ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በክልሉ በቱሪዝም ዘርፍ 978 ሚሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል
Sep 7, 2026 381
ጂንካ፥ ጳጉሜ 2/2018 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በቱሪዝም ዘርፍ 978 ሚሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወይኒቱ መልኩ በክልሉ በተጠናቀቀው በጀት አመት ከቱሪዝም ዘርፍ 500 ሚሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን አስታውሰዋል። ይሁን እንጂ ለዘርፉ በተሰጠው ትኩረት ከእቅድ በላይ 978 ሚሊዮን ብር መገኘቱን ተናግረዋል። በክልሉ የቱሪዝም መዳረሻዎችን የማልማትና የማስተዋወቅ ስራ በስፋት በመሰራቱና የጎብኚዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ለገቢው ማደግ በምክንያትነት ጠቅሰዋል። የሙሩሌ የቁጥጥር አደን ቦታ፣ የማጎና የማዜ ብሔራዊ ፓርኮች የኮንሶ ባህላዊ መልክዓ ምድር ዓለም አቀፍ መካነ ቅርስ በክልሉ ከሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎች ዋነኞቹ እንደሆኑ ጠቁመዋል። የአርባምንጭ አዞ እርባታ፣ የባንባላ ተንጠልጣይ ድልድይ፣ የዳሞ ተራራና የጌዴኦ ትክል ድንጋዮች መካነ ቅርስም በስፋት እየተጎበኙ ያሉ የመስህብ ስፍራዎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል። በበጀት አመቱ 13 ሚሊዮን የሀገር ውስጥና የውጪ ቱሪስቶች የመስህብ ስፍራዎቹን መጎብኘታቸውን ተናግረዋል። በክልሉ የጎብኚዎች ቁጥር መጨመርም ለቢዝነስ ቱሪዝም መነቃቃት እና ለስራ እድል ፈጠራ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አስታውቀዋል። የማጎ ብሔራዊ ፓርክ አስተዳዳሪ አቶ ኤርቦር ሌለ በበኩላቸው ፓርኩን ለመመልከት ወደ ስፍራው የሚመጡ ጎብኚዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል። ፓርኩ ከ80 በላይ አጥቢ፣ ከ250 በላይ የአዕዋፍና 14 ዓይነት የዓሣ ዝርያዎችን የያዘ መሆኑን አመልክተዋል።
በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የሀገሪቱን የማንሰራራት ጉዞ የሚያፋጥኑ ናቸው
Sep 7, 2026 371
አዲስ አበባ ፤ ጳጉሜን 2/2018 (ኢዜአ) ፦ በአዲስ አበባ የተገነቡ የቱሪዝም መዳረሻዎችና ሌሎች የመሠረተ ልማት ሥራዎች የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ የሚያፋጥኑ መሆናቸውን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጳጉሜን 02 "የማንሰራራት ቀን"ን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የተገነቡ የቱሪዝም መዳረሻዎችንና የመሠረተ ልማት ሥራዎችን ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች አስጎብኝቷል። በጉብኝት መርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉ ጎብኚዎች በአዲስ አበባ የተገነቡ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ከተማዋ ለአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ እንድትሆን ያስቻሉ ናቸው ብለዋል፡፡ አስተያየት ሰጪ ሻምበል ዋኘው አባይ እንዳሉትም ከተማዋ ከዚህ ቀደም ከነበራት ገጽታ በተለየ መልኩ ውብና ጽዱ መሆኗን ገልጸው፤ የወንዝ ዳርቻ፣ የኮሪደር ልማትና የቱሪዝም መዳረሻዎች የሀገሪቱን ዕድገት የሚያንሰራሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። አቶ ገዛኸኝ አሰፋ በበኩላቸው የመሠረተ ልማት ሥራዎቹ ለዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠሩ፣ ለነዋሪዎችና ለጎብኚዎች ምቹ አካባቢን የፈጠሩ መሆናቸውን በአካል ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል፡፡ እነኚህም የኢትዮጵያን የማንሰራራት ግስጋሴ የሚያፋጥኑ ናቸው ብለዋል፡፡ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን በመገናኛ ብዙኃን ከማየት ባለፈ በአካል መጥተው በመጎብኘታቸው መደሰታቸውን የገለጹት ሐጂ ሸምሱ አባስ ፤ የከተማዋ ዕድገት ለሀገር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሙኒኬሽን ኃላፊ ልደት ሙለታ ጳጉሜን 02 "የማንሰራራት ቀን"ን ምክንያት በማድረግ በለውጡ ዓመታት ለነዋሪዎች ውብና ጽዱ ከተማን ለመፍጠርና በቱሪዝም ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎችን ማስጎብኘታቸውን ገልጸዋል። ባለፉት ዓመታት የተገነቡ የቱሪዝም መዳረሻዎች፣ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ተግባራት የሀገሪቱን ዕድገት ያረጋገጡ መሆናቸውንም ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጳጉሜን 02 "የማንሰራራት ቀን"ን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የተገነቡ የቱሪዝም መዳረሻዎችንና የመሠረተ ልማት ሥራዎችን ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች አስጎብኝቷል። በጉብኝት መርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉ ጎብኚዎች በአዲስ አበባ የተገነቡ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ከተማዋ ለአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ እንድትሆን ያስቻሉ ናቸው ብለዋል፡፡ አስተያየት ሰጪ ሻምበል ዋኘው አባይ እንዳሉትም ከተማዋ ከዚህ ቀደም ከነበራት ገጽታ በተለየ መልኩ ውብና ጽዱ መሆኗን ገልጸው፤ የወንዝ ዳርቻ፣ የኮሪደር ልማትና የቱሪዝም መዳረሻዎች የሀገሪቱን ዕድገት የሚያንሰራሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። አቶ ገዛኸኝ አሰፋ በበኩላቸው የመሠረተ ልማት ሥራዎቹ ለዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠሩ፣ ለነዋሪዎችና ለጎብኚዎች ምቹ አካባቢን የፈጠሩ መሆናቸውን በአካል ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል፡፡ እነኚህም የኢትዮጵያን የማንሰራራት ግስጋሴ የሚያፋጥኑ ናቸው ብለዋል፡፡ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን በመገናኛ ብዙኃን ከማየት ባለፈ በአካል መጥተው በመጎብኘታቸው መደሰታቸውን የገለጹት ሐጂ ሸምሱ አባስ ፤ የከተማዋ ዕድገት ለሀገር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሙኒኬሽን ኃላፊ ልደት ሙለታ ጳጉሜን 02 "የማንሰራራት ቀን"ን ምክንያት በማድረግ በለውጡ ዓመታት ለነዋሪዎች ውብና ጽዱ ከተማን ለመፍጠርና በቱሪዝም ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎችን ማስጎብኘታቸውን ገልጸዋል። ባለፉት ዓመታት የተገነቡ የቱሪዝም መዳረሻዎች፣ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ተግባራት የሀገሪቱን ዕድገት ያረጋገጡ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
በደቡብ ወሎ ዞን በተለያዩ ዘርፎች የተመዘገቡ ውጤቶች የኢትዮጵያ የማንሰራራት ተምሳሌት ናቸው
Sep 7, 2026 376
ቃሉ፤ ጳጉሜን 2/2018(ኢዜአ)፡-በደቡብ ወሎ ዞን በኢንቨሰትመንት፣ በቱሪዝም፣ በግብርና፣ በፍራፍሬ እና የኮሪደር ልማት መስኮች የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶች የኢትዮጵያ ማንሰራራት በተጨባጭ የሚያረጋግጡ መሆናቸውን የዞኑ መስተዳድር ገለፀ። በዞኑ የማንሰራራት ቀን ምክንያት በማድረግ በቃሉ ወረዳ እና ሀርቡ ከተማ የተለያዩ የልማት ሥራዎች ጉብኝት ተካሂዷል። በጉብኝቱ የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ እንድሪስ ይማም እንደገለጹ፣ በዞኑ በተለያዩ የልማት ሥራዎች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል። በተለይ በኢንቨሰትመንት፣ በቱሪዝም፣ በግብርና፣ የፍራፍሬ እና ኮሪደር ልማትን ጨምሮ በከተማ ልማት፣ በንጹህ መጠጥ ውሃና በሌሎችም የተመዘገቡ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች የኢትዮጵያ እያንሰራራች መሆኑን ያመላክታሉ ነው ያሉት። በከተሞቹ የጠጠር ማምረቻ፣ የኮሪደር ልማት፣ ተንጠልጣይ ድልድይና ሌሎችም ልማቶች ተስፋ ሰጪ እና የኢትዮጵያን ማንሰራራት ለማስቀጠል የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልፀዋል። የዞኑ ማዕድን ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አህመድ አበባው በበኩላቸው፣ በዞኑ ከሚገኘው በርካታ የማዕድን ሀብት በአግባቡ እና በዘላቂነት ተጠቃሚ ለመሆን እየተሰራ ነው ብለዋል። የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በከተማው በተሰሩ ሰፋፊ ልማቶች ተጠቃሚ መሆናቸውን የተናገሩት ደግሞ የሀርቡ ከተማ ነዋሪ ሸህ ሰይድ ሀሰን እና ሹምነሽ ኢብራሂም ናቸው። በተለይ የኮሪደር ልማቱ የከተማውን ውበት በማሳመር ለነዋሪዎች ምቹ የሥራ አከባቢን የፈጠረ ሲሆን በወረዳው እየተገነቡ ባሉ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀዋል። ከዚህ ውስጥም በተገነቡ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ችግራቸው በመቀረፉ መደሰታቸውን ገልጸዋል። በጉብኝቱ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አመራሮችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
የመደመር መንግስት በተለያዩ ዘርፎች ያከናወናቸው ተግባራት የኢትዮጵያን ማንሰራራት ለማረጋገጥ ያስቻሉ ናቸው
Sep 7, 2026 375
ደብረማርቆስ፤ ጳጉሜ 2/2018(ኢዜአ)፡- የመደመር መንግስት በተለያዩ ዘርፎች ያከናወናቸው ተግባራት የኢትዮጵያን ማንሰራራት በተግባር ለማረጋገጥ ያስቻሉ ናቸው ሲል የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ። ከተማ አስተዳደሩ የማንሰራራት ቀንን አስመልክቶ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር የፓናል ውይይት አካሒዷል። የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ የኋላ ደስታ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፤ የመደመር መንግስት ተግባራዊ ባደረጋቸው የኢንዱስትሪ፣ የከተማ ግብርናና የሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ከፍተኛ ስኬቶች ተመዝግበዋል። ከዚህ ውስጥም በከተማ አስተዳደሩ ከ10 ዓመት በፊት ከአስር በታች የነበረው የአምራች ኢንዳስትሪዎች ቁጥር አሁን ላይ ከ70 በላይ ማድረስ የተቻለ ሲሆን 39 የሚሆኑት ወደ ማምረት የተሸጋገሩ መሆኑን አረጋግጠዋል። በማህበራዊ ዘርፍም በቅድመ አንደኛ ደረጃ፣ በ1ኛና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተደራሽነት፣ ጥራትና አግባብነት ውጤታማ የሆኑ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቅሰዋል። ከ500 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪም ሞዴል ትምህርት ቤት ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ መገኘቱ የማንሰራራት ማሳያ እንደሆነም አብራርተዋል። በስራ እድል ፈጠራ፣ በከተማ ግብርና፣ በመሰረተ ልማት ግንባታና በሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች አበረታች ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን አስገንዝበዋል። ከተሳታፊዎች መካከል ሊቀ ካህናት ይትባረክ መኮነን እና ወንዳለ ተመስገን እንዳሉት ፤ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኮሪደርና ሌሎች ልማቶች የታየው ለውጥ ይበል የሚያሰኝ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል። በተለይ በከተማ ግብርና ፣ በኢንድስትሪ እና መሰል ስሰራዎች ላይ ያከናወናቸውን ተግባራት ውጤት መምጣቱን ተዘዋውረው መመልከታቸውን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ሀገራዊ ማንሰራራትን የሚያፀኑ ሜጋ የልማት ፕሮጀክቶች አከናውናለች
Sep 7, 2026 376
አዲስ አበባ ፤ ጳጉሜን 2/2018 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ሀገራዊ ማንሰራራትን የሚያፀኑ ሜጋ የልማት ፕሮጀክቶች ማከናወኗን የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ገለጸ። ዛሬ የጳጉሜን 2 የ"ማንሰራራት ቀን"ን ምክንያት በማድረግ የስድስት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ዐበይት የልማት እንቅስቃሴዎች የሚያሳይ የፎቶ አውደ ርዕይ ሲከፈት የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍራኦል ጣፋ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያን ማንሰራራት የሚያፀኑ የልማት ሥራዎች በፍጥነት እየተከናወኑ ነው። መንግስት በሁሉም ተቋማት የሕዝቡን ጥያቄዎች በመመለስ የኢትዮጵያን ተስፋ የሚያለመልሙ ትልልቅ ሜጋ ፕሮጀክቶችና ኢኒሼቲቮች ቀርፆ ወደ ስራ መግባቱን ገልጸዋል። የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎቱን የሚያዘምኑ በርካታ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች መከናወናቸውን ገልጸው፤ የፎቶ አውደ ርዕዩ ተቋማት በትብብርና በቅንጅት የፈጠሯቸውን ሀገራዊ የልማት ውጤቶችና አቅሞችን በግልጽ ያሳያል ብለዋል። በትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አመለወርቅ ህዝቅኤል፤ በትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የነዳጅ ወጪና የአየር ንብረት ለውጥን ታሳቢ ያደረገ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ግዢ እንደሚፈጸም ገልጸዋል። የሞጆ ደረቅ ወደብ የአረንጓዴ ሎጂስቲክስ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ ሀገራዊ የሎጅስቲክስ ምህዳሩን ያዘምነዋል ብለዋል። የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኢትዮጵያ በዴቻ፤ መንግሥት አዲስ አበባን ጨምሮ በርካታ ከተሞች ገቢራዊ ያደረገው የኮሪደር ልማት የነዋሪዎችን የአኗኗር ዘይቤ መቀየሩን ገልጸዋል። ከዚህም ባለፈ የመንግሥትና የግሉን አጋርነት በማጠናከር እስከ 10 ዓመታት ይወስዱ የነበሩ የቤት ግንባታዎችን በወራት ውስጥ በማጠናቀቅ ለከተሞች ዝማኔ ገንቢ ሚና ተወጥቷል ብለዋል። በቱሪዝም ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ኮንቬንሽን ቢሮ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ብዙዓለም ጌቱ በበኩላቸው፤ መንግሥት ለቱሪዝም ልማት ፖሊሲ በመቅረጽ ዘርፉ የሚያመነጨውን ኢኮኖሚ እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል። እንደ ጅማ አባ ጅፋርና የጎንደር ፋሲለደስ ያሉ ታሪካዊ ቅርሶች ከመጠገን ባለፈ በገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ የተገነቡ የቱሪዝም ሀብቶች ሀገሪቱን የቱሪስት መዳረሻ አድርጓታል ብለዋል።
ፖለቲካ
ወጣቶች በሀገር፣ አህጉርና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የሚያደርጉትን ተሳትፎ ለማጎልበት እየተሰራ ነው
Sep 7, 2026 398
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 2/2018 (ኢዜአ):-ወጣቶች በሀገር፣ አህጉርና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የሚያደርጉትን ተሳትፎ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ገለጸ። የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ለአንድ ወር ሲያካሂድ የቆየው የሁለተኛ ዙር የክረምት ሥልጠና (Summer Camp) ማጠቃለያ ምረቃ መርሃ ግብር አካሂዷል። የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር መሐመድ ራፊ አባራያ እንደገለጹት፤ በአፍሪካ ቀንድና በመላው አህጉራችን የሚታዩት ሁነቶች እጅግ ሰፊና እርስ በርስ የተሳሰሩ ታላላቅ ዕድሎችንና መልካም አጋጣሚዎችን የያዙ ናቸው። እነዚህን ዕድሎች አውጥቶ ለመጠቀምና ተስፋ ሰጪ ነገሮችን እውን ለማድረግ፤ በጥልቅ ዕውቀት የበለፀጉ አእምሮዎች፣ ገንቢና በጎ ውይይቶች፣ ከፍተኛ ሙያዊ ብቃት እንዲሁም በቁርጠኝነትና በተስፋ የሚሳተፉ አዳዲስ ብሩህ ትውልድ መሪዎች ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ ብለዋል። ሥልጠናው ወጣቶች ልምድ ካካበቱ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች እንዲማሩ፣ ሐሳብ እንዲለዋወጡና ወቅታዊ ጉዳዮችን እንዲመረምሩ ዕድል መፍጠሩን ተናግረዋል። ሥልጠናው ሠልጣኞቹ በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ቀንድና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉትን ሰፊ ዕድሎችና ነባራዊ ሁኔታዎች በጥልቀት እንዲረዱ ያደርጋል ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ ይህም ዕውቀታቸውንና አቅማቸውን በመጠቀም ለሀገሪቱ ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና የጎላና ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ታላቅ መንገድ ይከፍትላቸዋል ብለዋል። በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የባለድርሻ አካላት ሥልጠና ዳይሬክተር ጄነራል መላኩ ሙሉዓለም በበኩላቸው፤ ሥልጠናው ዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ላይ ያተኮረና 57 ሠልጣኞችን ያካተተ ነው። ሠልጣኞቹ ከሀገር አቀፍ ደረጃ የተወጣጡና በውጤትና በብቃት ተወዳድረው መመረጣቸውን አክለዋል። ሠልጠናው በሀገር፣ አፍሪካና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የንድፈ ሐሳብና የተግባር ልምምድ ያካተተ መሆኑን አመልክተው፤ ለአገሪቷ ዲፕሎማሲ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ወጣቶችን ለማፍራት ያስችላል ብለዋል። ከተመራቂ ወጣቶች መካከል አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡት እንደተናገሩት፤ ሥልጠናው በዲፕሎማሲ ዘርፍ ያላቸውን ዕውቀትና ክህሎት በማዳበር በዘርፉ የመሥራት ፍላጎታቸውን አሳድጎላቸዋል። ወጣት ፌኔት ሞቱማ እንዳለችው ሥልጠናው በቀጣይ በዲፕሎማሲ ዘርፍ ለመሰማራት ብቃቷን ያሳደገላት መሆኑን ገልጻለች። ወጣት ኪሩቤል በእውቀቱ በበኩሉ ስለ ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ፣ ብሔራዊ ጥቅምን ማስጠበቅና ዓለም አቀፍ ሁኔታዎች ግንዛቤ ማግኘቱን ተናግሯል። ወጣት ፍቅርዓለም ብርሃኑ ሥልጠናው በድርድር፣ በፕሮቶኮልና በዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ላይ አዳዲስ እይታዎችን ያላበሰውና በሀገሪቱ ዲፕሎማሲ ላይ አሻራውን ለማሳረፍ ተነሳሽነቱን የጨመረለት መሆኑን ገልጿል። ወጣት ሮዛ ዓለማው በበኩሏ በዲጂታል ዲፕሎማሲ ሀገሯን ለማገልገል መዘጋጀቷን ተናግራለች።
የጽናት ቀን በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የጸጥታ እና ደህንነት ተቋማት ያበረከቱትን አስተዋጽኦ በሚያሳይ መልኩ ይከበራል
Sep 7, 2026 469
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 2/2018 (ኢዜአ):- ነገ ጳጉሜን 3 የጽናት ቀን በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የጸጥታ እና ደህንነት ተቋማት ያበረከቱትን አስተዋጽኦ በሚያሳይ መልኩ እንደሚከበር ተገለጸ። ቀኑን የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ያከናወኑት ተግባራት እንደሚዘከሩም ተመላክቷል። የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ የበዓሉን አከባበር አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ቀኑን ማክበር የሚያስችል ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎች መታጠቁን ጠቁመው፣ የውስጥ እና የውጭ ፈተናዎችን በጽናት በመመከት ትልቅ ውጤት ማስመዝገቡን አንስተዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለሀገርና ለህዝብ ጥቅም መረጋገጥ መሰረት መሆኑንም ነው የገለጹት። የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስም የሰላም ዘብ በመሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝ ጠቁመው፤ በዚህም ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችንና ህገ-ወጥ ንግድን በመከላከልና በሌሎችም ተጠቃሽ ውጤት አስመዝግቧል ብለዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርም በኢትዮጵያ ላይ የሚቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን በብቃት በመመከት የሀገር አለኝታነቱን በተግባር እያረጋገጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎትም መረጃዎችን በመሰብሰብና በመተንተን ለባለድርሻ አካላት ተደራሽ በማድረግ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መከበር ቁልፍ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አብራርተዋል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትም የኢትዮጵያ ዲጂታል ጉዞ እንዲሳለጥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ምህዳር ግንባታ ላይ ውጤታማ ስራ እያከናወነ ነው ብለዋል። ነገ ጳጉሜን 3 የሚከበረው የጽናት ቀንም የጸጥታ እና ደህንነት ተቋማት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና የሚሰጥበት መሆኑን ምክትል ኮሚሽነሩ ገልጸው ለላቀ ውጤት እንደሚሰራም ጨምረው አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያና ቱርክዬን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በቁርጠኝነት ይሰራል
Sep 7, 2026 447
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 2/2018 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ እና ቱርክዬን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለጹ። የፖለቲካ ፓርቲዎች የምክክር መድረክ በደቡብ ኮሪያ ሴኡል እየተካሄደ ይገኛል። በምክክሩ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት አቶ አደም በጎንዮሽ የውይይት መድረክ፣ ከተርኪዬ አቻቸው፣ ከፍትህ እና ልማት ፓርቲ (አክ ፓርቲ /AK Party) ምክትል ፕሬዚዳንት ዛፌር ሲራካያ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል። ዘመናትን ያስቆጠረው የኢትዮ ተርኪዬ የሕዝብ ለሕዝብ እና የመንግስት ለመንግስት ግንኙነት በንግድ፣ በኢንቨስትመንት በዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ተባብሮ ለመስራት እድሎችን መፍጠሩ በውይይቱ ላይ ተመላክቷል። እነዚህን አጋጣሚዎች ይበልጥ አስፍቶ በፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነት ማስቀጠል እንዲቻል በብልፅግና ፓርቲ እና በአክ ፓርቲ መካከል በጋራ ለመስራት በ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተፈረመው የሁለትዮሽ ስምምነት አጋዥ እንደሆነ በውይይቱ ላይ ተነስቷል። በዋናነትም የጋራ ተጠቃሚነትን ለማስፋት የሁለትዮሽ ግንኙነትን በተለያዩ መስኮች አጠናክሮ በመቀጠል፣ የወጣቶች እና የሴቶች ክንፍን በጋራ የልምድ ልውውጥ መስኮች ተሳታፊ እንዲሆኑ በማድረግ እንዲሁም በአቅም ግንባታ መድረኮች የአመራሮችን አቅም በቀጣይነት እየገነቡ ለመሄድ የታቀዱ ስራዎች ወደ ተግባር ሊቀየሩ እንደሚገባ ተነስቷል። የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነትን ማጠናከር ለሀገራት ግንኙነት መጠናከር ያለው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ ብልፅግና ፓርቲ በቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራበት ገልጸዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የተርኪዬ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጣይብ ኤርዶጋን በተደጋጋሚ መገናኘት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ማድረሱን ጠቅሰዋል። እስከአሁን የተደረሱ የሁለቱ ሀገራት ስምምነቶችን ከግብ ለማድረስ ቀጣይነት ያለው ጥረት እንደሚደረግ አንስተዋል። በብልፅግና ፓርቲ እና በአክ ፓርቲ መካከል እ.አ.አ በ2025 የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት በአግባቡ ተፈፃሚነት እንዲኖረውም የጋራ መድረኮችን ከማካሄድ ባለፈ ዝርዝር አፈፃፀሙ ላይ ጠንካራ ክትትል የሚያደርግ አካል እንደሚመደብ ቃል ገብተዋል። በሚቀጥለው ዓመት ኢትዮጵያ የምታዘጋጀው የኮፕ32 ጉባዔም በተሳካ ሁኔታ እንዲፈፀም የኮፕ31 አስተናጋጅ የሆነችው ተርኪዬ ልምዷን በማካፈል ረገድ እያደረገች ያለውን ጥረት አድንቀው፣ ለሁለቱም ዝግጅቶች ስኬት የጋራ ትጋታቸው አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በጋራ አረጋግጠዋል። ቱርኪዬ በአዲስ አበባ ኤምባሲዋን የከፈተችበት እ.አ.አ በ2026 100ኛ ዓመቱን አስቆጥሯል። በሁለቱ ገዥ ፓርቲዎች መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር ለቀጣዩ ክፍለ ዘመን የጠበቀ ወዳጅነት ጠንካራ መሰረት የሚጥል መሆኑን አንስተዋል። አያይዘውም ይህንን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስና ወደ ከፍተኛ ሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ፋይዳ ለመቀየር ብልፅግና ፓርቲ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
ከሀገራዊ ምክክሩ የተገኙ ምክረ-ሃሳቦች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይቀርባሉ
Sep 7, 2026 489
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 2/2018 (ኢዜአ)፦ ከሀገራዊ ምክክሩ የተገኙ ምክረ-ሃሳቦች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚቀርቡ ምክር ቤቱ ገልጿል። ከሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የተገኙ ምክረ- ሃሳቦች በየፈርጁ እየተደራጁ መሆኑንና በቀጣይ ምክረ-ሃሳቦቹን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርብ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የኮሚሽኑ መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦ ኮሚሽኑ ከሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የተገኙ ምክረ-ሃሳቦችን በየፈርጁ በማደራጀት ላይ ይገኛል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሐምሌ 01 ቀን - ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤውን ሲያስተባብር መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡ በዚህ ሂደት ኮሚሽኑ በርካታ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ምክረ-ሃሳቦች ማሰባሰብ የቻለ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ለመመካከር ያሳዩት ቁርጠኝነት ውጤት ነው፡፡ ኮሚሽኑ በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 አንቀፅ 9 (10፣ 11፣ 12) በተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት መሠረት የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ አጀንዳዎችን፣ የምክክሮቹን ሂደት፣ በምክክሮቹ የተገኙ ምክረ-ሃሳቦችን እንዲሁም ምክረ- ሃሳቦቹ በተግባር ላይ ሊውሉ የሚችሉበትን ሥልት የሚገልጽ ሰነድ በማዘጋጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለአስፈጻሚ አካሉ እና ለሌሎች የሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት አቅርቦ፤ ለሕዝብም ይፋ እንደሚያደርግ፤ መንግሥት ከሀገራዊ ውይይቶች የሚገኙ ምክረ-ሃሳቦችን በተግባር ላይ ለማዋል እንዲችል ግልፅ እና ተጨባጭ የሆነ ዕቅድ እንዲዘጋጅ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ፤ እንዲሁም የምክረ-ሃሳቦቹን አፈፃፀም መከታተል የሚያስችል ሥርዓት እንደሚዘረጋ በአዋጁ ተደንግጓል፡፡ ይህንን መነሻ በማድረግ ኮሚሽኑ፦ በአሁኑ ሰዓት ከሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የተገኙ ምክረ-ሃሳቦችን በየፈርጁ በማደራጀት ላይ ይገኛል፤ በቀጣይ ምክረ-ሃሳቦቹን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባል፤ በመቀጠልም ምክረ-ሃሳቦቹን አግባብነት ባለው መንገድ ለሕዝብ ይፋ ያደርጋል፤ በመጨረሻም ምክረ-ሃሳቦቹን ለአስፈፃሚ በማቅረብ ተፈፃሚነታቸውን ይከታተላል፡፡
የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክክር ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ደቡብ ኮሪያ ገብተዋል
Sep 6, 2026 814
አዲስ አበባ ፤ ጳጉሜን 1 / 2018 (ኢዜአ)፦የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና ዋና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምክክር መድረክ (Inter-Continental Dialogue among Political Parties - ICDPP) ላይ ለመሳተፍ ሴኡል፣ ደቡብ ኮሪያ ገብተዋል። ከሴፕቴምበር 6 እስከ 9 ቀን 2026 ዓ.ም በሚካሄደው በዚህ ከፍተኛ አለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ከአፍሪካ፣ ኤሽያ፣ አውሮፓ፣ ላቲን አሜሪካ እና ሰሜን አሜሪካ የተወጣጡ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በአሁን ወቅት የተሳታፊዎች እንኳን በደህና መጣችሁ መርሃ ግብር እየተደረገ ይገኛል። ጉባኤው በዓለም አቀፍ ደረጃ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የጋራ ግንዛቤ እና ትብብር ማጠናከርን ዋና አላማው አድርጎ የተነሳ ሲሆን በቀጣይ ቀናት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።
የመንግሥት አዳዲስ እሳቤዎች በተለያዩ መስኮች የሚጨበጡ እመርታዎች እንዲመዘገቡ አድርገዋል - የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች
Sep 6, 2026 756
አዳማ ፤ ጳጉሜን 01/2018 (ኢዜአ) ፦ ያለፉት ዓመታት በመንግሥት አዳዲስ እሳቤዎችና በህዝቡ ትብብር በተለያዩ መስኮች የሚታዩና የሚጨበጡ እመርታዎች መመዝገባቸውን የተለያዩ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ገለጹ። የተለያዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ወደ አዲስ ዓመት በሚደረገው ሽግግር የጳጉሜን 1 'የእመርታ ቀን' አስመልክተው ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ ምክትል ሰብሳቢ አቶ በየነ ደሳለኝ፤ የጳጉሜን ቀናት በተለያዩ ስያሜዎች መከበራቸው ሀገሪቱ ያስመዘገበቻቸውን ስኬቶች በማንሳት ቀጣይ ስንቅ ለማድረግ የሚያነሳሳ ይሆናል ብለዋል። መንግሥት ባለፉት ዓመታት በሀገር በቀል እሳቤዎችና ፖሊሲዎች ሀገራዊ አቅሞችን መጠቀም ያስቻሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችንና በርካታ የልማት ኢንሼቲቮችን በመተግበር አስደናቂ እመርታዎች ማስመዝገቡን አንስተዋል። በተለይም በግብርናው ዘርፍ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ላይ የመጣው ለውጥ እና የታየው ስኬት ሊደነቅ የሚገባው ነው ብለዋል። የተለያዩ የግብርና ኢንሼቲቮች የተረጂነትና የጠባቂነት አስተሳሰብን በማስወገድ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የዜጎችን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ መሆኑንም አንስተዋል። በሌሎችም ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶችም እመርታ የተመዘገበባቸውና አመርቂ ውጤት የተገኘባቸው መሆኑን ገልጸዋል። በድምሩ ባለፉት ዓመታት በመንግሥት አዳዲስ እሳቤዎችና በህዝቡ ትብብር በተለያዩ መስኮች የሚታዩና የሚጨበጡ እመርታዎች የተመዘገቡበት መሆኑን ተናግረዋል። የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ሥራ አስፈጻሚ እና የኦሮሚያ ክልል አስተባባሪ አቶ ሀብታሙ ተሰማ፤ በመንግሥት ሀገር በቀልና አዳዲስ እሳቤዎች በመታገዝ ባለፉት ጥቂት አመታት አስደናቂ ውጤት መመዝገቡን ተመልክተናል ብለዋል። የውጭ ምንዛሪ እጥረትንና የዋጋ ግሽበትን በመቋቋም ጭምር የሀገሪቱን ገጽታ የቀየሩ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን በጥራት እና በፍጥነት በመፈጸም የላቀ እመርታ መታየቱንም አንስተዋል። በጥናት ላይ ተመስርቶ በሀገሪቱ አምራች ኢንዱስትሪዎች እንዲስፋፉ መደረጉ ለዜጎች ሰፊ የስራ እድልን ከመፍጠር ባለፈ የውጭ ምንዛሬ ወጪን በመቀነስ ረገድ ትርጉም ያለው ስራ ተሰርቷል ብለዋል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የምሥራቅ ሸዋ ዞን አስተባባሪ ወይዘሮ ሠናይት በላይ፤ በአዲሱ ዓመት መባቻ ላይ የጳጉሜን ቀናት በተለያዩ ስያሜዎች መከበራቸው በጎ ሀሳቦችን እንድናፈልቅ ልዩ ስሜት እንዲፈጠርብን ያደርጋል ብለዋል። መንግሥት በጥቂት ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በማሸጋገር በተለይም በመስኖ ስንዴን በማልማት ከሀገር ውስጥ ፍጆታ አልፎ ለውጭ ገበያ ማቅረብ መቻሉ ትልቅ እመርታ መሆኑን ገልጸዋል። በቱሪዝም፣ ዲጂታላይዜሽን፣ የአረንጓዴ አሻራ ልማት፣ በአትክልትና ፍሬፍሬ ልማት እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች እመርታ መመዝገቡን ማየት ችለናል ብለዋል።
የሀገራችንን ኢኮኖሚ በፅኑ መሠረት ላይ እየገነባን እንገኛለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Sep 6, 2026 770
አዲስ አበባ፤ጳጉሜን 1 /2018 (ኢዜአ)፦የሀገራችንን ኢኮኖሚ በፅኑ መሠረት ላይ እየገነባን እንገኛለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእመርታ ቀንን በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት፣አባቶቻችን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በደምና በአጥንታቸው አስከብረው ታላቅ ሀገር አውርሰውናል ብለዋል። ዛሬ ደግሞ እውነተኛ ሉዓላዊነትን እያረጋገጥን ያለነው ከልመናና ከጥገኝነት በተላቀቀው አዲሱና ታሪካዊው መንገዳችን ነው ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው በሚሊዮን በሚቆጠር ዶላር ስንዴ ከማስገባት ተነስተን ዛሬ የአፍሪካ ቀዳሚ ስንዴ አምራች በመሆን የሚሊዮን ዶላሮችን ወጪ ማስቀረት ችለናል ነው ያሉት። በ "ሌማት ትሩፋት" የምግብ ዋስትናን በተግባር እያረጋገጥን፣ በ "ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄም አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋትና የሥራ ዕድል በመፍጠር ሉዓላዊነታችንን እያረጋገጥን እንገኛለን። ከዚህ ቀደም የማይደፈሩና አይነኬ ይባልላቸው የነበሩ ከባድ የማክሮ-ኢኮኖሚ ሪፎርም ውሳኔዎችን በቁርጠኝነት በመተግበር፤ የሀገራችንን ኢኮኖሚ በፅኑ መሠረት ላይ እየገነባን እንገኛለን በማለት ገልፀዋል። እነዚህ ሁሉ ታላላቅ ድሎች ኢትዮጵያ በሚያጋጥሟት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች ሸብረክ ሳትል በፅናት መጓዝ መቻሏን የሚያረጋግጡ ህያው ምስክሮች መሆናቸውን ጠቁመዋል። ይህ የእመርታ ጉዟችን ለመጪው ዓመት የሰነቀው ተስፋ እጅግ ግዙፍ ነው ብለዋል። #EthiopiaDelivers
ኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባውን ሊያደርግ ነው
Sep 6, 2026 485
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት 74ኛው አስቸኳይ ስብሰባውን መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም በጅቡቲ ያካሂዳል። በስብሰባው ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮች ይሳተፋሉ። በቀጣናው ሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም በሌሎች አበይት ጉዳዮች ላይ ምክክር ይደረጋል። ይህ ስብሰባ አባል ሀገራት በቀጣናው ያለውን የጸጥታና የደህንነት ሁኔታ እና እየተከናወኑ ያሉ ቀጣናዊ ጥረቶችን በመገምገም ለሰላም፣ መረጋጋትና ትብብር ያላቸውን የጋራ አቋም እንዲያጠናክሩ መልካም አጋጣሚ እንደሚፈጥር ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በተጨማሪም ምክር ቤቱ የድርጅቱን ተልዕኮ እና በቀጣናው ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ላይ የሚያደርገውን ድጋፍ እና የኢጋድ ስምምነትን (IGAD Treaty) ተፈጻሚነት ማጠናከርን ጨምሮ በዋና ዋና ተቋማዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል። ስብሰባው የኢጋድ አባል ሀገራት በቀጣናው የሚገኙ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመቅረፍ እንዲሁም ለሕዝቦቻቸው ሰላም፣ መረጋጋትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት የሚያረጋግጡበት እንደሆነም ተገልጿል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከኢጋድ ቁልፍ የፖሊሲ አደረጃጀቶች መካከል አንዱ ሲሆን፣ የድርጅቱን ሥራዎች በመምራትና በአባል ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር ረገድ ጉልህ ሚና የሚጫወት ነው።

ማህበራዊ
በሲዳማ ክልል በክልላዊ እና በሀገር አቀፍ ፈተናዎች የተማሪዎች ውጤት እየተሻሻለ መጥቷል
Sep 7, 2026 76
ሀዋሳ፤ ጳጉሜን 2/2018 (ኢዜአ)፡-በሲዳማ ክልል የትምህርት ማህበረሰቡን በማሳተፍ በተከናወኑ ሥራዎች በክልላዊና በሀገር አቀፍ ፈተናዎች የተማሪዎች ውጤት መሻሻል ማሳየቱን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። የሲዳማ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በየነ በራሳ እንዳሉት በተጠናቀቀው የትምህርት ዘመን በክልሉ በሁሉም የትምህርት እርከኖች የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል። የትምህርት ማህበረሰቡን በማነቃነቅ ከመደበኛው የመማር ማስተማር ሥራው በተጨማሪ የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል መሰራቱን ተናግረዋል። በዚህም በክልላዊና በሀገር አቀፍ ፈተናዎች የተማሪዎች ውጤት እየተሻሻለ መምጣቱን ገልጸዋል። ባለፉት ዓመታት በ6ኛ እና በ8 ክፍል ክልላዊ ፈተና የተማሪዎች የማለፍ ምጣኔ ዝቅተኛ እንደነበር አቶ በየነ አስታውሰው፣ የትምህርት ማህበረሰቡን በማሳተፍ በተደረገ ጥረት በአሁኑ ወቅት የማለፍ ምጣኔው 62 በመቶ ደርሷል ብለዋል። በአስራ ሁለተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናም የተማሪዎች የማለፍ ምጣኔ እየተሻሻለ መምጣቱን ተናግረዋል። የሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምክትል ርዕሰ መምህርት ጽዮን ታደገ እንዳሉት፣ ተማሪዎች በፈተና ውጤታማ እንዲሆኑ ሙሉ ትኩረታቸውና ለትምህርት እንዲሰጡ ተደርጓል። በማጠናከሪያ ትምህርት፣ ተከታታይ ሞዴል ፈተናዎችን በመስጠትና የስነ ልቦና ድጋፍ በማድረግ ተማሪዎችን የማብቃት ሥራ መሰራቱን ገልጸው፣ በዚህም ዘንድሮ ትምህርት ቤቱ ያስፈተናቸው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ ማለፋቸውን ተናግረዋል። በወላጆቻቸው፣ በመምህራንና በትምህርት ቤቱ በተደረገላቸው ድጋፍ በሀገር አቀፍ ፈተናው ጥሩ ውጤት ማምጣታቸውን የተናገሩት ተማሪ ቤቴል ሲሳይ እና ተማሪ ልኡል አለማየሁ ናቸው። ተማሪ ቤቴል ሲሳይ 532፤ ተማሪ ልኡል አለማየሁ ደግሞ 539 ውጤት ያመጡ ሲሆን በሀገር አቀፍ ፈተና ውጤታማ የሚያደርገው ኩረጃ ሳይሆን በቂ ዝግጅት ማድረግ ብቻ መሆኑን ገልጸዋል። ተማሪዎቹ በቀጣይ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ ጊዜያቸውን ሙሉ በሙሉ በትምህርታቸው ላይ በማድረግ ውጤታማ ለመሆን መዘጋጀታቸውንም ተናግረዋል።
የእናቶችና ሕጻናትን ሞት ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት
Sep 7, 2026 163
ካራት፤ ጳጉሜን 2/2018 (ኢዜአ)፡-የእናቶችና ሕጻናትን ሞት ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጤና ሚኒስቴር ገለጸ። ፎር አፍሪካ የተሰኘ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በኮንሶ ዞን ካራት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ ያስገነባው የሶላር ሃይል ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል። የጤና ሚኒስቴር የስነ-ተዋልዶ፣ የቤተሰብ ዕቅድና የወጣቶች ጤና አገልግሎት ቡድን መሪ ሞቱማ በቀለ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው እንዳሉት፣ በሀገሪቱ የእናቶችና ሕጻናትን ሞት ለመቀነስ በተደረገ ጥረት ለውጥ ተመዝግቧል። በካራት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሶላር ሃይል መገንባቱ በሆስፒታሉ የጤና አገልግሎቱን ውጤታማ በማድረግ የእናቶችና ሕፃናት ሞት ለመቀነስ የሚደረገው ጥረት ይበልጥ ስኬታማ ያደርጋል ብለዋል። እንደሀገር የእናቶችና ሕጻናትን ሞት ለመቀነስና የጤና አገልግሎቱን ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አስገንዝበዋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ እንዳሻው ሽብሩ በበኩላቸው እንዳሉት፣ የክልሉ መንግስት ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በቅንጅት ባከናወነው ተግባር የተሻለ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ ተችሏል። በእዚህም የእናቶችና የሕጻናትን ሞት መቀነስን ጨምሮ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን ነው የገለጹት። በካራት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተገንብቶ ለምረቃ የበቃው የሶላር ፕሮጀክት ከሀይል አቅርቦት ጋር በተያያዘ ሲነሳ የነበረውን የመልካም አስተዳደር ችግር የሚፈታና የጤና ልማት ግቦችን ለማሳካት ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል። የፎር አፍሪካ ካንትሪ ዳይሬክተር ፀደቀ ደሳለኝ በበኩላቸው ድርጅቱ ከመንግስት፣ ከኮንሶ ልማት ማህበር እና ከማህበረሰቡ ጋር በመተባበር ከ120 ሺህ ዩሮ በሚበልጥ ወጪ የሶላር ሀይል ፕሮጀክት በካራት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለአገልግሎት ማብቃቱን ተናግረዋል። የሶላር ፕሮጀክቱ 128 ኪሎ ዋት ሃይል የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን ይህም ሆስፒታሉ ሃይል ሳይቆራረጥበት ለህብረተሰቡ አስተማማኝና የተሻለ የጤና አገልግሎት ለመስጠት ያስችለዋል ብለዋል፡፡ ካራት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከ1 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ የተናገሩት ደግሞ የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ገሌቦ ጎልቶሞ ናቸው። ዋና አስተዳዳሪው ፎር አፍሪካ እና ሌሎች ባለድርሻዎች ላበረከቱት አስተዋፅኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ትውልዱ የህብረተሰቡን ባህል፣ ታሪክ፣ ቋንቋና እሴት ጠብቆ የማስተላለፍ ኃላፊነት አለበት
Sep 7, 2026 136
አመያ፣ ጳጉሜን 2/2018 (ኢዜአ)፡-ትውልዱ የህብረተሰቡን ባህል፣ ታሪክ፣ ቋንቋና እሴት ጠብቆ የማስተላለፍ ኃላፊነት ያለበት መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የኮንታ ዘመን መለወጫ "ህንግጫ" በዓል በአመያ ከተማ በድምቀት ተከብሯል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) የኮንታ ዘመን መለወጫ ህንግጫ በአል በትውልድ ቅብብሎሽ የተገነባ ውድ ቅርስ ነው። በመሆም የበአሉን ታሪካዊ ዳራ ጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ በክልሉ ባለፉት አመታት በሁሉም ዘርፎች ብልጽግናን ማረጋገጥ የሚያስችሉ እምርታዊ ለውጦች ተመዝግበዋል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ እነዚህ ድሎች ኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን ላይ እንደሆነች ማሳያ ናቸው ብለዋል፡፡ በክልሉ ባለፉት አመታት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉም አመላክተዋል፡፡ የተያዘውን የማንሰራራት ጉዞ ለማፋጠን በሁሉም ዘርፍ የተጀመሩ የትብብርና የጋራ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል ። የኮንታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ በበኩላቸው ህንግጫ በትውልድ ቅብብሎሽ ሲከበር የመጣ የኮንታ የማንነትና አንድነት መገለጫ ነው ብለዋል። በአሉ የሕዝቡን አንድነት፣ ፍቅር፣ አብሮነትና ተስፋ ከማጠናከር ባለፈ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንዳለው አመልክተዋል። በበአሉ ላይ የፌደራል፣ የክልልና በየደረጃው ያሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
የአርቲስት እልፍነሽ ቀኖ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ነገ በአምቦ ይፈጸማል
Sep 7, 2026 97
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 2/2018 (ኢዜአ)፦ የአንጋፋዋ አርቲስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች እልፍነሽ ቀኖ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ነገ ጳጉሜን 03 ቀን 2018 ዓ.ም በክብር ሥነ-ሥርዓት ይፈጸማል። አዘጋጅ ኮሚቴው በሰጠው መግለጫ መሠረት፤ የአርቲስቷ አስከሬን ሽኝት ነገ ከጠዋቱ 11:00 እስከ 12:00 ከኮሪያ ሆስፒታል ወደ መኖሪያ ቤቷ የሚደረግ መሆኑን ገልጿል። ከጠዋቱ 12:00 እስከ 1:00 ባለው ጊዜ ደግሞ አስክሬን ከመኖሪያ ቤቷ ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም ይወሰዳል። የአርቲስቷ ወደጆች ጓደኞችና አድናቂዎችም ነገ ከጠዋቱ 1:00 እስከ 3:00 በአዲስ አበባ ስታዲየም ተገኝተው አሸኛኘት ካደረጉላት በኋላ ወደ አምቦ ሽኝት እንደሚደረግ አዘጋጅ ኮሚቴው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ገልጿል። የዕድሜ ልክ ትግሏን ለሰው ልጆች ነፃነትና ለህዝብ ድምፅነት የሰጠችው አርቲስት እልፍነሽ ቀኖ፣ በህይወት እያለች "ከዚህ ዓለም ስሰናበት ቀብሬ አምቦ ይሁን" ባለችው ኑዛዜ መሠረት፣ አስተባባሪ ኮሚቴው የጀግናዋን ፍላጎት በማክበር የመጨረሻ እረፍቷ በአምቦ ከተማ እንዲሆን መወሰኑ ተመላክቷል። በዜማዎቿ የሕዝብን ብሶትና ተስፋ ስታንጸባርቅ የኖረችው ይህች ታላቅ አርቲስት፣ በግል ሕይወቷም የሁለት ሴቶችና የአንድ ወንድ ልጅ እናት በመሆን መልካም ቤተሰብን ያፈራች እናት ነበረች።
ኢኮኖሚ
በክልሉ በቱሪዝም ዘርፍ 978 ሚሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል
Sep 7, 2026 381
ጂንካ፥ ጳጉሜ 2/2018 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በቱሪዝም ዘርፍ 978 ሚሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወይኒቱ መልኩ በክልሉ በተጠናቀቀው በጀት አመት ከቱሪዝም ዘርፍ 500 ሚሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን አስታውሰዋል። ይሁን እንጂ ለዘርፉ በተሰጠው ትኩረት ከእቅድ በላይ 978 ሚሊዮን ብር መገኘቱን ተናግረዋል። በክልሉ የቱሪዝም መዳረሻዎችን የማልማትና የማስተዋወቅ ስራ በስፋት በመሰራቱና የጎብኚዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ለገቢው ማደግ በምክንያትነት ጠቅሰዋል። የሙሩሌ የቁጥጥር አደን ቦታ፣ የማጎና የማዜ ብሔራዊ ፓርኮች የኮንሶ ባህላዊ መልክዓ ምድር ዓለም አቀፍ መካነ ቅርስ በክልሉ ከሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎች ዋነኞቹ እንደሆኑ ጠቁመዋል። የአርባምንጭ አዞ እርባታ፣ የባንባላ ተንጠልጣይ ድልድይ፣ የዳሞ ተራራና የጌዴኦ ትክል ድንጋዮች መካነ ቅርስም በስፋት እየተጎበኙ ያሉ የመስህብ ስፍራዎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል። በበጀት አመቱ 13 ሚሊዮን የሀገር ውስጥና የውጪ ቱሪስቶች የመስህብ ስፍራዎቹን መጎብኘታቸውን ተናግረዋል። በክልሉ የጎብኚዎች ቁጥር መጨመርም ለቢዝነስ ቱሪዝም መነቃቃት እና ለስራ እድል ፈጠራ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አስታውቀዋል። የማጎ ብሔራዊ ፓርክ አስተዳዳሪ አቶ ኤርቦር ሌለ በበኩላቸው ፓርኩን ለመመልከት ወደ ስፍራው የሚመጡ ጎብኚዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል። ፓርኩ ከ80 በላይ አጥቢ፣ ከ250 በላይ የአዕዋፍና 14 ዓይነት የዓሣ ዝርያዎችን የያዘ መሆኑን አመልክተዋል።
በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የሀገሪቱን የማንሰራራት ጉዞ የሚያፋጥኑ ናቸው
Sep 7, 2026 371
አዲስ አበባ ፤ ጳጉሜን 2/2018 (ኢዜአ) ፦ በአዲስ አበባ የተገነቡ የቱሪዝም መዳረሻዎችና ሌሎች የመሠረተ ልማት ሥራዎች የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ የሚያፋጥኑ መሆናቸውን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጳጉሜን 02 "የማንሰራራት ቀን"ን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የተገነቡ የቱሪዝም መዳረሻዎችንና የመሠረተ ልማት ሥራዎችን ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች አስጎብኝቷል። በጉብኝት መርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉ ጎብኚዎች በአዲስ አበባ የተገነቡ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ከተማዋ ለአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ እንድትሆን ያስቻሉ ናቸው ብለዋል፡፡ አስተያየት ሰጪ ሻምበል ዋኘው አባይ እንዳሉትም ከተማዋ ከዚህ ቀደም ከነበራት ገጽታ በተለየ መልኩ ውብና ጽዱ መሆኗን ገልጸው፤ የወንዝ ዳርቻ፣ የኮሪደር ልማትና የቱሪዝም መዳረሻዎች የሀገሪቱን ዕድገት የሚያንሰራሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። አቶ ገዛኸኝ አሰፋ በበኩላቸው የመሠረተ ልማት ሥራዎቹ ለዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠሩ፣ ለነዋሪዎችና ለጎብኚዎች ምቹ አካባቢን የፈጠሩ መሆናቸውን በአካል ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል፡፡ እነኚህም የኢትዮጵያን የማንሰራራት ግስጋሴ የሚያፋጥኑ ናቸው ብለዋል፡፡ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን በመገናኛ ብዙኃን ከማየት ባለፈ በአካል መጥተው በመጎብኘታቸው መደሰታቸውን የገለጹት ሐጂ ሸምሱ አባስ ፤ የከተማዋ ዕድገት ለሀገር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሙኒኬሽን ኃላፊ ልደት ሙለታ ጳጉሜን 02 "የማንሰራራት ቀን"ን ምክንያት በማድረግ በለውጡ ዓመታት ለነዋሪዎች ውብና ጽዱ ከተማን ለመፍጠርና በቱሪዝም ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎችን ማስጎብኘታቸውን ገልጸዋል። ባለፉት ዓመታት የተገነቡ የቱሪዝም መዳረሻዎች፣ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ተግባራት የሀገሪቱን ዕድገት ያረጋገጡ መሆናቸውንም ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጳጉሜን 02 "የማንሰራራት ቀን"ን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የተገነቡ የቱሪዝም መዳረሻዎችንና የመሠረተ ልማት ሥራዎችን ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች አስጎብኝቷል። በጉብኝት መርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉ ጎብኚዎች በአዲስ አበባ የተገነቡ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ከተማዋ ለአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ እንድትሆን ያስቻሉ ናቸው ብለዋል፡፡ አስተያየት ሰጪ ሻምበል ዋኘው አባይ እንዳሉትም ከተማዋ ከዚህ ቀደም ከነበራት ገጽታ በተለየ መልኩ ውብና ጽዱ መሆኗን ገልጸው፤ የወንዝ ዳርቻ፣ የኮሪደር ልማትና የቱሪዝም መዳረሻዎች የሀገሪቱን ዕድገት የሚያንሰራሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። አቶ ገዛኸኝ አሰፋ በበኩላቸው የመሠረተ ልማት ሥራዎቹ ለዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠሩ፣ ለነዋሪዎችና ለጎብኚዎች ምቹ አካባቢን የፈጠሩ መሆናቸውን በአካል ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል፡፡ እነኚህም የኢትዮጵያን የማንሰራራት ግስጋሴ የሚያፋጥኑ ናቸው ብለዋል፡፡ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን በመገናኛ ብዙኃን ከማየት ባለፈ በአካል መጥተው በመጎብኘታቸው መደሰታቸውን የገለጹት ሐጂ ሸምሱ አባስ ፤ የከተማዋ ዕድገት ለሀገር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሙኒኬሽን ኃላፊ ልደት ሙለታ ጳጉሜን 02 "የማንሰራራት ቀን"ን ምክንያት በማድረግ በለውጡ ዓመታት ለነዋሪዎች ውብና ጽዱ ከተማን ለመፍጠርና በቱሪዝም ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎችን ማስጎብኘታቸውን ገልጸዋል። ባለፉት ዓመታት የተገነቡ የቱሪዝም መዳረሻዎች፣ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ተግባራት የሀገሪቱን ዕድገት ያረጋገጡ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
በደቡብ ወሎ ዞን በተለያዩ ዘርፎች የተመዘገቡ ውጤቶች የኢትዮጵያ የማንሰራራት ተምሳሌት ናቸው
Sep 7, 2026 376
ቃሉ፤ ጳጉሜን 2/2018(ኢዜአ)፡-በደቡብ ወሎ ዞን በኢንቨሰትመንት፣ በቱሪዝም፣ በግብርና፣ በፍራፍሬ እና የኮሪደር ልማት መስኮች የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶች የኢትዮጵያ ማንሰራራት በተጨባጭ የሚያረጋግጡ መሆናቸውን የዞኑ መስተዳድር ገለፀ። በዞኑ የማንሰራራት ቀን ምክንያት በማድረግ በቃሉ ወረዳ እና ሀርቡ ከተማ የተለያዩ የልማት ሥራዎች ጉብኝት ተካሂዷል። በጉብኝቱ የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ እንድሪስ ይማም እንደገለጹ፣ በዞኑ በተለያዩ የልማት ሥራዎች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል። በተለይ በኢንቨሰትመንት፣ በቱሪዝም፣ በግብርና፣ የፍራፍሬ እና ኮሪደር ልማትን ጨምሮ በከተማ ልማት፣ በንጹህ መጠጥ ውሃና በሌሎችም የተመዘገቡ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች የኢትዮጵያ እያንሰራራች መሆኑን ያመላክታሉ ነው ያሉት። በከተሞቹ የጠጠር ማምረቻ፣ የኮሪደር ልማት፣ ተንጠልጣይ ድልድይና ሌሎችም ልማቶች ተስፋ ሰጪ እና የኢትዮጵያን ማንሰራራት ለማስቀጠል የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልፀዋል። የዞኑ ማዕድን ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አህመድ አበባው በበኩላቸው፣ በዞኑ ከሚገኘው በርካታ የማዕድን ሀብት በአግባቡ እና በዘላቂነት ተጠቃሚ ለመሆን እየተሰራ ነው ብለዋል። የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በከተማው በተሰሩ ሰፋፊ ልማቶች ተጠቃሚ መሆናቸውን የተናገሩት ደግሞ የሀርቡ ከተማ ነዋሪ ሸህ ሰይድ ሀሰን እና ሹምነሽ ኢብራሂም ናቸው። በተለይ የኮሪደር ልማቱ የከተማውን ውበት በማሳመር ለነዋሪዎች ምቹ የሥራ አከባቢን የፈጠረ ሲሆን በወረዳው እየተገነቡ ባሉ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀዋል። ከዚህ ውስጥም በተገነቡ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ችግራቸው በመቀረፉ መደሰታቸውን ገልጸዋል። በጉብኝቱ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አመራሮችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
የመደመር መንግስት በተለያዩ ዘርፎች ያከናወናቸው ተግባራት የኢትዮጵያን ማንሰራራት ለማረጋገጥ ያስቻሉ ናቸው
Sep 7, 2026 375
ደብረማርቆስ፤ ጳጉሜ 2/2018(ኢዜአ)፡- የመደመር መንግስት በተለያዩ ዘርፎች ያከናወናቸው ተግባራት የኢትዮጵያን ማንሰራራት በተግባር ለማረጋገጥ ያስቻሉ ናቸው ሲል የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ። ከተማ አስተዳደሩ የማንሰራራት ቀንን አስመልክቶ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር የፓናል ውይይት አካሒዷል። የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ የኋላ ደስታ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፤ የመደመር መንግስት ተግባራዊ ባደረጋቸው የኢንዱስትሪ፣ የከተማ ግብርናና የሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ከፍተኛ ስኬቶች ተመዝግበዋል። ከዚህ ውስጥም በከተማ አስተዳደሩ ከ10 ዓመት በፊት ከአስር በታች የነበረው የአምራች ኢንዳስትሪዎች ቁጥር አሁን ላይ ከ70 በላይ ማድረስ የተቻለ ሲሆን 39 የሚሆኑት ወደ ማምረት የተሸጋገሩ መሆኑን አረጋግጠዋል። በማህበራዊ ዘርፍም በቅድመ አንደኛ ደረጃ፣ በ1ኛና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተደራሽነት፣ ጥራትና አግባብነት ውጤታማ የሆኑ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቅሰዋል። ከ500 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪም ሞዴል ትምህርት ቤት ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ መገኘቱ የማንሰራራት ማሳያ እንደሆነም አብራርተዋል። በስራ እድል ፈጠራ፣ በከተማ ግብርና፣ በመሰረተ ልማት ግንባታና በሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች አበረታች ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን አስገንዝበዋል። ከተሳታፊዎች መካከል ሊቀ ካህናት ይትባረክ መኮነን እና ወንዳለ ተመስገን እንዳሉት ፤ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኮሪደርና ሌሎች ልማቶች የታየው ለውጥ ይበል የሚያሰኝ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል። በተለይ በከተማ ግብርና ፣ በኢንድስትሪ እና መሰል ስሰራዎች ላይ ያከናወናቸውን ተግባራት ውጤት መምጣቱን ተዘዋውረው መመልከታቸውን ተናግረዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ፤ የመጪው ዘመን የኢኮኖሚ ማንሰራራት መሰረት
Sep 7, 2026 104
አዲስ አበባ፤ጳጉሜን 2/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ ጉልህ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ትገኛለች። ባለፉት አምስት ዓመታት ተግባራዊ የተደረገው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ተከትሎም ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ይፋ መደረጉ ይታወቃል። የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂም ሁሉን አቀፍ እና ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የሚመራ ጠንካራ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለመገንባት ያለመ ነው። ይህም ፈጠራን፣ ምርምርን፣ ስታርት አፕን በማበረታታት፣ የሞባይልና ኢንተርኔት ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር በመጨመር የፋይናንስ አካታችነትን ያረጋገጡ የቴሌብርና መሰል የዲጂታል ክፍያ አማራጮች ማኅበረሰቡ የዕለት ተዕለት አሠራር አካል የሚሆኑበትን ዕድል ፈጥሯል። በፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያና መሶብ የአንድ ማዕከል የመንግሥት አገልግሎት መስጫ ማዕላትን በማበራከትም የተቀናጀ የመንግሥት አገልግሎት ምኅዳርን ፈጥሯል። ይህም የተገልጋዮችን ምልልስ፣ ወጪ፣ ጉልበትና ጊዜ በመቆጠብ፣ የመንግሥት አገልግሎት ውጤታማነትን በማጎልበት እንዲሁም መልካም አስተዳደርን በማስፈን የኢትዮጵያን የብዝኅ ኢኮኖሚ ማንሰራራት ጉዞ እያሳለጠ ይገኛል። በአጠቃላይ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የፐብሊክ መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት፣ የሰው ኃይል አቅምና ፈጠራን በማጎልበት በሁሉም ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ማጠናቀቂያና «ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ባስጀመሩበት ወቅት፤ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የኢትዮጵያን ብልፅግና ጉዞ የሚያፋጥን መሠረት መጣሉን አስታውሰዋል። የስትራቴጂው ትግበራ ሙሉ በሙሉ በስኬት መጠናቀቁም ለቀጣይ የዲጂታል ኢትዮጵያ አስተማማኝ ግንባታ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አስረድተዋል። የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ የትኩረት መስክ የብዝኅ ኢኮኖሚ ሥርዓትን በማሳለጥ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ማንሰራራት ጉዞ እያነጸ መሆኑን አብራርተዋል። የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂም በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን በማጎልበት ሁሉም ዜጋ አካታችና ፍትሐዊ የዲጂታል መሠረተ ልማት የሚያገኝበትን ሁኔታ እንደሚፈጥር ገልጸዋል። ለዚህም በስትራቴጂው መሠረት የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት፣ የኢንተርኔት ተደራሽነት፣ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ፣ የዲጂታል ገንዘብ ዝውውርና በተቋማት መካከል የዳታ ልውውጥ ውጤታማነት ለማሻሻል እንደሚሠራ ጠቅሰዋል። የሰው ሠራሽ አስተውሎት፣ የሳይበር ደኅንነትና የዳታ አስተዳደር ላይ ትኩረት በማድረግ የወጣቶችን የቴክኖሎጂ ክህሎት ማሳደግ፣ አዳዲስ ፈጠራዎችን እና የዲጂታል ሥራ ዕድሎችን ማስፋፋት የስትራቴጂው የትኩረት መስኮች መሆናቸውን ጠቅሰዋል። የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ዘመኑ የሚጠይቀው ጉዳይ በመሆኑ ኢትዮጵያ በዚህ መስክ ራሷን መቻል እንዳለባትም አስገንዝበዋል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) የ100 ቀናት የመንግሥት ሥራ አፈጻጸም ግምገማን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ ላይ እንደተናገሩት፤ የኢትዮጵያ የዲጂታላይዜሽን የትኩረት አቅጣጫ የኢኮኖሚ ማንሰራራት ጉዞውን የሚቀርጽ እመርታዊ ለውጥ አምጥቷል ብለዋል። በዚህም የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ የፈጠራቸው የኢትዮ-ኮደርስ፣ የመሶብ አንድ ማዕከል፣ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያና የዲጂታል ፋይናንስ ግብይቶች ፈጠራን በማበረታታት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን እያሳለጡ መሆናቸውን አንስተዋል። በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ መሠረተ ልማት ዝርጋታ ጎን ለጎን የዜጎችን ዲጂታል ክህሎት ለማሳደግ እየተከናወኑ ከሚገኙ ሥራዎች መካከል የኢትዮ-ኮደርስ ሥልጠና ተጠቃሽ ነው። ወጣት ባዩሽ ተስፋዬና ቀለሙ ዘለቀ እንደገለጹት፤ ከመደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን የኮደርስ ሥልጠና መውሰዳቸው የዲጂታል ክህሎታቸውን በማበልጸግ ተጠቃሚ እያደረጋቸው መሆኑን ገልጸዋል። ወጣት መሰረት አቦሰጥ እንደምትለውም፤ የኢትዮ-ኮደርስ ሥልጠና የሰው ሠራሽ አስተውሎትና ዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅሟን በማጎልበት ተጠቃሚ እያደረጋት ነው። ወጣት እሸቱ አበራ በበኩሉ፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስና በሌሎች ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ ዓይነ ሥውር ዜጎችም እንደ ማንኛውም ሰው የኮደርስ ሥልጠናን መውሰድና ተጠቃሚ በመሆን ከዘመኑ ጋር መራመድ እንደሚችሉ ዕድል መፍጠሩን ገልጿል።
መሶብ የአንድ ማዕከል፤ የመደመር መንግሥት የአገልግሎት ትራንስፎርሜሽን ማስፈንጠሪያ
Sep 6, 2026 244
መሶብ የአንድ ማዕከል፤ የመደመር መንግሥት የአገልግሎት ትራንስፎርሜሽን ማስፈንጠሪያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጭነት የተጀመረው የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ የዜጎችን እንግልት በመቀነስና የመንግሥት አሰራርን በማዘመን ረገድ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ ይገኛል። የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመንግሥት አሰራርን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማዘመን፣ የወረቀት ስራንና እንግልትን በማስቀረት ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና ግልጽ አገልግሎት ለመስጠት የተዘረጋ ስርዓት ነው። ፕሮጀክቱ አገልግሎት ፈላጊዎች በአንድ ማዕከል በርካታ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ታሳቢ ያደረገ ሲሆን፤ ይህም ህብረተሰቡ የመሬት አስተዳደር፣ የኢንቨስትመንት፣ የገቢዎችና ሌሎችንም የመንግሥት አገልግሎቶች በኦንላይንና በአካል ማግኘት የሚያስችል ነው። አገልግሎቱ በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በባህር ዳር እና በሌሎችም የክልሎች ከተሞች ተግባራዊ መሆን የጀመረ ሲሆን፤ ማዕከላቱን በየደረጃው እስከ ወረዳ ድረስ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተንቀሳቃሽ መሶብ አገልግሎትን በአዲስ አበባ ባስጀመሩበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ለረጅም ዘመናት የቆዩ የአገልግሎት አሰጣጥ ማነቆዎችን በመፍታት የተገልጋዮችን እርካታ ማሳደግ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተውታል። ይህንን ለማሳካት በመንግሥት፣ በግል ኩባንያዎችና በእያንዳንዱ ዜጋ ዘንድ የባህልና የአስተሳሰብ ለውጥ መምጣት እንዳለበትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል። ሀገሪቷን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር መንግሥት በትኩረት እየሰራባቸው ካሉ አምስት የኢኮኖሚ አምዶዎች መካከል ቴክኖሎጂ አንደኛው መሆኑን ነው በወቅቱ ያብራሩት። ቴክኖሎጂ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የቱሪዝም ዘርፍን ለማዘመን እንዲሁም ዲጂታል የአገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት ሁሉንም የልማት ዘርፎች የሚያቀናጅ ዋና መሣሪያ መሆኑን ገልጸዋል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡበት ሲሆን፤ በተለይም የአገልግሎት አሰጣጥን ወደ ዘመናዊና ዲጂታል ሥርዓት በመቀየር የዜጎችን እንግልት መቀነስ አስችሏል። የ“ዲጂታል 2030” ስትራቴጂ፣ ባለፉት አምስት ዓመታት የተገኙ ስኬቶችን ይበልጥ በማጠናከር ሀገራዊ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግርም አብራርተዋል። የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መሶብ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዮናስ አለማየሁ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ በሀገሪቷ ባሉ ከ108 በላይ ማዕከላት ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ተችሏል። የአገልግሎቱ አጠቃላይ ሀገር አቀፍ የተገልጋዮች እርካታ መጠን ከ99 በመቶ በላይ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈፃሚው ተናግረዋል። በዘመናዊ ተንቀሳቃሽ አገልግሎት መስጫዎች ማዕከላት በአካል መጥተው መገልገል ለማይችሉ ዜጎች አገልግሎት እየሰጡ መሆኑንና ተደራሽነትን ይበልጥ ለማስፋት እየተሰራ መሆኑን አጽንኦት መስጠታቸው ይታወሳል። በመዲናዋ የተዘረጋው የዲጂታል መሶብ አገልግሎት፣ በከተማ ደረጃ እየተካሄደ ላለው የዲጂታል ሽግግር ማሳያ ከመሆኑም በላይ በነዋሪዎች ዘንድ ትልቅ ተስፋን ጥሏል።
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ብልሹ አሠራርን በመቀነስ የተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግ አስችሏል - ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Sep 5, 2026 231
ጎንደር፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ)፦ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ብልሹ አሠራርን በመቀነስ የተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ። ርዕሰ መሥተዳድሩ አረጋ ከበደ የጎንደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ዛሬ መርቀው ሥራ አስጀምረዋል። ርዕሰ መሥተዳድሩ በዚሁ ወቅት መሶብ የአንድ ማዕከል የመንግሥት የአገልግሎት አሠጣጥ ሪፎርም አካል በመሆን ዘልማዳዊ እና እንግልት የበዛበትን አሠራር እየቀየረ ነው ብለዋል። የመንግሥት ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት በአንድ ማዕከል በማሠባሠብ፣ በማደራጀት፣ ዲጂታል በማድረግ፣ ብልሹ አሠራርን በመቀነስ የተገልጋዮችን እርካታ ለማሻሻል እያገዘ መሆኑንም አስረድተዋል። በክልሉ ስድስት መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን ተገልጋይን መሠረት ያደረገ በመሆኑ የነበረውን እንግልት የበዛበት አሠራር ሁለንተናዊ በሆነ መንገድ እየቀረ መሆኑን አንስተዋል። የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የተሻለ ተደራሽነትን፣ የላቀ ቅልጥፍናን፣ ግልጽነትን እና ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ መኾኑንም አንስተዋል። አገልግሎቱ የመንግሥት ተቋማትን በማቀናጀት፣ የእርስ በእርስ የመረጃ ልውውጣቸውን በማቀላጠፍ ለደንበኞች እርካታ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል። የጎንደር መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ሕንጻ የከተማዋን ቀደምት የኪነ- ሕንጻ ጥበብ በጠበቀ መንገድ በጥራት ተገንብቶ የተጠናቀቀ መሆኑንም አብራርተዋል። በቀጣይም በኮምቦልቻ፣ በደብረ ማርቆስ እና ደብረ ብርሃን ከተሞች የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ስራ እንደሚጀምሩም ነው የተናገሩት። በ2019 በጀት ዓመትም በክልሉ ሁሉም ወረዳዎች እና ከተሞች የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎትን የማስፋፋት ስራ እንደሚሠራም አመላክተዋል።
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎቱን ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ በዲጂታል ቴክኖሎጂ እያዘመነ ነው - ኢንጂነር አብዱልበር ሸምሱ
Sep 4, 2026 250
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎቱን ፈጣን፣ ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ በዲጂታል ቴክኖሎጂ እያዘመነ መሆኑን የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አብዱልበር ሸምሱ ገለጹ። የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ደንበኞች በዘመናዊ ዲጂታል አማራጭ የሚገለገሉበት የዲጂታል መተግበሪያ ዛሬ አስመረቋል። የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አብዱልበር ሸምሱ (ኢ/ር) በዚሁ ወቅት፤ ኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት የሚያሳልጥ የባሕር ላይ የትራንስፖርት አገልግሎት እየተሰጠ ነው ብለዋል። በዚህም የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለሀገሪቱ የሎጂስቲክስ ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት አሰራር እየተገበረ መሆኑን ተናግረዋል። ተቋሙ ለአፍሪካ ብቸኛ እና ታሪካዊ የባህር ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ሆኖ መቆየቱን ገልጸው፤ በአሁኑ ወቅትም ዓለም አቀፍ ደረጃን የሚመጥን አዲስ አሰራር ስርዓት እየተገበረ ይገኛል ብለዋል። ዛሬ የተመረቀው ዲጂታል ቴክኖሎጂ ደንበኞች እንግልት በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው እንዲሁም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን የሚያፋጥን እንደሆነ አስታውቀዋል። በቀጣዮቹ ዓመታት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ የሚጠናቀቁ ትላልቅ አዳዲስ ሲስተሞች እየተገነቡ መሆኑን ጨምረው አስታውቀዋል። በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተቋሙን ከዓለም አቀፍ አሰራሮች ጋር እኩል የሚያሰልፉ መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ የቦርድ አባልና የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በበኩላቸው ፤ የሎጂስቲክስ ሥርዓቱን የሚያዘምን ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል። በዚህም መንግሥት የየብስ ትራንስፖርት፣ የባቡርና የደረቅ ወደብ መሠረተ ልማቶችን ከመገንባት ባለፈ፣ የመርከቦች ቁጥር እንዲበራከት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የኢትዮጵያን የሎጂስቲክስ አቅም ለማጎልበት ከሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች በተጨማሪም የባሕር በር ባለቤትነት ምላሽ ለማረጋገጥ በዋና አጀንዳነት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ዛሬ የተመረቀው ዲጂታል ቴክኖሎጂም አገልግሎቱን ይበልጥ ለማሳለጥ ትልቅ ጥቅም እንደሚሰጥ አስታውቀዋል። የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ቅልጥፍናን ለማሳለጥ የቴክኖሎጂ አሠራር ወሳኝ መሆናቸውን የተናገሩት ደግሞ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍራሆል ጣፋ ናቸው። የኢትዮጵያ ዲጂታል 2030 ስትራቴጂንና የሎጂስቲክስ ዘርፍ ስትራቴጂን መሠረት በማድረግ የሎጂስቲክስ ዘርፉን ለማዘመንና አሠራሩን ዲጂታላይዝ የሚያደርጉ በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። የዲጂታል መተግበሪያውም ግልጽ፣ ፈጣንና ዘመናዊ አሠራር ሥርዓትን ለመገንባት የሚያስችል ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ተናግረዋል።
ስፖርት
አርሰናል ከቼልሲ፡ የሳምንቱ ተጠባቂ የሊግ ጨዋታ
Sep 6, 2026 215
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል ከቼልሲ ዛሬ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። የለንደን ደርቢ ጨዋታ ምሽት 12፡30 ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ይካሄዳል። አርሰናል እና ቼልሲ በተመሳሳይ በስድስት ነጥብ፣ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ሶስተኛና አራተኛ ደረጃን ይዘዋል። ባለሜዳው አርሰናል በሁለቱ የሊግ ጨዋታዎች አራት ግቦችን ሲያስቆጥር ምንም ግብ አላስተናገደም። ይህም የቡድኑን፣ በተለይም የተከላካይ መስመሩን ጥንካሬ የሚያሳይ ነው። ተጋጣሚው ቼልሲ በሁለት ጨዋታዎች ሰባት ግቦችን ከመረብ ሲያሳርፍ አምስት ግቦች ተቆጥረውበታል። ቼልሲ የማጥቃት እንቅስቃሴው ጥሩ የሚባል ቢሆንም በተከላካይ ክፍሉ ላይ ያሉ ድክመቶችን ማረም ይኖርበታል። ሁለቱ የለንደን ተቀናቃኝ ክለቦች በሊጉ ሲገናኙ የአሁኑ ለ69ኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 68 ጨዋታዎች አርሰናል በ28ቱ ድል ሲቀናው፣ ቼልሲ 20 ጊዜ አሸንፏል። በቀሪ 18 ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል። በነዚህ ጨዋታዎች አርሰናል 97 ግቦችን ከመረብ ሲያሳርፍ፣ ቼልሲ በበኩሉ 85 ጎሎችን አስቆጥሯል። ባለፉት አምስት የሊግ ግንኙነታቸው አርሰናል በሶስቱ ሲያሸንፍ፣ በቀሪዎቹ ሁለት ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርተዋል። ቼልሲ ለመጨረሻ ጊዜ አርሰናልን በሊጉ ያሸነፈው እ.አ.አ በ2021 ነው። የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ አርሰናል በአዲሱ የውድድር ዓመት ያደረጋቸውን ሁለት ጨዋታዎች በማሸነፍ ክብሩን የማስጠበቅ ጉዞውን በጥሩ ሁኔታ ጀምሯል። ተጋጣሚው ቼልሲም ሁለቱን የሊግ ጨዋታዎች በድል በመወጣት መልካም ጅማሮ አድርጓል። በመሆኑም የሁለቱ የለንደን ክለቦች ጨዋታ ጠንካራ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል። የ41 ዓመቱ ክሪስ ካቫናግ ተጠባቂውን ፍልሚያ በዋና ዳኝነት ይመሩታል። በሌላኛው መርሐ ግብር ኤቨርተን ከማንችስተር ዩናይትድ በሂል ዲኪንሰን ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ኤቨርተን ከሁለት ጨዋታዎች ማግኘት የቻለው አንድ ነጥብ ብቻ ሲሆን፣ ተጋጣሚው ማንችስተር ዩናይትድ ሶስት ነጥብ አለው። ባለሜዳው ኤቨርተን በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን ለማስመዝገብ ወደ ሜዳ ይገባል። በሁለተኛው ሳምንት ኤፕስዊች ታውንን 5 ለ 2 የረታው ማንችስተር ዩናይትድ ደግሞ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ይፋለማል። ጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር ይታይበታል ተብሎ ይጠበቃል።
አስቶንቪላ በሊጉ የመጀመሪያ ነጥቡን አገኘ
Sep 5, 2026 325
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሁል ሲቲ እና አስቶንቪላ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል። ማምሻውን በኤምኬ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አስቶንቪላ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ቢወስድም ባለሜዳው ሁል ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎችን በማድረግ የተሻለ ነበር። አስቶንቪላ በውድድር ዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢላማቸውን የጠበቁ የግብ ሙከራዎችን አድርጓል። ውጤቱን ተከትሎ አዲስ አዳጊው ሁል ሲቲ በሰባት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ በሊጉ ጥሩ አጀማመር አሳይቷል። አስቶንቪላ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ነጥቡን ያገኘ ሲሆን 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። እስከ አሁን በሊጉ ምንም ግብ አላስቆጠረም። በአራተኛ ሳምንት ሁል ሲቲ ከቼልሲ፣ አስቶንቪላ ከኖቲንግሃም ፎረስት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ዛሬ በሊጉ ከተደረጉ ሰባት ጨዋታዎች መካከል አምስቱ በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል።
ሲዳማ ቡና ከኤግሎንስ ጋር አቻ ተለያየ
Sep 5, 2026 208
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ):- በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ሲዳማ ቡና እና የቻዱ ኤግሎንስ ጋር ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል። ጨዋታው ማምሻውን በኢድሪስ ዴቢ ኢትኖ ስታዲየም ተካሄዷል። ሲዳማ ቡና ግብ ማስቆጠር ባይችልም መልካም የሚባል እንቅስቃሴ አድርጓል። የሁለቱ ክለቦች የመልስ ጨዋታ መስከረም 2 ቀን 2019 ዓ.ም በድሬዳዋ ስታዲየም ይካሄዳል። ሲዳማ ቡና በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ከሱዳኑ አል ሂላል እና ከብሩንዲው አይግል ኑዋር አሸናፊ ጋር ይጫወታል። ሁለቱም ክለቦች በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ላይ ሲወዳደሩ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
አካባቢ ጥበቃ
አረንጓዴ ዐሻራ የትውልዱ ዳግማዊ ዓድዋ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ምልክት
Sep 7, 2026 177
አረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ መትከል ብቻ አይደለም፤ አካባቢን ለኑሮ ምቹና ማራኪ ገጽታ ማላበስ፣ የተፈጥሮን ሥነ-ምህዳር መጠበቅ፣ ለዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መቋቋም ጠጠር መጣል፣ ኢትዮጵያ የዓለም ነባራዊ ሁኔታ የሚገዳትና ለመፍትሔውም በግንባር ቀደምትነት የምትሳተፍ መሆኗን ማሳያ ጭምር እንጂ። አረንጓዴ ዐሻራ ለኢትዮጵያ ወንዞቿን በደለል ከመሞላት፣ አፈሯን ከመሸርሸር መታደግ፣ የዜጎቿን የምግብ ዋስትና የማረጋገጥና ምድሯን አረንጓዴ የማልበስ ኢኒሼቲቭ ነው። ከሰባት ዓመት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ኢኒሼቲቭ ሲያስጀምሩ፤ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን በመቋቋም አይበገሬ ኢኮኖሚ መገንባት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ አንዱ ሰበዝ እንደሆነ በመናገር ነበር። ኢትዮጵያ ዛሬ ለምግብነትና ለደን ልማት አገልግሎት፣ ለአካባቢ ውበትና መናፈሻ የሚውሉ በርካታ ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል ታሪክ ሠርታለች። በአረንጓዴ ዐሻራ የደረቁ ሐይቆች አገግመዋል፤ በደለል የሚሞሉ ሐይቆችን መታደግ ተችሏል፤ የሚሸረሸረው ለም አፈርም ከመታጠብ ድኗል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አረንጓዴ ዐሻራ የተረጅነት ታሪክን በአዲስ ምዕራፍ በመተካት የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጉዞ ጅማሬ መሆኑን ገልጸዋል። አረንጓዴ ዐሻራ ዜጎች በአካባቢያቸው የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ በማስቻል ለኢኮኖሚ ማንሰራራት መሠረት እየጣለ መጥቷል ብለዋል። አረንጓዴ ዐሻራ ከኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ብልፅግና ጋር በቀጥታ የተሳሰረ ሀገራዊ ትልም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የትውልዱ ዳግማዊ ዓድዋና የኢትዮጵያ የማንሰራራት ምልክት መሆኑን ገልጸዋል። ትውልዱ እንደ ትናንቱ ዓድዋ ሁሉ የዛሬውን አረንጓዴ ዐሻራ ከአባቶቹ የወረሰው የሀገር ማስቀጠያ ስንቅ በማድረግ በታሪክ ያወሳዋል ብለዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)፤ የአረንጓዴ ዐሻራ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን መሪነትና የተለየ ሚና የሚያጎላ የድል ችቦ መሆኑን ገልጸዋል። በአረንጓዴ ዐሻራ የተመዘገበው ውጤት በአፍሪካ አህጉር የወካይነት ሚና እንዲኖራት ማስቻሉን በማንሳት፤ ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ ኩነቶችን ለማስተናገድ እምነት የሚጣልባት ሀገር ሆናለች ብለዋል። ይህም ኢትዮጵያ በአካባቢ ጥበቃና በአየር ንብረት ዲፕሎማሲ በዓለም አቀፍ ደረጃ በግንባር ቀደምትነት እንድትሰለፍ ማድረጉን ገልጸዋል። የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ፤ የአረንጓዴ ዐሻራ በአካባቢ ጥበቃ ብቻ የተገደበ ሳይሆን ለግብርና ምርትና ምርታማነት ገንቢ ሚና አለው ብለዋል። በኢትዮጵያ የሰብል ምርት ዕምርታዊ ለውጥ እንዲያስመዘግብ በማስቻል በስንዴ ምርት ብቻ ከተረጂነት ወደ ትርፍ አምራችነት በመሸጋገር የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጉዞ እያበሰረ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በአቮካዶና በሌሎች የሆርቲካልቸር ምርቶች ከሀገር ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከፍተኛ መጠን ያለው የውጭ ምንዛሪ እንድታገኝ አስችሏታል ብለዋል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብርና ሌሎች የተቀናጁ የተፋሰስ ጥበቃ ሥራዎች በውሃ ሀብት ልማት በኩል ጉልህ ለውጥ ማስገኘታቸውን ገልጸዋል። የአረንጓዴ ዐሻራ የሐይቆችን የደለል ክምችት በመቀነስ ብዙ ውሃ እንዲይዙ በማድረግ የግድቦችን ዕድሜ ማራዘም አስችሏል ብለዋል። የደረቁ ምንጮችና ሐይቆች እንዲያገግሙ አድርጓል ያሉት ሚኒስትሩ፤ የውሃና የተፈጥሮ ሀብትን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ማስቻሉን ገልጸዋል።
ጽዱ ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ በርካታ ውጤታማ ተግባራት እየተከናወኑ ነው
Sep 7, 2026 80
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 2/2018 (ኢዜአ):- ጽዱ ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ በርካታ ውጤታማ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍሬነሽ መኩሪያ ገለጹ። «ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ» በተሰኘው ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ማዕቀፍ የተዘጋጀና በአደገኛ ቆሻሻ አስተዳደር፣ በኤሌክትሮኒክስ ብክነት (e-waste) እንዲሁም በኬሚካሎች ደህንነቱ የተጠበቀ አያያዝና ማስወገድ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሂዷል። በመድረኩ የፌዴራልና የክልል አካባቢ ጥበቃ ተቋማት ኃላፊዎች፣ የጤና ቢሮዎች ተወካዮች፣ የምርምርና የአካዳሚክ ተቋማት ተመራማሪዎች እንዲሁም በግል ዘርፍ የሚንቀሳቀሱ የቆሻሻ አስተዳደር ኦፕሬተሮች ተገኝተዋል። የፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍሬነሽ መኩሪያ በወቅቱ እንደገለጹት፤ በሀገሪቱ «ጽዱ ኢትዮጵያን» በመፍጠር በኩል በርካታ አርዓያነት ያላቸው ተግባራት እየተከናወኑ ነው፡፡ በዚህም የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ በከፍተኛ ሁኔታ መቻሉንና ለአካባቢ ጥበቃና ጽዳት ጥሩ ውጤት እየተገኘ መሆኑን አመልክተዋል። በቀጣይም የሚሰራውን ስራ በማጠናከር ጽዱ ኢትዮጵያን ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ አመልክተዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘም በአካባቢ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ አገልግሎት የጨረሱ ኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችና ሌሎች ቆሻሻዎችን ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ መንግስት ችግሩን ለመከላከል የሕግ ማዕቀፎችን፣ ደረጃዎችንና የሕግ ማስፈጸሚያ ሥርዓቶችን በማጠናከር በኩል የሚጠበቅበትን ሚና እየተወጣ መሆኑንም ምክትል ዳይሬክተሯ አስታውቀዋል። በመሆኑም ችግሩን ይበልጥ ለመቅረፍ የሁሉም ርብርብ ወሳኝ መሆኑንና የመንግሥት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የምርምር ተቋማትና የሕብረተሰቡ ቅንጅታዊ አሠራር ይበልጥ መጠናከር እንዳለበት ጠቁመዋል። በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የአካባቢ ተከባሪነትና ተፈጻሚነት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አዲሱ ጥበቡ በበኩላቸው አደገኛ ቆሻሻ ዓለም አቀፍ ትኩረት የተሰጠው ችግር መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያም የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ቆሻሻዎችን መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችል ሥርዓት ዘርግታ እየሰራች ትገኛለች ብለዋል። የፒዩር ኧርዝ የቴክኒካል ፕሮግራሚንግ ዳይሬክተር በረከት ተስፋዬ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአካባቢ ጥበቃ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥታ ውጤታማ ተግባራት እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ድርጅታቸው ከመንግሥት ጋር የተቀናጀ አሠራር ዘርግቶ እየሰራ መሆኑንና በቀጣይም ይህ የጋራ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
አፍሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ በመቀየስ ረገድ መሪ ሚና መጫወት ይገባታል-ክላቨር ጋቴቴ
Sep 7, 2026 160
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 2/2018 (ኢዜአ)፦ አፍሪካ በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ድርድሮችና መፍትሔዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የጎላ ሚና መጫወት እንዳለባት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክላቨር ጋቴቴ ገለጹ፡፡ 14ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ እና ልማት ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። ጉባኤው "ከተስፋ ቃል ወደ ተግባር፤ የቤሌም-አንታልያ-አዲስ አበባ ፍኖተ ካርታ" በሚል መሪ ሐሳብ ነው እየተካሄደ ያለው። የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክላቨር ጋቴቴ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት፣ አፍሪካ ለዓለም አቀፍ የካርቦን ልቀት የምታበረክተው አስተዋጽኦ አራት በመቶ ቢሆንም የችግሩን ከባድ መዘዝ እየተሸከመች ትገኛለች። ሆኖም ይህ እውነታ ለአፍሪካ የተጎጂነት ታሪክ ብቻ ሆኖ ሊቀጥል እንደማይገባ ተናግረው አፍሪካ ያላትን ከፍተኛ የታዳሽ ኃይል አቅም፣ የማዕድን ሀብቶች፣ ወጣት የሰው ኃይል እና እያደገ ያለውን ገበያ በመጠቀም በዓለም አቀፍ ደረጃ መፍትሔዎችን በመቀየስ ረገድ መሪ ሚና መጫወት እንዳለባት ገልጸዋል። አፍሪካ እስከ እ.ኤ.አ 2030 ድረስ የተቀመጡ የአየር ንብረት ግቦችን ለመተግበር በየዓመቱ 277 ቢሊዮን ዶላር የሚያስፈልጋት ቢሆንም እያገኘች ያለችው ከፍላጎቷ 11 በመቶ ያህሉን ብቻ ነው ብለዋል። የአየር ንብረት እርምጃዎች ከኃይል ተደራሽነት፣ከኢንዱስትሪ ልማት እና ከሥራ እድል ፈጠራ ጋር ተያይዘው መከናወን እንዳለባቸው አሳስበዋል። ከ600 ሚሊዮን በላይ አፍሪካውያን አሁንም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ያላገኙ በመሆናቸው የታዳሽ ኃይልን ማስፋፋት የኢኮኖሚው መሠረት ሊሆን ይገባል ብለዋል። የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣናን በመጠቀም በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ሀብቶች ላይ እሴት በመጨመር አህጉራዊ የእሴት ሰንሰለት መገንባት ይቻላል ሲሉም ገልጸዋል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ስኬቶችን በማላቅ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቷል- ከንቲባ ከድር ጁሃር
Sep 6, 2026 159
ድሬዳዋ፣ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡- የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ስኬቶችን በማላቅ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የአየር ንብረት ለውጥ ሚዛንን ለመጠበቅ ትኩረት መሰጠቱን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ተናገሩ። የእምርታ ቀን በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ በመትከልና እና በሌሎች ዝግጅቶች በድሬዳዋ እየተከበረ ነው። "እምርታ ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሃሳብ በክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሀግብር ተካሂዷል። ከንቲባ ከድር ጁሃር በወቅቱ እንደተናገሩት፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎችን በማላቅ ለምግብ ዋስትና መረጋገጥና የአየር ሚዛን ለመጠበቅ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው። የመደመር መንግስት ባለፉት ዓመታት ተግባራዊ ካደረጋቸው እና የአገር የከፍታ ጉዞ ዕውን ከሆኑባቸው ተግባራት መካከል አንዱ የአረንጓዴ አሻራ መሆኑን አንስተዋል። በድሬዳዋ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብሮች ችግኞች የአካባቢውን ስነምህዳር በመለወጥ፣ የከርሰ ምድር ውሃ እንዲጨምር በማገዝና የተመናመነውን ደን በመመለስ ወሳኝ ሚና ማበርከታቸውን አስታውቀዋል። በተለይ በድሬዳዋ ሲከሰት የነበረን የጎርፍ አደጋን በላቀ ደረጃ በመቀነስና ውሃን ወደ ጥቅም ለመለወጥ እያበረከተ ያለው አስተዋፅኦ ለማስቀጠል ችግኞች በላቀ ህዝባዊ ተሳትፎ እየተተከሉ ይገኛሉ ብለዋል። ዛሬም በእምርታ ቀን በህዝብ እና በአመራሩ ተሳትፎ የተተከሉት ችግኞች የተገኘውን እመርታ ለማጠናከር ጉልህ ፋይዳ እንዳላቸው አንስተዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ግብርና፣ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኑረዲን አብደላ በበኩላቸው እንዳሉት፣ የእምርታ ቀን በአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር የተገኙ ውጤቶችን በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል መደላድል የተፈጠረበት ነው። በተለይ መርሀግብሩ የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር ውሀ ሀብት እንዲያድግ መሰረት በመጣሉ የገጠሩ ህብረተሰብ አነስተኛ መስኖ በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን በመጨመር ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር እያገዘ ይገኛል ብለዋል። የእምርታ ቀንን ምክንያት በማድረግ ዛሬ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሀግብር ላይ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Sep 4, 2026 350
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን እና ሁሉን አቀፍ ትብብራቸውን የበለጠ ለማላቅ እንደሚሰሩ አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ውይይቱ በአፍሪካ ህብረትና አሜሪካ መካከል ያለውን ለረጅም ጊዜ የቆየ አጋርነት ማጠናከር እና በአህጉሪቱ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የአፍሪካና አሜሪካን ትብብር ታሪካዊ መሆኑን አውስተው በህብረቱ፣ በአባል ሀገራት እና በአሜሪካ መካከል የሁለቱንም ወገኖች ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ጠንካራ አጋርነት መገንባት እንደሚገባ አሳስበዋል። በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሱዳን እየተደረጉ ላሉ አፍሪካ መር የሰላም ጥረቶች አሜሪካ እያደረገች ላለው ገንቢ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ በበኩላቸው አፍሪካ አሜሪካ ቀዳሚ ትኩረት የምትሰጣት አህጉር እንደሆነች ገልጸዋል። የጋራ ፍላጎቶችንና ግቦችን ከህብረቱ ኮሚሽንና ከአባል ሀገራት ጋር በመሆን ለማሳካት ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በዲፕሎማሲ፣ እንዲሁም በሰላምና ጸጥታ ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል። በውይይቱ ላይ በሱዳን ጉዳይ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የሰብአዊ እርዳታ ያለ ገደብ እንዲገባ እና በሲቪሎች የሚመራ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመር አጽንዖት ተሰጥቷል። በአፍሪካ ባለቤትነት የሚመሩ የሰላም ጥረቶች እና አሜሪካ የምትደግፋቸው የሰላም ሂደቶች በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር ከስምምነት ላይ ተደርሷል። በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት እና በሰላም መስኮች የሁለቱን ወገኖች ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ የትብብር መስኮች ተገምግመዋል። ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ህብረትና በአሜሪካ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ውስጥ የተደረጉ ስምምነቶችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። በሊቢያ ጉዳይ ዘላቂ የፖለቲካ መፍትሄ ማግኘት እንደሚያስፈልግም ተነስቷል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር እና ረዳት ሚኒስትሩ የሁለቱን ወገኖች ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና የትብብር አድማሱን ለማስፋት የጋራ ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያ 76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት ስብሰባ ታስተናግዳለች
Aug 5, 2026 1686
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ (RC76) ከነሐሴ 18 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ስብሰባው ከዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ነው። በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና መረጃ መሠረት፣ ስብስባው የቀጣናውን የጤና አጀንዳዎች ላይ መምከርና አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከርን ያለመ ነው። የ47ቱ የአፍሪካ ቀጣና አባል አገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የዓለም አቀፍ ጤና መሪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ለጋሾችና የዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮችን ጨምሮ ከ600 በላይ ተወካዮች በስብስባው ላይ ይሳተፋሉ። የስብሰባው ተሳታፊዎች በቀጣናዊ የጤና አቅዶች ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችን የሚገመግሙ ሲሆን በአዳዲስ ስትራቴጂዎችና የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ይመክራሉ። እንዲሁም የጤና ሥርዓቶችን ለማጠናከር፣ ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ተደራሽነትን ለማስፋፋት፣ የጤና ደህንነትን ለማሻሻልና የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትን ለማሳደግ የሚረዱ የጋራ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ካሶሎ፤ ስብሰባው አባል አገራት የቀጣናውን የጤና አጀንዳ እንዲቀርጹ፣ አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ እና በመላው አፍሪካ ጤናማ፣ አስተማማኝና ጠንካራ ማህበረሰቦችን የመገንባት ሂደት ለማፋጠን ትልቅ እድል የሚሰጥ ነው ብለዋል። ተወካዩ አክለውም የኢትዮጵያ ስብሰባውን ማስተናገድ፤ ለቀጣናዊ ወንድማማችነትና ለጋራ ትብብር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ አህጉራዊ ጉባኤ የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት ስኬቶች፣ በተለይም መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በማስፋፋትና በቅርቡ በክልል የተከሰተውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስ በመቆጣጠር ረገድ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማሳየት ዕድል እንደሚፈጥር መረጃው አመልክቷል። ስብስባው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፣ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን በመጠቀም ለጋራ የጤና ፈተናዎች የተቀናጀ አህጉራዊ ምላሽ ለመስጠት ስትራቴጂካዊ መድረክ እንድትሆን ያደርጋታል። በስብስባው ላይ የቴክኒክ ውይይቶች፣ አውደ ርዕዮች ፣ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችና የሕዝብ ግንኙነት ስራዎች የሚካሄዱ ሲሆን፣ እነዚህም በአፍሪካ ተቋማት መካከል የጤናው ዘርፍ የፈጠራ ስራዎችንና የእውቀት ልውውጥን የሚያጎሉ እንደሚሆኑ ተገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ የቀጣናዊ ጽሕፈት ቤቱ የበላይ አካል ሲሆን፤ በየዓመቱ በመሰብሰብ የቀጣናውን የጤና ፖሊሲ ይወስናል፣ የድርጅቱን ሥራዎች ይገመግማል፣ እንዲሁም በመላው አህጉሪቱ ለሚከናወኑ የጤና ተግባራት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች ያስቀምጣል።
ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች ነው- ሲኤንኤን
Aug 4, 2026 1342
የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ በኢትዮጵያ ላይ በሚያተኩረው ዘገባዋ በሀገሪቱ ኮረብቶች ያለውን ወርቅ ጨምሮ ከፍተኛ የብረት ማዕድናት አምራች ለመሆን እያደረገች ያለውን ጥረት መመልከቷን ተናግራለች። በዘገባዋ ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ከፍተኛ የሃይል ሚዛን መሆን እንደምትፈልግ ገልጻ፤በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘው ኩርሙክ የወርቅ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ የማዕድን ኢንቨስትመንቶች ውስጥ በዋናነት የሚጠቅስ መሆኑን ተናግራለች። በምዕራብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ከለበሱት ከፍተኛ የኮረብታ ስፍራዎች ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን የሚያስገኙ ከፍተኛ የወርቅ ሀብቶች እንዳሉ እና አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ብቅ እያሉ መሆኑን ትናገራለች። በሺዎች የሚቆጠሩ የግንባታ ባለሙያዎች እና ማዕድን አውጪዎች በኢትዮጵያ ግዙፍ የሆነውን የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ ግንባታ እያከናወኑ እንደሚገኝ ገልጻለች። በስፍራው የሚገኙ የማዕድን እና ጂኦሎጂ ባለሙያዎች የወርቅ ማዕድኑን የማጣራት ስራ እያከናወኑ መሆኑን ገልጻለች። ጋዜጠኛዋ የወርቅ ማጣራት እና ምርት ሂደቱን በተመለከተ ከባለሙያዎች ማብራሪያ ማግኘቷንም አመልክታለች። ወርቁን የማግኘት ሂደቱ እጅጉን ፈታኝ እና አድካሚ እንደሆነ ገልጻ፥ይሁንና ልፋቱ ትልቅ ጠቀሜታ የሚያስገኝ መሆኑን ተናግራለች። የወርቁን ግብአት ውጪ ሀገር ልኮ ከማጣራት ይልቅ በኩርሙክ የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ የራሱ ማጣሪያ ፕላንት እንዳለው በጉብኝቷ ወቅት መረዳቷን አመልክታለች። የሲኤንኤኗ ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ ወርቅ የሀገሪቷ ዋና የወጪ ንግድ ገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ገልጻለች። ባለፈው ዓመት በወርቅ የተገኘው የወጪ ንግድ ገቢ ከፍተኛ መሆኑን ተናግራለች። ይህም የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ውጥኖች በግልጽ የሚያሳይና ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች እንደምትገኝ ሲኤንኤን በዘገባው አስረድቷል።
የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር ይገባል
Jul 30, 2026 1617
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018 (ኢዜአ)፦የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተመለከተ፡፡ የአፍሪካ ህብረት በፓሲፊክ ውቅያኖስ ሙቀት የሚፈጠር የአየር ንብረት መዛባት (ኤልኒኖ) አስመልክቶ አስቸኳይ ስብስባውን ዛሬ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል። በህብረቱ የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር (ADREE) ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ የተዘጋጀው ስብሰባ እ.አ.አ በ2026 ይከሰታል ተብሎ የሚጠበቀውን የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተት ለመቋቋም እና አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከርን ያለመ ነው። ከፍተኛ የምክክር መድረኩ "የአፍሪካን ቅድመ ዝግጅት፣ የመቋቋም አቅም እና የአየር ንብረት እርምጃዎችን ማጠናከር" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። በስብሰባው ላይ በአካል ከተገኙት ተሳታፊዎች በተጨማሪ በበይነ መረብ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በሁነቱ ላይ ታድመዋል። የስብሰባው ዋና ትኩረት አፍሪካ ለኤልኒኖ የተቀናጀ ምላሽ እንድትሰጥ የጋራ ትብብርን መፍጠር ነው። በተጨማሪም በ31ኛው እና በ32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች (COP31) እና (COP32) ላይ የአፍሪካን ሚና ማሳደግ እና የአህሪቷን አጀንዳዎች ጎልተው እንዲታዩ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ይመክራል። ለአንድ ቀን የሚቆየው ስብስባ በባለሙያዎች እና በሚኒስትሮች ደረጃ ተከፍሎ ይካሄዳል። የአፍሪካ የሜቲዎሮሎጂ ትግበራዎች ልማት ማዕከል (ACMAD) የኤልኒኖ ክስተትን ትንበያ እና በአህጉሪቱ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ በተመለከተ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀርባል። በተጨማሪም በአየር ንብረት ለውጥ የአፍሪካ ተደራዳሪዎች ቡድን መሪነት አህጉሪቱ በመጪዎቹ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች የምታደርገው ተሳትፎ እና ለዓለም አቀፉ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ጉባኤ የሚደረጉ ዝግጅቶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል። የአፍሪካ የውሃ ሚኒስትሮች ምክር ቤትም (AMCOW) ከ 2026 የአፍሪካ ህብረት የዓመቱ መሪ ሀሳብ ጋር የተያያዘ ሪፖርት ያቀርባል። የአባል ሀገራት ሚኒስትሮችም ስለ ኤልኒኖ ተፅዕኖ እና አህጉራዊ ምላሽ መግለጫዎችን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ስብሰባው በኤልኒኖ ዙሪያ የተዘጋጀውን የድርጊት መርሃ ግብር፣ የባለሙያዎች ሪፖርት እና የጋራ የአቋም መግለጫ እንደሚያፀድቅም ተመላክቷል። በስብሰባው ከአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት በተጨማሪ የተለያዩ አጋር አካላት ተገኝተዋል። ኤልኒኖ (El Nino) በፓሲፊክ ውቅያኖስ የውሃ ሙቀት ከመደበኛው በላይ በመጨመሩ ምክንያት የሚከሰት ዓለም አቀፋዊ የከባቢ አየርና የአየር ንብረት መዛባት ክስተት ነው። የኤልኒኖ ተጽእኖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያልተለመደ የከፋ ድርቅን፣ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋንና የሙቀት መጠን መጨመርን በማስከተል በግብርና እና በሰዎች ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል።
ሐተታዎች
የስኬት መገለጫና የውጤት ማሳያዎች
Aug 28, 2026 529
አዲስ አበባ ነሀሴ 22/2018 (ኢዜአ) የስኬት መገለጫና የውጤት ማሳያዎች በኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብና የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ (Homegrown Economic Reform) እቅዶችን በመተግበር በበርካታ ዘርፎች መሠረታዊ ለውጦችን እና ስኬቶችን ማስመዝገብ ተችሏል። በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ በዲጂታል (አይሲቲ)፣ በማዕድን እና በቱሪዝም ዘርፎች የተመዘገቡት ስኬቶች የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብታዊ አቅም ከማሳደግ ባሻገር የወደፊት ዘላቂ እድገት መሠረት ያኖሩ መሆኑን መናገር ይቻላል። በመሆኑም በአምስቱ ዋና ዋና ሴክተሮች የመጡ ውጤቶችና የተመዘገቡ ስኬቶችን በወፍ በረር እንቃኛለን። 1. በግብርና ዘርፍ የስንዴ ምርትና የውጭ ኤክስፖርት: የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት መስፋፋት ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሰረት አስቀምጧል። ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የስንዴ ምርትን ወደ ውጭ ሀገር መላክ የቻለችበትን እመርታዊ ስኬትም አሳይቶናል። የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭን በመተግበር በወተት፣ በእንቁላል፣ በዶሮና የማር ምርት እንዲሁም በአትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ሩዝና ሻይ ልማትም ባለፉት አምስት አመታት እመርታዊ ለውጥ ተመዝግቧል። አርሶ አደሩ የመሬትና የውሃ ሀብቶችን አቃፊ በሆነ መንገድ በመጠቀም በዓመት ሁለትና ሶስት ጊዜ ማምረት የሚችልበት አሰራር ተዘርግቷል። በዚህም የቤተሰብ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ሁነኛ የገቢ ምንጭ የሆነበትን እድል ፈጥሯል። ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራስን የመቻል አቅም በመገንባት ላይ ይገኛል። በተለይም ደግሞ የቡና ምርታማነትና ጥራት በማደጉ ምክንያት በኤክስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማገኘት ተችሏል። በዘርፉ በቀጣይም የግብርናውን ዘርፍ ይበልጥ በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በሜካናይዜሽን በማስደገፍ ምርታማነትን የማሳደግ ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። የመስኖ መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት የዝናብ ጥገኝነትን ለመቀነስ መጣር እንዲሁም የግብርና ምርቶችን ጥራት በማሻሻልና በማቀነባበር ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን ዋጋ ማሳደግ ተገቢ ይሆናል። 2. የኢንዱስትሪ ዘርፍ ሀገራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ንቅናቄ በመፍጠር ቀደም ሲል ተቆልፈው የነበሩና በዝቅተኛ አቅምያመርቱ የነበሩ ፋብሪካዎች ወደ ሙሉ የማምረት አቅማቸው እንዲመለሱ ተደርጓል። የሀገር ውስጥ የምርት ፍላጎትን በመሸፈን ለውጭ ሀገር ምርቶች ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪም መቀነስ አስችሏል። ለሀገር ውስጥና ለውጭ ባለሀብቶች ምቹ የህግና የአሰራር ሁኔታዎችን በመፍጠር በርካታ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ ተችሏል። ከተገነቡት የተቀናጁ የግብርና ማቀነባበሪያ ፓርኮች (IAIPs) ጋር አርሶ አደሩን በማስሳሰር የግብአትና የምርት ትስስር እንዲጠናከር ተደርጓል። የአምራች ዘርፉ መስፋፋት ለብዙ ሺህ ዜጎች፣ በተለይም ለወጣቶች የሥራ እድል መፍጠር የታቸለበት ሆኗል። በቀጣይም የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በኃይል፣ በሎጂስቲክስና በግብአት አቅርቦት ሙሉ በሙሉ በመደገፍ ኤክስፖርትን ማሳደግ። የአምራች ኢንዱስትሪዎች 80% እና ከዚያ በላይ የሀገር ውስጥ ጥሬ ዕቃዎችን እንዲጠቀሙ ማበረታታት፣ በህዝብና በግል አጋርነት (PPP) አማካኝነት በትልልቅ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች ላይ የግሉን ዘርፍ አሳትፎ ማስፋፋት ትኩረት የሚደረግበት ይሆናል። 3. የዲጂታል (አይሲቲ) ዘርፍ የ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ስልት ስኬቶችን በማስቀጠል ወደ "ዲጂታል 2030" እቅድ መሸጋገር ተችሏል። በ"መሶብ" የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና በሌሎች ፖርታሎች አማካኝነት ህዝባዊ አገልግሎቶችን በበይነ-መረብ (Online) የመስጠት ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የዜጎችን መረጃ ማዕከላዊ የሚያደርግና ለፋይናንስ እንዲሁም ለሌሎች አገልግሎቶች መሠረት የሆነውን የፋይዳ መታወቂያ ፕሮጀክት በላቀ መልኩ ማሳካት ተችሏል። የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የኮደር ስልጠናም የዜጎችን የዲጂታል ክህሎት ለማሳደግ ታላቅ ሀገራዊ የስልጠና መርሃ ግብር ተዘርግቶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።የዲጂታል አገልግሎቶች መዘርጋታቸው የፊት ለፊት ግንኙነትን በመቀነስ ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን በመከላከል የኢንቨስትመንት ምህዳሩን አሳልጧል። የቴሌኮም ዘርፍ ውድድር: የቴሌኮም ዘርፉን ክፍት ማድረግን ተከትሎ የኢንተርኔትና የኔትወርክ ተዳራሽነትንና ጥራትን በየገጠሩ የማስፋት ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቶችን እና የባንክ አገልግሎቶችን ይበልጥ ዘመናዊና የተቀናጁ ማድረግም አስፈላጊ ይሆናል። የሀገሪቱን የዲጂታል መሠረተ ልማት ከሳይበር ጥቃቶች የመጠበቅ አቅምን ማጠናከር። 4. የማዕድን ዘርፍ በዘርፉ ይስተዋል የነበረውን ኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ንግድ በመግታት ህጋዊ አሰራርና ቁጥጥር እንዲሰፍን ተደርጓል። የህግና መመሪያዎች ማሻሻያ በማድረግ የማዕድን ዘርፉን ለውጭና ሀገር ውስጥ ኢንቨስትመንት ማራኪ የሚያደርጉ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ተደርገዋል። የወርቅ፣ የከሰል ድንጋይ፣ የሲሚንቶ ግብአቶችና የከበሩ ድንጋዮች ምርትን በማሳደግ ዘርፉ የሀገሪቱ ዋነኛ የውጭ ምንዛሬ ማግኛ እንዲሆን ተሰርቷል። በተለይም የከሰል ድንጋይ ምርትን በሀገር ውስጥ አምርቶ በመተካት ለፋብሪካዎች ግብአት ማቅረብ ተችሏል። 5. የቱሪዝም ዘርፍ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ( ዶ/ር)አነሳሽነት የተጀመሩት "ገበታ ለሸገር"፣ "ገበታ ለሀገር" እና "ገበታ ለትውልድ" ፕሮጀክቶች በመላ ሀገሪቱ በርካታ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን መገንባት ተችሏል። በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች የተከናወኑ የኮሪደር ልማቶች የከተሞችን ውበትና ለኑሮ ምቹነት ከመጨመራቸው ባሻገር ለከተማ ቱሪዝም ትልቅ እድል ፈጥረዋል። አዲስ አበባ በርካታ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችንና ኮንፈረንሶችን ባካሄደችበት የዲፕሎማሲና የኮንፈረንስ ማዕከልነቷን አጠናክራለች። የሀገሪቱን ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶች የመጠበቅ፣ የማደስና ለጎብኚዎች ምቹ የማድረግ ስራዎች በስፋት ተከናውነዋል። በድምሩ ባለፉት አምስት ዓመታት በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ በዲጂታል፣ በማዕድን እና በቱሪዝም ዘርፎች የተመዘገቡት ስኬቶች ሀገሪቷን ወደ ተሻለ የኢኮኖሚ ምዕራፍ ማሸጋገር አስችለዋል። በመሆኑም እነዚህን ስኬቶች አጠናክሮ ለማስቀጠል የታቀዱትን የወደፊት ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች በተቀናጀ መልኩ መተግበር፣ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ እና የግሉን ዘርፍ አሳታፊነት ማሳደግ በቀጣይ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት ዋነኛ የቤት ስራ ይሆናል።
የአረንጓዴ አሻራ ስኬት፦ኢትዮጵያን የአየር ንብረት ጥበቃ ሞዴል ያደረገ ኢኒሼቲቭ
Aug 23, 2026 629
የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በይፋ የተጀመረው በሐምሌ ወር 2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አማካኝነት ነው። በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስከ አሁን ከ54 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ 32ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) እ.አ.አ በ2027 በኢትዮጵያ በሚካሄድበት ወቅት የተተከሉ ችግኞችን ብዛት 65 ቢሊዮን የማድረስ እቅድ ተይዞ እየተሠራ ይገኛል። አረንጓዴ አሻራ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት ነው።ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ የምግብ ምርታማነትን በማሳደግ፣ የደን ሽፋንን በመጨመር፣ የተራቆተ መሬትን ወደ ነባር ይዞታው እንዲመለስ በማድረግ እና አይበገሬ የአረንጓዴ ኢኮኖሚን በመገንባት ረገድ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። በዚህም በ2011 ዓ.ም 17.2 በመቶ የነበረው የኢትዮጵያ የደን ሽፋን፣ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በተከናወነው ሥራ ወደ 23.6 በመቶ ማደግ ችሏል። ይህ ሀገራዊ እንቅስቃሴ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅና አግኝቷል።በሁለተኛው የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባኤ እንዲሁም በአዲስ አበባ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ሥራዋን ያስተዋወቀች ሲሆን፣ የአፍሪካ ሀገራትም ለአህጉሪቱ ትልቅ ተምሳሌት የሚሆን ኢኒሼቲቭ ሲሉ አድንቀውታል። ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን እንድታዘጋጅ መመረጧ በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል እያከናወነች ላለው ጥረት ዓለም አቀፍ እውቅና የተሰጠበት እና የሀገሪቱን የአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ውጤት የሚያሳይ ነው። ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ችግኞችን በመለገስ የአካባቢ ጥበቃ የጋራ አጀንዳ መሆኑን በተግባር አሳይታለች።ይህም አረንጓዴ ዲፕሎማሲ በሀገራት መካከል በጎ ግንኙነትንና አዎንታዊ የቀጣናዊ ትስስር ድልድይን እየገነባ ይገኛል። የድንበር ተሻጋሪ የወንዝ ተፋሰሶችን በመንከባከብ፣ የታዳሽ ኃይል አቅርቦትን ለጎረቤት ሀገራት በማዳረስ እና በጋራ ድንበሮች አካባቢ የደን ሽፋንን በማሳደግ ረገድ እያከናወነችው ያለው ሥራ አህጉራዊ ሰላምና ትብብርን የሚያጎለብት አዲስ የዲፕሎማሲ መንገድ ከፍቷል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት እና በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች የአህጉሪቱን ፍላጎትና ጥቅም ለማስከበር ግንባር ቀደም ተሟጋች ሆናለች። ለአየር ንብረት ለውጥ አነስተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ነገር ግን ለጉዳቱ በከፍተኛ ሁኔታ የተጋለጡ የአፍሪካ ሀገራት ፍትሃዊ የፋይናንስ እና የቴክኖሎጂ ድጋፍ እንዲያገኙ ድምፅ በመሆን አህጉራዊ መሪነቷን አስመስክራለች። ይህም አፍሪካውያን በራሳቸው ሀገር በቀል መፍትሔዎች የአየር ንብረት ጥበቃን ማረጋገጥ እንደሚችሉ ማረጋገጫ ሆኗል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና አምባሳደሮች የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ ለአካባቢ ጥበቃ አርአያ የሚሆን ዓለም አቀፍ ሞዴል ሲሉ አድንቀውታል። ኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይልን ከመጠቀም፣የካርቦን ልቀትን ከመቀነስ እና ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መስፋፋት ጋር አጣጥማ የምታካሂደው እንቅስቃሴ በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች ላይ እውቅና እንድታገኝ አስችሏታል።
ረብጣ ገንዘብ ከወጣባቸው ዝውውሮች እስከ አነጋጋሪ የህግ ለውጦች ፡ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አዲሱ የውድድር ዓመት ምን ይዞ መጣ?
Aug 21, 2026 632
በሙሴ መለሰ የዓለም እግር ኳስ አፍቃሪያን በጉጉት የሚጠብቀው የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ዛሬ በይፋ ይጀምራል። የዘንድሮው የውድድር ዘመን በሰኔ እና ሐምሌ ወራት የተካሄደውን የ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ተከትሎ፣ ለተጫዋቾች በቂ የእረፍት ጊዜ ለመስጠት ሲባል ከተለመደው አንድ ሳምንት ዘግይቶ እንዲጀምር ተደርጓል። የመክፈቻው ጨዋታ በኢምሬትስ ስታዲየም የባለፈው የውድድር ዘመን ሻምፒዮን አርሰናል እና ከ25 ዓመታት በኋላ ወደ ሊጉ በተመለሰው ኮቨንትሪ ሲቲ መካከል ምሽት አራት ሰዓት ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ይካሄዳል። ይህ አዲስ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት ላይ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ከፍተኛ ተሳትፎ አድርገዋል። እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት፣ የሊጉ ክለቦች ለተጫዋቾች ዝውውር ብቻ ከ2.14 ቢሊዮን ፓውንድ በላይ ወጪ አድርገዋል። ይህ የወጪ መጠን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሌሎች የአውሮፓ አራት ታላላቅ ሊጎች (ስፔን፣ ጣልያን ጀርመንና ፈረንሳይ) በጥምረት ካወጡት የገንዘብ መጠን በላይ ሆኗል። ሞርጋን ሮጀርስ ከአስቶን ቪላ ወደ ቼልሲ በ117 ሚሊዮን ፓውንድ በመዘዋወር የክረምቱ ውዱ ተጫዋች መሆን ችሏል። ኤሊዮት አንደርሰን ከኖቲንግሃም ፎረስት ወደ ማንቸስተር ሲቲ በ116 ሚሊዮን ፓውንድ አምርቷል። በተጨማሪም ሳንድሮ ቶናሊ ከኒውካስል ወደ ቶተንሃም በ100 ሚሊዮን ፓውንድ፣ እንዲሁም ብሩኖ ጉማሬሽ ከኒውካስል ዩናይትድ ወደ አርሰናል በ75 ሚሊዮን ፓውንድ መዘዋወራቸው የክረምቱን የዝውውር ገበያ ከሚጠቀሱ ዝውውሮች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ከዝውውር ወጪው ባሻገር፣ የዘንድሮው የውድድር ዘመን በአዳዲስ አሰልጣኞች የታጀበ ሆኗል። በሊጉ ታሪክ ከፍተኛው በተባለ ደረጃ ዘጠኝ ክለቦች ውድድሩን በአዲስ አሰልጣኞች ይጀምራሉ። ፔፕ ጋርዲዮላ ማንቸስተር ሲቲን በገዛ ፈቃዱ መልቀቁን ተከትሎ የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አሁን ላይ በሊጉ ረጅም ጊዜ (ሰባት ዓመታት) የቆየው አሰልጣኝ ሆኗል። የቼልሲው ዣቢ አሎንሶ፣ የማንቸስተር ሲቲው ኤንዞ ማሬስካ እና የሊቨርፑሉ አንዶኒ ኢራኦላ ከአዳዲሶቹ አሰልጣኞች መካከል ይጠቀሳሉ። ማይክል ካሪክ በማንቸስተር ዩናይትድ እንዲሁም ሮቤርቶ ዴ ዜርቢ በቶተንሃም ሆትስፐርስ የመጀመሪያ ሙሉ የውድድር ዓመታቸውን ይጀምራሉ። የሊጉ የተሳታፊዎች ስብጥርን በተመለከተ፣ ኮቨንትሪ ሲቲ ከ25 ዓመታት በኋላ ከሃል ሲቲ እና ኢፕስዊች ታውን ጋር በመሆን ከታችኛው ሊግ አድገው ሊጉን ተቀላቅለዋል። በተቃራኒው ዌስትሃም ዩናይትድ፣ በርንሌይ እና ዎልቨርሃምፕተን ዋንደረርስ ባለፈው የውድድር ዘመን መውረዳቸው የሚታወስ ነው። በተጨማሪም የእንግሊዝ ክለቦች ባለፈው ዓመት በአውሮፓ ባሳዩት አስደናቂ ብቃት ምክንያት፣ በዚህ የውድድር ዘመን ክብረ ወሰን የሆነ ዘጠኝ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በአውሮፓ ውድድሮች ላይ ይሳተፋሉ። አርሰናል፣ አስቶንቪላ፣ ሊቨርፑል፣ ማንቸስተር ሲቲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ በሻምፒዮንስ ሊግ የሚወዳደሩ ሲሆን፣ በርንማውዝ፣ ሰንደርላንድ እና ክሪስታል ፓላስ በዩሮፓ ሊግ እንዲሁም ብራይተን በኮንፈረንስ ሊግ አገራቸውን ይወክላሉ። የሊጉ አስተዳደር የክለቦችን የፋይናንስ ወጪ የሚቆጣጠር አዲስ የወጪ ገደብ (Squad Cost Ratio) መመሪያን ተግባራዊ አድርጓል። በዚህም መሠረት ክለቦች ለተጫዋቾች ደሞዝ እና ለዝውውር የሚያወጡት ጠቅላላ ወጪ ከገቢያቸው 85 በመቶ እንዳይበልጥ ተወስኗል። ህጉን የሚጥሱ ክለቦችም የነጥብ ቅነሳ ቅጣት ይገጥማቸዋል። የጨዋታ ፍጥነትን ለመጨመርና ሰዓት ማባከንን ለመግታት በርካታ አዳዲስ የዳኝነት ህጎች በይፋ ስራ ላይ ይውላሉ። በእጅ ውርወራ (Throw-in) እና በመልስ ምት (Goal-kick) ላይ ሰዓት ለሚያባክኑ ተጫዋቾች ዳኛው አምስት ሴኮንድ የሚቆጥር ሲሆን፣ ጊዜ ካለፈ እጅ ውርወራው ለተቃራኒ ቡድን ይሰጣል፤ የመልስ ምት ላይ ከሆነ ደግሞ የተቃራኒ ቡድን የማዕዘን ምት ያገኛል። ሌላው ሰዓት ማባከንን ለመቆጣጠር የወጣው ህግ ተጫዋቾች ታክመው ከወጡ በኋላ ወደ ሜዳ ለመመለስ ቢያንስ አንድ ደቂቃ ውጭ እንዲጠብቁ የሚያስገድደው ደንብ ነው። በተጨማሪም ተጫዋቾች በሚቀየሩበት ወቅት ከሜዳ ለመውጣት የ10 ሴከንድ ገደብ የተጣለባቸው ሲሆን፣ ይሁንና ጊዜው ካለፈ ተቀያሪው መግባት የሚችለው ጨዋታው በሚቀጥለው ጊዜ ሲቆም ብቻ ይሆናል። በዚህ የውድድር ዘመን የቪዲዮ ረዳት ዳኛ (VAR) ውሳኔዎችን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ ትልቅ ማሻሻያ ተደርጓል። አንድ ተጫዋች በሁለተኛ ቢጫ ካርድ ከሜዳ ሲሰናበት አጠራጣሪ ከሆነ ቫር ጣልቃ የመግባት ስልጣን ተሰጥቶታል፤ እንዲሁም በጨዋታ ወቅት በቫር እና በሜዳ ላይ ዳኛው መካከል የሚደረጉ የድምፅ ውይይቶች በሊጉ የጨዋታ ማዕከል በኩል ለደጋፊዎች በቀጥታ ይፋ ይደረጋሉ። በአጠቃላይ፣ የዘንድሮው የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ከአዳዲስ የህግ ለውጦች፣ ከከፍተኛ የዝውውር ወጪዎች እና አዳዲስ የአሰልጣኞች ሹመት ጋር ተያይዞ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረትን ስቧል። አርሰናል የዋንጫ ክብሩን ለማስጠበቅ፣ ማንቸስተር ሲቲ ያለ ፔፕ ጋርዲዮላ አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር፣ እንዲሁም አዳዲስ አሰልጣኞችና ክለቦች ህልማቸውን ለማሳካት የሚያደርጉት ፍልሚያ የእግር ኳስ አፍቃሪያን እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ የሚዘልቅ አስደሳች እና አጓጊ የእግር ኳስ ጊዜን እንደሚያሳልፉ አያጠራጥርም።
ቡሄ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ምስረታ ታሪካዊ ቁርኝት
Aug 19, 2026 825
በሙሴ መለሰ ዛሬ ነሐሴ 13 ቀን የቡሄ በዓል በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ ባለበት በዚህ ዕለት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አጀማመሩንና ምስረታውን ከዚህ በዓል ጋር ያለውን የጠበቀ ትስስር ወደ ኋላ መለስ ብሎ የሚታወስበት ነው። የክለቡ ምስረታና የቡሄ በዓል (የሆያ ሆዬ ጨዋታ) ቀጥተኛና የማይነጠል ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፣ ክለቡ በመስረታው ወቅት የነበረበትን የፋይናንስ እጥረት ቀርፎ የመጀመሪያውን ማሊያ ለመግዛት የበቃው በዚህ ዕለት በተሰበሰበ የሙልሙል ዳቦ ሽያጭ ነበር። የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድን መጀመሪያ ሲጠነሰስ በጆርጅ ዱካስና በአየለ አትናሽ አማካኝነት የነበረ ቢሆንም፣ ክለቡን በይፋ አደራጅቶ ለማቋቋም ግን የግድ የፋይናንስ አቅም ወይም ገንዘብ ያስፈልግ ነበር። ሆኖም ግን በሃገር ፍቅር ስሜት የተነሱት ዘጠኙ ወጣቶች ማለትም አየለ አትናሽ፣ ጆርጅ ዱካስ፣ ዮሐንስ ጥላሁን፣ ገብረመድህን ተፈሪ፣ ተፈራ ገብረእግዚአብሔር፣ ዓለማየሁ እጅጉ፣ መኮንን ደምሴ፣ አስፋው ያዕቆብ እና ክልቱ አያኖ ክለቡን በሚመሰርቱበት ወቅት ቤሳ ቤስቲን እንኳ ኪሳቸው ውስጥ ስላልነበራቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ተሰብስበው በሰፊው ተወያዩ። በዚህ የውይይት ወቅት ነው ገንዘብ ለማግኘትና የክለቡን መመስረት እውን ለማድረግ የቡሄ ቀን እጅግ መልካምና ትልቅ አጋጣሚ መሆኑን የተረዱት። ዘጠኙ ወጣቶች በአንድ ድምፅ ተስማምተው በታሪካዊው የቡሄ ዕለት ማለትም ነሐሴ 13 ቀን 1927 ዓ.ም. በጋራ በመሆን ቡሄ ጨፍረው (ሆያ ሆዬ ብለው) በሚያገኙት ማናቸውም ነገር የክለቡን የመጀመሪያ ማሊያ ለመግዛት ቁርጥ የሆነ ውሳኔ ላይ ደረሱ። በዚያን ጊዜ የነበረው የባህል ልማድ አሁን ካለው የተለየ በመሆኑ፣ ቡሄ ሲጨፈር የሚሰጠው ጥሬ ገንዘብ ሳይሆን ሙልሙል ዳቦ ነበር። በመሆኑም ዘጠኙ ተጫዋቾችና መስራቾች ቀደም ሲል ከሚጨፍሩበትና ለምደውት ከነበረው አካባቢ ራቅ ብለው በመንቀሳቀስ በየቤቱ በር እያንኳኩ በደመቀ ሁኔታ ጨፈሩ፤ በዚህም ጥረታቸው በርካታ ቁጥር ያለው የሙልሙል ዳቦ በአንድነት ማሰባሰብ ቻሉ ታሪካዊውን ስራ ሰሩ። ይሁን እንጂ የተሰበሰበውን ይህንን በርካታ ዳቦ ወደ ጥሬ ገንዘብ ለመቀየር አዲስ አበባ ውስጥ ወደሚገኘው ሰራተኛ ሰፈር ለሚገኙ ወዛደሮች ለመሸጥ ዳቦውን በከረጢት ይዘው ጉዟቸውን ጀመሩ። በዚህ የጉዞ መስመር ላይ ሳሉ ግን ያልተጠበቀ ፈተና ገጠማቸው፤ በመንገድ ላይ ያገኟቸው “ዱርዬዎች” ከተሰበሰበው ዳቦ ላይ የተወሰነውን ነጠቋቸው። ወጣቶቹ ተስፋ ሳይቆርጡ ጉዟቸውን በመቀጠል የተረፈውን ዳቦ ለሰራተኛ ሰፈሩ ወዛደሮች በመሸጥ ማሊያ መግዣ የሚሆን ጥሬ ገንዘብ በእጃቸው አስገቡ። ከዳቦው ሽያጭ የተገኘችው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን በወቅቱ መገበያያ በትክክል ሁለት ጠገራ ብር ነበረች። የክለባችው የመጀመሪያ መለያ ቡናና ነጭ ነበር። ቡናና ነጭ መሊያን የገዙት ግን ፈልገው አልነበረም በቂ ገንዘብ ስላልነበራቸው በሁለት ጠገራ ብር ከፒያሳ «ግሪካዊ አውግስታስ ዱስ» ከተባለ ሱቅ በርካሽ ስላገኙት ነበር። ይህ በቡሄ ዕለት የተጀመረው ታሪካዊ የማሊያ ግዢ በኋላ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በታህሣሥ ወር 1928 ዓ.ም. በይፋ ተመሠረተ። ክለቡ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለብ በመሆን ታሪካዊ ማዕረግንና ቀዳሚነትን ተቀዳጀ። በ1928 ዓ.ም. በይፋ የተመሰረተው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በታሪኩ የመጀመሪያውን የሜዳ ጨዋታ ያደረገው ከ"አራራት አርመን" ቡድን ጋር ነበር። በዚሁ ታሪካዊ የመጀመሪያ ጨዋታው ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚውን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። በዕለቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጠንካራ ተፎካካሪ ከነበረው የ"አራራት አርመን" ቡድን ጋር ለመጫወት ወደ ሜዳ ሲያመራ፣ አስቀድመው ከተመረጡትና ቡድኑን ካደራጁት ተጫዋቾች መካከል አንዱ ባልታወቀ ምክንያት ሳይመጣ ቀረ። በዚህ ድንገተኛ መቅረት ምክንያት ቡድኑ በሰው ጎደሎ ለመጫወት በተገደደበት ወሳኝ ሰዓት፣ መስራቾቹ በሜዳው አቅራቢያ መንገድ ላይ ሲጫወት ያገኙትን አንድ ታዳጊ ወጣት ተመለከቱ። ይህ ታዳጊ በወቅቱ ገና የ14 ዓመት ዕድሜ የነበረውና በኋላ ላይ የኢትዮጵያ ስፖርት ባልደረባ የሆነው ይድነቃቸው ተሰማ ነበር። ወጣቶቹም ያለ ምንም ቅድመ ዝግጅት ቡድኑን እንዲሞላ ድንገት ጋበዙት፤ እርሱም የቀረበለትን ጥሪ በደስታ ተቀብሎ በአጋጣሚ ወደ ሜዳ ገባ። ያለ ምንም ልምምድና ዝግጅት በድንገት የተሰለፈው ይድነቃቸው ተሰማ፣ በሜዳ ላይ ያሳየው አስደናቂ ችሎታና ቅልጥፍና ሁሉንም ያስገረመ ነበር። ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያውን ታሪካዊ ጨዋታ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ፣ ለክለቡ የመጀመሪያውን ድል ያስገኙትን ሁለቱንም ታሪካዊ የማሸነፊያ ግቦች ከመረብ ያሳረፈው ይኸው መንገድ ላይ ተገኝቶ በድንገት የተሰለፈው ታዳጊ ይድነቃቸው ነበር። ይህ ብቃት ገና በታዳጊነቱ በክለቡ ውስጥ ያለውን የማይተካ ቦታ ከማረጋገጡም በላይ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስን የድል ጉዞ በደመቀ ሁኔታ እንዲጀመር አድርጓል። ቡሄ በዓል እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ያላቸው ታሪካዊ ቁርኝት የክለቡን ጥልቅ ህዝባዊና ባህላዊ መሰረት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ህያው ምስክር ነው። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቀዳሚ ፋና ወጊ የሆነው ይህ ታላቅ ክለብ፣ በታሪካዊቷ የነሐሴ 13 ቀን የቡሄ ዕለት የመስራቾቹ የ"ሆያ ሆዬ" ጨዋታና ከተሰበሰበው ሙልሙል ዳቦ ሽያጭ ባገኟት ሁለት ጠገራ ብር የመጀመሪያውን ቡኒና ነጭ ማሊያ መግዛቱ፣ ክለቡ ከህዝብ ማህፀን የወጣ የህዝብ ሀብት መሆኑን ያረጋግጣል። ይህ ከባህልና ከትውፊት ጋር የተቆራኘ አስደናቂ አጀማመር፣ ከጊዜ በኋላ በ1928 ዓ.ም. ለይፋዊ ምስረታው በር ከፋች ከመሆኑም በላይ፣ በታሪካዊው የመጀመሪያ ጨዋታ ላይ እንደ ይድነቃቸው ተሰማ ያሉ የአፍሪካ እግር ኳስ ታላላቅ መሪዎችና ድንቅ ተሰጥኦዎች እንዲፈጠሩ መሰረት የጣለ የኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ነው።
ትንታኔዎች
የስንዴ አብዮት፦ የኢትዮጵያ ማንሰራራት አብነት
Sep 6, 2026 430
ኢትዮጵያ ዓመታዊ የስንዴ ፍላጎቷ ከ107 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ነው። ይህንን ፍላጎት ለማሟላት ለዓመታት ከ700 ሚሊዮን ዶላር እስከ 1 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ውድ የውጭ ምንዛሬ ለስንዴ ግዢ ስታወጣ ቆይታለች። ከዚህ ቀደም ሀገሪቱ ከዓመታዊ ፍላጎቷ መሸፈን የምትችለው ከ25 እስከ 30 በመቶ የሚሆነውን ብቻ ሲሆን፣ ቀሪውን በውጭ ግዢ ትሸፍን ነበር። በተለይም የዩክሬንና የሩሲያ ጦርነት በዓለም አቀፍ ደረጃ 30 በመቶ የሚሆነውን የስንዴ አቅርቦት በማወኩ ኢትዮጵያ ከባድ የአቅርቦት ፈተና ውስጥ እንድትገባ አድርጓት ነበር። ይህንን የረጅም ጊዜ ተግዳሮት በዘላቂነት ለመቅረፍ መንግሥት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን በስፋት በመተግበር፣አሲዳማ መሬቶችን በኖራ በማከም እና ረግረጋማ ቦታዎችን በቴክኖሎጂ በማድረቅ ታሪካዊ ለውጥ ለማምጣት እርምጃዎችን ወስዷል። በኩታ ገጠም እርሻና በዘመናዊ ማሽነሪዎች አጠቃቀም የታጀበው ይህ የልማት አብዮት ፍሬ አፍርቶ፣ ኢትዮጵያ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ከውጭ የምታስገባውን የንግድ ስንዴ ሙሉ በሙሉ አቁማለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በስንዴ ልማት የተመዘገበው ስኬት ከውጭ ማስገባትን ማቆም ላይ ብቻ ሳይወሰን፣ ሀገሪቱ ወደ ውጭ መላክ (ኤክስፖርት ማድረግ) የሚያስችል አቅም እንዳላት ያሳየ መሆኑን አመልክተዋል። በዚህም መሠረት የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን በይፋ የስንዴ ኤክስፖርት የተጀመረ ሲሆን፣ ለዚህ ስኬታማነት የተለያዩ ክልሎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል። ብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚና የኤክስፖርት ኮሚቴ ሀገሪቱ የሀገር ውስጥ ፍጆታዋን ሸፍና 32 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችል አቅም እንዳላት አረጋግጦ፣የ2.9 ሚሊዮን ኩንታል የውል ስምምነቶች ከረድኤትና ከሀገር ውስጥ ድርጅቶች ጋር ተፈራርሟል። ከሀገር ውስጥ አቅርቦት ባሻገር ኢትዮጵያ በ2015 ዓ.ም ለኬንያ ስንዴ ለመላክ ስምምነት የፈረመች ሲሆን፣ ጅቡቲም ከኢትዮጵያ ስንዴ መግዛት እንደምትፈልግ ገልጻ ከኢትዮጵያ የስንዴ ልማት ብዙ ተሞክሮ እንደምትወስድ አመላክታለች። የአፍሪካ ልማት ባንክ ስንዴ ከውጭ እንደማታስገባ እና ምርቷን ለጎረቤት ሀገራት ማስተላለፍ መጀመሯን በማድነቅ ለአህጉሪቱ እንደ ትልቅ የዕድገት ተሞክሮ አቅርቧል። የአሜሪካ የውጭ ግብርና ቢሮ ሪፖርቶችም በኢትዮጵያ የስንዴ ምርት ዘርፍ ትልቅ እመርታ እያሳየ መምጣቱን ጠቅሰው፣መንግሥት የመስኖ ልማትና የግብርና ኤክስቴንሽን ድጋፍ በማጠናከሩ ሀገሪቱ ከፍተኛ ምርት ማምረቷን አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ዓመታዊ የስንዴ ምርት ከ290 እስከ 340 ሚሊዮን ኩንታል (ከ29 እስከ 34 ሚሊዮን ቶን) በላይ መድረሱ ኢትዮጵያን በአፍሪካ አህጉር ቀዳሚ የስንዴ አምራች ሀገር አድርጓታል። የስንዴ ልማቱ አርሶ አደሩን ከቀድሞው ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ አላቆ፣ በኩታ ገጠም እርሻና በሜካናይዜሽን ታግዞ ወደ ሰፋፊ የንግድ ምርት እንዲገባ አስችሏል። የተሻሻሉ የስንዴ የሰብል ዝርያዎች መለቀቃቸው ለዚህ ውጤት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን፣ የምርት አቅርቦት ሰንሰለቱን ማዘመን በቀጣይነት በትኩረት እየተሠራበት ይገኛል። በምርት አቅም እና በኩታ ገጠም እርሻ የተመዘገቡት እነዚህ ሰፊ ስኬቶች፣ ሀገሪቱ በኢኮኖሚ አቅም እያደረገችው ያለውን ሁለገብ ማንሰራራት በግልጽ የሚያሳዩ አብነቶች ናቸው። ይህ ትልቅ ለውጥ ኢትዮጵያ ከድህነትና ከዕርዳታ ጥገኝነት ወጥታ የምግብ ሉዓላዊነቷን ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን፣ ለሌሎች አፍሪካ ሀገራትም ተስፋ የሚሰጥ አህጉራዊ አርዓያ መሆን መቻሏን አስመስክሯል። ይህ የምርት እመርታ በግብርናው ብቻ ሳይሆን፣ አጠቃላይ የሀገሪቱን ማንሰራራት የሚያረጋግጥ ትልቅ ምዕራፍ ነው። ለዘመናት በውጭ ዕርዳታና በለጋሾች ላይ ተወሰና የነበረችው ኢትዮጵያ፣ዛሬ በራሷ አቅም በመሥራት አህጉራዊ አርዓያ መሆን መቻሏ ትልቅ ስኬት ነው። የኢኮኖሚ ነፃነት እና የሉዓላዊነት ማዕቀፍን በማረጋገጥ ረገድም የስንዴ አብዮቱ የሀገርን አቅም የሚያሳይ ተምሳሌት ሆኗል። በመሆኑም በስንዴ ልማት የተገኘው ይህ ድል የግብርና ዘርፍ ስኬት ብቻ አይደለም፤ ኢትዮጵያውያን በቁርጠኝነትና በትጋት ከሠሩ ሀገርን ማሻገር እንደሚችሉ በተግባር ያረጋገጡበት ታላቅ የሀገር የማንሰራራት ማሳያ ነው።
የቡና ወጪ ንግድ እድገት - የኢትዮጵያ እመርታ አንዱ ማሳያ
Sep 5, 2026 326
ገና ወደ ውስጥ ሲገቡ ለምለም ቄጠማ በተጎዘጎዘበት ቤት እና ትኩስ በተቆላ ቡና ከደማቅ ፈገግታ ጋር አቀባበል ታደርጋለች። የቡናው ሽታ ደግሞ ልዩ መዐዛ አለው። አለምነሽ ሀብቱ ወደ ከተማ ከገባች በኋላ ድሮም የምትወደውን ቡና የሰርክ ስራዋ የእለት መተዳደሪያዋ አድርጋዋለች። ቡና ትወዳለች የአዘገጃጀት ድምቀቷንም ሌሎች ይወዱላታል። እሷ የምታዘጋጀውን የጀበና ቡና ለመጠጣት የመጣ ደንበኛዋ አትርፎ እንደወጣ እንዲሰማው የማድረግ ተሰጥኦ አላት። ቡና ትወዳለች ትጠጣለች ታጠጣለች ። እንደሷ ሁሉ ቡና ለኛ ለኢትዮጵያውያን አብሮን የሚውል፣ የሚያመሽ በብዙዎቻችን ቤት በቋሚነት የማይጠፋ ማህበራዊ መገናኛችን መመካከሪያችንም ጭምር ነው። በቡና ምርት በርካታ መሬትን ሸፍና ብዙ አርሶ አደሮችን እያሳተፈች የወጪ ንግዷን ለማሳደግ የምትጥረው ኢትዮጵያ ደግሞ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የምታገኝበት ዋንኛ የግብርና ኢኮኖሚው የጀርባ አጥንትም ነው። ባለፉት ዓመታት የቡና ምርትና ምርታማነት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የሀገሪቱን የወጪ ንግድ ድርሻም እያሳደገ መምጣቱን የተለያዩ መረጃዎች እያሳዩ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄ ማብራሪያ ሲሰጡ ለቡና ልማት የተሰጠው ትኩረት ኢትዮጵያን በአለም ሶስተኛዋ ቡና ላኪ ሀገር እንድትሆን ማስቻሉን ማንሳታቸው ይታወሳል። በተጠናቀቀው በጀት ዓመትም ከቡና ወጪ ንግድ የተገኘው ከ3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ ወደ ውጭ ከላከቻቸው ምርቶች ከፍተኛው እንደነበረም አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ከብራዚልና ከኮሎምቢያ በመቀጠል በዓለም 3ኛዋ ትልቋ የቡና ላኪ ሀገር መሆኗን እና በአፍሪካም ቀዳሚ ደረጃ ላይ መቀመጧን ገልጸዋል። የኢትዮጵያን የሀገር ውስጥ የቡና ፍጆታ ከመቻል አልፈን ለውጭ ገበያ በማቅረብ የመጣው ለውጥ የሀገራዊ የሪፎርሙ ስኬት መገለጫ ነው ማለታቸውም ይታወሳል። ይህ የአንድ ዓመት ምርት እንግዲህ ኢትዮጵያ ባለፉት 17 አመታት ቡናን ወደ ውጭ በመላክ ካገኘችው 3 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ጠቅላላ ገቢ ጋር ሲነጻጸር አስደማሚ ስኬት መሆኑ አያጠራጥርም። አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ለቡና ኤክስፖርት እድገት ስኬት አስተዋጽኦ ማበርከቱን በወቅቱ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቡናን ካልተከልን ፤ ካልተንከባከብን ፤ካልለቀምን፤ ካላጠብን፤ካላሸግንና ካላጓጓዝን ይህ ውጤት ሊመጣ አይችልም ብለውም ነበር። ኢትዮጵያ የአረቢካ ቡና መገኛ እንደመሆኗ የምርቱን እድገትና ዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ተፈላጊነቱን ለማሳደግ እየተከናወኑ ባሉ ተከታታይ ስራዎች ተጨባጭ ውጤቶች ተገኝተዋል። ባለፉት ተከታታይ ዓመታት የተከናወነ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በሌሎች ኢኮኖሚያዊ፣ አካባቢያዊና የተፈጥሮ ሥነ-ምህዳራዊ ግዙፍ አበርክቶው እንዳለ ሆኖ በቡና ምርት እድገት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ለዚህ ማሳያው ደግሞ መርሃ-ግብሩ ሲጀመር በ2011 ዓ.ም. ስድስት መቶ ሺህ ችግኝ የተተከለ ሲሆን ዓመታዊ ምርቱም 5 መቶ ሺህ ሜትሪክ ቶን ነበረ። በወቅቱ የተገኘው የውጭ ምንዛሪም 738 ሚሊዮን ዶላር ነበር። ይሄ ትኩረት በመቀጠሉም የቡና ችግኝ የመትከሉ ስራ አድጎ በ2017 ዓ.ም. ላይ 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን በዛው ዓመት 2 ነጥብ 65 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ማግኘት ተችሏል። ከላይ እንደተገለጸው የ2018 የቡና ወጪ ንግድ ገቢ 3 ነጥብ 1 መድረሱ ለዘርፉ የተሰጠውን ትኩረት እና የተመዘገበውን እመርታ የሚያሳይ ነው። ለዓመታት በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የቆየው የቡና ወጪ ንግድ ገቢ በአጭር ጊዜ መለወጥ እና ኢትዮጵያ ወደ ተለያዩ ሃገራት ከምትልካቸው የግብርና ምርቶች ከፍተኛውን ድርሻ ይዞ መቀጠሉ ለዘርፉ ለተሰጠው ትኩረት እና ለተገኘው ውጤት አንዱ መገለጫም ነው። የኢትዮጵያ ቡና በዓለም ገበያ ላይ ተፈላጊነቱ በየጊዜው እየጨመረም ይገኛል። ጀርመን፣ አሜሪካ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ጃፓን፣ ቤልጂየም እና ደቡብ ኮሪያ ከቀዳሚዎቹ የኢትዮጵያ ቡና ገዢዎች መካከል የሚጠቀሱ ሲሆን በቻይና እና በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የቡና ፍጆታና የመጠጣት ባህል በፍጥነት ማደጉ ለኢትዮጵያ አዳዲስ የገበያ እድሎችን ፈጥሯል። ይህ የኢትዮጵያ የእመርታ ጉዞ በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል ብልጽግናዋንም የምታረጋግጥ የዳበረ ኢኮኖሚ ያላትና የበለጠ ጠንካራ ሀገርነቷን የምታስቀጥልበት አዲስ ምዕራፍም ነው።
ለኢትዮጵያ የቤት ልማት አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ስምምነት
Sep 4, 2026 326
የኢትዮጵያ የከተሞች ዕድገት ፈጣን እየሆነ በመምጣቱ እና የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ በመሄዱ፣የዜጎችን የቤት ባለቤትነትን ጥያቄ በዘላቂነት መመለስ የመንግሥት አንዱ ዋና የትኩረት አቅጣጫ ሆኗል። ባለፉት ዓመታት የነበረው የቤት አቅርቦት በመንግሥት ትከሻ ላይ ብቻ የወደቀ በመሆኑ፣ ካለው ሰፊ የሕዝብ ፍላጎት ጋር አብሮ ለመሄድ ፈታኝ ሆኖ ቆይቷል። ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት መንግሥት አዲስ የቤት ልማት ፖሊሲ ቀርጾ በካቢኔ ማጽደቁ ይታወቃል። ፖሊሲው የዕድገቱን ፍጥነት እና የከተሞችን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ ነው። በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወኑ ያሉ የኮንስትራክሽንና የከተማ ልማት ሥራዎች ለዚህ ሰፊ ራዕይ ግልጽ ማሳያዎች ናቸው። በዚህ ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፤ መንግሥት ባለፉት አምስት ዓመታት ብቻ በመላ ሀገሪቱ 1.2 ሚሊዮን ቤቶችን መገንባት መቻሉን አስታውሰዋል። ይህንኑ ስኬት መሠረት በማድረግ፣ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት 1.5 ሚሊዮን አዳዲስ ተመጣጣኝ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት መንግሥት አጠቃላይ ዝግጅት አድርጎ እየሠራ እንደሚገኝ አመልክተዋል። አሁን ላይ አዲስ የግንባታ ቴክኖሎጂንና የረጅም ጊዜ የቤት ብድር ሥርዓትን በማስተዋወቅ የዜጎችን የቤት ባለቤትነት ጥያቄ በዘላቂነት ለመመለስ እየተሠራ መሆኑንም ጠቅሰዋል። አዲሱ የቤት ልማት ፖሊሲ ተቀርጾ በካቢኔ መጽደቁንና በሁሉም ክልሎች የተቀናጀ ንቅናቄ መጀመሩን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ግንባታው በመንግሥት በጀት ብቻ የሚወሰን ሳይሆን፣ የግሉ ዘርፍ እንዲሁም የመንግሥትና የግል አጋርነት መዋቅሮችን በስፋት መጠቀም እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የዜጎችን የመግዛት አቅም ያገናዘበና ፍላጎታቸውን የሚያስተናግድ አዲስ የፋይናንስ አሠራር መፈጠሩን ጠቅሰው፤ሰዎች ቤት በቀጥታ መግዛት ካልቻሉ በመንግሥት በሚመቻቸው አዲስ የሞርጌጅ ሥርዓት አማካኝነት ከገቢያቸው ላይ እየከፈሉ በረጅም ጊዜ ሂደት የቤት ባለቤት የሚሆኑበት ዕድል ይፈጠራል ብለዋል። ይህ ግብ የዜጎችን የቤት ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ የግሉን ዘርፍ በስፋት በማሳተፍ የሚሳካ መሆኑ በግልጽ ተቀምጧል። የሞርጌጅ ሥርዓት የቤት ፍላጎትን ለማሟላት የቀረበ ሌላኛው አማራጭ ሆኗል። የቤት መግዣ ብድር ሥርዓት (ሞርጌጅ) ማለት አንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ለመግዛት የሚያስፈልገውን ገንዘብ ከባንክ በብድር አግኝቶ፣ ያንን የተበደረውን ገንዘብ ከነወለዱ በረጅም ዓመታት መልሶ የሚከፍልበት የፋይናንስ አሠራር ነው። ይህ አሠራር አቅማቸው ውስን ለሆኑ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች በወር በወር እየከፈሉ የቤት ባለቤት የመሆን ልዩ ዕድል ይፈጥራል። የከፍተኛ የቤት ኪራይ ወጪን በማስቀረት ዜጎች በየወሩ የሚከፍሉት ገንዘብ በራሳቸው ንብረት ላይ የሚደረግ ጠቃሚ ኢንቨስትመንት እንዲሆን ያደርጋል። ይህንን ታላቅ ራዕይ ከግብ ለማድረስ በዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መካከል በሀገሪቱ የመጀመሪያው የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችል ታሪካዊ ስምምነት ተፈጽሟል። በ100 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ካፒታል የተቋቋመው እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋፅዖ የሚያደርግበት ይህ ተቋም፤ በባንክ ዘርፉ ውስጥ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠንን የሚቀርፍ እና በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ የሚሆን የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስን የሚያስገኝ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው ገልጸዋል። ይህ አጋርነት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገነቡና የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለማቅረብ እንዲሁም በፋይናንስ ሥርዓታችን ውስጥ የግል ዘርፉን ተሳትፎ ለማስፋት የተቀመጠውን ግብ የሚያሳካ ወሳኝ እርምጃ መሆኑንም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ፈጣን፣ ጠንካራ እና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ መገንባቷን እንደምትቀጥልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ማክታር ዲዮፕ በሰጡት አስተያየት፣ ይህ አጋርነት በኢትዮጵያ የከተሞች ልማት ላይ የግል ባለሀብቶች በስፋት እንዲሳተፉ ትልቅ ምቹ ምህዳር እንደሚፈጥር ገልጸዋል። ጠንካራ የቤት ፋይናንስ ገበያ የዜጎችን ሕይወት ለማሻሻል እና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለመደገፍ ቁልፍ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳዩ እንዲጀመር እንዲሁም ሂደቱ ላይ ክትትል በማድረግ እያከናወኑት ላለው ሥራና አመራር ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በዚህ የፋይናንስ ማዕቀፍ አማካኝነት ዜጎች ሙሉ የቤት መግዣ ገንዘብ እስኪኖራቸው ሳይጠብቁ በባንክ ብድር የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ይደረጋል።ግንባታው በመንግሥት በጀት ብቻ ሳይሆን በመንግሥት፣ በግል ዘርፍ፣ እንዲሁም በመንግሥትና በግል አጋርነት (PPP) ይከናወናል። የሞርጌጅ ፋይናንስ ሥርዓቱ የዜጎችን ማህበራዊ ዋስትና በማረጋገጥ የባለቤትነት ስሜት ከመፍጠር አኳያ ያለው ፋይዳ ቁልፍ የሚባል ነው። መንግሥት ብቻውን ሊያከናውነው የሚችለውን ግዙፍ የልማት ጫና፣የግሉን ዘርፍ እና ዓለም አቀፍ አጋሮችን በማስተባበር በጋራ መወጣት እንደሚቻል የዛሬው ስምምነት ግልጽ ማሳያ ነው። የ100 ቢሊዮን ብር ካፒታል ፈንድ እና የ1.5 ሚሊዮን ቤቶች ዕቅድ እውን መሆን፣ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ጉዞ የሚያፋጥንና ሁሉንም ዜጎች አካታች የልማት ባለቤት የሚያደርግ ታሪካዊ ምዕራፍ ነው።
የኮሪደር ልማት እና የነገዋ ኢትዮጵያ
Sep 4, 2026 237
በኢትዮጵያ አሁን ላይ በተለያዩ መስኮች እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች መጻኢውን ጊዜ ብሩህ ለማድረግ መሰረት የሚጥሉ ናቸው። ከእነዚህ ስራዎች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው የሀገሪቱን ከተሞች ገጽታና የነዋሪዎቿን የኑሮ ዘይቤ በከፍተኛ ደረጃ እየቀየረ ያለው የኮሪደር ልማት መርሃ ግብር ነው። ይህ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የኮሪደር ልማት ከተሞችን ለኑሮ ምቹ፣ ንጹህና ስልጡን በማድረግ ትልቅ ምዕራፍ ከፍቷል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ያስመዘገበው ስኬትና የፈጠረው አርአያነት አሁን ላይ አዲስ አበባን አልፎ በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች ተግባራዊ ተደርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት እንደገለጹት፣ የኮሪደር ልማት ከከተማ ውበትና ገጽታ ባለፈ የሀገሪቱን የዕድገት አቅጣጫ በከፍተኛ ደረጃ እየቀየረ ያለ እና የነገዋን ሀገር ዛሬ ላይ የመቅረጽ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው። በኮሪደር ልማቱ ለእግረኛ እና ለአካል ጉዳተኞች ፈታኝ የነበሩ መንገዶች ዛሬ ሰፊና ጥራት ባላቸው የኮንክሪት ንጣፎችና የብስክሌት መስመሮች ተተክተዋል። በከተሞች የሚገኙ የመዝናኛ ፓርኮች፣ የማረፊያ ስፍራዎች እንዲሁም ደረጃቸውን የጠበቁ ቦታዎች የዜጎችን ማኅበራዊና ሰብአዊ ክብር ከፍ ያደረጉ ሲሆን፤ እነዚህ ጥራት ያላቸው መሠረተ-ልማቶች የነገውን ጤናማ እና ማህበራዊ ፍትሕ የሰፈነበት ማህበረሰብ ለመፍጠር የተጣሉ ጠንካራ መሠረቶች ናቸው። የኮሪደር ልማት የከተሞችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ወደ ዘመናዊነት በመቀየር ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። በዘመናዊ የጎዳና ላይ መብራቶችና የደህንነት ካሜራዎች የታገዙ ከተሞች በቀን ብቻ ሳይሆን በሌሊትም የንግድና የኢኮኖሚ ማዕከል እንዲሆኑ በር በመክፈታቸው፣ የ24 ሰዓት የስራ ባህልን በመፍጠር ለአያሌ ወጣቶችና አነስተኛ ነጋዴዎች አዲስ የሥራ ዕድል ፈጥረዋል። በሌላ በኩል፣ ይህ ስትራቴጂካዊ ልማት ኢትዮጵያን ወደ ቋሚ የኮንፈረንስ፣ የንግድ እና የባህል ቱሪዝም መዳረሻነት እየቀየራትም ይገኛል። በተለይም የከተሞችን ማህበራዊ መስተጋብርና የሕዝቡን አንድነት በማጠናከር ረገድ የኮሪደር ልማቱ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ የላቀ ነው። በልማቱ የተፈጠረው የጋራ ትስስር የነገዋን ጠንካራ፣ ሰላማዊና በአብሮነት የታነጸች ሀገር ለመገንባት እንደ ትልቅ ማህበራዊ መሰረት ያገለግላል። የነገዋ ኢትዮጵያ በዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅም ያደገችና አሰራሯ የዘመነ መሆኑን የሚያረጋግጥ ተግባራዊ እርምጃ ከኮሪደር ልማቱ ጋር ተሳስሮ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል። ስራው ከቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር በቅንጅት በማከናወን ዘመናዊ የትራፊክ ቁጥጥር ሥርዓቶች እና የስማርት ከተማ መተግበሪያዎች መሰረተ ልማት አብሮ እየተዘረጋ ይገኛል። በተጨማሪም ከኮሪደር ልማት ጋር እየተከናወነ ያለው መጠነ ሰፊ የአረንጓዴ ስፍራዎች እና የወንዞች ዳርቻ ልማቶች ከተሞች ከአየር ንብረት ለውጥ ስጋትና ሙቀት በመከላከል ለትውልዱ ንጹህና ጽዱ መኖሪያን አካባቢን ለማስረከብና ጤናማ ማህበረሰብ ለመገንባት እያስቻለ ነው። በአጠቃላይ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ከአንድ ከተማ ገጽታ ማሻሻል ባሻገር፣ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ በርካታ ክልል ከተሞች ላይ በመስፋፋት ሀገራዊ ለውጥ ፈጥሯል ማለት ያስችላል። የዚህ ዘርፈ ብዙ የልማት ፍሬ ዛሬ ላይ የኑሮ ዘይቤን እያሻሻለ እንደሚገኘው ሁሉ፣ ለወደፊቱ ትውልድም የኩራት ምንጭ የሆነ ዘላቂ ሀብት ሆኖ ይሸጋገራል። ዛሬ በጥራትና ውብ ሆነው እየተሰሩ ያሉ መንገዶች፣ ዘመናዊ መናፈሻዎች፣ የህጻናት መጫወቻ ስፍራዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያዎች እና የዲጂታል መሰረተ ልማቶች የነገዋ ኢትዮጵያ የበለጸገች፣ ስልጡንና ለኑሮ ምቹ የማድረግ ራዕይን እውን የሚያደርጉ ናቸው።
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና
Jun 17, 2026 12835
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል። የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 22221
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 15255
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 20994
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
መጣጥፍ
የኢትዮጵያ የማዕድን ምርት እመርታ
Aug 21, 2026 1160
በሙሴ መለሰ የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ በአገር በቀል የኢኮኖሚና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ታግዞ፣ ባለፉት ዓመታት የታዩበትን የአሰራርና መዋቅራዊ ችግሮች በመቅረፍ ከፍተኛ የመነቃቃት ምዕራፍ ላይ ይገኛል። ዘርፉ በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት ቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት እንደገለጹት፣ ማዕድን በብዝኃ ዘርፍ የልማት ምልከታችን ውስጥ እና በሀገሪቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ቁልፍ ዘርፍ ሆኖ ይቀጥላል። ባለፉት ሶስት አሥርት ዓመታት ውስጥ የማዕድን ዘርፉ ለአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ያበረከተው አስተዋጽኦ ከ0 ነጥብ 8 በመቶ በታች የነበረ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ግን መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው የላቀ ትኩረት ከፍተኛ መዋቅራዊ ሽግግር እያመጣ ይገኛል። በ2018 በጀት ዓመት ከዘርፉ 5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ተችሏል። ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ92 በመቶ የገቢ ዕድገትና የ27 በመቶ የምርት መጠን ብልጫ ያሳየ ሲሆን፣ ምርቶቹም በዋናነት ወደ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ አሜሪካ፣ ጀርመን እና ቻይና ተልከዋል። በወጪ ንግድ እድገት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው የወርቅ ምርት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስምንት ወራት 22 ነጥብ 5 ቶን ለውጭ ገበያ የቀረበ ሲሆን እስከ ዓመቱ ማብቂያ 32 ቶን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። በባህላዊ መንገድ የሚመረተውን የወርቅ ምርት ለማዘመንም መንግሥት የማጣሪያና ማቀለጫ ፋብሪካዎችን በመገንባት ላይ ይገኛል። የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ከውጭ የሚገቡ ስትራቴጂክ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። በዚህም ለድንጋይ ከሰል ግዢ ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ ማስቀረት የተቻለ ሲሆን፣ የሲሚንቶ ምርትም ባለፉት ስምንት ዓመታት ከነበረበት 8 ሚሊየን ቶን አሁን ላይ በዓመት ወደ 14 ሚሊየን ቶን አድጓል። ሀገሪቱ በየዓመቱ ለማዳበሪያ ግዢ የምታወጣውን 2 ቢሊየን ዶላር ለማስቀረትም የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ተጀምሯል። በተጨማሪም በየዓመቱ ለብረት ምርት ግዢ የሚወጣውን 1 ቢሊየን ዶላር በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የሚያስችል ግዙፍ ፋብሪካ የመገንባት ስምምነት ተፈጽሞ ወደ ስራ ተገብቷል። የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በዘርፉ የተሰማሩ ፕሮጀክቶች ዋጋ 10 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ከለውጡ በፊት ከነበረውና ከ100 ሚሊየን ዶላር የማይበልጡ አነስተኛ ኢንቨስትመንቶች በከፍተኛ ደረጃ የለወጠ ስኬት ነው። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በአፋር ክልል የሚገኘውን ግዙፍ የፖታሽ ክምችት ለማልማት ፈቃድ አግኝቶ ወደ ሥራ ገብቷል። በተጨማሪም ታንታለምን እሴት ጨምሮ ለመላክ ከአሜሪካ ኩባንያ ጋር ድርድር እየተደረገ ሲሆን፣ ለባትሪና ቴክኖሎጂ ወሳኝ የሆኑትን ሊቲየም፣ ኮባልትና ኒኬልን ለማምረት ዝግጅት ተጠናቋል። የኢንቨስትመንት ምህዳሩን ሳቢ ለማድረግ የማዕድን ፈቃድ አሰጣጥ አሰራር ቅድሚያ የመጣን ቅድሚያ ማስተናገድ በሚል መርህ እንዲመራ ተደርጓል። የወጪ ንግድ ኮንትራት ምዝገባና መላኪያ ፈቃዶች፣ እንዲሁም የካዳስተር ሲስተም ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ኤሌክትሮኒክስ አሰራር ተሸጋግረዋል። በ2019 በጀት ዓመት ከዘርፉ 6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት የታቀደ ሲሆን፣ የመንግሥት ስትራቴጂካዊ እቅድ እ.አ.አ. በ2030 የማዕድን ወጪ ንግድ ገቢን ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ በማድረስ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ አምስት ቀዳሚ የማዕድን አምራች ሀገራት ተርታ ማሰለፍ ነው። በዘርፉ እየተካሄደ ያለው መዋቅራዊ ሽግግር ኢትዮጵያ በውጭ ምርቶች ላይ ያላትን ጥገኝነት በመቀነስ ወደ ኢንዱስትሪ መሪነት የምታደርገውን ጉዞ ያፋጥነዋል። የወርቅ፣ የተፈጥሮ ጋዝ፣ የፖታሽ እና የቴክኖሎጂ ማዕድናት በሀገር ውስጥ እሴት ተጨምሮባቸው ለዓለም ገበያ መቅረባቸው ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ የንግድ መድረክ ላይ የሚኖራትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ያረጋግጣል።
የአረቡ ዓለም ከግብፅ ምን አተረፈ?
Aug 19, 2026 923
የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ አካሄድ በታሪካዊ እውነታዎች እና በኢኮኖሚያዊ ትስስር ላይ እየተመሠረተ በመጣበት በአሁኑ ወቅት፣ ጊዜ ያለፈባቸው የጂኦ ፖለቲካዊ የመጠላለፍ አካሄዶች ዋጋ ቢስነትና ጥቅም አልባነት በግልጽ እየታየ ይገኛል። ለብዙ አስርት ዓመታት ግብፅ የዓረብ ሊግን ለራሷ ጠባብ ፍላጎቶች እና ጂኦፖለቲካዊ አጀንዳዎች ማስፈጸሚያነት በሰፊው ስትጠቀምበት ቆይታለች። ሆኖም ይህ ጥቅምና ጉዳትን ብቻ መሰረት ያደረገ ግንኙነት አንድ መሠረታዊ ጥያቄ ያስነሳል፦ ለመሆኑ የዓረቡ ዓለም ከግብፅ በምላሹ ያገኘው ትርፍ ምንድን ነው? ለዚህ ጥያቄ አጭሩ መልስ ምንም የሚል ነው ሲል “What Has the Arab World Gained from Egypt? Why Ethiopia Belongs in the Arab League?” ፀሐፊው እና በፖለቲካና ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ በቋሚነት የሚተነትነው አስተያየት የሚሰጠው ጅብሪል ላሞ በኢዜአ እንግሊዘኛ ገጽ ባሳፈረው ሐተታ ላይ ፣ የግብጽ ፖሊሲዎች እንዲሁም ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀው አምባገነናዊ አስተዳደር የጋራ ጥንካሬን ከመፍጠር ይልቅ የቀጣናውን አለመረጋጋት ማባባሳቸውን ገልጿል። እነዚህ ፖሊሲዎች፣ በምሥራቅ አፍሪካ እና በቀይ ባሕር አካባቢም ውጥረትን እያባባሱ እንደሚገኙ አመልክቷል። እነዚህ አካባቢዎች ለዓረቡ ዓለም የራቁ አይደሉም፤ ይልቁንም ለዓረቡ ዓለም ደኅንነት፣ የባሕር ንግድ፣ የኃይል አቅርቦት እንዲሁም የምግብ ዋስትና እጅግ ወሳኝ እና ስትራቴጂካዊ ማዕከላት ናቸው። የግብፅ ከፋፋይ ቀጣናዊ አካሄድ ከታዩባቸው ጉልህ ማሳያዎች አንዱ በኤርትራ ጉዳይ እና በሰፊው የኢትዮጵያ ግዛት አንድነት ላይ የነበራት ታሪካዊ ጣልቃ ገብነት ነው። ኢትዮጵያን ለማዳከም እና ቀጣናዊ ተፅዕኖዋን ለመግታት በግብጽ ታስበው የተደራጁ ተገንጣይ ኃይሎችን እና ፖለቲካዊ ፕሮጀክቶችን በግልጽ ትደግፍ እንደነበረ ፀሐፊው አውስቷል። ከኢትዮጵያ የኤርትራ መገንጠል በምሥራቅ አፍሪካ ቀውስ የተሞላ ታሪክ ውስጥ አቢይ ክስተት ሲሆን፣ የውጭ ጂኦፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነቶች የሀገራትን እጣ ፈንታ እንዴት እንደሚያናጉ በግልጽ የሚያሳይ ነው። የዲፕሎማሲ ታሪክ እንደሚያስረዳው፣ የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ እና የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ቡትሮስ ቡትሮስ-ጋሊ፣ ኢትዮጵያን ለማዳከም ታስቦ የተዘረጋውን የኤርትራን የመገንጠል ፕሮጀክት በመደገፍና በማፋጠን ረገድ ትልቅ ሚና ነበራቸው። በተጨማሪም ግብጽ በደቡባዊ የቀይ ባህር ቀጣና የምታካሂደው ቀውስ የመፍጠር እንቅስቃሴ፣ ለዓለም አቀፍ የባህር ንግድና ለቀጣናው ደህንነት ቀጥተኛ ስጋት ደቅኗል። በባብ-ኤል-ማንደብ የባሕር ወሽመጥ አካባቢ ውጥረቶችን በመቀስቀስ እና ተላላኪ ታጣቂ ቡድኖችን በማንቀሳቀስ፣ ወሳኝ የሆኑ የባህር መተላለፊያዎችን የጂኦፖለቲካዊ ግጭት መድረክ አድርጋዋለች። ይህም ለጠቅላላው የዓረብ ዓለም የኢነርጂና የምግብ አቅርቦት መሰረት የሆነውን የደህንነት መዋቅር አደጋ ላይ ጥሎታል፤ ሲሉ ጅብሪል ላሞ ያብራራሉ። ጅብሪል ላሞ በጽሑፉ ላይ እንዳሰፈረው፣ የግብፅ ግልጽ የራስ ወዳድነት እንቅስቃሴዎች ቀጣናዊ ውጥረትን የሚፈጥሩ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ወደ ዓረብ ሊግ መቀላቀል ግን ለዓረቡ ዓለም እጅግ ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኝ ለውጥ አምጪ ዕድል ይዞ ይመጣል። በመደመር ፍልስፍና አሳታፊ ማዕቀፍ ሥር፣ ኢትዮጵያ ከማግለል ፖሊሲ ይልቅ የዓረቡን ዓለም ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማስተሳሰር የሚያስችል የላቀ የዲፕሎማሲ አቅም አላት። በዚህም የአፍሪካ ዋነኛ የዲፕሎማሲ ማዕከል እና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ የባለብዙ ወገን ትብብሮችን በመቅረጽ ረገድ ያላትን የካበተ ልምድ ታካፍላለች። የኢትዮጵያ ወደ ዓረብ ሊግ የመቀላቀል ጥረት ጊዜያዊ የፖለቲካ ስሌት ሳይሆን፣ የተፈጥሮ የታሪክ ጥሪ ነው። ከ135 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ፣ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እና ጥልቅ የሥልጣኔ መሠረት ያላት ይህች የቀይ ባሕር ሀገር፣ አባልነቷ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቅ መካከል ስትራቴጂካዊ ድልድይ ይፈጥራል። ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር ያላት ቁርኝት በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት በጋራ ታሪክ፣ ባህል እና የደም ትስስር ላይ የተገነባ ነው። እንደ ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ባሉ የትምህርት ተቋማት፣ የኢትዮጵያ ጥናቶች በታሪክ ደረጃ ከመካከለኛው እና ከቅርብ ምሥራቅ ታሪክ (Near Eastern Studies) ተመድቦ መጠናቱ፤ የኢትዮጵያ ስልጣኔ ከቀጣናው ጋር ያለውን ጥልቅ ታሪካዊ ውህደት የሚያረጋግጥ ሕያው ማሳያ ነው። የባብ-ኤል-ማንደብ የባህር ወሽመጥ በጭራሽ መሰናክል አልነበረም፤ ይልቁንም ንግድን፣ ባህልን እና ማህበረሰቦችን በቀይ ባሕር በኩል ያገናኘ ዋንኛ መተላለፊያ ሆኖ አገልግሏል። ከንጉሥ አብረሃ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ በኢትዮጵያውያን እና በመካከለኛው ምሥራቅ ሕዝቦች መካከል የጋራ የደም ትስስር እንደነበር የሚያረጋግጡ ዘመናዊ የስነ ህይወት( ጄኔቲክስ) ጥናቶች፣ የዚህን ታሪካዊ ቁርኝት እውነተኛነት በግልጽ ያሳያሉ። በቋንቋና በባህል ረገድ የኢትዮጵያ መንግሥት መሠረት ታሪካዊ ትስስር ያለው ነው። የሀገሪቱ የቋንቋና የሥነ-ጽሑፍ ውርስ ከዓረብኛ፣ አራማይክና ዕብራይስጥ ጋር በጽኑ የተሳሰረ ሲሆን፣ ይህም በምሥራቅ አፍሪካና በአረቢያ ልሳነ-ምድር መካከል ያለውን ጥልቅ የጋራ የሥልጣኔ ቁርኝት ያረጋግጣል። ኢትዮጵያ በእስልምና ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ አላት። የመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች ወደ ኢትዮጵያ ተስደው በንጉስ ነጃሺ ከለላ ማግኘታቸው የእስልምናን ህልውና የታደገ ታሪካዊ ክስተት ሲሆን፣ ይህም ሀገሪቱን ከዓረቡ ዓለም ጋር በጽኑ አስተሳስሯታል። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ፣ የዓረብ ሊግን በኢትዮጵያ ላይ እንደ ተቋማዊ ተፅዕኖ ማሳደሪያ መሣሪያ ግብጽ ስትጠቀምበት ቆይታለች። ግብፅ የውጭ ፖሊሲ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ዕድገት፣ የህዳሴውን ግድብም ሆነ የባሕር በር ጥያቄን እንደ ሥጋት በሚያይ ጊዜ ያለፈበት ስሌት ላይ የተመሠረተ ነው። ግብፅ የራሷን የውሃ አቋም በሊጉ ላይ በመጫን፣ ተቋሙ ከኢትዮጵያ ጋር አላስፈላጊ ውጥረት ውስጥ እንዲገባ አድርጋለች። ጅብሪል ላሞ እንዳመለከተው፣ ከግብጽ የአግላይነት ፖሊሲ ይልቅ የዘመኑ ነባራዊ ሁኔታዎች ሙሉ ትብብርን የሚጠይቁ ናቸው። በመደመር መርህ፣ ኢትዮጵያ ለዓረቡ ዓለም ለዘመናት ከቆዩ የጥላቻ መንገዶች በላቀ ሁኔታ የተሻሉ ጥቅሞችን ማቅረብ ትችላለች። እያደገ የመጣው የኢንዱስትሪ እና የአረንጓዴ ኃይል አቅሟ፣ ኢትዮጵያን ለቀይ ባህር ቀጣና የመረጋጋት ምሰሶ አድርጓታል። የመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና የውሃ እጥረት እና የምግብ ዋስትና ሥጋት በተጋረጠበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያ የውሃ ሀበት እና ለም መሬት ለቀጣናው ወሳኝ የግብርና-ኢንዱስትሪ አጋር ያደርጋታል። የዓረብ ሊግ አባል ሀገራት የ21ኛውን ክፍለ ዘመን ብሔረተኝነት በመሻገር፣ የቀይ ባህርን ቀጣና የሥልጣኔ እውነታ መቀበል ይኖርባቸዋል። አረብ ሊግ እንደ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ኮሞሮስ እና ሞሪታኒያ አባል ሀገራት መያዙ፣ ስብስቡ የተለያዩ ቀጣናዊ እውነታዎችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑን ያሳያሉ። የዓረብ ሊግ ሙሉ አባልነት የኢትዮጵያን አፍሪካዊ ማንነት ሳይቀንሰው፣ አህጉሩን ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር የሚያገናኝ ዋነኛ ድልድይ የሚያደርጋት በመሆኑ፤ ሊጉ የኢትዮጵያን አጋርነት በመቀበል ለአዲስ አበባ ተገቢውንና ሕጋዊ ቦታዋን የሚሰጥበት ጊዜ አሁን እንደሆነ በመግለጽ ጅብሪል ላሞ ፅሁፉን ቋጭቷል።