ለምርጫው ስኬታማነት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አደርጋለሁ - ኢጋድ - ኢዜአ አማርኛ
ለምርጫው ስኬታማነት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አደርጋለሁ - ኢጋድ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21/2018 (ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) በኢትዮጵያ ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማነት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸ።
ምርጫው ነጻ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ፣ ተዓማኒ እና አካታች እንዲሆን የድርሻውን እንደሚወጣም አስታውቋል።
በኢጋድ የኢትዮጵያ ምርጫ ታዛቢ ተልዕኮ ሰብሳቢ ስፔሺዮሳ ዋንዲራ ካዚብዌ(ዶ/ር) የተመራ ልዑክ ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት የምርጫ ትብብር ጋር በመሆን የምርጫውን ሂደትን መደገፍ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክሯል።
በውይይቱም የሲቪል ማህበረሰቦች የዴሞክራሲ ሂደቶችን፣ የምርጫ ዝግጅት እና የአካባቢ ምርጫን በመታዘብ ረገድ የሚኖራቸውን ሚና በተመለከተ ምክክር መደረጉን ኢጋድ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል።
ተዓማኒ እና አካታች ምርጫ ለማካሄድ የመራጮች የሲቪክ ትምህርት አስፈላጊ መሆኑ በውይይቱ መነሳቱን ተጠቅሷል፡፡
ውይይቱ ኢጋድ በኢትዮጵያ ነጻ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ፣ ተዓማኒ እና አካታች ምርጫ እንዲኖር የሚያደርገው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አካል መሆኑንም አስታውቋል፡፡