በሐረሪ ክልል ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ለተከላ ተዘጋጅተዋል - ኢዜአ አማርኛ
በሐረሪ ክልል ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ለተከላ ተዘጋጅተዋል
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 20/2018 (ኢዜአ)፦ በሀረሪ ክልል በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን የክልሉ የግብርና ልማት ቢሮ አስታውቋል።
የክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ነስረዲን አህመድ እንደገለጹት በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ይተከላሉ።
ከሚተከሉ ችግኞች ውስጥም ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት የፍራፍሬና የደን ችግኞች መሆናቸውን ገልጸዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ከ200 ሺህ በላይ የሚሆኑት ለእንስሳት መኖ የሚያገለግሉ ችግኞች መሆናቸውንም ገልጸዋል።
በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ የችግኝ ጣቢያዎች እየተከናወነ በሚገኘው ስራም ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠር መቻሉን አንስተዋል።
በአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር እስከ አሁን የተከናወኑ ውጤታማ ተግባራት የክልሉን የደን ሽፋን በማሳደግና የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እያሻሻሉ መምጣታቸውንም ነው የተናገሩት።