ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ አታፍ አዲስ አበባ ገቡ
Feb 10, 2026 35
አዲስ አበባ፤የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ አታፍ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በ48ኛው የአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ እየገቡ ነው። የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ አታፍም ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ደኤታ በረኦ ሀሰን አቀባበል አድርገውላቸዋል። 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን፤ ከጉባኤው አስቀድሞ የካቲት 4 እና 5 ቀን የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት 48ኛው መደበኛ ስብሰባ ይካሄዳል። የዘንድሮው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ “ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” የሚል መሪ ሃሳብ ተሰጥቶታል።
ብልፅግና ፓርቲ የኢትዮጵያን የተጽዕኖ አድማስ ለማስፋትና የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት ይሠራል
Feb 10, 2026 60
አዲስ አበባ፤ የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦ ብልፅግና ፓርቲ የኢትዮጵያን የተጽዕኖ አድማስ ለማስፋትና የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት እንደሚሠራ በምርጫ ማኒፊስቶው ማረጋገጡን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ገለጹ፡፡ ብልፅግና ፓርቲ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምርጫ ማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክቱን ይፋ ያደረገ ሲሆን ፓርቲው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወከልበት የምርጫ ምልክቱ የስንዴ ነዶ መሆኑን አስታውቋል። አቶ አደም ፋራህ በዚሁ ወቅት፤ ፓርቲው በ"መደመር" እሳቤ በመመራት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለዘመናት የቆዩ መዋቅራዊ ስብራቶችን በመጠገን፣ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት ሲሠራ ቆይቷል ብለዋል። ፓርቲው ህዝብን በማሳተፍ፣ በጽናትና ቁርጠኝነት ስኬቶችን ሲያረጋግጥ መቆየቱን ጠቅሰው፤ የህዝብ ይሁንታ በማግኘት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውጤታማ ጉዞ ማስቀጠል የሚያስችለውን የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ማኒፊስቶ አዘጋጅቶ ይፋ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡ ማኒፌስቶው ብልፅግና ፓርቲ በመደመር እሳቤ በመመራት እስካሁን ያስመዘገባቸውን ስኬቶች፣ ወቅታዊ ሁኔታዎችንና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በዝርዝር የያዘ መሆንን አብራርተዋል። ማኒፌስቷችን ትናንትን ማከምን፣ ዛሬን በአግባቡ መጠቀምንና ነገን መተንበይን ማዕከል ያደረገ ነው ሲሉም አስታውቀዋል። በማኒፌስቶው ትልቅ ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች መካከል የዲፕሎማሲው ዘርፍ ቀዳሚውን ስፍራ መያዙን ጠቁመው፤ ፓርቲው በቀጣይ አምስት ዓመታት የኢትዮጵያን የተጽዕኖ አድማስ ለማስፋትና የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት እንደሚሰራ በማኒፌስቶው ይፋ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ ከጎረቤትና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት፣ ከብሪክስ አባል ሀገራትና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰራም በማኒፌስቶው መገለጹን አስታውቀዋል፡፡ እንዲሁም በዓለም አቀፍ የኃይል አሰላለፍ ውስጥ የሚዛናዊነት መርህን በመከተል የኢትዮጵያን ተደማጭነት ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ተካትቷል ብለዋል። ብልፅግና ፓርቲ በማኒፌስቶው ይፋ እንዳደረገው፤ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከሀገራቸው ጋር ያላቸውን ትስስር የሚያጠናክሩ አዳዲስ ኢኒሼቲቮችን ተግባራዊ ማድረግና የዜጎችን ክብር ማስጠበቅ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ተመላክቷል፡፡ አባይን በፍትሃዊነት የመጠቀምና አስተማማኝ የባህር በር የማግኘት መብታችንን ለማስከበር የጀመርናቸውን ጥረቶች እንደምናሰፋ በማኒፌስቶው በግልጽ ተቀምጧል ብለዋል፡፡ ለዚህም ሰላማዊ፣ ህጋዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረጉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በማኒፌስቶው ማካተቱን አረጋግጠዋል።
የጤና አገልግሎትን ለማሻሻል የህክምና ግብዓት የተሟላላቸው ጽዱ የጤና ተቋማትን ማስፋት ላይ ትኩረት ተደርጓል
Feb 10, 2026 73
ባህርዳር ፤የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል የጤና አገልግሎትን ለማሻሻል የህክምና ግብዓት የተሟላላቸው ጽዱ የጤና ተቋማትን ማስፋት ላይ ትኩረት መደረጉ ተመላከተ። በባህርዳር የሚገኘው የአዲስ አለም የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ያስገነባው የማስፋፊያ ክፍሎች ግንባታና የግቢ ውበት ተጠናቅቆ ተመርቋል። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር)፤ የክልሉን የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ለማስፋትና አገልግሎቱን ለማዘመን እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ውጤታማ እየሆኑ ነው ብለዋል። በክልሉ ጤናማ ዜጋ ለማፍራት የተጀመሩ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የጤና ተቋማትን በግብዓትና በሰው ሃይል ማሟላት ይገባል ብለዋል። ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የ25 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ የጤና ተቋማት ተደራሽነትን ማስፋት፣ አገልግሎትን ማዘመንና የህክምና ግብዓትን ማሟላት ላይ ትኩረት ማድረጉን አመልክተዋል። ከዚህ ባለፈ የጤና ተቋማትን ጽዱ፣ አረንጓዴና ውብ በማድረግ ምቹ የስራ አካባቢን መፍጠር ሌላው ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ነው ብለዋል።ይህም እንደ ሀገር የተያዘውን የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የሚያግዝ መሆኑን አንስተዋል። የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አብዱል ከሪም መንግስቱ በበኩላቸው፣ ጽዱ በሆነና ንጽህናው በተጠበቀ ተቋም የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶች የተገልጋዩን እርካታ እንደሚጨምሩ ተናግረዋል። በዚህም የአዲስ አለም ሆስፒታልን ጨምሮ በክልሉ 58 ሆስፒታሎች ለጤና ባለሙያዎችና ለህክምና ፈላጊዎች ምቹ ከባቢ ለመፍጠር የማስፋፊያ ግንባታዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል። የአዲስ አለም የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ጸዳሉ ዓለሙ፤ የማስፋፊያ ግንባታው የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል። ከማስፋፊያ ግንባታዎቹ መካከል 14 የጽኑ ህክምና፣ የላቦራቶሪና ሌሎች የህክምና አገልግሎት መስጫ ክፍሎች እንደሚገኙ ጠቁመው፣ ግቢውን ጽዱና አረንጓዴ የማድረግ ሥራ መከናወኑንም አንስተዋል።
ብልፅግና ፓርቲ ቀጣይነት ያለው በዲጂታል የታገዘ አገልግሎት ማስፋፋት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫው ነው
Feb 10, 2026 77
አዲስ አበባ፤የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦ብልፅግና ፓርቲ ቀጣይነት ያለው በዲጂታል የታገዘ አገልግሎት ማስፋፋት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫው መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር! የብልፅግና ፓርቲ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ይፋ ማድረጊያ መድረክ ተካሄዷል። በመድረኩም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ፣ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፓርቲው ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ፣ የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት እና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አመራር አባላት ተገኝተዋል። ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር! የብልፅግና ፓርቲ የዘንድሮው የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በመሪ መልዕክትነት ተሰይሟል። የብልፅግና ፓርቲ የዘንድሮው ሰባተኛው ጠቅላላ የምርጫ ምልክት የስንዴ ነዶም የመደመር፣ የአንድነትና የትብብር ተምሳሌትነትን የሚወክልና የምርታማነት መገለጫ መሆኑ ተገልጿል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ተመስገን ጥሩነህ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ብልፅግና ከትናንት የሚወሰዱ እሴቶችን በመገንዘብ፣ የሚወረሱትን እና የሚወገዱትን አምዶችን አውቋል። ከነዚህም በመነሳት አዋጭ የሆነውን የኢትዮጵያ ጉዞ መተለሙን ጠቁመው፤ የብልፅግና የምርጫ ማኒፌስቶ የያዘውም ይህንኑ መሆኑን ተናግረዋል። በሁለቱ ምርጫዎች መካከል የተፈጠረው አንዱ እመርታ ዲጂታላይዜሽን መሆኑን አመላክተዋል። ብልፅግና ፓርቲ ለዲጂታላይዜሽን በሰጠው ልዩ ትኩረት እና ባከናወናቸው ስራዎች ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቁመዋል። የዲጂታል ፋይናንሲንግ አካታችነት ከማረጋገጥ አኳያ ፓርቲው በተጨባጭ ለማስፋፋት ሰፊ ርብርብ ማድረጉን ገልጸዋል። ብልፅግና ፓርቲ ቀጣይነት ያለው በዲጂታል የታገዘ አገልግሎት ማስፋፋት ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫው መሆኑንም ተናግረዋል። አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ከማድረግ ባለፈ እርስ በእርሳቸው ማስተሳሰር ተገቢ መሆኑን ገልጸው፤ በዚህም አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል መስጠት መጀመሩን አንስተዋል። የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በፌዴራል ደረጃ ተግባራዊ መደረጉን እና አሁን ላይ አገልግሎቱ ወደ ክልል እና ከተማ አስተዳደሮች መስፋፋቱን ጠቁመዋል። መሶብ በተጀመረባቸው አካባቢዎች የተገልጋዮች እርካታ በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉን ማረጋገጥ መቻሉን ገልጸዋል። የዲጂታል ኢኮኖሚ ዋነኛው ምሰሶ የሰው ሀብት ልማት መሆኑን ገልጸው፤ ለዚህም የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠናን ተግባራዊ ማድረጉን ተናግረዋል። ብልፅግናን መምረጥ በዲጂታል ኢትዮጵያ ነጋችንን ብሩህ ማድረግ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ኢኒሼቲቮች የተገኙ ውጤቶች ኢትዮጵያውያን ቀና ማለት እንደሚችሉ ያሳዩበት መሆኑንም ነው የተናገሩት።
የአፋርን ህዝብ ባህል፣ወግና የዳኝነት ስርዓት በማልማት ለትውልድ ለማስተላለፍ እየተሰራ ነው
Feb 10, 2026 62
ሰመራ፤ የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦ የአፋርን ህዝብ ባህል፣ ወግና የዳኝነት ስርዓት በማልማት ለትውልድ ለማስተላለፍ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ተናገሩ። የአፋር ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትን (አፋር መድዓ) በመንግስታቱ ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስ እና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ለማስመዝገብ ያለመ ኮንፍረንስ በሠመራ ከተማ እየተካሄደ ነው። በመርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፤ የአፋር ህዝብ በትውልድ ቅብብሎሽ እዚህ ያደረሳቸውን ባህል፣ ወግና ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ ይሰራል ብለዋል። “አፋር መድዓ” የአፋር ማህበረሰብ ሁሉን አቀፍ መተዳደሪያ ስርዓት ሲሆን በማህበረሰቡ እንቅስቃሴ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠውና የተጣላን የሚያስታርቅ የአብሮነት ዕሴት የሆነ ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት መሆኑን ገልጸዋል። የአፋር መድዓ ዋነኛ ግብ አጥፊን መቅጣት ብቻ ሳይሆን፣ ተበዳይ ካሳ እንዲያገኝ ማድረግ እና በሁለቱ ወገኖች መካከል ዘላቂ እርቅ ማውረድ በመሆኑ ለትውልድ ማሻገር እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል፡፡ አፋር መድዓን ጨምሮ የማህበረሰቡን ባህል፣ ወግና የዳኝነት ስነ ስርዓት በማልማትና ጠብቆ ለትውልድ በማስተላለፍ ረገድ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውንም ተናግረዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልመሃዲ በበኩላቸው እንዳሉት፤ የአፋር ህዝብ ትውፊቱ ሳይበረዝ እዚህ ያደረሰውን ባህላዊ የአስተዳደርና የዳኝነት ስርዓት ጠብቆ ለትውልድ ለማሻገር በሚደረገው ጥረት ሚኒስቴሩ እገዛ ያደርጋል። የለውጡ መንግስት በመደመር እሳቤ መሠረት ባህላዊ ሃብቶችንና ሀገራዊ ቅርሶች አስተማማኝ የልማት ሐይል እንዲሆኑ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓቶች ሳይበረዙ ለትውልድ እንዲተላለፉና ዓለም ዓቀፍ እውቅና እንዲያገኙ ከወትሮ በተለየ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል። የአፋር ባህላዊ ዕሴት የሆነውን “አፋር መድዓ” በዘመናዊ መልኩ ከመጠቀም ባለፈ በሳይንስ ጥናት የተደገፈ ሆኖ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ለማስመዝገብ እንደሚሰራም ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል። በመርሃ ግብሩ የፌዴራልና የክልል የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የክልሉ የጎሣ መሪዎችና የሐይማኖት አባቶች እንዲሁም የጅቡቲ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ያካተተ ልዑካን ቡድን ተገኝቷል። መርሃ ግብሩ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ የዳኝነት ስርዓቱ ከክልሉ አልፎ የዓለም ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ የሚያስችሉ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት የሚደረግባቸው መሆኑም ተገልጿል።
ፖለቲካ
የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ አታፍ አዲስ አበባ ገቡ
Feb 10, 2026 35
አዲስ አበባ፤የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ አታፍ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በ48ኛው የአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ እየገቡ ነው። የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ አታፍም ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ደኤታ በረኦ ሀሰን አቀባበል አድርገውላቸዋል። 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን፤ ከጉባኤው አስቀድሞ የካቲት 4 እና 5 ቀን የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት 48ኛው መደበኛ ስብሰባ ይካሄዳል። የዘንድሮው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ “ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” የሚል መሪ ሃሳብ ተሰጥቶታል።
ብልፅግና ፓርቲ የኢትዮጵያን የተጽዕኖ አድማስ ለማስፋትና የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት ይሠራል
Feb 10, 2026 60
አዲስ አበባ፤ የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦ ብልፅግና ፓርቲ የኢትዮጵያን የተጽዕኖ አድማስ ለማስፋትና የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት እንደሚሠራ በምርጫ ማኒፊስቶው ማረጋገጡን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ገለጹ፡፡ ብልፅግና ፓርቲ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምርጫ ማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክቱን ይፋ ያደረገ ሲሆን ፓርቲው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወከልበት የምርጫ ምልክቱ የስንዴ ነዶ መሆኑን አስታውቋል። አቶ አደም ፋራህ በዚሁ ወቅት፤ ፓርቲው በ"መደመር" እሳቤ በመመራት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለዘመናት የቆዩ መዋቅራዊ ስብራቶችን በመጠገን፣ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት ሲሠራ ቆይቷል ብለዋል። ፓርቲው ህዝብን በማሳተፍ፣ በጽናትና ቁርጠኝነት ስኬቶችን ሲያረጋግጥ መቆየቱን ጠቅሰው፤ የህዝብ ይሁንታ በማግኘት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውጤታማ ጉዞ ማስቀጠል የሚያስችለውን የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ማኒፊስቶ አዘጋጅቶ ይፋ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡ ማኒፌስቶው ብልፅግና ፓርቲ በመደመር እሳቤ በመመራት እስካሁን ያስመዘገባቸውን ስኬቶች፣ ወቅታዊ ሁኔታዎችንና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በዝርዝር የያዘ መሆንን አብራርተዋል። ማኒፌስቷችን ትናንትን ማከምን፣ ዛሬን በአግባቡ መጠቀምንና ነገን መተንበይን ማዕከል ያደረገ ነው ሲሉም አስታውቀዋል። በማኒፌስቶው ትልቅ ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች መካከል የዲፕሎማሲው ዘርፍ ቀዳሚውን ስፍራ መያዙን ጠቁመው፤ ፓርቲው በቀጣይ አምስት ዓመታት የኢትዮጵያን የተጽዕኖ አድማስ ለማስፋትና የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት እንደሚሰራ በማኒፌስቶው ይፋ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ ከጎረቤትና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት፣ ከብሪክስ አባል ሀገራትና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰራም በማኒፌስቶው መገለጹን አስታውቀዋል፡፡ እንዲሁም በዓለም አቀፍ የኃይል አሰላለፍ ውስጥ የሚዛናዊነት መርህን በመከተል የኢትዮጵያን ተደማጭነት ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ተካትቷል ብለዋል። ብልፅግና ፓርቲ በማኒፌስቶው ይፋ እንዳደረገው፤ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከሀገራቸው ጋር ያላቸውን ትስስር የሚያጠናክሩ አዳዲስ ኢኒሼቲቮችን ተግባራዊ ማድረግና የዜጎችን ክብር ማስጠበቅ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ተመላክቷል፡፡ አባይን በፍትሃዊነት የመጠቀምና አስተማማኝ የባህር በር የማግኘት መብታችንን ለማስከበር የጀመርናቸውን ጥረቶች እንደምናሰፋ በማኒፌስቶው በግልጽ ተቀምጧል ብለዋል፡፡ ለዚህም ሰላማዊ፣ ህጋዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረጉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በማኒፌስቶው ማካተቱን አረጋግጠዋል።
ብልፅግና ፓርቲ ቀጣይነት ያለው በዲጂታል የታገዘ አገልግሎት ማስፋፋት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫው ነው
Feb 10, 2026 77
አዲስ አበባ፤የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦ብልፅግና ፓርቲ ቀጣይነት ያለው በዲጂታል የታገዘ አገልግሎት ማስፋፋት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫው መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር! የብልፅግና ፓርቲ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ይፋ ማድረጊያ መድረክ ተካሄዷል። በመድረኩም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ፣ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፓርቲው ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ፣ የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት እና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አመራር አባላት ተገኝተዋል። ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር! የብልፅግና ፓርቲ የዘንድሮው የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በመሪ መልዕክትነት ተሰይሟል። የብልፅግና ፓርቲ የዘንድሮው ሰባተኛው ጠቅላላ የምርጫ ምልክት የስንዴ ነዶም የመደመር፣ የአንድነትና የትብብር ተምሳሌትነትን የሚወክልና የምርታማነት መገለጫ መሆኑ ተገልጿል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ተመስገን ጥሩነህ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ብልፅግና ከትናንት የሚወሰዱ እሴቶችን በመገንዘብ፣ የሚወረሱትን እና የሚወገዱትን አምዶችን አውቋል። ከነዚህም በመነሳት አዋጭ የሆነውን የኢትዮጵያ ጉዞ መተለሙን ጠቁመው፤ የብልፅግና የምርጫ ማኒፌስቶ የያዘውም ይህንኑ መሆኑን ተናግረዋል። በሁለቱ ምርጫዎች መካከል የተፈጠረው አንዱ እመርታ ዲጂታላይዜሽን መሆኑን አመላክተዋል። ብልፅግና ፓርቲ ለዲጂታላይዜሽን በሰጠው ልዩ ትኩረት እና ባከናወናቸው ስራዎች ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቁመዋል። የዲጂታል ፋይናንሲንግ አካታችነት ከማረጋገጥ አኳያ ፓርቲው በተጨባጭ ለማስፋፋት ሰፊ ርብርብ ማድረጉን ገልጸዋል። ብልፅግና ፓርቲ ቀጣይነት ያለው በዲጂታል የታገዘ አገልግሎት ማስፋፋት ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫው መሆኑንም ተናግረዋል። አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ከማድረግ ባለፈ እርስ በእርሳቸው ማስተሳሰር ተገቢ መሆኑን ገልጸው፤ በዚህም አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል መስጠት መጀመሩን አንስተዋል። የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በፌዴራል ደረጃ ተግባራዊ መደረጉን እና አሁን ላይ አገልግሎቱ ወደ ክልል እና ከተማ አስተዳደሮች መስፋፋቱን ጠቁመዋል። መሶብ በተጀመረባቸው አካባቢዎች የተገልጋዮች እርካታ በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉን ማረጋገጥ መቻሉን ገልጸዋል። የዲጂታል ኢኮኖሚ ዋነኛው ምሰሶ የሰው ሀብት ልማት መሆኑን ገልጸው፤ ለዚህም የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠናን ተግባራዊ ማድረጉን ተናግረዋል። ብልፅግናን መምረጥ በዲጂታል ኢትዮጵያ ነጋችንን ብሩህ ማድረግ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ኢኒሼቲቮች የተገኙ ውጤቶች ኢትዮጵያውያን ቀና ማለት እንደሚችሉ ያሳዩበት መሆኑንም ነው የተናገሩት።
የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመወዳደሪያ ምልክት የስንዴ ነዶ መሆኑን ይፋ አደረገ
Feb 10, 2026 124
አዲስ አበባ፤ የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመወዳደሪያ ምልክት የስንዴ ነዶ መሆኑን ይፋ አድርጓል። "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!" የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ይፋ ማድረጊያ መድረክ በማካሄድ ላይ ይገኛል። በመድረኩም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሀላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ፣ የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት እና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አመራር አባላት ተገኝተዋል። "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!" የብልፅግና ፓርቲ የዘንድሮው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመሪ መልዕክትነት ተሰይሟል። የብልፅግና ፓርቲ የዘንድሮው 7ኛው ጠቅላላ የምርጫ ምልክት የስንዴ ነዶ የመደመር፣ የአንድነትና የትብብር ተምሳሌትነትን የሚወክልና የምርታማነት መገለጫ መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመጪው ግንቦት 24/2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማሳወቁ ይታወቃል።
የጎንደር ወጣቶች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም ተዘጋጅተዋል
Feb 10, 2026 86
ጎንደር፤ የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፡- በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን እንደሚጠቀሙ የጎንደር ከተማ ወጣቶች ገለጹ፡፡ ምርጫ ዜጎች ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ለመረጡት ፓርቲ ስልጣንን በውክልና የሚሰጡበት የፖለቲካ ሥርዓት መገለጫ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ወጣቶች አመላክተዋል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ወጣቶች እንዳሉት፤ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የዜጎች ተሳትፎ የሚረጋገጥበትና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መሰረት የሚጣልበት ሆኖ እንዲጠናቀቅ የነቃ ተሳትፎ ለማድረግ ተዘጋጅተዋል። ወጣት ሞገስ አራጋው እንደገለጸው፣ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሃዊና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ወጣቶች የጎላ ሚና አላቸው። በኢትዮጵያ የተጀመሩ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸውና የዜጎችን ኑሮ አንዲያሻሽሉ ሰላማዊ ምርጫ በማካሄድ የሀገረ መንግስት ግንባታው ላይ የነቃ ተሳትፎ ለማድረግ መዘጋጀቱን አመልክቷል። ወጣት ወንድማገኝ ሽመልስ በበኩሉ ለሀገሪቷ ሰላምና ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ምርጫ የማይተካ ሚና እንዳለው ተናግሯል። 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊና በህዝብ አመኔታን ያተረፈ እንዲሆን የድርሻዬን እወጣለሁ ብሏል። ወጣቱ ትውልድ የነገ ሀገር ተረካቢ እንደመሆኑ በምርጫው ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የሀገሪቷን መጻዒ ዕድል የተሻለ ለማድረግ ሃላፊነቱን ሊወጣ አንደሚገባ ነው ያነሳው። በኢትዮጰያ የተጀመሩ የልማትና የሰላም ግንባታ ሥራዎች የበለጠ እንዲጠናከሩ ጠቅላላ ምርጫው በተሳካ ሁኔታ ሊካሄድ ይገባል ያለችው ደግሞ ወጣት መጽሄት ተከለወይን ናት። በጠቅላላ ምርጫው በመምረጥ በመሳተፍ ዴሞክራሲያዊ መብቷን ለመጠቀም ዝግጁ መሆኗንም ነው የገለጸችው። 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም የሚካሄድ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳውቋል።
የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ እየገቡ ነው
Feb 10, 2026 156
አዲስ አበባ፤የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በ48ኛው የአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ እየገቡ ይገኛሉ። በዚህም ዛሬ ጠዋት የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዲሰላም አብዲ አሊ እና የሞሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሐመድ ሳሌም መርዙግ አዲስ አበባ ገብተዋል። በተጨማሪ የሴራሊዮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲሞቲ ሙሳ ካባ እና የሰሃራው አረብ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሐመድ የሥለም ቤይሳት አዲስ አበባ ገብተዋል። ሚኒስትሮቹ ቦሌ አለምአቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። ትናንት አመሻሽም የናይጄሪያ፣ የማላዊ፣ የዛምቢያ፣ የቡሩንዲ፣ የኮንጎ ሪፐብሊክ፣ የቦትስዋና፣ የናሚቢያ፣ የዚምባቡዌ፣ የኮትዲቯር እና የቤኒን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገብተዋል። 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤም ጅማሮውን የካቲት 4 እና 5 ቀን 2018 ዓ.ም በ48ኛው የሕብረቱ የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ በማድረግ የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም የአህጉሪቱ አባል ሀገራት መሪዎች በተገኙበት ጉባኤው የሚካሄድ ይሆናል። የዘንድሮው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤም “ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄድ ይሆናል። የሕብረቱ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤትም በመደበኛ ስብሰባው ለ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል። የሚኒስትሮች የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው ለ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ እየገቡ ነው
Feb 9, 2026 135
አዲስ አበባ፤ የካቲት 2/2018(ኢዜአ)፦ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በ48ኛው የአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ እየገቡ ይገኛሉ። በዚህም የናይጀሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሱፍ ማይታማ ቱጋር፣ የማላዊ የውጭ ጉዳይና አለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ጆርጅ ታፓቱላ (ዶ/ር)፣ የዛምቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙላምቦ ሀይምቤ እና የቡርንዲ የውጭ ጉዳይ፣ የቀጣናዊ ትስስር እና ልማት ትብብር ሚኒስትር ኢዶዋዮርድ ቢዚማና፣ የኮንጎ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጀን ክሏዴ ጋኮሶ እና የቦትስዋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፌንዮ ቡታሌዛሬ አመሻሽ አዲስ አበባ ገብተዋል። በተጨማሪም የናሚቢያ የአለም አቀፍ ግንኙነትና ንግድ ሚኒስትር ሰልማ አሺፓላ ሙሳቪይ፣ የዝቧቡዌ የውጭ ጉዳይና የአለም አቀፍ ንግድ ሚኒስትር ፕሮፌሰር አሞን ሙርዊራ፣ የኮትዲቯር የውጭ ጉዳይና የአለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ካባ ኒያል እንዲሁም የቤኒን የውጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ዋና ጸሃፊ አምባሳደር አኮቪ ማርቲኒያን ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል። ሚኒስትሮቹ ቦሌ አለምአቀፍ ኤርፓርት ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል። የሚኒስትሮች የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው ለ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
ወጣቶቹ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤታማነት የድርሻቸውን ይወጣሉ
Feb 9, 2026 187
መቱ፡ የካቲት 2/2018ኢዜአ)፡-የኢሉአባቦር ወጣቶች ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤታማነት የድርሻቸውን እንደሚወጡ አረጋገጡ። በኢሉአባቦር ዞን በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫና ድሕረ-ምርጫ ሂደቶች የመራጮችን ተሳትፎ አስመልክቶ ለወጣቶች የግንዘቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል። ስልጠናው በምርጫ ሂደቶች ወጣቶች በቂ ግንዛቤ ይዘው በንቃት የሚሳተፉበትን ዕድል የሚፈጥር ነው ተብሏል። የኢሉአባቦር ዞን ወጣቶች ማሕበር ሊቀመንበር ቢቂላ ኮይና፣ ወጣቶች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በንቃት እየተሳተፉ መሆኑን አመልክቷል። 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ጉዞ የሚያሳልጥና የወጣቱን መጻዒ ዕድል የሚወስን እንደመሆኑ ወጣቱ በምርጫ ሂደቱ ንቁ ተሳታፊ ሊሆን እንደሚገባ አንስቷል። በጠቅላላ ምርጫው የመምረጥና የመመረጥ መብቱን ከመጠቀም ባለፈ ለምርጫው ሰላማዊ ሂደትና ውጤታማነት የድርሻውን እንደሚወጣ አረጋግጧል። ወጣት በፈቃዱ እንዳለና ወጣት አምሪሳ ከድር በበኩላቸው፣ ምርጫው ሰላማዊነትና ዴሞክራሲያዊ ሂደቱን ጠብቆ እንዲካሄድ የዜግነት ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል። የምርጫው ሂደት ሰላማዊ እንዲሆን የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ነው ወጣቶቹ ያረጋገጡት። የዞኑ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ መሐመድጠሃ አባፊጣ፣ ምርጫ ዕድሜው 18 ዓመት የሆነው ማንኛውም ዜጋ ዴሞክራሲያዊ መብቱን እንዲጠቀም ዕድል የሚሰጥ ነው ብለዋል። ወጣቶች ከቅድመ ምርጫ አስከ ድህረ-ምረጫ ያለው ሂደት ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት ቁርጠኛ መሆን እንዳለባቸው አመልክተዋል። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመምረጥ፣ በመመረጥ ፣በማስመረጥና በታዛቢነት በመሳተፍ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
ፖለቲካ
የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ አታፍ አዲስ አበባ ገቡ
Feb 10, 2026 35
አዲስ አበባ፤የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ አታፍ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በ48ኛው የአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ እየገቡ ነው። የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ አታፍም ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ደኤታ በረኦ ሀሰን አቀባበል አድርገውላቸዋል። 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን፤ ከጉባኤው አስቀድሞ የካቲት 4 እና 5 ቀን የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት 48ኛው መደበኛ ስብሰባ ይካሄዳል። የዘንድሮው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ “ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” የሚል መሪ ሃሳብ ተሰጥቶታል።
ብልፅግና ፓርቲ የኢትዮጵያን የተጽዕኖ አድማስ ለማስፋትና የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት ይሠራል
Feb 10, 2026 60
አዲስ አበባ፤ የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦ ብልፅግና ፓርቲ የኢትዮጵያን የተጽዕኖ አድማስ ለማስፋትና የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት እንደሚሠራ በምርጫ ማኒፊስቶው ማረጋገጡን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ገለጹ፡፡ ብልፅግና ፓርቲ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምርጫ ማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክቱን ይፋ ያደረገ ሲሆን ፓርቲው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወከልበት የምርጫ ምልክቱ የስንዴ ነዶ መሆኑን አስታውቋል። አቶ አደም ፋራህ በዚሁ ወቅት፤ ፓርቲው በ"መደመር" እሳቤ በመመራት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለዘመናት የቆዩ መዋቅራዊ ስብራቶችን በመጠገን፣ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት ሲሠራ ቆይቷል ብለዋል። ፓርቲው ህዝብን በማሳተፍ፣ በጽናትና ቁርጠኝነት ስኬቶችን ሲያረጋግጥ መቆየቱን ጠቅሰው፤ የህዝብ ይሁንታ በማግኘት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውጤታማ ጉዞ ማስቀጠል የሚያስችለውን የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ማኒፊስቶ አዘጋጅቶ ይፋ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡ ማኒፌስቶው ብልፅግና ፓርቲ በመደመር እሳቤ በመመራት እስካሁን ያስመዘገባቸውን ስኬቶች፣ ወቅታዊ ሁኔታዎችንና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በዝርዝር የያዘ መሆንን አብራርተዋል። ማኒፌስቷችን ትናንትን ማከምን፣ ዛሬን በአግባቡ መጠቀምንና ነገን መተንበይን ማዕከል ያደረገ ነው ሲሉም አስታውቀዋል። በማኒፌስቶው ትልቅ ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች መካከል የዲፕሎማሲው ዘርፍ ቀዳሚውን ስፍራ መያዙን ጠቁመው፤ ፓርቲው በቀጣይ አምስት ዓመታት የኢትዮጵያን የተጽዕኖ አድማስ ለማስፋትና የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት እንደሚሰራ በማኒፌስቶው ይፋ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ ከጎረቤትና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት፣ ከብሪክስ አባል ሀገራትና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰራም በማኒፌስቶው መገለጹን አስታውቀዋል፡፡ እንዲሁም በዓለም አቀፍ የኃይል አሰላለፍ ውስጥ የሚዛናዊነት መርህን በመከተል የኢትዮጵያን ተደማጭነት ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ተካትቷል ብለዋል። ብልፅግና ፓርቲ በማኒፌስቶው ይፋ እንዳደረገው፤ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከሀገራቸው ጋር ያላቸውን ትስስር የሚያጠናክሩ አዳዲስ ኢኒሼቲቮችን ተግባራዊ ማድረግና የዜጎችን ክብር ማስጠበቅ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ተመላክቷል፡፡ አባይን በፍትሃዊነት የመጠቀምና አስተማማኝ የባህር በር የማግኘት መብታችንን ለማስከበር የጀመርናቸውን ጥረቶች እንደምናሰፋ በማኒፌስቶው በግልጽ ተቀምጧል ብለዋል፡፡ ለዚህም ሰላማዊ፣ ህጋዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረጉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በማኒፌስቶው ማካተቱን አረጋግጠዋል።
ብልፅግና ፓርቲ ቀጣይነት ያለው በዲጂታል የታገዘ አገልግሎት ማስፋፋት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫው ነው
Feb 10, 2026 77
አዲስ አበባ፤የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦ብልፅግና ፓርቲ ቀጣይነት ያለው በዲጂታል የታገዘ አገልግሎት ማስፋፋት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫው መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር! የብልፅግና ፓርቲ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ይፋ ማድረጊያ መድረክ ተካሄዷል። በመድረኩም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ፣ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፓርቲው ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ፣ የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት እና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አመራር አባላት ተገኝተዋል። ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር! የብልፅግና ፓርቲ የዘንድሮው የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በመሪ መልዕክትነት ተሰይሟል። የብልፅግና ፓርቲ የዘንድሮው ሰባተኛው ጠቅላላ የምርጫ ምልክት የስንዴ ነዶም የመደመር፣ የአንድነትና የትብብር ተምሳሌትነትን የሚወክልና የምርታማነት መገለጫ መሆኑ ተገልጿል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ተመስገን ጥሩነህ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ብልፅግና ከትናንት የሚወሰዱ እሴቶችን በመገንዘብ፣ የሚወረሱትን እና የሚወገዱትን አምዶችን አውቋል። ከነዚህም በመነሳት አዋጭ የሆነውን የኢትዮጵያ ጉዞ መተለሙን ጠቁመው፤ የብልፅግና የምርጫ ማኒፌስቶ የያዘውም ይህንኑ መሆኑን ተናግረዋል። በሁለቱ ምርጫዎች መካከል የተፈጠረው አንዱ እመርታ ዲጂታላይዜሽን መሆኑን አመላክተዋል። ብልፅግና ፓርቲ ለዲጂታላይዜሽን በሰጠው ልዩ ትኩረት እና ባከናወናቸው ስራዎች ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቁመዋል። የዲጂታል ፋይናንሲንግ አካታችነት ከማረጋገጥ አኳያ ፓርቲው በተጨባጭ ለማስፋፋት ሰፊ ርብርብ ማድረጉን ገልጸዋል። ብልፅግና ፓርቲ ቀጣይነት ያለው በዲጂታል የታገዘ አገልግሎት ማስፋፋት ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫው መሆኑንም ተናግረዋል። አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ከማድረግ ባለፈ እርስ በእርሳቸው ማስተሳሰር ተገቢ መሆኑን ገልጸው፤ በዚህም አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል መስጠት መጀመሩን አንስተዋል። የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በፌዴራል ደረጃ ተግባራዊ መደረጉን እና አሁን ላይ አገልግሎቱ ወደ ክልል እና ከተማ አስተዳደሮች መስፋፋቱን ጠቁመዋል። መሶብ በተጀመረባቸው አካባቢዎች የተገልጋዮች እርካታ በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉን ማረጋገጥ መቻሉን ገልጸዋል። የዲጂታል ኢኮኖሚ ዋነኛው ምሰሶ የሰው ሀብት ልማት መሆኑን ገልጸው፤ ለዚህም የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠናን ተግባራዊ ማድረጉን ተናግረዋል። ብልፅግናን መምረጥ በዲጂታል ኢትዮጵያ ነጋችንን ብሩህ ማድረግ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ኢኒሼቲቮች የተገኙ ውጤቶች ኢትዮጵያውያን ቀና ማለት እንደሚችሉ ያሳዩበት መሆኑንም ነው የተናገሩት።
የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመወዳደሪያ ምልክት የስንዴ ነዶ መሆኑን ይፋ አደረገ
Feb 10, 2026 124
አዲስ አበባ፤ የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመወዳደሪያ ምልክት የስንዴ ነዶ መሆኑን ይፋ አድርጓል። "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!" የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ይፋ ማድረጊያ መድረክ በማካሄድ ላይ ይገኛል። በመድረኩም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሀላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ፣ የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት እና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አመራር አባላት ተገኝተዋል። "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!" የብልፅግና ፓርቲ የዘንድሮው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመሪ መልዕክትነት ተሰይሟል። የብልፅግና ፓርቲ የዘንድሮው 7ኛው ጠቅላላ የምርጫ ምልክት የስንዴ ነዶ የመደመር፣ የአንድነትና የትብብር ተምሳሌትነትን የሚወክልና የምርታማነት መገለጫ መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመጪው ግንቦት 24/2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማሳወቁ ይታወቃል።
የጎንደር ወጣቶች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም ተዘጋጅተዋል
Feb 10, 2026 86
ጎንደር፤ የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፡- በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን እንደሚጠቀሙ የጎንደር ከተማ ወጣቶች ገለጹ፡፡ ምርጫ ዜጎች ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ለመረጡት ፓርቲ ስልጣንን በውክልና የሚሰጡበት የፖለቲካ ሥርዓት መገለጫ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ወጣቶች አመላክተዋል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ወጣቶች እንዳሉት፤ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የዜጎች ተሳትፎ የሚረጋገጥበትና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መሰረት የሚጣልበት ሆኖ እንዲጠናቀቅ የነቃ ተሳትፎ ለማድረግ ተዘጋጅተዋል። ወጣት ሞገስ አራጋው እንደገለጸው፣ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሃዊና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ወጣቶች የጎላ ሚና አላቸው። በኢትዮጵያ የተጀመሩ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸውና የዜጎችን ኑሮ አንዲያሻሽሉ ሰላማዊ ምርጫ በማካሄድ የሀገረ መንግስት ግንባታው ላይ የነቃ ተሳትፎ ለማድረግ መዘጋጀቱን አመልክቷል። ወጣት ወንድማገኝ ሽመልስ በበኩሉ ለሀገሪቷ ሰላምና ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ምርጫ የማይተካ ሚና እንዳለው ተናግሯል። 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊና በህዝብ አመኔታን ያተረፈ እንዲሆን የድርሻዬን እወጣለሁ ብሏል። ወጣቱ ትውልድ የነገ ሀገር ተረካቢ እንደመሆኑ በምርጫው ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የሀገሪቷን መጻዒ ዕድል የተሻለ ለማድረግ ሃላፊነቱን ሊወጣ አንደሚገባ ነው ያነሳው። በኢትዮጰያ የተጀመሩ የልማትና የሰላም ግንባታ ሥራዎች የበለጠ እንዲጠናከሩ ጠቅላላ ምርጫው በተሳካ ሁኔታ ሊካሄድ ይገባል ያለችው ደግሞ ወጣት መጽሄት ተከለወይን ናት። በጠቅላላ ምርጫው በመምረጥ በመሳተፍ ዴሞክራሲያዊ መብቷን ለመጠቀም ዝግጁ መሆኗንም ነው የገለጸችው። 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም የሚካሄድ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳውቋል።
የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ እየገቡ ነው
Feb 10, 2026 156
አዲስ አበባ፤የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በ48ኛው የአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ እየገቡ ይገኛሉ። በዚህም ዛሬ ጠዋት የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዲሰላም አብዲ አሊ እና የሞሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሐመድ ሳሌም መርዙግ አዲስ አበባ ገብተዋል። በተጨማሪ የሴራሊዮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲሞቲ ሙሳ ካባ እና የሰሃራው አረብ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሐመድ የሥለም ቤይሳት አዲስ አበባ ገብተዋል። ሚኒስትሮቹ ቦሌ አለምአቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። ትናንት አመሻሽም የናይጄሪያ፣ የማላዊ፣ የዛምቢያ፣ የቡሩንዲ፣ የኮንጎ ሪፐብሊክ፣ የቦትስዋና፣ የናሚቢያ፣ የዚምባቡዌ፣ የኮትዲቯር እና የቤኒን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገብተዋል። 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤም ጅማሮውን የካቲት 4 እና 5 ቀን 2018 ዓ.ም በ48ኛው የሕብረቱ የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ በማድረግ የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም የአህጉሪቱ አባል ሀገራት መሪዎች በተገኙበት ጉባኤው የሚካሄድ ይሆናል። የዘንድሮው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤም “ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄድ ይሆናል። የሕብረቱ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤትም በመደበኛ ስብሰባው ለ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል። የሚኒስትሮች የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው ለ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ እየገቡ ነው
Feb 9, 2026 135
አዲስ አበባ፤ የካቲት 2/2018(ኢዜአ)፦ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በ48ኛው የአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ እየገቡ ይገኛሉ። በዚህም የናይጀሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሱፍ ማይታማ ቱጋር፣ የማላዊ የውጭ ጉዳይና አለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ጆርጅ ታፓቱላ (ዶ/ር)፣ የዛምቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙላምቦ ሀይምቤ እና የቡርንዲ የውጭ ጉዳይ፣ የቀጣናዊ ትስስር እና ልማት ትብብር ሚኒስትር ኢዶዋዮርድ ቢዚማና፣ የኮንጎ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጀን ክሏዴ ጋኮሶ እና የቦትስዋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፌንዮ ቡታሌዛሬ አመሻሽ አዲስ አበባ ገብተዋል። በተጨማሪም የናሚቢያ የአለም አቀፍ ግንኙነትና ንግድ ሚኒስትር ሰልማ አሺፓላ ሙሳቪይ፣ የዝቧቡዌ የውጭ ጉዳይና የአለም አቀፍ ንግድ ሚኒስትር ፕሮፌሰር አሞን ሙርዊራ፣ የኮትዲቯር የውጭ ጉዳይና የአለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ካባ ኒያል እንዲሁም የቤኒን የውጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ዋና ጸሃፊ አምባሳደር አኮቪ ማርቲኒያን ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል። ሚኒስትሮቹ ቦሌ አለምአቀፍ ኤርፓርት ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል። የሚኒስትሮች የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው ለ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
ወጣቶቹ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤታማነት የድርሻቸውን ይወጣሉ
Feb 9, 2026 187
መቱ፡ የካቲት 2/2018ኢዜአ)፡-የኢሉአባቦር ወጣቶች ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤታማነት የድርሻቸውን እንደሚወጡ አረጋገጡ። በኢሉአባቦር ዞን በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫና ድሕረ-ምርጫ ሂደቶች የመራጮችን ተሳትፎ አስመልክቶ ለወጣቶች የግንዘቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል። ስልጠናው በምርጫ ሂደቶች ወጣቶች በቂ ግንዛቤ ይዘው በንቃት የሚሳተፉበትን ዕድል የሚፈጥር ነው ተብሏል። የኢሉአባቦር ዞን ወጣቶች ማሕበር ሊቀመንበር ቢቂላ ኮይና፣ ወጣቶች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በንቃት እየተሳተፉ መሆኑን አመልክቷል። 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ጉዞ የሚያሳልጥና የወጣቱን መጻዒ ዕድል የሚወስን እንደመሆኑ ወጣቱ በምርጫ ሂደቱ ንቁ ተሳታፊ ሊሆን እንደሚገባ አንስቷል። በጠቅላላ ምርጫው የመምረጥና የመመረጥ መብቱን ከመጠቀም ባለፈ ለምርጫው ሰላማዊ ሂደትና ውጤታማነት የድርሻውን እንደሚወጣ አረጋግጧል። ወጣት በፈቃዱ እንዳለና ወጣት አምሪሳ ከድር በበኩላቸው፣ ምርጫው ሰላማዊነትና ዴሞክራሲያዊ ሂደቱን ጠብቆ እንዲካሄድ የዜግነት ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል። የምርጫው ሂደት ሰላማዊ እንዲሆን የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ነው ወጣቶቹ ያረጋገጡት። የዞኑ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ መሐመድጠሃ አባፊጣ፣ ምርጫ ዕድሜው 18 ዓመት የሆነው ማንኛውም ዜጋ ዴሞክራሲያዊ መብቱን እንዲጠቀም ዕድል የሚሰጥ ነው ብለዋል። ወጣቶች ከቅድመ ምርጫ አስከ ድህረ-ምረጫ ያለው ሂደት ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት ቁርጠኛ መሆን እንዳለባቸው አመልክተዋል። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመምረጥ፣ በመመረጥ ፣በማስመረጥና በታዛቢነት በመሳተፍ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
ማህበራዊ
የጤና አገልግሎትን ለማሻሻል የህክምና ግብዓት የተሟላላቸው ጽዱ የጤና ተቋማትን ማስፋት ላይ ትኩረት ተደርጓል
Feb 10, 2026 73
ባህርዳር ፤የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል የጤና አገልግሎትን ለማሻሻል የህክምና ግብዓት የተሟላላቸው ጽዱ የጤና ተቋማትን ማስፋት ላይ ትኩረት መደረጉ ተመላከተ። በባህርዳር የሚገኘው የአዲስ አለም የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ያስገነባው የማስፋፊያ ክፍሎች ግንባታና የግቢ ውበት ተጠናቅቆ ተመርቋል። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር)፤ የክልሉን የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ለማስፋትና አገልግሎቱን ለማዘመን እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ውጤታማ እየሆኑ ነው ብለዋል። በክልሉ ጤናማ ዜጋ ለማፍራት የተጀመሩ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የጤና ተቋማትን በግብዓትና በሰው ሃይል ማሟላት ይገባል ብለዋል። ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የ25 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ የጤና ተቋማት ተደራሽነትን ማስፋት፣ አገልግሎትን ማዘመንና የህክምና ግብዓትን ማሟላት ላይ ትኩረት ማድረጉን አመልክተዋል። ከዚህ ባለፈ የጤና ተቋማትን ጽዱ፣ አረንጓዴና ውብ በማድረግ ምቹ የስራ አካባቢን መፍጠር ሌላው ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ነው ብለዋል።ይህም እንደ ሀገር የተያዘውን የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የሚያግዝ መሆኑን አንስተዋል። የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አብዱል ከሪም መንግስቱ በበኩላቸው፣ ጽዱ በሆነና ንጽህናው በተጠበቀ ተቋም የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶች የተገልጋዩን እርካታ እንደሚጨምሩ ተናግረዋል። በዚህም የአዲስ አለም ሆስፒታልን ጨምሮ በክልሉ 58 ሆስፒታሎች ለጤና ባለሙያዎችና ለህክምና ፈላጊዎች ምቹ ከባቢ ለመፍጠር የማስፋፊያ ግንባታዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል። የአዲስ አለም የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ጸዳሉ ዓለሙ፤ የማስፋፊያ ግንባታው የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል። ከማስፋፊያ ግንባታዎቹ መካከል 14 የጽኑ ህክምና፣ የላቦራቶሪና ሌሎች የህክምና አገልግሎት መስጫ ክፍሎች እንደሚገኙ ጠቁመው፣ ግቢውን ጽዱና አረንጓዴ የማድረግ ሥራ መከናወኑንም አንስተዋል።
የአፋርን ህዝብ ባህል፣ወግና የዳኝነት ስርዓት በማልማት ለትውልድ ለማስተላለፍ እየተሰራ ነው
Feb 10, 2026 62
ሰመራ፤ የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦ የአፋርን ህዝብ ባህል፣ ወግና የዳኝነት ስርዓት በማልማት ለትውልድ ለማስተላለፍ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ተናገሩ። የአፋር ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትን (አፋር መድዓ) በመንግስታቱ ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስ እና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ለማስመዝገብ ያለመ ኮንፍረንስ በሠመራ ከተማ እየተካሄደ ነው። በመርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፤ የአፋር ህዝብ በትውልድ ቅብብሎሽ እዚህ ያደረሳቸውን ባህል፣ ወግና ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ ይሰራል ብለዋል። “አፋር መድዓ” የአፋር ማህበረሰብ ሁሉን አቀፍ መተዳደሪያ ስርዓት ሲሆን በማህበረሰቡ እንቅስቃሴ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠውና የተጣላን የሚያስታርቅ የአብሮነት ዕሴት የሆነ ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት መሆኑን ገልጸዋል። የአፋር መድዓ ዋነኛ ግብ አጥፊን መቅጣት ብቻ ሳይሆን፣ ተበዳይ ካሳ እንዲያገኝ ማድረግ እና በሁለቱ ወገኖች መካከል ዘላቂ እርቅ ማውረድ በመሆኑ ለትውልድ ማሻገር እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል፡፡ አፋር መድዓን ጨምሮ የማህበረሰቡን ባህል፣ ወግና የዳኝነት ስነ ስርዓት በማልማትና ጠብቆ ለትውልድ በማስተላለፍ ረገድ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውንም ተናግረዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልመሃዲ በበኩላቸው እንዳሉት፤ የአፋር ህዝብ ትውፊቱ ሳይበረዝ እዚህ ያደረሰውን ባህላዊ የአስተዳደርና የዳኝነት ስርዓት ጠብቆ ለትውልድ ለማሻገር በሚደረገው ጥረት ሚኒስቴሩ እገዛ ያደርጋል። የለውጡ መንግስት በመደመር እሳቤ መሠረት ባህላዊ ሃብቶችንና ሀገራዊ ቅርሶች አስተማማኝ የልማት ሐይል እንዲሆኑ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓቶች ሳይበረዙ ለትውልድ እንዲተላለፉና ዓለም ዓቀፍ እውቅና እንዲያገኙ ከወትሮ በተለየ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል። የአፋር ባህላዊ ዕሴት የሆነውን “አፋር መድዓ” በዘመናዊ መልኩ ከመጠቀም ባለፈ በሳይንስ ጥናት የተደገፈ ሆኖ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ለማስመዝገብ እንደሚሰራም ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል። በመርሃ ግብሩ የፌዴራልና የክልል የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የክልሉ የጎሣ መሪዎችና የሐይማኖት አባቶች እንዲሁም የጅቡቲ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ያካተተ ልዑካን ቡድን ተገኝቷል። መርሃ ግብሩ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ የዳኝነት ስርዓቱ ከክልሉ አልፎ የዓለም ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ የሚያስችሉ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት የሚደረግባቸው መሆኑም ተገልጿል።
በዞኑ ባለፉት ስድስት ወራት ከ112 ሺህ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች ዲጂታል መታወቂያ ወስደዋል
Feb 10, 2026 54
መቱ ፤የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦በኢሉአባቦር ዞን በበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት ከ112 ሺህ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች የዲጂታል መታወቂያ መውሰዳቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ። የኢሉአባቦር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መሐመድጠሃ አባፊጣ፣ የዞኑ ነዋሪዎች የዲጂታል መታወቂያ የዲጂታል ኢትዮጵያን ጉዞ ለማፋጠን የሚያግዝ መሆኑን ተገንዝበው መታወቂያውን እየወሰዱ መሆኑን ገልጸዋል። የዲጂታል መታወቂያ በቴክኖሎጂው የእድገት ዘርፍ ከተያዙ ሀገራዊ አቅጣጫዎች አንዱ መሆኑን አስታውሰው ሁሉም የዞኑ ነዋሪዎች መታወቂያውን እንዲያገኙ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። በተያዘው ዓመት ከ164 ሺህ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች መታወቂያውን እንዲያገኙ ታቅዶ በግማሽ ዓመቱ ከ112 ሺህ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች የዲጂታል መታወቂያ ማግኘት መቻላቸውን ገልጸዋል። ለስኬታማነቱ በዞኑ ሁሉም ወረዳዎች ከባንኮችና ከኢትዮ ቴሌኮም ቅርንጫፎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል። በቀጣይም በዞኑ ሁሉም ነዋሪዎች የዲጂታል መታወቂያ መያዝ እንዲችሉ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስረድተዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የዞኑ ነዋሪዎች በበኩላቸው፤ የዲጂታል መታወቂያ አንድ ሰው አንድ ማንነት ብቻ እንዲኖረው በማድረግ ህገ ወጥ ተግባራትን ለመከላከል ያግዛል ብለዋል። የዲጂታል መታወቂያ ለሁሉም ዜጎች ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት መረጋገጥ ትልቅ አስተዋጽዖ እንዳለውም ተናግረዋል። በተጨማሪም በመንግስት የሚከናወኑ ልማቶች በትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሰረቱ እንዲሆን ያስችላል ብለዋል።
ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት የበኩላችንን እንወጣለን − የወላይታ ሀገር ሽማግሌዎች
Feb 10, 2026 79
ወላይታ ሶዶ ፤ የካቲት 3/2018 (ኢዜአ):- ሀገራዊ ምክክሩ ብሔራዊ መግባባትና ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የሚያስችል በመሆኑ ለስኬታማነቱ የድርሻችንን እንወጣለን ሲሉ የወላይታ ሀገር ሽማግሌዎች ተናገሩ። በኢትዮጵያ መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ለተፈጠሩ ልዩነቶችና አለመግባባቶች ወሳኝ ምክንያቶችን በጥናትና በሕዝባዊ ውይይቶች በመሰብሰብ፣ በተለዩ አጀንዳዎች ላይ ሀገራዊ ምክክሮችን ለማካሄድ የምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞ እየሰራ ነው። ምክክሩ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲሁም በመንግሥት እና በሕዝብ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል፣ መተማመን የሰፈነበትና ከዚህ ቀደም ያልተሄደበትን የቆዩ አለመግባባቶችን ለመፍታት የሚያስችል አዲስ አካሄድ እንደሆነም ታምኖበታል። ኮሚሽኑም በአሁኑ ወቅት አሳታፊ በሆነ መልኩ በተለያዩ አካላት የሚነሱ አጀንዳዎችን በማሰባሰብ የማጠቃለያ የምክክር ምእራፍ ላይ መድረሱ ይታወቃል። ከሀገራዊ ምክክሩ ጋር ተያይዞም ኢዜአ ያነጋገራቸው የወላይታ ዞን ሀገር ሽማግሌዎች፤ ሀገራዊ ምክክሩን አስመልክቶ ማሕበረሰቡን በማወያየትና ግንዛቤን በመፍጠር ለስኬታማነቱ እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል የወላይታ ሀገር ሽማግሌዎች ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰይፉ ለታ እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያውያን መካከል ከጥንት ጀምሮ የነበረውን የመወያየት፣ የመመካከርና አብሮ የመኖር እሴትን ለማስቀጠል ምክክሩ አስፈላጊ ነው። በአሁኑ ወቅት በተለያየ ምክንያት እየተሸረሸረ የመጣውን ይህንኑ የቆየ እሴት ለማስቀጠል ምክክር ማድረግ ምትክ የማይገኝለት ጉዳይ ነው ያሉት። መንግስትም ይህንኑ በመገንዘብ በዜጎች መካከል ምክክሮችን በማካሄድ የተፈጠሩ ችግሮችን በውይይትና በመተማመን እንዲፈቱ እያከናወነ ያለው ተግባር በሀገሪቱ ሰላምን ለማጽናት ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል ነው ያሉት። ሁላችንም መጠሪያችን አንዲት ኢትዮጵያ ናት ያሉት አቶ ሰይፉ "በአንድነት ሰርተንና ለምተን የሀገራችንን ከፍታ ለማረጋገጥ ችግሮቻችንን ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ እናምጣ" ሲሉም መክረዋል። "እኛ ኢትዮጵያውያን የብሔርና የኃይማኖት ልዩነት ሳይገድበን ተከባብረን ተዋደን ለዘመናት የመኖር ድንቅ ባህል ያለን ህዝቦች ነን" ይህንኑ ማስቀጠል ይጠበቅብናል ያሉት ደግሞ ሌላው የምክር ቤቱ አባል አቶ አብርሃም ባቾሬ ናቸው። በወላይታ "አዋሲያ"፣ "ሲጋ" እና "ጭማቴታ" የተሰኙና ችግሮች ሲፈጠሩ ለመፍታት ጥቅም ላይ የሚውሉ ባህላዊ እሴቶች ያሉ መሆኑን አንስተዋል። የሀገር ሽማግሌዎች ለኮሚሽኑ ስራ ስኬታማነት የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑን አመልክተው በቤተሰብ፣ በጎረቤት ፣በዕድርና በእምነት ተቋማትም ጭምር ግንዛቤ የመፍጠራ ላይ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ችግሮችን በሰከነ ፣ ህዝብን ባማከለና የሁሉንም ድምጽ ባሳተፈ መልኩ ለመፍታት ውይይቶችንና ምክክሮችን ማድረግ አስፈላጊ ነው ያሉት ደግሞ የምክር ቤቱ አባል አቶ ዳንኤል ደሳለኝ ናቸው መንግስት በወሰደው ቁርጠኛ አቋም ኮሚሽኑ በይፋ ወደስራ በመግባቱ ጠንካራ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠርና ያደሩ ቁርሾዎች ለማስወገድ ወሳኝ መሆኑን ነው የገለጹት። የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠልም ውይይቶችንና ምክክሮችን ለማድረግና ችግሮች በዘላቂነት እንዲፈቱም ያላሰለሰ ጥረት እንደሚያደርጉም ነው ያረጋገጡት።
ኢኮኖሚ
በክልሉ የግብይት ሥርዓቱን በማዘመንና አምራችና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የገበያ መረጋጋት ለመፍጠር ትኩረት ተሰጥቷል
Feb 10, 2026 100
ደብረ ብርሃን፤ የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የግብይት ሥርዓቱን በማዘመንና አምራችና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የገበያ መረጋጋት ለመፍጠር ትኩረት መደረጉን በምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የከተማና መሰረተ ልማት አስተባባሪ አህመዲን መሐመድ(ዶ/ር) ገለጹ። የገበያ ሥርዓቱን የማዘመን ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር በ196 ሚሊየን ብር ያስገነባው 2ኛ ደረጃ የገበያ ማዕከል ተመርቋል። በምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የከተማና መሰረተ ልማት አስተባባሪ አህመዲን መሐመድ(ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፤በክልሉ የግብይት ሥርዓቱን በማዘመንና አምራችና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የገበያ መረጋጋት ለመፍጠር ትኩረት ተሰጥቷል። የክልል መንግስት የዜጎችን የኑሮ ጫና ለማቃለል የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝም ተናግረዋል። በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ ግዙፍ የልማት ሥራዎች የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት በተግባር ያረጋገጡ መሆናቸውንም ገልጸዋል። በክልሉ የግብይት ሥርዓቱን በማዘመንና አምራችና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የገበያ መረጋጋት ለመፍጠር እየተሰራ ነው ብለዋል። በተያዘው በጀት ዓመት ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በ7 ከተሞች እየተገነቡ ያሉ የገበያ ማዕከላትም የግብይት ሥርዓቱን ማዘመን የሚያስችሉ መሆናቸውን አስታውቀዋል። የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ሃላፊ ኢብራሂም መሐመድ በበኩላቸው፣ በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የልማት እንቅስቃሴዎች የዜጎችን ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ መሆናቸውን ተናግረዋል። አምራችና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የግብይት ሰንሰለቱን ለማሳጠርም በክልሉ ስምንት የገበያ ማዕከላት ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አስታውሰዋል። እነዚህ የገበያ ማዕከላት ገበያውን በማረጋጋት በኩል ቀጥተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው ብለዋል። ከገበያ ማዕከላቱ ባለፈ የቅዳሜና እሁድ ገበያ ተደራሽነትን በማስፋት የሕብረተሰቡን የኑሮ ጫና ለማቃለል እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል። ከተማዋ በፈጣን የዕድገት ጉዞ ላይ እንደመሆኗ አምራችና ሸማቹን በቀጥታ የሚያገናኙ የገበያ ማዕከላት ወሳኝ መሆናቸውን የተናገሩት ደግሞ የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት ናቸው። የገበያ ማዕከላቱ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ገበያ በማረጋጋት በኩል ቁልፍ ሚና እንደሚጫወቱ አንስተዋል። በከተማዋ የተገነባው የ2ኛ ደረጃ የገበያ ማዕከል የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለሕብረተሰቡ ተደራሽ ያደርጋል ብለዋል።
አርሶ አደሮች አሪቲን በማልማት ተጠቃሚ ሆነዋል
Feb 10, 2026 61
ሳውላ ፤የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦ የአሪቲ ተክልን በማልማት እያገኘነው ያለው ገቢ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ አድርጎናል ሲሉ የጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለጹ። በኢትዮጵያ ገጠራማው በተለይ በደጋማ አካባቢ የሚበቅለው የአሪቲ ተክል በዓላት ሲመጡ ለጉዝጓዝና ለመልካም መዓዛነት ጥቅም ላይ ይውላል። የአሪቲ ተክልን ከጉዝጓዝ ባለፈም በተለያዩ ዓለማት ክፍሎችም ለባሕላዊና ዘመናዊ ሕክምና ከማዋል ባለፈ መዓዛማ ተክል ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ለሽቶ መስሪያነት ጥቅም ላይ ይውላል። በጎፋ ዞንም ከሚለማው የቅመማ ቅመምና መዓዛማ ተክሎች መካከል አሪቲ አንዱ ነው። በዞኑ ኮረሪማ፣ በርበሬ፣ ሚጥሚጣና ሌሎች የቅመማ ቅመምና የሰብል ምርቶችን በማልማት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ እየቀረበ ይገኛል። በወረዳው በአካባቢ ጥበቃ በለማ መሬት ላይ የአሪቲ ተክልን እያለሙ የሚገኙ አርሶ አደሮች እንደሚሉት በአሪቲ ምርት ላይ ተሰማርተው በሄክታር እስከ 16 ኩንታል ምርት በማግኘት ተጠቃሚ ሆነዋል። አርሶ አደር ፍጹም ጨሌ በዛላ ወረዳ የዳዳ ገላይሳ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው፤ የአሪቲ ተክልን በዓመት ሶስት ጊዜ እያለሙ ይገኛሉ። በነዚሁ ጊዜያት በሶስት ሄክታር መሬት ላይ የሚያለሙትን የአሪቲ ተክል ለገበያ በማቅረባቸው ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን ለማሳደግ እንደረዳቸው ገልፀዋል። በሚያገኙት ገቢም ቤተሰባቸውን በተገቢው መንገድ ለማስተዳደር መሰረት እንደሆናቸው አስረድተዋል። በሄክታር 16 ኩንታል ምርት እንደሚያገኙ የሚገልጹት አርሶ አደሩ በኩንታል ከ1 ሺህ 600 እስከ 2 ሺህ ብር ድረስ ገቢ እንደሚያገኙም ገልጸዋል። የገልተሜ ናንቴ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር በላይ በርገኔ በበኩላቸው፤ ባላቸው አንድ ሄክታር ማሳ ላይ አሪቲን በማልማት ላይ እንደሚገኙ ይናገራሉ። ምርቱን ለገበያ በማቅረብ በሚገኘው ገቢም ቤተሰባቸውን ለማስተዳደር እንደቻሉም ነው ያነሱት። አሪቲ አንዴ ከተተከለ እና ምርቱን በአግባቡ መንከባከብ ከተቻለ የሚገኘው ጥቅም ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው ምርቱ ተጨማሪ ገቢን ለማግኘት አስችሎኛል ብለዋል። ምርቱን በተገቢው መንገድ በመንከባከብም በሄክታር እስከ 16 ኩንታል ምርት እንደሚሰበስቡም ነው ያመለከቱት። የጎፋ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊና የቅመማ ቅመም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኑርአዲስ አደም በበኩላቸው፤በዞኑ ከ8 ሺህ 200 ሄክታር በላይ መሬት በአሪቲ ተክል መልማቱን ተናግረዋል። በዚሁ በአሪቲ ተክል ከተሸፈነው መሬትም በዓመት 8 ሺህ ቶን ምርት እንደሚሰበሰብና ለሀገር ውስጥና ለውጪ ገበያ እንደሚቀርብ ገልፀዋል። ባለፉት ስድስት ወራትም ከ2 ሺህ ቶን በላይ የአሪቲ ምርት ወደ መካከለኛው ምስራቅ፣ ጅቡቲ፣ ኡጋንዳና ሳዑዲ አረቢያ ገበያዎች መላኩን ተናግረዋል። የአሪቲ ምርት ተፈላጊነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ በስፋት እየለማ ሲሆን ምርቱንም በአብዛኛው የሽቶ ፋብሪካዎች እንደሚረከቡት ነው ያነሱት።
የመንግስት ሁለንተናዊ ድጋፎች የኢትዮጵያ ቡና በዓለም አቀፍ ያለውን ተወዳዳሪነት እያሳደገው ነው
Feb 10, 2026 94
አዲስ አበባ፤ የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦ መንግስት ለቡናው ዘርፍ እያደረገ ያለው ሁለንተናዊ ድጋፍ የኢትዮጵያ ቡና በዓለም አቀፍ ገበያ ያለውን ተወዳዳሪነትና ተመራጭነት በከፍተኛ ደረጃ እንዳሳደገው የዘርፉ ላኪዎች ገለጹ። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ቡና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ተፈላጊነት እየጨመረ ከመምጣቱ በላይ አዳዲስ የገበያ መዳረሻዎች እየጨመሩ ይገኛሉ። ይህንን ተከትሎም ሀገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘው የውጭ ምንዛሬ ከጊዜ ወደ ጊዜ እድገት እያሳየ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ በ2017 በጀት ዓመት 469 ሺህ ቶን ቡና ለዓለም ገበያ በመላክ 2 ነጥብ 65 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘት ችላለች። ይህም በሀገሪቱ የቡና ታሪክ ከፍተኛው የገቢ መጠንና የጥራት ደረጃ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን፤ መንግስት ይህንን ውጤት በማስቀጠል በያዝነው ዓመት የሚገኘውን ገቢ ወደ ሦስት ቢሊየን ዶላር ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የቡና ላኪዎች እንደገለጹት፤ በቡናው ዘርፍ እየመጣ ላለው ዕድገትና ስኬት የመንግስት ድጋፍ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ የታደሰ ደስታ ስፔሻላይዝድ ኮፊ ኤክስፖርት ዳይሬክተር ገብረመስቀል ሃይሉ እንዳሉት፤ መንግስት ለዘርፉ የሰጠው ልዩ ትኩረት የኢትዮጵያ ቡና ከአውሮፓ፣ አሜሪካና ቻይና አልፎ በሁሉም የዓለም ክፍሎች ተፈላጊ እንዲሆን አድርጎታል። በዚህም የድርጅታቸው የደንበኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን አረጋግጠዋል፡፡ ቀደም ሲል ጥቂት የነበሩ የቡና መዳረሻዎች አሁን ላይ በስፋት መጨመራቸውንና ከዓለም አቀፍ ገዢዎች የሚመጣው ግብረ-መልስ እጅግ አዎንታዊ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የትራኮን ትሬዲንግ ኮፊ ሶርሲንግ ማናጀር ሳሚ ኤሊያስ ናቸው፡። በተለይም መንግስት ለመሬት አቅርቦትና ለወጪ ንግድ ሂደቶች እያደረገ ያለው ድጋፍ ላኪዎች በሙሉ አቅማቸው እንዲሰሩ አግዟቸዋል ብለዋል። የኤማ ኮፊ መስራችና ስራ አስኪያጅ መውሃ ሰይድ በበኩላቸው፤ ቡናን በጥራትና በብዛት ማቅረብ ለሀገር ኢኮኖሚ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ መንግስት እያደረገ ያለው የፋይናንስ ድጋፍ ስራቸውን እንዳቀለለላቸውና ውጤታማ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል። ላኪዎቹ በቀጣይም ጥራት ያለው ምርት በማቅረብ የውጭ ምንዛሬ ግኝቱን ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆናቸውን በመግለጽ፣ መንግስት እያደረገ ያለው ሁለንተናዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ የፍትሃዊነት እና አብሮ የማደግ መርህን መሰረት ያደረገ ነው
Feb 10, 2026 76
ድሬዳዋ፤ የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ የፍትሃዊነትና አብሮ የማደግ መርህን መሰረት ያደረገ መሆኑን የፖለቲካ ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት ምሁር ፕሮፌሰር ብሩክ ሐይሉ ተናገሩ። የባህር በር ቀጥተኛ የኢንቨስትመንት ዕድልን ከማስፋቱ ባሻገር የአንድ ሀገር ዳር ድንበር እንዲከበር ያለው ፋይዳ ቀላል የሚባል አይደለም። ይሁንና እነዚህን ጉዳዮች ከግምት ባለማስገባት ኢትዮጵያ በተፈጸመባት በደል ከባህር በር እንድትርቅ የተደረገበት ሁኔታ በዝምታ ዓመታትን የዘለቀ ነገር ግን በብዙዎች ዘንድ ቁጭት አሳድሯል። በመሆኑም አሁን ላይ ዝምታው ተሰብሮ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ የትውልድ ጥያቄና የሀገር የህልውና ጉዳይ ሆኖ ቀጥሏል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት ምሁር ፕሮፌሰር ብሩክ ሐይሉ፤ ኢትዮጵያ እና ቀይ ባህር ላይነጣጠሉ መልክዓ ምድር፣ ተፈጥሮና ታሪክ ያጋመዳቸው ናቸው ብለዋል። ኢትዮጵያ ያለ ቀይ ባህር በብዙ መመዘኛዎች ህልውናዋ አደጋ ላይ የሚወድቅ መሆኑን ሁሉም የሚገነዘበው እውነታ መሆኑን አንስተው የባህር በር ባለቤት መሆኗ የግድ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ የፍትሃዊነትና አብሮ የማደግ መርህን መሰረት ያደረገ በመሆኑ አጠቃላይ የቀጣናው ሀገራት ተገንዝበው ለተግባራዊነቱ በጋራ ሊቆሙ ይገባል ነው ያሉት። የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ አሁን ላይ የትውልድ ጥያቄ ሆኖ መነሳቱ በዓለም አቀፍ ህግ፣ በታሪክም ይሁን በመልክዓ ምድር ተገቢነትን መሰረት ያደረገ ነው ብለዋል። በመሆኑም የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በዓለም አቀፍ ህግ፣ በሰላማዊ ድርድርና በዲፕሎማሲያዊ ጥረት ተገቢው ምላሽ ሊሰጠው ይገባል ነው ያሉት።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን ተጠቅመው ብቁ የሰው ሃይል የሚያፈሩበት ዕድል ተፈጥሯል
Feb 10, 2026 83
ጎንደር ፤የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰው ሰራሽ አስተውሎት(AI) ቴክኖሎጂን ተጠቅመው ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ሃይል የሚያፈሩበት ዕድል መፈጠሩን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂውን ለማስተዋወቅና ተደራሽነቱን ለማስፋት ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራርሟል። ሥምምነቱን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ይታገሱ ደሳለኝና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አስራት አጸደወይን (ዶ/ር) ፈርመውታል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ይታገሱ ደሳለኝ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኢትዮጵያ የምትፈልገውን የሰለጠነ የሰው ሃይል እንዲያፈሩ የአቅም ግንባታ ላይ የተለያዩ ድጋፎች እየተደረጉ ነው። ከተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ኢንስቲትዩቱ በሚያደርግላቸው ድጋፍ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ የመመረቂያ ጥናታቸውን እያካሄዱ መሆኑን ተናግረዋል። ኢንስቲትዩቱ በሰው ሰራሽ አስተውሎት በመታገዝ አምስት የሀገር ውስጥ ቋንቋዎችን ማበልጸጉን ጠቅሰው፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ዘርፉን ለጥናትና ምርምር የበለጠ እንዲጠቀሙበት ጠይቀዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን እውን ለማድረግ ወሳኝ ሚና እንዳለው የተናገሩት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ ቴክኖሎጂው ለብዝሃ-ዘርፎች ዕድገት ወሳኝ ሚና ይጫወታል ብለዋል። ጎንደር ዩንቨርሲቲ በጤናው ዘርፍ ያለውን የካበተ ልምድ በሰው ሰራሽ አስተውሎት በማስደገፍ የጤና መረጃ ሥርዓትን የበለጠ ሊያዘምን ይገባል ብለዋል። የጎንደር ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አስራት አጸደወይን (ዶ/ር) በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው የሰለጠነ የሰው ሃይል ለማፍራት በዘርፉ አዳዲስ የትምህርት ፕሮግራሞችን ከፍቶ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል ብለዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን ለማካሄድ አዎንታዊ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። ዩንቨርሲቲው በሰው ሰራሽ አስተውሎት የምርምር ማዕከል በማቋቋም ከሀገር ባለፈ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የመሆን ግብ ይዞ እየሰራ እንደሆነም አስረድተዋል። ስምምነቱ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ከመጠቀም ባለፈ ኢትዮጵያ የራሷን ቴክኖሎጂ ማበልጸግ የሚያስችላትን ዕድል የሚፈጥር መሆኑንም አንስተዋል።
የዲጅታል ኢትዮጵያ መተግበር የፋይናንስ ስርዓቱን በማዘመን ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት እያስቻለ ነው
Feb 10, 2026 94
አርባምንጭ፤የካቲት 3/2018 (ኢዜአ:-የዲጅታል ኢትዮጵያ መተግበር የፋይናንስ ስርዓትን በማዘመን ዜጎች ባሉበት ሆነው ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ እያስቻለ መሆኑን የፋይናንስ ዘርፍ አመራሮችና ተገልጋዮች ገለጹ። ዘርፉን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማስደገፍ የተደረጉ ጥረቶች ዘመናዊ አሰራርና ፈጣን አገልግሎት በማስፈን ለሀገራዊ ዕድገቱ ጉልህ ሚና እንዲጫወት እያደረገ ይገኛል። የፋይናንስ ዘርፍ አመራሮችና ተገልጋዮች እንደተናገሩት፤ የዲጂታል ኢትዮጵያ መርሃ ግብር የፋይናንስ ስርዓትን በማዘመን ዜጎች ባሉበት ሆነው ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ እያስቻለ ነው። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ጉጆ ለኢዜአ እንዳሉት፥ የዲጂታል አሰራሩ የፋይናንስ አገልግሎትን በማቀላጠፍ በዜጎች አኗኗር ላይ መሠረታዊ ለውጥ አምጥቷል። የዲጂታል አገልግሎቱ በተለይ የንግዱ ማህበረሰብ ወደ ፋይናንስ ተቋማት ሳይመጡ ባሉበት ሆነው አገልግሎቱን ለማግኘት እንዲችሉ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። አዲስ የንግድ ምዝገባ ማድረግ፣ የንግድ ፈቃድ እድሳትና ሌሎች አገልግሎቶች በዲጂታል ስርዓት እየተሰጡ መሆኑን ገልጸዋል። ባለፉት 6 ወራት ከ107 ሺህ በላይ የንግድ ፈቃድ የታደሰ ሲሆን ከእነዚህም ከ57 ሺህ በላይ የሚሆኑት በኢ-ትሬድና በወረዳ ኔት አገልግሎት ተሰጥቷል ብለዋል። በክልሉ ባሉ 12 ዞኖችና 3 ሪጂዮ ፖሊስ ከተሞች የሚገኙ ነጋዴዎች በተፈጠረው የዲጂታል ስርዓት ዜጎች ካሉበት ሆነው አገልግሎት እንዲያገኙ በማስቻሉ በርካታ ችግሮችን መቅረፉን አቶ ሳሙኤል ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አርባ ምንጭ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ደረጀ ማርቆስ በበኩላቸው፥ "ዲጂታል ኢትዮጵያ እውን እንዲሆን የፋይናንስ ሴክተሮች አገልግሎት መዘመን አስፈላጊ ነው" ብለዋል። ከ87 በመቶ በላይ የባንኩ የፋይናንስ እንቅስቃሴ በዲጂታል ስርዓት ውስጥ ነው ያሉት ስራ አስኪያጁ ባንኩ ባዘጋጃቸው የተለያዩ የክፍያ አማራጮች ተጠቅመው፥ ደንበኞች ቤታቸው ወይም ስራ ቦታቸው ሆነው አገልግሎት እያገኙ መሆኑን ገልጸዋል። በሞባይል ባንኪንግ በመታገዝ ደንበኞች ጊዜና ቦታ ሳይገድባቸው እንዲሁም በኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎት የግልና የመንግስት ድርጅቶች ግብይትና ለሰራተኞቻቸው ክፍያዎችን እንዲፈጽሙ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል ብለዋል። የደንበኞችን ብሔራዊ መታወቂያ ከባንኩ ስርዓት ጋር በማቆራኘት አስተማማኝ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ እያስቻለ መሆኑንም አቶ ደረጀ አስረድተዋል። የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎታቸውን ዲጂታላይዝ ማድረጋቸው ከወጪና እንግልት ታድጎናል ያለው ደግሞ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪ ወጣት ሀርዲዶ ዶሎቦ ነው።
ማዕከሉ በአርብቶ አደሩ አካባቢ ምርታማነትን ለማሳደግ የጀመረውን የጥናትና ምርምር ስራ አጠናክሮ መቀጠል አለበት - ቋሚ ኮሚቴው
Feb 10, 2026 87
ጂንካ፤የካቲት 3/2018(ኢዜአ) :- የጂንካ ግብርና ምርምር ማዕከል በአርብቶ አደሩ አካባቢ የእንስሳት እና የሰብል ምርታማነትን ለማሳደግ የጀመረውን ውጤታማ የጥናትና ምርምር ስራ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሃ፣ መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ። የቋሚ ኮሚቴው አባላት በጂንካ ግብርና ምርምር ማዕከል የሚሰሩ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የጥናትና ምርምር ስራዎችን ተመልክተዋል። አባላቱ በአፈር ላይ የሚሰሩ የጥናትና ምርምር፣ የመኖ ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ፣ ዘመናዊ ዶሮ እንስሳትና ዓሳ እርባታ፣ የሰብል ምርምርን ጨምሮ በምርምር ማዕከሉ የሚከናወኑ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ተመልክተዋል። የቋሚ ኮሚቴው አባል አቶ አጉ ዱባን፣ ማዕከሉ ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች እየሰራ መሆኑን ተመልክተናል ብለዋል። በተለይም በአርብቶ አደሩ አካባቢ ያሉ ጸጋዎች ላይ በማተኮር የእንስሳት እና የሰብል ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያግዙ ውጤታማ የጥናትና ምርምር ስራ እያካሄደ መሆኑን ማረጋገጣቸውን ጠቁመዋል። የምርምር ማዕከሉ ምርታማነትን የሚጨምሩ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማላመድ ለአርብቶ አደሩ በሳይንሳዊ ጥናት የታገዘ ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም መታዘባቸውን ገልጸዋል። በቀጣይም በአርብቶ አደሩ አካባቢ ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚሰሩ የልማት ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የድጋፍና ክትትል ስራው ይጠናከራል ብለዋል። የምርምር ማዕከሉ ዳይሬክተር ተክሌ ዮሴፍ (ዶ/ር) ማዕከሉ አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማላመድ የሰብልና የእንስሳት ምርታማነትን ለመጨመር እየሰራ ይገኛል ። በዚህም በማዕከሉ በሰብልና በእንስሳት እርባታ ላይ የሚካሄዱ የጥናትና ምርምር ስራዎች በአርሶና በአርብቶ አደሩ አካባቢ ተጨባጭ ለውጥ እያመጡ ስለመሆናቸው ገልጸዋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዮት መብራቴ (ዶ/ር) በበኩላቸው የምርምር ማዕከላት ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በማካሄድ በግብርናው ዘርፍ ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ እገዛ እያደረጉ መሆኑን አንስተዋል ። በተለይ እንደ ሀገር የተጀመረውን የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ለማሳካት በሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር የታገዘ ድጋፍ ለማድረግ የምርምር ማዕከላት ጥረታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አስረድተዋል። በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የአርብቶ አደር አካባቢ ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር ተክለዮሐንስ ብርሃኑ (ዶ/ር)፤ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተጀመረውን ጥረት ለማሳካት የጥናትና ምርምር ስራዎች ወሳኝ ሚና አላቸው ብለዋል ። በምርታማነታቸው የተረጋገጡ አዳዲስ የሰብልና እንስሳት ዝርያዎች ማፍለቅ፣ ማላመድና ምርት መስጠት የማይችሉ አሲዳማ መሬትን በኖራ የማከም እና መሰል ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍቱ ለሀገር-አቀፍ ፈተናው የተሻለ ዝግጅት ለማድረግና የላቀ ውጤት ለማምጣት ያግዛል
Feb 10, 2026 95
ሰቆጣ ፤የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፡-ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍቱ ለሀገር-አቀፍ ፈተናው የተሻለ ዝግጅት ለማድረግና የላቀ ውጤት ለማምጣት የሚያግዝ መሆኑን የሰቆጣ ከተማ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ገለጹ። የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ በሰቆጣ ያስገነባው ''ሰላም የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ሰማዕታት መታሰቢያ ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት'' ትናንት መመረቁ ይታወሳል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የሰቆጣ ከተማ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዲጂታል ቤተ-መጻሕፍቱ ግንባታ የበለጠ እንዲያነቡና ተጨማሪ ዕውቀት እንዲታጠቁ የሚያነሳሳ መሆኑን ተናግረዋል። የ12ኛ ክፍል ተማሪው ሳህለጊዮርጊስ ደባሹ በከተማዋ ደረጃውን የጠበቀ ቤተ-መጻሕፍት ባለመኖሩ በክፍል ከሚሰጣቸው ትምህርት ውጭ ተጨማሪ መጽሐፍት ለማግኘት ይቸገሩ እንደነበር አስታውሷል። የዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት ለአገልግሎት መብቃት ዘመኑ የሚጠይቀውን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕውቀት እንዲገበዩና ብቁና ተወዳዳሪ ለመሆን ያስችላል ነው ያለው። ዘንድሮ ለሚወስደው ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና የተሻለ ዝግጅት ለማድረግና የላቀ ውጤት ለማምጣትም የዲጂታል ቤተ-መጻሕፍቱ ግንባታ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጿል። ተማሪ እሌኒ ቢምረውና ተማሪ አዱኛ ንጉሴ በበኩላቸው ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍቱ የሚፈልጉትን መጽሐፍት በቀላሉ በማግኘት ራሳቸውን እንዲያበቁ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል። ከመደበኛ ትምህርት ባለፈ ለጠቅላላ ዕውቀት የሚሆኑ አባሪ መጽሐፍትን በማንበብ የዕውቀት አድማስንና እይታን ለማስፋት ወሳኝ መሆኑንም አመልክተዋል። የዋግ ስዩም አድማሱ ወሰን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ መክብብ እንዳሉት የዲጂታል ቤተ-መጻሕፍቱ ለተማሪዎች ውጤት መሻሻል ትልቅ አስተዋፅኦ አለው። ተማሪዎች አስፈላጊውን አጋዥ መጽሐፍት በቀላሉ እንዲያገኙ ከማስቻሉም ባለፈ ሀገር አቀፍ ፈተናውን በብቃት እንዲወጡና የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ የሚያግዝ መሆኑን አመልክተዋል። የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ የሰራዊት አባላት በ70 ሚሊዮን ብር በሰቆጣ ከተማ ያስገነቡት የዲጂታል ቤተ-መጻሕፍትን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በይፋ መመረቃቸው ይታወሳል።
ስፖርት
የዓለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክላጋን የአትሌቲክስ መሰረተ ልማቶችን ጎበኙ
Feb 10, 2026 90
አዲስ አበባ፤ የካቲት 3/2018 (ኢዜአ)፦ የዓለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክላጋን የአትሌቲክስ መሰረተ ልማቶችን ዛሬ ማለዳ ጎብኝተዋል። የውድድር ዋና ዳይሬክተሩ ፒርስ ኦክላጋን በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ግብዣ መሰረት ለጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። ዋና ዳይሬክተሩ በዓለም አትሌቲክስ እውቅና ያገኘው የአደይ አበባ ዓለም አቀፍ የመለማመጃ ትራክ እና የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚን ጎብኝተዋል። ፌዴሬሽኑ በቀጣይ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እና የአንድ ቀን ውድድሮች (One day meeting) ጨምሮ ሌሎች ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ውድድሮችን ለማዘጋጀት የሚያደርገው ዝግጅት የዳይሬክተሩ ጉብኝት ወሳኝ መሆኑ ተመላክቷል። በተጨማሪም የስፖርት ዲፕሎማሲ ግንኙነትን የማጠናከር ፋይዳ እንዳለውም የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመለክታል። የዓለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክላጋን ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ መኪዩ መሀመድ፣ ከፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን እና ከፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ ከዌስትሃም ዩናይትድ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል
Feb 10, 2026 94
አዲስ አበባ፤ የካቲት 3/2018 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ዛሬ ይጀመራል። በዕለቱ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ። በለንደን ስታዲየም ዌስትሃም ዩናይትድ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ምሽት 5 ሰዓት ከ15 ላይ ይጫወታሉ። ዌስትሃም ዩናይትድ በ23 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ማንችስተር ዩናይትድ በ44 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ካለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች መካከል ሶስቱን ያሸነፈው ዌስትሃም ዩናይትድ በጥሩ ወቅታዊ ብቃት ላይ ይገኛል። በጊዜያዊው አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ የሚመራው ማንችስተር ዩናይትድ በሊጉ ያለፉትን አራት ተከታታይ ጨዋታዎች አሸንፏል። ዌስትሃም ዩናይትድ ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት እያደረገ ባለው ብርቱ ፉክክር ሶስት ነጥብ እጅጉን ወሳኝ ነው። በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ እየተፎካከረ የሚገኘው ዩናይትድ በሊጉ አምስተኛ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ይጫወታል። ማንችስተር ዩናይትድ ለመጨረሻ ጊዜ በሊጉ አምስት ተከታታይ ጨዋታዎችን ያሸነፈው እ.አ.አ በ2023/24 የውድድር ዓመት ነው። ጨዋታው ጠንካራ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል። የ43 ዓመቱ ሳይመን ሁፐር ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል። በሌላኛው መርሐ-ግብር ቼልሲ ከሊድስ ዩናይትድ ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ላይ በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ቼልሲ በ43 ነጥብ አምስተኛ፣ ሊድስ ዩናይትድ በ29 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዘዋል። ሁለቱም ቡድኖች በሊጉ ተከታታይ ድላቸውን ለማስመዝገብ ይፋለማሉ። ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከኒውካስትል ዩናይትድ እና ኤቨርተን ከቦርንማውዝ በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ላይ ይጫወታሉ።
በሊጉ ተስተካካይ መርሐ-ግብር ሀዲያ ሆሳዕና ፋሲል ከነማን አሸነፈ
Feb 9, 2026 85
አዲስ አበባ፤ የካቲት 2 /2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ሀዲያ ሆሳዕና ፋሲል ከነማን 1 ለ 0 አሸንፏል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሱራፌል ተመስገን በ60ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። በሊጉ ስድስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ሀዲያ ሆሳዕና በ24 ነጥብ ደረጃውን ከ15ኛ ወደ 10ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉ ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል። በአንጻሩ በሊጉ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ፋሲል ከነማ በ33 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል። ፋሲል ከነማ የሊጉ መሪ መሆን የሚችልበትን እድል መጠቀም አልቻለም። ሁለቱ ቡድኖች በ16ኛው ሳምንት ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ በጥምቀት በዓል ምክንያት ተራዝሞ በተስተካካይ መርሐ-ግብርነት መያዙ የሚታወስ ነው።
በተጠባቂው የደርቢ ጨዋታ ፒኤስጂ ማርሴይን አሸነፈ
Feb 9, 2026 113
አዲስ አበባ፤ የካቲት 2/2018 (ኢዜአ)፦ በፈረንሳይ ሊግ አንድ 21ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሐ-ግብር ፒኤስጂ ማርሴይን 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል። ትናንት ማምሻውን በፓርክ ደ ፕሪንስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኡስማን ደምበሌ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ክቪቻ ክቫርትሽኬሊያ፣ ካንግ ኢን-ሊ እና የማርሴዩ ፋኩንዶ መዲና በራሱ ላይ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ደምበሌ በፒኤስጂ ማልያ 50ኛ እና 51ኛ ግቦቹን አስቆጥሯል። በጨዋታው ፒኤስጂ ከፍተኛ ብልጫ ወስዷል። በውድድር ዓመቱ 16ኛ ድሉን ያስመዘገበው ፒኤስጂ በ51 ነጥብ የሊጉን መሪነት ከሌንስ ተረክቧል። በአንጻሩ በሊጉ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ማርሴይ በ39 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል። የ "Le Classique" ደርቢ በፒኤስጂ አሸናፊነት ተጠናቋል።
አካባቢ ጥበቃ
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ ያስመዘገበቻቸው ስኬቶች በአፍሪካ የውሃ ዋስትናን ለማረጋገጥ አርዓያነት ያለው ተግባር ነው
Feb 9, 2026 125
አዲስ አበባ፤ የካቲት 2/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራና ተፋሰስ ልማት ያስመዘገበቻቸው ስኬቶች በአፍሪካ የውሃ ዋስትናን ለማረጋገጥ አርዓያነት ያለው ተግባር ነው ሲሉ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ በአፍሪካ ሕብረት የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ባህል ምክር ቤት "የአጀንዳ 2063 ግቦች ለማሳካት ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ" የሚለውን የ39ኛው የሕብረቱን መሪ ቃል በተመለከተ የሲቪል ማህበረሰብ ቅድመ ስብሰባ አካሂዷል፡፡ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ በአፍሪካ ከ400 ሚሊየን በላይ ዜጎች የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ይገጥማቸዋል፡፡ በአህጉሪቱ ከ700 ሚሊየን በላይ ዜጎች በተለይም ወጣቶች፣ ሴቶችና የገጠር ነዋሪዎች የንጽህና አጠባበቅ (ሳኒቴሽንና ሀይጅን) ጉድለት ችግር እንደሚያጋጥማቸው ገልጸዋል፡፡ የአፍሪካ ሕብረትም የአጀንዳ 2063 አንዱ ግብና የዘንድሮው ዓመት መሪ ሀሳብ ያደረገውም ውሃ የዜጎች መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ ነው ብለዋል፡፡ በአህጉሪቷ ዘላቂ የውሃ አቅርቦት እና የአካባቢ ንጽህናን ማረጋገጥ ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማስመዝገብ እና ውሃ ወለድ በሽታን ለመከላከል ወሳኝ መሆኑንም አንስተዋል፡፡ የውሃ ሀብታችን የኢኮኖሚያችን አቅም፣ የህልውናችን መሰረት ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታተ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ትብብር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ዓመታት ዘላቂ የውሃ ሀብት ልማትን ለማረጋገጥ ተጨባጭ የተግባር ውጤት ማስመዝገቧን ገልጸው፤ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ48 ቢሊየን በላይ ችግኞችን ተክላለች ብለዋል፡፡ እነዚህ የተተከሉ ችግኞች የፅድቀት መጠንም ከ90 በመቶ በላይ ሲሆን፤ በዚህ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ ማዳን እንደተቻለ ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ እና ተፋሰስ ልማት ያስመዘገበቻቸው ስኬቶች አፍሪካውያን በትብብር የንጹህ መጠጥ ውሃና ንጽህናን ማረጋገጥ እንደሚችሉ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ የወንዝ ዳርቻ እና ኮሪደር ልማት ስራ በአዲስ አበባ ከተማ ጀምራ ወደ ተለያዩ ክልሎች ማስፋቷን ያነሱት ሚኒስትሩ፤ ይህም የወንዞችን ውበትና የውሃ ንጽህናን መጠበቅ አስችሏል ብለዋል፡፡ የአፍሪካ የገጸ ምድርና ከርሰ ምድር የውሃ ሀብት እንዳይበከል አስፈላጊውን የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ማከናወን እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ በመሆኑም እንደ አፍሪካ በጋራ በመተባበር ከቻልን አንዳችን ለአንዳችን በረከት እንሆናለን፤ ንጹህ የከርሰ ምድር ውሃ ይኖረናልም ብለዋል፡፡
የበልግ አብቃይ የሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ይኖራቸዋል
Feb 9, 2026 115
አዳማ ፤ የካቲት 2/2018 (ኢዜአ)፦በአብዛኛው የበልግ አብቃይ የሀገሪቱ አካባቢዎች መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የበጋ ወቅት የአየር ፀባይ ትንበያ ግምገማና የበልግ ወቅት ትንበያ ይፋ ማድረጊያ መድረክ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በአዳማ ማካሄድ ጀምሯል። ኢንስቲትዩቱ በዚሁ መድረክ ላይ ይፋ እንዳደረገው የበልግ ወቅት የአየር ትንበያ በልግ ዋነኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚኖራቸው ጠቁሟል። በዚሁ መሰረት የቦረና እና ጉጂ ዞኖች ፣ሲዳማ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ከመደበኛ በላይ ዝናብ ያገኛሉ። እንዳሁም የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል እና የምእራብና ደቡብ ምእራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ደግሞ መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚያገኙ ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል። በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት እየተስተዋሉ ከሚገኙ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በሰሜን ምእራብ በመካከለኛው፣ በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይም መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ይኖራል። በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት መጠን በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን ምእራብ እና በደቡብ ምእራብ አካባቢዎች ላይ ከመደበኛ በላይ እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ። የበልግ ወቅት የዝናብ አጀማመር በደቡብ አጋማሽ አካባቢዎች ላይ ቀደም ብሎ የሚጀመር ሲሆን በአወጣጥ ረገድ ግን በተወሰኑ ቀናቶች ዘግይቶ ይወጣል ተብሏል። ይህን የዝናብ መጠንና ስርጭት በአግባቡ መጠቀምና በዚህ ወቅት የሚካሄደውን የግብርና እንቅስቃሴ እና ሌሎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስራዎች ከባለሙያዎች ጋር በመመካከር ማከናወን ያስፈልጋል ተብሏል። በዘንድሮ የበልግ ወራት የዝናብ መጠንም ለግብርና ስራ አመቺ መሆኑ ተገልጿል።
ኢትዮጵያ የጀመረችውን ሁሉን አቀፍ የልማት ጉዞ ለማሳካት የአየር ንብረት መረጃዎችን በአግባቡ ስራ ላይ ማዋል ይገባል
Feb 9, 2026 121
አዳማ ፤ የካቲት 2/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የጀመረችውን ሁሉን አቀፍ የልማት ጉዞ ለማሳካት የአየር ንብረት መረጃዎችን በአግባቡ ስራ ላይ ማዋል እንደሚገባ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስገነዘበ። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የበጋ ወቅት የአየር ፀባይ ትንበያ ግምገማና የበልግ ወቅት ትንበያ ይፋ ማድረጊያ መድረክ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በአዳማ ማካሄድ ጀምሯል። መድረኩን በንግግር የከፈቱት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር አማካሪ አቶ ሞቱማ መቃሳ እንዳሉት፤ ኢንስቲትዩቱ የሚቲዎሮሎጂ መረጃዎችን አስተማማኝነትና ቅልጥፍና በማሳደግ ሁለንተናዊ ልማትን ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩሉን እየተወጣ ነው። የሚቲዎሮሎጂ መረጃዎቹ ለግብርና፣ ለውሃና ኢነርጂ፣ ለትራንስፖርት፣ ለአካባቢ ጥበቃና ለአደጋ አመራር፣ ለኢንሹራንስና ለኢንዱስትሪ ዘርፎች በሳይንሳዊ መንገድ ተተንትነው መቅረባቸውን ገልፀዋል። እነዚህ የትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃዎች ለውሳኔ ሰጪዎችና ለተጠቃሚው ማህበረሰብ ከፍተኛ እገዛ አድርገዋል ብለዋል። ኢትዮጵያ የጀመረችውን ሁሉን አቀፍ የልማት ጉዞን ለማሳካት የአየር ንብረት መረጃዎችን በአግባቡ ስራ ላይ ማዋል እንደሚገባም አማካሪው አሳስበዋል። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፈጠነ ተሾመ በበኩላቸው፤ ኢንስቲትዩቱ ከአየር ሁኔታና ፀባይ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች በየወቅቱ ለተጠቃሚዎች እየሰጠ ይገኛል ብለዋል። የበጋ፣ የበልግ፣ የክረምት የአየር ሁኔታና ፀባይ ትንበያዎችና የቅድመ ማስጠንቀቂያ አገልግሎቶች ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች በማዋል ውጤት ማስገኘታቸውን አንስተዋል። የበጋ ወቅት የአየር ሁኔታ በጊዜና በቦታ ትንበያ ከክስተቶች ጋር በእጅጉ የተጣጣመ መሆኑን አስረድተዋል። በዛሬው መድረክም የአገራችን የበልግ ወቅት ዝናብ አዎንታዊና አሉታዊ ተፅእኖን ለመቋቋም ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ነው ብለዋል። ህብረተሰቡም በኢንስቲትዩቱ የሚሰጠውን ትንበያ እና ቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃ በሚገባ በመከታተል ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባው ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡
በጋምቤላ ክልል የሙቀቱ መጠን እየጨመረ በመምጣቱ በመንግስት የስራ ስዓት ላይ ለውጥ ተደረገ
Feb 7, 2026 135
ጋምቤላ፤ ጥር 30 /2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል የሙቀቱ መጠን እየጨመረ በመምጣቱ የመንግስት የስራ ስዓት ላይ ለውጥ መደረጉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና ካቢኔ ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ኡቶው ኡኮት፤ የሙቀቱ መጠን እየጨመረ በመምጣቱና ለስራ አስቸጋሪ በመሆኑ ከፊታችን ሰኞ የካቲት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የስራ ሰዓት ለውጥ መደረጉን ገልጸዋል። የተደረገው የሰዓት ለውጥ ለቀጣዮቹ ሶስት ወራት የሚቀጥል መሆኑን ጠቁመው በዚሁ መሰረት ሁሉም የመንግስት ተቋማት ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስበዋል። በለውጡ መሰረትም ቀደም ሲል ከጧቱ 1:00 እስከ 6: 30 የነበረው ከ1:00 አስከ 5:30 እንዲሆን እንዲሁም ከስዓት በኋላ ከ9:00 እስከ 11:30 የነበረው 10:00 እስከ 12:30 ይሆናል ብለዋል። የስራ ስዓት ለውጡ ወይና ደጋ የአየር ንብር ያላቸውን የመንጌሽና የጎደሬ ወረዳዎችን እንደማይጨምር የገለጹት ኃላፊው የክልሉ የመንግስት ሰራተኛች በተጠቀሰው ጊዜ ወደ ቢሮ በመግባት ስራቸውን በትጋት እንዲያከናውኑ አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያ ሜትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የጋምቤላ ክልል የሜትሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል ተወካይ ነብዩ ፈረደ፤ በአሁኑ ወቅት የክልሉ አማካይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን 41.4 ድግሪ ሴልሸስ መሆኑን ጠቁመዋል። የሌሊቱ ዝቅተኛው የሙቀት መጠን ደግሞ 25 ነጥብ 6 ድግሪ ሴልሸስ መሆኑን ጠቁመው ባለፉት ወራት የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በአማካኝ ከ35 ድግሪ ሴልሸስ የለሊቱ ደግሞ 22 ዲግሪ ሸልሰስ በታች እንደነበር አስታውሰዋል። በክልሉ የሞቃታማ ወራት የሚባሉት የካቲት፣ መጋቢትና ሚያዚያ ወራት ሲሆኑ በእነዚህ ወራት ውስጥ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን እስከ 45 ድግሪ ሴልሸስ የሚደርስበት ጊዜ እንዳለ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የኢጋድ የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ተሳትፎ እና ቀጣናዊ የትኩረት መስኮች
Feb 9, 2026 93
አዲስ አበባ፤ የካቲት 2/2018(ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ሰላም እና የውሃ ሀብቶችን ጨምሮ ቀጣናዊ የትኩረት መስኮች ላይ ትኩረት ያደረገ ተሳትፎ እንደሚኖረው አስታወቀ። የህብረቱ ጉባኤ የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በመል መሪ ሐሳብ በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ይካሄዳል። ቀደም ብሎ የካቲት 4 እና 5 ቀን 2018 ዓ.ም 48ኛው የህብረቱ የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ይካሄዳል። በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ የተመራ ልዑክ በጉባኤው ላይ ይሳተፋል። ኢጋድ በቀጣናው ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ይዞ እንደሚቀርብ አስታውቋል። ሰላም እና ደህንነት፣ የአየር ንብረት፣ የውሃ ሀብቶች እና ቀጣናዊ ትስስር ከአጀንዳዎቹ መካከል በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው። ኢጋድ በጉባኤው የሚኖረው ተሳትፎ ከቀጣናዊ አጀንዳዎች እና ከአጀንዳ 2063 ግቦች ጋር የተቆራኙ መሆናቸውን አመልክቷል። በዋና ጸሀፊው የሚመራው ልዑክ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን፣ ከህብረቱ አባል ሀገራት ጋር በተለያዩ ቀጣናዊ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር ተመላክቷል። ኢጋድ የቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች የቅንጅት እና የትብብር ማዕቀፍ ሊቀ መንበርነት በጉባኤው ላይ ለደቡባዊ አፍሪካ ልማት ትብብር ኮንፈረንስ(ሳዴክ) ያስረክባል። ይህም ለአህጉራዊ ትብብር ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ ገልጿል። በሚኖሩት ምክክሮች እና ውይይቶች ኢጋድ የአፍሪካ ቀንድ የትኩረት መስኮችን ወደ አህጉራዊው መድረክ በማምጣት የሰላም፣ አይበገሬነትና የጋራ ብልጽግና አጀንዳዎች ለማሳለጥ እንደሚሰራ መግለጹን ኢዜአ ከተቋሙ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ኮሚሽነሮች
Feb 8, 2026 208
የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የሕብረቱ የሥራ አስፈጻሚ እና አሥተዳደራዊ ክንፍ ነው። ኮሚሽኑ የሕብረቱን የዕለት ተዕለት ሥራዎችን የሚያከናውን ሲሆን፤ ፖሊሲዎችን ይተገብራል። በተጨማሪም የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት፣ ከቀጣናዊ ተቋማት እና አደረጃጀቶች ጋር ያላቸው ትብብር እንዲጠናከር የማስተባበር ሚና ይወጣል። የሕብረቱን በጀት እና ሀብቶችም ያሥተዳድራል። የተለያዩ የአፍሪካ ሕብረት አደረጃጀቶች የተሰጣቸውን ኃላፊነት በሚገባ እንዲወጡም ድጋፍ ያደርጋል። ኮሚሽኑ በሊቀ መንበር የሚመራ ሲሆን፤ ምክትል ሊቀ መንበር እና የተለያዩ ዘርፎች የሚመሩ ኮሚሽነሮችንም ይዟል። በአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ሊቀ መንበርነት የሚመራው የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን በሥሩ ሥድስት ኮሚሽኖች አሉት። እነሱም:- የግብርና፣ ገጠር ልማት ብሉ ኢኮኖሚና ዘላቂ ከባቢ አየር ኮሚሽን - በኢስዋቲኒው ሞሰስ ቪላካቲ የሚመራ፤ የኢኮኖሚ ልማት፣ የንግድ፣ ኢንዱስትሪ እና ማዕድን ኮሚሽን - በኢኳቶሪያል ጊኒዋ ፍራንቺስካ ቻቹፕ ቤሎቤ የሚመራ፤ የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽን - በብሩንዲያዊው ፕሮፌሰር ጋስፓርድ ባያንኪምቦና የሚመራ፤ የመሠረተ ልማትና ኢነርጂ ኮሚሽን - በደቡብ አፍሪካዊቷ ሌራቶ ማታቦጅ የሚመራ፤ የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደኅንነት ኮሚሽን - በናይጄሪያዊው አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ የሚመራ፤ የጤና፣ ሰብዓዊ ጉዳዮችና የማኅበራዊ ልማት ኮሚሽን - በጋናዊቷ አምባሳደር አማ ትውም አሞን የሚመራ፤ ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ኮሚሽነሮች መካከል ሦስቱ ሴቶች ናቸው። አንድ ኮሚሽነር ለአራት ዓመት የሚያገለግል ሲሆን፤ ኮሚሽነር ለመሆን በሚደረግ ምርጫ በድጋሚ ለመመረጥ መወዳዳር ይችላል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር የሆኑት መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እ.አ.አ በ2025 በአዲስ አበባ በተካሄደው 38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ በተካሄደ ምርጫ፤ ለአራት ዓመት በሊቀ መንበርነት እንዲመሩ መመረጣቸው ይታወሳል። እንዲሁም አልጄሪያዊቷ አምባሳደር ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ እ.አ.አ በ2025 በተካሄደው ምርጫ የኮሚሽኑ ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው ተመርጠዋል። አምባሳዳር ሰልማ ከሩዋንዳዊቷ ዶክተር ሞኒክ ንሳንዛባጋንዋ በኋላ፤ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው የተመረጡ ሁለተኛ ሴት ባለሥልጣን ናቸው። 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም፤ ከዚህ ቀደም ብሎ ደግሞ 48ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት የካቲት 4 እና 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡ የዘንድሮው ጉባዔ “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በመል መሪ ሐሳብ ይካሄዳል፡፡ ኢትዮጵያም ጉባዔው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ዝግጅቷን አጠናቅቃለች።
የአፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ የምታስተናግዳቸው አህጉራዊ ሁነቶች
Feb 4, 2026 334
በሙሴ መለሰ የዓለም ስርዓት በፍጥነት እየተቀያየረ ይገኛል። አፍሪካ በዚህ ተለዋዋጭ ስርዓት ውስጥ የሚገባትን ቦታ የመያዝ ጉዳይ የመነጋገሪያ አጀንዳ ከሆነ ሰነባብቷል። አፍሪካ በርካታ ወጣት የያዘች እና ብዝሃ የተፈጥሮ ፀጋዎች ያሏት አህጉር ናት። በአፍሪካ ተግባራዊ የተደረገው አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና በቀጣናው የንግድ ትስስርን በማሳለጥ እድገትን የማፋጠን ተስፋ ተጥሎበታል። አፍሪካ እድሎቿን በሚገባ ለመጠቀምና የሚስተዋሉ ፈተናዎቿን ለመሻገር ምላሽ የምትሰጥበት የልማት እና እድገት ጉዞዋን ከመበየን ባለፈ በዓለም መድረክ የሚኖራትን ሚናም ይወስናል። በአህጉር ደረጃ የተቀመጡ እንደ አጀንዳ 2063 እና የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ያሉ አህጉራዊ ማዕቀፎች እንዲሳኩ ጠንካራ የፖለቲካ ቁርጠኝነት ያስፈልጋል። መንግስታት፣ የግሉ ዘርፍ እና የልማት አጋሮች ትብብራቸው ማጠናከር ይኖርባቸዋል። የተገቡ ቃልኪዳኖችን ወደ ሚለካ ውጤት ለመቀየር ዘላቂነት ያለው አመራር ሰጪነት፣ ኢንቨስትመንትን ማጠናከር እና ተከታታይነት ያለው ውይይቶችን ማድረግ ይገባል። ውሳኔ ሰጪዎችን በአንድ መድረክ የሚያገናኙ ቀጣናዊ እና አህጉራዊ መድረኮች በአጀንዳዎች ላይ የተቀናጀ የተግበባር ምላሽ ለመስጠት ቁልፍ ሚና አላቸው። አፍሪካ እድሎቿን በመጠቀም እና ፈተናዎቿን በማለፍ መንገድ ላይ በሆነችበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ሁለት ወሳኝ አህጉራዊ ሁነቶችን ታስተናግዳለች። 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ይካሄዳል። የዘንድሮው መሪ ሀሳብ በአፍሪካ የውሃ ደህንነትና ንጽህና አጠባበቅ ላይ ትኩረቱን አድርጓል። “ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” የመሪዎች ጉባኤ መሪ ሀሳብ ነው። ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተረጋገጠ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓት ዘላቂ ልማት፣ አካታች እድገት፣ ጤናማ ማህበረሰብና ጠንካራ ስነ ምህዳር መገንባት፣ የተፈጥሮ ሀብት ዘላቂ አጠቃቀምና የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ከአጀንዳ 2063 ግቦች ጋር የተሳሰረ መሆኑ ተገልጿል። የመሪዎች ጉባኤው በመሪ ሀሳቡ በጥልቀት በመምከር የተለያዩ የውሳኔ ሀሳቦች ያስተላልፋል ተብሎም ይጠበቃል። ከመሪዎቹ ጉባኤ አስቀድሞ 48ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ የካቲት 4 እና 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል። 51ኛው የአፍሪካ ህብረት ቋሚ ኮሚቴ ተወካዮች (PRC) ስብሰባ ከጥር 4 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተካሂዷል። በስብሰባው የሕብረቱ ተቋማት አመራሮች፣ የሕብረቱ አባል ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ተሳትፈዋል። ስብሰባው የካቲት 4 እና 5 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 48ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ እንዲሁም የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚከናወነው 39ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ ረቂቅ አጀንዳዎች ላይ መክሯል። ኮሚቴው በ2026 የአፍሪካ ህብረት መሪ ሀሳብ ላይ ምክረ ሀሳቦችን አቅርቧል። የኮሚቴው መደበኛ ስብሰባ ለዋናው ጉባኤ እንደ ይፋዊ የዝግጅት ስብሰባ የሚያገለግል ነው። ከአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ማግስት ሌላኛው በኢትዮጵያ የሚካሄደው ዘጠነኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም ነው። የቢዝነስ ፎረሙ የካቲት 9 እና 10 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን(ኢሴኤ) ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሁነቱን አዘጋጅተውታል። “የአፍሪካን መጻኢ ጊዜ በፋይናንስ መደገፍ፤ ስራ እና ኢኖቬሽን ለዘላቂ ትራንስፎርሜሽን” የፎረሙ መሪ ሀሳብ ነው። የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም በአፍሪካ የልማት እና የኢኮኖሚ እድገት ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን በማድረግ በየዓመቱ የሚካሄድ ከፍተኛ አህጉራዊ የምክክር መድረክ መሆኑን የኢሲኤ መረጃ ያመለክታል። በፎረሙ ላይ አጋርነትና የኢንቨስትመንት መጠንን ማሳደግ በተለይም የመንግስት እና የግል የተቀናጀ የፋይናንስ አቅርቦትን ጨምሮ የተለያዩ የፋይናንስ አማራጮችን ማስፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ይወያያል። የወጣቶችን የኢኖቬሽን ስራ ከፋይናንስ አቅርቦት ጋር የሚያስተሳስር የአፍሪካ የወጣቶች አይበገሬነትና ትራንስፎርሜሽን ማዕቀፍ ይፋ ይሆናል። በኢሲኤ የበለጸገውና የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ የፋይናንስ ቃል ኪዳኖችን ትግበራ የሚከታታልና የሚቆጣጠር ስርዓትም በፎረሙ ይፋ ሆኖ ወደ ትግበራ ይገባል። ለሁለት ቀናት በሚቆየው ሁነት ላይ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች የምክክር መድረኮችና የባለሙያዎች ውይይቶች ይደረጋሉ። አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችና የፈጣራ ባለሙያዎችን ከባለሀብቶች እና ፋይናንስ አቅራቢዎች ጋር የሚያገናኝ አውደ ርዕይም ይካሄዳል። ሁነቶቹ ቃል ኪዳኖችን ወደ ተጨበጡ የኢኮኖሚ ፕሮጀክቶች ለመቀየር አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉም ተመላክቷል። ከአህጉራዊ ሁነቶቹ ባሻገር የባለብዙ ወገን መድረክ የሆነው የአፍሪካ እና ጣልያን ጉባኤ የካቲት 6 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ ካለፈው ታሪካዊ ግንኙነቶች ፣ እያደገ ከመጣው የኢኮኖሚ ትብብር እና የጋራ ፈተናዎችን የመፍታት ቁርጠኝነት አኳያ በአፍሪካ እና በጣልያን መካከል አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት እንደሆነ ታምኖበታል። ኢትዮጵያ አህጉራዊ ሁነቶቹን ማዘጋጀቷ በአፍሪካ ዲፕሎማሲ ውስጥ ጸንቶ የቆየውን የመሪነት ሚናዋን እንዲሁም የአህጉራዊ ምክክር፣ የባለብዙ ወገን ውይይቶችና ስትራቴጂካዊ ሀሳቦች የሚንሸራሸሩባት ማዕከልነቷንም አጉልቶ የሚያሳይ ነው። የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባ በኮሪደር ልማት እና በከተማ ማዘመን ስራ በፍጥነት እየተለወጠች ሲሆን የሁነቱ ተሳታፊዎች ከስብሰባው ባለፈ የመዲናዋን አዲስ መልክ የመመልከት እድል ያገኛሉ። የእነዚህ አህጉራዊ ስብሰባዎች ስኬት የሚለካው በአቋም መግለጫ ሳይሆን አጋርነትን በማጠናከር፣ የኢንቨስትመንት ፍሰትን በማሳደግና የሚጨበጥ ውጤት በአህጉሪቱ በማስመዝገብ ነው። በዚህ ወሳኝ ወቅት ኢትዮጵያ የምታዘጋጃቸው አህጉራዊ ሁነቶች አህጉራዊ ትስስርን በማጠናከርና በዓለም ጉዳዮች ላይ የአፍሪካን ድምጽ ከፍ ለማድረግ መልካም አጋጣሚ ይፈጥራል። ኢትዮጵያ ሁነቶቹን ለማስተናገድ ዝግጅቷን አጠናቃ እንግዶቿን በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች። አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችና የፈጣራ ባለሙያዎችን ከባለሀብቶች እና ፋይናንስ አቅራቢዎች ጋር የሚያገናኝ አውደ ርዕይም ይካሄዳል። ሁነቶቹ ቃል ኪዳኖችን ወደ ተጨበጡ የኢኮኖሚ ፕሮጀክቶች ለመቀየር አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉም ተመላክቷል። ከአህጉራዊ ሁነቶቹ ባሻገር የባለብዙ ወገን መድረክ የሆነው የአፍሪካ እና ጣልያን ጉባኤ የካቲት 6 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ ካለፈው ታሪካዊ ግንኙነቶች ፣ እያደገ ከመጣው የኢኮኖሚ ትብብር እና የጋራ ፈተናዎችን የመፍታት ቁርጠኝነት አኳያ በአፍሪካ እና በጣልያን መካከል አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት እንደሆነ ታምኖበታል። ኢትዮጵያ አህጉራዊ ሁነቶቹን ማዘጋጀቷ በአፍሪካ ዲፕሎማሲ ውስጥ ጸንቶ የቆየውን የመሪነት ሚናዋን እንዲሁም የአህጉራዊ ምክክር፣ የባለብዙ ወገን ውይይቶችና ስትራቴጂካዊ ሀሳቦች የሚንሸራሸሩባት ማዕከልነቷንም አጉልቶ የሚያሳይ ነው። የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባ በኮሪደር ልማት እና በከተማ ማዘመን ስራ በፍጥነት እየተለወጠች ሲሆን የሁነቱ ተሳታፊዎች ከስብሰባው ባለፈ የመዲናዋን አዲስ መልክ የመመልከት እድል ያገኛሉ። የእነዚህ አህጉራዊ ስብሰባዎች ስኬት የሚለካው በአቋም መግለጫ ሳይሆን አጋርነትን በማጠናከር፣ የኢንቨስትመንት ፍሰትን በማሳደግና የሚጨበጥ ውጤት በአህጉሪቱ በማስመዝገብ ነው። በዚህ ወሳኝ ወቅት ኢትዮጵያ የምታዘጋጃቸው አህጉራዊ ሁነቶች አህጉራዊ ትስስርን በማጠናከርና በዓለም ጉዳዮች ላይ የአፍሪካን ድምጽ ከፍ ለማድረግ መልካም አጋጣሚ ይፈጥራል። ኢትዮጵያ ሁነቶቹን ለማስተናገድ ዝግጅቷን አጠናቃ እንግዶቿን በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች።
በኒጀር በደረሰ ጥቃት መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው የአስካይ አየር መንገድ አውሮፕላኖች ተጠግነው በቅርቡ አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ
Feb 3, 2026 207
አዲስ አበባ፤ ጥር 26/2018(ኢዜአ)፦ በኒጀር ዋና ከተማ በደረሰ ጥቃት መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት የአስካይ አየር መንገድ አውሮፕላኖች ተጠግነው በቅርቡ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ ፡፡ አየር መንገዱ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጠው ማብራሪያ ባለፈው ሐሙስ ጥር 21/ 2018 ዓ.ም ሌሊት በኒጀር ዋና ከተማ ኒያሚ አውሮፕላን ማረፊያ በደረሰው ጥቃት ሁለት የአስካይ አየር መንገድ ቦይንግ 737 አውሮፕላኖች መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ፡፡ አውሮፕላኖቹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አጋር የሆነው የአስካይ አየር መንገድ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አማካኝነት ከአውሮፕላን አከራዮች የተከራያቸው እና በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የተመዘገቡ መሆናቸውን አስረድቷል፡፡ በአውሮፕላኖቹ ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመገምገም የተላከው የቴክኒክ ቡድን ጉዳቱ መጠነኛ መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን አውሮፕላኖቹ ተጠግነው በቅርቡ ወደ አገልግሎት እንደሚገቡም ተገልጿል ::
ሐተታዎች
ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ያልዘነጉ የቦረና ቅን ልቦች
Jan 25, 2026 477
የሆስፒታሎችን የሕክምና ቁሳቁስ ፍላጎት በመገንዘብ አሳድጎ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ያልዘነጉ የቦረና ቅን ልቦች። ዶክተር አብዱራህማን ሮኔ ይባላሉ። ትውልድና ዕድገታቸው በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ተልተሌ በተሰኘ አካባቢ ነው። የቀለም ትምህርት በሀገር ቤት ከተከታተሉ በኋላ ወደ ሀገረ አሜሪካ በማቅናት ኑሯቸውን በዚያው አድርገዋል። ለበርካታ ዓመታት ሕይወታቸውን በአሜሪካን ሀገር እየመሩ የሚገኙት ዶክተር አብዱራህማን ከሁለት ዓመታት በፊት ለቤተሰብ ጥየቃ ወደ ትውልድ አካባቢያቸው ቦረና አቀኑ። የጉዟቸው ዓላማ ለዓመታት የናፈቋቸውን ቤተሰቦቻቸውን ለመጠየቅ ብቻ እንደነበር ያስታውሳሉ። በቤተሰብ ጥየቃ ቆይታቸውም በቦረና ዞን ተልተሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን የሚጎበኙበት አጋጣሚ ተፈጠረ። ጉብኝታቸውም ሆስፒታሉ በኪነ-ሕንፃ የተዋበ መሆኑን ነገር ግን የህክምና ግብዓት እጥረት ያለበት ሆኖ ማግኘታቸውን ይናገራሉ። በተልተሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ምልከታቸው በሕክምና ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ታካሚዎች ሲቸገሩ ማየታቸው የወቅቱ አሳዛኝ ትውስታ እንደነበርና ይህን እጥረት ወደ አሜሪካን ሀገር ሲመለሱ የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው መወሰናቸውን አስታውሰዋል። ዶክተር አብዱረሃማን በተልተሌ አካባቢ ተወልደውና አድገው ለሕክምና ባለሙያነት ያበቃቸውን ትምህርት የቀሰሙ ሰው በመሆናቸው በሆስፒታሉ የተመለከቱት የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት የሺዎችን ሕይወት የሚታደግ ሰብዓዊ ፕሮጀክት የሚቀረጽበት ሃሳብ እንዲወለድ ምክንያት ሆኗል። ከዚያም የራሳቸውን የሕክምና ሙያ ዕውቀትና በውጭ ያካበቱትን ግንኙነት በመጠቀም መነሻቸውን ባለፈው ዓመት ለተልተሌ እና ሜጋ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ዘመናዊ የሕክምና ቁሳቁስ በድጋፍ ማበርከታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ዓመትም የሞያሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ጨምሮ ለሶስት ትላልቅ የጤና ተቋማት ዘመናዊ ሕክምና መሳሪያዎችን አበርክተዋል። እነኚህ የሕክምና መሳሪያዎች አሳድጎ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ያስታወሱበት በጎ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል። በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ያስተማራቸውን ማህበረሰብ በማስታወስ መንግስት የዜጎችን የሕክምና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ለማስፋት የሚያደርገውን ጥረት እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል። ሌላኛው በአሜሪካን ሀገር በሕክምና ሙያ የሚያገለግሉት ዶክተር ዋቆ ዳደቻ በበኩላቸው፤ ሁሉም ዜጋ በትብብር መስራት ከቻለ የማህበረሰብን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ይቻላል ይላሉ። ይህ የሆስፒታሎችን የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት ለማሟላት የሚደረገውን ተሳትፎ ሁሉም በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ዜጎች ሊማሩበት የሚገባ በጎ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግስት የሕክምና ተቋማትን ጥራትና ደረጃ ለማሻሻል የሚያደርገውን ጥረት በማገዝ አሳድጎ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ማሰብ እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ፤ በውጭ የሚኖሩ የሕክምና ሙያተኞች የሚያደርጉት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ በአርዓያነት የሚወሰድ ነው ብለዋል። በዶክተር አብዱራህማን መሪነት ለቦረና አካባቢ ሆስፒታሎች የተደረገው የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍም የተቋማቱን የጤና አገልግሎት ጥራት በማስጠበቅ በኩል ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን በመግለጽ። በቀጣይም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የህዝባቸውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በማገዝ በኩል የበኩላቸውን ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ አቅርበዋል።
እኩል አጋርነትን መፍጠር፤ አዲሱ የአፍሪካ እና ጣልያን የትብብር ምዕራፍ
Dec 30, 2025 812
የአፍሪካ እና ጣልያን ግንኙነት የጀመረው በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ጣልያን እ.አ.አ በ1947 የተፈራረመቻቸው የሰላም ስምምነቶች ቅኝት ግዛት እና የአንድ አካል የፖለቲካ የበላይነት እንዲያከትም አድርጓል። በድህረ ቅኝ ግዛት ዘመን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላት ግንኙነት ከቅኝ አገዛዝ የሁለትዮሽ ትስስር ወደ የኢኮኖሚ ትብብር ተሸጋግሯል። ወቅቱ አፍሪካውያን ሉዓላዊነታቸውን የበለጠ ያረጋገጡበትና ጣልያን ከአፍሪካ ጋር በአዲስ መልክ አጋርነቷን ያደሰችበት ነበር። ከቅኝ ግዛት በኋላ የአፍሪካ እና የጣልያን ትብብር በባህል መስክ ላይ ብቻ የተገደበ ነው። የንግድ እና የቴክኒክ ትብብሩ ውስን ነበር። እ.አ.አ ከ1990ዎቹ መግቢያ አንስቶ የአፍሪካ እና ጣልያን ስትራቴጂክ አጋርነት እያበበ የመጣበት ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል። የዲፕሎማሲ ሚሲዮኖች እና የንግድ ቢሮዎች መጨመር እንዲሁም የኢኮኖሚ ትብብር አድማስ መስፋት የትብብሩ መገለጫ ሆኗል። ዘመናዊው የአፍሪካ እና ጣልያን አጋርነት ከእርዳታ ወደ የጋራ እድገት ምዕራፍ መሸጋገር ችሏል። የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲው የሁለቱን ወገኖች የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትብብር አጠናክሯል። የልማት ትብብሩ እርዳታን ከመለገስ ወጥቶ እድገት ተኮር ሆኗል። ከደህንነት ጋር በተያያዘም የፍልሰት አስተዳደር እና ሽብርተኝነት መዋጋት አንዱ የትብብር መገለጫ ነው። የጣልያን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የአፍሪካ እና ጣልያን የባለፈው ጊዜ የነበሩ ፈተናዎች እውቅና በመስጠት አሁን ላይ የሁለቱን ወገኖች የጋራ ፍላጎት ማስጠበቅ ላይ ትኩረቱን አድርጓል። የፖሊሲው ሰነድ “ ዋጋ እና ክብርን ማዕከል ያደረገ” ዲፕሎማሲ በሚልው እሳቤው ከአፍሪካ ጋር ላለው ወዳጅነት ከፍተኛ ግምት እንደሚሰጥ አስቀምጧል። እ.አ.አ በ2024 በሮም የተካሄደው የጣልያን-አፍሪካ ጉባኤ ላይ በቅርብ ጊዜያት ከነበሩ ከፍተኛ መድረኮች መካከል ይጠቀሳል። በጉባኤው ላይ የ45 የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት መሪዎች፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና የልማት አጋሮች ተሳትፈዋል። ጉባኤው የተካሄደበት ዓመት ጣልያን የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ሊቀ መንበር የነበረችበት ወቅት ሲሆን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላትን ትብብር ማጠናከር የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ አንኳር ትኩረት ሆኗል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በወቅቱ ጉባኤውን የአፍሪካ እና ጣልያን ትብብርን በአዲስ መልክ የበየነና ትብብሩ እኩል በቆሙ ወገኖች መካከል ያለ ትስስር እንደሆነ አንስተዋል። ሜሎኒ የሰጪ እና ተቀባይ ዘመን እንዳበቃና የጋራ እድገት እና የጋራ ፍላጎት ላይ የተመረኮዘ ግንኙነት አዲሱ የትብብር ምዕራፍ እንደሆነም ተናግረዋል። በወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር የነበሩት ሙሳ ፋቂ ማህማት የጣልያንን አዲሱን የፖሊሲ ለውጥ ያደነቁ ሲሆን አፍሪካ ከቃል ባለፈ እውነተኛ አጋርነትን ትፈልጋለች ብለዋል። የፖሊሲ ሽግግሩ ፍትሃዊነትን ያረጋገጠ እና እኩልነትን መሰረት ያደረገ ዓለም መፍጠርን ያማከለ መሆን እንዳለበትም አንስተዋል። ጣልያን የገባቻቸውን ቃሎች ወደ ተግባር መቀየር አለባት ሲሉም ማህማት ተናግረው ነበር። በጉባኤው ላይ ይፋ ከተደረጉ ቁልፍ ማዕቀፎች አንዱ የማቴይ እቅድ (The Mattei Plan) ይገኝበታል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ይፋ ያደረጉት የማቴይ ፕላን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላት የኢኮኖሚ እና የልማት ትብብር ማጠናክርን ያለመ ነው። የ5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ የስትራቴጂክ ማዕቀፉ በጣልያኑ የብሄራዊ የዘይት እና ነዳጅ ኩባንያ መስራች ኤነሪኮ ማቴይ የተሰየመ ነው። ኩባንያው ከአፍሪካ ጋር ከአጭር ጊዜ እርዳታ የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ ትብብርን በማስቀደም እየሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል። የአፍሪካን የኢኮኖሚ እድገት መደገፍ፣ የስራ እድሎችን ማስፋት፣ አፍሪካን የአውሮፓ የኢነርጂ አቅራቢ አጋር የማድረግ ስራን ማስተዋወቅ፣ ለአፍሪካውያን የኢኮኖሚ ችግሮች መፍትሄ በመስጠት ኢ-መደበኛ ፍልሰትን ከምንጩ ማድረቅ እንዲሁም ከበጎ አድራጎት የተላቀቀ የጋራ ተጠቃሚነት እና ትብብርን መፍጠር የእቅዱ አበይት አላማዎች ናቸው ። ለአራት ዓመታት የሚቆየው የማቴይ እቅድ በአፍሪካውያን በበጎ መልኩ የታየ ሲሆን እቅዱ ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ጠንካራ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ ተነስቷል። እ.አ.አ በ2023 የአፍሪካ እና የጣልያን የንግድ ልውውጥ 59 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ መድረሱን ይፋዊ መረጃዎች ያመለክታሉ። የንግድ ልውውጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል። የአፍሪካ ሀገራት በዋናነት የተፈጥሮ ጋዝ፣ ድፍድፍ ነዳጅ፣ የብረታ ብረት እና ማዕድናት ምርቶች እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ምርቶች የሆኑ ጥሬ እቃዎችን ወደ ጣልያን ይልካሉ። ጣልያን የኢንዱስትሪ ማሽን እና መሳሪያ፣ እሴት የተጨመረባቸው እቃዎች እና የማኑፋክቸሪንግ ምርቶች እንዲሁም የኤሌክትሪክ እቃዎች ወደ አፍሪካ ከምትላካቸው ምርቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። አጠቃላይ የንግድ ምጣኔው ሲታይ ጣልያን በገቢ አብዛኛውን ድርሻ ትይዛለች። ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ተፈጥሮ ሀብት፣ ኢነርጂ፣ መሰረተ ልማት፣ ትራንስፖርት፣ ትምህርት፣ ምርምር፣ ጤና፣ ቴክኖሎጂ፣ የፍልሰት አስተዳደር፣ ደህንነት እና አስተዳደር ከአፍሪካ እና ጣልያን የትብብር መስኮች መካከል ይገኙበታል። የ2026 የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ በየካቲት ወር አጋማሽ 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መቀመጫ እና የአህጉሪቷ መዲና ናት። ይህም ጉባኤውን የአፍሪካ ዋንኛ የዲፕሎማሲ አጀንዳ ያደርገዋል። ኢትዮጵያ በታሪክ በፓን አፍሪካ ፖለቲካ ውስጥ የመሪነት ሚና ያላት ሀገር ናት። በአሁኑ ሰዓትም በርካታ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ሁነቶችን እያዘጋጀች ትገኛለች። የሁለቱን ወገኖች አጋርነት የበለጠ ያጠናክረዋል ተብሎ ይጠበቃል። የማቴይ እቅድ ትግበራ፣ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብር፣ የአፍሪካን ተሰሚነት መጨመር፣ ፍልሰትን ጨምሮ በጋራ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ አቋም መያዝ፣ የአጋርነት እና የመግባቢያ ስምምነቶች የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤው ውጤቶች ናቸው። የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ ካለፈው ታሪካዊ ግንኙነቶች ፣ እያደገ ከመጣው የኢኮኖሚ ትብብር እና የጋራ ፈተናዎችን የመፍታት ቁርጠኝነት አኳያ በአፍሪካ እና በጣልያን መካከል አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት እንደሆነ ታምኖበታል። የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከል በሆነችው አዲስ አበባ የሚደረገው ጉባኤ አፍሪካ መር አጋርነት ለመፍጠር እና የአፍሪካን ተሰማኒነት ለመጨመር መልካም አጋጣሚን የሚፈጥር ነው።
አፍሪካውያን ሀገር በቀል አሰልጣኞች ጎልተው የታዩበት የአፍሪካ ዋንጫ !
Dec 28, 2025 762
35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል።24 ሀገራት በስድስት ምድቦች ተከፍለው ጨዋታቸውን እያደረጉ ነው። በውድድሩ ላይ ከሚሳተፉ 24 ሀገራት 12ቱ በአፍሪካውያን የሚሰለጥኑ ናቸው። የአዘጋጇ ሀገር ሞሮኮ አሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉዊ ከዛው ከሀገራቸው ናቸው። የ50 ዓመቱ አሰልጣኝ በ22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ሞሮኮን ለግማሽ ፍጻሜ አድርሰዋል።ሀገሪቷ በዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ የደረሰች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ ሀገር ሆናለች። ከእ.አ.አ 2022 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን እየመሩት የሚገኙት ሬግራጉዊ ሞሮኮን ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ የአፍሪካ ዋንጫ ባለቤት የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። የወቅቱ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ኮትዲቭዋር አሰልጣኝ የ41 ዓመቱ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድኑ ተጫዋች ኤመርሰን ፋኤ ነው። ፋኤ እ.አ.አ በ2023 በኮትዲቭዋር አስተናጋጅነት በተካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቡድኑን በመምራት ዋንጫውን እንዲያነሳ አድርጓል። በውድድሩ መሐል በውጤት ማጣት የተሰናበቱትን ፈረንሳዊውን አሰልጣኝ ጂን-ሉዊስ ጋሴት በመተካት በጊዜያዊነት አሰልጣኝ የተሾመው ፋኤ ቡድኑን ለዋንጫ ማብቃቱ አስወድሶታል። በዘንድሮው ውድድር ዋንጫውን ለማንሳት የቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው ሀገራት ተርታ የተመደበችው ሴኔጋል አሰልጣኝ የ41 ዓመቱ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ፓፔ ታው ነው። ፓፔ ታው በተጫዋችነት ዘመኑ ለሴኔጋል ባደረጋቸው 16 ጨዋታዎች አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። አሰልጣኙ ሴኔጋል ለ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ እንድታልፍ አድርጓል። ከሶስት ዓመት በፊት በአልጄሪያ በተካሄደው የሰባተኛው የአፍሪካ አገራት ሻምፒዮና(ቻን) ሴኔጋል ዋንጫውን ስታነሳ የቡድኑ አሰልጣኝ ሆኖ መርቷል። የሰባት ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ግብጽ የምትሰለጥነው በቀድሞ ኮከቧ ሆሳም ሀሰን ነው። በተጫዋችነት ዘመኑ በአፍሪካ ዋንጫ 11 ግቦችን አስቆጥሯል። በ177 ጨዋታዎች 69 ግቦችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ የብሄራዊ ቡድኑ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው። ሆሳም ሀሰን የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ በተጫዋችነት በማንሳት ስኬታማ አሰልጣኝ ነው። ሌላኛው የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ካሜሮን አሰልጣኝ የ56 ዓመቱ ዴቪድ ፓጉ ነው። ካሜሮናዊው አሰልጣኝ የተሾሙት ከሰሞኑ ነው። ቤልጂየማዊውን አሰልጣኝ ማርክ ብራይስን በመተካት ቡድኑን እንዲመሩ ኃላፊነት ተጠሎባቸዋል። በካሜሮን እግር ኳስ ባላቸው የታክቲክ መረዳት እና ብቃት የሚሞካሹት ፓጉ ቡድኑን አንድ በማድረግ የተሻለ ውጤት ያመጣሉ የሚል እምነት ተጥሎባቸዋል። ሌላኛው የውድድሩ ተሳታፊ ሀገር ዛምቢያ ናት።የ48 ዓመቱ የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን የቀድሞ ተከላካይ ሞሰስ ሲቾኔ የቡድኑ የወቅቱ ዋና አሰልጣኝ ናቸው። ከእ.አ.አ 2022 እስከ 2024 በጊዜያዊነት እና በረዳት አሰልጣኝነት ያገለገሉት ሲቾኔ በ2025 ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾመዋል። ምስራቅ አፍሪካን በውድድሩ ከሚወክሉ ሶስት ሀገራት መካከል አንዷ ሱዳና ናት። ጋናዊው ጀምስ ክዌሲ አፒያ የቡድኑ አሰልጣኝ ናቸው። አፒያ ከእ.አ.አ 2023 አንስቶ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛሉ። የጋቦን አሰልጣኝ ቲዬሪ ሞዩማ የብሄራዊ ቡድኑ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ነበር። ለ11 ዓመታት ለጋቦን ተጫውተዋል። ከእ.አ.አ 2023 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን በአሰልጣኝነት እየመሩ ይገኛል። የ44 ዓመቱ ደቡብ አፍሪካዊ ሞሬና ራሞሬቦሊ የቦትስዋና ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ናቸው። ከእ.አ.አ 2025 አንስቶ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛል። ሞሬና ከዚህ ቀደም የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ነበሩ። የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ቡርኪናፋሶ አሰልጣኝ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድን የአማካይ ተጫዋች ብራማ ትራኦሬ ነው። አሰልጣኙ ከእ.አ.አ ማርች 2024 አንስቶ ቡርኪናፋሶን እየመራ ይገኛል። ትራኦሬ ቡድኑ የተሻለ ውጤት እንዲያመጣ የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። የአንድ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ የሆነችው ቱኒዚያ አሰልጣኝ የቀድሞ የቡድኑ የተከላከይ መስመር ተጫዋች ሳሚ ትራቤልሲ ናቸው። የ57 ዓመቱ አሰልጣኝ ለቱኒዚያ ብሄራዊ ቡድን ለ10 ዓመታት በተጫዋችነት አገልግሏል። ብሄራዊ ቡድኑን ከእ.አ.አ 2025 ቱኒዚያን እየመራ ይገኛል። በአፍሪካ ደቡባዊ ክፍል የምትገኘው ሞዛምቢክ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ከሚሳተፉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት። ፍራንቺስኮ ኩዌሪዮል ኮንዴ ጁኒየር (ቺኩዊኒዮ ኩንዴ) የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ናቸው። የ60 ዓመቱ አንጋፋ አሰልጣኝ ለሞዛምቢክ ለ15 ዓመታት በተጫዋችነት አገልግለዋል። ለሀገራቸው በ43 ጨዋታዎች 12 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ኩንዴ ከእ.አ.አ 2021 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛሉ። የናይጄሪያ አሰልጣኝ የሆነው ኤሪክ ቼሌ የኮትዲቭዋር፣ ማሊ እና ፈረንሳይ ጥምር ዜግነት ያላቸው አሰልጣኝ ናቸው። ይሁንና ቼሌ የአፍሪካ የዘር ግንድ ቢኖራቸውም በፈረንሳይ መወለዳቸው የውጭ ሀገር ዜጋ ውስጥ እንዲካተት አድርጎታል። የአፍሪካውያን አሰልጣኞች በአፍሪካ ዋንጫ የማሰልጠን ምጣኔ ከሌሎቹ ወቅቶች አንጻር የአሁኑ የተሻለ ነው ማለት ይቻላል። ይህም ሀገር በቀል አሰልጣኞች እየተሰጣቸው ያለውን ትኩረት ያሳያል። 12 ሀገራት በውጭ ሀገር ዜጎች ይሰለጥናሉ። በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ አፍሪካውያን የሚያሰለጥኗቸው ወይስ የውጭ ሀገር ዜጋዎች የሚመሯቸው ሀገራት ዋንጫውን ያነሳሉ? የሚለው ጉዳይ ትኩረትን ስቧል።
የኢትዮጵያ ዲጂታል ዘመን
Dec 22, 2025 982
የኢትዮጵያ ዲጂታል ዘመን የዲጂታል ቴክኖሎጂ የተጀመረው በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። በወቅቱ የኤሌክትሮኒክ መሳሪዎችን ተጥቅሞ መረጃን በመተንተን እና መረጃን እንደ ልዩ ገጽታ በመጠቀም እና መለያ ቁጥር (ኮድ) በመስጠት አገልግሎት ላይ ይውል ነበር። ከዛ ጊዜ በኋላ በርካታ የኮምፒዩተር ፕሮግራሞች እና ማሽኖች ተፈብርከው ጥቅም ላይ መዋል ጀምረዋል። እ.አ.አ በ1946 በአሜሪካ የፔንሲሊቫኒያ ዩኒቨርሲቲ ጥቅል አገልግሎት የሚሰጥ የመጀመሪያውን የኤሌክትሮኒክ ዲጂታል ኮምፒዩተር በመስራት የዲጂታል ዘመን ጅማሮን አበሰረ። ከእ.አ.አ 1943 እስከ 45 ባለው ጊዜ ውስጥ የተሰራው ይህ ኮምፒዩተር ባለቤቶች ጆን ማውችሊ እና ጄ ፕሬስፐርት ኤከርት ናቸው። በ150 ኪሎ ዋት ኃይል የሚሰራው ኮምፒዩተር በሴኮንዶች ውስጥ በርካታ ስራዎችን ያከናውን ነበር። ኮምፒውተሩ በወቅቱ በነበሩ ባለሙያዎች ማርሽ ቀያሪ እና መሰረት ጣይ የሚል ስያሜ አግኝቷል። የዘመናዊ የዲጂታል ስርዓቶች ምሰሶ ነው የሚባለው ኢንተርኔት የተጀመረው እ.አ.አ በ1960ዎቹ መጀመሪያ ነበር። “አርፓኔት” የተሰኘ የአሜሪካ የጥናት ፕሮጀክት ኮምፒዩተሮችን ዘመኑ ከደረሰበት የኔትወርክ ስርዓቶች ጋር በማገናኘት የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲጀመር ምክንያት ሆኗል። እንግሊዛዊው የኮምፒዩተር ሳይንቲስት ቲም በርነርስ ሊ እ.አ.አ 1969 “ወርልድ ዋይድ ዌብ” (WWW) በመፍጠር ትስስርን ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ አሸጋግሯል። ድረ ገጾችን በመፍጠር እና በህዝብ ደረጃ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሰፋ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። ዲጂታል ቴክኖሎጂ ከኮምፒዩተር መሰራት ተነስቶ ወደ ዓለም አቀፍ የትስስር መሰረተ ልማትነት የተቀየረ ሲሆን በየዕለት ተዕለት የሰዎች ኑሮ፣ማህበራዊ መስተጋብር፣ ንግድ እና የመንግስታት አሰራር ላይ ከፍተኛ ለውጥ ከማምጣት ባለፈ ዘርፎች በቴክኖሎጂ እንዲቃኙ አድርጓል። ዓለም ላይ አሁን ካለው ህዝብ 73 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ነው። የዲጂታል ኢኮኖሚ የዓለምን ጥቅል ዓመታዊ ምርት (ጂዲፒ) የ15 በመቶ ድርሻን እንደሚያግዝ የተለያዩ ጥናቶች ያመለክታሉ። ሞባይል ለኢንተርኔት መስፋፋት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል። ሀገራት እ.አ.አ 2025 በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ ክላውድ ኮምፒዩቲንግ፣ ኔትወርኪንግ እና ለሌሎች ትራንስፎርሜሽ ስራዎች ያወጡት ኢንቨስትመንት ከአራት ትሪሊዮን ዶላር በላይ እንደሚልቅም ይገመታል። በአፍሪካ የሞባይል የገንዘብ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ480 ሚሊዮን በላይ ተሻግሯል። ዲጂታል ስርዓቱን የሚያሳልጡ መሰረተ ልማቶች እና የዳታ ማዕከላት በአፍሪካ መንግስታት እና የልማት አጋሮች ትብብር እየተገነቡ ነው። ዲጂታል ኢኮኖሚ ለኢኮኖሚ እድገት፣ ለትምህርት እና ክህሎት፣ ለመንግስት የአሰራር ውጤታማት፣ ለፋይናንስ አካታችነት እና ኮሙኒኬሽን ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል። ኢትዮጵያ ከእ.አ.አ 2020 በፊት የዲጂታል ምህዳሯ የተገደበ ነው ማለት ይቻላል። ዝቅተኛ የኢንተርኔት አገልግሎት ተደራሽነት፣ ለቴሌኮም አገልግሎት ከፍተኛ ክፍያ ወጪ የሚወጣበት እና በቴሌኮም አገልግሎት የመንግስት ብቻ የበላይነት የሚታይበት ነበር። ከለውጡ በኋላ መንግስት የቅድሚያ ትኩረት ከሰጣቸው ዘርፎች አማካኝነት ዲጂታል ተጠቃሽ ነው። የዲጂታል ዘርፍ ከብዝሃ የኢኮኖሚ ምንጮች አንዱ ሆኖ ነው።ዲጂታላይዜሽን ለኢኮኖሚ ዕድገት ያለውን ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባት ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል። ኢትዮጵያ ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ አካታች የሆነ የዲጂታላይዜሽን ስትራቴጂ በማዘጋጀት ወደ ትግበራ ካስገባች ሰነባብታለች። ኢትዮጵያ ከእ.አ.አ 2020 አንስቶ ለአምስት ዓመታት የሚቆይ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በማዘጋጀት ስተገብር ቆይታለች። ስትራቴጂው የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እና መንግስታዊ አገልግሎቶችን ዲጂታል የማድረግ አላማ ያደረገ ነው። በዚህም 900 ገደማ የሚሆኑ መንግስታዊ አገልግሎቶች ዲጂታላይዝድ ሆነዋል።3000 የሚሆኑ የዲጂታል አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አግኝተዋል። የፋይዳ መታወቂያ ኢኒሼቲቭ አማካኝነት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች የዲጂታል መታወቂያ ባለቤት ሆነዋል። የሞባይል እና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በከፍተኛ መጠን ጨምሯል። የአራተኛ እና አምስተኛው ትውልድ የኢንተርኔት አገልግሎት እየሰፋ መጥቷል።የዲጂታል ክህሎትም ተስፋ ሰጪ እድገት ታይቶበታል። የቴሌኮም ዘርፉ ለውጭ ክፍት እንዲሆን መንግስት ባስቀመጠው የፖሊሲ አቅጣጫ መሰረት ሳፋሪኮም ኩባንያ የቴሌኮም አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን “ምፔሳ” የተሰኘ የሞባይል የገንዘብ አገልግሎት እየሰጠም ይገኛል። የመንግስት የዲጂታል ፖሊሲዎች እና የህግ ማዕቀፎች ለዘርፉ ምቹ ምህዳር በመፍጠር ትስስር እንዲሰፋ እና አገልግሎቶች እንዲዘምኑ አስችሏል። ኢትዮጵያ ከአምስት በፊት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በማቋቋም በርካታ ስራዎችን አከናውናለች። ባለፉት አራት ተከታታይ ዓመታት በክረምት መርሃ ግብር (ሰመር ካፕም) ወጣቶች ሲማሩ እንደቆዩ አውስተው በዘርፉ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መረጃ ያሳያል። ሁሉንም ዘርፍ የሚነካው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በግብርና፣ጤና፣ አገልግሎት እና ሌሎች ዘርፎች ላይ በመግባት ስራን እያቀላጠፈ ይገኛል። በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት የሚሰበሰቡ ዳታዎች ለመንግስት እና ግል ተቋማት አገልግሎት ላይ እየዋሉ እንደሚገኝም ተገልጿል። መንግስት ወጣቶች በሰው ሰራሽ አስተውሎት አማካኝነት ሀገርን አልፎም ዓለምን የሚጠቅሙ ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያቀርቡ የሚያደርገውን ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ቴሌብር፣ መሶብ እና ዘመንን ጨምሮ ያሉ የዲጂታል አገልግሎቶች የዘርፉን እድገት በማሳለጥ ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት የዲጂታል 2030ን ስትራቴጂ ይፋ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የታለመለትን ግብ አሳክቶ መጠናቀቁን ገልጸዋል።ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 በይፋ ያበሰሩ ሲሆን ተደራሽነትን ማስፋት፣ለዜጎች እኩል እድል መፍጠር እንዲሁም በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ደግሞ የስትራቴጂው ቁልፍ መሰረታዊ ትልሞች መሆናቸውን አመልክተዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ተደራሽ፣ ፍትሃዊ እና አስተማማኝ የዲጂታል ምህዳር መፍጠር ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ብለዋል።ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ም ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት በማድረግ መዘጋጀቱን አንስተዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ሦስት ቁልፍ ትልሞች እንዳሉት የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እነዚህም ተደራሽነትን ማስፋት፤ እኩል እድል ማመቻቸትና በተቋማትና ህዝብ መካከል መተማመንን መፍጠር መሆናቸውን አብራርተዋል። ትልሞቹ እንዲሳኩም በተለይ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ስራ እንደሚከናወን ጠቁመው፤ ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ እንዲያሻሽል ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል። በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ስራዎች የመደመር መንግስት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እንዲሳካም ሁሉም በትብብር መስራት እንዳለበት ነው ጥሪ ያቀረቡት። የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እንደገለጹት፥ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በቴሌኮም ዘርፍ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነው። ለአብነትም የሞባይል ደንበኞች ቁጥርን 97 ሚሊዮን ማድረስ የተቻለ ሲሆን፣ ከዚህም ውስጥ 57 ሚሊዮኑ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ሆነዋል ሲሉ አንስተዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚዋ አክለው እንደገለጹት፥ አንድ ሺህ ሰላሳ ከተሞችም የ4ጂ ኔትወርክ ተደራሽ ሆነዋል ነው ያሉት። በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የሞባይል ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር 128 ሚሊዮን የሚደርስ ሲሆን፣ የ5ጂ ኔትወርክ ሽፋንን 100 ከተሞች ይደርሳል ብለዋል። በ2030 የዲጂታል ክፍያን ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት አንጻር አሁን ካለበት ከሰባት እጥፍ በላይ እንዲያድግም በልዩ ትኩረት ይሰራል ሲሉም አረጋግጠዋል።ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት፣ አካታችነት እና ማህበራዊ ለውጥ ቁልፍ ምሰሶ ነው። ስትራቴጂው በሚገባ ከተተገበረ፣ በቂ የዲጂታል መሰረተ ልማቶች ከተገነቡ እና ዜጎች በንቃት ከተሳተፉ ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘመን ትሩፋቶች ተጠቅማ ትልሞቿን ማሳካት እንደምትችል አያጠራጥርም።
ትንታኔዎች
ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 2, 2026 857
ክፍል ሁለት የቀጠለ የኢትዮጵያ ዘጠነኛ ተሳትፎ በአህጉራዊው መድረክ እ.አ.አ 1982 ኢትዮጵያ በሊቢያ አስተናጋጅነት በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለዘጠነኛ ጊዜ ተሳትፎዋን ማድረግ ቻለች። በውድድሩ ላይ አሁንም ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት ከአልጄሪያ፣ዛምቢያና ናይጄሪያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዎቿን አድርጋለች። በምድብ ጨዋታዎቹ በናይጄሪያ 3 ለ 0 እንዲሁም በዛምቢያ 1 ለ 0 የተሸነፈች ሲሆን ከአልጄሪያ ጋር ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይታለች። ኢትዮጵያ በምድቧ አንድ ነጥብ ብቻ በመያዝ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። በፍጻሜው ጨዋታ ጋና ሊቢያን በመለያ ምት በማሸነፍ ለሶስተኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካው ዋንጫ የተመለሰችበት ታሪካዊ ሁነት ኢትዮጵያ ከ13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በኋላ በአህጉራዊው የእግር ኳስ ውድድር መድረክ ለመሳተፍ ሶስት አስርት ዓመታታን መጠበቅ ግድ ሆኖባታል። በነዚህ 30 ዓመታት ጊዜ ውስጥ 15 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ተካሄደዋል። እ.አ.አ በ2013 በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ ውድድሩ ዳግም ተመለሰች። ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ያለፈችበት መንገድ ልብ አንጠልጣይ ነበር። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2012 በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ከሱዳን ጋር ባደረገችው የመጨረሻ ዙር የደርሶ መልስ ጨዋታ በመጀመሪያ ዙር ኦምዱርማን ላይ 5 ለ 3 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች። ሱዳን ጨዋታውን ያሸነፈችው በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በተቆጠሩ ሁለት አጨቃጫቂ የፍጹም ቅጣት ምት በግቦች ነበር። ጥቅምት 4 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ለሚደረገው የመልስ ጨዋታ በስታዲየሙ ዙሪያ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ በርካታ ተመልካች ተሰልፎ ነበር። ጨዋታው በመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ምንም መጠናቀቁ በስታዲየሙ የተገኘውን ተመልካች ጭንቅ ውስጥ ከቶ ነበር። ጭንቀቱ በስታዲየሙ ላሉት ብቻ ሳይሆን በቴሌቪዥን መስኮት ለሚከታተሉት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንም ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴ ያደረጉት ዋልያዎቹ አዳነ ግርማ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ቻሉ። ይሁንና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው ለመሳተፍ አንድ ተጨማሪ ጎል ያስፈልጋታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ወሳኟን ሁለተኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳረፈ። ግቡ ሲቆጠር በስታዲየሙ ተመልካቾች ላይ የነበረው ስሜት በከፍተኛ ደስታ የተሟላ ሲሆን ስሜታቸውንብ በእንባ የገለጹም ነበሩ። ጨዋታው በድምር ውጤት 5 ለ 5 ተጠናቆ ከሜዳ ውጪ ብዙ ባስቆጠረ በሚል ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ዳግም ወደ አፍሪካ ዋንጫ መመለስ ቻለች። ከጨዋታው በኋላ በአዲስ አበባ ስታዲየም፣በመስቀል አደባባይና በመዲናዋ የተለያዩ አውራ ጎዳናዎች፣መንደሮችና የተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ባሉ ክፍሎች የነበረው የደስታ ስሜትና ፈንጠዝያ የሚረሳ አልነበረም። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም የደስታው ተቋዳሽ ነበሩ። ኢትዮጵያን ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫው እንድትመለስ ያደረጉት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ነበሩ። ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ 16 አገራት በስድስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። ኢትዮጵያም በምድብ ሶስት ከቡርኪናፋሶ፣ናይጄሪያና ዛምቢያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከዛምቢያ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። አዳነ ግርማ በ65ኛው ደቂቃ ለኢትዮጵያ ግቡን አስቆጥሯል። በሁለተኛው ጨዋታ ኢትዮጵያ በቡርኪናፋሶ የ4 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዳለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ በናይጄሪያ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ከምድቧ ሳታልፍ ቀርታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ብትመለስም በውድድሩ ላይ ያስመዘገበችው ውጤትና ያሳየችው ብቃት የእግር ኳስ ቤተሰቡን ያስደሰተ አልነበረም። ይሁንና ብሔራዊ ቡድኑ ከደቡብ አፍሪካ ሲመለስ በአዲስ አበባ ስታዲየም በበርካታ ደጋፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል። በፍጻሜው ጨዋታ ናይጄሪያ ቡርኪናፋሶ 1 ለ 0 በማሸነፍ የአፍሪካን ዋንጫን ለሶስተኛ ጊዜ አንስታለች። ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈችው እ.አ.አ በ2021 ካሜሮን ባዘጋጀችው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነበር። ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደ ውድድሩ የተመለሰችው ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ካሜሮን፣ቡርኪናፋሶና ኬፕቨርዴ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። ኢትዮጵያ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በኬፕቨርዴ 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛው ጨዋታ ዋልያዎቹ በአዘጋጇ አገር ካሜሮን 4 ለ 1 ተሸንፈዋል። በጨዋታው ኢትዮጵያ አጥቂው ዳዋ ሁቴሳ በአራተኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ብትችልም ቪንሰንት አቡበከርና ቶኮ ኢካምቢ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር የማይበገሩትን አንበሶች አሸናፊ አድርገዋል። በወቅቱ በአሰልጣኝ ውበቱ የተመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ከቡርኪናፋሶ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። ለብሔራዊ ቡድኑ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ጌታነህ ከበደ በፍፁም ቅጣት ምት ነበር። ኢትዮጵያ በምድቡ አንድ ነጥብ ብቻ በማግኘት ከምድቧ የመጨረሻውን ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። የኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ በቁጥሮች ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የ11 ጊዜ ተሳትፎ ኢትዮጵያ 31 ጨዋታዎችን አድርጋ 8ቱን ስታሸንፍ 19 ጊዜ ተሸንፋለች። አራት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥታለች። በነዚህ 31 ጨዋታዎች ኢትዮጵያ 33 ግቦችን ስታስቆጥር 67 ጎሎችን አስተናግዳለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ በሰፊ ግብ ያሸንችባቸው ጨዋታዎች ሁለት ናቸው። እ.አ.አ በ1962 ራሷ አዘጋጅታ ራሷ በወሰደችው ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቱኒዚያና ግብጽን በተመሳሳይ 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው በሰፊ የግብ ልዩነት የተሸነፈችው እ.አ.አ በ1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሲሆን በወቅቱ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ውጤት ተረታለች። ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ በውድድሩ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግብ ያስተናገደችበት ሲሆን 12 ጎሎች ተቆጥረውባታል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግቦችን ያስቆጠረችባቸው ውድድሮች እ.አ.አ በ1952 እና በ1968 በቅደም ተከተል ሶስተኛውንና ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ባዘጋጅበት ወቅት ነው። በነዚህ ውድድሮች ላይ በተመሳሳይ ስምንት ግቦችን አስቆጥራለች። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ አዘጋጅታለች። ኢትዮጵያውያኖቹ አጥቂዎች ሉቺያኖ ቫሳሎና መንግስቱ ወርቁ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ በተመሳሳይ 8 ግቦችን በማስቆጠር በአፍሪካ ዋንጫ የምንጊዜም የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ዝርዝር ውስጥ 21ኛ እና 22ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። እንደ መውጫ ኢትዮጵያ ሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አትሳተፍም። የአፍሪካ እግር ኳስ መስራችና ፈር ቀዳጅ እየተባለች የምትጠራው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ተሳትፎዎቿ ከሰሜን፣ደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አገራት ጋር ብርቱ ፉክክር በማድረግ መልካም የሚባል ውጤት አስመዝግባለች። ይሁንና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአፍሪካ ዋንጫ ያላት ተሳትፎ እየተቀዛቀዘ መጥቶ ብሔራዊ ቡድኑ ከምድቡ ማለፍ እየተሳነው ነው። የስፖርት ቤተሰቡና ተንታኞች ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን መገንባት አለመቻሉ፣የእግር ኳስ እድገቱ ወደ ኋላ መቅረቱ፣ የአጥቂ መስመሩ ክፍል የአጨራረስ ድክመት፣ ለወጣት ተጫዋቾች እድል አለመስጠት፣የአሰልጣኞች በየጊዜው መለዋወጥ፣ለእገር ኳሱ የሚሰጠው ትኩረት የሚጠበቀውን ያህል አለመሆኑና እግር ኳሱ በስፖርቱ ባለፉ ሰዎች አለመመራቱን ጨምሮ በርካታ ምክንያቶች ይቀመጣሉ። ጠንካራና ተወዳዳሪ ቡድን የመገንባት ስራ ትኩረት ያሻዋል። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2029 የሚካሄደውን 37ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥያቄ ማቅረቧ የሚታወቅ ነው። በዚህም ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፍ ጠንካራና አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን መገንባት የሚያስችል "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት ተጀምሯል፡፡ “ሮድ 2029"ን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ከሁሉም አካባቢዎች 85 ብቃት ያላቸው ታዳጊዎች ተመርጠው ለዘጠኝ ወራት ስልጠና ወስደው ብቃት ያላቸው ተመርጠዋል፡፡ ከእነዚህ ታዳጊዎች መካከል 26ቱ በብቃታቸው ተመርጠው የ"ሮድ 2029" ግብን ማሳካት የሚያስችል የክፍል ውስጥ እና የሜዳ ላይ ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ታዳጊዎቹ ኢትዮጵያ በህዳር ወር ባስተናገደችው ከ17 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማህበር ምክር ቤት ዞን (ሴካፋ) ተሳትፎ አድርጓል። የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በውድድሩ ላይ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ በሞሮኮ በሚካሄደው 16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ ይታወቃል። "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት በአሜሪካዊ እና ኢትዮጵያዊ አሰልጣኞች ጥምረት የሚካሄድ ሲሆን በኢትዮጵያ ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል። በዲጂታል አማራጮች ተደግፎ በንድፈ ሀሳብና በተግባር የሚሰጥ ሥልጠና መሆኑን በማንሳት፤ በእስካሁኑ ሂደት ተስፋ ሰጭ ውጤት ታይቶበታል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2029 የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እንድትመረጥ የቴክኒክ ጉዳዮችን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑንን ፌዴሬሽኑ አመልክቷል። ታዳጊዎችን እግር ኳስ ልማት፣ የስፖርት መሰረተ ልማቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን እንዲያሞሉ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መስፋት ተስፋ ሰጪ ጅማሮዎች ነው። መንግስት የጀመራቸው ስራዎች በተጠናከረ መልኩ መቀጠል ይኖርባቸዋል። አጠቃላይ የእግር ኳሱ እደግት የስፖርት ባለድርሻ አካላትን የጋራ ትብብር ይጠይቃል። ተስፋ ሰጪ እና ብርሃን ፈንጣቂ ጅማሮዎችን ነገ ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በዓለም መድረክ በእግር ኳሱ ስኬታማ ለመሆን መሰረት የሚጥሉ ናቸው።
የአፍሪካ እግር ኳስ ፈር ቀዳጇ ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 1, 2026 811
ክፍል አንድ እንደ መነሻ እ.አ.አ የካቲት 8 ቀን 1957 በአፍሪካ እግር ኳስ ውስጥ ታሪካዊ ከሚባሉ ቀናት ውስጥ አንዱ ነው። በካርቱም ግራንድ ሆቴል ሱዳን፣ኢትዮጵያ፣ግብጽና ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካን እግር ኳስ በበላይነት የሚመራውን ተቋም ለመመስረት ምክክር ላይ ናቸው። አህጉሪቷን የሚወክለው ኮንፌዴሬሽን ለማቋቋም መነሻ የሆነው ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር(ፊፋ) እ.አ.አ በ1956 በፖርቹጋል ሊዝበን ባካሄደው ዓመታዊ ኮንግረስ ላይ የአፍሪካ አገራት ተወካዮች ከሌሎች አህጉራዊ የእግር ኳስ ማህበራት ጋር ያደረጓቸው መደበኛ ምክክሮች ናቸው። በካርቱም የተሰበሰቡት አራት አገራት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በይፋ መሰረቱ። ግብጻዊውን አብደል አዚዝ አብደላ ሳሌምን በሙሉ ድምጽ የካፍ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት አድርገው መረጡ። ካፍን ያቋቋሙት አገራት እ.አ.አ በ1957 የአፍሪካ ዋንጫ በሱዳን እንዲካሄድ ወሰኑ። የመጀመሪያውን የካፍ መተዳደሪያና የውድድር ደንቦች ያዘጋጁት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ናቸው። የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎና የፎርፌ ውጤት የመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ ከየካቲት 10 እስከ 16 1957 በሱዳን ካርቱም ተካሄዷል። በውድድሩ ላይ ሱዳን፣ኢትዮጵያና ግብጽ ተሳታፊ ነበሩ። በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ማንችስተር ሲቲ ከሰንደርላንድ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው አስቀድሞ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ትሳተፋለች ተብሎ የነበረው ደቡብ አፍሪካ ከአገሪቷ በነበረው የአፓርታይድ የዘር መድሎ ምክንያት ከውድድሩ ውጪ ሆናለች። ደቡብ አፍሪካ ከውድድሩ ውጪ የሆነቸው በአፓርታይድ ሕግ ነጮች ሙሉ በሙሉ በነጭ ወይም በሙሉ የተገነባ ብሔራዊ ቡድን እንጂ መቀላቀል አንችልም በማለታቸው ምክንያት ነው። በዚህም ምክንያት ከደቡብ አፍሪካ ጋራ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዋን ልታደርግ የነበረችው ኢትዮጵያ 2 ለ 0 በፎርፌ በማሸነፍ ለፍጻሜው አልፋለች። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ሱዳንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜ አለፈች። እ.አ.አ የካቲት 16 1957 በካርቱም ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ኢትዮጵያን 4 ለ 0 በማሸነፍ ታሪካዊውን የአፍሪካ ዋንጫ አነሳች። አራቱንም ግቦች ያስቆጠረው የፊት መስመር ተጫዋቹ መሐመድ ዲያብ አል-አታር ሲሆን በአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ አራት ግቦችን ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋችና በአምስት ግቦች የመጀመሪያው የውድድሩ ኮከብ ግቢ አግቢ በመሆን ድርብ ታሪክ ጽፏል። ኢትዮጵያ በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች። በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ምንም የማጣሪያ ውድድር አልተደረገም። በመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ግብ ጠባቂ ሚካኤል ጊላ ተከላካዮች አየለ ተሰማ፣መኩሪያ ከበደ አስፋው፣አዳሙ ዓለሙ፣አዳል ተክለስላሴ አማካዮች ናስር በርሄና ሳሙኤል ዘውዴ አጥቂዎች አብርሃም ባይሩ፣አምደስላሴ ነጸረ፣አስፋው ብርሃኔና ከበደ መታፈሪያ ናቸው። በአፍሪካ ዋንጫና እግር ኳስ ፈር ቀዳጅ ከሆኑ አገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋን በሱዳን አሀዱ ብላ ጀመረች። የኢትዮጵያ ሁለተኛ ተሳትፎ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1959 በግብጽ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ አድርጋለች። ሱዳን ሌላዋ በውድድሩ ላይ የተሳተፈች አገር ናት። የውድድሩ ፎርማት በአገራቱ መካከል እርስ በእርስ በሚደረጉ ጨዋታዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘገበው ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የሚያነሳበት ነበር። በዚሁ መሰረት ኢትዮጵያ በውድድሩ ባደረገቻቸው ጨዋታዎች በግብጽ 4 ለ 0፤ በሱዳን 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በፍጻሜው ግብጽ ሱዳንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ብቸኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያነሳችበት ታሪካዊ አጋጣሚ ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የተካሄደው በኢትዮጵያ አዘጋጅነት እ.አ.አ በ1962 ነው። የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሩ ቀደም ብለው ከተካሄዱት ሁለት የአፍሪካ ዋንጫዎች ለየት የሚያደርገው አራት አገራት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉበት ነው። ኢትዮጵያ የውድድሩ አዘጋጅ በመሆኗ ሀገራችን በቀጥታ ለውድድሩ ስታልፍ ፤ በተመሳሳይ የግብፅ ቡድንም የ1959 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ዋንጫ አሸናፊ ቡድን ስለነበር በቀጥታ ለ3ኛ የአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፉ ዩጋንዳና ቱኒዚያ የማጣሪያ ጨዋታ አድርገው ለአፍሪካ ዋንጫ አልፈዋል። በሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ሲሆኑ ውድድሩን ያስተናገደው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ስታዲየም(የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) ነበር። ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዋ ቱኒዚያን 4 ለ 2 አሸንፋለች። አጥቂው ሉቺያኖ ቫሳሎ በ32ኛው በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ያስቆጠረችው የመጀመሪያ ግቧ ሆኖ ተመዝግቧል። ቫሳሎ በ75ኛው ደቂቃ በጨዋታ ግብ አስቆጥሯል። አጥቂው መንግስቱ ወርቁ እና ግርማ ተክሌ ቀሪዎችን ግቦች ለኢትዮጵያ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ዩጋንዳን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜው ከኢትዮጵያ ጋር ደረሰች። በፍጻሜው ጨዋታ አሊ መሐመድ ባዳዊ አብደል ፋታህ በ35ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት በግብ ግብጽን መሪ ማድረግ ችላ ነበር። ከእረፍት መልስ ግርማ ተክሌ በ74ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጋለች። በ75ኛው ደቂቃ አሊ መሐመድ ባዳዊ አብደል ፋታህ በድጋሚ ግብጽን መሪ ያደረገች ግብ አስቆጠረ። አጥቂው መንግስቱ ወርቁ በ84ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን በድጋሚ አቻ አደረገ። ጨዋታው በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት በመጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሬ ሰዓት አምርቷል። በጭማሬ 30 ደቂቃው ኢታሎ ቫሳሎ በ101ኛው እና መንግስቱ ወርቁ በ118ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ግቦች ኢትዮጵያ 4 ለ 2 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ አህጉራዊውን ዋንጫ ከፍ አድርጋለች። በፍጻሜው ጨዋታ ሁለት ግቦች ያስቆጠረው አጥቂው መንግስቱ ወርቁ በአጠቃላይ በውድድሩ ላይ ሶስት ጎሎችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ ጨርሷል። ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት አገራት የተሳተፉበት የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ እ.አ.አ በ1963 በጋና አስተናጋጅነት በተካሄደው አራተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነው። በውድድሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት ብሔራዊ ቡድኖች የተሳተፉ ሲሆን በሁለት ምድብ እያንዳንዳቸው ሶስት አገራት ተደልድለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። የውድድሩ ፎርማት በየምድቡ አንደኛ ሆኖ የጨረሰ አገር ወደ ፍጻሜው እንዲሁም ሁለተኛ የወጡ አገራት ለደረጃው ያለፉበት ነበር። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ጋና ቱኒዚያ ጋር ተደልድላች። በአክራ ስፖርት ስታዲየም ኢትዮጵያ ከጋና ጋር ባደረገችው ጨዋታ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ አጥቂው መንግስቱ ወርቁ ሁለት እንዲሁም ግርማ ተክሌና ግርማ ተስፋዬ ባስቆጠሯቸው አንድ አንድ ግቦች ቱኒዚያን 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ ከምድቡ ሁለተኛ ሆና በማጠናቀቋ ለደረጃ ጨዋታ የቀረበች ሲሆን በግብጽ 3 ለ 0 ተሸንፋለች። በፍጻሜው ጋና ሱዳንን 3 ለ 0 በማሸነፍ ዋንጫውን አነሳች። ኢትዮጵያ ለአምስተኛ ተከታታይ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1965 በቱኒዚያ አስተናጋጅነት በተካሄደው አምስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለተከታታይ አምስተኛ ጊዜ ተሳትፋለች። በውድድሩ ላይ ስድስት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከቱኒዚያና ሴኔጋል ጋር ተደልድላለች። በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በቱኒዚያ 4 ለ 0 ተሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሁለተኛው የምድብ ጨዋታዋ በሴኔጋል 5 ለ 1 ተሸንፋለች። በጨዋታው ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ነበር። በፍጻሜው ጋና ቱኒዚያን 3 ለ 2 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካን ዋንጫ ማንሳት ችላለች። ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ 1968 የተካሄደውን ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያዘጋጀችው ኢትዮጵያ ነበረች። ውድድሩን ያስተናገደው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ስታዲየም(የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) ነበር። በሻምፒዮናው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከኮትዲቭዋር፣አልጄሪያና ዩጋንዳ ጋር የተደለደለች ሲሆን ሶስቱንም የምድብ ጨዋታዎቿን አሸንፋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ግርማ አስመሮም ተስፋይ በጨዋታና ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች ዩጋንዳን 2 ለ 1 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሁለተኛ ጨዋታዋ በኩረጽዮን ገብረሕይወት ባስቆጠራት ግብ ኮትዲቭዋርን 1 ለ 0 ረታለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ አጥቂው መንግስቱ ወርቁና ሸዋንግዛው አጎናፍር በጨዋታ እንዲሁም ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች አልጄሪያን 3 ለ 1 በማሸነፍ ከምድቧ አንደኛ በመውጣት ለግማሽ ፍጻሜው አልፋለች። ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜው ጨዋታዋን ያደረገችው ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ነበር። ራውል አልበርት ኪዱሙ ማንታንቱ በሶስተኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን መሪ አድርጎል። ሊኦን ሙንጋሙኒ በ16ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ የኮንጎን መሪነት ወደ 2 ለ 0 ከፍ አድርጓል። ሉቺያኖ ቫሳሎ በ25ኛው ደቂያ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን ወደ ጨዋታው እንድትመለስ አድርጓል። መንግስቱ ወርቁ በ65ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጓል። መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአቻ ውጤት መጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሪ 30 ደቂቃ አመራ። በጭማሬ ሰዓቱ ሊኦን ሙንጋሙኒ በ100ኛው ደቂቃ ያስቆጠራትን ግብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን አሸናፊ በማድረግ ወደ ፍጻሜው እንድታልፍ አድርጎታል። ኢትዮጵያ ለደረጃው ባደረገችው ጨዋታ ላውረን ፖኩ ባስቆጠራት ግብ 1 ለ 0 ተሸንፋ ለሁለተኛ ጊዜ ባዘጋጀችው ውድድር አራተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ኢትዮጵያ ከፍተኛ ግብ ያስተገደችበት ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሱዳን እ.አ.አ 1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ለሰባተኛ ጊዜ በአህጉራዊው የውድድር መድረክ ተሳትፋለች። በውድድሩ ላይ ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከኮትዲቭዋር፣ካሜሮንና ሱዳን ጋር ተደልድላለች። ኢትዮጵያ በምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዋ በሱዳን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ተረታለች። በሁለተኛው ጨዋታም በካሜሮን 3 ለ 2 የተሸነፈች ሲሆን መንግስቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ሁለቱንም ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፏል። በመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ተሸንፋለች። መንግስቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን ግብ ከመረብ ላይ ያሳረፈ ተጫዋች ነበር። በዚህ ጨዋታ አጥቂው ላውረን ፖኩ አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በምድቡ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ያጠናቀቀች ሲሆን በውድድሩ 12 ግቦችን ተቆጥረውባታል። በፍጻሜው ሱዳን ጋናን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከስድስት ዓመታት ቆይታ በኋላ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ስምንተኛ ተሳትፎዋን ለማድረግ ስድስት ዓመት መጠበቅ ነበረባት። እ.አ.አ በ1976 ራሷ ለሶስተኛ ጊዜ ባዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ በድጋሚ ወደ ውድድር ተሳትፎ ተመልሳለች። በውድድሩ ላይ አሁንም የተሳተፉ አገራት ቁጥር ስምንት ነበር። ኢትዮጵያ በውድድሩ በምድብ አንድ ከግብጽ፣ዩጋንዳና ጊኒ ጋር ተደልድላለች። በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በሰለሞን ሽፈራውና ተስፋዬ ስዩም ግቦች ዩጋንዳን 2 ለ 0 አሸንፋለች። በሁለተኛ ጨዋታዋ ኢትዮጵያን በጊኒ የ2 ለ 1 ሽንፈት አጋጥሟታል። ሰለሞን ሽፈራው ኢትዮጵያን ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። መሐመድ አሊ ለኢትዮጵያ ግቧን ያስቆጠረ ተጫዋች ነው። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአራት ነጥብ ከምድቧ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቋ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ማለፍ ሳትችል ቀርታለች። በፍጻሜው ሞሮኮ ጊኒን በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ማንሳት ቻለች። ይቀጥላል ….
ብክነትን መቀነስ የኃይል አቅርቦትን ማሳደግ፤ የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳ
Dec 8, 2025 1395
አፍሪካ በዓለማችን በታዳሽ ኃይል እምቅ ሀብቶችን የያዘች አህጉር ናት። የዓለም 60 በመቶ የፀሐይ ኃይል ሀብት የሚገኘው በአፍሪካ ነው። አህጉሪቱ ከፀሐይ በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ቴራዋት ሰዓት ኢነርጂ የማመንጨት አቅም አላት። ይሁንና በፀሐይ የምታመነጨው ኃይል ድርሻ አነስተኛ መሆነን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (ኢሲኤ) የእ.አ.አ 2023 ጥናት ያመለክታል። የዓለም ባንክ ተቋም የሆነው ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን በበኩሉ አፍሪካ 25 በመቶ የዓለም የንፋስ ኃይል አቅም ያላት ሲሆን 180 ሺህ ቴራ ዋት ሰዓት ማመንጨት እንደምትችል ይገልጻል። ይሁንና በዓለም ላይ በዘርፉ ያላት ድርሻ ከአንድ በመቶ በታች መሆኑን ያነሳል። ሃይድሮ ፓወር የአፍሪካ ሌላኛው የኢነርጂ ሀብት ማሳያ ነው። የአህጉሪቷ ወንዞች እና ተፋሰሶች በየዓመቱ 1 ሺህ 500 ቴራ ዋት ሰዓት የማመንጨት አቅም ቢኖራም ጥቅም ላይ የዋለው 10 በመቶውን ብቻ ነው። የናይል ተፋሰስ፣ የኮንጎ ተፋሰስ እና የዛምቤዚ ተፋሰሶችን የያዘችው አፍሪካ ከፍተኛ የሃይድሮ ፓወር አቅሟን መጠቀም አልቻለችም ይላል የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ጥናት። ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ ያለው የእንፋሎት ኃይል ሌላኛው ትልቅ እድል ነው። የአፍሪካ የእንፋሎት (ጂኦተርማል) አቅም ከ15 እስከ 20 ጊጋዋት መሆኑን የአፍሪካ ኢነርጂ ምክር ቤት መረጃ ያሳያል። አፍሪካ ከዓለም የኢነርጂ ምርት ውስጥ ከአራት በመቶ በታች እንዲሁም በታዳሽ ኃይል ደግሞ ከ1 ነጥብ 6 በመቶ ያነሰ ድርሻ እንዳላት መረጃዎች ያመለክታሉ። የአፍሪካ የኢነርጂ ምህዳር ሁለት ተጻራሪ እውነታዎችን የያዘ ነው። አህጉሪቷ የዓለምን 17 በመቶ ህዝብ ብትይዝም በዓለም የኢነርጂ አጠቃቀም ያላት ድርሻ ከአራት በመቶ በታች ነው። በአሁኑ ሰዓት 600 ሚሊዮን ገደማ የሚሆን የአፍሪካ ህዝብ የኤሌክትሪክ ኃይል እንደማያገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ። 21 በመቶ አፍሪካውያን ብቻ ንጹህ የማብሰያ ነዳጅ እና ቴክኖሎጂዎችን ያገኛሉ። ባህላዊ የምግብ ማብሰያ አማራጮች ለጤና አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ናቸው። በአፍሪካ ከከተሜነት መስፋፋት እና ከፈጣን የህዝብ እድገት ጋር በተያያዘ የኢነርጂ ፍላጎት በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል። እ.አ.አ በ2040 የአፍሪካ ህዝብ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ህዝብ እንደሚያልፍ ትንበያዎች ያሳያሉ። በተለይም የህዝብ ብዛት መጨመሩ በኢነርጂ አቅርቦት ላይ ጫና ያሳድራል። ከእ.አ.አ 2014 እስከ 2023 የአፍሪካ የታዳሽ ኢነርጂ በእጥፍ አድጎ ከ32 ነጥብ 5 ጊጋ ዋት ወደ 62 ነጥብ 1 ጊጋ ዋት ማደጉ መልካም የሚባል እምርታ መሆኑን የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ይገልጻል። የአፍሪካ ሌላኛው ፈተና የምትጠቀመውን ኢነርጂ የብክነት ምጣኔ ነው። በበቂ ሁኔታ ባልተደራጀው የኢነርጂ ስርዓት ምክንያት አፍሪካ በየዓመቱ በቢሊዮን ዶላሮች የሚገመት ገንዘብ ታጣለች። እንደ ዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ መረጃ ከሆነ አፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀሟን የምታሻሽል ከሆነ 30 በመቶ የኢነርጂ ወጪዋን መቀነስ ትችላለች። ይህም የአፍሪካ መንግስታት ለማህበራዊ ልማት የሚያወጡትን በጀት እንደሚያሳድግ እና አዲስ የኃይል ማመንጫዎችን ሳትገነባ የካርቦን ልቀትን መቀነስ የምትችልበትን እድል ይፈጥርላታል። ኢትዮጵያ ከወራጅ ወንዞች በአመት 124 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ያላት ሲሆን ከ36 እስከ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የከርሰ ምድር የውሃ ሃብት እንዳላት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከገፀ ምድር የውሃ ሃብቷ 83 በመቶ የሚገኘው ከተከዜ፣ ባሮ፣ አባይና ጊቤ ኦሞ ወንዞች ነው። አንዱ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚመነጨው ካላት የውሃ ሀብት ነው። ኢትዮጵያ በውሃ፣ በፀሐይ፣ በነፋስ እና በጂኦ-ተርማል የኃይል አማራጮች በአጠቃላይ ከ300 እስከ 400 ጊጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላት መረጃዎች ያሳያሉ። በ10 ዓመት መሪ ልማት እቅዱ ኢትዮጵያ አሁን እያመነጨች ያለውን 4 ሺህ 818 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ 17 ሺህ ሜጋ ዋት ለማሳደግ አቅዳለች። ከለውጡ በኋላ በኢነርጂው ዘርፍ ያለውን አቅም ለመጠቀም የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎች ተከናውነዋል። ከስራዎቹ መካከል ለሶስት አስርት ዓመታት ስራ ላይ የነበረውን የኢነርጂ ፖሊሲ ማሻሻል ይገኝበታል። ፖሊሲው ከ2013 ዓ.ም አንስቶ የማሻሻያ ዝግጅት ሲደረግበት ቆይቷል። የፖሊሲ ማሻሻያው የተዘጋጀው አሁን ያለውን ሀገራዊ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ነባራዊ እውነታ መሰረት ባደረገ መልኩ ነው። ለኢነርጂ ፖሊሲው ማሻሻል ምክንያቶች ከሆኑት መካከልም ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ፣ ከአረንጓዴ ልማት፣ ከ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድና ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር ማጣጣም በማስፈለጉ እንደሆነም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብም በአፍሪካ ግዙፉ የኢነርጂ ፕሮጀክት ሲሆን ለቀጣናው እና ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አቅምን ይዞ መጥቷል። ከፖሊሲው ትኩረት አንዱ ከአገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ለጎረቤት አገራት ኃይል በማቅረብ ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር እንደሆነም በሰነዱ ላይ ሰፍሯል። በ10 ዓመቱ የመሪ ልማት እቅዱም ዜጎችን በስፋት የአሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የማድረግ ግብ ተይዟል። ከዚህ ባሻገር በእቅዱ ኢትዮጵያ የቀጣናው ሀገራትን በኃይል የማስተሳሰር ዕቅድ ሰንቃ እየሰራች ትገኛለች። በእቅዱ ለጎረቤት አገራት እየቀረበ ያለውን 2 ሺህ 803 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ወደ 7 ሺህ 184 ጊጋ ዋት ሰዓት የማሳደግ ውጥን ተይዟል። የአፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀምን ለማሻሻል እና ብክነትን ለመቀነስ የተቀናጀ ምላሽ የመስጠት ጉዳይ ጊዜ የማይሰጠው ነው። የአፍሪካ ህብረት ያዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የኢነርጂ ውጤታማነት ኮንፍረንስ (Energy Efficiency Conference) ታህሳስ 2 እና 3 ቀን 2018 ዓ.ም በህብረቱ ዋና መቀመጫ በአዲስ አበባ ይደረጋል። ኮንፍረንሱ እ.አ.አ በ2024 በአዘርባጃን ባኩ በተካሄደው 29ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ-29) ይፋ የተደረገው የአፍሪካ ኢነርጂ ውጤታማነት ጥምረት ማዕቀፍ ስር የሚካሄድ ነው። የጥምረቱ ማዕቀፍ በአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መጽደቁ ይታወቃል። “የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳን በስትራቴጂካዊ አጋርነት ውጤታማ ማድረግ” የኮንፍረንሱ መሪ ሀሳብ ነው። አህጉራዊው ሁነት የተዘጋጀው የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተቋም በሆነው የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን እና በኢትዮጵያ መንግስት ትብብር ነው። ኮንፍረንሱ የኢነርጂ ውጤማነትን በማረጋገጥ የአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት፣ ዘላቂ ልማት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የተግባር ምላሽ አቀጣጣይ ሞተር የማድረግ አላማ ያለው መሆኑ ተገልጿል። የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ራሺድ አሊ አብደላ ኮንፍረንሱን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት የኢነርጂ ውጤማነት የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ዋንኛ ሀብት ነው ሲሉ ተናግረዋል። የኢነርጂ ውጤማነት የኃይል ብክነት፣ የካርቦን ልህቀት እና ወጪ ለመቀነስ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል። ኮንፍረንሱ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ አመራሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ፣ ተመራማሪዎች እና ባለሙያዎችን በአንድ መድረክ የሚያገናኝ ነው። ባለድርሻ አካላቱ በአፍሪካ ዘላቂ የኢነርጂ ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን የሚያስችሉ ውጤታማ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ፖሊሲዎች ላይ በመምከር ቀጣይ ስራዎች ላይ የጋራ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጡ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የአፍሪካ ከፍተኛ እና በሰፊው ጥቅም ላይ ያልዋለ የታዳሽ ኢነርጂ አቅም በቀጣይ የዓለም የኢነርጂ ሽግግር እና አቅርቦት ውስጥ ትልቅ ሚና የሚጫወት ነው። የኢነርጂ አቅሙን ትሩፋቶች የመጠቀም ጉዳይ አነስተኛ ነው ማለት ይቻላል። ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ያላቸውን የታዳሽ ኃይል ምንጭን ለመጠቀም እየወሰዷቸው የሚገኟቸው እርምጃዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው። የኢነርጂ ውጤታማነትን ማሳደግ፣ የተቀናጁ ፖሊሲዎች፣ የተቀናጀ ቀጣናዊ የኃይል ቋቶችን መፍጠር፣ የኢነርጂ ፋይናንስን ማሳደግ እና የመንግስታት የፖለቲካ ቁርጠኝነት የአፍሪካ ኢነርጂ አቅሞች ወደ ዘላቂ ልማት፣ የኢነርጂ ደህንነት የማረጋገጥ፣ የአየር ንብረትን የሚቋቋም ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባትን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶች ይዞ ይመጣል።
ማድያት እና ህክምናው
Sep 29, 2025 3697
ማድያትን ለማከም አስቸጋሪ መሆኑንና በታካሚዎች ላይም የሥነ ልቡና እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያመጣ የሚችል መሆኑን የቆዳ ሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ስለ ማድያት መንስዔ፣ ስለሚከሰትበት የሰውነት ክፍል፣ ማድያት ያለበት ሰው ማድረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ቆዳን ስለሚያስቆጣ ሠርካዊ ልማድ እና ሕክምናውን በተመለከተ በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ዶክተር አደራጀው ብርሃን ከኢዜአ ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም፤ በቆዳ ውስጥ ያሉ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) ከመጠን በላይ ቀለም ሲያመርቱ ማድያት ተከሰተ እንደሚባል ገልጸዋል። ለዚህም መንስዔው የተፈጥሮ ተጋላጭነት ከተለያዩ ቀስቃሽ ምክንያቶች ጋር የሚያደርጉት መሥተጋብር መሆኑን አስረድተዋል። 👉 የማድያት መንስዔ ምንድን ነው? 1ኛ. የሆርሞን ለውጥ፡- በእርግዝና ወቅት ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሲጠቀሙ የሚኖር የሆርሞን ለውጥ ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ያደርጋል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። 2ኛ. የፀሐይ ጨረር፡- ከልክ ያለፈ ፀሐይ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) በብዛት ቀለም እንዲያመርቱ ስለሚያነቃቃ፤ የፀሐይ ጨረር ዋነኛ ቀስቃሽ እና አባባሽ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። 3ኛ. የዘር ሐረግ፡- በቤተሰብ ውስጥ ማድያት ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ይናገራሉ። 4ኛ. የቆዳ ዓይነት፡- ጥቁሮች (ከቡናማ እስከ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው) ንቁ ቀለም አምራች ሴሎች ስላሏቸው ለማድያት የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት። 5ኛ. ሌሎች መንስዔዎች፡- ሙቀት (የሚታዩ እና የማይታዩ ጨረሮች እንዲሁም የምድጃ እሳት)፤ የተለያዩ መድኃኒቶችና የመዋቢያ ምርቶች፤ የእንቅርት ዕጢ ህመሞች እንዲሁም ጭንቀት ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውንም የሕክምና ባለሙያው አስገንዝበዋል። 👉 ማድያት በየትኛው የቆዳ ክፍል ላይ ይከሰታል? ማድያት ከሚከሰትበት የቆዳ እና የሰውነት ክፍሎች አንጻር በሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል ዶክተር አደራጀው አንስተዋል። እነሱም 1ኛ. ከሚከሰትበት የቆዳ ክፍል አንጻር፡- ማድያት በውስጠኛውም ሆነ በላይኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ወይም በሁለቱም ላይ ሊከሰት ይችላል ብለዋል። 2ኛ. ከሚከሰትበት የሰውነት ክፍሎች አንጻር፡- የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት 60 በመቶ ማድያት ግንባር፣ ጉንጭ፣ አፍንጫ፣ የላይኛው ከንፈር እና አገጭ ላይ ይከሰታል ብለዋል። 30 በመቶው ደግሞ ጉንጭ እና አፍንጫ ላይ እንዲሁም 10 በመቶው የአገጭ መስመርን ተከትሎ እንደሚከሰት አስረድተዋል። በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከፊት የሰውነት ክፍሎች በተጨማሪ በደረት፣ አንገት እና ክንድ ላይ የሚከሰትበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቁመዋል። 👉 የማድያት ባሕርይ ማድያት የቆዳ ቀለም ለውጥ ያመጣል፤ በግራና በቀኝ የፊት ክፍል ይወጣል። የማሳከክ ወይም የህመም ስሜት እንደሌለውም ዶክተር አደራጀው አስረድተዋል። • ማድያት በላይኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ነጣ ወይም ጠቆር ያለ ቡናማ የሆነ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አመላክተዋል። • ማድያት በውስጠኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ሰማያዊ ግራጫ ወይም ጠቆር ያለ ግራጫ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አንስተዋል። • ማድያት በሁለቱም የቆዳ ክፍሎች ላይ ሲከሰት፡- የተቀላቀለ የቡናማ እና ግራጫ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይም ባለሙያው አብራርተዋል። 👉 ማድያት ያለበት ሰው ምን ዓይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባዋል? 1ኛ. ወርቃማ ጥንቃቄ፡- • ተከታታይና ጥብቅ የሆነ የፀሐይ መከላከያ መጠቀም ይገባል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። በዚህም መሠረት ከቤት ከመውጣት ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ቀደም ብሎ የፀሐይ መከላከያ ክሬሞችን መቀባትና በሁለት ሠዓት ልዩነት እየደረቡ መቀባት። • በሌላ በኩል ከ4 እስከ 10 ሠዓት ያለው የፀሐይ ሙቀት ለቆዳ ህመም አጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ ከፀሐይ መከላከያ ክሬም በተጨማሪ ጥላና ኮፍያን መጠቀም እንደሚገባ መክረዋል። 2ኛ. ቆዳን የሚያስቆጣ የቆዳ እንክብካቤ (መስተካከል ያለበት ልማድ)• ቆዳን የሚያስቆጡ መታጠቢያዎች(ሳሙናን ጨምሮ ሌሎችም) እንዲሁም መዋቢያዎችና የሚቀቡ ነገሮች (ኮስሞቲክስን ጨምሮ ሌሎችም) አለመጠቀም ይገባል ይላሉ። • ለቆዳ ተስማሚ የሆኑ ማለስለሻዎችን በደንብ መጠቀም እንደሚገባም ይመክራሉ። 3ኛ. በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ መጠቀም • በሐኪም የታዘዘ መድኃኒትን በአግባቡ(ሳያቆራርጡ) መጠቀም እንደሚመከር ያስረዱት ዶክተር አደራጀው፤ እንደ ማድያቱ እና እንደ ሰዎቹ ቆዳ ዓይነት መድኃኒቱ ለውጥ የሚያሳይበት ጊዜ ስለሚለያይና ከ8 እስከ 12 ሣምንት ሊወስድ ስለሚችል ታግሶ በደንብ ቢጠቀሙ መልካም ነው ይላሉ። 4ኛ. የተለያዩ የሕክምና አማራጮችን መጠቀም• የሕክምና ባለሙያው እንደሚመክሩት፤ በዘርፉ ያሉ የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን ለምሳሌ እንደ ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ ያሉትን በሐኪም ምርመራ መሠረት መጠቀም ይገባል። 5ኛ. ከወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የተከሰተ ማድያት ከሆነ ከሕክምና ባለሙያ ጋር በመመካከር ሌላ አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አንስተዋል። እንዲሁም ጭንቀትን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። 👉 የማድያት ሕክምናን በተመለከተ የማድያት ሕክምና በጣም አስቸጋሪ ከሚባሉትና ረጂም ጊዜ ከሚወስዱ እንዲሁም በመመላለስ ከሚያስቸግሩ የቆዳ ሁኔታዎች አንዱ መሆኑን ዶክተር አደራጀው ገልጸዋል። በሕክምና ማድያቱ የጠፋላቸው ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ በሌላ በኩል በሕክምና ሂደት የማድያቱ ሁኔታ ከነበረበት እየቀነሰ ለውጥ የሚታይበት ሁኔታ አለ ብለዋል። ይህን ለውጥ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ማስቀጠል እንደሚገባም ይመክራሉ። እንክብካቤው ከተቋረጠ ግን ማድያቱ እንደገና የሚመለስበት ሁኔታ መኖሩን አስገንዝበዋል። 👉 የማድያት ሕክምና አማራጮች የሚቀቡ መድኃኒቶች፣ የሚዋጡ መድኃኒቶች፣ ሌሎች የሕክምና አማራጮች(ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ)፣ የፀሐይ መከላከያ አማራጮችን በአግባቡ አዘውትሮ መጠቀም እንደሚገባ ይመክራሉ።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 3357
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2201
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 8007
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6494
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
"ጉማታ" በረከትን የመጋራት እሴት!!
Feb 6, 2026 162
"ጉማታ" በረከትን የመጋራት እሴት!! በያንተስራ ወጋየሁ -ዲላ ቀን ቀንን እየወለደ ጊዜ ሳያቋርጥ እንደ ዥረት መፍሰሱን አያቆምም። ትናንት አዲስ የነበረው አሮጌው የሚባልበት፣ ዛሬ አዲስ ሆኖ ነገ አሮጌ ለመባል ይሮጣል። ወቅቶች ይፈራረቃሉ፣ ይመሻል፣ ይነጋል፣ ትናንት ለዛሬ፣ ዛሬ ለነገ እንዲህ እንዲህ እየተቀባበሉ ዘመን ዘመንን እየተካ ዛሬ ላይ ተደርሷል። በጥምር ግብርናውና በቡናው የሚታወቀው ጌዴኦ ትናንትን ሸኝቶ ዛሬን እንደ አዲስ ለመቀበል ሽር ጉድ እያለ ነው። በክረምቱ የተዘራው ሰብል ተሰብስቦ ወደ ጎተራ እንዳስገባ ጌዴኦ አዲስ ዓመቱን ‹‹ዳራሮ››ን ይቀበላል። ዳራሮ የተጣላ የሚታረቅበት፣ ቂም የያዘ ቂምና ቁርሾውን የሚተውበት፣ ወጣቶች የሚተጫጩበት፣ አዛውንቶች ወደ ሽምግልና የሚሸጋገሩበት እሴቶችን በውስጡ የያዘ ነው። "ያገኘሁትን ምርት ብቻዬን አልበላም" ብሎ የሚያምነው የጌዴኦ አርሶ አደር ካመረተው ምርት ለመሪው፣ ልጆች ለወላጆችና ለአሳዳጊዎቻቸው፣ አዲስ ተጋቢዎች ለአማቾቻቸው፣ ቂም የያዘ ሰው እንዲሁ የተቀየመውን ሰው ይቅርታ ለመጠየቅ ጉማታ ይዘው ይሄዳሉ። "ጉማታ" በጌዴኦ ዘመን መለወጫ ወቅት የሚፈጸም ስጦታ ነው። ጉማታ በቤት ውስጥ ተዘጋጅቶ ወደ ታላላቆች ቤት ወይም ወደ ማኅበረሰቡ አደባባይ የሚወሰድ በመሆኑ፣ የግለሰብን ደስታ ወደ ማህበረሰባዊ ደስታ የሚቀይር ድልድይ ነው። በአጠቃላይ ጉማታ ከሌለ የዳራሮ በዓል ሙሉ አይሆንም። ጉማታ የጌዴኦን ሕዝብ አንድነት የሚያጸና፣ ትውልድን ከትውልድ የሚያስተሳስር ሀገር በቀል እሴት ነው። በዳራሮ በዓል አከባበር ውስጥ "ጉማታ" እጅግ አስፈላጊና ትልቅ ትርጉም ያለው ባህላዊ የክብር ስጦታ የመስጠት ሥርዓት ነው። "ጉማታ" ማለት በቀጥታ ትርጉሙ "ስጦታ" ማለት ቢሆንም፣ በጌዴኦ ባህል ግን ከስጦታ በላይ ነው። ምስጋናን፣ ፍቅርን፣ አክብሮትንና በረከትን የመጋራት መገለጫ ነው። የጌዴአ ባህላዊ የባሌ ስርዓት መሪ ሆነው የሚሰየሙት አባ ገዳ ለህዝብ ከመጸለይ፣ ከማስታረቅና ክፉን በማውገዝ ህዝቡ ተፈጥሮን እንዲንከባከብ ከማስተማር ውጭ አይዘሩም፣ አይነግዱም፣ አልፎም እንሳስትን አያረቡም፡፡ የዳራሮ በዓልን ተከትሎ ህዝቡ የሚያቀርብላቸውን "ጉማታ" በመቀበል ባህላዊ የመሪነት ሚናቸውን በአግባቡ ከመወጣት ውጪ። ኑሮው ከጥምር እርሻ ጋር የተቆራኘው የጌዴኦ ሕዝብ ዘርቶ ካጨደው፣ አርብቶ ካገኘው ከብት፣ አንቦ ከቆረጠው ማር፣ ከሁሉም በአይነት በአይነቱ ሸክፎ ዳራሮ ወደ ሚከበርበት ሶንጎ (አደባባይ) ይተማል። ለጉማታ ከሚቀርቡ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ስጦታዎች አንዱ ማር ነው። ማር በጌዴኦ ዘንድ የጣፋጭ ዘመንና የጤና ምልክት ተደርጎ ይወሰዳልና ዋናው ስጦታ ነው። ጌዶኦዎች ቡና፣ ቅቤና ባህላዊ ምግቦች፣ የቁም እንስሳት በግና ስንጋ እንዲሁም ገንዘብ በመያዝ በበዓሉ ውስጥ የጉማታ ስርዓት ሲደርስ ተሽቀዳድመው ለአባ ገዳው በመስጠት ምርቃት ይቀበላሉ። "ጉማታ" የተቀበለው ሰው የሚመርቀው ምርቃት በሰጪው ሕይወት ላይ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ ይታመናልና ከስጦታው ይልቅ ምርቃቱ ትልቅ ዋጋ አለው። "ያገኘሁትን ምርት ብቻዬን አልበላም" ብሎ የሚያምነው ጌዴኦ በረከትን ማካፈል ለቀጣዩ ዓመት ተጨማሪ በረከት እንደሚያገኝ ስለሚያውቅ ጉማታ መስጠት የዘመናት ቅርሱ ነው። ጉማታ ከአባ ገዳና ከባህል ሽማግሌዎች ባለፈ አርሶ አደሩ ከማጋኖ (ከፈጣሪ) ያገኘውን በረከት ለሚወዳቸውና ለሚያከብራቸው ሰዎች የሚያቀርብበት መንገድ መሆኑን የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) ገልጸዋል። ልጆች ለወላጆቻቸውና ለቤተሰብ አባላት ላሳደጓቸውና ለሰጧቸው ምርቃት ምስጋናቸውን ለመግለጽ ጉማታ ይዘው ይሄዳሉ። በቅርቡ ጋብቻ የመሠረቱ ወጣቶች ወደ አማቾቻቸው ቤት ጉማታ ይዞ በመሄድ ዝምድናቸውን ያጠናክራሉ። በዓመቱ ውስጥ ቅሬታ ወይም ቂም ካለ፣ በዳራሮ ወቅት ጉማታ ይዞ በመሄድ ይቅርታ ይጠየቃል። ጉማታ የሰውን ልብ ለማለስለስና አዲስ ዓመትን በሰላም ለመጀመር ያገለግላል ተብሎ ስለሚታመን። ጉማታ በቤት ውስጥ ተዘጋጅቶ ወደ ታላላቆች ቤት ወይም ወደ ማህበረሰቡ አደባባይ የሚወሰድ በመሆኑ፣ የግለሰብን ደስታ ወደ ማህበረሰባዊ ደስታ የሚቀይር ድልድይ ስለመሆኑም ነው ዋና አስተዳዳሪው የጠቆሙት። በአጠቃላይ ጉማታ ከሌለ የዳራሮ በዓል ሙሉ አይሆንም። ጉማታ የጌዴኦን ሕዝብ አንድነት የሚያጸና፣ ትውልድን ከትውልድ የሚያስተሳስር ሀገር በቀል እሴት ነው። ይህም የመደጋገፍ እሴትን ከማጠናከር በተጓዳኝ ህዝቡ የመንግስት ገቢን እንዲሁም በማህበረሰብ ተሳትፎ ለሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንዲሆን መሰረት የጣለ ነው ይላሉ። የዘንድሮው ዳራሮ ከቤት በተለይም ከአባ ገዳው መኖሪያ አንስቶ በሶንጎዎችና በየደረጃው በሚገኙ መዋቅሮች በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ጭምር እየተከበረ መሆኑን ያነሱት አስተዳዳሪው ጉማታም ዋናው የበዓሉ እሴት ሆኖ እየተከበረ ነው ብለዋል። ባህልና ማንነትን በማስጠበቅና በማዳበር፣ ባህሉ ወደ ወጣቶች እንዲተላለፍ በማበረታታት እንዲሁም የጌዴኦ ባህልን ለሌሎች ህዝቦች ለማስተዋወቅና የማህበረሰብ አንድነትና ባህላዊ እሴትን ለማጠናከር እያገለገለ ያለው የጌዴኦ ዘመን መለወጫ ዳራሮ ጥር 29 እና 30 በዲላ ከተማ ይከበራል። የዳራሮ በዓል የጌዴኦን ሕዝብ የሥራ ባህል፣ የተፈጥሮ ጥበቃ ዕውቀትና የሰላም እሴት ለዓለም የሚያሳይ ትልቅ አጋጣሚ ነው። ይህ በዓል በተለይ የጌዴኦ የባህላዊ መልክዓ ምድር (Cultural Landscape) በዩኔስኮ (UNESCO) በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ተከትሎ፣ አሁን ላይ ከቤትና ከአደባባይ አልፎ ዓለም አቀፋዊ ትኩረት እያገኘ ያለ ታላቅ እሴት ሆኗል። የዓመት ሰው ይበለን!!
ዕድሜ ያልገደበው የልማት አርበኝነት
Jan 14, 2026 505
ዕድሜ ያልገደበው የልማት አርበኝነት ብርቱዎች ነገን በማሰብ ሁሌም ታትረው ይሰራሉ፤ ይደክማሉ፤ ይጥራሉ…ለቀጣዩ ትውልድም ጥሪት በማስቀመጥ አሻራቸውን ያኖራሉ። አገር የምትገነባው በትውልድ ቅብብሎሽ ነው። “አባት ያበጀው፤ ለልጅ ይበጀው” እንደሚባለው ልጆች ከአባቶቻቸው ያገኙትን ጥሪት በአዲስ እውቀትና አሰራር ለአገር እድገት በሚበጅ መልኩ አጠናክረው መጠቀማቸው አይቀርም። “ዕድሜ ጸጋ ነው” የሚለው አባባል አንዳንዴ በዕድሜ ብንገፋም ጠንክረን ከሰራን ብዙ ነገር እናያለን ከሚለው ጋር የተያያዘ ነው። በሰቆጣ ከተማም እድሜ ሳይገድባቸው በልማት ውጤታማ የሆኑ ግለሰቦች ለዚህ ማሳያ ናቸው። የከተማዋ ነዋሪ የ67 ዓመቱ አቶ ብርሃኑ አወቀ እና የ83 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ አቶ ታደሰ አዳነ ዕድሜያቸው ቢገፋም ጠንክሮ ከተሰራ ውጤታማ መሆን እንደሚቻልና ዕድሜ ጸጋ ሆኖ ብዙ ለውጥ ማየት እንደሚቻል ማሳያ ናቸው። ግለሰቦቹ ከዕድሜ ብዛት ጉልበቴ ደከመ፣ አይኔ ፈዘዘ፣ እጄም ተሳሰረ…ሳይሉ ጊዜያቸውን በደን፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ሥራ በማሳለፍ ለወጣቶች የልማት አርአያነት ያለው ተግባር እየፈጸሙ ነው። አቶ ብርሃኑ አወቀ በሰቆጣ ከተማ ዳርቻ የሚገኝ አለቱ ያገጠጠና የተራቆተ አካባቢን ከሌላ አካባቢ ለም አፈር በማምጣትና በመደልደል አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ደን በማልማት ውጤታማ ስራ እያከናወኑ ነው። ከመንግስት ሥራ በጡረታ ከወጣሁ ጀምሮ ጠንክሬ በመስራት የምለወጥበትን ሥራ ማሰብ ስነበረብኝ፤ የቆሻሻ መጣያ ሆኖ ለዘመናት የቆየን ጭንጫ መሬት ጠርጌና ደልድዬ ማልማት ችያለሁ ይላሉ ወደኋላ መልስ ብለው የተነሱበትን ሁኔታ ሲያስታውሱ። ግማሽ ሄክታር በማይሞላ መሬት ላይ ፓፓያ፣ ሙዝ፣ ዘይቱና፣ ጌሾ፣ ቡና፣ ማንጎና አቮካዶ አልምተዋል። በተጨማሪም ቆስጣ፣ ቲማቲም፣ ጥቅል ጎመንና ሽንኩርት በማምረት ከቤት ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጨማሪ ጥሪት አፍርተዋል። ጊዜን በአግባቡ ተጠቅሞ ተግቶ መስራት ከተቻለ ሀብት ማፍራትና ህይወትንም መለወጥ እንደሚቻል የገለጹት አቶ ብርሀኑ፣ ወጣቱም ከእሳቸው የሥራ ትጋት በመማር በአካባቢው ያለውን ፀጋ ለይቶ በማልማት ሊጠቀም ይገባል ሲሉ ይመክራሉ። ሌላው የ83 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ አቶ ታደሰ አዳነ ባለፉት 18 ዓመታት በተሰማሩበት የአትክልትና ደን ልማት ሥራ የአካባቢያቸውን ገጽታ ቀይረዋል። የዕድሜ ዘመናቸውን በውትድርናና በመንግስት ሠራተኝነት በማገልገል ሃገራዊ ግዳጃቸውን ሲወጡ ነው የቆዩት። ከመንግስት ሥራ በጡረታ ከተገለሉ በኋላም ቤት ውስጥ መቀመጥን አልመረጡት። አካፋና ዶማቸውን ይዘው ባላቸው ትንሽ መሬት ላይ ጌሾ፣ ዘይቱና እና ማንጎ በማልማት ምርቱን ከቤት ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ ሆነዋል። በአካባቢያችን ያሉ ፀጋዎችን በአግባቡ ለይተን ማልማት ከቻልን ድህነትን ማስወገድ የሚከብድ አይሆንም ያሉት አቶ ታደሰ፣ የተራቆተና በጎርፍ የተጎዳን መሬት በማልማት አካባቢውን ሳቢና ማራኪ ማድረጋቸውን ነው የገለጹት። ወጣቱም ከእሳቸው አርአያነት ያለው ተግባር በመማር በአካባቢው እጁ ላይ ባለ ሀብት ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል በተግባር ማሳየት እንዳለበት መክረዋል። የዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ግብርና መምሪያ የአትክልትና ፍራፍሬ መስኖ ውሃ አጠቃቀም ቡድን መሪ አቶ ደሳለኝ አዳነ እንደገለጹት፤ በብሔረሰብ አስተዳደሩ 24ሺህ 847 አርሶ አደሮች በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ተሰማርተዋል። ከአርሶ አደሮቹ መካከል ዕድሜ ሳይገድባቸው ወደ ልማት የገቡ አረጋዊያን እያከናወኑት ያለው የግብርና ልማት ሥራ ለወጣቱ ትልቅ ትምህርት እንደሚሆንም ተናግረዋል። ከእነሱ ልምድ በመውሰድ በዞኑ ወጣቶች፣ ሴቶችና አረጋዊያን በጓሮና ባላቸው መሬት ላይ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲያለሙ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ይህም በዞኑ የሚስተዋለውን የስርዓተ ምግብ ችግር ለማሻሻል ያግዛል ብለዋል።