ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በአፋር ክልል በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ችግር ለገጠማቸው ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ እየተደረገ ነው
Oct 14, 2026 79
ሰመራ ጥቅምት 4/2019 (ኢዜአ) ፦በአፋር ክልል በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ችግር ለገጠማቸው ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ እየተደረገ ነው። ከአዳማ የእህል ማከማቻ ማዕከላዊ መጋዘን በመጀመሪያው ዙር የተጫነው ሰብዓዊ ድጋፍ በክልሉ የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ወገኖች በመከፋፈል ላይ ይገኛል። በዛሬው ዕለትም በቢዱ ወረዳ ጊሪፎ ቀበሌ ለበርካታ ወገኖች ተደራሽ የተደረገ ሲሆን ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖችም ምስጋና አቅርበዋል። በተፈጥሮ መዛባት ምክንያት በአካባቢው በተከሰተው ድርቅ ለችግር መጋለጣቸውን የገለጹት ነዋሪዎቹ ድጋፍ ባስፈለገን ጊዜ ደርሶልናል ብለዋል። ድጋፍ ከተደረገላቸው መካከል ወይዘሮ መይረም አብዱ፤ የተደረገልን ድጋፍ ልጆቻችን እና አጠቃላይ ቤተሰቡ ላጋጠመን የምግብ እጥረት መፍትሄ የሚሆነን ነው ብለዋል። መንግስት በአካባቢው ያጋጠመውን የተፈጥሮ አደጋ በመረዳት ፈጣን ምላሽና ድጋፍ በማድረጉ አመስግነዋል። ሌላኛዋ የድጋፉ ተጠቃሚ ወይዘሮ አሲያ መሐመድ፤ በአካባቢው ያጋጠመውን ችግር መንግስት አውቆ አስፈላጊውን ድጋፍ ስላደረገልን እናመሰግናለን ብለዋል። በመንግስት ድጋፍ ባይደረግላቸው እርሳቸውና ቤተሰባቸው የከፋ ችግር ላይ ይወድቁ እንደነበር ተናግረዋል። በመሆኑም እርሳቸውን ጨምሮ ሌሎችም የአካባቢው ነዋሪዎች የተደረገላቸው ድጋፍ ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን ገልጸዋል። የአፋር ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የክምችት ጥራትና ቁጥጥሮ ቡድን መሪ አቶ መሐመድ አብደላ፤ በክልሉ የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ እየተዳረሰ መሆኑን ተናግረዋል። ክልሉ በራሱ አቅም ድጋፍ ለሚሹ አካባቢዎች የሰብአዊ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱንና አሁንም በማድረግ ላይ መሆኑን አንስተው ከኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር የተላከውንም የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚሹ ወገኖች እየደረሰ መሆኑን ገልጸዋል። የቢዱ ወረዳ የአርሻና ተፈጥሮ ሃብት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ የሱፍ መሐመድ፤ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በአካባቢው የተከሰተው ድርቅ ነዋሪዎችን ለችግር መዳረጉን ገልጸዋል። በመሆኑም መንግስት ያለውን ችግር በመረዳት የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽ ማድረጉ ወቅታዊና አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፤ በጠንካራ ወታደራዊ አቅምና ዲሲፕሊን የታነጸው የአፍሪካ የሰላም ዘብ!!
Oct 14, 2026 158
ኢትዮጵያ ለትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ እና ታላቅ ርዕይ የሚመጥን የመከላከያ ሰራዊት ገንብታለች። ይህ የሀገር መከታ ሰራዊት በታጠቃቸው ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ብቻ ሳይሆን በተላበሰው ወታደራዊ ዲሲፕሊን ለዓለም ምሳሌ የሆነ ድል አድራጊ ሰራዊት መሆኑን አስመስክሯል። በማድረግ አቅሙም ጠላቶች ከሩቅ የሚሸሹት ሆኗል። ኢትዮጵያ የአሸናፊዎች ምድር ናት። የአሸናፊነት ተምሳሌትም ጭምር። የኢትዮጵያ የአሸናፊ ምድርነት እና ምሳሌነት ሁነኛው ማሳያ ደግሞ የሀገር መከላከያ ሰራዊቷ ጀግንነት የሚቀዳ ነው። ሰራዊቱ የቅድመ አያቶቹና አያቶቹን የድል አድራጊነት መንፈስ ከነሙሉ ክብሩ በትውልድ ቅብብሎሽ የተረከበ ብቻ ሳይሆን ያስቀጠለ የድል ፋና ወጊ ሰራዊት ነው። ይህን የአሸናፊነት ስነልቦና ለተላበሰ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ግንባታ የመደመር መንግሥት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ በመስራቱ የተቋሙን የማድረግ አቅም በከፍተኛ ሁኔታ አሳድጓል። ለዚህም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዓለም አቀፍ ደረጃ የውጊያ መልክ ተቀይሮ ወደ አራተኛው ትውልድ ጦርነት በመሸጋገር በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በሰው አልባ አውሮፕላኖችና በሌሎች ወታደራዊ ቴክኖሎጂዎች አቅምን ማጉልበት ቁልፍ ጉዳይ ነው ያሉት። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገር ብቻ ሳይሆን የምስራቅ አፍሪካ፣ የአፍሪካና የዓለም የሰላምና የጀግንነት ተምሳሌትነቱን በተግባር ያረጋገጠ ክንደ ብርቱ ኃይል ነው። በጥብቅ ወታደራዊ ዲሲፕሊን የሚመራው ይህ ጀግና ሰራዊት የኢትዮጵያን ጥቅምና ሉዓላዊነት ለመፈታተን ለሚዳዳቸው ማናቸውም የውስጥ ተላላኪዎችና የውጭ ላኪዎች ፈጣንና የማያዳግም ምላሽ በመስጠት ሰላምን በብርቱ ክንዱ የማረጋገጥ አቅሙ አለው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ሰራዊቱ የኢትዮጵያ ወኔና የጀግንነት ምልክት መሆኑን የገለጹት የሰራዊቱ ሁለንተናዊ የማድረግ አቅም መጎልበትም ኢትዮጵያ ሉዓላዊ አንድነቷን አስከብራ የምትቀጥል የክንደ ብርቱዎች ምድር መሆኗን ያመላክታል። ይህ ጀግና የሀገር መከታ ሰራዊት ከጊዜ ወደ ጊዜ ሁለንተናዊ ዝግጁነቱን እያጠናከረ ይገኛል። ህዝባዊ ወገንተኝነቱንም በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ግዳጆች በተግባር አረጋግጧል፤ እያረጋገጠም ይገኛል። የኮሪያ፣ ኮንጎ፣ ሩዋንዳ፣ ኮትዲቯር፣ ቡሩንዲ፣ ላይቤሪያ እንዲሁም የሱዳን ዳርፉር ጋራና ተራራ፣ ሸለቆና ረባዳማ ስፍራ፣ ሜዳና ሸንተረር የጀግናው ሰራዊት ታሪክ ዘካሪ ሕያው ምስክሮች ናቸው። በአሁኑ ወቅትም በሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳንና ሱዳን ከቅድመ አያቶቹ የተረከበውን ለዓለም ሕዝብ ሰላምን የመቆም ታሪካዊ ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ ይገኛል። ኢትዮጵያን ከከፍታ ማማዋ ለማሳነስ የግብፅ፣ ሻዕቢያና ሌሎች ታሪካዊ ጠላቶችን ተልዕኮ ያነገቡ የውስጥ ባንዳዎች ከንቱ ቅዠት በማምከን የሀገር አለኝታነቱን በተግባር የሚያስመሰክር ሰራዊት ነው። ኢትዮጵያ ሉዓላዊ አንድነቷንና ሰላሟን አስጠብቃ ለመቀጠሏ ምስጢሩ ይህ የሀገር ኩራት እና የትውልድ ባለአዳራ ሰራዊት መሆኑም በትውልድ ቅብብሎሽ ተገነባው አኩሪ የታሪክ ገድሉ ሕያው ምስክር ነው። የአንዲት ሀገር ሁለንተናዊ የማድረግ አቅም ከሚለካባቸው መስፈርቶች መካከል አንዱ በመከላከያ ሰራዊት ግንባታዋ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይስማሙበታል። ለዚህም ነው የመከላከያ አጠቃላይ አቅሞች ኢትዮጵያ እያንሰራራች እና አስተማማኝ አቅም ላይ እንዳለች በግልጽ ያመላክታሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መግለጻቸው። ለጎረቤት ሀገራት ሰላም እና ደህንነት መረጋገጥ የህይወት መስዋዕትነት ጭምር በመክፈል ወገንተኝነቱንና ጀግንነቱን በተግባር ማስመስከሩ ዓለም የሚያውቀው ተምሳሌታዊ ክንደ ብርቱ ሰራዊት ነው። በሁለንተናዊ የማድረግ አቅሙ የሚታወቀው ይህ የሀገር መከታ ትላንት ላይ ተቸክለው ለቆሙ ማናቸውም ኋላ ቀር ስብስቦች ፍቱን መድኃኒት ነው። ከታሪካዊ ስህተቱና ከሀገር ከሃዲነቱ ያልተማረው ሕገወጡ የሕወሓት ጠባብ ቡድን ከዚህ ጀግና ሰራዊት ፊት መቆም ከቶውንም አይችልም። ይህም በተደጋጋሚ ታይቷል። የዚህ ጠባብና ተላላኪ ቡድን እኩይ ተግባር “ካልጠገቡ አይዘሉ ካልዘለሉ አይሰበሩ” ዓይነት ሆነና በሀገር መከላከያ ሰራዊት በተወሰደበት ፈጣን እርምጃ ድራሹ ጠፍቷል። የአኩሪ ገድል ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ዛሬም እንደ ትላንቱ በስልጣንና በዘረፋ ስካር ውስጥ ለተዘፈቀውና ሀገር ለማፍረስ ከውስጥ ባንዳዎችና ከውጭ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በመሆን ለተከተለው የጥፋት መንገድ ሁሉንም በሚያስተምር መልኩ ፈጣን ምላሽ የመስጠት ሀገር የማጽናት ተልዕኮውን በብቃት የመወጣት ተግባሩን በጀግንነት ቀጥሏል። ዛሬም ሆነ ወደፊት የኢትዮጵያ ብቸኛ መሻት ልማትን ማፋጠንና የቀጣናውን ሀገራት በኢኮኖሚ በማስተሳሰር የጋራ ብልፅግናን ማረጋገጥ ነው። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምና ሉዓላዊነት ላይ ለሚቃጡ ማናቸውም የውስጥና የውጭ ትንኮሳዎች ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚችል የሰላምና ደኅንነት ተቋም መገንባቱም መከላከያ ሰራዊት ሁነኛ አብነት ነው። በዚህ መሠረት ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የወታደራዊ ተቋሟን የማድረግ አቅም በላቀ ደረጃ እያሳደገች ትገኛለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሁን ላይ ኢትዮጵያ የታጠቀቻቸው በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በተለያዩ ቴክኖሎጂዎች የታገዙት ድሮኖች ጦርነትን ማስቀረት ብቻ ሳይሆን ጦርነትን ባጠረ ጊዜ መጨረስ የሚያስችሉ ናቸው ሲሉ መግለጻቸው። የኢትዮጵያ የታሪክ ድርሳናት ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟንና ሉዓላዊነቷን ለመግፈፍ የሚመጡ የውጭ ወራሪዎችንና የሚሰነዘሩ ማናቸውም ጥቃቶችን በድል አድራጊነትና ሉዓላዊነቷን ከማስከበር የማትበገር ሀገር መሆኗን ያመላክታሉ። ለዚህ ነው አባቶቻችን “ኢትዮጵያን የነካ የለውም በረካ” ሲሉ የሚገልጹት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተደጋጋሚ ኢትዮጵያ ትፈተናለች እንጂ አትሸነፍም ሲሉ መደመጣቸውም ይህንን መሠረት በማድረግ ነው።
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለግማሽ ፍጻሜ አለፈ
Oct 14, 2026 93
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 4/2019 (ኢዜአ)፦ በ17ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ተጠባቂ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ከዩጋንዳ ጋር አቻ ተለያየች። ማምሻውን በኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ተቀይሮ የገባው ዘሚካኤል ምንያህል በ71ኛው ደቂቃ ኢትዮጵያን መሪ አድርጓል። ዘሚካኤል በውድድሩ ላይ ሁለተኛ ግቡን አስቆጥሯል። አርኖልድ ካዬምባ በ78ኛው ደቂቃ ዩጋንዳን አቻ አድርጓል። ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት በአራት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ ምርጥ ሁለተኛ ሆና ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች። ኢትዮጵያ ምርጥ ሁለተኛ የሆነችው በምድብ ሶስት በተመሳሳይ አራት ነጥብ ያላትን ታንዛንያን በግብ ክፍያ በመብለጧ ምክንያት ነው። የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ሶስት የግብ ክፍያ፣ የታንዛንያ አቻው ሁለት ግብ ክፍያ አላቸው። የግማሽ ፍጻሜ መርሐ ግብር ቅዳሜ ጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ.ም ይካሄዳል። የማጣሪያ ውድድሩ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ይቆያል። በውድድሩ ከአንድ እስከ ሶስት የሚወጡ ሀገራት ሴካፋ ዞንን ወክለው በአፍሪካ ዋንጫ ይሳተፋሉ። 17ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ በ2027 በሞሮኮ አስተናጋጅነት ይካሄዳል። በውድድሩ ላይ 16 ሀገራት ይሳተፋሉ።
ምክር ቤቱ 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል
Oct 14, 2026 83
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 4/2019 (ኢዜአ)፦የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ1ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ.ም ያካሂዳል፡፡ ምክር ቤቱ በነገ መደበኛ ስብሰባው በህገ- መንግስቱ አንቀጽ 55/19/ እና በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ስነምግባር ደንብ ቁጥር ቁጥር 6/2008 አንቀጽ 152 መሰረት የምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ለመሰየም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡ እንዲሁም በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ስነምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀጽ 4/1/ (መ) እና አንቀጽ 5/4/(መ) መሰረት የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች አደረጃጀት፣ ተግባርና ኃላፊነት ለመወሰን የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪም ምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴዎች ዕጩ አመራር እና አባላትን ምደባ አስመልክቶ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ እንደሚያፀድቅ የምክር ቤቱ መረጃ ያመለክታል፡፡
የድል ከፍታን በሞራል ልዕልና ያጀበ ሕዝባዊ ሠራዊት
Oct 14, 2026 87
ትልቅ ሀገር ፣ ትልቅ ህዝብ ፣ ታላቅ ርዕይ #የመደመር_መንግሥት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከሕዝብ አብራክ የወጣ፣ለሕዝብ ደኅንነትና ለሀገር ሉዓላዊነት የቆመ፣ሕዝብንም ደጀኑ ያደረገ ተቋም ነው።ሀገርንና ሕዝብን የሚያውኩ ባንዳዎችንና ባዳ ኃይላትን የሴራና የጥፋት መረብ እየበጣጠሰ የሕዝብ አለኝታነቱን እያስመሰከረ ነው። ጠንካራ ሠራዊትነቱ በዘመናዊ ትጥቁና በውጊያ አቅሙ ብቻ ሳይሆን ከሕዝብ በተቀበለው አደራ፣ የሕዝብንና የሀገርን ደኅንነት በሚጠብቅበት ቁርጠኝነት፣ በሚያሳየው ሰብዓዊነትና በሚያስጠብቀው ሀገራዊ ክብር ጭምር የተረጋገጠ ነው። ይህ የሠራዊቱ የሕዝባዊነት መርህ በዘመናዊ አደረጃጀቱ ውስጥ ባለፈባቸው ከምዕተ ዓመት የተሻገሩ ዓመታት ሀገሬውና ዓለም የመሰከረለት ነው። ከሀገር መከላከልና ሉዓላዊነትን ከማስጠበቅ ባሻገር፣ በተለያዩ ዘመናት ለሕዝብ ደኅንነትና ለሰብዓዊ አገልግሎት ባለው ቁርጠኝነትም ይወሳል። ይህ የልዕልና ታሪኩ በኢትዮጵያ ምድር ብቻ የተገደበ አይደለም። በሶማሊያ፣ በላይቤሪያ፣ በኮንጎ፣ በዳርፉር፣ በአቢዬና በሌሎችም የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች የኢትዮጵያ ሠራዊት ያሳየው ተሳትፎና ዲሲፕሊን የተሞላበት አበርክቶ በአፍሪካ ሰላምና መረጋጋት ውስጥ ያለውን ሚና ያስመሰክራል።በእነዚህ ተልዕኮዎች ውስጥ ሠራዊቱ የተሸከመው አደራ የሀገሩን ስም ከማስጠራት ባሻገር ለሰላም የሚደረገውን የአፍሪካ የጋራና የወንድማማችነት ጥረትም ከፍ ያደረገ ሆኗል። የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሕዝባዊነቱን ዛሬም የሀገርን ዳር ድንበር በሚያስከብርባቸው ቦታዎች ሁሉ በተጨባጭ ሥራዎቹ እያሳየ ነው። ሠራዊቱ የድል ከፍታን በሞራል ልዕልና፣ ወታደራዊ ብቃትን በዲሲፕሊን፣ የጥንካሬ መገለጫንም በሰብዓዊነት በማጀብ እያሳየ ያለው ጥረት የሚደንቅ ነው።የአሸናፊነት ልዕልና በሌላው ላይ በሚኖር ወታደራዊ ብልጫ ብቻ አይገለጽም፤ ከአሸናፊነት ጋር የሚመጣውን ኃላፊነት በጥበብ፣ በሕግና በሰብዓዊነት በመወጣትም ጭምር ይመዘናል። ሠራዊቱ ሕገወጥና ጽንፈኛ ቡድኖች የሚፈጽሙትን ትንኮሳ በማምከን ሰላምን እያጸና፣ የሕዝብን ደኅንነት እየጠበቀ፣ሕብረተሰቡ የተለመደ ማኅበራዊ ኑሮውን ያለምንም ስጋት እንዲመራ እያደረገ ያለው ሚና የሕዝባዊነቱ ጉልህ መገለጫ ነው።ሠራዊቱ ሕዝቡ ውስጥ ገብቶ፣ሕዝቡን አረጋግቶ፣ ከሕዝቡ ጋር በመሆን አካባቢውን ከጥፋት ኃይሎች ሲያጸዳ ያሳየው ሙያዊ ሥነ ምግባር የኢትዮጵያን ጠንካራ ተቋማዊ አቅም የሚያመላክት ነው። የኢትዮጵያ የድል አብሳሪ የሆነው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የ130 ሚሊዮን ሕዝብ ሀገርን፣ ግዙፍ ኢኮኖሚ እየገነባች ያለች ሀገርን፣ የቀጣናው መልህቅና የአፍሪካ ተምሳሌት የሆነች ትልቅ ሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅም ዛሬ ራሱን በግዙፍ የሰው ኃይል፣ በሥልጠና ብቃትን፣ በፈጠራ ቴክኖሎጂን ታጥቆ የወትሮ ዝግጁነት ላይ ይገኛል።የታሪካዊ ጠላትን የጥፋት አጀንዳ የተሸከሙ ባንዳዎችን አከርካሪ በመስበር ሀገርን በክብር የልማት ሥራዋን እንድታፋጥን አይተኬ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። መከላከያ ሠራዊት አሁን የዕድሜውን ያህል ራሱን ከዘመኑ ጋር እያራመደ ይገኛል። በራስን መቻል የመደመር መንግሥት ስትራቴጂ መሠረት ከቀላል የጦር መሣሪያዎች ጀምሮ የተራቀቁ የድሮን ቴክኖሎጂዎች ማምረት ጀምሯል።ከሆሚቾ የተተኳሽ መሣሪያዎች እስከ ስካይዊን የድሮን ማምረቻ ድረስ ግዙፍ ኢንዱስትሪዎችን በማንቀሳቀስና በማምረት ለሌሎች ሀገራትም የሚተርፍ አቅም እየገነባ ነው። ጦርነትን ከሩቅ የሚያስቀርና ውጊያን በፍጥነት የሚጨርስ ግዙፍ ሠራዊት የገነባችው ኢትዮጵያ መዳከሟን የሚመኙ፣ አትችልም የሚሉትን ሁሉ በድሎቿ እየረታች ጉዞዋን ቀጥላለች።በአራቱም አድማስ ሰላማዊነትን በማስቀደም የሚተነኩሷትን ደጋግመው እንዲያስቡ በሚያደርግ ጠንካራ እርምጃዋ እያሳፈረች ትገኛለች። ሠራዊቱም የሀገርን ጥቅምና ደህንነት በሁሉም አውድ በአስተማማኝ እያስጠበቀ ነው። የሀገር ብሔራዊ ጥቅም ከባሕር የሚመነጩ ስጋቶችን በመቀነስም የሚረጋገጥ በመሆኑ የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት የትውልዱ የአርበኝነት ጥያቄን መሠረት በማድረግ የመርከቦቿንና የቀጣናውን ደኅንነት የሚያስጠብቅ ግዙፍ የባሕር ኃይል ገንብቷል።የሀገር ጥቅምና ደኅንነት በየብስና በባሕር ብቻ ሳይሆን በአየርም ጭምር የሚረጋገጥ እንደመሆኑ ሰማዩ የእኛ ነው በሚል መርህ 4ኛ ትውልድ ቴክኖሎጂን በመታጠቅ ወደ አምስተኛ ትውልድ ቴክኖሎጂ እየገሰገሰ የሚገኘውን ግዙፍ አየር ኃይል ያደራጀው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያን ደኅንነትና የአየር ክልል በአስተማማኝ ሁኔታ እየጠበቀ ይገኛል። የሀገር መከላከያ ሠራዊቱ የትልቅ ሀገርና የትልቅ ሕዝብ ሠራዊት ነው።በታላቅ ርዕይም ከሀገር እስከ ዓለም አቀፍ ተልዕኮዎች ራሱን እያበቃና እያዘጋጀ ጉዞውን ቀጥሏል።ሠራዊቱ ከሕዝብ አብራክ የወጣ የሕዝብ ልጅ ነው፤ ለሕዝብ ደኅንነት የቆመ የሕዝብ ጋሻ ነው፤ በችግር ጊዜ የሕዝብ ደጀን ነው። የእውነተኛ ጀግንነት ልዕልናም ድልን በሰብዓዊነት፣ኃይልን በዲሲፕሊን፣ አሸናፊነትን በሞራል ጥንካሬ ማጀብ ነው።ይህ የሕዝባዊነት መንፈስ በተሰማራባቸው ሥፍራዎች ሁሉ ይታያል። ከሀገር እስከ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ የኢትዮጵያ ሠራዊት ምስጉንና ጀግና መሆኑ ሁልጊዜም ሲወሳ ይኖራል።
ፖለቲካ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
Oct 14, 2026 121
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 4/2019 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር የስልክ ውይይት አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ከማርኮ ሩቢዮ ጋር በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊ እና በባለብዙ ወገን የጋራ ትኩረትን በሚሹ ጉዳዮች ላይ እጅግ ፍሬያማ የሆነ የስልክ ውይይት ማካሄዳቸውን ገልጸዋል። ያካሄድነው ውይይት በኢትዮጵያና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለውን እድሜ ጠገብ ወዳጅነት ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊና ተግባራዊ አጋርነት ለማሳደግ በሁለቱም አገራት በኩል ያለውን ቁርጠኝነት ማረጋገጫ ነው ሲሉ ገልጸዋል። ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ በተመለከተ የሰጠችውን ማረጋገጫ አድንቀዋል። የሁለትዮሽ ትብብራችንን ለማጠናከር እንዲሁም በቀጣናዊና ባለብዙ ወገን መድረኮች ቅድሚያ በምንሰጣቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ አብረን ለመሥራት ያለንን ቁርጠኝነት አረጋግጣለሁ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።
በመደመር መንግስት የተፎካካሪ ፓርቲዎችን በማሳተፍ በጋራ ሀገርን የመገንባት ቁርጠኛ ነን- የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
Oct 14, 2026 167
ሆሳዕና፤ ጥቅምት 4/2019(ኢዜአ)፦ በመደመር መንግሥት የተፎካካሪ ፓርቲዎችን በማሳተፍ በጋራ ሀገርን የመገንባት ቁርጠኝነት መኖሩን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለፀ። የጋራ ምክር ቤቱ በመደመር መንግስት ምስረታና ቀጣይ በትብብር በሚሰሩ ተግባራት ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል። የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ደምስ ገብሬ በሰጡት መግለጫ፤ በመደመር መንግስት የተፎካካሪ ፓርቲዎችን በማሳተፍ በጋራ ሀገርን የመገንባት ቁርጠኝነት መኖሩን ገልጸዋል። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ የመንግስት ምስረታውን ካከናወነው ብልጽግና ፓርቲ ጋር እንደከዚህ ቀደሙ በጋራ እንደሚሰሩም ተናግረዋል፡፡ የመደመር መንግስት በሀገር ሰላምና ልማት መጠናከር ዙሪያ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመስራት የበለፀገች ሀገርን በጋራ ለመገንባት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ምስረታ ስለማከናወኑም ገልጸዋል፡፡ የጋራ ምክር ቤቱ በመደመር መንግስት የሚተገበሩ የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የሰላም ማስጠበቅና የልማት ስራዎችን በትብብር በመስራት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንደሚወጣም ሰብሳቢው ገልጸዋል። የጋራ ምክር ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ በረከት ከድር በበኩላቸው፤ የመደመር መንግስት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ አካታችነትን ማዕከል ያደረገ መንግስት መመስረቱን ተናግረዋል። ይህም በኢትዮጵያ የሀሳብ ብዝሃነትን መሰረት ያደረገ የትብብር ዴሞክራሲ ስርዓትን በመተግበር ረገድ ተምሳሌት እንደሚያደርገው ጠቅሰዋል። በዚሀም በክልሉ የተፎካካሪ ፓርቲዎችን ያሳተፈ የአመራር አደረጃጀት ከመፍጠር ባሻገር በምክር ቤቱ 27 መቀመጫዎች ለተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮች ስለመለቀቃቸውም አስረድተዋል። የመደመር መንግስት የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን በማካተት ከተናጠል ይልቅ በጋራ ሀገር ለመገንባት ያለውን ተነሳሽነት በምስረታው ማረጋገጡን የገለጹት ደግሞ የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ ሊቀ መንበርና የምክር ቤቱ ፀሐፊ አቶ ፈድሉ ጁሃር ናቸው፡፡ ፓርቲያቸው አዲስ ከተመሰረተው መንግስት ጋር በቅንጅት በመስራት የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደቱን የተሻለ ለማድረግ እንደሚሰራም ገልጸዋል። በእናት ፓርቲ የሆሳዕናና አካባቢ ፀሐፊና የጋራ ምክር ቤቱ ስራ አስፈፃሚ አቶ ተመስገን ሹመቱ በበኩላቸው፤ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አሸናፊ የሆነው የመደመር መንግስት ምስረታ የዲሞክራሲ ባህልንና የመድብለ ፓርቲ መርህን ተከትሎ የተፈፀመ ነው ብለዋል፡፡
የመደመር መንግሥት ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን የማጎልበት ማዕከላዊ እሳቤ ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል
Oct 14, 2026 267
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 4/2019 (ኢዜአ)፦ የመደመር መንግሥት ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን የማጎልበት ማዕከላዊ እሳቤ አካታች የፖለቲካ ምኅዳርን በማስፋት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች ለማስከበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ምሁራን ገለጹ። ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ባካሄደው 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ጉባዔው ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር)ን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክትም፤ የመደመር መንግሥት አካታችነትንና አሳታፊነትን በማጎልበት የኢትዮጵያን ብልፅግና የሚያረጋግጥ መሠረት መጣሉን ገልጸዋል። ብልፅግና ፓርቲ ለዴሞክራሲ ስርዓት መጎልበት ባለው ቁርጠኝነት የመደመር መንግሥት የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎን እያሳደገ መሆኑንና ይህም ለብሔራዊ ጥቅም መጠበቅ አይነተኛ ሚና እንዳለው አስረድተዋል። ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በፈተናዎች የታጀበ ቢሆንም ሕዝቡ ያሳየው ቁርጠኝነት የሚደነቅ መሆኑን ጠቁመው የምርጫ ሂደቱ የዴሞክራሲ ባሕል እያደገ ስለመምጣቱም አመላካች ነው ብለዋል። በምርጫ ሂደት አሸናፊና ተሸናፊ ሊኖር ቢችልም ኢትዮጵያ አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ዜጋ እንደማይኖራትና በወንድማማችነት መንፈስ የሀገርን ዕድገት ለማስቀጠል እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። በቀጣይም የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ፍላጎት ለማስጠበቅ በሁሉም መስክ በትብብር እንደሚሰራ ገልጸዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው ምሁራን እንዳሉት፤ የመደመር መንግሥት አካታችና አሳታፊ የፖለቲካ ምኅዳር የኢኮኖሚ ዕድገትን በማፋጠን ብሔራዊ ጥቅሞችን ለማስጠበቅ ጉልህ አስተዋፅኦ ይኖረዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝምና አስተዳደር መምህርና ተመራማሪ ተስፋዬ ጂማ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ የመደመር መንግሥት የዴሞክራሲ ምኅዳርን በማስፋት በትብብር ላይ የተመሠረተ አውድ ፈጥሯል። ይህ የትብብርና አንድነት እሳቤም የኢትዮጵያን ዕድገትና ብልፅግና ለማፋጠን የተወሰደ ቁርጠኛ አቋም እንደሆነ ገልጸዋል። የመደመር መንግሥት ማዕከላዊ እሳቤም ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ነው ያሉት ምሁሩ፤ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን በማሳተፍ የዴሞክራሲ ምኅዳሩን ማስፋቱም ትብብርን ለማጎልበት ጉልህ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል። የመደመር መንግሥት የባሕር በር ባለቤትነትን ለማረጋገጥ ያቀረበው ፍትሐዊና ምክንያታዊ ጥያቄም የሉዓላዊነትና ሕልውና ጉዳይ መሆኑን አስረድተዋል። የሥነ-አመራርና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ጌትዬ ትርፌ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የመደመር መንግሥት አካታች የአመራር መዋቅር አዳዲስ አመራሮችን ለማፍራት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል። አዲሱ አካታችና አሳታፊ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች መዋቅርም የኢትዮጵያን ፈጣን የዕድገት መሻት ለማፋጠን የሚያስችል አቅም ለማጎልበትም ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመንግሥት ምስረታ ወቅት ያስተላለፏቸው የቀጣይ የልማት የትኩረት መስኮችም ኢትዮጵያ ማሳካት የምትሻቸውን ብሔራዊ ጥቅምና ፍላጎቶች ማዕከል ያደረጉ መሆናቸውን አንስተዋል። ይህም የሀገር ውስጥ ስብራቶችን በማከም ቀጣናዊ የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል አቅም የሚገነባ መሆኑንም አብራርተዋል። በቀጣይም ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን የበለጠ በማጎልበት የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች ግንባታን በማፋጠን ለሕዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በትኩረት መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
የመደመር እሳቤ፡ ለአፍሪካ የጋራ ብልፅግና አዲስ መንገድ
Oct 14, 2026 205
ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን የነጻነት፣ የሉዓላዊነት እና የጥቁር ህዝቦች ኩራት ተምሳሌት በመሆን በአፍሪካ አህጉር ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ አላት። ቅኝ ያልተገዛችው፣ ሉዓላዊነቷን ያላስደፈረችው እና ክብሯን አስጠብቃ ለዘመናት የቆየችው ኢትዮጵያ፤ አፍሪካውያንን ከቅኝ ግዛት ለመላቀቅ ባደረጉት ትግል ውስጥ ፋና ወጊ እና የነጻነት ተምሳሌት በመሆን ታሪካዊ አሻራዋን አሳርፋለች። ይህ ታሪካዊ ሚናዋ ዛሬም ድረስ በአዲስ መልክ እየቀጠለ ይገኛል። የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እና የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ምስረታ ላይ ትልቅ አሻራ ያላት ኢትዮጵያ የህብረቱ ዋና መቀመጫ በመሆን የአህጉሪቷ የዲፕሎማሲ መናኸሪያ ናት። ሀገሪቱ የአፍሪካውያን ነጻነት እና ራስን መቻል የሚያቀነቅነውን የፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ ነፍስ እንዲዘራና ህያውነት እንዲላበስ በማድረግ የአህጉሪቱ ትልሞች እውን እንዲሆኑ የላቀ ሚና ተጫውታለች። በታሪክ የታየው ይህ የፓን አፍሪካኒዝም ስንቅ፣ ዛሬ ላይ በመደመር ፍልስፍና ታድሶ ድንበር ተሻጋሪ አህጉራዊ ኃይል እየሆነ መጥቷል። የአዲሱ የመደመር መንግሥት ምስረታ የሀገሪቱን የውስጥ ፖለቲካዊ ምዕራፍ የሚያድስ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም የመደመር እሳቤ የኢትዮጵያን ወሰን አልፎ ለመላው አፍሪካውያን የሚጠቅም አህጉራዊ ፍልስፍና መሆኑን በተግባር ያሳየበት ክስተት ነው። መደመር ሀገሪቷ ያሏት መልካም እሴቶች ላይ መጨመርን፣ ጉድለቶችን መሙላትን፣ ያለፈውን ስህተት አርሞ መልካሙን ማስቀጠልን እና በጋራ ማደግን የሚያስተምር ሀገር በቀል ፍልስፍና ቢሆንም፣ ዛሬ ላይ ግን ድንበር ተሻግሮ ለአህጉራዊው የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ፣ ለአፍሪካ ህብረት መጠናከር እና ለአፍሪካውያን በራስ የመተማመን መንፈስ አዲስ መነቃቃትን እየፈጠረ ይገኛል። ይህ እሳቤ ለአፍሪካ ጥንካሬ ያለው አንድምታ ከፍተኛ ነው። አፍሪካውያን ያላቸውን የተፈጥሮ እና የሰው ሀብት አስተባብረው በዚሁ ድንበር ተሻጋሪ የመደመር እሳቤ ከተመሩ፣ ከማንኛውም ጥገኝነት መውጣት ይችላሉ። ፍልስፍናው በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ግንኙነት በማጠናከር፣ ከፉክክር ፈንታ በትብብር ላይ የተመሰረተ አህጉራዊ ትስስርን ለመገንባት አስተማማኝ መሰረት እየሆነ ነው። በዚህ ማዕቀፍ ስር ኢትዮጵያ «የአፍሪካ ችግሮች በአፍሪካውያን ይፈቱ» የሚለውን የጸና አቋሟን ይበልጥ አጠናክራለች። አዲሱ የመደመር መንግሥት አፍሪካውያን የራሳቸውን ችግር በራሳቸው አቅምና እውቀት እንዲፈቱ የሚያስችሉ ስራዎችን በወሰን ተሻጋሪ ወንድማማችነት መንፈስ በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል። ይህ ድንበር የተሻገረው የመደመር እይታ አፍሪካውያን እንደ አፍሪካ ህብረት ያሉ አህጉራዊና ቀጣናዊ ተቋማት ላይ ያላቸውን እምነት የሚያጠናክር እና የውጭ ጣልቃ ገብነትን በጋራ ለመመከት የሚያስችል ትልቅ አህጉራዊ አቅም የሚፈጥር ነው። በመሆኑም በመደመር ፍልስፍና የሚመራ ጠንካራ የኢትዮጵያ መንግስት ምስረታ ለአፍሪካ እድገት እና ሰላም የሚኖረው ፋይዳ የጎላ ነው። ጠንካራ ኢትዮጵያ ማለት ለአፍሪካ ቀንድ አስተማማኝ ሰላም፣ ለምስራቅ አፍሪካ የኢኮኖሚ ትስስር ምሰሶ እና ለመላው አህጉሪቱ የነጻነት ፋኖስ ናት። የመደመር እሳቤ የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሮ ለአህጉሪቱ መፍትሔ መሆን መቻሉ፤ አፍሪካውያን በኢኮኖሚ ራሳቸውን እንዲችሉ እና በዓለም መድረክ ላይ የሚገባቸውን ክብርና ቦታ እንዲያገኙ ለማድረግ የጎላ ሚና ይጫወታል።
የጣና ፎረም ታዳሚዎችን ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጅት ተደርጓል
Oct 13, 2026 388
ባህርዳር፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦ በባህር ዳር ከተማ የሚካሄደው የጣና ፎረም ታዳሚዎችን ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጅት መደረጉን የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው ፎረሙን ለማዘጋጀት እየተደረገ ባለው ዝግጅትና የኮሙኒኬሽን ስራዎች ላይ በማተኮር ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል። የቢሮው ኃላፊ አቶ አባይ መንግስቴ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ከጥቅምት 13 እስከ 15 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ በባህርዳር ከተማ የሚካሔደው የጣና ፎረምን ስኬታማ በሆነ መንገድ ለማጠናቀቅ የተሟላ ዝግጅት ተደርጓል። ፎረሙ የኢትዮጵያን ገጽታ በሚገነባና እድገቷን አጉልቶ በሚያሳይ መልኩ የሚካሔድ መሆኑን ተናግረዋል። የጣና ፎረም አፍሪካውያን የራሳቸውን ችግር በራሳቸው ጥበብና አመራር ለመፍታት የሚካሄድ መሆኑንም አክለዋል። በባህርዳር ከተማ እስካሁን የተካሄዱ 11 የፎረሙ ስብሰባዎችም በአህጉሩ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመለየት ለመሪዎች ጉባኤ የመፍትሄ ሃሳብ በማቅረብ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል። በዚህም በአፍሪካ ሰላምና መረጋጋትን በማስፈን እድገትና ልማትን በማፋጠን ላይ በመምከር የመፍትሄ ሃሳቦችንና የቀጣይ እቅጣጫዎች እንዲመነጩ መደረጉን ጠቅሰዋል። በተጨማሪም አፍሪካ ያላትን ሃብት ተጠቅማ እንዳትለማ እንቅፋት በሆኑ ህገ- ወጥ የሰዎችና የገንዘብ ዝውውር ላይ በመወያየት ችግሩ የሚፈታበትን መንገድ ማመላከት እንደተቻለ አመልክተዋል። “በአፍሪካ የሰላም መንገዶች፣ የኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነትና የጂኦፖለቲካ ለውጥ” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደውን የዘንድሮው የ12ኛው የጣና ፎረም በአፍሪካ ሰላም፣ መረጋጋትና እድገት ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ለመላው የጥቁር ህዝቦች ነጻነት እንደታገለችው ሁሉ ዛሬም የራሷን ልማትና እድገት በማረጋገጥ ወደ አህጉሩ አባል ሀገራት እንዲስፋፋ የበኩሏን ኃላፊነት እየተወጣች እንደምትገኝ አስረድተዋል። በባህርዳር ከተማ የሚገኙ ሆቴሎችና ሌሎች የአገልግሎት መስጫ ተቋማትም ለፎረሙ የሚመጡ የአፍሪካ መሪዎችን እንዲሁም ከፍተኛ ተመራማሪዎችና ባለሙያዎችን ለማስተናገድ የሚያስችል ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። 12ኛው የጣና ፎረም በባህርዳር ከተማ ከጥቅምት 13 እስከ 15 ቀን 2019 ዓ.ም ይካሄዳል።
የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ልዑል ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ
Oct 13, 2026 391
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን ቢን አብዱልአዚዝ አል ሳዑድ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል። 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ባካሄደው 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ጉባዔው ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር)ን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል። የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን ቢን አብዱልአዚዝ አል ሳዑድ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንኳን ደስ አለዎት ለማለት እወዳለሁ ብለዋል። አልጋ ወራሹ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ስኬትን፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ቀጣይነት ያለው እድገት እና ብልጽግናንም ተመኝተዋል።

ማህበራዊ
በአፋር ክልል በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ችግር ለገጠማቸው ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ እየተደረገ ነው
Oct 14, 2026 79
ሰመራ ጥቅምት 4/2019 (ኢዜአ) ፦በአፋር ክልል በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ችግር ለገጠማቸው ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ እየተደረገ ነው። ከአዳማ የእህል ማከማቻ ማዕከላዊ መጋዘን በመጀመሪያው ዙር የተጫነው ሰብዓዊ ድጋፍ በክልሉ የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ወገኖች በመከፋፈል ላይ ይገኛል። በዛሬው ዕለትም በቢዱ ወረዳ ጊሪፎ ቀበሌ ለበርካታ ወገኖች ተደራሽ የተደረገ ሲሆን ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖችም ምስጋና አቅርበዋል። በተፈጥሮ መዛባት ምክንያት በአካባቢው በተከሰተው ድርቅ ለችግር መጋለጣቸውን የገለጹት ነዋሪዎቹ ድጋፍ ባስፈለገን ጊዜ ደርሶልናል ብለዋል። ድጋፍ ከተደረገላቸው መካከል ወይዘሮ መይረም አብዱ፤ የተደረገልን ድጋፍ ልጆቻችን እና አጠቃላይ ቤተሰቡ ላጋጠመን የምግብ እጥረት መፍትሄ የሚሆነን ነው ብለዋል። መንግስት በአካባቢው ያጋጠመውን የተፈጥሮ አደጋ በመረዳት ፈጣን ምላሽና ድጋፍ በማድረጉ አመስግነዋል። ሌላኛዋ የድጋፉ ተጠቃሚ ወይዘሮ አሲያ መሐመድ፤ በአካባቢው ያጋጠመውን ችግር መንግስት አውቆ አስፈላጊውን ድጋፍ ስላደረገልን እናመሰግናለን ብለዋል። በመንግስት ድጋፍ ባይደረግላቸው እርሳቸውና ቤተሰባቸው የከፋ ችግር ላይ ይወድቁ እንደነበር ተናግረዋል። በመሆኑም እርሳቸውን ጨምሮ ሌሎችም የአካባቢው ነዋሪዎች የተደረገላቸው ድጋፍ ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን ገልጸዋል። የአፋር ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የክምችት ጥራትና ቁጥጥሮ ቡድን መሪ አቶ መሐመድ አብደላ፤ በክልሉ የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ እየተዳረሰ መሆኑን ተናግረዋል። ክልሉ በራሱ አቅም ድጋፍ ለሚሹ አካባቢዎች የሰብአዊ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱንና አሁንም በማድረግ ላይ መሆኑን አንስተው ከኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር የተላከውንም የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚሹ ወገኖች እየደረሰ መሆኑን ገልጸዋል። የቢዱ ወረዳ የአርሻና ተፈጥሮ ሃብት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ የሱፍ መሐመድ፤ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በአካባቢው የተከሰተው ድርቅ ነዋሪዎችን ለችግር መዳረጉን ገልጸዋል። በመሆኑም መንግስት ያለውን ችግር በመረዳት የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽ ማድረጉ ወቅታዊና አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
በከተማ አስተዳደሩ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ621 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የልማት ስራ ተከናውኗል
Oct 14, 2026 95
ደሴ ፤ ጥቅምት 4/2019 (ኢዜአ)፦በደሴ ከተማ አስተዳደር በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ621 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የልማት ስራ መከናወኑ ተገለጸ፡፡ በክረምቱ ወቅት በተካሄደው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ621 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የልማት ሥራዎች መከናወናቸውንም የከተማ አስተዳደሩ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ አስታውቋል። የከተማ አስተዳደሩ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠናቀቂያና የ2019 የበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መድረክ ዛሬ በደሴ ከተማ ተካሂዷል። የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ በከተማ አስተዳደሩ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተመዘገበው አበረታች ውጤት በበጋውም ወራት ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል። የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንደ ሀገር የመተጋገዝ፣ የመተባበርና የአብሮነት ባህልን በማስቀጠል የዜጎችን ሁለንተናዊ ችግር ከማቃለሉ ባለፈ የልማት ክፍተቶችን መሙላት እያስቻለ ነው ብለዋል። በበጋው ወቅት ለማካሄድ የታሰበው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማህበረሰቡን በተሻለ መንገድ ተጠቃሚ የሚያደርግ እንዲሆንም የተለያዩ እቅዶች ተግባራዊ እንደሚደረጉ ነው ያመለከቱት። የከተማ አስተዳደሩ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሪት ትግስት አበበ በበኩላቸው፤ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለማቃለል ተችሏል ነው ያሉት። በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ከ181 ሺህ በላይ ዜጎችን በማሳተፍ ከ130 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም ገልጸዋል። በክረምቱ ወቅት የ296 አቅመ ደካሞችን ቤት በማደስና በአዲስ በመገንባት፣ 3ነጥብ 5 ሚሊዮን ችግኝ በመትከል፣ 2 ሺህ 800 ዩኒት ደም የመለገስና ሌሎች ተግባራትን በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለማከናወን መቻሉንም ተናግረዋል። በተጨማሪም ከ2 ሺህ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካማ ወገኖች ነጻ ምርመራና ሕክምና እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገር፣ 10 ሺህ ሄክታር የሚሆን የአቅመ ደካሞችን መሬት በማረስ በዘር የመሸፈንና የመንከባከብ ሥራ መሰራቱን ተናግረዋል። የተካሄዱት የበጎ ፈቃድ ሥራዎች በገንዘብ ሲተመኑ ከ621 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያስወጡ መሆናቸውን ጠቁመው፤ የክረምቱን ተሞክሮ በመቀመር በበጋው ወራት የላቀ አፈጻጸም ለማስመዝገብ እንደሚሰራ አስረድተዋል። ከበጎ ፈቃደኞች መካከል ወይዘሮ የሺ ገዛኸኝ በሰጡት አስተያየት፤ በክረምት የነበረውን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በበጋውም ወቅት ለመቀጠል ተዘጋጅተናል ብለዋል። በመድረኩ የከተማና የክፍለ ከተማ አመራሮች፣ በጎ ፈቃደኞችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
በሸገር ከተማ የመሶብ አንድ ማዕከል ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዩን እርካታ እያሳደገ ነው
Oct 14, 2026 62
ሸገር፣ ጥቅምት 04/2019 (ኢዜአ)፡- የሸገር መሶብ የአንድ ማዕከል ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን ፍላጎት በብቃት እያሟላ እንደሚገኝ የከተማ አስተዳደሩ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ገለጸ። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የተለያዩ ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎቶች በአንድ ጣራ ስር በማሰባሰብ ዜጎች ጊዜያቸውንና ጉልበታቸውን ቆጥበው ለእንግልት ሳይዳረጉ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል የተጀመረ አሰራር ነው። በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ አስተዳደርም የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስና አገልግሎትን ወደ ማህበረሰቡ ይበልጥ ለማቅረብ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በማስፋፋት ላይ ይገኛል። አገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ ግልጽ፣ ተጠያቂነት ያለው እና ዘመናዊ ለማድረግ ፋይሎችን በዲጂታል በተደራጀ መልኩ በመያዝ በአጭር ደቂቃዎች ውስጥ አገልግሎት እየተሰጠ ያለ አሰራር ነው። የከተማው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ካሳሁን ጆብር ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ በ2019 በጀት ዓመት በከተማው የማህበረሰቡን ፍላጎት ለማሟላት ዋናውን ማዕከል ጨምሮ አራት ቅርንጫፎች በመክፈት በአጠቃላይ በአምስት ማዕከላት በቴክኖሎጂ የታገዘ ቀልጣፋ አገልግሎት እየተሰጠ ነው። በእነዚህ ማዕከላት በተደረገ እንቅስቃሴ፣ በአንደኛው ሩብ ዓመት አገልግሎት ለማግኘት ከቀረቡት 165 ሺህ 91 ዜጎች መካከል አስፈላጊውን መስፈርት ያሟሉ ከ161 ሺህ በላይ የሚሆኑት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን አስታውቀዋል። በመሶብ የአንድ ማዕከል የአገልግሎት አሰጣጥ የማህበረሰቡን ፍላጎት 99 ነጥብ 9 በመቶ ማድረስ መቻሉን ጠቁመው፣ ይህም የህብረተሰቡን እርካታና ተጠቃሚነት በብቃት ማሳደጉን አረጋግጠዋል። የተገልጋዮች ፋይል በተደራጀ መልኩ መያዙ አገልግሎቱን ቀልጣፋ አድርጎታል ያሉት ስራ አስኪያጁ፤ ይህም ህብረተሰቡ ለእንግልትና ለአላስፈላጊ ወጪ ሳይዳረግ ጊዜውን በአግባቡ በመጠቀም ሙሉ ትኩረቱን ወደ ልማት ስራዎች እንዲያዞር አስችሎታል ብለዋል። በማዕከሉ በአማካኝ በ24 ደቂቃዎች ውስጥ ተገልጋዩ የሚፈልገውን አገልግሎት ማግኘት መቻሉን ያነሱት አቶ ካሳሁን፤ ይህ አሰራር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታትና የልማት ሥራዎችን በማፋጠን የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው አብራርተዋል። እንዲሁም ተበትነው የነበሩትን አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ አንድ ማዕከል በማምጣት በአጭር ጊዜ ውስጥ ግልጽና የተሟላ አገልግሎት በመስጠት፤ ማህበረሰቡ በመንግስት ላይ ያለውን እምነትና ተሳትፎ በተጨባጭ ማሳደጉን ጠቁመዋል። በዚህም የመንግሥት ገቢን በማሳደግ፣ ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ በማድረግ እና የተያዙ የልማት ግቦችን በማፋጠን ረገድ ማዕከሉ የጎላ ሚና ያለው መሆኑን አስገንዝበዋል። በሸገር ከተማ የአገልግሎቱን ተደራሽነት ለማስፋት በሁሉም ክፍለ ከተሞች ማዕከላት እንደሚቋቋሙ የገለጹት አቶ ካሳሁን፣ በተያዘው በጀት ዓመትም ተጨማሪ አራት ማዕከላት ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆኑ ተናግረዋል።
በአርብቶ አደሩ አካባቢ የተጀመረው የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም የተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎና ውጤታማነት አሳድጎታል
Oct 14, 2026 74
ጂንካ፤ ጥቅምት 4/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ኦሞ ዞን በአርብቶ አደሩ አካባቢ የተጀመረው የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም የተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎና ውጤታማነት ከማሳደግ አንጻር ሚናው የላቀ መሆኑ ተገለጸ። የደቡብ ኦሞ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መልካሙ ሺበሺ ለኢዜአ እንደገለጹት በዞኑ በ188 ትምህርት ቤቶች ውስጥ የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም እየተካሄደ ነው። በዚህም እስካሁን ድረስ 66 ሺህ 337 ተማሪዎች የምገባ ፕሮግራሙ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል። ይህም የተማሪዎች መጠነ ማቋረጥና መቅረትን በማስቀረት በትምርት ጥራት ላይ አዎንታዊ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አመልክተዋል። ፕሮግራሙ የአርብቶ አደሩን የትምህርት ተሳትፎና ውጤታማነት ከማሳደግ አንፃር ሚናው የላቀ መሆኑም አቶ መልካሙ ገልጸዋል። በዞኑ የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ከተጀመረባቸው መካከል የቀይ አፈር አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምክትል ርዕሰ መምህርት ይሳለሙሽ ሽቱ በበኩላቸው እንዳሉት፣ ካለፉት ዓመታት ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም በተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎና በትምህርት ጥራት ላይ አዎንታዊ ሚና እየተጫወተ ነው። የክልሉ መንግስት የተለያዩ አካላትን በማስተባበር ዘንድሮም የምገባ ፕሮግራሙን ማስቀጠሉን ገልጸው፣ ፕሮግራሙ ወደትምህርት ቤት የሚመጡ ተማሪዎችን ቁጥር በየጊዜው እንዲጨምር አድርጓል ብለዋል። በተለይ እንደ ቀይ አፈር ከተማ ባሉ አርብቶ አደር አካባቢዎች የተማሪዎች ምገባ መጀመሩ ለመማር ማስተማር ሥራው ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጾ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። በደቡብ ኦሞ ዞን የበና ፀማይ ወረዳ የቀይ አፈር አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በበኩላቸው የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም ትምህርታቸውን በተረጋጋ ሁኔታ ለመከታተል እንዳስቻላቸው ተናግረዋል። ተማሪዎች እንደገለጹት በትምህርት ቤቱ የተጀመረው የምገባ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሳይቸገሩ ለመከታተልና ሙሉ ጊዜቸውን ለትምህርታቸው እንዲሰጡ አስችላቸዋል። ከተማሪዎቹ መካከል የ6ኛ ክፍል ተማሪ ሷሊ ሰኢድ፤ በትምህርት ቤቱ የተጀመረው የምገባ ፕሮግራም የተማሪዎችን የትምህርት ፍላጎት በማሳደግ ውጤታማ እንዲሆኑ እያደረገ ነው። በተለይ ቁርስ ለመብላት በቤታቸው ያባኩኑት የነበረውን ጊዜ በማስቀረት በመግቢያ ሰዓት በትምህርት ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዲገኙ እንዳስቻላቸው ገልጻ፣ ይህም ትምህርታቸውን በተሻለ መልኩ ለመከታተል እንዳስቻላቸው ተናግራለች። ሌላዋ የዚሁ ትምህርት ቤት የ6ኛ ክፍል ተማሪ አድናቆር አክሊሉ በበኩሏ ምግብ ሳይበላ የሚመጣ ተማሪ ትምህርቱን በአግባቡ ለመከታተል ይቸገራል ብላለች። የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም መጀመሩ ይህን በማስቀረት ተማሪዎች ከትምህርት ቤት እንዳያረፍዱና እንዳይቀሩ ከማድረግ ባለፈ ትምህርታቸውን ተረጋግተው እንዲማሩ አስችሏል ብላለች።
ኢኮኖሚ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የካዳስተር ስርዓትን በመዘርጋት ህገወጥ የመሬት ወረራን የመከላከል ስራ በትኩረት እየተከናወነ ነው
Oct 14, 2026 96
ዲላ ፤ ጥቅምት 4/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የካዳስተር ስርዓትን በመዘርጋት ህገወጥ የመሬት ወረራን የመከላከል ስራ ቅንጅታዊ በሆነ መልኩ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ መሬት አስተዳደር ቢሮ ገለጸ። በክልሉ መሬትን በህጋዊ መንገድ የመመዝገብ፣ በአግባቡ የማስተዳደር እና ህገወጥነትን የመከላከል ስራ ላይ ትኩረት ያደረገ የምክክር መድረክ በዲላ ከተማ ተካሄዷል። የቢሮው ምክትል ኃላፊ ዳንኤል ዳሌ (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት፤ በክልሉ ውስን የሆነውን የከተማ መሬት በአግባቡና በዘመናዊ መንገድ ለማስተዳደር በትኩረት እየተሰራ ይገኛል። በክልሉ በሚገኙ ከተሞች ከ58 ሺህ በላይ ያልተመዘገቡ የግል ይዞታዎች ተለይተው ህጋዊ የማድረጉ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል። ቢሮው እስካሁን በአግባቡ ያልተመዘገቡና ህጋዊ የመሬት ይዞታዎችን ቆጥሮ በመለየትና በዘመናዊ መንገድ ዝርዝር መረጃዎችን በማደራጀት የመለየት ተግባር መከናወኑን ተናግረዋል። ህግን ባልተከተለ መንገድ የተያዙ መሬቶችን በመለየት ወደ መንግስት መሬት ባንክ እንዲገቡ የማድረግ ተግባር እየተከናወነ መሆኑን የቢሮው ምክትል ኃላፊ ገልፀዋል። ይህም ህገወጥነትን በመከላከል ለመልካም አስተዳደር ችግሮች ምላሽ ከመስጠት ባለፈ የመሬት ካዳስተር ስርዓትን ለመዘርጋት እያስቻለ መሆኑን አስረድተዋል። በተለይ የከተሞችን የመሬት ሀብት በአግባቡ ማስተዳደርና ማዘመን የከተሞችን እድገት እያፋጠነ መሆኑንም አክለዋል። የዲላ ከተማ መሬት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ አቶ ምህረቱ አበበ በበኩላቸው፤ በከተማው በተያዘው በጀት ዓመት 429 ያልተመዘገቡ የግል ይዞታዎችን በመለየት ህጋዊ የማድረጉ ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል። ይህም በከተማው የሚገኙ መሬቶችን ሙሉ በሙሉ ወደ ካዳስተር ስርዓት ለማስገባት የሚደረገውን ጥረት እያገዘ መሆኑንም ተናግረዋል።
የዓለም አቀፍ የብድር ሽግሽግ አሰራር ፈጣንና ግልጽ የጊዜ ሰሌዳ ሊኖረው ይገባል - ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)
Oct 14, 2026 109
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 4/2019 (ኢዜአ)፦ የዓለም አቀፍ የብድር ሽግሽግ አሰራር ፈጣንና ግልጽ የጊዜ ሰሌዳ ሊኖረው እንደሚገባ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ገለጹ። የ2026 የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና የዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ በታይላንድ ባንኮክ እየተካሄደ ነው። ከዓመታዊው ስብሰባ ጎን ለጎን የዓለም አቀፍ የሉዓላዊ ብድር ውይይት ተደርጓል። በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የብድር ሽግሽግ ተሞክሮዎችን እና ልምዶችን አቅርበዋል። የብድር ማቃለያ ጥያቄ ለሚያቀርቡ አዳዲስ ሀገራት ሂደቱ የተሳለጠ እና ግልጽ የሆነ የጊዜ ሰሌዳን የተከተለ መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። በተጨማሪም በአበዳሪዎች መካከል የተሻለ ቅንጅት እንዲኖር እና ለማማከር አገልግሎት የሚፈጸሙ ክፍያዎች ገና ከጅምሩ ገደብ ሊጣልባቸው እንደሚገባ አሳስበዋል። ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የሉዓላዊ ብድር ውይይት መድረክ ቅድሚያ እንዲሰጥ የምትፈልጋቸውን ጉዳዮችንም አስቀምጠዋል። አይኤምኤፍ እና የዓለም ባንክ እርስ በእርስ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባቸው አመልክተዋል። የብድር ሽግሽግ ካመጠናቀቁ በኋላ የብድር ምዘናቸው በጊዜያዊነት ዝቅ ላለ ሀገራት የተቀመጡ ጠበቅ ያሉ የብድር ማግኛ መስፈርቶችን ማሻሻል እንደሚያስፈልግ አንስተዋል። ሀገራዊ የልማት እቅዶችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመደገፍ የሚሰጡ አዳዲስ የፋይናንስ አቅርቦቶችን በቅንጅት መምራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በሁለቱ ተቋማት ዓመታዊ ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል። ልዑኩ ከስብሰባው ጎን ለጎን የተለያዩ ውይይቶችን በማድረግ ላይ ነው።
ከተሞች ወቅታዊ ፍላጎቶችን ከማሟላት ባለፈ ዘመን ተሻጋሪ ውርስ መተው በሚያስችል መልኩ መገንባት አለባቸው
Oct 14, 2026 164
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 4/2019 (ኢዜአ)፦የከተሞች ልማት ወቅታዊ ፍላጎትን ማሟላት ብቻ ሳይሆን ለወደፊቱ ትውልድ የሚሻገር ዘላቂ ውርስ መተው በሚያስችል መልኩ መገንባት እንዳለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባዋ ይህንን ያሉት በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ከንቲባዊ አመራር ኢኒሼቲቭ (African Mayoral Leadership Initiative) አባል ሀገራት የከተማ ከንቲባዎች ፎረም ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በንግግራቸው፤ አዲስ አበባ የጋራ ታሪክን በማቀናጀትና የወደፊት ተስፋን በመገንባት ላይ እንደምትገኝ ጠቁመዋል። የከተማዋ ገጽታ በቤቶች ልማት፣ በመንገዶች፣ በትራንስፖርት፣ በዲጂታልና በሕዝብ አገልግሎቶች እንዲሁም በማኅበራዊ ልማት ኢንቨስትመንቶች አማካኝነት በከፍተኛ ደረጃ እየተቀየረ መሆኑንም ገልጸዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አርቆ አስተዋይ አመራር የሚመራው የመደመር መንግሥት፤ ጥንካሬን በማቀናጀትና የጋራ ትብብርን በማጠናከር የተሻለና የጎላ ውጤት ለማስመዝገብ ትልቅ መሠረት መጣሉን ተናግረዋል። የወደፊት ዕጣ ፈንታ ከልጆች እንደሚጀምር በመገንዘብ፣ አዲስ አበባን ሕፃናትን ለማሳደግ ከሁሉ የተሻለች የአፍሪካ ከተማ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ እንደሚገኝም አመላክተዋል። ውጤት ተኮር አሠራሮችን በማጠናከር ከፍተኛ ለውጦች መመዝገባቸውንና የከተማዋ የገቢ አቅም በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መምጣቱንም አብራርተዋል። የአፍሪካ ከተሞች እርስ በርስ በመማማር፣ አዳዲስ አሠራሮችንና ሃሳቦችን ወደ አካባቢያዊ እውነታዎች በማላመድ የነዋሪዎችን ሕይወት ማሻሻል እንደሚችሉ የጠቆሙት ከንቲባዋ፤ ሁሉም ከተሞች በዓላማ፣ በራዕይ እና ዘመን ተሻጋሪ ውርስ መተው በሚያስችል መልኩ ሊገነቡ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው በጋና የታማሊ ከተማ ከንቲባ አላጂ አዳም፤ አዲስ አበባ በቅድመ ህጻናት ልማት (ECD) ሥራዎች እያከናወነቻቸው ያሉ ተግባራትን አድንቀው ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ተግባራዊ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡ በማሊ የሊሎንጓይ ከተማ ከንቲባ ሌክስ ባንዳ በበኩላቸው፤ አዲስ አበባ አረንጓዴ ሆናለች፤ ለመኖሪያም ምቹ ሆናለች፤ በዚህም በርካታ ልምድ አግኝቻለሁ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በክልሉ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የማር ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ እያደረገ ነው
Oct 14, 2026 97
ሆሳዕና፤ ጥቅምት 4/2019 (ኢዜአ)፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እየተተገበረ ያለው የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የማር ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕርግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በክልሉ እየተተገበረ ያለው የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የማር ምርትና ምርታማነት በማሳደግ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ እያደረገ ነው። ባለፉት ዓመታት የሌማት ትሩፋት ፕሮግራሙን ተከትሎ የንብ ሀብት ልማቱን ከአረንጓዴ አሻራና ከተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ጋር አቀናጅቶ በተሰራው ስራ በርካታ የንብ መንደሮችን መፈጠር ተችሏል ብለዋል፡፡ በዚህም ከብዝሀ ሕይወት ጥበቃ ስራው በተጨማሪ በርካታ ዜጎችን በንብ ማነብ ሥራ በማሰማራት በዘርፉ ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበ መምጣቱን ጠቁመዋል። ባለፉት ዓመታት በመርሃ ግብሩ በተሰራው ሥራም የክልሉ ዓመታዊ የማር ምርት መጠን ከ3 ሺህ ቶን ወደ 8ሺህ ቶን ለማሳደግ መቻሉንም ሀላፊው አስረድተዋል። በክልሉ የማር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል ምቹ ከባቢያዊ ምህዳር መኖሩን የገለጹት አቶ ኡስማን፣ በማር ምርት በባለፉት ዓመታት የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠል የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ስድስት የአርሶ አደር የማር ማቀነባበሪያ ኢንዱስቱሪዎችን ወደ ተግባር ማስገባት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል። በክልሉ ሀድያ ዞን ሌሞ ወረዳ የታችኛው አምቢቾ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር አለሙ ዳምጠው፤ የንብ ማነብ ስራቸውን ከመደበኛ ግብርና ስራቸው ጎን ለጎን እያስኬዱ መሆናቸውን ተናግረዋል። በዚህም በየዓመቱ እስከ 60 ኪሎ ግራም የማር ምርት ለገበያ በማቅረብ ተጨማሪ ገቢ እያገኙ መሆናቸውን ተናግረዋል። በሌሞ ወረዳ አምቢቾ ጎዴ ቀበሌ የሚኖሩት አርሶ አደር ግርማ አሾሮ በበኩላቸው፤ የአረንጓዴ አሻራ ልማትና የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች በንብ ማነብ ዘርፍ ለተሰማሩ አርሶ አደሮች ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ተናግረዋል። በግብርና ባለሙያ የተደረገላቸው ድጋፍ የንብ ማነብ ሥራቸውን ከባህላዊ ቀፎ ወደ ዘመናዊ ለማሸጋገር እንዳገዛቸውም ጠቁመዋል። ይህም በዓመት እስከ 50 ኪሎ ግራም ማር አምርተው ለገበያ በማቅረብ ተጨማሪ ገቢ በማግኘት ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እንዳስቻላቸው ተናግረዋል፡፡
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና መርሃ ግብር የዲጂታል ዕውቀትና ክህሎታችንን እያዳበረልን ነው
Oct 14, 2026 136
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 4/2019 (ኢዜአ)፦የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና መርሃ ግብር ከመደበኛው ትምህርት በተጨማሪ የዲጂታል ዕውቀትና ክህሎታቸውን እያዳበረላቸው መሆኑን በአዲስ አበባ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ገለጹ። ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ የመደመር መንግሥት በብዝኃ ኢኮኖሚ መርህ ቀርጾ ከተገበራቸው የግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድንና ቱሪዝም ዘርፍ የኢኮኖሚ ዕድገት አዕማዶች መካከል የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ አንዱ ነው። የመደመር መንግሥት የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂም በሁሉም ዘርፍ የዜጎችን የዲጂታል ፈጠራ፣ ዕውቀትና ክህሎት በማበልጸግ የተቋማትን አገልግሎት እያሳለጠ ይገኛል። በአዲስ አበባ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችና ርዕሰ መምህራን ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ በዘርፉ ተወዳዳሪ ዜጋን መገንባት የሚያስችል አቅም እየፈጠረ ነው። የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ከመደበኛው የመማር ማስተማር የትምህርት መርሃ ግብር በተጨማሪ የፈጠራ ዕውቀትና ክህሎታቸውን የሚያሻሽል ምኅዳር እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል። በለም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪ ኤልያስ ለገሰ፤ የትምህርት ቤታቸውን የአይሲቲ ቤተ-ሙከራ በመጠቀም የዲጂታል ዕውቀትና ክህሎቱን እያሳደገ መሆኑን ገልጿል። በዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ መሠረት ተግባራዊ በተደረገው የአምስት ሚሊዮን ኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና መሠረት የፋንዳሜንታል ፕሮግራሚንግ ስልጠና መውሰዱን አስታውቋል። ስልጠናውን መውሰዱም የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎቱን በማስፋት በሌሎች የስልጠና መስኮችን ጭምር ለመከታተል እንዳነሳሳው ተናግሯል። በትምህርት ቤቱ የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሜሮን አጥናው በበኩሏ፤ የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና ተማሪዎች የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎታቸውን ለማሳደግ መልካም ዕድል መፍጠሩን ገልጻለች። በዚህም በአምስት ሚሊዮን የኢትዮ-ኮደርስ የስልጠና መስኮች መካከል የዳታ ሳይንስ ስልጠና በመውሰድ በቀጣይም ሌሎቹን ለመሰልጠን ዕድሉን እንደምትጠቀም ተናግራለች። የኢትዮጵያ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ልማት ስልጠና ከመደበኛ ትምህርት በተጨማሪ የፈጠራ ክህሎታችንን እያሳደገው ነው ያለው ደግሞ በድልበር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ተማሪ አማኑኤል አዳነ ነው። በተለይም ተማሪዎች ባሉበት ቦታ ሁሉ የዲጂታል ክህሎታቸውን የሚያሻሽሉበት መንገድ መኖሩ ተጨማሪ ዕውቀት የሚያገኙበትን ዕድል እንደፈጠረላቸው አንስቷል። በትምህርት ቤቱ የ12ኛ ክፍል ተማሪ በአምላክ ቸርነት በበኩሏ፤ ቴክኖሎጂን ከትምህርቷ ጋር በማዛመድ ዓለም አቀፍ የዲጂታል ተወዳዳሪነቷን ለማጎልበት እየተጠቀመችበት መሆኑን ገልጻለች። የዲጂታል ትምህርት መሠረተ ልማቶችም የማጠናከሪያ ትምህርት አማራጮችን የሚያገኙበት ወሳኝ ዕድል እንደፈጠረላቸውም ተናግራለች። የድልበር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዋና ርዕሰ መምህር ደጀኔ ተስፋዬ፤ ዓለም አቀፍ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ፈጣን ዕድገትን መሠረት በማድረግ የአይሲቲ ቤተ-ሙከራ ተደራጅቶ እየተሰራበት ነው ብለዋል። በዚህም ተማሪዎች የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎታቸውን ማጎልበት የሚችሉበት የመማር ማስተማር የትምህርትና ስልጠና እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የለም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዋና ርዕሰ መምህር ሰለሞን ዲሮ በበኩላቸው፤ በዲጂታል ክህሎት የዳበረ ዜጋ ለማፍራት ተማሪዎች የኢትዮ-ኮደርስና የአይሲቲ ትምህርትና ስልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ ነው ብለዋል።
አምቦ ዩኒቨርሲቲ የተሻሻሉ የሰብልና የእንስሳት ዝርያዎችን ለአርሶ አደሮች በማቅረብ ተጠቃሚ እያደረገ ነው
Oct 13, 2026 343
አምቦ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፡-አምቦ ዩኒቨርሲቲ የተሻሻሉ የሰብል እና የእንስሳት ዝርያዎችን ለአካባቢው ለአርሶ አደሮች በማስተዋወቅና በማቅረብ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያሳድጉ እያገዘ መሆኑን አስታወቀ። በዩኒቨርሲቲው ጉደር ማሞ መዘመር ካምፓስ በምርምር እየተከናወኑ ያሉ የግብርና ሥራዎች በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የግብርና ባለሙያዎች እና ግንባር ቀደም አርሶ አደሮች ዛሬ ተጎብኝቷል። በዚህ ወቅት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ብዙነሽ ሚደቅሳ እንዳሉት፤ ዩኒቨርሲትው ከመማር ማስተማር ሥራው ጎን ለጎን የአካባቢውን ማህብረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ ሳይንሳዊ ምርምሮችን እያከናወነ ይገኛል። በዚህም የተሻሻሉ የሰብል እና የእንስሳት ዝርያዎችን ለአርሶ አደሮች በማስተዋወቅና በማቅረብ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ እያገዘ መሆኑን ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲው በ2018/2019 የምርት ዘመንም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በ73 ሄክታር መሬት ላይ በምርምር የተሻሻሉ የጤፍ፣ ስንዴ፣ የበቆሎ፣ የባቄላ፤ እና የቦሎቄ ዘሮችን እያለማ መሆኑን ተናግረዋል። ለአርሶ አደሩ የተሻሻለ ዝርያ ከማቅረብና ሙያዊ ድጋፍ ከመስጠት በተጨማሪ፣ በእፅዋት በሽታ ቁጥጥር ላይ ተግባር ተኮር ሥልጠና እየሰጠ መሆኑንም አንስተዋል። በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የጉደር ማሞ መዘመር ካምፓስ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር አማን ሪቂቱ በበኩላቸው፤ የመስክ ጉቡኝቱ ዋና ዓላማ የዩኒቨርሲቲው አዳዲስ የምርምር ውጤቶች እና የማሕበረሰብ አገልግሎቶችን ለማስተዋወቅና ተሞክሮ ለመለዋወጥ መሆኑን ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው በምርምር የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ ከመስጠት ባለፈ የሆሮ እና የቦራና የወተት ላሞችን ዝርያ በማዳቀል ለአካባቢው አርሶ አደሮች እያከፋፈለ መሆኑን ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪ በግብርና ባለሙያዎች ሙያዊ ድጋፍ በመስጠት ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እየሰራ ይገኛል ብለዋል። የቶኬ ኩታዬ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ንጌሴ ለሊሣ በበኩላቸው ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ በድጋፍ ያገኙትን የቦሎቄ ምርጥ ዘር በግማሽ የእርሻ ማሳቸው ላይ እያለሙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡ ዩኒቨርሲቲው ምርጥ ዘር ከማቅረብ በተጨማሪ በመዳበሪያ አቅርቦት፣ በሰብል በሽታ ቁጥጥርና መሰል ሙያው እገዛዎችን በመስጠት ምርትና ምርታማነታችን እንዲጨምር እያገዘን ነው ብለዋል። አርሶ አደር ተገኝ በፍቃዱ በዩኒቨርሲቲው ዝርያዋ የተሻሻለ የወተት ላም ድጋፍ እንደተደረገላቸው ገልፀው የወተት ምርታማነታቸውን ለማሳደግ ጠንክረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሜቴዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የሀገሪቱን ልማት የመደገፍ አቅሙን እያሳደገ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Oct 13, 2026 153
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሜቴዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የሀገሪቱን ልማት የመደገፍ አቅሙን እያሳደገ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱን በጎበኙበት ወቅት እንዳሉት፤ እንደ ሜቴዎሮሎጂ ያሉ ተቋማት አቅማቸው መጎልበቱ የአየር ፀባይ ሁኔታ አደጋዎችና ጉዳቶችን አስቀድሞ ለመከላከል ያስችላል። ድርቅ እና የአየር ንብረት ለውጥን የመሳሰሉ ክስተቶችን አስቀድሞ የመተንበይ አቅም ላይ ክፍተቶች እንደነበሩ አውስተዋል። መንግስት ባለፉት ዓመታት ባከናወናቸው የሪፎርም ስራዎች ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን በቅድመ-ማስጠንቀቂያ መልክ ማቅረብ መቻሉ፣ አስፈላጊውን ቅድመ-ዝግጅት በማድረግ ሊደርስ ሚችለውን ጉዳቶችን ለመግታት እንዳስቻለ አመልክተዋል። አስተማማኝ የሜቴዎሮሎጂ መረጃዎችን ወደ ተግባራዊ መመሪያዎች መቀየር የዜጎችን ሕይወት ከማዳን ባለፈ ሀገራዊ ሀብትን የመጠበቅ እና በመረጃ የተደገፈ ውሳኔ የመስጠት አቅምን እንደሚያጎለብትም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት። በተለይም በግብርናው ዘርፍ የሚሰጡ የትንበያ መረጃዎች የእርሻ ጊዜን ለማፋጠን ወይም ለማዘግየት፣ ተስማሚ የዘር ዓይነቶችን ለመምረጥ እና የማዳበሪያ አጠቃቀምን አስቀድሞ ለመወሰን መልካም አጋጣሚ መፍጠራቸውን ተናግረዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ባለፉት ስምንት ዓመታት የተከናወነው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከሜቴዎሮሎጂ መረጃዎች ጋር በማቀናጀት በመካሄዱ የተሻለ ውጤት መገኘቱን ተናግረዋል። ችግኞች የንፋስ ግፊትን በመመከት፣ ዝናብ በመሳብ እና የጎርፍ አደጋን በመቀነስ ረገድ የሚጫወቱትን ሚና ተቋሙ ሳይንሳዊ በሆነ ዳታ መደገፉን አመልክተዋል። የኢንስቲትዩቱ ድጋፍ ለብዙ ዘርፎች ጠቀሜታ ያለውና የውሳኔ መስጠት አቅምና ዝግጁነትን የሚያጠናክር እንደሆነም ነው ያብራሩት። ዘርፎችን በውጤታማነት ለመምራት አስተማማኝ ዳታ ማግኘት ወሳኝ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የተቋሙን አቅም የበለጠ ማጠናከር ወሳኝ መሆኑንም አንስተዋል። በአሁኑ ወቅት ተቋሙ ከሳተላይት ምልከታ ባሻገር በመላ ሀገሪቱ ባስቀመጣቸው የዳታ ማዕከላት እና የመረጃ መሰብሰቢያ ጣቢያዎች አማካይነት መረጃዎችን በወቅቱ በመሰብሰብ፣ በማቀናጀት እና በጥልቀት በመተንተን ለአገልግሎት ማብቃት የሚችልበት አስተማማኝ ደረጃ ላይ መድረሱን አመልክተዋል። የተቋሙ ስራዎች ብልጽግናን ለማረጋገጥ የተያዘውን ውጥን ለማሳካት ወሳኝ ሚና እንደሚወጣም አንስተዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ደረጃ የጎላ እና የሚያኮራ የሜቴዎሮሎጂ አቅም ባለቤት መሆኗን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ወደፊት የራሷን ሳተላይት ተጠቅማ መረጃዎችን በቀጥታ ከሳተላይቱ የምታስተሳስርበትን መንገድ ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል። አንጋፋው ተቋም አሁን ያለበትን ደረጃ ተማሪዎች፣ ተመራማሪዎች እና ወጣቶች እንዲጎበኙና ትምህርት እንዲወስዱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልእክት አስተላልፈዋል።
ማዕከሉ አዳዲስ የሰብል ዝርያዎችን በማላመድ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየሰራ ነው
Oct 13, 2026 192
አሶሳ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦የአሶሳ ግብርና ምርምር ማዕከል የአካባቢውን ስነ-ምህዳር የሚላመዱ አዳዲስ የሰብል ዝርያዎችን በማውጣት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማላቅ እየሰራ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ ገለጸ። የአሶሳ ግብርና ምርምር ማዕከል በኩርሙክ ወረዳ አጉቤላ ቀበሌ እያለማ የሚገኘው የሰሊጥ ሰብል ልማት የመስክ ምልከታ ተካሄዷል። በምልከታው ላይ የተገኙት የቢሮው ኃላፊ አቶ ባበክር ሀሊፋ እንደተናገሩት፤ በክልሉ በምርምር የተረጋገጡ አዳዲስ የሰብል ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ በማቅረብ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሠራ ይገኛል። የአሶሳ ግብርና ምርምር ማዕከል በማሽላ፣ በበቆሎ እና በተለያዩ የቅባት እህሎች የሚያወጣቸውን የምርምር ውጤቶች በአሁኑ ሰዓት አርሶ አደሩ በስፋት እየተጠቀመባቸው መሆኑንም ገልጸዋል። በኩርሙክ ወረዳ እየለማ የሚገኘው የሰሊጥ ዝርያ ምርትና ምርታማነቱ የተረጋገጠ እንዲሁም የአካባቢውን ሥነ ምሕዳር መላመድ የሚችል መሆኑን በተግባር ያሳየ ነው ብለዋል። ይህም አርሶ አደሩ በግብርና ሥራ ተሳታፊ እንዲሆንና በክልሉ የቅባት እህሎችን ምርታማነት ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቁመዋል። የአሶሳ ግብርና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ደስታ በቀለ በበኩላቸው፤ ማዕከሉ በየጊዜው የሚያወጣቸው የምርምር ሥራዎች ከምርታማነታቸው በተጨማሪ የአርሶ አደሩን ጉልበት እና ወጪ የሚቆጥቡ መሆናቸውን ተናግረዋል። በኩርሙክ ወረዳ እየለማ የሚገኘው የሰሊጥ ሰብል ቁመና በቀጣይ አርሶ አደሩ በስፋት እንዲያለማ የሚያደርግና ተባይን መቋቋም የሚችል መሆኑንም አስረድተዋል።
ስፖርት
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለግማሽ ፍጻሜ አለፈ
Oct 14, 2026 93
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 4/2019 (ኢዜአ)፦ በ17ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ተጠባቂ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ከዩጋንዳ ጋር አቻ ተለያየች። ማምሻውን በኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ተቀይሮ የገባው ዘሚካኤል ምንያህል በ71ኛው ደቂቃ ኢትዮጵያን መሪ አድርጓል። ዘሚካኤል በውድድሩ ላይ ሁለተኛ ግቡን አስቆጥሯል። አርኖልድ ካዬምባ በ78ኛው ደቂቃ ዩጋንዳን አቻ አድርጓል። ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት በአራት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ ምርጥ ሁለተኛ ሆና ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች። ኢትዮጵያ ምርጥ ሁለተኛ የሆነችው በምድብ ሶስት በተመሳሳይ አራት ነጥብ ያላትን ታንዛንያን በግብ ክፍያ በመብለጧ ምክንያት ነው። የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ሶስት የግብ ክፍያ፣ የታንዛንያ አቻው ሁለት ግብ ክፍያ አላቸው። የግማሽ ፍጻሜ መርሐ ግብር ቅዳሜ ጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ.ም ይካሄዳል። የማጣሪያ ውድድሩ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ይቆያል። በውድድሩ ከአንድ እስከ ሶስት የሚወጡ ሀገራት ሴካፋ ዞንን ወክለው በአፍሪካ ዋንጫ ይሳተፋሉ። 17ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ በ2027 በሞሮኮ አስተናጋጅነት ይካሄዳል። በውድድሩ ላይ 16 ሀገራት ይሳተፋሉ።
ኢትዮጵያ ከዩጋንዳ - ተጠባቂው የሴካፋ ማጣሪያ ጨዋታ
Oct 14, 2026 104
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 4 /2019 (ኢዜአ)፦ በ17ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ኢትዮጵያ ከዩጋንዳ ጋር ዛሬ ጨዋታዋን ታደርጋለች። የሁለቱ ሀገራት የምድብ ሁለት መርሐ ግብር ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ በኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም ይካሄዳል። ኢትዮጵያ ከትናንት በስቲያ ከብሩንዲ ጋር ባደረገችው የምድቡ የመጀመሪያ ጨዋታ 3 ለ 0 አሸንፋለች። ዘሚካኤል ምንያህል፣ አክረም አብዱሰላም እና አብዲሳ ጉተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ዩጋንዳ በመጀመሪያ ጨዋታዋ ብሩንዲን 8 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፋለች። በአሜሪካዊው አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር የሚመራው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተጋጣሚውን ካሸነፈ ወደ ግማሽ ፍጻሜው በቀጥታ ያልፋል። የአቻ ውጤት ብሔራዊ ቡድኑን በምርጥ ሁለተኝነት ወደ ግማሽ ፍጻሜ ማለፍ የሚችልበት እድል አለ። በጋናዊው ላሪስ ኪንግስተን የሚሰለጥነው የዩጋንዳ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ማሸነፍ ወይም አቻ መውጣት በቀጥታ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ያሳልፈዋል። ጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር ይታይበታል ተብሎ ይጠበቃል። በምድብ አንድ አዘጋጇ ሩዋን ከሱዳን ጋር ምሽት አንድ ሰዓት ላይ ጨዋታን ታደርጋለች። በሌላኛው መርሐ ግብር ሶማሊያ ከኬንያ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። የማጣሪያ ውድድሩ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ይቆያል። በውድድሩ ከአንድ እስከ ሶስት የሚወጡ ሀገራት ሴካፋ ዞንን ወክለው በአፍሪካ ዋንጫ ይሳተፋሉ። 17ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ በ2027 በሞሮኮ አስተናጋጅነት ይካሄዳል። በውድድሩ ላይ 16 ሀገራት ይሳተፋሉ።
ማንችስተር ሲቲ ከፒኤስጂ እና ሮማ ከሪያል ማድሪድ : የሻምፒዮንስ ሊጉ ተጠባቂ መርሐ ግብሮች
Oct 14, 2026 93
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 4/2019 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሊግ ምዕራፍ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይካሄዳሉ። ምሽት አራት ሰዓት ላይ ማንችስተር ሲቲ ከፒኤስጂ በኢትሃድ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ የእግር ኳስ አፍቃሪያንን ቀልብ ስቧል። ማንችስተር ሲቲ በመጀመሪያ ጨዋታው ፖርቶን 2 ለ 0 ረትቷል። የባለፉት ሁለት የሻምፒዮንስ ሊግ ውድድሮች አሸናፊው የፈረንሳዩ ፒኤስጂ ስሎቫን ብራቲስላቫን 6 ለ 1 ረምርሟል። ሁለቱ ክለቦች በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሲገናኙ የአሁኑ ለስምንተኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው ሰባት ጨዋታዎች ሲቲ በአራቱ ድል ሲቀናው ፒኤስጂ ሁለት ጊዜ አሸንፏል። በቀሪው አንድ ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል። በሰባቱ ጨዋታዎች ላይ ማንችስተር ሲቲ 11 ግቦችን ሲያስቆጥር ፒኤስጂ 10 ጎሎችን ከመረብ ላይ አሳርፏል። ቡድኖቹ ለመጨረሻ ጊዜ እ.አ.አ በ2024/25 የውድድር ዓመት በተገናኙበት ጨዋታ ፒኤስጂ 4 ለ 2 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። ጨዋታው ጠንካራ ፉክክር ይታይበታል ተብሎ ይጠበቃል። ሮማ እና ሪያል ማድሪድ ምሽት አራት ሰዓት ላይ በስታዲዮ ኦሊምፒኮ የሚያደርጉት ጨዋታም ትኩረትን ስቧል። የጣልያኑ ክለብ በመጀመሪያ ጨዋታው ከፊነርባቼ ጋር አንድ አቻ ተለያይቷል። የ15 ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ሪያል ማድሪድ በበኩሉ ኢንተር ሚላንን በሜዳው አስተናግዶ 2 ለ 1 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። ክለቦቹ በሻምፒዮንስ ሊጉ ከዚህ ቀደም ካደረጓቸው 12 ጨዋታዎች ማድሪድ ስምንቱን በማሸነፍ የበላይነቱን ይዟል። ሮማ ሶስት ጊዜ ሲያሸንፍ በቀሪው ጨዋታ ነጥብ ተጋርተዋል። ለመጨረሻ ጊዜ በተገናኙበት የእ.አ.አ 2018/19 የውድድር ዓመት የምድብ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ 2 ለ 0 አሸንፏል። በሌሎች መርሐ ግብሮች ላስክ ከሊቨርፑል እና ፌይኖርድ ከኮሞ በተመሳሳይ ምሽት 1 ሰዓት ከ45 ላይ ይጫወታሉ። አስቶንቪላ ከፊነርባቼ፣ ቦዶ ግሊምት ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ፣ ሪያል ቤቲስ ከፖርቶ፣ ስሎቫን ብራቲስላቫ ከስቱትጋርት እና ሻካታር ዶኔስክ ከኤኢኬ አቴንስ በተመሳሳይ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
አርሰናል እና ባርሴሎና ድል ሲቀናቸው ማንችስተር ዩናይትድ ሽንፈት አስተናግዷል
Oct 14, 2026 116
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 4/2019 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ማምሻውን ተካሄደዋል። ማምሻውን በኤምሬትስ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አርሰናል ሊልን 3 ለ 0 አሸንፏል። ጁሪየን ቲምበር፣ ኤበሬቺ ኤዜ እና ቡካዮ ሳካ ግቦቹን አስቆጥረዋል። የባለፈው ዓመት የፍጻሜ ተፋላሚ አርሰናል ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል። በሌላኛው መርሐ ግብር ባርሴሎና ጋላታሳራይን 4 ለ 1 ረትቷል። በራምስ ፓርክ በተደረገው ጨዋታ ጆአኦ ካንሴሎ፣ ፌርሚን ሎፔዝ፣ አንቶኒ ጎርደን እና ካሪም አዲዬሚ ግቦቹን ከመረብ ላይ አገናኝተዋል። አሌክሲ ባትራኮቭ ለጋላታሳራይ ጎሉን አስቆጥሯል። ባርሴሎና ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል። አትሌቲኮ ማድሪድ ማንችስተር ዩናይትድን 2 ለ 0 ረትቷል። በዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ በተካሄደው ጨዋታ ፓብሎ ባሪዮስ እና አዴሞላ ሉክማን ግቦቹን አስቆጥረዋል። የማንችስተር ዩናይትዱ ሌኒ ዮሮ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል። የማድሪዱ ክለብ የመጀመሪያ ደሉን ሲያስመዘግብ ዩናይትድ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናግዷል። ባየር ሙኒክ ከቫይኪንግ ሶስት አቻ ተለያይቷል። ሃሪ ኬን በጨዋታ እና በፍጹም ቅጣት ምት ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ሉዊስ ዲያዝ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። ጂያኒ ስቴንነስ፣ ፒተር ክርስቲያንሰን እና ሄርማን ሀውገን ለኖርዌው ክለብ ግቦቹን አስቆጥረዋል። የባየር ሙኒኩ ኮከብ ማይክል ኦሊሴ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። በሌሎች መርሐ ግብሮች ክለብ ብሩዥ ኢንተር ሚላንን 4 ለ 3፣ ቪያሪያል ናፖሊን 3 ለ 1 እና አርቢ ላይፕዚግ ፒኤስቪ አይንድሆቨንን 1 ለ 0 አሸንፈዋል። ዛሬ አስቀድመው በተደረጉ ጨዋታዎች ስፖርቲንግ ሊዝበን ሌንስን እና ሳባህ ስላቪያ ፕራግን በተመሳሳይ 2 ለ 0 አሸንፈዋል።
አካባቢ ጥበቃ
ኢትዮጵያና ዴንማርክ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ትብብራቸውን እንደሚያጠናክሩ ገለጹ
Oct 14, 2026 108
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 4/2019 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ እና ዴንማርክ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያላቸውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን በገንዘብ ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ሱኔ ክሮግስትሩፕ ፈርመዋል። በተደረገው ስምምነት መሰረት ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ያሏትን ቅድመ አጀንዳዎችና የትኩረት አቅጣጫዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅና ለማሳየት የሚያስችላትን የገንዘብ ድጋፍ ዴንማርክ እንደምታቀርብ ተመላክቷል። ይህ አዲስ ስምምነት ዴንማርክ ቀደም ሲል ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ሁነቶች ላይ ስታደርግ የቆየችውን ንቁ ተሳትፎ መሰረት በማድረግ የተፈጸመ ሲሆን የሁለቱን ሀገራት ዘላቂ የወደፊት ወዳጅነትና አጋርነት የበለጠ እንደሚያጠናክርም ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ለሀገሪቱ ልማትና አቅም ወሳኝ ሥራዎችን የሚያከናውን የረጅም ዘመን እድሜ ያለው ተቋም ነው
Oct 13, 2026 148
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የተሟላ የአየር ትንበያ አገልግሎት በመስጠት ለሀገሪቱ ልማትና አቅም ወሳኝ ሥራዎችን የሚያከናውን የረጅም ዘመን እድሜ ያለው ተቋም ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል፡፡ ጉብኝታቸውን አስመልክተው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ተቋሙ የተሟላ የአየር ትንበያ አገልግሎት በመስጠት ለሀገሪቱ ልማትና አቅም ወሳኝ ሥራዎችን የሚያከናውን የረጅም ዘመን እድሜ ያለው ተቋም ነው ብለዋል። ጉብኝቱ እየተለዋወጠ ያለውን የአየር ፀባይና የአየር ንብረት ሁኔታዎችን ለመረዳት እና ምላሽ ለመስጠት ያለንን አቅም ለማጠናከር ሚቲዎሮሎጂያዊ መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የሳይንሳዊ ምርምር እና የቴክኖሎጂ ዕድገት ያለውን የላቀ ጠቀሜታ ያረጋገጠ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ሲሉም ገልጸዋል። እንደ ኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ያሉ ተቋማትን ማጠናከር እጅግ አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል። ግብርና፣ ውሃ፣ ጤና፣ አቪዬሽን እና የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራርን ጨምሮ ቁልፍ ዘርፎች የሚደገፉባቸውን አገልግሎቶች ለማሻሻል በሰው ኃይል አቅም ግንባታ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እና በመረጃ መሠረተ-ልማት ላይ መዋዕለ-ንዋይ ማፍሰስ ወሳኝ ነውም ብለዋል። በተለይም አደጋዎችን አስቀድሞ ለመተንበይ፣ የትኞቹ አካባቢዎች ላይ ጣልቃ ገብነት ይበልጥ እንደሚያስፈልግ ለመወሰን፣ እንዲሁም ወቅታዊና ውጤታማ በሆነ መንገድ እንድንንቀሳቀስ ለማድረግ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶች ያላቸው ጠቀሜታ አበረታቶኛል ሲሉም ገልጸዋል። አስተማማኝ መረጃ ወደ ተግባራዊ መመሪያዎች ሲቀየር ሕይወትን ይታደጋል፣ ሐብትን ይጠብቃል፣ እንዲሁም የተሻለ ውሳኔ ለመስጠት ያግዛል ብለዋል።
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚያስችል አረንጓዴ ኢኮኖሚ እየገነባች ነው
Oct 12, 2026 115
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2 /2019 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚያስችል አረንጓዴ ኢኮኖሚ እየገነባች መሆኗን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ከ192 አባል ሀገራት የመጡ ሳይንቲስቶች፣ ውሳኔ ሰጪዎች፣ የሚቲዎሮሎጂ ባለሙያዎች እና የዘርፉ ተመራማሪዎች የተገኙበትንና ከጥቅምት 2 እስከ 6 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆየውን ዓለም አቀፍ ፎረም ማካሄድ ጀምሯል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን መቋቋም የሚያስችል የአረንጓዴ ኢኮኖሚ አቅም እየገነባች ነው። በዚህም መንግሥት የአየር ንብረት ተለዋዋጭነትን የሚቋቋም አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂን በመተግበር የታዳሽ ኃይል ምንጮችን እያስፋፋ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አመራር የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የሀገሪቱን የደን ሽፋን ከ17 ነጥብ 2 በመቶ ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ማሳደጉንም አመልክተዋል። የዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ መንግሥታት አቀፍ ባለሙያዎች ፓናል ሰባተኛው የግምገማ ሪፖርት ውስጥ ለፖሊሲ አውጪዎች ተግባራዊ መፍትሔዎች እንዲቀርቡ፣ በታዳጊ ሀገራት ያሉ የመረጃ ክፍተቶች እንዲሞሉና የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነትን በትክክል ለመለየት እንዲረዳ ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፈጠነ ተሾመ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በአፍሪካ ድርቅ፣ ጎርፍ፣ የሙቀት መጨመርና የዝናብ ሁኔታ መለዋወጥ እየተባባሱ ነው ብለዋል። አህጉሪቱ ለዓለም አቀፍ የግሪንሃውስ ጋዝ ልቀት ያላት አስተዋጽኦ እጅግ አነስተኛ ቢሆንም፤ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎች ግን ከፍተኛ ተጋላጭ መሆኗን አስረድተዋል። ለዚህም የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶችን፣ የአየር ንብረት መረጃ አገልግሎቶችን፣ የምልከታ መረቦችንና የምርምር አቅሞችን ማሳደግ የሕብረተሰቡን ሕይወት ለመታደግና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በኢንስቲትዩቱ አማካይነት የአየር ሁኔታና የአየር ንብረት ምልከታ መረቦችን በማስፋፋት፣ የትንበያ አገልግሎቶችን በማሻሻል እንዲሁም የአየር ንብረት ምርምርን በመደገፍ ለቀጣናዊና ዓለም አቀፍ ትብብሮች የላቀ አስተዋጽኦ እያደረገች መሆኑን ጠቁመዋል። የዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ መንግሥታት አቀፍ ባለሙያዎች ፓናል ሪፖርቶች ለመንግሥታት፣ ለተመራማሪዎችና ለልማት አጋሮች የአየር ንብረት ስጋቶችን በትክክል ለመረዳትና ውጤታማ ምላሾችን ለማዘጋጀት ጠቃሚ መሠረት እንደሚሆኑ ገልጸዋል። በሰባተኛው የግምገማ ዙር የሚካሄዱ ውይይቶች ሳይንሳዊ ግኝቶችን ለፖሊሲ አውጪዎችና ለማኅበረሰቡ የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያግዙ ተናግረዋል።
አረንጓዴ ዐሻራ የኢትዮጵያን የደን ሽፋን በማሳደግ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ትሩፋት እያስገኘ ነው
Oct 9, 2026 283
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን የደን ሽፋን በማሳደግ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ትሩፋት እያስገኘ መሆኑን የኢትዮጵያ ደን ልማት ገለጸ። ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ የመደመር መንግሥት ምሥረታ እና ሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ሥነ ሥርዓት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ተካሂዷል። በዚህም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ለቀጣይ አምስት ዓመታት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት፤ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የተተከሉት 56 ቢሊዮን ችግኞች የተራቆቱ መሬቶችን በማገገም ጉልህ ፋይዳ እያስገኙ መሆኑን ገልጸዋል። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብሩም የግብርና ምርታማነትን በማገዝ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ ያስገኘ ዓለም አቀፍ ተነሳሽነት ነው። በኢትዮጵያ ደን ልማት የተፈጥሮ ደን መሪ ሥራ አስፈጻሚ ካብታሙ ግርማ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ደን የአካባቢ መራቆትና የሥነ-ምኅዳር ደህንነትን በመጠበቅ ለግብርና ምርታማነት ጉልህ ጠቀሜታ አለው። የደን ሽፋን ዕድገትም አየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን በመቀነስ ብርቅዬ እንስሳትና የብዝኅ ሕይወት ደኅንነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንደሚኖረው ገልጸዋል። የመደመር መንግሥት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ለደን ልማት የሰጠው ትኩረት የአካባቢ ተጽዕኖ ውጤታማነትን በማሻሻል ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ተናግረዋል። ይህም ዜጎች በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ተያያዥ የልማት መስኮች የሚሰማሩበትን ዕድል በመፍጠር ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፋይዳ እያስገኘ መሆኑን አንስተዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጭነት በ2011 ዓ.ም. የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራም 17 ነጥብ 2 በመቶ የነበረውን ደን ሽፋን ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ማሳደጉን አስታውሰዋል። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የደን ጥበቃ ውጤታማነትን በማላቅ የተስተካከለ ሥነ-ምኅዳርና የብዝኅ ሕይወት እንዲፈጠር እያደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። በተለይም የተራቆቱ አካባቢዎች እንዲያገግሙ በማድረግ ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ እፅዋት ልማትን በማስፋፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ መሠረት እየጣለ መሆኑን አብራርተዋል። የህብረተሰቡን የደን ጥበቃና እንክብካቤ ባህል በማሻሻል የደን አስተዳደር ሥርዓት ውጤታማነትን ማሳደግ የሚያስችል አቅም መፈጠሩንም አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ደን ልማትም የተራቆቱ አካባቢዎች እንዲያገግሙ፣ የደን ሀብት በዘላቂነት እንዲጠበቅና እንዲለማ የሚያስችል ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ አንስተዋል። በተጨማሪም የደን ውጤቶች ምርታማነትን በማሻሻል የደን ሀብት ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ተጠቃሚነትን በማላቅ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የዓለም አቀፍ የብድር ሽግሽግ አሰራር ፈጣንና ግልጽ የጊዜ ሰሌዳ ሊኖረው ይገባል - ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)
Oct 14, 2026 109
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 4/2019 (ኢዜአ)፦ የዓለም አቀፍ የብድር ሽግሽግ አሰራር ፈጣንና ግልጽ የጊዜ ሰሌዳ ሊኖረው እንደሚገባ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ገለጹ። የ2026 የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና የዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ በታይላንድ ባንኮክ እየተካሄደ ነው። ከዓመታዊው ስብሰባ ጎን ለጎን የዓለም አቀፍ የሉዓላዊ ብድር ውይይት ተደርጓል። በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የብድር ሽግሽግ ተሞክሮዎችን እና ልምዶችን አቅርበዋል። የብድር ማቃለያ ጥያቄ ለሚያቀርቡ አዳዲስ ሀገራት ሂደቱ የተሳለጠ እና ግልጽ የሆነ የጊዜ ሰሌዳን የተከተለ መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። በተጨማሪም በአበዳሪዎች መካከል የተሻለ ቅንጅት እንዲኖር እና ለማማከር አገልግሎት የሚፈጸሙ ክፍያዎች ገና ከጅምሩ ገደብ ሊጣልባቸው እንደሚገባ አሳስበዋል። ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የሉዓላዊ ብድር ውይይት መድረክ ቅድሚያ እንዲሰጥ የምትፈልጋቸውን ጉዳዮችንም አስቀምጠዋል። አይኤምኤፍ እና የዓለም ባንክ እርስ በእርስ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባቸው አመልክተዋል። የብድር ሽግሽግ ካመጠናቀቁ በኋላ የብድር ምዘናቸው በጊዜያዊነት ዝቅ ላለ ሀገራት የተቀመጡ ጠበቅ ያሉ የብድር ማግኛ መስፈርቶችን ማሻሻል እንደሚያስፈልግ አንስተዋል። ሀገራዊ የልማት እቅዶችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመደገፍ የሚሰጡ አዳዲስ የፋይናንስ አቅርቦቶችን በቅንጅት መምራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በሁለቱ ተቋማት ዓመታዊ ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል። ልዑኩ ከስብሰባው ጎን ለጎን የተለያዩ ውይይቶችን በማድረግ ላይ ነው።
ኢትዮጵያ ሰፊ የኢንቨስትመንት እድሎች ያሏት ሀገር ናት - በኢትዮጵያ የሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር አብደላ ቢን ሀሰን አል-ዛህራኒ
Oct 13, 2026 107
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ሰፊ የኢንቨስትመንት እድሎችና አማራጮች ያሏት ሀገር መሆኗን በኢትዮጵያ የሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር አብደላ ቢን ሀሰን አል-ዛህራኒ ገለጹ። በኢትዮጵያ እና በሳዑዲ ዓረቢያ መካከል ያለው ወዳጅነት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በኢንቨስትመንት እና በቱሪዝም ዘርፎች በከፍተኛ ሁኔታ እየጎለበተ መምጣቱን አምባሳደሩ ከኢዜአ ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል። የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ለግንኙነቱ ማደግ ያላቸው ቁርጠኝነት እና የጉብኝት ልውውጦች የትብብር መስኮችን በማስፋት ለአዲስ ስትራቴጂካዊ አጋርነት በር መክፈቱን አመልክተዋል። በቅርብ ወራት በሪያድ እና በአዲስ አበባ መካከል የተደረጉ ጉብኝቶች የሁለቱን ሀገራት የኢኮኖሚና የኢንቨስትመንት ትስስር ወደ አዲስ ምዕራፍ ማሸጋገሩን ተናግረዋል። በዚህም ኢኮኖሚን ጨምሮ የሁለቱን ሀገራትና ህዝቦች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስምምነቶችን ለማጠናቀቅ ሰፊ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ ነው ያሉት። የንግድና የኢንቨስትመንት ልውውጡን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የሁለቱ ሀገራት ኤምባሲዎች የንግድ አጋርነትን በማስፋፋት ረገድ የጎላ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም የግል ባለሀብቶችንና በኢንቨስትመንት ዘርፍ ፍላጎት ያላቸውን አካላት ያሰባሰበ የሳዑዲ-ኢትዮጵያ የቢዝነስ ካውንስል ተቋቁሟል። ይህ የቢዝነስ ካውንስል ባለፉት ወራት በርካታ ስብሰባዎችን ያካሄደ ሲሆን፣ በቅርቡም ሌላ ስብሰባ በማካሄድ በሁለቱ ሀገራት የንግድ ማህበረሰብ መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከርና አዳዲስ የኢንቨስትመንት እድሎችን ለመዳሰስ አቅዷል። ስለ ሁለትዮሽ የንግድ ልውውጥ መጠን ማብራሪያ የሰጡት አምባሳደሩ፤ እአአ በ2025 ሳዑዲ ዓረቢያ ከኢትዮጵያ ያስገባችው የወጪ ንግድ መጠን ወደ ሁለት ቢሊዮን የሳዑዲ ሪያል መጠጋቱን ገልጸዋል። ከዚህ ውስጥ የኢትዮጵያ ቡና 80 በመቶ ድርሻ የሚይዝ ሲሆን፣ ከሳዑዲ ወደ ኢትዮጵያ የተላከው ምርት ደግሞ 184 ሚሊዮን ሪያል መድረሱንም ነው የጠቆሙት። ሁለቱ ሀገራት የንግድ ልውውጡን የበለጠ ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላቸው የጠቆሙት አምባሳደሩ ይህን ለማድረግ የሚያስችል ሰፊ አቅም እንዳለ አንስተዋል። ኢትዮጵያ ያልተነካ ሰፊ ሀብት ያላት መሆኗን ገልጸው፤ የሳዑዲ አረቢያ ባለሀብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ የሚችሉባቸው እድሎች መኖራቸውን አንስተዋል። አምባሳደሩ በማዕድን፣ በእርሻ፣ በቱሪዝም እና በውሃ ሀብት ዘርፎች ላይ ሳዑዲ ዓረቢያ አስፈላጊውን የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ አብራ ለመስራት ዝግጁ መሆኗንም አረጋግጠዋል።
አይኤምኤፍ ከገንዘብ ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚፈልግ ገለጸ
Oct 13, 2026 129
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ከገንዘብ ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጋር ያለውን የትብብር አድማስ ማስፋት እንደሚፈልግ አስታወቀ። የ2026 የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና የዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ በታይላንድ ባንኮክ እየተካሄደ ነው። የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከስብሰባው ጎን ለጎን ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የፊሲካል ጉዳዮች ክፍል እና ከገንዘብና ካፒታል ገበያዎች የስራ ክፍል ጋር የሁለትዮሽ ውይይቶችን አድርጓል። ከአይኤምፊ ፊስካል ጉዳዮች ዘርፍ ጋር በተካሄደው ውይይት፣ ለገንዘብ ሚኒስቴር በሚደረጉ የአቅም ግንባታ ሥራዎች ላይ ትኩረቱን አድርጓል። ድርጅቱ ለሚኒስቴሩ እየሰጠ የሚገኘውን የቴክኒክ ድጋፍ አፈጻጸም ተገምግሟል። በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሪፎርም አጀንዳዎች መሠረት በቀጣይ ተጨማሪ ድጋፍ የሚደረግባቸውን ዕድሎችና የትብብር መስኮች ላይ ምክክር ተደርጓል። በተያያዘም፣ ከተቋሙ የገንዘብና ካፒታል ገበያዎች የስራ ክፍል ጋር በተካሄደው ውይይት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሚሰጡ የአቅም ግንባታ ድጋፎች ላይ ያተኮረ ነው። ውይይቱ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት በኩል ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እየተደረገ ያለውን የቴክኒክ ድጋፍ ያካተተ ነው። የተቋሙን የማስፈጸም አቅም የበለጠ ለማጠናከርና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የጀመረውን የሪፎርም አጀንዳ ለማጠናከር የሚያስችሉ ተጨማሪ የድጋፍ መስኮችን የመለየት ሥራ ተከናውኗል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የተመራው ልዑክ ከስብሰባው ጎን ለጎን የተለያዩ ውይይቶችን እያደረገ ይገኛል።
የአፍሪካ ህብረት እና ተመድ ያላቸውን የጋራ ውጥኖች በቁርጠኝነት ለመተግበር እንደሚሰሩ ገለጹ
Sep 21, 2026 1167
አዲስ አበባ፤ መስከረም 10/2019 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ ኢኮኖሚና ፍትሃዊ ዓለምን ለማስፈን በጋራ እያከናወኑ የሚገኘውን ስራ ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከመስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም አንስቶ በኒው ዮርክ እየተካሄደ ይገኛል። “መተማመንን ዳግም መገንባት እና አዳዲስ ለውጦችን በአግባቡ መምራት፣ ለሁሉም የሚሰራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን መፍጠር” የጉባኤው መሪ ሀሳብ ነው። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በጉባኤው ላይ ለመታደም ኒው ዮርክ ይገኛሉ። ከጠቅላላ ጉባኤው ጎን ለጎን ስትራቴጂካዊ ትብብር ማጎልበት፣ የሰላምና ደህንነት ማዕቀፎችን ማጠናከርና አፍሪካን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ሪፎርሞች ላይ ያተኮረ ከፍተኛ የምክክር መድረክ ተካሄዷል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ መድረኩን በጋራ መርተውታል። ስብስባው ሁለቱ ተቋማት አፍሪካ መዋቅራዊ ፈተናዎችን ለመፍታት እያደረገች ያለቻቸውን ጥረቶች ለመደገፍና ፍትሃዊ የዓለም ስርዓትን ለመፍጠር ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ይበልጥ ያረጋገጠ መሆኑን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። የዓለም አቀፍ የፋይናንስ አወቃቀርን ማሻሻል፣ ዘላቂ የእዳ አስተዳደር እና የአፍሪካ ሀገራት ከቁልፍ የማዕድን ሀብቶች ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ ውይይት ከተደረገባቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ሁለቱ ወገኖች በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ህብረት እና የተመድን ትብብር ያለውን ስትራቴጂካዊ ፋይዳ አጽንኦት ሰጥተዋል። የተቋማቱ ሶስት ነባር የትብብር ማዕቀፎች በአዲስ መልክ ለማደስ እና እ.አ.አ በ2026 ትግበራው የሚጠናቀቀውን የጋራ ፍኖተ ካርታ የተፈጻሚነት ገደብ ለማራዘም መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ያሉ የሰላም እና የደህንነት ተግዳሮቶችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የአፍሪካ ህብረት ቁልፍ አጋር ሆኖ እንደሚቀጥል ዳግም አረጋግጧል። የአፍሪካን የሰላምና ደህንነት መዋቅር ማጠናከር፣ ግጭትን አስቀድሞ የመከላከል ዲፕሎማሲና የእርቅ ሂደትን በሚገባ መተግበርና ለአፍሪካ ፈተናዎች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ማረጋገጥ የሚያስችል በቂ አቅም መገንባት እንደሚያስፈልግ በስብሰባው ላይ ተነስቷል። በውይይቱ በሳሄል ቀጠና፣ በሊቢያ፣ በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያሉ ወቅታዊ ጉዳዮችና የሰላም ጥረቶች ተገምግመዋል። በስብስባው ላይ ግጭቶች፣ በዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ የተፈጠሩ መስተጓጎሎች እና የባህር በር መስመሮችን መዝጋትን ጨምሮ ሌሎች ውጫዊ ሁኔታዎች በአፍሪካ ኢኮኖሚ እና ምግብ ዋስትና ላይ ተጨማሪ ጫና እየፈጠሩ መሆኑ ተነስቷል። የአየር ንብረት ለውጥ እያደረሰ ያለው ጉዳትም ምክክር ተደርጎበታል። ሁለቱ ወገኖች በውይይቶች ጠንካራ የጋራ ግብረ መልስ መስጫ ማዕቀፍ ለመፍጠር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። የአፍሪካ ህብረት እና ተመድ ፍኖተ ካርታ ዝግጅን ለማጠናቀቅ፣ በአፍሪካ ሀገራት የሰላም ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር፣ የምግብ ዋስትና ተግዳሮቶችን ለመፍታትና ለድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ የአሰራር ማዕቀፎችን ለመቅረጽ በቅርበት እንደሚሰሩ መግለጻቸውን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ እስከ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።
ሐተታዎች
የድል ከፍታን በሞራል ልዕልና ያጀበ ሕዝባዊ ሠራዊት
Oct 14, 2026 87
ትልቅ ሀገር ፣ ትልቅ ህዝብ ፣ ታላቅ ርዕይ #የመደመር_መንግሥት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከሕዝብ አብራክ የወጣ፣ለሕዝብ ደኅንነትና ለሀገር ሉዓላዊነት የቆመ፣ሕዝብንም ደጀኑ ያደረገ ተቋም ነው።ሀገርንና ሕዝብን የሚያውኩ ባንዳዎችንና ባዳ ኃይላትን የሴራና የጥፋት መረብ እየበጣጠሰ የሕዝብ አለኝታነቱን እያስመሰከረ ነው። ጠንካራ ሠራዊትነቱ በዘመናዊ ትጥቁና በውጊያ አቅሙ ብቻ ሳይሆን ከሕዝብ በተቀበለው አደራ፣ የሕዝብንና የሀገርን ደኅንነት በሚጠብቅበት ቁርጠኝነት፣ በሚያሳየው ሰብዓዊነትና በሚያስጠብቀው ሀገራዊ ክብር ጭምር የተረጋገጠ ነው። ይህ የሠራዊቱ የሕዝባዊነት መርህ በዘመናዊ አደረጃጀቱ ውስጥ ባለፈባቸው ከምዕተ ዓመት የተሻገሩ ዓመታት ሀገሬውና ዓለም የመሰከረለት ነው። ከሀገር መከላከልና ሉዓላዊነትን ከማስጠበቅ ባሻገር፣ በተለያዩ ዘመናት ለሕዝብ ደኅንነትና ለሰብዓዊ አገልግሎት ባለው ቁርጠኝነትም ይወሳል። ይህ የልዕልና ታሪኩ በኢትዮጵያ ምድር ብቻ የተገደበ አይደለም። በሶማሊያ፣ በላይቤሪያ፣ በኮንጎ፣ በዳርፉር፣ በአቢዬና በሌሎችም የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች የኢትዮጵያ ሠራዊት ያሳየው ተሳትፎና ዲሲፕሊን የተሞላበት አበርክቶ በአፍሪካ ሰላምና መረጋጋት ውስጥ ያለውን ሚና ያስመሰክራል።በእነዚህ ተልዕኮዎች ውስጥ ሠራዊቱ የተሸከመው አደራ የሀገሩን ስም ከማስጠራት ባሻገር ለሰላም የሚደረገውን የአፍሪካ የጋራና የወንድማማችነት ጥረትም ከፍ ያደረገ ሆኗል። የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሕዝባዊነቱን ዛሬም የሀገርን ዳር ድንበር በሚያስከብርባቸው ቦታዎች ሁሉ በተጨባጭ ሥራዎቹ እያሳየ ነው። ሠራዊቱ የድል ከፍታን በሞራል ልዕልና፣ ወታደራዊ ብቃትን በዲሲፕሊን፣ የጥንካሬ መገለጫንም በሰብዓዊነት በማጀብ እያሳየ ያለው ጥረት የሚደንቅ ነው።የአሸናፊነት ልዕልና በሌላው ላይ በሚኖር ወታደራዊ ብልጫ ብቻ አይገለጽም፤ ከአሸናፊነት ጋር የሚመጣውን ኃላፊነት በጥበብ፣ በሕግና በሰብዓዊነት በመወጣትም ጭምር ይመዘናል። ሠራዊቱ ሕገወጥና ጽንፈኛ ቡድኖች የሚፈጽሙትን ትንኮሳ በማምከን ሰላምን እያጸና፣ የሕዝብን ደኅንነት እየጠበቀ፣ሕብረተሰቡ የተለመደ ማኅበራዊ ኑሮውን ያለምንም ስጋት እንዲመራ እያደረገ ያለው ሚና የሕዝባዊነቱ ጉልህ መገለጫ ነው።ሠራዊቱ ሕዝቡ ውስጥ ገብቶ፣ሕዝቡን አረጋግቶ፣ ከሕዝቡ ጋር በመሆን አካባቢውን ከጥፋት ኃይሎች ሲያጸዳ ያሳየው ሙያዊ ሥነ ምግባር የኢትዮጵያን ጠንካራ ተቋማዊ አቅም የሚያመላክት ነው። የኢትዮጵያ የድል አብሳሪ የሆነው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የ130 ሚሊዮን ሕዝብ ሀገርን፣ ግዙፍ ኢኮኖሚ እየገነባች ያለች ሀገርን፣ የቀጣናው መልህቅና የአፍሪካ ተምሳሌት የሆነች ትልቅ ሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅም ዛሬ ራሱን በግዙፍ የሰው ኃይል፣ በሥልጠና ብቃትን፣ በፈጠራ ቴክኖሎጂን ታጥቆ የወትሮ ዝግጁነት ላይ ይገኛል።የታሪካዊ ጠላትን የጥፋት አጀንዳ የተሸከሙ ባንዳዎችን አከርካሪ በመስበር ሀገርን በክብር የልማት ሥራዋን እንድታፋጥን አይተኬ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። መከላከያ ሠራዊት አሁን የዕድሜውን ያህል ራሱን ከዘመኑ ጋር እያራመደ ይገኛል። በራስን መቻል የመደመር መንግሥት ስትራቴጂ መሠረት ከቀላል የጦር መሣሪያዎች ጀምሮ የተራቀቁ የድሮን ቴክኖሎጂዎች ማምረት ጀምሯል።ከሆሚቾ የተተኳሽ መሣሪያዎች እስከ ስካይዊን የድሮን ማምረቻ ድረስ ግዙፍ ኢንዱስትሪዎችን በማንቀሳቀስና በማምረት ለሌሎች ሀገራትም የሚተርፍ አቅም እየገነባ ነው። ጦርነትን ከሩቅ የሚያስቀርና ውጊያን በፍጥነት የሚጨርስ ግዙፍ ሠራዊት የገነባችው ኢትዮጵያ መዳከሟን የሚመኙ፣ አትችልም የሚሉትን ሁሉ በድሎቿ እየረታች ጉዞዋን ቀጥላለች።በአራቱም አድማስ ሰላማዊነትን በማስቀደም የሚተነኩሷትን ደጋግመው እንዲያስቡ በሚያደርግ ጠንካራ እርምጃዋ እያሳፈረች ትገኛለች። ሠራዊቱም የሀገርን ጥቅምና ደህንነት በሁሉም አውድ በአስተማማኝ እያስጠበቀ ነው። የሀገር ብሔራዊ ጥቅም ከባሕር የሚመነጩ ስጋቶችን በመቀነስም የሚረጋገጥ በመሆኑ የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት የትውልዱ የአርበኝነት ጥያቄን መሠረት በማድረግ የመርከቦቿንና የቀጣናውን ደኅንነት የሚያስጠብቅ ግዙፍ የባሕር ኃይል ገንብቷል።የሀገር ጥቅምና ደኅንነት በየብስና በባሕር ብቻ ሳይሆን በአየርም ጭምር የሚረጋገጥ እንደመሆኑ ሰማዩ የእኛ ነው በሚል መርህ 4ኛ ትውልድ ቴክኖሎጂን በመታጠቅ ወደ አምስተኛ ትውልድ ቴክኖሎጂ እየገሰገሰ የሚገኘውን ግዙፍ አየር ኃይል ያደራጀው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያን ደኅንነትና የአየር ክልል በአስተማማኝ ሁኔታ እየጠበቀ ይገኛል። የሀገር መከላከያ ሠራዊቱ የትልቅ ሀገርና የትልቅ ሕዝብ ሠራዊት ነው።በታላቅ ርዕይም ከሀገር እስከ ዓለም አቀፍ ተልዕኮዎች ራሱን እያበቃና እያዘጋጀ ጉዞውን ቀጥሏል።ሠራዊቱ ከሕዝብ አብራክ የወጣ የሕዝብ ልጅ ነው፤ ለሕዝብ ደኅንነት የቆመ የሕዝብ ጋሻ ነው፤ በችግር ጊዜ የሕዝብ ደጀን ነው። የእውነተኛ ጀግንነት ልዕልናም ድልን በሰብዓዊነት፣ኃይልን በዲሲፕሊን፣ አሸናፊነትን በሞራል ጥንካሬ ማጀብ ነው።ይህ የሕዝባዊነት መንፈስ በተሰማራባቸው ሥፍራዎች ሁሉ ይታያል። ከሀገር እስከ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ የኢትዮጵያ ሠራዊት ምስጉንና ጀግና መሆኑ ሁልጊዜም ሲወሳ ይኖራል።
በጽናትና በሕብር የተገነባች የጀግኖች ሀገር-ኢትዮጵያ
Oct 14, 2026 115
ኢትዮጵያ በታሪክ ሂደት ያጋጠሟትን ፈተናዎች በሚገባ በድል እየተወጣች ለዛሬ በቅታለች። ፈተናዎች ባጋጠሙ ቁጥር የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድነት ከመንግስት ጎን ተሰልፎ ሀገር የማጽናት ሚናውን በላቀ ደረጃ እየተወጣ ቆይቷል። ዛሬም የኢትዮጵያ ህዝብ ከአባቶቹ እና ከአያቶቹ የወረሰውን የጀግንነት ታሪክ ሀገር ለማጽናት እና ልማትን ለማፋጠን እየተጠቀመበት ነው። በተለይም የዛሬው ትውልድ ልክ እንደ አባቶቹ ሀገር በማጽናት ተግባር ላይ እየተሳተፈ ይገኛል። ለዚህ ነው ኢትዮጵያ በጽናትና በአንድነት የተገነባች የጀግኖች ምድር ልትባል የሚገባት። ኢትዮጵያ በረጅም የታሪክ ጉዞዋ በርካታ ፈታኝ ሁነቶችን፣ የውጭ ወረራዎችንና የውስጥ ውስብስብ ችግሮችን አልፋ ለዛሬ የበቃች ታላቅ ሀገር ናት። በየዘመናቱ ያጋጠሟት ፈተናዎች ሁሉ ሀገሪቱን የሚያፈርሱ ሳይሆን፣ ይልቁንም የህዝቧን ጥንካሬ፣ ጽናትና ሀገራዊ ፍቅር ይበልጥ አጎልብተው የሚያወጡ ሆነው አልፈዋል። ጠላቶቿ እንደሚመኙላትን መንገድ ሳይሆን ወዳጆቿን የምታኮራ ሀገር ሆና ቀጥላለች። የኢትዮጵያ ህዝብ በታሪኩ የሀገሩ ነጻነት በተደፈረ፣ ህልውናዋም በተፈተነ ቁጥር ልዩነቶቹን ወደ ጎን በመተው ሀገር የማጽናት ታሪካዊ ሚናውን በላቀ ደረጃ ተወጥቷል። ከአድዋ ድል እስከ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ፍጻሜ ኢትዮጵያውያን ‘አይችሉትም’፣ ‘አያደርጉትም’ የተባለውን ሁሉ ፈጽመው አይበገሬነታቸውን አስመስክረዋል። በቅርብ ጊዜም የሀገር ህልውና ማስጠበቅ ላይ የታየው የህዝቡ አንድነት፣ ለሀገር ህልውና የሚከፈለውን መስዋዕትነት እና የጽናት ጥግ ያሳያል። ዛሬም ቢሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ከአባቶቹና ከአያቶቹ የወረሰውን የጀግንነት፣ የአይበገሬነትና የሀገር ፍቅር እሴት በመጠቀም ሀገር የማጽናትና የልማት ስራዎችን የማፋጠን ተግባሩን አጠናክሮ ቀጥሏል። ለዚህ እንደምሳሌ የሚጠቀሱት የመደመር መንግሥት የልማት ውጥኖች የህዝቡን ተስፋ እና አንድነት የበለጠ ያለመለሙ፤ለፍጻሜያቸውም ታላቅ ቁርጠኝነት እየታየ ነው። በአጭር ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያን በምግብ ራስን ለማስቻል እና ከውጭ የሚገባውን ስንዴ በመተካት ወደ ውጭ መላክ የሚያስችል ትልቅ ሀገራዊ እንቅስቃሴ አሳክታለች። የደን ሽፋን መጨመር፣ የአፈር መሸርሸርን መከላከል፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን መቀነስ እና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ያለመ ዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ ውጥን በተከታታይ እየተገበረች ነው። በዚህ ሂደት የህዝቡ ተሳትፎ እና ንቃት በተጨባጭ ታይቷል። በተጨማሪም አዲስ አበባን ጨምሮ በዋና ዋና ክልል ከተሞች የተጀመረ፣ የከተሞችን ጽዳት፣ ውበት፣ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እንዲሁም የተፈጥሮና የታሪክ ሀብቶችን በማልማት ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ላይ ማዋልና የቱሪዝም ዘርፍን ማሳደግ እና የኢኮኖሚ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ማድረግ፣ የዲጂታል ክፍያዎችን ማስፋፋት፣ የቴሌኮም ዘርፍን ክፍት ማድረግ እና የመንግስት አገልግሎቶችን በኦንላይን በማቅረብ ሂደት የህዝቡ የለውጥ ፍላጎትና ድጋፍ በገሃድ የታየ ነው። በተለይም የዛሬው ሀገር ተረካቢ ወጣት በውስጥ እና በውጪ ጠላቶች በሚጎነጎኑ ሴራዎች ሳይሸወድና ሳይታለል፣ አባቶቹ ያቆዩለትን ሀገራዊ ፍቅርና ጀግንነት መነሻ በማድረግ በልማት፣ በሰላምና ሀገር በማጽናት ተግባር ላይ በንቃት እየተሳተፈ ይገኛል። ይህ ወጣቱ ላይ የሚንጸባረቀው የሀገር ፍቅር ስሜት ኢትዮጵያ ያሰበቻቸውን ማሳካት እንድትችል ከማድረግ ባለፈ በቀጣናውም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽኖ ፈጣሪ እንድትሆን ማረጋገጫ ማህተም ነው። በመሆኑም፣ አባቶቻችን በደማቸውና በአጥንታቸው ያቆዩአትን ኢትዮጵያ፣ የዛሬው ትውልድ ደግሞ በእውቀቱ፣ በጉልበቱና ሕብረ ብሔራዊ አንድነቱን በማጽናት ለነገዋ የበለጸገች ሀገር የጣለውን መሰረት አጠናክሮ ይገነባታል። ኢትዮጵያን የመገንባት የቅብብሎሽ ስራ ዛሬም በአንጸባራቂ ድል እየታጀበ ቀጥሏል።
ምክክር የሀገር ሥር፤ ኢትዮጵያ የመግባባት ተራራን በምክክር የምታንጽ ሀገር!!
Oct 13, 2026 152
ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ ኢትዮጵያ የጥንታዊ ሥልጣኔ፣ የረጅም ዘመን ታሪክና በሕብር የተሸመነ የሕዝብ ብዝኅ ጸጋ የተቸራት ሀገር መሆኗ የአደባባይ ሐቅ ነው። የሕዝቦቿ ቱባ እሴቶች፣ መከባበር፣ አንድነትና አብሮነት ለዘመናት የዘለቁ ውድ ሀብቶቿ ናቸው። የገዳ ሥርዓትን ጨምሮ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊ እንዲሁም ሌሎች የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቱባ የእርቅ ሥርዓቶችና የአብሮነት እሴቶች ሀገር በቀል የመግባባት ዴሞክራሲ ጸጋዎች ሆነው ዘልቀዋል። እነዚህ ሀብቶች የተቸራት ኢትዮጵያ በየዘመናቱ በነበሩ የተለያዩ መንግሥታት የፖለቲካ አስተዳደር ሥርዓቶች ምክንያት የተከሰቱ የአለመግባባት ስብራቶችን አስተናግዳለች። ይህም በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና የመግባባት ዴሞክራሲ ላይ እንቅፋት በመፍጠር በዜጎች መካከል መጠራጠር እንዲነግስ አድርጎ ቆይቷል። በዜጎች መካከል በጊዜ ሂደት እየተንሰራፋ የመጣው አለመግባባትም የሀገርን እድገት በማቀጨጭ ለብሔራዊ ጥቅም ተጋላጭነት አሉታዊ ጫና አሳድሯል። በዚህም በ2010 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሀገራዊ ለውጥ ማግስት የመደመር መንግሥት መሰረታዊ ሀገራዊ ስብራቶችን ለመጠገን መንገድ ከፍቷል። ለአብነትም የፖለቲካ እስረኞችን መፍታት፣ በውጭ ሀገር የነበሩ ተቃዋሚ ኃይሎች ወደ ሀገር እንዲመለሱ ማድረግና የፖለቲካ ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት የሚያስችል ሁኔታ ፈጥሯል። ይህም የተለያዩ አመለካከቶችን በሰላማዊ ውይይት አስተናግዶ ሀገርን በጋራ የመሥራት ባህልን ለማጠናከር የታለመ ቁርጠኛ እርምጃ ነው። በተጨማሪም በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 ዓ.ም የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኢትዮጵያ መሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚስተዋሉ ልዩነቶችን በሰላማዊና አካታች ምክክር ለመፍታት ተቋቁሟል። ኮሚሽኑም የአለመግባባትና የልዩነት ምንጮችን በመለየት በሁሉም ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች እና በውጭ በሚኖሩ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በየምዕራፉ የአጀንዳ ማሰባሰብና የተሳታፊዎች ልየታ አከናውኗል። ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮም በአዲስ አበባ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ዋናው የምክክር ጉባኤ ለበርካታ ቀናት ተካሂዷል። በዋናው ጉባኤም ከመላ ኢትዮጵያና ከውጭ ሀገራት የተውጣጡ 4 ሺህ የሕዝብ ወኪል ተመካካሪዎች በ10፣ በ50፣ በ250፣ በ500 እና በሥራ ቡድኖች በመደራጀት በመሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ምክረ ሀሳቦችን ማፍለቅ የቻሉበት ታሪካዊ መድረክ ሆኗል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት ይፋዊ የምክክር ምክረ ሀሳቦች የርክክብ ሥነ-ስርዓት ተካሂዷል። በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተቀመሩ የተመካካሪዎች ምክረ ሀሳቦችንም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ተረክበዋል። የሀገራዊ ምክክሩ ምክረ ሀሳቦች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚስተዋሉ መሰረታዊ ልዩነቶችን በሰላማዊ ምክክር የመፍታት ባህል መገንቢያ ቁልፍ አጀንዳዎች ናቸው። መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በተከናወነው ሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንደኛ መደበኛ ስብሰባ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን በጠቅላይ ሚኒስትርነት በሰየመበት ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያ የብዝኅ ሥልጣኔ፣ የአስደናቂ ታሪክና እሴቶች ምድር መሆኗን ገልጸዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያውያንን ሕብረ ብሔራዊነት በማጎልበት አለመግባባቶችን በሰለጠነ ምክክር በመፍታት ጠንካራ ሀገረ መንግሥት መገንባት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል። አለመግባባቶችን በጠብመንጃ ለመፍታት መሞከር ጥፋቱ የከፋ መሆኑንም አስገንዝበዋል። በዚህም ኢትዮጵያውያን በጋራና በትብብር ችግሮቻቸውን በመቅረፍ የሀገራቸውን ሥልጣኔ ለማረጋገጥ ለአንድ ዓላማ መሥራትና መትጋት እንዳለባቸው ጠቁመዋል። የምትበለጽግ ብቻ ሳይሆን ዓለምን የምትቀይር የሰለጠነች ኢትዮጵያን መገንባት ለነገ የማይተላለፍ የጋራ የቤት ሥራ መሆኑንም አሳስበዋል። የመደመር መንግሥት የሕገ-መንግሥትና የአሰራር ማሻሻያ በማድረግ ጭምር የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ምክረ ሀሳቦችን በመተግበር በመሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባትን ለመገንባት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። ከዚህ አንጻር የሽግግር ፍትሕና የዕርቅ ሂደት እንዲሁም ሀገራዊ ምክክር ለዘላቂ ሰላምና ለሀገራዊ መግባባት ወሳኝ መደላድሎች ናቸው። የኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ የወንጀል ምርመራና ክስ፣ እውነትን መፈለግ፣ ዕርቅ፣ በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ምህረትና ማካካሻን በማካተት ፍትሕን፣ ተጠያቂነትንና የሕግ የበላይነትን ለማጠናከር ጉልህ ሚና ይጫወታል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ምክረ ሀሳቦችም ለዘመናት የቆዩ የአለመግባባት ችግሮችን በውይይት በመፍታት በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ መግባባትን በመገንባት የመተማመን ባህልን ለማጎልበት የማይተካ ሚና አላቸው። የመደመር መንግሥት አካታች የፖለቲካ ምኅዳር፣ የሽግግር ፍትሕና ሀገራዊ ምክክር የኢትዮጵያን የቆዩ የአለመግባባት ችግሮች በሰላማዊና በሕጋዊ መንገድ ለመፍታት የተዘረጉ አስፈላጊ የፖለቲካ ቁርጠኝነት ማዕቀፎች ናቸው። የእነዚህ ሂደቶች ዘላቂ ውጤት በሕዝብ ተሳትፎ፣ በተቋማት ኃላፊነትና በሁሉም ዜጎች መካከል በሚፈጠር መተማመን ላይ ይታነጻል። ይህም ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከርና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን በማሳደግ ለሁሉም ዜጎች የሚጠቅም ዘላቂ ሰላምና ብልፅግና ለመገንባት ወሳኝ ነው። የኢትዮጵያ ታላቅነት በጥንታዊ ታሪኳ፣ በሥልጣኔዋና በተፈጥሮ ሀብቷ የታነጸ የአብሮነት ማኅተም ነው። የኢትዮጵያውያንን በሕብር የተሸመነ ጸጋ በአንድ የጋራ ሀገራዊ ዓላማ አሰባስቦና አስተባብሮ ማስቀጠልም ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታን በጽኑ አለት ይገነባል። ሀገር በቀል የመግባባት ዴሞክራሲ ግንባታም ወደ ዘላቂ ሰላም፣ የጋራ ብልፅግና እና የሥልጣኔ ከፍታ ያሸጋግራል። ለዚህም ነው በጦር መሣሪያ ከታገዘ ኋላቀር የጉልበት አካሄድ ይልቅ በሐሳብ የበላይነት የተመሰረተ ምክክር የመተማመን ድልድይን በመገንባት የጋራ ሀገራዊ አስተሳሰብ የመቅረጽ ከፍተኛ ኃይል አለው የሚባለው። ሀገራዊ ምክክር ምክክር ምክረ ሃሳቦችም ልዩነቶችን በጸጋ ተቀብሎ በአብሮነት የመኖር ባህል ማጠናከሪያ መሰረቶች ናቸው። ብዝኅ ድምፅ በነፃነት የሚሰሙበት፣ ቅሬታዎች በሰላማዊ መንገድ የሚፈቱበት፣ ታሪካዊ ቁስሎች በእውነትና በፍትሕ የሚታከሙበት እንዲሁም የጋራ ችግሮች በጋራ የሚቋጩበት ምኅዳር መፍጠር የምክክሩ ማዕከላዊ ዓላማ ነው። የምክክር ሂደቱም በአንድነትና በመከባበር ላይ የተመሰረተ አብሮነትን በማጎልበት፣ የሃሳብ ልዩነቶችን በሥልጡን መንገድ የመፍታት ባህልን ያዳብራል። የመደመር መንግሥት የፖለቲካ ምኅዳርን የማስፋት፣ የሽግግር ፍትሕን የማጠናከር፣ ዕርቅን የማሳለጥና የሀገራዊ ምክክር ምክረ ሀሳቦችን አሰናስሎ የመተግበር ቁርጠኝነት አለው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ምክረ ሀሳቦችም በሐሳብ የበላይነት የተመሰረተ ሀገር ግንባታን በማነጽ ሰላማዊ አብሮነትን የሚያጎናጽፍ መሰረት ናቸው። ሀገር ግንባታ በአንድ ትውልድ ብቻ የሚጠናቀቅ ሥራ ባለመሆኑ ዛሬ የምንመሰርተው የጋራ መግባባት ባህል ለነገው ትውልድ የምናወርሰው ግዙፍ ሀገራዊ እሴት ነው። ትልቅ ሀገር የሚገነባውም ከትልቅ ሕዝብ በሚመነጭ ትልቅ ሐሳብ፣ የጋራ ዓላማና የጋራ ኃላፊነትን በሚጋራ ትውልድ ነው። ኢትዮጵያ የታሪኳን ክብር በሥልጣኔ ከፍታ የሕዝቦቿን ሕብረ ብሔራዊነት ወደ የጋራ ኃይል፣ ሕብረ ብሔራዊነቷንም ወደ የጋራ መፍትሔ እየለወጠች ነው። የምክክር ሂደቱ ምክረ ሀሳቦችም ዘላቂ ሀገር ግንባታን የሚያጎለብቱ ናቸው። የመግባባት ተራራ በአንድ ሌሊት አይገነባም። በትውልድ ቅብብሎሽ በሥልጡን የዴሞክራሲ መግባባት ባህልና በተቋማት የማስፈጸም ውጤታማነት በሚፈጠር ቀጣይነት ያለው የመተማመን ተግባር እውን ይሆናል። ምክክር የሀገር ሥር ነው፤ መግባባትም የአንድነት ድልድይ ነው። ፍትሕ ደግሞ የዘላቂ ሰላም መሰረት ነው። ኢትዮጵያ በብዝኅነቷ የምትኮራ፣ በአንድነቷ የምትጸና፣ በሥልጣኔዋ የምትበለጽግና በጋራ ርዕይዋ ወደ ታላቅ ከፍታ የምትራመድ ሀገር እንድትሆን የመግባባት ተራራን በጋራ እንገንባ!!
የጣና ፎረም ሂደቱና ውጤቱ
Oct 12, 2026 198
የጣና ፎረም ሂደቱና ውጤቱ ምን ይመስላል? የአፍሪካ መሪዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ ምሁራንና ሌሎችንም በአንድ መድረክ በማሰባሰብ እንዲመክሩ በማሰብ የተቋቋመው ጣና ፎረም ለአህጉራዊ ዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲሁም ለጠንካራ የትብብር ግንኙነት ወሳኝ መድረክ ሆኗል። በዚህም የጣና ፎረም ላለፉት አስራ አንድ ተከታታይ አመታት ተካሂዶ ዘንድሮም 12ኛው መድረክ በውቢቷ ባህር ዳር ሊካሄድ ቀን ተቆርጦለታል። በአፍሪካ ግጭትን መከላከል፣ ለችግሮች የጋራ መፍትሄ ማበጀት ላይ የሚያተኩረው መድረክ አፍሪካ ችግሮቿን በራሷ አቅም ለመፍታት የሚያስችል ጠንካራ ትብብር በመፍጠር ለተግባራዊነቱ ለመትጋት የሚያስችል ነው። በመሆኑም በየአመቱ የሚካሄደው የጣና ፎረም ዓላማ በአፍሪካ የሰላም ፖሊሲዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ መፍጠር፣ የአህጉሪቱን ድምፅ ማጠናከር፣ የክልላዊ ትብብርን ማሳደግና የሚነሱ ሀሳቦች ወደ ተጨባጭ ውጤት እንዲሸጋገሩ ማድረግ ይሆናል። በዚሁ መሰረትም የዘንድሮው የጣና ፎረም “በአፍሪካ የሰላም መንገዶች፡ የኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነትና የጂኦፖለቲካ ለውጥ” የሚል መሪ ሃሳብ በማንገብ በጣና ሀይቅ ዳርቻ ከጥቅምት 13 እስከ 15 ቀን 2019 ዓ.ም ይካሄዳል። ከ250 በላይ እንግዶች በሚታደሙበት ፎረም ላይ የተለያዩ አገራት መሪዎች፣ የተቋማት ሃላፊዎች፣ የቀድሞ መሪዎች የሚገኙ ሲሆን ለጉባኤው መሳካትም ኢትዮጵያ የተሟላ ዝግጅት ማድረጓ ታውቋል። በአህጉሪቷ የሚስተዋሉ ግጭቶችን መከላከል፣ ሰላምና ደኅንነትም ማስጠበቅ እንዲሁም ሁለንተናዊ የትብብር ግንኙነትን ማጠናከር ይሆናል። በተለይም በአገራት መካከል በቀጥታ፣ በግልጽና በጥልቀት የውይይት አውዶችን በማስፋት በጋራ መስራትን የሚያበረታታ ነው። በፎረሙ ላይ የሚነሱ ጥልቅ ትንታኔዎችና የተለያዩ ምክረ ሐሳቦች ለፖሊሲ ግብአት፣ ለተቋማዊ ለውጥና ለተግባት ተኮር እንቅስቃሴዎች ጉልህ ፋይዳ የሚኖረው መሆኑ ይታመናል። አፍሪካ በዓለም አቀፍ የሰላም፣ የደኅንነትና የፖለቲካ መድረኮች ላይ በሚኖራት ተሳትፎ የተደራጀና የተቀናጀ አቋም በመያዝ ለመቅረብ ጣና ፎረም ወሳኝ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። የጣና ፎረም የግጭት መፍትሔ አስፈጻሚ ተቋም ባይሆንም፣ ውሳኔ ሰጪዎች አዲስ አቅጣጫ እንዲያዩ፣ የጋራ ግንዛቤ እንዲፈጥሩና ለቀጣይ እርምጃዎች መሠረት እንዲያኖሩ የሚያግዝ መሆኑም ይታመናል። የጣና ፎረም ያለፉት 11 መድርኮች የአፍሪካ የሰላምና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ በመምከር የመፍትሄ አመላካች ሃሳቦች የሚነሱበት ስለመሆኑ መናገር ይቻላል። በመድረኮቹ ከአፍሪካ የውስጥ ግጭቶችና የሰላም ግንባታ እስከ ክልላዊ ትብብር፣ የዓለም የኃይል ሚዛን፣ የኢኮኖሚ ልማትና የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ጥቅሞችና ተፅእኖዎቻቸው ላይ የጋራ ግንዛቤ የመያዝ እድል ተፈጥሯል። የሰላምን ጉዳይ ከፖለቲካ፣ ከኢኮኖሚ፣ ከአስተዳደርና ከዓለም አቀፍ ግንኙነት ጋር አስተሳስሮ በማየት የመፍትሄ አቅጣጫዎች ተመላክተውበታል። የ11ኛው ጣና ፎረም፣ “አፍሪካ በለውጥ ላይ ባለ የዓለም ሥርዓት” (Africa in an Evolving Global Order) በሚል መሪ ሃሳብ ሲካሄድ የአገራት መሪዎች፣ ቀድሞ መሪዎች፣ ሚኒስትሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ ምሁራን፣ ወጣቶች የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮችና ሌሎችም ታድመውበት በስኬት ተከናውኗል። በፎረሙ ከተነሱት አበይት ጉዳዮች መካከልም በአፍሪካ ሕብረት፣ በኢጋድ እና በተባበሩት መንግሥታት መካከል የሰላምና ደኅንነት ቅንጅትን የማጠናከር። በተለይም በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ማምጣት እንዲሁም እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥና የዘመኑ ክስተትና በፍጥነት እየደገ የመጣው ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ላይ ያተኮረ ነበር። በትምህርት፣ በቴክኖሎጂ፣ በኢንዱስትሪና በኃይል ልማትና ቀጣናዊ ትስስርን በተመለከተም በስፋት ተመክሮበታል። በመሆኑም የጣና ፎረም የውይይትና የፖሊሲ ሐሳቦች ማፍለቂያ እንዲሁም የምክረ ሐሳብና መፍትሄዎች ማመላከቻ መድርክ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። የአፍሪካ መሪዎች፣ ምሁራን፣ ዲፕሎማቶችና የተለያዩ የፖለቲካና ማህበራዊ እንዲሁም የንግድ ተቋማት ተወካዮች የሰላምና ደኅንነት ጉዳዮችን በቀጥታ የሚወያዩበት የተለመደ መድረክም ሆኗል። የፎረሙ ዋና ስኬትም በአህጉራዊ ሰላምና መረጋጋት ላይ የታዩ መሻሻሎች፣ የተፈቱ ችግሮችና የተተገበሩ ፖሊሲዎችን መጥቀስ ይቻላል። በ2026 ከጥቅምት 23 እስከ 25 በባሕር ዳር የሚካሄደው 12ኛው ጣና ፎረም፣ “በአፍሪካ የሰላም መንገዶች፡ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የጂኦፖለቲካ ለውጥ” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄድ ይሆናል። የዘንድሮው መሪ ሃሳብ የሚያመለክተውም ለዘላቂ ሰላም የኢኮኖሚያዊ ልእልና ፣ የሀብት አጠቃቀም፣ የኢንዱስትሪ አቅምና ሌሎችንም ያካተተ ነው። ከፎረሙ የሚጠበቁ አበይት ነጥቦች መካከልም አፍሪካ የተፈጥሮ ሀብቷንና የዲጂታል አቅሟን ለራሷ ልማትና ለዜጎቿ ጥቅም እንዴት ማዋል ትችላለች? የዓለም የኃይል ሚዛን እየተቀያየረ ባለበት ሁኔታ አፍሪካ የጋራ ፍላጎቷን እንዴት ማስጠበቅ ትችላለች? የሥራ ዕድል፣ የኢንዱስትሪ እድገት፣ የአፍሪካ የኢኮኖሚ ውህደትን በተመለከተ የሚነሱ ጣቀሚ ሃሳቦች እንደሚኖሩ ይጠበቃል። የአገራት የንግድ፣ የመሠረተ ልማት፣ የሃይል ልማት ትስስርን ማጠናከርም ሌላው ትኩረት ይሆናል።
ትንታኔዎች
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፤ በጠንካራ ወታደራዊ አቅምና ዲሲፕሊን የታነጸው የአፍሪካ የሰላም ዘብ!!
Oct 14, 2026 158
ኢትዮጵያ ለትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ እና ታላቅ ርዕይ የሚመጥን የመከላከያ ሰራዊት ገንብታለች። ይህ የሀገር መከታ ሰራዊት በታጠቃቸው ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ብቻ ሳይሆን በተላበሰው ወታደራዊ ዲሲፕሊን ለዓለም ምሳሌ የሆነ ድል አድራጊ ሰራዊት መሆኑን አስመስክሯል። በማድረግ አቅሙም ጠላቶች ከሩቅ የሚሸሹት ሆኗል። ኢትዮጵያ የአሸናፊዎች ምድር ናት። የአሸናፊነት ተምሳሌትም ጭምር። የኢትዮጵያ የአሸናፊ ምድርነት እና ምሳሌነት ሁነኛው ማሳያ ደግሞ የሀገር መከላከያ ሰራዊቷ ጀግንነት የሚቀዳ ነው። ሰራዊቱ የቅድመ አያቶቹና አያቶቹን የድል አድራጊነት መንፈስ ከነሙሉ ክብሩ በትውልድ ቅብብሎሽ የተረከበ ብቻ ሳይሆን ያስቀጠለ የድል ፋና ወጊ ሰራዊት ነው። ይህን የአሸናፊነት ስነልቦና ለተላበሰ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ግንባታ የመደመር መንግሥት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ በመስራቱ የተቋሙን የማድረግ አቅም በከፍተኛ ሁኔታ አሳድጓል። ለዚህም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዓለም አቀፍ ደረጃ የውጊያ መልክ ተቀይሮ ወደ አራተኛው ትውልድ ጦርነት በመሸጋገር በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በሰው አልባ አውሮፕላኖችና በሌሎች ወታደራዊ ቴክኖሎጂዎች አቅምን ማጉልበት ቁልፍ ጉዳይ ነው ያሉት። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገር ብቻ ሳይሆን የምስራቅ አፍሪካ፣ የአፍሪካና የዓለም የሰላምና የጀግንነት ተምሳሌትነቱን በተግባር ያረጋገጠ ክንደ ብርቱ ኃይል ነው። በጥብቅ ወታደራዊ ዲሲፕሊን የሚመራው ይህ ጀግና ሰራዊት የኢትዮጵያን ጥቅምና ሉዓላዊነት ለመፈታተን ለሚዳዳቸው ማናቸውም የውስጥ ተላላኪዎችና የውጭ ላኪዎች ፈጣንና የማያዳግም ምላሽ በመስጠት ሰላምን በብርቱ ክንዱ የማረጋገጥ አቅሙ አለው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ሰራዊቱ የኢትዮጵያ ወኔና የጀግንነት ምልክት መሆኑን የገለጹት የሰራዊቱ ሁለንተናዊ የማድረግ አቅም መጎልበትም ኢትዮጵያ ሉዓላዊ አንድነቷን አስከብራ የምትቀጥል የክንደ ብርቱዎች ምድር መሆኗን ያመላክታል። ይህ ጀግና የሀገር መከታ ሰራዊት ከጊዜ ወደ ጊዜ ሁለንተናዊ ዝግጁነቱን እያጠናከረ ይገኛል። ህዝባዊ ወገንተኝነቱንም በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ግዳጆች በተግባር አረጋግጧል፤ እያረጋገጠም ይገኛል። የኮሪያ፣ ኮንጎ፣ ሩዋንዳ፣ ኮትዲቯር፣ ቡሩንዲ፣ ላይቤሪያ እንዲሁም የሱዳን ዳርፉር ጋራና ተራራ፣ ሸለቆና ረባዳማ ስፍራ፣ ሜዳና ሸንተረር የጀግናው ሰራዊት ታሪክ ዘካሪ ሕያው ምስክሮች ናቸው። በአሁኑ ወቅትም በሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳንና ሱዳን ከቅድመ አያቶቹ የተረከበውን ለዓለም ሕዝብ ሰላምን የመቆም ታሪካዊ ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ ይገኛል። ኢትዮጵያን ከከፍታ ማማዋ ለማሳነስ የግብፅ፣ ሻዕቢያና ሌሎች ታሪካዊ ጠላቶችን ተልዕኮ ያነገቡ የውስጥ ባንዳዎች ከንቱ ቅዠት በማምከን የሀገር አለኝታነቱን በተግባር የሚያስመሰክር ሰራዊት ነው። ኢትዮጵያ ሉዓላዊ አንድነቷንና ሰላሟን አስጠብቃ ለመቀጠሏ ምስጢሩ ይህ የሀገር ኩራት እና የትውልድ ባለአዳራ ሰራዊት መሆኑም በትውልድ ቅብብሎሽ ተገነባው አኩሪ የታሪክ ገድሉ ሕያው ምስክር ነው። የአንዲት ሀገር ሁለንተናዊ የማድረግ አቅም ከሚለካባቸው መስፈርቶች መካከል አንዱ በመከላከያ ሰራዊት ግንባታዋ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይስማሙበታል። ለዚህም ነው የመከላከያ አጠቃላይ አቅሞች ኢትዮጵያ እያንሰራራች እና አስተማማኝ አቅም ላይ እንዳለች በግልጽ ያመላክታሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መግለጻቸው። ለጎረቤት ሀገራት ሰላም እና ደህንነት መረጋገጥ የህይወት መስዋዕትነት ጭምር በመክፈል ወገንተኝነቱንና ጀግንነቱን በተግባር ማስመስከሩ ዓለም የሚያውቀው ተምሳሌታዊ ክንደ ብርቱ ሰራዊት ነው። በሁለንተናዊ የማድረግ አቅሙ የሚታወቀው ይህ የሀገር መከታ ትላንት ላይ ተቸክለው ለቆሙ ማናቸውም ኋላ ቀር ስብስቦች ፍቱን መድኃኒት ነው። ከታሪካዊ ስህተቱና ከሀገር ከሃዲነቱ ያልተማረው ሕገወጡ የሕወሓት ጠባብ ቡድን ከዚህ ጀግና ሰራዊት ፊት መቆም ከቶውንም አይችልም። ይህም በተደጋጋሚ ታይቷል። የዚህ ጠባብና ተላላኪ ቡድን እኩይ ተግባር “ካልጠገቡ አይዘሉ ካልዘለሉ አይሰበሩ” ዓይነት ሆነና በሀገር መከላከያ ሰራዊት በተወሰደበት ፈጣን እርምጃ ድራሹ ጠፍቷል። የአኩሪ ገድል ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ዛሬም እንደ ትላንቱ በስልጣንና በዘረፋ ስካር ውስጥ ለተዘፈቀውና ሀገር ለማፍረስ ከውስጥ ባንዳዎችና ከውጭ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በመሆን ለተከተለው የጥፋት መንገድ ሁሉንም በሚያስተምር መልኩ ፈጣን ምላሽ የመስጠት ሀገር የማጽናት ተልዕኮውን በብቃት የመወጣት ተግባሩን በጀግንነት ቀጥሏል። ዛሬም ሆነ ወደፊት የኢትዮጵያ ብቸኛ መሻት ልማትን ማፋጠንና የቀጣናውን ሀገራት በኢኮኖሚ በማስተሳሰር የጋራ ብልፅግናን ማረጋገጥ ነው። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምና ሉዓላዊነት ላይ ለሚቃጡ ማናቸውም የውስጥና የውጭ ትንኮሳዎች ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚችል የሰላምና ደኅንነት ተቋም መገንባቱም መከላከያ ሰራዊት ሁነኛ አብነት ነው። በዚህ መሠረት ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የወታደራዊ ተቋሟን የማድረግ አቅም በላቀ ደረጃ እያሳደገች ትገኛለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሁን ላይ ኢትዮጵያ የታጠቀቻቸው በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በተለያዩ ቴክኖሎጂዎች የታገዙት ድሮኖች ጦርነትን ማስቀረት ብቻ ሳይሆን ጦርነትን ባጠረ ጊዜ መጨረስ የሚያስችሉ ናቸው ሲሉ መግለጻቸው። የኢትዮጵያ የታሪክ ድርሳናት ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟንና ሉዓላዊነቷን ለመግፈፍ የሚመጡ የውጭ ወራሪዎችንና የሚሰነዘሩ ማናቸውም ጥቃቶችን በድል አድራጊነትና ሉዓላዊነቷን ከማስከበር የማትበገር ሀገር መሆኗን ያመላክታሉ። ለዚህ ነው አባቶቻችን “ኢትዮጵያን የነካ የለውም በረካ” ሲሉ የሚገልጹት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተደጋጋሚ ኢትዮጵያ ትፈተናለች እንጂ አትሸነፍም ሲሉ መደመጣቸውም ይህንን መሠረት በማድረግ ነው።
የመደመር እሳቤ፡ ለአፍሪካ የጋራ ብልፅግና አዲስ መንገድ
Oct 14, 2026 205
ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን የነጻነት፣ የሉዓላዊነት እና የጥቁር ህዝቦች ኩራት ተምሳሌት በመሆን በአፍሪካ አህጉር ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ አላት። ቅኝ ያልተገዛችው፣ ሉዓላዊነቷን ያላስደፈረችው እና ክብሯን አስጠብቃ ለዘመናት የቆየችው ኢትዮጵያ፤ አፍሪካውያንን ከቅኝ ግዛት ለመላቀቅ ባደረጉት ትግል ውስጥ ፋና ወጊ እና የነጻነት ተምሳሌት በመሆን ታሪካዊ አሻራዋን አሳርፋለች። ይህ ታሪካዊ ሚናዋ ዛሬም ድረስ በአዲስ መልክ እየቀጠለ ይገኛል። የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እና የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ምስረታ ላይ ትልቅ አሻራ ያላት ኢትዮጵያ የህብረቱ ዋና መቀመጫ በመሆን የአህጉሪቷ የዲፕሎማሲ መናኸሪያ ናት። ሀገሪቱ የአፍሪካውያን ነጻነት እና ራስን መቻል የሚያቀነቅነውን የፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ ነፍስ እንዲዘራና ህያውነት እንዲላበስ በማድረግ የአህጉሪቱ ትልሞች እውን እንዲሆኑ የላቀ ሚና ተጫውታለች። በታሪክ የታየው ይህ የፓን አፍሪካኒዝም ስንቅ፣ ዛሬ ላይ በመደመር ፍልስፍና ታድሶ ድንበር ተሻጋሪ አህጉራዊ ኃይል እየሆነ መጥቷል። የአዲሱ የመደመር መንግሥት ምስረታ የሀገሪቱን የውስጥ ፖለቲካዊ ምዕራፍ የሚያድስ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም የመደመር እሳቤ የኢትዮጵያን ወሰን አልፎ ለመላው አፍሪካውያን የሚጠቅም አህጉራዊ ፍልስፍና መሆኑን በተግባር ያሳየበት ክስተት ነው። መደመር ሀገሪቷ ያሏት መልካም እሴቶች ላይ መጨመርን፣ ጉድለቶችን መሙላትን፣ ያለፈውን ስህተት አርሞ መልካሙን ማስቀጠልን እና በጋራ ማደግን የሚያስተምር ሀገር በቀል ፍልስፍና ቢሆንም፣ ዛሬ ላይ ግን ድንበር ተሻግሮ ለአህጉራዊው የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ፣ ለአፍሪካ ህብረት መጠናከር እና ለአፍሪካውያን በራስ የመተማመን መንፈስ አዲስ መነቃቃትን እየፈጠረ ይገኛል። ይህ እሳቤ ለአፍሪካ ጥንካሬ ያለው አንድምታ ከፍተኛ ነው። አፍሪካውያን ያላቸውን የተፈጥሮ እና የሰው ሀብት አስተባብረው በዚሁ ድንበር ተሻጋሪ የመደመር እሳቤ ከተመሩ፣ ከማንኛውም ጥገኝነት መውጣት ይችላሉ። ፍልስፍናው በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ግንኙነት በማጠናከር፣ ከፉክክር ፈንታ በትብብር ላይ የተመሰረተ አህጉራዊ ትስስርን ለመገንባት አስተማማኝ መሰረት እየሆነ ነው። በዚህ ማዕቀፍ ስር ኢትዮጵያ «የአፍሪካ ችግሮች በአፍሪካውያን ይፈቱ» የሚለውን የጸና አቋሟን ይበልጥ አጠናክራለች። አዲሱ የመደመር መንግሥት አፍሪካውያን የራሳቸውን ችግር በራሳቸው አቅምና እውቀት እንዲፈቱ የሚያስችሉ ስራዎችን በወሰን ተሻጋሪ ወንድማማችነት መንፈስ በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል። ይህ ድንበር የተሻገረው የመደመር እይታ አፍሪካውያን እንደ አፍሪካ ህብረት ያሉ አህጉራዊና ቀጣናዊ ተቋማት ላይ ያላቸውን እምነት የሚያጠናክር እና የውጭ ጣልቃ ገብነትን በጋራ ለመመከት የሚያስችል ትልቅ አህጉራዊ አቅም የሚፈጥር ነው። በመሆኑም በመደመር ፍልስፍና የሚመራ ጠንካራ የኢትዮጵያ መንግስት ምስረታ ለአፍሪካ እድገት እና ሰላም የሚኖረው ፋይዳ የጎላ ነው። ጠንካራ ኢትዮጵያ ማለት ለአፍሪካ ቀንድ አስተማማኝ ሰላም፣ ለምስራቅ አፍሪካ የኢኮኖሚ ትስስር ምሰሶ እና ለመላው አህጉሪቱ የነጻነት ፋኖስ ናት። የመደመር እሳቤ የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሮ ለአህጉሪቱ መፍትሔ መሆን መቻሉ፤ አፍሪካውያን በኢኮኖሚ ራሳቸውን እንዲችሉ እና በዓለም መድረክ ላይ የሚገባቸውን ክብርና ቦታ እንዲያገኙ ለማድረግ የጎላ ሚና ይጫወታል።
ኢትዮጵያ በመደመር መንግሥት ታላቅ የልማት ጉዞ ላይ ትገኛለች
Oct 13, 2026 349
ኢትዮጵያ በታሪኳ የታላቅነት፣የሥልጣኔና የሉዓላዊነት ምሳሌ ሆና የኖረች ሀገር ናት።በዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ የነበረችው ኢትዮጵያ፣ የሰው ዘር መገኛ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ የራሷን መገበያያ በጥንት ዘመን ፈጥራ፣ ፊደላትን ቀርጻ፣ እንደ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ያሉ ዓለምን ያስደመሙ የኪነ ህንጻ ሥራዎችን የከወነች ኃያል ሀገር ናት። የስልጣኔ ሀገረ መንግሥት ተብለው ከሚጠቀሱት ጥቂት ሀገራት አንዷ የሆነው ኢትዮጵያ የዓለም ተቋማትን በመመስረት፣ ለግፉዓን ድምፅ በመሆን፣ በዓለም የፖለቲካ አውድ ግዘፍ የነሳውና ብዙ ለውጦችን ያመጣው የዓድዋ ድል ባለቤቷ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ቅስማቸውን በመስበርና በማንበርከክ ድል አድርጋ የአድዋን ታላቅ ድል ለአፍሪካውያንና ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ የነፃነትና የብሥራት ምልክት አድርጋ አስረክባለች። ሆኖም ይህ ታላቅ የታሪክ ኩራትና የሉዓላዊነት ወደር የለሽ ክብር ሀገሪቱን ወደ ዘመናዊ የኢኮኖሚ ብልጽግናና ተወዳዳሪነት በበቂ ሁኔታ ሳይቀይራት ለረጅም ዘመናት ቆይቷል። ታዲያ የዚህ ሁሉ የስልጣኔና የድል ውርስ ባለቤቷ ሀገር እንዴት ወደኋላ ቀረች? በተከታታይ በነበሩ የሥልጣን ሽኩቻዎች፣የውስጥ ግጭቶችና የፖለቲካ አለመረጋጋቶች ምክንያት ሀገራዊ አቅምና የሰው ኃይል ለግንባታ ሳይሆን ለጥፋት ሲውል ቆይቷል። በተጨማሪም የጠንካራና ዘላቂ ተቋማት አለመገንባታቸው እንዲሁም የፖሊሲ ውሳኔዎች ከተጨባጭ የሕዝብ ፍላጎት ይልቅ በርዕዮተ-ዓለም አክራሪነት ላይ መመሥረታቸው ኢኮኖሚውንም ፖለቲካውንም በእጅጉ ጎድቶታል።ዓለም በኢንዱስትሪ፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂና በዘመናዊ ግብርና እየመጠቀች በሄደችበት ወቅት ኢትዮጵያ በባህላዊ የአመራረት ዘይቤና በውጭ እርዳታ ጥገኝነት ውስጥ ታስራ በመቆየቷ ከዓለም አቀፍ ውድድር ወደኋላ ቀርታለች።የሀገር ሀብት፣ የምሁራን እውቀት፣ የግሉ ዘርፍና የመንግሥት ጥረት ሳይቀናጁና ሳይደጋገፉ በየፊናቸው በመጓዛቸው የታሰበውን ሀገራዊ ስኬት ማምጣት ሳይቻል ቀርቷል። ይህንን የታሪክና የልማት ክፍተት ለማረቅ የተነሳው የመደመር መንግሥት የትናንትን ጥፋቶች ማረም፣ መልካም ስኬቶችን ማስቀጠልና የነገን ብልጽግና የሚያረጋግጥ አዲስ ሀገራዊ ምዕራፍ መክፈትን ዓላማ አድርጎ ተነሳ። የመጀመሪያው የትኩረት አቅጣጫ የተበታተኑ ሀገራዊ አቅሞችን ማለትም የሕዝብን፣ የመንግሥትን፣ የግሉን ዘርፍ፣ የምሁራንንና የዳያስፖራውን አቅም በማቀናጀት ለጋራ ልማት ማሰለፍ ነው። ሁለተኛው ሀገሪቱን ከእርዳታና ከተወሰኑ ዘርፎች ጥገኝነት በማውጣት ግብርናን፣ አምራች ኢንዱስትሪን፣ ማዕድንን፣ ቱሪዝምንና ዲጂታል ኢኮኖሚን የእድገት መሪ የሚያደርግ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ሪፎርም መተግበር ነው። ሦስተኛው ደግሞ ፕሮጀክቶች በወረቀት ላይ ብቻ ሳይቀሩ በመሬት ላይ ፈጣን፣ ጥራት ያለውና ተጨባጭ ውጤት እንዲያመጡ የሚያስችል አዲስ የተቋማትና የአፈጻጸም ባህል መገንባት ነው። የተመዘገቡ ተጨባጭ ድሎች የመደመር መንግሥት በሁሉም መስክ በትልቁ ማሰብ፣ ጀምሮ መጨረስን ባህል አድርጎታል። በዚህም ኢትዮጵያ እንድታንሰራራ ያስቻሉ ግዙፍ የልማት ምዕራፎችን እያሳካ ይገኛል። በግብርናው ዘርፍ ኢትዮጵያ የመስኖ ስንዴ ልማትን በማስፋት በዓመት 33 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ስንዴ በማምረት በአፍሪካ ቀዳሚዋ የስንዴ አምራች ሆናለች። ራሷን ችላም ወደ ውጭ መላክ ጀምራለች። የግብርና ሜካናይዜሽንና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማስፋት የሰብል ምርትን ከ335 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ኩንታል ማሳደግ ተችሏል። በኢኮኖሚና በኢንቨስትመንት ዘርፍ የወጪ ንግድ ገቢን 11 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ማድረስ የተቻለ ሲሆን፣ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰትም 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። በተጨማሪም የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የ15 ነጥብ 8 በመቶ ዕድገት ማስመዝገብ ችሏል። በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የአምራች ኢንዱስትሪውን በማነቃቃት ከውጭ የሚገቡ ስትራቴጂክ ምርቶችን መተካት ተጀምሯል።ኢትዮጵያ ለውጭ ገበያ ተወዳዳሪ የሆኑ ምርቶችንም በማምረት ላይ ትገኛለች። በማዕድን ዘርፍም አፈር የለበሱ የከበሩ ማዕድናትን እየገለጠች ወደ ጥቅም በመቀየር ላይ ናት። የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የድንጋይ ከሰል ማምረቻና ማጠቢያዎች የወርቅ ፋብሪካዎችና ግዙፍ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካዎችን ወደ ሥራ እየገቡ ናቸው። የመደመር መንግሥት በመሠረተ ልማትና በሜጋ ፕሮጀክቶች በኩል የትርክትና የአፈጻጸም ለውጥ ፈጥሯል። የማይጠናቀቅ ፕሮጀክት፣ የማይገነባ መሰረተ ልማት የለም በሚል ከለውጡ በፊት የነበሩ የተንከባለሉ ፕሮጀክቶችን በማፋጠን አሳክቷል።ለዚህ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን ከነበረበት ውስብስብ የፕሮጀክት አስተዳደር በማላቀቅ በራስ አቅም በዜጎች ደምና ላብ ለውጤት አብቅቷል። ኃይል አመንጭቶ የቀጣናው የብርሃን ማዕከል እንዲሆን አድርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ይፋ ባደረጓቸው የጉባ ብስራት ሜጋ ፕሮጀክቶችም የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን፣ የነዳጅ ማጣሪያ፣ የጋዝ ማምረቻ፣ የሰላማዊ ኒውክሌር ኃይል ማብለያ ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ ገብተዋል። ኢትዮጵያ በመደመር ነገን የተሻለ የማድረግ ሀገራዊ ዕይታ በኮሪደር ልማት ከተማና ገጠሩን ወደ ዘመናዊ የኑሮና የሥራ ማዕከልነት እየቀየረች ትገኛለች።በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ኢኒሼቲቭ ከአዲስ አበባ በጀመረው የከተማ የኮሪደር ልማት የከተሞችን ውበትና የኑሮ ደረጃ በእጅጉ አሻሽሏል።በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ እየተገነባ ነው።ከ56 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ለአፍሪካ ተምሳሌት የሆነች ሀገር መፍጠር ተችሏል። በቱሪዝምና በሀገር ገጽታ ግንባታ በኩል የገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች የተፈጥሮ፣ የታሪክና የባህል ሀብቶችን ወደ ላቀ የኢኮኖሚና የቱሪዝም አቅም ቀይረዋል።የመደመር መንግሥት የቀጣይ ጉዞ ርዕይ ኢትዮጵያን በጠንካራ መሠረት ላይ የቆመች፣ በራሷ አቅም የምትተማመንና በቀጣናው፣በአፍሪካና በዓለም ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀገር ማድረግ ነው። በመጀመሪያ በምግብ ራስን በመቻል፣ የወጪ ንግድ አቅምን በማሳደግና ከውጭ ጫናዎች ነፃ የሆነ ጠንካራ የፋይናንስና የኢንዱስትሪ መሠረት በመገንባት የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ነው። በሁለተኛ ደረጃ በሰላማዊ የፖለቲካ ባህል አማካይነት ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት የተደመረ ሀገራዊ የፖለቲካ ካፒታል የተፈጠረባትና የሕግ የበላይነት የጸናባት ሀገር ማድረግ ነው። ከጎረቤት ሀገራት ጋርም በልማት፣ በኃይል አቅርቦትና በሰጥቶ መቀበል ዲፕሎማሲ ጠንካራ ትስስር የመፍጠር ትልሞችን ማስቀጠል ላይ የመደመር መንግሥት አበክሮ እየሠራ ይገኛል። የባሕር በርና የንግድ ወጪ አማራጮችን በፍትሐዊነትና በሕጋዊ መንገድ ማረጋገጥ ነው። በአራተኛ ደረጃ ጥራት ያለው ትምህርት፣የጤና ሽፋንና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተደራሽነትን በማስፋት ለነገዋ ዓለም ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ኃይል ማፍራት የመደመር መንግሥት ዋና አጀንዳ ነው። የኢትዮጵያ ታላቅ የልማት ጉዞ የትናንት ህልሞችን ወደ ዛሬ ተጨባጭ ድል የመቀየር ሁለንትናዊ ጉዞ ነው።የመደመር መንግሥት ርዕይ ኢትዮጵያን የትናንት ታሪኳን የምትመለከት ብቻ ሳትሆን፣ የነገው ብልጽግናዋ አስተማማኝ የሆነ፣ ዜጎቿ በክብርና በፍትህ የሚኖሩባት ባለታሪክና ባለድል ሀገር አድርጎ ለማስረከብ የትውልድ አደራን በመፈጸም ላይ ይገኛል።
ፈተናን ወደ ዘላቂ ስኬት-በመደመር እሳቤ የተገለጠ ሀገራዊ አቅም
Oct 12, 2026 382
የአንድ ሀገር ታላቅነትና ብልፅግና የሚለካው በገጠሟት ፈተናዎች ስፋት ሳይሆን፣ እነዚያን ፈተናዎች ወደ ልማትና ዘላቂ ስኬት ለመቀየር በሚወሰዱ ቆራጥ ሀገራዊ እርምጃዎች ነው። ኢትዮጵያ በታሪኳ አያሌ መዋቅራዊ፣ጂኦፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎችን አልፋ የተጓዘች ሀገር እንደመሆኗ መጠን፤በአሁኑ ወቅት የነበሩባትን ማነቆዎች ወደ አዲስ ዕድል በመቀየር ላይ ትገኛለች። ይህ ሂደት በንድፈ-ሃሳብ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በመሬት ላይ በሚታዩ ዘለቄታዊ ታላላቅ ፕሮጀክቶችና መዋቅራዊ ማሻሻያዎች እውን እየሆነ ይገኛል። ይህ አዲስ የተግባር ምዕራፍ ደግሞ የሀገሪቱን ዕድገትና ትውልድ ተሻጋሪ ጉዞ በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት የተነደፈው የመደመር እሳቤ ቀጥተኛ ነጸብራቅ ነው። የመደመር ፍልስፍና የነበሩ በጎ እሴቶችንና ስኬቶችን ይዞ መቀጠልን፣ጉድለቶችን ማስተካከልን እና አዳዲስ ፈጠራዎችን ማመንጨትን እንደ ስትራቴጂ የሚይዝ በመሆኑ፣በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ እየተተገበሩ ያሉ ታላላቅ ፕሮጀክቶችና መዋቅራዊ ማሻሻያዎችም ይህንን እሳቤ በተግባር ያረጋገጡ ናቸው። ለዘመናት ያጋጠሙትን የምግብ ዋስትና ችግሮች፣ የምንዛሬ እጥረትና የገበያ መዛባቶች ለመቅረፍ የተወሰዱት አገራዊ እርምጃዎች የዚሁ ችግርን ወደ እድል የመቀየር ስትራቴጂ ዋና ማሳያ ናቸው። ኢትዮጵያ ለዘመናት የስንዴ እህልን ከውጭ ለማስገባት ታወጣ የነበረውን በዓመት እስከ አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ የውጭ ምንዛሬ በማስቀረትና አገራዊ የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ረገድ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ትልቅ ታሪካዊ እመርታ አስመዝግቧል። ሀገሪቱ አሁን ላይ የስንዴ ምርትን ለሀገር ውስጥ ፍጆታ ማብቃት ብቻ ሳይሆን ወደ ውጭ ገበያ ኤክስፖርት ማድረግ ወደምትችልበት ደረጃ ተሸጋግራለች። በቅርብ የምርት ዘመናት ኢትዮጵያ 33 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ስንዴ በማምረት በአፍሪካ ቀዳሚዋ ስንዴ አምራች ሀገር ለመሆን የበቃች ሲሆን፣ ይህ ስኬት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ፣ ከአቮካዶና ሆርቲካልቸር እስከ አግሮ-ፕሮሰሲንግ ያሉ አዳዲስ አቅሞችን በመጠቀምና አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በመተግበር የሀገር ውስጥ አምራቾች ከዓለም አቀፍ ገበያ ጋር እንዲገናኙና አገራዊ የውጭ ምንዛሬ ገቢ እንዲያድግ አስችሏል። ይህም የመደመር እሳቤ የሀገር ውስጥ አቅምን በመጠቀም የውጭ ጥገኝነትን እንዴት እንደሚቀንስ በተግባር ያሳየበት ተጨባጭ ማሳያ ነው። በሌላ በኩል የተፈጥሮ ሀብትንና የከተሞችን አቅም ጥቅም ላይ ማዋል ባለመቻሉ ሲፈጠሩ የነበሩትን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅፋቶች ለመፍታት አዳዲስ ሀገራዊ የልማት ሞዴሎች በመተግበር ላይ ይገኛሉ። በዚህም ከተሞችን የዘመናዊና ጤናማ አኗኗር ማሳያ ማድረግ ተችሏል።በዋና ዋና ከተሞች የሚከናወኑት የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች፣ ነባር መጨናነቆችን፣ የመሰረተ ልማት እጥረቶችንና የከተማ አስተዳደር ጉድለቶችን በመቅረፍ ከተሞችን ዘመናዊ፣ ፅዱ፣ እና ለኑሮ ተስማሚ አድርገዋቸዋል። ይህም የከተሞችን ውበትና ደረጃ ከማሳደግ ባሻገር ለንግድ፣ ለቱሪዝም እና ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል። በተመሳሳይ ሁኔታ በገበታ ፕሮጀክቶች አማካይነት ያልተነኩ የተፈጥሮ ውበቶችንና ታሪካዊ ስፍራዎችን ወደ ኢኮኖሚያዊ ሀብትነት በመቀየር እንደ ወንጪ፣ ጎርጎራ፣ ኮይሻ፣ ሀላላ ኬላ እና ደምቢ ኢኮ-ሎጂ ያሉ ደረጃቸውን የጠበቁ የቱሪዝም መዳረሻዎች የሀገሪቱን የቱሪዝም ገፅታ ከመቀየር ባለፈ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥረዋል። ይህ የልማት ግንባታ ከመንግስት በጀት ብቻ ሳይሆን በህዝባዊ ተሳትፎና በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የታገዘ በመሆኑ የመደመርን የሀብት አጠቃቀም ጥበብ በግልጽ ያሳያል።በተለይም በክረምት ወራት የተከናወኑ በሺዎች የሚቆጠሩ አቅመ-ደካሞችን ቤቶች ማደስ፣ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል እና አዳዲስ የመማሪያ ክፍሎችን መገንባት የመንግስትን ከፍተኛ በጀት በማስቀረት የላቀ የካፒታል አቅም መፍጠር ችሏል። የአንድ ሀገር የእድገት ጉዞ የሚረጋገጠው የማህበረሰቡን አስተሳሰብ፣ የፖለቲካ ባህል እና የማህበራዊ ትስስር እሴቶችን በአዲስ መልክ በመገንባት እንደሆነ የመደመር እሳቤ በጥብቅ ያሰምርበታል። በኢትዮጵያ ወቅታዊ እውነታ ውስጥ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እና ሀገራዊ ምክክር ሀገሪቱን በጠንካራ መሰረት ላይ ለማቆም እየተተገበሩ ያሉ ተጨማሪ የመዋቅርና የአስተሳሰብ አምዶች ናቸው። የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የማህበራዊ ካፒታል ግንባታ እና የወጣትነት ሀይልን ለሀገር ግንባታ የማዋል ፍልስፍና በተግባር የገለጠ ስራ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ልዩነቶችን በኃይል፣በግጭት እና በጠመንጃ የመፍታት አደገኛ ልማድን በማስወገድ፤ በሰለጠነ፣ አሳታፊ እና በውይይት የማመን ባህል የመተካት ትልቅ መሰረት ተጥሏል። ይህም ቀጣይነት ላለው ሀገረ-መንግሥት ግንባታ እና ዘላቂ ሰላም የሚጠቅም የፖለቲካ ባህል ሽግግር የፈጠረ ሲሆን፣ ልዩነቶችን በመደመር ውበት የመቀየር ጥበብ ማሳያ ነው። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የገጠሟትን ዘመናዊና ታሪካዊ ፈተናዎች ወደ ልማትና ወደ ዘላቂ ስኬት የመቀየር ትልቅ አቅም እንዳላት በተግባር እያረጋገጠች ትገኛለች። በመደመር ፍልስፍና የሚመሩት እነዚህ ፕሮጀክቶች እና መዋቅራዊ ማሻሻያዎች ኢትዮጵያን በምስራቅ አፍሪካ እና በአፍሪካ አህጉር ውስጥ የምታደርገውን የማንሰራራት ጉዞ እውን የሚያደርጉ ናቸው። የኢትዮጵያ ነገ ብሩህ የሚሆነው ፈተናዎች በሌሉበት ሳይሆን፣ ያሉትን ፈተናዎች በመደመር እሳቤ ወደ ተሻገረ ዕድል የመቀየር አቅሟ እንደሆነ ይህ ታሪካዊ ጉዞ ይመሰክራል።
ልዩ ዘገባዎች
ከዓባይ እስከ ቀይ ባሕር
Oct 9, 2026 230
ነጋሪ መጽሔት የዓባይ ውሃ አጠቃቀምና የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት በስፋት ተንትናለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በመደመር መንግሥት ምሥረታ ላይ፣ “የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ያለ ባሕር በር እውን ሊሆን አይችልም” በማለት ሀገሪቱ የባሕር መዳረሻ እንድታገኝ በትጋት እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል። ይህ ጥረት በሰላማዊ ውይይት፣ በጋራ ተጠቃሚነትና በ“ሰጥቶ መቀበል” መርሕ እንደሚመራ በማስገንዘብ፣ ጉዳዩን ከአፍሪካ ቀንድ፣ ከቀይ ባሕርና ከመካከለኛው ምሥራቅ እየተለወጡ ካሉ የጂኦፖለቲካና የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ጋር አያይዘው አቅርበዋል። መጽሔቷም በመስከረም 2019 ዓ.ም. እትሟ “የኢትዮጵያ የትንሳኤ መንገድ፡ ከዓባይ እስከ ቀይ ባሕር ፖለቲካ የዘለቀው ፍጥጫ” በሚል ርዕስ ባቀረበችው ትንታኔ፣ የውሃ ሀብት፣ የባሕር መዳረሻ፣ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮችና የቀጣናዊ ደኅንነት ጉዳዮች በሀገራት መካከል ባለው የኃይል አሰላለፍ ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ ዳስሳለች። እንደ መጽሔቷ ትንታኔ፣ ዓባይና ቀይ ባሕር በተፈጥሮ የተለያዩ የውሃ አካላት ቢሆኑም፣ በዘመናዊው የጂኦፖለቲካ ስሌት ውስጥ በውሃ አጠቃቀም፣ በኢኮኖሚያዊ ጥቅም፣ በባሕር መዳረሻና በደኅንነት ጉዳዮች የተሳሰሩ ናቸው። የዓባይ ወንዝ ለኢትዮጵያና ለተፋሰሱ ሀገራት ለኃይልና የልማት ጥቅም ሲኖረው፣ ቀይ ባሕር ደግሞ አፍሪካን፣ እስያንና አውሮፓን የሚያገናኝ ወሳኝ የዓለም አቀፍ የንግድና የባሕር መተላለፊያ ነው። በተለይም የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ የዓባይ ውሃን በፍትሐዊነትና በጋራ ተጠቃሚነት የማስተዳደር ጥያቄና የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት በቀጣናው የፖለቲካና የደኅንነት ስሌቶች ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ መጽሔቷ በስፋት ተንትናለች። የ1929 እና የ1959 የውሃ ስምምነቶች የላይኛውን ተፋሰስ ሀገራትን ጥቅም በበቂ ሁኔታ እንዳልተካተቱ በመግለጽ፣ የወንዙ ውሃ አጠቃቀም በፍትሐዊነት፣ በትብብርና በጋራ ጥቅም ላይ በተመሠረተ ማዕቀፍ መመራት እንዳለበት አመልክታለች። ኢትዮጵያ በ1993 ዓ.ም በኋላ የባሕር በር መዳረሻዋን ማጣቷን ተከትሎ፣ ጉዳዩ ከኢኮኖሚያዊ ጥቅም ባለፈ ከብሔራዊ ደኅንነትና ከረጅም ጊዜ የልማት ፍላጎት ጋር እንደተያያዘ መጽሔቷ አትታለች። የባሕር በር መዳረሻ ማግኘት የንግድ ወጪን ለመቀነስ፣ የወደብ አማራጮችን ለማስፋትና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለመደገፍ ወሳኝ መሆኑንም አብራርታለች። በሌላ በኩል፣ ቀይ ባሕር ከእስያ፣ ከአፍሪካና ከአውሮፓ የንግድ መስመሮችን የሚያገናኝ ስትራቴጂካዊ የባሕር መተላለፊያ በመሆኑ፣ በአካባቢው ያለው የደኅንነት ሁኔታ ከአካባቢያዊ ግንኙነቶች ባለፈ ዓለም አቀፋዊ የንግድ ፍሰትን ይነካል። መጽሔቷ የቀይ ባሕር የጂኦፖለቲካ አስፈላጊነት ከስዊዝ ቦይና ከባብ-ኤል መንደብ የባሕር መተላለፊያ ጋር በማያያዝ የዳሰሰች ሲሆን፣ በአካባቢው የሚካሄዱ የኃይል ፉክክሮች የንግድና የደኅንነት ስጋቶችን እንደሚያባብሱ ተንትናለች። መጽሔቷ በትንታኔዋ የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት ከቀጣናው ሀገራት የፖለቲካ አቋሞች ጋር በማያያዝ የተለያዩ ትንታኔዎችን አቅርባለች። ሆኖም እነዚህ በመጽሔቷ የቀረቡ የፖለቲካ ትንታኔዎች ሲሆኑ፣ የተጠቀሱ አቋሞችንና ክሶችን ከተረጋገጡ እውነታዎች መለየት ያስፈልጋል። መጽሔቷ በዓባይ ውሃ አጠቃቀምና በባሕር መዳረሻ ጉዳይ ዙሪያ የሚነሱ አለመግባባቶች በግጭት ሳይሆን በውይይት፣ በድርድርና በጋራ ተጠቃሚነት መርሕ መፍትሔ ማግኘት እንዳለባቸው አጉልታለች። የውሃ ሀብትን በፍትሐዊነት ማስተዳደርና የባሕር መዳረሻ ጉዳይን በሰላማዊ ስምምነት መፍታት ለቀጣናዊ መረጋጋት፣ ለኢኮኖሚ ትብብርና ለዘላቂ ልማት ወሳኝ መሆናቸውን በትንታኔዋ አመልክታለች። የመጽሔቱ ሊንክ https://www.ena.et/web/negari/w/negari_9696604
ከአዲሱ መንግስት ምን ይጠበቃል?
Oct 5, 2026 392
ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት በሀገሪቷ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን የማስቀጠል፤ በተለይም የተጀመሩ ግዙፍ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችን ለስኬት ማብቃት ትልቁ የቤት ስራ ነው የሚሆነው። በከተሞች እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማትና የስማርት ሲቲ ግንባታ፣ የዲጂታል አገልግሎቶችን የማስፋት፣ የአረንጓዴ አሻራ ልማትን ማስቀጠል ሌላኛው ሀገራዊ ሃላፊነት ነው የሚሆነው። የኢትዮጵያ ልማት በከተሞች ጋር ብቻ የሚወሰን ባለመሆኑ በገጠር አካባቢዎች የተጀመሩ የገጠር ትራንስፎርሜሽን የልማት ስራዎችንም ማስቀጠል የግድ ይላል። የገጠር ትራንስፎርሜሽን ዋነኛ ዓላማም የገጠሩን ህዝብ አኗኗር ማዘመን፣ የመሠረተ ልማትና የመሰረታዊ አገልግሎት ተደራሽነትን ማሻሻል፣ የገጠር ኢኮኖሚን ማጠናከርና የገጠር ነዋሪዎችን ከዘመናዊ የምርትና የገበያ ሥርዓት ጋር ማስተሳሰር መሆን አለበት። ኢትዮጵያ በተፈጥሮ፣ በታሪክ፣ በባህልና በሃይማኖት የበለፀገች ሀገር በመሆኗ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን መፍጠር፣ ያሉትን የመጠበቅና የማልማት እንዲሁም ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ሀብቶችን መጠበቅ፣ የቱሪስት ቆይታን ማራዘምና ከቱሪዝም ጋር የተሳሰሩ የስራ እድሎችን የማስፋት ጉዳይ የአዲሱ መንግስት ዋነኛ ትኩረት ሆኖ ይቀጥላል። በግብርናው ዘርፍም በምርትና ምርታማነት፣ በመስኖ ልማት፣ በስንዴ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በቡና፣ በሆርቲካልቸርና በሌሎችም የግብርና ዘርፎች የተጀመሩ ስራዎች በዘላቂነት እንዲቀጥሉ ማድረግ ይጠበቃል። ከምርት መጨመር ባሻገር የግብርና ምርቶችን ማቀነባበር፣ የገበያ ትስስርን ማሻሻል፣ የማከማቻና የመጓጓዣ ስርዓትን ማዘመን እና የአርሶ አደሩን ገቢ የማሳደግ ጉዳይ ትኩረት ይፈልጋል። የምርትና ምርታማነት መጨመር በመጨረሻም ከውጭ የሚገቡ የምግብ ምርቶችን በመተካት፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ አቅም በማሳደግ ከተረጅነት ለመውጣት የሚደረገውን ጥረት ማሳካት ይጠበቅበታል። የማዕድን ልማት፣ ዲጂታላይዜሽንና የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን ጉዳይም ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ይሆናል። የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የምርትና የገበያ አቅርቦትን ማሳደግ፣ የአቅርቦት ሰንሰለትን ማሻሻል፣ ህገወጥ የገበያ አሰራሮችን መቆጣጠርና የዜጎችን የመግዛት አቅም ማሻሻል ይጠበቃል። የኑሮ ውድነት ችግር በአንድ መፍትሄ የሚፈታ ባለመሆኑ የገቢ፣ የምርት፣ የገበያና የፋይናንስ ፖሊሲዎችን በተቀናጀ መልኩ ማስኬድ ያስፈልጋል።
የአካታች ሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ፅኑ መሰረት
Oct 5, 2026 272
መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):- አዲሱ የመንግስት ምስረታ - አካታች የፖለቲካ ስርአት ግንባታ መሰረት ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ በምክር ቤት አብላጫ መቀመጫ ያገኘው ብልጽግና ፓርቲ መንግስት የመመስረት ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ በዛሬው እለት ይሄው የሚከናወን ይሆናል። በፓርላማው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መቀመጫ ያገኙ በመሆኑ የፖለቲካ ክርክሮችና የሃሳብ ብዝሃነት የሚስተናገዱበት እንደሚሆንም ይጠበቃል። በኢትዮጵያ አካታችና አሳታፊ የፖለቲካ ስርአት ግንባታ መሰረት ያኖረው አዲሱ የመንግስት ምስረታ ሂደት የክልሎች ተጠናቆ በዛሬው እለት የፌዴራል መንግስት ምስረታ እውን ይሆናል። ባለፉት ዓመታት የተመዘገበው የአካታችነት ስኬት የመንግሥት ከፍተኛ የአመራር እርከኖች፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤትና የፍትህ ተቋማት አመራሮች ላይ የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮችን፣ የሴቶችንና የወጣቶችን ፍትሃዊ ስብጥር በተግባር ማሳየት ያስቻለ ነው። ከባለፉት አምስት አመታት ተሞክሮ በመነሳትም የዘንድሮው ምርጫ በብዙ መስፈርቶች ዴሞክራሲያዊ፣ አሳታፊ እና አካታች መሆኑን በተግባር ያሳየና የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ፅኑ መሰረት ያኖረ ሆኗል። በተቋማዊ አካታችነትና ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር በተወሰዱ እርምጃዎችም ጉልህ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ሁሉንም የፖለቲካና የኅብረተሰብ ክፍሎች ያቀፈው ሀገራዊ የምክክር ሂደት በሀገሪቷ የቆዩ ልዩነቶችን በምክክር ለመፍታት አዲስ ምእራፍ የከፈተ ሆኗል። ከዚህ ጎን ለጎን የጽንሰ-ሐሳብ፣ የቋንቋና የባህል ስብጥሮችን ያከበሩ የትምህርትና የባህል ፖሊሲዎች መተግበራቸው፣ ዜጎች በቋንቋቸው የመማርና አገልግሎት የማግኘት መብታቸው እንዲሰፋ በማድረግ ረገድም ትልቅ ስኬት ታይቷል። በመሆኑም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አብላጫ ድምፅ ያገኘው የብልፅግና ፓርቲ የሚያቋቁመው አዲሱ መንግስት በቀጣይ ሁለንተናዊ አካታችነትን በማረጋገጥ ረገድ ብዙ እንደሚሰራ ይጠበቃል። ገዢው ፓርቲ መወዳደር የሚችልባቸውን አካባቢዎች በመተው ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እድሉን መስጠቱ በምክር ቤቱ የተለያዩ ድምፆች እንዲስተጋቡ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ሆኗል። በመሆኑም ጠቅላላ ምርጫው የፖለቲካ ተሳታፊነትንና ውክልናን በማስፋት ረገድ ጉልህ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነበር ማለት ይቻላል። በተጨማሪም በውሳኔ ሰጪነትና በፖለቲካ ውድድር ውስጥ የሴቶች፣ የወጣቶችና የልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ እንዲያድግ በመደረጉ ህዝባዊ ወካይነት ያለው የምርጫ ሂደትን ለማከናወን አስችሏል። ምርጫ አስተዳደሩንና አሰራሩን አሳታፊና ፍትሃዊ በማድረግ ረገድ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል የታዩት እርምጃዎች ሌላው የአካታችነት ማሳያዎች ናቸው። የድምፅ መስጫ ጣቢያዎችን ተዳራሽ ማድረግ፣ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሆኑ የምርጫ ግብዓቶችን ማዘጋጀት እና በምርጫ ታዛቢነት የሲቪክ ማህበራትን፣ የሀገር ውስጥና የውጪ ምርጫ ታዛቢዎችን ማሳተፍ ተችሏል። ይህም የህብረተሰቡ ልዩ ልዩ ክፍሎች ያለምንም ገደብ የመምረጥ መብታቸውን እንዲጠቀሙና በሂደቱ ላይ ያላቸው እምነት እንዲጎለብት አድርጓል። በመሆኑም በዛሬው እለት የሚመሰረተው መንግሥት ልዩ ልዩ የፖለቲካና የማህበረሰብ ክፍሎችን ድምፅ በማስተናገድና ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠር ጠንካራ የሀገረ መንግስት ግንባታ መሰረት የሚያኖር እንደሚሆን ይጠበቃል።
የመደመር መንግሥት-የብሔራዊ ጥቅም ዘብ
Oct 5, 2026 280
ኢትዮጵያ ዛሬ አዲስ መንግሥት ትመሠርታለች።ይህ መንግሥት የዛሬውን ትውልድ ብቻ ሳይሆን፤የመጪውንም ትውልድ ፍላጎት በጽኑ መሠረት ላይ የሚያቆም ሥራ የሚሠራ ነው። አዲሱ መንግሥት ትልቅ የሕዝብ አደራ የሚቀበልና የነገዋን ኢትዮጵያ በከፍታ ላይ የሚያስቀምጥ እንደሚሆን እሙን ነው። ኢትዮጵያ በታሪኳ እጅግ ውስብስብ የሆኑ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ፈተናዎች አልፋ ዛሬ አዲስ የምዕራፍ ላይ ትገኛለች። አዲሱ መንግስት ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን፣ ሉዓላዊነቷን እና የሕዝቦቿን የጋራ እድገት ለማረጋገጥ ባደረገችው ያላሰለሰ ጥረት ውስጥ ቀጣይ ጉዞዋን በተሻለ መልኩ የሚያስቀጥል መንግሥት ይሆናል። ይህ ታሪካዊ ጉዞ በቀላሉ የተገኘ አልነበረም። ሕዝቡ የወደፊት ዕጣ ፈንታውን በቃላት ሳይሆን በተግባር ለመወሰን፣ መብቱን በድምፁ በመጠቀም ታሪካዊ አደራውን ለመወጣት ውስብስብ ፈተናዎችን አልፏል። በፈተና ውስጥ አልፎ የሰጠው ድምፅ ተራ የምርጫ ሂደት ሳይሆን፤ የሀገርን ሕልውና የማስከበር፣የብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ እና ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር የማስረከብ ጽኑ ፍላጎት መግለጫ ነበር። ዛሬ የሚመሠረተው አዲስ መንግሥት የዚሁ የሕዝብ አደራና የጽናት ውጤት ነው።ይህ የመደመር መንግሥት የሀገሪቱን ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ እና ቀጣናዊ ጥቅሞች ያስከብራል፤ የኢትዮጵያን የሉዓላዊ ድንበር እና የወደፊት ሕልውና በጠንካራ ዲፕሎማሲና በውስጥ አንድነት ይጠብቃል። የዛሬዎቹን አጣዳፊ ጥያቄዎች ለመመለስ ብቻ ሳይሆን፣ መጪው ትውልድ የሚተማመንባት፣ በኢኮኖሚ የበለጸገች እና ብሔራዊ ጥቅሟን የምታስጠብቅ ሀገር መንግስት ይመሰርታል። ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን በሁለት ውኃዎች ላይ አድርጋ በጽናት እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች። የአባይን ውኃ ለሁለንተናዊ እድገቷ መጠቀም ጀምራለች፤ ሕዳሴንም ጨርሳ የማድረግ አቅሟን አረጋግጣለች።ይህ ጉዞ ቀላል አልነበረም፤ሀገሪቱ በውስጥና በውጭ በርካታ ፈተናዎችን፣ ተፅዕኖዎችንና ጫናዎችን አልፋ ነው እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰችው። ዛሬ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን የበለጠ የሚያስከብርላትን የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ አንሥታ ጉዳዩን ዓለም አቀፍ አጀንዳ አድርጋዋለች። የመደመር መንግሥት ኢትዮጵያ ኢ-ፍትሐዊና ባልተገባ መልኩ ያጣችውን የባሕር በሯን እንድታገኝ በትክክለኛው መንገድ ይጓዛል፤ ግቡንም ያሳካል። ዛሬ የሚመሠረተው አዲስ መንግሥት ለነገዋ ኢትዮጵያ ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ መደላደል የሚፈጥር ነው፤ የሀገሪቱን የባሕር በር ፍላጎት፣የዓባይ ወንዝ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት፣የውስጥ ደኅንነትና የኢኮኖሚ ነፃነት አፅንኦት ሰጥቶ ማስጠበቅ ነው።ልዩነቶችን በማቀናጀትና አቅሞችን በመደመር የሀገርን ሕልውና አስተማማኝ ማድረግም ሌላው ከመደመር መንግስት የሚጠበቅ ነው። ከምንም በላይ ኢትዮጵያ የበርካታ ዘመናት ታሪካዊ ጠላቶቿንና ተላላኪዎቻቸውን እኩይ ሴራ ትበጣጥሳለች።የውስጥና የውጭ ጫናዎችን በህዝቦቿ ጽናት፣የአንድነት መንፈስና የማይናወጥ ሀገራዊ ወኔ እያሸነፈች ትቀጥላለች።ለነፃነቷና ሉዓላዊነቷ ሳትበገር በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ወደ ላቀ የልማት፣ የብልፅግናና የዕድገት ከፍታ ወደ ፊት መገስገሷን ትቀጥላለች። ዛሬ የሚመሰረተው አዲሱ የመደመር መንግሥትም የሕዝቡን ተስፋና እምነት ወደ መሬት በማውረድ፣የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም አክብሮና አስከብሮ ለመጪው ትውልድ የምትመችና በጽኑ መሠረት ላይ የተገነባች ሀገርን የማስረከብ ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት።
መጣጥፍ
ባህር ዳር የጣና ፎረም እንግዶቿን ለመቀበል ተዘጋጅታለች
Oct 14, 2026 94
ከኢትዮጵያ የተፈጥሮ ውበት ማሳያዎች መካከል የምትጠቀሰው፣ የጣና ሐይቅ ፈርጥና የአባይ ወንዝ መሰረት የሆነችው ባህር ዳር ለ12ኛው የጣና ፎረም ታዳሚዎቿን በክብር ለመቀበል እጇን ዘርግታ እየጠበቀች ትገኛለች። በጣና ሐይቅ ውበት፣ በዛንባባዎቿ አጀብ፣ በኮሪደር ልማቷ ፈክታና ደምቃ እንግዶቿን አርሂቡ እያለች ትገኛለች። የጣና ፎረም የተሰናዳባት ባህር ዳር ከተማ ከመስተንግዶም በላይ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት፣ የቱሪዝም አቅሟንና የሕዝቡን እንግዳ ተቀባይነት የምታሳይበት መልካም አጋጣሚ ነው ማለት ይቻላል። በዚሁ መሰረትም የጣናን ውበት በጣናነሽ እና ሌሎችም ዘመናዊ ጀልባዎቿ ለማስቃኘት፣ የቱሪዝም መስህቦቿን ለማስጎብኘት፣ በኢትዮጵያዊ መስተንግዶ አብልቶና አጠጥቶ አስደስቶ ለመሸኘት የተሟላ ዝግጅት ተደርጓል። ከጥቅምት 13 እስከ 15 ቀን 2019 ዓ.ም. «በአፍሪካ የሰላም መንገዶች፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የጂኦፖለቲካ ለውጥ» በሚል መሪ ሐሳብ የሚካሄደው 12ኛው የጣና ፎረም ከ250 በላይ ተሳታፊዎች እንደሚገኙበት ይጠበቃል። በመድረኩም የአገራት መሪዎች፣ የተቋማት ኃላፊዎች፣ የቀድሞ መሪዎች፣ ምሁራንና ባለሙያዎች የሚመክሩ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ታላቅ መድረክ ላይ የታደሙ እንግዶች የጣና ሐይቅን ልዩ ውበትና የቱሪዝም አቅም፣ የአካባቢውን የታሪክ፣ የባህልና መንፈሳዊ ቅርሶች መስህብ የመጎብኘት እድል ይኖራቸዋል። በተጨማሪም የከተማዋ ኮሪደር ልማት፣ የአረንጓዴ ስፍራዎችና የመዝናኛ ቦታዎች ቀልብን የሚገዙ ሆነው ያገኟቸዋል። በመሆኑም ባህር ዳር ከጣና ፎረም በተጓዳኝ የቱሪዝም አቅሟን የምታስተዋውቅበት እንደሚሆን ይጠበቃል። የአንድ ከተማ ውበት በሕንፃዎቿ፣ በመንገዶቿና በተፈጥሮ ሀብቷ ብቻ አይመዘንም። ለእንግዶቿ በምታሳየው አክብሮት፣ በነዋሪዎቿ ደግነትና በሕዝቧ የባህል እሴቶችም ጭምር ይገለጻል። በዚህ ረገድ የባህር ዳርና አካባቢው ሕዝብ ያለው እንግዳ ተቀባይነት ለከተማዋ ሌላ ተጨማሪ አቅም ሆኖ እናገኘዋለን። እንግዳን ተቀብሎ በፍቅርና በአክብሮት ማስተናገድ፣ መንከባከብና መንገድ ማመላከት የኢትዮጵያውያን የቆየና ይበልጥ እየዳበረ የመጣ ውብ ባህል ነው። በጣና ፎረምም ይህ እሴት በተግባር የሚገለጽበት በመሆኑ የባህር ዳርና አካባቢው ህዝብ ሽር ጉድ ብሎ እንግዶቹን እየተጠባበቀ ይገኛል። የጉባኤው ውጤት በውይይት አዳራሹ ብቻ ሳይወሰን፣ በከተማዋ ልማት፣ በአካባቢው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴና በቱሪዝም ዘርፍ አዎንታዊ ሚና ይኖረዋል። በመሆኑም የከተማዋ አስተዳደሩ፣ የቱሪዝምና የንግድ ዘርፎች፣ የመስተንግዶ ተቋማትና ማኅበረሰቡ በቅንጅት መሥራት ወሳኝ ነው። የከተማዋ ውበትና የሕዝቧ እንግዳ ተቀባይነት ከፎረሙ ዓላማ ጋር ተደምሮ መልካም ስም የሚገነባበት ይሆናል። በጣና ሐይቅ ዳርቻ በውበት የምትደምቀው፣ በልማት የምትለወጠውና በእንግዳ ተቀባይነቷ የምትታወቀው ባህር ዳር እንግዶቿን በክብር ለመቀበል ዝግጁ ነች። የጣና ፎረም ታዳሚዎችም ከጉባኤው ባሻገር የጣናን ውበት እያደነቁ እየተዝናኑ መልካም ትዝታ የሚያተርፉ ይሆናል። የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አባይ መንግስቴ፤ በባህር ዳር የጣና ፎረም ታዳሚዎችን ተቀብሎ ለማስተናገድ የተሟላ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል። በባህርዳር ከተማ የሚገኙ ሆቴሎችና ሌሎች የአገልግሎት መስጫ ተቋማትም ለፎረሙ የሚመጡ እንግዶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጁ ስለመሆናቸው ተናግረዋል።
የሸማ ጥበብ-የጋሞዎች ባህላዊ ማንነት እና የኢኮኖሚ መሠረት
Oct 11, 2026 278
አርባ ምንጭ፤ ጥቅምት 1 /2019 (ኢዜአ):- የሸማ ጥበብ-- የጋሞዎች ባህላዊ ማንነት እና የኢኮኖሚ መሠረት በሳሙኤል አየነው (ኢዜአ አርባ ምንጭ ቅርንጫፍ) በኢትዮጵያ ሀገር በቀል ዕውቀቶችና ጥበባት ታሪክ ውስጥ የጋሞ ማኅበረሰብ የሸማ ሥራ ልዩና የጎላ ስፍራ አለው። ከጥንት ጀምሮ ከጥጥ ምርት ጋር የተሳሰረው ይህ ዕውቀት፣ ልብስን ከመልበስ ፍላጎት አልፎ የትውልድ ማንነት፣ የውበት መግለጫ እና የታሪክ ማኅደር ሆኖ ዘልቋል። በጥጥ ፈትል ላይ በሚያርፉ ደማቅ ቀለማትና ልዩ ንድፎች የሚታወቀው የጋሞ የሸማ ጥበብ፣ እንደ «ዱንጉዛ» ያሉ የክብር አልባሳትን ለአለም በማስተዋወቅ አርባ ምንጭንና አካባቢዋን "የጥበብ ምድር" የሚያስብል እና የታሪክ ባለቤት አድርጓቸዋል። የጋሞ የሸማ ጥበብ ተራ የሙያ ክህሎት ሳይሆን በቤተሰብ አባላት የጋራ ድርሻና ትብብር የሚከናወን፣ ትውልድ ከትውልድ የሚወርሰው ሕያው ባህላዊ እሴት ነው። ሴቶች ጥጥ በመፍተል፣ ወንዶች በዕውቀታቸው በመሸመን፣ ህፃናት ደግሞ በመደወር የሚካፈሉበት ይህ የሙያ ክፍፍል ማኅበራዊ ትስስርን ያጠናክራል። ከባህላዊ መግለጫነቱ ባሻገር የጋሞዎች የሸማ ጥበብ ለአካባቢውና ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክት የሀብት ምንጭ ነው። ሙሉ በሙሉ በእጅ በሚከናወነውና ሳይበረዝ በቆየው በዚህ ሀገር በቀል ጥበብ የተመረቱ አልባሳትና ብርድ ልብሶች፣ በአሁኑ ወቅት ከሀገር ውስጥ ገበያ አልፈው በዘመናዊ ዲዛይኖች በመታገዝ በአውሮፓና በአሜሪካ ገበያዎች ዘንድ ትልቅ አድናቆትን አትርፈዋል። ይህም ጥበቡ ለብዙዎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ረገድ ጉልህ ድርሻ እንዲኖረው አድርጎታል። በሀገራችን ከሚታወቁ ሀገር በቀል ዕውቀቶች መካከል አንዱ የጋሞዎች መገለጫ የሆነው የሸማ ጥበብ ነው። የሸማ ጥበብ ደግሞ ከጥጥ ምርት የሚሠራ በመሆኑ ጋሞዎች ከጥጥ ምርት ጋር ያላቸው ቁርኝት ከጥንት ጀምሮ የዘለቀ ነው። ጥጥ ለጋሞዎች ከልብስ እስከ ጉርስ፣ ከጉርስ እስከ ውርስ በመሆን ትውልድ ተሻግሮ እያገለገለ የሚገኝ ሀብት ነው። በተለያየ መልክ በመሠራቱ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ዜጎችን ቀልብ እያማለለ ያለው የሸማ ጥበብ "ጋሞ የጥበብ ምድር" ተብሎ እንዲጠራም ምክንያት ሆኗል። ይህን ተከትሎ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በ1890ዎቹ የጥበብ አልባሳት እንዲሠሩላቸው በሚል አፄ ምኒልክ በቁጥር 50 የሚሆኑ የሸማ ጥበብ ያላቸውን ጋሞዎች ከዶርዜ አካባቢ ወደ መሐል ሀገር እንደወሰዷቸው ይነገራል። በዚህ መልክ የሸማ ጥበብና ዕውቀቱ አዲስ አበባን ጨምሮ ወደ መሐል ሀገር እና ሌሎች ትላልቅ ከተሞች የተስፋፋ ሲሆን፣ የአርባ ምንጭ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካም ይህን ፀጋ ተከትሎ ሊመሠረት ችሏል። በግብርና ልማት እና በሽመና የሚተዳደረው የጋሞ ማህበረሰብ በማሳው ጥጥን በስፋት ማምረት ከህልውናው ጋር የተያያዘ በመሆኑ ዛሬም ድረስ በአካባቢው ጥጥ በስፋት እየተመረተ ይገኛል። የጋሞዎች የሸማ ጥበብ በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ ስፍራ ያለው፣ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረና ማንነትን የሚገልጽ ሀገር በቀል ዕውቀት ነው። በጥጥ ከሚሠሩ ባህላዊ አልባሳት መካከል አንዱ የማንነታቸው መገለጫ የሆነው ‹‹ዱንጉዛ›› ነው። ይህም የጋሞ ማህበረሰብ ታዋቂና የክብር ልብስ ሲሆን፣ ቀይ፣ ጥቁርና ቢጫ የመሳሰሉ ደማቅ ቀለሞችንና ልዩ ንድፎችን የያዘ ነው። ከዚህ በተጨማሪ እንደ ቁሌ፣ አሰራ፣ ፈርዣ፣ ቡሉኮ፣ ጋቢ፣ ኩታ፣ ባርኔጣ እና ያኖ የመሳሰሉ የተለያዩ የባህል ልብሶችና ብርድ ልብሶች ይመረታሉ። ልብሶቹ ውበትን ከማንጸባረቅ ባለፈ እንደ "ዮ ማስቃላ" ባሉ የዘመን መለወጫ በዓላት ከፍተኛ ቦታ አላቸው። የሸማ ጥበብ ለብዙ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠረ፣ የቱሪዝም መሳቢያ እና የጋሞ ህዝብ የኢኮኖሚ መሠረት በመሆኑ ልጆች ከወላጆች የሚወርሱት ነገር ቢኖር አንዱ የሸማ ጥበብ ነው። የሸማ ሥራ የሚከናወነው እንደ ቤተሰብ የሥራ ድርሻ በመከፋፈል ሲሆን፣ በዚህም ሴቶች ጥጥ በመፍተል፣ ወንዶች በመሸመን እንዲሁም ልጆች በመደወር ኃላፊነታቸውን ይወጣሉ። የሸማ ጥበቡን ልዩ የሚያደርገው በእጅ ብቻ የሚሠራ፣ ያልተበረዘና ያልተከለሰ ሀገር በቀል ሀብት መሆኑ ነው። ይህም በአሁኑ ሰዓት በዘመናዊ ዲዛይን በመታገዝ ከሀገር ውስጥ እስከ አውሮፓና አሜሪካ ገበያዎች በስፋት የሚገኝ ሲሆን፣ የሥራ ዕድል በመፍጠርና የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ረገድ የራሱን ድርሻ እያበረከተ ይገኛል። በቅርቡ 6ኛው አለም አቀፍ የጥጥ ቀን ''ጥጥ ለበጎነት፡ በንግድ፣ እሴት በመጨመር እና በትብብር የበለጸገ ሕይወትን መገንባት'' በሚል መሪ ሐሳብ በታሽከንት፣ ኡዝቤኪስታን የተከበረ ሲሆን የጥጥ ምርትን ከጥሬ ዕቃነት ባሻገር እሴት በመጨመር ወደ ከፍተኛ ውጤት ማሸጋገርን፣ የዓለም አቀፍ ንግድ ዕድሎችን ማስፋፋትን እና የአምራች ማኅበረሰቦችን የኢኮኖሚ ተደራሽነት ማሳደግን ያለመ ውይይት በማካሄድ መጠናቀቁ ይታወሳል።