ቀጥታ፡

በክልሉ ያሉ እምቅ ሃብቶችን በማልማትና የጋራ እሴቶችን በማጎልበት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ጥረት ይደረጋል-   ርዕሰ መስተዳድር  ጥላሁን ከበደ 

ሀዋሳ ፤ መስከረም 2/2018 (ኢዜአ)፦ በክልሉ ያሉ እምቅ ሃብቶችን በማልማትና የጋራ እሴቶችን በማጎልበት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ጥረት ይደረጋል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፤ በክልሉ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በማሳካት በቀጣይም ለተሻለ ስኬት ለመብቃት የተደረጉ ዝግጅቶችን በማስመልከት ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በማብራሪያቸውም በክልሉ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡ መሆኑን አንስተው በቀጣይ ለላቀ ውጤት ተዘጋጅተናል ብለዋል። 

በየደረጃው ያለው አመራር በቁርጠኝነት ለውጤት ለመብቃት መስራት እንዳለበት አስገንዝበው የህዝቡ የልማት ተሳትፎም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።

በመሆኑም በክልሉ ያሉ እምቅ ሃብቶችን በማልማትና የጋራ እሴቶችን በማጎልበት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ጥረት ይደረጋል ሲሉ ርእሰ መስተዳድሩ አረጋግጠዋል።

በክልሉ የገቢ አቅምን ማሳደግ፣ ከተሞችን ማዘመንና ለነዋሪዎች ምቹ ማድረግ የስራ እድል ፈጠራ እና ኢንቨስትመንትን የማስፋፋት ስራ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን አንስተዋል።

በክልሉ ያለውን እምቅ ሃብት በማልማት፤ የቡና እና የአትክልትና ፍራፍሬ ልማትን በማጠናከር እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጅነት የመውጣት ጥረትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የቱሪዝም መዳረሻዎችንና የማእድን ሃብቶችን በማልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ የሚታዩ ማነቆዎችን በመፍታት በክልሉ ሁለንተናዊ ልማትን ለማሳካት ተዘጋጅተናል ሲሉም አረጋግጠዋል።

በ2018 በትጋት፣ ጽናትና ብቃት በመስራት የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ ለማሳካት በሚደረገው ጥረት ክልሉ ሁነኛ አቅም ሆኖ ለመገኘት የሚያስችለው ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም