በአፋር ክልል የዲጂታል አሰራርን በመተግበር አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቷል - ኢዜአ አማርኛ
በአፋር ክልል የዲጂታል አሰራርን በመተግበር አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቷል

ሰመራ፤ጳጉሜን 5/2017(ኢዜአ)፦በአፋር ክልል የዲጂታል አሰራርን በመተግበር የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ትኩረት መሰጠቱ ተገለጸ።
"ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ" በሚል መሪ ሐሳብ ጳጉሜን 5 የነገው ቀን በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል።
በዕለቱ የተገኙት በብልፅግና ፓርቲ የአፋር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ መሐመድ አህመድ የዲጂታል አሰራርን በመተግበር የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንሰራለን ብለዋል።
አዲሱን ዓመት ስንቀበልም በለውጥ አመታት የተከናወኑ የልማት ስራዎችን በተሻለ ፍጥነትና ጥራት የምናስቀጥልበትና የዲጂታል አሰራርን እውን የምናደርግበት ነው ብለዋል።
በዲጂታላይዜሽን ዘርፍ የተጀመሩ የኢትዮ-ኮደርስና ዲጂታል መታወቂያ ትግበራን በቴክኖሎጂ በማገዝ ተግባራዊ እናደርጋለን ብለዋል።
በክልሉ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለማስጀመር የተጀመሩ ስራዎችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
የክልሉ የሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ መሐመድ አህመድ በበኩላቸው ባለፉት ሰባት የለውጥ ዓመታት የተመዘገቡ የልማት ውጤቶችን እናጠናክራለን ብለዋል።
በዚህም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ዲጂታላይዜሽን ማስፋፋት ላይ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በዕለቱ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና የሠመራ ከተማ ነዋሪዎች በተገኙበት የፓናል ውይይት ተካሄዷል።