ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
የአፍሪካ የትምህርት ኢኖቬሽን ኤክስፖ በአዲስ አበባ ይካሄዳል
Jul 11, 2026 48
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦ የ2026ቱን የአፍሪካ የትምህርት ኢኖቬሽን ኤክስፖ በመጪው ሐምሌ 6 እና 7 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ያዘጋጀው ይህ ኤክስፖ፤ “በትምህርት ዘርፍ የዲጂታል ሽግግርን ማፋጠንና ለአፍሪካ የክህሎት ዘመን የአዳዲስ መፍትሔዎችን ተደራሽነት ማስፋት” በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚካሄድ ታውቋል። ይህ አህጉራዊ ኤክስፖ በአፍሪካ የትምህርትና ክህሎት ሥርዓት ውስጥ ያሉ የጥራት፣ የተደራሽነትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ክፍተቶችን በቴክኖሎጂ አማካኝነት ለመፍታት ያለመ ነው። መድረኩ በተለይም አዳዲስ የቴክኖሎጂ መፍትሔዎችን በማስተዋወቅ የአፍሪካን የትምህርት ዘርፍ ማዘመን በሚቻልባቸው ስትራቴጂዎች ላይ ይመክራል። በኤክስፖው በትምህርት፣ በከፍተኛ ትምህርት፣ በቴክኒክና ሙያ እንዲሁም በሮቦቲክስ ዘርፎች ከፍተኛ ተፅዕኖ ማምጣት የቻሉ ከ20 በላይ አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎች ለዕይታ ይቀርባሉ። በተጨማሪም በዲጂታል ትምህርት፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI)፣ በአረንጓዴ ክህሎቶች፣ በምርምርና በኢንዱስትሪ አጋርነት ላይ ያተኮሩ ውይይቶች የሚካሄዱ ሲሆን፤ ውይይቶቹም ከአህጉራዊ የትምህርትና የሳይንስ ስትራቴጂዎች ጋር የተጣጣሙ መሆናቸው ተገልጿል። በኤክስፖው ከ300 በላይ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ በትምህርት ዘርፍ የተሰማሩ የፈጠራ ባለቤቶች፣ ተመራማሪዎች፣ የልማት አጋሮች እና የቴክኖሎጂ መሪዎች በአካል እንደሚገኙ ይጠበቃል። ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሌሎች ታዳሚዎችም በበይነ መረብ አማካኝነት በሁነቱ ላይ እንደሚሳተፉ ኢዜአ ከአፍሪካ ኅብረት ያገኘው መረጃ ያሳያል። ኤክስፖው በአጠቃላይ በአፍሪካ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ የዲጂታልና የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን አጠቃቀም ለማፋጠን ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተመላክቷል። ይህም አፍሪካ ለቀጣይ የኢኮኖሚ ሽግግር ብቁና ዝግጁ የሆኑ ባለሙያዎችን ለማፍራት እንዲሁም የአህጉሪቱን የሰው ኃይል አቅም ለማጠናከር ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥርላት ታምኖበታል።
በአዲስ አበባ የተገነቡ የመንገድ መሠረተ ልማቶች ለትራፊክ ፍሰቱ መሳለጥ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው
Jul 11, 2026 94
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ የተገነቡ የመንገድ መሠረተ ልማቶችና የኮሪደር ልማት ሥራዎች ለትራፊክ ፍሰቱ መሳለጥ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ አስተያየታቸውን የሰጡ አሽከርካሪዎች ገለጹ። የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታ በማዘመን እና ዘመናዊ የመንገድ መሰረተ-ልማቶችን በመዘርጋት፣ የትራፊክ ፍሰትን ከማቀላጠፍ ባለፈ ለነዋሪዎች ምቹ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና ቀልጣፋ አካባቢን መፍጠር አስችሏል፡፡ ሰፊና ደረጃቸውን የጠበቁ የእግረኛ መንገዶች በመገንባታቸው የከተማዋን ነዋሪዎች ሰላማዊ እንቅስቃሴ ከማረጋገጡም በላይ፣ የመንገድ ተጠቃሚዎችን ደህንነት በማስጠበቅ የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው። አስተያየታቸውን የሰጡ አሽከርካሪዎች በከተማዋ የተሰሩት አዳዲስ መንገዶች እና የኮሪደር ልማት ስራዎች የትራፊክ ፍሰቱን በማሳለጥ አዎንታዊ ለውጥ አምጥተዋል ብለዋል። አሽከርካሪ የሆኑት ኃይሌ ዘመድኩን እና ጤናዬ ጠንክር እንደገለጹት፤ የኮሪደር ልማቱ ለትራፊክ ፍሰት አመቺ እና ዘመናዊ መንገዶችን በመፍጠር ስጋት የለሽ የማሽከርከር ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል። የከተማዋን ገጽታ በእጅጉ የቀየሩት እነዚህ ውብና ሰፋፊ መንገዶች፣ የዲዛይን ጥራታቸውና የተሟላ የመንገድ ምልክቶቻቸው ለትራፊክ አደጋ መቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ ብለዋል። የኮሪደር ልማት ለከተማዋ ውበት ብቻ ሳይሆን፣ ለአሽከርካሪዎች የላቀ የደህንነት ስሜትና የጉዞ ቅልጥፍናን የሰጠ ስኬታማ የልማት ስራ መሆኑን ጠቅሰዋል። አሽከርካሪ ብሩክ ግሩም፤ የኮሪደር ልማቱ የነበረውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ በመቅረፍ ተሽከርካሪዎች በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ በማድረጉ ጉዞን በአጭርና በአስተማማኝ ሁኔታ ማከናወን ተችሏል ብለዋል። የመንገድ አቅም መጨመሩ ለትራፊክ ፍሰቱ መሻሻል ብቻ ሳይሆን፣ አደጋዎችን በእጅጉ በመቀነስ ለአሽከርካሪዎች ትልቅ የደህንነት እፎይታን የፈጠረ ውጤታማ የልማት ስራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ዘርጋ እንደገለጹት፤ የተከናወኑት የኮሪደር ልማት ስራዎች የትራፊክ ፍሰቱን በማቀላጠፍና የከተማዋን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሰላማዊ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው። ይህ ዘመናዊ የመንገድ አውታር እግረኞች በደህንነት ተጠብቀው በፍጥነት እንዲንቀሳቀሱ ምቹ ሁኔታን በመፍጠሩ፣ በያዝነው በጀት ዓመት በሰውና በንብረት ላይ ይደርስ የነበረውን የመንገድ አደጋ በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ ተችሏል ብለዋል። ፕሮጀክቱ የመንገድ ደህንነትን በማረጋገጥና የትራፊክ መጨናነቅን በማስወገድ፣ በከተማዋ ለሚደረግ ማንኛውም አይነት የጉዞ እንቅስቃሴ አስተማማኝና ቀልጣፋ አማራጭ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በዞኑ የተገኘው ሰላም የግብርና ስራችንን በተረጋጋና በተደራጀ መልኩ ለማከናወን አስችሎናል - አርሶ አደሮች
Jul 11, 2026 92
ገንዳውኃ፤ ሐምሌ 4/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን የተገኘው ሰላም የግብርና ስራቸውን በተረጋጋና በተደራጀ መልኩ ማከናወን እንዳስቻላቸው አርሶ አደሮች ተናገሩ። አርሶ አደር ሱሌማን ዳውድ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የአካባቢያችን ሰላም ለማስጠበቅ ባደረግናቸው ጥረቶች የእርሻ ስራችን በተገቢው መንገድ ለማከናወን አስችሎናል። በአሁኑ ወቅትም በ10 ሄክታር መሬታቸውን በሰሊጥ፣ በአኩሪ አተርና ሌሎች ሰብሎች ለመሸፈን የዘር ስራ መጀመራቸውን ነው የገለጹት። አርሶ አደር ደጀኔ አሰፋ በበኩላቸው፣ ዞኑ ለግብርና ልማት ያለው ፀጋ ለወጭ ንግድ የሚሆኑ ምርቶችን በስፋት ለማምረት እንዳስቻላቸው ገልጸዋል። በዘንድሮው ክረምትም ባለኝ 20 ሔክታር መሬት ላይ ጥጥ፣ ሰሊጥ፣ አኩሪ አተርና ሌሎች ሰብሎችን በመዝራት እስከ 200 ኩንታል ምርት ለማግኘት እየሰራሁ ነው ብለዋል። በአካባቢው የተፈጠረው ሰላም አርሶ አደሩ፣ ባለሃብቱና የጉልበት ሰራተኛው ተረጋግቶ እንዲሰራ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን የገለጹት ደግሞ በእርሻ ኢንቨስትመንት የተሰማሩት አቶ ቃሲም እንድሪስ ናቸው። ያላቸውን 65 ሄክታር መሬት በዘመናዊ መንገድ በማልማት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አንዳርጌ ጌጡ እንደገለጹት፤ ማሕበረሰቡ የአካባቢውን ሰላም ለማረጋገጥ ከአመራሩ እና ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል። በዚህም አስተማማኝ ሰላም እየተፈጠረ በመምጣቱ በዘመናዊ ትራክተሮችና ሜካናይዜሽን ታግዞ የግብርና ስራን ለማቀላጠፍ እንተቻለ ነው የተናገሩት። በተገኘው ሰላም ለአርሶ አደሩና ባለሃብቱ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶችና የምርት ማሳደጊያ ግብዓትን በወቅቱ ለማቅረብም እንደተቻለ ነው ያመለከቱት። በዘንድሮው የመኸር እርሻ 529 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ከ450 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በዘር ተሽፍኗል ብለዋል። የዞኑ ህብረተሰብም ሰላም የሁሉም መሰረት መሆኑን በመገንዘብ ከጸጥታ አካላት ጎን በመሰለፍ ያረጋገጠውን ሰላም አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው አስገንዝበዋል።
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ከ60 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ተሸፍኗል
Jul 11, 2026 108
ደሴ፤ ሐምሌ 4/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በመኸር እርሻ ከ60 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። የመምሪያው ኃላፊ ተገኝ አባተ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በዞኑ በ2018/19 የምርት ዘመን ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራስን ለመቻል የሚያግዙ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ። በዚህም በመኸር እርሻ 231 ሺህ 566 ሄክታር መሬት በማልማት ከሰባት ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን ገልጸዋል። የዝናቡ ወቅት ቀድሞ በጀመረባቸው አካባቢዎች እስካሁን ከ60 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን ማሳ በዘር መሸፈኑንም ነው ያመለከቱት። አርሶ አደሩ የተሻሻሉ አሰራሮችንና ቴክኖሎጅዎችን እንዲጠቀም በማድረግ ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ ከ160 ሺህ ኩንታል በላይ ዘመናዊ ማዳበሪያ መሰራጨቱን ነው የገለጹት። የዝናብ መዘግየት ባለባቸው አካባቢዎች ደግሞ የመስኖ አማራጭን በመጠቀም የመኸር ሰብል ልማቱን እንዲያከናውኑ ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በሰሜን ወሎ ዞን ባለፈው የመኸር ምርት ዘመን ከለማው 231ሺህ ሄክታር መሬት አምስት ነጥብ ስምንት ሚሊየን ኩንታል ምርት መገኘቱን ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ወጣቶች ዓመቱን ሙሉ በሚያከናውኗቸው የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ
Jul 11, 2026 118
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018(ኢዜአ)፦ ወጣቶች በክረምትና በበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በመሳተፍ ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ የወጣቶች ክንፍ የጽሕፈት ቤት ኃላፊ መለሰ አባተ ገለጹ፡፡ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን በማስመልከት የደም-ልገሳ መርሐግብር አከናውነዋል፡፡ አባላቱ ይህንን አርዓያነት ያለው ተግባር በቀጣይም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል። በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ወጣቶች ክንፍ የጽሕፈት ቤት ኃላፊ መለሰ አባተ እንደገለጹት፤ ወጣቶቹ ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ዓመቱን ሙሉ በተለያዩ የልማትና የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል። በዚሁ መሠረት የክረምት የበጎ ፈቃድ መርሐ ግብሩ አካል የሆነ የደም ልገሳ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት የተከናወነ ሲሆን፣ ከ1 ሺህ በላይ ወጣቶች ደም በመለገስ አርዓያነታቸውን ማሳየታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ወጣቶቹ በማኅበረሰብ አገልግሎት ተሳትፏቸው የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ለሀገራዊ አብሮነትና ለዜግነት ግዴታ መወጣት ትልቅ ሚና ያለው በመሆኑ፣ ተሳትፏቸውን በቀጣይም በላቀ ሁኔታ እንደሚያጠናክሩት አረጋግጠዋል። የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ አባላት፣ በደም እጥረት ምክንያት የሚከሰቱ ጉዳቶችን ለመቀነስ ትኩረት አድርገው በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ። በዛሬው ዕለት በተከናወነው የደም ልገሳ መርሐ ግብር ላይ የተሳተፉ ወጣቶች እንደገለጹት፤ ደም መለገስ የሰው ልጅን ሕይወት የመታደግ አርዓያነት ያለው ተግባር ነው ብለዋል። በመርሐ ግብሩ ላይ አስተያየታቸውን ከሰጡት ወጣቶች መካካል ብርቱካን ገብሬ እንዳለችው ደም መለገስ መስጠት ከባድ ኃላፊነትና ሰብአዊ ግዴታ መሆኑን ተናግራለች፡፡ ወጣት ጉዲና ስሜ ደም መለገስ የዘወትር ተግባሩ እንደሆነ ገልጾ፣ ደም ከመለገስ ባለፈም በሌሎች የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ተሳትፎውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል። በደም ልገሳ መርሐ ግብር ላይ ለሰባተኛ ጊዜ መሳተፏን የገለጸችው አዲስ ሙሉጌታ በበኩሏ በጎ ፈቃደኝነት የህሊና እረፍት የሚሰጥ ተግባር መሆኑን ጠቅሳለች፡፡ ወጣቶች እያከናወኑት የሚገኘው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ የዜግነት ግዴታቸውን ከመወጣት ባሻገር ለማኅበረሰቡ ደኅንነት ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።
ፖለቲካ
ምክክር ኮሚሽኑ የለያቸው አጀንዳዎች አለመግባባቶችን በዘላቂነት በመፍታት የኢትዮጵያን መፃኢ ዕድል የሚወስኑ ናቸው
Jul 11, 2026 243
ቦንጋ ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦በምክክር ኮሚሽኑ የተለዩት አጀንዳዎች አለመግባባቶችን በዘላቂነት በመፍታት የኢትዮጵያን መፃኢ ዕድል የሚወስኑ መሆናቸውን የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ። ለዓመታት ሲከናወን የቆየው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደት ታሪካዊ ጉባኤ ሊጀመር ጥቂት ቀናት ቀርተውታል። ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በሚጀመረው በዚህ ወሳኝ ጉባኤ ላይ ለመመካከር ከመላው ሀገሪቱ የተወከሉ 4 ሺህ ተመካካሪዎች አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ኮሚሽኑ በዛሬው ዕለት ከሐምሌ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሚካሄደውን ዋናው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሂደት አስመልክቶ ለተመካካሪዎች በዓድዋ ድል መታሰቢያ የቅድመ ምክክር ማብራሪያና ገለፃ አድርጓል። በጉዳዩ ላይ ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለፁት፤ በኮሚሽኑ የተለዩት አጀንዳዎች አለመግባባቶችን በዘላቂነት በመፍታት የኢትዮጵያን መፃኢ ዕድል የሚወስኑ ናቸው። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል መምህር ፍቅረየሱስ ሀብተጊዮርጊስ፤ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለሀገራዊ ጉባኤው በሚመች መልኩ አደራጅቶ ያቀረባቸው ስምንቱ ዋና ዋና አጀንዳዎች እጅግ አስፈላጊና መሠረታዊ መሆናቸውን ገልጸዋል። እነዚህ አጀንዳዎች ላለመግባባት መንስኤ በመሆን ልዩነትን ሲፈጥሩ የነበሩ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት፣ ሀገራዊ መግባባትንና አንድነትን የሚያጠናክሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ ወንድሙ ካኪሎ በበኩላቸው፤ አጀንዳዎቹ አለመግባባቶችን በዘላቂነት በመፍታት ሀገራዊ እሳቤዎችን የሚያጎለብቱ እንዲሁም ዘላቂ ሰላምን የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል። አጀንዳዎቹ የግጭት መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችን በመፍታት፣ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍን የሚከፍቱ መሆናቸውንም አክለዋል። ለሀገራዊ ጉባኤው የቀረቡ አጀንዳዎች ስር ሰደው የቆዩ ችግሮችን ከመሠረቱ ለመፍታት የሚያስችሉና ሲያጋጥሙ ለነበሩ ችግሮች ውይይትን አማራጭ በማድረግ መፍትሄ ለመሻት አስፈላጊ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ አቶ አዳሙ እሼቱ ናቸው።
ሀገራዊ ምክክሩ ስር የሰደዱ ችግሮችን በሰለጠነ መንገድ በመፍታት ለሀገራዊ መግባባት ትልቅ ምዕራፍ የሚከፍት ነው
Jul 11, 2026 174
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ምክክሩ ስር የሰደዱ ችግሮችን በሰለጠነ መንገድ በመፍታት ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታና ሀገራዊ መግባባት ትልቅ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑን ምሁራን ገለጹ፡፡ ለዓመታት ሲከናወን የቆየው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደት ታሪካዊ ጉባኤ ሊጀመር ጥቂት ቀናት ቀርተውታል። ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በሚጀመረው በዚህ ወሳኝ ጉባኤ ላይ ለመመካከር ከመላው ሀገሪቱ የተወከሉ 4 ሺህ ተመካካሪዎች አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ኮሚሽኑ በዛሬው ዕለት ከሐምሌ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሚካሄደውን ዋናው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሂደት አስመልክቶ ለተመካካሪዎች በዓድዋ ድል መታሰቢያ የቅድመ ምክክር ማብራሪያና ገለፃ አድርጓል። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተመራማሪዎች ለኢዜአ እንዳሉት፤ ሀገራዊ ምክክሩ ችግሮችን በውይይት በመፍታት የሀገር ሰላምና አንድነትን ያጸናል። ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የምክክር ኮሚሽን አቋቁማ ወደ ተግባራዊ ውይይት ለመግባት መወሰኗ ትልቅ እርምጃ ነው። ይህ አካሄድ የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ ረገድ የጎላ ሚና እንደሚኖረውም አስታውቀዋል። ኮሚሽኑ ከወረዳ ጀምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማወያየት ስምንት ወሳኝና አንኳር አጀንዳዎችን መለየቱ ለምክክሩ ውጤታማነት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ጠቁመዋል። እነዚህ የተመረጡ አጀንዳዎች ኢትዮጵያውያን በቀጣይ ሀገረ መንግስት ግንባታና ልማት ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርላቸውም አክለዋል። የምክክር ሂደቱ በሕግና በአዋጅ በተቋቋመ ኮሚሽን የሚመራና ዘላቂ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ያለመ በመሆኑ፤ አፍሪካና የተቀረው ዓለም ተሞክሮ ሊወስድበት የሚችል አርዓያነት ያለው ተግባር መሆኑን ምሁሩ ገልጸዋል፡፡ ይህ ስልጡን አካሄድ ኢትዮጵያውያን ችግሮቻቸውን በራሳቸው መፍታት እንደሚችሉ በዓለም መድረክ የሚያሳዩበት እንደሚሆንም ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና አመራር ትምህርት ክፍል መምህር ኡጁሉ ኡኮክ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሀገራዊ ምክክሩ ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምን በማስፈን ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት አመልክተዋል። ምክክሩ ዜጎች በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር አለመግባባቶች እንዲቀረፉና በጋራ ልማት ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ዕድል እንደሚፈጥርም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። በተመሳሳይ በዚሁ ዩኒቨርሲቲ የልማታዊ ተግባቦትና የሚዲያ ጥናት መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ዘለቀ ተሾመ (ዶ/ር)፤ ሀገራዊ ምክክሩ አንድነቷ የተጠናከረና ዘላቂ ሰላም የሰፈነባት የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር የሚጣል ታሪካዊ መሠረት መሆኑን አብራርተዋል። ለዚህ ታሪካዊ አጋጣሚ ስኬታማነትም እያንዳንዱ የማህበረሰብ ክፍል የበኩሉን ንቁ ተሳትፎና ጥረት ማድረግ እንዳለበት ተናግረዋል።
ዲፕሎማሲው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በዘላቂነት በማስጠበቅና ቀጠናዊ ትስስሩን በማፋጠን በኩል ለሌሎች አርዓያ እየሆነ ነው
Jul 11, 2026 328
ደሴ፤ ሐምሌ 4/2018(ኢዜአ)፦ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በዲፕሎማሲው መስክ የተመዘገቡ ስኬቶች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በዘላቂነት በማስጠበቅና ቀጠናዊ ትስስሩን በማፋጠን በኩል ለሌሎች አርዓያ እየሆነ መምጣቱን የወሎ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለፁ። በወሎ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ተባባሪ ፕሮፌሰር ቴዎድሮስ ካሴ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ብልሃትና ጥበብ የተሞላበት የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ አካሄድ ውጤት እያመጣ ይገኛል። በተለይም በሰጥቶ መቀበል መርህ፣ በጋራ ተጠቃሚነትና በትብብር መስራት ላይ ጸንቶ የዘለቀው ዲፕሎማሲው የዓለምን ቀልብ የሳበና ተቀባይነት ያገኘ ነው ብለዋል። ይህም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በዘላቂነት በማስጠበቅና ቀጠናዊ ትስስሩን በማፋጠን በኩል አርዓያነት ያለው ተግባር በመሆኑ፣ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ሞዴል መሆኑን ገልጸዋል። የባህር በር ጥያቄን የመሰሉ ወቅታዊ አጀንዳዎችን በማንሳት የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥና በትብብር ለመስራት መጠቀም ላይ የታየው ለውጥም የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል። በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በቱሪዝም፣ በቴክኖሎጂ፣ በጤናና በሌሎችም መስኮች የተመዘገበው እድገትና ለውጥ የኢትዮጵያን ተፈላጊነት በማሳደግ ለዲፕሎማሲው ስኬት መሰረት መሆኑን አስረድተዋል። ይህም በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ የተፈጠረውን ውጥረት ከማርገብ ባለፈ፣ የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት እንዲያገኝ እያስቻለ መሆኑን አመልክተዋል። በዩኒቨርሲቲው የታሪክ መምህርና ተመራማሪ ረዳት ፕሮፌሰር ጋሻው መሀመድ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መስክ ያስመዘገበችው ድል ለሌሎች ሀገራት ተሞክሮ የሚሆን ነው ብለዋል። በተለይ የሰጥቶ መቀበል መርህን አህጉራዊ የጋራ አጀንዳዎች ለማድረግ የተደረገው ጥረት የበለጠ ትኩረት የሳበና የኢትዮጵያን አቃፊነት ለዓለም ያስረዳ መሆኑን ገልጸዋል። ይህም ብሔራዊ ጥቅሟን በማስጠበቅ ከበርካታ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት እንድታጠናክርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ተቀባይነት ያጎለበተ ነው ሲሉ ገልጸዋል። በተለይ ከኢትዮጵያ አልፎ አህጉራዊና ቀጠናዊ አጀንዳዎች ላይ ማተኮሯ ታላቅነቷን ያረጋገጠና የቀድሞ ገናና ታሪኳን የሚመልስ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል። የባህር በር ጥያቄው በሰላማዊ መንገድ ምላሽ እንዲያገኝና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም እንዲጠበቅ ምሁራን ባለን እውቀት የድርሻችንን እንወጣለን ሲሉም አረጋግጠዋል፡፡
የህገ ወጡን የህወሃት ቡድን ግፍና በደል ሸሽተው ከቀያቸው የተሰደዱ የትግራይ ተወላጆች ምን ይላሉ?
Jul 11, 2026 328
ሰቆጣ፤ ሐምሌ 4/2018(ኢዜአ)፦ የህገ ወጡን የህወሃት ቡድን ግፍና በደል ሸሽተው ከቀያቸው የተሰደዱ የትግራይ ተወላጆች ምን ይላሉ? በትግራይ ክልል ይኖሩበት ከነበረው አካባቢ ተፈናቅለው በሰቆጣ ከተማ ከሚገኙት የክልሉ ተወላጆች መካከል ጉዲፋይ አበራ፣ ህገ ወጡ የህወሃት ቡድን በየእለቱ የሚፈጽማችው ግፍና በደል እየተባባሰ መጥቶ የክፋትን ጥግ አልፏል ይላሉ። በገጠርም ይሁን በከተማ ሰርተን እንዳንበላ እና ወጥተን እንዳንገባ አፈናውና ዘረፋው እጅጉን የበረታ ሆኖብናል ነው የሚሉት። በክልሉ ከህፃን እስከ አዋቂ በግዳጅ ለውጊያ እያፈሰ መሆኑን አንስተው ህዝቡ በስጋትና በጭንቀት ውስጥ እየኖረ ነው ብለዋል። በተለይም ልጆቻችን በዚህ ኋላ ቀር ቡድን የእሳት እራት እንዳይሆኑብን ቀያችንን በመልቀቅ ወደ ሰቆጣ መጥተናል ሲሉ ተናግረዋል። በክልሉ አጋጣሚውን ያገኙ ሁሉ የህገ-ወጡን የህወሃት ቡድን ግፍና በደል ሸሽተው ወደ አጎራባች ክልሎች፣ ወደ አዲስ አበባ እና ወደ ውጭ ሀገራት ጭምር እየተሰደዱ ያሉ በርካቶች መሆናቸውን ገልጸዋል። ለክልሉ ቀውስ ከህገ-ወጡ የህወሃት ቡድን በተጨማሪ የሻእቢያ መንግስት ቀጥተኛ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን አንስተው ህዝቡ መፍትሄ ይሻል ብለዋል። ሌላው አስተያየት ሰጪ የክልሉ ተወላጅ ሙላት አወቀ እና የማነ ንጉስ የህገ-ወጡን የህወሃት አፈና በመሸሽ የራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ህይወት ለመታደግ ወደ ሰቆጣ እንደመጡ ይናገራሉ። ከወንጀል ተጠያቂነት ለማምለጥ የሚጥረው ይህ ቡድን የትግራይን ህዝብ መደበቂያና ማምለጫ አድርጎ ጥፋቱን ቀጥሏል ሲሉም ተናግረዋል። የትግራይ እናቶች በልጆቻቸው ላይ እየተፈጸመ ባለው አፈና፣ ግፍና በደል ሀዘን ላይ መሆናቸውን አንስተው ሕዝቡ የሚታደገው ይፈልጋል ብለዋል። የትግራይ ክልል ህዝብ ሰላምና ልማት አጥብቆ የሚሻ መሆኑን ገልጸው በግፈኛ የጥፋት ቡድን ታፍኖ መያዙ አሳዛኝ ነው ይላሉ።
ሀገራዊ ምክክሩ ለሀገር ግንባታ የሚቀመጥ ጠንካራ መሠረት ነው
Jul 11, 2026 337
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦ሀገራዊ ምክክሩ ለሀገር ግንባታ የሚቀመጥ ጠንካራ መሠረት ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሐምሌ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሚካሄደውን ዋናው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሂደት አስመልክቶ ለተመካካሪዎች በዓድዋ ድል መታሰቢያ ማብራሪያና ገለፃ እያደረገ ይገኛል። ባለፉት ዓመታት ከወረዳ ጀምሮ እስከ ክልል፣ በፌዴራል ደረጃ እንዲሁም በውጭ ሀገራት የሚኖሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ሲያሳትፍ የቆየው ይኸው ሃገራዊ የምክክር ሂደት፣ ስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎችን መለየቱ ይታወቃል። በአሁኑ ወቅትም እነዚህን መሠረታዊ አጀንዳዎች ይዘው በሀገሪቱ የጋራ እጣ ፈንታ ላይ ለመምከር ከሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎችና ከውጭ ሀገራት የተውጣጡ አራት ሺህ ተመካካሪዎች አዲስ አበባ ገብተዋል። የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ይህ ሀገራዊ ምክክር ኢትዮጵያውያን በእኩልነት ስለ ሀገራቸው የወደፊት ዕጣ ፈንታ በቀጥታ የሚመካከሩበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው። ይህ ጉባኤ ሀገሪቱ ያሏትን ዘመናዊና ሀገር በቀል ዕውቀቶች እንዲሁም ጠንካራ የውይይት እሴቶችን አቀናጅቶ የሚመራ ልዩ መድረክ መሆኑንም ገልጸዋል። ዋና ኮሚሽነሩ ዓድዋ የኢትዮጵያውያን የጋራ የነፃነትና የክብር አሻራ መሆኑን አስታውሰዋል። ትላንት አባቶቻችን ያለ ምንም ልዩነት በአንድነት ቆመው ወራሪውን ጠላት ድል ያደረጉበትና በመላው ዓለም የነፃነት ተምሳሌት የሆነ ታሪክ የፃፉበት ዓድዋ ዛሬም ለእኛ ትልቅ ማስተማሪያ ነው ብለዋል። በመሆኑም ዓድዋ እና ሀገራዊ ምክክሩ በነፃነት፣ በእኩልነትና በአንድነት መርህ ላይ አንድ መሆናቸውን ዋና ኮሚሽነሩ አንስተዋል። በእኛ ዘመን ለሀገር ግንባታ የምናስቀምጠው ይኸው ጠንካራ የምክክር መሠረት፣ በቀጣይም በልጆቻችን ዘንድ እንደ ትልቅ ታሪካዊ ድል የሚወሳ ይሆናል ሲሉም ገልፀዋል። የኢትዮጵያውያን የጋራ የነፃነትና የክብር አሻራ የሆነው የዓድዋ ድል፣ አሁን ለተጀመረው ሀገራዊ ምክክር በትልቅ መማሪያነት ሊያገለግል እንደሚገባ ጠቅሰዋል፡፡
ሀገራዊ ምክክሩ ዘላቂ ሰላምና መግባባት የሰፈነባትን ሀገር ለትውልድ ለማሻገር ያስችላል
Jul 10, 2026 1051
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 3/ 2018 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ለዘመናት ለቆዩ ያለመግባባቶች በሰለጠነ መንገድ በመመካከር ሀገራዊ መግባባት በመፍጠር፣ሰላምና ልማት በማስፈን ለትውልድ ለማሸጋገር የሚያስችል መሆኑን የሴቶች አደረጃጀት ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ገለጹ። የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ከመጪው ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን፤ የዋናው ጉባኤ ተሳታፊ የሀገር ውስጥና የውጭ የሕዝብ ወኪሎችም አዲስ አበባ እየገቡ ይገኛሉ። በዋናው የምክክር ጉባኤም የሀገር ግንባታ፣ የመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ፣ የፖለቲካ ሥርዓት፣ የፖለቲካ ውክልና እና የምርጫ ሥርዓት፣ የፌዴራል ከተሞች (አዲስ አበባና ድሬዳዋ) ጉዳይ፣ የሃይማኖት ጉዳዮች፣የተቋማት ግንባታ፣የሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብቶች፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች፣የአርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ጉዳይ፣ ሙስናና መልካም አስተዳደር እንዲሁም የሰላም ግንባታ የተሰኙ ስምንት ዐበይት አጀንዳዎች የሚመከርባቸው ይሆናል። የሴት አደረጃጀትና ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ችግሮቻችንን በምክክር ከመፍታት ይልቅ የኃይል አማራጭን በመከተል የፖለቲካ ፍላጎትን ለማስፈጸም የሚደረግ ጥረት አዋጭ አይደለም። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ለዘመናት ለቆዩ ያለመግባባቶች በሰለጠነ ውይይት በመመካከር ሀገራዊ መግባባትን፣ሰላምና ልማት የሰፈነባትን ሀገር ለትውልድ ለማሸጋገር ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው ገልጸዋል። ሀገራዊ ምክክሩ የሴቶችን ተሳትፎና አካታችነት የሚያረጋግጥና ሴቶች በዜጎች መካከል ሀገራዊ መግባባት እንዲፈጠር ያላቸውን ፅኑ ፍላጎት ከግብ የሚያደርስ ስልጡን መንገድ መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር ገነት ስዩም እንዳሉት፤ ሴቶች ሀገራዊ መግባባትን በመገንባት ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ሀገራዊ ጉዳዮችና ጥያቄዎች አሏቸው። በዚህም በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰብና የተሳታፊ ልየታ ሂደት የነበረውን የሴቶች ንቁ ተሳትፎ በማሳደግ፣በዋናው ጉባኤም በወኪሎች አማካኝነት የሚሳተፉበት ዕድል መፈጠሩን አስረድተዋል። በዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የተካተቱ ዐበይት አጀንዳዎች የሴቶችንና የማህበረሰቡን የዘመናት ጥያቄ በስልጡን የውይይት መድረክ ትኩረት አግኝተው መፍትሔ እንደሚያገኙ እምነታቸውን ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማኅበር ፕሬዝዳንት እናትዓለም እንዳለ በበኩላቸው፤ ለዘመናት በቆዩ አለመግባባቶች በሚከሰቱ ግጭቶች ሴቶች ግንባር ቀደም ተጠቂና የጉዳት ሰለባዎች ናቸው ብለዋል። በሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰቢያና የተሳታፊ ልየታ ሂደትም ሴቶችን የሚመለከቱ የሕግና ፍትሕ፣ የሰብዓዊ መብት፣ የፍትሕ ተጠቃሚነትና የፖለቲካ ተሳትፎ አጀንዳዎች ተጠናቅረው መቅረባቸውን አስታውቀዋል። የሴቶች አጀንዳዎችም በዋናው የምክክር ጉባኤ በተካተቱ ስምንት ዐበይት አጀንዳዎች ውስጥ መካተታቸውን አስረድተዋል። የጉባኤው ተሳታፊ የሕዝብ ወኪሎችም ስልጡን ምክክርን በማስቀደም፣ጠንካራ ሀገረ መንግሥትና ሀገራዊ መግባባትን የሚያመጡ ምክረ ሃሳቦችን በታላቅ ኃላፊነት ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ለጫናዎች ያልተበገረ ስኬታማ የዲፕሎማሲ ስራ አከናውናለች- ምሁራን
Jul 10, 2026 1173
ጅማ፤ ሐምሌ 3/ 2018 (ኢዜአ):- ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት ለጫናዎች ያልተበገረ ስኬታማ የዲፕሎማሲ ስራ ማከናወኗን የጅማና የመቱ ዩኒቨርሲቲዎች ምሁራን ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሰሞኑን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የውጭ ግንኙነትን በተመለከተ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፤ ውስብስብ፣ አሻሚና ኢ-ተገማች በሆነ ዓለም ዲፕሎሚያዊ አካሄድ ፕራግማቲክ (ተለዋዋጭ) ሊሆን እንደሚገባ ማንሳታቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም አካሄዱ 3ቱ መ'ዎችን ማለትም መቋቋም፣ መጠቀም መግራት የሚባሉትን ተግባራዊ በማድረግ የዓለምን ተለዋዋጭ ባህሪ በመቋቋም የኢትዮጵያን የውሳኔ ሉዓላዊነት ማስጠበቅ መሆኑን አመልክተዋል። ይህንኑ በማስመልከት ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ ምሁራን እንደገለፁት፤ ኢትዮጵያ ለየትኛውም አካል ያልወገነ፣ ሚዛናዊ እና ጥንቃቄ የተሞላበት ዲፕሎማሲ መከተሏ ባለፉት አምስት ዓመታት ስኬቶችን እንድታስመዘግብ አድርጓታል። ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት ለጫናዎች ያልተበገረ ስኬታማ የዲፕሎማሲ ስራ ማከናወኗንም ገልጸዋል። በመቱ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህር ተገኝ ደምሴ፤ ያለፉት ዓመታት የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ጉዞ ቀላልና አልጋ በአልጋ እንዳልነበር ይናገራሉ። በተለይም ሀገሪቱ ከታሪካዊ ጠላቶቿ የሚሰነዘሩባትን ሴራዎች ጨምሮ በርካታ ጫናዎችን ብታስተናግድም፣ በሳል የሆነ የውሃ ዲፕሎማሲ ሥራ በመሥራት እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ማሳካት መቻሏን ገልጸዋል። የዲፕሎማሲ ስራ ለአንድ ሀገር የእድገት ጉዞ እጅግ ወሳኝ በመሆኑ ዓለም አቀፍ ህጎችን ባከበረ መልኩ መንግስት የተከተለው የዲፕሎማሲ አቅጣጫ የውስጥ እና የውጭ ጫናዎችን በመቋቋም የሚፈለገው ስኬት እንዲመዘገብ አድርጓል ብለዋል። በዚህም ኢትዮጵያ በራሷ ጥረትና ሀብት "ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ" በሚል መርህ በገጠሟት ፈተናዎች ጸንታ በመቆየት የግድብ ግንባታውን ማጠናቀቋ በቀጣናው ያላትን ተሰሚነት ማሳደግ መቻሉን አመልክተዋል። በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በያሉበት የሀገራቸው ዲፕሎማት ሆነው ኢትዮጵያ እንደ ባሕር በር ያሉ አስፈላጊ መብቷን በሴራ ማጣቷን በማስረዳት ምላሽ እስኪያገኝ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። በጅማ ዩኒቨርሲቲ የህግ እና አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር ደሊል አህመድ በበኩላቸው፤ ባለፉት አምስት ዓመታት ኢትዮጵያ ትልልቅ ዓለም አቀፍ ኩነቶችን ማስተናገዷና እንደ ብሪክስ ያሉ ስብስቦችን መቀላቀሏ በዲፕሎማሲው ዘርፍ የተገኘ ትልቅ ስኬት መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሕግን ባከበረ መልኩ ፍትሐዊ አካሄድን መከተሏ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ማጠናቀቅ የመሰሉ ዲፕሎማሲያዊ ስኬቶችን ልታስመዘግብ መቻሏን ጠቅሰዋል። በኢኮኖሚው ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት፣ የጸጥታና የዲሞክራሲ ተቋማት ግንባታ በአንድም በሌላም መልኩ ለዲፕሎማሲው መጽናት ጠንካራ መሠረት እየሆኑ መምጣታቸውንም ምሁሩ አክለዋል። ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ዓለም አቀፍ ታዛቢ ተቋማት በተገኙበት ማካሄዷ የዚሁ የዲፕሎማሲ ስኬት አንዱ መገለጫ ነው ብለዋል። የባሕር በር ጉዳይ ኢትዮጵያ በታሪክም በሕግም የሚገባት ፍትሐዊ መብት መሆኑን ያብራሩት ምሁሩ፤ ይህንን ለማሳካት ሁለንተናዊ ጥረቶች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል። ባለፉት አምስት ዓመታት የተመዘገቡ ዲፕሎማሲያዊ ስኬቶችን በማስቀጠል፣ ይበልጥ ውጤታማ ለመሆን ሁላችንም በጋራ ልንሰራ ይገባል ሲሉም ምሁራኑ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ሀገራዊ ምክክሩ ለጠንካራ የሀገር ግንባታ እና ለዘላቂ አንድነት መሰረት እየጣለ ነው
Jul 10, 2026 1044
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2018(ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ምክክሩ ለጠንካራ የሀገር ግንባታ እና ለዘላቂ አንድነት መሰረት እየጣለ መሆኑን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዝዳንቶችና የሥራ ኃላፊዎች ገለጹ። በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞ ባለፉት ዓመታት በአጀንዳ ማሰባሰብ እና በተሳታፊዎች ልየታ ላይ ሰፊ ሥራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል። ኮሚሽኑ ከመጪው ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሚያካሂደው ዋናው ሀገራዊ ጉባኤም ስምንት ዐበይት አጀንዳዎችን ለሕዝብ ይፋ አድርጓል። የሀገር ግንባታ፣ የመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ፣ የፖለቲካ ሥርዓት፣ የፖለቲካ ውክልና እና የምርጫ ሥርዓት፣ የፌዴራል ከተሞች አዲስ አበባና ድሬዳዋ ጉዳይ፣ እንዲሁም የሃይማኖት ጉዳዮች ከአጀንዳዎቹ መካከል ናቸው። የተቋማት ግንባታ፣ የሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብቶች፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የአርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ጉዳዮች፣ ሙስናና መልካም አስተዳደር እንዲሁም የሰላም ግንባታ ጉዳዮችም በዋናው ጉባኤ ምክክር የሚደረግባቸው አጀንዳዎች ናቸው። የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ይታሰብ ስዩም፤ ኢትዮጵያ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ የሀገረ-መንግሥት ግንባታ ታሪክ ያላት ሀገር መሆኗን አንስተዋል። ሆኖም በታሪክ ሂደት ላይ ያጋጠሙ የፖለቲካ፣ የማኅበራዊና የኢኮኖሚ ቅራኔዎች ለተለያዩ ግጭቶችና አለመግባባቶች መንስኤ ሆነው ቆይተዋል ብለዋል። ኢትዮጵያውያን ለዘመናት አብረው የኖሩ፣ በችግር ጊዜ የሚደጋገፉና በመካከላቸው ያለው ማኅበራዊ ትስስር እጅግ የጠበቀ ሕዝቦች ናቸው ሲሉም ተናግረዋል። ይህንን ጠንካራ የእርስ በርስ ትስስር እና የዳበረ የባህል እሴት በመጠቀም፣ ማንኛውንም ችግሮች በጠረጴዛ ዙሪያ በመወያየት መፍታት እንደሚቻል ገልጸዋል። ለዚህም የተጀመረው የምክክር ሂደት ሀገራዊ መግባባትንና ዘላቂ ሰላምን ከማረጋገጥ አኳያ ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑንም ጠቁመዋል። የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት መሐመድ ኡስማን (ዶ/ር)፤ በኢትዮጵያ ለዘመናት የዘለቁና ውይይት እንዲሁም ምክክር የሚፈልጉ በርካታ ችግሮች መኖራቸውን አንስተዋል። ልዩነቶችን በሐሳብ የበላይነትና በጋራ መግባባት ማስተናገድ መቻሉ ለሀገር አንድነትና ሉዓላዊነት ያለው ፋይዳ እጅግ የጎላ ነው ብለዋል። ይህ የሀገራዊ ምክክር ሂደት የሀገር ግንባታ ሂደት ዘላቂነት እንዲኖረውና ጤናማ የትውልድ ቅብብሎሽ እንዲኖር ለማድረግ ወሳኝ መሆኑንም ተናግረዋል። በመሆኑም አሁን የሚደረጉ ምክክሮች የትውልድ ቅብብሎሹ ስኬታማ እንዲሆንና መጪው ትውልድ የውይይትና የሰላም ባህልን እንዲያጎለብት አስተዋጽኦ ይኖረዋል ነው ያሉት። የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አስማማው ዘገየ (ዶ/ር) ፤ ሀገራዊ ምክክሩ ለሀገር አንድነትና ለጠንካራ የሀገር ግንባታ መሠረት እየጣለ እንደሚገኝ አመልክተዋል። ምክክሩ አሁን ያሉ ችግሮችን ከመፍታት ባለፈ ለቀጣዩ ትውልድ የተረጋጋችና የበለጸገች ሀገርን ለማስረከብ ያስችላል ብለዋል። የትምህርት ተቋማት በምክክሩ ሂደት ንቁ ተሳትፎ ማድረጋቸውን ገልጸው፣ ይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አክለዋል።

ማህበራዊ
ወጣቶች ዓመቱን ሙሉ በሚያከናውኗቸው የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ
Jul 11, 2026 118
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018(ኢዜአ)፦ ወጣቶች በክረምትና በበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በመሳተፍ ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ የወጣቶች ክንፍ የጽሕፈት ቤት ኃላፊ መለሰ አባተ ገለጹ፡፡ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን በማስመልከት የደም-ልገሳ መርሐግብር አከናውነዋል፡፡ አባላቱ ይህንን አርዓያነት ያለው ተግባር በቀጣይም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል። በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ወጣቶች ክንፍ የጽሕፈት ቤት ኃላፊ መለሰ አባተ እንደገለጹት፤ ወጣቶቹ ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ዓመቱን ሙሉ በተለያዩ የልማትና የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል። በዚሁ መሠረት የክረምት የበጎ ፈቃድ መርሐ ግብሩ አካል የሆነ የደም ልገሳ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት የተከናወነ ሲሆን፣ ከ1 ሺህ በላይ ወጣቶች ደም በመለገስ አርዓያነታቸውን ማሳየታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ወጣቶቹ በማኅበረሰብ አገልግሎት ተሳትፏቸው የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ለሀገራዊ አብሮነትና ለዜግነት ግዴታ መወጣት ትልቅ ሚና ያለው በመሆኑ፣ ተሳትፏቸውን በቀጣይም በላቀ ሁኔታ እንደሚያጠናክሩት አረጋግጠዋል። የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ አባላት፣ በደም እጥረት ምክንያት የሚከሰቱ ጉዳቶችን ለመቀነስ ትኩረት አድርገው በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ። በዛሬው ዕለት በተከናወነው የደም ልገሳ መርሐ ግብር ላይ የተሳተፉ ወጣቶች እንደገለጹት፤ ደም መለገስ የሰው ልጅን ሕይወት የመታደግ አርዓያነት ያለው ተግባር ነው ብለዋል። በመርሐ ግብሩ ላይ አስተያየታቸውን ከሰጡት ወጣቶች መካካል ብርቱካን ገብሬ እንዳለችው ደም መለገስ መስጠት ከባድ ኃላፊነትና ሰብአዊ ግዴታ መሆኑን ተናግራለች፡፡ ወጣት ጉዲና ስሜ ደም መለገስ የዘወትር ተግባሩ እንደሆነ ገልጾ፣ ደም ከመለገስ ባለፈም በሌሎች የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ተሳትፎውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል። በደም ልገሳ መርሐ ግብር ላይ ለሰባተኛ ጊዜ መሳተፏን የገለጸችው አዲስ ሙሉጌታ በበኩሏ በጎ ፈቃደኝነት የህሊና እረፍት የሚሰጥ ተግባር መሆኑን ጠቅሳለች፡፡ ወጣቶች እያከናወኑት የሚገኘው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ የዜግነት ግዴታቸውን ከመወጣት ባሻገር ለማኅበረሰቡ ደኅንነት ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።
የህፃናት መብትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Jul 11, 2026 280
ሀረር፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦ የህፃናት መብትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ሁሉን አቀፍ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ገለጹ። ‘የተጠበቁ ህጻናት ለበለፀገ ትውልድ’’ በሚል መሪ ሃሳብ የአፍሪካ ህፃናት ቀን ማጠቃለያ ፕሮግራም በሐረር ከተማ ተካሂዷል። በስነ ስርአቱ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር፣ ሚኒስትር ዴዔታዎች፣ የህጻናት ፓርላማ አፈ ጉባዔዎች፣ ታዳጊ ህፃናትና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል። የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በወቅቱ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት፤ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለነገ ሀገር ተረካቢ ህጻናት አስፈላጊው መሰረተ ልማቶች የማሟላት ስራ እየተከናወነ ነው። በተለይም ውብ፣ ምቹና ጽዱ የመዝናኛ እንዲሁም የህጻናት ማቆያና መንከባከቢያ ማዕከላትንና የመጫወቻ ስፍራዎች የመገንባትና የማስፋፋት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል። ከዚሁ ጎን ለጎን የህጻናት ድጋፍና እንክብካቤ፣ በተለያዩ ዘርፎች ተሷትፏቸውን የማጎልበት እንዲሁም በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ተጎጂ እንዳይሆኑ የመጠበቅ፣ ከጥቃት የመከላከልና ሌሎች በርካታ ስራዎችም ስለመከናወናቸው አመልክተዋል። ከማህበረሰቡና ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ህፃናትን መብትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ሁሉን አቀፍ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል ። የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር በበኩላቸው፤ በክልሉ በከተማም ሆነ በገጠር ያሉ ህጻናት መብት፣ ደህንነትና ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የልማት ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል። የህጻናት ሁለንተናዊ እድገት ስኬታማ የሚሆነው በመንግስት ጥረት ብቻ አለመሆኑን ጠቁመው በክልሉ በገጠርና በከተማ ያሉ ህጻናት እኩል ተጠቃሚና ተደራሽነትን ለማጎልበት የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎን ማጎልበት እንደሚገባ አመልክተዋል። በሀገሪቱ የህጻናትን መብት በማስከበር ረገድ መሻሻሎች እየታዩ መሆኑን የተናገረችው ደግሞ የሀገር አቀፍ የህጻናት ፓርላማ ዋና አፈ ጉባዔ ህፃን ብሌን ድልአርጋቸው ናት። የህጻናትን መብትና ደህንነት የማስጠበቅና ተጠቃሚነትን ከማጎልበት አንጻር መንግስትና ባለድርሻ አካላት እያከናወኑ የሚገኘው ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቃለች።
በትምህርት ዘርፍ ብቁ፣ ተወዳዳሪና በሥነ-ምግባር የታነጸ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለማፍራት ውጤታማ ተግባራት እየተከናወኑ ነው
Jul 11, 2026 216
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018(ኢዜአ)፦ በትምህርት ዘርፍ ብቁ፣ ተወዳዳሪና በሥነ-ምግባር የታነጸ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለማፍራት ውጤታማ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በመገኘት፣ የትምህርት ዘርፍን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፤ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በተከናወኑ የተቀናጁ ተግባራት በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም የትምህርት መሠረትን ከታች ጀምሮ ለማጠናከር በትኩረት መሠራቱን ጠቁመው፤ ባለፉት ሰባት ዓመታት ውስጥ ብቻ 35 ሺህ የሚሆኑ ቅድመ-መደበኛ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን ተናግረዋል። ይህ የመዋዕለ ሕፃናት ግንባታ ቁጥር እጅግ ከፍተኛና ለዘርፉ የተሰጠውን ልዩ ትኩረት የሚያሳይ መሆኑንም አብራርተዋል። በየደረጃው በሚገኙ የትምህርት ዘርፎች የተከናወኑ እነዚህ ዘርፈ-ብዙ ተግባራት፣ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ደረጃ በደረጃ በማሻሻል በኩል ከፍተኛ ሚና እያበረከቱ እንደሚገኙም አስገንዝበዋል። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አየለች እሸቴ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ትምህርት ትውልድ የሚቀረጽበትና ሀገር ወደ ብልጽግና ጉዞ የምትሻገርበት መሠረት መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም መንግሥት ባለፉት የለውጥ ዓመታት በአጠቃላይ በትምህርት ዘርፉ ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት የትምህርት ተደራሽነትንና ጥራትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ሥርዓተ ትምህርት ቀርጾ በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። በዚህም የትምህርት ተደራሽነትን ከማስፋት ባለፈ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየተከናወኑ የሚገኙ በርካታ ተግባራት ውጤት እያስመዘገቡ ነው ብለዋል። የትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በተሠራው ሥራ በርካታ የቅድመ-መደበኛ፣ የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን ጠቁመዋል። በተለይም ባለፉት የለውጥ ዓመታት "ትምህርት ለትውልድ" በሚል መሪ ሀሳብ የተጀመረው ንቅናቄ ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች ባሳተፈ መልኩ በመሰራቱ ትልቅ ውጤት እንደተመዘገበበት አረጋግጠዋል። በዚህ ንቅናቄ አማካኝነት ከ17 ሺህ በላይ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን፣ ከ39 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች ደግሞ ዕድሳት ተደርጎላቸው የውስጥ ግብዓት እንዲሟላላቸው መደረጉን አስታውቀዋል። መንግሥት የትምህርት ጥራት ማረጋገጥ እንዲቻል ከመሠረቱ መጀመር አለበት በሚል ለቅድመ-መደበኛ ትምህርት ልዩ ትኩረት መስጠቱን ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልጸዋል። በዚህም መሠረት የቅድመ-አንደኛ ትምህርት ቤቶች በከተሞች ብቻ ሳይሆን በገጠርም ጭምር በከፍተኛ ሁኔታ እንዲስፋፋ መደረጉን አመልክተዋል። ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ የሰው ኃይልን ማጠናከርና የመምህራንን አቅም መገንባት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው ከዚህ አንጻር ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ ከ113 ሺህ በላይ መምህራን የአቅም ግንባታ ሥልጠና እንዲወስዱ መደረጉን ተናግረዋል። በተጨማሪም በክልሎች ከቅድመ-አንደኛ እስከ መካከለኛ ደረጃ ባሉ የትምህርት እርከኖች ላይ መምህራንን የማብቃትና አቅምን የመገንባቱ ሥራ በተጠናከረ መልኩ መቀጠሉንም ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልጸዋል። በሥነ-ምግባር የታነጹ፣ ሥራ ፈጣሪና ሀገር ተረካቢ ዜጎችን ለማፍራት በትምህርት ዘርፉ ውጤታማ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል።
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የዜጎችን የመደጋገፍ እሴት ከፍ የሚያደርግ ነው
Jul 11, 2026 255
ሰቆጣ ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአንድነት፣የትብብርና የመደጋገፍ እሴትን ከፍ ለማድረግ እያስቻለ መሆኑን በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ አስታወቀ። በአስተዳደሩ የ2018 የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ በሰቆጣ ከተማ በዛሬው እለት ተጀምሯል። የመምሪያው ኃላፊ ወይዘሮ ትበርህ ታደሰ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የማህበረሰቡን ችግሮች በተደራጀ መልኩ በመፍታት የመደጋገፍ ባሕልን ለማሳደግ እያስቻለ ነው። በአስተዳደሩ በክረምቱ ወቅት በሚካሄደው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 197 ሺህ በላይ ዜጎችን በማሳተፍ 584 ሺህ 860 የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የማድረግ ስራ መጀመሩን ገልጸዋል። በአገልግሎቱ የአቅመ ደካማ ወገኖችን ቤቶች በአዲስ የመገንባትና የመጠገን፣ ችግኝ የመትከል፣ ደም የመለገስ ፣ የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠትና በሌሎች 17 የስራ ዘርፎች እንደሚከናወን አስረድተዋል። በዘንድሮው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአንድነትና የትብብር እሴትን ይበልጥ በሚያጎለብት መልኩ ለማካሄድ በተሻለ መልኩ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ አስረድተዋል። በብልፅግና ፓርቲ የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዳግም ባይነሳኝ በበኩላቸው፤ ከለውጡ ዓመታት ወዲህ እየተካሔዱ ባሉ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ስኬት እየተመዘገበበት ነው ብለዋል። በዚህም ወጣቶችን በማስተባበር፣ በመደገፍና በማበረታታት ጥራት ያለውና ችግር ፈች የሆነ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲሰጡ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል። የሰቆጣ ከተማ ነዋሪ የሆነው ወጣት ጥላሁን አበበ ፤ ከጓደኞቹ ጋር በመሆን በየዓመቱ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመሳተፍ ወገኖቹን እያገለገለ እንደሚገኝ ነው የተናገረው። በዘንድሮ ክረምትም የአቅመ ደካሞችን ቤት በመጠገን የጀመሩትን ስራ በአረንጓዴ አሻራና በሌሎች የልማት ስራዎች አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልጿል፡፡ የመኖሪያ ቤታቸው የተጠገነላቸው ወይዘሮ ሙሉ አያሌው በበኩላቸው ፤ የተደረገልኝ የበጎ ፈቃድ ስራ ክረምቱን ያለ ስጋት ለማሳለፍ የሚያስችለኝ ነው በማለት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ኢኮኖሚ
በአዲስ አበባ የተገነቡ የመንገድ መሠረተ ልማቶች ለትራፊክ ፍሰቱ መሳለጥ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው
Jul 11, 2026 94
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ የተገነቡ የመንገድ መሠረተ ልማቶችና የኮሪደር ልማት ሥራዎች ለትራፊክ ፍሰቱ መሳለጥ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ አስተያየታቸውን የሰጡ አሽከርካሪዎች ገለጹ። የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታ በማዘመን እና ዘመናዊ የመንገድ መሰረተ-ልማቶችን በመዘርጋት፣ የትራፊክ ፍሰትን ከማቀላጠፍ ባለፈ ለነዋሪዎች ምቹ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና ቀልጣፋ አካባቢን መፍጠር አስችሏል፡፡ ሰፊና ደረጃቸውን የጠበቁ የእግረኛ መንገዶች በመገንባታቸው የከተማዋን ነዋሪዎች ሰላማዊ እንቅስቃሴ ከማረጋገጡም በላይ፣ የመንገድ ተጠቃሚዎችን ደህንነት በማስጠበቅ የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው። አስተያየታቸውን የሰጡ አሽከርካሪዎች በከተማዋ የተሰሩት አዳዲስ መንገዶች እና የኮሪደር ልማት ስራዎች የትራፊክ ፍሰቱን በማሳለጥ አዎንታዊ ለውጥ አምጥተዋል ብለዋል። አሽከርካሪ የሆኑት ኃይሌ ዘመድኩን እና ጤናዬ ጠንክር እንደገለጹት፤ የኮሪደር ልማቱ ለትራፊክ ፍሰት አመቺ እና ዘመናዊ መንገዶችን በመፍጠር ስጋት የለሽ የማሽከርከር ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል። የከተማዋን ገጽታ በእጅጉ የቀየሩት እነዚህ ውብና ሰፋፊ መንገዶች፣ የዲዛይን ጥራታቸውና የተሟላ የመንገድ ምልክቶቻቸው ለትራፊክ አደጋ መቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ ብለዋል። የኮሪደር ልማት ለከተማዋ ውበት ብቻ ሳይሆን፣ ለአሽከርካሪዎች የላቀ የደህንነት ስሜትና የጉዞ ቅልጥፍናን የሰጠ ስኬታማ የልማት ስራ መሆኑን ጠቅሰዋል። አሽከርካሪ ብሩክ ግሩም፤ የኮሪደር ልማቱ የነበረውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ በመቅረፍ ተሽከርካሪዎች በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ በማድረጉ ጉዞን በአጭርና በአስተማማኝ ሁኔታ ማከናወን ተችሏል ብለዋል። የመንገድ አቅም መጨመሩ ለትራፊክ ፍሰቱ መሻሻል ብቻ ሳይሆን፣ አደጋዎችን በእጅጉ በመቀነስ ለአሽከርካሪዎች ትልቅ የደህንነት እፎይታን የፈጠረ ውጤታማ የልማት ስራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ዘርጋ እንደገለጹት፤ የተከናወኑት የኮሪደር ልማት ስራዎች የትራፊክ ፍሰቱን በማቀላጠፍና የከተማዋን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሰላማዊ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው። ይህ ዘመናዊ የመንገድ አውታር እግረኞች በደህንነት ተጠብቀው በፍጥነት እንዲንቀሳቀሱ ምቹ ሁኔታን በመፍጠሩ፣ በያዝነው በጀት ዓመት በሰውና በንብረት ላይ ይደርስ የነበረውን የመንገድ አደጋ በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ ተችሏል ብለዋል። ፕሮጀክቱ የመንገድ ደህንነትን በማረጋገጥና የትራፊክ መጨናነቅን በማስወገድ፣ በከተማዋ ለሚደረግ ማንኛውም አይነት የጉዞ እንቅስቃሴ አስተማማኝና ቀልጣፋ አማራጭ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በዞኑ የተገኘው ሰላም የግብርና ስራችንን በተረጋጋና በተደራጀ መልኩ ለማከናወን አስችሎናል - አርሶ አደሮች
Jul 11, 2026 92
ገንዳውኃ፤ ሐምሌ 4/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን የተገኘው ሰላም የግብርና ስራቸውን በተረጋጋና በተደራጀ መልኩ ማከናወን እንዳስቻላቸው አርሶ አደሮች ተናገሩ። አርሶ አደር ሱሌማን ዳውድ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የአካባቢያችን ሰላም ለማስጠበቅ ባደረግናቸው ጥረቶች የእርሻ ስራችን በተገቢው መንገድ ለማከናወን አስችሎናል። በአሁኑ ወቅትም በ10 ሄክታር መሬታቸውን በሰሊጥ፣ በአኩሪ አተርና ሌሎች ሰብሎች ለመሸፈን የዘር ስራ መጀመራቸውን ነው የገለጹት። አርሶ አደር ደጀኔ አሰፋ በበኩላቸው፣ ዞኑ ለግብርና ልማት ያለው ፀጋ ለወጭ ንግድ የሚሆኑ ምርቶችን በስፋት ለማምረት እንዳስቻላቸው ገልጸዋል። በዘንድሮው ክረምትም ባለኝ 20 ሔክታር መሬት ላይ ጥጥ፣ ሰሊጥ፣ አኩሪ አተርና ሌሎች ሰብሎችን በመዝራት እስከ 200 ኩንታል ምርት ለማግኘት እየሰራሁ ነው ብለዋል። በአካባቢው የተፈጠረው ሰላም አርሶ አደሩ፣ ባለሃብቱና የጉልበት ሰራተኛው ተረጋግቶ እንዲሰራ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን የገለጹት ደግሞ በእርሻ ኢንቨስትመንት የተሰማሩት አቶ ቃሲም እንድሪስ ናቸው። ያላቸውን 65 ሄክታር መሬት በዘመናዊ መንገድ በማልማት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አንዳርጌ ጌጡ እንደገለጹት፤ ማሕበረሰቡ የአካባቢውን ሰላም ለማረጋገጥ ከአመራሩ እና ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል። በዚህም አስተማማኝ ሰላም እየተፈጠረ በመምጣቱ በዘመናዊ ትራክተሮችና ሜካናይዜሽን ታግዞ የግብርና ስራን ለማቀላጠፍ እንተቻለ ነው የተናገሩት። በተገኘው ሰላም ለአርሶ አደሩና ባለሃብቱ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶችና የምርት ማሳደጊያ ግብዓትን በወቅቱ ለማቅረብም እንደተቻለ ነው ያመለከቱት። በዘንድሮው የመኸር እርሻ 529 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ከ450 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በዘር ተሽፍኗል ብለዋል። የዞኑ ህብረተሰብም ሰላም የሁሉም መሰረት መሆኑን በመገንዘብ ከጸጥታ አካላት ጎን በመሰለፍ ያረጋገጠውን ሰላም አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው አስገንዝበዋል።
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ከ60 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ተሸፍኗል
Jul 11, 2026 108
ደሴ፤ ሐምሌ 4/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በመኸር እርሻ ከ60 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። የመምሪያው ኃላፊ ተገኝ አባተ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በዞኑ በ2018/19 የምርት ዘመን ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራስን ለመቻል የሚያግዙ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ። በዚህም በመኸር እርሻ 231 ሺህ 566 ሄክታር መሬት በማልማት ከሰባት ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን ገልጸዋል። የዝናቡ ወቅት ቀድሞ በጀመረባቸው አካባቢዎች እስካሁን ከ60 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን ማሳ በዘር መሸፈኑንም ነው ያመለከቱት። አርሶ አደሩ የተሻሻሉ አሰራሮችንና ቴክኖሎጅዎችን እንዲጠቀም በማድረግ ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ ከ160 ሺህ ኩንታል በላይ ዘመናዊ ማዳበሪያ መሰራጨቱን ነው የገለጹት። የዝናብ መዘግየት ባለባቸው አካባቢዎች ደግሞ የመስኖ አማራጭን በመጠቀም የመኸር ሰብል ልማቱን እንዲያከናውኑ ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በሰሜን ወሎ ዞን ባለፈው የመኸር ምርት ዘመን ከለማው 231ሺህ ሄክታር መሬት አምስት ነጥብ ስምንት ሚሊየን ኩንታል ምርት መገኘቱን ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በወጪ ንግድ የተመዘገበውን ውጤት ይበልጥ ለማሳደግ በምርት ጥራትና እሴት መጨመር ላይ ትኩረት ተደርጓል - ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)
Jul 11, 2026 112
ሀዋሳ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ):- በሀገሪቱ በወጪ ንግድ የተመዘገበውን ውጤት ይበልጥ ለማሳደግ በምርት ጥራትና እሴት መጨመር ላይ በትኩረት እንደሚሰራ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ። ሚኒስትሩ የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክን የሥራ እንቅስቃሴ የጎበኙ ሲሆን፣ በፓርኩ የአቮካዶ፣ ዘይትና ቡናን የሚያቀናብሩ ኩባንያዎችን ተመልክተዋል። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደተናገሩት፤ መንግሥት የወጪ ንግድ ገቢን ለማሳደግ በእሴት መጨመር ሥራ ላይ የሚደረጉ ጥረቶችን ለማጠናከር ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል። በተለይም በግብርናው ዘርፍ ያለውን አቅም በአግባቡ በመጠቀምና ገበያው በሚፈልገው መልኩ እሴት ጨምሮ መላክ ላይ የተጀመሩ ጥረቶች የሚጠናከሩ ናቸው ብለዋል። በፓርኩም በአቮካዶና በቡና ዘርፍ በመሰማራት እሴት በመጨመር የወጪ ገቢ ግኝትና ተኪ ምርት ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎችን መመልከታቸውን ጠቅሰው፤ ተግባሩን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በዘንድሮ ዓመት ከወጪ ንግድ ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ በማግኘት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ መቻሏን ያወሱት ሚኒስትሩ፤ በፓርኩ የሚታዩ እንቅስቃሴዎችን ማሳደግ ይገባልም ብለዋል። በእስካሁኑ ሂደትም ተኪ ምርቶች ላይ እንደሀገር እየተገኘ ያለውን ውጤት ለማጠናከር የሚደረጉ ጥረቶች አበረታች መሆናቸውንም ጠቅሰዋል። በዚህ ሂደት ደግሞ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፓርኮች መቋቋማቸው ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል። በኢንዱስትሪ ፓርኩ ቡናን በማቀነባበር ስራ ላይ የተሰማራው የ“መይ መይ ቡና ፕሮሰሲንግ” ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ጄይ ሰን፣ በመንግሥት በተደረገላቸው ድጋፍ ታግዘው ወደ ሥራ መግባታቸውን ጠቅሰዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የአፍሪካ የትምህርት ኢኖቬሽን ኤክስፖ በአዲስ አበባ ይካሄዳል
Jul 11, 2026 48
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦ የ2026ቱን የአፍሪካ የትምህርት ኢኖቬሽን ኤክስፖ በመጪው ሐምሌ 6 እና 7 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ያዘጋጀው ይህ ኤክስፖ፤ “በትምህርት ዘርፍ የዲጂታል ሽግግርን ማፋጠንና ለአፍሪካ የክህሎት ዘመን የአዳዲስ መፍትሔዎችን ተደራሽነት ማስፋት” በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚካሄድ ታውቋል። ይህ አህጉራዊ ኤክስፖ በአፍሪካ የትምህርትና ክህሎት ሥርዓት ውስጥ ያሉ የጥራት፣ የተደራሽነትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ክፍተቶችን በቴክኖሎጂ አማካኝነት ለመፍታት ያለመ ነው። መድረኩ በተለይም አዳዲስ የቴክኖሎጂ መፍትሔዎችን በማስተዋወቅ የአፍሪካን የትምህርት ዘርፍ ማዘመን በሚቻልባቸው ስትራቴጂዎች ላይ ይመክራል። በኤክስፖው በትምህርት፣ በከፍተኛ ትምህርት፣ በቴክኒክና ሙያ እንዲሁም በሮቦቲክስ ዘርፎች ከፍተኛ ተፅዕኖ ማምጣት የቻሉ ከ20 በላይ አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎች ለዕይታ ይቀርባሉ። በተጨማሪም በዲጂታል ትምህርት፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI)፣ በአረንጓዴ ክህሎቶች፣ በምርምርና በኢንዱስትሪ አጋርነት ላይ ያተኮሩ ውይይቶች የሚካሄዱ ሲሆን፤ ውይይቶቹም ከአህጉራዊ የትምህርትና የሳይንስ ስትራቴጂዎች ጋር የተጣጣሙ መሆናቸው ተገልጿል። በኤክስፖው ከ300 በላይ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ በትምህርት ዘርፍ የተሰማሩ የፈጠራ ባለቤቶች፣ ተመራማሪዎች፣ የልማት አጋሮች እና የቴክኖሎጂ መሪዎች በአካል እንደሚገኙ ይጠበቃል። ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሌሎች ታዳሚዎችም በበይነ መረብ አማካኝነት በሁነቱ ላይ እንደሚሳተፉ ኢዜአ ከአፍሪካ ኅብረት ያገኘው መረጃ ያሳያል። ኤክስፖው በአጠቃላይ በአፍሪካ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ የዲጂታልና የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን አጠቃቀም ለማፋጠን ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተመላክቷል። ይህም አፍሪካ ለቀጣይ የኢኮኖሚ ሽግግር ብቁና ዝግጁ የሆኑ ባለሙያዎችን ለማፍራት እንዲሁም የአህጉሪቱን የሰው ኃይል አቅም ለማጠናከር ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥርላት ታምኖበታል።
በዞኑ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የፈጠራ እና የቴክኖሎጂ መፍለቂያ ስፍራዎች እንዲሆኑ ትኩረት ተደርጓል
Jul 11, 2026 176
ጅማ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦በጅማ ዞን የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የፈጠራ እና የቴክኖሎጂ መፍለቂያ ስፍራዎች እንዲሆኑ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ። የጅማ ቴክኒክና ሙያ ክላስተር በ23 የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ሲያሰለጥናቸው የቆዩትን 2 ሺህ 35 ሰልጣኝ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል። የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ቲጃኒ ናስር እንደገለጹት፤ የበለጸጉ ሀገራት ለስኬት ሊበቁ የቻሉት በቴክኖሎጂ መስፋፋት እና ጥራቱን በጠበቀ የትምህርት አሰጣጥ ላይ ትኩረት በማድረጋቸው ነው። በዞኑም ቴክኖሎጂን ለማስፋፋትና ትምህርትን ተደራሽ ለማድረግ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በትኩረት እየተሰራ በመሆኑ ዕቅዱን ከግብ የሚያደርስ ነው ብለዋል። ከዚህ ጎን ለጎን የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የፈጠራ እና የቴክኖሎጂ መፍለቂያ ስፍራዎች እንዲሆኑ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል። ዞኑ በርካታ ተፈጥሯዊ ጸጋዎች ያሉት በመሆኑ ዛሬ የተመረቁ ወጣቶች ያሉትን ምቹ ሁኔታዎች በመጠቀም ከስራ ጠባቂነት ተላቅቀው የስራ ዕድል ፈጥረው ለብዙ ወጣቶች መትረፍ እንዳለባቸውም አክለዋል። የጅማ ዞን የስራ ዕድል ፈጠራ እና ክህሎት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ የዚያድ አባገሮ በበኩላቸው፤ ተመራቂዎቹ ባገኙት ሙያና በቀሰሙት ልምድ ከራሳቸው አልፈው ለዜጎች ስራ መፍጠር እንደሚገባቸው ተናግረዋል። የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የፈጠራ እና የቴክኖሎጂ መፍለቂያ ስፍራዎች በመሆናቸው፣ ተመራቂዎቹ የቀሰሙትን እውቀት በተግባር ማዋል አለባቸው ብለዋል። ከጅማ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አራት ነጥብ ውጤት በማምጣት የተመረቀው ይሳኮር ብርሃኑ፣ በተማረበት መስክ ስራ ለመፍጠር መዘጋጀቱን ተናግረዋል። የተለያዩ ሀገራት በቴክኖሎጂ የደረሱበትን ሁኔታ ዘወትር እንደሚከታተል የተናገረው ወጣቱ፣ ሀገራችንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የቴክኖሎጂ ጉዞዋ እያደገ በመሆኑ በዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞ ውስጥ የድርሻውን እንደሚወጣ ገልጿል። በተመሳሳይ አራት ነጥብ ያመጣው ሌላኛው ተመራቂ ደጀን ገብሬ፤ በተማረው የሙያ መስክ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ሰፊ የስራ እድልን በመፍጠር ከራሱ አልፎ ለሌሎች ለመትረፍ አቅዷል። ሌላኛዋ ተመራቂ ቤተልሔም በየነ፤ የትምህርት ቆይታዋ ስኬታማ እንዲሆን መምህራኖቿ እና ቤተሰቦቿ አስፈላጊውን ድጋፍ ሲያደርጉላት እንደነበር ገልጻለች። አክላም፣ በቀጣይ ባገኘችው ዕውቀትና ልምድ ራሷንና ቤተሰቧን ለመለወጥ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ አስታውቃለች።
በዞኑ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ ቀልጣፋና ግልጽነት የሰፈነበት አሰራርን በማረጋገጥ እያገዘ ነው
Jul 10, 2026 830
መቱ፤ ሐምሌ 3/2018 (ኢዜአ):- የኢሉአባቦር ዞን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ ቀልጣፋና ግልጽነት የሰፈነበት አሰራርን በማረጋገጥ የህብረተሰቡን እንግልት እየቀነሰ መሆኑ ተገለጸ። የኢሉአባቦር ዞን ያዮ ወረዳ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በዛሬው ዕለት ተመርቆ አገልግሎት ጀምሯል። የኢሉአባቦር ዞን አስተዳዳሪ አቶ እንዳልካቸው ተፈሪ፤ የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ ማህበረሰቡን በታማኝነትና በቅንነት ለማገልገል ታልሞ የተቀረጸ ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በዞኑ ወደ ስራ የገቡ ማዕከላትም የህብረተሰቡን የአገልግሎት ተደራሽነት የሚያሰፋ፣ ፍትሃዊና ቀልጣፋ አሰራርን እያሰፈኑ መሆኑን ተናግረዋል። ይህም የተገልጋዩን ድካምና እንግልት ማስቀረት እያስቻለ መሆኑንም ገልጸዋል። በያዮ ወረዳ ስራ የጀመረው የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 32 የስራ ክፍሎችን በአንድ ላይ ያካተተ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ በቀጣይም አሰራሩን በሁሉም የዞኑ ወረዳዎች ለማስፋፋት በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል። ከወረዳው ነዋሪዎች መካከል ቄስ ሳሙኤል ደምሴና ወይዘሮ ወርቄ ተፈራ፤ ማዕከሉ የተገልጋዩን መጉላላት የሚያስቀርና የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን የሚያሻሽል በመሆኑ ስራ መጀመሩ አስደስቷቸዋል። ብልሹ አሰራሮችን በመቀነስ ረገድ መንግስት እየወሰዳቸው የሚገኙት መሰል እርምጃዎች አበረታች መሆናቸውንም ጠቅሰዋል። ወይዘሮ ገላኔ ኮርሳና አቶ ጀማል ኢብራሂም በበኩላቸው፤ የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ ህዝቡን ከምልልስና ከተጨማሪ ወጪ የሚታደግ መሆኑን አንስተዋል። የመንግስት አገልግሎት ሰጪ መስሪያ ቤቶችም ከተለመደውና ለቅሬታ ከሚዳርጉ ብልሹ አሰራሮች በመላቀቅ፣ ማህበረሰቡን በታማኝነት የማገልገል ባህላቸውን ሊያሳድጉ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ የዲጂታል ኢንቨስትመንት የቁልፍ መሰረተ ልማት ተቋማትን ደኅንነት መጠበቅ የሚያስችል አቅም ፈጥሯል
Jul 10, 2026 855
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/ 2018 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ የዲጂታል መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት የዜጎችንና የቁልፍ መሰረተ ልማት ተቋማትን ደኅንነት መጠበቅ የሚያስችል አቅም መፍጠሩን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ገለጹ። ዓለም አቀፉ የፓርላማ የመረጃ ደኅንነት ፎረም ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ስብሰባውን በአዲስ አበባ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ማካሄድ ጀምሯል። በመድረኩ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀም፣ የሳይበር ደኅንነት፣ ቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ፣ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርና መሰል ዓለም አቀፍ አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ በስፋት ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ የደኅንነት ፈተናዎችን በአፋጣኝ ምላሽ የሚሰጥና በአጋርነት መርህ ላይ የተመሰረተ በርካታ ስኬታማ ሥራዎችን እያከናወነች ነው። በዚህም ቀጣናዊ ጠንካራ የትብብር ማዕቀፎችን በመዘርጋት፣ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርንና በሰዎች መነገድ ወንጀልን ለመከላከል እየሰራች መሆኗን ገልጸዋል። ቀጣናዊ ሰላምና ደኅንነትን በማስጠበቅ፣ የሽብር ቡድኖችን እንቅስቃሴ ከማክሸፍ ባሻገርም፣ ልማትን በማፋጠን ድኅነትና ሥራ አጥነትን በጋራ ለመቀነስ አስደናቂ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑን አንስተዋል። የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት የሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ የዲጂታል መሠረተ ልማትና ሳይበር ደኅንነት አቅምን በማጎልበት የዜጎችንና ቁልፍ ብሔራዊ ተቋማትን ለመጠበቅ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ያካሄደችው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫም አካታች፣ ነፃና ፍትሐዊ እንዲሁም ለሕገ-መንግሥታዊ አስተዳደርና ለሕግ የበላይነት ያላትን ቁርጠኝነት ያሳየ መሆኑን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በበኩላቸው፤ በአሁኑ ወቅት ዓለም እያጋጠሟት ያሉ ስጋቶች ውስብስብና በፍጥነት የሚቀያየሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። መንግሥታትም የሳይበር ወንጀሎችን ለመከላከል የመረጃ ልውውጥና ሕጋዊ ማዕቀፎችን በማጣጣም ትብብራቸውን ማሳደግ እንዳለባቸው ገልጸዋል። የኢትዮጵያና አሜሪካ የጤና ዘርፍ አጋርነት ውጤታማ ተግባራትን እያከናወኑ ነው ያሉት አምባሳደሩ፤ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመዋጋትም በትብብር እየተሰራ ነው ብለዋል። የፎረሙ መስራችና ሊቀመንበር ሮበርት ፒተንገር ፤ ፎረሙ ኢትዮጵያ ለልማትና ዴሞክራሲ ያላትን ቁርጠኝነት እንዲሁም የመሪዎቿን ርዕይ ለመላው ዓለም ለማሳየት ዕድል የሚፈጥር ነው ብለዋል።
ስፖርት
አስተዳደሩ በአዲሱ በጀት ዓመት ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍራት ለሚያስችሉ ተግባራት ትኩረት ይሰጣል
Jul 11, 2026 118
ደብረብርሃን፤ ሐምሌ 4/2018(ኢዜአ)፦ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር በአዲሱ በጀት ዓመት ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍራት ለሚያስችሉ ተግባራት ትኩረት እንደሚሰጥ አስታወቀ። የደብረ ብርሃን ከተማ ስፖርት ምክር ቤት የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ላይ የሚመክር ጉባኤውን ዛሬ አካሂዷል። የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባና የስፖርት ምክር ቤቱ ሰብሳቢ በድሉ ውብሸት በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ከተማዋ በኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝምና ኢንቨስትመት ተመራጭ እየሆነችና እያደገች ትገኛለች። በአዲሱ በጀት ዓመትም ይሕንኑ እድገት በተሟላ መልኩ ለማስቀጠል ስድስት ደረጃቸውን የጠበቁ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንደሚገነቡ ገልጸዋል። ስፖርት ወጣቶችን በስብዕና ለመገንባት፣ ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር የሚያግዝ በመሆኑ ባለሃብቱና ማሕበረሰቡ በመሰረተ ልማት ግንባታው በንቃት እንዲሳተፍ ነው የጠየቁት። የከተማ አስተዳደሩ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ ተክለዮሃንስ ኃይለጊዮርጊስ በበኩላቸው፤ የስፖርት ዘርፉን በመደገፍ ብቁና ተወዳዳሪ ሰፖርተኞችን ለማፍራት ርብርብ ይደረጋል ብለዋል። ምክር ቤቱ በ2019 በጀት ዓመት ለሚካሄዱ የስፖርት መሰረተ ልማት ግንባታዎች ከ27 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ማጽደቁን ገልጸዋል። በከተማ አስተዳደሩ 12 ካርታና ፕላን ያላቸው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መኖራቸውም ነው የተገለፀው።
የማስ ስፖርት መጠናከር የዜጎችን የአብሮነት እሴት ያጎለብታል
Jul 11, 2026 397
ሐረር፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦ የማስ ስፖርት እንቅስቃሴዎች መጠናከር ጤናማ ትውልድ እንዲኖር ከማስቻል ባለፈ የዜጎችን የአብሮነት እሴት የሚያጎለብት መሆኑን የሐረሪ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ገለጸ። በሐረር ከተማ በሚገኘው የአባድር ፕላዛ መናፈሻ ስፍራ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄዷል። ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በተከናወነው በዚህ መርሃ ግብር ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አዘጋጆች፣ የሴክተር መስሪያ ቤት ሰራተኞች፣ ወጣቶች፣ ህጻናትና በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሙራድ አብዲ፤ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለአካል ጥንካሬ፣ ለአእምሮ እድገት እንዲሁም ጤናማና ብቁ ዜጋን ለማፍራት ያለውን ጠቀሜታ አብራርተዋል። የክልሉ መንግስት 'ስፖርት ለሁሉም፣ በሁሉም ስፍራ' በሚል መርህ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም አንስተዋል። የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከጤና ጥቅሙ ባለፈ የዜጎችን የአብሮነት እሴት የሚያጎለብትና በራሱ የሚተማመን ትውልድ ለመቅረጽ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል። መሰል ስፖርታዊ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ኮሚሽነሩ አስገንዝበዋል። የሐረሪ ክልል ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሚ አብዱልዋሲ በበኩላቸው፤ በክልሉ የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ ሰፋፊ የኮሪደር ልማትና የቅርስ ጥበቃ ስራዎች በስፋት ተከናውነዋል ብለዋል። እነዚህ ስራዎች አደጋ ተደቅኖባቸው የነበሩ ቅርሶችን ለመታደግ ከማስቻላቸው ባለፈ፣ ሐረርን ለነዋሪዎቿና ለጎብኚዎቿ ይበልጥ ውብ፣ ሳቢና ማራኪ ማድረግ መቻሉን ጠቅሰዋል። ኮሚሽነሩ አክለውም፣ በክልሉ መጪው ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም “ሩጫ በህያው ሙዚየም” በሚል መሪ ሀሳብ ሀገር አቀፍ የሩጫ ውድድር እንደሚካሄድ ጠቁመው፤ የዛሬው የአካል ብቃት እንቅስቃሴም የዚሁ ትልቅ ስፖርታዊ ክስተት ማሟሟቂያና የስፖርት ቱሪዝምን የማስተዋወቂያ አካል መሆኑን ተናግረዋል።
አርጀንቲና ከስዊዘርላንድ፣ ኖርዌይ ከእንግሊዝ፤ ግማሽ ፍጻሜ ለመግባት የሚደረጉ ተጠባቂ ፍልሚያዎች
Jul 11, 2026 433
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ የሚገቡ ቀሪ ሁለት ሀገራት የሚለዩባቸው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ። ከሌሊቱ 10 ሰዓት አርጀንቲና ከስዊዘርላንድ በካንሳስ ሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። አርጀንቲና 16 ውስጥ ግብጽን 3 ለ 2 በመርታት ወደ ሩብ ፍጻሜው ገብታለች። የወቅቱ የዓለም ዋንጫ ባለቤት አርጀንቲና በጨዋታው እስከ 80ኛው ደቂቃ 2 ለ 0 ብትመራም በ13 ደቂቃዎች ውስጥ ውጤቱን በመቀልበስ አሸንፋለች። የደቡብ አሜሪካዋ ሀገር በውድድሩ ተሳትፎ ታሪኳ ለ10ኛ ጊዜ ሩብ ፍጻሜ ገብታለች። ተጋጣሚዋ ስዊዘርላንድ ኮሎምቢያን በመለያ ምት 4 ለ 3 በማሸነፍ ከ72 ዓመታት በኋላ ወደ ሩብ ፍጻሜው ገብታለች። ጨዋታው በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ እና 30 ደቂቃ ግብ አልተቆጠረበትም። ስዊዘርላንድ ስምንት ውስጥ ስትገባ የአሁኑ ለአራተኛ ጊዜ ነው። ሁለቱ ሀገራት በዓለም ዋንጫው ከዚህ ቀደም አንድ ጊዜ ተገናኝተዋል። እ.አ.አ በ2014 በብራዚል በተካሄደው 20ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ 16 ወስጥ ተገናኝተው አርጀንቲና በሊዮኔል ሜሲ ጎል 1 ለ 0 ስዊዘርላንድን በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍጻሜው አልፋለች። ቡድኖቹ ከ12 ዓመታት በኋላ በመድረኩ በድጋሚ ተገናኝተዋል። ሁለቱ ሀገራት በውድድሮች እና የወዳጅነት ጨዋታዎች ሰባት ጊዜ ተገናኝተው አርጀንቲና አምስቱን በማሸነፍ የበላይነቱን ይዛለች። በቀሪ ሁለት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል። ስዊዘርላንድ እስከ አሁን አርጀንቲናን አሸንፋ አታውቅም። በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ 8 ግቦችን ያስቆጠረው የ39 ዓመቱ አርጀንቲናዊ ሊዮኔል ሜሲ፣ የውድድሩን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት እየመራ ይገኛል። ሜሲ በዓለም ዋንጫው በአጠቃላይ 21 ግቦችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪም ነው። አርጀንቲናዊው ኮከብ በዛሬው ጨዋታ ልዩነት ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል። በዓለም ዋንጫው ለስዊዘርላንድ አራት ግቦችን ያስቆጠረው የ29 ዓመቱ ብሬል ኢምቦሎ፣ በዚህ ጨዋታ ላይ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ቁልፍ ተጫዋች ነው። በሌላኛው የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ኖርዌይ ከእንግሊዝ በሚያሚ ስታዲየም ከሌሊቱ ስድስት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። በ16ቱ የጥሎ ማለፍ መርሐ ግብር ኖርዌይ ባልተጠበቀ ሁኔታ ብራዚልን 2 1 ለ በመርታት በታሪኳ በዓለም ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ አልፋለች። ተጋጣሚዋ እንግሊዝ ከአዘጋጅ ሀገራት መካከል አንዷ በሆነችው ሜክሲኮ በተፈተነችበት ጨዋታ 3 ለ 2 በማሸነፍ ስምንት ውስጥ ገብታለች። ሶስቱ አናብስቶች በዓለም ዋንጫ ተሳትፏቸው ወደ ሩብ ፍጻሜ ሲያልፉ የአሁኑ ለ10ኛ ጊዜ ነው። የአውሮፓ ሀገራቱ ከዚህ ቀደም በዓለም ዋንጫው ተገናኝተው አያውቁም። በተለያዩ ውድድሮች እና የወዳጅነት ጨዋታዎች ላይ 12 ጊዜ ተገናኝተው እንግሊዝ ሰባት ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ስትይዝ ኖርዌይ በሁለት ጨዋታዎች ድል ቀንቷታል። በቀሪ ሶስት ጨዋታዎች ላይ አቻ ተለያይተዋል። እንግሊዝ በ12ቱ ጨዋታዎች ላይ 28 ጎሎችን ከመረብ ላይ ስታሳርፍ ኖርዌይ ሰባት ግቦችን አስቆጥራለች። እ.አ.አ በ1937 ለመጀመሪያ ጊዜ በተገናኙበት ጨዋታ እንግሊዝ 6 ለ 0 ማሸነፏን መረጃዎች ያመለክታሉ። በዓለም ዋንጫው ላይ ሰባት ጎሎችን ያስቆጠረው የኖርዌው አርሊንግ ሃላንድ እና ስድስት ግቦችን ከመረብ ላይ ያሳረፈው እንግሊዛዊው ሃሪ ኬን በዛሬው ጨዋታ ልዩነት ይፈጥራሉ ተብለው የሚጠበቁ ተጫዋቾች ናቸው። የኖርዌው አምበል ማርቲን ኦዴጋርድ እና የእንግሊዙ ጁድ ቤሊንግሃም መሐል ክፍል ላይ የሚኖራቸው ፉክክርም ትኩረትን ስቧል። እንግሊዝ የማሸነፊያ የቅድሚያ ግምቱን አግኝታለች። ባልተጠበቀ ሁኔታ ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀለችው ኖርዌይ፣ ያለ ጫና መጫወቷ አሸንፋ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ልታልፍ የምትችልበትን እድል ይፈጥርላታል። የዛሬ ጨዋታ አሸናፊዎች በግማሽ ፍጻሜው ይገናኛሉ።
ስፔን ለግማሽ ፍጻሜ አለፈች
Jul 10, 2026 710
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ሁለተኛ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ስፔን ቤልጂየምን 2 ለ 1 አሸንፋለች። ማምሻውን በሎስ አንጀለስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፋቢያን ሩዊዝ ስፔንን መሪ ያደረገችውን በ30ኛ ደቂቃ ከመረብ ላይ አሳርፏል። ጎሉ በጥሩ የኳስ ቅብብል የተገኘ ነበር። ቻርልስ ዲ ኬቴላር በ41ኛው ደቂቃ በግንባሩ በመግጨት ያስቆጠረው ጎል ቤልጂየምን አቻ አድርጓል። ዲ ኬቴላር በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ብዛት ሶስት አድርሷል። ተቀይሮ የገባው ሜኬል ሜሪኖ በ88ኛው ደቂቃ የአሸናፊነቷን ጎል ለስፔን አስቆጥሯል። የ30 ዓመቱ ሜሪኖ 16 ውስጥ ስፔን ፖርቹጋልን ስታሸንፍ ተቀይሮ በመግባት ግብ በማስቆጠር ስፔንን አሸናፊ ማድረጉ የሚታወስ ነው። ተጫዋቹ ምርጥ ተቀያሪነቱን በሁለቱ ጨዋታዎች ላይ አሳይቷል። ስፔን በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ግብ አስተናግዳለች። የ29 ዓመቱ የስፔን ግብ ጠባቂ ኡናይ ሲሞን በዓለም ዋንጫው ከ649 ደቂቃዎች በኋላ ግብ ተቆጥሮበታል። ሲሞን በውድድሩ ላይ ለረጅም ሰዓታት ግብ ሳይቆጠርበት የቆየ ግብ ጠባቂ በመሆን አዲስ ክብረ ወሰን ሰብሯል። ስፔን በኳስ ቁጥጥር እና የግብ እድሎችን በመፍጠር ተሽላ ተገኝታለች። የቤልጂየም የአጨዋወት ስልት መከላከል እና በመልሶ ማጥቃት ላይ ያተኮረ ነበር። የአማዱ ኦናና እና ዩሪ ቲሊማንስ በጉዳት ምክንያት አለመሰለፍ የቤልጂየምን የአማካይ ክፍል አሳስቶታል። የ34 ዓመቱ የቤልጂየም ግብ ጠባቂ ቲቦ ኮርቶዋ በጉዳት ምክንያት 71ኛው ደቂቃ ተቀይሮ ወጥቷል። ውጤቱን ተከትሎ ስፔን ለግማሽ ፍጻሜ አልፋለች። ለሶስተኛ ጊዜ አራት ውስጥ ገብታለች። ስፔን ለዋንጫ ለማለፍ ከፈረንሳይ ጋር የምታደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው። ቤልጂየም በዓለም ዋንጫው ለሶስተኛ ጊዜ ወደ ግማሽ ፍጻሜ የማለፍ ህልሟ ሳይሳካ ቀርቷል።
አካባቢ ጥበቃ
የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ለዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ እና የስነ-ምህዳር መታደስ ትልቅ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል
Jul 11, 2026 167
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተራቆቱ አከባቢዎች መልሰው እንዲያገግሙ በማድረግና የአፈር መሸርሸርን በመከላከል ለዘላቂ አካባቢ ጥበቃና ለስነ-ምህዳር መታደስ ትልቅ ሚና በመጫወት ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ለሊሴ ነሜ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቋቋም፣ የደን ሽፋንን ለማሳደግና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችለውን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተገበረች ይገኛል። በዚህ ታላቅ ሀገራዊ ንቅናቄ እስከ አሁን ባሉት ዓመታት ከ48 ቢሊዮን በላይ የደን፣ የፍራፍሬና የጥላ ችግኞችን ማልማት ተችሏል። በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሐሳብ በሀገር አቀፍ ደረጃ ስምንት ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ዕቅድ ተይዞ ወደ ትግበራ ተገብቷል። የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አካባቢን ከብክለትና ከዕፅዋት መራቆት የምንጠብቅበት፣ እንዲሁም የተዛባውን የተፈጥሮ ሚዛን የምናስተካክልበት ዋነኛና ውጤታማ መንገድ መሆኑን አንስተዋል። በአገሪቱ እየተተገበረ ያለው ይህ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የተራቆቱ መሬቶችን መልሶ በማገገም፣ የአፈር መሸርሸርን በመከላከል እና የከርሰ ምድር ውሃ እንዲጠራቀም በማድረግ ለአካባቢ ጥበቃና ለሥነ-ምህዳር መታደስ የጎላ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አስታውቀዋል። ከዚህም ባሻገር ዘላቂ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም፣ የአየር ብክለትን ለመቀነስና ለቀጣዩ ትውልድ ምቹና አረንጓዴ ሀገርን ለማስረከብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አመልክተዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የሀገሪቱን የደን ሽፋን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደጉን የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ይህም ለሀገር ውስጥ የአየር ንብረት መረጋጋት ብቻ ሳይሆን ለዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ጥበቃም ጭምር ትልቅ በረከት መሆኑን ገልጸዋል። የአረንጓዴ አሻራና ሰው ሠራሽ ደን ሥራ አስፈጻሚ አበሩ ጠና በበኩላቸው፤ ከመርሀ ግብሩ ጅምር ጀምሮ የተተከሉት ችግኞች ከአካባቢ ጥበቃ ባሻገር ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥቅም እያስገኙ መሆናቸውን ገልጸዋል። የፍራፍሬና ሌሎች ምግብ ነክ ችግኞች የምግብ ዋስትናን ከማጠናከር ባለፈ ለውጭ ገበያ ቀርበው የውጭ ምንዛሬ ማስገኘትንና የሥራ ዕድል ፈጠራን እየደገፉ እንደሚገኙ አመልክተዋል። መርሀ ግብሩ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ ያላትን ዓለም አቀፍ አስተዋጽኦ እያጠናከረ ሲሆን ለካርቦን ገበያ ተጠቃሚነትም ምቹ መሠረት እየፈጠረ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል። የጉለሌ እፅዋት ማዕከል የምርምርና ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ደበላ ብሩ በበኩላቸው፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በተለይ ሀገር በቀል ዕፅዋትን በማስፋፋት የሥነ-ምህዳር ሚዛንን ለመጠበቅ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጸዋል። ሀገር በቀል ዕፅዋት ከአካባቢው የአፈርና የአየር ንብረት ጋር ተስማሚ በመሆናቸው በቀላሉ የሚለሙ መሆናቸውን አንስተው፤ የመሬት ለምነትን፣ የከርሰ ምድር ውሃ ክምችትንና የአፈር ጥበቃን በማጠናከር የተፈጥሮ ሀብትን ለመጠበቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው ገልጸዋል።
ኢዜአ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ያለውን ተግባራዊ ተሳትፎ አጠናክሮ ይቀጥላል
Jul 11, 2026 138
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ሕብረተሰቡን ከማንቃት ባለፈ በተግባር በመሳተፍ ግንባር ቀደም ሚናውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ሥራ አስፈጻሚው ሰይፈ ደርቤ ገለጹ። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) አመራሮችና ሰራተኞች "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሐሳብ በእንጦጦ ፓርክ የአረንጓዴ ዐሻራቸውን አሳርፈዋል። የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰይፈ ደርቤ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ለአረንጓዴ ዐሻራ ልዩ ትኩረት ሰጥታ የችግኝ ተከላን ባህል አድርጋዋለች። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እያስመዘገበች ያለውን ስኬት ለማስቀጠል እንዲሁም ለዓለም ስጋት የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል የምትጫወተውን ሚና ለዓለም በማሳወቅ በኩል ኢዜአ የበኩሉን እንደሚወጣ ተናግረዋል። ሀገር ያስቀመጠችውን ግብ እንዲሳካ ኢዜአ ማኅበረሰቡን ከማንቃትና መረጃ ከማስተላለፍ ባሻገር፣ በግንባር ቀደምነት በተግባር የመሳተፍ ሚናውን እንደሚያጠናክርም አስታውቀዋል። በተለይም ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ማዕከል እንድትሆን የሚከናወኑ ተግባራትን በማስተዋወቅና ግንዛቤ በመፍጠር በኩል የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። በመርሐ ግብሩ የተሳተፉ የኢዜአ አመራሮችና ሠራተኞች በበኩላቸው፣ ለመጪው ትውልድ የተሻለች ሀገርን ለማስረከብ ዐሻራቸውን በማኖራቸው መደሰታቸውን ጠቅሰዋል። በኢዜአ የይዘት ፕሮግራም ዳይሬክተር ራሄል አበበ፣ መርሐ ግብሩ የሀገሪቱን የደን ሽፋን ከመጨመር ባለፈ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዲፕሎማሲ እንድትታወቅ ትልቅ አቅም እየፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል። የነጋሪ መጽሄት ምክትል ዋና አዘጋጅ የሺመቤት ደመቀ በበኩላቸው፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች መረጃ ተደራሽ ከማድረግ ጎን ለጎን በተግባር በመሳተፍ ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚገባቸው ተናግረዋል። ችግኞችን ከመትከል ባሻገር ለፍሬያማነታቸው መንከባከብ አስፈላጊ መሆኑንም አስገንዝበዋል። የውጭ ቋንቋ ዴስክ ከፍተኛ አዘጋጅ ሄኖክ ታደለ በሰጠው አስተያየት፣ ኢትዮጵያ የደን ሽፋንን ለማሳደግ የምትሠራው ሥራ ለዓለም ሀገራት አርዓያ እየሆነ መሆኑን ጠቁሟል። ሌሎች የኢዜአ ባለሙያ የሆኑት ሬድዋን ሸምደስር እና ሰርካለም ዘለቀ በበኩላቸው፣ የለመለመች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ዐሻራቸውን በማሳረፋቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ስራው በተጓዳኝ ለልማትና ማህበራዊ አገልግሎት የላቀ ሚናውን እየተወጣ ነው
Jul 11, 2026 138
ባህርዳር ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ስራው በተጓዳኝ ለልማትና ማህበራዊ አገልግሎት የላቀ ሚናውን እየተወጣ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ገለጹ። የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራቸውን በጥበበ ግዮን ህክምና እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ አኑረዋል። የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር)፤ የአረንጓዴ አሻራ ኢንሸቲቭ እንደ ሀገር ለውጥና ስኬት እየተመዘገበበት መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሰራተኞች የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በጥበበ ግዮን ህክምና እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ችግኞችን በመትከል ጀምረዋል ብለዋል። ዩኒቨርሲቲው ባለፉት ዓመታት በስሩ በሚገኙ ዘጠኝ ካምፓሶች ችግኞችን በመትከል ፅዱ፣ ውብና ምቹ የመማሪያ አካባቢ ከመፍጠር ባለፈ ለተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ የድርሻውን እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል። እንዲሁም ከመማር ማስተማር ስራው በተጓዳኝ ለልማትና ማህበራዊ አገልግሎት የላቀ ሚናውን እየተወጣ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል። በእለቱ አሻራቸውን ካኖሩት መካከል በዩኒቨርሲቲው የምድረ ግቢ ውበት ዳይሬክተር አማረ ቢተው(ዶ/ር)፣ ዩኒቨርሲቲው በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ጠንካራ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል ብለዋል። በተያዘው ዓመትም 15 ሺህ 200 ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት መደረጉንና ለዚህም 37 ሄክታር የመካነ እፅዋት መሬት መዘጋጀቱን ጠቁመው ስራው በዛሬው እለት የተጀመረ መሆኑን ተናግረዋል። እስካሁን በተደረገው ጥረትም ዩኒቨርሲቲው 54 ሄክታር መሬት በአረንጓዴ ልማት መሸፈኑን አስረድተዋል። በዛሬው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ መምህራንና ሰራተኞች ተሳትፈዋል።
የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ለዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ ግንባር ቀደም ማሳያ ነው
Jul 11, 2026 282
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ለዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ ግንባር ቀደም ማሳያ ነው ሲሉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ገለፁ። ዓለምን እየፈተኑ ከሚገኙ ተፈጥሯዊ አደጋዎች መካከል የአየር ንብረት ለውጥ መዛባት በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። ይህንን ተጽዕኖ ለመከላከልም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ የጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ተጨባጭ ለውጥ እያስገኘ ዘንድሮ ስምንተኛ ዓመቱን ይዟል። በእነዚህ ዓመታት በተከናወኑ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሮች የሃገሪቱ የደን ሽፋን እንዲጨምርና ተስማሚ የአየር ንብረት እንዲፈጠር ከማድረጉም በላይ ለግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነት ዕድገት ከፍተኛ ሚና ማበርከቱን የተለያዩ አካላት ይገልጻሉ። ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል አርአያነት ያለው ተግባር የፈጸመች ሲሆን በዘንድሮው ዓመትም ''ተስፋን እንትከል'' በሚል መሪ ሐሳብ ስምንት ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡ ኢዜአ ያነጋገራቸው የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፤ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር እያከናወነችው ያለው ተግባር ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ትልቅ አርአያ የሚሆን እጅግ አስደናቂ ስኬት መሆኑን አድንቀዋል። በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብርሃም ንጉሴ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ የምታካሂደው የአረንጓዴ አሻራ ፖሊሲና የችግኝ ተከላ ሂደት እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። የአየር ንብረት ጉዳይ መላውን ዓለም የሚያሳስብ ዓለም አቀፋዊ ክስተት በመሆኑ ኢትዮጵያ ይህንን ሂደት በተለይም ከአፍሪካ አህጉር በግንባር ቀደምትነት እየመራችው እንደምትገኝ አብራርተዋል። በኢትዮጵያ የስሪላንካ አምባሳደር ኒርማላ ፓራናቪታ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነቱን የአረንጓዴ ልማት መርሐግብር መተግበሯ እጅግ ብልህነት የተሞላበት አካሄድ መሆኑን ገልጸዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ለሀገር የኢኮኖሚ እድገት ትልቅ አበርክቶ ያለው መሆኑን በመግለጽ፣ ስሪላንካ በዚህ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር በቅንጅት ለመሥራት ያላትን ፍላጎት ተግባራዊ የምታደርግበትን መንገድ እያጠናች መሆኗን ጠቅሰዋል፡፡ በኢትዮጵያ የፓኪስታን የንግድና ኢንቨስትመንት ጉዳዮች ተወካይ ባሲት ሳሊም ሻህ በበኩላቸው፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ለኢትዮጵያ የተለየ ውበትና መስህብ ከመለገሱም በላይ፣ ከአየር ብክለት የጸዳ አካባቢን ለማስፋፋት ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብና መሪዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለዚህ ከፍተኛ ደረጃ መብቃት መቻላቸው ሊደነቅ የሚገባው ተግባር ነው ብለዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት አለብን-መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
May 25, 2026 18334
አዲስ አበባ፤ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። 63ኛው የአፍሪካ ቀን ''የ63 ዓመታትን ዓመታት አንድነት፣ ትስስርና ልማት፤ አብረን እናክብር” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። በዝግጅቱም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ ጨምሮ የሕብረቱ አባል ሀገራት ዲፕሎማቶችና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላት ሚና በየ ጊዜው እየታደሰ መምጣቱን ገልጸዋል። የአህጉሪቷ የሕዝብ ቁጥርና የኢኮኖሚ ዕድገትም በጥቂት ዓመታት ውስጥ የአፍሪካን ጥቅል የሀገር ውስጥ ዕድገት ምጣኔ 10 ትሪሊዮን ዶላር ያደርሰዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። የአፍሪካ ወጣቶችም ሌሎች አህጉራት ጭምር የሚመኟቸው የአህጉሪቷ ዕድገትና ብልፅግና አቅም መሆናቸውን አንስተዋል። በቀጣይም የአፍሪካዊያንን የአንድነት ኃይል የበለጠ በማጎልበት የአህጉሪቱን ዕምቅ ፀጋዎች ለሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና መቀየር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ በበኩላቸው፥የአፍሪካዊያን ባህልና ዕሴት ለአህጉሪቷ መፃኢ ዕድል፣ ዕድገትና ብልፅግና የሚተርፍ የጥንካሬ ምንጭ ነው ብለዋል። የአፍሪካን የትብብር አቅም በማጎልበት የአህጉሪቷ ዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥና የራስን የተሻለ ዕድል መቅረፅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ለዚህም በሁሉም ዘርፍ የአፍሪካን የኢኮኖሚ ዕድገት በማስፋት የአህጉሪቱን ዕምቅ የልማት ፀጋ ወደ ዘላቂ ብልፅግና መቀየር እንደሚገባ ተናግረዋል። በአህጉሪቷ ላይ የደረሱ በደሎች ፍትሕ እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገርም ለአጀንዳ 2063 ስኬት በቁርጠኝነት በመስራት የወደፊት እጣ ፋንታ መወሰን እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። በየዓመቱ የአፍሪካ ቀን መከበር የጀመረው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁን የአፍሪካ ህብረት እ.ኤ.አ በ1963 መመስረቱን እንደሆነ ይታወቃል። የዘንድሮው የአፍሪካ ቀንም የህብረቱ ኮሚሽን ከህብረቱ ሰራተኞች ማኅበር፣ አባል ሀገራት፣ ከህብረቱ አደረጃጀቶችና ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች ጋር በመተባበር ተዘጋጅቷል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ ነው
May 13, 2026 12075
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ በጸጥታ፣ በዘላቂ ልማት እና በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ተቋማዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፈርመውታል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በዚሁ ወቅት በሰጡት መግለጫ፣ የአፍሪካ ህብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል። አጋርነታቸውን ይበልጥ ተቋማዊ የሚያደርገው ይህ ስምምነት በቁልፍ ዘርፎች ላይ የተመዘገቡ ስኬቶችንና የወደፊት ዕቅዶችን መነሻ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ በቋሚ አባልነት አለመካተቷን ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነት ነው ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ ይህም የምክር ቤቱን ተቀባይነትና ውጤታማነት እንደሚጎዳው አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ሊስተካከል እንደሚገባ ጠቅሰው አፍሪካ ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወጥታ ለአረንጓዴ ኢነርጂ ሽግግር የማምረቻና የማጣሪያ ማዕከል መሆን እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው፣ የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ እና የተባበሩት መንግሥታት የ2030 አጀንዳ የተጣጣሙ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ፈተናዎችን ለመፍታት በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ማሻሻያ ተደርጎ የአፍሪካ ሀብቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በናይሮቢ የተካሄደው የ"አፍሪካ ፎርዋርድ" (Africa Forward) ጉባኤ ውጤቶች ክትትል እንዲደረግባቸው አሳስበዋል፡፡ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብትን ጨምሮ ቋሚ መቀመጫና ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራት የሚለውን የአህጉሪቱን ጥያቄ በድጋሚ አረጋግጠዋል። ይህ ስምምነት በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለውን ስልታዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል። 10ኛው የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወቃል፡፡
አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ነው
May 13, 2026 10870
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ተግባር መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት እየተካሄደ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የመንግስታቱ ድርጅት በሁሉም ዘርፎች ቀዳሚ ተግባር አፍሪካን የማድረግ የፖለቲካም ሆነ የሞራል ግዴታ አለበት። አፍሪካ አህጉራዊ ግጭቶችን በማርገብ፣ አህጉራዊ ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናና ሌሎች የሰላምና ጸጥታ ኢኒሼቲቮች አስደናቂ መሆናቸውን ገልጸዋል። አፍሪካ በዓለም ሁለንተናዊ እንቅስቀሴ ላይ ያላት ሚና የጎላ መሆኑን እንገነዘባለን ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ በታሪክና በዓለም ኢ-ፍትሐዊ አሰራር የደረሰባትን በደል ለመቀልበስ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት ባልወጡበት ወቅት የተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት አህጉሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረጋቸው ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ ባልተሳተፈችበት የተቋቋሙ የዓለም አቀፍ ተቋማት ኢ-ፍትሐዊነት አፍሪካን ብዙ አሳጥቷታል ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካ ለመፍታት የተጀመሩ ኢንሼቲቮችን መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት አፍሪካዊ ግጭቶች በአፍሪካ ማዕቀፍ እንዲፈቱ በመሪነት ከመሳተፍ ባለፈ የአፍሪካ ሕብረትን ጥረት እንደሚደግፍ ጠቁመዋል። አፍሪካ በወሳኝ ማዕድናትና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም እንዳላት ገልጸው፤ ሀብቷን እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ የምታቀርብበትን መንገድ መቀየስ ይገባል ብለዋል።
አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም ለማቋቋም ወሰነች
May 13, 2026 10769
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የተዛባውን የዓለም የፋይናንስ ስርዓት የሚያጣጥም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (African Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እየተካሄደ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መድረኩ በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ፣ ዘላቂ ልማት፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አስተዳደርና በተለዋዋጭ ዓለም የአፍሪካ ፈተናዎች ዙሪያ የሚያተኩር ነው። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትን ጨምሮ የዓለም ነባራዊ ሁኔታ በአሕጉሪቱ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚደረግ ጥረት ቢኖርም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሰቃዩበትና የሚሰደዱበት አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል። ይሄውም በአፍሪካ አስተማማኝና ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን በመጥቀስ፣ ከጸጥታ ባለፈ በመልካም አስተዳደር፣ በልማትና የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት አስቻይ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል። በአፍሪካ የልማት ፋይናንስ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን የገለጹት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር፤ ዓለም አቀፉ የፋይናንስ አስተዳደር የአጀንዳ 2063 እና 2030 ግቦችን ለማሳካት እንቅፋት ፈጥሯል ብለዋል። በተለይም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተቋቋሙና አሁንም ያለው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት ለአፍሪካ ፍላጎትና እውነታ ምላሽ የማይሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል። በመሆኑም አፍሪካን ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ስርዓት ጋር ለማጣጣም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (Africa Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን ገልጸዋል። ይሄውም የአፍሪካ ሕብረት በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ሲሰራ ቆይቶ እ.አ.አ በመጪው ሰኔ ወር 2026 በሞሪሼስ በይፋ እንደሚጀመር አስታውቀዋል። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በአፍሪካ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ገልጸው፤ በብዙ ሀገራት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ንሯል፤ በአንዳንድ ሀገራት የነዳጅ ዋጋ ከ100 እስከ 150 በመቶ ጨምሯል ነው ያሉት። የአፍሪካ ሕብረት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በትብብር ሲሰራ መቆየቱን በመጥቀስ፣ የእርስ በርስ ትብብሩን ለማጠናከር በቅርበት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ተቋማት አጋርነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው በመግለጽ፤ በተቋማቱ መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ትብብር ወደፊት ማሻገር ያስፈልጋል ብለዋል።
ሐተታዎች
ላሊበላ፦ ከዓለም አቀፍ ቅርስነት እስከ ባህል ዲፕሎማሲ ማዕከልነት
Jul 9, 2026 890
በሙሴ መለሰ ከ40 በላይ ኤምባሲዎችን ጨምሮ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የተወከሉ ከ70 በላይ ከፍተኛ ዲፕሎማቶችና የልማት አጋሮች ከአፍሪካ እጅግ አስደናቂ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶች መገኛ በሆነችው በታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማ ከሰሞኑ ጉብኝት አድርገዋል። ይህ ታሪካዊ ጉብኝት በዓለም አቀፍ ደረጃ የላሊበላን ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የመንከባከብና የመጠበቅ የጋራ ቃልኪዳንን በድጋሚ ለማደስ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ይህን ዲፕሎማሲያዊ ጉብኝት ያዘጋጀው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ከቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፣ ከአማራ ክልል መንግሥት፣ ከላሊበላ ከተማ አስተዳደር እና በፈረንሳይ መንግሥት ድጋፍ ከሚንቀሳቀሰው “ዘላቂ ላሊበላ” ፕሮጀክት (Sustainable Lalibela Project) ጋር በመሆን ነው። ላሊበላ እ.አ.አ በ1978 በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ መዝገብ ላይ የሰፈሩት ድንቅ አብያተ ክርስቲያናትን ይዛለች። ከስምንት መቶ ዓመታት በፊት (በ13ኛው ክፍለ ዘመን) ከአንድ ወጥ አለት ተፈልፍለው የታነጹት 11ዱ ታሪካዊ አብያተ ክርስቲያናት፤ ዛሬም ድረስ መላውን ዓለም በአድናቆት የሚጎበኛቸው፣ የጥንታዊ ምህንድስና እና የመንፈሳዊነት ጥልቅ መገለጫዎች መሆናቸውን ዩኔስኮ ጉብኝቱን አስመልክቶ ባወጣው ጽሁፍ ላይ አመልክቷል። በጉብኝቱ የተሳተፉት ዲፕሎማቶች እንደ ቤተ መድኃኔዓለም፣ ቤተ ማርያም፣ ቤተ ጊዮርጊስ፣ ቤተ አማኑኤል እና ቤተ ቅዱስ መርቆሬዎስ ያሉትን አብያተ ክርስትያናት ተመልክተዋል። ዲፕሎማቶቹ ላሊበላን “ከዚህ ዓለም ስሪት የላቀ እፁብ ድንቅ ጥበብ” ሲሉ አድናቆታቸውን ገልጸዋል። ቅርሶቹ የጥንታውያኑን አባቶች ድንቅ የምህንድስና ጥበብና የስነ-ህንጻ ልህቀት ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ መሆናቸውን በአድናቆት ተናግረዋል። ዲፕሎማቶቹ ከአብያተ ክርስቲያናቱ ጉብኝት ባሻገር ከነዋሪው፣ ከአካባቢው ማህበረሰብ እና ከሃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት አድርገዋል። ይህ ውይይት ልዑካኑ የላሊበላን ህያው ቅርስ ለመጠበቅ የሚደረጉ ጥረቶችን እና ይህንን ታሪካዊ ስፍራ ለቀጣዩ ትውልድ ለማቆየት እየገጠሙ ያሉ ወቅታዊ ተግዳሮቶችን መፍታት ስለሚቻልበት ሁኔታ በተሻለ መልኩ ለመረዳት አስችሏቸዋል። ጉብኝቱ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በቅርቡ በአካባቢው ከተከሰቱ ፈተናዎች በኋላ፣ የላሊበላን የቱሪዝም እንቅስቃሴ መልሶ ለማገገም እና ለማነቃቃት ትልቅ ዕድል ፈጥሯል። ጎብኚዎቹ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ባህል ሰዎችን በማቀራረብና የእርስ በርስ መግባባትን በማጠናከር ረገድ ስላለው የማይተካ ሚና አጽንኦት ሰጥተዋል። ዩኔስኮ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ እና ከሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ፣ ለፈረንሳይ መንግሥት እና ለጉብኝቱ መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት በሙሉ ምስጋናውን አቅርቧል። ጉብኝቱ የላሊበላን ባህላዊ፣ መንፈሳዊና ኢኮኖሚያዊ ትሩፋቶች እና እሴቶች ባሉበት ለተተኪው ትውልድ ለማሻገር ያለውን ዓለም አቀፍ ቁርጠኝነት ያረጋገጠ መሆኑን ድርጅቱ አመልክቷል። ዩኔስኮ በቅርሱ አያያዝ፣ ጥበቃ እና ቀጣይነት ላለው አስተዳደር ዙሪያ ከኢትዮጵያ መንግስት እና ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ቴክኒካዊ ትብብር እና በአቅም ግንባታ ለበርካታ አስርት አመታት በቅርበት ሲሰራ መቆየቱንና የቅርሱን ዓለም አቀፍ ሀብትነት ጠብቆ ለማቆየት ይህንኑ ተግባሩ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም በጽሁፉ አረጋግጧል።
የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር
Jul 5, 2026 1676
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 28/2018(ኢዜአ):- የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን? ኢትዮጵያ እያከናወነች ነው የገጠር ትራንስፎርሜሽን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጭነት የተጀመረው የከተሞች ኮሪደር ልማት ወደ ገጠሩም ተስፋፍቶ የገጠሩን ማህበረሰብ አኗኗርና አመጋገብ እንዲሁም ጤናን መሰረት በማድረግ የገጠር ኮሪደር ልማት በመከናወን ላይ ይገኛል። ለጤናም ይሁን ለኑሮ ምቹ ባልሆነ ሁኔታ ለዘመናት በተመሳሳይ ሁኔታ የኖረው አርሶና አርብቶ አደሩ አሁን ላይ መሰረታዊ የአኗኗር ለውጥ እያመጣ ይገኛል። በገጠር የኮሪደር ልማት የሰዎችና እንስሳት መኖሪያ እየተለየ፤ በባዮ ጋዝ እና በፀሃይ ብርሃን በሚሰራ የሃይል ምንጭ መብራት ማግኘትና ምግብ መስራት የተቻለበት፤ በጓሮ የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬዎችን መመገብ የሚቻልበት ዘመናዊ አኗኗር ጀምረዋል። የገጠር ትራንስፎርሜሽን የልማት እንቅስቃሴው በጅምር ላይ ቢሆንም በብዙ አካባቢዎች እየተስፋፋ ሞደል መንደሮች እየተበራከቱ መጥተዋል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ምዕራብ አባያ ወረዳ ሀማሳ በ79 ነጥብ 4 ሄክታር መሬት ላይ የተሰራው ሞዴል መንደር የዚሁ ጥረት ማሳያ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በይፋ ተመርቆ ለነዋሪዎች የተላለፈው የሀማሳ ሞዴል መንደር በአንድ ግቢ ውስጥ የንጽህና መጠበቂያ፣ የተደራጀ የቤት እንስሳት ማቆያ፣ በባዮ ጋዝ የሚሰራ የሃይል አቅርቦትን እንዲሁም የተሟላ የጓሮ ግብርናን ማእከል አድርጎ የተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም መንግሥት በተለያዩ የገጠር አካባቢዎች ሞዴል ቤቶችን መስራቱን አስታውሰው ከዚህ በመነሳት ነዋሪዎቹ በራሳቸው ተነሳሽነት የራሳቸውን መኖሪያዎች መገንባት ጀምረዋል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸው ''ንጽህና ካለ ጤና አለ፤ ምግብ ካለ ጤና አለ፤ የተስተካከለ ኮሪደር ካለ ሰላም አለ። እነዚህ ጉዳዮች ከፍተኛ ግምት ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል። የዜጎቻችንን ሕይወት ይቀይራሉ፤ የአኗኗር ዘዬአችንን ያሻሽላሉ፤ ኢትዮጵያን ወደ ምናስበው ከፍታ ወደ ምናስበው መሻሻል የመውሰድ አቅም አላቸው'' ሲሉም ተናግረዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ቀጥሎ በጋሞ ዞን የ'ዮ ሆልዲንግ’ የድንጋይ ከሰል ፋብሪካን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ተመልክተዋል። ከጥቂት ዓመታት በፊት ለኢንዱስትሪ ግብአት የሚሆን የድንጋይ ከሰል ከውጭ ሀገር ለማስገባት እስከ 300 ሚሊዮን ዶላር ውጪ የሚደረግ መሆኑን አንስተዋል። አሁን ላይ በኢትዮጵያ የተለያዩ የከሰል ማምረቻ ፋብሪካዎች ተመርቀው ወደ አገልግሎት መግባታቸውንና ይህም የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ከመሙላት ባለፈ ለውጭ ገበያ የማቅረብ እድል ይፈጥራል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአርባምንጭ ዘመናዊ የኮንፈረንስ ሪዞርት መርቀው ስራ ያስጀመሩ ሲሆን በዶርዜ ሎጅ እና አካባቢው መሰረተ ልማቶችን እንዲሁም የአርባ ምንጭ ከተማን የኮሪደር ልማት፤ በከተማዋ የሚገኘውን ኩሪፍቱ ሪዞርትና ስፓንም ጎብኝተዋል። በሁሉም ዘርፎች ኢትዮጵያ ማከናወኗን አጠናክራ ቀጥላለች፤ እድገትና ማንሰራራቷ ላይቀለበስ ጉዞውን ቀጥሏል። ከዩኔስኮ ምርጥ አምስት ቅርሶች አንዱ የቱሪዝም ሚኒስቴር በዚህ ሳምንት እንዳስታወቀው የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት በዓለማችን ከፍተኛ ተጓዦች ከተመረጡ የዩኔስኮ ምርጥ አምስት ቅርሶች መካከል አንዱ ሆኗል። በዩሮኒውስ የዜና አውታር በተደረገ ጥናት፤ ሁሉንም የዓለም ክፍሎች ያዩ አንጋፋ ተጓዦች ካስቀመጧቸው ተወዳጅ የዩኔስኮ የዓለም ቅርሶች መካከል የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት በግንባር ቀደምትነት ተቀምጧል። በዚሁ ሳምንትም ከአርባ በላይ ሀገራት እና ከአሥር በላይ ዓለም አቀፍ ተቋማት የተወከሉ ዲፕሎማቶች የላሊበላ ከተማና ውቅር አብያተክርስቲያናትን ጎብኝተዋል። ይህ ከፍተኛ የዲፕሎማቶች ልዑክ በቆይታው ከ800 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠሩትን፣ የሕንጻ ጥበብ እና የኢንጂነሪንግ ጥበብ ማስተርፒስ እንዲሁም የሃይማኖትና የታሪክ ሕያው ምስክር የሆኑትን የዓለም ቅርስ የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናትን ጎብኝተዋል። የኢትዮጵያ አስተማማኝ መከታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ በመከላከያና ስትራቴጂክ የደህንነት ጥናት መስክ ያሰለጠናቸውን ተመራቂዎች በዚሁ ሳምንት አስመርቋል። በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ ሰራዊቱ የውስጥ ባንዳና የውጭ ታሪካዊ ጠላቶችን ከንቱ ህልም በማምከን የሀገርን ሉዓላዊነት በአስተማማኝ መልኩ እየጠበቀ ይገኛል ብለዋል። የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄና ቀጣናዊ የትብብር መርህ ለማደናቀፍ ታሪካዊ ጠላቶችና የውስጥ ባንዳዎች ግንባር ፈጥረው እየሰሩ መሆኑን አንስተዋል። ኢትዮጵያን ከባሕር ለማስወጣት የተጠቀሙበት የረጅም ዘመናት ሴራም ዛሬ ላይ “ፅምዶ” በሚል የተሰለፉ አካላት ስለመኖራቸው ተናግረዋል። የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአደረጃጀት ልዩ እና በዘመናዊ ትጥቅ ተጠናክሮ በማንኛውም ሁኔታ ለሀገሩ ክብርና ሉአላዊነት መጠበቅ አስተማማኝ የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል ብለዋል። የ12ኛ ክፍል ፈተና በሳምንቱ በሁሉም የሀገሪቷ አካባቢዎች የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ስኬታማ በሆነ መልኩ ተከናውኗል። በሁሉም አካባቢዎች ተፈታኞች በበይነመረብ (ኦንላይን) እንዲሁም በወረቀት እንደየ ዝግጅቱና ምቹ ሁኔታውን መሰረት በማድረግ ፈተናውን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ። በገጠር ኮሪደር አዲስ የህይወት ምእራፍ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ካፋ ዞን የጊምቦ ወረዳ በተገነባው ሞዴል የገጠር መንደር የሚኖሩ አርሶ አደሮች አዲስ የህይወት ምእራፍ መጀመራቸውን ገልጸዋል። የኤሌክትሪክና ሌሎች አገልግሎቶች የተሟላለት የገጠር ሞዴል መኖሪያ መንደር የአኗኗር ዘይቤያችንን ምቹና ዘመናዊ አድርጎታል ያሉት ነዋሪዎቹ ይህንን ላደረጉ ሁሉ እናመሰግናለን ብለዋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ የተገነባውን የገጠር ሞዴል መኖሪያ መንደር መመረቃቸው ይታወሳል፡፡ የግብርናና ገጠር ሽግግርን እውን በማድረግ የአርሶ አደሩን አኗኗር ለማዘመን እየተሰራ መሆኑን ገልፀው የመብራት፣ የውሃ፣ የመንገድን ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶችን አርሶ አደሩ በአቅራቢያው ማግኘት የሚያስችልና የኢኮኖሚ አቅሙን የሚያሳድጉ መሆናቸውን በወቅቱ ተናግረዋል። በቀጣይም ተግባሩን በማስፋት ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረግን ፍልሰት ለማስቀረት በቁርጠኝነት እንሰራለን ብለዋል። የአረንጓዴ አሻራ በሸገር ከተማ ቡራዩ ክፍለ ከተማ አኔ ዲማ ወረዳ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ሰኣዳ አብዱረህማንና የከተማው ከንቲባ ተሾመ አዱኛ(ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎችም የአከባቢው ማህበረሰብ በተገኙበት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተካሄዷል። የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ሰዓዳ አብዱረህማን በወቅቱ፤ ዛሬ የምንተክላቸው ችግኞች ለሀገራችን ብቻ ሳይሆን ለመላው ዓለም የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ የሚሰጡ ናቸው ብለዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የአየር ንብረት ለውጥን ከመከላከል ባለፈ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ለትውልድ ቀጣይነት አስተማማኝ ዋስትና ጭምር መሆኑን ተናግረዋል። የሸገር ከተማ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር)፤ በሸገር ከተማ የአካባቢውን አረንጓዴነት ለማረጋገጥና ኢኮኖሚውን ለመደገፍ በተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራት በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 19 ነጥብ 1 ሚሊዮን የተለያዩ ዝርያ ያላቸውና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት ተደርጎ ወደ ተግባር ገብተናልም ብለዋል። የባቡር መስመር ጥገና የአዋሽ-ኮምቦልቻ- ሃራ ገበያ ባቡር መስመር ፕሮጀክት ጥገናን በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታውቋል። የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በቅርቡ የጥገና ስራው የተጀመረውን የአዋሽ-ኮምቦልቻ- ሃራ ገበያ የባቡር መስመር ፕሮጀክት የጥገና ሂደት በዚሁ ሳምንት ጎብኝተዋል። ከአዋሽ -ኮምቦልቻ -ሃራ ገበያ 392 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውን ፕሮጀክት በአራት አቅጣጫ የጥገና ሥራው እየተከናወነ መሆኑም ታውቋል። ለልማት ተነሽዎች የተገነቡ ቤቶች በዚሁ ሳምንት የጅማ ከተማ አስተዳደር ለልማት ተነሺዎች ያስገነባውን 300 መኖሪያ ቤቶች መርቆ ማስረከቡን እንመለከታለን። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ሃላፊ ጌቱ ገመቹ፤ በክልሉ በገጠርም ይሁን በከተሞች ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን ገልጸዋል። የጅማ ከተማ ከንቲባ ጠሃ ቀመር፤ በከተማው በርካታ ፕሮጀክቶች በመንግስት እየተከናወኑ እንደሆኑና የተጠናቀቁትም ለአገልግሎት ክፍት እየተደረጉ እንደሚገኙ ገልጸዋል። በከተማዋ በዚህ አመት 80 የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን ጠቅሰው ዛሬ ለልማት ተነሺዎች ተገንብተው የተላለፉ መኖሪያ ቤቶች የዚሁ ጥረት አንድ አካል ናቸው ብለዋል። እነዚህ መኖሪያ ቤቶች ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መሆኑን ጠቁመው ግንባታቸው ተጠናቆ ለ300 አባወራና እማወራዎች ተላልፈዋል ብለዋል።
ለአስም በሽታ አጋላጭ ምክንያቶችና ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች
Jun 29, 2026 4179
የጤና ነገር በዮሐንስ ደርበው ለአስም በሽታ አጋላጭ ምክንያቶችና ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች የድንገተኛ እና ጽኑ ህሙማን ሐኪም ዶክተር ፍጹም አሸብር ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ለአስም ስለሚያጋልጡ መንስኤዎች፣ ምልክቶች፣ መደረግ ስላለበት ጥንቃቄና ሕክምናው አብራርተዋል። • ምንድንነት የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት፤ አስም ለረጅም ጊዜ የሚኖር የመተንፈሻ አካላት ህመም ነው። የመተንፈሻ አካላት በቀላሉ፣ በተለያየ ሁኔታና መጠን መዘጋት ሲያጋጥም ‘አስም’ እንደሚባልም አስረድተዋል። በኢትዮጵያ በገዳይነታቸው ቀዳሚ ከሆኑ አምስት በሽታዎች አንዱ እየተስፋፋ ያለው የጉበት ስብን (ቅባት) እንዴት መከላከል ይቻላል? የኪንታሮት ህመም እንዳይከሰት መከላከል የሚቻልበት ብልኀት አለ? ሾተላይ ምንድነው? እንዴትስ ይከሰታል? ቀድሞ መከላከልስ ይቻላል? • ምልክቶች የትንፋሽ ማጠር፣ የደረት መጨናነቅ እና ሳል ከአስም ምልክቶች መካከል መሆናቸውን ጠቁመዋል። ምልክቶቹም በአብዛኛው በሌሊት ወይም በማለዳ እንደሚባባሱ አስገንዝበዋል። • የአስም ዓይነቶች 1. የአለርጂ አስም፡- ይህ የአስም ዓይነት በአለርጂዎች የሚቀሰቀስ መሆኑን ገልጸዋል። ለምሳሌ አቧራ፣ የአበባ ዱቄት (ዘር)፣ የእንስሳት አይነ ምድር ሽታዎች ለዚህኛው አስም አጋላጭ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። 2. አለርጂ ያልሆነ አስም፡- ይህ ደግሞ በኢንፌክሽን፣ በቀዝቃዛ አየር እንዲሁም በተበከለ አየር የሚነሳ የአስም ዓይነት መሆኑን ነው ያስረዱት። 3. በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ምክንያት የሚመጣ አስም፡- አካላዊ እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት እንዲሁም ከሥራ በኋላ የሚከሰት የአስም ዓይነት መሆኑን ገልጸዋል። 4. ከሥራ ጋር የተያያዘ አስም፡- በሥራ ቦታ ተጋላጭነት ምክንያት የሚቀሰቀስ የአስም ህመም ዓይነት መሆኑን አስረድተዋል። 5. ከባድ የአስም በሽታ፡- ይህኛው የአስም ህመም ዓይነት ለመቆጣጠር አስቸጋሪ እና ባብዛኛው ባዮሎጂካል ሕክምናን የሚፈልግ መሆኑንም ተናግረዋል። • አጋላጭ (ለህመሙ መባባስ) መንስዔዎች አለርጂዎች (የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን፣ የዓየር ብክለት፣ ጭስ)፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ ቀዝቃዛ የዓየር ሁኔታ፣ ጭንቀት እንዲሁም የጄኔቲክ ቅድመ-ዝንባሌ ለአስም ህመም ከሚያጋልጡ እና ህመሙን ከሚያባብሱ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውን አብራርተዋል። • አስም ያለባቸው ሰዎች ምን ዓይነት ጥንቃቄ ያድርጉ? 👉ከአቧራ፣ ጭስ፣ አለርጂዎችዎች መራቅና መጠንቀቅ፤ 👉 በኢንፍሉዌንዛ እና በኒሞኮካል ክትባቶች ወቅታዊ ክትባቶችን መውሰድ፤ 👉 በቀዝቃዛ የዓየር ሁኔታ ሙቀት የሚሰጡ መከላከያ ልብሶችን መልበስ፤ 👉 ጥሩ እንቅልፍ መተኛት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ የተመጣጠነ አመጋገብን ማዘውተር እና መሰል ተግባራት የአስም ህመም እንዳይባባስ ያግዛሉ ብለዋል ባለሙያው። የጡት ካንሰርን ለመከላከል … ሕጻናትን ለውስብስብ ችግር እየዳረገ ያለው የስኳር ህመም (Diabetes) እንደዋዛ የበርካቶችን በር የሚያንኳኳው በዓለም ላይ አሳሳቢ ደረጃ ከደረሱ የህመም ዓይነቶች አንዱ • ሕክምናው የአስም ህመም የማስታገሻ እና የመቆጣጠሪያ (የረዥም ጊዜ) ሕክምናዎች እንዳሉት ያስታወቁት ባለሙያው እንደ ህመሙ ሁኔታ ስለሚወሰን ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ እንደሚገባ መክረዋል። በተለይም ምልክቶቹ በተባባሱበት ወቅት ከፍተኛ የዓየር ትቦ መዘጋት ደረጃ ላይ እንዳይደርስ በጊዜ ሕክምናውን ማግኘት አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት አንስተዋል። ከ 3 እስከ 10 በመቶ ያህሉ የዓለም ሕዝብ በአስም ተጠቂ መሆኑንም ጠቁመዋል። #Ethiopian_News_Agency #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #ኢዜአ #የጤና_ነገር
በኢትዮጵያ በገዳይነታቸው ቀዳሚ ከሆኑ አምስት በሽታዎች አንዱ -የሳምባ ምች (ኒሞኒያ)
Jun 28, 2026 3904
የጤና ነገር በዮሐንስ ደርበው በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ፣ የሳምባ እና የጽኑ ህሙማን ሰብስፔሻሊስት ዶክተር እስማኤል ሙሐመድ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የሳምባ ምች መንስዔዎችን፣ ምልክቶቹን፣ መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎችና ሕክምናው ሳይንሳዊ ገለጻ አድርገዋል። · ምንድንነት እንደ ዶክተር እስማኤል ማብራሪያም፤ የሳምባ ምች (ኒሞኒያ) ማለት ሳምባ ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽ ነው። ይህም በተለያዩ ምክንያቶች እንደሚከሰት ያስረዳሉ። · የሳምባ ምች ከተለመዱት የሳምባ ህመሞች በምን ይለያል? ከተለመዱት የሳምባ ህመሞች (አስም፣ ብሮንካይትስ፣ ሲኦፒዲና ሌሎችም …) የሳምባ ምች እንደሚለይም ነው የሚገልጹት። ይህን ሲያብራሩም፤ የተለመዱት የሳምባ ህመሞች (አስም፣ ብሮንካይትስ፣ ሲኦፒዲና ሌሎች …) የሚያጠቁት የሳምባ አየር ቱቦን መሆኑን ገልጸዋል። በአንጻሩ ኒሞኒያ የሚያጠቃው፤ ካርበንዳይ ኦክሳይድ የሚወጣበትንና ኦክስጅን የሚገባበትን (ጋዝ ኤክስቸንጅ የሚካሄድበትን) የታችኛውን የሳምባ ክፍል መሆኑን አስገንዝበዋል። · መንስዔዎች እንደ ሕክምና ባለሙያው ገላጸ፤ የሳምባ ምች በርካታ መንስዔዎች አሉት። ከእነዚህም መካከል በዋናነት የሳምባ ምች የሚከሰተው በቫይረስ (40 በመቶ ገደማ) እና በባክቴሪያ (እስከ 50 በመቶ ገደማ) መሆኑን ያብራራሉ። በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ቢሆን በፈንገስ (ከ5 በመቶ በታች) ምክንያት የሚከሰት የሳምባ ምች መኖሩን አንስተዋል። ባብዛኛው በቫይረስና በባክቴሪያ ምክንያት የሚከሰት የሳምባ ምች በትንፋሽ አማካኝነት ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍም አረጋግጠዋል ባለሙያው። · ምልክቶቹ ህመሙ ሳምባን እንደሚያጠቃ ያወሱት ባለሙያው፤ ከምልክቶቹ መካከል አንዱ ሳል ማሳል መሆኑን ገልጸዋል። ሳሉ ደረቅ ወይም አክታ ያለው ሊሆን እንደሚችል በመጠቆም፤ የአክታው ቀለምም ነጭ፣ ቢጫ፣ ደም የቀላቀለ ወይም የዛገ ብረት የሚመስል ሊሆን እንደሚችል ያስረዳሉ። በተጨማሪም ይላሉ፤በሁለቱም ወይም በአንዱ በኩል የደረት ውጋት እና የትንፋሽ ማጠር (ለመተንፈስ መቸገር) ከምልክቶቹ መካከል ናቸው። እንዲሁም የሳምባ ምቹ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ፤ ራስን መሳት፣ መረበሽ (ኮንፊውዝ መሆን ነገሮችን ወይም ሁኔታዎች ላይ የመዘባረቅ ነገር) ሊስተዋል እንደሚችል አንስተዋል። · ወደ ሕክምና ተቋም መቼ ይሂዱ? በቀላሉ የማይጠፋ ከ24 እስከ 48 ሠዓት የሚቆይ ከፍተኛ ትኩሳት ሲኖር፣ ከፍተኛ የድካም ስሜት ካለ፣ ከፍተኛ የትንፋሽ ማጠር ሲስተዋል፣ ኮንፊውዝ መሆን (ነገሮችን መዘበራረቅ) ሲኖር፣ ራስን መሳት ካለ እንዲሁም እነዚህ ምልክቶች ዝቅተኛ ቢሆኑ እንኳ ተጓዳኝ ህመሞች ማለትም (የስኳር፣ የኤች አይ ቪ፣ የካንሰር ታካሚ (ኬሞ ቴራፒን ጨምሮ ለካንሰር ህመም መድኃኒት እየወሰዱ ከሆነ)፣ የበሽታ መከላከል ዐቅምን የሚቀንሱ መድኃኒቶች (እንደ ፕሪኒሶሎ ያሉና መሰል) የሚጠቀሙ ከሆነ ወደ ሕክምና በመሄድ ዕርዳታ ማግኘት ይኖርባቸዋል ነው ያሉት። ምክንያቱም እነዚህ ታካሚዎች ቶሎ ካልታከሙ፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሳምባ ምቹ የህመም ደረጃ ከፍ እያለ በመሄድ ለሕይዎት የሚያሰጋበት ሁኔታ ስለሚፈጠር ነው ብለዋል። ·ሳምባ ምችና የአየር ሁኔታ ብርድ (ቀዝቃዛ ዓየር) በራሱ የሳምባ ምች እንደማያመጣ የሚገልጹት ባለሙያው፤ በአንጻሩ የሳምባ ምች እንዲከሰት ምቹ ሁኔታዎችን ሊፈጥር ይችላል ብለዋል። ይህንም በምሳሌ ሲያስረዱ፤ አንድ ሰው ቀዝቃዛ አየር ወደ ውስጥ በሚስብበት ወቅት በሰውነት ውስጥ በሚገኝ የአየር ቱቦ ላይ የሚገኙት ሲሊያ የተሰኙ ስትራክቸሮች ተግባራቸውን በአግባቡ ማከናወን ይሳናቸዋል ብለዋል። የሲሊያ ዋና ተግባርም ከአየር ጋር ወደ ውስጥ የሚገቡትን ቆሻሻ፣ ባክቴሪያ፣ ቫይረስ እና ፈንገስ በመግፋት ከሰውነት እንዲወጣ ማድረግ መሆኑን በማስገንዘብ። በተጨማሪም አንድ ሰው ቀዝቃዛ አየር በሚስብበት ጊዜ የበሽታ መከላከል ሠራዊት ተግባርን እንደሚቀንሰው ነው ያስረዱት። አክለውም በሳይንስ ብርድ መመታት የሚባል ህመም እንደሌለ በመግለጽ፤ ሰዎች በቀዝቃዛ አየር ውስጥ ሲቆዩ በሽታ የመከላከል ዐቅማቸው ስለሚቀንስ ምናልባት ሳምባ ምችን ጨምሮ ለተለያዩ ህመሞች ሊጋለጡ የሚችሉበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል አብራርተዋል። · የሳምባ ህመም እና የሳምባ ምች አንድ ነው ወይስ ይለያያል? በሕክምና ቋንቋው ‘ኒሞኒያ’ የሚባለው በአማርኛ የሳምባ ምች መሆኑን በመግለጽ፤ ህመሙም ሳምባ ላይ በሚከሰት ኢንፌክሽን የሚፈጠር መሆኑን ነው ያስረዱት ዶክተር እስማኤል። በተለየ በሽታ አምጭ ተኅዋስያን ምክንያት የሚከሰተው የሳምባ ህመም ‘ቲበርክሎሲስ’ ወይም የሳምባ ቲቢ (የሳምባ ነቀርሳ) እንደሚባል በመግለጽ በቀላሉ መፈወስ ስለማይቻል መድኃኒቱም ረዘም ላለ ጊዜ (እንደሁኔታው እስከ 6 ወርና ከዚያ በላይ) እንደሚወሰድና ከሳምባ ምች ጋር የማይገናኝ መሆኑን ተናግረዋል። · የተባባሰ ጉንፋን እና የሳምባ ምች ጉንፋን በቫይረስ ኢንፌክሽን የሚከሰት እንደመሆኑ፤ አንድ ሰው በቫይረስ ኢንፌክሽን ሲጠቃ ባክቴሪያዎች ይህን ሁኔታ ተጠቅመው ኢንፌክሽን ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል የሕክምና ባለሙያው። ስለዚህ ቫይረሱ ሳምባ አካባቢ ያሉ የአየር ቱቦዎችን ስለሚያጠቃ ለባክቴሪያ መራባት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራሉ ይላሉ። በዚህም መሠረት አንድ ሰው ጉንፋን ይዞትና እየቆየበት ሲሄድ፤ በተደራቢነት የባክቴሪያ ኒሞኒያ (የሳምባ ምች) ሊያጠቃው እንደሚችል አስረድተዋል። · ለሳምባ ምች በይበልጥ እነማን ተጋላጭ ናቸው? የሳምባ ምች ተጋላጭነት በዕድሜ ክልል ተወስኖ ሊታይ እንደሚችል ገልጸው፤ በዚህም መሠረት ከ65 ዓመት በላይ እና ከ5 ዓመት በታች ያሉ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የተለያዩ ህመሞች ያሉባቸው (የስኳር፣ የኤች አይ ቪ እና የካንሰር ታካሚዎች እንዲሁም በሽታ የመከላከል ዐቅም ለመቀነስ መድኃኒት የሚወስዱ) ከሌላው ሕብረተሰብ አንጻር ለሳምባ ምች ተጋላጭ ናቸው ብለዋል። · የአሳሳቢነት ሁኔታ የሳምባ ምች አሳሳቢነት ከፍተኛ መሆኑን የሕክምና ባለሙያው አሃዛዊ ማስረጃዎችን በመጥቀስ አስረድተዋል። ለምሳሌ በኢትዮጵያ በተለይም በገዳይነታቸው ደረጃ ከሚጠቀሱት አምስት በሽታዎች መካከል እንደሚመደብ አንስተዋል። የሳምባ ምች በአብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል ሊከሰት የሚችል መሆኑን በመግለጽ፤ የጥናቶች ውጤቶች እንደሚያመላክቱት በኢትዮጵያ ከ25 እስከ 30 በመቶ የሚደርሰው የማኅበረሰብ ክፍል በሳምባ ምች ሊጠቃ ይችላል ብለዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃም ከ20 እስከ 25 በመቶ የሚደርሰው የዓለም ሕዝብ በሳምባ ምች የመጠቃት ዕድል እንዳለው አመላክተዋል። የሞት ምክንያት ከመሆን አንጻርም ይላሉ ዶክተር እስማኤል፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከአምስት ዓመት በታች በሆኑ ሕጻናት ሞት ውስጥ እስከ 25 በመቶ የሚሆነው ምክንያቱ የሳምባ ምች መሆኑን ይናገራሉ። በተመሳሳይ በዓለም ላይ ከ18 እስከ 20 በመቶ ያህሉ የሞት ምክንያት የሳምባ ምች ነው ይላሉ። · የሳምባ ምችን መከላከል ይቻላል? ዶክተር እስማኤል እንዳረጋገጡት፤ የሳምባ ምችን አስቀድሞ መከላከል ይቻላል። ዋናው መከላከያውም ክትባት መሆኑን በመግለጽ። በተለይም ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ሕጻናት የሳምባ ምች ክትባት በመከተብ ለበሽታው እንዳይጋለጡ መካለከል ይቻላል ብለዋል። ተጓዳኝ ህመም ያለባቸው፣ ከ65 ዓመት በላይ የሆናቸው እንዲሁም ቋሚ የሳንባ ህመም ያለባቸው ክትባቱን በመውሰድ ኒሞኒያን መከላከል እንደሚችሉ አስረድተዋል። በተጨማሪም በምግብ እጥረት ሊከሰት የሚችልን የሳምባ ምች የአመጋገብ ሥነ-ሥርዓትን በማስተካከል አስቀድሞ መከላከል እንደሚቻል አመላክተዋል። በትንፋሽ ስለሚተላለፍ በሳምባ ምች ከተጠቃ ሰው ጋር ንክኪ ባለማድረግ፤ ማስክ በመጠቀም፣ በተፋፈገ (በጣም በተጨናነቅ) ሁኔታ ውስጥ ባለመሆን ተስፋፊነቱን መከላከል እንደሚቻልም ጠቁመዋል። · ሕክምና የሳምባ ምች እንደሚታከም ያስገነዘቡት ዶክተር እስማኤል፤ እንደ በሽታው ደረጃ የሚወሰን ሆኖ ሕክምናው ከተመላላሽ በሆስፒታል ተኝቶ እስከ መታከም ሊደርስ እንደሚችል አስረድተዋል። በዚህም መሠረት የህመሙ ደረጃ ከፍተኛ ካልሆነ በተመላላሽ፤ ከፍተኛ ከሆነ ከ5 እስከ 7 አንዳንዴም ከዚያ በላይ ለሆኑ ቀናት እንደሚታከም አክለዋል። ምልክቶች እንደታዩ ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ አዋጭና ቶሎ ለመፈወስ እንደሚረዳ አስገንዝበዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #የጤና_ነገር
ትንታኔዎች
ምክክር-ለኢትዮጵያ ብሩህ ነገ
Jul 3, 2026 2613
ምክክር-ለኢትዮጵያ ብሩህ ነገ (በቀደሰ ተክሌ ከኢዜአ-ሚዛን አማን ቅርንጫፍ) ጥቃቅን ችግሮች እያደጉ ሔደው ሀገር የማፍረስ አደጋን ከመደቀናቸው በፊት ከሥር መሠረቱ ማስተካከያ ማድረግ ብቸኛው መንገድ ሁሉን አካታች ሀገራዊ ምክክርን ማካሔድ ነው። በዚህም ራሳቸውን ከመጥፋት ታድገው ሀገር በሚል ስያሜ ሕልውናቸውን ያቆዩ ሀገራት አሉ። ከእነዚህም መካከል በአካታች ምክክር ከግጭት ወደ ዘላቂ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የተሸጋገሩትን ማንሳት ይቻላል። ለአብነት የቱኒዚያ ሀገራዊ ምክክር በዓለም ላይ ካሉ የቅርብ ጊዜ ስኬታማ ተሞክሮዎች ቀዳሚው ነው። እ.አ.አ በ2011 የ"አረብ አብዮት" መነሻ የነበረችው ቱኒዚያ፣ የፖለቲካ መሪዎች መገዳደል እና ከፍተኛ አለመረጋጋት ገጥሟት ነበር። አራት የሲቪክ ማህበራት (የሰራተኞች ማህበር፣ የጠበቆች ማህበር፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና የነጋዴዎች ማህበር) በጋራ በመሆን "የቱኒዚያ ብሔራዊ ምክክር ኳርትት አቋቋሙ። ፖለቲከኞችን አስገድደው በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲቀመጡ አደረጉ። በዚህም ሳቢያ ሀገሪቱ አዲስ እና ሁሉን አቀፍ ህገ-መንግስት ቀረጸች፤ ሰላማዊ ምርጫ ተካሄደ፤ ሀገሪቱ ወደ ለየለት የእርስ በእርስ ጦርነት ከመግባት ዳነች። ይህንን ምክክር የመሩት አራት ድርጅቶችም እ.አ.አ በ2015 የኖቤል የሰላም ሽልማትን አግኝተዋል። ደቡብ አፍሪካም ለዘመናት የዘለቀውን የዘረኝነት እና የአፓርታይድ ስርዓት ያቆመችው በጦርነት ሳይሆን በሁሉን አካታች ብሔራዊ ምክክር ነው። በኔልሰን ማንዴላ የሚመራው ኤ.ኤን.ሲ እና የነጮች ገዥ ፓርቲ በጥላቻ ፋንታ "ለነገዋ ሀገር" በሚል ይቅርታን እና ድርድርን አስቀደሙ። በምክክሩ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና የነገዶች ተወካዮች በሙሉ ተሳትፈዋል። ያለምንም ደም መፋሰስ የስልጣን ሽግግር ተደረገ፤ በአለም ላይ እጅግ ተራማጅ የሚባል አዲስ ህገ-መንግስት ተቀረጸ፤ "የእውነትና የእርቅ ኮሚሽን" በማቋቋም ያለፈው ቁስል እንዲሻር ተደረገ። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሁዋን ማኑኤል ሳንቶስን የኖቤል ተሸላሚነት ያበቃው ምክክር የተካሄደው በኮሎምቢያ መንግስት እና በኤፍ.ኤ.አር.ሲ አማፂያን መካከል ለአምስት አስርት ዓመታት የዘለቀው እና ከ200 ሺህ በላይ ዜጎች ላለቁበት ጦርነት እልባትን ሰጥቷል። ምክክሩ ከሀገር ውጭ (በኩባ እና ኖርዌይ) በተደረጉ ድርድሮች የተደገፈ ሲሆን፣ ዋናው ትኩረቱ ግን የአርሶ አደሩን የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ፣ የፖለቲካ ተሳትፎ እና የአደንዛዥ ዕፅ ንግድን ማቆም ላይ ያተኮረ ነበር አማፂያኑ ሙሉ በሙሉ ጦርነቱን አቁመው ነፍጣቸውን አስረክበው፤ ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲነት በመቀየር ሰላማዊ ትግላቸውን እንዲቀጥሉ ያስቻለ ነው። ኢትዮጵያም ዛሬ ለዘመናት ሲንከባለል የመጣን ዕዳ በጫንቃዋ ላይ ተሸክማ ቆማ ያንን አሳራፊ መድኃኒት ሽታለች። በዘመነኛው ዓለም ውስጥ ሆና በትላንት በሽታ ትታመማለች። የቀደሙት የጣሉት የስህተት እርሾ ዛሬም ከሊጥ ጋር እየተቦካ የኮመጠጠ የአኗኗር ሥርዓትን ትውልዱ እንዲጋፈጥ ምክንያት መሆን ከጀመረ ከራርሟል። ይህም የማይነጋ ሌሊት መስሎ ታይቶ ብዙዎችን ለቀቢጸ-ተስፋ ዳርጓል። የሰላም በር ዘግቶ ሰላም መፈለግ፣ መክፈቻ ቁልፍ በእጅ ይዞ ወደ ሌላ ማማተር ሆነና ነገሩ፤ ችግሩ ከነግሳንግሱ እያደገ ጥቁር ደመናን በሀገሬ ሰማይ ላይ ለመጋረድ አቅሙን ተጠቀመ። ሆኖም እንደተባለው የማይነጋ ሌሊት፣ የማይፈታ ሕልም የለም። "ፈጣሪም ሀገርን ያለ አንዳች አይተውም" ነውና ቃሉ፤ የተስፋ ብርሃን በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር ፈነጠቀ። ወደ ውስጥ የሚመለከት፣ የራስ ማንነትን በኢትዮጵያዊ ቀለም የሚፈትሽ፣ ችግርን ሳይሆን መፍትሔን አነፍንፎ ገሃድ የሚያወጣ፣ ሀገር በቀል ዕውቀትን ያከበረና መልካም የሆኑ ነባር እሴቶችን ለችግሮቻችን ወጌሻ ያደረገ የለውጥ ተስፋ ከተፍ አለ። የመጋቢት ብስራት ኢትዮጵያን ወደ ፍካት ለመለወጥ በሀገር ፍቅር ስሜት አዳዲስ የሰላም መንገዶችን መክፈት ጀምሯል። ከመገፋፋት ይልቅ መደመርን፣ ከመካሰስም ይቅርታን የሚያስቀድመው የመደመር መንግሥት ሁሉንም ወገን አሸናፊ የሚያደርግ ሀሳብ ይዞ የምክክር ኮሚሽንን በማቋቋሙ አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያስብል ተግባር በኢትዮጵያ ተወጠነ። በፖለቲካ እሳቤም ሆነ በሐሰት ትርክት አልያም የማያግባባ የትኛውንም ጉዳይ በመምዘዝ አኩርፎ ነፍጥ ማንገብን ልምድ ያደረገ የፖለቲካ ሥርዓት ባለበት፤ በአንጻሩ አቅም ኖሮት ሥልጣን የጨበጠ በሀሳብ የተቃረነውን በሚኮንንበትና ቀፍድዶ በወህኒ ቤት በሚያሰቃይባት ምድር በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ መመካከር ትልቅ ትርጉም አለው። ይህ በደማቅ የታሪክ ቀለም የሚመዘገብ ክስተትም ነው። ምክክር በባህላችን አብሮን የኖረ የማንነታችን አካል የሆነ እሴታችን ቢሆንም ለፖለቲካው ሜዳ ግን እንግዳ ነገር ነውና። ጠላቶቻችን የኢትዮጵያን ሰላምና ዕድገት ማየት አይሹምና ሂደቱን ለማደናቀፍ ጥረዋል። በዚህም የመለወጥ መንገዳችንን ለመዝጋት ብዙ ጉድጓዶችን ምሰዋል። ጉድጓድ ለማዘጋጀት ከሩቅ ያመጡት ቁሳቁስ የለም፤ ከራሳችን ጋር አብሮ ባደገው የዘርኝነት፣ የጽንፈኝነትና አክራሪነት ገሶ (ትልቅ የጉድጓድ መቆፈሪያ) ነው እንጂ። በተለይ የኢትዮጵያ ጌጥ የሆነው ብዝኃ-ብሔር እና ሃይማኖት ብዙ ሳይደክሙ ያጠመዷቸው ፈጣን ውጤት የሚያስገኙላቸው ወጥመዶች ነበሩ። የወል ትርክት በሐሰተኛ ትረካ ተሞልቶ ለብዙዎች ሕይወት መጥፋት መንስኤ ሆነ። ጠንካራዋ ሀገር ኢትዮጵያ ግን መሠረቶቿ ዓለት ላይ ስለሆኑ ይህ ሁሉ የጥፋት ጎርፍና ነፋስ ሊያነቃንቃት አልቻለም። ይልቁንም በጽናት ቆማ ወጀብ ማዕበሉን ጸጥ የሚያደርግ ሀገርኛ መሣሪያ ታጥቃለች - የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን! በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር እና ተመራማሪ አማረ ፈንታው (ዶ/ር) እንደሚሉት፤ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን መቋቋምና በአግባቡ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን አጠናቆ አጀንዳ መለየት መቻሉ የኢትዮጵያውያንን የሥነ-ልቦና እና የሞራል ከፍታ ማሳያ ነው። ለዚህም አመክንዮ ሲያስቀምጡ፤ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለችግር መፍቻ ወደ ጠረጴዛ ሳይሆን ወደ ጫካ የሚሮጥ የፖለቲካ ሥርዓትን ነው ስታስተናግድ የቆየችው ብለዋል። ዛሬ ላይ ግን ያ ልክ አለመሆኑን የተረዳ ትውልድ በስብዕና ሞራል ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖን አሳድሮ በጥይት ሳይሆን በሀሳብ ለማሸነፍ ራሱን አዘጋጅቷል። በጦር ግንባር ሳይሆን በጠረጴዛ ዙሪያ መፍትሔ ሊያገኝ ከራሱ ጋር ተስማምቷል። ይህ የመማርና የማደግ ውጤት ነው። የትናንት አካሔድ ሞትና ችግርን እንጂ ብልጽግናን አላተረፈም። መመካከር በእጃችን የነበረ አውጥተን ያልተጠቀምንበት ሀብታችን ነው። እንደ ተፈጥሮው ሁሉ እሴታችን የተሸፈነበት አቧራ በምክክር ተራግፎ በአብሮነት እና ዘላቂ ሰላም የምንደምቅባትን ጀንበር ልናይ ንጋት ላይ ተቃርበናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ትልቅ ተስፋ የጣለበት ጉዳይና ውጤቱን አጥብቆ የሻተበት አጀንዳ ምን ይሆን ተብሎ ቢጠና፤ "የምክክር ኮሚሽን ወደ ተግባር መግባት" ከሚለው በላይ ሌላ አጀንዳ ይኖራል ብሎ በልበ-ሙሉነት መግለጽ አይቻልም። ያለ ልዩነት ሁሉም ደግፎ በብርቱ ናፈቀው። የጥንት የአያት ቅድመ-አያቱ ወግ ነባርና አዲስ ሳይሆንበት በብርሃን ፍጥነት ዓላማውን ተረዳ። ተረድቶም ሳይቀር ተስፋውን ወደ ሚጨበጥ ውጤት ለመቀየር ባለው አቅም ሁሉ ለመደገፍ ተረባረበ። ዕድል የገጠመውም በቁርጠኝነት ሂደቱ ላይ ተሳተፈ። የዚህ ድምር ውጤት የምክክር ኮሚሽኑ ለኢትዮጵያ የነበሩ አለመግባባቶች ቁልፍ መፍቻዎች ናቸው ያላቸውን 8 ዋና ዋና የምክክር አጀንዳዎችን በስኬት ለመለየት አበቃው። የምክክሩ አጀንዳ ልየታ ሥርዓት ከአጀንዳ መለየት ያለፈ ትርጉም ያለው ነው። ስኬታማ የተቋም ግንባታ አንጸባራቂ ክስተት ጭምር እንጂ። አካታችነትን ባረጋገጠ መልኩ የሁሉንም አካባቢ ወግ፣ ባህልና ሥርዓት ተገንዝቦ ለሀገር የሚሆን አጀንዳ በስኬት መሰብሰብ የተቋማዊ ብቃት ማሳያ ነው። ይህም ኢትዮጵያ ማድረግ የምትችል መሆኗን ገላጭ ሌላኛው የድል ገጽ ቢባል ግነት አይሆንም። አጀንዳዎቹ የኢትዮጵያን መሠረታዊ ችግሮች መፍታት የሚያስችሉ ናቸው። ኃይል የተሞላበት የፖለቲካ ሥርዓትን በመገርሰስ ወደ ዴሞክራሲያዊ እና የተሟላ የሰላም ደሴት የሚያሸጋግር አጋጣሚ እንደሚሆንም ዶ/ር አማረ ይገልጻሉ። ምክክሩ ለኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ ወሳኝ ምዕራፍ ሲሆን በታሪክ ድርሳን የምናስቀምጠውና ወደፊት መጪው ትውልድ የሚያወሳው ኩነት ነው ብለዋል። መምህር ቢመርቅ በርሁን በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር ናቸው። እርሳቸው የምክክር ኮሚሽንን ተግባር ለኢትዮጵያ ያለውን መልካም ዕድልነት ሲገልጡ፤ ስር የሰደዱ ችግሮችን ከሥር የሚነቅል መሣሪያ ብለውታል። ከግለሰቦች የፖለቲካ ትርክት ተላቆ ወደ ተቋማዊ አሠራር መሸጋገሪያ ድልድይም እንደሆነ እንዲሁ። ኢትዮጵያ በበርካታ ነጠላ ትርክቶች ለሰላም እጦት ተዳርጋለች፣ በግለሰቦች ግላዊ ፍላጎት ብዙዎች ሕይወታቸውን ገብረዋል። ይህ የመጠፋፋት ሰንሰለት ይበጠስ ዘንድ ምክክሩ አስፈላጊ ነው። ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተግባራት ስኬት አካታችነት ትልቅ አቅም እንደሆነውም መምህር ቢመርቅ ያነሳሉ። በኮሚሽኑ የተሠራው የአጀንዳ ማሰባሰብና ልየታ እንዲሁም የምክክሩ ተሳታፊ መረጣ ሂደት በተማሩ ኃይሎች አልያም በፖለቲካ ልሂቃን ላይ ብቻ መሠረት ያደረገ አይደለም። በታችኛውም እርከን ወርዶ አርሶ አደሩን፣ አካል ጉዳተኛውንና ሌሎችንም ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችን የጉዳዩ ባለቤቶች ናችሁ ብሎ ማሳተፉ በጎ ውጤት አመልካች ቅድመ-ሂደት ነበር ነው ያሉት። የአካታችነቱ ወሰን መስፋት ሰፊውን የማኅበረሰብ ጥያቄ ይዞ ለመነሳት አስችሎታል። የሁሉም ጥያቄ በስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ማለትም፦ በሀገር ግንባታ፣ በመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ እንዲሁም በፖለቲካ ሥርዓት፣ በፖለቲካ ውክልና እና በምርጫ ሥርዓት፣ በፌዴራል ከተሞች (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የድሬዳዋ አስተዳደር) ጉዳይ፣ በሃይማኖት ጉዳዮች፣ በተቋማት ግንባታ፣ በሕግ የበላይነት እና በሰብዓዊ መብቶች፣ በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም በአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ጉዳዮች፣ በሙስና እና መልካም አስተዳደር እንዲሁም በሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ሥር ተጠልሏል። እነዚህ አጀንዳዎች በአንድም በሌላም የመከፋፈል፣ በጎሪጥ የመተያየትና የጥርጣሬ መንፈስን በመንዛት ዜጎች እርስ በእርስ ከመተማመንና በአብሮነት ከመቀጠል ይልቅ "የኔ" የሚል አጥር ውስጥ እንዲገቡ ያደረጉ ናቸው። በሌላ በኩል "ተበደልኩ"ን ወልደው ኩርፊያን አስፍተዋል። ይህም በአንድ ወገን ሳይሆን ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ በተለያየ መጠን የሚንጸባረቅ ችግር ነው። አሁን የመጣ ሳይሆን ትናንት የነበረ፣ ለዛሬ የተዘራና እንክርዳድ እያበቀለ ያለ የግጭት ዘር ነው። ሀገራዊ የሆኑ የፖለቲካ እና ማኅበራዊ ጉዳዮችን የአስተዳደር ሥርዓት ፈትሾ እውነትን እና ለነገ የሚበጀውን የወል ትርክት በሕዝብ ይሁንታ ሊያጸና ቀጠሮ የያዘው ኮሚሽኑ፤ በሁሉም ዜጎች ትብብር ሀገራዊ ድልን ያጎናጽፋል። ሰላምና ስኬት ለኢትዮጵያችን! አበቃሁ!!
በመደመር የተቃኘ ኢትዮጵያን የሚመጥን የከተሜነት ጉዞ
Jul 3, 2026 2428
በዮሐንስ ደርበው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ጥቅምት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተገኙ ጊዜ፤ የኮሪደር ልማት ዓላማ ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማ መገንባት መሆኑን ገልጸዋል። ከተማ ሲለማ ደግሞ ለነዋሪም ሆነ ለጎብኚ፤ ለዐይንም፣ ለጤናም ለእንቅስቃሴም ውበትና ምቾት ማላበሱ አይካድም። ትናንትን ከዛሬና ከነገ ጋር ማስተሣሠር የኢትዮጵያ የማከናወን ዐቅም ማሳያ ወደ መግባባት መሸጋገሪያው ድልድይ! የኮሪደር ልማት ጽዱ ከተሞችን ይሠራል፤ከትራንስፖርት፣ ከትራፊክ ምልክቶች፣ ከብስክሌትና እግረኛ መንገድ ደኅንነት ጋርም ተጣጥሞ ተሠርቷል። በዚህ ዐውድ የኮሪደር ልማት ውበትም ምቾትም ነው። መሠረተ-ልማት ተጠብቆ ለረጅም ጊዜ እንዲጠቅምም የኮሪደር ልማት ሚና የላቀ ነው። ኢትዮጵያ በከተሞቿ እና ገጠራማ አካባቢዎቿ የኮሪደር ልማት እያከናወነች ነው። ይህ በኢትዮጵያ ከውበት በላይ ነው። · ማኅበራዊ መሥተጋብርን በመጠገን፡- ኢትዮጵያውያን ከሚታወቁባቸው አንዱ በየዐውዱ የሚገለጠው ጥብቅ ማኅበራዊ መሥተጋብራቸው ነው። በጋራ መንቀሳቀስ፣ መጫወት፣ ከቤት ወጣ ብለው መመካከር የኑሯቸው አካል ነው። ይሁን እንጂ በተለይም ከተሜው ከወዳጅ ጋር በኅብረት በእግር ወይም በብስክሌት ለመንቀሳቀስ፣ አረፍ ብሎ የሚያወጋበት በቂ አረንጓዴ ስፍራና ፓርኮች ባለመኖራቸው ማኅበራዊ መሥተጋብሩ እየላላ የመጣ ይመስላል። አሁን የኮሪደር ልማት በደረሰባቸው ከተሞች፤ሰዎች ሲያሻቸው በእግር አሊያም በብስክሌት ከወዳጆቻቸው ጋር የልባቸውን እያወጉ ለመንቀሳቀስ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። ሰዎች በእንቅስቃሴያቸው መሐል ዐረፍ ማለት ቢሹም ችግር የለም፤ አሁን እንደ ድሮ አይደለምና። አረንጓዴ መናፈሻ ስፍራ ፍለጋ ከከተማ መውጣት አያሻም። በሌላ በኩል ወጣቶች እና ሕጻናት ኳስ የሚጫወቱበት ስፍራ መመቻቸቱ ጤናን ከመጠበቅ ባሻገር፤ ማኅበራዊ መሥተጋብራቸውን ያጠናክራል። · ጤናማ አከባቢን በመፍጠር፡- የኮሪደር ልማት ለሰው ልጆች ከቸራቸው ጥቅሞች አንዱ፤ ጤናማ ከባቢን መፍጠር ነው። በተለይም በደካማ የፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ለሚታሙ ከተሞች የኮሪደር ልማት ሁነኛ መፍትሔ ሆኗል። ይህ ደግሞ በቀጥታ ከነዋሪዎች ጤና ጋር ይገናኛል። ደግሞም በንጹህ አካባቢ የመኖር መብትን ማስጠበቅ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ በኮሪደር ልማት ሰፋፊ መንገድ ከመሥራት ባለፈ ታዳጊዎች እግር ኳስ የሚጫወቱባቸው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና የእግረኛ መንገዶች ተሠርተዋል ያሉትም ለዚሁ ነው። · በሥራ ዕድል ፈጠራ፡- የኮሪደር ልማት የዘመቻ ሥራ አይደለም።በትንሹ በአንድ ከተማ ወይም አካባቢ ተጀምሮ እየሰፋ ይቀጥላል። በዚህ ሂደት የሚፈጠረውን የሥራ ዕድል ማሰብ አያዳግትም። እንዲሁም የኮሪደር ልማት ሥራዎች ሲከናወኑ፤ ለሥራ ዕድል ፈጠራ የሚያገለግሉ የመኪና ማቆሚያ፣ ሱቆች እና መሰል ለንግድ ተግባራት እንዲበጁ ተደርገው ነው። የኮሪደር ልማት ከከተሜነት ዕድገት ጋር የተሣሠረ ልማት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መናገራቸው ይታወሳል። · በገጽታ ግንባታ ረገድ፡- ከተሞች ሲጸዱና ምቹ ሲሆኑ በዓለም ዘንድ መታወቂያ ይሆናሉ። ነዋሪም በኩራት ስለአካባቢው በየሄደበት አምባሳደር ሆኖ ይመሠክራል። ቱሪስቶችንም ይስባሉ። የቆይታ ጊዜያቸውንም ለማራዘም ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረክታሉ። ዓለም አቀፍ፣ አኅጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ጉባዔዎች እንዲካሄድባቸውም እንዲመረጡ ያስችላል። በከተሞች ከሚሠራው የኮሪደር ልማት ባሻገር፤ የገጠር ኮሪደር ልማት በውጤታማነት እየተሠራ ነው። ይህም ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ፍትሐዊ መሰረተ-ልማት ለዜጎች መቅረቡን ያሳያል። ኮሪደር ልማት ኢትዮጵያውያን የተሻለ ኑሮ ይገባቸዋል በሚል የተጀመረ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ተናግረዋል። የተሟላ ብልጽግና የምናረጋግጠው በዚሁ መንገድ ነውም ብለዋል። የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገውን ፍልሰት በመቀነስ የተመጣጠነ ዕድገት በሁሉም አካባቢ ለማምጣት የገጠር ኮሪደር ልማት መጠናከር ጠቀሜታው የጎላ ነው። የገጠር ኮሪደር ልማት ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ሥነ-ምኅዳራዊ ፋይዳን ጨምሮ ብዙ ጥቅም አለው፤ ይህም ዘላቂ ልማትና የተረጋጋ ኅብረተሰብ ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። የከተሞች መዋብና ምቹ መሆን ለነዋሪው ነው፤ በቀጥታ ተጠቃሚውም ሕዝቡ። ስለዚህ መንግሥት ከሚያከናውናቸው በተጨማሪ ባለሃብቱ፣የመንግሥትም ሆኑ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ኅብረተሰቡ የኮሪደር ልማትን በተነሳሽነት ለማስፋፋት መትጋት ይጠበቅበታል።
ትላንትን ከዛሬና ከነገ ጋር ማስተሳሰር - የመደመር መንግስት እይታ በቱሪዝም
Jul 1, 2026 2462
በዮሐንስ ደርበው ቱሪዝም ልዩ ትኩረት የተሰጠው በመላው ዓለም ከፍተኛ ገንዘብ የሚንቀሳቀስበት ዘርፍ ነው። ይህ ዘርፍ በአህጉራችን አፍሪካም ከፍተኛ ገቢ የሚያገኙበት ሃገራት እንዳሉ ይታወቃል። ቱሪዝም ከገቢነት ከኢኮኖሚያዊ እቅምነት ባለፈ ትውልድን ያስተሳስራል ብሄራዊ ትርክትን ለመገንባትም ያግዛል ። ትላንትን ከዛሬ ዛሬንም ከነገ ጋር የሚያስተሳስር ነው። “ሀገራችን ከቱሪዝም ልታገኛቸው የምትችላቸውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና አካባቢያዊ ጥቅሞች ሁሉ ከቀረው ዓለም ጋር ተወዳድራ እንድታገኝ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጎብኚ ወደ ሀገራችን መሳብ አለብን። ለዚህም የተለያዩ ስልታዊ መላዎች ነድፈን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን (የመደመር መንግሥት 273)። የቱሪዝም ኢንዱስትሪ የለውጡ መንግሥት እመርታዎችን ካስመዘገበባቸው ዘርፎች አንዱ ነው። መንግስት ከአምሥቱ የትኩረት መስኮች አንዱ አንድርጎም በጥናት፣ አካባቢያዊ ፀጋን ዐውቆና ለይቶ በተደመረ ዐቅም ባከናወናቸው ሥራዎች በገበታ ለሸገር፣ በገበታ ለሀገር፣ በገበታ ለትውልድ፣ በኮሪደር ልማት፣ በወንዝ እና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት እሠየው ያሰኙ ተግባራት አከናውኗል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው ከእንጦጦ - ቀበና የተከናወነው የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትም ለጎብኚም ለነዋሪም ምቹ ከባቢን በመፍጠር ረገድ እየተደረገ ያለውን ትጋት ያስረዳል። ምረቃውን ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባጋራው መረጃ፤ “መቆሸሽ እኛ አይገባንም፣ መጠልሸት እኛ አይገባንም፣ ማነስ እኛ አይገባንም! ሠርተን እንደምንችል ማሳየት ያስፈልጋል” ሲል የሥራውን ማራኪነትና ውበት ገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በዚሁ ወቅት፤ የተሰጠንን ሕዝባዊ አደራ በታማኝነት፣ በጽኑ ትጋት እና በቅንነት በመፈጸም የዜጎቻችንን የኑሮ ጥራት ለማሻሻልና መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የጀመርነውን ጉዞ አበክረን እንቀጥላለን ሲሉ በቀጣይ ካለፈው የበለጠ እንደሚሠራ አመላክተዋል። ገንዘብን፣ ዕውቀትን፣ ጉልበትን፣ ሐሳብን፣ የአመራር ብቃትን ስንደምር የሚከሰተው ነገር እንደዚህ ያለው ውበት ይሆናል ሲሉም አስገንዝበዋል። በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው (ገጽ 256) ላይም፤ “የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ሀገራት በዘመናቸው ሁሉ የሠሩትንና ተፈጥሮ ያደለቻቸውን መልካም ገጽታ በኩራት ለዓለም የሚያስተዋውቁበት፣ ‘ሀገሬ ይሄንን ትመስላለች’ የሚሉበት መድረክ ነው። ሀገርን በሚያኮራና ለሌሎች ለመጋበዝ በማያሳፍር መልኩ መገንባት፣ ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ መሠረቱ ነው።” ያሉትም የበለጸገች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ በቁጭት መነሳታቸውን ይገልጻል። ነገን ዛሬ እየሠራች ያለችው ኢትዮጵያ ካላት ላይ ሳትነፍግ የገንዘብም ሆነ የሰው ኃብቷን ቱሪዝም ላይ ስታውል፤ አንድም የኢንዱስትሪውን ዐዋጭነት ብሎም የዜጎቿን በየዘርፉ ዘላቂ ተጠቃሚነት በመገንዘብ ነው። እዚህ ላይ ለሀገር ገቢ በማስገኘት እና የሥራ ዕድል በመፍጠር ዘርፉ የሚያበረክተውን ጥቅም ማጤን ይገባል። በአዲስ አበባ ከተከናወኑ ቁልፍ የቱሪዝም ልማቶች መከካከል፤ የመስቀል ዐደባባይ ቅርስን ማንበርና ማዘመን፣ ከአዲስ አበባ ልማት ጋር ተሣሥሮ የተገነባው የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ በአዲስ መልክ የታደሠው ብሔራዊ ቤተ-መንግሥት፣ የአምሥቱ ዕውቀት ተኮር ማዕከላት (አብርኾት ቤተ-መጻሕፍት፣ ሳይንስ ሙዝየም፣ የሀገር በቀል ዕጽዋት ማሳያ፣ የአንድነት ቤተ-መዛግብት እና የማዕድን ሙዝየም) ግንባታ፣ የአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ማዕከል እና ሌሎችም ይገኙበታል። በሌላ በኩል ደግሞ ጎብኚዎች የሚያርፉበት ሎጂና ሆቴሎች ግንባታም በስፋት እየተከናወነ ይገኛል። ገበታ ለሸገር ብሎ ከአዲስ አበባ የተነሳው የቱሪዝም ልማት በገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ ወደ ክልሎች ተስፋፍቶ ደረጃቸውን የጠበቁ ሎጂዎች እንዲገነቡ አስችሏል። የተገነቡት ሎጂዎች ደግሞ ለጎብኚዎቹ ምቾትን የሚያስጠብቁ መሠረተ-ልማቶችን ስበዋል። በርካታ ጎብኚ መሳብና ገቢን ማሳደግ፣ በጎ ገጽታን መሸጥ፣ ለዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር፣ የበለጸገች ኢትዮጵያ ዕውን ማድረግ እየተከናወኑ ላሉ ተግባራት ሁሉ ግቦች ናቸው። መንግሥት ዕምቅ የጎብኚዎች መስኅብ ዐቅም የሆኑና አቧራ ለብሰው የተደበቁትን ፀጋዎች ውበታቸውን ገላልጦ እያሳዬ ያለውም ለዚህ ነው። ቱሪዝም በቀጥታ ዜጎች (ሰዎች) የሚጠቀሙበት ኢንዱስትሪ ነው። ለዚህ ደግሞ ሰዎች ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠርና መጠበቅ ይኖርባቸዋል።መሠረተ-ልማቶችን በመጠበቅ እንዲሁም ከመንግሥት ጎን በመሆን በሚፈለጉበት ሁሉ ንቁ ተሳትፎ በማድረግም ይጠበቅባቸዋል።
ምክክር - ወደ መግባባት መሸጋገሪያው ድልድይ!
Jun 24, 2026 6199
በዮሐንስ ደርበው በአመለካከት መለያየት ሥሪቱ ተፈጥሯዊ ነው። ሰዎች ልክ በመልክ፣ ቁመት ውፍረት ወይም ቅጥነት ሥብጥር፤ ምድርም በተፈጥሮ አቀማመጥ እና በዓየር ጠባይዋ ወጥ እንዳልሆኑት ሁሉ ማለት ነው። ለአንድ ሕዝብ እና ሀገር ብልጽግና ሲባል ከተበተነ ይልቅ የተደመረ ሐሳብ በእጅጉ ይጠቅማል። ሀገርኛ ብኂላችን “ከአንድ ብርቱ ሁለት መድኃኒቱ” ብሎ መሰባሰብን እንደሚሰብከው። የዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ጀምሮ ይካሄዳል - የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ትውልዱ ዛሬንም ነገንም በሚጠቅመው የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ ንቁ ተሳታፊ መሆን ይጠበቅበታል የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኮኖሚያዊ ትሩፋት ከሥሪታቸው አንጻር ዕሳቤዎች የግድ ተጨፍልቀው አንድ እንዲሆኑ ባይጠበቅም፤ ሀገርና ሕዝብን ወዳስቀደመው በይበልጥ ገዥ ሐሳብ መቅረብ ግን ተገቢ ይሆናል። በአንጻሩ በተለያዩ ዋልታዎች ቆሞ መጓተት ለማን ይጠቅማል? በምክክር ሁሉንም አሸናፊ አድርጎ መቋጨት እየተቻለ ለበርካታ ዓመታት የሐሳብ ልዩነቶች የወለዷቸው ግጭቶች፤ እንደ ሀገር አያሌ ሰብዓዊ፣ ቁሳዊ፣ ሥነ-ልቡናዊ እና ማኅበራዊ ክስረቶች ማስከተላቸውን ታሪክ ይነግረናል። የለውጡ መንግሥት ለኢትዮጵያ ከቸራቸው ትልልቅ ጉዳዮች የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሙ አንዱ ነው። ሀገራዊ ምክክር በአንድ ሀገር ውስጥ የምንኖር ሕዝቦች ራሳችንን በታማኝነት ፈትሸን በሐሳብ ልዩነቶች ላይ ለመነጋገር መፍቀዳችንን የሚጠይቅ ሂደት እንደመሆኑ፤ በቁጥር የማይተመኑ ረቂቅ የሆኑ ዋጋዎች አሉት። ይህም ፍላጎትን በኃይል ለመተግበር ሕይወትና ንብረት ከሚያወድመው ጦርነት ይልቅ አዋጭ የመግባቢያ መንገድ መሆኑን ያሳያል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ሀገራዊ የምክክር ጉባዔው ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል። እዚህ ደረጃ ከመደረሱ በፊት በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ኮሚሽኑ በየጊዜው ማሳወቁም ይታወሳል። ሀገራዊ ምክክር በአካታችና አሳታፊ ውይይት ወደ የጋራ መግባባት መድረሻ አትራፊ መንገድ ነው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንም ኃላፊነቱን ለመወጣት ለምክክር በሩን ለሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል ክፍት አድርጓል። በዚህም መሠረት ከዳያስፖራው፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በተለያዩ ክልሎች ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩና ሰላምን ከመረጡ ብሎም ከመላው ኢትዮጵያውያን ጋር በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መክሮ፤ አጀንዳዎችንም ተቀብሏል። ኮሚሽኑ የመጨሻው የምክክር ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ የሚገልጹት ዋና ኮሚሽነሩ፤ አካታች የምክክር ጉባዔ ለማካሄድ በማንኛውም ጊዜ ወደ ምክክሩ ለሚመጡ አካላት በሩ ክፍት መሆኑንም አረጋግጠዋል። የኪንታሮት ህመም እንዴት ይከሰታል? እንዳይከሰት መከላከል የሚቻልበት ብልኀትስ አለ? 👉 ሀገራዊ ምክክር ምን ይጠግናል? የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሥራ በሆነው የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ገጽ 384 ላይ እንደተቀመጠው፤ በሀገረ-መንግሥት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ሕዝብ ተመካክሮ፣ የጋራ መግባባት ላይ ደርሶ፣ የተግባባባቸውን በሕግና በሥርዓት አጽንቶ፤ ያልተግባባባቸውን ለወደፊት ምክክሮች አቆይቶ አልተጓዘም። በዚህ የተነሣ በየጊዜው ቅሬታ፣ ኩርፊያ፣ አብዮት፣ ዐመጽ ይፈጠራል። ነገሮች በተናጠል እየቀረቡ ለፖለቲካ ነጋዴዎች ምቹ ሁኔታ ይመቻቻል። ሁለንተናዊ ዕይታ ይጠፋል። ሀገራዊ ምክክር ይህን የዘመናት ስብራት ይጠግናል። 👉 ሀገሬው ለበለጸገችና ጠንካራ ሀገሩ ምን ይጠበቅበታል? መንግሥት በኢትዮጵያ የሐሳብ ገበያን ባሕል ለማድረግ እየተከተላቸው ካሉ መንገዶች አንዱ ሀገራዊ ምክክር ነው። በመደመር መንግሥት መጽሐፍ (ገጽ 383) ላይ እንደሰፈረው ደግሞ፤ በኢትዮጵያ የሚደረገው ሀገራዊ ምክክር የተለያዩ ሐሳቦች በአንድ መድረክ ቀርበው፤ በምክክርና ውይይት ጎልብተው አሰባሳቢና አስማሚ ሆነው የሚወጡበት መድረክ ነው። ስለሀገር የሚያገባው ሁሉም አካል በመሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ሐሳብ አዋጥቶና ተነጋግሮ መግባባት የሚፈጥርበት ምኅዳር መሆኑም ተገልጿል። ስለዚህ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሚከናወነው ለዚህ ታሪካዊ ሁነት መሳካት ኢትዮጵያውያን ከኮሚሽኑ ጎን በመሆን የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል። በሀገራዊ የምክክር ጉባዔው ለመሳተፍ የተመረጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች እና የባለ ድርሻ አካላት ወኪሎችም ውጤታማ ጉባዔ ማካሄድ የሚችሉበትን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል። ሀገራዊ ምክክር በአንድ በኩል፤ አንድነትና ኅብረትን በማጠናከር ልሂቃንና ሕዝብ ለአንድ ከፍ ላለ ዓላማ በአንድ ላይ እንዲቆሙ ያደርጋል። በዚህም ጥረቶች ሁሉ በአንድ አቅጣጫ እንዲፈስሱ ያደርጋል። በሌላ በኩል ፖለቲካዊ መረጋጋትና ሰላምን በመፍጠር የመንግሥት ትኩረት፣ ሀብትና ጊዜ ሳይበታተን ብልጽግናን ለማረጋገጥ ብቻ እንዲውል ያደርጋል (የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ገጽ 403)። #እንመካከር! #በምክክር_ከሰፈር_እስከ_ሀገር_የተሻለ_ነገን_እንገንባ! #ኢዜአ #Ethiopian_News_Agency #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #ኢትዮጵያ_እየመከረች_ነው
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና
Jun 17, 2026 8836
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል። የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 19836
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 12885
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 18635
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
መጣጥፍ
ቱሪዝም- የኢትዮጵያ የማከናወን ዐቅም ማሳያ
Jun 29, 2026 5218
በዮሐንስ ደርበው “ሀገራችን ከቱሪዝም ልታገኛቸው የምትችላቸውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና አካባቢያዊ ጥቅሞች ሁሉ ከቀረው ዓለም ጋር ተወዳድራ እንድታገኝ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጎብኚ ወደ ሀገራችን መሳብ አለብን። ለዚህም የተለያዩ ስልታዊ መላዎች ነድፈን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን (የመደመር መንግሥት 273)። የቱሪዝም ኢንዱስትሪ የለውጡ መንግሥት እመርታዎችን ካስመዘገበባቸው ዘርፎች አንዱ ነው። መንግሥት ከአምሥቱ የትኩረት መስኮች አንዱ አንድርጎም በጥናት፣ አካባቢያዊ ፀጋን ዐውቆና ለይቶ በተደመረ ዐቅም ባከናወናቸው ሥራዎች በገበታ ለሸገር፣ በገበታ ለሀገር፣ በገበታ ለትውልድ፣ በኮሪደር ልማት፣ በወንዝ እና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት እሠየው ያሰኙ ተግባራት አከናውኗል። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! በገበታ ለሸገር የተገለጠው የተደመረ ዐቅም - ለኢትዮጵያ ስኬቶች እንደማሳያ የመልከ መልካሟ ብዙ መልኮች ለአስም በሽታ አጋላጭ ምክንያቶችና ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው ከእንጦጦ - ቀበና የተከናወነው የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትም ለጎብኚም ለነዋሪም ምቹ ከባቢን በመፍጠር ረገድ እየተደረገ ያለውን ትጋት ያስረዳል። ምረቃውን ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባጋራው መረጃ፤ “መቆሸሽ እኛ አይገባንም፣ መጠልሸት እኛ አይገባንም፣ ማነስ እኛ አይገባንም! ሠርተን እንደምንችል ማሳየት ያስፈልጋል” ሲል የሥራውን ማራኪነትና ውበት ገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በዚሁ ወቅት፤ የተሰጠንን ሕዝባዊ አደራ በታማኝነት፣ በጽኑ ትጋት እና በቅንነት በመፈጸም የዜጎቻችንን የኑሮ ጥራት ለማሻሻልና መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የጀመርነውን ጉዞ አበክረን እንቀጥላለን ሲሉ በቀጣይ ካለፈው የበለጠ እንደሚሠራ አመላክተዋል። ገንዘብን፣ ዕውቀትን፣ ጉልበትን፣ ሐሳብን፣ የአመራር ብቃትን ስንደምር የሚከሰተው ነገር እንደዚህ ያለው ውበት ይሆናል ሲሉም አስገንዝበዋል። በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው (ገጽ 256) ላይም፤ “የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ሀገራት በዘመናቸው ሁሉ የሠሩትንና ተፈጥሮ ያደለቻቸውን መልካም ገጽታ በኩራት ለዓለም የሚያስተዋውቁበት፣ ‘ሀገሬ ይሄንን ትመስላለች’ የሚሉበት መድረክ ነው። ሀገርን በሚያኮራና ለሌሎች ለመጋበዝ በማያሳፍር መልኩ መገንባት፣ ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ መሠረቱ ነው።” ያሉትም የበለጸገች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ በቁጭት መነሳታቸውን ይገልጻል። ነገን ዛሬ እየሠራች ያለችው ኢትዮጵያ ካላት ላይ ሳትነፍግ የገንዘብም ሆነ የሰው ኃብቷን ቱሪዝም ላይ ስታውል፤ አንድም የኢንዱስትሪውን ዐዋጭነት ብሎም የዜጎቿን በየዘርፉ ዘላቂ ተጠቃሚነት በመገንዘብ ነው። እዚህ ላይ ለሀገር ገቢ በማስገኘት እና የሥራ ዕድል በመፍጠር ዘርፉ የሚያበረክተውን ጥቅም ማጤን ይገባል። በአዲስ አበባ ከተከናወኑ ቁልፍ የቱሪዝም ልማቶች መከካከል፤ የመስቀል ዐደባባይ ቅርስን ማንበርና ማዘመን፣ ከአዲስ አበባ ልማት ጋር ተሣሥሮ የተገነባው የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ በአዲስ መልክ የታደሠው ብሔራዊ ቤተ-መንግሥት፣ የአምሥቱ ዕውቀት ተኮር ማዕከላት (አብርኾት ቤተ-መጻሕፍት፣ ሳይንስ ሙዝየም፣ የሀገር በቀል ዕጽዋት ማሳያ፣ የአንድነት ቤተ-መዛግብት እና የማዕድን ሙዝየም) ግንባታ፣ የአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ማዕከል እና ሌሎችም ይገኙበታል። በሌላ በኩል ደግሞ ጎብኚዎች የሚያርፉበት ሎጂና ሆቴሎች ግንባታም በስፋት እየተከናወነ ይገኛል። ገበታ ለሸገር ብሎ ከአዲስ አበባ የተነሳው የቱሪዝም ልማት በገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ ወደ ክልሎች ተስፋፍቶ ደረጃቸውን የጠበቁ ሎጂዎች እንዲገነቡ አስችሏል። የተገነቡት ሎጂዎች ደግሞ ለጎብኚዎቹ ምቾትን የሚያስጠብቁ መሠረተ-ልማቶችን ስበዋል። በርካታ ጎብኚ መሳብና ገቢን ማሳደግ፣ በጎ ገጽታን መሸጥ፣ ለዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር፣ የበለጸገች ኢትዮጵያ ዕውን ማድረግ እየተከናወኑ ላሉ ተግባራት ሁሉ ግቦች ናቸው። መንግሥት ዕምቅ የጎብኚዎች መስኅብ ዐቅም የሆኑና አቧራ ለብሰው የተደበቁትን ፀጋዎች ውበታቸውን ገላልጦ እያሳዬ ያለውም ለዚህ ነው። ቱሪዝም በቀጥታ ዜጎች (ሰዎች) የሚጠቀሙበት ኢንዱስትሪ ነው። ለዚህ ደግሞ ሰዎች ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠርና መጠበቅ ይኖርባቸዋል።መሠረተ-ልማቶችን በመጠበቅ እንዲሁም ከመንግሥት ጎን በመሆን በሚፈለጉበት ሁሉ ንቁ ተሳትፎ ማድረግም ይጠበቅባቸዋል። ዜጎች ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ቁርጠኝነታቸውን ያረጋገጡበት ጠቅላላ ምርጫ ምክክር - ወደ መግባባት መሻጋገሪያው ድልድይ! ያልተቋረጠ የስኬት ጉዞ #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #Ethiopian_News_Agency #ቱሪዝም #PMOEthiopia #በኢዜአ_ዐይን #PMOEthiopia #EthiopiaDelivers
ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት - የሕዝብ ድምጽ
Jun 26, 2026 3795
ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት - የሕዝብ ድምጽ ኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ፍኖቷ ለአፍሪካ አርአያ ሆና አሳይታለች... የአፍሪካውያን ቀንዲል ናት። የክፉ ቀን መሸሸጊያቸው፣ የመከራ ጊዜ መጽናኛቸው፣ የነጻነት ተምሳሌትና የጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነችው ኢትዮጵያ፣ በረጅም ዘመናት ታሪካዊ መስተጋብር የተፈጠረ የሀገረ መንግሥት መዋቅር ባለቤት ናት። በተፈጥሮ ጸጋዎች፣ ምድሯን ሰንጥቀው በሚያልፉ ወንዞቿ የምትታወቅ አገር ናት። የተለያዩ ማዕድናት በብዛት የሚገኙባት ከመሆኗም በላይ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህልና እሴቶች ሕብር ሠርተው፣ ተስማምተው የሚኖሩባት የታሪክ ማህደር ናት። ይሁን እንጂ ይህ ታሪካዊ ግርማ ሞገስና የነጻነት አርማነት፣ በውስጣዊ የፖለቲካ ጉዞዋ ውስጥ ካጋጠሟት መዋቅራዊ ስብራቶችና የሥልጣን ፍትጊያዎች ሊታደጋት አልቻለም። ለዘመናት በሀገሪቷ የሰፈነው የሥልጣን ሥርዓት የሰፊውን ሕዝብ ፍላጎትና ተሳትፎ ያገለለ፣ በጥቂት የሕብረተሰብ ክፍሎችና ልሂቃን ፍላጎት ላይ ብቻ የተመሠረተ ነበር። ይህ አካሄድ በሀገሪቱ ታሪክ ውስጥ አንዱን ሥርዓት በሌላው እየተካ፣ የተተካው አገዛዝ ደግሞ የባሰ ጭቆናን ይዞ የሚመጣበትን አዙሪት ፈጥሯል። ከብዙ መቶ ዓመታት የዘውድ አገዛዝ በኋላ የመጣው ወታደራዊ ሥርዓት፣ በመቀጠልም ለ30 ዓመታት ገደማ የዘለቀው የአንድ ወገን የበላይነት የሰፈነበት አብዮታዊ ዴሞክራሲ ሀገሪቱንና ዜጎቿን ለከፍተኛ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ዳርገው አልፈዋል። ይህ ዓይነቱ የመከራና የጭቆና ሰንሰለት ግን በ2010 ዓ.ም በተቀጣጠለው ሀገራዊ ለውጥ ተገርስሶ ወደ አዲስ የፖለቲካና የዴሞክራሲ ምሕዳር ተሸጋግሯል። ያለፉትን ስምንት ዓመታት የኢትዮጵያን የፖለቲካ ጉዞ ስንመረምር፣ ሀገሪቷ ከአሮጌውና ከተለመደው የአፈና ሥርዓት ወጥታ አዲስ የዴሞክራሲ ሥርዓት ለመገንባት ቁርጠኛ አቅም ይዛለች። ይህ ወቅት የዜጎች የፖለቲካ ተሳትፎ መብት በተግባር የተረጋገጠበትና የሐሳብ ብዝኃነት የተስተናገደበት ምዕራፍ ነው። ከዚህ ቀደም የሥልጣን ማራዘሚያ ሆነው ያገለግሉ የነበሩ ዋና ዋና ተቋማት ገለልተኛና ነፃ ሆነው እንዲደራጁ መደረጉ የለውጡ ትልቁ ስኬት ሆኖ ሊጠቀስ ይችላል። በዚህ የሽግግር ሂደት ውስጥ የለውጡ የመጀመሪያ ፍሬ የታየው በ2013 ዓ.ም የተካሄደው ስድስተኛው ምርጫ ነበር። በወቅቱ የነበሩትን ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ተቆቁሞ ሕዝቡ ያሳየው የባለቤትነት ስሜት የዴሞክራሲ ናፍቆቱን በግልጽ ያሳየ ነው። ይህንን ተሞክሮ መሠረት በማድረግ፣ በዘንድሮው የ2018 ዓ.ም የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይበልጥ የነቃ አስደናቂ የፖለቲካ ተሳትፎ አሳይቷል። ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደው ይህ ታሪካዊ መድረክ፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያላቸውን የማይናወጥ አቋም አሳይተውበታል። ከንጋት እስከ እኩለ ሌሊት ረጅም ሰዓታትን ተሰልፈው የተፈጥሮ የአየር ንብረት ተጽዕኖዎችንና ልዩ ልዩ ፈተናዎችን በሙሉ በትዕግሥት በመሻገር ድምፃቸውን ሰጥተዋል። ይህ ሂደት የሚያሳየው ሕዝቡ የሥልጣን ምንጭነቱን በተግባር የተረዳበትና ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የወሰነበት ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን ነው። በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ጉዞና የውስጥ መረጋጋት ሁልጊዜም በከፍተኛ ትኩረት የሚከታተሉት ጉዳይ ነው። ላለፉት ዓመታት በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ የሚነሱ ሥጋቶችና የጂኦፖለቲካ ጫናዎች ቢኖሩም፣ ይህ በስኬት የተጠናቀቀው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሀገሪቷን የውስጥ ጥንካሬና ሉዓላዊነት በተግባር ያስመሰከረ ሆኗል። በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በነፃነትና በሰላም ድምፅ የሰጡበት ይህ ሂደት፣ ኢትዮጵያ የራሷን የውስጥ ጉዳይ በራሷ ዜጎች ፍላጎት የመወሰን ሙሉ አቅም እንዳላት ለዓለም አሳይቷል። ምርጫው ከሁሉ በላይ ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት ታላቅ ታሪካዊ ክስተት ነው። ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምፁን በመስጠት የሀገሩን ሉዓላዊነትና አንድነት አስከብሯል። የፖለቲካ ሥልጣን የሚገኘው በጠመንጃ አፈሙዝ ወይም በሁከት ሳይሆን በሕዝብ የላቀ ውሳኔ ብቻ መሆኑን በማረጋገጥ፣ ሀገራችን ካለፈችባቸው የፖለቲካ ስብራቶች በላይ ከፍ ብላ እንድትቆም አድርጓታል። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች ያላትን ተደማጭነትና የድርድር አቅም ከፍ የሚያደርግ ነው። የምርጫው ዝርዝር ስኬቶች ምን ምን ናቸው የሚለውን ስንመለከት፦ 👉የአፈሙዝ ድምፅንና የጽንፈኛ ዛቻን ያሸነፈው የሕዝብ ጽናት ግንቦት 24 ታሪካዊ ቀን ናት። በዚህች ታሪካዊ ዕለት፣ በየምርጫ ጣቢያው በነቂስ ወጥቶ ድምፁን የሰጠው ሕዝብ ያሳየው የነጻነት፣ የሉዓላዊነት እና የጽናት ማረጋገጫ ነው። ምርጫውን ለማደናቀፍና ሕዝቡን ለማስፈራራት የተቃጡ የአፈሙዞች ድምፆችና የሁከት ዛቻዎች ነበሩ፤ ነገር ግን ሕዝብ ከመምረጥ አላፈገፈገም። መራጮች የጽንፈኛ ኃይሎችን ዛቻ ወደ ጎን ትተው፣ የአካላቸውን ሕመም፣ የበሽታን ሥቃይ፣ አልፎ ተርፎም የወሊድ ምጥንና የቅርብ ዘመድ ሞት ያመጣውን ጥልቅ ሐዘን በሕሊናቸውና በሥጋቸው ተሸክመው ነበር ረጅሙን ሰልፍ ተሰልፈው ይበጀኛል ያሉትን በካርዳቸው የመረጡት። ይህ የሚያሳየው እውነት ለኢትዮጵያውያን የምርጫ ካርድ ሰላማቸውን የሚገዙበት፣ መብታቸውን የሚያስከብሩበትና የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውን በገዛ እጃቸው የሚወስኑበት ብቸኛ የነጻነት አዋጃቸው መሆኑን ነው። ሕዝቡ ከምርጫ ውጭ በሆነ መንገድ፣ በኃይል ወይም በሁከት ሥልጣን ለመያዝ ምኞትና የቆየ የሥልጣን ናፍቆት ላላቸው ወገኖች በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ግልጽና የማያሻማ መልዕክት አስተላልፏል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የኃይልና የሁከት አካሄድን እንደማይቀበል፣ በድምፅ ላይ ብቻ የተመሠረተ ሕጋዊ ሥርዓትን ለማፅናት እንደሚታገል አረጋግጧል። ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ይህን ጉዳይ በተመለከተ በአፅንኦት ሲያነሱ፤ "የዘመናችን ዲሞክራሲ አስተምህሮቱ ሰላምና ዕድገት፣ ቋንቋው ደግሞ መምረጥና መመረጥ ብቻ በመሆኑ የፖለቲካ ቅኝታችሁንና አካሄዳችሁን ከዚሁ ስልጡን መስመር ጋር ማስተካከል ይበጃችኋል። ካሁን በኋላ የሕዝብ ድምፅ ያልጎበኘው፣ የምርጫ ካርድ ያልዳሰሰው የፖለቲካ ሥልጣን መያዣ መንገድ በኢትዮጵያ ዝግ መሆኑን እነሆ እንዳየነው መሠረት የጣለ ስለሆነ ይህኑ ስልጡን መንገድ ለመቀበል የማትፈቅዱ ሁሉ ግን ግፋ ቢል የዘመናችን የፖለቲካ ድርሳን ሲጻፍ ልትሆኑ የምትችሉት የግርጌ ማስታወሻ ብቻ ነው።" ብለዋል። ስለሆነም ከዴሞክራሲያዊ፣ ሰላማዊና ሕጋዊ አካሄድ ውጭ የሚደረግ ሙከራ የጥፋት ተዋናይ ከመሆን ባሻገር ለሀገር የሚያተርፈው አንዳች ነገር እንደሌለ በዚህ ስሑት መንገድ ላይ የሚገኙ አካላት ሊገነዘቡ ይገባል። 1. ምርጫው በቁጥሮች ሲገለጽ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በጉልህ የሚጠቀሱ አኃዛዊ መረጃዎች አሉት። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ተስፋዬ ንዋይ እንደገለጹት፤ ቦርዱ ከ120 ሚሊዮን በላይ የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን በውጭ ሀገር አሳትሞ ካስመጣ በኋላ፣ ከምርጫው 4 ቀናት በፊት በሀገሪቱ ባሉት ከ52 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች በታማኝነትና በጥንቃቄ ማድረስ ተችሏል። ይህንን እጅግ ግዙፍና ውስብስብ የሎጂስቲክስ ሥራ ሙሉ በሙሉ ያከናወኑት የቦርዱ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ብቻ መሆናቸው ተቋማዊ አቅሙ ምን ያህል እንደጎለበተ ማሳያ ነው። የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ እንደተናገሩት፤ የቦርዱ ሠራተኞችና የምርጫ አስፈጻሚዎች በዕረፍት ቀናትና በሌሊት በመጋዘን ውስጥ ጭምር እያደሩ የቁሳቁስ ማሸግ ሥራዎችን በትጋት አከናውነዋል። ሩቅና ተደራሽነታቸው አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ደግሞ ቁሳቁሶችን በእግር፣ በእንስሳት ጀርባና በጀልባ ጭምር በማጓጓዝ፣ ወንዞችን ለመሻገር የራሳቸውን የፕላስቲክ ጀልባ ሠርተው ሀገራዊ አደራቸውን ተወጥተዋል። በድምፅ መስጫ ቀን ሥራቸውን ከንጋት እስከ ንጋት በልዩ ብርታት ፈጽመዋል። ይህ ልብ የሚነካ እውነታ የሚያሳየው፣ የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታና የሕዝብ ድምፅ እንዲከበር የሚደረገው ጥረት ከፍተኛ ዋጋ ያለው የተናጥልና የጋራ ትጋት የሚጠይቅ መሆኑን ነው። ሰፊ ተሳትፎ፦ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎችና 80 የግል ዕጩዎች ተሳትፈዋል። 10 ሺህ 438 የፖለቲካ ፓርቲና የግል ዕጩዎች ተወዳድረዋል። ቦርዱ ለመጀመሪያ ጊዜ ፓርቲዎች ፖሊሲዎቻቸውን ለሕዝብ የሚያስተዋውቁበት የክርክር መድረክ ያዘጋጀ ሲሆን፤ ይህ ተግባር ፓርቲዎች ከምርጫው ውጭም ራሳቸውን ለሕዝብ የሚያቀርቡበትን ባህል ያዳብራል። የመራጮችና አስፈጻሚዎች ቁጥር፦ በአጠቃላይ 54 ሚሊዮን 57 ሺህ 861 መራጮች የተመዘገቡ ሲሆን፤ ምርጫውን ለማስፈጸም ከ350 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል። ታዛቢዎችና ወኪሎች፦ ከ260 ሺህ በላይ የፖለቲካ ፓርቲ ወኪሎች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ያሰማሯቸው ከ60 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች፣ እንዲሁም 63 የአፍሪካ ኅብረት እና 26 የኢጋድ ታዛቢዎች ተሳትፈዋል። ለመራጩ ሕዝብ የሥነ ዜጋና የመራጮች ትምህርት ለመስጠት መስፈርቱን ላሟሉ 169 ሀገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ፈቃድ ተሰጥቷል። እንዲሁም 21 ሚሲዮኖችና አንድ የውጭ ሀገር የምርጫ አስፈጻሚ ተቋም ምርጫውን ተመልክተዋል። የአየር ሰዓት አጠቃቀም፦ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎች ነፃ የአየር ሰዓት የማግኘት መብት ስለነበራቸው ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 752.5 ነፃ የሬዲዮ ሰዓት፣ 57.5 ነፃ የቴሌቪዥን ሰዓትና 576 የጋዜጣ ኮለምን በዘመናዊ የዕጣ ማውጣት ሥርዓት ተደልድሎ እንዲጠቀሙ ተደርጓል። መገናኛ ብዙኃን፦ 73 የሀገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙኃንን የወከሉ 1 ሺህ 827 የሀገር ውስጥና 45 የውጭ ጋዜጠኞች ለዘገባ ሥራ ተሰማርተዋል። የሕግ ማሻሻያ እና ዲጂታላይዜሽን፦ አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ተሻሽሎ በአዋጅ ቁጥር 1394/2017 ተተክቷል። ቦርዱ 10 አዳዲስ መመሪያዎችን አጽድቋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር፦ ለመጀመሪያ ጊዜ በገለልተኛ ባለሙያዎች የሚመራ፣ እያንዳንዳቸው 2 ሰዓት የሚወስዱ 19 የክርክር መድረኮች በቦርዱ ተዘጋጅተዋል። 14ቱ በአማርኛ፣ 5ቱ በክልል ቋንቋዎች (አፋን ኦሮሞ፣ ሶማሊኛ፣ ሲዳምኛ፣ አፋርኛ) ተካሂደው በሰባት መገናኛ ብዙኃን በፕራይም ታይም ተላልፈዋል። አካታችነት፦ 28 ሺህ 632 የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችና ከ20 ሺህ በላይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ጨምሮ ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች በልዩ የምርጫ ጣቢያዎች እንዲመዘገቡ ተደርጓል። የቅሬታ አፈታትና ክትትል፦ የቅድመ አደጋ ማሳወቂያ ሥርዓት (Early Warning System) ተዘርግቷል። 663 የምርጫ ክልል ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎችና ልዩ የአጣሪ ጉባኤ ተደራጅተው 129 አቤቱታዎችን መርምረዋል። የሕግ ጥሰት በተገኘባቸው ጣቢያዎች ውጤት እንዲሰረዝ እና በፈጻሚዎች ላይ አስተዳደራዊና የወንጀል ተጠያቂነት እንዲኖር ተወስኗል። 2. ጠንካራና ገለልተኛ ተቋም፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የሀገር ውስጥ አቅም ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ መጠነ ሰፊ ተቋማዊና ሕጋዊ ማሻሻያዎች የተደረጉበት ከመሆኑም በላይ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር ረገድ ሀገራዊ አቅምን በተግባር ያሳየ ነበር። የዚህ ምርጫ ትልቁ ትርፍ ጠንካራና የማይናወጡ ብሔራዊ ተቋማትን መገንባት መቻላችን ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያሳየው ፍጹም ገለልተኝነት፣ የሕግ የበላይነትን የማስከበር ብቃት እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች የመተግበር አቅም፣ ተቋማት ከግለሰቦችና ከፖለቲካ ጫና በላይ መሆናቸውን ያስመሰከረ ነው። ይህም ለቀጣዩ ትውልድ የሚሻገር አስተማማኝ የመንግሥት መዋቅር መሠረት ነው። ለምርጫው ስኬት ግንባር ቀደም ተጠቃሽ የሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነው። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ መራጮችን በትዕግሥት በማስተናገድ፣ ብቁ አስፈጻሚዎችን በማሰማራትና ሂደቱን በታማኝነት በመምራት ረገድ ቦርዱ አድናቆት የተቸረው ሥራን ፈጽሟል። የሠራተኞቹ ቀንና ሌሊት መትጋት እንዲሁም በግንባር ቀደምትነት የሚመሩት አመራር አባላት ያሳዩት ቁርጠኝነት የላቀና ለሀገር ኩራት የሆነ ተግባር ነው። በዚህ ምርጫ ውስጥ ትልቁን ትኩረት የሳበውና ለመጀመሪያ ጊዜ በሥራ ላይ የዋለው የዲጂታል የመራጮች ምዝገባ ሥርዓት ነው። ይህ ዘመናዊ አሠራር ለምርጫው ከተመዘገቡ ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች መካከል ከ5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በአካል መጓዝ ሳይጠበቅባቸው፣ ባሉበት ቦታ ሆነው በነፃነት እንዲመዘገቡ ዕድል ፈጥሯል። ቴክኖሎጂው የመራጮችን ማንነት በፎቶግራፍ ጭምር በማረጋገጡ በድምፅ መስጫ ቀን ሊፈጠሩ የሚችሉ ግድፈቶችንና ማጭበርበሮችን በከፍተኛ ደረጃ መከላከል ተችሏል። የዚህ ሥርዓት ዋነኛውና ትልቁ ድል ደግሞ ሙሉ በሙሉ ወጣት ኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የበለጸገ መሆኑ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ የዚህን የቴክኖሎጂ ስኬት አስፈላጊነት ሲያብራሩ፤ "እነዚህ የዲጂታል የምዝገባ ሥርዓቶች በውጭ ሀገር አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶች የለሙ ሳይሆን በራሳችን ወጣት ኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የተገነቡ ናቸው። ይህም ተቋሙን ከውጭ አቅራቢዎች ጥገኝነት ነፃ በማድረግ በራሱ አቅም እንዲቆምና ለወደፊቱ ማሻሻያዎችን በራሱ እንዲያከናውን መሠረት ጥሏል።" ይህ እርምጃ ቦርዱ የውጭ የቴክኒክ ጥገኝነትን በመቀነስ የሀገር ውስጥ አቅምን ለመገንባትና የሉዓላዊነትና የደኅንነት ዋስትናን በራስ ቴክኖሎጂ ለማረጋገጥ የቻለበትን ስትራቴጂካዊ አካሄድ በግልጽ ያሳያል። በተጨማሪም በስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ በውጭ ዜጎች ይሠራ የነበረው የቴክኒክ ድጋፍ በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ሠራተኞች መተካቱ የተሳካ የእውቀት ሽግግር መኖሩን አሳይቷል። 3. ሕጋዊ ማሻሻያዎች፣ አካታችነትና ተጠያቂነት ዴሞክራሲ እውነተኛ ትርጉም የሚኖረው ዜጎች፣ በተለይም ሴቶችና አካል ጉዳተኞች ያለ ፍርሃትና ጫና፣ ደኅንነታቸው ተጠብቆ በፖለቲካዊ ሂደቶች እኩል መሳተፍ ሲችሉ ነው። ይህንን እውን ለማድረግ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። ለምሳሌ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር በታዛቢነት በመሳተፍ፣ ሴቶች የዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን በነፃነት እንዲጠቀሙና በሂደቱ በንቃት እንዲሳተፉ አስችሏል። ቦርዱ የሴቶችን መብት ከማስከበር ባለፈ፣ ጾታዊ ጥቃትና ትንኮሳን ለመከላከል የሚያስችል ፖሊሲ ቀርጾ ተግባራዊ አድርጓል። ከዚህም በላይ በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ግብረ ኃይል ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ አቋቁሟል። በተጨማሪም የምርጫውን ግልጽነትና ተዓማኒነት ለማረጋገጥ ቀድሞ የነበረው አዋጅ ቁጥር 1162/2011 በአዋጅ ቁጥር 1394/2017 እንዲተካ የተደረገ ሲሆን፣ ቦርዱ ይህንን መነሻ በማድረግ 10 አዳዲስ መመሪያዎችን አጽድቋል። በነዚህ ማሻሻያዎች ውስጥ የሴቶችና የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ ማሳደግ እንደ ዋና መርህ የተወሰደ ነው። 4. ፈተናዎችን መጋፈጥና ገለልተኝነትን ማስከበር ይህ ሁሉ ስኬት ግን ያለ ፈተና አልመጣም። ምርጫው በተያዘለት ጊዜ አይካሄድም የሚሉ ጥርጣሬዎችና የተሳሳቱ መረጃዎች ተቋሙን ፈትነውት ነበር። ሆኖም ቦርዱ ጫናዎችን በመቋቋም ሕግና መርህን ብቻ ተከትሎ በመሥራት ምርጫውን ለስኬት ማብቃቱን ወይዘሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ያረጋግጣሉ። ቦርዱ በምርጫው ወቅት የተቋሙን ነፃነት ከማንኛውም ዓይነት ጫናና ጣልቃገብነት በመጠበቅ በሕግና በመርህ ላይ ተመሥርቶ ውሳኔዎችን ሲያሳልፍ ቆይቷል። በምርጫ አፈጻጸም የአሠራር ግድፈቶች እና ከፖለቲካ ፓርቲዎች የቀረቡ ቅሬታዎችን በመመርመር በአንዳንድ የምርጫ ክልሎች በድምፅ መስጫው ቀን ጭምር አስፈጻሚዎችን አሰናብቷል፤ በምርጫ ውጤቶች ላይም ውሳኔ ሰጥቷል። ይህም ቦርዱ ለሕግ የበላይነትና ለምርጫ ታማኝነት ያለውን ጽኑ አቋም ያሳያል። የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት በአንድ ተቋም ወይም በጥቂት ግለሰቦች ብቻ ሳይሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ መራጮች በፀሐይና በዝናብ ሳይበገሩ በትዕግሥት የሰጡት ድምፅ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የጸጥታ አካላት፣ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች (እንደ አፍሪካ ኅብረትና ኢጋድ) እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት የጋራ ጥረት ውጤት ነው። 5. የምርጫው ግልጽነትና ዓለም አቀፍ እውቅና የምርጫውን ታሪካዊ ሂደትና ተዓማኒነት ለማረጋገጥ የሀገር ውስጥና የውጭ አካላት በሰፊው ተሳትፈዋል። ሂደቱን ለመዘገብ 73 ለሚሆኑ የሀገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙኃን ፈቃድ የተሰጠ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 1 ሺህ 827 ጋዜጠኞች የዘገባ ሥራቸውን አከናውነዋል። ከ260 ሺህ በላይ የፖለቲካ ፓርቲ ወኪሎች እና ከ64 ሺህ በላይ ሀገር በቀል የሲቪል ማኅበራት ታዛቢዎች በሂደቱ ላይ ተሳትፈዋል። በተለይም በምርጫ ቦርድ ዕውቅና የተሰጣቸው 55 የሀገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች 60 ሺህ 277 ታዛቢዎችን በማሰማራት ሂደቱን የተከታተሉ ሲሆን፤ 169 ድርጅቶች ደግሞ ለመራጮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሰጥተዋል። በአህጉር ደረጃም የኬንያ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሩትና ከ60 በላይ ታዛቢዎችን ያቀፈው የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን እና 26 የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነመንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ታዛቢዎች ሂደቱን በታዛቢነት ተከታትለዋል። ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ምርጫው ግልጽ፣ አሳታፊና ተዓማኒ ሆኖ በስኬት መካሄዱንም አረጋግጠዋል። 👉የአፍሪካ ህብረት እና የኢጋድ ታዛቢ ቡድኖች ምስክርነት የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ የኬንያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በሰጡት መግለጫ፣ የምርጫው ዕለት ሰላማዊ፣ ሥነ ሥርዓት የሰፈነበት እና ግልፅነት የታየበት መሆኑን ነው ያረጋገጡት። በቴክኖሎጂ የታገዘ የመራጮች ምዝገባ መተግበሩ ወጣቶችን መሳቡን፣ ዜጎች በትዕግሥት ሰልፍ በመያዝ ጥልቅ ፍላጎታቸውን ማሳየታቸውን፣ የሎጂስቲክስ ዝግጅቱ የተሟላ መሆኑንና የምርጫ ሰዓት መራዘሙ የሚደነቅ መሆኑን ጠቁመዋል። በመስተንግዶ ረገድም ወንበሮችና የምግብ አቅርቦቶች መኖራቸው ረጅሙን ሰልፍ ታጋሽ እንዳደረገውና ለአረጋውያንና አካል ጉዳተኞች ቅድሚያ መሰጠቱን አረጋግጠዋል። የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ለኢትዮጵያውያን ባስተላለፉት መልዕክት "ቅኝ ግዛትን በአንድነት የተከላከለች Couch፣ ለአፍሪካ ነፃነት የቆመች እና የአህጉሪቱ ዋና ከተማ በሆነች ሀገር ውስጥ የተደረገው ይህ ምርጫ ትልቅ ምዕራፍ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን በታሪካቸው ሊኮሩ ይገባል፤ ወደፊት ለመራመድም በሕዝቦች መካከል ያለውን የፖለቲካ እና የማኅበረሰብ ውይይት ይበልጥ ማሳደግ፣ ወደ ኋላ የተተዉ የሚሰማቸውን አካላት ወደ መድረኩ በማምጣት እና አካታችና የተባበረች ኢትዮጵያን መገንባት ያስፈልጋል" ብለዋል። በሌላ በኩል፣ የኡጋንዳ የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ስፔሲዮዛ ዋንዲራ ካዚብዌ የሚመራው የኢጋድ (IGAD) የምርጫ ታዛቢ ቡድን በሰባት ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች 28 ጣቢያዎችን በመጎብኘት የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱን አውጥቷል። ቡድኑ ጣቢያዎቹ በሰዓታቸው መከፈታቸውን፣ በቂ ቁሳቁስና አስፈጻሚዎች እንደነበሩ፣ የሳጥኖች አስተሻሸግ የድምፅ ምስጢራዊነትን ያረጋገጠ መሆኑንና የድምፅ አሰጣጡ ያለምንም መሰናክል በጥሩ ሁኔታ መካሄዱን በመታዘብ ምስክርነቱን ሰጥቷል። ለአረጋውያን፣ ሕፃናት ለያዙ ሴቶችና አካል ጉዳተኞች ቅድሚያ መሰጠቱንና መራጮች የሚቀመጡባቸው ወንበሮች መኖራቸውን የጠቀሰው ሪፖርቱ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን በማዘጋጀትና በመምራት ረገድ ከፍተኛ አስተዳደራዊና ኦፕሬሽናል አቅም ማሳየቱን አጉልቷል። የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን ለሰላማዊና ተዓማኒ ምርጫ የተደረገውን የጋራ ቁርጠኝነት ያደነቀ ሲሆን፣ "ይህ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ እና ምርጫ ዕድገት ላይ በተለይም የምርጫ አስተዳደርን ለማሻሻል፣ አካታችነትን እና ተዓማኒነትን ለማሳደግ የተነደፉ ዋና ዋና ቴክኖሎጂያዊ እና ተቋማዊ ማሻሻያዎች የተስተዋሉበት ትልቅ ምዕራፍ ነው" ሲል ቡድኑ ምስክርነታቸውን በአፅንኦት የገለጹት። የአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደኅንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ "ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው። በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ይበልጥ እንዲጠናከርና ቀጣይነት ያለው መሻሻል እንዲመዘገብ አብረን ለመሥራት ያለንን ጽኑ ቁርጠኝነት እናረጋግጣለን።" ሲሉ ነው የተደመጡት። 6. የምርጫው ውጤት፣ የሕዝቡ ጽናትና የአሸናፊው ፓርቲ ከባድ ሸክም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ ባደረገው ውጤት መሠረት፣ ብልፅግና ፓርቲ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 438 መቀመጫዎችን በማግኘት አሸንፏል። በሌላ በኩል ተፎካካሪ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎችም በምክር ቤቶቹ ወንበሮችን ማግኘት የቻሉ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) 13፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ስድስት፣ ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ሦስት፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ሦስት፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ ሦስት፣ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ሁለት ወንበሮችን አሸንፈዋል። በሌላ በኩል ኦብነግ፣ ጉህዴን፣ አርጎባ አንድነት ጀበርቲ፣ የአፋር ሕዝብ ፓርቲ፣ የወላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ፣ የሶማሌ ፌዴራሊስት ፓርቲ፣ ኅብረት ለዴሞክራሲና ለነጻነት፣ ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት፣ የጌዴዮ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት እያንዳንዳቸው አንድ ወንበር ሲያገኙ 8 የግል ተወዳዳሪዎችም ምክር ቤት ለመግባት አሸንፈዋል። ይህን ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ከሌሎች ጊዜያት ለየት የሚያደርገው ታላቅ ክስተት፣ መራጩ ሕዝብ በታጋሽነት ተሰልፎ የመምረጥ መብቱን ለመጠቀም ያሳየው ወደር የለሽ ጽናት ነው። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ይህንን የሕብረተሰብ አደራ "አሸናፊው ፓርቲ ትልቅ ሀገራዊ ሸክም የተጣለበት መሆኑን ብልፅግና ፓርቲ በሚገባ ይረዳል። ፓርቲያችን በማኒፌስቷችንና በአጠቃላይ በምርጫ ቅስቀሳችን ወቅት ለሕዝብ ቃል የገባናቸውን በተግባር ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት ይንቀሳቀሳል" ብለዋል፡፡ 👉የፉክክርና የትብብር ሚዛን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምሕዳር በቀጣይነት ሊመራበት የሚገባው ስልጡን መስመር በፉክክርና በትብብር መካከል ያለውን ሚዛን ጠብቆ መጓዝ ነው። ብልፅግና ፓርቲ ከሌሎች ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና በሀገር ግንባታ ላይ ሚና ካላቸው አካላት ጋር በብሔራዊ ጥቅም ላይ በትብብር ለመሥራት ያለው አቋም የጸና መሆኑን የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ በሰጡት አስተያየት፤ "ባለፉት ዓመታት የጀመርነውን በፉክክርና በትብብር መካከል ሚዛን ጠብቆ የሚሄድ ጥረታችንን በቀጣይ አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል። በምንሠራቸው ሥራዎች ሁሉ ሕዝቡን በማሳተፍ፣ በየጊዜው የሕዝቡን ግብረ መልስ በመስማት፣ ያንን እንደ ግብዓት ተጠቅመን የእቅድ አካል አድርገን ወደ ተግባር ለመተርጎም በቁርጠኝነት እንንቀሳቀሳለን።" ብለዋል። ይህ ዕይታ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሕዝብን ድምፅና ግብረ መልስ በየጊዜው የሚያዳምጥ፣ እንዲሁም ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ለሀገር ጥቅም በጋራ የመሥራትን ስልጡንና አካታች የአሠራር ሥርዓት መከተል መጀመሩን ያሳያል። 7. ዴሞክራሲና ምርጫው የሚገለጽባቸው አራቱ ምሰሶዎች ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ማለት አማራጭ የሌለው የህልውና ጉዳይና የሁለንተናዊ ብልጽግናችን መሠረት ነው። ብዝኃነትን በአግባቡ ማስተናገድ፣ ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥና ጠንካራ ሀገር መገንባት የሚቻለው በዴሞክራሲያዊ ምሰሶዎች ላይ በመመሥረት ብቻ ነው። መንግሥት ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ሲሠራ ቆይቷል። በዚህ ሂደት ውስጥ የሲቪል ማኅበራት ሚና የማይተካና አዎንታዊ ሚና አላቸው። መራጩን ሕዝብ ከማስተማር፣ ሕገ መንግሥታዊ የመምረጥ መብቱን እንዲጠቀም ከማስቻል፣ እስከ ሰላም እሴት ግንባታና በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ድልድይ በመሆን የዜጎችን ባለቤትነት ከማረጋገጥ አኳያ የላቀ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ እንደገለጹት፣ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት በአራት ዋና ዋና ምሰሶዎች ላይ የቆመ ነው። አንደኛው ምሰሶ፦ ምርጫ የሰላም ዋስትና መሆኑን መረዳት ነው። ሕዝቡ ልዩነቶችን በፀብና በአምባጓሮ ከመፍታት አዙሪት ተላቆ፣ በሰላማዊ መንገድ የመሻገር ባህልን መርጧል። በነቂስ ድምፁን መስጠቱ ኋላ ቀር የአመፃ መንገድን ለሚከተሉ ሁሉ "በቃችሁ" የሚል መልዕክት ያስተላለፈበት ሲሆን፣ የሰፊው ሕዝብ ማዕበላዊ ድምፅ ከአሮጌው የብጥብጥ ባህል መላቀቅ እንደሚፈልግ ማረጋገጫ ነው። ሁለተኛው ምሰሶ፦ የምርጫ ውግንና ከሕዝብ ጋር መሆኑን ማወቅ ነው። የምርጫ ተዓማኒነትና ክብሩ የሚገለጠው ሥልጣን ከሚመነጭበት ከሰፊው ሕዝብ ሉዓላዊ መብትና ፍላጎት ጋር የተሳሰረ በመሆኑ ነው። ምርጫ ከሚሰጠው ኃላፊነት በላይ ለእያንዳንዱ ዜጋ የዕለት ተዕለት ሕይወት መሻሻልና ከሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ጋር የተቆራኘ መሆኑን ሕዝቡ በትክክል ተገንዝቧል። ሦስተኛው ምሰሶ፦ የምርጫው የፖሊሲ ሐሳቦችና አማራጮች ከፍታ የታየበት ነው። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የክርክር መድረኮች ተፎካካሪ ፓርቲዎች ያነሷቸውን የፖሊሲ አማራጮች ሕዝቡ በጥንቃቄ አዳምጧል። እነዚህ ሐሳቦች ለሀገር ዕድገት፣ ለጠንካራ መንግሥትና ለሰከነ የፖለቲካ ባህል ግንባታ መሠረት እንዲሆኑ በእያንዳንዱ ዜጋ ሕሊና ማስረፅ፣ በሰነድ በማዘጋጀትም መተግበር ይገባል። አራተኛው ምሰሶ፦ ምርጫ እንደ ማኅበራዊ ሀብት፤ ምርጫ ፖለቲካዊ ኩነት ብቻ ሳይሆን ትልቅ ማኅበራዊ ሀብት መሆኑን በተግባር አሳይቷል። ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የዚህን ማኅበራዊ እሴት አንድምታ ሲያብራሩም "ሕዝባችን ስለ ኢትዮጵያዊ ቀናነቱና ፍቅሩ ጩኸቱን ሳይሆን የምርጫ ካርድ ድምፁን፣ ስላቅና ሃኬትን ሳይሆን ትሑትነቱን፣ የትኛውንም የፖለቲካ ሐሳብ ቢያራምድ እንኳን ማኅበራዊና ሀገራዊ ፍቅሩን ከጎኑ ላለው ወገኑ አለመንፈጉን ያየንበት እጅግ የተዋበ መድረክ ነበር። ስለዚህ የኢትዮጵያ ምርጫ ከፖለቲካዊ ፋይዳው ባልተናነሰ ሁኔታ ማኅበራዊ ፋይዳውም ከፍ ያለ ትልቅ የማኅበራዊ መሠረትን የሰጠው ነው።" ብለዋል። 8. የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ታሪካዊ ሚና፦ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ስብራቶች የመፈወስ ዕድል ኢትዮጵያ በረጅም ዘመን የሀገረ መንግሥትና የፖለቲካ ሥርዓት ጉዞዋ ውስጥ በርካታ አኩሪ ታሪኮችን ብታስመዘግብም፣ በሂደቱ ውስጥ የተፈጠሩና ዛሬም ድረስ ሀገራዊ አንድነቷን፣ ሰላሟንና የዴሞክራሲ ግንባታዋን እየተፈታተኑ ያሉ ሥር የሰደዱ የፖለቲካ ስብራቶች መኖራቸው አይካድም። እነዚህን ለዘመናት የዘለቁ ስብራቶች በመጠገን ረገድ ይህ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሀገሪቱን ወደ አዲስ ምዕራፍ ሊያሻግር የሚችል ታሪካዊና ስትራቴጂካዊ ዕድል ይዞ መጥቷል። ምርጫው በበሰለና አካታች መንገድ በመመራቱ በሀገሪቱ የፖለቲካ ታሪክ ላይ ጉልህና አዎንታዊ አሻራ ማሳረፍ የሚችልባቸው ዋና ዋና አቅጣጫዎች አሉት። እነዚህም፦ የቅቡልነት ስብራትን ማከም፦ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የመንግሥታት ሥልጣን አመጣጥ አብዛኛውን ጊዜ ከኃይል ፖለቲካ ወይም ሙሉ በሙሉ ነፃ ካልሆኑ ምርጫዎች ጋር የተያያዘ በመሆኑ፣ የመንግሥት ሕዝባዊ ቅቡልነት ማጣት ለግጭቶች መነሻ ሲሆን ቆይቷል። ይህ ምርጫ ነፃና ታማኝ ሆኖ መካሄዱ አሸናፊው አካል ከሕዝብ የሚሰጠው እውነተኛ የሥልጣን አደራ እንዲኖረው ያደርጋል፤ ይህም በገዥው አካልና በሕዝቡ መካከል ያለውን መተማመን በማደስ ረገድ ትልቅ ዕድል ይሰጣል። የሰላማዊ ሥልጣን ሽግግር ባህልን መገንባት፦ ሥልጣንን በአፈሙዝ የመያዝ ልምድ ሀገሪቱን በተደጋጋሚ ለድቀት የዳረጋት መሆኑ ብዙ ትምህርት ሰጥቷል። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሁሉም ወገኖች የሕዝብን ድምፅ አክብረው የሚቀበሉበት ድባብ መፈጠሩ ምርጫን ብቸኛ የሥልጣን መያዣና መልቀቂያ መንገድ የማድረግ አዲስና ጤናማ የፖለቲካ ባህል በሀገሪቷ ውስጥ እንዲለመድ ያደርጋል። በተቋማት ላይ ያለውን አመኔታ ማደስ፦ ሕዝቡ እንደ ምርጫ ቦርድ፣ ፍርድ ቤቶችና የዴሞክራሲ ተቋማት ባሉ ገለልተኛ መሆን በሚገባቸው ተቋማት ላይ ያለው እምነት መሸርሸሩ ሌላው ስብራት ሲሆን፣ ይህንንም ምርጫ በስኬትና በገለልተኝነት ማካሄድ መቻሉ የተቋማቱን ነፃነትና ብቃት በተግባር የሚያሳይ በመሆኑ ዜጎች በሀገሪቷ የሕግ የበላይነት ላይ ያላቸው እምነት መልሶ እንዲያገግም ያደርጋል። ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር፦ አካታች የሆነ ምርጫ ማካሄድ መሣሪያ ያነሱ ወይም በሰላማዊ መንገድ የሚያምፁ የፖለቲካ ኃይሎች ቅሬታቸውን በሕዝብ ድምፅ እንዲፈትሹ በር ይከፍታል። ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያን የዘመናት የፖለቲካ ስብራቶች ለመፈወስ የራሱ አሻራ ሊያኖር የሚችለው ሂደቱ ፍትሐዊ፣ ግልጽና በርካታ የፖለቲካ ኃይሎችን ያሳተፈ፣ ከ54 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በንቃት የተሳተፈበት በመሆኑ ነው። በዚህም ምርጫው በተሳካ ሁኔታ መካሄዱ በራሱ ወደ ሰፊው ብሔራዊ ምክክር ለመሻገር እንደ ትልቅ መነሻ ሆኖ ያገለግላል። ማጠቃለያ፦ ምርጫው ለአፍሪካ ዴሞክራሲ የብርሃን ፍኖት አፍሪካ በፖለቲካዊ አለመረጋጋቶች፣ በወታደራዊ ኃይሎች ጣልቃ ገብነትና ኢ-ሕገመንግሥታዊ መንገድ መምራት፣ የመንግሥት ግልበጣዎች እየተፈተነች ባለችበት በዚህ የታሪክ ምዕራፍ፣ ኢትዮጵያ በሰላማዊና ስልጡን መንገድ ምርጫዋን ማጠናቀቋ ለአህጉሪቱ አዲስ ፍኖተ ዴሞክራሲ ሆና እንድትወጣ አድርጓታል። 'የአፍሪካ ችግሮች የአፍሪካውያን መፍትሔዎች' የሚለውን መርህ በተግባር በማሳየት፣ የራሳችንን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በራሳችን አቅም መቅረጽ እንደምንችል ለዓለም አሳይተናል። በዚህ አስቸጋሪ አህጉራዊ ድባብ ውስጥ፣ የፓን አፍሪካኒዝም ማዕከልና የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊና ፍትሐዊ መንገድ በስኬት ማጠናቀቋ ለአፍሪካ ትልቅ ተስፋን የሚሰጥ ነው። ኢትዮጵያ ለጫናዎች ሳትበገር፣ በራሷ ሁለንተናዊ አቅም ያከናወነችው ይህ ታሪካዊ መድረክ ሀገር በቀል ዴሞክራሲን እና አህጉራዊ ሉዓላዊነትን ያረጋገጠ በመሆኑ ለመላው አፍሪካ ኩራትና ተምሳሌት ሆኗል። የአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደኅንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ፤ አህጉሪቱ ካለችበት ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ዲሞክራሲ አማራጭ የሌለው መንገድ መሆኑን ገልጸው፤ ሰላምና ልማት ሊመጡ የሚችሉት በጠመንጃ ኃይል ሳይሆን ሕዝብ በነፃነት የራሱን መሪ በሚመርጥበት ስልጡን መንገድ ብቻ መሆኑን ተናግረዋል። ኮሚሽነሩ አክለውም፦ "አህጉራችን ከዲሞክራሲ ውጭ ሌላ ምርጫ የላትም። ወደፊት ለመራመድ፣ ዕድገትን ለማረጋገጥና በተለይም ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት ከሁሉ የተሻለው መንገድ ዴሞክራሲ ብቻ ነው" ሲሉ በአፅንኦት ጠቅሰዋል። በአጠቃላይ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ፣ ኢትዮጵያ ተቋማዊ አቅሟንና ሕጋዊ መሠረቷን በማጠናከር ወደ ተሻለ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የተሻገረችበት እና የጋራ የትብብር አቅምን ያሳየችበት አዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ ሆኖ በስኬት ተጠናቋል። ለዚህም ስኬት በየሚናቸው አስተዋጽኦ ላበረከቱ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ዕጩዎች፣ ሲቪል ማኅበራት፣ የጸጥታ ኃይሎች፣ የአፍሪካ ኅብረትና የኢጋድ ታዛቢ ቡድኖች፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች እንዲሁም ሀገር በቀል ታዛቢ ድርጅቶች በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋና ይገባቸዋል። በምርጫው ወቅት የተሰጠው የሕዝብ አመኔታና ድምፅ ለተመራጮች ትልቅ አደራና ኃላፊነትን ጥሏል። ያሸነፉ ፓርቲዎችና ዕጩዎች ይህንን ታሪካዊ አደራ በመሸከም ለሕዝብ ፍላጎት ቅርብ የሆነ አገልግሎት በመስጠት፣ በታማኝነት፣ በቅንነትና ንጹሕ በሆነ ሕሊና በመሥራት የሕዝቡን ተስፋ ወደ ተጨባጭ ውጤት የመቀየር ግዴታ አለባቸው። የምርጫው ትልቁና የመጨረሻው ስኬት የሚለካው በተመራጮችና በሕዝብ መካከል በሚገነባው መተማመን፣ በሚረጋገጠው ዘላቂ ሰላምና ለሁሉም ተጠቃሚነትን በሚያሰፍነው ሀገራዊ ዕድገትና ብልጽግና ብቻ ነው።