የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ለሀገር ዕድገትና ለህዝብ ተጠቃሚነት ይበጃል የሚሉትን ለመምረጥ ተዘጋጅተዋል - ኢዜአ አማርኛ
የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ለሀገር ዕድገትና ለህዝብ ተጠቃሚነት ይበጃል የሚሉትን ለመምረጥ ተዘጋጅተዋል
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21/2018(ኢዜአ)፦ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ለሀገር ዕድገትና ለህዝብ ተጠቃሚነት ይበጃል የሚሉትን ለመምረጥ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ድምፅ ለመስጠት ተዘጋጅተው እየተጠባበቁ መሆኑን ተናገሩ።
ኢትዮጵያ የፊታችን ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ታካሂዳለች።
በባህርዳር ከተማ የደጃዝማች በላይ ዘለቀ እና አፄ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተሞች ነዋሪዎች ለምርጫው ዝግጁ መሆናቸውን ለኢዜአ ገልጸዋል።
ምርጫው ለሀገር የሚበጅን በድምፃችን የምንመርጥበት ታሪካዊ መድረክ በመሆኑ በአግባቡ ለመጠቀም ተዘጋጅተናል ብለዋል።
የመራጭነት ካርዳቸው የነገ እጣ ፈንታቸውን የሚወስን ቁልፍ መሣሪያ መሆኑንም ተናግረዋል።
ዜጎችም የዴሞክራሲ መብታቸውን በመጠቀም በምርጫ ድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ በወሰዱት ካርድ ድምፅ በመስጠት ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚኖርባቸው አንስተዋል።
የምርጫ ካርድ የወሰደ እያንዳንዱ ዜጋ ይህንን ወሳኝ ዴሞክራሲያዊ መብቱን ተጠቅሞ፣ ለህዝብ ጥቅም መከበር የሚሠራን አካል የመምረጥ ኃላፊነት አለብን ብለዋል።