል። "የዛሬውም ትውልድ ኩሩ ኢትዮጵያዊ የሆነው ትናንት ጀግኖች አባቶቻችን በከፈሉት ሁለንተናዊ መስዋእትነት መሆኑን መገንዘብ ይገባል "ብለዋል። በመሆኑም ከቤተሰብ ጀምሮ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አመልክተው መልካም ፍሬ ለማየት መልካም ዘር መዝራት እንደሚገባ ጠቁመዋል። የወላይታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ ዶክተር ዳንኤል ዳሌ በበኩላቸው ዘንድሮ የጳጉሜ አምስቱ ቀናት ትርጉም በሚሰጥ መልኩ በተለያዩ ሁነቶች መከበራቸውን ተናግረዋል። የዛሬ ህጻናት ነገን በተሻለ ተስፋ እንዲጠብቁና ለዛም እንዲሰሩ ከስር ጀምሮ በመልካም መንገድ ኮትኩቶ ማሳደግ እንደሚገባም አመልክተዋል። አክለውም "እኛ ከአባቶቻችን የተረከብናትን ውብ አገር ለቀጣይ ትውልድ በሚበልጥ ደረጃ ለማስረከብ ልንጥር ይገባል" ብለዋል። መርሃግብሩ ላይ በህጻናትና ወጣቶች የተዘጋጁ የተለያዩ ትርዒቶችና ዝግጅቶች ቀርበዋል።

ማህበራዊ
የልማት ስራዎች የሁሉንም ተሳትፎና ተጠቃሚነት መሰረት በማድረግ ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Sep 11, 2024 66
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2017(ኢዜአ):- የልማት ስራዎች የሁሉንም ተሳትፎና ተጠቃሚነት መሰረት በማድረግ ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባዋን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በመዲናዋ 21ኛው የምገባ ማእከል በይፋ ስራ አስጀምረዋል።   የምገባ ማእከሉ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አየር ጤና አካባቢ በበረከት ወርቁ (በበረከት ገበሬዋ) ድጋፍ የተገነባ ነው፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር፤ በአዲስ አበባ የተገነቡ የምገባ ማእከላት በቀን አንድ ጊዜ በራሳቸው መመገብ የማይችሉ ወገኖችን የሚመግቡ ናቸው ብለዋል። ለማእከላቱ እውን መሆንም የተለያዩ የግል ተቋማትና ባለሃብቶች እያደረጉት ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የምገባ ማዕከላቱ ወገኖችን ከመመገብም ባለፈ ለብዙዎች የስራ እድል እየፈጠሩ ስለመሆኑም ገልጸዋል። ከበረከት ወርቁ ጋር በመተባበር አየር ጤና አካባቢ የተገነባው 21ኛው የተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከልም በዛሬው እለት ለአገልግሎት በቅቷል ብለዋል። የማእከሉን ግንባታ አጠናቀው ያስረከበችው ባለሃብቷ በረከት ወረቁ፤ ለዜጎች የሚጠቅም በጎ ተግባር መፈፀም ከምንም በላይ የላቀ ደስታ የሚፈጥር መሆኑን ተናግራለች። የተገነባው የምገባ ማዕከል በራሱ ገቢ እንዲተዳደር የግብርና ምርቶች የሚሸጡበት ሱቆች የተካተቱበት ስለመሆኑ ጠቅሳለች። ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር በቀጣይም 22ኛውን የተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከል ለመገንባት ዝግጁ መሆኗን ባለሃብቷ አረጋግጣለች።
ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመትን በሚኖሩባቸው አገራት አከበሩ
Sep 11, 2024 76
አዲስ አበባ፤መስከረም 1/2017 (ኢዜአ):- በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን የአዲስ ዓመት በዓልን አክብረዋል። በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አዲስ ዓመትን ኢትዮጵያውያን፣ የኢትዮጵያ ወዳጆች፣ የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ሌሎች ተቋማት አመራሮች እንዲሁም ተቀማጭነታቸውን ኬንያ ያደረጉ ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ በተገኙበት ተከብሯል። በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ የኢትዮጵያ አዲስ አመት እንደ አገር አንድነታችን የምንጠናክርበትና የወደፊት የጋራ እድሎቻችንን በጋራ የምንቀበልበት ልዩ ቀን ነው ብለዋል። የዘንድሮውን አዲስ ዓመት ስናከብር ኢትዮጵያና ኬንያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበት 60ኛውን ዓመት ጭምር በማክበር እንደሆነ ገልጸዋል።   የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዴኒስ ምቡሩ ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈዋል። በሕንድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በአገሪቷ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን አዲስ ዓመትን አክብሯል።   የኤምባሲው ምክትል ሚሲዮን መሪ አምባሳደር ብዙነሽ መሰረት ኢትዮጵያ የ13 ወራት የዘመን አቆጣጠር ያላት አገር መሆኗንና ይህም በአገር ውስጥና በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመትን በጋራ እንዲያከብሩ የሚያደርግ ልዩ አጋጣሚ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት በተለያዩ መስኮች ስኬት ማስመዘገቧንና ይህንንም በአዲሱ ዓመት ዘላቂ ልማትን እውን በማድረግ አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ከሕንድ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጎልበት እንደምትሰራም ገልጸዋል። በበዓሉ አከባበር ላይ ኢትዮጵያውያን፣ የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ የንግዱ ማህበረሰብና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።   በተመሳሳይ የአዲስ ዓመት በዓል በጣልያን ሮም ተከብሯል። በጣልያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ አዲሱ አመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነትና የምንበለጽግበት ጊዜ እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። አዲሱ ዓመት የተሻለች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስረከብ ተግተን የምንሰራበት፣ እጅ ለእጅ ተያይዘን ልማትን ለማረጋገጥ ጠንካራ ርብርብ የሚደረግበትና በጋራ የምንቆምበት ዓመት ነው ብለዋል:: የዳያስፖራ ተወካዮችም በበኩላቸው ኤምባሲው ዳያስፖራው ከአገሩ ጋር ያለውን ትስስር እንዲያጠናከር እያከናወነ ያለውን ስራ አመስግነው በአዲሱ ዓመት ለተሻለ ውጤት እንደሚተጉ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ የ2017 አዲስ ዓመት አንካራ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተከብሯል።   በተርኪዬ የኢትዮጵያ አምባሳደር አደም መሐመድ አዲስ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ እና የስኬት ዘመን እንዲሆን ተመኝተዋል። የኤምባሲው ዲፕሎማቶችና ሰራተኞች በአዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያ ልማት፣ሰላምና ዲሞክራሲ ግንባታ ስራ የበለጠ አስተዋጽኦ በሚያበረክት መልኩ የዲፕሎማሲ ስራዎችን በተቀናጀና በላቀ ሁኔታ እንዲያከናውኑ አሳስበዋል። ጀርመን፣ኩዌትና ዩናይትድ ኪንግደም በዓሉ ከተከበረባቸው አገራት መካከል ይገኙበታል።
በቀን አንዴ መመገብ ለማይችሉ ወገኖቻችን 21ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል የአዲስ ዓመት ስጦታ አድርገን እነሆ ብለናል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Sep 11, 2024 113
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2017(ኢዜአ):- በቀን አንዴ እንኳን መመገብ ለማይችሉ ወገኖቻችን 21ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል የአዲስ ዓመት ስጦታችን አድርገን እነሆ ብለናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። በአዲስ ዓመት በቀን 1 ሺህ ሰዎችን የሚመግበውን 21ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አየር ጤና አካባቢ መርቀን በቀን አንዴ እንኳን መመገብ ለሚቸገሩ ወገኖቻችን መልካም አዲስ ዓመት ብለን ምገባ አስጀምረናል ብለዋል።   ከተማችንን ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት ለማድረግ ከጀመርናቸው ስራዎች አንዱ በቀን አንዴ እንኳን መመገብ የሚቸገሩ ወገኖቻችንን መመገብ ሲሆን 21ኛውን የምገባ ማዕከል በረከት ገበሬዋ ገንብታ አስረክባናለች ሲሉም ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል። በቀጣይም ሙሉ ወጪውን ችላ 22ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ገንብታ ለወገኖቿ ለማስረከብ ቃል መግባቷንም ጠቁመዋል። ለበጎነቷ በተጠቃሚ ነዋሪዎቹ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ላመሰግናት እወዳለሁ ሲሉም አክለዋል በመልዕክታቸው።
ኢኮኖሚ
የምርት አቅርቦት የተሳለጠ በማድረግ የዋጋ መረጋጋት ለመፍጠር የመንግሥትና የግል አጋርነት ተጠናክሮ ይቀጥላል
Sep 10, 2024 99
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2016(ኢዜአ)፦ የምርት አቅርቦት የተሳለጠ በማድረግ የዋጋ መረጋጋት ለመፍጠር የመንግሥትና የግል አጋርነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለፁ። በባሮክ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ከነሐሴ 20 እስከ ጳግሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ሲካሄድ የቆየው ባዛርና ኤክስፖ ዛሬ ማምሻውን ተጠናቋል። በመዝጊያ መርኃ ግብሩ የተገኙት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ በመላ አገሪቱ አማራጭ የገበያ እድሎችን የማስፋት ሥራ ሲሰራ ቆይቷል።   በተለይም የቅዳሜና እሁድ ገበያዎችና መሰል የገበያ እድሎች በዓል ወቅት አስፈላጊ ምርት በማቅረብ ዋጋ በማረጋጋትና የኅብረተሰቡን ፍላጎት ተደራሽ በማድረግ ትልቅ አስተዋጽዖ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል። በዚህም መንግሥት በተለይም ከግሉ ዘርፍ ጋር በመተባበር ውጤታማ ሥራ መሰራቱን ጠቅሰው በቀጣይም የምርት አቅርቦት የተሳለጠ በማድረግ የዋጋ መረጋጋት ለመፍጠር የመንግሥትና የግል አጋርነት ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። በሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው ባዛርና ኤክስፖ አስመጪዎችና አምራቾች ከሸማች በቀጥታ የኅብረተሰብ ክፍል ጋር በመገበያየት የምርት አቅርቦት የተሳለጥ ማድረጋቸው ገልጸዋል። እንደዚህ አይነት የንግድ ባዛርና ኤግዚቢሽኖች ዓመት በዓል ተንተርሰው የሚፈጠሩ ሰው ሰራሽ የገበያ እጥረትን ለመከላከል አስተዋጽኦ የሚያደርጉ መሆኑንም ገልጸዋል። በዚህ ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች በትክክለኛው የማምረቻ ዋጋ ሸቀጦች ለገበያ በማቅረብ የሚያደርጉትን አስተዋጽዖ አጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል።    
በአዲስ አበባ የዛሬ የዋዜማ የገበያ ውሎ ምን ይመስላል?
Sep 10, 2024 105
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2016(ኢዜአ)፦ ኢዜአ በአዲስ አበባ በሚገኙ የተለያዩ የገበያ ሥፍራዎች ተዘዋውሮ የዶሮ፣ የእንቁላል፣ የቁም እንስሳና የሌሎች ግብይቶችን ተመልክቷል። በሸጎሌ ገበያ ሲገበያዩ ያገኘናቸው አቶ ወንድወሰን ከበደ ከባለፈው የፋሲካ በዓል ጋር ሲነጻጸር የዘንድሮ ገበያ የዋጋ ጭማሪ አሳይቷል ብለዋል። በተለይም ቀደም ባለው የበዓል ገበያ የበግ ዋጋ ከ10 አስከ 11 ሺህ ብር ይገዛ እንደነበር ገልፀው አሁን ላይ 16 እና 17 ሺህ መድረሱ ይናገራሉ። የቁም ከብት በብዛት መግባቱን ገልፀው ዋጋቸው ከ40 እስከ 200 ሺህ ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ የተናገሩት ደግሞ በዛው በሸጎሌ ገበያ ያገኘናቸው አቶ ጥላሁን በርሄ ናቸው። አቶ ጥላሁን በዘንድሮው የአዲስ ዓመት ገበያ መጠነኛ ጭማሪ እንጂ ቅናሽ እንደሌለ ጠቁመዋል። በሌላ በኩል በመገናኛ ሾላ ገበያ ያገኘናቸው አቶ ቴዎድሮስ ተሾመ በዘንድሮው የአዲስ ዓመት በዓል የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ አለመኖሩ ይናገራሉ።   የሸኖ፣ የጎጃምና የወለጋ አንድ ኪሎ ቅቤ ቂቤ መያዛቸው ገልፀው ከ750 እስከ 900 ብር ድረስ፤ ቆጮ ከ200-250 ብር፤ በተመሳሳይ ማር ከ500 እስከ 700 ብር ድረስ እንደሚሸጥ ነግረውናል። ከሌሎች ምርቶች በተለየ ሁኔታ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ካሳዩ ምርቶች መካከል ኮረሪማ እንደሚገኝበትም ለማወቅ ችለናል። በአዲሱ ገበያ አካባቢ በሚገኘው ሾላ ገበያ ያገኘናቸው ወይዘሮ አልማዝ ገመዳ የዶሮ ዋጋ ከባለፈው የፋሲካ በአል ሲነፃፀር የዋጋ ጭማሪ ማሳየቱ ገልጸዋል። እንቁላል ከ12 ብር ጀምሮ እስከ 18 ብር ድረስ እየተሸጠ እንደሚገኝም ተዘዋውረን ተመልክተናል። ሸማቾቹ ነጋዴው ማኅበረሰብ የወቅቱ ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶች ሊያቀርቡ ይገባል ብለዋል። የኢትዮጵያ መገለጫ የሆነው መተጋገዝና መተባበራችን በማስቀጠል ያለው ለሌለው በማካፈልና በመተጋገዝ በደስታ ልናሳልፈው ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።
በክልሉ ጠንካራ የፓርቲ አደረጃጀት መፍጠር የሚያስችሉ ተቋማትን የመገንባት ሥራ እየተሰራ ነው - አቶ አብርሀም ማርሻሎ 
Sep 10, 2024 99
ሀዋሳ ፤ጳጉሜን 05/2016 (ኢዜአ)፦ ሲዳማ በክልል ጠንካራ የፓርቲ አደረጃጀት መፍጠር የሚያስችሉ ተቋማትን የመገንባት ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝ በብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈቤት ኃላፊ አቶ አብርሀም ማርሻሎ ገለፁ ። በሀዋሳ ከተማ አራት ክፍለ ከተሞች ላይ በአባላትና ደጋፊዎች የሚገነቡ የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈትቤት ሕንፃዎች ሥራ ለማስጀመር መሠረት ድንጋይ የማኖርና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ተካሂዷል፡፡ በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሀም ማርሻሎ እንደገለጹት፤ በክልሉ ጠንካራ የአመለካከትና የሰው ኃይል አደረጃጀት ከመፍጠር ባለፈ ህዝብን በተሻለ ትጋት ማገልገል የሚያስችል ተቋማዊ አደረጃጀት ለመፍጠር ምቹ ሕንፃዎች መገንባት አስፈልጓል፡፡ በክልል ደረጃ እስከ 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ሊፈጁ የሚችሉ 48 ሕንፃዎች እንደሚገነቡ አቶ አብርሀም አብራርተዋል ፡፡ የሕፃዎቹ ግንባታ እስከ አራት ወር ድረስ እንደሚጠናቀቅ ጠቁመው፤ዲዛይናቸውና ሥነ ውበታቸው ለከተሞች መልካም ገፅታ እንደሚፈጥሩና ለሌሎች ማስተማሪያ እንደሚሆኑም አመልክተዋል። ለህንፃዎቹ ግንባታ ከአባላቱና ከደጋፊዎች የሚያገኘውን ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሰርቶ ለማጠናቀቅ የሚያስችል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡   የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ መኩሪያ ማርሻዬ በከተማዋ አራት ክፍለ ከተሞች ላይ የሚገነቡት ሕንፃዎች አጠቃላይ እስከ 300 ሚሊዮን ብር እንደሚፈጁ ጠቅሰዋል። ለእዚህም አባላትና ደጋፊዎቹ በገንዘብ፣ በዓይነትና በሙያ የተገኘ ድጋፍ የፓርቲውን አባላት ጥንካሬ እና በማንኛውም ተልዕኮ ላይ ያላቸውን ተነሳሽነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።   በገቢ ማሰባሰቢያው ላይ ድጋፍ ካደረጉ መካከል በግንባታ ማዕድን ቁፋሮና አቅራቢነት ሥራ ላይ የተሰማሩት አቶ ቦንጌ ዋኤ ለሕንፃ ግንባታው አሸዋና ጠጠር ከማቅረብ ባለፈ 1 ሚሊዮን 100 ሺህ ብር ለመስጠት ቃል መግባታቸውን ተናግረዋል ፡፡ "ከፓርቲውና ከመንግስት ጎን በመቆም አገራችንን ማልማት አለብን" ከሚል እሳቤ ተነስተው ድጋፉን ማድረጋቸውን ተናግረዋል ፡፡ በሆቴልና በሕንፃ ሥራ ተቋራጭ ሥራ ላይ የተሰማሩት አቶ ጌቱ መታፈሪያ በሕንፃ ግንባታው አስፈላጊውን ሁሉ ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡ "በፓርቲው አመራር ሰጪነት በከተማችን የኮሪዳር ልማትን ጨምሮ በርካታ የልማት ሥራዎች እየተሰሩ ነው" ያሉት አቶ ጌቱ፤ "አቅሜ በፈቀደው ሁሉ እስከመጨረሻው ድረስ ድጋፍ እያደረግኩ ቀጥላለሁ" ብለዋል ፡፡ በመርሀ ግብሩ ላይ የክልልና የከተማ አስተዳደሩ የፓርቲና የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም አባላትና ደጋፊዎች የተገኙ ሲሆን በጥሬ ገንዘብ 221 ሚሊዮን ብር ቃል ተገብቷል ፡፡  
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ለግብርና ናሙና ቆጠራ የሚውል የድጋፍ ሥምምነት ከፋኦ ጋር ተፈራረመ
Sep 10, 2024 107
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ለግብርና ናሙና ቆጠራ ስራ ድጋፍ የሚያገኝበት ሥምምነት ከዓለም ምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ጋር ዛሬ ተፈራርሟል። ሥምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በከር ሻሌ (ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ የፋኦ ተወካይ ፋራይ ዚሙድዚ ፈርመውታል። በስምምነቱ አማካኝነት አገልግሎቱ 475 ሺህ ዶላር የገንዘብና የሙያ ድጋፍ ያገኛል።   የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በከርሻሌ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት፤ ለዓለም አቀፍና ለአገር አቀፍ ለግብርና ፓሊሲ ግብዓት የሚሆን የግብርና ናሙና ቆጠራ በ2017 እንደሚካሄድ ተናግረዋል። የቆጠራውን መረጃ የግብርናውን ትራንስፎሜሽንን ለማፋጠንና አዳዲስ የግብርና ሥልቶችን በመቀየስ የዘርፉን ምርትና ምርታማነት ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።። ሥምምነቱ የባለሙያዎችን የቴክኖሎጂን የመጠቀም አቅም የሚያሳድግ፣ ልምድና ተሞክሮ እንዲገኙ የሚያስችል በመሆኑ ባለሙያዎች ጥራት ያለውና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ቆጠራ እንዲያካሂዱ ያስችላል ነው ያሉት።   በኢትዮጵያ የፋኦ ተወካይ ፋራይ ዚሙድዚ በበኩላቸው፤ ድርጅቱ ኢትዮጵያ የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እያደረገች ያለውን ጥረት እንደሚደግፍ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የምታካሂደው የግብርና ቆጠራ ለዓለም አቀፍና ለአገሪቱ የግብርና ፖሊሲዎች ግብዓት የሚውል መሆኑን አመልክተዋል። ድጋፉ የግብርና ናሙና ቆጠራው ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና ጥራት ያለው እንዲሆን የሚያስችል ነውም ብለዋል።  
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የክህሎት ውድድር እየተሳተፈች ነው
Sep 11, 2024 63
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2017 (ኢዜአ):-ኢትዮጵያ በፈረንሳይ ሊዮን እየተካሄደ ባለው 47ኛው የዓለም አቀፉ የክህሎት ውድድር እየተሳተፈች ትገኛለች። የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን “የክህሎት ኦሊምፒክ” የሚል ስያሜ ያገኘውን ውድድር ትናንት በይፋ አስጀምረዋል።   ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታዎች በሶስት ክህሎት ዘርፎች (ICT and Networking, CNC Machine, Furniture Making ) ተወክላ ውድድሩ ላይ እየተሳተፈች እንደምትገኝ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በውድድሩ ላይ ተሳታፊ የሆነችው በ2016 በጀት አመት የዓለም ክህሎት ማህበረሰብ (World Skills Member ) አባል መሆኗን ተከትሎ እንደሆነ አመልክተዋል። ዓለም አቀፉ የክህሎት ውድድር እስከ መስከረም 5 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል። በውድድሩ ላይ ከ70 አገራት የወጣጡ 1 ሺህ 400 ወጣቶች ይሳተፋሉ። ወጣቶቹ የተለያዩ የክህሎትና የፈጠራ ስራዎቻቸውን በማቅረብ ውድድራቸውን ያደርጋሉ። የውድድሩ አላማ በየጊዜው እየተለወጠች ባለው ዓለም የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ያላቸውን ወሳኝ ሚና ማሳየት መሆኑ ተገልጿል።
ኢትዮጵያ ራዕይ ያላቸውና የሚተጉ የፈጠራ ወጣቶች ካሏት በአጭር ጊዜ መለወጥና ማደግ ትችላለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Sep 9, 2024 198
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ራዕይ ያላቸውና የሚተጉ የፈጠራ ወጣቶች ካሏት በአጭር ጊዜ ወለወጥና ማደግ ትችላለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የ2016 ዓ ም ሰመር ካምፕ ሰልጣኞች የምርቃት መርሐግብር ተካሂዷል። በመርሐ ግብሩ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት፤ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ላይ የተጀመረው ሥራ ለነገ መልካም ፍሬ ዛሬ የሚዘራ ምርጥ ዘር ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለመጀመሪያና ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እየሰጠ ያለው ስልጠና ለኢትዮጵያ መፃኢ ትውልድ የተሻለ የፈጠራ ሰው መሆን ወሳኝ ነው ብለዋል።   ተማሪዎች መንግሥት ለቴክኖሎጂ ትኩረት መስጠቱንና ለሥራቸው ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረ መሆኑን መገንዘብ አለባቸው ብለዋል። ለአብነትም በዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ቴክኖሎጂ አንዱ የዕድገት መሠረት ሆኖ በእቅድ እየተሠራበት መሆኑን ገልጸዋል። ሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎችን ለማዘመን ቴክኖሎጂ ወሳኝ ሚና ስለሚጫወት ትኩረት ተሰጥቶታል ነው ያሉት። በቅርቡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዲጂታል ፊርማን በይፋ ማስጀመሩን ጠቅሰው፤ይህ በሀገር ልጆች የተሠራ እና ለቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ፋይዳው የላቀ መሆኑን አንስተዋል። በሀሰተኛ ማንነት የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመቀነስና ወጥ አሠራርን ለመተግበር ኢትዮጵያውያን ዲጂታል መታወቂያ እንዲኖራቸው የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አንስተዋል። አሁን ላይ ለ10 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች ምዝገባ የተደረገ ሲሆን፥ የዲጂታል መታወቂያ ትግበራ ለወጣቶችና ታዳጊዎች ጠቀሜታው የላቀ መሠረተ ልማት ነው ብለዋል። የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ስልጠና በቴክኖሎጂ እውቀት ብቁ ወጣቶችን በማፍራት ለፈጠራና ለተወዳዳሪነት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነው ብለዋል። በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የተጀመሩ የዲጂታል ሥራዎችም ለፈጠራ ሰዎች ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥሩ አንስተዋል። አገራት በቴክኖሎጂ ያደጉት ለወጣቶችና ታዳጊዎች በሰጡት ትኩረት መሆኑን አንስተዋል።   ኢትዮጵያ በትጋት ስኬታማ ፈጠራን የሚያከናውኑ ወጣቶች ካሏት፤ በቅርቡ ቴክኖሎጂን ከሚፈጥሩ አገራት ጎራ መሰለፍ እንደምትችልም አንስተዋል። በመሆኑም ተማሪዎች በስልጠና ቆይታቸው ያገኙትን እውቀት በመጠቀም በፈጠራና በትጋት ለለውጥ ማዋልና መመራመር ይገባቸዋል ነው ያሉት። የእነዚህ ተስፈኛ ታዲጊ ወላጆችም ልጆቻቸውን በአግባቡ እየቀረፁ በመሆናቸው ሊኮሩ እንደሚገባ ጠቅሰዋል። ኢንስቲትዩቱ የተፈጠረለትን ዓላማ እያሳካ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የዛሬ ተመራቂዎች ከራሳቸው ባለፈ ለብዙዎች የእንጀራ ምንጭ የሚሆኑ ናቸው ብለዋል።   የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር)፣ ለሁለት ወራት በቆየው ስልጠና ከመላ ሀገሪቱ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 200 ተማሪዎች ተከታትለዋል ብለዋል። የዘንድሮው የሰመር ካምፕ ስልጠና ሰልጣኞች የቴክኖሎጂ ስብጥርን፣ ፈጠራና ችሎታን ያሳዩበት በግልና በቡድን ስኬታማ መሆንን በተግባር ያረጋገጡበት መሆኑን ጠቅሰዋል። ተማሪዎች በቀጣይ ጉዟቸው አዲስ ነገርን የማወቅ ሂደታቸው ላይ ፈተናዎች ለዕድገት እድል መሆኑን በመረዳት መትጋትና መሥራት እንደሚገባቸው አንስተዋል።      
የኢትዮጵያን ስም በዓለም ከፍ አድርገው የሚያስጠሩ ቴክኖሎጂዎችን እንፈጥራለን- የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ተመራቂ ተማሪዎች
Sep 9, 2024 155
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2016(ኢዜአ)፦የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን አደራ በመቀበል የሀገራቸውን ስም የሚያስጠሩ ችግር ፈች ቴክኖሎጂዎችን ለመፍጠር እንደሚተጉ የ2016 ሰመር ካምፕ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ተመራቂ ተማሪዎች ተናገሩ። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ላለፉት ሁለት ወራት ሲያሰለጥናቸው የነበሩ የ2016 ሰመር ካምፕ ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል። በስልጠናው ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ 200 ተማሪዎች ስለ ኮምፒውተር ቋንቋ፣ ስለ ሰው ሰራሽ አስተውሎት የመረጃ ትንተና፣ ስለ ማሽን ማላመድና ሌሎችም የቴክኖሎጂ ጉዳዮች በቂ ስልጠና መከታተላቸው ታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በምርቃቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ተማሪዎች ያገኙትን እውቀት በመጠቀም ኢትዮጵያን ወደ ፊት የሚያራምድ ራዕያቸውን ለማሳካት እንዲተጉ አደራ ብለዋል። ያነጋገርናቸው ሰልጣኞች በበኩላቸው ስልጠናው በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዙሪያ በቂ እውቀት ያገኙበት፣ በተግባር የታገዘና ለፈጠራ የሚያነሳሳ ነው ብለዋል።   የ11ኛ ክፍል ተማሪው ኖላዊ ሰይፈ ፥ በስልጠናው ያገኙት እውቀት በተግባር ልምምድ የታገዘና ለፈጠራ መንገድ ከፋች ነበር ብሏል።   የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ወስዶ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ውጤት በመጠባበቅ ላይ የሚገኘው ተማሪ ናሆም መስፍን፥ ለሰው ሰራሽ አስተውሎት እውቀት አስፈላጊ ስለሆነው የኮምፒውተር ቋንቋ ሌሎች መሰረታውያን ግንዛቤ ማግኘቱን ተናግሯል።   የ10ኛ ክፍል ተማሪዋ መልካም አስራት በበኩሏ፥ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ ፕሮጀክትን እውን የማድረግ የሀሳብ አድማሷን ወደ ተግባር የሚለውጥ ስልጠና ማግኘቷን አንስታለች። ተማሪ ኮኬት ግርማ ስልጠናው ውስን ግንዛቤ በነበራት ጉዳዮች ላይ በቂ እውቀት የጨበጠችበትና አርቲፊሻለ ኢንተለጀንስን የተረዳችበት ስልጠና መሆኑን ተናግራለች። ተማሪዎቹ ሀገራዊ ችግሮችን የሚፈቱ ፕሮጀክቶችንም ፈጥረዋል። ለአብነትም ተማሪ ኖላዊ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ "የማዳበሪያ አጠቃቀም አማካሪ" መተግበሪያን መስራቱን ያነሳል። በዚህም በሀገሪቱ ያለውን የማዳበሪያ አጠቃቀም ችግር በመቅረፍ የአፈርን መጎዳት ለመከላከል ግብ ይዟል። መተግበሪያው የግብርና ባለሙያዎች ለአርሶ አደሮቹ በቀላሉ የአፈር ማዳበሪያ አጠቃቀምን ለማስረዳት ያግዛቸዋል ነው ያለው። ተማሪ መልካም በበኩሏ የኮሌራ በሽታ አምጭ ተህዋስን በውሃ ውስጥ መኖር አለመኖሩን የሚለይ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መሳሪያ መፍጠሯን ገልጻለች። መሳሪያው ወደ ተግባር ቢውል ለሀገሯና ለአፍሪካ የኮሌራ ችግርን ለመቅረፍ ያስችላል ትላለች። የዲጅታል መሳሪያዎችን የሰው ሰራሽ አስተውሎት እንዲኖራቸው የማላመድና መረጃን ተንትኖ ውሳኔ የመስጠት ፕሮጀክትን ቀርጾ እየሰራ እንደሚገኝ የተናገረው ደግሞ ተማሪ ናሆም ነው። አሁን ላይ በሀገሪቱ የዳታ ማዕከል እየተስፋፋ መምጣቱና ዲጅታል የመረጃ ማሰባሰብ ስራዎች መጀመራቸውም ለእርሱና መሰል ፕሮጀክቶች መሳካት እንደሚያግዝ ነው ያነሳው። ተማሪዎቹ አክለውም አሁን ላይ በኢትዮጵያ የተጀመሩ የዲጅታላይዜሸን ስራዎችና መሰረተ ልማቶች ለፈጠራ ስራዎቻቸው ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥሩ ጠቁመዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተሰጣቸው አደራ ለለውጥ የሚያነሳሳ እንደሆነ ገልጸዋል። ሀገራቸውን በእውቀትና በትጋት በማገልገልና ችግር ፈች ቴክኖሎጂዎችን በማመንጨት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጣቸውን አደራ እውን እንደሚያደርጉም ጠቁመዋል። በቴክኖሎጂው መስክ ኢትዮጵያን የሚያኮራ እና ስሟን በዓለም ከፍ አድርጎ የሚያስጠራ ፈጠራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
የአቪዬሽን ኢንዱስትሪውን ከትምህርት ተቋማት ጋር በማቀናጀት የሰለጠነ የሰው ኃይል የማፍራት ተግባር እየተከናወነ ነው
Sep 7, 2024 210
ጅማ፤ ጳጉሜን 2/2016(ኢዜአ):- የአቪየሽን እንዱስትሪውን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በማቀናጀት የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራትና ዘርፉን በጥናትና ምርምር የመደገፍ ተግባር እያከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታወቀ። ባለስልጣኑ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የአቪዬሽንና የህዋ ሳይንስ የስልጠና መርሃ ግብር መስጠት ሊጀምር መሆኑም ተገልጿል። ዛሬ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የተቋማቱ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የአቪዬሽን ሳይንስ አካዳሚው በይፋ ተከፍቷል። የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ጌታቸው መንግስቴ በወቅቱ እንደገለፁት፤ መርሃ ግብሩ ከትምህርት ተቋማት ጋር በመቀናጀት ዘርፉን በሰው ሀይል ለማጎልበት ያግዛል። የአቪዬሽን ሳይንስ የስልጠና መርሀ ግብር ከተቋሙ ውጪ ለመጀመርያ ጊዜ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ሊሰጥ ስምምነት ላይ ተደርሶ በይፋ የተከፈተ መሆኑንም ገልጸዋል። ኢንዱስትሪው ሰፊና የሰለጠነ የሰው ኃይልን የሚፈልግ መሆኑን ያነሱት ዳይሬክተሩ በውስጡም የአቪዬሽንና የህዋ ሳይንስን ያጠቃለለ ነው ብለዋል። ዘርፉን በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ በስልጠና የሰው ኃይል ፍላጎትን ለማሟላትና ለቴክኖሎጂ ሽግግር ትልቅ ሚና እንዳለው ተናግረዋል። ስልጠናው ከከፍተኛ የትምህርት ተቋም ጋር በቅንጅት መሰጠቱ ኢንዱስትሪውን በጥናትና ምርምር ለመደገፍ እና የልህቀት ማዕከል ለማድረግ ያስችላል ብለዋል። የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል አባ ፊጣ በበኩላቸው በዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ የዘርፉ ተቋማት ጋር በመተባበር የአቪዬሽን ሳይንስና የኤሮ-ስፔስ ኢንጂነሪንግ አካዳሚ መከፈቱን ገልፀዋል። ዩኒቨርሲቲው አካዳሚውን ለመክፈት ካቀደ የቆየ ቢሆንም ለሁለት ዓመት ዝግጅት ሲደረግ ቆይቶ ዛሬ ላይ እውን ሊሆን መቻሉ ለአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ትልቅ እመርታ ነው ብለዋል። የአቪዬሽንና የኢሮ-ስፔስ ኢንጂነሪንግ አካዳሚን በመክፈቱ ሂደት የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ፣ የአየር ኃይልና የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑንም ገልፀዋል። በጅማ ዩኒቨርሲቲ አራት መደበኛ የትምህርት መርሀ ግብሮችና ሁለት የእስፔሻላይዜሽን ኮርሶች የሚሰጡ ሲሆን በቀጣይ ሴሚስተርም መሰጠት እንደሚጀምሩ ጠቁመዋል። በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ የባለስልጣኑና የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር አባላት፣ የአካባቢው አስተዳደር ኃላፊዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።
ስፖርት
መንግስት አካል ጉዳተኞች በስፖርቱ ያላቸውን ተሳትፎ ለማጠናከር በትኩረት ይሰራል -ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ
Sep 10, 2024 117
አዲስ አበባ፤ጳጉሜን 5/2016(ኢዜአ)፦መንግስት አካል ጉዳተኞች በስፖርቱ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ገለጹ። በ17ኛው የፓራሊምፒክ ጨዋታዎች የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብቷል። ልዑካን ቡድኑ ዛሬ ማለዳ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል ተደርጎለታል።   የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ አትሌቶች በፓራሊምፒክ ውድድር ከባለፉት ጊዜያት የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብና ስሟ በመልካም እንዲነሳ ስላደረጋችሁ ኮርተንባችኋል እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። መንግስት በስፖርት ፖሊሲው ትኩረት ከሰጣቸው ጉዳዮች መካከል አካል ጉዳተኞች በስፖርቱ ያላቸውን ተሳትፎ ማሳደግ አንዱ መሆኑን ገልጸው ይህን የበለጠ ለማጠናከር በትኩረት ይሰራል ብለዋል። መንግስት በውድድሩ ተሳትፎ ላደረገውና አመርቂ ውጤት ላስመዘገበው የልዑካን ቡድን የእውቅናና ሽልማት እንደሚያዘጋጅ ጠቁመዋል። በ1500 ሜትር ሙሉ ለሙሉ የአይነ ስውር ምድብ (T-11) የራሷን የዓለም ክብረ ወሰን በማሻሻል የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘችው አትሌት ያየሽ ጌቴ ውድድሩ ፈታኝ ቢሆንም ጫናዎችን በመቋቋም ለማሸነፍ በመቻሏ ደስተኛ እንደሆነች ገልጻለች።   በቀጣይ በተለያዩ ርቀቶች በመወዳደር ኢትዮጵያን ለማስጠራት እቅድ እንዳላት ተናግራለች። የአትሌት ያየሽ ጌቴ አሯሯጭና አሰልጣኝ ክንዱ ሲሳይ የወርቅ ሜዳሊያ መገኘቱንና የዓለም ክብረ ወሰን መሻሻሉ ድርብ ድል መሆኑን ገልጿል። ለፖራሊምፒክ ስፖርት ትኩረት መስጠት ከተቻለ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ውድድሩ ማሳያ መሆኑን አመልክቷል። በ1500 ሜትር ጭላንጭል ውድድር(T-13) የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘችው አትሌት ትዕግስት ገዛኸኝ እንደ ቡድን የተደረገው ዝግጅት ለውጤቱ መገኘት ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጻለች። በሁለት ተከታታይ የፓራሊምፒክ ጨዋታዎች የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘት አዲስ ታሪክ በመስራቷና የኢትዮጵያን ስም ከፍ በማድረጓ ክብር ይሰማኛል ብላለች። በ150ዐ ሜትር አይነ ስውራን ምድብ(T-11) የብር ሜዳሊያ ያገኘው አትሌት ይታያል ስለሺ በመጀመሪያ ተሳትፎው ባስመዘገበው ውጤት መደሰቱን ገልጾ አገሩን ወክሎ በመወዳደሩ ኩራት እንደተሰማው ተናግሯል። በቀጣይ ዓለም አቀፍ ውድድሮች አገሩን በመወከል የወርቅ ሜዳሊያ እንደሚገኝ ሙሉ እምነት አለኝ ሲል ገልጿል። የኢትዮጵያ ፖራሊምፒክ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ንጋቱ ሀብተማርያም ለውድድሩ ለሁለት ወራት ገደማ የተደረገው ዝግጅት ለውጤቱ መምጣት አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጿል። በቀጣይ ውድድሮች ውጤታማ ለመሆን የተሳታፊ አትሌቶችና የውድድር አይነቶችን መጨመርና ለፓራሊምፒክ ስፖርት የበለጠ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ አመልክቷል። ከነሐሴ 22 እስከ ጳጉሜን 3 ቀን 2016 ዓ.ም በፓሪስ በተካሄደው 17ኛው የፓራሊምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በ2 የወርቅና 1 የብር በድምሩ ሶስት ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከዓለም 44ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች። ኢትዮጵያ በዘንድሮው ፓራሊምፒክ ያገኘችው የሜዳሊያ ብዛት እ.አ.አ በ2021 በቶኪዮ በተካሄደው 16ኛው የፓራሊምፒክ ጨዋታዎች ካገኘችው አንድ የወርቅ ሜዳሊያ የተሻለ ሆኖ ተመዝግቧል። ኢትዮጵያ ቶኪዮ ላይ 56ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ የሚታወስ ነው።
በፓራሊምፒክ ጨዋታዎች የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ
Sep 10, 2024 106
አዲስ አበባ ፤ ጳጉሜን 5/2016 (ኢዜአ)፦ በ17ኛው የፓራሊምፒክ ጨዋታዎች የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብቷል። ልዑካን ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነትና የዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ(ዶ/ር) እና የኮሚቴው አመራሮች እንዲሁም ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል። ከነሐሴ 22 እስከ ጳጉሜን 3 ቀን 2016 ዓ.ም በፓሪስ በተካሄደው 17ኛው የፓራሊምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በ2 የወርቅና 1 የብር በድምሩ ሶስት ሜዳሊያዎችን በማግኘት 44ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች። ኢትዮጵያ በዘንድሮው ፓራሊምፒክ ያገኘችው የሜዳሊያ ብዛት እ.አ.አ በ2021 በቶኪዮ በተካሄደው 16ኛው የፓራሊምፒክ ጨዋታዎች ካገኘችው አንድ የወርቅ ሜዳሊያ የተሻለ ሆኖ ተመዝግቧል። ኢትዮጵያ ቶኪዮ ላይ 56ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ የሚታወስ ነው።
በክልሉ "የኅብር ቀን"  የስፖርት ዘርፉን በማነቃቃት የእርስ በእርስ ግንኙነትን በሚያጠናክር አግባብ ታስቦ እየተከበረ ነው 
Sep 9, 2024 175
ባህርዳር፤ ጳጉሜን 4/2016(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል "የኅብር ቀን"ን የስፖርት ዘርፉን ከማነቃቃት ባለፈ ሰላምንና የእርስ በእርስ ግንኙነትን በሚያጠናክር አግባብ ታስቦ እየተከበረ መሆኑን የክልሉ ወጣትና ስፖርት ቢሮ ገለጸ። ጳጉሜን 4 ''የኅብር ቀን'' የባህር ዳር ከተማ እና ሰሜን ጎጃም ዞን በጋራ በስፖርታዊ ጨዋታዎችና በሰብዓዊ ድጋፍ ታስቦ በመከበር ላይ ይገኛል። የክልሉ ወጣትና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ እርዚቅ ኢሳ እንዳሉት፤ ፤ ስፖርት ህብረ ብሄራዊነትን በመጠበቅ ለጋራ ግብ በጋራ መስራት እንደሚቻል ማሳያ ነው። "የኅብር ቀን" በክልሉ የስፖርት ዘርፉን ከማነቃቃት ባለፈ ሰላምንና የእርስ በእርስ ግንኙነትን የበለጠ በሚያጠናክር አግባብ ታስቦ በመከበር ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በክልሉ የስፖርት ዘርፉን በመደገፍ በአካል ብቃቱ የጎለበተ ትውልድ ከመገንባት ባሻገር ህብረ ብሔራዊነትን በማጉላት ለላቀ ስኬት የሚያበቁ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል። የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር እና የሰሜን ጎጃም ዞን በጋራ "የኅብር ቀን"ን በስፖርታዊ እንቅስቃሴ መከበሩ ቀኑን የበለጠ እንዲጎላ እንዳደረገው አስረድተዋል። ስፖርት አካላዊና አዕምሯዊ ብቃቱ የተሟላ ዜጋ ከማፍራት ባሻገር የአንድነትና የጥንካሬ መገለጫ ነው ያሉት ደግሞ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው ናቸው። ስፖርት የሰላም መሆኑን ጠቅሰው፤ "የኅብር ቀን" ሲከበርም ሰላምንና አንድነትን ይበልጥ በሚያጎለብት አግባብ መሆን እንዳለበት አመልክተዋል። መረሃ-ግብሩ በስፖርታዊ ጨዋታና በሰብዓዊ ድጋፍ ታስቦ እየተከበረ ሲሆን፤ በአከባበሩ ሥነ-ሥርዓት ላይ የክልል፣ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር፣ የሰሜን ጎጃም ዞን አመራር አባላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። ጳጉሜን -4" ኅብራችን ለሰላማችን" በሚል መሪ ሃሳብ " የኅብር ቀን" የኢትዮጵያዊያን ቋንቋ፣ ባህል፣ ታሪክ፣ እምነት፣ መልክዓ ምድርና ማኅበራዊ መስተጋብር በሚያንጸባርቅ መልኩ ታስቦ ይውላል። የኢትዮጵያዊያን ኅብረ ብሔራዊ ማንነት የጥንካሪ መሰረት በመሆኑ በዕለቱ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ተንጸባርቆ እንደሚውልም ታውቋል።  
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ሁለተኛ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዋን ዛሬ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ታደርጋለች
Sep 9, 2024 146
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2016 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሁለተኛ የምድብ ማጣሪያ የሜዳ ጨዋታውን ዛሬ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ያካሂዳል። የብሔራዊ ቡድኑ ጨዋታ ከምሽቱ 4 ሰዓት 60 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው ቤንጃሚን ምካፓ ስታዲየም ይከናወናል። በምድብ 8 የምትገኘው ኢትዮጵያ በመጀመሪያ ጨዋታዋ ከታንዛንያ ጋር ያለ ምንም ግብ አቻ መለያየቷ ይታወቃል። ውጤቱንም ተከትሎ በአንድ ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ተጋጣሚው የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታው የጊኒ አቻውን 1 ለ 0 በማሸነፍ ሶስት ነጥብ አግኝቷል። በ48 ዓመቱ ፈረንሳዊ አሰልጣኝ ሰባስቲየን ዲሳብሬ የሚመራው የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ብሔራዊ ቡድን በሶስት ነጥብ ምድቡን እየመራ ይገኛል። በአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከመጀመሪያው ጨዋታ በኋላ ባሉት ቀናት ልምምዱን በታንዛንያ ሲያደርግ ቆይቷል። ዋልያዎቹ የመጨረሻ ልምምዳቸውን ትናንት ማምሻውን ጨዋታው በሚካሄድበት ቤንጃሚን ምካፓ ስታዲየም ማድረጋቸውን ኢዜአ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በልምምድ ላይ ህመም አጋጥሞት የነበረው አብነት ደምሴ እንዲሁም ጉዳት ላይ የነበረው ወገኔ ገዛኸኝ ወደ ልምምድ መመለሳቸውንም ገልጿል። ሀገራቱ በሁሉም ውድድሮች ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 6 ጨዋታዎች ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አራት ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ስትይዝ ኢትዮጵያ አንድ ጊዜ አሸንፋ አንድ ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥተዋል። በፊፋ የሀገራት የእግር ኳስ ሰንጠረዥ ኢትዮጵያ 143ኛ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ 6ዐኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። የ38 ዓመቱ አልጄሪያዊ ላህሉ ቤንብራሃም የሁለቱን ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ በዋና ዳኝነት ይመራሉ። በምድብ 8 የሚገኙት ጊኒና ታንዛንያ ነገ ከምሽቱ 1 ሰዓት ኮትዲቯር በሚገኘው ቻርልስ ኮናን ባኒ ስታዲየም ይጫወታሉ። በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ 48 ሀገራት በ12 ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በውድድሩ ላይ 24 ሀገራት ይሳተፋሉ።
አካባቢ ጥበቃ
በክልሉ ችግኝ የተተከሉባቸው ስፍራዎችን በመለየትና ባለቤት በመስጠት   እንክብካቤ እየተደረገ  ነው
Sep 8, 2024 211
ዲላ ፤ ጳግሜ 3/2016 (ኢዜአ) ፡- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በመደበኛና በአረንጓዴ አሻራ መረሃ ግብር ችግኝ የተተከሉባቸው ስፍራዎችን በመለየትና ባለቤት በመስጠት የተጠናከረ ጥበቃና እንክብካቤ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ደን አከባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ ገለጸ። ቢሮው የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸምና የታያዘው ስራ ዘመን ዕቅድ ግምገማ በዲላ ከተማ አካሂዷል። በዚህ ወቅት የቢሮው ሃላፊ አቶ ግዛቴ ግጄ እንዳሉት፤ በክልሉ ባለፈው የበጀት ዓመት ከ79 ሺህ 700 ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ባላቸው ችግኞች ተሸፍኗል። ሶስት ሺህ ሄክታር የቀርከሃ ደንን ጨምሮ ለሀገር በቀልና ለፍራፍሬ ችግኞች ትኩረት ተሰጥቶ ስለመተከሉም ጠቅሰዋል። በመደበኛና በአረንጓዴ አሻራ መረሃ ግብር ችግኝ የተተከለባቸው ስፍራዎችን ለይቶ ካርታ በማዘጋጀትና ባለቤት በመስጠት የተጠናከረ ጥበቃና እንክብካቤ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይ ከ4 ሺህ 900 ሄክታር በላይ የሚሸፍኑ ተራሮችን ጨምሮ በሌሎችም አካባቢዎች አርሶ አደሩ፣ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እያስተዳደሩ እንደሚገኙም አስረድተዋል። ይህም አማካይ የጽድቀት መጠን ከማሻሻል ባለፈ የደን ሽፋንን በማሳደግ ለግብርና ልማት አስተዋጾኦው የጎላ ነው ብለዋል። በተራቆቱና ተራራማ አካባቢዎች ልማትን በማጠናከር የአደጋ መጠንን ከመቀነስ ባሻገር የግብርና ልማትን ማጎልበት የቀጣይ ትኩረት መሆኑን አመላክተዋል። በተለይ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ደን የይዞታ ማረጋገጫ እንዲኖራቸው ከማድረግ ባለፈ ለ"ካርቦን ፋይናንስ" ሽያጭ የሚያግዙ መረጃዎችን ለማደራጀት በትኩረት እንደሚሰራም ተናግረዋል።   በዞኑ የተራቆቱና ለናዳ የተጋለጡ ተራሮችን በመለየት የአፈርና ውሃ ጥበቃ እንዲሁም የችግኝ ተከላ በማካሄድ ለማልማት ርብርብ እየተደረገ ነው ያሉት ደግሞ የወላይታ ዞን ደንና አከባቢ ጥበቃ ልማት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መርክነህ ማሌዳ ናቸው። ችግኝ የተተከሉባቸው ቦታዎችን ባለቤት በመስጠት ጥበቃና እንክብካቤ እየተደረገለት መሆኑን አመልክተዋል። በግምገማው መድረክ የክልል የዞንና የወረዳ የዘርፉ አመራር አባላትና ባለሙያዎች፣የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን፤ ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መረሃ ግብሩ ተጠናቋል።  
በክልሉ የልማት እንቅስቃሴን ከአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ጋር በማስተሳሰር ንጹህ አካባቢን ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ ነው
Sep 6, 2024 263
ዲላ ፤ ጳጉሜን 01/2016 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የልማት እንቅስቃሴዎችን ከአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ጋር በማስተሳሰር ንጹህና ጤናማ አካባቢን ለመፍጠር ህብረተሰቡን ያሳተፈ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ደንና አካባቢ ጥበቃ ልማት ቢሮ ገለጸ። የውሃ ብክለትና ድምጽ ሁከት ግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄ መድረክ በክልል ደረጃ በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ የክልል፣ የዞንና የከተማ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና የዘርፉ ባለሙያዎች እንዲሁም የሃይማኖት ተቋማት መሪዎችና የኢንዱስትሪ ባለቤቶች እየተሳተፉ ናቸው። የቢሮው ኃላፊ አቶ ግዛቴ ግጄ በወቅቱ እንደገለጹት፤ በክልሉ ባለፉት አምስት ወራት "ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ" በሚል በተከናወኑ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ለውጦች እየመጡ ነው።   በተለይ የልማት እንቅስቃሴዎችን ከአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ጋር በማጣጣም ንጹህና ጤናማ አካባቢን ለመፍጠር ህብረተሰቡን ያሳተፈ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። "አካባቢን ከብክለት መከላከል ትውልድን የመጠበቅ ጉዳይ ነው" ያሉት አቶ ግዛቴ፤ ይሁንና ዛሬም የውሃ ብክለትና የድምጽ ሁከት ለክልሉ አሳሳቢ ችግር መሆኑን አንስተዋል ። በተለይ ከተሞች ቆሻሻ የማመንጨት አቅማቸው ማደግና የአወጋገድ ሥርዓት የዘመነ ያለመሆን አካባቢን ለጉዳት መዳረጉን አንስተዋል። ይህም ህብረተሰቡን የጤና ችግር ተጋላጭነታቸውን ከማስፋት ባለፈ ብዝሃ ሕይወትን እያወከ መሆኑን አስረድተዋል። እንዲሁም ከኢንዲስትሪዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት ከትራንስፖርትና የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት የሚለቀቁ ከመጠን ያለፉ ድምጾች የክልልን ህዝቦች በሰላም የመኖር መብት ከማወክ ባለፈ አካላዊና ስነ ልቦናዊ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን ገልጸዋል። የንቅናቄ መድረኩም ችግሩን በመለየትና በማሳወቅ የተቀናጀ መፍትሄ ለመስጠት ያለመ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለዚህም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በነቂስ መሳተፍ እንዳለበት አሳስበዋል። በተለይ በክልል ምክር ቤት የጸደቁ የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማና የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር አዋጆችን መሰረት የውሃ ብክለትና የድምጽ ሁከት የሚያስቀጣ መሆኑን ጠቅሰው፤ ህብረተሰቡ ብክለትን በመከላከል የድርሻውን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።    
አረንጓዴ አሻራ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የ10 ዓመት ብዝሃ ሕይወት እቅድ ጋር ሊተሳሰር ነው
Sep 6, 2024 252
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 1/2016(ኢዜአ)፡-የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርን ከተመድ የ10 ዓመት ብዝሃ ሕይወትን ዳግም ወደ ነባር ሕልውናው የመመለስ እቅድ ጋር የማስተሳሰር ፍላጎት እንዳለው የድርጅቱ የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም አስታወቀ። በኮትዲቭዋር ላለፉት ሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 10ኛው የአፍሪካ የአካባቢ ሚኒስትሮች ልዩ ጉባኤ ዛሬ ተጠናቋል። ልዩ ጉባኤው “ድርቅን በመቋቋም፤ የመሬት መራቆት እና በረሃማነት የመዋጋት ርምጃ የማፋጠን ጥረትን ማሳደግ” በሚል መሪ ሀሳብ ተከናውኗል።   የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መኮንን ከጉባኤው ጎን ለጎን ከተመድ የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ኢንገር አንደርሰንና ከተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ማዕቀፍ (UNFCCC) ዋና ፀሐፊ ሳይመን ስቲል ጋር ተወያይተዋል። ሚኒስትር ዴኤታው ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች የአየር ንብረትና የከባቢ አየር ፖሊሲዎች ቀርጻ በቁርጠኝነት እየተገበረች መሆኑን ገልጸዋል። መንግስት የአየር ንብረትን ለውጥን ለመከላከል የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርን እየተገበረ እንደሚገኝና እስከ አሁን ከ32 ቢሊዮን በላይ ችግኝ መተከሉን አመልክተዋል። በአረንጓዴ አሻራ የኢትዮጵያ የደን ሽፋን 2011 ዓ.ም ከነበረበት 17 ነጥብ 2 በመቶ በ2015 ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ከፍ ማለቱን ጠቅሰዋል። አረንጓዴ አሻራና የሌማት ትሩፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የምግብ ስርዓትን ለመለወጥ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኝ ነው ሚኒስትር ዴኤታው የገለጹት። የተመድ የተለያዩ ተቋማት የኢትዮጵያን የአየር ንብረት ለውጥና ከባቢ አየር ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ውጤታማነት የሚያደርጉት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በጉባኤው ያላትን መሪነት ተጠቅማ በሕዳር ወር 2017 ዓ.ም በአዘርባጃን ባኩ በሚካሄደው 29ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP29) የአፍሪካን ድምጽ አንድ ለማድረግ እየሰራች ነው ብለዋል። የተመድ የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ኢንገር አንደርሰን አረንጓዴ አሻራን ጨምሮ የአካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ኢኒሺዬቲቮች ላይ እየወሰደች ያለው የአመራርነት ሚና አድንቀዋል። የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራሙ አረንጓዴ አሻራ የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በቅርቡ ይፋ ያደረጉት የ10 ዓመት ብዝሃ ሕይወት ዳግም ወደ ሕልውናው የመመለስ እቅድ (UN Decade of Ecological Restoration) ጋር ለማጣጣምና ለማስተሳሰር ፍላጎት አለው ብለዋል። ፕሮግራሙ ከኢትዮጵያ ጋር በአካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥን መከላከል ላይ ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚፈልግም አመልክተዋል። የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ማዕቀፍ (UNFCCC) ዋና ፀሐፊ ሳይመን ስቲል ኢትዮጵያ እየተገበረቻቸው ያሉ የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጠሚያ እቅዶች በመተግበር እያሳየች ያለው ቁርጠኝነት አድንቀዋል። ዋና ፀሐፊው ኢትዮጵያ ለእቅዶቹ ተፈጻሚነት የሚያስፈልጋትን ሀብት ለማፈላለግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸው ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ መናገራቸውን ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ እያስከተላቸው ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ቁርጠኛ አቋም ይዛ እየሰራች ነው
Sep 5, 2024 271
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 30/2016 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ እያስከተላቸው ያሉ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ለመፍታት ቁርጠኛ አቋም ይዛ እየሰራች እንደምትገኝ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መኮንን ገለጹ። በኢትዮጵያ የሚመራው 10ኛው የአፍሪካ የአካባቢ ሚኒስትሮች ልዩ ጉባኤ ዛሬ በኮትቭዋር አቢጃን መካሄድ ጀምሯል።   ልዩ ጉባኤው “Raising Ambition for Accelerating Action on Drought Resilience and Combating Land Degradation and Desertification” በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ነው። የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መኮንን በጉባኤው መክፈቻ ባደረጉት ንግግር የመሬት መራቆት፣ የበረሃማነት መስፋፋትና ድርቅ የአፍሪካ ቁልፍ የልማትና የደህንነት ተግዳሮቶች ናቸው ብለዋል። የአየር ንብረት ለውጥ የሁሉም ችግሮች ምንጭና አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑንም ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መንግስትና ሕዝብ የመሬት መራቆት፣ የበረሃማነት መስፋፋትና ድርቅ መቋቋሚያ ተጨባጭ እርምጃዎችን በቁርጠኝነት እየወሰደ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያ የደን ሽፋን 2011 ዓ.ም ከነበረበት 17 ነጥብ 2 በመቶ በ2015 ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ማደጉን ነው ሚኒስትር ዴኤታው በማሳያነት የጠቀሱት። በዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ ችግኝ መተከሉንና ነሐሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ 615 ነጥብ 7 ሚሊዮን ችግኝ መተከሉን ገልጸዋል። የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን ሕዝብ በማስተባበር የተከናወነው ተግባር ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እየወሰደች ላለው ተጨባጭ እርምጃ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል። ሚኒስትር ዴኤታው የኢትዮጵያን እድገት የሚያፋጥኑ የተለያዩ የፖሊሲ እርምጃዎች እየወሰደች መሆኗንም ገልጸዋል። የምግብና የስርዓተ ምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጫ ፕሮግራሞች፣ የከተሞች ዘላቂ ልማትና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ማበረታቻ እየተወሰዱ ካሉ እርምጃዎች እንደሚጠቀሱና ሌሎች አገራትም ተሞክሮ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ የአፍሪካ የአካባቢ ሚኒስትሮች ጉባኤ መሪነት ከተቀበለችበት ነሐሴ 2015 ዓ.ም አንስቶ በርካታ የጉባኤውን ውሳኔዎች እንዲተገበሩ በማድረግ ከፍተኛ የመሪነት ሚና እየተጫወተች እንደምትገኝም ነው ሚኒስትር ዴኤታው የገለጹት። የአፍሪካ የአካባቢ ሚኒስትሮች ጉባኤ አፍሪካ በዓለም አቀፍ የአካባቢ መድረኮች በአንድ ድምጽ መወከል ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው የአፍሪካ ሀገራትን በአካባቢ ልማት የሚያስተሳስሩ የፖሊሲ እርምጃዎች አስፈላጊ መሆናቸውን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ለነዚህ ተግባራት ስኬታማነት አበክራ እንደምትሰራም በመግለጽ። ጉባኤው እስከ ነገ የሚቆይ ሲሆን የተለያዩ ውሳኔዎችና የጋራ አቋሞችን ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት በማደግ ላይ የሚገኙ አገራትን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ እንዲሰሩ  የማሻሻያ ስራዎች ተጀምረዋል - አንቶኒዮ ጉተሬዝ 
Sep 5, 2024 332
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 30/2016 (ኢዜአ)፡- የመንግስታቱ ድርጅት ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት በማደግ ላይ የሚገኙ አገራትን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ እንዲሰሩ የማሻሻያ ስራዎች መጀመሩን የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ50 የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች የታደሙበት የቻይና-አፍሪካ የትብብር ጉባዔ ትናንት በቤጂንግ ተከፍቷል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የቻይናን ያልተቋረጠ ድጋፍ ታደንቃለች ብለዋል። በጉባኤው ላይ የተገኙት የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ከሲጂቲኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ አፍሪካ የቅኝ አገዛዝ ድርብ ተጠቂ መሆኗን ጠቅሰው ጉዳቱ የሚጀምረው ራሱ የቅኝ አገዛዝ ካደረሰባት ጫና መሆኑን አስታውቀዋል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት ያደረሱባት የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ሌላው ጫና መሆኑን ተናግረዋል። የቅኝ አገዛዙ ድርብ ጫና በፈጠረባቸው ፈተና በርካታ የአፍሪካ አገራት ህልውናቸውን በራሳቸው አቅም ማስቀጥል የማይችሉ እንደነበሩ ገልጸዋል። በዚህም አፍሪካ በዓለም አደባባይ በበቂ ሁኔታ መወከል አለመቻሏን በማንሳት ተግባሩን ነጥለን ካየነው በተለይም አህጉሪቱ በኢኮኖሚና በፋይናንስ ዘርፍ የደረሰባት መገለል በጣም አሳሳቢ መሆኑን ተናግረዋል። ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት በማደግ ላይ የሚገኙ አገራትን ፍላጎት በበቂ ሁኔታ ለመሸፈን አለመፈለጋቸውና አገራቱ በተቋማቱ ውስጥ በሚፈለገው ልክ አለመወከላቸው ችግሩን አባብሶታል ብለዋል። ይሀንን ችግር ለመፍታት የመንግስታቱ ድርጅት ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማትን አሰራር ለማሻሻል ስራዎች መጀመሩን ጠቅሰዋል። ማሻሻያው በማደግ ላይ የሚገኙ አገራትን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ እንዲተገበር እየሰራን ነው ብለዋል። ቻይና ዘላቂነት ያለውን የምዕተ ዓመቱን የልማት ግብ ለማሳካትና የራሷን ጨምሮ በማደግ ላይ ያሉ አገራትን ፍላጎት ለሟሟላት ከፍተኛ ኃላፊነት ወስዳ እየሰራች መሆኑን ዋና ፀሐፊው አስረድተዋል። የቻይና አፍሪካ ግንኙነት የደቡብ-ደቡብ ትብብርን የሚያንጸባርቅ መሆኑን በመጥቀስ ቻይና አፍሪካ የምትፈልገውን ኢንቨስትመንት በማቅረብ በኩል የሚጠበቅባትን ሚና እየተወጣች መሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ በመሰረተ ልማት፣ ትምህርትና ጤና ዘርፍ ያሉባትን ጉድለቶች ለመሙላት በምታደርገው ጥረት የቻይና እገዛ ከፍተኛ ቦታ ይይዛል ብለዋል። ቻይና ለአፍሪካ አገራት እያደረገች ያለው እገዛ ትልቅ እድል ይዞ መምጣቱን የተናገሩት ዋና ፀሐፊው አጀንዳ 2030ን ለማሳካት የቻይና አስተዋጽኦ ከፍተኛ ቦታ እንዳለው ተናግረዋል። ዘላቂነት ያለውን የምዕተ ዓመቱን የልማት ግብ ለማሳካት ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማትን ማሻሻል ዋነኛው እርምጃ መሆኑን አስታውቀዋል። ለሦስት ቀናት በሚካሔደው የቻይና-አፍሪካ የትብብር ጉባዔ እአአ እስከ 2027 በሚኖረው የቻይና እና አፍሪካ ግንኙነት የትብብር ሰነዶች ላይ ውይይት ተደርጎ ስምምነት እንደሚፈረም ይጠበቃል።  
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቻይና-አፍሪካ ትብብርን ይደግፋል - አንቶኒዮ ጉቴሬዝ
Sep 5, 2024 289
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 30 /2016(ኢዜአ)፡- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቻይናና አፍሪካ ትብብርና አጋርነትን እንደሚደግፍ የድርጅቱ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ። የቻይና-አፍሪካ ጉባኤ ዛሬ በቤጂንግ መካሄድ ጀምሯል። የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር ላይ ዓለም በግጭቶችና ማህበራዊ ቀውሶች ውስጥ እያለፈች እንደምትገኝና ተግዳሮቶቹ ለእድገትና ልማት ትልቅ ፈተና መሆናቸውን ገልጸዋል። የአፍሪካ አገራት በእዳ ቀውስ ፈተና ውስጥ መግባታቸውንና ለዘላቂ ልማት መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ መቸገራቸውን አመልክተዋል። ኢ-ፍትሐዊና ጊዜው ያለፈበት ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት ማሻሻያ እንደሚያስፈልገውና የፋይናንስ ተቋማት ፍትሐዊ በሆነ መልኩ የፋይናንስ አቅርቦትን ተደራሽ ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። በማደግ ላይ የሚገኙ አገራት ፈታኝ የገበያ ሁኔታዎች ተቋቁመው የዘላቂ ልማት ግቦችን እንዲያሳኩ የሚያደርግ የፋይናንስ ድጋፍ ማዕቀፍ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። ይህም የአገራትን የፋይናንስ ተደራሽነት በማሳደግ የመካከለኛና የረጅም ዘመን መፍትሔ እንዲያበጁ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል። በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓቱ ፍትሐዊ ማሻሻያ ለማድረግ የአፍሪካና ቻይና ሚና ቁልፍ መሆኑን ነው ዋና ፀሐፊው የገለጹት። ከዚህ አኳያም የደቡብ-ደቡብ ትብብር የአገራትን አቅም ለመገንባትና የልማት ግቦችን በጋራ እውን ለማድረግ የሚያስችል ማዕቀፍ እንደሆነ ተናግረዋል። ቻይና ከአፍሪካ ጋር ያላት አጋርነት የደቡብ-ደቡብ ትብብር ዋንኛ ምሰሶ ነው ብለዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቻይና-አፍሪካ ትብብርና አጋርነት እንደሚደግፍ ዋና ፀሐፊው ገልጸዋል።
ባንኩ የአየር ንብረት ለውጥን ለመደገፍ ከ150 ሚሊየን ዶላር  በላይ ድጋፍ አገኘ
Sep 5, 2024 312
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 29/2016(ኢዜአ)፦በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚደገፈው አረንጓዴ የአየር ንብረት ፈንድ በአፍሪካ ቀንድ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚውል 151 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማጽደቁን የአፍሪካ ልማት ባንክ ማስታወቁን ዥንዋ ዘገበ። በአፍሪካ ልማት ባንክ የሚደገፈው ይኸው ፕሮግራም "በአፍሪካ ቀንድ ለምግብና ለኑሮ ተስማሚ የአየር ንብረት ለውጥን መገንባት" የሚለው የባንኩ ቡድን የገንዘብ ድጋፍ በጅቡቲ፣ በሶማሊያ፣ በኬኒያ፣ በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን 4 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሰዎችን ተጠቃሚ እንደሚሆኑም አመልክቷል። የአፍሪካ ልማት ባንክን ጠቅሶ እንደዘገበው "አዲሱ የገንዘብ ድጋፍ ማኅበረሰብ ተኮርና የሥርዓተ-ፆታ መመጣጠንን የሚቋቋም መፍትሄዎችን ይደግፋል" መባሉን ዥንዋ ዘግቧል። ዘላቂ የመሬት አስተዳደር ተግባራትን የአየር ንብረት ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ተደራሽነት፣ ታዳሽ ኃይል፣ የህብረት ስራ ማህበራት አቅም ግንባታ፣ አግሪ ቢዝነስ እና የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ተቋማት፤የብድር፣የአየር ንብረት አገልግሎት፣ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶች፣ እና የኢንሹራንስ የመረጃ ጠቋሚ ጉዳዮችን ማሻሻል የሚሉት መፍትሄዎችን እንደሚረዳ ባንኩ መግለጹን ዘገባው ጠቅሷል። የባንኩ የግብርና እና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ዳይሬክተር ማርቲን ፍሬጌን የአፍሪካ ልማት ባንክ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ቁርጠኛ መሆኑን መግለጻቸውን ዘገባው አመልክቷል። የአረንጓዴ የአየር ንብረት ፈንድ ድጋፍ ማሰባሰብ የአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድን ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገርና ቀጣይነት ያለው የግብርና ሥርዓትን በአፍሪካ ቀንድ ለማሳደግ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል፣በዚህም በድራችን በጣም ተጋላጭ ከሆኑ አካባቢዎች በአንዱ የምግብ ዋስትናን ያሻሽላል ብለዋል ሲል ጠቅሷል። ለፕሮግራሙ ከጸደቀው የገንዘብ ድጋፍ ውስጥ 90 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ሲሆን የ60 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ብድር መሆኑን ዥንዋ በዘገባው አመልክቷል። የአፍሪካ ልማት ባንክ በ2025 በመጀመሪያ ሩብ ዓመት ተግባራዊ ማድረግ የሚጀምረው ድጋፍ እንደሚያስተዳድርና ፕሮግራሙን እንደሚቆጣጠርም ማስታወቁንም ዘገባው ጠቅሷል። የአፍሪካ ቀንድ ከአየር ንብረት ጋር በተያያዘ ያልተስተካከለ የዝናብ ስርጭት፣ለሙቀት መጨመር፣ ለድርቅና ጎርፍ አደጋዎች ተጋላጭ መሆኑን የአፍሪካ ልማት ባንክ ማመልከቱን ዘገባው አንስቷል። የአየር ንብረት ለውጥ ለሰው፣ ለእንስሳትና ለሰብልና በሽታዎች መጨመርና ለየመሬት መራቆትን በማባባስ ምርታማነትን እንዲቀንስ ማድረጉንም ባንኩ መግለጹን አንስቷል።
ሐተታዎች
የጸጥታና ደኅንነት ተቋማት የሪፎርም ስራዎች የሉዓላዊነት ጽኑ መሰረቶች
Sep 7, 2024 316
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 2/2016(ኢዜአ)፦በጸጥታና ደኅንነት ተቋማት የተከናወኑ የሪፎርም ስራዎች የኢትዮጵያን የሉዓላዊ ክብር የሚያጸኑ መሰረቶች ናቸው። የኢትዮጵያ የዘመን መሸጋገሪያ የሆነችው አስራ ሶስተኛዋ የጳጉሜ ወር ቀናት ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በተለያየ ስያሜ በሀገር አቀፍ ደረጃ በድምቀት እየተከበሩ ይገኛሉ። ለአብነትም ባለፈው ዓመት "ጳጉሜ-1 የበጎ ፈቃድ፣ ጳጉሜ-2 የአምራችነት፣ ጳጉሜ-3 የሰላም፣ ጳጉሜ-4 የአገልጋይነት እና ጳጉሜ-5 የአንድነት ቀን" በሚል ስያሜዎች በመላ ኢትዮጵያ በድምቀት ተከብረዋል። ዘንድሮም የጳጉሜ ቀናት "ጳጉሜ-1 የመሻገር፣ ጳጉሜ-2 የሪፎርም፣ ጳጉሜ-3 የሉዓላዊነት፣ ጳጉሜ-4 የሕብር እና ጳጉሜ-5 የነገ ቀን" በሚሉ ስያሜዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያየ ዝግጅት በመከበር ላይ ይገኛሉ። ዛሬ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ የሚገኘው የሪፎርም ቀን ባለፉት የለውጥ ዓመታት በሁሉም መስክ በተከናወኑ የሪፎርም ስራዎች የተገኙ ውጤቶች የሚዳሰሱበት ለላቀ አገልግሎትም የቤት ስራ የሚወሰድበት ነው። የጸጥታና ደኅንነት ተቋማት በዚህ ረገድ በአርአያነት የሚጠቀሱ ሲሆን ጠንካራ የሪፎርም ስራዎች ተከናወነውባቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ከሀገራዊ ለውጡ ማግስት በጸጥታና ደኅንት ተቋማት የተወሰደው የለውጥ እርምጃ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስቀጠል ጉልህ ፋይዳ እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል። "በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚጸና የድል ሰራዊት" በሚል መሪ ሃሳብ 116ኛው የመከላከያ ሠራዊት የምስረታ በዓል በተከበረበት ወቅትም የኢትዮጵያ ሠራዊት ሰላምን የሚጠብቅና የሚያጸና የህዝብ ልጅ ነው ብለዋል።   በሀገር ውስጥና በዓለም የሰላም ማስከበር ተልዕኮም የመፈጸም አቅሙን በብቃት በመወጣት ውድ ህይወቱን ከፍሎ የሰላም፣ የልማትና የአንድነት ምልክትነቱን አስጠብቆ የቀጠለ ኃይል መሆኑን ገልጸዋል። በሀገር መካከለያ ሠራዊት የተካሄደው የሪፎርም እርምጃ በአስተሳሰብ፣ በአደረጃጀትና በማድረግ አቅም የአፍሪካ የሰላም ተምሳሌትና ምንጭ የሆነ ሠራዊት መገንባት አስችሏል ብለዋል። በዚህም መከላከያ ሠራዊትን በአየር ኃይል፣ በምድር ኃይል፣ በባህር ኃይልና በሳይበር ደኅንነት እንዲደራጅ በማድረግ ትናንት፣ ዛሬ እና ነገን በማሰናሰል የተሟላ ቁመና እንዲኖረው መደረጉን ገልጸዋል። የተፈጠረው ጠንካራ አደረጃጀትም በተግባር የተፈተነ፤ ውጊያን ማድረግና መፈጸም የሚችል የድል ባለቤት የሆነ ሠራዊት የተገነባበት ስኬታማ የሪፎርም ስራ መሆኑን ተናግረዋል። የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ መከላከያ ሠራዊት ዘመናትን ባስቆጠረ ተቋማዊ ግንባታ ሂደት ፈተናን በጽናት በማለፍ የሀገርን ህልውና ያስጠበቀ ኃይል ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ የጀግና አርበኞች ሀገር መሆኗ በጽናት ተፈትኖ ነጥሮ የወጣ፣ ጠንካራ ማንነትና ብቃትን የተላበሰ የማይበገር የመከላከያ ሠራዊት እንዲኖራት ያስቻለ መሆኑን ገልጸዋል።   በአየር ኃይል 88ኛ ዓመት ክብረ በዓል ወቅት በኢትዮጵያ የትጥቅ ዝግጁነትና ዘመናዊ ጦር የማቋቋም ስራ ከ116 ዓመታት በፊት መሰረት ተጥሎ በሂደትም ዛሬ ላይ በእጅጉ መዘመኑን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅትም ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ሁኔታን ታሳቢ ያደደረገ በምድር ጦር፣ አየር ኃይል፣ በባህር ኃይል እና በሳይበር ደህንነት ትልቅ አቅም ያለው ዘመናዊ ተቋም የመገንባት ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አንስተዋል። ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተካሄዱ የሪፎረም ተግባራት መከላከያ በአደረጃጀት፣ በሥነ-ልቦና እና በትጥቅ አቅም ትልቅ ዕምርታ እንዲያመጣ አቅም የፈጠሩ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፤ ኢትዮጵያ ነሀሴ 12 ቀን 1921 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፕላን ባለቤት መሆኗን አስታውሰዋል። የአየር ኃይል ከ88 ዓመታት በፊት ተቋቁሞ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚዳፈሩ ኃይሎችን በመፋለም በተከፈለ ውድ መስዋትነት በርካታ ገድል ፈጽሞ በትውልድ ቅብብሎሽ እዚህ የደረሰ ተቋም ነው ብለዋል።   ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህም የአየር ኃይልን የዕድሜ አንጋፋነት መነሻ በማድረግ በሰው ሃይል፣ በትጥቅና በመሰረተ ልማት ግንባታ ስራ የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚመጥን የለውጥ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ፤ ሀገራዊ ለውጡ ለሰላምና ደኅንነት ተቋማት ስኬታማ የለውጥ እርምጃ በር የከፈተ ወሳኝ የታሪክ እጥፋት መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም በተወሰደ ተቋማዊ የሪፎርም ስራ የሀገርንና የዜጎችን ብሔራዊ ደኅንነት ማስጠበቅ የሚያስችል የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት እንዳስቻለ ገልጸዋል። በተወሰዱ የለውጥ እርምጃዎች አስተዳደሩ ኢትዮጵያን የራሷ የሰርቲፊኬት ቋትና የዲዛይን ሥርዓት የምታሳልጥበት ይፋዊ የቁልፍ የመሰረተ ልማት ሶፍትዌር ባለቤት እንድትሆን ያስቻላት መሆኑን ገልጸዋል። ይፋዊ የቁልፍ የመሰረተ ልማት ሥርዓቱም የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር የተቋቋመበትን የቁልፍ ተቋማትን ደኅንነት የማስጠበቅ ተልዕኮ የሚመግብ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራልና የወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊ ዘላለም መንግሥቴ፤ ሀገራዊ ለውጡ በዜጎች የወንጀል ምርመራ ላይ ይፈጸም የነበረውን ሰቆቃ መነሻ በማድረግ ተቋማዊ የማሻሻያ እርምጃ እንዲወሰድ አንዱ ገፊ ምክንያት ነበር ብለዋል። በዚህም ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በፍትሕና ጸጥታ ተቋማት ላይ ስኬታማ የለውጥ እርምጃ በመውሰድ በቴክኖሎጂ የዘመነ ስኬታማ ተቋማዊ ግንባታ መፍጠር እንደተቻለ ገልጸዋል። በመጀመሪያዎቹ ሁለት የለውጥ ዓመታትም ዜጎች ወንጀል ፈጽመው ሲገኙ ሕግና ፖሊሳዊ ሥነ-ምግባር የተከተለ የምርመራ ማካሄድ የሚያስችል አቅም መፍጠር እንደተቻለ ተናግረዋል።  
የኢትዮጵያ አረንጓዴ ትሩፋት፡ የደን መልሶ ልማት ጥረት
Aug 23, 2024 859
በአየለች ደምሴ (ኢዜአ) በታሪክ ውስጥ፣ መጠነ ሰፊ የደን መልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች ለአካባቢ ጥበቃ የሚደረጉ ጅምሮች ከፍተኛ አዎንታዊ ተጽዕኖ አሳድረዋል። በጣም ከሚያስደንቁ ምሳሌዎች አንዱ የቻይናው ታላቁ አረንጓዴ ግንብ ነው ፣ በ1978 የጎቢ በረሃ ወረራውን ለመፍታት የተጀመረው ሀውልት ፕሮጀክት ነው። ይህ ታላቅ ስራ በሰሜናዊ ቻይና በቢሊዮን የሚቆጠሩ ዛፎችን በመትከል የበረሃውን ግስጋሴ ለማስቆም ያለመ ነው። ባለፉት አሥርተ ዓመታት ውጤቶቹ ተለውጠዋል፡ የበረሃው ስርጭት ተገድቧል፤ የአሸዋ አውሎ ነፋሶች ድግግሞሽ ቀንሷል፤ ቀደም ሲል የተራቆተው የነበሩ አከባቢዎች ተመልሰው አገግመዋል። የታላቁ አረንጓዴ ግንብ ስኬት ከአካባቢያዊ ጥቅሞች በላይ ነው። የአካባቢውን ስነ-ምህዳሮች በማደስ፤ የግብርና ምርታማነትን በማሻሻል፤ በረሃማነት ለተጎዱ ማህበረሰቦች ኢኮኖሚያዊ እድል ፈጥሯል። ይህ የደን መልሶ ማልማት ፕሮጀክት የአየር ንብረት ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ረገድ የዛፎችን ኃይል ከማጉላት ባለፈ እንደዚህ አይነት ውጥኖች ዘላቂ ልማትን እንዴት እንደሚያጎለብቱና ለበረሃማነት ተጋላጭ በሆኑ ክልሎች ችግርን የመቋቋም አቅምን እንደሚያሳድጉ ያሳያል። ከእነዚህ ዓለም አቀፋዊ ስኬቶች በመነሳት ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ ተነሳሽነት የራሷን ታላቅ የደን መልሶ ልማት ጉዞ ጀምራለች። ከአምስት ዓመታት በፊት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ልማት የደን መጨፍጨፍን ለመከላከል፣ በተለያየ ምክንያት የተራቆተን መሬት ወደነበረበት ለመመለስ እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የታለመ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ነው። ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በ2011 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን ተግባራዊ ካደረገችበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከ32 ነጥብ 5 ቢሊዮን በላይ ችግኞን በመትከል ለአካባቢ ጥበቃና ለዘላቂነት ልማት ያላትን ጥልቅ ቁርጠኝነት ያረጋገጠ ተግባር ነው። የአረንጓዴ አሻራ ልማት ውጥን አዲስ ከፍታ ላይ ለመድረስ ተዘጋጅቷል።ዓርብ ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ዜጐች በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል። ጎልማሶች 20 ታዳጊዎች ደግሞ 10 ችግኞችን እንዲተክሉም አሳስበዋል። ይህ የድርጊት መርሃ ግብር ጥሪ ለዚህ ታሪካዊ ክስተት የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማበርከት ያለውን አገራዊ ኩራት እና የጋራ ኃላፊነት አጉልቶ ያሳየ ነው። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አስፈላጊነት ከሯሷ ከኢትዮጵያም አልፎ ድንበር ተሻጋሪ ነው። ዛፎች ካርቦን ዳይኦክሳይድን ከከባቢ አየር በመሳብ፣ አፈርን በማረጋጋት እና ብዝሃ ህይወትን በመደገፍ የአየር ንብረት ለውጥን ተጽዕኖን በመከላከል ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ጤናማ ስነ-ምህዳርን ለመጠበቅ፣ የውሃ ዑደትን ለመቆጣጠር እና ለዱር እንስሳት መጠለያ ለማቅረብ ወሳኝ ናቸው። በከተሞች አካባቢ ዛፎች የአየር ጥራትን ይጨምራሉ የከተማ ሙቀት ደሴት ተፅእኖን ይቀንሳሉ፤ በአጠቃላይ የህይወት ጥራትን ያሻሽላሉ ምድር ከአየር ንብረት ለውጥና የአካባቢ መራቆት ተጽእኖዎች ጋር ስትታገል፣ እነዚህን ተግዳሮቶች በመከላከል ረገድ የደን መልሶ ማልማት ሚና ከጊዜ ወደ ጊዜ ያለው ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እየታየ መጥቷል። አረንጓዴው ውርስ የዛፍ ተከላ ዘመቻ ብቻ አይደለም እሱ ለአካባቢያዊ ዘላቂ ልማት እና መቋቋም ሰፋ ያለ ቁርጠኝነትን ይወክላል። ኢትዮጵያ በደን መልሶ ማልማት ላይ ኢንቨስት በማድረግ የወደፊት ህይወቷን ለማስጠበቅ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅምን ለመገንባት ንቁ ተሳትፎ እያደረገችና እርምጃ እየወሰደች ነው። ይህ ተነሳሽነት አንድ ሀገር የአካባቢ ተግዳሮቶችን ለማስወገድ እና ለሌሎች አርዓያ ለመሆን እንዴት አንድ ላይ መሰባሰብና መተባበር እንደሚቻል የሚያሳይ ጠንካራ ተምሳሌት ሆኖ ያገለግላል። ኢትዮጵያ ለዚህ ታሪካዊ ተግባር ስታዘጋጅ የዓለም ማህበረሰብ በጉጉት ይከታተላል። የአረንጓዴው አሻራ ልማት ተነሳሽነት ኢትዮጵያ ለአካባቢያዊ ሁለንተናዊ ልማትና ዕድገት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያንፀባርቅ ነው። ከዚህም ባሻገር ለዓለም አቀፉ የደን መልሶ ልማት እንቅስቃሴና የአየር ንብረት ለውጥ እርምጃ አስተዋጽኦ ያደርጋል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዛፎችን በመትከል ኢትዮጵያ የራሷን የደን ሽፋን ከማሳደግ ባለፈ ለወደፊትም የተስፋና የቁርጠኝነት መልዕክት እያስተላለፈች ነው። የአረንጓዴው አሻራ ልማት ተነሳሽነት የአካባቢ ጥበቃ እና የጋራ ተግባር መንፈስን ያጠቃልላል። እንደ ቻይና ታላቁ አረንጓዴ ግንብ ካሉ ዓለም አቀፍ የደን መልሶ ልማት ስራዎች ስኬት በመነሳት ኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ዛፎችን ለመትከል የወጠነችው እቅድ የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ረገድ ትልቅ ምዕራፍ ነው። ዛፎች ሲተከሉና ሥሮቻቸው መሬት ሲይዙ፣ ለኢትዮጵያና ለዓለም የበለጠ ብሩህ፣ ቀጣይነት ያለው የወደፊት ጊዜን ያመለክታሉ።  
በሴቶችና በማህበረሰብ የተጠበቁ የተፈጥሮ ደኖች ለአረንጓዴ አሻራችን
Aug 23, 2024 779
በሚስባህ አወል (ኢዜአ) ሴት አርሶ አደር ሜሪ ኦፍሬ በናይጀሪያ ኦሎን መንደር ነዋሪ ስትሆን፤ የአምስት ልጆች እናት ነች። ባለቤቷን ሞት ነጥቋት ልጆቿን የምታሳድገው ብቻዋን ነው። በመንደሯ አፊ ተብሎ የሚጠራ ጥብቅ ደን አለ። ሜሪ ኦፍሬ ኑሮዋን የምትመራው በዚህ ጥብቅ ደን አቅራቢያ ባላት አነስተኛ የእርሻ ማሳን ከዚሁ ጥብቅ ደን በምታገኘው ትሩፋት እንደሆነ ነው ለአልጄዚራ የገለጸችው። ጠንካራዋ ሜሪ አፍሬ ከመንደሯ ሴቶች ጋር በመተባበር የአካባቢቸውን ስነ ምህዳር ለመጠበቅ በማህበር ከተደራጁ አባሎቿ ጋር በመሆን በዓለም አማቀፍ ደረጀ የሚታወቀውን ይሄንኑ በአቅራቢያቸው የሚገኘውን ኦፊን ጥብቅ ደን ከህገ-ወጥ ጨፍጫፊዎች መጠበቅ ከጀመሩም ሰነባብተዋል። በናይጄሪያ ክሮስ ሪቨር ግዛት የሚገኘው ይኸው ታዋቂ የኦፊን ደን በህገወጥ መንገድ ለማገዶ እንጨትና ለሌሎች አገልግሎት የሚውሉ ዛፎችን በሚቆርጡ ደን በሚመነጥ ህገ-ወጥ አካላት ሳቢያ የመጥፋት አደጋ ከተጋረጠባቸው የደን ሀብቶች መካከል አንዱ ሆኖ ነበር።የአፊን ጥብቅ የደን ሀብት በናይጄሪያ ብቻ ሳይሆን፤በዓለም ላይ ከፍተኛ የደን ጭፍጨፋ እንሚካሄድባቸውና በተደጋጋሚ ስማቸው ከሚጠራ አካባቢዎች ግንባር ቀደም ተጠቃሽ እንደሆነም መረጃዎች ያመለክታሉ። የአፊ ጥብቅ ደንም ሆነ በውስጡ የተጠለሉ የዱር እንሰሳትና የሚገኙ ብዝሃ ህይወቶች ዝርያቸው ተመናምኖ ለመጥፋት ተቃርቦ እንደነበር አልጀዚራ የሰራው ዘጋቢ ፊልም ያመለክታል። ሜሪ አፍሬን ጨምሮ በአካባቢዋ በማህበር የተደራጁ ሴቶች የአፊን ጥብቅ የደን ሀብት ከህገ-ወጥ ጨፍጫፊዎች ከመጠበቅ ባለፈ ስነየአካባቢውን ስነምህዳ ልምላሜውን ጠብቆ አረንጓዴ እንደለበሰ የዛረውን ትውልድ እየጠቀመ ለተተኪው ትውልድ እንዲሸጋገር ችግኞችን በመትከልና ተንከባክቦ በዘላቂነት ለማልማት ቁልፍ ሚና እንዳላቸውና ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ አልጀዚራ በዘጋቢ ፊልም ጠቅሷል። በዘጋቢ ፊልሙ እንደሚያመለክተው ሜቤሪ አንፍሬና ባልደረቦቿ ጥብቅ የደን ሀብቱን ለመጨፍጨው ወደ አካባቢያቸው የሚመጡ ህገ-ወጥ የደን ጨፍጫፊዎችን በመከታተልና ለአካባቢው የጥበቃ አካላት በማጋለጥ የአፊን ጥብቅ ደን ለመታደግ ያላቸው ሚና የላቀ ነው። ሜሪና አንፍሬ እና ባልደረቦቿ የኦፊ ጥብቅ የደን ሀብት ተራራው፣ጋራ ኮረብታውን፣ ሜዳ ሸንተረሩን፣ በጥቅሉ የአካባቢውን የስነ ምህዳር በአግባቡ ጠብቆ፣ አልምቶና ተንከባክቦ በማቆየት የሚያገኙት ትሩፋት ምን ያህል የሕይወት መድን እንደሆናቸው ጠንቅቀው የተረዱ ናቸው። በመሆኑም አንዳቸው ለአንዳቸው የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች የሕልውናቸው መሰረት መድን እንደሆኑም ነው የሚገልጹት። ከአንፊ ጥብቅ ደን ለምግብነትና ለባህላዊ መደኃነትነት የሚውሉ የተለያዩ የፍራፍሬዎች እንደሚያገኙ ሜሪ አፍሬ ትገልጻለች። እነዚን የአፊን ጥብቅ ደን ገፀ-በረከቶች ምግብነትም ባህላዊ መድኃኒት እየተጠቀሙበት በመሆኑ የመጠበቁን፣ የማልማቱንና የመንከባከቡን ተግባር የሚከውኑት በፍላጎትና በደስታ ነውም ትላለች። በተለይ ለእሷ ይህን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለውንና ልጆቿን የምታሳድግበትን የአንፊ ጥበቅ ደንን ከህገ-ወጥ ጨፍጫፊዎች ጠብቆ መከላከል፣ ማልማትና መንከባከብ ደስታዋም መዝናኛዋም ጭምር እንደሆነ ትገልጻለች። በማህበር የተደራጁት ሴቶች የአንፊ ጥብቅ ደንን ከህገ-ወጥ ጨፍጫፊዎች ለመጠበቅ፣ ችግኞችን በመትከል ለማልማትና ለመንከባከብ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ አስመልክቶ በየጊዜው ተገናኝተው እንደሚመካከሩም ነው አልጀዚራ በዘጋቢ ፊልሙ ያመላከተው። በአገራችን ኢትዮጵያ በሴቶች ብቻ ያሳተፈ ሳይሆን በመላ ማህበረሰብ ተሳትፎ የተጠበቀ የተፈጥሮ የደን ሀብት በዚህ በመገባደድ ላይ በሚገኘው ዓመት መጀመሪያ አካባቢ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሣይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) መመዝገቡን ስንቶቻችን እናስታውሳል አልያም እናውቃለን? የጌዴኦ ህዝብ በጥምር ግብርና ሥራዎች የዕጽዋዕት፣ የፍራፍሬ፣ የሰብል ምርቶችና በጣዕሙ የሚታወቀውን የይርጋጨፌ ቡና በማምረት ይታወቃል።ህብረተሰቡ ሀገር በቀል ዕውቀት ተጠቅሞ የአካባቢው የአየር ፀባይና የተፈጥሮ ሚዛን የተስተካከለና ለህይወት ተስማሚ እንዲሆን፣የመሬት አጠባበቅ፣ አጠቃቀም፣ አያያዝና አስተዳደር ልምዱ በዩኔስኮ እንዲመዘገብም አስችሎታል። በደቡብ ኢትዮጵያ ቀልብን ከሚስቡ የቱሪዝም ኃብቶች መካከል የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር በእጅጉ አስደማሚ ነው። ለዚህ መነሻው በተለያዩ ረጅም ዕድሜን ባስቆጠሩ ጥቅጥቅ ባሉ ግዙፍ ሀገር በቀል ዛፎችና ደንና ጫካ ተፈጥሮ አስጊጣ ያስዋበች መሆኑ ነው።ጌዴኦ ደን ብቻ ሳይሆን ጥምር የግብርና ልማት የሚካሄድበትም ነው። ቡናው ከዋርካው ፡ ከዋንዛው ጋርና መሰል ሀገር በቀል ዛፎች ጋር ተሰናስሎ አብሮ በጥምር የሚለማበት ነው፡፡ የይርጋ ጨፌ ቡና የሀገር በቀል ዛፎችና የተለያዩ ፍራፍሬዎች ተክሎች ተሰናስለውና መስተጋብር ፈጥረው ጥላ ከለላ በመሆናቸው ተፈጥሯዊ ጣዕሙን ይዞ በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳጅና ተወዳዳሪ የሆነው ። ጌዴኦ በትውልድ ቅብብሎሽ ተጠብቆ የዘለቀው ይኸው የተፈጥሮ ደን ዛሬ ላይ በመላ ሀገሪቱ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል ሀገራችን በየዓመቱ በሕዝብ ንቅናቄ እየተተገበረ በሚገኘው የአረንጋዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብርን ተግባራዊ እያደረገች ትገኛለች።ይህም በጌዴኦ አካባቢ የሚታየው የቆየ ጥብቅ ደን አያያዝና የጥምር ግብርና ልምታ በመላ ሀገራችን ተዳርሶ ባህል እንዲሆን ያስችላል። አገራችን ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ አሕመድ አነሳሺነት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በሁለት አቤይት ምዕራፎች በየዓመቱ የክረምት ወቅት እተገበረችው የሚገኘው የአረንጋዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የደን ሽፋንን ለማሳደግና የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ በሀገራችን የበርካታ አእዋፋት፣ እንስሳትና አዝርዕት መገኛ እነቶን ጭምር ይዛ እንድትቀጥል የሚያስችል ጭምር ነው። ይህም ሰው ከተፈጥሮ ጋር እንዴት ሰናስሎ፣ ተጋምዶና ተዛምዶ መኖር እንደሚችል የሚያሳይ ነው። በዘንድሮው የአረንጋዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል የታቀደ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ዓርብ ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ሀገራችን ቀን ቆርጣና ዝግጅቷን አጠናቃለች። ኢትዮጵያ “አረንጓዴ አሻራ” ብላ የሰየመችው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ማካሄድ ከጀመረች ዘንድሮ 6ኛ ዓመት ላይ ደርሳለች። ከ2011 ዓ.ም እስከ 2014 ዓ.ም ባካሄደችው የመጀመሪያ ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 20 ቢሊዮን ችግኞች ለመትከል አቅዳ 25 ቢሊዮን ችግኞችን መትከል ከዕቅድ በላይ ማሳካቷን ከግብርና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል። ሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በ2015 ዓ.ም መጀመሩ ይታወሳል። ባለፉት አምስት ተከታታይ ዓመታት በተካሄዱት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሮች ከ32 ነጥብ 5 ቢሊዮን በላይ ችግችግኞች መተከላቸውን የሚኒስትሩ መረጃ ያሳያል። የጌዴኦ ህዝብ በጥምር ግብርና ልማት ልምድን በመቀመር በሴቶችና በማህበረሰቡ ሁለንተናዊ ተሳትፎ የተጠበቁ የተፈጥሮ የደኖ አብቶችን ተንከባክቦና ጠብቆ በማቆየት በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሮች በነቂስ ወጥተን በመሳተፍ አገራችንን አረንጓዴ ለማልበስ እያደረግነውን ያለውን ብርቱ ጥረትና ትጋት አጠናክረን በመቀጠል ሁላችንም የተሻለች ኢትዮጵያን ለልጆቻችን እናውርስ።  
በሐርላ ታሪካዊት ስፍራ- ታሪካዊ አሻራ
Aug 22, 2024 920
በምሥራቅ ኢትዮጵያ ቀደምት ስልጣኔ አሻራ ካረፈባቸው ታሪካዊ ስፍራዎች አንዷ ናት-ሐርላ። ሐርላ ከ10 ኛው እስከ 16 ኛው ክፍለ ዘመናት የዘለቀች የሥመ ገናና ስልጣኔ ባለቤት ናት። የሐርላ ስልጣኔ ውጥን እና አሻራ በድሬዳዋ በስተሰሜን ምሥራቅ ጉብታ ስፍራ ላይ ትገኛለች። በሥነ ምድር ቁፋሮ ምርምሮች የ11ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሳንቲሞች በሐርላ ተገኝተዋል፡፡ የሐርላ ነዋሪዎች የንግድ ግብይትና የባሕል ትስስር ከኢትዮጵያ ባለፈ ከዓረቡ ዓለም፣ ከቤዛንታይን የክርስቲያን ግዛተ አፄ፣ ከደቡብ እስያ፣ ከግብጽና በተዘዋዋሪ መንገድም ከሩቅ ምስራቅ ክፍላተ ዓለማት ጋር የተዘረጋ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ዋቢ ናቸው። በተለያዩ ክፍለ ዘመናት የነበሩ የቻይና፣ የቤዛንታይን፣ የሕንድ፣ የስሪላንካና ሌሎች ሀገራት ስርዎ መንግስታት ሳንቲሞችና መገልገያ ቁሶች በሐርላ የአርኪኦሎጂ ቁፋሮ መገኘታቸውም ለዚህ ታሪካዊ ዕውነታ ሁነኛ አብነት ነው። የሐርላ ከተማ መገኛ ከዛሬዋ ድሬዳዋ ራስጌ ይሁን እንጂ ግዛቷ ግን የዛሬዎቹን ሶማሊያና ጂቡቲ ያካትት እንደነበር የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ዳንኤል ክብረት(ዲ/ን) በቅርቡ ባሳተሙት 'የትርክት ዕዳና በረከት' በተሰኘው መፅሀፋቸው አትተዋል። "በከተማዋ ውስጥ ዋና የከተማው መንደር፤ የኢንዱስትሪ ሥፍራ፣ ሦስት መስጊዶች፣ የውኃ ጉድጓዶች፣ በሰሜን ፣ በምዕራብና በምሥራቅ የመቃብር ሥፍራዎች እና በዙሪያዋ ደግሞ የመከለያ ግንብ ነበራት" ሲሉም ጠቅሰዋል። እንደ ድሬዳዋ ሁሉ የሐርላ ሥልጣኔ መገለጫ ኅብረ ብሔራዊነት ነበር። "በከተማዋ አፋሮች፣ ሐረሪዎች፣ ሶማሌዎች፣ ዓረቦች፣ ፋርሶች፣ የስዋሂሊ አካባቢ ሰዎች እና ሕንዶች ይኖሩባት ነበር። በከተማዋ በቁፋሮ የተገኙት መስጊዶች አሠራራቸው ከታንዛንያና ከዘይላ ጋር የተመሳሰለ ነው" ሲሉ የሕብረ ብሔራዊነት መልኳን አብራርተዋል። ሐርላ በ16ኛው ክፍለ ዘመን በተለያዩ ምክንያቶች ተዳከማ ስልጣኔዋን ለሐረር ለቃለች። በዳንኤል ክብረት (ዲ/ን) ሀታታ ሐረር ከሐርላ ስልጣኔ "የእስልምና ሥልጣኔ ማዕከል መሆንን፣ ከመካከለኛው ኢትዮጵያና ከውጭው ዓለም የነበረውን የባህል፤ የእምነትና የንግድ ግንኙነትና የከተሜነትን ባህል" አስቀጥላለች፡፡ ከድሬዳዋ በስተምሥራቅ ወጣ ብላ የምትገኘዋ የሐርላ መንደር ነፋሻማና ቀዝቃዛ አየር አላት። የጥንት ስልጣኔ የታሪክ አሻራ ያላቸው የዛሬዋ ሐርላ መንደር ነዋሪዎች ደግሞ በታሪካዊቷ ሐርላ ለትውልድ የሚሻገር አረንጓዴ አሻራቸውን እያሳረፉ ነው። የሐርላ ቀበሌ ሊቀመንበር መሀቡ ዲኔ የሐርላ አካባቢ ተዳፋታማ ስፍራዎች ከፍተኛ መራቆት ደርሶባቸው እንደበር ያስታውሳሉ።   ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን የቀበሌውን ማህበረሰብ በማወያየትና በማሳመን በአካባቢው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ተግባራት ሲከናወን መቆየቱን ጠቅሰዋል። በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ያስጀመሩት የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ተግባራዊ በመደረጉ በአካባቢው ተጨባጭ ለውጥ መምጣቱን ያነሳሉ። አሁንም አካባቢውን ከንክኪ ነጻ በማድረግ፣ እርከን በመስራት እና በችግኝ በመሸፈን ነጩ ተራራ ለምለሙ ተራራ የሚል ስም እንዲኖርው እየሰራን ነው ብለዋል። በቀጣይም አካባቢው በዘላቂነት እንዲያገግም ብሎም በድሬዳዋ ከተማ ላይ የሚደርሰውን የጎርፍ አደጋ ለመከላከል እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የግብርና፣ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊ አቶ ኑረዲን አብደላ እንደሚሉት ከሐርላና አካባቢው ተራራማ ቦታዎች የሚነሳው የጎርፍ አደጋ በድሬዳዋ ህዝብ እና በመሰረተ ልማቶች ላይ መልከ ብዙ ጉዳቶችን ሲያደርስ ቆይቷል።   በዚህም ባለፉት ዓመታት በተተገበረው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ድሬዳዋን ከጎርፍ አደጋ ለመጠበቅ ሐርላና አካባቢውን በሚያካትተው የደቻቶ ወንዝ ተፋሰስ ላይ ሰፋፊ የአካባቢ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል። ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር በሐርላ አካባቢ የተተከሉ ችግኞች አካባቢውን እየለወጡት መሆኑን ገልጸዋል። የሐርላ ተዳፋታማ ስፍራ መራቆቱን ተከትሎ አካባቢው ነጭ ተራራ የሚል ስያሜ እንደነበረው አስታውሰው፤ አሁን ግን ህብረተሰቡን በማስተባበር በተሰሩ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ገፅታውን በመቀየር የተራቆተው ቦታ እያገገመ መምጣቱን ተናግረዋል። ከተማ አስተዳደሩ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ችግኞች ለመትከል ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልፀዋል። የታሪካዊቷ ሐርላ መንደር አካባቢም በነገው ዕለት በስፋት ችግኝ ከሚተከልባቸው የተለዩ ስፍራዎች አንዱ መሆኑን አንስተዋል። ሐርላ ከድሬዳዋ አቅራቢያ የተሻለ የአየር ንብረት ያላት በመሆኗ ወደፊት አካባቢውን በማልማት ለኢኮቱሪዝም አገልግሎት መጠቀም እንደሚቻል ነው ያነሱት። በሞቃታማዋና ለጎርፍ ተጋላጭ በሆነችው ድሬዳዋ የሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ ከችግኝ መትከል ያለፈ ልዩ ትርጉም እንዳለው ጠቅሰዋል። በዚህም ህብረተሰቡ በነገው የችግኝ ተከላ ንቅናቄ በነቂስ ወጥቶ አሻራውን እንዲያሳርፈ ጥሪ አቅርበዋል። ከሚተከሉ ችግኞች መካከል 35 በመቶ የሚሆኑት ለምግብነት የሚውሉ እና የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ አይተኬ ሚና ያላቸው የችግኝ ዝርያዎች እንደሆኑ ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከተማ አስተዳደሩ ለጎረቤት ሀገር ጅቡቲ በየዓመቱ ችግኞችን እንደሚያበረክት አስታውሰው፤ ዘንድሮም 100 ሺህ ችግኞች ማዘጋጀቱን ገልጸዋል። ይህም የጋራ ችግር የሆነውን የአየር ንብረት ተጽእኖ ለመቋቋም ካለው ፋይዳ ባሻገር የህዝብ ለህዝብ ትስስርና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱን ይበልጥ ለማጎለበት ያግዛል ብለዋል።  
ትንታኔዎች
አረንጓዴ አሻራ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ የሥራ ዕድል ፈጠራ
Aug 30, 2024 611
በክፍሌ ክበበው (ኢዜአ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በ2011 ዓ.ም ነበር የተጀመረው። በዚሁ በመጀመሪያው ዙር የአረንጓዴ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 23 ሚሊዮን ህዝብ ተሳትፎ ከ4 ነጥብ 7 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። በዚህም በመርሃ ግብሩ እስከ 2014 ዓ.ም ድረስ በሕዝብ ተሳትፎ ለአራት ዓመታት በተካሄደው የመጀመሪያው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃግብር 20 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ 25 ቢሊዮን ችግኞችን መትከል በስኬት ተጠናቋል። የመጀመሪያው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም የተጀመረው “40 ዛፍ በነፍስ ወከፍ” በሚል መሪ ሀሳብ ሲሆን፤ በአንድ ጀምበር 200 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ ከ353 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል እ.ኤ.አ በሐምሌ 2017 በሕንድ የአካባቢ ጥበቃ ዘመቻ በ12 ሰዓታት 66 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ተይዞ የነበረውን የዓለም ክብረወስን ኢትዮጵያ መረከብ ችላለች። የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከመጀመሪያው ምዕራፍ አንስቶ ከዓመት ዓመት የኅብረተሰቡን ተሳትፎን እያሳደገ በስኬት እየተጠናቀቀ ከዚህ ደርሷል። በ2015 ዓ.ም መተግበር በጀመረው በሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 25 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል የታቀደ ሲሆን፤በተለይ ለምግብነት የሚውሉ ተክሎች ትኩረት እንደተሰጠ መረጃዎች የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከዚህም ባሻገር ችግኞችን ለጎረቤት አገራት በመስጠት ኢትዮጵያ ችግኞችን በመትከል ዓለም ዓቀፍ ፈተና የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥ ለመቅረፍ እያደረገች ያለው እንቅስቃሴ አርዓያነቷን ያሳየችበት መሆኑ ዓለም ዓቀፍ ተቋማት የመሰከሩለት ሀቅ ነው። በዘንድሮው ለስድስተኛ ጊዜ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ 615 ነጥብ 7 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የአረንጓዴ አሻራ ሥራው በስኬት መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዕለቱ አብስረዋል። ይኸው የችግኝ ተከላ መርሃግብር ነሐሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም “የምትተክል ሀገር፤ የሚያጸና ትውልድ” በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደው ለጥምር ደን፣ ለምግብነት እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን የመትከል ለአረንጓዴ ልማት እና ለአረንጓዴ አካባቢ መላ ኢትዮጵያውያን ለትውልድና ለዓለም የሚተርፍ በስኬት ተጠናቋል። “ያሰብነውን ሳናሳካ ጀምበር የሚጠልቅብን አይደለንም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የተሳተፉ 29 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዜጎች በ318 ነጥብ 4 ሄክታር በሚሸፍኑ ሥፍራዎች ላይ ችግኞችን መትከላቸውን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እንዳሉት በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እስካሁን ባለው ሂደት 39 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ጠቅሰው፤ በአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የተከልናቸውን ችግኞች ሲደመሩ ወደ 40 ቢሊዮን ይደርሳሉ ፡፡ ይህ ስኬት ለአየር ንብረት ለውጥ ሚዛን ለመጠበቅ፣ የአፈር መራቆትን ለመመከት እና የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እንዲሁም ምድራችንን አረንጓዴ ለማልበስ እና ልምላሜን ለመመለስ ሳንበገር ሰርተናል ብለዋል። በዘንድሮ ዓመት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከ7 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የሚተከሉ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነው ለምግብነት፣ ለመድሐኒትነትና የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል እና የተቀረው ደግሞ ለውበትና ለአከባቢ ጥበቃ የሚውል መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል። እንደሳቸው ገለጻ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የአየር ንብረትን በማሻሻል እና ብዝሃ ህይወትን በመደገፍ ኢትዮጵያን የሚጠቅም ብቻ ሳይሆን፤ ወደፊት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚደረጉ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች አርአያነት ያለው ተግባር መሆኑን ሁሉም ኢትዮጵያዉያንን እና ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ የሚያስማማ ነው። የተተከሉት ችግኞች ሲጸድቁ ስነምህዳሩን ከማሻሻል፤ የአፈር መሸርሸርና መከላትን ከመከላከል እንዲሁም የሥራ ዕድልን ለበርካቶች ከመፍጠር አኳያ ጠቀሜታቸው ከፍተኛ ነው። የተጎዳና የተራቆተ አካባቢ ላይ የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች አካባቢያቸውን ለምግብነት እና ለአየር ንብረት ለውጥ በደን ለማልበስ በሚደረግላቸው ቴክኒካዊ ድጋፍ ተጠቅመው አኗኗራቸውን ለመለወጥ ያስችላል። የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሚገኙ ምንጮች እንዲጎለብቱ፣ ድርቅን ለመቋቋም የሚያስችል አረንጓዴ ምህዳር እንዲፈጠር የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ገባሮች እንዲጠናከሩ እያደረገ መሆኑን እና ጎርፍን በመከላከል፣ የአፈር መከላትን በማስቀረት፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው። ከዚህም በተጨማሪ የአረንጓዴ አሻራ እና የተፋሰስ ልማቱ በተራቆቱ አካባቢዎች የደን ሀብት መልሶ እንዲያገግምና ደርቀው የነበሩ ምንጮች መልሰው እንዲመነጨናና የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር እያገዘ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፉት ዓመታት ችግኞች በመተከላቸው የአፍሪካ ኩራት የሆነው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከሚጠበቀው በላይ ውሃ መያዙን ገልጸው፤ ግድቡን ከደለል ለመታደግ፣ በቂ ዝናብ፣ ምግብና መድሃኒት ለማግኘት በዓባይ ተፋሰስ አካባቢዎች በቀጣይ ችግኞችን አብዝቶ መትከል ይጠበቅብናል፣ ይህም የታችኛው የተፋሰሱ ሀገሮችም በቂ ውሃ እንዲያገኙም ያስችላል ብለዋል። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአፈር ደለል እንዳይሞላ፣ በአካባቢው ሥነ ምህዳሩን ለመጠበቅ እና ረጅም ዓመት አገልግሎት መስጠት እንዲችል በተፋሰሱ ዙሪያ ችግኞች በቀጣይነት መትከል ይገባል። የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በተፋሰስ ልማት ምንጮችን በማጎልበት እየለማ ያለው የውሃ ሀብትም የአካባቢውን ሥነ ምህዳር ለመጠበቅ ተጨማሪ አቅም ሆኗል። በግብርና ልማት በአገር አቀፍ ደረጃ በበጋ መስኖ ልማት የበጋ ስንዴ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት እንዲጨምር በማድረግ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እና የሥራ ዕድልን በመፍጠር የበከሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በተፋሰስ ልማት እየለማ ያለው የውሃ ሀብትም የአካባቢውን ሥነ ምህዳር ለመጠበቅ ተጨማሪ አቅም ሆኖ ለግብርና ልማት እና የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር ለጎረቤት አገራትም ጭምር የሚተርፍ ሆኗል። በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃግብር ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ትንበያዎች ያመላክታሉ።እ.ኤ.አ. በ 2012 የተመሰረተው እና በብሪታኒያ ዕርዳታ የሚደገፈው ኤፍኤስዲ አፍሪካ ለወደፊቷ አፍሪካ ፋይናንስን ለመስራት የሚተጋ የልማት ኤጀንሲ ባወጣው አዲስ የትንበያ ሪፖርት እንደሚያመለክተው በአረንጓዴ ኢኮኖሚ እ.ኤ.አ. በ2030 ከሦስት ሚሊዮን በላይ ቀጥተኛ ሥራዎችን መፍጠር የሚያስችል ነው። ኤፍኤስዲ አፍሪካ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ በአፍሪካ የፋይናንስ ገበያዎች ውስጥ ያሉ የሥርዓት ተግዳሮቶችን ለመፍታት መጠነ ሰፊ እና የረጅም ጊዜ ለውጥን ለመፍጠርን ዓላማ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ነው።ባለፈው ወር መጨረሻ ይፋ ባደረገው ትንበያ በ2030 አሥራ ሁለት "አረንጓዴ" ንዑስ ዘርፎች ያለውን አዲስ ቀጥተኛ የስራ ዕድል የሚተነብይ "በአፍሪካ የአረንጓዴ ሥራዎች ትንበያ " በሚል ርዕስ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን ዘገባ የፈጠራ ሥራዎችን ከሚደግፈው ሾርትሊስት (Shortlist) ከተባለው ተቋም ጋር አሳትመዋል። እ.አ.አ በ2030 በአህጉሪቱ እስከ 3 ነጥብ 3 ሚሊዮን የሚደርሱ በታዳሽ ኃይል ዘርፍ በተለይም ከአብዛኛዎቹ በፀሐይ ኃይል አዳዲስ ቀጥተኛ ሥራዎች እንደሚፈጠሩ በትንበያ ሪፖርቱ አመልክቷል።በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ በዋና ዋና የአረንጓዴ እሴት ሰንሰለቶች ማለትም በካርቦን ንግድ፣ በተፈጥሮ ሀብት ልማት እና በታዳሽ ኃይል ያለውን የሰው ኃይል ፍላጎት ለመጀመሪያ ጊዜ በጥልቀት የተተነተነው ጥናቱ ለአምስት አገሮች፤ ኢትዮጵያ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኬኒያ፣ ናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ያተኮረ ዝርዝር ትንበያ አውጥቷል። በዚህም ኢትዮጵያ ከሃይድሮ ኤሌክትሪክ 33 ሺህ ሥራዎች ቀዳሚ ቀጣሪ እንደምትሆን በተቋማቱ ጥናት ተካቷል። በዚሁ ጥናት ከ377 ሺህ በላይ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የታገዘ የስማርት ግብርና ቴክኖሎጂ ልማት እና ግብርና እና ተፈጥሮ እስከ 700 ሺህ የሚደርሱ ሥራዎችን እንደሚፈጥርም በሪፖርቱ ተጠቅሷል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ በፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት መካከለኛ ገቢ ያላት ሀገር ለመሆን ጠንካራ ቁርጠኝነትን እያሳየች መሆኑን ኤፍኤስዲ አፍሪካ (FSD Africa) በዘገባው ጠቅሷል። በኢትዮጵያ ዝቅተኛ የካርቦን ኢነርጂ ልማትን በማረጋገጥ፣ ሰፊ የደን ክምችቷን በመጠበቅ እና ግብርናዋ የአየር ንብረትን የመለማመድ እና የመቋቋም አቅምን ማሳደግ በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው። ኢትዮጵያ ሀገራችን በአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተገኘበት እና የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል ያላትን ቁርጠኝነት የታየበት እና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለውና አበርክቶው የላቀ በመሆኑ ኢትዮጵያዉያን ይህንን እየዳበረ የመጣውን በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ኢትዮጵያን አረንጓዴ በማልበስ፣ የለማች፣ ያደገችና የበለጸገች አገር ለተተኪው ትውልድ የማስረከቡን ባሕል በበለጠ ሊያጸኑት ይገባል።
10 ሄክታር ማሳን ወደ ፍራፍሬ ደን የለወጡ ብርቱ አርሶ አደር
Aug 27, 2024 702
የድሬዳዋ ሕዝብ በተወለዱበት ቀዬ ስም ''ጀማል በዴሳ'' ሲላቸው የንግዱ ማኅበረሰብ ደግሞ ቀደም ብሎ በነበራቸው ጠንካራ የጫት ንግድ እንቅስቃሴ "ጀማል ቁጩ"ይላቸዋል። በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር መልካ ጀብዱ አካባቢ ሰፊ ማሳ ላይ አትክልትና ፍራፍሬ የሚያለሙት እኚህ ብርቱ አርሶ አደር ትክክለኛ ስማቸው አቶ ጀማል አህመድ ዚያድ ይባላል። ከምስራቅ ሐረርጌ ወደ ድሬዳዋ ያመሩት ጀማል አህመድ ከ12 ዓመታት በፊት 100 ፍሬ ፓፓያ በመትከል ነበር የፍራፍሬ ልማትን አሐዱ ብለው የጀመሩት። የፓፓያውን ፍሬያማነትና ይዛላቸው የመጣውን የኢኮኖሚ ትሩፋት በማየት 15 ሺህ ፍሬ ፓፓያ በመትከል የምርት መጠናቸውን አሳድገዋል።   አርሶ አደር ጀማል በዚህ ሳይገቱ ሁሉንም ዓይነት የፍራፍሬ ዛፎች በማልማት ዛሬ ላይ ከ10 ሄክታር በላይ ማሳን በዓይነትና በብዛት የፍራፍሬ ቋሚ ተክሎች በመሸፈን ማሳቸውን ጫካ አስመስለውታል። በተጨማርም ሰብልና የፍራፍሬ ዛፎችን እንዲሁም ስኳር ድንችን አጣምረው እያለሙ ነው።   ጥቅጥቅ ደን ከመሰለው የጀማል ማሳ ብርቱካንን ጨምሮ የፍራፍሬ ምርቶች በየቀኑ ድሬዳዋና አካባቢው ወደሚገኙ ሆቴሎችና መሰል አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በቀጥታ ይሰራጫሉ። ለምግብነት ከሚውሉ ቋሚ ሰብሎች በተጨማሪም ለከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት የሚውሉ ልዩ ልዩ ችግኞችን በሳይንሳዊ ዘዴ በማዘጋጀትም ችግኝ ለሚፈልጉ ደንበኞቻቸው በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። በመልካ ጀብዱ በሚገኘው የጀማል አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ለ24 ሰዎች ቋሚ የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፤ አርሶ አደሩ በዓመት ከ13 እስከ 15 ሚሊዮን ብር ገቢ እንደሚያገኙ ይገልጻሉ። ጀማል የግብርና ኢንቨስትመንታቸውን ከድሬዳዋ ባሻገር በሌሎች የምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ለማስፋት እንቅስቃሴ ጀምረዋል። የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና ድሬዳዋን ልክ እንደ ዱባይ የንግድ መዳረሻ የመሆን እድል ፈጥሮላታል የሚሉት አርሶ አደር ጀማል፤ ከግብርና ሥራቸው ባሻገር በዓለም አቀፍ ንግድ ውስጥ ለመሰማራትም ፈቃድ ወስደዋል። የግብርና ሥራቸው ሌሎች የአካባቢው በርካታ አርሶ አደሮች በአትክልትና ፍራፍሬ በማልማት የተሻለ ሕይወት እንዲመሩ ምክንያት መሆናቸውን ጀማል ያነሳሉ። በድሬዳዋና አካባቢው የከርሰ-ምድር ውኃን በአጭር ጥልቀት ቆፍሮ ማግኘት ይቻላል የሚሉት ጀማል፤ በፀሐይ ኃይል የሚሰራ የውኃ ፓምፕን ጨምሮ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ለማኅበረሰቡ ቢቀርቡ፤ አርሶ አደሮች ከራሳቸው አልፈው ለአገር የሚተርፍ ምርት ማግኘት እንደሚችሉ ይናገራሉ።   ከራሳቸው ጥረት ባሻገር ከከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አንስቶ በከፍተኛ አመራሮች በኩል ትልቅ ድጋፍና ዕገዛ እንደተደረገላቸው ገልጸው፤ በተለይም በግብርና ባለሙያዎች ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የግብርና፣ ውኃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊ መሐመድ አሚን፤ ጀማል በራስ ተነሳሽነት ውጤታማ የሆኑ የሞዴሎች ሞዴል አርሶ አደር ናቸው ይላሉ። በተለይም ከመደበኛ ሰብሎች ባሻገር አትክልትና ፍራፍሬ በማልማት የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንደሚቻል ማሳያ ብርቱ አርሶ አደር እንደሆኑ መስክረዋል። ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች አርሶ አደሮች ልምድና ተሞክሯቸውን በማጋራትም ትልቅ ሚና እየተወጡ መሆኑን ጠቅሰዋል። ከምግብ ሰብሎች ባሻገር ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ችግኞችን በማልማት ለከተማው የራሳቸውን አበርክቶ እየተጫወቱ መሆኑን ገልፀው፤ በዚህ ዓመት ብቻ ከ100 ሺህ በላይ ችግኞችን ማዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።   ድሬዳዋ በብርቱካን፣ በመንደሪን፣ በሮማን፣ በአምበሾክና በሌሎች ፍራፍሬ ዓይነቶች በጣም የታወቀች እንደነበረች አስታውሰው፤ ከተማ አስተዳደሩ ይህን ነባር ስም ዳግም ለመመለስ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም የተለያዩ የአትክልትና ፍራፍሬ ክላስተሮች ተደራጅተው በስፋት እየለሙ መሆኑን ጠቅሰው፤ እስካሁን ጀማልን የመሰሉ ከ300 በላይ አርሶ አደሮች በፍራፍሬ ምርት መሰማራታቸውን አመልክተዋል። የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና መከፈቱ ለዚህ ተጨማሪ ዕድል መሆኑን ጠቅሰው፤ በየዓመቱ የሚመረተውን የፍራፍሬ ምርት ጥራት በማሳደግ ለውጭ ገበያ ተደራሽ ለመሆን እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የሚደረግ ተጋድሎ
Aug 25, 2024 698
አለማችን በአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ውስጥ መገኘቷን ተከትሎ የታላላቅ አገራት መሪዎችን ጨምሮ ባለሙያዎች መፍትሄ ለማምጣት ደፋ ቀና እንዲሉ አስገድዷቸዋል። ሰዎች የሚከተሏቸው ያልተገቡ የአኗኗ ዘይቤዎች ተፈጥሮን እያራቆቱ መሄዳቸው እየዋለ ሲያድር በየፈርጁ መልሶ ራሳቸውን ዋጋ እያስከፈላቸው ይገኛል። ቀውሱ ድሃና ሃብታም የሚባሉ ሃገራትን ሳይለይ የጥፋት በትሩን ሁሉም ላይ አሳርፏል። የአየር ንብረት ለውጡ ቀድሞ የበላቸውም ሆነ ቀጣዩ ቀውስ የሚያሰጋቸው የተለያዩ አገራት ችግሩን ለመከላከል ልዩ ትኩረት ሰጥተው መስራትና አጀንዳቸው ብሎም የፖሊሲያቸው አካል አድርገው መንቀሳቀስ ከጀመሩ ዋል አደር ብለዋል። ሁሉም በየፊናቸው የዓለም ስጋት ለሆነው ቀውስ መፍትሔ የሚሉትን ተግባር በማከናወን ላይ ናቸው። ለአለም አየር ንብረት ለውጥ ያደጉ አገራት የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱ ቢሆንም የችግሩ ዋነኛ ገፈት ቀማሾች ግን ታዳጊ አገራት ናቸው። አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በተደጋጋሚ ድርቅ፣ ጎርፍና ተያያዥ ችግሮች በየጊዜው እየተፈተነች ትገኛለች። በተለይም ከፍተኛ የካርበን መጠን ወደ ከባቢ አየር በመልቀቅ ለአየር ንብረት ተፅእኖ ያላት አስተዋጽኦ አራት በመቶ ብቻ ቢሆንም በቀውሱ ግን ዋነኛዋ ገፈት ቀማሽ እሷ ራሷ ሆናለች። ኢትዮጵያም የአየር ንብረት ለውጥ እያስከተለ ባለው ተፅዕኖ ከፍተኛ ተጋላጭ በመሆን በተደጋጋሚ ለሚከሰት የድርቅ ፣የጎርፍና የመሬት መንሸራተት አደጋ ተጋላጭ መሆኗ አልቀረም። ኢትዮጵያ ይህንን ምስል ለመለወጥና ዓለም አቀፍ ችግሩን ለመከላከልና ለመቋቋም የአረንጓዴ ልማት መርኃ ግብር ነድፋ ተግባራዊ እንቀስቃሴዎችን ከጀመረች ዓመታት ተቆጥረዋል። በዚህ ረገድ በተለይም ባለፉት አምስት ዓመታት በተቀናጀ ሁኔታ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ተጠቃሽ ነው። ለአረንጓዴ አሻራ መነሻ የሆኑ ገፊ ምክንያቶች ምን ነበሩ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የቴክኒክ ኮሚቴ አስተባባሪ አደፍርስ ወርቁ (ዶ/ር) እንደሚሉት፣ የስነ-ምህዳር መጎሳቆል ለመርኃ ግብሩ መጀመር አንዱ ገፊ ምክንያት ነው። ኢትዮጵያ ካላት 112 ሚሊዮን ሄክታር የቆዳ ስፋት 54 ሚሊዮን ሄክታሩ በተለያየ ደረጃ የተጎሳቆለ መሆኑን ጥናቶችን ጠቅሰው ተናግረዋል ። በሌላ በኩል በዓመት የሚጨፈጨፈው ከ 92 ሺ ሄክታር በላይ ደን የስነ-ምህዳር መዛባቱን አባብሶታል። ይህም በአገሪቷ ከፍተኛ የስነ-ምህዳር መጎሳቆልና የደን መመናመን እንዲፈጠር ማድረጉን ነው ዶክተር አደፍርስ የሚገልጹት። በእነዚህ ምክንያቶች ኢትዮጵያ ለተደጋጋሚ የድርቅ፣ የጎርፍና የመሬት መንሸራተት አደጋዎች ተጋላጭ ከመሆን ባለፈ ምርትና ምርታማነት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ አድርጓል። የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብሩ በ2011 ዓ-ም ሲጀመር የተዛባውን ስነ-ምህዳር ማሻሻልና ኢኮኖሚውን መደገፍን ዓላማ አድርጎ መነሳቱን ነው አስተባባሪው የሚያስታውሱት። ለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የቦታ መረጣና ችግኝ ማፍላትን ጨምሮ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት አስቀድሞ በመጀመሩ ውጤት መገኘቱን ነው ያነሱት። የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ እንደሚሉት፣ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራን የምትተገብረው ለትውልድ የሚተርፍ ጸጋን ለማውረስ ነው። ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚን ለመገንባትና ከተረጂነት ለመውጣት የአካባቢን ስነ-ምህዳር መጠበቅና መንከባከብ ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል። ባለፉት ዓመታት ገቢራዊ የሆነው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ቀጥተኛ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትንና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ አይነተኛ ሚና መጫወቱን ነው ያብራሩት። መርኃ ግብሩ የከተማ ልማትን የቱሪዝምና ኢንዱስትሪ ዘርፉን ቀጥተኛ ተጠቃሚ በማድረግ ከተረጂነት ለመላቀቅ የሚደረገውን ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ የሚደግፍ አገራዊ እሳቤ ነውም ብለዋል። ባለፉት አምስት ዓመታት በተደረጉ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብሮች ከ32 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን የህዝቡን ማህበራዊ ትስስር የበለጠ ያጠናከሩ እንደነበሩም አስታውቀዋል። የደን ማልማት ሥራዎችም በአየር ንብረት ሥርዓቱ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ከማምጣት ባሻገር የኢትዮጵያ የደን ሽፋን እንዲጨምርና ከ2 ነጥብ 8 ቢሊየን ቶን የካርበን ክምችት እንዲኖር ማስቻሉንም መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ምን ውጤቶችን እያስገኘ ነው ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የተተከሉ ችግኞች የኢትዮጵያን የደን ሽፋን ከነበረበት 17 በመቶ ወደ 23 በመቶ ከፍ እንዲል አድርገዋል። በእርሻ ቦታዎች አካባቢ የሚተከሉ ዛፎች አፈርን በመጠበቅ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። ተደጋጋሚ ድርቅና ጎርፍ ያጠቃቸው የነበሩ ክልሎች ላይ የውሃ መጠንን በመጨመርና የመኖ አቅርቦትን በማሻሻል ተጨባጭ ለውጥ መጥቷል። 2016 ዓ.ም. ''የምትተክል ሀገር፤ የሚያጸና ትውልድ!'' በሚል መሪ ሀሳብ በ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ 7 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞችን የመትከል መርኃ ግብር እንደቀጠለ ነው። በዚህም እስካሁን 6 ነጥብ 8 ቢሊየን ችግኞች መተከላቸውን የግብርና ሚኒስቴር አረጋግጧል። መርኃ ግብሩ በተጠናከረ መልኩ ቀጥሎ ነሃሴ 17 ቀን 2016 በተከናወነው የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ ከ 615 ሚሊየን በላይ ችግኞችን መትከል ተችሏል። ለተከላው በተለይም የአካባቢ መራቆት ይታይባቸው የነበሩ 8 ሺህ ተፋሰሶች የቦታ መጠነ-ልኬትና የካርታ ዝግጅት ቀደም ብሎ መከናወኑ ይታወቃል። የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር እያሱ ኤልያስ፤ በዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር በሁሉም ረገድ የአፈርና የስነ-ምኅዳር ሁኔታን ታሳቢ ያደረጉ ችግኞች የሚተከሉ መሆናቸውን ነው የገለጹት። ከተዘጋጁት ችግኞች መካከል 56 በመቶ ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ዝርያዎች ሲሆኑ፤ ቀሪዎቹ ለደን ልማትና ለአካባቢ ጥበቃ የሚያገለግሉ ናቸው። በየዓመቱ የሚተከሉ ችግኞች የጽቅደት መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና የህብረተሰቡም ችግኞችን የመንከባከብ ባህል እየጎለበተ መምጣቱን በበጎ አንስተዋል ። ትውልዱ በአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር እያሳየ ያለው ተሳትፎና ተነሳሽነት ለአለም ፈተና መፍትሄ የሚሰጥ የዘመኑ አርበኝነት ተምሳሌትና የአለም ችግር መፍቻ ቁልፍ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነው። አለምን በብዙ እየፈተነ ካለው የአየር ንብረት ለውጥ ጋር ኢትዮጵያውያን የሚያደርጉት ተጋድሎ ለሌሎች ተምሳሌት የሚሆንና የኢትዮጵያን ጥረት ለመደገፍ የሚያነሳሳ ተግባር መሆኑ እሙን ነው። በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በተቀናጀና በተናበበ መልኩ መከናወኑ ደግሞ አገሪቷ በቀጣይ ካርቦን በመሸጥ የምታገኘው ገቢ እንዲጨምር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። በአለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥን የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባር የሚፈለገው ግብ እንዲመታ ከተፈለገም በተለይ ለአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው ምእራባውያን አገራት እንደ ኢትዮጵያ ካሉ አገራት ጋር በቅርበት መስራት የግድ ይላቸዋል፡፡ የዘርፋ ምሁራንም "ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ሌሎች አገራትን የሚታደግ ስራ እየሰራች በመሆኑ ለምታበረክተው አስተዋጽኦ ተገቢው ዕወቅና ሊቸራት እንዲሁም ገንዘብን ጨምሮ አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግላት ይገባል "እያሉ ናቸዉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአንድ ጀንበር የ600 ሚሊዮን የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር መጠናቀቁን ሲያበስሩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ''ያሰብነውን ሳናሳካ ጀንበር የምትጠልቅብን አይደለንም፣ በአንድ ጀንበር 615 ነጥብ 7 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል ችለናል''ነው ያሉት። ሁሉም ከተባበረና ለአንድ ዓላማ በጋራ ከቆመ የማይቻል ነገር አለመኖሩን ከኛ ከኢትዮጰያውያን በላይ ማን ሊረዳ ይችላል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉትም በአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላው ህጻናት ተስፋቸውን ተክለዋል፣ወጣቶች ጽናታቸውን አሳይተዋል፣ አረጋውያን ውርስ አኑረዋል፣ ኢትዮጰያውያን በአጠቃላይ ከሊቅ እስከ ደቂቅ በነቂስ ወጥተው የማይደበዝዝና የማይጠፋ አሻራቸውን ለመጪው ትውልድ አኑረዋል። በአንድ ቀኑ የጋራ ርብርብ ከ29 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በ318 ነጥብ 4 ሄክታር መሬት ላይ በጂኦስፓሺያል በተደገፈ መረጃ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል። ይህም ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የሚደረግ ተጋድሎ መሆኑን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ አጽንኦት የሰጡት።        
በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን እንተክላለን
Aug 22, 2024 869
በቃለአብ ጳውሎስ (ኢዜአ) ኢትዮጵያውያን በወርሃ ነሐሴ አጋማሽ በዕለተ ዓርብ በነቂስ ወጥተው በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን የተለያዩ ችግኞችን ለመትከል ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል። በዚህም ኢትዮጵያና ልጆቿ የዓለም ክብረ ወሰን በጃጀቸው ለማድረግ ነገን በናፍቆት እየጠበቁ ነው። ዓርብ ከነሀሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎ "የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የአረንጓዴ አሻራ አሻራችንን ለቀጣይ ትውልድ የምናኖርበት ዕለት ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በመላ ኢትዮጵያውያን ተሳትፎ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ባለፉት ዓመታት በተከታታይ በተካሄዱ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሮች በመላ ኢትዮጵያ በመጀመሪያዉ ምዕራፍ ከ32 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የደንን የፍራፍፍሬና ለሌሎች ግልጋሎት የሚውሉ የችግኞች ተተክለዋል። ለተተከሉት ችግኞች በዘርፉ ሙያተኞች ጭምር በተደረገው ከትትል ከመካከላቸውም 90 በመቶ ያዕሉ መፅደቃቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የተፈጥሮ ሃብትና የሕይወታዊ ሃብት ጥበቃ ሥራ ሲጠናከርና ተከታታይነት ባለው መንገድ ሲሰራ ከአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ነጻ የሆነና መልካምድራዊ አቀማመጥን መሰረት ያደረገ አካባቢያዊ የአየር ንብረት እንዲኖር የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ እድል ይሰጣል፡፡ የልምላሜ ስነ ልቦናዊ፤ ሠላም፤ ደስታ፤ ፍቅርና ተስፋዎችም ይሰጣሉ፡፡ በመጀመሪያው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በመላ አገሪቱ በተተከሉ ችግኞች ቀደም ሲል ተራቁተው የነበሩና የአፈር መሸርሸር አጋጥሟቸው የነበሩ አከባቢዎች በአሁኑ ወቅት ወደ ቀድሞ ገፅታቸው እየተመለሱና መሬቱም እያገገመ መሆኑን የግብርና ባለሙያዎች ምስክርነታቸውን እየሰጡ ነው፡፡ የአረንጓዴ አሻራ ሥራችን በተለያዩ ዘርፎች ውጤቶችን እያሳየን ይገኛል፡፡ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ቀጣይነት ባለው መንገድ በተከታታይ መካሄድ ከጀመረ ጀምሮ ቀደም ሲል ተደጋጋሚ ለድርቅ ተጋላጭ የነበሩ አካባቢዎች ዝናብ ማግኘት ጀምረዋል፤ በደን በተሸፈኑ አከባቢዎች የጎርፍ አደጋን መቀነስ ተችሏል፤ የደረቁ ምንጮችና ሀይቆች እንደገና ቀድሞ ወደ ነበሩበት መመለስ ችለዋል፤ ለበጋና የመኸር እርሻ ተስማሚ የሆነ ዝናብ ማግኘት ተችሏል፡፡ ከሥራ እድል ፈጠራነት አንጻር ለእንስሳት መኖነት፣ ለንብ ማነብ፣ ለካርቦን ሽያጭ በሚውሉ ተግባራት ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታ ፈጠሯል።ከዚህም ባሻገር ኢትዮጵያ ለጎረቤቶቿ ችግኞችን አዘጋጅታ በመስጠት ምር”የአረነጓዴው አሻራ መርሃ ግብር አካል እንዲሆኑና መልካም ጉርብትናቸው ተጠናክሮ እነዲቀጥል በማድረግ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ገበር ለዲፕሎማሲ ግንኝነት መጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በ132 ሺህ 144 የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች የተዘጋጁ ከ7 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የተለያየ ፋይዳ ያላቸው ችግኞች ለመትከል በመላ ኢትዮጵያ የቅድመ-ተከላ ዝግጅቶች ተጠናቀው በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ በመርሃ ግብሩ ከሚተከሉት ችግኞች መካከል ተከላ 25 በመቶ የሚሆነው በዓባይ ተፋሰሶች የሚተከል ይሆናል፡፡ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ዝግጅትና ተከላ ለበርካታ ወጣቶችና ሴቶች ሰፊ የስራ እድል እየፈጠ እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በዘንድሮው የችግኝ ተከላ በ6 ሺህ 200 ተፋሰሶች የስነ-አካላዊ ስራ በመስራት በስነ-ህይወታዊ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ተግባራት እየተከናወኑ ነው፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ ለተከላ የተዘጋጁ ችግኞች ዘርፈ ብዙ ገቢ የሚየስገኙ አትክልትና ፍራፍሬ፤ ጥምር ደን፤ ለከተሜነት ዉበት የሚዉሉ እና ለደን የሚዉሉ ናቸዉ፡፡ ለሁለተኛው አረንጓዴ አሻራ ሁለተኛ ዓመት የአረንጓድ አሻራ ስኬት የሁላችንም ተሳትፎና ዝግጁነት ከወዲሁ ይጠበቃል፡፡ እ.አ.አ. ከ1970 ጀምሮ እየተከበረ ያለው የዓለም 'የመሬት ቀን'ም ጤናማና ዘላቂ ከባቢ መገንባት፣ ለነገ ትውልድ የተሻለ ዓለም ማውረስን ለማበረታታት ያለመ ነው። የዓለም አርሶ አደሮች የአዝዕርት ዝርያዎችን ጠብቀውና አላምደው ዘመናትን ተሻግረዋል። ዳሩ በኢንዱስትሪና እርሻ መስፋፋት ሳቢያ 75 በመቶው የዕጽዋት ዝርያ መጥፋቱን የተባበሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት መረጃ ያሳያል። "ሚሊኒየም ኢኮሲስተም አሰስመንት" የተሰኘ ድረ-ገፅ እንዳስነበበው ደግሞ ከ60 ሺህ እስከ 100 ሺህ የሚደርሱ የዕፅዋት ዝርያዎች የሕልውና አደጋ ተደቅኖባቸዋል። በዚህም ባለድርሻ አካላት በየፊናቸው ችግኝ ተከላን በማስፋፋት የተፈጥሮ ሚዛንን ለመመለስ እጎተጎቱ ነው። መንግሥታትም እንደየነባራዊ ሁኔታቸው የራሳቸው ተሞክሮ አላቸው። የተፈጥሮ ሚዛን መዛባት፣ የምድር መጎሳቆልና የዕጽዋት መመናመን ጉዳይ ያሳሰባቸው ግለሰቦች፣ ማህበራት፣መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት በየፊናቸው አመርቂ ተግባራት አከናውነዋል፤ እያከናወኑም ይገኛሉ። ኢትዮጵያም በተፈጥሮ ኃብት፣ በደን ሀብት ልማት፣ ጥበቃና እንክብካቤ ዘርፍ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወንና ልምዷን ለማካፈል በዓለም ላይ ተጠቃሽ ተሞክሮ ሰንቃ ሀገር ሆናለች። ኢትዮጵያ ከአጠቃላይ ምድራዊ ስፋቷ 60 በመቶ በደን ኃብት የተሸፈነ እንደነበር ታሪክ ያስረዳል። በሂደት ግን በብዝኃ-ሕይወት መመናመን ምክንያት ጥቅል የደን ሽፋን ወደ 3 በመቶ መውረዱ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተደረጉ ጥናቶች ደግሞ የኢትዮጵያ የደን ሽፋን ከ17 በመቶ በላይ ዕድገት መሳየቱ ይነገራል። የኢትዮጵያን የደን ልማት ጅማሮ መቼት በእርግጠኝነት ለመናገር አዳጋች እንደሆነ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ይዘትና ቅርጹ ይለያይ እንጂ ነባር የችግኝ ተከላ ባህልና ልምድ እንዳለው ያወሳሉ። ያም ሆኖ በሺህ ዘመናት ባለታሪኳ ኢትዮጵያ ደን ድንናን መንግሥታዊ ቁርጠኝነት ወስደው የሰሩ መሪዎችም ነበሯት። ለአብነትም በመካከለኛው እና በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ተሞክሮዎችን ማውሳት ይቻላል። ከመካከለኛው ዘመን ታሪክ የኢትዮጵያ ንጉሠ-ነገሥት መካከል አፄ ዳዊት ከ1375- 1404 በነበሩ የግዛት ዘመናቸው ደን ጭፍጨፋና የእንስሳትን አደን ለመከላከል በአገሪቱ ሰባት የአካባቢ ጥበቃ ጣቢያዎች አቋቁመው እንደነበር ዜና መዋዕላቸው ይናገራል። ልጃቸው አፄ ዘርዓ ያዕቆብም በጅባት፣ በወፍ ዋሻ፣ የወጨጫን፣ መናገሻና የየረር ጋራዎችን የደን ክምችት ጥበቃ አጠናክረዋል፤ ‘የንጉሥ የደን ክልል’ አሰኝተው ኢትዮጵያን የደን ካባ ለማልበስ ጥረዋል። ችግኞችን አፍልቶ የመትከል ሥራዎች ደግሞ በአፄ ልብነ-ድንግል ዘመነ-መንግሥት ስለመጀመራቸው ይወሳል። ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ በሚገኘው የሱባ ደንም ንጉሠ-ነገሥቱ ከወፍ ዋሻ የዛፍ የሱባ/መናገሻ/ ደን ውስጥ ዛፎችን ስለመትከላቸው ይነገራል። በእርግጥ በመካከለኛው ዘመን ደን የመንከባከብና ዛፍ የመትከል ጅማሮ በዘመነ-መሳፍንት እንደተዳከመ ይነገራል። ሌላው በደን ድነና ታሪካቸው የሚነሳው አፄ ምኒልክ ናቸው። የአፄ ዘርዓ ያዕቆብን ‘የንጉሥ ደን ጥብቅ ሥፍራ’ ፅንሰ-ሃሳብን አጠናክረዋል። በዘመናቸው ያጋጠማቸውን ፈተናም ለደን ድንና ተጨማሪ ኃይል የገፋፋቸው ይመስላል። አፄ ምኒልክ የደን የሕግ ማዕቀፍ አውጥተዋል፤ አማካሪም ቀጥረዋል። ደን ሁሉ የመንግሥት ንብረት እንዲሆንም ደንግገዋል። ፈጥኖ-አደግ የዛፍ ዝርያዎችን ከውጭ አስመጥተዋል። ዛሬ አገሪቷን የተቆጣጠረው አውስትራሊያዊው ባሕር ዛፍ (ኢካሊፕተስ) የትመጣነቱ ዳግማዊ ምኒልክ መሆኑ እሙን ነው። አፄ ምኒልክ በመንግሥት ከሚለማው ደን በተጨማሪ ተራው ዜጋ በባለቤትነት በደን ልማት እንዲሳተፍም አዋጅ አውጥተው እንደነበር የመዕዋለ ዜና ዘጋቢያቸው ጸሐፊ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ ወልደ አረጋይ ጽፈዋል። አዋጁም ዛፍ የተከለ የመሬት ግብሩን ምሬዋለሁ የሚል ነበር። ለደን ጨፍጫፊዎችም ንብረታቸውን እንዲወረስና ብርቱ ቅጣት እንዲቀጡ ሕግ አርቅቀው እንደነበር ይወሳል። አፄ ምኒልክ ራሳቸው ከተከሏቸው የዛፍ ችግኞች መካከል በእንጦጦ ማርያም ቤተክርስቲያን እና በደቡብ ወሎ ወረኢሉ ከተማ የሚገኙት ተጠቃሽ ናቸው። በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ-መንግሥትም ዛፍ መትከል ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ተግባር እንደነበር ይነገራል። በደርግ ዘመን የተከሰተው ድርቅና ረሀብ ደግሞ በኢትዮጵያ ለሌላ ተጨማሪ የችግኝ ተከላ ዘመቻ መንስዔ ሆኗል። በደርግ ሥርዓተ-መንግሥት ችግኝ ተከላ እንደ አፄ ምኒልክ ለችግኝ ተካዩ ማበረታቻ የሚያሰጥ ተግባር ሆኖ እንደነበር ይነገራል። በአካባቢ ጥበቃ ጠንካራ የሕግ ማዕቀፎች ተቀርጸው ገቢራዊ ተደርገዋል። በወቅቱ የተደረገው የተራቆቱ አካባቢዎችን በተለይም ተራሮችን ዛፍ የመትከል ዘመቻ ፍሬ አፍርቷል። ዛሬ በበርካታ የአገሪቷ አካባቢዎች የደን ጸጉር የለበሱ ተራሮች ሕያው ምስክር ሆነዋል። የደርግ ዘመን አረንጓዴ አሻራዎች ዛሬ የተራሮች አረንጓዴ ዕንቁ ሆነዋል። በደርግ ዘመነ-መንግሥትም የአካባቢ ጥበቃን የተመለከቱ ፖሊሲዎች ተቀርፀዋል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ከደን መመናመንና ከተፈጥሮ ኃብት መራቆት ጋር ተያይዞ አፍሪካና ኢትዮጵያ ያጋጠማቸውን ቀውሶችና ያለባቸውን ተግዳሮቶች ለምዕራቡ ዓለም አስረድተዋል፤ ተሟግተዋልም። አቶ መለስ አረንጓዴ ኢኮኖሚ እስከማለት ድረስ የዘለቁበትና ለምዕራቡ ዓለም ያስተዋወቁት ፓኬጅም የሚጠቀስ ነው። የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ቢኖሩም ዳሩ በዘመነ-ኢሕአዴግ በአገር ውስጥ ከፍተኛ የደን ውድመት የደረሰበት ወቅት እንደነበር ጥናቶች ይጠቁማሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አረንጓዴ ኢኮኖሚን፣ የአካባቢ ጥበቃንና የተፈጥሮ ኃብት መንከባከብን ትልቅ ትኩረት ሰጥተውታል። ከ2011 ዓ.ም የክረምት ወቅት ጀምሮ በየዓመቱ ‘አረንጓዴ አሻራ’ ገቢራዊ እያደረጉ ይገኛሉ። በመላ አገሪቱ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች እያሳተፈ መርሃ-ግብሩ እንደቀጠለ ነው። ኢትዮጵያን በአፍሪካና በዓለም አቀፍ መድረክ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ተምሳሌት ያደረገ ተግባር ነው። አሁን ላይ ደግሞ የችግኝ መትከል ባህል ከመንግሥት ቅስቀሳና ከግለሰቦች ጥረት ባለፈ ሀገራዊ ቅርፅ የያዘ ሲሆን ባለፉት አምስት ዓመታት የተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ትልቁ ማሳያ ነው። በመሪዎች ደረጃ ይህን አነሳን እንጂ በየዘመኑ በአረንጓዴ አሻራ ላይ ጉልህ አስተዋጽዖ ያበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማትም ተፈጥረዋል፡፡ ዛፍ እንደ ቅርስ፣ እንደ ሐውልት ታሪክ ማስተላለፊያ ነውና በየዘመኑ ትጉ ሰዎች ለትውልድ ቅርስ ትተው አልፈዋል። የአረንጓዴ አሻራ ፋይዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ2012 የዓለም አካባቢ ቀን በተከበረበት ዕለት “ብዝኃ- ሕይወትን መጠበቅና መንከባከብ ቅንጦት ሳይሆን ህልውና መሆኑን አይተናል” በማለት የአካባቢ ደኅንነት የሕልውና ጉዳይ መሆኑን አረጋግጠዋል። እንደ ሌላው ክፍላተ-ዓለም ሁሉ ኢትዮጵያም በአየር ንብረት ለውጥና የአካባቢ መራቆት ችግር ተጋርጦባታል፤ ለጎርፍ አደጋ፣ ለአፈር መሸርሸር፣ ለደን መጥፋትና ለብዝኃ-ሕይወት ኪሳራ ዳርገዋታልም ብለዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ዕድገት ሁኔታዎችን የማመቻቸት አካል መሆኑን በመግለጽ፤ ይህ ግብ በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ 20 ቢሊዮን ችግኞን ለመትከል ራዕይ እንድትሰንቅ እንዳስገደዳትም ተናግረው ነበር። ይህ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ደግሞ ‘አረንጓዴ አሻራ’ ተሰኝቷል።የመጀመሪያው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ገብር ክዋኔም በአራት ዓመታት 20 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ተወጥኖ፤ አፈጻጸሙ ከዕቅድ በላይ ሆኖ 25 ቢሊዮን ችግኞችን መተከላቸውን መረጃዎች ያስረዳሉ። የአራት ዓመታት የመጀመሪያው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተጠናቆ ሁለተኛው ምዕራፍ በቀዳሚው ዓመት መጀመሩ ይፋ ሆፐኖ ዘንድሮ ሁለት ብሏል። በኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ አጀማመር የመጀመሪያው ምዕራፍ አረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በ2011 ዓ.ም በይፋ ሲጀመር አንድ ሰው 40 ችግኞችን እንዲተክል ተሰልቶ በድምሩ 4 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ግብ ተቀምጦ ነበር። መላ ከ20 ሚሊዮን የሚልቁ ኢትዮጵያውያን የመሪያቸውን የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐበይን ፈለግ ተከትለው ለመርሃ ገብሮቹ ተግተው በመረባረባቸው ከዕቅድ የ5 ቢሊዮን ብልጫ ያለው ችግኝ በመትከል ከተቀመጠው ግብ በላይ ተሳክቷል። በሁለተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በ2012 ዓ.ም 5 ቢሊየን ችግኞች ለመትከል ታቅዶ ከዕቅድ በላይ ተሳክቷል። በተለይ የፍራፍሬ ተክሎች ትኩረት ተሰጥቶት ነበር። በ2013 ዓ.ም የተካሄደው ሦስተኛው ዙር አረንጓዴ አሻራ "ኢትዮጵያን እናልብሳት" በሚል መሪ ሀሳብ ተተግብሮ ሯል። ይህም ዙር ችግኞችን ለጎረቤት አገራት በመስጠት ኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ አርዓያ እንድትሆን በማስቻል ድንበር ዘለል በመሆኑ ለየት ያለ ባህሪ የነበረው ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ለጎረቤት አገራት ችግኞችን በመለገስ የልማት አቅጣጫዋ ከጎረቤቶቿ ጋር አብሮ የመልማት፣ የማደግና የመበልጸግ መሆኑን በተግባር አስመስክራለች። ሰኔ 14 ቀን 2014 ዓ.ም "አሻራችን ለትውልዳችን" በሚል መሪ ሀሳብ በይፋ የተጀመረው አራተኛው ዙር አረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር 6 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ ከዕቅድ በላይ መሳካቱ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በቅርቡ ባቀረቡት ሪፖርት እንዳስታወቁት በመጀመሪያው ምዕራፍ የአረንጋዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 25 ቢሊዮን ችግኞች ተተክለዋል። በችግኝ ተከላው በየዓመቱ በአማካይ 20 ሚሊዮን ሕዝብ ተሳትፏል። ከተተከሉት ችግኞች መካከል 52 በመቶ የጥምር ደን እርሻ፣ የፍራፍሬ እና የእንስሳት መኖ ናቸው። ሀገር በቀል ዝርያዎች ከፍተኛ ትኩረት ማግኘታቸውን አንሰተዋል። የፅድቀት መጠናቸው ደግሞ ከ90 በመቶ በላይ ተሻግሯል። የችግኝ ጣቢያዎች ብዛት፣ ደረጃ፣ ጥራትና አቅም አድጓል። ከመጀመሪያው ምዕራፍ ትሩፋቶች መካከል አረንጓዴ የአኗኗር ዘይቤ መፈጠሩ፣ የደን ጭፍጨፋ ምጣኔ በግማሽ እንዲቀንስ ማስቻሉ፣ ወጣቶችና ሴቶችን ጨምሮ ለብዙዎች የገቢ ምንጭና የሥራ ዕድል ፈጥሯል። የተራቆቱ አካባቢዎችና ተፋሰሶች እንዲያገግሙ አስችሏል። ባገገሙ ተፋሰሶችም በርካታ አርሶና አርብቶ አደሮች በንብ ማነብና በእንስሳት መኖ ልማት በመሳተፍ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኙ እና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸው ተረጋግጧል። ለአብነትም በመርሃ ገበሮቹ የተተከሉ የአቮካዶ ምርት ለውጭ ገበያ በመቅርቡ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሁለተኛዋ አቮካዶ አምራች ለመሆን መብቃቷንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ሁለተኛው ምዕራፍ ሁለተኛው ዙር የዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር መሪ ሀሳብ 'ነገን ዛሬ እንትከል' የሚል ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በአፋር ክልል የሁለተኛው ምዕራፍ የመጀመሪያ ዙር ማስጀመራቸው ይታወሳል። በዚህ ወቅት እንዳሉት በቀጣይ አራት ዓመታት በሚተገበረው ሁለተኛው ምዕራፍ 25 ቢሊዮን ችግኞች ይተከላሉ። እስከ መስከረም 2017 ዓ.ም በሚዘልቀው የዘንድሮው መርሃ- ግብርም 60 በመቶ የጥምር ደን እርሻ ችግኞች፣ 35 በመቶ ደግሞ የደን ችግኞች ሲሆኑ 5 በመቶ ለከተማ ውበት የሚውሉ ችግኞች ናቸው። ለልጆቻችን ዕዳ ሳይሆን ልማትን ማሸጋገር እንደሚገባም ተናግረዋል። በዚህም ዛሬ ያለው ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን የማሸጋገር ታሪካዊ ኃላፊነት እንዳለበትም በአጽንዖት አስገንዝበዋል። ነገን ዛሬ የመትከል ሥራችንን በአስተማማኝ ሁኔታ እያረጋገጥን በውጤታማነት ለመቀጠል እየሰራን ነው' ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የጥራት ጉዳይ የአረንጓዴ አሻራ ትኩረት እንደሚሆን ገልጸዋል። በተለይም ለፍራፍሬ እና ሀገር በቀል ዛፎች ቀዳሚ ትኩረት መሰጠቱን አስታውሰዋል። እንደየመልክዓ-ምድሩ ዓይነት ተስማሚና በአጭር ጊዜ ለምግብነት የሚደርሱ የፍራፍሬ ችግኞችን በመትከል የራስ ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ያለመ ነው። ውበት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራና ገቢ አበርክቶ ያላቸው ችግኞች ላይ ይተኩሯል። ሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሮች ዓመታት በአጠቃላይ 50 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል የኢትዮጵያን ገፅታ መለወጥ፣ በአፍሪካ ቀዳሚ የአቮካዶ አምራች ሀገር ማድረግ መሻት ያላት ሲሆን፤ ለስኬታማነቱም ጥራት ያለው ፖሊሲ ገቢራዊ እንደሚደረግ አንስተዋል። ያለ ልዩነት ለነገው ትውልድ የተሻለች ሀገርን ለማስረከብ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ስኬት መረባረብ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ገበር 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞች ተዘጋጅተዋል። የሚተከሉ ችግኞችን በቴክኖሎጂ መከታተል የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት ተዘርግቶ ክትትል ይደረጋል። በሁለተኛው ምዕራፍ አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የምግብ ዋስትናን እና የሕዝብን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ፣ የካርቦን ፋይናንስ ገቢን በሚያሳድግና የአፍሪካ 2063 አጀንዳ ስኬትን በሚያግዝ መልኩ ይተገበራል። የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ የአገራችንን የነገ ዕጣ ፈንታ የሚወስን፣ ጊዜውን የሚዋጅ ተግባር ነው። ኢትዮጵያ በተፈጥሮ የተቸረችው አየር ንብረትና መልክዓ-ምድር ለዚህ የሚጋብዝ ነው። ደን ልማት ዘላቂ ሥራ መሆን አለበት። ባለቤትነት እንዲጨምርም በወል መሬት ብቻ ሳይሆን በግል ይዞታም አረንጓዴ አሻራ መተግበር አለበት። የደን ልማት አካል የሆነው አረንጓዴ አሻራ አገራዊ ፋይዳው ሁለንተናዊ ነው። የአረንጓዴ አሻራ ልማት አገራዊ ፋይዳው ባለፈ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ በረከቶችን ተሸክሟል። የደን ልማት የቅንጦት ሳይሆን የሕልውና ጉዳይ ነው የሚባለው ለዚህ ነው።የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ውጥን በአገሩ ጉዳይ አንድ የሆነው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነገ በነቂስ ወጥቶ እንደሚያሳካውና ኢትዮጵያው የዘርፉን የክብረ ወሰን ባለቤት እንደምትሆን ሁሉም እርግጠኛ ሆኖ ነገን በጉጉት እየጠበቀ ነው። የነገ ሰው ይበለን!  
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 19466
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 22248
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 12803
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል።   “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል።   ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 14156
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 38663
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 31148
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 22248
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 19466
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 16752
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 16101
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 16038
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 15734
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 38663
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 31148
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 22248
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 19466
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
ለዘመናት ጥያቄ ምላሽ ሰጪው ጭላንጭል ተስፋ
Aug 8, 2024 1467
በትንሳኤ ገመቹ (ኢዜአ) የዛሬው የ76 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ ያኔ በለጋነታቸው፤ ዳገት፣ ቁልቁለት፣ ሜዳ ሳይመርጡ እንዳሻቸው በሚቦርቁበት፣ ሮጠው በማይጠግቡበት፣ ገና ታዳጊ ሳሉ በ13 ዓመት ዕድሜያቸው በደረሰባቸው የተሽከርካሪ አደጋ ነው ሁለት እግሮቻቸውን ያጡት። ይሁንና ይህ ጉዳታቸው ሳይበግራቸው በብዙ ውጣ ውረድና እልህ አስጨራሽ ትግል በትምህርታቸው እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ መዝለቅ ችለዋል። እኚህ ሰው ካለሙበት ለመድረስ በርካታ ውጣ ውረዶችን አልፈዋል። ትውልድና ዕድገታቸው በአዲስ አበባ መሆኑ በተሽከርካሪ ወንበር (ዊልቼር) ድጋፍ ወደ ትምህርት ቤት የመሄድ ዕድልን ሰጥቷቸዋል፤ የሥራ ዓለምንም ተቀላቅለዋል። ይህ ስኬታቸው ግን እንዲሁ እንደዋዛ የተገኘ አልነበረም። የመዲናዋ የእግረኛም ሆኑ የተሽከርካሪ መሄጃ አስፓልት መንገዶች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያላደረጉ፤ ለዊልቼር መንቀሳቀሻ በቂ ቦታ የሌላቸውና አስቸጋሪ መሆናቸው እንቅስቃሴያቸውን በእጅጉ አክብዶባቸዋል፤ ለዓመታት በዊልቼር የተመላለሱባቸው ለእግረኛ እንኳን የማይመቹ የተቦረቦሩ፣ ወጣገባ፣ ዳገታማና ቁልቁለታማ መንገዶች ተጨማሪ የሕይወት ፈተናዎቻቸው ነበሩ። አዛውንቱ በታዳጊ፣ በወጣትነት እና በጉልምስናም ዕድሜያቸው በእጅጉ የፈተኗቸውን እነዚያን የስቃይ ጊዜያት “መቼም አልረሳቸውም” ሲሉ እንደ እርሳቸው የአካል ጉዳት የገጠማቸውን ሰዎች የዕለት ተዕለት ተግዳሮቶች ይገልጻሉ፤ አቶ አለበል ሞላ። ዓለም አቀፋዊ የአካል ጉዳተኝነት ሁኔታ በዓለም-አቀፉ የአካል ጉዳተኞች መብት ኮንቬንሽን አንቀፅ አንድ እንደተመለከተው አካል ጉዳተኝነት ከረጅም ጊዜ የአካል፣ የአዕምሮ ወይም የስሜት ህዋሳት እክል ጋር የሚኖሩና በአመለካከትና በአካባቢያዊ ጋሬጣዎች ምክንያት በማኅብረሰቡ ውስጥ ሙሉና ትርጉም ያለው ተሳትፎ በእኩልነት ማድረግ የማይችሉ ሰዎችን ያጠቃልላል። አካል ጉዳት ማለት፤ የአካል ክፍልን ማጣት ወይም የተግባር መገደብን የሚያመላክት ፅንሰ-ሀሳብ ነው። አካል ጉዳተኝነት ማለት ደግሞ ከሌሎች ሰዎች ጋር እኩል ተሳትፎ እንዳያደርጉ የሚያደርግ የአካል ጉዳት፣ የአመለካከት ችግርና አካባቢያዊ መሰናክሎች ድምር ውጤት ነው። በዓለም ላይ የተለያየ አይነት አካል ጉዳተኝነት የሚያጋጥም ሲሆን፤ ዓይነ-ስውርነት፣ መስማት መሳን፣ የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት፣ ማየትና መስማት መሳን እንዲሁም ተደራራቢ የአካል ጉዳት ዋና ዋናዎቹ ናቸው። የዓለም ጤና ድርጅት እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር 2023 ያወጣው መረጃ እንደሚያመላክተው 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ያህል ሰዎች የተለያየ አይነት የአካል ጉዳት ያጋጥማቸዋል። ይህ አሃዝ 16 በመቶ የሚሆነውን የዓለም ሕዝብ ቁጥር የሚወክል ነው። ይህም የአካል ጉዳት ከስድስት ሰዎች በአንዱ ላይ አለ ማለት ነው። እነዚህ ዜጎች ከአካል ጉዳተኝነት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ተያያዥ የጤና እክሎች የሚያጋጥማቸው መሆኑንም መረጃው ያሳያል። ድብርት፣ አስም፣ የስኳር በሽታ፣ ስትሮክ፣ አላስፈላጊ የሰውነት ክብደት መጨመር፣ የአፍ ጤና እክልና ሌሎችም ተያያዥ በሽታዎች ከአካል ጉዳተኝነት ጋር ተያይዘው ከሚከሰቱት መካከል ይጠቀሳሉ። በዓለም ላይ ስለ አካል ጉዳተኝነት ያለው ስያሜ የተለያየ ነው። ለምሣሌ በተለያዩ አገራት ያለው ቴክኖሎጂ፣ የሰዎች አመለካከት፣ ከድጋፍ አሰጣጥና ከመሰረተ ልማት ተደራሽነት ጋር ተያይዞ ለአካል ጉዳተኝነት የሚሰጠው ስያሜ እንዲለያይ አድርጓል። ለአብነት ለዓይነስውራን ልዩ የዓይን መነፅርና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ማቅረብ በሚችሉ አገራት ዓይነስውራን እንደ አካል ጉዳተኛ አይታዩም። የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው ሕፃናት ወደ ትምህርት ቤት የማይሄዱት በወላጆቻቸው የተዛባ አመለካከትና ትምህርት ቤቶች ለልዩ ፍላጎት ማስተማሪያ ተገቢውን ቁሳቁስ ማሟላት ባለመቻላቸው እንጂ ሕፃናቱ መማር ስለማይችሉ ወይም ቢማሩ ስለማይለወጡ አይደለም። ይህን ማሟላት በቻሉ አገራት የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው ልጆች እንደ አካል ጉዳተኛ ሊቆጠሩ አይችሉም። በሌላ በኩል በተሽከርካሪ ወንበር (ዊልቼር) ለሚንቀሳቀስ ሰው ትምህርት ቤትም ሆነ ወደ ስራ ቦታ ለመሄድ የሚያዳግተው አካል ጉዳቱ ሳይሆን፤ ለመንቀሳቀስ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ሳይፈጠርለት ሲቀር ብቻ ነው። የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባሕል ተቋም (ዩኔስኮ) መረጃ እንደሚያሳየው በታዳጊ አገራት 90 በመቶ አካል ጉዳተኛ ልጆች ትምህርታቸውን አይከታተሉም። እ.ኤ.አ 1998 ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥናት የአካል ጉዳተኛ ጎልማሶች ዓለም አቀፋዊ የማንበብ ደረጃ ሦስት በመቶ ሲሆን የአካል ጉዳተኛ ሴቶች ደግሞ አንድ በመቶ ብቻ መሆኑን አመላክቷል። አካል ጉዳተኝነት በአፍሪካ በአፍሪካ ከ80 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የተለያየ አይነት የአካል ጉዳት እንዳለባቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ ያሳያል። በአህጉሪቱ በተለይም በየጊዜው የሚከሰቱ አለመረጋጋቶች፣ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች በርካቶችን ለአካልና ለአዕምሮ ጤና ጉዳት የሚዳርጉ ምክንያቶች ሆነው ይጠቀሳሉ። የአብዛኞቹ የአፍሪካ አገራት ፈተናዎች የሆኑት የምጣኔ ሀብት እና የመሠረተ ልማት ችግሮች አካል ጉዳተኞችን የበለጠ ጫና ውስጥ የሚከቱ ከመሆናቸው ባሻገር ተገቢውን ድጋፍ እንዳያገኙ ተግዳሮት ሆነው ቆይተዋል። አካል ጉዳተኝነት በኢትዮጵያ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የዓለም ጤና ድርጅትና የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ 20 ሚሊዮን ዜጎች ከተለያየ ዓይነት የአካል ጉዳት ጋር እንደሚኖሩ ግምት አስቀምጠዋል። ይሁንና የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ከተካሄደ በርካታ ዓመታትን ያስቆጠረ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ምን ያህል አካል ጉዳተኞች እንዳሉ ትክክለኛ መረጃ ማግኘትን አዳጋች አድርጎታል። እነዚህ ዜጎች በጎጂ ልማዶችና በተዛባ አመለካከት እንዲሁም በሕግጋት እና በአፈጻጸማቸው ክፍተት ሳቢያ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን እየተጋፈጡ እንደሆነም ይጠቁማሉ። በኢትዮጵያ ለአካል ጉዳተኞች የሚመጥን የመሠረተ ልማት አውታር ግንባታ አለመኖርና የአገልግሎት አሰጣጥ ጉድለት በርካቶችን ለከፍተኛ እንግልትና ለተጨማሪ የጤና እክል እንዲጋለጡ አድርጓቸዋል። በመንገዶች ላይ የቁም እና የወለል ምልክቶች አለመኖር፤ በሕንፃዎች ላይ አካል ጉዳተኞችን የሚደግፉ መወጣጫዎች እጥረት፤ የመጸዳጃ እና ሌሎችም ተያያዥ አገልግሎቶች ላይ አካል ጉዳተኞች ተደጋጋሚ ቅሬታ እንዲያነሱም አድርጓል። ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ስምምነትን (Convention) ተቀብላ የሕጓ አካል አድርጋለች። የአካል ጉዳተኞች የሥራ ሥምሪት እና የሕንፃ አዋጆች ጸድቀው ወደ ስራ ተገብቷል። ከ60 በመቶ በላይ አካል ጉዳተኞችን ለቀጠረ ድርጅት ከታክስ እና ከቀረጥ ነፃ የሚያደርግ መመሪያ ወጥቶ ስራ ላይ ውሏል። ይሁን እንጂ አካል ጉዳተኞችን እኩል ተሳታፊና ፍትሃዊ ተጠቃሚ ያደርጋሉ ተብለው የወጡ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች መሬት ላይ ወርደው በተጨባጭ ምን ለውጥ አመጡ? አፈፃፀማቸውስ? የሚለው አሁንም ድረስ የበርካቶች ጥያቄ ነው። በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 41 ንዑስ አንቀፅ 5 እንደተደነገገው “መንግሥት የአካልና የአዕምሮ ጉዳተኞችን፣ አረጋዊያንና ያለ ወላጅ ወይም ያለ አሳዳጊ የቀሩ ሕፃናትን ለማቋቋምና ለመርዳት የአገሪቱ የኢኮኖሚ አቅም በፈቀደው ደረጃ እንክብካቤ ያደርጋል” የሚል ድንጋጌ ተቀምጧል። መንግሥት አካል ጉዳተኞችን በሚችለው አቅም መርዳት እንዳለበት የሚገልጸው ይህ ድንጋጌ በራሱ ትችት የሚቀርብበት ነው። ድንጋጌው አካል ጉዳተኞች አምራች እንዳልሆኑ እንዲሰማቸው የሚያደርግ መሆኑን ከሚተቹት መካከል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የልዩ ፍላጎትና የአካቶ ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ተክለማርያም (ዶ/ር) አንዱ ናቸው። እንደ እርሳቸው፤ በዚህ አንቀፅ አካል ጉዳተኞችን ዕድሜያቸው ካልደረሱ ሕፃናት እንዲሁም ስራ ሰርተው ከጨረሱ አረጋዊያን እኩል ቦታ መስጠቱ ተገቢ አይደለም። አካል ጉዳተኞች በውክልና ካልሆነ ንብረታቸውን ማውረስ እንደማይችሉ በሕገ መንግሥቱ መደንገጉ አካል ጉዳተኞች “አልችልም” የሚል የበታችነት ስሜት እንዲሰማቸው የሚያደርግ ነው። አካል ጉዳተኞች ሁኔታዎች ከተመቻቹላቸውና ዕድሉ ከተሰጣቸው ለራሳቸውም ሆነ ለሀገራቸው ያላቸው አበርክቶ ከፍተኛ ነው። ስለሆነም ይህ ለትርጉም ተጋላጭ የሆነውን አንቀፅ ማስተካከልና የኅብረተሰቡን አመለካከት መቀየር ካልተቻለ አካል ጉዳተኞች በሀገራዊ ጉዳዮች እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ የመሆን ዕድላቸው የሚፈለገውን ያህል አይሆንም። የአካል ጉዳት ያለባቸውን ዜጎች የተመለከቱ ሕጎች ተፈጻሚ እንዳይሆኑ የሚያደርጉ አመራሮችና ፈጻሚዎችን ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ ስለመሆኑ የሚጠቁሙት ተባባሪ ፕሮፌሰሩ፤ ሕጉን አስገዳጅ ማድረግ እስካልተቻለ ድረስ ክፍተቱ ሊፈታ አይችልም። ትምህርት ሚኒስቴር የሚያወጣቸው ፖሊሲና ስትራቴጂዎች አካቶ ትምህርትን የሚደግፉ ቢሆኑም፤ በየትምህርት ቤቶቹ ያለው አተገባበር ላይ ክፍተት መኖሩን አመልክተው፤ ይህም ከአመራር አካላት በጎ ፈቃደኝነትና ግንዛቤ ጋር ተያይዞ የሚፈጠር ነው ይላሉ። በኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ ቀደም ካሉት ዓመታት ከነበረው የተሻለ ግንዛቤ ቢፈጠርም፤ አሁንም 90 በመቶ የሚሆኑት ከትምህርት ውጭ ከመሆናቸውም ባለፈ አንዳንድ የሚወጡ ሕጎች አካል ጉዳተኞችን የዘነጉ ናቸው። አካል ጉዳተኞች የትምህርት ዕድል ማግኘታቸው በኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያደርጋል። ይህም ካላቸው ከፍተኛ ቁጥር አኳያ ለአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት ዕድገትና ለድህነት ቅነሳ የድርሻቸውን እንዲወጡ ያስችላል ሲሉም ያክላሉ። በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ የሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዲግሪ ተማሪዎች የአካቶ ትምህርትን እንዲወስዱ መደረጉ አበረታች ውጤት መሆኑን የሚጠቅሱት ተባባሪ ፕሮፌሰሩ፤ “መሰል አስገዳጅ ሁኔታዎች የተዛባ አመለካከትን በዘላቂነት ለመፍታት ያስችላሉ” ይላሉ። በሕገ-መንግሥቱ አንቀፅ 9/4/ ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የሀገሪቷ ሕግ አካል እንዲሆኑ ይደነግጋል። ኢትዮጵያ ካፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች (Conventions) ውስጥ አንዱ ዓለም-አቀፍ የአካል ጉዳተኞች መብት ስምምነት ሲሆን፤ በዚህ የሕገ መንግሥት ድንጋጌ መሰረት ኮንቬንሽኑ የአገሪቷ የሕግ አካል ሆኗል ማለት ነው። በተጨማሪም የሕገ-መንግሥቱ አንቀፅ 25 ስለእኩልነት መብት ሲዘረዝር ሁሉም ሰዎች በዘር፣ በብሔር፣ በቀለም፣ በፆታ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ፣ በማኅበራዊ አመጣጥ፣ በሃብት፣ በትውልድ ወይም በሌላ አቋም ምክንያት ልዩነት ሳይደረግባቸው እኩልና ተጨባጭ የሕግ ዋስትና የማግኘት መብት እንዳላቸው ይደነግጋል። በዚህ አንቀፅ በአካል ጉዳት ምክንያት ልዩነት መደረግ እንደሌለበት በግልፅ ባያስቀምጥም "በሌላ አቋም ምክንያት" የሚለው ሐረግ አካል ጉዳትንም እንደሚጨምር ታሳቢ ይደረጋል ማለት ነው። በሕገ-መንግሥቱ አንቀፅ 41 ንዑስ አንቀፅ 5 ስለአካል ጉዳተኞች መብት በግልፅ ያስቀመጠ ሲሆን፤ አንቀፁ “መንግሥት የአካልና የአዕምሮ ጉዳተኞችን ለማቋቋምና ለመርዳት የአገሪቷ ኢኮኖሚ በሚፈቅደው መጠን እንክብካቤ ያደርጋል” ይላል። ይህ አንቀፅ አካል ጉዳተኞች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ የሰጠው መብት ቢኖርም ወደ መሬት ወርዶ ተጨባጭ ለውጥ ከማምጣት አኳያ በርካታ ቀሪ ስራዎች አሉ። ሀገሪቷ ከምትከተለው እኩል የሥራ ዕድል መርሆ ጋር የሚጣጣም፣ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሥራ ሁኔታ የሚፈጥርና በሥራ ሥምሪት የሚደርስባቸውን አድልዎ በፍርድ መድረኮች በቀላሉ ለማስረዳት የሚያስችል አሠራር መዘርጋት ወሳኝ በመሆኑ ስለ አካል ጉዳተኞች የስራ ስምሪት መብት የሚደነግግ የአካል ጉዳተኞች የሥራ ሥምሪት መብት አዋጅ ቁጥር 568/2000 ወጥቶ ተግባራዊ ሆኗል። በዚህ አዋጅ ላይ እንደተመላከተው፤ የሥራው ጠባይ የማይፈቅድ ካልሆነ በቀር የተፈላጊ ችሎታ መመዘኛዎችን አሟልቶ የተገኘና በውድድር ውጤቱ ብልጫ ነጥብ ያገኘ ማንኛውም የአካል ጉዳተኛ በምንም ዓይነት መልኩ መድልዎ ሳይደረግበት፣ በማንኛውም መሥሪያ ቤት ወይም ድርጅት ውስጥ የሚገኝን ክፍት የሥራ ቦታ በቅጥር፣ በዕድገት፣ በድልድል ወይም በዝውውር የመያዝ መብት አለው። በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር በሚሰጥ የሥልጠና ፕሮግራም የመሳተፍ መብት እንዳለውና የተፈላጊ ችሎታ መመዘኛዎችን አሟልቶ የተገኘና ለውድድር ውጤት እኩል ወይም ተቀራራቢ ነጥብ ያገኘ ማንኛውም አካል ጉዳተኛ በምንም ዓይነት መልኩ መድልዎ ሳይደረግበት የተመደበበት የሥራ መደብ የሚያስገኘውን ደመወዝና ሌሎች ጥቅሞች የማግኘት መብት እንዳለው አዋጁ ያትታል። የአካል ጉዳተኞች መብቶች ኮንቬንሽን ስምምነት አዋጅ ቁጥር 676/2002 ላይ እንደተመላከተው፣ የስምምነቱ ዋነኛ ዓላማ ሁሉም አካል ጉዳተኞች በሁሉም ዓይነት ሠብዓዊ መብቶችና መሠረታዊ ነፃነቶች ረገድ ሙሉ እና እኩል ተጠቃሚነት ያላቸው ስለመሆኑ ማረጋገጥ፣ ማሳደግና ለነዚሁ ጥበቃ ማድረግ፣ ብሎም ተፈጥሯዊ ክብራቸውን ከፍ ማድረግ ነው። በዚሁ አዋጅ ስለ ሥራ እና ቅጥር በተቀመጠው አንቀፅ 27 ንዑስ አንቀፅ (ሀ) ላይ ምልመላን፣ ጊዜያዊም ሆነ ቋሚ ቅጥርን፣ በቋሚ ስራ ላይ መቀጠልን፣ የሙያ ዕድገትን፣ ደህንነቱ የተጠበቀና ጤናማ የሥራ ሁኔታዎችን ጨምሮ ተያያዥነት ያላቸውን ጉዳዮች ሁሉ አስመልክቶ በአካል ጉዳት ላይ የተመሰረተ ማናቸውም አይነት አድልዎ እንዳይፈፀም ይከለክላል። የዚሁ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (ለ) ደግሞ ከወከባ መጠበቅንና ለቅሬታዎች የመፍትሄ ምላሽ ማግኘትን ጨምሮ እኩል ዋጋ ላለው ሥራ እኩል ዕድሎችንም ሆነ እኩል ክፍያ የማግኘት፣ ደህንነታቸው የተጠበቀና ጤናማ የሥራ ሁኔታዎችን ጨምሮ ከሌሎች ጋር በእኩል ደረጃ ለአካል ጉዳተኞች ትክክለኛና ምቹ የሥራ ሁኔታ የማግኘት መብት መስጠቱን ያትታል። ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ድርጅት (አይ.ኤል.ኦ) እ.ኤ.አ በ2021 ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያሳየው በዓለማችን ዕድሜያቸው ለሥራ ከደረሰ ዜጎች 386 ሚሊዮን የሚገመቱት የአካል ጉዳት አለባቸው። በአንዳንድ ታዳጊ አገራትም የአካል ጉዳተኞች ሥራ አጥነት እስከ 80 በመቶ ይደርሳል። ይህም የሚያሳየው አሰሪዎች አካል ጉዳተኞችን የመቅጠር ፍላጎት እንደሌላቸውና ‘አካል ጉዳተኞች መስራት አይችሉም’ የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ መያዛቸውን ነው። አካል ጉዳተኝነት ያልበገራቸው ብርቱዎች በጽሁፉ መግቢያ የተዋወቅናቸው የ76 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ አቶ አለበል ሞላ ገና የ13 ዓመት ታዳጊ እያሉ በደረሰባቸው የተሽከርካሪ አደጋ ሁለት እግሮቻቸውን አጥተዋል። አቶ አለበል አዲስ አበባ ተወልደው ማደጋቸው በተሽከርካሪ ወንበር (ዊልቼር) ድጋፍ ወደ ትምህርት ቤትም ሆነ ወደ ስራ ተመላልሰው ለመማርና ለመስራት የሰጣቸው ዕድል ቢኖርም የከተማዋ የእግረኛም ሆኑ የአስፓልት መንገዶች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያላደረጉ፤ ለዊልቼር መንቀሳቀሻ በቂ ቦታ የሌላቸው መሆናቸው እንቅስቃሴያቻውን በእጅጉ አክብዶባቸዋል። ከመኖሪያቸው ወደ ትምህርት ቤትና ወደ ስራ ቦታቸው በዊልቼር በሚመላለሱበት ጊዜ በመንገዱ ወጣገባነት ይገጥማቸው የነበረውን ፈተና እና ያሳለፉት ስቃይ እጅግ ከባድ እንደነበር ያስታውሳሉ። ይሁንና አቶ አለበል በርካታ ውጣ ውረዶችና ተግዳሮቶችን አልፈው ትምህርታቸውን በመከታተል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማኔጅመንት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን መያዝ ችለዋል። በመንግሥት መሥሪያ ቤት ተቀጥረው ለ25 ዓመታት አገልግለዋል። ሥራ ለመቀጠር አጋጥሟቸው የነበረውን እልህ አስጨራሽ ትግል አሁንም ድረስ በቁጭት ነው የሚያስታውሱት። ያንን ጊዜ “አስከፊና ተስፋ አስቆራጭ” ሲሉ ይገልፁታል። በፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 ለአካል ጉዳተኞች የሚጠበቁ የሥራ ሁኔታዎችን በተመለከተ እንደተቀመጠው አካል ጉዳተኞች በቅጥር፣ በደረጃ ዕድገት፣ በዝውውር፣ በድልድል፣ በትምህርትና ሥልጠና አፈጻጸም የተጨማሪ ድጋፍ እርምጃ ተጠቃሚ መሆን አለባቸው። ማንኛውም የመንግሥት መስሪያ ቤት የሥራ አካባቢው ለአካል ጉዳተኛ ሠራተኞቹ ምቹ መሆኑን ማረጋገጥ፣ ለሥራ የሚያስፈልጉ መሣሪያዎችንና ቁሳቁሶችን ማሟላትና ስለአጠቃቀማቸው አስፈላጊውን ሥልጠና እንዲያገኙ ማድረግ አለበት። በሌላ በኩል ማንኛውም የመንግሥት መስሪያ ቤት ረዳት ለሚያስፈልገው የአካል ጉዳተኛ የመንግሥት ሠራተኛ ተገቢውን ድጋፍ የሚሰጥ ረዳት እንዲመደብለት የማድረግ ኃላፊነት የተጣለበት ሲሆን፤ በሌሎች ሕጎች ለአካል ጉዳተኞች የተሰጡ መብቶች ለዚህ አዋጅ አፈጻጻም ተግባራዊ እንደሚሆኑ ያስቀምጣል። ይሁን እንጂ ለአቶ አለበል ይህ የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ በወረቀት ላይ ብቻ የሰፈረ የህልም እንጀራ ነው። “ስራ ለመቀጠር ማስታወቂያ በወጣባቸው የመንግሥትና የግል ተቋማት አካል ጉዳት ከሌለባቸው ጋር ተወዳድሮ ማለፍ ትልቅ ፈተና ነበር፤ ፈተናውን በጥሩ ነጥብ አልፌ እንኳን ለቃለ-መጠይቅ ዊልቸሬን እየገፋሁኝ ስገባ ከጠያቂዎቹ ፊት ላይ ያለውን ስሜት በመረዳት ነበር ስራውን እንደማላገኝ እርግጠኛ የምሆነው’’ይላሉ። የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን አጠናቀው ከተመረቁ ከአራት ዓመታት በኋላ በአንድ የመንግሥት ተቋም ውስጥ በጀማሪ ባለሙያነት የመቀጠር ዕድል ማግኘታቸውንና ይህን ዕድል በመጠቀም አካል ጉዳተኝነት ምንም አይነት ስራ ከመስራት ወደኋላ እንደማያስቀር ለማሳየት ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ይናገራሉ። ይሁንና እንደ ትናንቱ ሁሉ ዛሬም ሆነ ነገ ሁሉም አካል ጉዳተኞችን የሚመለከትበትን መነፅር መጥረግ እንዳለበት አጽንኦት የሚሰጡት አቶ አለበል በተለይም እውቀትና ችሎታው ኖሯቸው እኩል ዕድል ባለማግኘታቸው በከፋ ችግር ውስጥ የሚገኙ አካል ጉዳተኞችን ለመታደግ እያንዳንዱ ዜጋ በሰብዓዊነት ስሜት ሊንቀሳቀስ፣ መንግሥትም ለጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ያስገነዝባሉ። አቶ አለበል ያለፉበትን የሕይወት ውጣ ውረድ መንገድ ዛሬም በርካታ አካል ጉዳተኞች ይመላለሱበታል። የ12ኛ ክፍል ተማሪዋ ዓይናለም መክብብ ከእነዚህ መካከል አንዷ ነች። ዓይናለም ስትወለድ ጀምሮ ዓይነስውር ናት። ዩኒቨርሲቲ ገብታ ሕግ የመማር ከፍተኛ ፍላጎት ያላት ዓይናለም ለምን ሕግ ማጥናት እንደፈለገች ስትጠየቅ “በሀገራችን ዓይነስውራንን ጨምሮ የተለያየ የአካል ጉዳት ያለባቸው ዜጎች አካል ጉዳት ከሌለባቸው እኩል የትኛውንም አገልግሎት የማግኘት መብታቸው በአግባቡ ተከብሮ ከፍተኛ በሚባሉ የሥራ ቦታዎች ላይ በኃላፊነት እንዲመጡ ካለኝ ፅኑ ፍላጎት ነው” ትላለች። ዓይናለም የምትማርበት ትምህርት ቤት ከብሬል አቅርቦት ጀምሮ የተለያዩ ችግሮች ያሉበት ቢሆንም፤ እርሷ ግን በትምህርቷ ከዓይናማዎች እኩል፤ አንዳንዴም ከእነርሱም በላይ የላቀ ውጤት እያስመዘገበች ትገኛለች። ለዚህ ስኬቷም “እችላለሁ’’ የሚል ጠንካራ ሥነ-ልቦና እንዲኖራት ወላጆቿ ያሳደሩባትን አዎንታዊ ተጽዕኖ በምክንያትነት ትጠቅሳለች። በኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ የሚወጡ ሕጎች በትክክል አይፈፀሙም የሚለውን ቅሬታ ዓይናለምም ትጋራዋለች። ለምን አይፈፀሙም የሚል ጥያቄ ሲነሳም “ሰሚ ጆሮ እና ተመልካች ዓይን” የለም ነው ምላሿ። አካል ጉዳተኞች በከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት ላይ ሆነው አገራቸውን እና ሕዝባቸውን እንዲያገለግሉ የሚያግዝ አረንጓዴ መብራት አይታይም። “በፈተና ውስጥም ቢሆን፤ በዩኒቨርሲቲ ቆይታዬ ሕግ አጥንቼ በጥሩ ውጤት እንደምመረቅና ያሰብኩትን እንደማሳካ እርግጠኛ ነኝ” የምትለው ዓይናለም፤ እንደ አገር ለአካል ጉዳተኞች ያለውን ሁለንተናዊ አመለካከት ማስተካከል በተለይም የሕግ ተፈጻሚነትን ማሻሻል የቅድሚያ ቅድሚያ የስራ ትልሟ ስለመሆኑ ትገልፃለች። የሕጎች የተፈጻሚነት ክፍተት በኢትዮጵያ ለአካል ጉዳተኞች ያለው አመለካከት የተንሸዋረረ ነው በሚል የሚነሳውን ቅሬታ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዓባይነህ ጉጆም ይስማሙበታል። በአገሪቷ አካል ጉዳተኞችን አስመልክቶ የሚወጡ ሕጎች በትክክል አካል ጉዳተኞችን እየደገፉ ካለመሆኑ ባሻገር አካል ጉዳተኞችን ብቻ አስመልክቶ የወጣ የሕግ ማዕቀፍ አለመኖሩንም አጥብቀው ይተቻሉ። አካል ጉዳተኞች ለሚያነሷቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ የሚሰጥ አሰራር መዘርጋት የግድ ስለመሆኑ አፅንኦት የሚሰጡት አቶ ዓባይነህ “አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ የሚወጡ ሕጎችና አሰራሮች በ’እኔ አውቅልሃለሁ’ እሳቤ የወጡና አካል ጉዳተኛውን የማይወክሉ ናቸው” ይላሉ። በአጠቃላይ በሀገሪቷ አካል ጉዳተኞችን አስመልክተው የሚወጡ ሕጎች ተፈጻሚነታቸው ዝቅተኛ ነው። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት በአካል ጉዳተኛው ቦታ ሆኖ ችግሩን አለመረዳትና የተቆርቋሪነት ስሜት አለመኖሩ ነው ሲሉም ያክላሉ። በኢትዮጵያ ሕንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2001 በሀገሪቷ የሚገነቡ ሕንፃዎች ማሟላት ስለሚገባቸው አጠቃላይ ግዴታዎች ያስቀመጠ ሲሆን፤ በአንቀፅ 36 ስር የሚገነቡ ሕንፃዎች ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ ሊሆኑ እንደሚገባ አስፍሯል። የሕንፃ አዋጁ ይውጣ እንጂ አብዛኞቹ የሚገነቡ ሕንፃዎች አካል ጉዳተኞችን ያላማከሉ ናቸው። ሕጉ አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ እንዲያደርጉ የማያስገድድ በመሆኑ ሕንፃ ገንቢዎቹ ስለአካል ጉዳተኞች መብት ግድ እንዳይሰጣቸው አድርጓል። መንግሥት አካል ጉዳተኞችን በሀገሪቷ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎች ተሳታፊ ለማድረግ ጉዳታቸውን ታሳቢ ያደረገ ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንዳለበት በአፅንኦት የሚገልጹት አቶ ዓባይነህ ፌዴሬሽኑ አካል ጉዳተኞች በሀገሪቷ ሁለንተናዊ ልማት ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ፣ ወጥነት ያለው የአካል ጉዳተኞች ሕግ እንዲወጣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ጥረት እያደረገ ስለመሆኑ ነው ያስረዱት። በኢትዮጵያ የሚገነቡ ሕንፃዎችና መንገዶች ከዲዛይን ጀምሮ አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ እንዲሆኑ ማኅበሩ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን እና ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል። የዚህ ስምምነት ዋና ዓላማ አዳዲስ የሚገነቡ መንገዶችና ሕንፃዎች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ እንዲያደርጉ እንዲሁም ነባር ሕንፃዎችንም ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የማድረግ ሁኔታን መፍጠር ነው። አካል ጉዳተኞች በሀገሪቷ ሁለንተናዊ ልማት ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ሁሉንም ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ እንደሚያሳድግ የሚገልጹት ዋና ዳይሬክተሩ ለአብነትም ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ስራ ውጤታማነት አካል ጉዳተኞች የድርሻቸውን መወጣት እንዲችሉ በንቃት የሚሳተፉበትን ዕድል ማመቻቸት እንደሚገባም ጠቁመዋል። የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እያሱ ሰለሞን በመዲናዋ ለዓይነስውራን እና ዊልቼር ለሚጠቀሙ አካል ጉዳተኞች ታስበው የተገነቡ የእግረኛ መንገዶች መኖራቸውን ይናገራሉ። ይሁንና ሁሉም ቦታ ላይ ያሉ መንገዶች የተገነቡት አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ተደርገው ነው ማለት ግን አይቻልም። ይህን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን ጋር በጋራ እየተሰራ ነው ይላሉ። ለአካል ጉዳተኞች ምቹ አካባቢ መፍጠር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ግዴታ ስለመሆኑ ያነሱት አቶ እያሱ በተለይ የእግረኛን ጨምሮ የመንገድ መሰረተ ልማቶች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ እንዲሆኑ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ሲሉም በአፅንኦት ይገልፃሉ። ቀደም ባለው ጊዜ በተቋማቸው የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ ከሌሎች የሥራ ዘርፎች ጋር ተቀናጅቶ ይሰራ እንደነበር በማስታወስ ይህም ጉዳዩ በቂ ትኩረት እንዳያገኝ ከማድረግ ባለፈ አካል ጉዳተኞችን አስመልክቶ የሚሰሩ ስራዎች ውጤታማ እንዳይሆኑ አድርጓል የሚሉት ደግሞ በሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የአካል ጉዳተኞች ግንዛቤ ማስጨበጥ ዴስክ ኃላፊ አቶ ሲሳይ ብርሃኑ ናቸው። አቶ ሲሳይ አክለውም ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ የአካል ጉዳተኞችን ጉዳይ ብቻ የሚከታተል የሥራ ክፍል ተቋቁሞ ወደ ተግባር መግባቱን እና በዚህም ለውጦች መምጣታቸውን ይገልጻሉ። ቀደም ባሉት ዓመታት ስለ አካል ጉዳተኞች የነበረው የተዛባ አመለካከት አሁን አሁን የተወሰኑ መሻሻሎችን ቢያሳይም፤ በርካታ ቀሪ ስራዎች መኖራቸውን አልሸሸጉም። አካል ጉዳተኞችን አስመልክቶ የሚወጡ ሕጎች ተፈጻሚነት ላይ ጉልህ ክፍተቶች አሉ በሚለው አስተያየት አቶ ሲሳይ ይስማማሉ። በተለይ ኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች መብት ኮንቬንሽንን ተቀብላ ያጸደቀች ቢሆንም፤ ወደ ተግባር ከመቀየር አኳያ በርካታ ክፍተቶች ይስተዋላሉ። እንደ አቶ ሲሳይ ገለፃ እያንዳንዱ የመንግሥት ተቋም አካል ጉዳተኞችን አካቶ መስራት እንዳለበት በኮንቬንሽኑ ተቀምጧል። ይሁንና በየተቋማቱ ከአመራር እስከ ባለሙያ ድረስ አካል ጉዳተኞችን ተደራሽ ሊያደርግ የሚችል አገልግሎት ከመስጠት አኳያ ገና ብዙ ቀሪ ስራዎች አሉ። ለአካል ጉዳተኞች አገልግሎት ከመስጠት አኳያ በርካታ ተቋማት ተደራሽ አይደሉም። በዊልቼር ለሚንቀሳቀሱ፣ ለዓይነስውራን እና መስማት ለተሳናቸው ዜጎች የተቋማት አገልግሎት ተደራሽነት ላይ ብዙ ሊሰራ ይገባልም ይላሉ። ጭላንጭሉ ተስፋ… አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ በአንዳንድ ሕጎች ላይ ቀደም ሲል ይስተዋሉ የነበሩ ድክመቶችን የማረም ጥረት ተጀምራል። ለአብነት በኢትዮጵያ የሚገነቡ ሕንፃዎች ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ አለመሆናቸው ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲቀርብበት ቆይቷል። ይህን ችግር ለመፍታት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የሕንፃ አዋጁ እንዲሻሻል በጋራ እየሰራ ነው። በማሻሻያ አዋጁ ላይ የአካል ጉዳተኞች ማኅበራት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉና አስፈላጊውን ግብዓት እንዲጨምሩም ተደርጓል። አካል ጉዳተኞች ከቀረጥ ነፃ ተሽከርካሪ ማስገባት የሚያስችላቸው መመሪያ ተግባራዊ እንዲሆን ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመሆን የአካል ጉዳተኞችን መረጃ የማደራጀት ሥራ እንዲከናወንና በተሰጣቸው ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተደረገ ነው። አካል ጉዳተኞች በፌዴራልና በክልል ደረጃ በጉዳት አይነታቸው ተደራጅተው የእኩል ዕድል ተጠቃሚነታቸውና ተሳትፏቸው እንዲጨምር ድጋፍና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል። ያም ሆኖ አሁንም አንድ ትልቅ ችግር አለ፤ “በኢትዮጵያ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ከተካሄደ ዓመታትን ያስቆጠረ በመሆኑ ምን ያህል አካል ጉዳተኞች እንዳሉ ትክክለኛው መረጃ አይታወቅም” ይላሉ። ይህም አካል ጉዳተኞችን እንደ ጉዳት አይነታቸው ለይቶ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ከባድ ፈተና ሆኗል። አካል ጉዳተኞችን አስመልክቶ የሚወጡ ሕጎች በአግባቡ ተፈጻሚ እንዲሆኑ የጉዳዩ ባለቤቶች የሆኑት ተቋማት የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ፤ ራሳቸው አካል ጉዳተኞችም ለመብቶቻቸው መከበር ይበልጥ መታገል እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። ይህም ብቻ አይደለም የአካል ጉዳተኞች እኩል ተጠቃሚነት ጉዳይ በአንድ ተቋም ብቻ የሚሰራ ባለመሆኑ የሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል ድጋፍ ይሻል።
በኦሊምፒክ ስፖርት ለመጀመሪያ ጊዜ የተካተተው ብሬክ ዳንስ
Jul 29, 2024 1803
በይስሐቅ ቀለመወርቅ እንደ መነሻ የኦሊምፒክ ውድድር በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ የስፖርት ዓይነቶችን በማካተት ዘንድሮ ለ33ኛ ጊዜ በፈረንሳይ ከተማ ፓሪስ እየተከናወነ ይገኛል። ከዛሬ አራት ዓመት በፊት በጃፓን ቶኪዮ በተከናወነው ኦሊምፒክ ስድስት የስፖርት ዓይነቶች ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሊምፒክ ጨዋታዎች እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡ የተካተቱት ስፖርቶች፤ ካራቴ፣ ስኬትቦርዲንግ፣ ቤዝቦልና ሶፍትቦል፣ በገመድና ያለገመድ ግርግዳ መውጣት (Sport climbing) እና በውሃ ላይ መንሸራተት (Surfing) ናቸው።   በፈረንሳይ እየተከናወነ በሚገኘው 33ኛው የበጋ ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ "ብሬኪንግ" ወይም "ብሬክ ዳንስ" የሚባለው የዳንስ ዓይነት በኢሊምፒክ ጨዋታዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ተካቷል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1970ዎቹ በብሮንክስ ጎዳናዎች ላይ የበቀለው ዳንስ፤ ለኒውዮርክ አፍሪካ አሜሪካዊ ማኅበረሰብ ምስጋና ይግባውና፤ በፓሪስ ኦሊምፒክ አንዱ ስፖርታዊ ውድድር ሆኖ ቀርቧል። ብሬክ ዳንስ ምንድነው? ብሬክ ዳንስ በአርባን ፖፕ፣ በሂፖፕና ራፕ በሚባሉ የሙዚቃ ዓይነቶች የሚሰራ የዳንስ እንቅስቃሴ ሲሆን አራት ዓይነት እንቅስቃሴዎች የሚደረጉበት ስልት ነው፡፡ "ቶፕ ሮክ" የሚባለው ደግሞ የመጀመሪያው ስልት ነው። በቶፕ ሮክ ዳንሰኛው ወይም ዳንሰኛዋ ቆመው በእግር እንቅስቃሴ ይጀምሩና፤ የማማሟቂያ እንቅስቃሴዎችን በማስከተል ወደ ሞቀ እንቅስቃሴ የሚገቡበት ነው። ሁለተኛው "ዳውን ሮክ" የሚባል ሲሆን፤ እጅና እግርን ወለል ላይ በማሳረፍ፤ ሰውነትን በተለያየ መንገድ እንዲተጣጠፍ በማድረግ፤ ፈጣን እንቅስቃሴ የሚደረግበት ስልት ነው። ሦስተኛው "ፓወር ሙቭ" የሚባለው የብሬክ ዳንስ ክፍል ሲሆን፤ በፍጥነት አክሮባት በመሥራት ዳንሰኞች ትርኢት የሚያሳዩበት ነው። አራተኛውና የመጨረሻው የብሬክ ዳንስ ክፍል ደግሞ፤ "ፍሪዝ" የሚባለውና እየደነሱ በመሀል ቆም በማለት መልሶ ወደ ዳንስ እንቅስቃሴ የሚገባበት ነው። የብሬክ ዳንስ ውድድር አጀማመርና ወደ ኦሊምሊክ ያደረገው ጉዞ የመጀመሪያው የብሬክ ዳንስ ውድድር የተከናወነው፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1990 አሜሪካን ውስጥ ነበር። በተለይ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2004 ጀምሮ፤ "ሬድ ቡል ቢሲ ዋን" የሚባለውና በሁለቱም ፆታዎች የሚከናወነው ዓመታዊ የብሬክ ዳንስ ሻምፒዮና፤ ስመጥር የዘርፉ ውድድር ነው። ዓለም አቀፉ የዳንስ ስፖርት ፌዴሬሽን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2018 ፤ የብሬክ ዳንስን በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ በተደረገው የበጋ የወጣቶች ኦሊምፒክ ላይ አስተዋውቆ ነበር። አሁን ላይ በተጀመረው 33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ ውድድር ደግሞ፤ ብሬክ ዳንስ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ተካቶ ውድድር ይደረግበታል። ውድድሩም ፓሪስ በሚገኘው "ላኮንኮርድ" ከሚባለው የኦሊምፒክና፣ የፓራ ኦሊምፒክ መንደር 5 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኝ ቦታ ላይ ይከናወናል። በሁለቱም ፆታዎች በሚደረገው የብሬክ ዳንስ ውድድር አንድ ሀገር በወንድም በሴትም በተመሳሳይ 16 ተወዳዳሪዎችን የሚያሰልፍ ሲሆን፤ ተወዳዳሪዎች ዲጄዎች በሚያጫውቷቸው ሙዚቃዎች ታጅበው ውድድሩን ያከናውናሉ። 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ከሐምሌ 19 ጀምሮ በፈረንሳይ ፓሪስ እየተከናወነ ሲሆን እስከ ነሐሴ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ይከናወናል። በውድድሩ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ 206 ሀገራት እየተሳተፉ ሲሆን፤ 10 ሺህ 714 ስፖርተኞች በ32 የስፖርት ዓይነቶች ውድድራቸውን እያደረጉ ነው።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም