ቀጥታ፡

የፋሲል እግር ኳስ ክለብ የጎዳና ላይ የቤተሰብ የሩጫ ውድድር መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2018 (ኢዜ)፡- 7ኛው ዙር የፋሲል እግር ኳስ ክለብ የጎዳና ላይ የቤተሰብ የሩጫ ውድድር በጎንደር ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

ውድድሩን ያስጀመሩት የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ እና የፋሲል እግር ኳስ ክለብ ፕሬዚዳንት ቻላቸው ዳኘው ናቸው።


 

በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የጎንደር ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተስፋ መኮንን፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አሥራት አፀደ ወይን (ዶ/ር)፣ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የፋሲል ከነማ የስፖርት ደጋፊ ማኅበር  የሥራ ኃላፊዎችና ደጋፊዎች ተገኝተዋል።  


 

በሩጫ ውድድሩ ከ12 ሺህ በላይ ሰዎች እንደሚሳተፉ እና በክለቡ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብርም 6 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱ ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም