ቀጥታ፡

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰበትን ድል አስመዘገበ  

አዲስ አበባ፤ ጥር 8 /2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ እዮብ ገብረማርያም እና ሀሰን ሁሴን የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ቢኒያም ካሳሁን ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል።


 

ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ25 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል።

በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ17 ነጥብ ከነበረበት 12ኛ ደረጃ ወደ 13ኛ ዝቅ ብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም