ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካን መረቁ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካን መረቁ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 15/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሴራሚክ ፋብሪካው የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ጉዞ አካል እና የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ እመርታ ትልቅ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
ቁልፍ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን መሰል ፋብሪካዎች ግንባታ፣ ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንቶችን በመሳብ በመላ ሀገሪቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በተግባር ያረጋገጠ ነው ብለዋል።
ፋብሪካው የዓለም ዓቀፍ ጥራትና ተወዳዳሪነት መስፈርቶችን የሚያሟሉ የሴራሚክ ምርቶችን የሚያቀርብ ሲሆን፣ ለምርቱ የሚያስፈልጉትን ጥሬ ዕቃዎች ከ80 በመቶ በላይ ከሀገር ውስጥ ዐቅም እንደሚያገኝ ጠቁመዋል።
ይህ ስኬት ኢትዮጵያ የራሷን የተፈጥሮ ሀብትና እምቅ ጸጋ የመጠቀም ብቃቷን ከመገንባቱ ባሻገር፣ ከውጭ ገቢ ምርቶች ላይ ያለንን ጥገኝነት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚቀንሰውም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት።