በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምረቃ ላይ የተገኙት ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ወደ ሀገራቸው ተሸኙ - ኢዜአ አማርኛ
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምረቃ ላይ የተገኙት ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ወደ ሀገራቸው ተሸኙ

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2017(ኢዜአ)፦ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የምረቃ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ሚያርዲት በኢትዮጵያ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተሸኝተዋል።
የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ(ዶ/ር) እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኝት ለፕሬዝዳንቱ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል ።