ቀጥታ፡

ምድረ ገነት ሽሬ እና ሀድያ ሆሳዕና ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 34ኛ ሳምንት ምድረ ገነት ሽሬ እና ሀድያ ሆሳዕና አንድ አቻ ተለያይተዋል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ እዮብ አለማየሁ በ35ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ጎል ሀድያ ሆሳዕናን መሪ ሆኗል።

ዳንኤል ዳርጌ በ88ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፈው ጎል ለምድረ ገነት ሽሬ አንድ ነጥብ አስገኝቷል።

ምድረ ገነት ሽሬ በ38 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ላይ ይገኛል።

ሀድያ ሆሳዕና በ43 ነጥብ ደረጃውን ከ13ኛ ወደ 11ኛ ከፍ አድርጓል።

ቡድኖቹ በተመሳሳይ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች አላሸነፉም።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም