ሸገር ከተማ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል - ኢዜአ አማርኛ
ሸገር ከተማ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ34ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሸገር ከተማ ፋሲል ከነማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሄኖክ አዱኛ በ90ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ግቧን አስቆጥሯል።
ከሁለት ተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ሸገር ከተማ በ43 ነጥብ ደረጃውን ከ14ኛ ወደ 11ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉም ዘጠነኛ ድሉን አስመዝግቧል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ፋሲል ከነማ በ46 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።
ቡድኑ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ድል አልቀናውም።