ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ለቀጣናው ጸጥታ እና መረጋጋት ብሎም ልማትን ለማረጋገጥ ያላቸውን ጽኑ አቋም አረጋገጡ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ለቀጣናው ጸጥታ እና መረጋጋት ብሎም ልማትን ለማረጋገጥ ያላቸውን ጽኑ አቋም አረጋገጡ

አዲስ አበበ፤ጳጉሜን 5/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ለቀጣናው ጸጥታ እና መረጋጋት ብሎም ልማትን ለማረጋገጥ ያላቸውን ጽኑ አቋም አረጋግጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሀሰን ሼህ መሃሙድን ዛሬ ጠዋት በጸህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ ከፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ጋር የጋራ ፍላጎት ባለን ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል ብለዋል።
በዚህም በቀጠናችን ፀጥታ እና መረጋጋት ብሎም ልማትን ለማረጋገጥ ያለንን ፅኑ አቋም በድጋሜ አረጋግጠናል ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት።