ቀጥታ፡

ጆዜ ሞሪንሆ የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ


አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21/2018 (ኢዜአ)፦ ፖርቹጋላዊ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ የሪያል ማድሪድ ቀጣይ ዋና አሰልጣኝ ለመሆን የሚያስችላቸውን ውል ተፈራርመዋል።

የ63 ዓመቱ ሞሪንሆ እስከ ሰኔ 2029 (እ.አ.አ) በሚዘልቅ የሶስት ዓመት ውል ወደ ስፔኑ ክለብ ዳግም ተመልሰዋል።

አሰልጣኙ ከሪያል ማድሪድ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መጠናቀቅ በኋላ በይፋ ትውውቅ እንደሚያደርጉ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የስፖርት መገናኛ ብዙሃን መረጃ ያመለክታል።

ሞሪኒሆ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የቤኔፊካ አሰልጣኝ ነበሩ።

ከዚህ ቀደም ከ2010 እስከ 2013 (እ.ኤ.አ) ለሶስት የውድድር ዓመታት ሪያል ማድሪድን ማሰልጠናቸው ይታወሳል።

በአሰልጣኝነት ቆይታቸውም የላሊጋ፣ የኮፓ ዴል ሬይ እና የስፔን ሱፐር ካፕ ዋንጫዎችን ከክለቡ ጋር አንስተዋል።

በተለይም በ2011/12 የውድድር ዘመን ክለቡ ሪከርድ የሆነ 100 ነጥብ በመሰብሰብ የላሊጋ ሻምፒዮን እንዲሆን ማድረጋቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም