የመምረጥ መብታችንን በመጠቀም ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መጎልበት የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማበርከት ተዘጋጅተናል - ኢዜአ አማርኛ
የመምረጥ መብታችንን በመጠቀም ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መጎልበት የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማበርከት ተዘጋጅተናል
ወልቂጤ፤ ግንቦት 21/2018(ኢዜአ)፦ የመምረጥ መብታቸውን በመጠቀም ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መጎልበት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት መዘጋጀታቸውን የጉራጌ ዞን ነዋሪዎች ገለጹ።
በምርጫ ካርዳቸው ለሀገርና ለሕዝብ ይበጃል ለሚሉት አካል ድምፅ ለመስጠት መዘጋጀታቸውንም ኢዜአ ያነጋገራቸው የዞኑ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የመምረጥ መብታቸውን በመጠቀም ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መጎልበት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት መዘጋጀታቸውንም አስታውቀዋል።
ከወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች መካከል መምህር ፍቃዱ ቶማስ በጠቅላላ ምርጫው ሀገርና ሕዝብን ያሻግራል ብለው ለሚያምኑበት ፓርቲ ድምፃቸውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የዜጎች የነቃ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ እሳቸውም በምርጫው የሚወክላቸውን ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
ሌላኛው የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ አቶ አብድራህማን ጅላሉ በበኩላቸው፤ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ የአንድ ሰው ድምፅ ትልቅ ዋጋ እንዳለው ጠቅሰዋል።
የፊታችን ሰኞ በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ በመስጠት የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
የአበሽጌ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘሮ ዙርያሽ ቶፊቅ በበኩላቸው፤ ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም የሚያምኑበት^ን ተወዳዳሪ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
የምርጫ ጉዳይ የዜጎች የጋራ ጉዳይ በመሆኑ ድምፅ ለመስጠት ቀኑን በጉጉት እየጠበቁ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ነዋሪው አብዱልሃኪም ጀማል ናቸው።
የምርጫ ካርድ የወሰዱ ዜጎች ሁሉ ድምፃቸውን በመስጠት ዲሞክራሲያዊ ተሳትፏቸውን እንዲያረጋግጡም መክረዋል።