የአፍሪካ ህብረት እና የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን በአህጉራዊ ትስስር ያላቸውን አጋርነት ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2017(ኢዜአ)፦የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) በአህጉራዊ ትስስር አጀንዳ ያላቸውን ትብብር የበለጠ ለማላቅ እንደሚሰሩ አስታወቁ።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በዓለም የንግድ ድርጅት(ጄኔቫ) የአፍሪካ ህብረት ቋሚ መልዕክተኛ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (ኢሴኤ) ዋና ፀሐፊ ክላቫር ጋቴቴ ጋር ተወያይተዋል።


 

ሁለቱ ወገኖች አፍሪካ በዓለም መድረክ አንድ የጋራ ድምጽ እንዲኖራት ማድረግ ያለውን ወሳኝ ጠቃሜታ አጽንኦት ሰጥተው መክረውበታል።

የአፍሪካ ህብረት እና ኢሲኤ በንግድ፣ቀጣናዊ ትስስር እና የአፍሪካ የአዕምራዊ ንብረትን የበለጠ አጀንዳ ማራመድ ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ኢዜአ ከኢሲኤ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።


 

ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በዓለም የንግድ ድርጅት(ጄኔቫ) የአፍሪካ ህብረት ቋሚ መልዕክተኛ ሆነው በሐምሌ ወር 2017 ዓ.ም መሾማቸው የሚታወስ ነው።

የአፍሪካ ህብረት እና ኢሲኤ ትብብራቸውን እ.አ.አ በ1960ዎቹ መግቢያ ላይ መጀመራቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም