ቀጥታ፡

በብሔረሰብ አሥተዳደሩ በሞዴል መንደሮች የገጠር ኮሪደር ልማት ሥራ ይከናወናል

ሰቆጣ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፡- የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በሰባት ሞዴል መንደሮች የገጠር ኮሪደር ልማት ሥራ ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታወቀ።

በአሥተዳደሩ የገጠር ኮሪደር ልማትን ለማሳካት ያለመ የንቅናቄ መድረክ ዛሬ በሰቆጣ ከተማ ተካሂዷል።

የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የመንገድ መምሪያ ኃላፊ ፀጋው እሸቴ በዚሁ ወቅት፤ ከዚህ ወር መጨረሻ ጀምሮ ወደ ተግባር የሚገባው የገጠር ኮሪደር ልማት በሕዝብ ተሳትፎ ታጅቦ ይከናወናል ብለዋል።


 

በሁሉም ወረዳዎች ሰባት ሞዴል መንደሮችን በመለየት የገጠር ኮሪደር ልማት እንደሚከናወን የገለጹት ደግሞ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አዲስ ወልዴ ናቸው።

በገጠር ኮሪደር ልማት ቅንጅታዊ አሠራርን በመከተል የአርሶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል እንደሚሠራ ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም