ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መቻል፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ሃዋሳ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ውሎ ሶስት ጨዋታዎች ተደርገዋል።

መቻል ሸገር ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል። ትዕግስት ወርቁ፣ ስንታየሁ ኤርኮ እና ቤተልሄም መንተሎ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

በሌላኛው መርሃ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ልደታ ክፍለ ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል።

ዳግማዊት አለማየሁ ሁለት ግቦችን ስታስቆጥር ንግስት ኃይሉ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።

አስራት አለሙ ለልደታ ክፍለ ከተማ ብቸኛዋን ጎል አስቆጥራለች።

ሃዋሳ ከተማ በታደለች አብርሃም ጎል ባህር ዳር ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ጨዋታዎቹን ተከትሎ የሶስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም