ቀጥታ፡

20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነገ ይጀመራል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 2/2018 (ኢዜአ)፦ በጃፓን ቶኪዮ የሚካሄደው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነገ ጅማሮውን ያገኛል።

በሻምፒዮናው ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ 200 ገደማ ሀገራት የተወጣጡ ከ2000 በላይ አትሌቶች እንደሚሳተፉ የዓለም አትሌቲክስ መረጃ ያመለክታል። 

አትሌቶች በ49 የውድድር አይነቶች ላይ ይሳተፋሉ።

በሻምፒዮናው መክፈቻ ቀን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚጠበቁባቸው የፍጻሜ ውድድሮች ይካሄዳሉ።

ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 ላይ በሚደረገው የሴቶች የ10 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር ጉዳፍ ጸጋይ፣ ፅጌ ገብረሰላማ፣ ፎይተን ተስፋይ እና እጅጋየሁ ታዬ ይወዳደራሉ።

ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ላይ በሚደረገው የሴቶች ማራቶን ፍጻሜ አትሌት ትዕግስት አሰፋ፣ ሱቱሜ አሰፋ እና ትዕግስት ከተማ ይሳተፋሉ።

የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እስከ መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም