ቀጥታ፡

በጋምቤላ ከተማና አካባቢው የጥቅምት በዓልን በድምቀት ለማክበር ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው

ጋምቤላ፤ ጥር 9/2018(ኢዜአ)፡-በጋምቤላ ከተማና አካባቢው የጥቅምት በዓልን በድምቀት ለማክበር የተለያዩ ዝግጅቶች እያደረጉ መሆናቸውን በከተማው በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተሰማሩ ወጣቶች ገለጹ።

የጥምቅት በዓል በልዩ ድምቅትና ድባብ ከሚከበርባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ ጋምቤላ ነው።

ዘንድሮም በዓሉ በተለመደው ድምቀት እንዲከበር የጋምቤላ ከተማና አካባቢው ወጣቶች በዓሉ የሚከበርባቸውን ቦታዎች የማስዋብና የማስተካከል ሥራዎች እያከናወኑ መሆናቸውን ለኢዜአ ገልጸዋል።


 

በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ሲሳተፉ ካገኘናቸው ወጣቶች መካከል ወጣት ተስፋዬ ድልነሳው በሰጠው አስተያየት የጥምቀት በዓል በልዩ ድምቀትና ድባብ እንዲከበር በጋምቤላ ከተማ የተለያዩ የበጎ ፋቃድ አገልግሎት ሥራዎችን እያከናወኑ መሆናቸውን ተናግሯል።

በተለይም ታቦታቱ የሚያልፉባቸው መንገዶችን የማጽዳትና ማስተካከልን ጨምሮ ከተማውን በሰንደቅ ዓላማ የማስዋብና የማሸብረቅ ሥራዎች እያከናወኑ መሆናቸው ገልፅዋል።

በአሉ በድቀምትና በስኬት እንዲከበር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎችን እያከናወኑ መሆናቸውን የገለጸው ደግሞ ሌላው የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ተሳታፊ ወጣት ሚስጥር ኢስጢፋኖስ ነው።


 

ታቦታቱ የሚያልፉባቸውን መንገዶችን የማስተካከልና አካባቢውን የማጽዳት ስራዎችን እያከናወኑ መሆናቸውንና በቀጣይ በበዓሉ ወቅትም ሁለንተናዊ ድጋፋ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ገልጿል።

ሌላው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተሳታፊ ወጣት አሸናፊ ገብረማሪያም በሰጠው አስተያየት ከጥር 1 ቀን 2018 ጀምሮ የአካባቢው ወጣቶች የተለያዩ የበጎ ፈቃድ ሥራዎችን ሲያከናወኑ መቆየታቸውን ተናግሯል።


 

በተለይም የጥምቀት በዓል የሚከበረበትን ቦታ በአፈር የመደልደል፣ በሰንደቅ ዓላማዎች የማስዋብና የማሸብረቅ ተግባራትን እያከናወኑ እንደሚገኙ ገልጿል።

የጋምቤላ ከተማ የመድኃኒያለም ቤተክርስቲያን አስተዳደር መላከ ፀሐይ ቄስ እሸቴ አስማረ እንዳሉት የከተራና ጥምቀት በዓልን በድምቅት ለማክበር ከጥር 1 ቀን 2018 ጀምሮ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ተናግረዋል። 


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም