አዲስ አበባ የ"ስማርት ሲቲ" ግንባታ ልምዷን ለቤኒን ሪፐብሊክ አካፍላለች - ኢዜአ አማርኛ
አዲስ አበባ የ"ስማርት ሲቲ" ግንባታ ልምዷን ለቤኒን ሪፐብሊክ አካፍላለች
አዲስ አበባ፤ነሃሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቤኒን ሪፐብሊክ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ኢኖቬሽን እና ፈጠራ ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን ለተመራ የልዑክ ቡድን አዲስ አበባ እየተገበረች ያለውን ስማርት ሲቲ ግንባታ ጋር በተያያዘ ልምድ አካፍለዋል።
ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ቤኒን የጀመረችውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማሳካት በከተማችን ተግብረነው ውጤታማ እየሆነ ያለውን Smart City (ስሉጥ ከተማ) ግንባታን በተመለከት ልምድ ማካፈላቸውን ገልጸዋል።
በተለይም በዋና ዋና ግቦች (Smart Economy, Smart Environment, Smart Governance, Smart Living, Smart Mobility, Smart People) እና ለስኬቶቻችን መሰረት የሆኑት የተቋማት ቅንጅት፣ የህጎችና ደንቦች ትግበራ፣ የሕዝብ ተሳትፎ፣ የመንግሥትና የግል ዘርፍ ቅንጅታዊ ሥራዎችን ለልዑክ ቡድኑ አካፍለናል ነው ያሉት።