በሀገራዊ ምክክር ጉባዔው የአጀንዳ ምክረ-ሃሳቦች ለስራ ቡድኖች መቅረብ ጀመሩ - ኢዜአ አማርኛ
በሀገራዊ ምክክር ጉባዔው የአጀንዳ ምክረ-ሃሳቦች ለስራ ቡድኖች መቅረብ ጀመሩ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ከእያንዳንዱ 500 አባላት ካሉት የሥራ ቡድን በተመረጡ 30 አባላት አማካኝነት አጀንዳዎች ተቀናጅተው መዘጋጀታቸውን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ።
በዚህም መሠረት የተዘጋጁት የምክረ ሐሳብ ሰነዶች ለስምንቱ የሥራ ቡድኖች መቅረብ መጀመራቸውን አመልክቷል።
የተጠናቀሩ የአጀንዳ ሃሳቦች ላይ የመወያየቱ ሂደት በመጪው ሰኞ ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።
ይህ የምክክር ደረጃ በአንድ አጀንዳ ላይ የሚወያዩ 500 ተመካካሪዎች በጉዳዩ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ የመጨረሻ የምክረ ሐሳብ ሰነድ ለማዘጋጀት ጥልቅ ውይይት የሚያካሂዱበት መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ እየተካሄደ ይገኛል።