ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 54 ሚሊየን 57 ሺህ 861 መራጮች ተመዝግበዋል
May 29, 2026 245
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21/2018(ኢዜአ)፦ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 54 ሚሊየን 57 ሺህ 861 መራጮች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሃይሉ፤ በመጪው ሰኞ የሚካሄደውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም ምርጫውን ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጸዋል። ቦርዱ ለመጀመሪያ ጊዜ ባዘጋጀው የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር መድረክ ፓርቲዎች ፕሮግራማቸውንና አማራጭ ሃሳባቸውን ለመራጩ ህዝብ እንዲያቀርቡ መደረጉን አብራርተዋል። በመመሪያው መሰረትም ለፖለቲካ ፓርቲዎች የአየር ሰዓት ድልድል ተደርጎ ፓርቲዎች ሃሳቦቻቸውን ለህዝብ ተደራሽ ማድረጋቸውንም ጠቁመዋል። የመራጮች ትምህርት ለሚሰጡ 169 ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ቦርዱ ፈቃድ መስጠቱን ጠቁመው ምርጫውን ለሚታዘቡ 55 የሀገር ውስጥ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንዲታዘቡ ፈቃድ መስጠቱን አስረድተዋል። ከአፍሪካ ህብረት 59 አባላት ያሉት ታዛቢዎች ቡድን መምጣቱን ገልጸው፤ ከኢጋድ ደግሞ 26 አባላት ያሉት ቡድን እንደሚታዘቡም አክለዋል። ቦርዱ በጥቅሉ ለ68 መገናኛ ብዙሃን ምርጫውን እንዲዘግቡ ፈቃድ መስጠቱን ጠቁመው ከዚሁ ወስጥ 56 የሀገር ውስጥ ሲሆኑ 12 ደግሞ የውጭ መገናኛ ብዙሃን መሆናቸውን ገልፀዋል። የቁሳቁስ ስርጭቱ ቀድሞ በተያዘው መርሐ ግብር መሠረት በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑንና የቁሳቁስ ስርጭቱ በተያዘለት ጊዜ ሙሉ በሙሉ ተደራሽ ሆኖ የምርጫ ጣቢያዎች ለምርጫው ሙሉ ዝግጅታቸውን እንደሚያጠናቅቁ ሰብሳቢዋ ተናግረዋል። በምርጫው ድምጽ ለመስጠት 54 ሚሊየን 57 ሺህ 861 መራጮች መመዝገባቸውን ጠቁመዋል። በመመሪያው መሰረትም የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ መቋቋሙን ሰብሳቢዋ ጨምረው ገልጸዋል።
ለምርጫው ስኬታማነት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አደርጋለሁ - ኢጋድ
May 29, 2026 194
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21/2018 (ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) በኢትዮጵያ ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማነት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸ። ምርጫው ነጻ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ፣ ተዓማኒ እና አካታች እንዲሆን የድርሻውን እንደሚወጣም አስታውቋል። በኢጋድ የኢትዮጵያ ምርጫ ታዛቢ ተልዕኮ ሰብሳቢ ስፔሺዮሳ ዋንዲራ ካዚብዌ(ዶ/ር) የተመራ ልዑክ ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት የምርጫ ትብብር ጋር በመሆን የምርጫውን ሂደትን መደገፍ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክሯል።   በውይይቱም የሲቪል ማህበረሰቦች የዴሞክራሲ ሂደቶችን፣ የምርጫ ዝግጅት እና የአካባቢ ምርጫን በመታዘብ ረገድ የሚኖራቸውን ሚና በተመለከተ ምክክር መደረጉን ኢጋድ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል። ተዓማኒ እና አካታች ምርጫ ለማካሄድ የመራጮች የሲቪክ ትምህርት አስፈላጊ መሆኑ በውይይቱ መነሳቱን ተጠቅሷል፡፡ ውይይቱ ኢጋድ በኢትዮጵያ ነጻ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ፣ ተዓማኒ እና አካታች ምርጫ እንዲኖር የሚያደርገው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አካል መሆኑንም አስታውቋል፡፡
ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት እየተጠናቀቀ ነው
May 29, 2026 388
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21/2018(ኢዜአ)፦ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የምርጫ ቁሳቁሶችን የማሰራጨት ሥራም በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሃይሉ፤ በመጪው ሰኞ የሚካሄደውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም ምርጫውን ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት እየተጠናቀቀ ነው ብለዋል። ቦርዱ ለመጀመሪያ ጊዜ ባዘጋጀው የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር መድረክም ፓርቲዎች ፕሮግራማቸውንና አማራጭ ሃሳባቸውን ለመራጩ ህዝብ እንዲያቀርቡ መደረጉን አብራርተዋል። በመመሪያው መሰረትም ለፖለቲካ ፓርቲዎች የአየር ሰዓት ድልድል ተደርጎ ፓርቲዎች ሃሳቦቻቸውን ለህዝብ ተደራሽ እንዲሆን መደረጉንም ጠቅሰዋል። የመራጮች ትምህርት ለሚሰጡ 169 ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ቦርዱ ፈቃድ መስጠቱን ጠቁመው፤ ምርጫውን ለሚታዘቡ 55 የሀገር ውስጥ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንዲታዘቡ ፈቃድ መስጠቱንም ተናግረዋል። ከአፍሪካ ህብረት 59 አባላት ያሉት ታዛቢዎች ቡድን መምጣቱን ገልጸው፤ ከኢጋድ ደግሞ 26 አባላት ያሉት ቡድን እንደሚታዘቡም አክለዋል። ቦርዱ በጥቅሉ ለ68 መገናኛ ብዙሃን ምርጫውን እንዲዘግቡ ፈቃድ መስጠቱን ጠቁመው፤ ከዚሁ ወስጥ 56 የሀገር ውስጥ ሲሆኑ 12 ደግሞ የውጭ መገናኛ ብዙሃን መሆናቸውን ገልፀዋል። የቁሳቁስ ስርጭቱ ቀድሞ በተያዘው መርሐ ግብር መሠረት በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመው፤ የቁሳቁስ ስርጭቱ በተያዘለት ጊዜ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ የምርጫ ጣቢያዎችም ለምርጫው ሙሉ ዝግጅታቸውን እንደሚያጠናቅቁም ሰብሳቢዋ አስታውቀዋል።
በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ ለመስጠት ተዘጋጅተናል
May 29, 2026 259
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21/2018(ኢዜአ)፦ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን በሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ይበጀናል ለሚሉት ፓርቲ ድምጻቸውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም መራጮች ድምፅ የሚሰጡበት ቀን ነው። የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫ ቦርድ ባዘጋጀው መድረክ ለምርጫ ክርክሩ በ19 ዙር ያካሄደ ሲሆን፤ ክርክሩም በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም ዲጂታል አማራጮች ለመራጩ ህዝብ ተደራሽ ተደርጓል። የፊታችን ሰኞ በሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዙሪያ ኢዜአ ያነጋገራቸው የመዲናዋ ነዋሪዎች እንደገለጹት፤ ይበጀናል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ ዕለቷን በጉጉት እየተጠባበቁ መሆናቸውን ገልጸዋል። ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል እሸቱ ያደታ፤ በምርጫ ወቅት የአንድ ሰው ድምፅ ለሀገር ግንባታና ለዴሞክራሲ ሥርዓት መጎልበት ወሳኝ ሚና እንዳለው ተናግረዋል። ነገ ሀገርን የሚጠቅመውንና የሚመራውን ለይቶ መምረጥ የሚያስችላቸውን ዝግጅት እንዳጠናቀቁም ገልጸዋል። ሌላኛዋ የመዲናዋ ነዋሪ አበራሽ ገብረመድህን በበኩላቸው፤ ፓርቲዎች ያደረጉትን የፖሊሲ አማራጭ ክርክሮችንና ፕሮግራሞችን በንቃት ሲከታተሉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል። በዚህም ለኢትዮጵያና ህዘቦቿ ተጠቃሚነት ለሚሰራ ፓርቲ ድምፅ መስጠት የሚያስችል ግንዛቤ መያዛቸውንና በዕለቱም ድምጽ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል። ምርጫ ለአንድ ሀገር የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ልምምድ መጎልበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ያሉት ደግሞ ሌላኛው የመዲናዋ ነዋሪ ሀብታሙ ኪዳኔ ናቸው። ለዚህም ለሀገር ዕድገትና ለህዝብ ተጠቃሚነት የተሻለ እንደሚሰራ እምነት የሚጥልበትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ ለመምረጥ የምርጫ ካርድ የወሰደችውና ቀኑን በጉጉት እየተጠባበቀች መሆኑን የገለጸችው ወጣት ባንቻየሁ በሪሁን፤ ሀገርን ለሚመራና ለሚያሻግር ድምፄን ለመስጠት ዝግጁ ነኝ ብላለች። ሌላው ያነጋገርነው ወጣት አቤል ሀይሉ በበኩሉ፤ የምርጫ ካርድ አንድ ድምፅ የሀገርን መጻኢ ዕድል በመወሰን ረገድ ትልቅ ድርሻ ስላለው በፓርቲዎች ክርክር መነሻነት የሚበጀውን ፓርቲ ለመምረጥ በዝግጅት ላይ መሆኑን ተናግሯል። የአንድ ሰው ድምጽ ዋጋ ስላለው የወሰድኩትን የምርጫ ካርድ የምፈልገውን በመምረጥ የዜግነት ድርሻዬን ለመወጣት ተዘጋጅቻለሁ ያለችው ደግሞ ለምለም ዘለቀ ናት። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #ENA
የሚታይ

የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የክርክር መድረክ የፓርቲዎች ተሳትፎ ጎልቶ የታየበት ነው
May 29, 2026 484
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21/2018(ኢዜአ)፦ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የክርክር መድረክ የፓርቲዎች ተሳትፎ ጎልቶ የታየበት እንደነበረ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ተስፋዬ ነዋይ ገለጹ። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም መራጮች ድምፅ የሚሰጡበት ቀን ነው። የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫ ቦርድ ባዘጋጀው መድረክ ለምርጫ ክርክሩ በ19 ዙር ያካሄዱ ሲሆን፤ ክርክሩም በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም ዲጂታል ሚዲያ አማራጮች ለመራጩ ህዝብ ተደራሽ ተደርጓል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር ማጠናቀቂያ እና የጥሞና ጊዜ ማብሰሪያ መርሃ ግብር አካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራር አባላት፣የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ጨምሮ የመገናኛ ብዙኃን ተወካዮች ተገኝተዋል። የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ተስፋዬ ነዋይ በዚሁ ወቅት፤ ቦርዱ የምርጫ ሂደት ውጤታማነትን ማስጠበቅ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መስራቱን ገልጸዋል። ቦርዱ ለመጀመሪያ ጊዜ ባዘጋጀው የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክር መድረክም የፓርቲዎች የጎላ ተሳትፎ የተንጸባረቀበት እንደነበር ተናግረዋል። የክርክር መድረኩ ፓርቲዎች በሃሳብ የበላይነት የተመሰረተ ጭብጥ ተኮር ክርክር በማድረግ በሞዴልነት የሚወሰድ መሆኑንም አብራርተዋል። በዚህም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖሊሲ አማራጭ ሃሳባቸውን በሰለጠነ አግባብ ለመራጩ ህዝብ በቀጥታ በማስተላለፋቸው መራጩ ህዝብ ግንዛቤ መያዙን አንስተዋል። የክርክር ሂደቱን በስኬት ለማከናወን በተደረገው ዝግጅት ገለልተኛ ሙያተኞች፣ አስተባባሪዎች፣ ምሁራንና ተባባሪ አካላት በአቅም ግንባታ ስልጠና መሳተፋቸውን ጠቅሰዋል። የተለያዩ የመገናኛ ብዙኅን ሙያተኞች በሂደቱ መሳተፋቸውም ትልቅ የስኬት ምዕራፍ መሆኑን ገልጸዋል። በክርክር ሂደቱ ብዝኅነትና ሕብረ ብሔራዊነትን በሚያንፀባርቅ መልኩ አማርኛን ጨምሮ በተለያዩ የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች እንዲተላለፍ በማድረግ ስኬታማ ስራ መሰራቱን አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ ከተሞች የመሬት ይዞታ ካዳስተር ምዝገባ ሥርዓት የገቢ አቅማቸውን በማሳደግ ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ ነው
May 29, 2026 512
አዲስ አበባ፤ግንቦት 21/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ከተሞች የመሬት ይዞታ ካዳስተር ምዝገባ ሥርዓት የከተሞችን የገቢ አቅም በማሳደግ ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፈንታ ደጀን ገለጹ። ከተሞች የገቢ አቅማቸውን በመጠቀም ብድር ማግኘት የሚችሉበትን ሥርዓት ለመዘርጋት እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል። የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ፈንታ ደጀን ለኢዜአ እንዳሉት፤ ከተሞች ለአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው ናቸው። የኢትዮጵያ ከተሞች እስከ 58 በመቶ ለአጠቃላይ ሀገራዊ የምርት ድርሻ እያበረከቱ እንደሚገኙ ገልጸዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ በኮሪደር፣ወንዝ ዳርቻና ዲጂታላይዜሽን የተከናወኑ ስኬታማ የልማት ተግባራት ስሉጥ ከተሞችን በመፍጠር ከፍተኛ ጠቀሜታ እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል። ዘመናዊ የከተሜነት ምኅዳር የመፍጠር ሥራም ዜጎች ፈጣንና ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት የሚያገኙበት አስቻይ ሁኔታ እየፈጠረ መሆኑን አንሰተዋል። የከተሞች ማዘጋጃ ቤታዊና የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ወደ ዲጂታል ሥርዓት መሸጋገሩም ፈጣንና ቀልጣፋ ምኅዳር መፍጠሩን አስረድተዋል። በተለይም በአንድ ማዕከል አገልግሎት ዜጎች የመንግሥት አገልግሎቶችን በተማከለ ሥርዓት በጥራትና ፍጥነት የሚያገኙበት ዕድል እንደፈጠረ ተናግረዋል። የከተሞችን የመሬት ይዞታ በፍትሐዊነት ለማስተዳደርም ምዝገባ እየተካሄደ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ 6 ነጥብ 6 ሚሊየን ፐርስል የከተማ መሬት ውስጥ 33 በመቶው ባለፉት ሶስት ዓመታት መመዝገቡን ጠቅሰው፤ በካዳስተር ስርዓት መሬትን የማስተዳደር ስራ በስፋት እየተሰራ ነው ብለዋል። ለአብነትም የአዳማ ከተማን ጨምሮ ሌሎች ከተሞች የመሬት ምዝገባ ማጠናቀቃቸው አብራርተዋል። የከተሞችን ሃብትና ገቢ የማመንጨት አቅም ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራትም ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገቡ እንደሚገኙ አብራርተዋል። በዚህም አሁን ላይ የከተሞች ገቢ ከአራት ዓመታት በፊት ከነበረበት 10 ቢሊዮን ብር ወደ 80 ቢሊየን ብር ማድረስ እንደተቻለ ገልጸዋል። ይህም የከተሞችን ገቢ የመሰብሰብ አቅም በማሳደግ በሚያመነጩት ገቢ መጠን በመጠቀም ብድር የሚያገኙበት ሥርዓት እየተዘረጋ መሆኑን ተናግረዋል።
ፓርቲዎች የፖሊሲ አማራጭ ሃሳባቸውን ለህዝብ ማስተዋወቅ የቻሉበትን መድረክ በመፍጠር ተጨባጭ ተግባራት ተከናውነዋል
May 29, 2026 400
አዲስ አበባ፤ግንቦት 21/2018(ኢዜአ)፦በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ፓርቲዎች የፖሊሲ አማራጭ ሃሳባቸውን ለህዝብ ማስተዋወቅ የቻሉበትን መድረክ በመፍጠር በኩል ተጨባጭ ተግባራት መከናወናቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሀይሉ ገለጹ። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም መራጮች ድምፅ የሚሰጡበት ቀን ጥቂት ቀናት ቀርተውታል። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫውም 47 ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአጠቃላይ 10 ሺህ 934 ዕጩዎችን በማስመዝገብ በመገናኛ ብዙኅን አማካኝነት የፖሊሲ አማራጭ ሃሳቦቻቸውን ለህዝብ በስፋት የማስተዋወቅ ስራ ተሰርቷል። የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫ ቦርድ ባዘጋጀው መድረክ ለምርጫ ክርክሩ በ19 ዙር ያካሄዱ ሲሆን፤ክርክሩም በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም ዲጂታል አማራጮች ለመራጩ ህዝብ ተደራሽ ተደርጓል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሀይሉ፤በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ፓርቲዎች የፖሊሲ አማራጭ ሃሳባቸውን ለህዝብ ማስተዋወቅ የቻሉበትን መድረክ መፍጠር እንደተቻለ ገልጸዋል። መራጩ ህዝብም በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ድምፅ በመስጠት ወኪሎቹን እንዲመርጥ ለማስቻል የምርጫ ቅስቀሳና ክርክር ክህሎት ማዳበሪያ የተግባር ልምምድ ስልጠና መሰጠቱን አስታውሰዋል። በፖሊሲ ጥናት ምሁራንና ሙያተኞች በመታገዝ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አማራጭ ሃሳብ ልዩነትና ተመሳሳይነት የሚለካበትን መረጃ የመሰብሰብ ሥራ በጥንቃቄ መሰራቱን ተናግረዋል። የክርክር ሂደቱን ቅርፅ ውጤታማነት ለማስጠበቅ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽ ሙያተኞች የተሳተፉበት ተከታታይ ውይይት በማድረግ ፖለቲካ ፓርቲዎች ከተለምዷዊ ክርክር ወጣ ያለ ክርክር አካሂደዋል ብለዋል። የክርክር ሂደቱ ተጋባዥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችና ገለልተኛ ተቋማት ወኪሎችም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ጥያቄ የሚያቀርቡበት ዕድል እንደተፈጠረ አንስተዋል። በዚህም የፖለቲካ ፓርቲዎች ከታዳሚ በሚቀርብላቸው ጥያቄ የህዝብን ፍላጎት በመረዳት መለካት የሚችሉበትን የክርክር ቅርፅ መስጠት እንደተቻለ አብራርተዋል። የክርክር መሪዎችም ረጅም ጊዜ በሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን የሰሩና ገለልተኝነታቸውን ለማረጋገጥ ለፓርቲዎች በመላክ አስተያየት እንዲሰጡበት መደረጉን ጠቅሰዋል። የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ፖሊሲና የፕሮግራም ዓላማ ለህዝብ በግልፅ በማስተዋወቅ መራጮች በቂ ግንዛቤ የሚያገኙበትን ዕድል መፈጠሩን አስረድተዋል። በምርጫ ሂደቱ የጥሞና ጊዜም ዜጎች በየቤታቸው ለማን ድምፅ መስጠት እንዳለባቸው ሃሳብ የሚያሰላስሉበትና ፓርቲዎችም ዕጩዎች ያለውን ድባብ የሚከታተሉበት መሆኑን አንስተዋል። በቀጣይም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ሂደቱን ነጻ፣ ፍትሐዊ፣ ተዓማኒ፣ ገለልተኛ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አበክሮ እየሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል። በግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሚካሄደው ምርጫም የአፍሪካ ሕብረት፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) እና የሀገር ውስጥ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በታዛቢነት እንደሚታደሙ አስታውቀዋል። የምርጫ ሂደቱን ለመጎብኘት ጥያቄ ያቀረቡ 16 የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላትንም ምላሽ ለመስጠት በሂደት ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል።
የአቮካዶን ምርታማነት በማሳደግ ከዘርፉ የሚገኘውን ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ለማሻሻል እየተሰራ ነው
May 29, 2026 475
አዲስ አበባ፤ግንቦት 21/2018(ኢዜአ)፦ የአቮካዶን ምርታማነት በማሳደግ ከዘርፉ የሚገኘውን ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ደሳለኝ ተሻለ ገለጹ፡፡ በግብርና ሚኒስቴር አዘጋጅነት በብሔራዊ የአቮካዶ ልማት ፕሮግራም ዙሪያ የዘርፉን ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።   በመድረኩ ላይ የተገኙት የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ደሳለኝ ተሻለ እንዳሉት፤ የአቮካዶ ምርት በአገር ደረጃ ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው የግብርና ምርት ኢኒሼቲቮች ውስጥ አንዱ ሲሆን፣ ምርትና ምርታማነቱን በማሳደግ ረገድ ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። ይህ ብሔራዊ የአቮካዶ ልማት ፕሮግራም በአገሪቱ እያደገ የመጣውን የፍራፍሬ ፍላጎት ለማሟላትና የኢትዮጵያን የኤክስፖርት አቅምን ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመዋል። የአቮካዶ ምርት ለተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እንዳሉትም አብራርተዋል። ሚኒስቴሩ አገር አቀፍ የአቮካዶ ልማትን ይበልጥ ለማስፋፋት፣ ምርታማነትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርና የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ የዘርፉን ተዋናዮች፣ አምራቾችና ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ በቅንጅት እየሠራ ይገኛል ብለዋል። በዚህም መሠረት ከፍተኛ ምርት የሚሰጡና የተለያዩ በሽታዎችን የሚቋቋሙ ተመራጭ የአቮካዶ ዝርያዎች ለአርሶ አደሮች ተሰራጭተው ከፍተኛ ውጤት እያስገኙ መሆናቸውን ገልጸዋል። አነስተኛ አምራች አርሶ አደሮችን በክላስተር በማደራጀት፣ ዘመናዊ የኩሬ አጠቃቀምና የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂ ስልጠናዎችን በመስጠት የምርት ጥራትን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ማድረግ የሚያስችል አሠራር እየተዘረጋ መሆኑን ጠቁመዋል። ይህም አርሶ አደሩን በቀጥታ ከዓለም አቀፍ ገበያ ጋር ለማስተሳሰር ትልቅ ሚና ይጫወታል ብለዋል። ይህ ብሔራዊ ፕሮግራም የአርሶ አደሩን የኑሮ ዘይቤና ገቢ ከመቀየር ባለፈ፣ በግብርናው ዘርፍ የሚገኘውን የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ገቢ በከፍተኛ መጠን ለማሳደግ የተቀረጸ ስትራቴጂካዊ እርምጃ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 54 ሚሊየን 57 ሺህ 861 መራጮች ተመዝግበዋል
May 29, 2026 245
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21/2018(ኢዜአ)፦ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 54 ሚሊየን 57 ሺህ 861 መራጮች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሃይሉ፤ በመጪው ሰኞ የሚካሄደውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም ምርጫውን ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጸዋል። ቦርዱ ለመጀመሪያ ጊዜ ባዘጋጀው የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር መድረክ ፓርቲዎች ፕሮግራማቸውንና አማራጭ ሃሳባቸውን ለመራጩ ህዝብ እንዲያቀርቡ መደረጉን አብራርተዋል። በመመሪያው መሰረትም ለፖለቲካ ፓርቲዎች የአየር ሰዓት ድልድል ተደርጎ ፓርቲዎች ሃሳቦቻቸውን ለህዝብ ተደራሽ ማድረጋቸውንም ጠቁመዋል። የመራጮች ትምህርት ለሚሰጡ 169 ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ቦርዱ ፈቃድ መስጠቱን ጠቁመው ምርጫውን ለሚታዘቡ 55 የሀገር ውስጥ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንዲታዘቡ ፈቃድ መስጠቱን አስረድተዋል። ከአፍሪካ ህብረት 59 አባላት ያሉት ታዛቢዎች ቡድን መምጣቱን ገልጸው፤ ከኢጋድ ደግሞ 26 አባላት ያሉት ቡድን እንደሚታዘቡም አክለዋል። ቦርዱ በጥቅሉ ለ68 መገናኛ ብዙሃን ምርጫውን እንዲዘግቡ ፈቃድ መስጠቱን ጠቁመው ከዚሁ ወስጥ 56 የሀገር ውስጥ ሲሆኑ 12 ደግሞ የውጭ መገናኛ ብዙሃን መሆናቸውን ገልፀዋል። የቁሳቁስ ስርጭቱ ቀድሞ በተያዘው መርሐ ግብር መሠረት በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑንና የቁሳቁስ ስርጭቱ በተያዘለት ጊዜ ሙሉ በሙሉ ተደራሽ ሆኖ የምርጫ ጣቢያዎች ለምርጫው ሙሉ ዝግጅታቸውን እንደሚያጠናቅቁ ሰብሳቢዋ ተናግረዋል። በምርጫው ድምጽ ለመስጠት 54 ሚሊየን 57 ሺህ 861 መራጮች መመዝገባቸውን ጠቁመዋል። በመመሪያው መሰረትም የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ መቋቋሙን ሰብሳቢዋ ጨምረው ገልጸዋል።
ለምርጫው ስኬታማነት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አደርጋለሁ - ኢጋድ
May 29, 2026 194
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21/2018 (ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) በኢትዮጵያ ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማነት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸ። ምርጫው ነጻ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ፣ ተዓማኒ እና አካታች እንዲሆን የድርሻውን እንደሚወጣም አስታውቋል። በኢጋድ የኢትዮጵያ ምርጫ ታዛቢ ተልዕኮ ሰብሳቢ ስፔሺዮሳ ዋንዲራ ካዚብዌ(ዶ/ር) የተመራ ልዑክ ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት የምርጫ ትብብር ጋር በመሆን የምርጫውን ሂደትን መደገፍ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክሯል።   በውይይቱም የሲቪል ማህበረሰቦች የዴሞክራሲ ሂደቶችን፣ የምርጫ ዝግጅት እና የአካባቢ ምርጫን በመታዘብ ረገድ የሚኖራቸውን ሚና በተመለከተ ምክክር መደረጉን ኢጋድ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል። ተዓማኒ እና አካታች ምርጫ ለማካሄድ የመራጮች የሲቪክ ትምህርት አስፈላጊ መሆኑ በውይይቱ መነሳቱን ተጠቅሷል፡፡ ውይይቱ ኢጋድ በኢትዮጵያ ነጻ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ፣ ተዓማኒ እና አካታች ምርጫ እንዲኖር የሚያደርገው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አካል መሆኑንም አስታውቋል፡፡
ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት እየተጠናቀቀ ነው
May 29, 2026 388
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21/2018(ኢዜአ)፦ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የምርጫ ቁሳቁሶችን የማሰራጨት ሥራም በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሃይሉ፤ በመጪው ሰኞ የሚካሄደውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም ምርጫውን ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት እየተጠናቀቀ ነው ብለዋል። ቦርዱ ለመጀመሪያ ጊዜ ባዘጋጀው የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር መድረክም ፓርቲዎች ፕሮግራማቸውንና አማራጭ ሃሳባቸውን ለመራጩ ህዝብ እንዲያቀርቡ መደረጉን አብራርተዋል። በመመሪያው መሰረትም ለፖለቲካ ፓርቲዎች የአየር ሰዓት ድልድል ተደርጎ ፓርቲዎች ሃሳቦቻቸውን ለህዝብ ተደራሽ እንዲሆን መደረጉንም ጠቅሰዋል። የመራጮች ትምህርት ለሚሰጡ 169 ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ቦርዱ ፈቃድ መስጠቱን ጠቁመው፤ ምርጫውን ለሚታዘቡ 55 የሀገር ውስጥ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንዲታዘቡ ፈቃድ መስጠቱንም ተናግረዋል። ከአፍሪካ ህብረት 59 አባላት ያሉት ታዛቢዎች ቡድን መምጣቱን ገልጸው፤ ከኢጋድ ደግሞ 26 አባላት ያሉት ቡድን እንደሚታዘቡም አክለዋል። ቦርዱ በጥቅሉ ለ68 መገናኛ ብዙሃን ምርጫውን እንዲዘግቡ ፈቃድ መስጠቱን ጠቁመው፤ ከዚሁ ወስጥ 56 የሀገር ውስጥ ሲሆኑ 12 ደግሞ የውጭ መገናኛ ብዙሃን መሆናቸውን ገልፀዋል። የቁሳቁስ ስርጭቱ ቀድሞ በተያዘው መርሐ ግብር መሠረት በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመው፤ የቁሳቁስ ስርጭቱ በተያዘለት ጊዜ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ የምርጫ ጣቢያዎችም ለምርጫው ሙሉ ዝግጅታቸውን እንደሚያጠናቅቁም ሰብሳቢዋ አስታውቀዋል።
በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ ለመስጠት ተዘጋጅተናል
May 29, 2026 259
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21/2018(ኢዜአ)፦ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን በሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ይበጀናል ለሚሉት ፓርቲ ድምጻቸውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም መራጮች ድምፅ የሚሰጡበት ቀን ነው። የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫ ቦርድ ባዘጋጀው መድረክ ለምርጫ ክርክሩ በ19 ዙር ያካሄደ ሲሆን፤ ክርክሩም በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም ዲጂታል አማራጮች ለመራጩ ህዝብ ተደራሽ ተደርጓል። የፊታችን ሰኞ በሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዙሪያ ኢዜአ ያነጋገራቸው የመዲናዋ ነዋሪዎች እንደገለጹት፤ ይበጀናል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ ዕለቷን በጉጉት እየተጠባበቁ መሆናቸውን ገልጸዋል። ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል እሸቱ ያደታ፤ በምርጫ ወቅት የአንድ ሰው ድምፅ ለሀገር ግንባታና ለዴሞክራሲ ሥርዓት መጎልበት ወሳኝ ሚና እንዳለው ተናግረዋል። ነገ ሀገርን የሚጠቅመውንና የሚመራውን ለይቶ መምረጥ የሚያስችላቸውን ዝግጅት እንዳጠናቀቁም ገልጸዋል። ሌላኛዋ የመዲናዋ ነዋሪ አበራሽ ገብረመድህን በበኩላቸው፤ ፓርቲዎች ያደረጉትን የፖሊሲ አማራጭ ክርክሮችንና ፕሮግራሞችን በንቃት ሲከታተሉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል። በዚህም ለኢትዮጵያና ህዘቦቿ ተጠቃሚነት ለሚሰራ ፓርቲ ድምፅ መስጠት የሚያስችል ግንዛቤ መያዛቸውንና በዕለቱም ድምጽ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል። ምርጫ ለአንድ ሀገር የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ልምምድ መጎልበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ያሉት ደግሞ ሌላኛው የመዲናዋ ነዋሪ ሀብታሙ ኪዳኔ ናቸው። ለዚህም ለሀገር ዕድገትና ለህዝብ ተጠቃሚነት የተሻለ እንደሚሰራ እምነት የሚጥልበትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ ለመምረጥ የምርጫ ካርድ የወሰደችውና ቀኑን በጉጉት እየተጠባበቀች መሆኑን የገለጸችው ወጣት ባንቻየሁ በሪሁን፤ ሀገርን ለሚመራና ለሚያሻግር ድምፄን ለመስጠት ዝግጁ ነኝ ብላለች። ሌላው ያነጋገርነው ወጣት አቤል ሀይሉ በበኩሉ፤ የምርጫ ካርድ አንድ ድምፅ የሀገርን መጻኢ ዕድል በመወሰን ረገድ ትልቅ ድርሻ ስላለው በፓርቲዎች ክርክር መነሻነት የሚበጀውን ፓርቲ ለመምረጥ በዝግጅት ላይ መሆኑን ተናግሯል። የአንድ ሰው ድምጽ ዋጋ ስላለው የወሰድኩትን የምርጫ ካርድ የምፈልገውን በመምረጥ የዜግነት ድርሻዬን ለመወጣት ተዘጋጅቻለሁ ያለችው ደግሞ ለምለም ዘለቀ ናት። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #ENA
የመምረጥ መብታችንን በመጠቀም ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መጎልበት የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማበርከት ተዘጋጅተናል
May 29, 2026 271
ወልቂጤ፤ ግንቦት 21/2018(ኢዜአ)፦ የመምረጥ መብታቸውን በመጠቀም ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መጎልበት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት መዘጋጀታቸውን የጉራጌ ዞን ነዋሪዎች ገለጹ። በምርጫ ካርዳቸው ለሀገርና ለሕዝብ ይበጃል ለሚሉት አካል ድምፅ ለመስጠት መዘጋጀታቸውንም ኢዜአ ያነጋገራቸው የዞኑ ነዋሪዎች ተናግረዋል። የመምረጥ መብታቸውን በመጠቀም ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መጎልበት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት መዘጋጀታቸውንም አስታውቀዋል። ከወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች መካከል መምህር ፍቃዱ ቶማስ በጠቅላላ ምርጫው ሀገርና ሕዝብን ያሻግራል ብለው ለሚያምኑበት ፓርቲ ድምፃቸውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የዜጎች የነቃ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ እሳቸውም በምርጫው የሚወክላቸውን ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። ሌላኛው የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ አቶ አብድራህማን ጅላሉ በበኩላቸው፤ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ የአንድ ሰው ድምፅ ትልቅ ዋጋ እንዳለው ጠቅሰዋል። የፊታችን ሰኞ በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ በመስጠት የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። የአበሽጌ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘሮ ዙርያሽ ቶፊቅ በበኩላቸው፤ ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም የሚያምኑበት^ን ተወዳዳሪ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። የምርጫ ጉዳይ የዜጎች የጋራ ጉዳይ በመሆኑ ድምፅ ለመስጠት ቀኑን በጉጉት እየጠበቁ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ነዋሪው አብዱልሃኪም ጀማል ናቸው። የምርጫ ካርድ የወሰዱ ዜጎች ሁሉ ድምፃቸውን በመስጠት ዲሞክራሲያዊ ተሳትፏቸውን እንዲያረጋግጡም መክረዋል።
የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ለሀገር ዕድገትና ለህዝብ ተጠቃሚነት ይበጃል የሚሉትን ለመምረጥ ተዘጋጅተዋል
May 29, 2026 249
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21/2018(ኢዜአ)፦ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ለሀገር ዕድገትና ለህዝብ ተጠቃሚነት ይበጃል የሚሉትን ለመምረጥ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ድምፅ ለመስጠት ተዘጋጅተው እየተጠባበቁ መሆኑን ተናገሩ። ኢትዮጵያ ​የፊታችን ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ታካሂዳለች። በባህርዳር ከተማ የደጃዝማች በላይ ዘለቀ እና አፄ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተሞች ነዋሪዎች ለምርጫው ዝግጁ መሆናቸውን ለኢዜአ ገልጸዋል። ምርጫው ለሀገር የሚበጅን በድምፃችን የምንመርጥበት ታሪካዊ መድረክ በመሆኑ በአግባቡ ለመጠቀም ተዘጋጅተናል ብለዋል። የመራጭነት ካርዳቸው የነገ እጣ ፈንታቸውን የሚወስን ቁልፍ መሣሪያ መሆኑንም ተናግረዋል። ዜጎችም የዴሞክራሲ መብታቸውን በመጠቀም በምርጫ ድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ በወሰዱት ካርድ ድምፅ በመስጠት ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚኖርባቸው አንስተዋል። የምርጫ ካርድ የወሰደ እያንዳንዱ ዜጋ ይህንን ወሳኝ ዴሞክራሲያዊ መብቱን ተጠቅሞ፣ ለህዝብ ጥቅም መከበር የሚሠራን አካል የመምረጥ ኃላፊነት አለብን ብለዋል።  
በወሰድነው ካርድ ይወክለናል ለምንለው ድምጻችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናል - የደሴ ከተማና የደቡብ ወሎ ዞን ነዋሪዎች
May 29, 2026 264
ደሴ፤ ግንቦት 21/2018(ኢዜአ)፦ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በወሰድነው ካርድ ይወክለናል ለምንለው ድምጻችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናል ሲሉ የደሴ ከተማና የደቡብ ወሎ ዞን ነዋሪዎች ገለጹ። ነዋሪዎቹ የፊታችን ሰኞ ግንቦት 24/2018 ዓም በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም ይወክለናል ለሚሉት አካል ድምጽ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የደሴ ከተማ እንዲሁም በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ ነዋሪዎች፤ በምርጫ ካርዳቸው ለሚፈልጉት ድምጽ በመስጠት ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል። የደሴ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ፀጋዬ ረታ እና ወይዘሮ እታፈራሁ ከበደ እንደገለጹት፤ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት እንደሚሳተፉ ገልጸዋል። በወሰዱት ካርድ ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም ይወክለናል ለሚሉት አካል ድምጽ እንደሚሰጡም አረጋግጠዋል። በተመሳሳይ በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘሮ የተመኝ እንድሪስና ወይዘሮ ፋጡማ መሀመድ በበኩላቸው፤ የፊታችን ሰኞ ካርድ በወሰዱበት የምርጫ ጣቢያ በማለዳ በመገኘት ድምጻቸውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
በጭሮ አንድ እና በነገሌ ምርጫ ክልል ለድምፅ መስጫ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች እየተሰራጩ ነው
May 29, 2026 371
ነገሌ ቦረና/ጭሮ፤ ግንቦት 21/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በጭሮ አንድ እና በነገሌ ምርጫ ክልል ለድምፅ መስጫ የሚያገለግሉ የምርጫ ቁሳቁሶች እየተሰራጩ መሆኑን የምርጫ ክልሎቹ አስተባባሪዎች ገለጹ። በጭሮ አንድ ምርጫ ክልል ስር ለሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለድምፅ መስጫ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን የማሟላት ስራ መጠናቀቁን የምርጫ ክልሉ አስታውቋል። የምርጫ ክልሉ አስተባባሪ አቶ መሐመድ ቡሹራ እንደገለፁት በጭሮ ወረዳና ጭሮ ከተማ 120 የምርጫ ጣቢያዎች ለድምፅ መስጫ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ሙሉ በሙሉ ተዳርሷል። በምርጫ ክልሉ ስር በተደራጁ የምርጫ ጣቢያዎች ተገቢውን ስልጠና የወሰዱ 720 የምርጫ አስፈፃሚዎች መመደባቸውም ገልፀዋል። የምርጫ ጣቢያዎቹ ለድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ምቹና የተሟሉ በመሆናቸው በዕለቱ ከማለዳው 12:00 ሰዓት የድምፅ መስጠት ሂደቱ ይጀመራል ብለዋል። በተመሳሳይ በነገሌ ምርጫ ክልል ወደ የምርጫ ጣቢያው ቁሳቁስ እየደረሰ መሆኑን የምርጫ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ገልጿል። የምርጫ ክልሉ አስተባባሪ አቶ አባይነህ ወርቁ ከማዕከል ወደ ነገሌ ምርጫ ክልል አስፈላጊው የምርጫ ቁሳቁስ ገብቶ፣ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ከትናንት ጀምሮ እየተሰራጨ ነው ብለዋል። በዞኑ 5 ወረዳዎች በሚገኙት 167 የምርጫ ጣቢያዎች ቁሳቁስ እየደረሰ መሆኑን ገልጸው፤ ለሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ዛሬና ነገ ሙሉ በሙሉ እንደሚደርስም ተናግረዋል። በተመሳሳይ በአምቦ አንድ ምርጫ ክልል ስር ለሚገኙ 105 የምርጫ ጣቢያዎች አስፈላጊው ግብዓት እየተሰራጨ መሆኑን የምርጫ ክልሉ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ ምስጋና ሳደሳ ገልጸዋል። የምርጫ ክልሉ በአምቦ ከተማና በአምቦ ወረዳ የሚገኝ ሲሆን የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ስርጭቱ በእቅዱ መሰረት እየተከናወነ መሆኑንም አክለዋል። እየተሰራጩ ካሉ ቁሳቁሶች መካከል የድምፅ መስጫ ወረቀቶች፣ የድምፅ መስጫ ሳጥኖች እና ሌሎች ለምርጫው ቀን የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ይገኙበታል ብለዋል።

ማህበራዊ
መራጩ ሕዝብ ሰላሙ ተጠብቆ ድምፁን እንዲሰጥ አስተማማኝ ዝግጅት ተደርጓል- የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን
May 29, 2026 225
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21/2018(ኢዜአ)፦ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ እና ስኬታማ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ፣ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በከፍተኛ ቅንጅት እና ቁርጠኝነት እየተሠራ መሆኑን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ። ኮሚሽኑ በክልሉ እያከናወነ ያለውን መጠነ-ሰፊ የሰላም ማስከበር ሥራ አስመልክቶ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ድሪባ መኮንን በሰጡት መግለጫ፣ የምርጫው የቅድመ-ዝግጅት ምዕራፍ ከተጀመረበት ጊዜ አንሥቶ ከክልሉ እና ከፌዴራል የፀጥታ መዋቅሮች የተወጣጣ የጋራ ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ ቀጣይነት ያለው ሥራ በትኩረት ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ጠቅላላ ምርጫውን ለማደናቀፍ እና በሕዝብ ላይ ሁከት ለመፍጠር የተንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ኃይሎችን የመለየት እና ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ የመውሰድ ሥራ መከናወኑን ጠቅሰዋል። ከዚህ ባሻገር በተከናወነው የተቀናጀ እና በተደራጀ የፀጥታ ማስከበር ሥራ፣ ለምርጫው ሂደት ስኬታማነት እጅግ ወሳኝ የሆኑት የምርጫ ቁሳቁሶች ያለምንም የፀጥታ እንቅፋት እና መስተጓጎል በተፈለገው ቦታ እና ጊዜ በሰላም መሰራጨታቸውን ተናግረዋል። የምርጫው ሂደት ፍፁም ሰላማዊ፣ ነጻ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች የተጀመረው የፀጥታ ጥበቃ እና የክትትል ሥራ ምርጫው ተጠናቅቆ ውጤት እስኪገለጽ ድረስ ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመላክቷል። በመሆኑም የክልሉ ነዋሪዎች እና መራጮች በፍፁም ራስ መተማመን በምርጫው ዕለት በነቂስ ወጥተው ድምፃቸውን እንዲሰጡ ኮሚሽኑ ጥሪውን አቅርቧል። በየአካባቢው በልዩ ሁኔታ የተደራጀው የጋራ የፀጥታ ግብረ-ኃይልም አጠቃላይ የምርጫው ሂደት እስኪጠናቀቅ ድረስ የሰላም እና የሕግ የበላይነትን የማስከበር ኃላፊነቱን በትጋት እንደሚወጣ አስታውቀዋል።
የጤና ነገር
May 29, 2026 195
በዮሐንስ ደርበው በዓለም ላይ አሳሳቢ ደረጃ ከደረሱ የህመም ዓይነቶች አንዱ … በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ዶክተር ሞላወርቅ አየለ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በዓለምም ሆነ በሀገራችን ትኩረት ከሚሹ የህመም ዓይነቶች አንዱ ስለሆነው የደም ግፊት ማብራሪያ ሰጥተዋል። በቆይታቸውም፤ ለደም ግፊት አጋላጭ ስለሆኑ ምክንያቶችና ሊደረግ ስለሚገባው ጥንቃቄም እንዲሁም ከደም ግፊት መድሃኒት አወሳሰድ ጋር በተያያዘ ሳይንሳዊ ማብራሪያዎችን እና ምክረ ሐሳቦችን አቅርበዋል። · የደም ግፊት ምንድን ነው? ደም በደም ሥሮቻችን ሲያልፍ፤ የሚለካው መጠን “የደም ግፊት” እንደሚባል ዶክተር ሞላወርቅ ያስረዳሉ። የላይኛው (ሲስቶሊክ ወይም ከፍተኛው) የደም ግፊት መጠን ልብ በምትኮማተርበት ጊዜ ደም ወደ ደም ሥር ሲረጭ የሚለካው መሆኑንም ይገልጻሉ። የታችኛው (ዲያስቶሊክ ወይም ዝቅተኛው) የደም ግፊት መጠን ደግሞ ልብ ደም ለመቀበል ለአፍታ ዕረፍት በምታገኝበት ጊዜ የሚከሰት የግፊት ደረጃ መሆኑንም ይገልጻሉ። · የደም ግፊት ደረጃዎች እና ማስጠንቀቂያቸው ዶክተር ሞላወርቅ እንደሚሉት፤ የጤናማ ሰው የደም የግፊት መጠን 120 በ 80 እና በታች መሆን ይኖርበታል። በሌላ በኩል ግን ይላሉ፤ የላይኛው ከ120 እስከ 129 የታችኛው ደግሞ ከ80 በታች ከሆነ “ከፍ ያለ ወይም የጨመረ የደም ግፊት ደረጃ” ይባላል። የላይኛው ከ130 እስከ 139 ወይም የታችኛው ከ80 እስከ 90 ከሆነ ደግሞ “ደረጃ አንድ የደም ግፊት” እንደሚባል ያስረዳሉ። የላይኛው ከ140 በላይ ሲሆን እና የታችኛው ከ90 በላይ ከሆነ ደግሞ “ደረጃ ሁለት የደም ግፊት” እንደሚባል ነው የሚገልጹት። በሌላ በኩል “የከፋ የደም ግፊት ደረጃ” የሚባል እንዳለ ጠቁመው፤ ይህም የላይኛው ከ180 በላይ እና የታችኛው ከ120 በላይ ሲሆን ነው በማለት ያብራራሉ። · ለደም ግፊት መጨመር መንስዔዎቹ ምንድን ናቸው? በዋናነት ሁለት ዓይነት የደም ግፊት መኖሩን ያነሱት የሕክምና ባለሙያው፤ ከፍተኛ የደም ግፊት እና መንስዔው የሚታወቅ የደም ግፊት መሆኑን አስረድተዋል። በዋናነት ወይም በአብዛኛው ከ90 እስከ 95 በመቶ የሚሆነው ከፍተኛ ደም ግፊት የሚባለው መሆኑን ገልጸው፤ በርካታ መንስዔዎች ሊኖሩት እንደሚችሉ ቢገመትም ሁሉም በውል እንደማይታወቁ ያነሳሉ። ከበርካታ መንስዔዎቹ መካከልም፤ በቤተሰብ የሚወረስ (ተላላፊ)፣ አካባቢያዊ ምክንያቶች እንዲሁም የአኗኗር ዘይቤ የሚሉት እንደሚገኙበት ጠቁመዋል። የአኗኗር ዘይቤ ሲባልም፤ የአመጋገብ ሥርዓት በተለይም ጨው የበዛበት ምግብ፣ ክብደት መጨመር፣ አካባቢያዊ ሁኔታዎች (አልኮል መጠጣት፣ ሲጋራ ማጨስ)፣ የስኳር ታማሚ መሆን የሚሉት ይጠቀሳሉ ይላሉ። · ለደም ግፊት በተለይም እነማን ተጋላጭ ናቸው? ዕድሜ በጨመረ ቁጥር የደም ግፊት የመከሰት ዕድሉም እንደሚጨምር ጠቅሰው፤ በዚህም መሠረት ባብዛኛው ዕድሜያቸው ከፍ ያሉ ሰዎች ተጋላጭ መሆናቸውን ይናገራሉ። እንዲም በቤተሰብ የደም ግፊት ኬዝ ያለባቸው ሰዎች፣ የማንነት ሁኔታ (ኢትኒክ ግሩፕ) ለምሳሌ፡- በጥቁሮች (አፍሪካውያን)፣ በኤስያውያን፣ በደቡብ ኤስያውያን ላይ ከፍተኛ የደም ግፊት ሊከሰት እንደሚችል ይገልጻሉ። እንደ ዶክተር ሞላወርቅ ማብራሪያ፤ በአጠቃላይ አጋላጭ ምክንያቶች በሁለት ተከፍለው ሊታዩ ይችላሉ። አንደኛው፡- ልንከላከላቸው (ልንቀንሳቸው) የምንችላቸው መሆናቸውን በመግለጽ ይህም የአመጋገብ ሥርዓትን ማስተካከል፣ ክብደት መቀነስ፣ አልኮልና ሲጋራ ማቆም እና መሰል መሆናቸውን አብራርተዋል። ሁለተኛው፡- ልንከላከላቸው የማንችላቸው መሆናቸውን ገልጸው ይህም፤ የዕድሜ መጨመር፣ የማንነት ሁኔታ (ኢትኒሲቲ) እና በቤተሰብ የሚተላለፍ የሚሉትን ጠቅሰዋል። · የደም ግፊትን አስቀድሞ መከላከል ይቻላል? የደም ግፊ ከተከሰተ መቆጣጠር እንጅ ማዳን እንደማይቻል ገልጸው፤ ከላይ እንደተጠቀሰው አስቀድሞ መከላከል ወይም ማዘግየት የሚቻል እና መከላከል የማይቻል የደም ግፊት ደረጃ መኖሩን አስረድተዋል። · የደም ግፊት በውል የሚታወቅ ምልክት አለው? የደም ግፊት ሲከሰት ምልክት እንደሌለው በማንሳት፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ “ዝምተኛው ገዳይ” እስከመባል መድረሱን ዶክተር ሞላወርቅ ያነሳሉ። ግፊቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ግን፤ በአንድ ወይም በሁለት የሰውነት አካል ላይ ችግር ሊደርስ እንደሚችል ከዚህም ሲያልፍ እስከ ሞት እንደሚያደርስ ይጠቅሳሉ። በተያያዘም፤ የራስ ምታት፣ የዐይን ብዥ ብዥ ማለት፣ ትንፋሽ ማጠር፣ የድካም ስሜት፣ አንገት የመያዝ ዓይነት ስሜቶች የደም ግፊቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ሊስተዋሉ የሚችሉ መሆናቸውን አብራርተዋል። አክለውም፤ በአብዛኛው በሕብረተሰቡ ላይ የደም ግፊት ምልክት ሳያሳይ ከፍተኛ ደረጃ ይደርስና ድንገት በጨመረ ጊዜ፤ ለሞት፣ ለአደጋ፣ ለልብ ድካም፣ አጣዳፊ ለሆነ የልብ ህመም፣ በጭንቅላት ላይ የደም መፍሰስ፣ የኩላሊት ድክመት፣ በደም ሥሮች በአግባቡ ደም እንዳይተላለፍ ማድረግ፣ ለዐይነ ስውርነት መዳረግን ጨምሮ መሰል ጉዳቶችን ሊያስከትል እንደሚችል አስገንዝበዋል። · መድኃኒት አወሳሰድ ላይ መደረግ ያለበት ጥንቃቄ ዶክተር ሞላወርቅ እንደገለጹት፤ አንድ ሰው ደም ግፊት እንዳለበት ከተነገረው በኋላ ሕክምናውም እንደ ደም ግፊቱ ደረጃ ይለያያል። ይህንም በምሳሌ ሲያስረዱ፤ የላይኛው ከ120 እስከ 129 ከሆነ “የጨመረ ግፊት” ይባላል፤ እዚህ ላይ ሰውየው ጥንቃቄ እንዲያደርግ፣ አመጋገቡን እንዲያስተካክል፣ ስፖርት እንዲሠራ፣ ክብደት እንዲቀንስ፣ ሱስ (ሲጋራ፣ አልኮል) እንዲቀንስ ክትትል ይደረጋል ብለዋል። ስለዚህ መድኃኒት ሳይጀምር የአኗኗር ዘይቤን በማስተካከል የደም ግፊቱን ሊቀንሰው (ሊቆጣጠረው) ይችላል ማለት ነው ሲሉም ይገልጻሉ። “ደረጃ አንድ ግፊት” የሚለው ላይ ከደረሱ ግን ሕክምና የሚጀምሩም የማይጀምሩም እንዳሉ ተናግረዋል። ይህም ማለት የላይኛው ከ130 እስከ 139 የታችኛው ከ80 እስከ 90 ከደረሰ ሕክምና የሚጀምሩት የስኳር ህመም ያለባቸው፣ የስትሮክ ህመም ያለባቸው፣ ከልብና ደም ሥር የተገናኙ ህመሞች ያሉባቸው ከሆኑ ቢያንስ አንድ የግፊት መድኃኒት መጀመርና ክትትል ማድረግ አለባቸው ይላሉ። በሌላ በኩል ግን ይላሉ ዶክተር ሞላወርቅ፤ ሰዎች “ደረጃ ሁለት ግፊት” ላይ ከደረሱ (የላይኛው ከ140 የታችኛው ከ90 በላይ ከሆነ) ሁሉም መድኃኒት መጀመር እንዳለባቸው በአጽንዖት ገልጸዋል። የሚጀምሩት መድኃኒትም አሁን ባለው በተሻሻለው የሕክምና ዘይቤ ሁለት መድኃኒቶች የሚጀምሩበት ሁኔታ እንዳለ ነው የሚያስረዱት። የአኗኗር ዘይቤን ማስተካከል ግን ለሁሉም የግፊት ዓይነቶች መሠረት (የሚመከር) መሆኑን አስገንዝበዋል። ስለዚህ መድኃኒት ጀምሬያለሁ ብሎ የአኗኗር ዘይቤው ላይ ቸልተኝነት ሊኖር እንደማይገባም ነው የሚመከሩት። በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከግፊት ጋር በተያያዘ ወደ ሆስፒታል መጥተው የሚታከሙ ታካሚዎች አብዛኞቹ፤ ጀምረው ያቋረጡ፣ ለመጀመር ፍላጎት የሌላቸው፣ ቅድመ ምርመራ ባለማድረግ ምክንያት ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ የተጎዱ ናቸው ሲሉ አብራርተዋል። ስለዚህ የግፊት መድኃኒት ከተጀመረ ሊቋረጥ እንደማይችል አስጠንቅቀዋል። በየጊዜው ክትትል ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም አክለዋል። በሂደት እንደ ግፊቱ ሁኔታ መድኃኒቶች ሊቀነሱም ሊጨመሩም እንደሚችሉ አመላክተዋል። · የመስፋፋት ደረጃ የዓለም ጤና ድርጅት በ2024 ያወጣውን መረጃ ዋቢ አድርገው፤ 1/3ኛው የዓለም ሕዝቦች በደም ግፊት እንደሚጠቁ ዶክተር ሞላወርቅ አንስተዋል። ከእነዚህ መካከልም፤ 7 ነጥብ 6 ሚሊየን ገደማው በአንድም በሌላም ምክንያት ከደም ግፊት ጋር በተያያዘ ሕይወታቸውን እንደሚያጡ ጠቁመዋል። አብዛኞቹ የደም ግፊት ታማሚዎች ቁጥር የሚመዘገበው ደግሞ በመካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም ሀገራችንን ያካትታል ሲሉ ገልጸዋል። በሀገራችን ደረጃም ይላሉ ዶክተር ሞላወርቅ፤ የቅርብ ጊዜ መረጃዎች ባይኖሩም ከግፊት ጋር በተያያዘ በ2001 ላይ በ35 ሳይቶች የተጠኑ ጥናቶች ውጤቶች እንደሚያመላክቱት ከ21 እስከ 25 በመቶ ያህሉ ሕዝብ በደም ግፊት የሚጠቃ ነው ይላሉ። በአብዛኛው ደግሞ ከተማ ላይ እንደሚበዛ ጠቁመው፤ በተለይም አዲስ አበባ ላይ እስከ 30 በመቶ እንደሚደርስ የጥናቶቹ ውጤቶች ማመላከታቸውን ተናግረዋል። አብዛኞቹ ኬዞች ደግሞ ዕድሜያቸው ከፍ ያለ፣ ክብደታቸው የጨመረ፣ አልኮል እና ሲጋራ የሚጠቀሙ እና የስኳር ህመም ያለባቸው ሰዎች ጋር የሚገናኙ መሆናቸውን አስረድተዋል። እንደ ዓለም አቀፍ ደረጃም ኬዙ ካለባቸው መካከል ግማሽ ያህሉ ግፊት እንዳለባቸው እንኳን እንደማያውቁ ነው የሚገልጹት። ለግፊት ሕክምና ትክክለኛ ክትትል አድርገው ግፊታቸውን በአግባቡ የሚቆጣጠሩት ከ 5 ሰዎች 1 መሆኑንም ጥናቶች ያሳያሉ ብለዋል። · ምክረ ሐሳብ በሀገራችን በሕብረተሰቡ ዘንድ ለደም ግፊት መለካት ኬዙ ከተገኘም የሕክምና ክትትል የማድረግ ሁኔታዎች ዝቅተኛ መሆናቸውን አንስተዋል። ስለዚህ ሕብረተሰቡ የደም ግፊት ምልክት ሳያሳይ ከአካል ጉዳት እስከ ሞት ሊያደርስ እንደሚችል ተገንዝቦ፤ የደም ግፊቱን የመለካት ልምምዱን ሊያዳብር እንደሚገባ ዶክተር ሞላወርቅ መክረዋል። በሌላ በኩል እንደ ሀገራችን ባሉ ሆስፒታሎች በጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ወይም መቋረጥ (ስትሮክ) ካለባቸው ሰዎች ከ70 እስከ 85 በመቶው ከደም ግፊት ጋር በተያያዘ የሚከሰት መሆኑን ገልጸው፤ ድንገተኛ ግፊት መጨመር ከልብ እና ከደም ሥሮች ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ጉዳት እያመጣ መሆኑን አስገንዝበዋል። በዓለምም ሆነ እንደ ሀገር አሳሳቢ ደረጃ ከደረሱ የህመም ዓይነቶች አንደኛው ግፊት መሆኑንም አረጋግጠዋል። ስለዚህ የደም ግፊትን መለካት፣ የአኗኗር ዘይቤን ማስተካከል፣ ከሱስ መራቅ፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማዘውተር ለጤናማ ሕይወት ከፍተኛ ሚና እንዳለው መክረዋል። #የጤና ነገር #ኢዜአ #የደም_ግፊት
የኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ስኬት ዜጎች ጤናማ ህይወት የሚመሩበትን አስቻይ ምኅዳር እየፈጠረ ነው
May 29, 2026 167
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ስኬት ዜጎች ጤናማ ህይወት የሚመሩበትን አስቻይ ምኅዳር እየፈጠረ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ገለጸ። የኢትዮጵያ አካባቢ ጤና አጠባበቅ ባለሙያዎች ማኅበር 8ኛውን ዓመታዊ የሳይንሳዊ የምርምር ኮንፍረንስ ''ለተሻለች ፕላኔት ጤና፤ ዘመናዊና መቋቋም የሚችሉ የውሃ፣ ሳኒቴሽንና ሃይጅን ቴክኖሎጂዎች'' በሚል መሪ ሀሳብ እያካሄደ ይገኛል።   በጤና ሚኒስቴር የማህበረሰብ ተሳትፎና የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ መሪ ሥራ አስፈፃሚ እስራኤል አታሮ በመድረኩ፤ የአካባቢ ጥበቃ ጤናማ ዜጋና ማህበረሰብ ለመገንባት ጉልህ ፋይዳ አለው ብለዋል። ለዚህም ዜጎች የሚጠቀሟቸውን የውሃ፣ የአየርና የአካባቢ ሥነ-ምኅዳራዊ ጤናማነትና ደኅንነት መጠበቅ እንደሚያስፍልግ ገልጸዋል። የአካባቢ ጤንነትን ለመጠበቅ የሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር ውጤታማነትን በማሳደግ የቴክኖሎጂ አቅምን ማጎልበት እንደሚገባ አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ የስኬት ጉዞ ዜጎች ጤናማ ህይወት የሚመሩበትን አስቻይ ምኅዳር እየፈጠረ መሆኑን አንስተዋል። ማኅበሩ በሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ በማመስገን፤ የውሃ፣ ሳኒቴሽንና ሃይጅን ሥርዓትን ለማዘመን በሚከናወኑ ተግባራት የዘርፉ ተዋናዮች ገንቢ ሚናቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።   ​የኢትዮጵያ አካባቢ ጤና አጠባበቅ ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር አርጋው አምበሉ በበኩላቸው፤ የተሻለ የመኖሪያ ከባቢና ንፅህና የዜጎች ምርጫ ሳይሆን ጤናን የመጠበቅ ግዴታ ነው ብለዋል። ለዚህም የውሀ የሳኔቴሽንና የሃይጅን አገልግሎቶች ውጤታማ የሚሆኑባቸውን ቴክኖሎጂዎች ማፍለቅና ወደ ተግባር መቀየር እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።   የውሃ፣ ሳኒቴሽንና ሃይጅን አገልግሎት ለዜጎች አስፈላጊና መሠረታዊ ጉዳዮች ናቸው ያሉት ደግሞ የወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ተወካይ ተመስገን ሳሙኤል ናቸው። የኢትዮጵያን የውሃ፣ ሳኒቴሽንና ሃይጅን አገልግሎት በቴክኖሎጂ ለማዘመን በሚደረገው ጥረት ከመንግስት ጋር በትብብር እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።   የክርስቲያን እፎይታና ልማት ማኅበራት ኮንሶርቲየም በኢትዮጵያ ተወካይ በርሄ ፍሰሀ በበኩላቸው፤ ጤናማና ደኅንነቱ የተጠበቀ አካባቤ የዜጎችን ጤንነት ለመጠበቅ ጉልህ ፋይዳ አለው ብለዋል። በጉባኤው ለአካባቢ ጤና መጠበቅ ጉልህ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና እና ዕውቅና ተበርክቷል።
በኢትዮጵያ የሀሳብ ልዩነትን በሰለጠነ ምክክር መፍትሔ በመስጠት ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር የሚያስችል ጠንካራ መሠረት እየተጣለ ነው
May 29, 2026 164
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የሀሳብ ልዩነትን በሰለጠነ ምክክር መፍትሔ በመስጠት ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር የሚያስችል ጠንካራ መሠረት እየተጣለ መሆኑን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ገለፁ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በዋና ዋና ክንውኖቹ፣ አሁን የደረሰበትን ደረጃና በቀሪ ሥራዎች ዙሪያ ከቲንክ ታንክ፣ የግልና የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል። ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በዚሁ በመድረኩ፤ ኮሚሽኑ የሃሳብ ልዩነቶችን በሰለጠነ መንገድ ማስኬድ የሚያስችል ተቋም ሆኖ መገንባቱን ገልጸዋል። በዚህም እጅግ መሠረታዊ በሆኑ ዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባትን ለመፍጠር የሰለጠነ የምክክር አውድ በመዘርጋት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በምክክር ሂደቱም በወረዳ ደረጃ በተካሄዱ የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረኮች የነበረው ተሳትፎ 93 ከመቶ መሆኑ የአጀንዳ ማሰባስብና ተሳታፊ ልየታ ሂደቱን አሳታፊና አካታችነት እንደሚያሳይ አንስተዋል። በምክክር መድረኮቹም የመምህራን ማኅበር፣ ዕድሮች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የኃይማኖት ተቋማትና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ዳኞች፣ የወረዳ አስተዳደር ተወካዮችና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መሳተፋቸውን አስገንዝበዋል። ታላላቅ ህዝባዊ የምክክር መድረኮችን በመፍጠር ኮሚሽኑ በቀጥታ አጀንዳዎችን የማሰባሰብና ተሳታፊ የመለየት ሥራ መሰራቱን አስረድተዋል። በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚኖሩ ዜጎችን ለማሳተፍ በደቡብ አፍሪካ፣ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች፣ ስዊድንና እንግሊዝ የአጀንዳ ማሰባሰብና ተሳታፊ ልየታ ክርክሮች መካሄዳቸውን ተናግረዋል። የእስካሁኑ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት በየደረጃው መግባባት ላይ ለመድረስና ለቀጣይ ሀገራዊ ምክክር ጠንካራ መሰረት መጣል መቻሉ አንስተዋል። በቀጣይም ዋናው የምክክር ጉባኤ ለማካሄድ አስፈላጊ ዝግጅቶች እየተደረጉ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
ኢኮኖሚ
የኢትዮጵያ ከተሞች የመሬት ይዞታ ካዳስተር ምዝገባ ሥርዓት የገቢ አቅማቸውን በማሳደግ ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ ነው
May 29, 2026 512
አዲስ አበባ፤ግንቦት 21/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ከተሞች የመሬት ይዞታ ካዳስተር ምዝገባ ሥርዓት የከተሞችን የገቢ አቅም በማሳደግ ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፈንታ ደጀን ገለጹ። ከተሞች የገቢ አቅማቸውን በመጠቀም ብድር ማግኘት የሚችሉበትን ሥርዓት ለመዘርጋት እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል። የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ፈንታ ደጀን ለኢዜአ እንዳሉት፤ ከተሞች ለአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው ናቸው። የኢትዮጵያ ከተሞች እስከ 58 በመቶ ለአጠቃላይ ሀገራዊ የምርት ድርሻ እያበረከቱ እንደሚገኙ ገልጸዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ በኮሪደር፣ወንዝ ዳርቻና ዲጂታላይዜሽን የተከናወኑ ስኬታማ የልማት ተግባራት ስሉጥ ከተሞችን በመፍጠር ከፍተኛ ጠቀሜታ እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል። ዘመናዊ የከተሜነት ምኅዳር የመፍጠር ሥራም ዜጎች ፈጣንና ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት የሚያገኙበት አስቻይ ሁኔታ እየፈጠረ መሆኑን አንሰተዋል። የከተሞች ማዘጋጃ ቤታዊና የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ወደ ዲጂታል ሥርዓት መሸጋገሩም ፈጣንና ቀልጣፋ ምኅዳር መፍጠሩን አስረድተዋል። በተለይም በአንድ ማዕከል አገልግሎት ዜጎች የመንግሥት አገልግሎቶችን በተማከለ ሥርዓት በጥራትና ፍጥነት የሚያገኙበት ዕድል እንደፈጠረ ተናግረዋል። የከተሞችን የመሬት ይዞታ በፍትሐዊነት ለማስተዳደርም ምዝገባ እየተካሄደ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ 6 ነጥብ 6 ሚሊየን ፐርስል የከተማ መሬት ውስጥ 33 በመቶው ባለፉት ሶስት ዓመታት መመዝገቡን ጠቅሰው፤ በካዳስተር ስርዓት መሬትን የማስተዳደር ስራ በስፋት እየተሰራ ነው ብለዋል። ለአብነትም የአዳማ ከተማን ጨምሮ ሌሎች ከተሞች የመሬት ምዝገባ ማጠናቀቃቸው አብራርተዋል። የከተሞችን ሃብትና ገቢ የማመንጨት አቅም ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራትም ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገቡ እንደሚገኙ አብራርተዋል። በዚህም አሁን ላይ የከተሞች ገቢ ከአራት ዓመታት በፊት ከነበረበት 10 ቢሊዮን ብር ወደ 80 ቢሊየን ብር ማድረስ እንደተቻለ ገልጸዋል። ይህም የከተሞችን ገቢ የመሰብሰብ አቅም በማሳደግ በሚያመነጩት ገቢ መጠን በመጠቀም ብድር የሚያገኙበት ሥርዓት እየተዘረጋ መሆኑን ተናግረዋል።
የአቮካዶን ምርታማነት በማሳደግ ከዘርፉ የሚገኘውን ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ለማሻሻል እየተሰራ ነው
May 29, 2026 475
አዲስ አበባ፤ግንቦት 21/2018(ኢዜአ)፦ የአቮካዶን ምርታማነት በማሳደግ ከዘርፉ የሚገኘውን ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ደሳለኝ ተሻለ ገለጹ፡፡ በግብርና ሚኒስቴር አዘጋጅነት በብሔራዊ የአቮካዶ ልማት ፕሮግራም ዙሪያ የዘርፉን ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።   በመድረኩ ላይ የተገኙት የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ደሳለኝ ተሻለ እንዳሉት፤ የአቮካዶ ምርት በአገር ደረጃ ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው የግብርና ምርት ኢኒሼቲቮች ውስጥ አንዱ ሲሆን፣ ምርትና ምርታማነቱን በማሳደግ ረገድ ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። ይህ ብሔራዊ የአቮካዶ ልማት ፕሮግራም በአገሪቱ እያደገ የመጣውን የፍራፍሬ ፍላጎት ለማሟላትና የኢትዮጵያን የኤክስፖርት አቅምን ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመዋል። የአቮካዶ ምርት ለተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እንዳሉትም አብራርተዋል። ሚኒስቴሩ አገር አቀፍ የአቮካዶ ልማትን ይበልጥ ለማስፋፋት፣ ምርታማነትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርና የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ የዘርፉን ተዋናዮች፣ አምራቾችና ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ በቅንጅት እየሠራ ይገኛል ብለዋል። በዚህም መሠረት ከፍተኛ ምርት የሚሰጡና የተለያዩ በሽታዎችን የሚቋቋሙ ተመራጭ የአቮካዶ ዝርያዎች ለአርሶ አደሮች ተሰራጭተው ከፍተኛ ውጤት እያስገኙ መሆናቸውን ገልጸዋል። አነስተኛ አምራች አርሶ አደሮችን በክላስተር በማደራጀት፣ ዘመናዊ የኩሬ አጠቃቀምና የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂ ስልጠናዎችን በመስጠት የምርት ጥራትን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ማድረግ የሚያስችል አሠራር እየተዘረጋ መሆኑን ጠቁመዋል። ይህም አርሶ አደሩን በቀጥታ ከዓለም አቀፍ ገበያ ጋር ለማስተሳሰር ትልቅ ሚና ይጫወታል ብለዋል። ይህ ብሔራዊ ፕሮግራም የአርሶ አደሩን የኑሮ ዘይቤና ገቢ ከመቀየር ባለፈ፣ በግብርናው ዘርፍ የሚገኘውን የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ገቢ በከፍተኛ መጠን ለማሳደግ የተቀረጸ ስትራቴጂካዊ እርምጃ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በደቡብ ኦሞ ዞን በዘንድሮው የበልግ እርሻ ለገበያ ተኮር ሰብሎች ትኩረት ተሰጥቷል
May 29, 2026 279
ጂንካ፤ግንቦት 21/2018(ኢዜአ):- በደቡብ ኦሞ ዞን በዘንድሮ የበልግ እርሻ ለገበያ ተኮር ሰብሎች ትኩረት በመስጠት መሰራቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። የደቡብ ኦሞ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ምንላርገው አዲሱ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ በዞኑ በዘንድሮ የበልግ እርሻ 108 ሺህ ሄክታር መሬት መልማቱን ገልጸዋል።   አጠቃላይ ከለማው መሬት ወደ 4 ሚሊዮን የሚጠጋ ምርት ለማግኘት እንደታቀደም ጠቅሰዋል። በዘንድሮ የበልግ እርሻ ለገበያ ተኮር እና የኢንዱስትሪ ግብዓት ለሚሆኑ ስንዴ፣ ሰሊጥ፣ ካሳቫ እና ማሾ ሰብሎች ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል። ቀደም ሲል አርሶና አርብቶ አደሩ ውስን ሰብሎችን ብቻ በማልማት ለገበያ የሚያቀርብበትን ሁኔታ በመቀየር ገበያ ተኮር የሆነ አመራረት በመከተል በኩታ ገጠም በስፋት የሚያለሙበት ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል። ከዚህም ባሻገር አርሶና አርብቶ አደሩ በአካባቢው ያልተለመዱ እንደ ሩዝ እና ካሳቫ ምርቶችን ማምረት መጀመራቸውን አንስተው፥ በዚህም የገቢ አቅማቸው እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል።   በዞኑ ሳላማጎ ወረዳ ገሮ ቀበሌ በካሳቫ ምርት የተሰማሩት አርሶ አደር አለሙ ላስታ፥ በዘንድሮ የበልግ አዝመራ 17 ሄክታር መሬት ላይ ካሳቫ እያለሙ መሆናቸውን ገልጸዋል ። መንግስት የእርሻ መሬት እና የእርሻ ትራክተር በማቅረብ እገዛ እያደረገላቸው መሆኑን ገልፀው፥ የግብርና ባለሙያዎችም ገበያ ተኮር የሆኑ ሰብሎችን እንዲያለሙ ሙያዊ ድጋፍ እያደረጉላቸው መሆኑን ገልጸዋል። ካሳቫ በአንድ ሄክታር እስከ 300 ኩንታል ምርት የሚያስገኝ እና ቶሎ የሚደርስ ሰብል መሆኑ ደግሞ ይበልጥ ተመራጭ አድርጎታል ነው ያሉት አርሶ አደሩ።   ሌላው የወረዳው አርሶ አደር አድማሱ ጩሉ፥ በዘንድሮ የበልግ አዝመራ በኩታ ገጠም 8 ሄክታር መሬት ላይ ሩዝ እያለሙ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ሩዝ ውሃ በሚተኛባቸው ረግረጋማ ቦታዎች ምርት የሚሰጥ በመሆኑ ሩዝ እያለሙ መሆኑን ገልጸዋል። በአካባቢው ቀደም ሲል በቆሎ እና ማሽላ በስፋት የማልማት ልምድ እንደነበር ጠቁመው፥ አሁን ላይ በመንግሥት ድጋፍ ገበያ ተኮር የሆኑ ሰብሎችን በማልማት የተሻለ ገቢ ማግኘት መጀመራቸውን ገልጸዋል።
የመስኖ ግድቦች ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የሚደረገውን ጉዞ እያፋጠኑ ነው
May 28, 2026 785
ነገሌ ቦረና፣ግንቦት 20/2018 (ኢዜአ)፦በምሥራቅ ቦረና ዞን አነስተኛና መካከለኛ የመስኖ ግድቦች ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የሚደረገውን ጉዞ እያፋጠኑ መሆኑን የዞኑ መስኖና አርብቶ አደር ጽሕፈት ቤት ገለጸ። የምሥራቅ ቦረና ዞን አብዛኛው ነዋሪ ሕይወትና መተዳደሪያው አርብቶ አደርነትና ከአነስተኛ የእርሻ ሥራ ጋር የተያያዘ ነው። አካባቢው በተደጋጋሚ ጊዜ በሚከሰት ድርቅና በተለዋዋጭ የአየር ንብረት መዛባት ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የውኃ እጥረት ሲያጋጥመው ቆይቷል። ይህንን ለመፍታት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ትኩረት የተሰጠው አነስተኛና መካከለኛ የመስኖ መሠረተ ልማቶችን ማስፋፋት ላይ ነው። የመስኖ ግድቦቹ መገንባት ማኅበረሰቡ መደበኛውን የዝናብ ወቅትን ብቻ ከመጠበቅ ወጥቶ፣ ያለውን የከርሰ ምድርና የገፀ ምድር ውኃ በአግባቡ በመጠቀም በዓመት ሁለትና ሦስት ጊዜ እንዲያመርት ዕድል ፈጥሯል። የዞኑ መስኖና አርብቶ አደር ጽሕፈት ቤት እንዳስታወቀው፤በዞኑ ቆላማ ወረዳዎች የተገነቡ ሁለት የመስኖ መሠረተ ልማቶች እየሰጡ ባለው አገልግሎት ዘርፈ ብዙ ጥቅም እያስገኙ ነው። በጽሕፈት ቤቱ የዲዛይንና ቁጥጥር ቡድን መሪ ኢንጂነር ተስፋሁነኝ ዳንኤል እንደገለጹት፤ ፕሮጀክቶቹ በተለይም ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚደረገው ሽግግር ውስጥ ትልቅ እገዛ እያደረጉ ነው። በተለይም በዞኑ በሊበንና በጎሮዶላ ወረዳዎች የተገነቡት ግድቦቹ ነዋሪውን ወደ መስኖ ልማት ማስገባት ያስቻሉ ሲሆን ለምርታማነት ዕድገትም አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው ብለዋል። እነዚህ የመስኖ ፕሮጀክቶች ከ8 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ የዝናብ ውኃ የማጠራቀም አቅም እንዳላቸውም ገልጸዋል። የመስኖ ፕሮጀክቶቹ ከ465 ሄክታር በላይ መሬትን በዘመናዊ መስኖ ከማልማት ጎን ለጎን፣ የአካባቢውን የመኖና የውኃ ችግር የሚያቃልሉ መሆናቸውንም አስረድተዋል። በተጨማሪም ግድቦቹ ለአሳ ሀብት ልማትና ለቱሪዝም መዳረሻነት አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርገው የተገነቡ መሆናቸውን ጠቁመው፤ ለአብነትም በዞኑ ድቤ አዳማ መስኖ ፕሮጀክት ግድብ ውስጥ እስካሁን ከ10 ሺህ በላይ የአሳ ጫጩቶች መለቀቃቸውን ገልጸዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የዞኑ ነዋሪዎች እንዳሉት፥የመስኖ ፕሮጀክቶቹ በዘመናዊ መስኖ ልማት የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ ያግዛቸዋል። በዞኑ ሊበን ወረዳ የሲሚንቆ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ቃሲም ገመዳ እንደገለጹት፤ አካባቢው በድርቅና በዝናብ እጥረት ሳቢያ በተደጋጋሚ የመኖና የውኃ ችግር ያጋጥመው ነበር። ቀደም ሲል መኖና ውኃ ፍለጋ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለከፍተኛ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ሲጋለጡ መቆየታቸውንም ያስታውሳሉ። በአካባቢያቸው በተገነባው የመስኖ ፕሮጀክት የበጋ ስንዴን በዘመናዊ መስኖ በማልማት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንዲሁም የእንስሳት መኖና የውኃ ችግርን ለማቃለል እንደሚያግዝ ጠቁመው፥የበጋ ስንዴ፣ ቲማቲም፣ድንችና ሽንኩርት በመስኖ ለማልማት ተዘጋጅተዋል። ሌላው ነዋሪ አቶ ጉዮ ጃተኒ በበኩላቸው፤ ቀደም ሲል መደበኛ ሥራቸውን ትተው የእንስሳት መኖና የመጠጥ ውኃ ፍለጋ ሩቅ መንገድ ይጓዙ እንደነበር ያስታውሳሉ። በአካባቢያቸው የተገነቡት የመስኖ ፕሮጀክቶች ከአካባቢያቸው ሳይርቁ የበጋ ስንዴ በማምረት ችግሩን በዘላቂነት ለመቋቋም እንዳስቻላቸው ገልጸዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በዲጂታል ክህሎት ራሳችንን እያበቃን ነው - ተማሪዎች
May 28, 2026 649
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 20/2018(ኢዜአ)፦ በአምስት ሚሊየን የኢትዮ-ኮደርስ መርሃ ግብር በመታገዝ በዲጂታል ክህሎት ራሳቸውን እያበቁ መሆናቸውን አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ገለጹ። የአምስት ሚሊየን ኢትዮ ኮደርስ መርሃ ግብር በዲጂታል ሳይንስ ዘርፎች እንደ አንድሮይድ ማበልጸግ፣ ዳታ አናሊቲክስ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና የዌብ ዲዛይን መሰረታዊ ስልጠናዎችን ያካተተ ነው። የመርሃ ግብሩ ዋነኛ ዓላማና ግብ አምስት ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን በዲጂታል ክህሎት በማብቃት፣ ሀገሪቱ በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ያላትን ተወዳዳሪነት ማረጋገጥ ነው። ይህም ለወጣቶች ዓለምአቀፋዊ ዕውቅና ያለው ሰርቲፊኬት እና የስራ ዕድሎችን በመፍጠር በኩል ዓይነተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎቹ እንደገለጹት ከመደበኛው ትምህርት በተጨማሪ ራሳቸውን ከዲጂታሉ ዓለም ጋር ለማላመድ ጥረት እያደረጉ ነው። በለም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው አቢጊያ ዳንኤል፣ ወደፊት የሶፍትዌር ኢንጂነር የመሆን ህልሟን ለማሳካት በትምህርት ቤትና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተመቻቹ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕድሎችን እየተጠቀመች መሆኗን ገልጻለች። በዚሁ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው አላዛር ማስሬ፣ በዲጂታል ዘርፍ ራሱን እያበቃ መሆኑን ገልጾ፤ ትውልዱ ነገ ተወዳዳሪ ዜጋ ለመሆን ራሱን ከቴክኖሎጂ ጋር ማላመድ የግድ መሆኑን ተናግሯል። በድልበር አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው አቤል ሙሉጌታ በበኩሉ፣ የአምስት ሚሊየን ኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና መውሰዱን ገልጾ፣ ተማሪዎች ከቴክኖሎጂ ጋር ለመራመድ የተፈጠረውን መልካም አጋጣሚ እንዲጠቀሙበት መክሯል። የዌብ ዲዛይን ስልጠና መውሰዱንና ይህም በዘርፉ ያለውን መሰረታዊ እውቀት እንዳስጨበጠው የተናገረው ደግሞ ተማሪ ፍራኦል ተሾመ ነው።   የለም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ሰለሞን ዲሮ ትምህርት ቤቱ ከተለያዩ አካላት ጋር በመተባበር በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስና በሌሎች የቴክኖሎጂ ዘርፎች ለተማሪዎች ስልጠናዎችን እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል።   የድልበር አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምክትል ርዕሰ መምህር ተመስገን ቶሊና በበኩላቸው፣ ተማሪዎችና መምህራን የ5 ሚሊየን ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና እንዲወስዱ ትምህርት ቤቱ ድጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል።
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የምርምር ቴክኖሎጂዎችን እያጎለበተ ነው
May 28, 2026 716
ሐረማያ፤ ግንቦት 20/2018 (ኢዜአ)፦ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የምርምር ቴክኖሎጂዎችን እያጎለበተ እንደሚገኝ አስታወቀ። ዩኒቨርሲቲው 43ኛውን ዓመታዊ የምርምርና የማህበረሰብ ተሳትፎ ግምገማ ጉባዔ ’’ለአካባቢ ተስማሚ ፈጠራና ስነ ምህዳር ጥበቃ ለጽኑ ማህበረሰብ ግንባታ’’ በሚል መሪ ሀሳብ እያካሄደ ነው። የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ምክትል ፕሬዝዳንት ይስሃቅ ዩስፍ(ዶ/ር) በወቅቱ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው በግብርና፣ በጤና፣ በቴክኖሎጂ፣ በትምህርት፣ በህግ፣ በህብረተሰብ ሳይንስና በሌሎችም የምርምር ተግባራት እያከናወነ ነው።   በተለይም ዘንድሮ ዩኒቨርሲቲው 116 ፕሮጀክቶች ላይ የምርምር ስራ እያከናወነ መሆኑን ጠቁመው፤ ከዚህ ውስጥም 42ቱ መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲው ከ1 ቢሊየን ብር በላይ በጀት በመመደብ የሚያከናውናቸው የጥናትና ምርምር ቴክኖሎጂዎችም የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጡ እንደሚገኙም አስታውቀዋል። ዩኒቨርሲቲው በዘንድሮ ዓመትም ከ95 በላይ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሩ ማሰራጨቱን አመልክተዋል። በዩኒቨርሲቲው ከተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እና አስተዳደር ጋር በተያያዘ በድሬዳዋ አስተዳደር፣ በሐረማያ ሀይቅ፣ በአዴሌ፣ ደንጋጎ እና ሌሎች ተፋሰስ አካባቢዎች ላይ የተቀናጀ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል። በማህበረሰብ አገልግሎትና ተሳትፎ በኩልም ከ150ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ነፃ የህግ አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ በጤና፣ በትምህርትና በሌሎች ዘርፎች አመርቂ ተግባራት ማከናወኑን አንስተዋል። የግምገማ መድረኩ ዩኒቨርሲቲው የሚያከናውናቸውን አበረታች ስራዎች ለማስቀጠልና የሚስተዋሉ ውስንነቶች ለመቅረፍ እንደሚያስችል ተመላክቷል። ዩኒቨርሲቲው ለ43ኛ ጊዜ በሚያካሂደው የምርምርና የማህበረሰብ ተሳትፎ ጉባዔ 32 የምርምር ውጤቶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሏል። ለሶስት ቀናት በተሰናዳው በዚሁ ጉባዔ ላይ የዩኒቨርሲቲው ምሁራንና ተመራማሪዎች፣ ሴክተር መስሪያ ቤቶች፣ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም የማህበረሰብ ተወካዮች፣ አባ ገዳዎችና ሃደ ሲንቄዎች እየተሳተፉ ነው።
በክልሉ የመንግስት አገልግሎትን ጥራትና ተደራሽነት ለማሳደግ ተቋማት በሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ እንዲደራጁ እየተደረገ ነው
May 26, 2026 1003
አምቦ፤ ግንቦት 18/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል የመንግስት አገልግሎትን ጥራትና ተደራሽነት ለማሳደግ ተቋማት በሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ እንዲደራጁ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አወሉ አብዲ ገለጹ። በአምቦ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ፕሮጀክቶች ምረቃና መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።   መንግስት የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በገባው ቃል መሰረት በርካታ ፕሮጀክቶችን በጥራትና በብዛት ገንብቶ ለአገልግሎት እያበቃ ይገኛል። በዚህም መሰረት በአምቦ ከተማ አስተዳደር ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ በርካታ ፕሮጀክቶችን ገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ አድርጓል። ከፕሮጀክቶቹ መካከል የአምቦ ከተማ አስተዳደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና ለተለያዩ ቢሮዎች አገልግሎት የሚውል ባለ አምስት ወለል ህንፃ፣ በርካታ ሼዶችና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውሉ ግንባታዎች ተጠናቀው ተመርቀዋል። በወቅቱም የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አወሉ አብዲ እንደገለፁት፤ በክልሉ የመንግስት አገልግሎትን ጥራትና ተደራሽነትን ለማሳደግ ተቋማት በሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ እየተደራጁ ይገኛሉ ብለዋል። ለዚህም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በማዘመን የተገልጋይን እርካታ ለማሳደግ የማይተካ ድርሻ አለው ነው ያሉት። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የህዝቡን የመልካም አስተዳደር ችግር በመፍታት ህብረተሰቡ ጊዜና ጉልበቱን በልማት ላይ እንዲያውል ተደማሪ አቅም እንደሚሆን ጠቁመዋል። እንዲሁም የመንግሥት አገልግሎትን ከአድሎ የጸዳና ጥራት ያለው በማድረግ ብልሹ አሰራርን በማስወገድ በኩል ሚናው የጎላ ነው ብለዋል፡፡   የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ በበኩላቸው፤ መንግሥት ከተሞችን ለኑሮና ለቱሪዝም ዘርፍ ተመራጭ ለማድረግ በርካታ ተግባራት ማከናወኑን አንስተዋል። የአምቦ ከተማን የቱሪስት ማዕከል ለማድረግ የወንጪ-ዳንዲ-ኢኮቱሪዝም መንደር እና ሎጅ እንዲሁም ሌሎች ኢንዱስትሪዎች እንዲስፋፉ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ በከተማዋ የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመንግስት የአገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋና ዘመናዊ ለማድረግ የሚያግዝ መሆኑን የገለፁት ደግሞ የአምቦ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሃጫሉ ገመቹ ናቸው፡፡   ዛሬ በከተማው ከተመረቀው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በተጨማሪ ሼዶች፣ የከተማ ኮሪደር ልማትና ሌሎች ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ በከተማዋ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት እንደሚያሳድጉም ጨምረው ተናግረዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ጠንካራ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ ሥርዓት መገንባት የሚያስችል አቅም እየተፈጠረ ነው
May 26, 2026 679
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 18/2018(ኢዜአ)፦ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ጠንካራ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ ሥርዓት መገንባት የሚያስችል አቅም እየተፈጠረ መሆኑን የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ገለጸ። የአእምሯዊ ንብረት ዘርፍ ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን ከሀገራዊ የአእምሯዊ ንብረት ምዝገባና ጥበቃ ጋር ማቀናጀት ላይ ያተኮረ የባለድርሻ አካላት ውይይት ተካሂዷል።   የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወልዱ ይመስል፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ የግዙፍ ኩባንያዎች ሃብት ከፍተኛው ድርሻ ወደ አእምሯዊ ንብረት እየተቀየረ ነው ብለዋል። በኢትዮጵያም የአእምሯዊ ንብረት ለኢኮኖሚ ዕድገት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ የፖሊሲ፣ የሕግና የዲጂታል የአእምሯዊ ንብረት አስተዳደር ሥርዓት እየተዘረጋ መሆኑን ገልጸዋል። የአእምሯዊ ንብረት ምዝገባ ሥርዓቱን በአስቻይ የአሰራር ምኅዳር ለሀገር የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የራሱን ድርሻ እንዲወጣ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ከሀገር ውስጥና ዓለምአቀፍ ሕግና ስምምነቶች ጋር የተጣጣመ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ ለውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት፣ ለጥናትና ምርምር ሥራ መሳለጥ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለውም አስረድተዋል። የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጥበቃ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነትና የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት የንግድና ፈጠራ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ አይነተኛ ሚና እንደሚኖረው አንስተዋል።   የአእምሯዊ ንብረት ዘርፍ የሕግ አማካሪ ኤልያስ ፍቅሩ፤ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ ዓለምአቀፍ ፈጠራና ኢንቨስትመንትን በማበረታታት ወሳኝ ፋይዳ አለው ብለዋል። የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጥበቃ ሥርዓት መጠናከር ፈጠራና ኢንቨስትመንትን በማበረታታት ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነትን ማሳደግ እንደሚያስችል ገልጸዋል።   በኢትዮጵያ የቅጂና ተዛማች መብቶች የጋራ አስተዳደር ማኅበር የቦርድ አባል አርቲስት ጸደንያ ገብረማርቆስ፤ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ የሚደረግላቸው ምርቶች ለኢኮኖሚ ዕድገት ጉልህ ፋይዳ አላቸው ብላለች። ለዚህም የኪነ-ጥበብ ሥራ ቅጂና ተዛማጅ የሕግ ግንዛቤን በማጎልበት ጠንካራ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ አቅም መገንባት እንደሚያስፈልግ ተናግራለች።
ስፖርት
በዝናብ የተቋረጠው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታ ነገ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንዲቀጥል ተወሰነ
May 29, 2026 182
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ34ኛ ሳምንት መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ስታዲየም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በኢትዮ ኤሌክትሪክ መካከል እየተካሄደ የነበረው ጨዋታ በከባድ ዝናብ ምክንያት ተቋርጧል። ጨዋታው በ34ኛው ደቂቃ ላይ በስታዲየሙ ላይ በጣለው ከባድ ዝናብና ሜዳው ውኃ በመቋጠሩ ምክንያት ሊቋረጥ እንደቻለ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል። ይህን ተከትሎ የተቋረጠው ጨዋታ ነገ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ከ30 አንስቶ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከቆመበት ደቂቃ ጀምሮ እንደሚቀጥል ታውቋል። ጨዋታው እስከተቋረጠበት ደቂቃ ድረስም ሁለቱም ቡድኖች ግብ ሳያስቆጥሩ በባዶ ለባዶ ውጤት ላይ ነበሩ። በሌላ በኩል ዛሬ 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ሊደረግ ታስቦ የነበረው እና በዝናብ ምክንያት ያልተካሄደው የወላይታ ድቻ እና የነገሌ አርሲ የ34ኛ ሳምንት ጨዋታ ሐሙስ ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንዲደረግ መወሰኑን ማህበሩ አስታውቋል።
አካባቢ ጥበቃ
በሐረሪ ክልል ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ለተከላ ተዘጋጅተዋል
May 28, 2026 777
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 20/2018 (ኢዜአ)፦ በሀረሪ ክልል በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን የክልሉ የግብርና ልማት ቢሮ አስታውቋል። የክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ነስረዲን አህመድ እንደገለጹት በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ይተከላሉ። ከሚተከሉ ችግኞች ውስጥም ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት የፍራፍሬና የደን ችግኞች መሆናቸውን ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪም ከ200 ሺህ በላይ የሚሆኑት ለእንስሳት መኖ የሚያገለግሉ ችግኞች መሆናቸውንም ገልጸዋል። በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ የችግኝ ጣቢያዎች እየተከናወነ በሚገኘው ስራም ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠር መቻሉን አንስተዋል። በአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር እስከ አሁን የተከናወኑ ውጤታማ ተግባራት የክልሉን የደን ሽፋን በማሳደግና የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እያሻሻሉ መምጣታቸውንም ነው የተናገሩት።
የቴፒ ግብርና ምርምር ማዕከል በምርምር ያወጣቸውን ችግኞች ለአርሶ አደሩ እያሰራጨ ነው
May 28, 2026 440
ሚዛን አማን፤ ግንቦት 20/2018(ኢዜአ)፦ የቴፒ ግብርና ምርምር ማዕከል በምርምር ያወጣቸውን የቡና፣ የቅመማቅመም እና የፍራፍሬ ችግኞች ለአርሶ አደሮች እያሰራጨ መሆኑን ገለጸ። ማዕከሉ በገበያ ተፈላጊ የሆኑ የካካዎ፣ የቫኔላና ሌሎች የቅመማቅመም ችግኞችን ለመጪው ክረምት ተከላ ለአርሶ አደሮች እያሰራጨ መሆኑን አስታውቋል። የቴፒ ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ደረጀ ቱሉ (ደ/ር) እንዳሉት፣ ማዕከሉ የአርሶ አደሩን ምርታማነት የሚያሻሽሉና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያሳድጉ ከ70ዐ ሺህ በላይ የቅመማቅመም ችግኞችን እያዘጋጀ ይገኛል።   ችግኞቹ በመጪው ክረምት የሚተከሉ ሲሆን ለአካባቢ ሥነ ምህዳር ተስማሚና ምርታማነታቸው በምርምር የተረጋገጡ መሆናቸውን ገልጸዋል። በክረምቱ የሚተከሉ ችግኞች ምርታማነታቸው ከፍ ያለ ከመሆኑ በላይ የአካባቢው ሥነ ምህዳር ለመጠበቅ ተደማሪ አቅም እንደሚሆኑም አስረድተዋል። የሸካ ዞን ግብርና፣ ደን፣ አካባቢ ጥበቃና ኅብረት ሥራ መምሪያ ምክትል ኃላፊ አለምሰገድ ኃይለኢየሱስ በበኩላቸው ማዕከሉ ምርታማነታቸው በምርምር የተረጋገጡ የቅመማቅመምና ሌሎች ችግኞችን ለአርሶ አደሩ ማቅረቡን ተናግረዋል።   በዚህም የአርሶ አደሩን ምርታማነት በማሳደግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱን ለማሳደግ እንደቻለ አክለዋል። ተግባሩን በማስቀጠልም ማዕከሉ በበጋ ወራት ያፈላቸውን ችግኞች ለክረምቱ ወቅት ተከላ ለአርሶ አደሮች እያሰራጨ መሆኑንም ገልጸዋል።   በዞኑ የየኪ ወረዳ አርሶ አደር መሐመድ ታዬ እና አርሶ አደር አየለች አናሞ በበኩላቸው ከምርምር ማዕከሉ የሚቀርቡ ዝርያዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ምርት የሚሰጡና ምርታማነታቸው ያደገ መሆኑን በተግባር ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል።   ዘንድሮ በራሳቸው ያዘጋጁትንና በማዕከሉ የተዘጋጁ ችግኞችን በመትከል ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ ወደ ሥራ መግባታችውን አመልክተዋል።  
የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ለቀጣናው ብልፅግና የላቀ ሚና አለው
May 23, 2026 1340
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 15/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የተረጋጋ ማህበረሰብ ለመፍጠር እንዲሁም ብልፅግናን ለማጎልበት የላቀ ሚና እንዳለው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሰላምና ደህንነት ዘርፍ ዳይሬክተር ኮማንደር አበበ ሙሉነህ ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የራሷን የተፈጥሮ ሀብት ከመንከባከብ ባለፈ፣ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚከሰቱ አደጋዎችን በጋራ ለመከላከል የአካባቢውን አገራት አብሮ የመልማት ዕቅድ ይዛ እየሠራች ስለመሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህም በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ለጎረቤት አገራት በርካታ ችግኞችን ማበርከቷ ይታወቃል፡፡ የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ በኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚከሰቱ የተፈጥሮ መዛባቶችን ለመከላከል፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና አካባቢን ለመታደግ ታስቦ በከፍተኛ ሀገራዊ ቁርጠኝነት እየተተገበረ የሚገኝ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው። ይህ ንቅናቄ በአገር ውስጥ ካስገኛቸው ሁለንተናዊ ጥቅሞች ባሻገር፣ ለጎረቤት አገራትና ለጠቅላላው የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ትስስር ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ የምታከናውነው የተፈጥሮ ጥበቃ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለቀጣናው አገሮች የሚተርፍ ከፍተኛ ፋይዳ ያለው ነው፡፡ የኢጋድ ሰላምና ደህንነት ዘርፍ ዳይሬክተር ኮማንደር አበበ ሙሉነህ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ በቀጣናው እንደ ጎርፍ፣ የበረሃ አንበጣ እና ድርቅ ያሉ ተፈጥሯዊ አደጋዎች የሰዎችን መፈናቀልና ስደት ይፈጥራሉ፡፡ በዚህም ዜጎች ከአካባቢያቸው ችግሩ ወደ ሌለባቸው አካባቢዎችና ድንበሮችን አቋርጠው የሚሰደዱበትን ሁኔታ የሚፈጠር ሲሆን፤ ይህም በቀጣናው ላይ የሚያሳድረው ጫና ቀላል እንዳልሆነ አመልክተዋል። ይህንን ተግዳሮት ለመቋቋም በኢትዮጵያ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ውጤቶችን እያሳየ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ አሁን ላይ የሚታየው መደበኛ የዝናብ ሁኔታ ስኬት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ተከትሎ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እየተጠናከረ በሄደ ቁጥር በቀጣናው የተረጋጋ ማህበረሰብ ለመፍጠር፣ ሰላምና ብልፅግናን ለማጎልበት የራሱ የሆነ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው አንስተዋል። ይህንን የኢትዮጵያን መልካም ተሞክሮ በመረዳት እንደ ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ጅቡቲ ያሉ የጎረቤት አገራት ተመሳሳይ አረንጓዴ ልማቶችን እየተከተሉ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ከዋና ዋና ዓላማዎቹ መካከል አንዱ የግብርና እና የአካባቢ ጥበቃ ልማት መሆኑን ያነሱት ዳይሬክተሩ፤ ይህንን የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እና የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ሀሳብ በጽኑ እንደሚደግፈው ገልጸዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በ2011 ዓ.ም የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ባለፉት ዓመታት በከፍተኛ ተነሳሽነት ሲተገበር ቆይቷል። በመርሀግብሩ እስከ 2017 ዓ.ም ድረስ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ለአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ጉልህ ድርሻ እየተጫወተ ይገኛል። ይህ ግዙፍ ብሔራዊ የልማት ፕሮጀክት በኅብረተሰቡ ዘንድ ችግኞችን የመትከልና የመንከባከብ በጎ ባህል እንዲዳብርና የአካባቢ ጥበቃ ግንዛቤ እንዲያድግ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል። በተለይም በችግኝ ማፍላት፣ በተከላና ተያያዥ ሥራዎች ላይ ለበርካታ ዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር በሀገሪቱ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ላይ አዎንታዊ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።  
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት አለብን-መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
May 25, 2026 1523
አዲስ አበባ፤ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። 63ኛው የአፍሪካ ቀን ''የ63 ዓመታትን ዓመታት አንድነት፣ ትስስርና ልማት፤ አብረን እናክብር” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። በዝግጅቱም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ ጨምሮ የሕብረቱ አባል ሀገራት ዲፕሎማቶችና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላት ሚና በየ ጊዜው እየታደሰ መምጣቱን ገልጸዋል። የአህጉሪቷ የሕዝብ ቁጥርና የኢኮኖሚ ዕድገትም በጥቂት ዓመታት ውስጥ የአፍሪካን ጥቅል የሀገር ውስጥ ዕድገት ምጣኔ 10 ትሪሊዮን ዶላር ያደርሰዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። የአፍሪካ ወጣቶችም ሌሎች አህጉራት ጭምር የሚመኟቸው የአህጉሪቷ ዕድገትና ብልፅግና አቅም መሆናቸውን አንስተዋል። በቀጣይም የአፍሪካዊያንን የአንድነት ኃይል የበለጠ በማጎልበት የአህጉሪቱን ዕምቅ ፀጋዎች ለሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና መቀየር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ በበኩላቸው፥የአፍሪካዊያን ባህልና ዕሴት ለአህጉሪቷ መፃኢ ዕድል፣ ዕድገትና ብልፅግና የሚተርፍ የጥንካሬ ምንጭ ነው ብለዋል። የአፍሪካን የትብብር አቅም በማጎልበት የአህጉሪቷ ዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥና የራስን የተሻለ ዕድል መቅረፅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ለዚህም በሁሉም ዘርፍ የአፍሪካን የኢኮኖሚ ዕድገት በማስፋት የአህጉሪቱን ዕምቅ የልማት ፀጋ ወደ ዘላቂ ብልፅግና መቀየር እንደሚገባ ተናግረዋል። በአህጉሪቷ ላይ የደረሱ በደሎች ፍትሕ እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገርም ለአጀንዳ 2063 ስኬት በቁርጠኝነት በመስራት የወደፊት እጣ ፋንታ መወሰን እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። በየዓመቱ የአፍሪካ ቀን መከበር የጀመረው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁን የአፍሪካ ህብረት እ.ኤ.አ በ1963 መመስረቱን እንደሆነ ይታወቃል። የዘንድሮው የአፍሪካ ቀንም የህብረቱ ኮሚሽን ከህብረቱ ሰራተኞች ማኅበር፣ አባል ሀገራት፣ ከህብረቱ አደረጃጀቶችና ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች ጋር በመተባበር ተዘጋጅቷል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ ነው
May 13, 2026 3367
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ በጸጥታ፣ በዘላቂ ልማት እና በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ተቋማዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፈርመውታል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በዚሁ ወቅት በሰጡት መግለጫ፣ የአፍሪካ ህብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል። አጋርነታቸውን ይበልጥ ተቋማዊ የሚያደርገው ይህ ስምምነት በቁልፍ ዘርፎች ላይ የተመዘገቡ ስኬቶችንና የወደፊት ዕቅዶችን መነሻ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ በቋሚ አባልነት አለመካተቷን ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነት ነው ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ ይህም የምክር ቤቱን ተቀባይነትና ውጤታማነት እንደሚጎዳው አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ሊስተካከል እንደሚገባ ጠቅሰው አፍሪካ ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወጥታ ለአረንጓዴ ኢነርጂ ሽግግር የማምረቻና የማጣሪያ ማዕከል መሆን እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው፣ የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ እና የተባበሩት መንግሥታት የ2030 አጀንዳ የተጣጣሙ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ፈተናዎችን ለመፍታት በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ማሻሻያ ተደርጎ የአፍሪካ ሀብቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በናይሮቢ የተካሄደው የ"አፍሪካ ፎርዋርድ" (Africa Forward) ጉባኤ ውጤቶች ክትትል እንዲደረግባቸው አሳስበዋል፡፡ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብትን ጨምሮ ቋሚ መቀመጫና ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራት የሚለውን የአህጉሪቱን ጥያቄ በድጋሚ አረጋግጠዋል። ይህ ስምምነት በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለውን ስልታዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል። 10ኛው የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወቃል፡፡
አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ነው
May 13, 2026 2212
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ተግባር መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት እየተካሄደ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የመንግስታቱ ድርጅት በሁሉም ዘርፎች ቀዳሚ ተግባር አፍሪካን የማድረግ የፖለቲካም ሆነ የሞራል ግዴታ አለበት። አፍሪካ አህጉራዊ ግጭቶችን በማርገብ፣ አህጉራዊ ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናና ሌሎች የሰላምና ጸጥታ ኢኒሼቲቮች አስደናቂ መሆናቸውን ገልጸዋል። አፍሪካ በዓለም ሁለንተናዊ እንቅስቀሴ ላይ ያላት ሚና የጎላ መሆኑን እንገነዘባለን ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ በታሪክና በዓለም ኢ-ፍትሐዊ አሰራር የደረሰባትን በደል ለመቀልበስ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት ባልወጡበት ወቅት የተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት አህጉሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረጋቸው ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ ባልተሳተፈችበት የተቋቋሙ የዓለም አቀፍ ተቋማት ኢ-ፍትሐዊነት አፍሪካን ብዙ አሳጥቷታል ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካ ለመፍታት የተጀመሩ ኢንሼቲቮችን መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት አፍሪካዊ ግጭቶች በአፍሪካ ማዕቀፍ እንዲፈቱ በመሪነት ከመሳተፍ ባለፈ የአፍሪካ ሕብረትን ጥረት እንደሚደግፍ ጠቁመዋል። አፍሪካ በወሳኝ ማዕድናትና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም እንዳላት ገልጸው፤ ሀብቷን እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ የምታቀርብበትን መንገድ መቀየስ ይገባል ብለዋል።
አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም ለማቋቋም ወሰነች
May 13, 2026 2129
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የተዛባውን የዓለም የፋይናንስ ስርዓት የሚያጣጥም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (African Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እየተካሄደ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መድረኩ በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ፣ ዘላቂ ልማት፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አስተዳደርና በተለዋዋጭ ዓለም የአፍሪካ ፈተናዎች ዙሪያ የሚያተኩር ነው።   የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትን ጨምሮ የዓለም ነባራዊ ሁኔታ በአሕጉሪቱ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚደረግ ጥረት ቢኖርም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሰቃዩበትና የሚሰደዱበት አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል። ይሄውም በአፍሪካ አስተማማኝና ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን በመጥቀስ፣ ከጸጥታ ባለፈ በመልካም አስተዳደር፣ በልማትና የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት አስቻይ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል። በአፍሪካ የልማት ፋይናንስ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን የገለጹት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር፤ ዓለም አቀፉ የፋይናንስ አስተዳደር የአጀንዳ 2063 እና 2030 ግቦችን ለማሳካት እንቅፋት ፈጥሯል ብለዋል። በተለይም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተቋቋሙና አሁንም ያለው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት ለአፍሪካ ፍላጎትና እውነታ ምላሽ የማይሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል። በመሆኑም አፍሪካን ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ስርዓት ጋር ለማጣጣም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (Africa Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን ገልጸዋል። ይሄውም የአፍሪካ ሕብረት በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ሲሰራ ቆይቶ እ.አ.አ በመጪው ሰኔ ወር 2026 በሞሪሼስ በይፋ እንደሚጀመር አስታውቀዋል። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በአፍሪካ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ገልጸው፤ በብዙ ሀገራት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ንሯል፤ በአንዳንድ ሀገራት የነዳጅ ዋጋ ከ100 እስከ 150 በመቶ ጨምሯል ነው ያሉት። የአፍሪካ ሕብረት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በትብብር ሲሰራ መቆየቱን በመጥቀስ፣ የእርስ በርስ ትብብሩን ለማጠናከር በቅርበት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ተቋማት አጋርነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው በመግለጽ፤ በተቋማቱ መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ትብብር ወደፊት ማሻገር ያስፈልጋል ብለዋል።
ሐተታዎች
የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር
May 24, 2026 1714
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 16/2018 (ኢዜአ)፡-የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በሀገራችን ሁሉም ክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን? የመደመር ማሳያ ከሳምንቱ አበይት ክስተቶች መካከል የኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የጋምቤላ ክልሎች በአሶሳ ከተማ ያስገነቡት የጋራ ሰላምና ልማት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት የህንፃ ምረቃ ይጠቀሳል። በክልሎቹ ትብብር የተከናወነው የህንፃ ግንባታ በመደመር እሳቤ የዜጎችን የጋራ ሰላም ለማስጠበቅና የልማት ተጠቃሚነትን እውን ማድረግ ጥረት ማሳያ ነው።   መርሃ ግብሩ ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሐሰን፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ እና የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) የተገኙበት ነበር። በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላም ላይ ያተኮረው መድረክ በሶማሌ ክልል ጂግጂጋ ከተማ የተካሄደውና በቀጣናው ሰላምና ደህንነት ላይ ያተኮረው ፎረምም በእዚህ ሳምንት ዐበይት ጉዳይ ነበር። ፎረሙ የተካሄደው “ቀጣናዊ ተቋማትን ማጠናከር ለአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ” በሚል መሪ ሀሳብ ሲሆን የተዘጋጀውም በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት፣ በሰላም እና ፖለቲካዊ ምክክር ማዕከል (CRPP)፣ በሶማሌ ክልል መንግስት እና በሌሎች አጋር አካላት ነው።   በፎረሙ መክፈቻ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ፣ የፌደራል መንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ከፍተኛ አመራሮች፣ የማህበረሰብ መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፤ መድረኩ የውጭ ተዋናዮች ሳይገቡበት የቀጣናው አካላት በራሳቸው ጉዳይ፣ ፖሊሲና እርስ በእርስ ግንኙነት ላይ ብቻ የሚመክሩበት መሆኑን ጠቅሰዋል። እርስ በእርስ ለመተዋወቅ፣ ግልጽነትን ለመፍጠርና ጠንካራ ትስስርን ለመገንባት የሚያስችል በመሆኑም በቀጣናው ግጭቶች ለመቀነስ በእጅጉ እንደሚረዳ ነው ያነሱት። ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ምሁራን ጥልቅ ውይይት በማድረግ ለቀጣናው ፈተናዎች ተጨባጭ መፍትሄና አቅጣጫ እንዲያስቀምጡም ያግዛል ብለዋል። የጉባ ላይ ብስራቶች ተግባራዊ ልማት የሳምንቱ የበረራ ቅኝታችን የሚጀምረው ወደ ሶማሌ ክልል ጎዴ ይሆናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሊኮ ዳንጎቴ ጋር በመሆን በስፍራው እየተገነባ ያለውን የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ የግንባታ ሂደት ተመልክተዋል።   ከጉብኝታቸው በኋላም በምግብ ራስን የመቻል ጥረትን ለማሳካት የመሬት፣ ውሃ እና የሚያለማ የሰው ሃይል አስፈላጊ መሆኑን አንስተው በዚህ ሁሉ ኢትዮጵያ በቂ ሃብት ያላት መሆኑን ገልጸዋል። በምርጥ ዘርና ማዳበሪያ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እነዚህን ካሟላን ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች የሚተርፍ ነገር ማድረግ ይቻላል ሲሉ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካን ጨምሮ የኒውክለር ሃይል ማመንጫ፣ የቢሾፍቱ አየር መንገድ፣ የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ፣ የነዳጅ ማጣሪያና የቤቶች ልማት ግዙፍ ፕሮጀክቶች ግንባታ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሲመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ ያደረጓቸው የጉባ ብስራቶች መሆናቸው ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሞጆ ከተማ የተገነባውን የግራንዴር ሴራሚክ ማምረቻ ፋብሪካ መርቀው ስራ ያስጀምሩትም በዚሁ ሳምንት ነበር።‎ ‎በግራንዴር ሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተገነባው ፋብሪካ፣ መሰረት ልማቱ በ300 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ፣ የዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ የሴራሚክና የፎርሲሌን ንጣፎች ማምረቻ ፋብሪካ ነው። የፋብሪካው መገንባት የውጭ ምርት ጥገኝነት ከመቀነስ ባለፈ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ የሚያደርጋት መሆኑ ታውቋል። የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ ጉብኝት በዚሁ ሳምንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ ወደ ምስራቅ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በመጓዝ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል። በድሬዳዋ ቆይታቸው ብርቱካንና ሌሎች የፍራፍሬ ልማት ሥራዎች እንዲሁም የእንስሳት ሀብት ልማት ስራን ተመልክተዋል።   ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጉራዋ ወረዳም የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና የግብርና ልማት ሥራዎችንም ጎብኝተዋል። ከጉብኝታቸው በኋላ ባስተላለፉት መልእክትም የጋራ ሙለታ ተፈጥሯዊ የልማት ፀጋና ከፍታም ታሪክን፣ ውብ መልክዓ ተፈጥሮን የታደለ፣ የኢትዮጵያን ሜዳና ተራሮች ምርት የሚታፈስባቸው የማድረግ ሀገራዊ ጉዞ ትልቅ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል።   የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ማሳያዎች የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በኮንታ ዞን ኮይሻ ወረዳ ተገኝተው 142 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው የንፁህ መጠጥ ውሃና የመንገድ ፕሮጀክቶችን መርቀው ሥራ ያስጀመሩትም በዚህ ሳምንት ነበር። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር በለውጡ ዓመታት ከልማት የራቁ አካባቢዎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚ ለማድረግ ብዙ መሰራቱን አንስተዋል። የኮንታ ኮይሻ ወረዳ የንጽህ መጠጥ ውሃና የመንገድ ፕሮጀክቶች ለዚሁ ማሳያ ናቸው ብለዋል።   በተመሳሳይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፤ በአፋር ክልል የተለያዩ ወረዳዎች የተገነቡ የንጹህ መጠጥ እና የመስኖ ፕሮጀክቶች መርቀው ለአገልግሎት አብቅተዋል።   የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ በተለይ አርብቶ አደሮች ውሃ ለማግኘት ሩቅ አካባቢዎች ሲሄዱ ይደርስባቸው የነበረን እንግልት የሚያስቀር ነው። የመስኖ ፕሮጀክቱም የክልሉ አርብቶና አርሶ አደሮች በአካባቢው ያለውን ሰፊ መሬት በማልማት ምርታማ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል። በፕሮጀክቶቹ ምረቃ ላይ የፌዴራልና የክልሉ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።   በሲዳማ ክልልም በፌደራል መንግስት ድጋፍ በ460 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የዳዬ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታም ተመርቋል። ፕሮጀክቱ 75 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው። ፕሮጀክቱ የተመረቀው በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ (ዶ/ር) ነው።   በሌላ በኩል የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ ከ543 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ 52 የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን መመረቃቸው ሌላው የሳምንቱ ክስተት ነበር። በዞኑ ለምረቃ ከበቁ የልማት ፕሮጀክቶች መካከል የትምህርት፣ የጤና፣ የውሃና ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶች ይገኙበታል። ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በዞኑ ቃሉ ወረዳ በ365 ሚሊዮን ብር የተገነባውን የዲርማ ወንዝ መስኖ ፕሮጀክትንም መርቀዋል።   ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ወጪ የሚደረግበት የሃዋሳ ከተማ ዘመናዊ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ፕሮጀክት ግንባታ የማስጀመሪያ መርሃ ግብርም በዚህ ሳምንት ተካሂዳል። ለፕሮጀክቱ የመሰረት ድንጋይ በማስቀመጥ ያስጀመሩት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ (ዶ/ር) ናቸው፡፡   የፕሮጀክቱ ግንበታ ሲጠናቀቀ ሀዋሳ ከተማዋን ጽዱ በማድረግ የቱሪዝምና የኢንቨስመንት ማዕከልነቷን ያሳድገዋል ተብሏል። አቶ ደስታ የፕሮጀክቱ ግንባታ መንግስት ለከተሞች እድገት የሰጠውን ልዩ ትኩረት ያሳያል ሲሉም ነው የጠቀሱት። የከሰም መስኖ ግድብ የከሰም መስኖ ግድብ የጥገና ማሻሻያ ፕሮጀክትም በዚሁ ሳምንት ተመርቆ ሥራ ጀመሯል። ፕሮጀክቱ የተመረቀው በአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና በመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ነው። የማሻሻያ ግንባታ መጠናቀቅ ከሚሰጠው ዘላቂ የልማት አገልግሎት ባሻገር የአካባቢውን ማህበረሰብ ለዓመታት ሲፈታተን የነበረውን የጎርፍ ስጋት ያስቀራል ተብሏል።   በዚህ ወቅት ሚኒስትር አብርሃም (ዶ/ር) እንዳሉት፥ የከሰም መስኖ ግድብ ቀደም ሲል በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ እንደ ትልቅ ስጋት ይታይ ነበር። የጥገና ማሻሻያው በአካባቢው ማህበረሰብ የነበረውን ይህን የአደጋ ስጋት በማስቀረት ግድቡን ለታለመለት የመስኖ ልማት ለማዋል የሚያስችል ነው። ለፕሮጀክቱም 2 ቢሊዮን ብር በጀት መውጣቱን ሚኒስትሩ አንስተዋል።   የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፤ ፕሮጀክቱ ህብረተሰቡን ከስጋት ያዳነ እና በርካታ ጥቅሞች ያሉት ነው ብለዋል። የግድቡ ጥገና መጠናቀቅ የሀዝቡን የቆየ ጥያቄ የፈታ መሆኑንም አንስተዋል። የግንቦት - ታላቁ ሁነት ከ50 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ድምጻቸውን ለመስጠት የተመዘገቡበት ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሊካሄድ በጣት የሚቆጠሩ ቀናት ብቻ ቀርተውታል። የፓርቲዎች የምረጡኝ ቅስቀሳና የምርጫ ሂደቱን ስኬታማ የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል። ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ አጠቃላይ ዜጎችና የሚመለከታቸው ሁሉ ባለድርሻ አካላት ሀገራዊ ሃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ።   በዚሁ ሳምንት "ለዴሞክራሲያዊ ምርጫ ስኬት የመገናኛ ብዙሃን ሚ ና" በሚል መሪ ሃሳብ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ጋር በመተባበር በአዳማ ያዘጋጀው የውይይት መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሂዷል።   በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ፤ የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት የዜጎች ጠንካራ ተሳትፎና የዳበረ የዴሞክራሲ ልምምድ የታየበት መሆኑን አንስተዋል። ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅም መገናኛ ብዙሃን የላቀ ሚናቸውን አጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል። ከተረጅነት የመውጣት ሀገራዊ ጥረት በድሬዳዋ "ከተረጂነት ወደ ምርታማነት" በሚል መሪ ሃሳብ የተካሄደው የውይይት መድረክም ሌላው የእዚህ ሳምንት ዓቢይ ጉዳይ ነው። መድረኩን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የግብርና ሚኒስቴር በመተባበር ያዘጋጁት ነው። በመድረኩም በምግብ ራሱን የቻለ ትውልድ የመገንባት ጥረት የሀገርን ክብርና ሉአላዊነት እውን የማድረግ ቁልፍ አጀንዳ መሆኑ ተነስቷል።   በመድረኩ ላይ የተገኙት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) በምግብ ራሱን የቻለ ትውልድ የመገንባት ጥረት የሀገርን ክብርና ሉአላዊነት እውን የማድረግ ቁልፍ አጀንዳ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በቂና የተሟላ የውሃ ሀብት፣ የተማረና አምራች የሆነ ወጣት የሰው ኃይል እንዲሁም ለም የመሬት ፀጋዎች ያሉባት ሀገር በመሆኗ በማልማት እድገትና ማንሳራራትን ማስቀጠል ይቻላል ሲሉ ተናግረዋል።   ለእዚህም ዋናው መሠረታዊ ጉዳይም ያሉ አቅሞችን በመለየትና ህዝብን ወደ ላቀ ምርታማነት ደረጃ በማሸጋገር በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጡን ሥራ በላቀ ደረጃ ማስቀጠል መቻል መሆኑን አንስተዋል። ለሰላም ጥሪ የተሰጠ ምላሽ የሠላም ጥሪን የተቀበሉ የአማራ ክልል የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ የመረከብ፣ ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ የማድረግና የመልሶ ማቋቋም (ዲዲአር) መርሀግብርም በዚህ ሳምንት ተከናውኗል። በብሔራዊ ተሀድሶ ማዕከል ጠዳ ጊዜያዊ ማሰልጠኛ ማዕከል በተዘጋጀው መርሀግብር ላይ የተገኙት የሰላም ሚኒስትሩ መሀመድ እድሪስ የቀድሞ ታጣቂዎች ከስልጠና በኋላ ከምንም በላይ የሰላም ዘብ ሆነው የበደሉትን ህዝብ ለመካስ በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።   ታጣቂዎቹ ሠላምን አማራጭ በማድረግና የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለሠላም ያደረጉት አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል። የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን፣ መንግስት ለሠላም ባለው ጽኑ አቋምና ፍላጎት የሠላም ጥሪውን ተቀብለው የገቡ የቀድሞ ታጣቂዎችን በተሀድሶ ስልጠና እንዲያልፉ በማድረግ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመሩ እያደረገ ነው ብለዋል።   በተመሳሳይ የሰላም ጥሪውን የተቀበሉ የክልሉ የቀድሞ ታጣቂዎች በኮምቦልቻ የስልጠና ማዕከል ስልጠና የጀመሩ መሆኑ ይታወቃል። ሐረር- ፕሮጀክቶች ምረቃ የሐረሪ ክለል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በክልሉ እየተገነቡ የሚገኙትን የሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና ሌሎች የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ጉብኝትም ሌላው የእዚህ ሳምንት ኩነት ነበር። በዚህ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት በግንባታ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች በአሁኑ ወቅት በተሻለ አፈጻጸም ላይ ይገኛሉ።   በተለይም የሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መገንባት የክልሉን የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት የበለጠ በማሳደግ ረገድ ፋይዳው የላቀ መሆኑን ነው ያነሱት። በዘመናዊ ትምህርት የታነፀና በእውቀት የበለፀገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን በማፍራት ረገድ ያለው አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑንም አንስተዋል። ፕሮጀክቶቹ በፍጥነትና በጥራት ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ ለማስቻል በአስተዳደሩ በኩል ተገቢው ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግም አረጋግጠዋል። የጂግጂጋ ከተማ ተለዋጭ መንገድ ፕሮጀክት 672 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነባው የጂግጂጋ ከተማ ተለዋጭ መንገድ ፕሮጀክት በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ በይፋ የተመረቀውም በዚህ ሳምንት ነው። በምረቃው ላይ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ አብዱራህማን፣ የክልሉ የመንገዶች ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢድሪስ ሙሴ እና ሌሎችም ተገኝተዋል።   የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ እንደገለጹት ተመርቆ ለአገልግሎት የበቃው የጂግጂጋ ከተማ ተለዋጭ መንገድ ፕሮጀክት የከተማውን የንግድ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ እንቅስቃሴ ለማሳለጥ የሚያስችል ነው። የከተማውን ገፅታ በመለወጥ ረገድም የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው ነው ያነሱት። የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በበኩላቸው የመንገድ ፕሮጀክቱ የጂግጂጋ ከተማን ልማትና ዕድገት በማፋጠን በኩል ያለው ጠቀሜታ ከፍ ያለ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ የመንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ አብዱራህማን አስተዳደሩ ሀገራዊ የመንገድ መሰረተ ልማት ዕቅድን ለማሳካት እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፣ የጂግጂጋ ከተማ ተለዋጭ የመንገድ ፕሮጀክትም የዚሁ አካል መሆኑን ጠቅሰዋል።   የመንገድ ፕሮጀክቱ 7 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን 30 ሜትር ስፋት እንዳለውም ታውቋል።  
የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር
May 17, 2026 2486
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፦ የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በሀገራችን ሁሉም ክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን። 👉የግንቦት - ታላቁ ሁነት የምርጫ ጉዳይ ወቅታዊና ሀገራዊ አጀንዳ ሆኖ በሁሉም አካባቢዎች የዜጎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ተጠናክሮ የቀጠለበት ሳምንት ነው። መራጮች ካርዳችንን ለሀገርና ለህዝብ ይበጃል የምንለውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ብለዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎችም በተመቻቸላቸው ነፃ የአየር ሰዓትና የጋዜጣ ዓምድ የፖሊሲ አማራጮቻቸውንና ማኒፌስቷቸውን እያስተዋወቁ ቀጥለዋል። የተለያዩ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችም ዜጎች የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የግንዛቤ ማጎልበቻ ትምህርት በመስጠት ሙያዊና ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ። ለዘንደሮው ጠቅላላ ምርጫ በመራጮች ትምህርት ላይ ለሚሰማሩ 169 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዕውቅና መስጠቱ ይታወቃል። 👉የመጠጥ ውሃ ችግሮችን የመፍታት ጥረት ማሳያዎች በሳምንቱ በወላይታ ዞን ከ150 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የሆቢቻ ወረዳ ብዝሃ ቀበሌ የንጹህ መጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል። ፕሮጀክቶቹን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ (ዶ/ር) መርቀዋል። የፕሮጀክቶቹ ተመርቀው ለአገልግሎት መብቃት ለአካባቢው ማህበረሰብ ተጠቃሚነት የላቀ ትርጉም እንዳለው ተነስቷል። በተመሳሳይ የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ በቀብሪደሃር ከተማ በ407 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚካሄድ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ አስጀምረዋል። ከለውጡ በኋላ በክልሉ ከ370 በላይ የጥልቅ ውሃ ጉድጓዶች ተቆፍረው ለአገልግሎት መብቃታቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። በዚህም የመጠጥ ውሃ ሽፋኑ ከ19 ወደ 52 በመቶ ማሳደግ መቻሉ ታውቋል። በምስራቅ ሐረርጌ ዞንም የደደር ከተማንና የአካባቢውን ማህበረሰብ የመጠጥ ውሃ ችግር ለመፍታት ታስቦ የተገነባው ፕሮጀክትም ተጠናቆ ለአገልግሎት የበቃው በዚሁ ሳምንት ነበር። የፕሮጀክቱ ምረቃ ላይ የኦሮሚያ ክልል መሬት ቢሮ ሃላፊ መሰረት አሰፋ፣ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር እና ሌሎችም የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል። የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ ደደር ከተማን ጨምሮ ሌሎች በወረዳው ሶስት ቀበሌዎች የሚገኙ ከ100 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ታውቋል። 👉የጤና ጉዳይ የጤና ሚኒስቴር የተቀናጀ የህክምና እና የምርመራ ዘመቻ ከግንቦት 3 እስከ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በስምንት ክልሎች በሚገኙ 154 ወረዳዎች የሚያካሄድ መሆኑ የተገለጸውም በዚሁ ሳምንት ነበር። ይሄው መርሃ ግብር የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በይፋ ተጀምሯል። መርሃ ግብሩ በተለይም ትምህርት ቤቶችን ማዕከል በማድረግ የሚከናወን ሲሆን ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል አላማ ያደረገ መሆኑም ተገልጿል። 👉ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና በግብርና ሚኒስቴር ትብብር "ከተረጂነት ወደ ምርታማነት" በሚል መሪ ሃሳብ በሐዋሳ ከተማ የተካሄደው የውይይት መድረክም የሳምንቱ አበይት ጉዳይ ነበር። በመድረኩ ላይ የተገኙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቴ አለነ፣ ሀገራዊ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጂነት የመውጣት ጥረት ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል። በግብርና ልማት በተለይም የስንዴ ምርታማነትን በማሳደግ ከራስ አልፎ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የተመዘገበውን የላቀ ስኬት ለአብነት ጠቅሰዋል። በሌሎች የተለያዩ የግብርና የልማት ስራዎችንም በተጠናከረ መልኩ በማከናወን ምርታማነትን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ተችሏል ብለዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)፤ ከተረጂነት የመውጣት ጉዳይ የብሔራዊ ጥቅም አካል ሆኖ የመንግስት ስትራቴጂክ አጀንዳ ተደርጎ በፖሊሲ አቅጣጫ እየተመራ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም ምርታማነትን በማሳደግ የሀገርን ብልጽግና እውን በማድረግ የኢትዮጵያን የድህነት ታሪክ መቀየር ይኖርብናል ብለዋል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ዋና ስራ አስፈፃሚ ሠይፈ ደርቤ በበኩላቸው፤ እንደ ሀገር በምግብ ራስን ለመቻል የተጀመረው ግብ እንዲሳካ በቂ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል። ለዚህም ሚዲያ የማይተካ ሚና ያለው መሆኑን ገልጸው ኢዜአ ይህንን ሀገራዊ ትልም ለማሳካት የይዘት ስራዎችን በስፋት ተደራሽ የማድረግ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። 👉የምግብ ስርዓት ሽግግር በጋምቤላ ክልል ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚተገበረው የምግብ ስርዓት ሽግግር እና የኒውትሪሽን ፍኖተ-ካርታ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በጋምቤላ ከተማ በይፋ የተካሄደውም በዚሁ ሳምንት ነው። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን(ዶ/ር)፤ በክልሉ የተሟላ ስርዓተ ምግብን በማረጋገጥ ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልፀዋል። 👉ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በአሶሳ በአሶሳ ከተማ ሞዴል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ የተጀመረው በዚሁ ሳምንት ነው። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፤ የትምህርት ቤቱን ግንባታ አስጀምረዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ እስካሁን 34 ሞዴል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተገነቡ መሆኑን ያስታወሱት የትምህርት ሚኒስትሩ፤ በአሶሳ ከተማ የሚገነባው ትምህርት ቤትም በአንድ ዓመት ተጠናቆ ለአገልግሎት ይበቃል ብለዋል። 👉የሰላምና አብሮነት እሴት ግንባታ የሐረሪ ክልል፣ የኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞንና የማያ ከተማ አስተዳደር "የህዝቦች ሰላምና አብሮነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ የህዝብ ለህዝብ የሰላምና አብሮነት ኮንፍረንስ የተካሄደውም በዚሁ ሳምንት ነው። የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፤ የሐረርጌ ህዝቦች ትስስር በሀገሪቱ የታሪክ ማህደር ውስጥ ልዩ ስፍራ የሚሰጠውና ለታላቅ ማህበራዊ ውህደት ተምሳሌት እንደሚሆን ገልጸዋል። የኮንፈረንሱም ዓላማ የሰላም እሴት ግንባታና የልማት ትስስርን ይበልጥ ማጠናከር ስለመሆኑ አንስተዋል። 👉የግብርና ልማትና ምርታማነት በአማራ ክልል ለዘንድሮው የመኸር እርሻ ከ81 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ የተፈጥሮ የአፈር ማዳበሪያ በማዘጋጀት ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ያስታወቀው በዚሁ ሳምንት ነው። የአፈር ለምነትን በዘላቂነት ለማሻሻል ለተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ከ76 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለማዘጋጀት ታቅዶ እስካሁን ከ81 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ ኮምፖስት መዘጋጀቱ ታውቋል። 👉በኦሮሚያ ክልልም ለዘንደሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አካል የሆነው ከ10 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በአቮካዶ ተክል እንደሚሸፈን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል። በቢሮው የአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ ኃላፊ ሙሐመድሳኒ አሚን፤ በመጪው ክረምት ለሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም አቮካዶን ጨምሮ አስር አይነት የተለያዩ የፍራፍሬ ችግኞች ስለመዘጋጀታቸውም ተናግረዋል። በተለይም አቮካዶ፣ ሙዝ፣ ዘይቱን፣ ፓፓያ፣ ግሽጣ፣ ብርቱካን፣ አፕል፣ ሎሚና ሌሎች የፍራፍሬ ችግኞች በስፋት መዘጋጀታቸውን ጨምረው ገልፀዋል። በክልሉ የአቮካዶ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሻሻሉና ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ ዝርያዎችን በማዳቀል የችግኝ ዝግጅት ላይ በስፋት እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት። በክልሉ እስካሁን ከ80 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመደበኛና በተሻሻሉ የአቮካዶ ችግኞች መሸፈኑንም ገልጸዋል። 👉የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፤ በክልሉ ሎካ አባያና ደራራ ወረዳዎች በበልግ ወቅት በኩታ ገጠም እየለማ ያለውን የበቆሎ ማሳ በመስክ የተመለከቱትም በዚሁ ሳምንት ነው። ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንደገለጹት በክልሉ የሰብል ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ገበያን የሚያረጋጋ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተደረጉ ባሉ ጥረቶች ውጤት እየተገኘ ነው። በዚህም በበልግ ወቅትም ፆም የሚያድር መሬት እንዳይኖር በማድረግና ግብአቶችን በወቅቱ በማቅረብ እየተከናወነ ባለው የእርሻ ስራ የምርት ቁመናው ተስፋ ሰጪ መሆኑን ጠቅሰዋል። በበልጉ ያለውን አመቺ የዝናብ ስርጭት እንዲሁም የቴክኖሎጂ አቅርቦት በመጠቀም የተሻለ ምርት ለማግኘት የተያዘውን እቅድ ለማሳካት አሁን ላይ ለማሳ እንክብካቤ ስራ ትኩረት መሰጠቱን አመልክተዋል። 👉የኢንዱስትሪ ከተማዋ ኮምቦልቻ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ በኮምቦልቻ ከተማ ተገኝተው የመረቋቸው የምግብ ዘይት እና የቆርቆሮ ማምረቻ ፋብሪካዎች ሥራ የጀመሩትም በዚሁ ሳምንት ነው። የከተማ አስተዳደሩ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሁሴን ሙሄ፤ በኮምቦልቻ የኢንዱስትሪ ልማት ይበልጥ እያንሰራራ ስለመሆኑ አንስተዋል። በኢንዱስትሪ ከተማዋ ኮምቦልቻ በድምሩ 69 አምራች ኢንዱስትሪዎች መኖራቸውን ገልጸው ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን በማምረትና ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡትን በመተካት ከፍተኛ የሃብት ምንጭ እየሆኑ ነው ብለዋል።
የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር
May 10, 2026 2728
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 2/2018 (ኢዜአ)፡- በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በሀገራችን ሁሉም ክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን? የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምልከታ- በሱሉልታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሳምንቱ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ በ2 ሺህ 150 ሄክታር መሬት ላይ የለማ የስንዴ ሰብል ጎብኝተዋል። መንግሥት በግብርናው ዘርፍ በወሰዳቸው ስትራቴጂካዊ እርምጃዎች እየተገኙ ያሉ ውጤቶች አመርቂና ለቀጣይ ሥራዎች ስንቅ መሆናቸውን በጉብኝታቸው ወቅት ተናግረዋል። መሬት ጦም ማደር የለበትም በሚል ጽኑ እምነት የተጀመረው የበጋ ስንዴ ልማት አስደማሚ ውጤት እያስመዘገበ ስለመሆኑም አንስተዋል። ከልመና ራሳችንን መገላገል አለብን፤ ሊታረስና ሊለማ የሚችል መሬት መታረስ አለበት በሚል ጽኑ እምነት የበጋ ስንዴ ልማት መጀመሩን አስታውሰው፤ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አሁን ላይ አስደማሚ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል። የቱሪዝም ልማት የወፍ በረር ጉዟችን የቀጠለ ሲሆን ከሱሉልታ ቀጥታ ወደ አማራ ክልል ባህር ዳር አምርተናል። የባህር ዳር መዳረሻችን በጣና ሐይቅ ደቡባዊ ዳርቻ ላይ በ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት ይሆናል። የሪዞርቱ ግንባታ ተጠናቆ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ ባሳምንቱ ተመርቆ በይፋ ስራ ጀምሯል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "ገበታ ለሀገር" እቅድ መሰረት በሐይቁ ሌላኛው አቅጣጫ ከሚገኘው የጎርጎራ ብርሃን (ጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት) ጋር በመቀናጀት የጣናን የቱሪዝም ቀጣና ለማነቃቃት አላማ በማድረግ ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት መገንባቱ ተመላክቷል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በባህርዳር ከተማ ቆይታቸው በ3 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የሚገነባውን ፎር ፖይንትስ ባይ ሸራተን ጣና የሆቴል ፕሮጀክት ግንባታም አስጀምረዋል። በሚድሮክ ኢንቨስትመንት የሚገነባው ይህ ዓለም አቀፍ ሆቴልም በ18 ወራት ውስጥ ተገንብቶ የሚጠናቀቅ መሆኑ ታውቋል። የመልካ ቁንጡሬ ሁነት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ከኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር የአፍሪካ ዓለም አቀፍ የቅርስ ቀንን በዩኔስኮ በተመዘገበው በመልካ ቁንጡሬ–ባልጩት አርኪዮሎጂና ፓሊዮንቶሎጂ መካነ ቅርስ ስፍራ በሳምንቱ በተለያዩ ዝግጅቶች አክብሯል። የአፍሪካ ዓለም አቀፍ የቅርስ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ10ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ4ኛ ጊዜ በመልካ ቁንጡሬ–ባልጩት አርኪዮሎጂና ፓሊዮንቶሎጂ መካነ ቅርስ ስፍራ ተከብሯል። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ህይወት ኃይሉ፤ ባህላዊና የተፈጥሮ ቅርሶች ለሀገር ገጽታ ግንባታና ለኢኮኖሚ ዕድገት ያላቸውን አስተዋጽኦ ለማጎልበት የሚያስችሉ ተግባራት ይቀጥላሉ ብለዋል። ሀዋሳ ሀይቅ ዳርቻ የሀዋሳ ሀይቅ ዳርቻ ልማት የዲዛይን ሥራ ተጠናቅቆ ለህዝብ ይፋ የተደረገውም በዚሁ ሳምንት ነው። የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በወቅቱ እንደገለጹት ከተማዋን ለኑሮ፣ ለስራ፣ ለቱሪዝምና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ለማድረግ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ውጤት እያስገኙ ነው። የልማት ስራዎቹ ከተማዋ ሀገር አቀፍ ስብሰባዎችን¸፣ ስፖርታዊ ውድድሮችና ሌሎች ኩነቶችን በማስተናገድ ተመራጭ እየሆነች እንድትመጣ አድርገዋታል ብለዋል። የሀይቅ ዳርቻ ልማቱ ለከተማዋ ተጨማሪ ውበትና የተወዳዳሪነት አቅም ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ጠቁመው ለተግባራዊነቱ በትብብር እንደሚሰራ አመላክተዋል። የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥሉ ብለዋል። የሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻን በማልማትና ከአካባቢው መስህቦች ጋር በማስተሳሳር ሀይቁን የቱሪዝም ማዕከል የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም ተናግረዋል። ጅማ ዞን ጎማ ሁለት በጅማ አጠር ያለ ቆይታችን ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጅማ ዞን ጎማ ሁለት የምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው መቅረባቸውን በማስተዋወቅ የቅስቀሳ መርሃ ግብር ተካሂዷል። በዚህ የቅስቀሳ ስነ ስርአት ላይ የፓርቲው አባላትና አመራሮች እንዲሁም ደጋፊዎች በመውጣት የተሳተፉበት መሆኑን ለማየት ችለናል።   በመርሃ ግብሩ ላይ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ነመራ ቡሊ፤ በፓርቲው አመራር ሰጪነት ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች እድገት እያስመዘገበች መሆኑን ገልጸው በመደመር እሳቤ የኢትዮጵያን እድገትና ማንሰራራት ለማስቀጠል ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል። በተመሳሳይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ርዕሰ መስተዳድሩ በሚወዳደሩበት ምስራቅ ጉራጌ ዞን ደቡብ ሶዶ ወረዳ የምርጫ ቅስቀሳና እጩ የማስተዋወቅ መርሐ ግብር የተካሄደውም በዚሁ ሳምንት ነበር። ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንዳሉት ብልፅግና ፓርቲ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችንን ሲያከናውን ቆይቷል። በባለፉት የለውጥ ዓመታት የሀገርን እድገትና የህዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን በመተግበር ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገቡን ተናግረዋል። የሽንሌ እመርታ በሳምንቱ በሶማሌ ክልል ሽንሌ ወረዳ የተገነባው የ10 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የኮንክሪት አስፋልት መንገድና በሽንሌ ጠቅላላ ሆስፒታል የተገነባው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በክልሉ ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ተመርቋል።   በሽንሌ ወረዳ የመርማርሳ ከተማን ከድሬዳዋ ጋር የሚያስተሳስር የ3 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታንም አስጀምረዋል። የተገነቡት የልማት ስራዎች በተለይም ለወረዳው እመርታ መሆኑን የገለጹት አመራሮቹ በክልሉ ያለውን እምቅ ሃብት የማልማትና የዜጎችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራዎች ይቀጥላሉ ብለዋል። ሳተላይት በሐረር የሳተላይት የመገኛ መረጃ መቀቢያ ጣቢያ ተከላ ስራ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በተገኙበት በዚሁ ሳምንት ተጀምሯል።   የሳተላይት የመገኛ መረጃ መቀበያ ጣቢያው በክልሉ ለሚከናወኑ የልማት ስራዎች ከፍተኛ እገዛ የሚያደርግ ሲሆን የመረጃ ግብዓት ከመሆን አኳያም ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተመላክቷል። የመንገድ ዲዛይን፣ አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ስራ ለሚያከናውኑ፣ የመሬት አጠቃቀምን በጥንቃቄ ለመቆጣጠር፣ ለይዞታ መረጋገጫና ሌሎችም የተሟላ መረጃ ለመስጠት የሚጠቅም መሆኑ ታውቋል።      
የአፍሪካዊው የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣረ  ዎዴ ማያ - በአዲስ አበባ
May 6, 2026 2536
ፐልስ ኦፍ አፍሪካ (Pulse of Africa-POA) ከኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ (AGA-Tech) ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁት ጉባኤ በአዲስ አበባ፣ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል። ይህ ጉባኤ ከሚያዚያ 29 እስከ 30 ቀን 2018 ዓ.ም "ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለተሻለች አፍሪካ" በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄድ አህጉራዊ መድረክ ነው። የአህጉሪቷ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ዳያስፖራዎች እና የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች የረጅም ጊዜ ትብብር የሚፈጥሩበት ይህ መድረክ፤ የአፍሪካን ትክክለኛ ትርክት ለዓለም ለማስተዋወቅ አልሟል። ታዋቂው የአፍሪካዊ ዲጂታል ታሪክ ተራኪ ጋናዊው በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) ጨምሮ የአህጉሪቷ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል። በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) በዲጂታል መገናኛ ብዙኅን የአፍሪካን ትክክለኛ ትርክትና ገፅታ ለዓለም የሚያስተዋውቅ ዓለም አቀፍ አንቱታን ያተረፈ የአህጉሪቷ የዘርፉ ፈርጥ ነው። ለኢትዮጵያ ጥልቅ ፍቅር ያለው ጋናዊው ታዋቂ ዩቲዩበርና የዲጂታል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) አዲስ አበባ ገብቷል። በጉባኤው ላይ የበርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) መገኘትም የአፍሪካን የዲጂታል ገፅታ መቀየር የሚያስችል የአህጉራዊ ይዘት ፈጠራ ትብብርን ለመፍጠር ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ይጠበቃል። የአየር በረራ መሐንዲስ ስልጡኑ በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) የዲጂታል ታሪክ ተራኪነት ጉዞ በሀገረ ቻይና ትምህርቱን በሚከታተልበት ወቅት ነበር የዩቱዩብ ይዘት ፈጠራን መሞከር የጀመረው። የመጀመሪያዎቹ የዲጂታል ይዘት ፈጠራ ሥራዎቹም አስቂኝ የነበሩ ቢሆንም ወላጅ አባቱ የአፍሪካን በጎ ገፅታ ለዓለም ማስተዋወቅ እንዳለበት የሰጡትን ምክር ተከትሎ ጉዞውን ቀይሯል። ባህላዊ ግንኙነትን ለማጠናከር የቻይንኛ ቋንቋ ቪዲዮዎችን ያዘጋጅ የነበረው ዎዴ ማያ፤ ወደ ጋና ተመልሶ በሰራቸው የመጀመሪያ ምዕራፍ ሥራዎቹ የሚፈለገውን ያህል ዕውቅና አላስገኙለትም ነበር። መነሻውን በአዲስ አበባ በማድረግ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ጉዞ በማድረግ አህጉሪቷን ለማስተዋወቅ ከሰራቸው ይዘቶች ውስጥ በሩዋንዳ የሰራው ቪዲዮ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ዕውቅናው እንዲናኝ አድርጎታል። ኢትዮጵያ በእርሱ አተራረክ ማዕከላዊ ስፍራ እንዳላት የሚናገረው ዎዴ ማያ፤ የአፍሪካን ያልተነገሩ ስኬቶችና የአፍሪካዊያን ፅናት በተከታታይ ለዓለም ማስተዋወቁን ተያይዞታል። አሁን ላይ የአፍሪካን ለውጥ፣ ተስፋና ዕድሎች ለዓለም ማህበረሰብ የሚያስተዋውቁ ዘጋቢ ፊልሞችን በመስራት የአህጉሪቷን ስሁት ትርክት በመቀየር ረገድ ጉልህ ስፍራ ከሚሰጣቸው ሰዎች አንዱ ሆኗል። በሚሊዮን የሚቆጠር ዕይታ ያላቸውን ዘጋቢ ፊልሞቹና የጉዞ ታሪኮችም ጊዜ ያለፈባቸው ስሁት ትርክቶችን በመሞገት የአፍሪካን ተስፋና ዕድሎች ለዓለም በመግለጥ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የኢትዮጵያን ዕድገትና ተስፋ ደጋግሞ የተረከው ዎዴ ማያ፤ በአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS) ወደ አዲስ አበባ መምጣቱም መድረኩን ተምሳሌታዊና ስልታዊ ያደርገዋል። ይህም የበርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) የግል ጉዞ ከመሆኑም በላይ፤ ኢትዮጵያ የአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ መድረክ ፈጠራና የታሪክ አተራረክ ለውጦች ማዕከላዊ ሚና በተግባር ያስመሰክራል። በዚህ ጉባኤ፤ እንደ ዎዴ ማያ ያሉ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች መሰባሰብ የአፍሪካን የዲጂታል ሥነ-ምኅዳር በማጠናከር ይዘት ፈጣሪዎች የአህጉራቸውን ትክክለኛ ገፅታ ለዓለም ለማስተዋወቅ ጉልህ ፋይዳ አለው። ለኢትዮጵያም የዎዴ ማያ መገኘት ሀገሪቱ ለአፍሪካ ዲጂታልና ባህላዊ ሕዳሴ ያላትን ቁርጠኝነት የበለጠ በማሳደግ አዲስ አበባን የአፍሪካ የዲጂታል ገፅታ ግንባታ ሃሳቦች መነሻነት በተግባር ያረጋግጣል።
ትንታኔዎች
 ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማ የመገንባት ሂደት እና የኮሪደር ልማት
May 24, 2026 2648
በኢዜአ ዐይን ...! በዮሐንስ ደርበው ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማ የመገንባት ሂደት እና የኮሪደር ልማት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ጥቅምት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተገኙ ጊዜ፤ የኮሪደር ልማት ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማ መገንባት መሆኑን ገልጸዋል። ከተማ ሲለማ ደግሞ ለነዋሪም ሆነ ለጎብኝ፤ ለዐይንም፣ ለጤናም ለእንቅስቃሴም ውበትና ምቾት ማላበሱ አይካድም። የኮሪደር ልማት ጽዱ ከተሞችን ይሠራል፤ከትራንስፖርት፣ ከትራፊክ ምልክቶች፣ ከብስክሌትና እግረኛ መንገድ ደኅንነት ጋርም ተጣጥሞ ተሠርቷል። በዚህ ዐውድ የኮሪደር ልማት ውበትም ምቾትም ነው። መሠረተ-ልማት ተጠብቆ ለረጅም ጊዜ እንዲጠቅምም የኮሪደር ልማት ሚና የላቀ ነው። እንግልትንና ብልሹ አሠራርን መቅረፊያ ብልኀት - መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለአንጀት ካንሰር አጋላጭ ምክንያቶች በውል ይታወቃሉ? ቀድሞስ መከላከል ይቻላል? የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካ ለአገልግሎት ክፍት መሆን ኢትዮጵያ በከተሞቿ እና ገጠራማ አካባቢዎቿ የኮሪደር ልማት እያከናወነች ነው። ይህ በኢትዮጵያ ከውበት በላይ ነው። ለምን ቢሉ? ዘርፈ-ብዙ ጥቅም ስላለው ይሆናል መልሱ። · ማኅበራዊ መሥተጋብርን በመጠገን፡- ኢትዮጵያውያን ከሚታወቁባቸው አንዱ በየዐውዱ የሚገለጠው ጥብቅ ማኅበራዊ መሥተጋብራቸው ነው። በጋራ መንቀሳቀስ፣ መጫዎት፣ ከቤት ወጣ ብለው መመካከር የኑሯቸው አካል ነው። ይሁንእንጅ በተለይም ከተሜው ከወዳጅ ጋር በኅብረት በእግር ወይም በብስክሌት ለመንቀሳቀስ፣ አረፍ ብሎ የሚያወጋበት በቂ አረንጓዴ ስፍራና ፓርኮች ባለመኖራቸው ማኅበራዊ መሥተጋብሩ እየላላ የመጣ ይመስላል። አሁን የኮሪደር ልማት በደረሰባቸው ከተሞች፤ሰዎች ሲያሻቸው በእግር አሊያም በብስክሌት ከወዳጆቻቸው ጋር የልባቸውን እያወጉ ለመንቀሳቀስ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። ሰዎች በእንቅስቃሴያቸው መሐል ዐረፍ ማለት ቢሹም ችግር የለም፤ አሁን እንደ ድሮ አይደለምና። አረንጓዴ መናፈሻ ስፍራ ፍለጋ ከከተማ መውጣት አያሻም። በሌላ በኩል ወጣቶች እና ሕጻናት ኳስ የሚጫወቱበት ስፍራ መመቻቸቱ ጤናን ከመጠበቅ ባሻገር፤ ማኅበራዊ መሥተጋብራቸውን ያጠናክራል። · ጤናማ አከባቢን በመፍጠር፡- የኮሪደር ልማት ለሰው ልጆች ከቸራቸው ጥቅሞች አንዱ፤ ጤናማ ከባቢን መፍጠር ነው። በተለይም በደካማ የፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ለሚታሙ ከተሞች የኮሪደር ልማት ሁነኛ መፍትሔ ሆኗል። ይህ ደግሞ በቀጥታ ከነዋሪዎች ጤና ጋር ይገናኛል።ደግሞም በንጹህ አካባቢ የመኖር መብትን ማስጠበቅ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ በኮሪደር ልማት ሰፋፊ መንገድ ከመሥራት ባለፈ ታዳጊዎች እግር ኳስ የሚጫወቱባቸው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና የእግረኛ መንገዶች ተሠርተዋል ያሉትም ለዚህ ነው። · በሥራ ዕድል ፈጠራ፡- የኮሪደር ልማት የዘመቻ ሥራ አይደለም።በትንሹ በአንድ ከተማ ወይም አካባቢ ተጀምሮ እየሰፋ ይቀጥላል። በዚህ ሂደት የሚፈጠረውን የሥራ ዕድል ማሰብ አያዳግትም። እንዲሁም የኮሪደር ልማት ሥራዎች ሲከናወኑ፤ ለሥራ ዕድል ፈጠራ የሚያገለግሉ የመኪና ማቆሚያ፣ ሱቆች እና መሰል ለንግድ ተግባራት እንዲበጁ ተደርገው ነው። የኮሪደር ልማት ከከተሜነት ዕድገት ጋር የተሣሠረ ልማት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መናገራቸው ይታወሳል። · በገጽታ ግንባታ ረገድ፡- ከተሞች ሲጸዱና ምቹ ሲሆኑ በዐለም ዘንድ መታወቂያ ይሆናሉ። ነዋሪም በኩራት ስለአካባቢው በየሄደበት አምባሳደር ሆኖ ይመሠክራል። ቱሪስቶችንም ይስባሉ። የቆይታ ጊዜያቸውንም ለማራዘም ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረክታሉ። ዐለም ዐቀፍ፣ አኅጉር ዐቀፍ እና ሀገር ዐቀፍ ጉባዔዎች እንዲካሄድባቸውም እንዲመረጡ ያስችላል። በከተሞች ከሚሠራው የኮሪደር ልማት ባሻገር፤ የገጠር ኮሪደር ልማት እየተሠራ ነው። ይህም ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ፍትሐዊ ልማት ለዜጎች መቅረቡን ያሳያል። ይህም ኢትዮጵያውያን የተሻለ ኑሮ ይገባቸዋል በሚል የተጀመረ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ተናግረዋል። የተሟላ ብልጽግና የምናረጋግጠው በዚሁ መንገድ ነውም ብለዋል። የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገውን ፍልሰት በመቀነስ የተመጣጠነ ዕድገት በሁሉም አካባቢ ለማምጣት የገጠር ኮሪደር ልማት መጠናከር ጠቀሜታው የጎላ ነው። የገጠር ኮሪደር ልማት ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ሥነ-ምኅዳራዊ ፋይዳን ጨምሮ ብዙ ጥቅም አለው፤ ይህም ዘላቂ ልማትና የተረጋጋ ኅብረተሰብ ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና ይጫዎታል። የከተሞች መዋብና ምቹ መሆን ለነዋሪው ነው፤ በቀጥታ ተጠቃሚውም ሕዝቡ። ስለዚህ መንግሥት ከሚያከናውናቸው በተጨማሪ ባለሃብቱ፣የመንግሥትም ሆኑ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ኅብረተሰቡ የኮሪደር ልማትን በተነሳሽነት ለማስፋፋት መትጋት ይጠበቅበታል። #የኮሪደር_ልማት #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #ኢትዮጵያ
ባሳለፍነው ሳምንት …
May 23, 2026 1243
በዮሐንስ ደርበው ከግንቦት 9 እስከ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … 👉የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካ ለአገልግሎት ክፍት መሆን የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ጉዟችን አካል እና የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ እመርታ ትልቅ ማሳያ የሆነው የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካ ተመርቆ አገልግሎት ጀምሯል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አስታውቀዋል። ‎ ‎​ፋብሪካው የዓለም ዓቀፍ ጥራትና ተወዳዳሪነት መስፈርቶችን የሚያሟሉ የሴራሚክ ምርቶችን የሚያቀርብ መሆኑንም ገልጸዋል። ለምርቱ የሚያስፈልጉትን ጥሬ ዕቃዎች ከ80 በመቶ በላይ ከሀገር ውስጥ ዐቅም ያገኛልም ብለዋል። ይህ ስኬት ኢትዮጵያ የራሷን የተፈጥሮ ሀብትና እምቅ ጸጋ የመጠቀም ብቃቷን ከመገንባቱ ባሻገር፤ በውጭ ገቢ ምርቶች ላይ ያለንን ጥገኝነት በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሰዋል ነው ያሉት። 👉ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በጎዴ ማዳበሪያ ፋብሪካ ፕሮጀክት ያደረጉት ጉብኝት ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የጎዴ የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ ሥራ የደረሰበትን ደረጃ ለመገምገም የፕሮጀክት ስፍራውን ጎብኝተዋል። በዚሁ ወቅትም፤ ይህ ሥራ ከመሠረተ-ልማት ግንባታም በላይ ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን፣ የምግብ ሉዓላዊነት፣ የኢንዱስትሪ ዕድገት እና በኢኮኖሚ ራስን የመቻል ጥረት ውስጥ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው ኢንቨስትመንት መሆኑን አስገንዝበዋል። በፕሮጀክቱ ስፍራ የሚታየው የሥራ ሂደት ፍጥነት አበረታች መሆኑን ጠቁመው፤ ይህን ግዙፍ እና እጅግ ጠቃሚ ሀገራዊ ፕሮጀክት ለመፈፀም ያለውን ቁርጠኝነት እና ትብብር በሚያንፀባርቅ ሁኔታ በተለያዩ የፕሮጀክቱ ክፍሎች ያሉት ግንባታዎች በዕቅዳችን መሠረት እየተጓዙ ይገኛሉ ሲሉም አረጋግጠዋል። 👉የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት “የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት” በተሰኘውና ኢትዮጵያ በመረጃና በስታቲስቲክስ የሉላዊነት ጉዞ ያስመዘገበችው ትልቅ ድል በተበሰረበት ሀገራዊ ጉባዔና ኤግዚቢሽን ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተገኝተው ነበር። በዚሁ ወቅትም፤ የተመለከቱት የዘርፉ እመርታ እጅግ አስደሳች ሆኖ አግኝቼዋለሁ ብለዋል። ‎ ‎መረጃ የዚህ ዘመን ስትራቴጂካዊ ሀብት እና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የሚገነባበት ቁልፍ የሉዓላዊነት ምሰሶ መሆኑንም አስገንዝበዋል። የተዋሰ አሊያም በውጭ አካላት ላይ ጥገኛ የሆነ መረጃ ሀገራዊ መሻታችንን ማሳካት ስለማያስችል፤ የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የራስን መረጃ በራስ ዐቅም መሰብሰብ እና መተንተን ወሳኝ ግብዓት ነው ብለዋል። ‎ ከሁሉም በላይ፤ የመረጃ አሰባሰብና ትንተና ሥራ በሀገር ልጆች ዕውቀትና ክኅሎት ሲከወን ማየት ታላቅ ሀገራዊ ኩራት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከዚህ በተጨማሪ የመረጃ ትኩረታችን በቁጥር በሚገለጹ ውጤቶች ላይ ብቻ ሳይሆን ሰው ተኮር በሆኑና በዜጎች ሕይወት በሚታዩ ተጨባጭ ለውጦችም ላይ መሆን አለበት ነው ያሉት። 👉ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሐረሪ ክልል ያደረጉት የልማት ሥራዎች ጉብኝት ባሳለፍነው ሳምንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሐረሪ ክልል የልማት ሥራዎች የጎበኙ ሲሆን በወቅቱም፤ በሐረሪ ክልል የተመለከትነው የገጠር ኮሪደር ልማት የአርሶ አደሩን የኑሮ ዘይቤ በመቀየሩ ረገድ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል። በሶፊ ወረዳ ቡርቃ ቀበሌ የተገነቡት ቤቶች የሰዎችን ማደሪያ ከሕጻናትና ከከብቶች ቤት የለዩ፣ የዶሮ እርባታ፣ ሻወርና መፀዳጃ ቤት እንዲሁም የጓሮ የሌማት ትሩፋትን ያካተቱ ሙሉ ፓኬጅ መሆናቸውን ገልጸዋል። የገጠር ኮሪደር ልማት የአርሶ አደሩን ጉልበትና ሀገር በቀል ዕውቀት በመጠቀም፣ በአነስተኛ ወጪ በአጭር ጊዜ ውስጥ ትልቅ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ማሳያ በመሆኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። በተመሳሳይ በሐረር ከተማ እየተከናወኑ ያሉትን የማር፣ የወተትና የዶሮ እርባታ የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን የጎበኙ ሲሆን፤ በከተማው በኢኒሼቲቩ በግለሰብና በመንግሥት ደረጃ ሼዶችን በመገንባት የማር፣ የወተት፣ የእንቁላልና የአሳ መንደሮችን የማቋቋም ሥራ በስፋት እየተሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። እንደ ሀገር የአመጋገብ ሥርዓታችንን ከመሠረቱ ለመቀየር እና በምግብ እራስን ለመቻል ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው ይህ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል። የእንስሳት፣ የዶሮና ዓሳ ዝርያ ማሻሻልና መኖ ማቀነባበሪያዎች ላይም ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራበት ይገኛል ነው ያሉት። 👉የኢትዮጵያ አየር መንገድ 80ኛ ዓመት ባሳለፍነው ሳምንት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ80ኛ ዓመት ክብረ በዓል የእራት መርሐ ግብር ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጽናት፣ የዕድገት እና የጥቁር ሕዝብ የከፍታ ዓርማ ነው ብለዋል። ሀገር ማጽናት የሚቻለው ተቋማትን በማጽናት ነው፤ በዘመናዊ ታሪካችን የገጠሙን የስብራት ወጀቦችን አልፎ፣ የኢትዮጵያን ስምና ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጎ ታሪክ እየጻፈ የተጓዘው አየር መንገዳችን የጽናታችን ግንባር ቀደም ማረጋገጫ ነው ሲሉ ገልፀዋል። ለሀገራችንም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማምጣት፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ በመደገፍ፣ ሀገራችንን በአቪዬሽን መሠረተ ልማት ከፍ በማድረግ፣ የቱሪዝም ዘርፉን በማገዝና በሌሎች ዘርፎች ባለው ግዙፍ አበርክቶው የዕድገታችን ምሰሶ ሆኗልም ነው ያሉት። ይህ ተቋም በሁለት እግሩ እንዲቆም ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ መሪዎችና ሠራተኞች ነበሩት፤ አሁንም አሉት፣ ወደፊትም ይኖሩታል። ይህ የተቋሙ አንጡራ ሀብት በመሆኑ የመንግስት ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም አረጋግጠዋል።
እንግልትንና ብልሹ አሠራርን መቅረፊያ ብልኀት - መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት
May 17, 2026 4781
በኢዜአ ዐይን …! በዮሐንስ ደርበው እንግልትንና ብልሹ አሠራርን መቅረፊያ ብልኀት - መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ለእንግልትና ብልሹ አሠራር አጋላጭ ሁኔታዎች ይስተካከሉን የሚሉ እሮሮዎች በተለያዩ ሕዝባዊ ውይይቶች ሲነሱ ቆይተዋል። በተለይም በአንዳንድ ተቋማት መንግሥታዊ አገልግሎት ለማግኘት እዚያም እዚህም መንከራተት፤ደግሞም ወረፋ በመጠበቅ መጉላላት ብሎም ለጊዜና ገንዘብ ወጪ መዳረግ ይስተዋላል የሚሉ ሐሳቦች ተስተጋብተዋል። ሾተላይ ምንድነው? እንዴትስ ይከሰታል? ቀድሞ መከላከልስ ይቻላል? ባሳለፍነው ሳምንት … መንግሥትም የተነሱ ቅሬታዎችን ማረቅ የሚያስችል አሠራር በመንደፍ ሚያዝያ 18 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አንድ ብሎ አስጀመረ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ማዕከሉ አገልግሎት ባስጀመሩበት ወቅትም ዜጎቻችን ላይ ምሬት የሚፈጥሩ አሠራሮችን ፈትሾ ማስተካከል ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው ብለው ነበር። አሁን ላይም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሁን በተለያዩ ከተሞች እየተስፋፋ ነው።መስፋፋቱም በማዕከላት ብዛት፣በአገልግሎት መስጫ መስኮቶች ቁጥር እና በአገልግሎት ዐይነቶች እየተገለጠ ነው። በዚህም በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 2 ሺህ 260 አገልግሎቶች በአንድ ቋት የተደራጁ ሲሆን ይህ አሃዝም ለዘርፉ የተሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት እና ያለውን ፈጣን እድገት ያመላክታል። ጉዳዩ የዜጎችን የአገልግሎት አሰጣጥ ማላቅ፤ ብልሹ አሠራርንም መቅረፍ ነውና መንግሥት በልዩ ትኩረት ይዞታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድሬዳዋ አሥተዳደርና በሐረሪ ክልል ጉብኝት ባደረጉበት ወቅትም፤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን የምልከታቸው አካል ማድረጋቸው ለጉዳዩ የተሰጠውን ከፍያለ ትኩረት ያሳያል። በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሶብ የሞባይል አገልግሎትን በመረቁበት ወቅት ደግሞ፤ ካቀድናቸው አምስት የልማት ምሰሶዎች መካከል ቴክኖሎጂን ለአገልግሎት ዘርፉ እንደ ዋነኛ መሣሪያ በመጠቀም፣ የአገልግሎት ቅልጥፍናንና ተደራሽነትን ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሠራን ነው ብለዋል። አክለውም፤በመሶብ አገልግሎቶች የታየው ከፍተኛ የደንበኞች ዕርካታ የዚህን የሥራ ሞዴል ውጤታማነት በግልጽ አረጋግጧል፤ ይህም አሠራሩን ይበልጥ ማስፋፋት አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል። ዜጎቻችን ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙና ትርጉም ያለው የጊዜ ቁጠባ እንዲያገኙ ለማስቻል፤ እነዚህን የተቀናጁ አገልግሎቶች ይበልጥ ተደራሽ የማድረግ ሥራችንን እንቀጥላለን ሲሉም አረጋግጠዋል። በተመሳሳይ በዚሁ ጉዳይ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባጋራው መረጃ መሶብ ተንቀሳቃሽ የአውቶቡስ አገልግሎት፤ አስፈላጊ የሆኑ የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀጥታ ወደ ማኅበረሰቡ ለማድረስ የተወሰደ ትልቅ እርምጃ ነው ብሏል። የስምንት ተቋማትን አገልግሎት በአንድ ላይ በማቀናጀት፣ ዜጎች ረጅም ርቀት ሳይጓዙ ወይም የተለያዩ ቢሮዎችን ማንኳኳት ሳያስፈልጋቸው ምቹ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ መፍትሔ ይሰጣል ማለቱም ይታወቃል። የፌዴራል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል አንተነህ ማሞ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ደግሞ፤ ዘመናዊና ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት ምኅዳር በመፍጠር የተገልጋዮችን እርካታ ማረጋገጥ ያስቻለ ስኬት ተገኝቷል ብለዋል። በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሚሰጡ የመንግሥት አገልግሎቶችም ዜጋ ተኮር፣ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍልና የተገልጋዮችን ፍላጎት ማዕከል ያደረጉ መሆናቸውን አብራርተዋል። በዲጂታል 2030 የአገልግሎት አሰጣጥ አመላካች ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚጠቀሱ 50 ሀገራት መካከል አንዷ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል። ዜጎች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በኦንላይን በየትኛውም ቦታ ሁሉንም አገልግሎቶች እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሠራ ስለመሆኑም እንዲሁ። አገልገሎቱን ያገኙ አስተያየት ሰጭዎች ለኢዜአ እንዳሉት፤ እንግልትን ያስቀረ፣ ጊዜና ወጭን የቀነሰ ነውና ይስፋፋ፤ ተጠናክሮም ይቀጥል። #መሶብ_የአንድ_ማዕከል_አገልግሎት #የዜጎችን_እንግልትና_ብልሹአሠራርን_መቅረፍ #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #በኢዜአ_ዐይን
ባሳለፍነው ሳምንት …
May 17, 2026 2821
በዮሐንስ ደርበው ከግንቦት 2 እስከ ግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … · ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ጋር መምከራቸው ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ዋና ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂየቫ ጋር መክረዋል። በዚሁ ወቅትም በኢኮኖሚያዊ እድገት፣ በአጋርነት እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል። ‎ለነበረን ጠቃሚ የሐሳብ ልውውጥና ቀጣይነት ላለው አጋርነትም ምስጋናዬ የላቀ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። · ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባዔ በኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ እና በፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በጋራ አዘጋጅነት በናይሮቢ በተካሄደው የአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባዔ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን ተሞክሮ አካፍለዋል። በዚሁ ወቅትም በተለይም የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማት እና የኃይል ሽግግርን በተመለከተው ውይይት ላይ ከተሞክሯችን የተቀዱ ከፍ ያሉ ሐሳቦች ተነስተዋል ብለዋል። አክለውም፤ ኢትዮጵያ በተነሱት ሁለት ዘርፎች የጀመረችውን ሥራ በማጠናከር የላቀ ሚና መጫወቷን ትቀጥላለች ሲሉ አረጋግጠዋል። · የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሳምንት የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንኳን ደህና መጡ ስል ሁልጊዜም በልዩ ኩራትና ደስታ ነው ሲሉ ተቀብለዋቸዋል። ከአቀባበሉ በኋላም፤ መሪዎች በጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። በዚህም መሠረት፤ በታዳሽ፣ የተቀናጀ እና ዘላቂ ኃይል እንዲሁም የዲጂታላይዜሽን ፕሮግራምን ለመተግበር የሚውል የ54 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ ብድርን ጨምሮ የ150 ሜጋ ዋት የጂኦተርማል የመንግሥትና የግል አጋርነት አዲስ የማዕቀፍ እና የፍኖተ ካርታ ስምምነት ተፈርሟል። · ‎ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የስምንት አስርት ዓመታት ጉዞ ‎ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የስምንት አስርት ዓመታት ጉዞን ምክንያት በማድረግ፣ "በሰላም አብሮ ለመኖር" በሚል መሪ ቃል ልዩ የመታሰቢያ ቴምብር ስብስብ ማውጣቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ አድርገዋል። ‎እነዚህ አራት ቴምብሮች እ.ኤ.አ. በ1945 በሳን ፍራንሲስኮ የተባበሩት መንግሥታት ቻርተርን ከመፈረም ጀምሮ፤ በኮንጎ የሰላም አስከባሪ ኃይሎችን እስከማሰማራት እና በአፍሪካ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደውን የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ እስከ ማስተናገድ ያለውን የጋራ ታሪካችንን የሚተርኩ ናቸው ብለዋል። በዓለም የፖስታ ኅብረት በኩል ለ192 ሀገራት የተሰራጩት እነዚህ ቴምብሮች፤ ለአንድ ወቅት ብቻ ሳይሆን ለትውልድ ሁሉ የሚተርፍ የታሪክ ዐሻራ ማሳያ መሆናቸውንም አስታውቀዋል። ‎በተያያያዘም፤ ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እና ለቡድናቸው፣ በዘመናዊው ታሪክ ውስጥ እጅግ ፈታኝ በሆነ ወቅት ላይ ሰላምን፣ ልማትን እና ሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር እያሳዩት ላለው ጽኑ አመራር ጥልቅ አድናቆታችንን እንገልጻለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። ‎የተባበሩት መንግሥታት የጸናው ሀገራት ከመከፋፈል ይልቅ ውይይትን ስለመረጡ መሆኑን አስገንዝበው፤ ‎ኢትዮጵያም ይህንኑ የሁልጊዜ ምርጫዋን ታጸናለች ሲሉ አረጋግጠዋል። · የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የአፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የአፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ባሳለፍነው ሳምንት ተካሂዷል። በዚሁ ወቅትም የምክክር ባህል እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበው፤ ጠንካራ የሲቪክ ማኅበረሰብ ባህል ግንባታ ደግሞ ያላሰለሰ የመነጋገር ልምምድ እና የሰከነ የወል መደማመጥን ግድ ይላል ብለዋል። የእስካሁን ሂደቱም በማኅበረሰባችን በየደረጃው የመደማመጥን ከፍ ያለ ጠቀሜታ አሳይቷል ሲሉም ገልጸዋል። ሂደቱ በሀገራችን ሁሉም ማዕዘናት የሚገኙ ከ90 በመቶ በላይ ኢትዮጵያውያንን አመለካከቶች እና የውይይት ውጤቶች ያንፀባረቀ ሆኗልም ነው ያሉት። ለሀገር ወሳኝ ፋይዳ የያዘው የምክክሩ ምዕራፍ ተጨባጭ ውጤት ወደሚያስገኘው ቀጣይ ምዕራፍ በሚሸጋገርበት በዚህ ወቅት፤ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለሀገራችን ሰላም፣ አንድነት እና ዘላቂ መረጋጋትን የሚያረጋግጥ የጋራ ፅኑ አቋም እና ገንቢ በሆነ መንገድ አስተዋፅኦ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል። · የገላን ኢንዱስትሪ ፓርክ መመረቅ ‎ ‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክን በመረቁበት ወቅት፤ ፓርኩ አስተማማኝ እና ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት በጀመርነው የብልጽግና ጉዞ ተደማሪ እመርታ ነው ብለዋል። ለመካከለኛ እና ከፍተኛ ኢንተርፕራይዞች ምቹ የንግድ ከባቢ ከመፍጠር ባሻገር በሺዎች ለሚቆጠሩ ወጣቶቻችን የሥራ ዕድል ይከፍታል ሲሉም ገልፀዋል። ‎ ‎ፓርኩ የሀገራችን አምራቾች አቅማቸውን በማጎልበት፣ ምርታማነታቸውን ማሳደግና ተወዳዳሪነታቸውን በመጨመር ለከተማችን፣ ለሀገራችንና ለቀጣናው የሚተርፉበት ታላቅ እድልን ይዟል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ተኪ ምርቶችን በማምረት በአምራቾችና በሸማቾች መካከል ቀጥተኛና ቀልጣፋ የንግድ ትስስር ይፈጥራል፤ ምርቶችን ደግሞ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የሀገራችንን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግ ጉልህ ሚና ይጫወታል ሲሉ አስረድተዋል። · ዓለም አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ጉባዔ መጀመር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባሳለፍነው ሳምንት ዓለም አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ጉባዔን ባስጀመሩበት ወቅት፤ ኢትዮጵያ ለልማት በምታደርገው ቆራጥ ጥረት ውስጥ የሰው ተኮር የልማት አቅጣጫ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ዋና ጉዳዮች አንዱ መሆኑን አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት መንግሥት መጪው ትውልድ ጤናማ፣ ብቁ እና ውጤታማ እንዲሆን የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራምን ማዕከል በማድረግ ሁሉን አቀፍ ሥራ እየተገበረ እንደሚገኝም ተናግረዋል። በመላ ሀገሪቱ ከ35 ሺህ በላይ የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በማስፋፋት የነጻና አስገዳጅ ትምህርት ተደራሽ እንዲሆን እያደረግን ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ልጆች ላይ መሥራት በነገ ሀገር ላይ መሥራት በመሆኑ ተባብረን፣ በጊዜ የለንም መንፈስና በትጋት እንሥራ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። · የፖሊሲ ቀን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት፤ ባሳላፍነው ሳምንት በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያው የፖሊሲ ቀን ተከብሯል። በዚሁ ወቅትም፤ ውጤታማ ፖሊሲ ለሀገራዊ ዕድገት የጀርባ አጥንት መሆኑን አስገንዝበው፤ መንግሥት በግልፅ፣ ተተግባሪና ጥራት ባላቸው ፖሊሲዎቹ ለሕዝብ የገባውን ቃል እየተገበረ ስኬትም እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል። ሀገራችን ወሳኝ ምዕራፍ ላይ በምትገኝበት በዚህ ወቅት ብሔራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ በጂኦ-ፖለቲካዊና በቴክኖሎጂ ለውጦች ላይ ቀድሞ ምላሽ የሚሰጡ ጥናቶች ያስፈልጋሉ ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግሥት በዕውቀት ላይ ኢንቨስት በማድረግ እና ለማስረጃዎች ዋጋ በመስጠት፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆነ የፖሊሲ ሥነ-ምኅዳር ለመገንባት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። ለዚህ ስኬት ሁላችንም በጋራ እንሥራ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።  
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ? 
Oct 13, 2025 8736
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 5128
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል።   በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 10905
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 9384
  ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 70098
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 59683
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 40113
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 37699
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 30365
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 29772
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 29255
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 28624
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 70098
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 59683
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 40113
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 37699
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
የከተማ ግብርናን ከጤና ሙያው ጋር ያጣመረው ወጣት
May 14, 2026 3331
በቀደሰ ተክሌ (ከሚዛን አማን) የሰው ልጅ የሕይወት ኡደት በጊዜ የታጠረ ነው። የሰውነት ሚዛን ተለክቶ ውብ ሆኖ የሚገኘው ደግሞ በዚህ የጊዜ ምጣኔ ውስጥ ስኬታማ ሥራ ሰርቶ ተገቢው ቦታ ላይ ሲገኙ ብቻ ነው። ጠንካራ ሰዎች በዕድሜ ዘመናቸው የተሰጣቸውን ጊዜ በአግባቡ ተጠቅመው ስኬት ላይ ይደርሳሉ። ለጊዜ ብዙም ትርጉምና ዋጋ የማይሰጡ ሰዎች ደግሞ እንቅስቃሴያቸውን በጊዜ ስለማይገደብና በዚያው ልክ ተሯሩጠው ስለማይሰሩ ስኬታማ ሳይሆኑ ዘመናቸውን በችግር ያሳልፋሉ። ሰው ሲፈጠር ይህን በማመዛዘን የተሻለውን መንገድ ይጠቀም ዘንድ ደግሞ አዕምሮ ተሰጥቶታል። ማንም ሰው በኑሮ ከመመራት ይልቅ ራሱ ኑሮን መምራት የሚችለው ጠንክሮ ሲሰራ ነው። የአንድ ጠንካራ የሥራ ሰው አንዱ መለኪያ ደግሞ የጊዜ አጠቃቀሙ ነው። ጊዜውን በማብቃቃት ካለው ሥራ ተጨማሪ ሥራ ፈጥሮ የሚሰራና ለበለጠ የሚተጋ ስኬታማ ሕይወትን መምራት ይችላል። በሚዛን አማን ከተማ ኢዜአ ያነጋገርው ወጣት ይህን በተግባር በማረጋገጥ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ነው። ወጣት ዳዊት ባይቴንስ ይባላል። ከተሰማራበት የጤና ዘርፍ ጎን ለጎን ባለው ትርፍ ጊዜ በከተማ ግብርና ሥራ ተሰማርቶ ተጠቃሚነቱን እያሳደገ ይገኛል። ሰርቶ ለመለወጥ ካላው ፍላጎትና ቁርጠኝነት የተነሳ በሕይወቱ ምንም አይነት ጊዜ እንዲባክንበት አይፈልግም። እያንዳንዷን ሰዓትና ደቂቃ ትርጉም ባለው መልኩ ለሥራ ያውላል። ይህ የመነጨው ደግሞ ከሥራ ወዳድነቱ ነው። ሲሰራ ውሎ ሲሰራ ቢያድር ደከመኝና ሰለቸኝን አያውቅም። ለእዚህ ባህሪው እርሾ የሆነው ደግሞ በልጅነቱ ወላጆቹን በግብርና ሥራ እያገዘ ማደጉ ነው። በትምህርቱም ወደ ኋላ ሳይል ጠንክሮ በመማር ስኬታማነቱን አስመስክሯል። የኮሌጅ ትምህርቱን በፋርማሲ የተመረቀው ወጣቱ በአሁን ወቅት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል በጤና ባለሙያነት እየሠራ ይገኛል። የጤና ተቋም ሥራው ቀንና ማታ በፈረቃ የሚሰራ በመሆኑ ከሆስፒታል ሥራው ውጪ ሲሆን ከተማ ወጥቶ በመዝናናት አሊያም በዋዛ ፈዛዛ የሚያሳልፈው ጊዜ የለውም። ከጤና ሥራው ጎን ለጎን በቤቱ ዙሪያ ያለውን ባዶ መሬት እያለማ ይገኛል። የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮችን ተከትሎ በተለይ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ ይህን የግብርና ልማት ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። የግብርና ሥራውን የጀመረው በጤና ሙያ ሥራው በወር ከሚያገኘው ደመወዝ ባሻገር ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ለማግኘት አስቦ ነው። "የግብርና ምርቱ ለቤት ውስጥ ፍጆታ ባውለው እንኳ ወጪዬን ይቀንሳል" የሚለውም ሌላው መነሻ ምክንያቱ ነበረ። በዚህም ባለው ጠባብ መሬት ላይ ቆስጣ፣ ጥቅል ጎመን፣ ካሮትና መሰል የጓሮ አትክልቶችን አልምቶ በመጠቀም "ምግቤን ከጓሮዬ" የሚለውንም ንቅናቄ በተግባር አሳይቷል። በጓሮ ያለማቸውን ምርቶች ለቤተሰብ ፍጆታ ማዋሉም ከወጪ እንደታደገው ነው የገለጸው። የአካባቢው መሬት ያለስስት ከሚያበቅላቸው ፍራፍሬዎች መካከል ሙዝ በቀዳሚነት ይጠቀሳል። ወጣት ዳዊትም በጓሮ አትክልት የጀመረውን ሥራ በማስፋት በቤቱ ዙሪያ የሙዝ ልማት ስራውን አጠናክሯል። የሙዝ ምርቱም ከቤት ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለገበያም እያቀረበ ነው። ዛፉም ጥላ ሆኖ እያገለገለው ነው። ሁሌም ለተጨማሪ ሥራ የሚተጋው ይህ ባለ ራዕይው ወጣት ምርጥ የቡና ዘር ከግብርና ባለሙያዎች በመውሰድ ችግኝ አዘጋጅቶ ለአርሶ አደሮች ያሰራጫል። አምና የቡና ችግኝ ተከላ ወቅት ከ15 ሺህ በላይ የቡና ችግኞችን በጓሮው አዘጋጅቶ በመሸጥ ተጠቃሚ ሆኗል። ከጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ባሻገር በቆሎ በማልማትም ተጠቃሚነቱን እያሳደገ ነው። ወጣት ዳዊት ባለው ጠባብ የከተማ ማሳ ላይ እነዚህን ልማቶች እያከናወነ ያለው በአንድ ጊዜ አይደለም። እንደ የአዝመራው ተስማሚነት አፈራርቆ የማልማት ጥበብንም ተክኗል። በቆሎ ደርሶ የተነሳበት ማሳ ላይ ሌሎች አትክልቶችን ያለማል። በሌላ በኩል ደግሞ ጥምር የእርሻ ሥርዓትን በመከተል በሙዝና ሌሎች ፍራፍሬዎች ስር ባለ ክፍት ቦታ ላይ ቡና ያለማል፤ የአትክልት ችግኞችንም ያዘጋጃል። ይህ ብልህነት የተሞላው የከተማ ግብርና ልማት ሥራው የከተማ ቤቱን የገጠር ሞዴል አርሶ አደር ማሳ አስመስሎታል። ወደፊት የተቀናጀ የግብርና ልማት ጣቢያን የመፍጠር ዓላማ እንዳለው የገለጸው ወጣቱ፣ በቅርቡም በንብ ማነብ ሥራ ውስጥ ለመሰማራት እየተዘጋጀ መሆኑን ነው የተናገረው። ለዚህም የቀፎ ግዥና የቀፎ ማስቀመጫ ቦታ ዝግጅት ሥራ ላይ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት በገበያ እየታየ ያለውን የዋጋ ንረት መቋቋም የሚቻለው ሰርቶ ውጤታማ ሲኮንና ገቢን ማሳደግ ሲቻል ነው የሚል እምነት አለው። ወጣቱ እንደሚለው ምርት የሚያመርት ሰው እየበዛ ሲመጣ ገበያው ይረጋጋል። በመሆኑም ሰዎች ሁሉንም ነገር ከገበያ ከመግዛት ይልቅ ባላቸው ትንሽ መሬት ላይ የተወሰነ ምርት በማምረት ለቤት ውስጥ ፍጆታ እንዲጠቀሙ ይመክራል። ከመደበኛ የመንግሥት ሥራው ጎን ለጎን የተሰማራበት የከተማ ግብርና ልማት ሥራ ወጪውን ከመቆጠብ አልፎ ተጨማሪ ገቢ እያስገኘለት በመሆኑ በቀጣይም ልማቱን ለማጠናከር ሞራል እንደሆነው ተናግሯል። እሱ እንደሚለው ከሆነ በአካባቢው በርካታ ወጣቶች የቤተሰቦቻቸውን ማሳ ትተው በከተማ ያለ ሥራ ጊዜያቸውን ሲያሳልፉ ማየት የተለመደ ነው። ነገር ግን ነገን የተሻለ ለማድረግ ዛሬ የወጣትነት ጊዜን ጠንክረን ልንሰራ ይገባል ይላል። ወጣቶችም ያላቸውን ጉልበትና ጊዜ በመጠቀም ሀብት ማፍራት የሚያስችላቸውን ሥራ መሥራት እንዳለባቸው ይመክራል። በተለይ የእርሻ መሬት ያላቸው ወጣቶች በግብርና ሥራ ራሳቸውን መለወጥ፣ ቤተሰቦቻቸውን መመገብ፣ ገበያ ማረጋጋትና በሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ውስጥ አሻራቸውን ማሳረፍ እንዳለባቸው ነው የገለጸው። የሚዛን አማን ከተማ ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ኅብረት ሥራ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን መንግሥቱ የወጣት ዳዊት ታታሪነት ለብዙዎች ተሞክሮ እንደሚሆን ነው የገለጹት። በተለይ የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮችን መሠረት በማድረግ ያከናወናቸው ተግባራት በትንሽ መሬት መስራት ከተቻለ ገበያን ማረጋጋት እንደሚቻል በተግባር ያሳየ ነው ብለዋል። ጽህፈት ቤቱ ወጣቱንና የእሱን ፈለግ ተከትለው የሚሠሩ ወጣቶችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። ኃላፊው እንዳሉት በአሁኑ ወቅትም በሌማት ትሩፋት የሥራ ዘርፎች ወጣቶች በብዛት እንዲሰማሩ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው። በራስ ተነሳሽነት ያላቸውን ጊዜ አብቃቅተው ወደልማት የገቡ እንደ ወጣት ዳዊት ያሉ ወጣቶች ቢበራከቱ ለግብርናው ዘርፍ ኢኮኖሚ የሚኖራቸው አዎንታዊ ሚናም የጎላ ነው። ማንም ሰው ኑሮን አሸንፎ ወጤታማ ለመሆን እንደ ወጣት ዳዊት በሥራ መትጋት ይኖርበታል። ወቅቱ ያለን ጊዜ አብቃቅቶ ተጨማሪ ሥራዎች መስራት የግድ የሚልበት ወቅት ነው። ለብዙዎች በቅጥር ሰርቶ በሚገኝ ገቢ ብቻ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት አስቸጋሪ በመሆኑ አማራጮችን መጠቀም ያስፈልጋል። ለእዚህም እንደወጣት ዳዊት በዙሪያችን ምን ሀብት አለ በሚል ለይቶ ጥቅም ላይ ማዋል ያስፈልጋል። ጊዜን ከጉልበት ጋር አጣምሮ መጠቀምም እንዲሁ ትኩረት ልንሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። የሰው ልጅ በሕጻንነትና በእርጅናው ዕድሜ የፈለገውን ማድረግ፣ ወጥቶና ወርዶ ሀብት ማፍራት አይችልም። ይህ የሚሆነው በወጣትነትና በጎልማሳነት ዕድሜ ብቻ ነው። በመሆኑም ለነገ ያለምነውን በጊዜው ማሳካት የምንችለው ዛሬ ጠንክረን ስንሰራ ነው። ስለዚህ የወጣትነት ዕድሜያችንን በውጤት ለማጀብ ጠንክረን ልንሠራበት ይገባል። ሥራ ክቡር ከመሆን በላይ ጠንክሮ የሰራውንም ያስከብራል፤ ይለውጣል፤ ሰላም !
አዲስ ምዕራፍ- ከዜጎች ደጃፍ እስከ እጅ ስልክ
Apr 25, 2026 3171
አዲስ ምዕራፍ- ከዜጎች ደጃፍ እስከ እጅ ስልክ በቁምልኝ አያሌው በአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ውስጥ የመንግሥት አገልግሎት ጥራት ከሰው ልጅ የደም ዝውውር ጋር ይመሰላል። በሌላ በኩልም፣ የአገልግሎት አሰጣጥ የዜጎች የሞራልና የፍትሕ ልዕልና መለኪያ ተደርጎ ይወሰዳል። መንግሥት ለዜጎቹ የሚያቀርባቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ጥራት፣ ፍጥነትና ፍትሐዊነትም የሀገርን ፖለቲካዊ መረጋጋትና የኢኮኖሚ አቅጣጫ የሚበይኑ መጋቢዎች ናቸው። ታዋቂው የፖለቲካል ኢኮኖሚ ምሁር ፍራንሲስ ፉኩያማ እንደሚሉት፤ "የመንግሥት ተቋማት ብቃት (State Capacity) ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለዴሞክራሲ መረጋጋት መሠረት ነው።" መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ሥርዓት የሕዝብ አመኔታን በመጨመርና ማህበራዊ እኩልነትን በማስፈን ለዘላቂ ሰላም የማይተካ ሚና ይጫወታል። ይህም ሀገርን በኢኮኖሚ ለማሳደግና ለማበልጸግ በሚደረገው ርብርብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ሌላኛው የኢኮኖሚክስ ምሁር ጆሴፍ ስቲግሊዝ በበኩላቸው፤ "ውጤታማ መንግሥት ማለት ዜጎቹን በግልጽነትና በተጠያቂነት የሚያገለግል፣ በሂደቱም የህዝብ አመኔታን መገንባት የሚችል ነው" ሲሉ አጽንኦት ይሰጣሉ። በአንፃሩ፤ የአገልግሎት ክፍተትና የአስተዳደር ጉድለት ለሀብት ብክነት፣ ለሙስና እና ብልሹ አሰራር በር በመክፈት ዜጎችን ለከፍተኛ ምሬት በማጋለጥ አመኔታን ያሳጣል። ይህንን እንግልት ለማቃለል ሀገራት አገልግሎትን የሚያዘምን ፈጣንና ቀልጣፋ የዲጂታል ሥርዓት እየዘረጉ ይገኛል። ኢትዮጵያም ይህንን መርህ በመከተል ዘገምተኛ አሰራር ከወለደው የ"እጅ መንሻ" (ሙስና) ልምምድ በመላቀቅ ዘመናዊና ግልጽ የዲጂታል ሽግግርን በማፋጠን ላይ ትገኛለች። ይህም ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባትና ሉዓላዊነትን የሚያጎናጽፍ ወሳኝ የልማት ምኅዳር እየፈጠረ ነው። የመደመር መንግሥት ዕሳቤ፤ በተቋማት ግንባታና አገልግሎት ጥራት!! በመደመር ፍልስፍና ውስጥ የመንግሥት ተቋማት ግንባታ የሀገር ግንባታ የጀርባ አጥንት ተደርገው ይወሰዳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው ገፅ-129 እንዳሰፈሩት፤ ''የመደመር መንግሥት ከውስብስብ ቢሮክራሲ ተላቀው የመደመር ለውጥ የሚያመጡ ተቋማት ውቅር ነው። በመሆኑም ተቋማት ከተለመደ ''የሥራ ሂደት መር'' አካሄድ መላቀቅ ይጠበቅባቸዋል። አደረጃጀታቸውንም ለሚያገለግሉት ሕዝብ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲያገኙ ወደሚረዳቸው አደረጃጀት መሸጋገር አለባቸው። ለመደመር መንግሥት ሕዝቡን ማገልገል ከቢሮክራሲ በላይ ነው'' በሚል አስገንዝበዋል። ለዚህም ነው ተቋማት የሰውን ልጅ አቅምና ዕውቀት አቀናጅተው ለጋራ ዓላማ የሚያውሉ ሕያው መዋቅሮች ናቸው የሚባለው።   በመደመር ዕሳቤ ጠንካራ ተቋማት ማለት በግለሰቦች ፍላጎትና ስሜት ላይ ያልተመሰረቱ ይልቁንም በሕግና በሥርዓት የሚመሩ መሆን አለባቸው። በመደመር መንግሥት መፅሐፍ ገፅ-130 እንደሰፈረው፤ ''በየተቋማት ያሉ የመንግስት ሠራተኞች ሕዝቡን ከቢሮክራሲው በላይ የሚመለከቱ እንዲሆኑ ይጠበቃል። አገልጋይነትን የተላበሱ መሆን ይጠበቅባቸዋል።'' መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ይህንን ዕሳቤ በተግባር የሚተረጉም ነው። ግለሰባዊ ንክኪን በመቀነስና አሰራርን በቴክኖሎጂ በመተካት ተቋማት ከግለሰቦች መልካም ፈቃድ ይልቅ በሥርዓት ወደሚመራ ተቋማዊ ብቃት መሸጋገርን ያሳያል። የአገልግሎት ጥራትና የዜጎች ክብር በመደመር መንግሥት ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ሰው ተኮር የልማት ነጥብ ነው። ''ለሕዝቡ ቅድሚያ የማይሰጥ አመራርም ሆነ ሠራተኛ የመደመር መንግሥት ወገን አይደለም። እንዲህ ዓይነቱን ግለሰብም ሆነ አይቶ እንዳላየ በማለፍ የማይታገል ሰው በመደመር መንግሥት ውስጥ ዕድል ፈንታ የለውም'' በሚል በመደመር መንግሥት መፅሐፍ የሰፈረው ግልፅ መልዕክትም መንግሥት የአገልጋይነት እንጂ የገዥነት መንፈስ ሊኖረው እንደማይገባ በጉልህ ያመላክታል። የአገልግሎት ጥራት መሻሻልም ዜጎች በሀገራቸው ተቋማት ክብራቸውና መብታቸው ተጠብቆ ያለ እንግልት የሚገለገሉበትን ምኅዳር ይፈጥራል። በተቋማት አገልግሎት የዜጋ እርካታ (Citizen Satisfaction) ዋነኛ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ዕድገት ምንጭ ተደርጎ ይወሰዳል። በመደመር መንግስት ዕይታ የብልሹ አሰራር መታገያ ስትራቴጂ በጩኸትና በቅጣት ብቻ የሚመጣ ሳይሆን አሰራርን በማዘመን ጭምር ነው። የመሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ሌብነትን የማይጋብዝ ሥርዓት የፈጠረ (Systemic Prevention) ስትራቴጂክ አቅጣጫ ሆኗል።   የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማትና የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመደመር መንግሥት መሠረታዊ የተቋማት ሪፎርም ትግበራን (Institutional Reform) የሚያሳዩ ናቸው። ይህም ተቋማትን ከመዋቅራዊ ሽግግርና ለውጥ ባለፈ የተቋማት ሠራተኞችን ከመንግሥት ሠራተኛነት ወደ ሕዝብ አገልጋይነት የአስተሳሰብ ለውጥ (Paradigm Shift)፣ ኋላ ቀር አሰራርን በዲጂታል የቴክኖሎጂ አማራጭ የሚተካ (Technology Integration)፣ አገልግሎትን ለሁሉም ዜጋ በእኩልነት፣ በቅርበትና ፍትሐዊነት የማዳረስ ፅንሰ ሃሳባዊ ግብን በተግባር ያረጋገጠ ሆኗል። ይህ ታላቅ ተግባርም ኢትዮጵያ በመደመር ዕሳቤ የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ የሚያፋጥንና ዜጎች በመንግሥታቸው ላይ ያላቸውን አመኔታ በጽኑ መሠረት ላይ የሚገነባ መሠረት ነው። የዲጂታል ኢትዮጵያ ርዕይና ስትራቴጂክ ሽግግር!! ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ለግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና አይሲቲ ዘርፎች ወሳኝ የልማት ዕድሎችን ፈጥሯል። በዚህ ሰፊ መርሃ ግብር ውስጥ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እንደ ዋነኛ የብልፅግና ምሰሶ ተወስዷል። በ"ዲጂታል ኢትዮጵያ-2025" ስትራቴጂ የተጀመረውና በስኬት የተጠናቀቀው ጉዞ ዛሬ ላይ ሀገሪቷን ወደ "ዲጂታል ኢትዮጵያ-2030" አሸጋግሯታል። ይህ ስትራቴጂ ዜጎች ካሉበት ቦታ ሆነው አገልግሎት የሚያገኙበትን ምኅዳር በመፍጠር በሰው ንክኪ የሚፈጠሩ ብልሹ አሰራሮችንና የአገልግሎት እንግልትን በማስቀረት ረገድ ታሪክ ቀያሪ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የልማትና ዕድገት ምሁሩ አማርትያ ሴን፤ "ልማት የሰው ልጅ ምርጫና የመገልገያ አቅሙን ማስፋፊያ መሣሪያ ነው" በማለት የሚገልጹት ስለልማት ከፍ ያለ ትርጉም ይሰጠናል። የኢትዮጵያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ዜጎች የሚያጋጥሟቸውን እንግልቶች በማስወገድ ትኩረታቸውን በልማት ላይ እንዲያደርጉ በማስቻሉ፣ ይህንን የልማት ፅንሰ-ሃሳብ በተግባር እየተረጎመ ይገኛል።   የአንድ ጣሪያ በረከትና የቅልጥፍና ተምሳሌት - መሶብ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዚያ 18/2017 ዓ.ም የተመረቀው የፌዴራል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ ለተቋማዊ ሽግግር መነሻ ሆኗል። ቁልፍ የመንግሥት አገልግሎቶች በአንድ ጣሪያ ስር መሰባሰባቸው የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ አሸጋግሮታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ይህ ማዕከል ዜጎች ጊዜያቸውንና ሀብታቸውን በመቆጠብ ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ለዘመናት የቆየውን ምሬት የሚቀለብስ የሪፎርም እርምጃ ነው። በወቅቱ ሲጀመር 12 የነበሩት ፌዴራል ተቋማት፤ አሁን ላይ 23 በመሻገር አገልግሎታቸውን እየሰጡ ይገኛል። ይህም የዜጎች እንግልት በማስቀረት ታላቅ እፎይታን ፈጥሯል። እነዚህ ተቋማት፦ የብሔራዊ መታወቂያ፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት፣ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ስልጠና ባለስልጣን፣ ኢትዮ ፖስታ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን፣ የኢትጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የፍትሕ ሚኒስቴር፣ ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች አገልግሎት ናቸው። መነሻውን አዲስ አበባ ከተማ የፌዴራል ተቋማት በአንድ በማሰባሰብ የጀመረው ይህ አገልግሎት አሁን ላይ በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ተደራሽ እየሆነ ነው። ይህም የመልካም አስተዳደር እጦትን የሚያቃልል ታሪክ ቀያሪ መደላድል ፈጥሯል። አዲስ መሶብ - የተንቀሳቃሽ አገልግሎት ተስፋ!! በመዲናችን ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎት፣ "መንግሥት ወደ ዜጋው ይሄዳል" (Citizen-Centric Governance) የሚለውን የዘመናዊ አስተዳደር ፍልስፍና በተግባር ያሳየ ነው። በፀሐይ ኃይልና በፈጣን ኔትወርክ የታገዘው ይህ ተንቀሳቃሽ አገልግሎት የስምንት ተቋማትን 36 ዓይነት አገልግሎቶች ወደ ህዝቡ ደጃፍ በማምጣት ረገድ ተምሳሌት ሆኗል።   የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ከተማዋ ለዘመናት ስር በሰደደ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ተተብትባ ብትቆይም፣ የመሶብ ዲጂታል አገልግሎት ግን ለተገልጋዩ እውነተኛ እፎይታን ይዞ መጥቷል። የቀጣዩ ዘመን ግብ - አገልግሎትን በእጅ ስልክ!! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀጣይ አገልግሎቱን ወደ ዜጎች የእጅ ስልክ የማሸጋገር ግብ መኖሩን አረጋግጠዋል። ይህ ሽግግር ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዲሆን የዲጂታል መታወቂያ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ዜጎችን በዲጂታል መታወቂያ መለየት መቻሉ የአሰራር ግልጽነትን ከመጨመሩም በላይ መንግሥት አገልግሎቱን ለማን እየሰጠ እንደሆነ በትክክል እንዲያውቅ ያስችለዋል።   ተገልጋይን አክብሮ፣ ስርቆትና "እጅ መንሻን" አስቀርቶ አገልግሎት መስጠት የባህል ለውጥ ይጠይቃል። ለዚህም ሲቪል ሰርቪሱን በማዘመን፣ ቴክኖሎጂንና የባህል ለውጥን በማቀናጀት የእጅ መንሻን ባህል የሚያስቀር መሠረት እየተጣለ ይገኛል። ለዚህ ለውጥ ስኬት እያንዳንዱ ዜጋና ተቋም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማት መርሃ ግብርና የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሙስናን በማድረቅ ፍቱን መፍትሔ እየሰጡ ይገኛሉ። ይህም ሀገሪቷን ከቆየችበት የ"እጅ መንሻ" አዙሪት አውጥቶ፣ ተቋማት ለዜጎች ክብር ወደሚያሳዩበት አዲስ ምዕራፍ አሸጋግሯታል። ይህ ጉዞ እመርታ ነው፤ ግልጽነትን በማንገስና የህዝብን እርካታ በመጨመር የብልጽግና ጉዞውን የሚያፋጥን ነው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም