ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ሰፊ ተጠቃሚነትን ለማግኘት የሚያስችሉ ሥራዎች በመከናወን ላይ ናቸው - ኢዜአ አማርኛ
ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ሰፊ ተጠቃሚነትን ለማግኘት የሚያስችሉ ሥራዎች በመከናወን ላይ ናቸው
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/ 2018 (ኢዜአ):- ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ሰፊ ተጠቃሚነትን ለማግኘት የሚያስችሉ ሥራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ገለጹ።
የፓርላማ መረጃና ደህንነት ፎረም በመካሄድ ላይ ነው።
ኢትዮጵያ ደኅንነቱ የተረጋገጠ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነቷን ለማሳደግ በትኩረት እየሠራች መሆኑ በፎረሙ ላይ ተመላክቷል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ከዘርፉ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ሥራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት ተወዳዳሪነት የሚያሳድጉ መሰረተ ልማቶች እየተገነቡ መሆኑን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ዘርፉን ለቅድመ ማስጠንቀቂያ፣ ለሰላም ግንባታ እና ለመንግሥታዊ አገልግሎቶች ጥቅም ላይ እያዋለች እንደምትገኝ አመልክተዋል።
ኤአይን በሕግ ለመምራት እና ሥጋቶችን ለመቀነስ የሚያስችሉ የሕግ ዝግጅቶች በስፋት በመከናወን ላይ እንደሚገኙም ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት ወቅታዊ የደኅንነት ሥጋቶች ላይ ያተኮሩ ጽሑፎች በፎረሙ ላይ በመቅረብ ላይ እንደሚገኙ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመለከታል።