ነገሌ አርሲ እና ምድረ ገነት ሽሬ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ነገሌ አርሲ እና ምድረ ገነት ሽሬ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 13/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 33ኛ ሳምንት ነገሌ አርሲ እና ምድረ ገነት ሽሬ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተካሄዷል።
ጨዋታውን ተከትሎ ነገሌ አርሲ በ52 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።
ነገሌ አርሲ የሁለተኝነት ደረጃን ከመቻል የመረከብ እና ከሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት የማጥበብ እድል አልተቀመበትም።
ምድረ ገነት ሽሬ በ37 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
ዛሬ አስቀድመው በተደረጉ የ33ኛ ሳምንት ጨዋታዎች የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና አርባምንጭ ከተማን 3 ለ 0 ሲረታ አዳማ ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ጨዋታዎቹን ተከትሎ 33ኛ ሳምንት ተጠናቋል።
የ34ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች በኋላ ከግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳል።