የከተማዋን ሰላም በማፅናት ለልማት በመትጋት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተዘጋጅተናል - ኢዜአ አማርኛ
የከተማዋን ሰላም በማፅናት ለልማት በመትጋት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተዘጋጅተናል

ባህርዳር፤ መስከረም 2/2018 (ኢዜአ) የከተማዋን ሰላም በማፅናት ለልማት በመትጋት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተዘጋጅተናል ሲሉ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ገለጹ።
በብልፅግና ፓርቲ የባህር ዳር ከተማ አመራሮች በፓርቲው ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ የውይይት መድረክ እያካሄዱ ነው።
በመድረኩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው፤ በለውጡ ዓመታት በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የፖለቲካው መስክ የላቁ ስኬቶች መመዝገባቸውን አንስተዋል።
በመሆኑም እነዚህን ውጤቶች ከፍ ባለ መልኩ ለማስቀጠል በተለይም የአመራር አባላቱ የሰላምና የልማት አርአያ በመሆን ለላቀ ውጤት መትጋት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።
የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆን ከሁላችንም ይጠበቃል ሲሉም አንስተዋል።
የአመራሩን የማስፈፀም አቅም እና የህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ታክሎበት ለተጀመረው የብልጽግና ጉዞ እና ለታለመው ግብ መሳካት በቅንጅት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
በዚህ ረገድ የከተማዋን ሰላም በማፅናት ለልማት በመትጋት የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራም ተናግረዋል።
የፓርቲው አመራሮች የውይይት መድረክ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል።