በወሰድነው ካርድ ይወክለናል ለምንለው ድምጻችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናል - የደሴ ከተማና የደቡብ ወሎ ዞን ነዋሪዎች - ኢዜአ አማርኛ
በወሰድነው ካርድ ይወክለናል ለምንለው ድምጻችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናል - የደሴ ከተማና የደቡብ ወሎ ዞን ነዋሪዎች
ደሴ፤ ግንቦት 21/2018(ኢዜአ)፦ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በወሰድነው ካርድ ይወክለናል ለምንለው ድምጻችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናል ሲሉ የደሴ ከተማና የደቡብ ወሎ ዞን ነዋሪዎች ገለጹ።
ነዋሪዎቹ የፊታችን ሰኞ ግንቦት 24/2018 ዓም በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም ይወክለናል ለሚሉት አካል ድምጽ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
ኢዜአ ያነጋገራቸው የደሴ ከተማ እንዲሁም በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ ነዋሪዎች፤ በምርጫ ካርዳቸው ለሚፈልጉት ድምጽ በመስጠት ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።
የደሴ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ፀጋዬ ረታ እና ወይዘሮ እታፈራሁ ከበደ እንደገለጹት፤ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት እንደሚሳተፉ ገልጸዋል።
በወሰዱት ካርድ ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም ይወክለናል ለሚሉት አካል ድምጽ እንደሚሰጡም አረጋግጠዋል።
በተመሳሳይ በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘሮ የተመኝ እንድሪስና ወይዘሮ ፋጡማ መሀመድ በበኩላቸው፤ የፊታችን ሰኞ ካርድ በወሰዱበት የምርጫ ጣቢያ በማለዳ በመገኘት ድምጻቸውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።