ቀጥታ፡

በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምረቃ ላይ የተገኙት የጂቡቲ እና የሶማሊያ ፕሬዝዳንቶች ወደ ሀገራቸው ተሸኙ

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2017(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ እና በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የምረቃ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የጂቡቲ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌህ እና የሶማሊያ ፌዴራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ በኢትዮጵያ የነበራቸውን ስኬታማ ቆይታ አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተሸኝተዋል።


 

ለፕሬዝዳንቶቹ በቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የክብር ሳሎን በመገኘት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም