ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በሶማሌ ክልል የመጣውን ለውጥና የተመዘገበውን ስኬት የሚገልጥ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ ለማከናወን ጥረት እየተደረገ ነው
Sep 12, 2025 131
ጅግጅጋ ፤ መስከረም 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሶማሌ ክልል የመጣውን ለውጥና የተመዘገበውን ስኬት የሚገልጥ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ ለማከናወን ጥረት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ ለሚገኙ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች የድህረ እውነት ዘመን የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና እና አስተዋጽኦ በተመለከተ ስልጠና ተሰጥቷል። በስልጠናው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ምክትል ቢሮ ሃላፊ በሺር ሼኽ ሰኢድ፤ በፈጣኑ የዲጂታል ዓለም ጠንካራና ከዘመኑ ጋር የሚራመድ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ ያስፈልጋል ብለዋል። ለዚህም የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች የላቀ ዝግጁነት የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ከዲጂታሉ ዓለም ፍጥነት ጋር በመራመድ ትክክለኛ መረጃዎችን በፍጥነት ማጋራትና ሀሰተኛ መረጃዎችን ማጋለጥ እንደሚገባ ተናግረዋል። በሶማሌ ክልል ባለፉት የለውጥ ዓመታት በርካታ አስደናቂ ስኬቶች መመዝገባቸውን አንስተው ከመጣው ውጤት አንፃር ሰፊ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ ይጠይቃል ብለዋል። በክልሉ ከተመዘገበው ውጤት አንፃር በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ እስካሁን የተሰራው ስራ በቂ ባለመሆኑ የመጣውን ለውጥና የተመዘገበውን ስኬት የሚገልጥ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ ለማከናወን ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ የመንግሥት መረጃ አስተዳደር እና አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብድረዛቅ ካፊ፤ የክልሉን ሰላም በማጽናትና የልማት ስራዎችን በማጠናከር ረገድ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ብዙ ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል ሲሉ ተናግረዋል። ከክልሉም ባለፈ ሀገርን በሚመለከት የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጋለጥ ፈጣን፣ እውነተኛና ትክክለኛ መረጃዎችን ማድረስ ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል። በኢትዮጵያ የጋራ የልማት አጀንዳ፣ ዘላቂ ሰላምና ብልፅግናን እውን ለማድረግ የሚያስችሉ ሰፊ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ገልፀው ህብረ ብሔራዊ አንድነትና የጋራ ትርክት በመገንባት ረገድ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ይበልጥ ተቀራርቦና ተቀናጅቶ መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።
በባሌ ዞን ከ800 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ
Sep 12, 2025 131
ሮቤ፤ መስከረም 2/2018 (ኢዜአ)፦ በባሌ ዞን ከ800 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስና የደንብ ልብስ ድጋፍ ተደረገ፡፡ ድጋፉን ያደረጉት በኦሮሚያ ልማት ማህበር የባሌ ቅርንጫፍና በኢትዮ ቴሌኮም የደቡብ ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን ጽህፈት ቤት መሆናቸውም ተመልክቷል። በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የዞኑ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተሻለ ዲሳሳ፤ የተደረገው ድጋፍ በትምህርት ቁሳቁስ ምክንያት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ለመግባት ችግር እንዳይገጥማቸው የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህ በፊት በዞኑ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 60 ሺህ ለሚሆኑ የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶች ድጋፍ መደረጉን አስታውሰው በተጨማሪም ኢትዮ ቴሌኮም እና የኦሮሚያ ልማት ማህበር ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል። የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሀኪም አልይ በበኩላቸው በዞኑ እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሁሉም ህፃናት መደበኛ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። የኦሮሚያ ልማት ማህበር የባሌ ቅርንጫፍና ኢትዮ- ቴሌኮም የደቡብ ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን ያደረጉት ድጋፍ ለሌሎች ተቋማትም ተሞክሮ የሚሆን ነው ብለዋል። የኦሮሚያ ልማት ማህበር የባሌ ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ ማስረሻ ቶላ፤ ማህበሩ በተለያዩ መስኮች ማህበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን አስታውሰው ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉም የዚሁ አካል ነው ብለዋል። በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ እንዳይርቁ ለማድረግ የበኩሉን ጥረት ማድረጉን አንስተው በቀጣይም አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም አረጋግጠዋል። የደቡብ ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን ተወካይ አቶ መሐመድ ሁሴን አብደላ፤ ኩባንያው የቴሌኮም አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ በማህበረሰባዊ አገልግሎት ድጋፍና ትብብር የሚያደርግ መሆኑን አንስተዋል። በዚህም መሰረት በዛሬው እለት ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል። ከድጋፉ ተጠቃሚ ተማሪዎች መካከል ተማሪ ሱመያ ሙአዝ፥ ተቋማቱ ላደረጉላት እገዛና ድጋፍ ምስጋናዋን አቅርባለች።
20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነገ ይጀመራል
Sep 12, 2025 131
አዲስ አበባ፤ መስከረም 2/2018 (ኢዜአ)፦ በጃፓን ቶኪዮ የሚካሄደው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነገ ጅማሮውን ያገኛል። በሻምፒዮናው ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ 200 ገደማ ሀገራት የተወጣጡ ከ2000 በላይ አትሌቶች እንደሚሳተፉ የዓለም አትሌቲክስ መረጃ ያመለክታል። አትሌቶች በ49 የውድድር አይነቶች ላይ ይሳተፋሉ። በሻምፒዮናው መክፈቻ ቀን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚጠበቁባቸው የፍጻሜ ውድድሮች ይካሄዳሉ። ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 ላይ በሚደረገው የሴቶች የ10 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር ጉዳፍ ጸጋይ፣ ፅጌ ገብረሰላማ፣ ፎይተን ተስፋይ እና እጅጋየሁ ታዬ ይወዳደራሉ። ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ላይ በሚደረገው የሴቶች ማራቶን ፍጻሜ አትሌት ትዕግስት አሰፋ፣ ሱቱሜ አሰፋ እና ትዕግስት ከተማ ይሳተፋሉ። የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እስከ መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።
በክልሉ ያሉ እምቅ ሃብቶችን በማልማትና የጋራ እሴቶችን በማጎልበት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ጥረት ይደረጋል- ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
Sep 12, 2025 110
ሀዋሳ ፤ መስከረም 2/2018 (ኢዜአ)፦ በክልሉ ያሉ እምቅ ሃብቶችን በማልማትና የጋራ እሴቶችን በማጎልበት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ጥረት ይደረጋል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፤ በክልሉ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በማሳካት በቀጣይም ለተሻለ ስኬት ለመብቃት የተደረጉ ዝግጅቶችን በማስመልከት ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም በክልሉ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡ መሆኑን አንስተው በቀጣይ ለላቀ ውጤት ተዘጋጅተናል ብለዋል። በየደረጃው ያለው አመራር በቁርጠኝነት ለውጤት ለመብቃት መስራት እንዳለበት አስገንዝበው የህዝቡ የልማት ተሳትፎም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል። በመሆኑም በክልሉ ያሉ እምቅ ሃብቶችን በማልማትና የጋራ እሴቶችን በማጎልበት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ጥረት ይደረጋል ሲሉ ርእሰ መስተዳድሩ አረጋግጠዋል። በክልሉ የገቢ አቅምን ማሳደግ፣ ከተሞችን ማዘመንና ለነዋሪዎች ምቹ ማድረግ የስራ እድል ፈጠራ እና ኢንቨስትመንትን የማስፋፋት ስራ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን አንስተዋል። በክልሉ ያለውን እምቅ ሃብት በማልማት፤ የቡና እና የአትክልትና ፍራፍሬ ልማትን በማጠናከር እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጅነት የመውጣት ጥረትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የቱሪዝም መዳረሻዎችንና የማእድን ሃብቶችን በማልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ የሚታዩ ማነቆዎችን በመፍታት በክልሉ ሁለንተናዊ ልማትን ለማሳካት ተዘጋጅተናል ሲሉም አረጋግጠዋል። በ2018 በትጋት፣ ጽናትና ብቃት በመስራት የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ ለማሳካት በሚደረገው ጥረት ክልሉ ሁነኛ አቅም ሆኖ ለመገኘት የሚያስችለው ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል።
በጉራጌ ዞን የተገነባው አማርድ 2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታው ተጠናቆ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው
Sep 12, 2025 113
ወልቂጤ ፤መስከረም 2/2018 (ኢዜአ)፡- በጉራጌ ዞን የተገነባው አማርድ 2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታው ተጠናቆ ተማሪዎችን እየተቀበለ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ። በዞኑ አዲስ የተገነባው አዳሪ ትምህርት ቤት የላቀ ውጤት ያላቸውን ተማሪዎች በማወዳደር በመቀበል ላይ ሲሆን በተያዘው ዓመት የመማር ማስተማር ስራውን ይጀምራል። የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፤ በ2018 ዓ.ም የአዳሪ ትምህርት ቤቱ ስራ መጀመር ትልቅ ስኬት መሆኑን አንስተው በዞኑ ትምህርትን የማስፋትና ጥራትን የማስጠበቅ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል። የአዳሪ ትምህርት ቤት በማቋቋም ከራሳቸው ተርፈው የሃገሪቱን ራዕይ ለማሳካት የሚችሉ በእውቀታቸው እና በስነ ምግባራቸው ምስጉን የሆኑ ተማሪዎችን ለማስተማር ጥረት ሲደረግ ቆይቷል ብለዋል። መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረትም የአዳሪ ትምህርት ቤቱ ግንባታ በ2013 ዓ/ም ተጀምሮ አሁን ላይ በማጠናቀቅ በተያዘው የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል ብለዋል። የአማርድ 2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት ዘመናዊ የመማሪያ ክፍሎችን ጨምሮ፣ ቤተ ሙከራ፣ ቤተ-መፃህፍት፣ የተማሪዎች ማደሪያና መመግቢያ ክፍሎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችና ሌሎች 19 ዓይነት ግብዓትን የያዘ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል ። ተማሪዎች ለትምህርት የሚያስፈልጉ ግብዓት ተሟልቶላቸው ሙሉ ጊዜያቸውን ትምህርታቸው ላይ እንዲያተኩሩ እንደሚደረግም አስረድተዋል። ለዚህም የመምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች ቅጥርን ጨምሮ ለትምህርት የሚያስፈልጉ የተማሪዎች ቀለብና የትምህርት ቁሳቁስ መሟላቱን አንስተዋል ። ተማሪዎች ወደ አዳሪ ትምህርት ቤቱ ሲገቡ በስነ-ምግባራቸው የተመሰገኑና ከ6ኛ ክፍል ጀምሮ ያላቸው የትምህርት አቀባበል ታሪክን መሰረት በማድረግ እንደሆነ የገለፁት ደግሞ የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወልደ ማርያም ናቸው። ትምህርት ቤቱ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን እንደሚቀበል ገልፀው በዘቢዳር ልማት ኢንሼቲቭ፣ በዞኑ አስተዳደር እና በሌሎች አካላት ጋር የጋራ ትብብር እንደሚተዳደርም ጠቁመዋል። አማርድ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዘንድሮ 120 ተማሪዎችን እንደሚቀበል የተገለፀ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ወደ ተግባር ሲገባ ደግሞ ከ1 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ እንደሚያስተናግድም ተመልክቷል።
ፖለቲካ
በሶማሌ ክልል የመጣውን ለውጥና የተመዘገበውን ስኬት የሚገልጥ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ ለማከናወን ጥረት እየተደረገ ነው
Sep 12, 2025 131
ጅግጅጋ ፤ መስከረም 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሶማሌ ክልል የመጣውን ለውጥና የተመዘገበውን ስኬት የሚገልጥ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ ለማከናወን ጥረት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ ለሚገኙ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች የድህረ እውነት ዘመን የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና እና አስተዋጽኦ በተመለከተ ስልጠና ተሰጥቷል። በስልጠናው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ምክትል ቢሮ ሃላፊ በሺር ሼኽ ሰኢድ፤ በፈጣኑ የዲጂታል ዓለም ጠንካራና ከዘመኑ ጋር የሚራመድ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ ያስፈልጋል ብለዋል። ለዚህም የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች የላቀ ዝግጁነት የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ከዲጂታሉ ዓለም ፍጥነት ጋር በመራመድ ትክክለኛ መረጃዎችን በፍጥነት ማጋራትና ሀሰተኛ መረጃዎችን ማጋለጥ እንደሚገባ ተናግረዋል። በሶማሌ ክልል ባለፉት የለውጥ ዓመታት በርካታ አስደናቂ ስኬቶች መመዝገባቸውን አንስተው ከመጣው ውጤት አንፃር ሰፊ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ ይጠይቃል ብለዋል። በክልሉ ከተመዘገበው ውጤት አንፃር በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ እስካሁን የተሰራው ስራ በቂ ባለመሆኑ የመጣውን ለውጥና የተመዘገበውን ስኬት የሚገልጥ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ ለማከናወን ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ የመንግሥት መረጃ አስተዳደር እና አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብድረዛቅ ካፊ፤ የክልሉን ሰላም በማጽናትና የልማት ስራዎችን በማጠናከር ረገድ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ብዙ ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል ሲሉ ተናግረዋል። ከክልሉም ባለፈ ሀገርን በሚመለከት የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጋለጥ ፈጣን፣ እውነተኛና ትክክለኛ መረጃዎችን ማድረስ ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል። በኢትዮጵያ የጋራ የልማት አጀንዳ፣ ዘላቂ ሰላምና ብልፅግናን እውን ለማድረግ የሚያስችሉ ሰፊ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ገልፀው ህብረ ብሔራዊ አንድነትና የጋራ ትርክት በመገንባት ረገድ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ይበልጥ ተቀራርቦና ተቀናጅቶ መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።
በክልሉ ያሉ እምቅ ሃብቶችን በማልማትና የጋራ እሴቶችን በማጎልበት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ጥረት ይደረጋል- ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
Sep 12, 2025 110
ሀዋሳ ፤ መስከረም 2/2018 (ኢዜአ)፦ በክልሉ ያሉ እምቅ ሃብቶችን በማልማትና የጋራ እሴቶችን በማጎልበት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ጥረት ይደረጋል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፤ በክልሉ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በማሳካት በቀጣይም ለተሻለ ስኬት ለመብቃት የተደረጉ ዝግጅቶችን በማስመልከት ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም በክልሉ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡ መሆኑን አንስተው በቀጣይ ለላቀ ውጤት ተዘጋጅተናል ብለዋል። በየደረጃው ያለው አመራር በቁርጠኝነት ለውጤት ለመብቃት መስራት እንዳለበት አስገንዝበው የህዝቡ የልማት ተሳትፎም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል። በመሆኑም በክልሉ ያሉ እምቅ ሃብቶችን በማልማትና የጋራ እሴቶችን በማጎልበት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ጥረት ይደረጋል ሲሉ ርእሰ መስተዳድሩ አረጋግጠዋል። በክልሉ የገቢ አቅምን ማሳደግ፣ ከተሞችን ማዘመንና ለነዋሪዎች ምቹ ማድረግ የስራ እድል ፈጠራ እና ኢንቨስትመንትን የማስፋፋት ስራ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን አንስተዋል። በክልሉ ያለውን እምቅ ሃብት በማልማት፤ የቡና እና የአትክልትና ፍራፍሬ ልማትን በማጠናከር እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጅነት የመውጣት ጥረትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የቱሪዝም መዳረሻዎችንና የማእድን ሃብቶችን በማልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ የሚታዩ ማነቆዎችን በመፍታት በክልሉ ሁለንተናዊ ልማትን ለማሳካት ተዘጋጅተናል ሲሉም አረጋግጠዋል። በ2018 በትጋት፣ ጽናትና ብቃት በመስራት የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ ለማሳካት በሚደረገው ጥረት ክልሉ ሁነኛ አቅም ሆኖ ለመገኘት የሚያስችለው ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል።
በጋምቤላ ክልል ያለውን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ የፀጥታ መዋቅሩ ይጠናከራል - ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ
Sep 12, 2025 115
ጋምቤላ ፤መስከረም 2/2018 (ኢዜአ)፡-በጋምቤላ ክልል ያለውን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ የፀጥታ መዋቅሩን የማጠናከሩ ተግባር እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ገለፁ። በክልሉ የቦንጋ ፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም የሰለጠኑ የአድማ ብተና የፖሊስ አባላትን ዛሬ አስመርቋል። ወይዘሮ ዓለሚቱ በምረቃው ስነ-ስርዓቱ ላይ እንዳሉት በክልሉ ያለውን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ የፀጥታ መዋቅሩን የማጠናከሩ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል። የክልሉን ሰላም አስተማማኝ በማድረግ የተጀመረውን የልማትና የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ መንግስት በሁሉም መስኮች ያልተቆጠበ ጥረት እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል። በተለይም የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ከማስጠበቅ ባለፈ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸው እንዲከበሩ በማድረግ ረገድ ስኬታማ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል ። ክልሉ አሁን ላይ ያለውን ሰላም ለማፅናትና አስተማማኝ ለማድረግ ተጨማሪ የአድማ ብተና የፖሊስ አባላትን በማሰልጠን ለማስመረቅ መብቃቱን ተናግረዋል። የዕለቱ ተመራቂ የአድማ ብተና የፖሊስ አባላትም በስልጠናው ያገኙትን ክህሎት ወደ ተግባር በመለወጥ የክልሉን ህዝብ ሰላምና ደህንነት በመጠበቅ ረገድ የተጣለባቸውን ኃላፊት በአግባቡ እንዲወጡ ርዕሰ መስተዳድሯ አስገንዝበዋል። የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ማህበር ኮር በበኩላቸው በክልሉ ያለውን አስተማማኝ ሰላም ለማጽናት የፀጥታ መዋቅሩን የማጠናከርና ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት የመስራት ተግባር በመከናወን ላይ መሆኑን ገልጸዋል። ዛሬ የተመረቁት የአድማ ብተና የፖሊስ አባላትም የዚሁ ጥረት አንዱ አካል መሆናቸውን ጠቁመው ይህም የፖሊስ ሰራዊቱን የማብቃት ተግባር ወደ ላቀ ደረጃ ያሳድገዋል ብለዋል። በቦንጋ የፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም ለሶስት ወራት ስልጠናቸውን የተከታተሉት የአድማ ብተና የፖሊስ አባላቱ በቆይታቸው የህግ፣ የሰብዓዊ መብትና መሠረታዊ የፖሊስ ሳይንስ ትምህርት የወሰዱ መሆናቸውም ተመላክቷል።
የከተማዋን ሰላም በማፅናት ለልማት በመትጋት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተዘጋጅተናል
Sep 12, 2025 102
ባህርዳር፤ መስከረም 2/2018 (ኢዜአ) የከተማዋን ሰላም በማፅናት ለልማት በመትጋት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተዘጋጅተናል ሲሉ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ገለጹ። በብልፅግና ፓርቲ የባህር ዳር ከተማ አመራሮች በፓርቲው ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ የውይይት መድረክ እያካሄዱ ነው። በመድረኩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው፤ በለውጡ ዓመታት በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የፖለቲካው መስክ የላቁ ስኬቶች መመዝገባቸውን አንስተዋል። በመሆኑም እነዚህን ውጤቶች ከፍ ባለ መልኩ ለማስቀጠል በተለይም የአመራር አባላቱ የሰላምና የልማት አርአያ በመሆን ለላቀ ውጤት መትጋት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል። የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆን ከሁላችንም ይጠበቃል ሲሉም አንስተዋል። የአመራሩን የማስፈፀም አቅም እና የህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ታክሎበት ለተጀመረው የብልጽግና ጉዞ እና ለታለመው ግብ መሳካት በቅንጅት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል። በዚህ ረገድ የከተማዋን ሰላም በማፅናት ለልማት በመትጋት የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራም ተናግረዋል። የፓርቲው አመራሮች የውይይት መድረክ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል።
በሁሉም መስክ የተሻለ ነገን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የድርሻችንን መወጣት አለብን -ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል
Sep 10, 2025 346
አዲስ አበባ ፤ ጳጉሜን 5/2017(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ በሁሉም መስክ የተሻለ ነገን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የድርሻችንን መወጣት አለብን ሲሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ። ጳጉሜን 5 የነገው ቀን ''ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ'' በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ መርኃ ግብሮች ተከብሯል። በመርሃግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፥ ኢትዮጵያ ወደ ትክክለኛ ከፍታዋ ለመሻገር እየሰራች ነው ብለዋል። እንደ ሀገር ከትናንት የተሻለ ዛሬንና ከዛሬ የተሻለ ነገን እየገነባን ነው ያሉት ሚኒስትሯ ይህን አጠናክሮ ለመቀጠል ብቃት ያለው የሰው ሃይልና የቴክኖሎጂ መዘመን ወሳኝ እንደሆነ ተናግረዋል። ኢትዮጵያውያን ነገን የተሻለ ለማድረግ የተጀመሩ ተግባራትን ለማሳካት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ኢኖቬሽን የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ፣ አይበገሬነትን ለማጽናት እና የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ወሳኝ ናቸው ብለዋል። ትናንት የተመረቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ታላቅ የለውጥ ማሳያ እንደሆነ ተናግረው፤ አዲስ የከፍታ ምዕራፍ መጀመሪያ መሆኑንም ገልጸዋል። በዲጂታል የጎለበተች፣ የምግብ ሉዓላዊነቷን ያረጋገጠች እና ለችግሮች የማትበገር ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ሁላችንም የበኩላችንን መወጣት አለብን ብለዋል። ነገዋን በራሷ የምትፈጥር ኢትዮጵያን እንገንባ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምረቃ ላይ የተገኙት የጂቡቲ እና የሶማሊያ ፕሬዝዳንቶች ወደ ሀገራቸው ተሸኙ
Sep 10, 2025 278
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2017(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ እና በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የምረቃ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የጂቡቲ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌህ እና የሶማሊያ ፌዴራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ በኢትዮጵያ የነበራቸውን ስኬታማ ቆይታ አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተሸኝተዋል። ለፕሬዝዳንቶቹ በቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የክብር ሳሎን በመገኘት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምረቃ ላይ የተገኙት ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ወደ ሀገራቸው ተሸኙ
Sep 10, 2025 259
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2017(ኢዜአ)፦ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የምረቃ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ሚያርዲት በኢትዮጵያ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተሸኝተዋል። የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ(ዶ/ር) እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኝት ለፕሬዝዳንቱ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል ።
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ለቀጣናው ጸጥታ እና መረጋጋት ብሎም ልማትን ለማረጋገጥ ያላቸውን ጽኑ አቋም አረጋገጡ
Sep 10, 2025 293
አዲስ አበበ፤ጳጉሜን 5/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ለቀጣናው ጸጥታ እና መረጋጋት ብሎም ልማትን ለማረጋገጥ ያላቸውን ጽኑ አቋም አረጋግጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሀሰን ሼህ መሃሙድን ዛሬ ጠዋት በጸህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ ከፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ጋር የጋራ ፍላጎት ባለን ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል ብለዋል። በዚህም በቀጠናችን ፀጥታ እና መረጋጋት ብሎም ልማትን ለማረጋገጥ ያለንን ፅኑ አቋም በድጋሜ አረጋግጠናል ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት።
ፖለቲካ
በሶማሌ ክልል የመጣውን ለውጥና የተመዘገበውን ስኬት የሚገልጥ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ ለማከናወን ጥረት እየተደረገ ነው
Sep 12, 2025 131
ጅግጅጋ ፤ መስከረም 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሶማሌ ክልል የመጣውን ለውጥና የተመዘገበውን ስኬት የሚገልጥ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ ለማከናወን ጥረት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ ለሚገኙ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች የድህረ እውነት ዘመን የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና እና አስተዋጽኦ በተመለከተ ስልጠና ተሰጥቷል። በስልጠናው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ምክትል ቢሮ ሃላፊ በሺር ሼኽ ሰኢድ፤ በፈጣኑ የዲጂታል ዓለም ጠንካራና ከዘመኑ ጋር የሚራመድ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ ያስፈልጋል ብለዋል። ለዚህም የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች የላቀ ዝግጁነት የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ከዲጂታሉ ዓለም ፍጥነት ጋር በመራመድ ትክክለኛ መረጃዎችን በፍጥነት ማጋራትና ሀሰተኛ መረጃዎችን ማጋለጥ እንደሚገባ ተናግረዋል። በሶማሌ ክልል ባለፉት የለውጥ ዓመታት በርካታ አስደናቂ ስኬቶች መመዝገባቸውን አንስተው ከመጣው ውጤት አንፃር ሰፊ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ ይጠይቃል ብለዋል። በክልሉ ከተመዘገበው ውጤት አንፃር በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ እስካሁን የተሰራው ስራ በቂ ባለመሆኑ የመጣውን ለውጥና የተመዘገበውን ስኬት የሚገልጥ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ ለማከናወን ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ የመንግሥት መረጃ አስተዳደር እና አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብድረዛቅ ካፊ፤ የክልሉን ሰላም በማጽናትና የልማት ስራዎችን በማጠናከር ረገድ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ብዙ ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል ሲሉ ተናግረዋል። ከክልሉም ባለፈ ሀገርን በሚመለከት የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጋለጥ ፈጣን፣ እውነተኛና ትክክለኛ መረጃዎችን ማድረስ ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል። በኢትዮጵያ የጋራ የልማት አጀንዳ፣ ዘላቂ ሰላምና ብልፅግናን እውን ለማድረግ የሚያስችሉ ሰፊ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ገልፀው ህብረ ብሔራዊ አንድነትና የጋራ ትርክት በመገንባት ረገድ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ይበልጥ ተቀራርቦና ተቀናጅቶ መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።
በክልሉ ያሉ እምቅ ሃብቶችን በማልማትና የጋራ እሴቶችን በማጎልበት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ጥረት ይደረጋል- ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
Sep 12, 2025 110
ሀዋሳ ፤ መስከረም 2/2018 (ኢዜአ)፦ በክልሉ ያሉ እምቅ ሃብቶችን በማልማትና የጋራ እሴቶችን በማጎልበት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ጥረት ይደረጋል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፤ በክልሉ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በማሳካት በቀጣይም ለተሻለ ስኬት ለመብቃት የተደረጉ ዝግጅቶችን በማስመልከት ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም በክልሉ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡ መሆኑን አንስተው በቀጣይ ለላቀ ውጤት ተዘጋጅተናል ብለዋል። በየደረጃው ያለው አመራር በቁርጠኝነት ለውጤት ለመብቃት መስራት እንዳለበት አስገንዝበው የህዝቡ የልማት ተሳትፎም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል። በመሆኑም በክልሉ ያሉ እምቅ ሃብቶችን በማልማትና የጋራ እሴቶችን በማጎልበት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ጥረት ይደረጋል ሲሉ ርእሰ መስተዳድሩ አረጋግጠዋል። በክልሉ የገቢ አቅምን ማሳደግ፣ ከተሞችን ማዘመንና ለነዋሪዎች ምቹ ማድረግ የስራ እድል ፈጠራ እና ኢንቨስትመንትን የማስፋፋት ስራ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን አንስተዋል። በክልሉ ያለውን እምቅ ሃብት በማልማት፤ የቡና እና የአትክልትና ፍራፍሬ ልማትን በማጠናከር እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጅነት የመውጣት ጥረትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የቱሪዝም መዳረሻዎችንና የማእድን ሃብቶችን በማልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ የሚታዩ ማነቆዎችን በመፍታት በክልሉ ሁለንተናዊ ልማትን ለማሳካት ተዘጋጅተናል ሲሉም አረጋግጠዋል። በ2018 በትጋት፣ ጽናትና ብቃት በመስራት የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ ለማሳካት በሚደረገው ጥረት ክልሉ ሁነኛ አቅም ሆኖ ለመገኘት የሚያስችለው ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል።
በጋምቤላ ክልል ያለውን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ የፀጥታ መዋቅሩ ይጠናከራል - ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ
Sep 12, 2025 115
ጋምቤላ ፤መስከረም 2/2018 (ኢዜአ)፡-በጋምቤላ ክልል ያለውን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ የፀጥታ መዋቅሩን የማጠናከሩ ተግባር እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ገለፁ። በክልሉ የቦንጋ ፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም የሰለጠኑ የአድማ ብተና የፖሊስ አባላትን ዛሬ አስመርቋል። ወይዘሮ ዓለሚቱ በምረቃው ስነ-ስርዓቱ ላይ እንዳሉት በክልሉ ያለውን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ የፀጥታ መዋቅሩን የማጠናከሩ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል። የክልሉን ሰላም አስተማማኝ በማድረግ የተጀመረውን የልማትና የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ መንግስት በሁሉም መስኮች ያልተቆጠበ ጥረት እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል። በተለይም የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ከማስጠበቅ ባለፈ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸው እንዲከበሩ በማድረግ ረገድ ስኬታማ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል ። ክልሉ አሁን ላይ ያለውን ሰላም ለማፅናትና አስተማማኝ ለማድረግ ተጨማሪ የአድማ ብተና የፖሊስ አባላትን በማሰልጠን ለማስመረቅ መብቃቱን ተናግረዋል። የዕለቱ ተመራቂ የአድማ ብተና የፖሊስ አባላትም በስልጠናው ያገኙትን ክህሎት ወደ ተግባር በመለወጥ የክልሉን ህዝብ ሰላምና ደህንነት በመጠበቅ ረገድ የተጣለባቸውን ኃላፊት በአግባቡ እንዲወጡ ርዕሰ መስተዳድሯ አስገንዝበዋል። የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ማህበር ኮር በበኩላቸው በክልሉ ያለውን አስተማማኝ ሰላም ለማጽናት የፀጥታ መዋቅሩን የማጠናከርና ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት የመስራት ተግባር በመከናወን ላይ መሆኑን ገልጸዋል። ዛሬ የተመረቁት የአድማ ብተና የፖሊስ አባላትም የዚሁ ጥረት አንዱ አካል መሆናቸውን ጠቁመው ይህም የፖሊስ ሰራዊቱን የማብቃት ተግባር ወደ ላቀ ደረጃ ያሳድገዋል ብለዋል። በቦንጋ የፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም ለሶስት ወራት ስልጠናቸውን የተከታተሉት የአድማ ብተና የፖሊስ አባላቱ በቆይታቸው የህግ፣ የሰብዓዊ መብትና መሠረታዊ የፖሊስ ሳይንስ ትምህርት የወሰዱ መሆናቸውም ተመላክቷል።
የከተማዋን ሰላም በማፅናት ለልማት በመትጋት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተዘጋጅተናል
Sep 12, 2025 102
ባህርዳር፤ መስከረም 2/2018 (ኢዜአ) የከተማዋን ሰላም በማፅናት ለልማት በመትጋት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተዘጋጅተናል ሲሉ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ገለጹ። በብልፅግና ፓርቲ የባህር ዳር ከተማ አመራሮች በፓርቲው ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ የውይይት መድረክ እያካሄዱ ነው። በመድረኩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው፤ በለውጡ ዓመታት በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የፖለቲካው መስክ የላቁ ስኬቶች መመዝገባቸውን አንስተዋል። በመሆኑም እነዚህን ውጤቶች ከፍ ባለ መልኩ ለማስቀጠል በተለይም የአመራር አባላቱ የሰላምና የልማት አርአያ በመሆን ለላቀ ውጤት መትጋት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል። የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆን ከሁላችንም ይጠበቃል ሲሉም አንስተዋል። የአመራሩን የማስፈፀም አቅም እና የህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ታክሎበት ለተጀመረው የብልጽግና ጉዞ እና ለታለመው ግብ መሳካት በቅንጅት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል። በዚህ ረገድ የከተማዋን ሰላም በማፅናት ለልማት በመትጋት የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራም ተናግረዋል። የፓርቲው አመራሮች የውይይት መድረክ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል።
በሁሉም መስክ የተሻለ ነገን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የድርሻችንን መወጣት አለብን -ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል
Sep 10, 2025 346
አዲስ አበባ ፤ ጳጉሜን 5/2017(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ በሁሉም መስክ የተሻለ ነገን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የድርሻችንን መወጣት አለብን ሲሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ። ጳጉሜን 5 የነገው ቀን ''ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ'' በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ መርኃ ግብሮች ተከብሯል። በመርሃግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፥ ኢትዮጵያ ወደ ትክክለኛ ከፍታዋ ለመሻገር እየሰራች ነው ብለዋል። እንደ ሀገር ከትናንት የተሻለ ዛሬንና ከዛሬ የተሻለ ነገን እየገነባን ነው ያሉት ሚኒስትሯ ይህን አጠናክሮ ለመቀጠል ብቃት ያለው የሰው ሃይልና የቴክኖሎጂ መዘመን ወሳኝ እንደሆነ ተናግረዋል። ኢትዮጵያውያን ነገን የተሻለ ለማድረግ የተጀመሩ ተግባራትን ለማሳካት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ኢኖቬሽን የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ፣ አይበገሬነትን ለማጽናት እና የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ወሳኝ ናቸው ብለዋል። ትናንት የተመረቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ታላቅ የለውጥ ማሳያ እንደሆነ ተናግረው፤ አዲስ የከፍታ ምዕራፍ መጀመሪያ መሆኑንም ገልጸዋል። በዲጂታል የጎለበተች፣ የምግብ ሉዓላዊነቷን ያረጋገጠች እና ለችግሮች የማትበገር ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ሁላችንም የበኩላችንን መወጣት አለብን ብለዋል። ነገዋን በራሷ የምትፈጥር ኢትዮጵያን እንገንባ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምረቃ ላይ የተገኙት የጂቡቲ እና የሶማሊያ ፕሬዝዳንቶች ወደ ሀገራቸው ተሸኙ
Sep 10, 2025 278
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2017(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ እና በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የምረቃ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የጂቡቲ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌህ እና የሶማሊያ ፌዴራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ በኢትዮጵያ የነበራቸውን ስኬታማ ቆይታ አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተሸኝተዋል። ለፕሬዝዳንቶቹ በቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የክብር ሳሎን በመገኘት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምረቃ ላይ የተገኙት ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ወደ ሀገራቸው ተሸኙ
Sep 10, 2025 259
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2017(ኢዜአ)፦ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የምረቃ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ሚያርዲት በኢትዮጵያ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተሸኝተዋል። የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ(ዶ/ር) እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኝት ለፕሬዝዳንቱ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል ።
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ለቀጣናው ጸጥታ እና መረጋጋት ብሎም ልማትን ለማረጋገጥ ያላቸውን ጽኑ አቋም አረጋገጡ
Sep 10, 2025 293
አዲስ አበበ፤ጳጉሜን 5/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ለቀጣናው ጸጥታ እና መረጋጋት ብሎም ልማትን ለማረጋገጥ ያላቸውን ጽኑ አቋም አረጋግጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሀሰን ሼህ መሃሙድን ዛሬ ጠዋት በጸህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ ከፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ጋር የጋራ ፍላጎት ባለን ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል ብለዋል። በዚህም በቀጠናችን ፀጥታ እና መረጋጋት ብሎም ልማትን ለማረጋገጥ ያለንን ፅኑ አቋም በድጋሜ አረጋግጠናል ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት።
ማህበራዊ
በባሌ ዞን ከ800 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ
Sep 12, 2025 131
ሮቤ፤ መስከረም 2/2018 (ኢዜአ)፦ በባሌ ዞን ከ800 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስና የደንብ ልብስ ድጋፍ ተደረገ፡፡ ድጋፉን ያደረጉት በኦሮሚያ ልማት ማህበር የባሌ ቅርንጫፍና በኢትዮ ቴሌኮም የደቡብ ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን ጽህፈት ቤት መሆናቸውም ተመልክቷል። በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የዞኑ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተሻለ ዲሳሳ፤ የተደረገው ድጋፍ በትምህርት ቁሳቁስ ምክንያት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ለመግባት ችግር እንዳይገጥማቸው የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህ በፊት በዞኑ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 60 ሺህ ለሚሆኑ የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶች ድጋፍ መደረጉን አስታውሰው በተጨማሪም ኢትዮ ቴሌኮም እና የኦሮሚያ ልማት ማህበር ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል። የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሀኪም አልይ በበኩላቸው በዞኑ እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሁሉም ህፃናት መደበኛ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። የኦሮሚያ ልማት ማህበር የባሌ ቅርንጫፍና ኢትዮ- ቴሌኮም የደቡብ ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን ያደረጉት ድጋፍ ለሌሎች ተቋማትም ተሞክሮ የሚሆን ነው ብለዋል። የኦሮሚያ ልማት ማህበር የባሌ ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ ማስረሻ ቶላ፤ ማህበሩ በተለያዩ መስኮች ማህበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን አስታውሰው ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉም የዚሁ አካል ነው ብለዋል። በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ እንዳይርቁ ለማድረግ የበኩሉን ጥረት ማድረጉን አንስተው በቀጣይም አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም አረጋግጠዋል። የደቡብ ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን ተወካይ አቶ መሐመድ ሁሴን አብደላ፤ ኩባንያው የቴሌኮም አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ በማህበረሰባዊ አገልግሎት ድጋፍና ትብብር የሚያደርግ መሆኑን አንስተዋል። በዚህም መሰረት በዛሬው እለት ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል። ከድጋፉ ተጠቃሚ ተማሪዎች መካከል ተማሪ ሱመያ ሙአዝ፥ ተቋማቱ ላደረጉላት እገዛና ድጋፍ ምስጋናዋን አቅርባለች።
በጉራጌ ዞን የተገነባው አማርድ 2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታው ተጠናቆ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው
Sep 12, 2025 113
ወልቂጤ ፤መስከረም 2/2018 (ኢዜአ)፡- በጉራጌ ዞን የተገነባው አማርድ 2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታው ተጠናቆ ተማሪዎችን እየተቀበለ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ። በዞኑ አዲስ የተገነባው አዳሪ ትምህርት ቤት የላቀ ውጤት ያላቸውን ተማሪዎች በማወዳደር በመቀበል ላይ ሲሆን በተያዘው ዓመት የመማር ማስተማር ስራውን ይጀምራል። የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፤ በ2018 ዓ.ም የአዳሪ ትምህርት ቤቱ ስራ መጀመር ትልቅ ስኬት መሆኑን አንስተው በዞኑ ትምህርትን የማስፋትና ጥራትን የማስጠበቅ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል። የአዳሪ ትምህርት ቤት በማቋቋም ከራሳቸው ተርፈው የሃገሪቱን ራዕይ ለማሳካት የሚችሉ በእውቀታቸው እና በስነ ምግባራቸው ምስጉን የሆኑ ተማሪዎችን ለማስተማር ጥረት ሲደረግ ቆይቷል ብለዋል። መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረትም የአዳሪ ትምህርት ቤቱ ግንባታ በ2013 ዓ/ም ተጀምሮ አሁን ላይ በማጠናቀቅ በተያዘው የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል ብለዋል። የአማርድ 2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት ዘመናዊ የመማሪያ ክፍሎችን ጨምሮ፣ ቤተ ሙከራ፣ ቤተ-መፃህፍት፣ የተማሪዎች ማደሪያና መመግቢያ ክፍሎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችና ሌሎች 19 ዓይነት ግብዓትን የያዘ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል ። ተማሪዎች ለትምህርት የሚያስፈልጉ ግብዓት ተሟልቶላቸው ሙሉ ጊዜያቸውን ትምህርታቸው ላይ እንዲያተኩሩ እንደሚደረግም አስረድተዋል። ለዚህም የመምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች ቅጥርን ጨምሮ ለትምህርት የሚያስፈልጉ የተማሪዎች ቀለብና የትምህርት ቁሳቁስ መሟላቱን አንስተዋል ። ተማሪዎች ወደ አዳሪ ትምህርት ቤቱ ሲገቡ በስነ-ምግባራቸው የተመሰገኑና ከ6ኛ ክፍል ጀምሮ ያላቸው የትምህርት አቀባበል ታሪክን መሰረት በማድረግ እንደሆነ የገለፁት ደግሞ የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወልደ ማርያም ናቸው። ትምህርት ቤቱ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን እንደሚቀበል ገልፀው በዘቢዳር ልማት ኢንሼቲቭ፣ በዞኑ አስተዳደር እና በሌሎች አካላት ጋር የጋራ ትብብር እንደሚተዳደርም ጠቁመዋል። አማርድ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዘንድሮ 120 ተማሪዎችን እንደሚቀበል የተገለፀ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ወደ ተግባር ሲገባ ደግሞ ከ1 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ እንደሚያስተናግድም ተመልክቷል።
ዕድሜው ለትምህርት የደረሰ ልጅን ወደ ትምህርት ቤት አለመላክ ያስጠይቃል - ትምህርት ሚኒስቴር
Sep 12, 2025 98
አዲስ አበባ፤ መስከረም 2/2018 (ኢዜአ)፦ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ነጻና ግዴታ መሆኑን በመገንዘብ ወላጅ ወይም አሳዳጊ ዕድሜው ለትምህርት የደረሰ ልጅን ወደ ትምህርት ቤት መላክ እንዳለበት ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ። በኢትዮጵያ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ከ7 ሚሊዮን በላይ ህጻናት በተለያዩ ምክንያቶች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ መግለጹ ይታወቃል። እነዚህን ልጆች ወደ ትምህርት ቤት የማስገባት ሀገራዊ ንቅናቄን በመቀላቀል የዜግነት ግዴታን በመወጣት ሁሉንም ወደ ትምህርት ቤት እንዲገቡ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም አመላክቷል። በሚኒስቴሩ የትምህርት ፕሮግራሞችና ሥርዓት ማሻሻል ዴስክ ኃላፊ ዳዊት አዘነ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ከቅድመ መደበኛ እስከ 8ኛ ክፍል ከተመዘገቡት ውስጥ ለ60 በመቶው የትምህርት ቤት ምገባ ተደራሽ ይደረጋል። የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ነጻ እና ግዴታ መሆን በትምህርት ሕጉ መደንገጉን አስታውቀው፤ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆችን ወደ ትምህርት ቤት አለመላክ በሕግ እንደሚያስጠይቅም አሳስበዋል። ወላጆች፣ አሳዳጊዎች፣ ሕብረተሰቡና ባለድርሻ አካላት ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆች ከትምህርት ገበታ ውጭ እንዳይሆኑ ሊረባረቡ ይገባል ነው ያሉት። በ2018 ከቅድመ መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል 31 ነጥብ 9 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለማስተማር መታቀዱን እና ከእነዚህ መካከል 15 ሚሊዮኑ ሴቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል። ሰላም ባልተረጋገጠባቸው አካባቢዎች፣ በኢኮኖሚ እጥረት እና የልጆችን ጉልበት በመፈለግ ምክንያት በ2017 የትምህርት ዘመን ከ7 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ እንደነበሩም አውስተዋል። በ2018 የትምህርት ዘመን በትምህርት ገበታ ላይ እንዲገኙ የታቀደው 31 ነጥብ 9 ሚሊዮንም ባለፈው ዓመት ከትምህርት ገበታ ውጭ የነበሩትን እንደሚያጠቃልል አስታውቀዋል። ዕቅዱን ለማሳካትም ሚኒስቴሩ በሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የተማሪዎች ተሳትፎ የንቅናቄ ሠነድ አዘጋጅቶ ከክልሎች እና ባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ በማድረግ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም መሠረት ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆች ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ ለማስቻል ለማኅበረሰቡና ባለድርሻ አካላት ግንዛቤ መፍጠር አንዱ የሠነዱ ትኩረት መሆኑን ጠቅሰዋል። የተማሪ ተሳትፎ ዕቅድን ለማካካስ የሚያስችሉ ሁነቶችን ማዘጋጀት ሁለተኛው የሠነዱ ትኩረት መሆኑን ጠቁመው፤ የምዝገባ ሳምንት፣ የግቢ ጽዳት ሳምንት፣ የቤት ለቤት ቅስቀሳ እንዲሁም የትምህርት ቁሳቁስ የማሰባሰቢያ ሳምንት እንዲዘጋጁ ማድረግ መሆኑን አብራርተዋል። ሦስተኛው ሰላምን የማጽናት ስራ እየተከናወነባቸው ባሉ አካባቢዎች ተማሪዎች በሚፈለገው ልክ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ በዋናነት የአካባቢው ማኅበረሰብ፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ትምህርት ቤቶችን ለመማር ማስተማር ምቹ እንዲሆኑ እንዲሠሩ ማድረግ ነው ብለዋል። ከነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ የትምህርት ምዝገባ እና ተጓዳኝ ተግባራት በጥሩ ሁኔታ እየተከናወኑ መሆኑን አረጋግጠዋል። ሁሉም ትምህርት ቤቶች ከመስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለትምህርት ክፍት ሆነው ማስተማር እንደሚጀምሩም አስታውቀዋል።
ደም በመለገስ የሰው ሕይወትን መታደግ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በኢሉባቦር ዞን ነዋሪዎች ተናገሩ
Sep 12, 2025 72
መቱ፤ መስከረም 2/2018 (ኢዜአ)፡- በኢሉባቦር ዞን ደም በመለገስ የሰው ሕይወትን መታደግ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች የሕብረተሰብ ክፍሎች ገለጹ። ከለጋሾቹ መካከል የሀሉ ወረዳ ነዋሪ ወጣት ስንታየሁ ግርማ በደም እጥረት ለሚቸገሩ ወገኖች ደሙን በመለገሱ ደስተኛ መሆኑን አንስቶ ይህ መልካም ስራ ለአዕምሮ ዕረፍት ነው ብሏል። "ልገሳውን እቀጥላለሁ" ያለው ወጣቱ ወጣቶችም ሆኑ ሌላው የሕብረተሰብ ክፍል በተግባሩ እንዲሳተፉ መልክት አስተላልፏል። በተለይም በወሊድ ምክንያት የሚጎዱ እናቶችን ሕይወት ለመታደግ በልገሳም ሆነ በማስተባበር የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ የገለጸው ደግሞ በመቱ ከተማ የወጣቶች አደረጃጀት ዘርፍ ተጠሪ ወጣት አቤኔዘር ተመስገን ነው። የመቱ ደም ባንክ ስራ አስኪያጅ አቶ አማረ ደስታ በበኩላቸው በበጀት ዓመቱ በደም እጥረት ምክንያት ሊደርስ የሚችለውን ችግር ለመከላከል ሰባት ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በሚሰበሰበው ደም መቱ ከተማን ጨምሮ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ እና ሸካ ዞኖችን ተደራሽ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል። በበጀት ዓመቱ የደም ለጋሾችን ለማብዛት የግንዛቤ ስራን ጨምሮ ሌሎች ስራዎችን በትኩረት እየሰሩ መሆኑንም ገልጸዋል። በአከባቢዎቹ በመደበኛነት ደም በመለገስ ከሚታወቁት ዜጎች ባሻገር በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ወጣቶችና ሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች ትልቅ እገዛ እያደረጉ እንደሚገኙም አክለዋል። በ2017 በጀት ዓመት ከ5 ሺህ 900 በላይ ዩኒት ደም መሰብሰብ መቻሉን ገልጸው፤ በ2018 በጀት ዓመት ሰባት ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ አቅደው እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
ኢኮኖሚ
ክልሉ በተያዘው ዓመት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካትን ቀዳሚ አጀንዳ አድርጎ እየሰራ ነው
Sep 12, 2025 110
ባህርዳር ፤ መስከረም 2/2018 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በተያዘው ዓመት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካትን ቀዳሚ አጀንዳ አድርጎ እየሰራ መሆኑን የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ። የክልሉ ሰላም እየተረጋጋ በመምጣቱ ተኪ ምርቶችን ከማምረት ጎን ለጎን ከ4 ሺህ 600 በላይ ባለሃብቶችን በአዲስ መልክ ወደ ክልሉ ለመሳብ ቢሮው ትኩረት መስጠቱም ተመላክቷል። የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ ለኢዜአ እንደገለጹት ቢሮው ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካትን ቀዳሚ አጀንዳ አድርጎ እየሰራ ነው። በተለይም በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከውጭ ይገቡ የነበሩ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት ለኢኮኖሚው ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው አንስተዋል። ከተኪ ምርቶች ውስጥም ምግብና ምግብ ነክ፣ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ መድኃኒትና ማህበረሰቡ በየዕለቱ የሚጠቀምባቸው የተለያዩ ምርቶች እንደሚገኙበትም ጠቁመዋል። በዚህም በበጀት ዓመቱ የክልሉ መንግስት ሊያወጣ የሚችለውን ከ560 ነጥብ 97 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ለማዳን ግብ አስቀምጦ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል። እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኙ የወጪ ምርቶችን በብዛትና በጥራት አምርቶ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። ከዚህም ከ167 ነጥብ 17 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ገቢ ለሀገሪቷ ለማስገኘት ቢሮው ትኩረት ሰጥቶ የድጋፍና ክትትል ተግባሩን አጠናክሮ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የክልሉ ሰላም እየተረጋጋ በመምጣቱም 4 ሺህ 600 የውጭና የሀገር ውስጥ ኢንቨስተሮች በበጀት ዓመቱ ወደ ክልሉ መጥተው መዋዕለ ንዋያቸውን ፈሰስ በማድረግ ራሳቸውንና ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን አስታውቀዋል። የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ብርሃን ገብረህይወት በበኩላቸው በከተማ አስተዳደራቸው ከ60 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች ተኪ ምርትን በብዛትና በጥራት እያመረቱ መሆኑን ተናግረዋል። ከሰባት የሚበልጡ ኢንዱስትሪዎች ደግሞ በውጭ ምንዛሬ ገቢ የሚያስገኙ ምርቶችን በትኩረት እያመረቱ ነው ብለዋል። በተለይም በቴክስታይልና ጋርመንት፣ በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ በኬሚካል፣ በቆዳና ቆዳ ውጤቶች ዘርፍ የተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ተኪ ምርት በማምረት ረገድ ላቅ ያለ ሚና እንዳላቸውም አብራርተዋል። በተያዘው ዓመትም የውጭና የሀገር ውስጥ ባለሃብቶችን ወደ ከተማዋ በመሳብ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካቱ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለአፍሪካዊያን ትልቅ ኩራት እና መነሳሳትን የሚፈጥር ነው
Sep 12, 2025 176
አዲስ አበባ፤ መስከረም 2/2018 (ኢዜአ)፦ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለአፍሪካዊያን ትልቅ ኩራት እና መነሳሳትን የሚፈጥር መሆኑን አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ተናገሩ፡፡ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ለቀጣናዊ ትስስር ያለው አበርክቶም የጎላ ስለመሆኑ አስተያየት ሰጪዎቹ ጠቁመዋል፡፡ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባለፈዉ ሳምንት ጳጉሜን 4 ቀን 2017 በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በይፋ መመረቁ ይታወቃል፡፡ ግድቡ የኃይል አቅርቦትን በመጨመርና የኢኮኖሚ ዕድገትን በማፋጠን ረገድ ለኢትዮጵያ ህዝብ የአዲስ ዓመት በረከት ተደርጎም የሚወሰድ ነው፡፡ በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙ የጎረቤት ሀገራት መሪዎች ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መግዛት እንደሚፈልጉም ባደረጉት ንግግር አረጋግጠዋል፡፡ ይህም ግድቡ ከኢትዮጵያ የተሻገረ አፍሪካዊ በረከት መሆኑን በግልጽ ያሳየም ሆኗል፡፡ ከዓለም 10 ታላላቅ ግድቦች አንዱ የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ በራስ አቅም መገንባቱ ለአፍሪካ ትልቅ ኩራት እና መነሳሳትን የፈጠረ ጉዳይ መሆኑንም የተለያዩ አፍሪካዋያን ተናግረዋል። በኢንቴቤ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የበረራ ተቆጣጣሪ የሆኑት ዛም ዛም ግድቡ ያለ አንዳች የውጭ ድጋፍ መገንባቱ የሚያኮራ ነው ብለዋል፡፡ በኬንያ አካባቢ፣ አየር ንብረት ለውጥ እና ደን ልማት ሚኒስቴር የአየር ንብረት ለውጥ ምክትል ዳይሬክተር ሚካኤል ኦኩሙ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ መንግስት እንደዚህ ዓይነት ግዙፍ እና አስደናቂ ግድብ መገንባቱ ትልቅ እንቅስቃሴ ነው ብለዋል፡፡ ግድቡ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካዊያን ትልቅ አበርክቶ እንደሚኖረውም ጠቁመዋል፡፡ በኢንቴቤ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የበረራ ተቆጣጣሪ ዛም ዛም ግድቡ ቀጣናዊ ትስስርን በማሳለጥ ረገድ ዓይነተኛ ሚና እንደሚጫወትም ገልጸዋል፡፡ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚመነጨው ንጹህ ሃይል በመሆኑ በአህጉሪቱ ለሚደረገው አየር ንብረት ለውጥ ትግል ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ጠቁመዋል፡፡ በኬንያ የአካባቢ፣ አየር ንብረት ለውጥ እና ደን ልማት ሚኒስቴር የአየር ንብረት ለውጥ ምክትል ዳይሬክተር ሚካኤል ኦኩሙ ግድቡ የኢትዮጵያን እና የአፍሪካ ሀገራትን ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም የሃይል አቅርቦቱ በቀጣናው ያለውን ኢንዱስትሪ ልማት እንደሚያፋጥንም ጠቁመዋል፡፡ የሕዳሴ ግድብ ባለፈዉ ሳምንት ጳጉሜን 4 ቀን 2017 በይፋ ሲመረቅ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የጂቡቲ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌህ፣ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼኽ መሐመድ፣ የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር፣ እና ሌሎች የአፍሪካ እና ካረቢያን ሀገራት መሪዎች መገኝታቸው ይታወቃል፡፡
በባሌ ዞን በሰው ሰራሽ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ዘዴ ውጤት እያገኙ መሆናቸውን አርሶ አደሮች ገለጹ
Sep 12, 2025 198
ሮቤ፤ መስከረም 2/2018(ኢዜአ) :-በሰው ሰራሽ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ዘዴ ጥሩ ውጤት እያገኙ መሆናቸውን በባሌ ዞን የዲንሾ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለፁ። በዞኑ በተያዘው በጀት ዓመት ከ97 ሺህ የሚበልጡ የእንስሳት ዝርያን በማሻሻል የወተትና ስጋ ተዋጽኦ ጥራትና መጠን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የገለጸው ደግሞ የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ነው። አስተያየታቸውን ከሰጡ የዲንሾ ወረዳ አርሶ አደሮች መካከል አቶ ሁሴን አብዱረህማን እንዳሉት፤ ከዚህ ቀደም ካላቸው ላሞች የሚያገኙት የወተት ምርት ከድካማቸው ጋር ሲነፃፀር እምብዛም አይደለም። ካለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ በሰው ሰራሽ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ዘዴ ከተዳቀሉ ከብቶቻቸው እያገኙ ያሉት የወተት ምርት በቀን በአማካይ ከሶስት ሊትር ወደ 15 ሊትር መጨመሩንና ተጠቃሚነታቸው ማደጉን ተናግረዋል። ከሶስት አመታት በፊት በዚህ ዘዴ ካዳቀሏት ላም የተገኘው ወይፈን ለእርሻ መድረሱን የጠቆሙት አርሶ አደሩ፤ በዘርፉ የተሻለ ተጠቃሚ ለመሆን ሌሎች ለሞቻቸውን እያዳቀሉ እንደሚገኙ አመልክተዋል። ወይዘሮ አሽረቃ ሱሌይማን በበኩላቸው በሰው ሰራሽ ዘዴ ከተዳቀሉ ላሞቻቸው እያገኙ ያሉት የወተት ምርት መጠን በቀን በአማካይ ከሶስት ወደ 10 ሊትር የጨመረ መሆኑን አንስተው፤ በዚህም የተሻለ ጥቅም ማግኘታቸውን ተናግረዋል። ከላሞቻቸው የሚያገኙትን ወተት በማኮናተር በሚያገኙት ገቢ በዲንሾ ከተማ የተሻላ መኖሪያ ቤት ከመሥራት ባለፈ ልጆቻቸውን በተሻለ ትምህርት ቤት እያስተማሩ መሆኑን አክለዋል። ከዚህ በፊት የነበራቸው የአካባቢው ዝርያ ላሞች የሚወልዷቸው ጥጆች አድገው በገበያ ጥሩ ገንዘብ ለማስገኘትም ሆነ የወተት ምርት የሚሰጡበት ጊዜ ከተዳቀሉት ጋር ሲነፃፀር ረዥም ጊዜ የሚያስጠብቅ መሆኑን ያነሱት ደግሞ ሌላው የወረዳው አርሶ አደር አቶ ተማም ጀማል ናቸው። በሰው ሰራሽ ዘዴ ተዳቅለው የሚወለዱ ጊደሮች ከሶስት ዓመት በታች በሆነ ጊዜ የሚወልዱ መሆናቸውን በማሳያነት አንስተዋል። የዲንሾ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርናና መሬት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዙቤር አብዱለጥፍ በበኩላቸው፣ በሰው ሰራሽ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ዘዴ የሚዳቀሉ ከብቶች ውጤታማነት ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል። በባህላዊ ዘዴ ከሚደረገው የእንስሳት ልማት የተሻለ የወተትና የስጋ ምርት እንደሚያስገኝ በመረጋገጡም የተጠቃሚ አርሶ አደሩ ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል። በተያዘው በጀት ዓመትም በወረዳው ከ12ሺህ የሚበልጡ ላሞች በሰው ሰራሽ ዘዴ በማዳቀል የተሻለ የወተትና የስጋ ምርት ለማግኘት ወደ ሥራ መገባቱን ተናግረዋል። በዞኑ በተያዘው ዓመት ከ97 ሺህ በላይ የሚሆኑ ላሞችን በሰው ሰራሽ ዘዴ ለማዳቀል ታቅዶ ወደ ስራ የተገባ መሆኑን ያነሱት ደግሞ የባሌ ዞን ግብርና ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ሙአዊያ ፉኣድ ናቸው። የእንስሳትና እንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን መጠንና ጥራት በመጨመር የአርሶና አርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የእንስሳት ዝርያን በሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ የማሻሻል ስራ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል። በዞኑ ከአካባቢው ላሞች በቀን የሚገኘው የወተት ምርት ከሶስት ሊትር እንደማይበልጥ የገለጹት ምክትል ሀላፊው በሰው ሰራሽ ስነ-ዘዴ ከተዳቀሉ ላሞች የሚገኘው የወተት ምርት በቀን በአማካይ ከ12 እስከ 15 ሊትር መሆኑን በማሳያነት አንስቷል። አቶ ሙአዊያ እንዳሉት በዞኑ በሰው ሰራሽ ዘዴ ከሚዳቀሉ ላሞች የሚገኘውን የወተት ምርት ከማሳደግ በተጓዳኝ በበጀት ዓመቱ ከ45 ሺህ 600 የሚበልጡ ጥጆችን ለማግኘት መታቀዱንም አክለዋል።
የሕዳሴ ግድብ ከኢትዮጵያውያን አልፎ ቀጣናዊ ትስስርን ያጠናክራል - በኢትዮጵያ የጀርመን ምክትል አምባሳደር ፈርዲናንድ ፎን ቫሄ (ዶ/ር)
Sep 12, 2025 165
አዲስ አበባ፤ መስከረም 2/2018 (ኢዜአ)፦ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እድገት ባለፈ የቀጣናው ሀገራትን ለማስተሳሰር ትልቅ አቅም ያለው መሆኑን በኢትዮጵያ የጀርመን ምክትል አምባሳደር ፈርዲናንድ ፎን ቫሄ (ዶ/ር) ገለጹ። ኢትዮጵያ ለውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የተመቸች ሀገር መሆኗንም ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ መመረቃቸው ይታወቃል። የሕዳሴ ግድብ ተጠናቆ መመረቅን አስመልክቶ ኢዜአ በኢትዮጵያ የጀርመን ምክትል አምባሳደር ፈርዲናንድ ፎን ቫሄ (ዶ/ር)ን አነጋገሯል። ምክትል አምባሳደሩ እንደገለጹት፤ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ቀጣናውንና ሌሎች አገራትን ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ ትስስርንም የሚያጠናክር ነው። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ከፍተኛ የአሌትሪክ ሀይል የማመንጨት አቅም ያለው መሆኑን ገልጸው፤ ጎረቤት አገራትም ሆኑ ከዚያም ባለፈ መልኩ በትብብር ከሰሩ ተጠቃሚነታቸውን ማሳደግ ይችላሉ ብለዋል። ግድቡ በኢትዮጵያውያን ትብብር እውን መሆኑን አውቃለሁ ያሉት አምባሳደሩ፤ በአሁኑ ወቅትም የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ ለምረቃ መብቃቱ የሚያኮራና የሚያስደስት ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ የካርበን ልቀትን ለመቀነስ፣ የታዳሽ ሀይል አጠቃቀምን ለማስፋፋት የሚከናወኑ ስራዎችን መመልከታቸው ገልጸው፤ ይህም የሚበረታታ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን በፀሐይና በሌሎች ታዳሽ የሀይል አማራጮች ላይ ጥናትና ምርምር እየሰሩ እንደሚገኙ አንስተዋል። በኢትዮጵያ የተከናወኑ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት ተስፋ የሚሰጡ መሆኑን ተናግረዋል። የህግ ማዕቀፍ መሻሻል፣ በርካታ የሰው ሀይል መኖሩና ሌሎች ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸው ለባለሀብቶች ኢንቨስት ለማድረግ የሚያስችሉ ሁኔታዎች ናቸው ብለዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው
Sep 10, 2025 203
ሀዋሳ፤ ጳጉሜን 5/2017(ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል በቴክኖሎጂ የተደገፈ ከወረቀት ነጻ አገልግሎት በመስጠት እንደ ሀገር ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑ ተገለጸ። “ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ማድረግ” በሚል መሪ ሀሳብ የነገው ቀን በሲዳማ ክልል ደረጃ በሀዋሳ ተከብሯል። የሲዳማ ክልል መንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ አስፋው ጎኔሶ በመርሀግብሩ ላይ እንዳሉት በክልሉ የሚሰጠውን አገልግሎት ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው። በክልሉ በሀዋሳ የአንድ መሶብ አገልግሎትን ለማስጀመር የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረዋል። ለዚህም በርካታ ተገልጋይ ያላቸው አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ተመርጠውና ለስራ ምቹ የሚሆን ህንጻ ተዘጋጅቶ የኔትወርክ ዝርጋታ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል። የአንድ መሶብ አገልግሎቱ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የሚሰጥበት ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ጠቁመዋል። የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ሀላፊ አቶ አሰፋ ጉራቻ በበኩላቸው እንደገለጹት በክልሉ በዲጂታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ ከወረቀት ነጻ የሆነ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዩን እርካታ ለማምጣት በትኩረት እየተሰራ ነው። ህብረተሰቡ ለእንግልት የሚዳረግባቸውን አገልግሎቶች በመለየት በአንድ ማዕከል ውስጥ ያለ ውጣውረድ በኦን ላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል ። የመሶብ አገልግሎቱ ትልቅ ፋይዳ እንዳለውና ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎችን እንደሚያግዝ ጠቁመዋል። የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ በራሶ የዲጂታል አገልግሎቱን በተሳካ ሁኔታ ለማስጀመር እንዲቻል የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕውቀት ያለው ትውልድ መፍጠር ዋና ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ለዚህም በኮደርስ ኢትዮጵያ እስካሁን ከ30 ሺህ በላይ የክልሉ ነዋሪዎች ስልጠና እንዳገኙ ጠቁመው እንደ ሀገር ዲጂታል ኢኮኖሚን ለማሳካት በክልሉ ቢያንስ 50 በመቶ የመንግስት ሰራተኛው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕውቀት እንዲኖረው ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አስታውቀዋል። “ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ማድረግ” በሚል መሪ ሀሳብ በተከበረው የነገው ቀን በዓል ላይ በክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ተጠሪ የሆኑ ተቋማትና ኤጀንሲዎች ሰራተኞች ተገኝተዋል።
በኦሮሚያ ክልል የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን በዲጅታል ቴክኖሎጂ በማስደገፍ ፈጣንና ቀልጣፋ እንዲሆን እየተደረገ ነው
Sep 10, 2025 154
አዳማ፤ ጳጉሜን 5/2017(ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን በዲጅታል ቴክኖሎጂ በማስደገፍ ፈጣንና ቀልጣፋ እንዲሆን እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል። በዛሬው የ"ነገው ቀን" መርሃ ግብር "ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ" በሚል መሪ ሀሳብ የአዳማ ከተማ አስተዳደር የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን አስጀምሯል። በከተማ አስተዳደሩ አገልግሎቱን ያስጀመሩት በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ከፍያለው ተፈራ፣ የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና(ዶ/ር) እና የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኃይሉ ጀልዴ ናቸው። በዚህ ወቅት በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ከፍያለው ተፈራ እንደገለጹት፤ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ በማሻሻል መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ለዲጂታል ኢትዮጵያ እውን መሆን ወሳኝ ነው። ዲጂታል ኢትዮጵያ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን በመተግበር ግልጸኝነትንና ተጠያቂነትን መዘርጋት ትኩረት እንደተሰጠው ተናግረዋል። በዛሬው እለት አገልግሎቱ አዳማን ጨምሮ በቢሾፍቱ፣ ሸገር እና ሻሸመኔ ከተሞች መጀመሩን አስታውቀዋል። በቀጣይም በሁለተኛው ምዕራፍ በበርካታ ከተሞች አገልግሎቱን ማስፋት የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ይህም ከመንግስት አገልግሎት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችንና መልካም አስተዳደርን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ገንቢ ሚና እንዳለው አስረድተዋል። የክልሉ መንግሥት የሕብረተሰቡን ጥያቄ በቅርበት ለመፍታትና የአገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ለማሻሻል በ5ሺህ ቀበሌዎች ሰራተኞችን በመመደብ አርሶ አደሩ ከቀዬው ሳይርቅ አገልግሎት እያገኘ መሆኑን ጠቅሰዋል። ይህም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት እንቅስቃሴዎችን በማሳለጥ የክልሉ ብሎም የሀገር መንሰራራትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንዳለው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በርካታ ተቋማት ቴክኖሎጂ በመጠቀም አገልግሎታቸውን በማዘመን ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። በአዳማ ዛሬ የተጀመረው የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ በዲጅታል ቴክኖሎጂ የተደገፈ ፈጣንና ቀልጣፋ እንዲሆን እንደሚያስችል አነስተዋል። አገልግሎቱ አስተማማኝና የተሳለጠ እንዲሆን የሰው ኃይልን ለማብቃት ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራም አንስተዋል። የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኃይሉ ጀልዴ በበኩላቸው፤ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በአስተዳደሩ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ በማድረግ ሙሉ በሙሉ መቀየር ማስቻሉን ተናግረዋል። በዚህም የመሬት አስተዳደር፣ ኢንቨስትመንት፣ ኮንስትራክሽንን ጨምሮ ከ100 በላይ አገልግሎቶችን በተቀላጠፈ መንገድ ለተገልጋዩ ሕብረተሰብ መስጠት እንደሚያስችል ገልጸዋል። ይህም የተገልጋዩን እርካታ እና የከተማዋን ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ ወሳኝነት እንዳለው አስረድተዋል።
በአፋር ክልል የዲጂታል አሰራርን በመተግበር አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቷል
Sep 10, 2025 186
ሰመራ፤ጳጉሜን 5/2017(ኢዜአ)፦በአፋር ክልል የዲጂታል አሰራርን በመተግበር የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ትኩረት መሰጠቱ ተገለጸ። "ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ" በሚል መሪ ሐሳብ ጳጉሜን 5 የነገው ቀን በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል። በዕለቱ የተገኙት በብልፅግና ፓርቲ የአፋር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ መሐመድ አህመድ የዲጂታል አሰራርን በመተግበር የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንሰራለን ብለዋል። አዲሱን ዓመት ስንቀበልም በለውጥ አመታት የተከናወኑ የልማት ስራዎችን በተሻለ ፍጥነትና ጥራት የምናስቀጥልበትና የዲጂታል አሰራርን እውን የምናደርግበት ነው ብለዋል። በዲጂታላይዜሽን ዘርፍ የተጀመሩ የኢትዮ-ኮደርስና ዲጂታል መታወቂያ ትግበራን በቴክኖሎጂ በማገዝ ተግባራዊ እናደርጋለን ብለዋል። በክልሉ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለማስጀመር የተጀመሩ ስራዎችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። የክልሉ የሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ መሐመድ አህመድ በበኩላቸው ባለፉት ሰባት የለውጥ ዓመታት የተመዘገቡ የልማት ውጤቶችን እናጠናክራለን ብለዋል። በዚህም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ዲጂታላይዜሽን ማስፋፋት ላይ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። በዕለቱ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና የሠመራ ከተማ ነዋሪዎች በተገኙበት የፓናል ውይይት ተካሄዷል።
በክልሉ በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት አሰጣጥን በማስፋት ለመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ይሰራል
Sep 10, 2025 157
ቦንጋ፤ ጳጉሜን 5/2017(ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት አሰጣጥን በማስፋት ለህዝቡ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ የመስጠቱ ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡ የጳጉሜን 5 'የነገው ቀን' "ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ" በሚል መሪ ሃሳብ በቦንጋ ከተማ ተከብሯል። የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አስራት አዳሮ በዚህ ጊዜ እንደተናገሩት የመንግስት አገልግሎትን ለማዘመን በቴክኖሎጂ የተደገፉ አሰራሮች ተጠናክረው ይቀጥላሉ። አገልግሎት አሰጣጥን ማዘመን ከአድሎ የፀዳ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የህዝቡን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት እንደሚያስችልም ተናግረዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የአንድ ማዕከል አገልግሎት በክልሉ በአምስት ተቋማት 15 አገልግሎቶችን ለማስጀመር ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን ገልጸዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የኮደርስ ስልጠናም በክልሉ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል፡፡ የክልሉ ዋና ኦዲተር አስራት አበበ በበኩላቸው የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ መዘመን ከኪራይ ሰብሳቢነት የፀዳ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎትን ለመስጠት የሚያግዝ በመሆኑ ተቋማት ትኩረት ሊሰጡት እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡ የፌደራል መንግስት ያመቻቸው የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠና አለም አቀፍ እውቅና ያለው ትልቅ እድል በመሆኑ በተገቢው መጠቀም ይገባል ብለዋል። የነገዋን ኢትዮጵያ የተሻለች ለማድረግ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ የገለጹት ደግሞ የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እንዳሻው ከበደ ናቸው፡፡ በዞኑ ፍርድ ቤት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ የማድረግ ጅምር ስራዎች መኖራቸውን ጠቁመው በሌሎች ተቋማትም ይጠናከራሉ ብለዋል፡፡ በመድረኩ የክልል፣ የዞንና የቦንጋ ከተማ አመራሮችና የመንግስት ሰራተኞች ተገኝተዋል።
ስፖርት
20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነገ ይጀመራል
Sep 12, 2025 131
አዲስ አበባ፤ መስከረም 2/2018 (ኢዜአ)፦ በጃፓን ቶኪዮ የሚካሄደው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነገ ጅማሮውን ያገኛል። በሻምፒዮናው ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ 200 ገደማ ሀገራት የተወጣጡ ከ2000 በላይ አትሌቶች እንደሚሳተፉ የዓለም አትሌቲክስ መረጃ ያመለክታል። አትሌቶች በ49 የውድድር አይነቶች ላይ ይሳተፋሉ። በሻምፒዮናው መክፈቻ ቀን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚጠበቁባቸው የፍጻሜ ውድድሮች ይካሄዳሉ። ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 ላይ በሚደረገው የሴቶች የ10 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር ጉዳፍ ጸጋይ፣ ፅጌ ገብረሰላማ፣ ፎይተን ተስፋይ እና እጅጋየሁ ታዬ ይወዳደራሉ። ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ላይ በሚደረገው የሴቶች ማራቶን ፍጻሜ አትሌት ትዕግስት አሰፋ፣ ሱቱሜ አሰፋ እና ትዕግስት ከተማ ይሳተፋሉ። የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እስከ መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከካፍ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ ማጣሪያ ውድድር ተሰናበተ
Sep 11, 2025 174
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በምድብ ሁለት በካፍ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ከብሩንዲው ቶፕ ገርልስ አካዳሚ ጋር ያደረገው ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል። ጨዋታው በካሳራኒ ስታዲየም ተከናውኗል። ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ከውድድሩ ውጪ ሆኗል። ቡድኑ በማሸነፍ ምርጥ ሁለተኛ ሆኖ የማለፍ እድሉን አልተጠቀመበትም። ንግድ ባንክ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታው በሩዋንዳው ራዮን ስፖርት 2 ለ 1 መሸነፉ የሚታወስ ነው። በምድብ ሁለት ራዮን ስፖርት በአራት ነጥብ ለግማሽ ፍጻሜ አልፏል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተካሄደው የሴካፋ ዞን ማጣሪያ በማሸነፍ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ መሳተፉ የሚታወስ ነው። የምድብ ጨዋታዎች ዛሬ ይጠናቀቃሉ። የግማሽ ፍጻሜ መርሃ ግብር መስከረም 4 ቀን 2018 ዓ.ም ይከናወናል። በኬንያ እየተካሄደ የሚገኘው የሴካፋ ዞን ማጣሪያ እስከ መስከረም 6 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ማጣሪያውን የሚያሸንፍ ክለብ ሴካፋን ወክሎ በካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ ይሳተፋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የካፍ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ ማጣሪያ ከቶፕ ጋርልስ አካዳሚ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል
Sep 11, 2025 130
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የካፍ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታውን ዛሬ ከብሩንዲው ቶፕ ገርልስ አካዳሚ ጋር ይጫወታል። ጨዋታው ከቀኑ 7 ሰዓት በካሳራኒ ስታዲየም ይካሄዳል። የሴካፋ ዞን ማጣሪያ በኬንያ እየተካሄደ ይገኛል። ኢትዮጵያን በሴካፋ ዞን ወክሎ በማጣሪያ ውድድሩ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በምድብ ሁለት ሁለተኛ እና የመጨረሻ ጨዋታውን ከብሩንዲው ቶፕ ገርልስ አካዳሚ ጋር ያከናውናል። በብርሃኑ ግዛው የሚመራው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመጀመሪያ ጨዋታው በሩዋንዳው ራዮን ስፖርት 2 ለ 1 መሸነፉ ይታወቃል። ተጋጣሚው ቶፕ ገርልስ አካዳሚ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታው ከራዮን ስፖርት ጋር ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይቷል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከምድቡ ምርጥ ሁለተኛ ሆኖ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ለማለፍ የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ይጠበቅበታል። ንግድ ባንክ በ2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተካሄደው የሴካፋ ዞን ማጣሪያ በማሸነፍ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ መሳተፉ የሚታወስ ነው። የሩዋንዳው ራዮን ስፖርት ምድቡን በአራት ነጥብ እየመራ ይገኛል። በምድብ አንድ የሚገኘው የኬንያው ኬንያ ቡሌትስ በስድስት ነጥብ ወደ ግማሽ ፍጻሜው የገባ የመጀመሪያ ቡድን ሆኗል። በውድድሩ ላይ ዘጠኝ ሀገራት በሶስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን እያካሄዱ ይገኛል። የሴካፋ ዞን ማጣሪያ እስከ መስከረም 6 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል። ማጣሪያውን የሚያሸንፍ ክለብ ሴካፋን ወክሎ በ2025/26 የካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ ላይ ይሳተፋል።
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መቻል፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ሃዋሳ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል
Sep 10, 2025 160
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ውሎ ሶስት ጨዋታዎች ተደርገዋል። መቻል ሸገር ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል። ትዕግስት ወርቁ፣ ስንታየሁ ኤርኮ እና ቤተልሄም መንተሎ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። በሌላኛው መርሃ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ልደታ ክፍለ ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል። ዳግማዊት አለማየሁ ሁለት ግቦችን ስታስቆጥር ንግስት ኃይሉ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች። አስራት አለሙ ለልደታ ክፍለ ከተማ ብቸኛዋን ጎል አስቆጥራለች። ሃዋሳ ከተማ በታደለች አብርሃም ጎል ባህር ዳር ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል። ጨዋታዎቹን ተከትሎ የሶስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል።
አካባቢ ጥበቃ
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋም የጀመረቻቸውን ኢንሼቲቮች በደቡብ ደቡብ ትብብር ማጠናከር ይገባል
Sep 12, 2025 167
አዲስ አበባ፤ መስከረም 2/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋም የጀመረቻቸውን ኢንሼቲቮች በደቡብ ደቡብ ትብብር ማጠናከር እንደሚገባ የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ገለጹ፡፡ የአፍሪካ የበካይ ጋዝ ልቀት መጠን ከአራት በመቶ ባይበልጥም በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ከፍተኛ ተጎጂ መሆኗ አልቀረም፡፡ በተለይም አፍሪካን ጨምሮ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ የሚደርስባቸውን ችግር የህልውና ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ሆኗል፡፡ አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋም የጎላ በካይ ጋዝ ከሚለቁ ሀገራት ከመጠበቅ የራሷን መፍትሔ መፈለግ አለባት የሚለው የብዙ ዓለም አቀፍ ተቋማት ምክረ ሀሳብ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር እንደ ቻይና እና ጃፓን በቴክኖሎጂ ከበለጸጉ ሀገራት ጋር በደቡብ ደቡብ ትብብር የቴክኖሎጂ አቅምን ማሳደግ እንደሚገባም ይገልፃሉ፡፡ የዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት ረዳት ዋና ጸሀፊ ቶማስ አሳሬ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአየር ንብረት ፋይናንስ በማመንጨት እና ጎረቤት ሀገራት በታዳሽ ኃይል በማስተሳሰር የጎላ አበርክቶ አለው፡፡ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በቢሊዬን የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ እየገነባች መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአመራር ቁርጠኝነት እና የኢትዮጵያ ህዝብ ተሳትፎ የላቀ አበርክቶ እንዳለው ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም የምታደርገውን ጥረት በደቡብ ደቡብ ትብብር ማጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡ የዓለም የእርሻና ምግብ ድርጅት ረዳት ዳይሬክተር ጀነራል እና የአፍሪካ ተጠሪ አበበ ኃይለገብርኤል (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የአየር ንብረት ለውጥ ፋይናንስን ከፍተኛ በካይ ጋዝ የሚለቁት ያደጉ ሀገራት እንዲሸፍኑ የወጡ የፓሪስ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ስምምነቶች በአግባቡ ገቢራዊ አልተደረጉም ብለዋል፡፡ የአፍሪካ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋም የደቡብ ደቡብ ትብብርን በማጠናከር የቴክኖሎጂ አቅማቸውን ማሳደግ እንዳለባቸውም ገልጸዋል፡፡ አፍሪካ የታዳሽ ሀይል፣ እምቅ የማዕድንና ሌሎች የተፈጥሮ ጸጋዎች ያሏት አህጉር መሆኗን በመጥቀስ፤ በደቡብ ደቡብ ትብብር ጸጋዋን የምትጠቀምበት ቴክኖሎጂ ማላመድ አለባት ብለዋል፡፡ በደቡብ ደቡብ ትብብር ማዕቀፍ እንደ ቻይና ያሉ ሀገራት በብዙ ተፈትነው መሰረት የያዘ የቴክኖሎጂ አቅም ገንብተዋል ያሉት ዶክተር አበበ ፤ አፍሪካ ዘግይታ መግባቷን /late comer advantage/ እንደ እድል መጠቀም እንዳለባት ገልጸዋል፡፡
ጉባኤው አፍሪካ ለዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ የመፍትሔ ማዕከል መሆኗን በግልጽ ያሳየ ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ
Sep 10, 2025 252
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2017(ኢዜአ)፦ ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ አፍሪካ የመፍትሔና የታዳሽ ኃይል ማዕከል መሆኗን ያሳየችበት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገለጹ፡፡ "ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት መፍትሄዎችን ማፋጠን፣ የአፍሪካን አረንጓዴ ልማት በፋይናንስ መደገፍ" በሚል መሪ ሀሳብ ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ዛሬ ተጠናቋል፡፡ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በመዝጊያ መርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ አፍሪካ ግልጽ አቋሟን ያንጸባረቀችበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ተጎጂ ብቻ ሳይሆን በአረንጓዴ ልማትና በታዳሽ ሀይል ዓለም አቀፍ የመፍትሔ ማዕከል መሆኗን አሳይቷል ብለዋል፡፡ ዓላማችን የበለጸገች፣ አይበገሬና አረንጓዴ አፍሪካን መፍጠር ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ የኤሌክትሪክ ሃይል የማያገኙ 600 ሚሊዮን አፍሪካውያን መኖራቸው ኢፍትሐዊነት መሆኑን የዓለም ማህበረሰብ ሊገነዘብ እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን የመቋቋም ተግባራችን ያለንን ሰፊ ሀብት፣ የታዳሽ ሃይል ልማትና የአየር ንብረት ለውጥ ፍትህ ላይ ማተኮር አለበት ብለዋል፡፡ በአፍሪካ ያለውን እምቅ የውሃና የጸሀይ ሀይል በመጠቀም ሁሉም ዜጎችና ድርጅቶች የኤሌክትሪክ ሃይል እንዲያገኙ ማድረግ እና በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ አፍሪካውያን በዓለም እንደ ተረጂ የምንታይበትን ትርክት በተባበረ አቅማችን መቀየርና የዓለም የመፍትሔ አካል መሆናችንን ማሳየት ይኖርብናል ብለዋል፡፡ አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ለዓለም የሚተርፍ መፍትሔ አላት ያሉት ፕሬዝዳንቱ ቢሊዮን ችግኞች በየዓመቱ የሚተከሉበት የአረንጓዴ ዐሻራ፣ የታዳሽ ኃይል ልማት፣ የአፈርና ውሃ ጥበቃን በምሳሌነት ጠቅሰዋል። የአዲስ አበባ የመሪዎች ቃል ኪዳን መጽደቅ ትልቅ እርምጃ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ በራሷ አቅም መፍትሔ እንደምታመጣ የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የመሪዎች ቃል ኪዳን የታዳሽ ኃይልና የአረንጓዴ ልማትን በማስፋት ነገን መገንባት፣ ወሳኝ ማዕድናትን ጨምሮ የአህጉሪቱን የተፈጥሮ ሀብት በራስ ማስተዳደርና መጠቀም፣ ጥብቅ ደኖችን ጨምሮ የተፈጥሮ ቅርሶቻችንን መጠበቅ ላይ ያተኮሩ ሦስት ምሰሶዎች እንዳሉት አስረድተዋል። የአዲስ አበባ የመሪዎች ቃል ኪዳን በአጭር ጊዜ ዕቅድ ወጥቶለት ሊተገበር የሚገባ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆነ ገበያ ተኮር የግብርና ፕሮግራም ይፋ አደረገች
Sep 10, 2025 151
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ምዕራፍ ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆነ ገበያ ተኮር የኮታ ገጠም የግብርና ፕሮግራምን ይፋ አድርጋለች። የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ(ዶ/ር)፥ መንግስት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የግብርና ሥራ ቅድሚያ በመስጠት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። ግብርና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ትልቁ አንቀሳቃሽ መሆኑን ገልጸው በወጪ ንግድ እና የሀገር ውስጥ የምግብ ፍጆታን በማሟላት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የመጀመሪያው ምዕራፍ ገበያ ተኮር የግብርና ፕሮግራም ትግበራ ከ4 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እንዳደረገና በጥራጥሬ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ አመርቂ ውጤት እንደተመዘገበበት ተናግረዋል። ሁለተኛው ምዕራፍ የተገኙ ስኬቶችን ማስቀጠል በሚቻልበት መንገድ መዘጋጀቱን አብራርተዋል። የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሤ(ዶ/ር) ፕሮግራሙ በርካታ ግቦች እንዳሉት ጠቅሰዋል። ፕሮግራሙ ኢትዮጵያ አነስተኛ የእርሻ ማሳ ያላቸው አርሶ አደሮች በኩታ ገጠም እርሻ ተጠቃሚ የሚያደርግ ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆነ ገበያ ተኮር ግብርናን ለማሳደግ ያላትን ጠንካራ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል። ፕሮግራሙ ግብርና የምግብ ዋስትና እና የኢኮኖሚ ለውጥ አንቀሳቃሽ የመሆን አቅሙን ለማጎልበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ጨምረዋል። በዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የልማት ፖሊሲ ምክትል ጸሐፊ ኦሌ ቶንኬ የዴንማርክ መንግስት ለኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ የ75 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል። ዴንማርክ ለኢኮኖሚ እድገት እና ለሥራ ፈጠራ አስፈላጊ በሆነው የግብርና ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር በመስራቷና የልማት አጋር በመሆኗ ኩራት እንደሚሰማትም ተናግረዋል።
ሦስተኛው በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ዕቅድ የአረንጓዴ ልማት ግቦችን የሚያሳካ ነው
Sep 10, 2025 209
አዲስ አበባ ፤ ጳጉሜን 5/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሦስተኛው በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ብሔራዊ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ የ10 ዓመት ዕቅድ የአረንጓዴ ልማት ግቦችን የሚያሳካ መሆኑን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መኮንን ገለጹ፡፡ ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ የሦስተኛ ቀን ውሎ የውይይት መድረክ ዛሬም በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ተካሂዷል። የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቀነስ በግብርና፣ የአፈር ማዳበሪያ፣ ታዳሽ ሀይል፣ የአየር ንብረት ፋይናንስ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት የሚያስችሉ ውይይቶች ተደርገዋል፡፡ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት የበካይ ጋዝ ልቀትን በመቀነስ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋም ሶስተኛውን በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ የ10 ዓመት ዕቅድ ይፋ አድርጓል። የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መኮንን ዕቅዱን ይፋ ባደረጉበት ወቅት፤ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ዕቅድ በፓሪስ ስምምነት መሰረት በየአምስት ዓመቱ ማሻሻያ እንደሚደረግበት አውስተዋል። ኢትዮጵያም እ.አ.አ ከ2025 እስከ 2035 የሚተገበር ሦስተኛውን በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ብሔራዊ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ዕቅድ ማውጣቷን ገልጸዋል። ዕቅዱ ከኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ ከ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ እና ከረጅም ጊዜ የካርበን ልቀት ስትራቴጂክ ዕቅድ ጋር የተጣጣመ መሆኑን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አማካይነት የደን ሽፋን ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ከፍ ማለቱን ገልጸው፤ በ2030 ወደ 30 በመቶ ለማሳደግ ታቅዷል ብለዋል። የአስር ዓመቱ ዕቅድ የግብርና ምርታማነትን፣ የከተማ መሰረተ ልማትን፣ የታዳሽ ኃይል አቅርቦትን እና የሰብል ምርታማነትን ተጨባጭ በሆነ መንገድ የሚያሳድግ ነው ብለዋል። በዶሮ እርባታ፣ በንብ ማነብ፣ በስጋ ምርት እንዲሁም በመስኖ ልማትና በሌሎች የግብርና ዘርፎች የተመዘገቡ ለውጦችን ማስቀጠል እንደሚችልም አመልክተዋል። ኢትዮጵያ ለብዝኃ ህይወትና ሥርዓተ ምህዳር ጥበቃ፣ የመሬት መሸርሸርን ለመከላከል ጠንካራና ዘላቂነት ያለው ኢኮኖሚ ለመገንባት በጀት መድባ እየሰራች ነው ብለዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ይጠይቃል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፣ ብሔራዊ ዕቅዱን ለማሳካት 98 ነጥብ 35 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም ለዕቅዱ መሳካት ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ በፋይናንስ፣ በቴክኒክ እና በቴክኖሎጂ ዕገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። በዓለም ባንክ የምሥራቅ አፍሪካ የአካባቢ ዘርፍ ማናጀር ፖል ማርቲን፤ ባንኩ በኢትዮጵያ ለዘላቂ ደን እና መሬት ልማት አስተዳደር ቅድሚያ በመስጠት በትብበር መስራቱን ገልጸዋል፡፡ በዚህም የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን መቋቋም የሚያስችል የአፈርና ውሀ ጥበቃ እንዲሁም የተራቆተ መሬት ማገገም ላይ ተጨባጭ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል፡፡ የዓለም ሪሶርስ ኢንስቲትዩት ግሎባል ዳይሬክተር ሜላኒ ሮብሰን የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ፣ የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ስርዓትና ሌሎችም ኢኒሼቲቮች የአረንጓዴ ልማትን የሚደግፉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥን በራሷ አቅም መቋቋም የሚያስችል እምቅ አቅም እንዳላት ያነሱትን ሀሳብ የኢትዮጵያ ኢኒሼቲቮች አረጋግጠዋል ነው ያሉት። የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ አጋርነት ዓለም አቀፍ ዳይሬክተር ፓብሎ ቬራ (ዶ/ር) በበኩላቸው ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም የምታደርገውን ጥረት አድንቀዋል፡፡ ኢትዮጵያ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ዕቅድ ትግበራ ያስመዘገበችው ስኬት በቀጣናውና በዓለም መሪ ያደርጋታል ብለዋል፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም የኢትዮጵያን ድንቅ ሥራዎች በሌሎችም ሀገራት መድገም እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ሦስተኛውን በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ብሔራዊ የአየር ንብረት ለውጥ ዕቅድ እንድታሳካ ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ ተናግረዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
አፍሪካውያን ለአህጉራቸው ሰላም እና ብልጽግና ያላቸውን ቁርጠኝነት ዳግም ሊያረጋግጡ ይገባል - መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
Sep 9, 2025 243
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2017(ኢዜአ)፦ አፍሪካውያን ለአህጉራቸው ሰላም እና ብልጽግና ያላቸውን ቁርጠኝነት በማጽናት የተሻለ መጻኢ ጊዜን ለመፍጠር በጋራ እንዲሰሩ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ጥሪ አቀረቡ። የአፍሪካ ህብረት ቀን ዛሬ እየተከበረ ይገኛል። ቀኑ የአፍሪካ ህብረት እ.አ.አ ሴፕቴምበር 9/1999 በሲርት ድንጋጌ አማካኝነት የተቋቋመበት ቀን የሚታወስበት ነው። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ቀኑን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት አፍሪካውያን ቀኑን ሲዘክሩ የአህጉሪቷን ለውጦች በማክበር እና ለአንድነት፣ ሰላምና ብልጽግና ያላቸውን ቁርጠኝነት ዳግም በማረጋገጥ ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል። የህብረቱ መመስረት ውሳኔ ለአፍሪካ ትብብር፣ ትስስር እና አጋርነት መሰረት የጣለ ነው ብለዋል። የአፍሪካ ህብረት ቀን የጋራ ጉዟችንን፣ የህዝባችንን አይበገሬነት እና ያጋመደንን የፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ የምናከብርበት ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሊቀ መንበሩ በመልዕክታቸው በአፍሪካ በተለያዩ መስኮች የተመዘገቡ ስኬቶችን አንስተዋል። በሰላምና ደህንነት፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና፣ የታዳሽ ኃይል ልማት፣ ዲጂታል ኢኖቬሽንና የወጣቶችን አቅም በመገንባት የተከናወኑ ስራዎች አፍሪካን በዓለም መድረክ ያላት ሚና እንዲያድግ አስተዋጽኦ ማድረጉን ነው ሊቀ መንበሩ የገለጹት። የአፍሪካ ህብረት ለአጋርነት፣ ትስስር እና ዘላቂ ልማት ያለውን ቁርጠኝነት ጠቅሰው መንግስታት፣ ሲቪክ ማህበረሰቡ፣ የግሉ ዘርፍ እና ወጣቱ ፈተናዎችን በጋራ በመሻገር አጀንዳ 2063 ይዞ የመጣችውን እድሎች እንዲጠቀም ጥሪ አቅርበዋል። ሁሉም አፍሪካውያን ክብራቸው ተጠብቆ የሚኖሩባት እና መጻኢ ጊዜያቸው ብሩህ የሆነች አህጉር እጅ ለእጅ በመያያዝ እንገንባ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የአፍሪካ ህብረት እና የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን በአህጉራዊ ትስስር ያላቸውን አጋርነት ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Aug 26, 2025 1049
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2017(ኢዜአ)፦የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) በአህጉራዊ ትስስር አጀንዳ ያላቸውን ትብብር የበለጠ ለማላቅ እንደሚሰሩ አስታወቁ። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በዓለም የንግድ ድርጅት(ጄኔቫ) የአፍሪካ ህብረት ቋሚ መልዕክተኛ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (ኢሴኤ) ዋና ፀሐፊ ክላቫር ጋቴቴ ጋር ተወያይተዋል። ሁለቱ ወገኖች አፍሪካ በዓለም መድረክ አንድ የጋራ ድምጽ እንዲኖራት ማድረግ ያለውን ወሳኝ ጠቃሜታ አጽንኦት ሰጥተው መክረውበታል። የአፍሪካ ህብረት እና ኢሲኤ በንግድ፣ቀጣናዊ ትስስር እና የአፍሪካ የአዕምራዊ ንብረትን የበለጠ አጀንዳ ማራመድ ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ኢዜአ ከኢሲኤ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በዓለም የንግድ ድርጅት(ጄኔቫ) የአፍሪካ ህብረት ቋሚ መልዕክተኛ ሆነው በሐምሌ ወር 2017 ዓ.ም መሾማቸው የሚታወስ ነው። የአፍሪካ ህብረት እና ኢሲኤ ትብብራቸውን እ.አ.አ በ1960ዎቹ መግቢያ ላይ መጀመራቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።
አፍሪካ ህብረት እና ጃፓን ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን የበለጠ ለማጎልበት በትብብር ይሰራሉ
Aug 24, 2025 863
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 18 /2017 (ኢዜአ)፦አፍሪካ ህብረት እና ጃፓን ያላቸውን ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን የበለጠ ለማጎልበት በትብብር እንደሚሰሩ አስታወቁ። ዘጠነኛው የጃፓን አፍሪካ ልማት ዓለም አቀፍ ፎረም(ቲካድ) በዮካሃማ መካሄዱን ቀጥሏል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ከፎረሙ ጎን ለጎን ከጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) ፕሬዝዳንት አኪሂኮ ታናካ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር የጃይካ ከአፍሪካ ህብረት ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት እንዲሁም ኢኮኖሚና ማህበራዊን ጨምሮ በአፍሪካ ቁልፍ ዘርፎች እያደረገ ያለውን ኢንቨስትመንት አድንቀዋል። ሊቀ መንበሩ እና ፕሬዝዳንቱ የአፍሪካ ህብረት እና ጃፓን ያላቸውን የጋራ ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል። ዘጠነኛውን የቲካድ ፎረም መንፈስ ወደ ዘላቂ የኢኮኖሚ ለውጥ በጋራ የመፍጠር ምዕራፍ ማሸጋገር እንደሚገባም አንስተዋል። ከነሐሴ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ፎረም የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ፤ የአህጉር በቀል መፍትሄዎች መድረክ
Aug 23, 2025 890
በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ አፍሪካውያን የአየር ንብረት በርቀት የሚያዩት ስጋት ሳይሆን የዕለት ተዕለት እውነታቸው ነው። በጎርፍ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች እና ተጠራርገው የሚወሰዱ ንብረቶች፣ በተከታታይ ድርቆች ምክንያት የሚያጋጥመው የምርታማነት መቀነስ የአየር ንብረት ለውጥ ከወለዳቸው ቀውሶች መካከል ይጠቀሳሉ። እነዚህ በተጨባጭ የዜጎችን ኑሮ እየተፈታተኑ ያሉ ችግሮች በአፍሪካ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስነ ምህዳር ላይ ለውጥ እንዲመጣ አስገድደዋል። የድህነት ምጣኔ እና የተፈናቃይ ዜጎች እየጨመረ መምጣት የአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ ተጽእኖዎችን በተግባር የገለጡ ጉዳዮች ሆነዋል። አፍሪካ ለዓለም የበካይ ጋዝ ልቀት ከአራት በመቶ በታች ድርሻ ቢኖራትም የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት ከፍተኛ ቀንበር የሚያርፍባት አህጉር ሆናለች። ከሳህል ቀጣና የበረሃማነት መስፋፋት እስከ ምስራቅ አፍሪካ ኃይለኛ ጎርፎች የአህጉሪቷ ዜጎች በጣም ውስን ድርሻ ባላቸው ጉዳይ የቀውሱ ከፍተኛ ሰላባ እየሆኑ ነው። አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ የአስቸኳይ ጊዜ ውስጥ ናት ቢባል ማጋነን አይሆንም። እንደ ዓለም አቀፉ የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት መረጃ ከእ.አ.አ 1991 እስከ 2022 ባለው ሶስት አስርት ዓመታት ባሉ እያንዳዱ አስርት ዓመታት በአፍሪካ በአማካይ የ0 ነጥብ 3 ዲግሪ ሴልሺየስ የሙቀት ጭማሪ ተመዝግቧል። እ.አ.አ በ2024 የዓለም ሙቀት በ1 ነጥብ 2 ዲግሪ ሴልሺየስ ጨምሮ በዓለም ታሪክ ከፍተኛው ሙቀት የተመዘገበበት ዓመት ነበር። 2024 በአፍሪካ የሙቀት መጠን 0 ነጥብ 86 በመቶ በመጨመር በአህጉሪቷ ታሪክ ከፍተኛው ሙቀት የተዘመገበበት ዓመት ሆኖም ተመዝግቧል። ከሙቀቱ በአሳሳቢ ሁኔታ መጨመር ባሻገር ድርቅ፣ ጎርፍ እና የምግብ ዋስትና ስጋት ላይ መውደቅ ሌሎች የአፍሪካ አየር ንብረት ለውጥ ፈተናዎች ናቸው። እ.አ.አ 2024 ደቡባዊ አፍሪካ ክፍል በቅርብ አስርት ዓመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ድርቅ አጋጥሟታል። በድርቁ ምክንያት ዛምቢያ እና ዚምባቡዌ የሰብል ምርታቸው በ50 በመቶ ቀንሷል። በምስራቅ እና ማዕከላዊ አፍሪካ በቅርብ ጊዜ የተከሰቱ ከባድ ጎርፎች ሚሊዮኖችን አፈናቅለዋል፤ የዜጎች ህይወት አመሰቃቅላዋል መሰረተ ልማቶችንም አውድመዋል። የዓለም አቀፉ ሜትሮሎጂ ድርጅት እና የአፍሪካ ልማት ባንክ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ደግሞ የአየር ንብረት ለውጥ የአፍሪካን ከሁለት እስከ አምስት በመቶ ጥቅል ዓመታዊ ምርት (ጂዲፒ) ወጪ እየወሰደ ይገኛል። አንዳንድ ሀገራት ለአየር ንብረት አስቸኳይ ምላሽ ዘጠኝ በመቶ ጥቅል ሀገራዊ ምርታቸውን ፈሰስ ያደርጋሉ። አፍሪካ በየዓመቱ ከ30 እስከ 50 ቢሊዮን ዶላር ለአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ አቅዶች ትግበራ ቢያስፈልጋትም ከዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ፋይናንስ ውስጥ የምታገኘው ገንዘብ ከአንድ በመቶ በታች ነው። የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት የ2024 የአፍሪካ ሪፖርት የአፍሪካ የግብርና ምርታማነት ከእ.አ.አ 1961 በኋላ በ34 በመቶ መቀነሱን ይገልጻል። የአፍሪካ ሀገራት ከውጭ ሀገራት ምግብ ለመግዛት የሚያወጡት 35 ቢሊዮን ዶላር ዓመታዊ ወጪ እ.አ.አ በ2025 ማብቂያ ወደ 110 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ከፍ እንደሚል ገልጿል። የበረሃማነት መስፋፋት፣ የብዝሃ ህይወት መመናመን፣ የጤና እክሎች፣ መፈናቀል እና የታሪካዊ ቅርሶች አደጋ ላይ መውደቅ አፍሪካ እየገጠሟት ያሉ የአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ ተጽእኖዎች ውጤት ናቸው። አፍሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ ቀውሶች ምላሽ ለመስጠት በየዓመቱ 250 ቢሊዮን ዶላር ቢያስፈልጋትም እያገኘች ያለችው 30 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ ስጋት አፍሪካ የጥያቄ አምሮት ኖሮባት የምታነሳው አጀንዳ ሳይሆን የፍትህ እና የህልውናዋ ጉዳይም ጭምር ነው። በአዲስ አበባ ከጳጉሜን 3 እስከ 5 ቀን 2017 ዓ.ም “ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት መፍትሄዎችን ማፋጠን፥ የአፍሪካን አረንጓዴ ልማት በፋይናንስ መደገፍ" በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ አህጉሪቷ እየገጠሟት ካሉ አንገብጋቢ ፈተናዎችን በዘላቂነት መሻገር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ይመክራል። የሀገራት መሪዎች፣ ተመራማሪዎችና ባለሙያዎች፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ተቋማት፣ ወጣቶች እና የግሉ ዘርፍ በአንድነት ይወያያሉ። በጉባኤው ላይ አረንጓዴ አሻራን ጨምሮ በታዳሽ ኢነርጂ፣ ዘላቂ ግብርና እና ተፈጥሮ ተኮር መፍትሄዎች ጨምሮ በአፍሪካ ያሉ አረንጓዴ የመፍትሄ ሀሳቦች የበለ ማላቅ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሀገራት ተሞክሯቸውን ያቀርባሉ። አፍሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ስራ በየዓመቱ የሚያጋጥማትን የ220 ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ አቅርቦት ክፍተት መሙላት እና አማራጭ የፋይናንስ ምንጮችን መጠቀም ላይ ምክክር ይደረጋል። በብራዚል ቤለም በሚካሄደው 30ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ (ኮፕ 30) ጨምሮ በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ድርድሮች ላይ የአፍሪካን ፍላጎቶች እና ጥቅሞች ማስጠበቅ የሚያስችል የጋራ እና ጠንካራ አቋም መያዝ ከጉባኤው የሚጠበቅ ውጤት ነው። የአፍሪካ ሀገራት በጉባኤው ላይ የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል የሚያስችሉ ተጨባጭና መሬት ላይ የወረዱ እቅዶቻቸው ላይ የሚያቀርቡ ሲሆን የገቡትን ቃል ኪዳን ወደ ተግባር መቀየራቸውን የሚከታተል የቁጥጥር ስርዓት ትግባራትን የሚያጠናክሩባቸው መንገዶችን በማቅረብ በአጠቃላይ ተጠያቂነትን ለማስፈን ቃልኪዳናቸውን ዳግም ያድሳሉ። አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮች ገፈት ቀማሽ ሳትሆን የመፍትሄዎች እና የአይበገሬነት ስራዎች ማሳያም ናት። የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ እና አከባቢ ጥበቃ ስራዎች፣ የኬንያ የእንፋሎት እና የፀሐይ ኃይል ኢንሼቲቮች እንዲሁም የሞሮኮ ኑር ኦውርዛዛቴ የጸሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አረንጓዴ ልማት ሊሆን የሚችል ብቻ ሳይሆን በተጨባጭ የሚሳካ መሆኑን አፍሪካ ማረጋገጫ እንደሆነች በግልጽ የሚያመላክት ነው። አፍሪካ ከዓለም ዋንኛ በካይ ጋዝ ለቃቂ ሀገራት ገንዘብ በመጠበቅ ብቻ ሳይሆን ሀገር በቀል የፋይናንስ እና ሀብት ማሰባሰብ አቅማቸውን የበለጠ ማሳደግ ይጠበቅባታል። የአዲስ አበባው ጉባኤም የአፍሪካ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ ፋይናንስ አቅርቦታቸውን እንዲጨምሩ ጥሪ የሚቀርብበት ነው። አፍሪካውያን እንደ አረንጓዴ አሻራ ያሉ ከንግግር ያለፉ ሀገር በቀል መፍትሄዎችን በመተግበር አይበገሬ አቅም ሊገነቡ ይገባል። የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ሀገር በቀል የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄዎችን ከዓለም አቀፍ አጋርነት ጋር ከማዛመድ አኳያ ያላው ሚና ወሳኝ የሚባል ነው። ጉባኤው አፍሪካ ከአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነት ትርክት ወደ መፍትሄ አፍላቂነት እና የግንባር ቀደም ሚና አበርካችነት ለመሸጋገር እንደ መስፈንጠሪያ የሚያገለግል ትልቅ እድል ነው። የአዲስ አበባው ጉባኤ ከስብስባ ባለፈ አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ቆርጣ ለተነሳችበት የተግባር ምላሽ ጉዞ እና የዓለም አቀፍ ተጠያቂነት መረጋገጥ የጋራ ትግል ውስጥ ትልቅ እጥፋት ሊሆን ይችላል።
ሐተታዎች
ከ500 በላይ ሥራዎችን የሚያሳልጠው ጉበት …
Sep 1, 2025 694
ጉበት ከ500 በላይ ሥራዎችን የሚያከናውን ዋነኛ እና ሁለገብ የሰውነታችን አካል ነው ይላሉ በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት እና የጨጓራ፣ አንጀት እና ጉበት ሰብ ስፔሻሊስት ዶክተር አብዲ ባቲ። የጉበት ተግባራት በአራት ዐቢይ ክፍሎች እንደሚከፈሉም ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አስረድተዋል። 👉 የመጀመሪያው ተግባሩ፤ ጎጂ ንጥረ ነገሮችን ከደም ውስጥ ማጽዳት፣ ቆሻሻ ምርቶችን ማስወገድ፣ የመድኃኒቶችን ሜታቦሊዝም ማከናወን፣ ከምንበላው፣ ከምንጠጣው እና ከምንተነፍሰው ሁሉ መርዞችን ማስወገድ ነው ይላሉ። 👉 እንዲሁም ሁለተኛው ተግባሩ፤ ቫይታሚኖችን፣ ማዕድናትን እና ኃይልን ማከማቸት መሆኑን ገልጸው፤ ለሰውነታችን ማበረታቻ ኃይል በሚያስፈልግበት ጊዜ ዝግጁ ማድረግ ነው ብለዋል። 👉 ሦስተኛው ተግባር ደግሞ፤ ለደም መርጋት እና ኢንፌክሽኖችን ለመዋጋት ፕሮቲኖችን ማመንጨት መሆኑን ያስረዳሉ። 👉 አራተኛው ተግባሩን ሲያብራሩም፤ ‘Bile’ የሚባል ንጥረ ነገር በማምረት ከሚወዷቸው (ከሚመገቧቸው) ምግቦች ውስጥ የሚገኘውን ስብ እንዲፈጭ ያደርጋል ሲሉ ገልጸዋል። ጉበትን ለህመም የሚያጋልጡ መንስኤዎች ምንድን ናቸው? • እንደ ዶክተር አብዲ ገለጻ፤ ጉበት ዘርፈ ብዙ ተግባራት ያለው ወሳኝ የሰውነት አካል እንደመሆኑ ለብዙ አደጋዎች ይጋለጣል። ከነዚህ አጋላጭ ምክንያቶች መካከል ከታች የተጠቀሱት ዋነኞቹ ናቸው ብለዋል። 👉 እንደ ሄፓታይተስ ቢ እና ሲ ባሉ ቫይረሶች በደም፣ በመርፌ ወይም ወሊድ ወቅት የሚተላለፉ፤ 👉 ከመጠን በላይ አልኮል መጠቀም፤ 👉 ከመጠን በላይ መወፈር ፤ 👉 የስኳር በሽታ፤ 👉 ከእፅዋት እና የተለያዩ እህሎች (ለምሳሌ ከማሽላ እና በቆሎ) ውስጥ የሚገኙ እንደ አፍላቶክሲን ያሉ መርዛማ ንጥረ ነገሮች ይገኙበታል ብለዋል። 👉 በተጨማሪም ከ40 ዓመት በላይ መሆን፣ በቤተሰብ የሚተላለፉ የጉበት በሽታዎች መኖር፣ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እና አደገኛ ልማዶች ለጉበት በሽታ ከሚያጋልጡ መንስዔዎች መካከል ናቸው ይላሉ። ከእነዚህ አጋላጭ መንስኤዎች አብዛኛዎቹ ሊወገዱ የሚችሉ እንዲሁም ቀድመን በማወቅ እና በመጠንቀቅ መከላከል የሚቻሉ ናቸው ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። ጉበትን በቀላል እና ጤናማ በሆኑ ልምዶች እንዴት ማበረታታት ይቻላል? • በየዕለቱ በቂ ንጹህ ውኃ በመጠጣት፤ • ጤናማ አመጋገብ በመከተል (እንደ ፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ጤፍ፣ ባቄላ እና ዓሣ በመመገብ)፤ • ከመጠን በላይ ስብን እና ስኳርን በመቀነስ፤ • አካላዊ እንቅስቃሴን በማዘውተር፤ • አልኮልን በመገደብ ወይም በጭራሽ ባለመጠቀም፤ • የሄፓታይተስ ክትባት በመውሰድ፤ • ያልተረጋገጡ እፅዋትን ከመጠቀም በመቆጠብ፤ • መድኃኒት ከመውሰድ በፊት የጤና ባለሙያ በማማከር እንዲሁም የግል እና የምግብ ንጽህናን በመጠበቅ የጉበትን ጤንነት መጠበቅ ይቻላል ብለዋል ዶክተር አብዲ። ሕክምናውን በተመለከተ o ዶክተር አብዲ እንዳሉት፤ አብዛኛዎቹ የጉበት በሽታዎች ሊታከሙ ይችላሉ፤ በጊዜ ከተደረሰም መቆጣጠር እና መዳን ይችላሉ። o ለሄፓታይተስ ቢ/ሲ ፀረ-ቫይረስ መድኃኒቶች ሕክምና መከታተል፤ o አልኮል መጠጣት በማቆም ጉበት በፍጥነት እንዲያገግም ማገዝ፤ o ለሰባ ጉበት፣ ለስኳር በሽታ እና ለኮሌስትሮል መብዛት በመድኃኒት ማከም፤ o አመጋገብን ማስተካከል፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፤ o የከፋ ደረጃ ላይ የደረሰ ከሆነ እንደደረጃው የተለያዩ ሕክምናዎች መኖራቸውን ጠቅሰው፤ እስከ ንቅለ ተከላ ድረስ ሊታከም ይችላል ብለዋል። ጉበት በዓለም አቀፍ ደረጃ…. 👉 በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ 2 ቢሊየን የሚጠጉ ሰዎች እንደ ሄፓታይተስ ቢ እና ሲ ያሉ የጉበት ህመሞች ተጋላጭ ናቸው። ለዚህም ከመጠን በላይ አልኮል መጠጣት፣ ውፍረት እና የስኳር በሽታ በሰፊው በዓለም አቀፍ ደረጃ ብዙዎችን ተጋላጭ ያደርጋሉ ነው ያሉት። 👉 በአፍሪካ ውስጥ ወደ 80 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች ለሄፓታይተስ ቢ በሽታ ተጋላጭነት ውስጥ ይኖራሉ። ከዚህ ውስጥ 60 በመቶው የሚሆነው በክትባት ውስንነት፣ በጤና አጠባበቅ ተደራሽነት እና በአፍላቶክሲን የተበከሉ (እንደ በቆሎ እና ማሽላ ባሉ) ሰብሎች ምክንያት ለአደጋ ተጋላጭ ነው ብለዋል። 👉 በኢትዮጵያም እስከ 7 በመቶ ያህሉ ሕዝብ ለሄፓታይተስ ቢ ተጋላጭ መሆኑን ነው ያመላከቱት። ለዚህም አልኮል አላግባብ መጠቀም፣ ጫት መጠቀም እና የስኳር በሽታ መጨመር ለብዙዎች በተለይም ከ40 ዓመት በላይ ለሆኑ ወንዶች ተጋላጭነትን እንደሚጨምር አስገንዝበዋል። 👉 በአጠቃላይ ክትባት በመውሰድ፣ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ በመከተል፣ ጤናማ አመጋገብ በማዘውተር ብሎም በወቅቱ በመታከም ተጋላጭነትን በመቀነስ የጉበት ጤንነትን መጠበቅ ይገባል ሲሉ መክረዋል።
አስም-የበርካቶች ሰቀቀን …
Aug 28, 2025 731
በወቅትና የአየር ሁኔታ ሳይገደብ የበርካቶች ስቃይ የሆነውን አስም እንዴት ማከም ይቻላል…? የድንገተኛ እና ጽኑ ህሙማን ሐኪም ዶክተር ፍጹም አሸብር ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ለአስም ስለሚያጋልጡ መንስኤዎች፣ ምልክቶች፣ መደረግ ስላለበት ጥንቃቄና ሕክምናው አብራርተዋል። • አስም ምንድን ነው? እንደ ዶክተር ፍጹም ገለጻ፤ አስም ለረጅም ጊዜ የሚኖር የመተንፈሻ አካላት ህመም ነው። የመተንፈሻ አካላት በቀላሉ፣ በተለያየ ሁኔታና መጠን መዘጋት ሲያጋጥም አስም ይባላል። • የአስም ህመም ምልክቶች ምንድን ናቸው? የትንፋሽ ማጠር፣ የደረት መጨናነቅ እና ሳል ከአስም ምልክቶች መካከል መሆናቸውን ያነሱት የሕክምና ባለሙያው፤ በአብዛኛው ምልክቶቹ በሌሊት ወይም በማለዳ እንደሚባባሱ ገልጸዋል። • የአስም ዓይነቶች 1. የአለርጂ አስም፡- ይህ የአስም ዓይነት በአለርጂዎች የሚቀሰቀስ መሆኑን ገልጸው፤ ለምሳሌ አቧራ፣ የአበባ ዱቄት (ዘር) ብናኝ፣ የእንስሳት ፍግ ሽታዎች አጋላጭ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። 2. አለርጂ ያልሆነ አስም፡- ይህ ደግሞ በኢንፌክሽን፣ በቀዝቃዛ አየር እንዲሁም በተበከለ አየር የሚነሳ የአስም ዓይነት መሆኑን ነው ያስረዱት። 3. በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ምክንያት የሚመጣ አስም፡- አካላዊ እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት እንዲሁም ከሥራ በኋላ የሚከሰት የአስም ዓይነት መሆኑን ያስረዳሉ። 4. ከሥራ ጋር የተያያዘ አስም፡- በሥራ ቦታ ተጋላጭነት ምክንያት የሚቀሰቀስ የአስም ህመም ዓይነት መሆኑን ገልጸዋል። 5. ከባድ የአስም በሽታ፡- ይህኛው የአስም ህመም ዓይነት ለመቆጣጠር አስቸጋሪ እና ባብዛኛው ባዮሎጂካል ሕክምናን የሚፈልግ መሆኑን አስረድተዋል። • ለአስም ህመም አጋላጭ ወይም ለህመሙ መባባስ መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው? አለርጂዎች (የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን፣ የአየር ብክለት፣ ጭስ)፤ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ፣ ጭንቀት እንዲሁም የጄኔቲክ ቅድመ-ዝንባሌ ለአስም ህመም ከሚያጋልጡ እና ህመሙን ከሚያባብሱ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውን ዶክተር ፍፁም ገልጸዋል። • አስም ያለባቸው ሰዎች ምን ይነት ጥንቃቄ ያድርጉ? ከአቧራ፣ ጭስ፣ አለርጂዎች መራቅና መጠንቀቅ፤ በኢንፍሉዌንዛ እና በኒሞኮካል ክትባቶች ወቅታዊ ክትባቶችን መውሰድ፤ በቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ ወቅት ሙቀት የሚሰጡ ልብሶችን መልበስ፤ ጥሩ እንቅልፍ መተኛት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ የተመጣጠነ አመጋገብን ማዘውተር እና መሰል ተግባራት የአስም ህመም እንዳይባባስ ያግዛሉ ብለዋል ባለሙያው። • ሕክምናውስ ምንድን ነው? የአስም ህመም የማስታገሻ እና የመቆጣጠሪያ (የረዥም ጊዜ) ሕክምናዎች እንዳሉት ያስታወቁት ባለሙያው እንደ ህመሙ ሁኔታ ስለሚወሰን ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ እንደሚገባ መክረዋል። በተለይም ምልክቶቹ በተባባሱበት ወቅት ከፍተኛ የአየር ትቦ መዘጋት ደረጃ ላይ እንዳይደርስ በጊዜ ሕክምናውን ማግኘት አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት አንስተዋል።
አሸንዳ- የፍቅርና የሰላም አጀንዳ
Aug 23, 2025 922
በአማረ ኢታይ የሴቶች በተለይም የልጃገረዶች በዓል መሆኑ የሚነገርለት የአሸንዳ በዓል ለማክበር አመቱ እስከሚደርስ ድረስ በጉጉትና በናፍቆት ይጠበቃል። አሸንዳ ይዋቡበታል፣ ቁንጅና ጎልቶ ይወጣበታል፣ ልጃገረዶችና ሴቶች ተሰባስበው የሚያዜሙበት፣ በስጦታ ጭምር የሚታጀብ ልዩ እና ውብ የአደባባይ በዓል ነው። የአሸንዳ በዓል ሲቃረብ በተለይ ልጃገረዶች ቀደም ብለው የመዋቢያ ጌጣጌጦችንና አልባሳትን አዘጋጅተው የበዓሉን መድረስ ይጠባበቃሉ። እለቱም ሲደርስ በተለየ ሁኔታ ተውበውና ደምቀው ከበሮ ይዘውና በጣእመ ዜማ ታጅበው ወደ አደባባይ በመውጣት ያከብሩታል። በዚህም መሰረት ትግራይ የአሸንዳ በዓል በየዓመቱ ከነሃሴ 16 ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በደማቅ ስነ ስርአት ይከበራል። እለቱ የልጃገረዶች የነፃነት ቀንም በመሆኑ የቤተሰብ፣ የዘመድ አዝማድ ቁጣ እና ይህን አድርጊ ይህን አታድርጊ የሚል ትእዛዝ እና ጫና አይኖርም። በመሆኑም አሸንዳ - የነፃነት፣ የፍቅርና የሰላም አጀንዳ ያነገበ በመሆኑ ከልጅ እስከ አዋቂ በየአመቱ በጉጉት የሚጠበቅ ደማቅ በዓል ነው። የአሸንዳ ልጆች ከበዓሉ ዋዜማ ጅማሮ እስከ ፍጻሜው ድረስ በየሰፈራቸው በቡድን በቡድን ተሰባስበው የሚጫወቱበት በመሆኑም የህብረት፣ የፍቅር፣ የሰላምና የአብሮነት ማሳያ ተደርጎም ይወሰዳል። ወላጆቻቸው አነስተኛ ገቢ ያላቸው ልጃገረዶችም ከእኩዮቻቸው፣ ከዘመድ አዝማድ እና ከጎረቤቶቻቸው የመዋቢያ ጌጣጌጦችን፣ አልባሳትና ሌሎች ቁሶችን ወስደው በዓሉን በደስታ የሚያሳልፉ ይሆናል። በዚህም መሰረት በዓሉ የመረዳዳት፣ የትብብርና ችግርን በመተጋገዝ ማለፍ እንደሚቻል የሚያመላክት ልዩ በዓል ነው። በዚሁ መሰረት የ2017 ዓ.ም የአሸንዳ በዓል በደማቅ ስነ ስርአት በመከበር ላይ ይገኛል። የፌደራል መንግስት እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች፣ በርካታ ቱሪስቶች ልጃገረዶችና ሌሎችም የበዓሉ ታዳሚዎች በተገኙበት በመከበር ላይ ነው። በክብር እንግድነት በመገኘት ንግግር ያደረጉት የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፤ ኢትዮጵያ በርካታ ውብ የሆኑ መገለጫዎች ያሏት ሀገር በመሆኗ አጉልተንና ለዓለም አስተዋውቀን የውበታችን ማሳያ እና የሃብት ምንጭ ጭምር ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል። የአሸንዳ በዓልን እሴት በመጠበቅ ለትውልድ ለማስተላለፍ ተቀናጅተን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል። በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች የሚከበሩ ባህላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶችን በማክበር ጠብቆ ማዝለቁ እንዳለ ሆኖ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎችን የማልማትና ታሪካዊ ቅርሶችን መጠበቅም ትኩረታችን ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል። በመጨረሻም የአሸንዳ በዓልን በድምቀት እያከበረ ለሚገኘው ለመላው የትግራይን ህዝብ በተለይም ለልጃገረዶች የሰላምና የፍቅር በዓል እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን ገልጸውላቸዋል። "የአሸንዳ በዓልን ማስዋብና ማድመቅ ለሰላምና ለአንድነት ያለንን መልካም ፍላጎትና ምኞት ማሳያ ነው። ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና እንዲለማ እንሰራለን።" በማለት መልእክታቸውን ያጋሩት ደግሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ናቸው። በጊዜያዊ አስተዳደሩ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አፅበሃ ገብረእግዛብሄር በበኩላቸው፣ ባህላዊ ይዘት ያለው የአሸንዳ በዓል ሳይበረዝ ትውፊቱን ጠብቆ እንዲቀጥል የክልልና የፌዴራል መንግስታት በጋራ እንሰራለን ብለዋል። በመቀሌ ከተማ እየተከበረ ባለው የአሸንዳ በዓል ከባህልና ስፖርት ሚኒስትሯ ሸዊት ሻንካ በተጨማሪ የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እና ሌሎችም ታድመዋል። አሸንዳ - የነፃነት፣ የፍቅርና የሰላም አጀንዳ ሆኖ መከበሩንም ቀጥሏል።
በሥራ ፈጠራ የስኬት ጉዞ የጀመረው ወጣት ተሞክሮ
Aug 22, 2025 895
(በያንተስራ ወጋየሁ - ከዲላ ኢዜአ ቅርንጫፍ) አንዳንዴ መዳረሻን የሚያሳምረው መነሻችን ነው ሲባል ይደመጣል።መነሻው ጥሩ ከሆነ ኋላ ለሚገኘው ስኬት መደላድል ይሆናል ለማለት ነው። ነገን አርቆ በማሰብና በማለም መስራት የህይወት ጉዞን ቀናና ስኬታማ ለማድረግ ጠቀሜታው የጎላ ነው። የሚገጥም ፈተናን እያሰቡ ወደኋላ ከማለት ይልቅ መፍትሄ በመፈለግ ወደስራ የገቡ ስኬት ሲያስመዘግቡ ይታያሉ። በዚህም ከራሳቸው ባለፈ ለሌሎችም ወጣቶች ሲተርፉ ይስተዋላል። በፈተና ወደኋላ ሳይል ከችግሩ የሚወጣበትን መንገድ በመፈለግ ስኬት ማስመዝገብ የጀመረው የወናጎ ከተማ ወጣት ኤፍሬም ጴጥሮስ ለእዚህ አንድ ማሳያ ነው። ወጣቱ በከተማው የቱቱፈላ ቀበሌ ነዋሪ ነው። በ2015 ዓ.ም በ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ያመጣው ውጤት ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የሚያስገባ አልነበረም። በዚህ ምክንያት ሁለት ዓመታተን እንዲሁ ያለስራ አባክኗል። ያለሥራና ያለትምህርት ባሳለፋቸው ሁለት ዓመታት ድብርት ውስጥ ገብቶ እንደነበር ያስታወሰው ወጣት ኤፍሬም በዚህ ሁኔታ ግን ህይወቱን መቀጠል አልፈለገም። በዙሪያው ለሀብት ምንጭ የሚሆኑ ነገሮችን ትኩረት ሰጥቶ ማሰላሰል ጀመረ። በወናጎ ከተማ ራሱን ከመለወጥ ባለፈ የአካባቢውን ማህበረሰብ መጥቀም የሚችልባቸውን የሥራ አማራጮችን ማየቱን ቀጠለ። በዚህ ወቅት ነበር በአዲስ እሳቤ የተጀመረውና ብዙዎች በስፋት በመሳተፍ ተጠቃሚ እየሆኑበት ያለው የሌማት ትሩፋት መርሀግብር ቀልቡን የገዛው። ይህ ሀገራዊ ኢንሼቲቭ ማህበረሰቡ ያለውን ልምድ የበለጠ በማስፋትና በማዘመን ተጠቃሚ እያደረገው በመምጣቱ የእሱንም ችግር ሊፈታ እንደሚችል ወጣቱ በማመኑ ቀዳሚ ትኩረት ያደረገው የዶሮ እርባታ ሥራ ላይ ነው። መንግስት ለማህበረሰቡ የዶሮ ጫጩቶችን በብዛት ማሰራጨት ተከትሎ ብዙች በዶሮ እርባታ ሥራ ተሰማርተዋል። የወናጎ ከተማ ነዋሪዎችም በዘርፉ ለመሰማራት ባላቸው ከፍተኛ ፍላጎት የዶሮ ጫጩቶችን በብዛት ሲረከቡ በየዕለቱ ማየቱ በውስጡ አንድ ነገር አጫረበት። በከተማው ለብዙ ሰዎች ለዶሮ እርባታ የሚሆን በቂ ስፍራ ማግኘት አዳጋች መሆኑ ለአምራቾች ትልቅ ፈተና ነው። ይህን የተረዳው ወጣቱ ለዚህ ችግር መፍትሄ ሊሆን የሚችል ነገር ቢሰራ አንድም ለራሱ ሥራ መፍጠር ነው፤ በሌላ ቡኩል የነዋሪዎችን ችግር መፍታት መሆኑን አሰበ። በአካባቢው ካሉ ግብአቶች በቀላል ወጪ ለማህብረሰቡ ይጠቅማል ያለውን ተንቀሳቃሽ የዶሮ ቤት ለመስራት ወሰነ። ጉዳዩን ከራሱና ከሌሎች ጋርም መከረበት። በእዚህም ወደስራው ለመግባት የሚያስችል ገንቢ ምክረ ሀሳብ አገኘ። ሀሳቡ አዲስና ለነዋሪውም የሚሰጠው ጥቅም የጎላ መሆኑ ደግሞ ይበልጥ አበረታታው። ይህም ተጨማሪ ብርታት ሆኖት ሀሳቡን ወደድርጊት በመቀየር "ተንቀሳቃሽ የዶሮ ቤት" በመስራት ለሽያጭ ማቅረብ ጀመረ። ተንቀሳቃሽ የዶሮ ቤቱ በጥቂት ቦታ በአንድ ጊዜ 120 የዶሮ ጫጩቶችን ለማርባት የሚያስችልና ሰፊ ቦታ የማይዝ መሆኑም በብዙዎች ዘንድ ተመራጭ እድርጎታል። ወጣት ኤፍሬም በወናጎ ከተማ ያለውን የቦታ ችግር ለመፍታት በአካባቢው ያለን ግብአት ተጠቅሞ የሰራው ተንቀሳቃሽ የዶሮ ቤት ዛሬ ከጌዴኦ ዞንና ወናጎ ከተማ ባለፈ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደረጃ በብዙዎች ዘንድ ተፈላጊ እየሆነ መጥቷል። ከስኬቶቹ መካካል በዚህ ሥራው በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ከመሆን ባለፈ ተስፋ ሰጪ ለውጥ እያሳየ ነው። የራሱን ሥራ ከፈጠረ ከአንድ ዓመት ያነሰ ጊዜ ቢሆነውም ከራሱና ከቤተሰቦቹ አልፎ ለሦስት የአካባቢው ወጣቶችም የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል። በወር ከአራት በላይ የተንቀሳቃሽ ዶሮ ቤቶችን በመሸጥ ከ100 ሺህ ብር በላይ ገቢ እንደሚያገኝ የሚናገረው ወጣቱ የዶሮ ቤት ሥራውም በህይወቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ ለውጥ እንዲያመጣና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነቱን እንዳሳደገው ይናገራል። በዚህም ሰርቶ ለመለወጥ ያለው ፍላጎት መነሳሳቱን የገለጸው ወጣቱ ጎን ለጎን የዶሮ እርባታ ሥራ ጀመረ። ተንቀሰቀሽ የዶሮ ቤት አዘገጅቶ ከመሸጥ ባለፈ ለሌሎች አርቢዎች ማስተማሪያ ይሆናል በሚል የ45 ቀን የእንቁላል ጣይ የዶሮ ጫጩቶችን በማርባት ለአካባቢ ማህበረሰብ እያቀረበ ይገኛል። ይህም ሥራውን በመጠንና በአይነት ለማስፋትና ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት አስችሎታል። የለውጡ ምክንያት "በአጭር ጊዜ ላሳየሁት ለውጥ ምክንያቱ ለሥራ ያለኝ ተነሳሽነት ነው" የሚለው ወጣቱ የተጠናከረ የገበያ ትስስርም እንዳለው ተናግሯል። በሚገጥም ችግር ተስፋ መቁረጥ መፍትሄ እንደማይሆን ለሌሎች ወጣቶች ይመክራል። ከዚያ ይልቅ በአካባቢ ያለን ሀብት ለልማት በማዋል ተጠቃሚነትን ለማሳደግ መስራት እንደሚገባ ነው የገለጸው። በተለይ ኑሮ ለውጥ ለማምጣት በሀገራዊ ኢንሼቲቮች በመሳተፍ ተጠቃሚ ለመሆን ተግቶ መስራት ይገባል ባይ ነው። የወጣቱን የዶሮ ቤት በመጠቀም በዶሮ እርባታ ሥራ ከተሰማሩ የወናጎ ከተማ ወጣቶች መካከል ወጣት አማኑኤል ቦጋለ አንዱ ነው። ተንቀሳቃሽ የዶሮ ቤቱ በውስን ስፍራ ዶሮ የማርባት ፍላጎቱን አሳክቶለታል። ሦስት ካሬ ብቻ የሚይዘውን የዶሮ ቤት በ20 ሺህ ብር በመግዛት በ120 የዶሮ ጫጩቶች ሥራውን ጀምሮ እያከናወነ ይገኛል። በአሁኑ ወቅትም ከራሱ ፍጆታ ባለፈ እንቁላል በመሸጥ ተጠቃሚ እየሆነ መምጣቱን ነው የተናገረው። የዶሮ ቤቱ የመመገቢያ፣ የማደሪያና ኩስ መጥሪግያ በዘመናዊ መንገድ የተዘጋጀለት መሆኑ ስራውን በቀላሉ ለማከናውን እንዳስቻለውም ገልጿል። የዶሮ ቤቱ እሱን ጨምሮ ለብዙዎች ከቦታ እጥረት ጋር በተያያዘ የነበረባቸውን ችግር እንደፈታ የገለጸው ወጣቱ፣ በሌማት ትሩፋት የተጀመረው የዶሮ እርባታ ሥራ ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን ተናግሯል። ይህን የሌማት ትሩፋት ሥራ የሚያጠናክሩ የፈጠራ ሥራዎች ደግሞ ተጠቃሚነትን ይበልጥ ስለሚያሳድጉ መስፋፋት እንዳለባቸውም ነው የተናገረው። በወናጎ ከተማ አስተዳደር ግብርና ዩኒት የእንስሳት ዘርፍ አስተባባሪ ወይዘሮ ፀደይ አጋደ በከተማዋ ከፍተኛ የሰዎች ጥግግት እንዳለ ያነሳሉ። ይሁን እንጂ የአካባቢውን ሀብቶች በመጠቀም ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ስራዎች ብዙዎች ተጠቃሚ እየሆኑና ህይወታቸውን እየለወጡ መጥተዋል። ነዋሪውም በዶሮ እርባታ ተሰማርቶ ተጠቃሚ ለመሆን ያለው ፍላጎት ከፍተኛ ነው። የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭን ተከትሎ በዶሮ እርባታ የሚሰማሩ ሰዎች ቁጥር ቢጨምርም የቦታ እጥረት ፈተና ሆኖ መቆየቱን ያነሳሉ። የህብረተሰቡን የቦታ ጥያቄ መፍታት ለአስተዳደሩ መሰረታዊ ተግዳሮት እንደነበር አስታውሰው፤ ወጣት ኤፍሬም በአካባቢ ከሚገኝ ግብዓት ተንቀሳቃሽ የዶሮ ቤት ስርቶ ለሽያጭ ማቅረቡ ችግሩን እያቀለለው መሆኑን ይናገራሉ። ወይዘሮ ፀደይ እንዳሉት በአሁኑ ወቅት በከተመው በሦስት የዶሮ መንድሮች የዶሮ እርባታ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል። በዚህም 14 በማህበር የተደራጁ እና ከ80 በላይ በግል የተሰማሩ ዶሮ አርቢዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው። የልማት ሥራው እንቁላልና ዶሮ ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እያስቻለ ነው። በወጣቱ የተሰራው ተንቀሳቃሽ የዶሮ ቤትም ከቦታ ጥበት ጋር በተያያዘ ከነዋሪዎች ሲነሳ የነበረውን ጥያቄ እየፈታ መሆኑን አስተባባሪዋ ይገልጻሉ። እንደወጣት ኤፍሬም የዜጎችን ችግር የሚፈቱና በመንግስት የሚከናወኑ የልማት ተግባራትን የሚያግዙ ፈጠራ የታከለባቸው ሥራዎች ልማቱ የበለጠ ስለሚያጠናክሩ የሚደገፉና የሚበረታቱ መሆናቸውን ነው የገለጹት። በየአካባቢው ያልተነኩ ሀብቶች አሉ። ዋናው ነገር ግን እነዚህን ሀብቶች እንዴት ወድልማት በመቀየር ተጠቃሚ መሆን ይቻላል የሚለው ነው። በተለይ ወጣቶች ሥራ የለም በሚል ምክንያት የማይተካ ጊዜን ያለአግባብ ማሳለፍ አይገባም። ህገወጥ ስደትን ምርጫ ማድረግም አግባብ እንዳልሆነ የወጣት ኤፍሬም ተሞክሮ እንድ ማሳያ ነው። መንግስት የዜጎችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የተለያዩ ኢኒሸቲቮችን ቀርጾ ወደተግባር አስገብቷል። በእነዚህ ኢኒሼቲቮች መሳተፍና እንዴት ስኬታማ መሆን እንደሚችሉ ቆም ብሎ ማሰብ ብቻ ነው ከእነሱ የሚጠበቀው። ያኔ መዳረሻቸውን አርቀው ማለም ይጀምራሉ። መነሻቸው መሰረት ከያዘ መዳረሻቸውን ማሳመር ይችላሉና ከወናጎ ከተማ ወጣት ኤፍሬም የስኬት ጉዞ ትምህርት መውሰድ ይገባል።
ትንታኔዎች
በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ 7 ቀናት የሚኖሯት ጳጉሜን…
Sep 5, 2025 423
ጳጉሜን በሦስት ዓመታት አምስት፣ በአራት ዓመታት ውስጥ ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት ውስጥ አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት ይኖሯታል። 👉 ‘ጳጉሜን’ ማለት ምንድን ማለት ነው? ‘ጳጉሜን’ የሚለው ስያሜ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል መምጣቱን በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የነገረ መለኮትና የሥነ-ልቡና መምህር አባ ጌዴዎን ብርሀነ ይገልጻሉ። ትርጉሙም “ተውሳክ ወይም ተረፍ” ማለት መሆኑን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አስረድተዋል። (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭) ላይም “በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን ተጨማሪ ሆና የምትመጣ መሆኗ ተገልጿል። በዚሁ መሠረት በሦስት ዓመት አምስት፤ በአራት ዓመት (በዘመነ ዮሐንስ) ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት እንደምትሆን ተመላክቷል። 👉 የጳጉሜን መሠረት? ይህን በተመለከተ መምህር አባ ጌዴዎን ሲያስረዱ፤ በየቀኑ የሚተርፉ ተረፈ ደቂቃዎችና ሰከንዶች ቀናትን እያስገኙ ተጠራቅመው ከዓመቱ በስተመጨረሻ አምስት ዕለታት ይተርፋሉ ይላሉ። በዚህም ጳጉሜን የተባሉ አምስት ዕለታት እንደሚገኙ ጠቁመው፤ አንድ ዓመት ደግሞ 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልኢት ይሆናል ሲሉ ይገልጻሉ። 15ቱ ኬክሮስ በአራት ዓመት ስድስት ጳጉሜንን ይወልዳል ያሉት መምህሩ፤ ስድስቱ ካልኢት ደግሞ በ600 ዓመት ሰባተኛ ጳጉሜንን ያስገኛሉ በማለት አብራርተዋል። 👉 ከጭማሬ ቀንነት በተለየ ያላት ትርጓሜ ምንድን ነው? እንደ መምህር አባ ጌዴዎን ገለጻ፤ ‘ጳጉሜን’ ከተጨማሪ ቀናትነት የተሻገረ ለኢትዮጵያውያን የማንነት ዐሻራ የእኩልነት ምልክት ናት። በዓለም ዘንድ ባለው የበላይነት እና ሌላውን አሳንሶ የማየት ዝንባሌ እንደነዚህ ያሉ የጥበብ መንገዶች የኢትዮጵያውያንን ማንነትና በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የቀዳሚነት ቦታም ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል አንዱ በመሆኑ የማንነት መገለጫ ናት ይላሉ። ምክንያቱም ከማንም ያልተወሰደ የራስ ማንነት መኖሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የመፈላሰፍ፣ የስልጣኔና አካባቢያቸውን በንቃት የመገንዘብ አቅም የሚያሳይ ስለሆነ ብለዋል። ጳጉሜን ኢትዮጵያን ከቀደምት ስልጡን ሀገራት መካከል ቀዳሚ የስልጣኔ ፋና የፈነጠቀባት ለመሆኗ ማሳያ ስለመሆኗም ይናገራሉ። የሰው ልጅ አካባቢውን በንቃት መገንዘብ መጀመሩ እና የሰማያዊ አካላትን የማይዋዥቁ ክስተቶች በመከታተል የማይታየውንና የማይሰፈረውን የጊዜ ርዝማኔ በብርሃናት እየሰፈረና እየለካ፤ ዕለታትን፣ ሳምንታትን፣ ወራትን፣ ወቅትን፣ ዓመታትን፣ አዝማናትን እና ሌሎች ዐውዳትን መቀመሩን ጠቅሰዋል። በዚህም የጊዜ ልኬት ከሥነ-ፈለክ እና ከሐሳበ-ከዋክብት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ እንዲሆን አድርጎታል ነው ያሉት። በአጭሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን ከሚያዩአቸው ተደጋጋሚ ሁነቶች በመነሳት የጊዜ አሃዶችን ወስነዋል፤ ክፍፍሎችንም በይነዋል ብለዋል መምህር አባ ጌዴዎን። በተለይም ለዕይታቸው ቅርብ የሆኑት የፀሐይ እና የጨረቃ ያለማቋረጥ መውጣት እና መግባት፣ የሚወጡበት እና የሚገቡበትም የጊዜ መጠን በአንጻራዊነት ቋሚ በመሆኑ ለቀን አቆጣጠራቸው ዋነኛ ግብዓቶች እንደሆኗቸው ተናግረዋል። በሂደትም የዑደታቸውን የጊዜ መጠን በሚገባ ተረድተው፣ የዑደታቸውን ህጸጾች ዐወቁ ይላሉ። በዚህ ብቻ ሳይገደቡ የሰማይ አሰሳን ከፀሐይ እና ጨረቃ ወደ ሌሎች አፍላካት፣ ወደ ከዋክብትም ጭምር ማስፋታቸውን ነው የሚገልጹት። በዚሁ መሠረት ኢትዮጵያ የራሳቸው የቀን መቁጠሪያ ቀመር ካላቸው ቀደምት ሀገራት መካከል አንዷ መሆን መቻሏን አስገንዝበዋል። ለዚህም በዋቢነት ከሚጠቀሱት ጥንታዊ መዛግብቶቿ መካከል መጽሐፈ ሄኖክን እና አቡሻኽርን አንስተዋል። 👉 ከነበረው ወደ ሌላኛው ዓመት መሻገሪያ እንደመሆኗ ሰዎች በዚህ ወቅት ምን አይነት ሥነ-ልቡናዊ ዝግጅት እንዲያደርጉ ይመከራል? ጊዜ የለውጥ መስፈሪያ (መለኪያ ወይም መለያ ድንበር) መሆኑን የሚገልጹት መምህር አባ ጌዴዎን፤ ለውጥ ያለጊዜ፣ ጊዜም ያለ ለውጥ አይሆኑም፤ ትርጉምም የለውም ይላሉ። ጊዜ በዚህ ዓለም የማይቋረጥ ሂደት፤ የማይቆም የለውጥ ጥያቄ መሆኑንም ያስገነዝባሉ። በዚህ የለውጥ ምክንያት የሰው ልጅ የሚኖረው ከተሰጠው ወይም ካለው እየቀነሰ እንጅ እየጨመረ እንዳልሆነም ይጠቅሳሉ። ስለዚህ ጳጉሜን የማንቂያ ደወል ናት፤ የአዲስ ዘመን ማብሰሪያ አዲስ ዘመን በለውጥ ምክንያት የተገኘ በመሆኑ ከነበረው የዕለታት ድምር ባሻገር አዲስ የሚል ቅጽል ይዞ መጥቷል ይላሉ። ስለዚህ ጳጉሜን ምን አዲስ ነገር አለ የሚል የሕይወት ጥያቄ አስከትላ የመጣች በልባችን ምኅዋር የምታቃጭል ናት ብለዋል። በጳጉሜን ብዙዎች በጽሞና ሆነው ራሳቸውን የሚያዳምጡባት ወደውስጥ በጥልቀት የሚመለከቱባት በመሆኗ ባለፉት ጊዜያት ያልተሳኩትን በቀጣይ ለማሳካት አዳዲስ ሐሳቦችን እና እቅዶችን በማዘጋጀት ለቀጣዩ ምዕራፍ የምታሻግር ናት በማለት ገልጸዋል።
የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት አንገብጋቢው ጉዳይ
Aug 6, 2025 1414
የባህር በር ጉዳይ በሀገራት ዘንድ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ግዙፍ ኢኮኖሚና ሰፊ ህዝብ ላላቸው ሀገራት ሕልውና ጉዳይ ሆኗል። በቱርክሜኒስታን አዋዛ ከተማ ሶስተኛው ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራት ጉባዔ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝም በጉባኤው መክፈቻ ላይ ቁልፍ መልዕክት አስተላለፈዋል። ዋና ፀሐፊው ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በተለይም መልኩ እየተለዋወጠ ባለው ዓለም፤ በአየር ንብረት ለውጥና መሰል ተጽዕኖዎች ሳቢያ መልከ ብዙ ፈተና እንደተደቀነባቸው ገልጸዋል። በተለይ ለአንዳንዶቹ ህልውናቸውን እየተፈታተነ ስለመሆኑም አጽንኦት ሰጥተዋል። የዋና ጸሐፊው ንግግርም ፦ ዛሬ ከዚህ የተሰባሰብነው ለማንክደው አንድ ዕውነት ነው። መልክዓ ምድር መዳረሻን መወሰን የለበትም። ነገር ግን በአፍሪካ፣ በኤዥያ፣ በላቲን አሜሪካና በአፍውሮፓ 32 ሀገራት ባህር በር ስለሌላቸው የማደግ ዕድላቸው ተገድቧል፤ ኢ-ፍትሃዊነትንም አስፍቷል። ሀገራችሁ አያሌ ተግዳሮቶች ተጋርጦባቸዋል። ዕድገታቸው እንዲወሰን፣ በከፍተኛ የወጪ ንግድ ትራንስፖርት እንዲበዘበዙና በዓለም ገበያ ተደራሽ እንዳይሆኑ ፈተና ገጥሟቸዋል። በርካቶች በጥሬ ዕቃ ኤክስፖርት እንዲወሰኑ፣ ለተለዋዋጭ ዓለም አቀፍ ገበያ እንዲጋለጡ ብሎም በጠባብ ኢኮኖሚያዊ መሰረት እንዲታጠሩ አድርጓቸዋል። በሌላ በኩል የዕዳ ጫና ለመልከ ብዙና ዘላቂነት ላለው ችግር ዳረጓቸዋል። አንድ ሶስተኛው የዓለማችን ባህር በር አለባ ሀገራትም ለደህንነት እንዲጋለጡና የግጭት አዙሪት ችግር እንዲገጥማቸው ተገደዋል። ምንም እንኳን 7 በመቶው የዓላማችን ህዝብ ድርሻ ቢይዙም በዓለም ኢኮኖሚ አንድ በመቶ ብቻ ድርሻ ይዘዋል። ይህም ምንጊዜም ኢ-ፍትሃዊነትና መገለል ሁነኛ ማሳያ ነው። ይህ የኢ-ፍትሃዊነት መልክ ዘላለማዊ መሆን የለበትም። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በዓለም የፋይናንስና የንግድ መዋቅር ውስጥ ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ ናቸው። በበይነ-ዓለም ትስስር በገሀድ በሚታይበት የዛሬው የዓለም መልክ ስርዓታዊ መድሎና መገለል በይፋ የደረሰባቸው ሀገራት ናቸው። ይህም በብዙ ምክንያቶችም የቅኝ ግዛት አሻራ ምልክት ነው። በቅርብ ጊዜ ትውስታዎች እንኳን ከኮቪድ 19 እስከ አየር ንብረት ለውጥ ቀውሶች፣ ከአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል እስከ ግጭት እንዲሁም በጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች ሳቢያ ባህር በር የሌላቸው ሀገራት ዘላቂ የልማት ግቦችን ዕውን ለማድረግ ተቸግረዋል። ይህ ጉባኤ ችግሮችን ከማንሳት ባሻግር መፍትሄዎች ላይ ማተኮር አለበት። የቀጣይ ዘመን የእድገት መሻት ጉዞን መቀየስ ብሎም ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራትን የማልማት ዕድሎች በጋራ መግለጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምክር ይገባል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም በዚህ ረገድ ከሀገራቱ ጎን የቆመ ነው። በቀጣይ አስርት ዓመታት በትብብር መሰራት ካለባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ መዋቅራዊ ሽግግርን ማሳለጥ እና ኢኮኖሚያዊ ስብጥርን ማብዛት ላይ መተኮር ይገባል። ምክንያቱም እነዚህ ሀገራት በሰው ሃይል እና በተፈጥሮ ሀብት የታደሉ ቢሆንም በፋይናንስ እጥረትና በገበያ እጦት ይህን አቅም ተጠቅመው መልማት አልቻሉም። ወሳኝ የሆኑ እሴት ጨማሪ ኢንዱስትሪዎችን መገንባት፣ ሀገር ውስጥ ፈጠራዎችን ማጎልበት እንዲሁም ለቀጣናው ለትውልድ ትሩፋት የሚያቋድስ አካታች ልማትን ዕውን ማድረግ ይሻል። የሀገራቱን የገበያና የመልክዓ ምድር ተግዳሮቶችን ለማቅለል አንዱ መፍትሄ የዲጂታላይዜሸን ሽግግር ነው። በዲጂታል ምህዳር ተደራሽነት ለማቅለልም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ስራዎች መጠንከር አለባቸው። የግል ዘርፉን ማጠናከርም ኢ-ፍትሃዊነትና ተደራሸነትን ችግርን ለማቅለል ያግዛል። ሀገራቱ በቋንቋ፣ በባህልና በጥበብ በጥልቅ የተቆራኙ ናቸው። በሀገራቱ መካከል ያለው የተቆራረጠ ሎጂስቲክስ፣ ያልተሳለጠ የድንበር ግብይት፣ የተሟላ መሰረተ ልማት አለመኖር በዓለም ገበያ ተወዳደሪና ተደራሽ ለመሆን አልቻሉም። በመሆኑም ድንበር ዘለል የሆኑ ትስስሮችን ማሳለጥ በተለይም ሀገራትን የሚያስተሳሰሩ ኮሪደሮችን መገንባት፣ የጭነት ሎጂስቲክስን ማሳለጥ፣ የሃይል እና የአየር ትራንስፖርት ትስስርን መጨመር ያስፈልጋል። ይህን መንገድ በመከተል በቀጣናውና በዓለም ገበያ መግባት ብሎም ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወደ እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን ማቅረብ መሸጋገር ይቻላል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የንግድ ግብይት መልክን መለወጥ፣ የትብብርና የጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተቃኘ አካሄድ መከተል ይገባል። ዓለም አቀፍ የባለብዙ ወገን የፋይናንስ ተቋማትም የበይነ ሀገራት የድንበር ላይ ትስስርና የጋራ ልማት ላይ ተገቢውን የኢንቨስትመነት ልማት ፋይናንስ ማቅረብ ይገባቸዋል። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በቀጣናው ደረጃ ከተሰባሰቡ ልማትን ዕውን ማድረግ ያስችላልና። ባህር በር አልባ ሀገራት ምንም እንኳን ከዓለማችን ሀገራት የበካይ ጋዝ ልቀታቸው ለከ3 በመቶ ያነሱ ቢሆነም የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ገፈት ቀማሾች ግን እንርሱ ናቸው። ከሰሃራ በርሃ መስፋፋት እስከ በረዶ የሚቀልጥባቸው ተራራማ ሀገራት፣ የኤስያ ሀገራት አስቸጋሪ የአየር ጸባይ ለውጥ፣ በከባድ ዝናብና አውሎንፋስ የሚመቱ የላቲን አሜሪካ ሀገራት ለዚህ ማሳያ ናቸው። የአየር ንብረት ለውጥ ባህር በር አልባ ሀገራትን እየበላቸው ነው። የአየር ንብረት ለውጥና ባህር በር አልባነት ተዳምሮ ዕድገታቸውን እንዲወሰን ለአንዳንዶቹም በህልውናቸው ላይ አደጋ ደቅኗል። በተባበሰው የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ሳቢያ በአንድ አዳር በሚደርስ የመሰረተ ልማት ውድመት የሀገራት ዓለም አቀፍ ንግድ ተሳትፎ አደጋ ውስጥ ይወድቃል። በመሆኑም ቃል የተገቡ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መቋቋሚያ ፋየናንስ መተግበር፣ ተዕጽኖ የሚቋቋም መሰረተ ልማት መዘርጋት ይሻል” በማለት ነበር መልዕክታቸውን ያስተላለፉት። በአረንጓዴ ልማት፣ በፋይናንስ ማሰባሰብ፣ በብድር አቅርቦት እና ወለድ አያያዝና ትግበራ ጉዳይም ልብ መባል ያለበትን ጉዳይ ጠቅሰዋል። ባህር በር አልባ ሀገራት በጋራ ነጋቸውን ለማሳመርና ፈተናዎቻቸውን ለመሻገር በትብብር እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ጥያቄዋን በይፋ ከገለጸች ውላ አድራለች፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የባህር በር ጥያቄ የህልውና ጉዳይ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወሳል።
ኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሽግግር ለምን አስፈለጋት?
Jul 19, 2025 1656
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቲኒዮ ጉቴሬዝ አነሳሽነት እ.አ.አ 2021 የተመድ የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በኒው ዮርክ በበይነ መረብ አማራጭ ተካሄዷል። “የህዝቦች ጉባኤ” እና “የመፍትሄ ጉባኤ” የሚሉ ስያሜዎች የተሰጠው ጉባኤ ላይ ከ193 ሀገራት የተወጣጡ ከ51 ሺህ በላይ ሰዎች ተሳትፈውበታል። በምግብ ስርዓት ላይ የተዘጋጀ ይህ ታሪካዊ ጉባኤ ዓለም አቀፍ ሁነት ዋንኛ ግቡ የነበረው የተመድ አባል ሀገራት የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን እንዲያመጡ እና ስርዓተ ምግብን ከዘላቂ ልማት ግቦች በተለይም ከግብ ሁለት ረሃብን ማጥፋት ጋር ማስተሳሰር ነው። ጉባኤው በአምስት ዓበይት የትኩረት ነጥቦች ላይ ያተኮረ ነበር። ለሁሉም ዜጋ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብ ተደራሽ ማድረግ፣ ከብክነት ወደ ዘላቂ የምግብ አጠቃቀም መሸጋገር፣ ተፈጥሮን ያማከለ የምግብ ምርማነትን ማሳደግ፣ እኩልነትን መሰረት ያደረገ የአኗኗር ሁኔታን ማጠናከር እና ለአደጋዎችና ጫናዎች የማይበገር ጠንካራ የምግብ ስርዓት መገንባት ጉባኤው የተወያየባቸው ጉዳዮች ናቸው። ጉባኤው በወቅቱ አባል ሀገራት ሁሉን አቀፍ የምግብ ስርዓትን በመፍጠር የዘላቂ ልማት ግቦችን እንዲያሳኩ ጥሪ አቅርቧል። የተመድ የዓለም የምግብ ደህንነት ኮሚቴ የምግብ እና የስነ ምግብ ከፍተኛ የባለሙያዎች ፓናል የስርዓተ ምግብ አካሄድ ከባቢ አየር፣ ዜጎች፣ ግብአቶች፣ ሂደቶች፣ መሰረተ ልማቶችና ተቋማትን ጨምሮ ሁሉንም ተዋንያን ያሳተፈ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል። ስርዓተ ምግብ ምርት፣ ማቀነባበር፣ ስርጭት፣ ማዘጋጀት፣ መመገብ እና የተረፈ ምግብ አወጋገድን አቅፎ የያዘ እና ይህም ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ከባቢ አየር ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ ያለው ነው። የባለሙያዎች ፓናሉ የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን ዜጎች፣ ምድር፣ ብልጽግና፣ ሰላም እና አጋርነት ላይ ያውጠነጠነ መሆኑን ይገልጻል። ፓናሉ ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት በምግብ ስርዓት ላይ ለውጥ ያመጣል ያላቸውን ስድስት ሀልዮታዊ ማዕቀፎችን ቀርጿል። ህይወት ያላቸው እና የቁስ አካላት ባህርያት፣ ከባቢ አየር የመጀመሪያው ነው። በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ቴክኖሎጂ፣ ኢኖቬሽንና መሰረተ ልማት ሲሆን ኢኮኖሚ እና ገበያ ሶስተኛውን ስፍራ ይይዛል። ፖለቲካ እና ተቋማዊ ሁኔታ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ ጉዳዮች እንዲሁም የስነ ሕዝብ ውቃሬ ሌሎች የምግብ ስርዓት ለውጥ አምጪ ምክንያቶች እንደሆኑ ተቀምጧል። ስድስቱ የምግብ ለውጥ አሳላጭ ሁኔታዎች ተፈጻሚ እና ውጤታማ የሚያደርጉ አራት ቁልፍ መስኮች እንዳሉም የባለሙያዎች ፓናሉ ያስቀምጣል። የምግብ ምርታማነትን የሚያሳድጉ ስርዓቶችን መደገፍ፣ የምግብ አቅርቦት ሰንሰለትን ማጠናከር፣ የዜጎችን የምግብ አጠቃቀም ባህሪያት ላይ ለውጥ ማምጣት እና የተመጣጠኑ ንጥረ ምግቦችን ብዝሃነት ማስፋት ቁልፍ የትኩረት ጉዳዮች ናቸው። የተቀመጡትን ማዕቀፎች፣ ለውጥን የመፍጠሪያ መንገዶች እና አስቻይ ሁኔታዎች ከፖሊሲ እና ሁሉን አቀፍ አስተዳደር ጋር በማቆራኘት የምግብ ስርዓት ላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚገቡ ባለሙያዎቹ ምክረ ሀሳባቸውን ያቀርባሉ። የኢትዮጵያ የስርዓት ምግብ ራዕይ (EFS) መነሾም በስርዓተ ምግብ ጉባኤው እ.አ.አ በ2030 መሳካት አለባቸው ብሎ ያስቀመጣቸውን የስርዓተ ምግብ ግቦች እውን ለማድረግ ያሉ ፈተናዎች እና እድሎች ናቸው። እ.አ.አ በ2024 የወጣው የኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሁሉን አቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ በጉባኤው የተቀመጡ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት እና የጉባኤውን ምክረ ሀሳቦች ለመተግበር ቁርጠኛ እንደሆነች ይገልጻል። የኢትዮጵያ መንግስት እ.አ.አ ዲሴምበር 2020 የኢትዮጵያ ስርዓተ ምግብ የአሰራር ሂደት ይፋ ያደረገ ሲሆን ሂደቱ እ.አ.አ ጃንዋሪ 2021 ተጀምሯል። የስርዓተ ምግብ ማዕቀፉ የኢትዮጵያን የስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ራዕይን በግልጽ ያስቀመጠ ነበር። በወቅቱ ሂደቱን ለማስጀመር የቀድሞ የግብርና ሚኒስትር ኡመር ሁሴን እና የቀድሞ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የመሯቸው የከፍተኛ ደረጃ ምክክሮች የተደረጉ ሲሆን ሰነዶችም ተቀርጸዋል። በስርዓት ምግብ ላይ ሁለት ብሄራዊ ምክክሮች የተደረጉ ሲሆን ምክክሮችን ተከትሎ የኢትዮጵያ ስርዓተ ምግብ ሂደት ይፋ ሆኗል። ምክክሮቹ የኢትዮጵያ ምግብ ስርዓት አሁናዊ ሁኔታ አና መጻኢ ሁኔታዎች፣ የኢትዮጵያን የምግብ ስርዓት የመለወጥ ጉዞ በሚል ርዕስ የተካሄዱ ናቸው። የስርዓተ ምግብ ሂደት ቀረጻው ላይ መንግስት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የሲቪክ ማህረሰቦች፣ የምርምር ተቋማት፣ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ተቋማት ያሉባቸው ከ120 በላይ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። ይፋ የሆነውም የስርዓተ ምግብ ሂደት ሰነድ እ.አ.አ በ2021 በጣልያን ሮም በአካል ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ ላይ ቀርቦ አዎንታዊ ምላሾችን አግኝቷል። የስርዓተ ምግብ ሂደት ማዕቀፉ ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ፣ ከ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ እንዲሁም ከሌሎች የፖሊሲ እና አሰራሮች ጋር የተጋመደ ነው። የኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሁሉን አቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ለውጥ እና ሽግግር ያስፈለገባቸውን ምክንያቶች ያስቀምጣል። የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ተደራሽነት በሚፈለገው ደረጃ ማረጋገጥ አለመቻል፣ ፈጣን የህዝብ እድገት፣ የክትመት መጠን መስፋፋት፣ የከባቢ አየር ጉዳት እና የአየር ንብረት ለውጥ፣ እኩል ያልሆነ የዜጎች አኗኗር፣ ደካማ የምግብ ስርዓት መሰረት፣ ግብርናን ለኢኮኖሚ ያለውን ድርሻ ማሳደግ እና የምግብ ስርዓትን ከብሄራዊና ዓለም አቀፍ ግቦችን ጋር ማሰናሰን ማስፈለጉ የስርዓተ ምግብ ለውጡ መሰረታዊ ለውጥ መነሻ ናቸው። ኢትዮጵያ በስርዓተ ምግብ ሽግግር ውስጥ ስንዴን ጨምሮ በተለያዩ ሰብሎች ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ፣ የንጥረ ነገሮችን ብዝሃነት በማስፋት፣ የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ተደራሽነትን በማሳደግ እና የግብርና ማቀነባበሪዎችን ቁጥር በመጨመር አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግባለች። በዚህም በዜጎች ጤና እና ገቢ እድገት ላይ ለውጦች መምጣታቸውን ሪፖርቱ ያሳያል። ብሄራዊ የምግብ ስርዓት ማዕቀፎች፣ በምክክሮች የዘርፉ ተዋንያን የማሳተፍ ሁኔታ እያደገ መምጣት፣ በምግብ ስርዓቱ በሰባቱ ስትራቴጂካዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ስር ለውጥ አምጪ ተብለው የተቀመጡ 24 መፍትሄዎች እና ተቋማዊ አቅም ግንባታ ሌሎች የታዩ አበረታች ለውጦች ናቸው። ሰባቱ ስትራቴጂካዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብን ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ፣ ጤናማ የአመጋገብ ሁኔታን መፍጠር፣ አሰራሮች እና ፖሊሲዎችን በተቀናጀ መንገድ መተግበር፣ በምግብ ስርዓቱ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እና አሰራሮችን መተግበር፣ የገበያ ተደራሽነት ማስፋት እና መረጃ አሰጣጥን ማጠናከር፣ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ህብረተሰብ ክፍሎችን መጠበቅ እና የማይበገር አቅም መገንባት እንዲሁም መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋት፣ ዘላቂነት ያለው የከተሜነት እድገትን መፍጠር እና ክህሎት ልማት ላይ ያተኮሩ ናቸው። ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን በሚፈለገው መጠን ተደራሽ አለማድረግ፣ ደካማ የምግብ ደህንነት መሰረተ ልማት፣ የግብርና ሜካናይዜሽን አለመስፋፋት፣ የከባቢ አየር ጉዳቶች፣ የቅንጅታዊ አሰራር ላይ ያሉ ክፍቶች እና የዜጎች የአኗኗር ሁኔታ ለይ ለውጦች ቢኖሩም አመርቂ አለመሆን፣ የፋይናንስ ውስንነት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ ቴክኖሎጂዎች ተደራሽነት በምግብ ስርዓቱ ዋና ፈተናዎች ተብለው የተቀመጡ ናቸው። የምግብ ስርዓትን አስተዳደርን እና የባለድርሻ አካላት ቅንጅትን ማጠናከር፣ የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ መዋቅሮችን መዘርጋት፣ የመንግስት እና የግል አጋርነትን ማጠናከር፣ አቅምን መገንባት እና የምግብ ስርዓት አጀንዳ ዘላቂነት ባለው እና በተቀናጀ ሁኔታ ለማህበረሰቡ ማስገንዘብ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተብለው ከተለዩ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ። የገበያ ትስስርን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ እቅዶች እና ስትራቴጂዎችን ማቀናጀት እንዲሁም ወጣቶች፣ ሴቶች እና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጨምሮ የስርዓተ ምግብ ትግበራው ሁሉን አካታችነት የበለጠ ማረጋገጥ ቀጣይ የቤት ስራ ተብለው የተያዙ ናቸው። በአጠቃላይ የስርዓተ ምግብ ማዕቀፉን በየጊዜው በመፈተሽ እና የሁኔታዎችን ተለዋዋጭነት ከግምት ውስጥ ባስገባ ሁኔታ የአስተዳደር መዋቅርን በማሻሻል እ.አ.አ በ2030 የተያዙ ግቦችን ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራ ሁሉን አቀፍ ሪፖርቱ ያመለክታል። በአዲስ አበባ ከሐምሌ 20 እስከ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄደው ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በስርዓተ ምግብ ላይ እያከናወነች ያለውን ስራ ለዓለም የማሳወቅ ስራ ታከናውናለች። በስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ያላትን ተሞክሮዎች በዋናው ጉባኤ እና በጎንዮሽ ሁነቶች ላይ ታቀርባለች። የጉባኤው ተሳታፊዎችም የኢትዮጵያን የስርዓተ ምግብ የተግባር ስራዎች እና ውጤቶች በመስክ ምልከታቸው ይቃኛሉ።
የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ አሻራ ያረፈበት የኢትዮ-ታንዛንያ ወዳጅነት
Dec 17, 2024 4839
የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። የታንዛንያ የውጭ ጉዳይ እና ምሥራቅ አፍሪካ ትብብር ሚኒስትር አምባሳደር ማሕሙድ ታቢት ኮምቦ በስብስባው ላይ ለመሳተፍ ትናንት አዲስ አበባ ገብተዋል። ስብስባው የኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የሁለትዮሽ ትስስር እና የጋራ ትብብር የማጠናከር ዓላማ የያዘ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት በየካቲት ወር 2016 ዓ.ም ከታንዛንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከነበሩት ጃንዋሪ ማካምባ ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት የኮሚሽኑን ስብስባ ለማካሄድ ከስምምነት መድረሳቸው አይዘነጋም። የኢትዮጵያና ታንዛንያ የሁለትዮሽ ወዳጅነት በቅርበት ለመረዳት የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄን ማየት ግድ ይላል። የመላው ጥቁር ሕዝቦች ንቅናቄ የሆነው ፓን አፍሪካኒዝም ጅማሮ በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። የፓን አፍሪካኒዝም መሰረት የሆነችው ኢትዮጵያ የንቅናቄው ፋና ወጊ በመሆን ወሳኝ ሚና ተጫውታለች። የፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ ላይ ከኢትዮጵያ ጋር አብረው በመቆም ትግል ሲያደርጉ ከነበሩት አገራት መካከል ታንዛንያ ትገኝበታለች። በፓን አፍሪካኒዝም ትግል ውስጥ ስማቸው በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ መሪዎች መካከል ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ እና የታንዛንያው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጁሊዬስ ኔሬሬ ተጠቃሽ ናቸው። መሪዎቹ ለአፍሪካ አገራት ከቅኝ አገዛዝ መውጣት ትልቅ ሚና በመጫወት ሕያው አሻራቸውን አሳርፈዋል። የኢትዮጵያና ታንዛንያ የሁለትዮሽ ግንኙነት በእነዚህ መሪዎች ጊዜ የተጀመረ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። አገራቱ በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጣር ግንቦት 25 ቀን 1963 የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (በአሁኑ መጠሪያው የአፍሪካ ኅብረት) መቋቋሙ ሲበሰር መስራች አባል አገራት ነበሩ። ኢትዮጵያና ታንዛንያ በየአገራቱ ኤምባሲያቸውን በይፋ በመክፈት የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናክር እየሰሩ ይገኛሉ። አገራቱ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማጠናከር የሚያስችላቸው በርካታ አቅሞች አሉ። ኢትዮጵያ እና ታንዛንያ ባላቸው የቁም እንሥሳት ኃብት ከአፍሪካ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ አገራት ናቸው። ሁለቱ አገራት በሚያደርጓቸው የጋራ ምክክሮች ይሄን ሰፊ ኃብት በመጠቀም የንግድ እና ኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከር እንደሚገባ በተደጋጋሚ ጊዜ ያነሳሉ። ግብርና፣ የሰብል ምርት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ እና አቪዬሽን ከሁለቱ አገራት የትብብር መስኮች መካከል በዋናነት ይጠቀሳሉ። የኢትዮጵያ አቪዬሽን አካዳሚ በርካታ ታንዛንያውያን ፓይለቶች እና ኢንጂነሮችን አሰልጥኖ አስመርቋል። አቪዬሽንም የሁለቱ አገራት ቁልፍ የትብብር መስክ በሚል ይነሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በየካቲት ወር 2016 ዓ.ም በታንዛንያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከታንዛንያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሁሉ ሀሰን ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። አገራቱ በወቅቱ በባህልና ኪነ-ጥበብ፣ በግብርና እንዲሁም በኤሌክትሪክ ኃይል ንግድ ላይ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቶቹ የሁለቱ አገራት ትብብር ይበልጥ ለማጠናክር ትልቅ ፋይዳ አላቸው። የዛሬው የኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባም የስምምነቶችን አፈፃጸም በመገምገም ትግበራውን ማፋጠን የሚያስችል አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል። ከሰሞኑ የምሥራቅ አፍሪካ ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት አካል የሆነው ከኬንያ ወደ ታንዛንያ የተዘረጋው የኤሌክትሪክ መስመር የሙከራ የኃይል አቅርቦት መጀመሩ ይታወቃል። የቀጣናው ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ (ሃይዌይ) ፕሮጀክት የመጀመሪያው የኃይል ትስስር ኢትዮጵያና ኬንያን ያስተሳሰረ መሆኑ ይታወሳል። የፕሮጀክቱ ሁለተኛ ክፍል ደግሞ ከኬንያ ወደ ታንዛኒያ የተዘረጋ ሲሆን የኤሌክትሪክ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ተጠናቆ የሙከራ ኃይል አቅርቦት መጀመሩን የውኃና ኢኒርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ይህ ቀጣናዊ የኃይል ትስስር በተመጣጣኝ ዋጋ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት በማረጋገጥ በሀገራት መካካል ትብብርን እና የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው። የኃይል አቅርቦት መጀመሩ ከኢትዮጵያ እና ታንዛንያ አልፎ በቀጣናው ያለውን ትስስር ለማፋጠን ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይታመናል። ሁለቱ አገራት በቅርቡ ወደ ትግብራ ምዕራፍ የገባው የናይል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን በአገራቸው ፓርላማ ማጽደቃቸው ይታወቃል። ስምምነቱ በናይል ተፋስስ የውኃ ኃብትን ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ በሆነ መልኩ በበጋራ ለመጠቀም የሚያስችል ነው። አገራቱም በውኃ ኃብት ያላቸውን ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክር ነው። የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ ያስተሳሰራቸው ኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ትብብራቸውን ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ማሸጋግር የሚያስችሉ ሰፊ እድሎች ከፊታቸው ይጠብቃቸዋል።
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 4746
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 3679
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
የአርሶ አደሮችን ጓሮና ኑሮ የለወጡ ቁጥሮች- “30-40-30”
Nov 15, 2024 5188
ለዛሬው ትውልድ ምግብ፣ ለመጪው ትውልድ ደግሞ ቅርስና ውርስ የሚሆን ሃብት የሰነቀው የ"30-40-30" ኢኒሼቲቭ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አርሶ አደሮች መንደር ተገኝቶ ስለ ’30-40-30’ አሃዞች አርሶ አደሮችን የሚጠይቅ ካለ የቁጥሮችን ትርጓሜና ስሌት በቅጡ መረዳት ይችላል። እነዚህ ቁጥሮች በገጠራማው የክልሉ አካባቢዎች አባውራዎች ዘንድ ሕይወትም፣ አስተሳስብም ለውጠዋልና። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኅላፊ አቶ ዑስማን ሱሩር የ’30-40-30’ ኢኒሼቲቭ የተጠነሰሰው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭን በመመርኮዝ ስለመሆኑ ያስታውሳሉ። እነዚህ ቁጥሮች የተራ አሃዝ ስያሜ ሳይሆኑ በክልሉ ግብርና ወደ እመርታ ለማስፈንጠር የተቀየሱና ትውልድ ተሻጋሪ ዓላማ የሰነቁ ናቸው። በ2014 ዓ.ም ጀምሮ እያንዳንዱ የክልሉ አርሶ አደር በሶስት ዓመታት ውስጥ ቢያንስ 100 የፍራፍሬ ዛፎች አልምቶ እንዲጠቀም መሰረት የሆኑም ናቸው። በኢኒሼቲቩ የለሙ ፍራፍሬዎች የአርሶ አደሩን ኑሮ ማሻሻል ያለሙ፣ 'ለዛሬው ትውልድ ምግብ፣ ለመጪው ትውልድ ደግሞ ቅርስና ውርስ ናቸው' ይላሉ። የምግብና ስነ-ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ ገቢ ምንጭ ማድረግ፣ ስራ ዕድል መፍጠር፣ ገበያ ማረጋጋት፣ ለኤክስፖርትና ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት ማቅረብን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ዓላማዎችም አሏቸው። በእያንዳንዱ አባውራ ጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲለማና ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል የተወጠነ ነው። በዚህም በ'30-40-30'ን እያንዳንዱ አባወራ ጓሮውን እንደየአካባቢው ስነ-ምህዳር በሙዝ፣ በፓፓያ፣ በማንጎ፣ በቡና፣ በአቮካዶና በሌሎች ፍራፍሬ ችግኞች እንዲያለማ ተደርጓል። 'ያልተሄደበትን መንገድ በመሄዳችን በትግበራ ሂደቱ ፈተናዎች ነበሩ' የሚሉት ሃላፊው፤ ዛሬ ላይ ግን የ30-40-30 ኢኒሼቲቭ ፍሬ የቀመሱትን ሁሉ አስተሳስብ ለውጧል ይላሉ። ኢኒሼቲቩ ባልተለመዱ አካባቢዎች የፍራፍሬ መንደሮች የተፈጠሩበት፣ የአርሶ አደሩ ኑሮና ጓሮ የተለወጠበት፣ የይቻላል አስተሳስብ የተፈጠረበት እንደሆነ ይናገራሉ። በክልሉ የ30-40-30 ኢኒሼቲቭ በመተግበር ከሴፍቲኔት የተላቀቁና ኑሯቸውን ያሻሻሉ አረሶ አደሮች ለዚህ ምስክር ናቸው። በስልጤ ዞን ውልባረግ ወረዳ ቶዴ ጠመዳ ነዋሪዎች አቶ ሀምዛ አሊዬ እና ባለቤታቸው አናጃ ኢሳ በሴፍትኔት ታቅፈው ሲረዱ የቆዩ ሲሆን በ30-40-30 ጓሯቸውን በቡና በማልማታቸው ዛሬ ገቢም፣ ምግብም ችለዋል። በ500 የቡና ችግኝ ድጋፍ ጀምረው በየዓመቱ እያሳደጉ ዛሬ ላይ ቡናቸውን ለቅመው በመሸጥ ገቢ ማመንጨትና ነሯቸውን መደጎም ችለዋል። ጓሯቸውን በማልማታቸውም ከሴፍትኔት መላቀቅ ብቻ ሳይሆን ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ያላቸው ማህበራዊ ህይወት እንዲሻሻል ስለማድረጉም ገልጽው፤ በቀጣይነትም ሌሎች ፍራፍሬዎችን ለማልማት ተዘጋጅተዋል። በውልባረግ ወረዳ ቢላዋንጃ ባቢሶ ቀበሌ ነዋሪው አቶ ኢክማላ መሀመድ እና ልጃቸው መካ ኢክማላ ደግሞ አካባቢውን ያልተለመደ የሙዝ መንደር በማድረግ ኑሯቸውን እንዳሻሻሉ ይናገራሉ። የ30-40-30 ንቅናቄ ሲጀመር በአካባቢው "ሙዝ አይለማም" በሚል የተሳሳተ እሳቤ ቅር እያላቸው ችግኞችን ወስደው የተከሉ ቢኖሩም በርካቶች በእምቢታ ጸንተው እንደነበር አስታውሰዋል። በሂደት ውጤቱ ሲታይ ግን የልማቱ ተሳታፊዎች በዝተው በውጤትና የስኬት መንገድ ላይ መቀጠላቸውን ተናግረዋል። ከሳዑዲ አረቢያ የ10 ዓመታት የስደት ቆይታ በኋላ የተመለሰው ልጃቸው መካ ኢክማላ የስደት አስከፊነትን በማንሳት ተፈጥሮ በሰጠችን ጸጋ ሳንጠቀም በመቆየታችን ይቆጨናለ ይላል። የ30-40-30 ንቅናቄም ወጣቶች ከስደት ይልቅ በጓሯቸው ሰርተው መለወጥ እንደሚችሉ ዐይን የገለጠ እና የአስተሳሰብ ለውጥም ያመጣ ስለመሆኑ ይናገራል። በሀድያ ዞን ሻሸጎ ወረዳ ዶዕሻ ጎላ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ይቴቦ ሽጉጤ፤ ኢኒሼቲቩን በመጠቀም ከሌሎች አርሶ አደሮች ጋር የሙዝ መንደር መስርተዋል። የክላስተር ሙዝ መንደራቸው በሶስት ዓመታት ውስጥ የቤተሰባቸው ኑሮ እንዲሻሻል ያደረገና በቀላሉ ጸጋን ተጠቅሞ መለወጥ እንደሚቻል ያረጋገጠ ስለመሆኑም ገልጸዋል። የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ ሙበራ ከማል፤ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚል ንቅናቄ በርካቶች በተለይም በፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ልማት ተሳትፈው ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል። በአካባቢ ያሉ ጸጋዎችን በመለየት የቡና፣ የሙዝና የአቮካዶ ክላስተር በማልማት ከፍጆታ አልፈው ለማዕከላዊ ገበያ እየቀረቡ ስለመሆኑም ይናገራሉ። በሀድያ ዞን የሻሸጎ ወረዳ ግብርና ፅህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር ወንዱ መለሰ፤ የ30-40-30 የፍራፍሬ ልማት ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱን ተናግረዋል። በሙዝ ክላስተር አርሶ አደሮች በትብብር ሰርተው እንዲለወጡ ያስቻለ መሆኑን ገልጸው፤ አርሶ አደሮችም ውጤቱን በማየት ወደተጨማሪ ልማት እየገቡ ይገኛሉ ብለዋል። የ30-40-30 ኢኒሼቲቩ 'ጥረት ካለ ስኬት እንዳለ ማሳየት የተቻለበት እና የግብርናው ዘርፍ አንኳር መሰሶዎችን ዕውን ለማድረግ ተስፋ ሰጭ ውጤት የተገኘበት መሆኑን አቶ ዑስማን ይገልጻሉ። በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የግብዓት ፍላጎት በመጨመሩ ተደራሽነቱን ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል። የ30 40 30 የፍራፍሬ ልማት ፕሮጀክት አንድ አርሶ ወይም አርብቶ አደር በመጀመሪያ ዓመት 30፣ በሁለተኛው ዓመት 40 እና በሶስተኛ ዓመት 30 የፍራፍሬ ችግኞችን በመትከል ተጠቃሚ የሚሆንበት መርሃ ግብር መሆኑ ይታወቃል።
መጣጥፍ
የሀመሯ እናት- የደስታ እንባ
Sep 11, 2025 214
የሀመሯ እናት- የደስታ እንባ በጣፋጩ ሰለሞን (ከጂንካ) በደቡብ ኦሞ ዞን የሚገኘው ሐመር ወረዳ የሐመር ብሔረሰብ ዘመን በተሻገሩ ባህላዊ ሥርዓቶች ይታወቃል። በዚህ አካባቢ ከሚዘወተሩትና በብዛት ከሚታወቁት ባህላዊ ሥርዓቶች መካከል “ኢቫንጋዲ እና ኡኩሊ” የተባሉ ባህላዊ ጨዋታዎች ይጠቀሳሉ። “ኡኩሊ”በሐመሮች ዘንድ በስፋት የሚታወቅ ባህላዊ ጨዋታ ሲሆን ለአቅመ አዳም የደረሰና ከብት ለመዝለል ዝግጁ የሆነ የሐመር ወጣት የሚጠራበት የማዕረግ ስም ነው፡፡ “ኡኩሊ” ከብት በሚዘለልበት ዕለት ሥርዓቱ በሚፈጸምበት ሥፍራ ላይ በቅርብም ይሁን በሩቅ ያሉ የወጣቱ ዘመዶች ተጠርተው የሚከናወን ባህላዊ ሥርዓት መሆኑ ይታወቃል። “ኢቫንጋዲ” ደግሞ በሐመሮች ዘንድ በስፋት የሚታወቅ ባህላዊ ጭፈራ ሲሆን ትርጉሙም “ኢቫን” ማለት “ ማታ” ሲሆን “ጋዲ” ማለት ደግሞ “ጭፈራ” ማለት መሆኑ ይነገራል። ኢቫንጋዲ በአዝመራና በደስታ ወቅት በሥራ የደከመን አእምሮና አካል ለማዝናናት ሲባል የሚከናወንና የሀመር ወጣቶች በጉጉት የሚጠብቁት ባህላዊ ጭፈራ ነው። በዚህ ባህላዊ ጨዋታ ላይ የሐመር ወጣት ወንዶችና ልጃገረዶች አምረውና ተውበው በጨረቃ ብርሃን ይጨፍራሉ። የኢቫንጋዲ ጭፈራ በሶስት ቀን አንድ ጊዜ በሐመር መንደሮች በምሽት ከጨረቃ ድምቀት ጋር አብሮ ይደምቃል። “በጨረቃ ብርሃን አየኋት በማታ ኢቫንጋዲው ቦታ” የተባለላቸው የሃመር ውብ ልጃገረዶችም ከጨረቃ ብርሃን ጋር ደምቀው የሚታዩበት ዕለት ይሆናል። በወጣትነታቸው በዚሁ ባህላዊ ሥርዓት ያለፉት የሀመሯ እናት- ወይዘሮ ባሎ ኡርጎ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ እናት ናቸው። በሐመር ወረዳ ዲመካ ከተማ የሚኖሩት ወይዘሮ ባሎ፤ በደሳሳ ጎጇቸው ሲያገኙ በልተው ሲያጡ ደግሞ ኩርምት ብለው ያሳለፉባቸው ጊዜያት እንዳሉ ያስታውሳሉ። በደሳሳ ጎጆ እየኖሩ ዝናብ ሲመጣ የጎርፍ፣ ብርድና ዶፉ ስጋት ላይ ጥሏቸው እንደኖሩ ያነሳሉ፤ በበጋ ወራት ደግሞ የሚነፍሰው ነፋስና ሀሩሩ ጸሃይ ይፈትናቸው እንደነበር ይናገራሉ። ከእለታት አንድ ቀን ወጣቶችና ጎልማሶች ጭምር ሰብሰብ ብለው መጥተው “ቤትዎን በነፃ ልናድስልዎት ነው ሲሉኝ አላመንኳቸውም ይላሉ። የእውነታችሁን ነው አልኳቸው? አዎን ቤትዎን አፍርሰን ልንሰራልዎት ነው” ብለው አረጋገጡልኝ በማለት ሁኔታውን በደስታ እንባ ታጅበው ያስታውሳሉ። በተባለው መሰረትም በክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የቤታቸው እድሳት ተጀምሯል። የኢዜአ ሪፖርተር በስፍራው ተገኝቶ ወይዘሮ ባሎን ባነጋገራቸው ወቅት “ሰው በሚያስፈልገኝ ጊዜ ሰዎች ሁነው የተገኙ ወገኖቼ ችግሬን ለመፍታት በአካል ተገኝተዋል፤ በጣም ደስ ብሎኛል፤ የመኖርን ተስፋ እንድሰንቅ አድርገውኛል በማለት ደስታቸውን በእንባቸው ጭምር ታጅበው ገልጸዋል። የሀመሯ እናት ቤታቸው በፍጥነት ታድሶ የሚረከቡ፣ በቀጣይም አስፈላጊው እገዛና ድጋፍ የሚደረግላቸው መሆኑን የቤቱን እድሳት ያስጀመሩት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኤካል ነትር አረጋግጠዋል። እንደ ወይዘሮ ባሎ፤ ያሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖችን የማገዝና የመደገፍ ሃላፊነት አለብን ያሉት ሃላፊው፤ የመረዳዳትና የመተጋገዝ ባህል ጎልቶ እንዲቀጥል ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል። የቢሮው የማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ለወገኖቻቸውያላቸውን አለኝታነት በተግባር በማሳየታቸውም አመስግነዋል። የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ፤ የዘንድሮ የክረምት በጎ ፈቃድ ተቋማት፣ግለሰቦች፣ወጣቶችና አዛውንቶች ሳይቀር የተሳተፉበት እና የበርካቶችን ችግር መፍታት የተቻለበት መሆኑን ተናግረዋል። የክልሉ መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች የወይዘሮ ባሎን ቤት ለማደስ በመምጣታቸው አመስግነው፤ ለሌሎች ተቋማትም አርአያ የሚሆን የመልካምነት ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል። በዞኑ በተያዘው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ቤቶችን ጨምሮ የዞኑን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣይም በዞኑ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖችን የመደገፍና ሰው ተኮር የልማት ስራዎችን በስፋት የማከናወን ተግባር በተጠናከረ መለኩ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።
የአባይ የቁጭትና የወቀሳ ጊዜ አበቃ!
Sep 9, 2025 262
የአባይ የቁጭትና የወቀሳ ጊዜ አበቃ! (በቀደሰ ተክሌ - ከሚዛን አማን) አኩርፎ ከቤት ቢወጣ ለመመለስ ሸምጋይ አጥቶ በሰው ሀገር ተንከራታች ልጓም አልባ ሆኖ የኖረው አባይ ከኢትዮጵያ አፈር፣ ማእድናትና ሌሎችንም ሃብቶች ጠርጎ በመውሰድ ለዘመናት ሲፈስ ኖሯል። ከኢትዮጵያ እምብርት በመነሳት አገራትን አቆራርጦ የሚያልፈው፣ የዓለማችን ታላቁ ወንዝ አባይ በጋና ክረምት ሳይል በመፍሰስ የብዙዎች የህይወት ምንጭ ሆኖ አሁንም ፍሰቱን ቀጥሏል። የኢትዮጵያ ልጅ የኢትዮጵያውያን አብሮነት ምሰሦ - የወንዞች ንጉሥ ታላቁ አባይ! አሁን ልጓም ተበጅቶለት በፍትሃዊነት ሁሉንም ለመጥቀም ተዘጋጅቶ የማይነጥፈው ጅረት ዘላለማዊ የመፍሰስ ሂደቱ እንደቀጠለ ነው። ኢትዮጵያውያን አመሉ ለከፋ፤ እሺ በጀ አልል ብሎ በእንቢታ ልቡን ባጸና ልጅ አብዝተው ያዝናሉ። የሀዘናቸው ጥግም በሕይወት ሳለ የሞተ ያክል በእንጉርጉሮ ሙሾ ያወርዱለታል። አባይም ይህ እጣ ፈንታ ገጥሞት "አመፀኛ ውሃ" ተብሎ በወቀሳ ተዚሞለታል። ለኢትዮጵያ ለዘመናት ሳይታዘዝ የኖረው አባይ የአዛዥ እጦት እንጂ በእምቢታ አልነበረም። በዚህ ውጣ በዚህ ግባ ባይ አጥቶ ቦዘነ። በዚህም ተራራውን እየሸሸ ቁልቁል እየተምዘገዘገ፣ ሲሻ እየጬሰ ቁልቁል ወርዶ ከዐለት ጋር እየተጋጨ መዳረሻውንና ማደሪያውን ይናፍቃል። በዚህም ቤቱን ረሳ። ወላጆቹን ትቶ ባእዳንን ብቻ ጦረ፣ ፊቱን በፍጹም ወደ ኋላ እንዳይመልስ እንደ ሎጥና ቤተሰቦቹ ተገዘተ። አባይ የባእዳንን ግዝት ከተፈጥሮ ጋር አስተባብሮ በመጠበቅ ሀገሩን ለቆ ከመውጣት ውጭ ቢደክመው የማረፍ፥ ቢመቸው የማልማት መብት ሊያገኝ አልቻለም። ይህ በኢትዮጵያ ልብ ውስጥ ቁጭት ፈጥሮ ከትውልድ ወደ ትውልድ ተሸጋገረ። ኢትዮጵያ ለታላቅ ልጇ ማረፊያ ሠርታ ጎጆ ልታወጣ ቋመጠች። ፈተናው በዛ የፖለቲካ መልክ ይዞም አቅሟን ተፈታተነ። ስደተኛው አባይን ስላሳረፉት እርሱም ስለመገባቸው የግል ሀብት አድርገው የቆጠሩት የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ጫና ፈጥረው የሀሳብ ጽንሱን ከታሪካዊና ቀጣናዊ ጠላቶች ጋር እየተባበሩ አቋረጡት። አባይን ገድቦ የመጠቀም የዘመናቱ የኢትዮጵያ መሪዎች ጉጉቱ ህልም ሆኖ ሐዘኑ ከነ ቁጭቱ ቀጠለ። እንጉርጉሮ ወቀሳ በበዛባቸው ስንኞች ቋጥሮ መዜሙን ቀጠለ። የኢትዮጵያ ዐይኖች ጀግንነት በአባይ ሲሸበብ ማየት አንገሸገሻቸው። የበይ ተመልካች መሆንና ከጓሯቸው ሞፈር አስቆርጦ መራብ አመማቸው። ኢትዮጵያዊነት ከዘመን ዘመን የማይነጥፍ፥ ልብ ለልብ የተሳሰረ ትውልድ ማንነት ማሳያ ሐውልት ነው። ትላንት ዛሬን እያቃና ነገን የሚገነባበት ሀገራዊ ራእይ ያላቸው መሪዎች ትስስር በአባይ ሲንጸባረቅ ይስተዋላል። ከ1929 እስከ 1950ቹ ያለው የአባይ ፖለቲካ ጉዳይ በብዙ ድርድሮችና ስምምነቶች ታጀበ። የጫና ፈተናው አየለና ገንብቶ የመጠቀም ጥንስስን ለቀጣይ ትውልድ እንዲሸጋገር አደረገ። ያኔ ነገን የተመለከተ ዐይን "ልጆቻችን ይሠሩታል" የሚል ቃል ሰጠና ኢትዮጵያ ልጆቿን በተስፋ ተጠባበቀች። ዘመን አለፈ ትውልድ ተተካ ልጆችም ተወለዱና የተስፋ ቀጠሮ ደረሰ ወርሃ መጋቢት 2003 ዓ/ም። በዚህ ቀን የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዜና በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ተበሰረ። ኢትዮጵያ እልል አለች፤ "እንጉርጉሮ ይብቃ" ተባለ በዜማ በዝማሬ አባይ ተሞገሰ። የአባይ የወቀሳ ጊዜ ተጠናቀቀ- የቁጭት ጊዜ አብቅቶ የስኬትና ማንሰራራት ጊዜ መጣ። ለግድቡ የ14 ዓመታት የግንባታ ሂደት ከአንድ ብር ጀምሮ አስተዋጽኦ ያደረጉ፣ በእውቀትና በጉልበት የተጉ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ የደስታ ቀንም እውን ሆነ። በጉባ ሰማይ ስር አዲስ ክስተት፣ አዲስ ምዕራፍ፣ አዲስ ስም ተተከለ። አባይ ከሚል ነጠላ ስም ወደ "ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ" ተሻገረ። የድግቡ ሃይቅም "ንጋት" የሚል መጠሪያ ወጥቶለት ለኢትዮጵያ የንጋት ጸሃይ እየወጣች መሆኑን ለሁላችንም ብስራት ሆነ። "እንኳንም ጀመርን፣ እንኳንም በር ተከተፈተልን" እንጂ ያሉት ልበ ኩሩና ክንደ ብርቱ ኢትዮጵያውያን ጫናዎችን በአይበገሬነት መንፈስ ድባቅ እየመቱ ጉዞ ወደ ፊት ቀጠሉ። ወደ ተግባር ገብተው "ሕይወታችንንም ቢሆን ለአባይ አንሰስትም" አሉ። ግድቡን እንሠራለን ብለው የጀመሩት ኢትዮጵያውያን ናቸው። ከነ አባባላቸው "የነብር ጭራን አይያዙ፥ ከያዙም አይለቁ" ነውና ሥራውን ስለጀመሩት የአባይ ግድብ ጉዳይ ቀዳሚ አጀንዳቸውና ደም ስራቸው ሆኖ ቀጠለ። እንደ ዐይን ብሌናቸው ያዩ፣ ይጠብቁት እና ይሳሱለት ጀመር። የአልሸነፍ ባይነት ወኔን ከጀግንነት ጋር አጣምረው የያዙ ኢትዮጵያውያን የጠላት ነቀፋና ፕሮጀክቱን የማኮላሸት ሴራን እንደ ድር አብረው ተከላከሉ። የ"እንችላለን" ትርክትን በተግባር ነፍስ እየዘሩ እጅ ለእጅ ተያይዘው ጉዟቸውን ከሕዳሴ ጋር ቀጠሉ። በጉባ ምድር ላይ የአንድነታቸውን ቋሚ ሐውልትም ተከሉ። ኢትዮጵያውን ከአድዋ ጦርነት ወዲህ የአንድ ቃል ተናጋሪ የአንድ ልብ መካሪ ሆነው የተከሰቱበትና በአንድ የተመሙበት ትልቁ የታሪክ አሻራ አባይ በሕዳሴ ሆነ። የተማሪ ቦርሳ፣ የእናቶች መቀነት፣ የአረጋውያን የጡረታ ደብተር፣ የአርሶ አደሮች ጎተራ፣ የአርብቶ አደሮች በረት፣ የመንግሥት ሠራተኛው ፔሮል፣ የነጋዴው ኪስ እና የዳያስፖራ ዋሌት ሳይቀር በአባይ ላይ አሻራ አለው። የሕዳሴው ግድብ ውዝግብ ኢትዮጵያ ራሷን በዓለም መድረክ ከፍ አድርጋ ያሳየችበት ትልቅ አጋጣሚ ነው። ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የደረሰውን ውሃ አይሞላ ክስ በብስለት መክታ እውነትን ለዓለም ሕዝብ አስገንዝባለች። በዚህም የዓለም አቀፍ ሕግ አዋቂነቷንና አክባሪነቷን፣ የጋራ ተጠቃሚነት ፍላጎቷንና ለሰላም ያላትን አቋም ቁልጭ አድርጋ አረጋግጣለች። ድርድሮችን በድል የሚቋጩ ልጆቿ ደግሞ ኢትዮጵያውያን በሁሉም ዘርፍ ብቁ የመሆናቸው ነጸብራቅ ሆነው ተከሰቱ። ዘርፈ ብዙ የዲፕሎማሲ ሥራው ከማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ እስከ ጉምቱ አምባሳደሮች በተናበበ መልኩ ብቅ ብሎ አጀብ አስብሏል። ድርድሩ በመስመሩ፣ የዲፕሎማሲ ሥራው በሜዳው ፖለቲካ እና ሌላው የሀገር ጉዳይ በየፈርጁ እየቀጠለ የሕዳሴው ግድብም ለደቂቃ እንኳ ሳይቆም ይሠራ ነበር። ይህ የመብቃት፣ የማደግ፣ በጥበብ የመበልጸግ፣ በሀሳብና አቅም የመብሰል ሀገራዊ ማሳያ ነው። ለብዙ የአፍሪካ ሀገራት ተሞክሮ የሚሆን አሻጋሪ የተግባር ልምምድ መሆኑም አያሻማም። ለዚህ ግድብ ስኬት ደግሞ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን መሪ ሆነው ብቅ ያሉትን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶር) ማንሳት ግድ ይላል። አዛዥ አጥቶ ቦዝኖ የነበረውን ጊዜ ለመካስ ና ብሎ የሚጣራውን አዛዥ "አቤት" ብሎ ትዕዛዝ ለመቀበል አባይ አላቅማማም። አሁን በሙሉ ልቡ ወደ ጫጉላ ቤቱ ገብቷል። የመስከረሙ ሙሽራ የቤት ሀብት ዘርፎ ለባዕድ አሳልፎ ከመስጠት ተቆጠበ። የበረሃው ሀሩር ሳይመታው በሀገሩ እፎይ ብሎ ብርሃንም ምግብም፣ ሀብትም ክብርም መሆን ጀመረና የኢትዮጵያን ክብር ዳግም ከፍ አደረገ። ሰው ተፈጥሮን ሲያዝ እሺ ይላል፥ ዝም ካሉት በራሱ ፍላጎት ይሔዳል። ይህ ተፈጥሯዊ የአባይ ግብር ተቀይሮ በሰዎች መታዘዝ ጀመረ። አፈርና ውሃ ማስቀረት ብቻ ሳይሆን ግዙፍ የብርሃን ምንጭ ሆኖ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ብርሃን መሆን ጀምሯል። በሕዳሴ ግድብ ታዞ ፊቱን ወደ ልማት ሥራ ያዞረው አባይ ያለፈውን ለመካስ ብዙ ጸጋዎችን ይዞ ተከሰቷል። የዓሳ ምርት፣ ግዙፍ ሀይቅ ከደሴቶች ጋር አንጣሎ በመያዝ የኢኮ ቱሪዝም ዘርፍ መሪ ሊሆን ቆርጦ ተነስቷል። አብሮ የመልማት የኢትዮጵያ ጽኑ ፍላጎት በወለደው እሳቤ ህዳሴ ግድብ የጎረቤት አገራት ሃብት ጭምር በመሆን ለማገልገል ተዘጋጅቷል። አባይ ሆይ ስምህ ከወቀሳ ወጥቶ በሙገሳ ስለተተካ እንኳን ደስ አለህ! እናቴ ሆይ የተፈታው መቀነትሽ ሀይል ስላመነጨ ለልጆችሽ ሀብት አውርሰሻልና ደስ ይበልሽ። ሀገሬ የብርሃን ዘመን ስለፈነጠቀብሽ እንኳን ደስ አለሽ! ሰላምና ፍቅር ለሁላችን ይሁን።