ቀጥታ፡

በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት ተደርጓል

አዳማ፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፡- በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት መደረጉን የምሥራቅ ሸዋ ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

የጽሕፈት ቤቱ ምክትል ኃላፊ አብነት ዘገየ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር በይፋ ከተጀመረ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተተክለዋል።




ይህም የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በተጨባጭ በማረጋገጥ ውጤት ማስገኘቱን ጠቁመው፤ የሰብል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የጎላ አስተዋጽዖ ማበርከቱን ለአብነት ጠቅሰዋል።

ለዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብርም ለደን ልማት የሚሆኑ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው 269 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኞች በሁሉም ወረዳዎች ችግኝ ጣቢያዎች አማካኝነት መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል።

ዘንድሮ በ45 ሺህ 563 ሔክታር ላይ የችግኝ ተከላ እንደሚካሄድም ነው ያመላከቱት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም