ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በጠቅላላ ምርጫው የሴቶችን የመምረጥና የመመረጥን ተሳትፎ የሚያሳድጉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራት እየተከናወኑ ነው
Apr 24, 2026 34
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፡- በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሴቶችንና ሌሎች ማህበረሰብ ክፍሎችን የመምረጥና የመመረጥን ተሳትፎ የሚያሳድጉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ ገለጸ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የዘንድሮውን ጠቅላላ ምርጫ ከየካቲት 28/2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የመራጮች ምዝገባ ለተጨማሪ 14 ቀናት ተራዝሞ ሚያዚያ 14/2018 ዓ.ም ምሽት ላይ ተጠናቋል። ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫም 50 ሚሊየን 514 ሺህ በላይ መራጮች በዲጂታልና በምርጫ ጣቢያ በአካል በመገኘት መመዝገባቸውን ቦርዱ ትናንት ሚያዚያ 15/2018 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። በቦርዱ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ድምፅ የሚሰጥ ሲሆን፤ 47 ተፎካካሪ ፓርቲዎችም 10 ሺህ 934 ዕጩዎችን በማስመዝገብ የፖሊሲ አማራጮቻቸውን ለህዝብ በማስተዋወቅ ላይ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ የፕሮግራም አስተባባሪ እዩኤል ዘላለም ለኢዜአ እንዳሉት፤ ምርጫ በአንድ ሀገር ውስጥ በህዝቦች ዘንድ ቅቡልነት ያለው መንግስት መመስረቻ መሳሪያ ነው። ኅብረት ለምርጫም የኢትዮጵያን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሕዊ፣ ዴሞክራሲያዊና አካታችነት ለማጠናከር የህዝብን ተሳትፎ የሚያሳደግ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። የምርጫ ሂደቱን ዴሞክራሲያዊነት፣ አካታችና አሳታፊነት ለማረጋገጥም የሴቶችንና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተሳትፎ የማንቃት ስራ እየሰሩ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በተለይም የሴቶችን የምርጫ ታዛቢነት፣የመምረጥና መመረጥ ተሳትፎን የሚያሳድጉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን በመገናኛ ብዙኅንና በአካል እየሰጡ መሆናቸውን አንስተዋል። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ሴቶችንና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎችን አሳታፊነት ለማረጋገጥም ''እኔ መርጣለሁ'' በሚል መሪ ሃሳብ የመራጮች ትምህርት ዘመቻ መጀመሩንም አስገንዝበዋል። የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ሴቶች የሚያነሷቸውን ጉዳዮች በፖሊሲ አማራጮቻቸው ላይ ያካተቷቸውን ጉዳዮች በሚገባ ማስተዋወቅ እንደሚኖርባቸው አስረድተዋል። ይህም ሴቶች ይበጀኛል ለሚሉት የፖለቲካ ፓርቲ ድምፅ የሚሰጡበትን ግንዛቤ ማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል። ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በመተባበር ለምርጫው ስኬት እየሰሩ መሆኑን ጠቁመው፥ በቀጣይም ሴቶች በምርጫ ሂደት ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የሚጠበቅባቸውን ገንቢ ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
በሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብር የተሰማሩ ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እያደገ ነው
Apr 24, 2026 57
ጎንደር፤ ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፦ በጎንደር ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብር በወተት ሀብት ልማት የተሰማሩ ወጣቶች ሀብትና ጥሪት በማፍራት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ማሳደግ መቻላቸውን ተናገሩ። ወጣት አስናቀ አብተው ለኢዜአ እንደገለጸው፤ በሁለት ላሞች የጀመረውን የወተት ሀብት ልማት ሥራ ይህን አሃዝ አሁን ወደ 17 አሳድጓል። የሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብሩ ሠርቶ መለወጥ የሚለውን ህልሜን ለማሳካት ረድቶኛል፤ በአሁኑ ወቅትም ለዘጠኝ ሰዎች የሥራ ዕድል ፈጥሬያለሁ ብሏል። በቀን ከ200 ሊትር በላይ ወተት ለገበያ በማቅረብም ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱን ማሳደጉን ጠቅሷል። በቀን ከ100 ሊትር በላይ ወተት ለገበያ በማቅረብ ላይ የሚገኘው ወጣት ዓለሙ ሲሳይ በበኩሉ፤ በአንዲት ላም የጀመረውን የወተት ሃብት ልማት ሥራ በአሁኑ ወቅት ወደ ሥድስት የሚታለቡ ላሞች ከፍ አድርጓል። የሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብር የአካባቢ ጸጋዎችን ለይቶ በመጠቀም ከራስ አልፎ ለሌሎችም የሥራ ዕድል በመፍጠር ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያሳድግ መሆኑን በተግባር ማረጋገጡንም ገልጿል። መርሐ-ግብሩ የወጣቱን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በተጨባጭ የሚያረጋግጥና በአጭር ጊዜ ሠርቶ መለወጥ እንደሚቻል የሚያመላክት የተግባር ትምህርት ቤት ነው ያለው ደግሞ ወጣት አምሳሉ አካሌ ነው፡፡ በወተት ሀብት ልማት ዘርፍ በመሰማራት ከአራት ላሞቹ የሚያገኘውን የወተት ምርት እሴት ጨምሮ ለገበያ በማቅረብ ራሱንና ቤተሰቡን በተሻለ መንገድ ማኖር እንደቻለም ነው ያመለከተው። የጎንደር ከተማ አሥተዳደር እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ መላኩ ደምሌ፤ ባለፉት ሶስት ዓመታት ተግባራዊ የተደረገው የሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብር ለወጣቱ ሰፊ የሥራ እድል ለመፍጠር አስችሏል ብለዋል፡፡ የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችንና ግብዓቶችን በመጠቀም የወተት ምርትን በማሳደግ በኩል 12 ቴክኒሻኖችን በማሰልጠን ከ14 ሺህ በላይ ላሞችን የማዳቀል ሥራ መከናወኑንም አብራርተዋል። በወተት ሀብት ልማት ዘርፍ የሚታየውን የእንስሳት መኖ እጥረት ለማቃለል እንዲቻልም በሰአት 30 ኩንታል የእንስሳት መኖ ማዘጋጀትና ማቀናበር የሚችል ዘመናዊ ፋብሪካ ማቋቋም መቻሉን አስረድተዋል፡፡ በከተማው በወተት ሀብት ልማት፣ በንብ ማነብ፣ በዶሮ እርባታና በእንስሳት ማድለብ እንዲሁም በዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ በክላስተር የተደራጁ ከ25 በላይ ኢንተርፕራይዞች ተቋቁመው ወደ ሥራ መግባታቸውን ጠቁመዋል።፡
የአዋሽ ሰባት የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት የረጅም ጊዜ ጥያቄያችንን መልሶልናል-ነዋሪዎች
Apr 24, 2026 39
አዋሽ ሰባት፤ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፡-በከተማው ትናንት ለአገልግሎት የበቃው የአዋሽ ሰባት የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት የረጅም ጊዜ ጥያቄያችንን መልሶልናል ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ። ወይዘሮ ከዲጋ አብዱ በሰጡት አስተያየት፤ ይህ ፕሮጀክት ዕውን በመሆኑ ቀደም ሲል ከሚደርስባቸው ወጪና እንግልት እንደታደጋቸው ተናግረዋል። አቶ ጌትነት ኃይሉ በበኩላቸው፥የፕሮጀክቱ ሥራ መጀመር የነበረውን የውኃ ችግር መቅረፉን፤ ለውኃ ፍለጋ የሚያደርጉትን ረጅም ጉዞና የጊዜ ብክነትም ማስቀረቱን ገልጸዋል። ለረጅም ጊዜ የቆየው የውኃ ችግራችን ተቀርፎ በየቤታችን ውኃ ማግኘት ችለናል ያሉት ደግሞ አቶ መንግሥቱ ሰፊነው ናቸው። የዚህ ፕሮጀክት ዕውን መሆን በየደጃቸው ውኃ ማግኘት እንዲችሉ ያደረገ በመሆኑ መደሰታቸውንና የዘመናት ጥያቄያቸውን የመለሰ መሆኑንም ተናግረዋል። የአዋሽ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አብዶ ዓሊ ደግሞ፤ የለውጡ መንግሥት የከተማዋን እድገት ለማፋጠን ሕዝብን ባሳተፈ መንገድ ስኬቶችን እያስመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል። የተገነባው የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክትም የሕብረተሰቡን የረጅም ጊዜ የመልካም አሥተዳደር ጥያቄ የፈታ ነው ብለዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ህብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ ሆነው መሾማቸው ኢትዮጵያ በዘርፉ ላሳየችው እመርታ ተግባራዊ ምላሽ ነው
Apr 24, 2026 84
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ህብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው መሾማቸው ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ላስመዘገበቻቸው እመርታዊ ውጤቶች ተግባራዊ ምላሽ ነው ሲሉ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ እፀገነት መንግሥቱ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ኅብረት የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው ተሹመዋል። ሹመቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዘርፉ ላሳዩት አመራርና ኢትዮጵያ በአህጉሪቷ የሰው ሰራሽ አስተውሎትንና የፈጠራ ሥራዎችን ለማስፋፋት እየተገበረች ላለው የላቀ ሚና የተሰጠ እውቅና መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ሹመቱ ኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን ሥነ ምግባራዊ መርሆች በተከተለ መልኩ በማልማት፣በመመራመር እንዲሁም ተግባራዊ በማድረግ በኩል ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር እንድትሆን ለተሰሩ ስራዎች እዉቅና የሰጠ ነው በሚል ገልጾታል። ይህም አህጉራዊ ትብብር የሚፈጠርበት ብሎም ለዘርፉ ተጨማሪ ሀይል እንደሚሆን ኢንስቲትዮቱ አስታውቋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እጸገነት መንግስቱ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመት እጅግ የሚያስደስትና ለበለጠ ስራ የሚያነሳሳ ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ትላንትን መርምራ፣ የዛሬን ተጨባጭ ሁኔታ ተረድታና ነገን በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እውቀት ላይ ተመስርታ ለመተንበይ የጀመረችው ሰፊ ስራ እውቅናን በማስገኘት ላይ እንዳለ አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተሰጣቸው ሹመት የመንግሥት የፈጠራ ተነሳሽነት እና የቴክኖሎጂ ቁርጠኝነት ውጤት መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆነውም ያስመዘገበው ውጤት ግን ለዛሬው ሽልማት ያበቃ የድካም ፍሬ መሆኑን አመልክተዋል። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ በአፍሪካ ቀዳሚ ተጠቃሽ ሀገር እንድትሆን የሚያደርጋትን በርካታ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን እያከናወነች እንደምትገኝ ተናግረዋል። ኢንስቲትዩቱ የሚፈልቁ በርካታ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ተቋማት እንደ የባህሪያቸው ወስደው ተግባር ላይ ሊያውሉት ይገባል ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዙ ስራዎችን በመጠቀም ውጤት እያሳዩ የሚገኙ ተቋማት እንዳሉ ተናግረዋል። በፍርድ ቤቶች የጉዳዮችን ፍሰት በማሳለጥና ቅልጥፍናን በማምጣት ረገድ የሰው ሰራሽ አስተውሎት እየተጫወተ ያለውን ከፍተኛ ሚና ለአብነት አንስተዋል፡፡ የሀገርን ደህንነትና ሰላምን ለማረጋገጥ ቴክኖሎጂው ሰፊ ፋይዳ እያበረከተ እንደሚገኝም ጨምረው አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ ያገኘችው እውቅና ለበለጠ ስራ መነሳሳትን የሚፈጥር መሆኑን የተናገሩት የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዋ፤በቀጣይም አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን በመጨመር ጉዞው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤታማ እንዲሆን ቅንጅታዊ ሥራዎች ተከናውነዋል
Apr 24, 2026 50
ጅግጅጋ፤ ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፦ በሶማሌ ክልል የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ውጤታማ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ዝግጅት መደረጉን ባለድርሻ አካላት ተናገሩ። ተማሪ መሐመድ አሕመድ ለኢዜአ እንዳለው፤ መምህራን ከሚያደርጉላቸው የማጠናከሪያ ድጋፍ ጎን ለጎን ከጓደኞቹ ጋር በመሆን እያጠኑ ነው። ፈተናው በበይነ መረብ የሚሰጥ በመሆኑ ከወዲሁ ቴክኖሎጂን በመለማመድ ዕውቀታቸውን ማጎልበት ላይ መሆናቸውን የገለጸው ደግሞ ተማሪ ካሊድ እስማኤል ነው። የሼክ አብዱሰላም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሠ መምህር አብዱልቃድር አብድራህማን እንደገለጹት፤ የግብዓት አቅርቦትና የሰው ኃይል ዐቅም ግንባታ ላይ በቅንጅት መሠራቱን አንስተው በዚህም የሀገር አቀፍ ፈተናን ውጤታማ ለማድረግ እየተሠራ ነው ብለዋል። በክልሉ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤቶች ማሻሻል ዳይሬክተር መሐመድ መታን በበኩላቸው፤ በ2018 ሀገር አቀፍ ፈተና ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጋቸውን አረጋግጠዋል። ፈተናውን ከ16 ሺህ በላይ ተማሪዎች እንደሚወስዱ ገልጸው፤ የተማሪዎቹን ውጤት ለማሻሻል ከመደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን የማጠናከሪያ ትምህርት እንዲሠጣቸው መመቻቸቱን ተናግረዋል። የተማሪዎቹን የትምህርት አቀባበል ለመለካት የሙከራ ፈተናዎችን በመስጠት በየጊዜው ክፍተቶችን በመለየት የማስተካከያ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን አመላክተዋል። የመማሪያ መጻሕፍትን ጨምሮ ሌሎች የትምህርት ግብዓቶች በበቂ ሁኔታ እንዲደርስ መደረጉንና በማጠናከሪያ ትምህርት ከ9ኛ እስከ 11ኛ ክፍል የመከለስ ሥራ መከናወኑንም ገልጸዋል።
ፖለቲካ
በየዘርፉ የልማት ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ርዕሠ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ
Apr 24, 2026 184
ሐረር፤ ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፡- በሐረሪ ክልል በሁሉም ዘርፎች የተከናወኑ የልማት ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉ የክልሉ ርዕሠ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ። የሐረሪ ክልል መንግሥት የአስፈጻሚ አካል የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መካሄድ ጀምሯል። ርዕሠ መሥተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ግምገማው በየዘርፉ የተቀመጡ ዕቅዶችን አፈጻጸም በመፈተሽ ለቀጣይ ተግባራት ራስን ከማዘጋጀት ባለፈ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው። አፈፃፀሙን ከዕቅዱ አንፃር መፈተሽና ውስንነቶችን ለይቶ በቀሪ ሦስት ወራት መፈጸም ይገባል ብለዋል። በማኅበራዊና ኢኮኖሚው ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎች ስኬቶችና ተግዳሮቶችን እንዲሁም ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን መፈተሽ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ቱሪዝም፣ ኢንቨስትመንትና ሌሎች ዘርፎች ለክልሉ ኢኮኖሚ እድገት እያበረከቱ የሚገኘውን አስተዋጽዖ መመልከት እንደሚገባም ጠቁመዋል። የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማጎልበት ሥራዎችን አጠናክሮ ከማስቀጠል አኳያም የተከናወኑ ሥራዎች እንዲሁ። የሕግ የበላይነትን ከማረጋገጥ እንዲሁም ሙስናና ብልሹ አሠራሮችን ከማስወገድ አንጻር የተከናወኑ ተግባራትን በጥልቀት መመልከት ይገባልም ብለዋል። ሰው ተኮር የሆኑ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አስታውቀዋል።
ስዊዲን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር የበለጠ ማጠናከር እንደምትፈልግ አስታወቀች
Apr 24, 2026 184
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፡- ስዊዲን በሁለትዮሽ እና ባለብዙወገን ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር የበለጠ ማጠናከር ትፈልጋለች ሲል የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞትዎስ (ዶ/ር) ከስዊድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪያ ማልመር ስቴነርጋርድ ጋር በስቶኮልም ተወያይተዋል። በውይይታቸውም፤ በአፍሪካ ቀንድ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል። በዚሁ ወቅትም ሀገራቱ ታሪካዊ እና ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ግንኙነት እንዳላቸው ያወሱት ሚኒስትሩ፤ ወዳጅነቱን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። የሀገራቱን ግንኙነት በንግድና ኢንቨስትመንት ረገድ የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈልግም ነው ያመላከቱት። የስዊዲን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተፈጠረው ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድል እንዲጠቀሙም ጥሪ አቅርበዋል። የስዊዲን አቻቸው በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያና ስዊድን ግንኙነት ጠንካራ መሆኑን ተናግረዋል። ስዊዲን በሁለትዮሽ እና ባለብዙወገን ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር የበለጠ ማጠናከር ትፈልጋለች ብለዋል።
ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 50 ሚሊየን 514 ሺህ በላይ መራጮች ተመዝግበዋል - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
Apr 23, 2026 1875
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15/2018 (ኢዜአ)፡- ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 50 ሚሊየን 514 ሺህ በላይ መራጮች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ገለጹ። የሰባተኛው ጠቅላላ የመራጮች ምዝገባ ትናንት ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ተጠናቋል። ዜጎች በምርጫዬ የሞባይል መተግበሪያ የዲጂታል አማራጭና በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት የመራጮች ምዝገባ አከናውነዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ የምራጮች ምዝገባ መጠናቀቅን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ፤ ቦርዱ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ የዕጩዎችና የመራጮች ምዝገባ መካሄዱን ተናግረዋል፡፡ በዚህም መሰረት ከጥር 1 ቀን እስከ የካቲት 1 ቀን ድረስ የዕጩዎች ምዝገባ መከናወኑን ገልጸዋል። እንዲሁም ከየካቲት 28 ቀን ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የመራጮች ምዝገባ ለተጨማሪ 14 ቀናት ተራዝሞ ትናንት ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ምሽት መጠናቀቁን ተናግረዋል። በዚህም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እስካሁን በደረሰው መረጃ መሰረት 50 ሚሊየን 514 ሺህ 155 መራጮች መመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡ ከ5 ሚሊየን 503ሺህ በላይ የሚሆኑት መራጮች የተመዘገቡት በዲጂታል አማራጭ ሲሆን ቀሪዎቹ በማንዋል የተመዘገቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በክልሉ ለተመዘገበው ልማትና መልካም አስተዳደር የምክር ቤቶች ሚና ከፍተኛ ነው
Apr 23, 2026 1043
ሚዛን አማን፤ ሚያዝያ 15/2018(ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ለተመዘገበው ልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች መጠናከር ምክር ቤቶች የላቀ ሚና እንደነበራቸው ተገለጸ ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤትና የዞን ምክር ቤቶች የጋራ ምክክር መድረክ በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ነው። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ለ7ኛ ጊዜ የሚደረገው የጋራ የምክክር መድረክ የልምድ ልውውጥና ውጤታማ ተሞክሮዎች የሚቀመሩበት ነው ። ምክር ቤቱ ከሕዝብ የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የምክር ቤቶችን አደረጃጀት በማጠናከርና የክልሉ ሕገ መንግስት ያስቀመጣቸውን ኃላፊነቶች በተገቢው መንገድ በመፈፀም ላይ ነው ብለዋል። ከዚህ ውስጥም ባለፉት ዓመታት የአስፈጻሚ አካላት ተግባራት ላይ ክትትል፣ ድጋፍና ቁጥጥር በማድረግ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍንና ልማቶች በተገቢው መንገድ እንዲከናወኑ የድርሻውን መወጣቱን አስረድተዋል ። በዚህም የሕዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ሥራዎች በስፋት መከናወናቸውን ገልጸዋል። የመንግስት የልማት ኢኒሼቲቮች የዜጎችን ኑሮን ለማሻሻል የሚያስችሉ በመሆናቸው በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው መተግበር እንዲችሉ ምክር ቤቶቹ ጥረት እያደረጉ መሆኑን አመልክተዋል። የቤንች ሸኮ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ጌድዮን ኮስታብ በበኩለቸው፤ በሕዝቦች መካከል አንድነትና የእርስ በእርስ ትስስርን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል። የዞኑን የልማት ሥራዎች መስክ ላይ ወርዶ በመከታተልና አቅጣጫ በማሳየት መልካም ተሞክሮዎች እንዲያድጉ ምክር ቤቱ ኃላፊነቱን ያጠናክራል ብለዋል። ለሁለት ቀናት በሚካሄደው የምክር ቤቶቹ የጋራ የምክክር መድረክ ላይ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤን ጨምሮ የስድስቱም ዞኖች አፈ ጉባኤዎችና ቋሚ ኮሚቴዎች ተገኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከፕሬዝደንት ኡመር ጌሌህ የተላከ መልዕክት በመያዝ የመጡትን የጂቡቲ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ እና አለምአቀፍ ትብብር ሚኒስትር አብዱልቃድር ሁሴን ኦማርን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀበሉ
Apr 23, 2026 1110
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15/2018(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከፕሬዝደንት ኡመር ጌሌህ የተላከ መልዕክት በመያዝ የመጡትን የጂቡቲ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ እና አለምአቀፍ ትብብር ሚኒስትር አብዱልቃድር ሁሴን ኦማርን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ ጠዋት ከፕሬዝደንት ኡመር ጌሌህ የተላከ መልዕክት በመያዝ የመጡትን የጂቡቲ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ እና አለምአቀፍ ትብብር ሚኒስትር አብዱልቃድር ሁሴን ኦማርን በጽሕፈት ቤታችን ተቀብያለሁ ብለዋል። በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ስላለው ትብብርም ተወያይተናል ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሪፎርም በፓርቲዎች መካከል የትብብርና የፉክክር ሚዛን ማስጠበቅ ያስቻለ ምኅዳር ፈጥሯል
Apr 22, 2026 1843
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሪፎርም በፓርቲዎች መካከል የትብብርና የፉክክር ሚዛን ማስጠበቅ ያስቻለ ምኅዳር መፍጠሩን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ገለጹ። የ2018 በጀት ዓመት ሦስተኛው የመቶ ቀናት እና የዘጠኝ ወራት ስራ አፈጻጸም ሪፖርት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተገምግሟል። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ በሰጡት ማብራሪያ፤ ባለፉት ስምንት ዓመታት በሁሉም ዘርፎች የተወሰዱ የሪፎርም እርምጃዎች ተጨባጭ ውጤቶች አስገኝተዋል ብለዋል። በዚህም በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የተወሰዱ የሪፎርም እርምጃዎች በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ በመፈጸም ተጠባቂ ውጤቶች እንዲመዘገቡ ማድረጉን ገልጸዋል። ይህም የኢትዮጵያና ህዝቦቿን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ እመርታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲመዘገብ ማስቻሉንም ተናግረዋል። ገዥው ፓርቲ በፖለቲካው መስክ የወሰዳቸው የሪፎርም እርምጃዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የትብብርና ፉክክር ሚዛንን ማስጠበቅ ያስቻለ ምኅዳር መፍጠሩን አስረድተዋል። በዚህም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምና ወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር የሚሰሩበትን ጤናማ የፉክክር መድረክ መፈጠሩን አንስተዋል። ገዥው ፓርቲም በየደረጃው የሥራ ኃላፊዎችን የመመደብ ሥልጣንና ኃላፊነት እንዳለው አስታውሰው፤ የትብብርና የሃሳብ ልዕልና ባህልን ለማዳበር የኢትዮጵያን የመግባባት ዴሞክራሲን ማጠናከር የሚያስችል የተሳትፎ ምኅዳር መፍጠሩን ገልጸዋል። ከፌዴራል እስከ ወረዳ በሚገኙ የመንግስት መዋቅሮችም ከ275 በላይ የሚሆኑ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ተመድበው ህዝባቸውንና ሀገራቸውን እያገለገሉ መሆኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሪፎርም በመሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባትና አንድነትን ለመፍጠር አካታች ሀገራዊ ምክክሩ የተሻለ የምክክር ምዕራፍ ላይ መድረሱንም ጠቁመዋል። በቀጣይም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሪፎርም ውጤታማነትን በማስቀጠል በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባትን ለመፍጠር የተጀመሩ ጥረቶች የበለጠ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አቶ አደም አረጋግጠዋል። መንግስትና ገዥው ፓርቲም መርህን በጠበቀ መልኩ ሀገራዊ ምክክሩ በህዝብና ባለድርሻ አካላት የላቀ ተሳትፎ ግቡን እንዲመታ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል። በሌላ መልኩ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም ሌሎች ሀገራት በአርዓያነት የሚወስዱት ተጨባጭ ውጤቶች እያስገኘ መሆኑን ተናግረዋል። ለአብነትም የኢትዮጵያ ብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የሀገር ውስጥ ፍጆታን በማሟላት የዓለም አቀፍ ወጪ ንግድ ተወዳዳሪነትን ማሳደግ የሚያስችል ስኬት ማስገኘቱን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት እንዲመረት እና የተለያዩ አምራች ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም በማሳደግ ንግድና ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታ እመርታዊ ውጤት ማስገኘቱን ጠቅሰዋል። በማህበራዊ ዘርፍም ፍትሕዊ የመሰረተ ልማት ተደራሽነቶች ጥራትና አካታችነትን በማስጠበቅ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማሳደጉን አስገንዝበዋል። በተለይም የትምህርት ለትውልድ መርሃ ግብር የቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት የትምህርት ጥራትን የሚያስጠብቅ ውጤት እየተገኘበት መሆኑን አስታውቀዋል። በአጠቃላይ በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና በዲፕሎማሲው መስክ የኢትዮጵያና ህዝቦቿን ክብር በማስጠበቅ ሁለንተናዊ ብልፅግናን የሚያረጋግጡ የልማት ድሎች መገኘታቸውን አብራርተዋል። በቀጣይም የመንግስት፣ የግሉ ዘርፍና የህዝብን ተሳትፎና አቅሞችን በመደመር ሁለንተናዊ ብልፅግና፣ የዳበረ ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር የሰፈነባት፣ ዘላቂና አዎንታዊ ሰላም ባለቤት ኢትዮጵያን መገንባት ይጠበቅብናል ብለዋል።
የኢትዮጵያን የተጽዕኖና የትብብር አድማስ ያሳደጉ ስትራቴጂካዊ የዲፕሎማሲ ስኬቶች ተመዝግበዋል
Apr 22, 2026 1135
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- ባለፉት የለውጥ ዓመታት የኢትዮጵያን የተጽዕኖና የትብብር አድማስ ያሳደጉ ስትራቴጂካዊ የዲፕሎማሲ ስኬቶች መመዝገባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ገለፁ። በኢኮኖሚ፣ በተቋም ግንባታና በአካባቢ የተከናወኑ ተግባራትም ለኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ስኬት የጀርባ አጥንት መሆናቸውን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። የ2018 በጀት ዓመት ሦስተኛው የመቶ ቀናት እና የዘጠኝ ወራት ስራ አፈጻጸም ሪፖርት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተገምግሟል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) በዲፕሎማሲ መስክ የተገኙ ውጤቶችን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በዚህም ባለፉት የለውጥ ዓመታት አበረታች የዲፕሎማሲ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ በአህጉራዊና በዓለም አቀፍ መድረኮች ያላት ተጽዕኖ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መምጣቱን አስታወቀዋል። የኢትዮጵያን አንኳር ስትራቴጂካዊ ፍላጎት የሆነው የባህር በር አጀንዳ በዓለም አቀፍ መድረኮችና በሁለትዮሽ ግንኙነቶች ትልቅ ትኩረት እንዲያገኝ ተደርጓል ብለዋል። ይህም የተለያዩ አካላት የኢትዮጵያን ጥያቄ እንዲገነዘቡና ለጉዳዩ በጋራ መፍትሔ መፈለግ አስፈላጊ መሆኑን እንዲረዱ በማድረግ ረገድ ትልቅ ድል መገኘቱን ገልጸዋል። ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጫናዎች ቢኖሩም፣ የኢትዮጵያ መንግሥትና ህዝብ ጫናዎቹን በመቋቋም የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ ወደ ስራ እንዲገባ ማድረግ መቻሉ ሌላኛው ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬት መሆኑን ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ የብሪክስ ሙሉ አባል ሀገር ሆና መመረጧና ንቁ ተሳትፎ መጀመሯ የሀገሪቱን ዓለም አቀፍ ተቀባይነት የሚያሳይ መሆኑንም ነው ያብራሩት። ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንትና ለኢኮኖሚ አጋርነት ያላት ተፈላጊነት እየጨመረ መምጣቱንም ጠቅሰዋል። የቅርብና የሩቅ ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙም አስረድተዋል። የከፍተኛ አመራሮች የጉብኝት ልውውጦችና የሚፈረሙ ስምምነቶች የኢትዮጵያ የትብብር አድማስ መስፋቱን የሚያሳዩ ተጨባጭ ውጤቶች ናቸው ብለዋል። ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ ኢትዮጵያ በተለያዩ ዓለም አቀፍ የውሳኔ ሰጪ ተቋማት ውስጥ በከፍተኛ ድምፅ ስትመረጥ መቆየቷን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በተለይም በግለሰብ ደረጃ የሚወከሉ የኢትዮጵያ እጩዎች በአፍሪካም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ መሆናቸው የሀገሪቱ ተጽዕኖ ፈጣሪነት እያደገ መምጣቱን የሚያረጋግጥ እንደሆነ ገልፀዋል። የዲፕሎማሲ ስኬቱ በተጨባጭ የሀገር ውስጥ ስራዎች ላይ የተመሰረተ መሆኑንም አብራርተዋል። የኢኮኖሚ ሪፎርሙ የሀገሪቱን ተቋማት በማጠናከር ለውጤት የበቁ አቅሞች እንዲሆኑ ማስቻሉንም አንስተዋል። በአካባቢ ጥበቃና በታዳሽ ኃይል ኢንቨስትመንት የተሰሩ ስራዎች ለሌሎች ሀገራት እንደ ተምሳሌት እየታዩ መሆናቸውን ነው የተናገሩት። የከተማና የገጠር ልማት እንቅስቃሴዎች ተደምረው ኢትዮጵያ ለትብብርና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ እንድትሆን አድርገዋታል ብለዋል። በኢኮኖሚ፣ በተቋም ግንባታና በአካባቢ ጥበቃ የተከናወኑ ተግባራት ለኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ስኬት የጀርባ አጥንት መሆናቸውንም ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።
በያዝነው ካርድ ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ለመጠቀም የምርጫውን ዕለት እየጠበቅን ነው
Apr 22, 2026 1125
ሀዋሳ/ቦንጋ ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- በያዝነው ካርድ ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ለመጠቀም የምርጫውን ዕለት እየጠበቅን እንገኛለን ሲሉ የሀዋሳና የቦንጋ ከተሞች ነዋሪዎች ገለጹ። በመጪው ግንቦት 24 ቀን 2018 ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የመራጮች ምዝገባ ዛሬ ይጠናቀቃል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የሃዋሳና የቦንጋ ከተሞች ነዋሪዎች ፤ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በያዝነው ካርድ ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ለመጠቀም የምርጫውን ዕለት እየጠበቅን እንገኛለን ብለዋል። አቶ አሸናፊ አለሙ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ ፣ የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣትና ይበጀኛል ያሉትን ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫ ካርድ በመውሰድ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ ያመቻቸው ተጨማሪ የምዝገባ ቀን በስራ መደራረብ ምክንያት ጊዜ ላላገኙ ዜጎች መልካም እድልን የፈጠረ በመሆኑ ካርድ ለመውሰድ አስችሎኛል ነው ያሉት፡፡ በምርጫው ንቁ ተሳታፊ ለመሆን የምርጫ ካርድ መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን በማመን በመጨረሻው ቀን ካርድ ወስጃለሁ የሚሉት ደግሞ የከተማዋ ነዋሪ አቶ ታረቀኝ ድቃሶ ናቸው፡፡ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው ለሀገር የሚጠቅም ፓርቲን ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ተናግረው የፓርቲዎቹን የምረጡኝ ቅስቀሳ እየተከታተሉ መሆኑን ተናግረዋል። ሌላው የከተማው ነዋሪ አቶ ሙሴ ኤልያስ በበኩላቸው፤ በተመቻቸላቸው ቀን ተጠቅመው የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን ተናግረው ለሀገር ልማት ይጠቅማል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡ የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው ፤ለጠቅላላ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም የሚያስችላቸውን ካርድ በመያዝ ድምጽ የመስጫ ቀኑን እየጠበቁ መሆናቸውን ተናግረዋል። በከተማው 03 ሸታ ምርጫ ጣቢያ ካርድ ሲወስዱ ያነጋገርናቸው የቦንጋ ትምህርት ኮሌጅ ተማሪዎች መቅደስ መኮንን እና መሠለች ወንድሙ ለመጀመሪያ ጊዜ በምርጫ ለመሳተፍ የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን ገልጸዋል። በመጨረሻ ቀንም ቢሆን ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም የሚያስችላቸውን ካርድ በመውሰዳቸው መደሰታቸውን ጠቁመው፣ ይበጀናል ያሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። ተማሪ ምናሉሽ አቱሞና ሰለሞን ኮያ በበኩላቸው በወሰዱት ካርድ ለሀገር ሰላምና ልማት ይበጃል ያሉትን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ብለዋል። ሌላው የቦንጋ ከተማ ነዋሪ አቶ አብዱልቃድር አደም በበኩላቸው፤ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

ማህበራዊ
በጠቅላላ ምርጫው የሴቶችን የመምረጥና የመመረጥን ተሳትፎ የሚያሳድጉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራት እየተከናወኑ ነው
Apr 24, 2026 34
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፡- በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሴቶችንና ሌሎች ማህበረሰብ ክፍሎችን የመምረጥና የመመረጥን ተሳትፎ የሚያሳድጉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ ገለጸ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የዘንድሮውን ጠቅላላ ምርጫ ከየካቲት 28/2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የመራጮች ምዝገባ ለተጨማሪ 14 ቀናት ተራዝሞ ሚያዚያ 14/2018 ዓ.ም ምሽት ላይ ተጠናቋል። ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫም 50 ሚሊየን 514 ሺህ በላይ መራጮች በዲጂታልና በምርጫ ጣቢያ በአካል በመገኘት መመዝገባቸውን ቦርዱ ትናንት ሚያዚያ 15/2018 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። በቦርዱ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ድምፅ የሚሰጥ ሲሆን፤ 47 ተፎካካሪ ፓርቲዎችም 10 ሺህ 934 ዕጩዎችን በማስመዝገብ የፖሊሲ አማራጮቻቸውን ለህዝብ በማስተዋወቅ ላይ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ የፕሮግራም አስተባባሪ እዩኤል ዘላለም ለኢዜአ እንዳሉት፤ ምርጫ በአንድ ሀገር ውስጥ በህዝቦች ዘንድ ቅቡልነት ያለው መንግስት መመስረቻ መሳሪያ ነው። ኅብረት ለምርጫም የኢትዮጵያን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሕዊ፣ ዴሞክራሲያዊና አካታችነት ለማጠናከር የህዝብን ተሳትፎ የሚያሳደግ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። የምርጫ ሂደቱን ዴሞክራሲያዊነት፣ አካታችና አሳታፊነት ለማረጋገጥም የሴቶችንና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተሳትፎ የማንቃት ስራ እየሰሩ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በተለይም የሴቶችን የምርጫ ታዛቢነት፣የመምረጥና መመረጥ ተሳትፎን የሚያሳድጉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን በመገናኛ ብዙኅንና በአካል እየሰጡ መሆናቸውን አንስተዋል። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ሴቶችንና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎችን አሳታፊነት ለማረጋገጥም ''እኔ መርጣለሁ'' በሚል መሪ ሃሳብ የመራጮች ትምህርት ዘመቻ መጀመሩንም አስገንዝበዋል። የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ሴቶች የሚያነሷቸውን ጉዳዮች በፖሊሲ አማራጮቻቸው ላይ ያካተቷቸውን ጉዳዮች በሚገባ ማስተዋወቅ እንደሚኖርባቸው አስረድተዋል። ይህም ሴቶች ይበጀኛል ለሚሉት የፖለቲካ ፓርቲ ድምፅ የሚሰጡበትን ግንዛቤ ማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል። ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በመተባበር ለምርጫው ስኬት እየሰሩ መሆኑን ጠቁመው፥ በቀጣይም ሴቶች በምርጫ ሂደት ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የሚጠበቅባቸውን ገንቢ ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የአዋሽ ሰባት የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት የረጅም ጊዜ ጥያቄያችንን መልሶልናል-ነዋሪዎች
Apr 24, 2026 39
አዋሽ ሰባት፤ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፡-በከተማው ትናንት ለአገልግሎት የበቃው የአዋሽ ሰባት የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት የረጅም ጊዜ ጥያቄያችንን መልሶልናል ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ። ወይዘሮ ከዲጋ አብዱ በሰጡት አስተያየት፤ ይህ ፕሮጀክት ዕውን በመሆኑ ቀደም ሲል ከሚደርስባቸው ወጪና እንግልት እንደታደጋቸው ተናግረዋል። አቶ ጌትነት ኃይሉ በበኩላቸው፥የፕሮጀክቱ ሥራ መጀመር የነበረውን የውኃ ችግር መቅረፉን፤ ለውኃ ፍለጋ የሚያደርጉትን ረጅም ጉዞና የጊዜ ብክነትም ማስቀረቱን ገልጸዋል። ለረጅም ጊዜ የቆየው የውኃ ችግራችን ተቀርፎ በየቤታችን ውኃ ማግኘት ችለናል ያሉት ደግሞ አቶ መንግሥቱ ሰፊነው ናቸው። የዚህ ፕሮጀክት ዕውን መሆን በየደጃቸው ውኃ ማግኘት እንዲችሉ ያደረገ በመሆኑ መደሰታቸውንና የዘመናት ጥያቄያቸውን የመለሰ መሆኑንም ተናግረዋል። የአዋሽ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አብዶ ዓሊ ደግሞ፤ የለውጡ መንግሥት የከተማዋን እድገት ለማፋጠን ሕዝብን ባሳተፈ መንገድ ስኬቶችን እያስመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል። የተገነባው የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክትም የሕብረተሰቡን የረጅም ጊዜ የመልካም አሥተዳደር ጥያቄ የፈታ ነው ብለዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤታማ እንዲሆን ቅንጅታዊ ሥራዎች ተከናውነዋል
Apr 24, 2026 50
ጅግጅጋ፤ ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፦ በሶማሌ ክልል የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ውጤታማ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ዝግጅት መደረጉን ባለድርሻ አካላት ተናገሩ። ተማሪ መሐመድ አሕመድ ለኢዜአ እንዳለው፤ መምህራን ከሚያደርጉላቸው የማጠናከሪያ ድጋፍ ጎን ለጎን ከጓደኞቹ ጋር በመሆን እያጠኑ ነው። ፈተናው በበይነ መረብ የሚሰጥ በመሆኑ ከወዲሁ ቴክኖሎጂን በመለማመድ ዕውቀታቸውን ማጎልበት ላይ መሆናቸውን የገለጸው ደግሞ ተማሪ ካሊድ እስማኤል ነው። የሼክ አብዱሰላም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሠ መምህር አብዱልቃድር አብድራህማን እንደገለጹት፤ የግብዓት አቅርቦትና የሰው ኃይል ዐቅም ግንባታ ላይ በቅንጅት መሠራቱን አንስተው በዚህም የሀገር አቀፍ ፈተናን ውጤታማ ለማድረግ እየተሠራ ነው ብለዋል። በክልሉ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤቶች ማሻሻል ዳይሬክተር መሐመድ መታን በበኩላቸው፤ በ2018 ሀገር አቀፍ ፈተና ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጋቸውን አረጋግጠዋል። ፈተናውን ከ16 ሺህ በላይ ተማሪዎች እንደሚወስዱ ገልጸው፤ የተማሪዎቹን ውጤት ለማሻሻል ከመደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን የማጠናከሪያ ትምህርት እንዲሠጣቸው መመቻቸቱን ተናግረዋል። የተማሪዎቹን የትምህርት አቀባበል ለመለካት የሙከራ ፈተናዎችን በመስጠት በየጊዜው ክፍተቶችን በመለየት የማስተካከያ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን አመላክተዋል። የመማሪያ መጻሕፍትን ጨምሮ ሌሎች የትምህርት ግብዓቶች በበቂ ሁኔታ እንዲደርስ መደረጉንና በማጠናከሪያ ትምህርት ከ9ኛ እስከ 11ኛ ክፍል የመከለስ ሥራ መከናወኑንም ገልጸዋል።
በጭሮ ከተማ የነዳጅ አቅርቦትና አጠቃቀም መንግሥት ባስቀመጠው አሠራር መሰረት እየተተገበረ ነው
Apr 24, 2026 73
ጭሮ፤ሚያዝያ 16/2018(ኢዜአ)፦በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጭሮ ከተማ የነዳጅ አቅርቦትና አጠቃቀም መንግሥት ባስቀመጠው አሠራር ብቻ እንዲከናወን እየተደረገ መሆኑን የከተማው የሥራ ዕድል ፈጠራና ንግድ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ተወካይ አቶ አደም የሱፍ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ የነዳጅ ስርጭቱን ሕጋዊነት በመከታተልና ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የአገልግሎት ዘርፎች በማዳረስ እጥረት እንዳይከሰት ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። የነዳጅ ስርጭቱን ሕጋዊነት የማረጋገጥና በአጥፊዎች ላይ የተለያዩ የቅጣት እርምጃዎች መወሰዳቸውንም አመልክተዋል። በሕገወጥ መንገድ ነዳጅን በማከማቸት ዋጋ ጨምረው ሲሸጡ የተገኙ በርካታ ግለሰቦች ከ30 ሺሕ እስከ 100 ሺሕ ብር መቀጣታቸውንም ገልጸዋል። በጭሮ ከተማ የነዳጅ ማደያ ባለቤት አቶ አብደላ መሐመድ በበኩላቸው፤ ከመንግሥት በወረደው አቅጣጫ መሠረት ነዳጁን በአግባቡና በቁጠባ በማሰራጨት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ባለፉት 30 ቀናት ውስጥ ከ240 ሺሕ ሊትር በላይ ነዳጅ በቁጠባና ቅድሚያ ለሚሰጣቸው አካላት በአግባቡ ማሰራጨታቸውን ጠቁመዋል። ችግሩ እስኪፈታ ድረስ መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡም ተናግረዋል።
ኢኮኖሚ
በሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብር የተሰማሩ ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እያደገ ነው
Apr 24, 2026 57
ጎንደር፤ ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፦ በጎንደር ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብር በወተት ሀብት ልማት የተሰማሩ ወጣቶች ሀብትና ጥሪት በማፍራት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ማሳደግ መቻላቸውን ተናገሩ። ወጣት አስናቀ አብተው ለኢዜአ እንደገለጸው፤ በሁለት ላሞች የጀመረውን የወተት ሀብት ልማት ሥራ ይህን አሃዝ አሁን ወደ 17 አሳድጓል። የሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብሩ ሠርቶ መለወጥ የሚለውን ህልሜን ለማሳካት ረድቶኛል፤ በአሁኑ ወቅትም ለዘጠኝ ሰዎች የሥራ ዕድል ፈጥሬያለሁ ብሏል። በቀን ከ200 ሊትር በላይ ወተት ለገበያ በማቅረብም ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱን ማሳደጉን ጠቅሷል። በቀን ከ100 ሊትር በላይ ወተት ለገበያ በማቅረብ ላይ የሚገኘው ወጣት ዓለሙ ሲሳይ በበኩሉ፤ በአንዲት ላም የጀመረውን የወተት ሃብት ልማት ሥራ በአሁኑ ወቅት ወደ ሥድስት የሚታለቡ ላሞች ከፍ አድርጓል። የሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብር የአካባቢ ጸጋዎችን ለይቶ በመጠቀም ከራስ አልፎ ለሌሎችም የሥራ ዕድል በመፍጠር ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያሳድግ መሆኑን በተግባር ማረጋገጡንም ገልጿል። መርሐ-ግብሩ የወጣቱን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በተጨባጭ የሚያረጋግጥና በአጭር ጊዜ ሠርቶ መለወጥ እንደሚቻል የሚያመላክት የተግባር ትምህርት ቤት ነው ያለው ደግሞ ወጣት አምሳሉ አካሌ ነው፡፡ በወተት ሀብት ልማት ዘርፍ በመሰማራት ከአራት ላሞቹ የሚያገኘውን የወተት ምርት እሴት ጨምሮ ለገበያ በማቅረብ ራሱንና ቤተሰቡን በተሻለ መንገድ ማኖር እንደቻለም ነው ያመለከተው። የጎንደር ከተማ አሥተዳደር እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ መላኩ ደምሌ፤ ባለፉት ሶስት ዓመታት ተግባራዊ የተደረገው የሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብር ለወጣቱ ሰፊ የሥራ እድል ለመፍጠር አስችሏል ብለዋል፡፡ የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችንና ግብዓቶችን በመጠቀም የወተት ምርትን በማሳደግ በኩል 12 ቴክኒሻኖችን በማሰልጠን ከ14 ሺህ በላይ ላሞችን የማዳቀል ሥራ መከናወኑንም አብራርተዋል። በወተት ሀብት ልማት ዘርፍ የሚታየውን የእንስሳት መኖ እጥረት ለማቃለል እንዲቻልም በሰአት 30 ኩንታል የእንስሳት መኖ ማዘጋጀትና ማቀናበር የሚችል ዘመናዊ ፋብሪካ ማቋቋም መቻሉን አስረድተዋል፡፡ በከተማው በወተት ሀብት ልማት፣ በንብ ማነብ፣ በዶሮ እርባታና በእንስሳት ማድለብ እንዲሁም በዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ በክላስተር የተደራጁ ከ25 በላይ ኢንተርፕራይዞች ተቋቁመው ወደ ሥራ መግባታቸውን ጠቁመዋል።፡
ለዜጎች በርካታ የሥራ ዕድል እየፈጠረ የሚገኘው አምራች ኢንዱስትሪ
Apr 24, 2026 112
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፡- በአምራች ኢንዱስትሪዎች በተፈጠረላቸው የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ከመሆናቸው ባሻገር ዕውቀትና ክኅሎታቸውን እያሳደጉ መሆኑን በተለያዩ ፋብሪካዎች የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች ገለጹ፡፡ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ትኩረት ከሰጣቸው ዋና ዋና ዘርፎች መካከል የአምራች ኢንዱስትሪውን ዐቅም ማሳደግ አንዱ ነው። ይህም በዋናነት የውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት የውጭ ምንዛሪን ለማዳን ያለመ ነው። ይህንን ተከትሎ በተከናወነው ተግባር ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ይወጣባቸው የነበሩ ምርቶች በሀገር ውስጥ እንዲመረቱ በማድረግ ረገድ ተጨባጭ ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛሉ። በተለይም ተኪ ምርቶችን በስፋት በማምረት ለሀገር ውስጥ ገበያ ከማቅረብ ባለፈ፤ ወደ ውጭ በመላክ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ከማግኘት አንጻር ከፍተኛ ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል። አምራች ኢንዱስትሪው ለወጣቶችና ለሴቶች ሰፊ የሥራ ዕድል እየፈጠረ ሲሆን፤ የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር እንዲኖር በማድረግ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ በማሻሻል ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተም ይገኛል፡፡ ኢዜአ በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች በመዘዋወር ያነጋገራቸው የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ተጠቃሚዎች እንዳሉት፤ በተፈጠረላቸው የሥራ ዕድል ተጠቅመው ኑሯቸውን እየለወጡ ነው። በጎበዝ ማኑፋክቸሪንግ ኤሌትሪክ ኢንዱስትሪ የምትሠራው ቅድስት አስማማው እንዳለቸው፤ በተፈጠረላት የሥራ ዕድል ገቢ ከማግኘቷ በተጨማሪ ክኅሎቷን እያሳደገላት ይገኛል። ሌላኛው የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ታምራት ተሰማ በበኩሉ፤ የአምራች ኢንዱስትሪዎች መስፋፋትን ተከትሎ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ከማድረጉ በተጨማሪ የዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግርን በማሳለጥ ረገድ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ተናግሯል። ይህንንም ተከትሎ ከዚህ በፊት በሌሎች ኢንዲስትሪዎች ከነበረው ልምድ አሁን ላይ በተሻለ ቴክኖሎጂ ራሱን ብቁ ማድረግ አንስቶ በፋብሪካው በሚከፈለው ክፍያ ራሱን ከማስተዳደር አልፎ ቤተሰብም እየደገፈ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡ በዳቼ ማኑፋክቸሪንግ የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ የሆነው እዮብ ዱሬሳ በበኩሉ በድርጅቱ የሥራ ልምድ ማግኘት መቻሉን ገልጾ፤ በሚከፈለው ክፍያም ከራሱ አልፎ ቤተሰቦቹን መደገፍ መቻሉን ተናግሯል፡፡ በዚሁ ፋብሪካ በተፈጠረላት የሥራ ዕድል የኢኮኖሚ ተጠቃሚነቷ ማደግ እንደቻለ የገለጸችው ደግሞ ሌላኛዋ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ አሚራ ጀማል ናት። በሁዋጃን ልዩ ኢኮኖሚክ ዞን የጎበዝ የፀሐይ ኃይል ሶላር ሴል ማምረቻ ሥራ አስኪያጅ በረከት ኃይሉ፤ መንግሥት ለኢንዱስትሪ ዘርፉ በፈጠረው ምቹ ምኅዳር ምርታቸውን ለተለያዩ ሀገራት እየላኩ መሆኑን ተናግረዋል። በመንግሥት እየተደረገ ያለው ድጋፍ የማምረት ዐቅማቸውን እንዳሳደገውም ገልጸዋል። ድርጅቱ ከ600 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩንም አስረድተዋል። የዳቼ የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ፕላንት ማኔጀር ዐቢይ በቀለ በበኩላቸው፤ ለዘርፉ የተሰጠው ትኩረት ትልቅ ዕድል እየፈጠረላቸው መሆኑን ይናገራሉ፡፡ መንግሥት በየጊዜው በሚያደርግላቸው ድጋፍና ክትትል ምርቶቻቸውን በጥራትና በፍጥነት በማምረት ወደገበያ ተዳራሽ ለማድረግ እንዳስቻላቸውም አንስተዋል። አሁን ላይ ድርጅቱ በአራት ፋብሪካዎች 46 ዓይነት የታሸጉ ምግቦችን እያመረተ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ እያቀረበ መሆኑንም አረጋግጠዋል። ፋብሪካው ሥራ ሲጀምር በ40 ሠራተኞች ብቻ መጀመሩን አውስተው፤ መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረትም ውጤታማ መሆን በመቻሉ አሁን ላይ ከ1 ሺ 300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በጅማ ዞን ባለፉት ዘጠኝ ወራት 52 ሺህ ቶን ቡና ለገበያ ቀርቧል
Apr 24, 2026 80
ጅማ፤ ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፡- በጅማ ዞን ባለፉት ዘጠኝ ወራት 52 ሺህ ቶን ቡና ለገበያ መቅረቡን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ቲጃኒ ተማም ተናገሩ። ኃላፊው ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የሚመረተው የቡና ምርት ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ለገበያ እየቀረበ ነው፤ አቅርቦቱም በየዓመቱ እያደገ መጥቷል። ለአርሶ አደሩ በየጊዜው የሚደረገው ድጋፍ፣ ክትትልና ሥልጠና የቡና ጥራትን በተሻለ ሁኔታ መጠበቅ እንዳስቻለም ገልጸዋል። ዘንድሮ 300 ሺህ ቶን የቡና ምርት መሰብሰቡን ገልጸው፤ ከዚህ ውስጥ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 52 ሺህ ቶን ቡና ለሀገር ውስጥና ለውጪ ገበያ ማቅረብ ተችሏል ብለዋል። ጥራት ያለው ቡናን ለገበያ በማቅረብ ሂደት ውስጥ መሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ድርሻ የላቀ መሆኑንም አመላክተዋል። የጅማ ዞን የኅብረት ሥራ ማኅበራት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ድማሙ ንጋቱ በበኩላቸው፤ በዞኑ 1 ሺህ 300 መሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበራትና 4 ዩኒየኖች እንደሚገኙ ገልጸዋል። በቡና ምርት ላይ የተሰማሩ ዩኒየኖች በቡና ጥራትና አቅርቦት ላይ በትኩረት እየሠሩ መሆኑን ተናግረዋል። ዘንድሮ 4 ሺህ 800 ቶን የታጠበና ስፔሻሊቲ ቡና ለዓለም ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የዕቅዱን 60 በመቶ ማቅረብ መቻሉን አረጋግጠዋል።
ከአፍሪካ አቪዬሽን መሪነት እስከ አህጉራዊ የኢኮኖሚ ትስስር
Apr 23, 2026 200
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት በቢሾፍቱ ከተማ በይፋ መጀመሯን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል። ጋዜጠኛ ዳንኤል ኦሊቫሬስ ጋሌጎ በሲኤንኤን የጉዞ ገጽ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ እንደገለጸው፣ ይህ ሜጋ ፕሮጀክት አፍሪካውያን ተጓዦች ከአህጉሩ ውጭ ባሉ እንደ ዱባይ፣ ፓሪስና ለንደን ባሉ ማዕከላት በኩል የሚያደርጉትን አድካሚ ጉዞ በማስቀረት፣ አዲስ አበባን የአህጉሪቱ ቀዳሚ የመገናኛ ማዕከል ለማድረግ ያለመ ነው። ከአዲስ አበባ ከተማ በስተደቡብ ምስራቅ 48 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ ግዙፍ ግንባታ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአቪዬሽን መሰረተ ልማት ተብሎ መጠቀሱን ጋዜጠኛው በዚሁ ጽሁፉ አመልክቷል። ስራው በይፋ የተጀመረው ባለፈው ጥር ወር ሲሆን፣ አውሮፕላን ማረፊያው በ2023 ዓ.ም (2030 እ.ኤ.አ) የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር፣ በዓመት 60 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም እንደሚኖረው በሲኤንኤን የጉዞ ገጽ ላይ ተመልክቷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፣ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በዓመት እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል። ይህም አውሮፕላን ማረፊያውን በዓለም ላይ በርካታ ተጓዦችን ከሚያስተናግደው የአትላንታው ሀርትስፊልድ-ጃክሰን አውሮፕላን ማረፊያ ካለው አቅም በላይ እንደሚያደርገው ዳንኤል ኦሊቫሬስ ጋሌጎ ባሰፈረው ጽሁፍ አብራርቷል። አውሮፕላን ማረፊያው ከመንገደኞች አገልግሎት ባለፈ፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠናን (AfCFTA) በላቀ ሁኔታ ለመደገፍ ታቅዶ የተገነባ መሆኑን ጋዜጠኛው በሲኤንኤን የጉዞ ገጽ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ በዝርዝር አስቀምጧል። በዓመት 3 ነጥብ 73 ሚሊዮን ቶን ጭነት የማስተናገድ አቅም ያለው ይህ መሠረተ ልማት፣ በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣውን የአፍሪካን የጭነት በረራ ፍላጎት በሚገባ ምላሽ መስጠት የሚችል መሆኑን ተጠቁሟል። የአውሮፕላን ማረፊያው የተርሚናል ዲዛይን በዓለም አቀፍ ደረጃ ዝነኛ በሆነው ዛሃ ሃዲድ አርክቴክትስ የቀረበ መሆኑን የጠቀሰው ጋዜጠኛው፣ዲዛይኑ የኢትዮጵያን ታላቁ ስምጥ ሸለቆና የተለያየ መልክዓ ምድራዊ ውበትን የሚያንፀባርቅ መሆኑን በጽሁፉ አካቷል። ተጓዦች በአውሮፕላን ማረፊያው ውስጥ ሲዘዋወሩ የኢትዮጵያን ባህልና ተፈጥሮ እንዲመለከቱ በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ ሲሆን፣ለዘላቂነት ቅድሚያ በመስጠት የፀሐይ ብርሃን ኃይልንና የዝናብ ውሃ አሰባሰብ ስርዓትን እንዲጠቀም ተደርጎ ተቀርጿል። በአጠቃላይ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ መጠናቀቅ፣ኢትዮጵያ በአፍሪካ አቪዬሽን ያላትን መሪነት ከማረጋገጡ ባለፈ የአህጉሪቱን የኢኮኖሚ ትስስር ወደ አዲስ ምዕራፍ እንደሚያሸጋግረው ጋዜጠኛው በሲኤንኤን የጉዞ ገጽ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ ደምድሟል። ይህ ፕሮጀክት ከሌሎች የአፍሪካ አየር መንገዶች ጋር በመተባበር የነጠላ የአፍሪካ አየር ትራንስፖርት ገበያን (SAATM) ወደ ተግባር ለመቀየር የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ እንደሚያግዝም ተመልክቷል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ህብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ ሆነው መሾማቸው ኢትዮጵያ በዘርፉ ላሳየችው እመርታ ተግባራዊ ምላሽ ነው
Apr 24, 2026 84
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ህብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው መሾማቸው ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ላስመዘገበቻቸው እመርታዊ ውጤቶች ተግባራዊ ምላሽ ነው ሲሉ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ እፀገነት መንግሥቱ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ኅብረት የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው ተሹመዋል። ሹመቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዘርፉ ላሳዩት አመራርና ኢትዮጵያ በአህጉሪቷ የሰው ሰራሽ አስተውሎትንና የፈጠራ ሥራዎችን ለማስፋፋት እየተገበረች ላለው የላቀ ሚና የተሰጠ እውቅና መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ሹመቱ ኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን ሥነ ምግባራዊ መርሆች በተከተለ መልኩ በማልማት፣በመመራመር እንዲሁም ተግባራዊ በማድረግ በኩል ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር እንድትሆን ለተሰሩ ስራዎች እዉቅና የሰጠ ነው በሚል ገልጾታል። ይህም አህጉራዊ ትብብር የሚፈጠርበት ብሎም ለዘርፉ ተጨማሪ ሀይል እንደሚሆን ኢንስቲትዮቱ አስታውቋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እጸገነት መንግስቱ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመት እጅግ የሚያስደስትና ለበለጠ ስራ የሚያነሳሳ ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ትላንትን መርምራ፣ የዛሬን ተጨባጭ ሁኔታ ተረድታና ነገን በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እውቀት ላይ ተመስርታ ለመተንበይ የጀመረችው ሰፊ ስራ እውቅናን በማስገኘት ላይ እንዳለ አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተሰጣቸው ሹመት የመንግሥት የፈጠራ ተነሳሽነት እና የቴክኖሎጂ ቁርጠኝነት ውጤት መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆነውም ያስመዘገበው ውጤት ግን ለዛሬው ሽልማት ያበቃ የድካም ፍሬ መሆኑን አመልክተዋል። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ በአፍሪካ ቀዳሚ ተጠቃሽ ሀገር እንድትሆን የሚያደርጋትን በርካታ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን እያከናወነች እንደምትገኝ ተናግረዋል። ኢንስቲትዩቱ የሚፈልቁ በርካታ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ተቋማት እንደ የባህሪያቸው ወስደው ተግባር ላይ ሊያውሉት ይገባል ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዙ ስራዎችን በመጠቀም ውጤት እያሳዩ የሚገኙ ተቋማት እንዳሉ ተናግረዋል። በፍርድ ቤቶች የጉዳዮችን ፍሰት በማሳለጥና ቅልጥፍናን በማምጣት ረገድ የሰው ሰራሽ አስተውሎት እየተጫወተ ያለውን ከፍተኛ ሚና ለአብነት አንስተዋል፡፡ የሀገርን ደህንነትና ሰላምን ለማረጋገጥ ቴክኖሎጂው ሰፊ ፋይዳ እያበረከተ እንደሚገኝም ጨምረው አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ ያገኘችው እውቅና ለበለጠ ስራ መነሳሳትን የሚፈጥር መሆኑን የተናገሩት የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዋ፤በቀጣይም አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን በመጨመር ጉዞው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩቱ ምርታማነትን ለማሳደግና አገልግሎትን ለማቀላጠፍ የጀመራቸውን ውጤታማ ተግባራት ማጠናከር አለበት
Apr 23, 2026 305
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምርታማነትን ለማሳደግና አገልግሎትን ለማቀላጠፍ የጀመራቸውን ውጤታማ ተግባራት አጠናክሮ መቀጠል አለበት። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነት የተቋቋመውን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተገምግሟል። ኢትዮጵያ በሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ በግልጽ ራዕይና ቁርጠኝነት ባስመዘገበችው ስኬት ለአፍሪካ አርዓያ መሆኗ ዛሬ ይፋ ተደርጋል። በዚሁ መሠረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሠራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው መሾማቸው ዛሬ ይፋ ተደርጓል። ሹመቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዘርፉ ላሳዩት አመራርና ኢትዮጵያ በአህጉሪቷ የሰው ሠራሽ አስተውሎትንና የፈጠራ ሥራዎችን ለማስፋፋት እየተገበረች ላለው የላቀ ሚና የተሰጠ ዕውቅና መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፤ ሹመቱ ኢትዮጵያ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን ሥነ-ምግባራዊ መርሆች በተከተለ መልኩ በማልማት፣ በመመራመር እንዲሁም ተግባራዊ በማድረግ በኩል ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር እንድትሆን ለተሠሩ ሥራዎች ዕውቅና የሰጠ ነው በሚል ገልጾታል። ይህም አህጉራዊ ትብብር የሚፈጠርበት ብሎም ለዘርፉ ተጨማሪ ኃይል እንደሚሆን ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል። ዛሬ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኢንስቲትዩት የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገምግሟል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር ኢ/ር) ባቀረቡት ሪፖርት፤ የኢንስቲትዩቱን ችግሮች ለመፍታት፣ ብቃትንና ምርታማነትን ለማሳደግ በመረጃ ላይ የተመሰረቱ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ስርዓቶችን ማበልጸግ ላይ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል። በተለይም የሥራ ሂደቶችን በማዘመን የተቋማትን ብቃትና ምርታማነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በትጋት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። ይህም በውሳኔ አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በመድፈን ለሀገራዊ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል። ባለፉት ዘጠኝ ወራት ችግር ፈቺ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ምርምሮችን ማከናወን፣ ማልማት እና ተደራሽ ማድረግን ጨምሮ ምርምሮችን በሳይንሳዊ መጽሔቶች ማሳተም፣ ምርምሮችን ፓተንት ማስገኘት ላይ ውጤታማ ሥራ መሠራቱን ተናግረዋል። በግብርና፣ በትምህርት፣ በፋይናንስ፣ በጂኦ ስፓሻል፣ በሮቦቲክስ እና በቋንቋ በዘጠኝ ወራቱ ለመሰብሰብ እና ለማዘጋጀት የሚያስችል መረጃ መሰብሰብ መቻሉን አስታውቀዋል። ችግር ፈቺ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ምርምሮችን ማልማት እና ተደራሽ በማድረግ ረገድ አበረታች ሥራ መሠራቱንም ጠቅሰዋል። ምርምሮቹን ዓለም አቀፍ ፓተንት የማስገኘት እና የማሳተም ሥራ በታቀደው ልክ መከናወኑንም አብራርተዋል። የዘርፉን ሥነ-ምኅዳር መገንባት የሚያስችል ደረጃውን የጠበቀ ሀገራዊ የሰው ሠራሽ አስተውሎት መሠረተ ልማት መገንባቱንም ነው ያስረዱት። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወይዘሮ እጸገነት መንግስቱ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ኢንስቲትዩቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውጤታማና ለሌሎች አርዓያ መሆን የሚችል አፈፃጸም አስመዝግቧል። ወጣቶች የሥራ ፈጣሪ እና የቴክኖሎጂ ባለቤት እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ እያከናወነ ያለው ሥራ አበረታች መሆኑንም ጠቅሰዋል። በሮቦቲክስ ዘርፍ እየተከናወነ ያለው ሥራና የተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ በማሳለጥ ረገድ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል። በዘጠኝ ወራቱ በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በፋይናንስ፣ በአገልግሎት እና በሌሎች ዘርፎች የታየው አፈፃፀም አበረታች ነው ሲሉም ተናግረዋል። የሀገሪቱን ምርታማነት በማሳደግና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን እያደረገ ያለው ጥረት የሚደነቅና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑንም አመላክተዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 463/2012 ተቋቁሞ በመስከረም 2013 ዓ.ም በይፋ ሥራውን የጀመረ ሲሆን፤ በ2014 ዓ.ም ወደ ኢንስቲትዩትነት በማደግ “አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለሁሉም!” በሚል መሪ ሐሳብ በጤና፣ ግብርና፣ አገልግሎት፣ ፋይናንስ፣ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ፣ ትምህርት እንዲሁም ሌሎች በርካታ ዘርፎች ውስጥ ቴክኖሎጂውን በማልማት ላይ የሚገኝ ተቋም ነው።
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ባካሄደው የሪፎርም ትግበራ በቴክኖሎጂ የታገዘ ቀልጣፋ የፍትሕ አገልግሎት እየሰጠ ነው
Apr 23, 2026 92
ባሕርዳር፤ ሚያዝያ 15/2018 (ኢዜአ)፡- ተቋማቸው ባካሄደው የሪፎርም ትግበራ በቴክኖሎጂ የታገዘ ቀልጣፋ የፍትሕ አገልግሎት መስጠት መቻሉን የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ዓለምአንተ አግደው ገለጹ። የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል። በዚሁ ወቅትም አቶ ዓለምአንተ እንደገለጹት፤ የፍርድ ቤቶችን አገልግሎት ዲጂታላይዝ ለማድረግ የተቀረጸው የሦስት ዓመት ስትራቴጂ አተገባበር ተስፋ ሰጭ ውጤቶችን እያሳየ መሆኑን ተናግረዋል። በመጀመሪያው ምዕራፍ የታቀዱ የመሠረተ-ልማት ዝርጋታ፣ የኔትወርክ ሥራዎች እና የስማርት ችሎቶች ግንባታ ሥራዎች በስኬት መከናወናቸውን አንስተዋል። ይህም ባለጉዳዮች ባሉበት ሆነው በኢ-ፋይሊንግ ሥርዓት ክስ መመስረት፣ ይግባኝ መጠየቅና የጉዳያቸውን ሂደት በሞባይል መተግበሪያ መከታተል የሚያስችል ዘመናዊ አሠራር ሥራ ላይ መዋሉን አስረድተዋል። በቪዲዮ ኮንፈረንስ የሚታገዙ ስማርት ችሎቶች በመዘርጋታቸውም ሕብረተሰቡ ካለበት ሆኖ ክርክሩን እንዲያካሂድ በማድረግ የባለጉዳዮችን ወጪና እንግልት መቀነስ ተችሏል ነው ያሉት። የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር መኳንንት አገኘሁ (ዶ/ር)፤ የፍርድ ቤቶችን አሠራር ዘመናዊ በማድረግ ቀልጣፋና ፍትሐዊ አገልግሎት ለመስጠት፣ የፍትሕ ተደራሽነትን ለማስፋት፣ የዳኝነት አገልግሎት ጥራትን በማሻሻል የሕዝብን እርካታ ለማረጋገጥ ያስቻሉ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ በግልጽ ራዕይና ቁርጠኝነት ባስመዘገበችው ስኬት ለአፍሪካ አርዓያ ሆናለች
Apr 23, 2026 93
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 15/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት በግልጽ ራዕይ፣ በሥነ-ምግባራዊ መርሆች በመመስረት በማልማት፣በመመራመርና በተግባር በማዋል ባስመዘገበችው ስኬት በዘርፉ የአፍሪካ መሪ እንድትሆን ተመርጣለች። በዚሁ መሠረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው መሾማቸው ዛሬ ይፋ ተደርጓል። ሹመቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዘርፉ ላሳዩት አመራርና ኢትዮጵያ በአህጉሪቷ የሰው ሰራሽ አስተውሎትንና የፈጠራ ሥራዎችን ለማስፋፋት እየተገበረች ላለው የላቀ ሚና የተሰጠ እውቅና መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ሹመቱ ኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን ሥነ ምግባራዊ መርሆች በተከተለ መልኩ በማልማት፣ በመመራመር እንዲሁም ተግባራዊ በማድረግ በኩል ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር እንድትሆን ለተሰሩ ስራዎች እዉቅና የሰጠ ነው በሚል ገልጾታል። ይህም አህጉራዊ ትብብር የሚፈጠርበት ብሎም ለዘርፉ ተጨማሪ ሀይል እንደሚሆን ኢንስቲትዮቱ አስታውቋል። በሌላ በኩል ኢንስቲትዩቱ ከኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው "የአካባቢ ብክለት ዲጂታል ሪፖርት ማድረጊያ ሥርዓት" ዛሬ በይፋ ሥራ ጀምሯል። ይህ አዲስ የለማ መተግበሪያ የአካባቢ ጥበቃና የብክለት ቁጥጥር ሥራን በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ የዳታ ትንተና በማከናወን ለማዘመን እንዳለመ ተጠቁሟል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር ኢ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ተቋሙ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ "ኤ.አይ ለሁሉም" በሚል መርህ ሀገራዊ የልማት ግቦችን የሚደግፉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እያመረተ ይገኛል። ይህ መተግበሪያ ህብረተሰቡ የብክለት ጥቆማዎችን በቀላሉ እንዲያደርስና በፈጣን የዳታ ትንተና አማካኝነት ተገቢው ምላሽ እንዲሰጥ የሚያስችል መሆኑንም አስረድተዋል። የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በረከት ፍስሃጽዮን በበኩላቸው፤ መንግሥት የአሁኑንና የቀጣዩን ትውልድ ተጠቃሚነት ታሳቢ ባደረገ የኢኮኖሚ ልማት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። አሁን የለማው መተግበሪያ መንግሥት በዘርፉ የሚወስዳቸውን የፖሊሲ ማሻሻያዎችና ፈጣን ምላሾች በዳታ ላይ የተመሠረተ እንዲሆኑ ለማድረግ እንደ ትልቅ ግብዓት የሚያገለግል መሆኑን ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሌሊሴ ነሜ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሥርዓቱ በተለይ በከተሞች የተገነቡ የኮሪደር ልማት፣ የወንዝ ዳርቻ እና የጽዳት ሥራዎችን በዘላቂነት ለመጠበቅ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል። ቴክኖሎጂው ተቋማቸው በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንዲያሳልፍና የብክለት ምንጮችን በቅርበት ለመቆጣጠር እንዲቻል አቅም ይፈጥራል ሲሉ ጠቁመዋል። "ፅዱ ኢትዮጵያን" እውን ለማድረግ ህብረተሰቡ በመተግበሪያው በኩል ጥቆማዎችን በመስጠት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። ይህ የዲጂታል ሪፖርት ማድረጊያ ሥርዓት መተግበር ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራና በከተሞች ውበት ረገድ የጀመረቻቸውን ስኬታማ ሥራዎች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማስደገፍ፣ የተሻለ የአየር ንብረት ለመፍጠር ለሚደረገው ጉዞ ትልቅ አበርክቶ እንደሚኖረው ተገልጿል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #AIForAfrica
ስፖርት
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 22ኛ ሳምንት ይጀመራል
Apr 24, 2026 80
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16 /2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ከ17 እና 18 ዓመት ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታዎች በኋላ ዛሬ በ22ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ይመለሳል። መቻል ከአዳማ ከተማ ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታሉ። መቻል በሊጉ እስከ አሁን 21 ጨዋታዎችን አድርጎ በ13ቱ አሸንፎ በሁለቱ ተሸንፎ ስድስት ጊዜ አቻ ወጥቷል። 38 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ 12 ጎሎች ተቆጥረውበታል። ቡድኑ በ45 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ተጋጣሚው አዳማ ከተማ በውድድር ዓመቱ ካከናወናቸው 21 ጨዋታዎች አምስት ጊዜ ሲያሸንፍ 10 ጊዜ ሽንፈት አስተናግዷል። በቀሪው ስድስት ጨዋታዎች አቻ ተለያይቷል። 15 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያገናኝ 38 ጎሎች አስተናግዷል። አዳማ ከተማ በ21 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል። መቻል ከ21ኛ ሳምንት የአቻ ውጤት በኋላ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል። አዳማ ከተማ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ከድል ርቋል። ማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ያስገኝለታል። በሌላኛው መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና ከሃዋሳ ከተማ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ሲዳማ ቡና እስከ አሁን በሊጉ 21 ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን ስምንቱን ሲያሸንፍ በዘጠኙ ሽንፈት አስተናግዷል። በአራት ጨዋታዎች አቻ ተለያይቷል። በ21ዱ ጨዋታዎች ላይ 20 ጎሎችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ 27 ግቦችን አስተናግዷል። ቡድኑ በ28 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል። ተጋጣሚው ሃዋሳ ከተማ በበኩሉ ካከናወናቸው 21 ጨዋታዎች መካከል በ12ቱ ድል ሲቀናው ሁለት ጊዜ ተሸንፏል። በቀሪ ሰባት ጨዋታዎች ነጥብ ጥሏል። 34 ግቦችን ሲያስቆጥር 12 ጎሎች ተቆጥረውበታል። ሃዋሳ ከተማ በ43 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ያላሸነፈው ሲዳማ ቡና ማሸነፍ ወደ ድል መንገድ ይመልሰዋል። በ21ኛ ሳምንት ከሸገር ከተማ ጋር ያለ ግብ አቻ የተለያየው ሃዋሳ ከተማ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል። ሸገር ከተማ ከልደታ ክፍለ ከተማ ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። አዲስ አዳጊው ሸገር ከተማ በ40 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል። ልደታ ክፍለ ከተማ በ18 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ባለፉት ሶስት የሊጉ ጨዋታዎች አቻ የወጣው ሸገር ከተማ ማሸነፍ ወደ ድል መንገድ ይመልሰዋል። ልደታ ክፍለ ከተማ ካሸነፈ ተከታታይ ድሉን ያስመዘግባል። የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 22ኛ ሳምንት እስከ ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ54 ነጥብ ሊጉን እየመራ ነው። የኢትዮ ኤሌክትሪኳ ዳግማዊት ሰለሞን በ22 ግቦች የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን እየመራች ነው። የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ ረድኤት አስረሳኸኝ በ16 ጎሎች ትከተላለች።
በኢትዮጵያ ዋንጫ ሶስተኛው የግማሽ ፍጻሜ አላፊ የሚለይበት ጨዋታ ዛሬ ይካሄዳል
Apr 24, 2026 67
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ቤንች ማጂ ቡና እና ኢትዮጵያ መድን ዛሬ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ጨዋታው ከቀኑ 9 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ይደረጋል። በጥሎ ማለፉ ቤንች ማጂ ቡና ደብረ ብርሃን ከተማን በመለያ ምት በማሸነፍ ስምንት ውስጥ ገብቷል። ኢትዮጵያ መድን ቢሾፍቱ ከተማን 2 ለ 0 በመርታት ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል። ቤንች ማጂ ቡና በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ በ27 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። የወቅቱ የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን በአሁኑ በወቅት በ31 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። እስከ አሁን በተደረጉ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች መቀሌ 70 እንደርታ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለግማሽ ፍጻሜ አልፈዋል።
ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለኢትዮጵያ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ አለፈ
Apr 23, 2026 102
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለተኛ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መቻልን በመለያ ምት አሸንፏል። በአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ያለ ግብ አቻ በመጠናቀቁ ወደ መለያ ምት አምርቷል። በዚህም ወልዋሎ 5 ለ 4 በማሸነፍ መቀሌ 70 እንደርታን ተከትሎ ግማሽ ፍጻሜ የገባ ሁለተኛ ቡድን ሆኗል።
መቻል እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለኢትዮጵያ የግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ይጫወታሉ
Apr 23, 2026 91
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15/2018 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል። ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ መቻል ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ሩብ ፍጻሜ ለመግባት በተደረጉ ጨዋታዎች መቻል ድሬዳዋ ከተማን፣ ወልዋሎ ንብ እግር ኳስ ክለብን ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው። ሁለቱም ቡድኖች በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚገኙ ናቸው። በዘንድሮው የውድድር ዓመት በሊጉ ባደረጓቸው ሁለት ጨዋታዎች መቻል አንድ ጊዜ ሲያሸንፍ በቀሪው ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል። በሊጉ መቻል በ44 ነጥብ ሁለተኛ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ32 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዘዋል። ትናንት በተደረገ የኢትዮጵያ ዋንጫ የመጀመሪያ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር መቀሌ 70 እንደርታ ቦዲቲ ከተማን 3 ለ 2 በማሸነፍ ለግማሽ ፍጻሜ አልፏል።
አካባቢ ጥበቃ
በምሥራቅ ወለጋ ዞን በመጪው ክረምት የሚተከሉ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች በስፋት እየተዘጋጁ ነው
Apr 23, 2026 100
ነቀምቴ፤ ሚያዝያ 15/2018(ኢዜአ)፦በምሥራቅ ወለጋ ዞን በመጪው ክረምት የሚተከሉ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች በስፋት እየተዘጋጁ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። በጽሕፈት ቤቱ የተፈጥሮ ሀብት ቡድን መሪ አቶ ደሳለኝ በለጠ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች በስፋት እየተዘጋጁ ነው። በዘንድሮው መርሐ ግብር ለሁሉም የችግኝ ዓይነቶች ትኩረት ቢሰጥም፣ ይበልጥ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ዝርያዎች ላይ ትኩረት ተደርጓል ነው ያሉት። እየፈሉ ከሚገኙት ችግኞች መካከል አትክልትና ፍራፍሬ፣ የደንና ጥምር ደን ዝርያዎች፣ ቀርከሃ፣ የእንስሳት መኖ የሚገኙበት መሆኑን ነው የተናገሩት። የእጽዋት ስብጥሩ ከአካባቢው አየር ንብረት ጋር የሚስማማና በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤት የሚሰጡ መሆናቸውን ገልጸዋል። ካለፉት ዓመታት ተሞክሮ በመነሳት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የጉድጓድ ዝግጅት መጀመሩን የጠቆሙት አቶ ደሳለኝ፤ የአየር ንብረት ጥናት፣ የአፈርና ውሃ ጥበቃ እንዲሁም የሕብረተሰቡን ተሳትፎ የሚያሳድጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል። ለዘንድሮው ተከላ የሚውል 107 ሺህ ሄክታር መሬት የተዘጋጀ ሲሆን፣ በዞኑ በሚገኙ 2 ሺህ 194 የመንግሥትና የግል የችግኝ ጣቢያዎችም የችግኝ እንክብካቤ ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው ችግኝ መትከል ከመደበኛ መርሐ ግብር ባለፈ የሥራ ባሕላቸው እየሆነ መምጣቱን ይናገራሉ። አስተያየታቸውን ከሰጡት መካከል ወይዘሮ አዲስዓለም በለጠ ባለፉት ዓመታት በተተከሉ ችግኞች በአካባቢው የተፈጥሮ ሀብት ለውጥ መታየቱን ገልጸዋል። አቶ ተሰማ መኮንንም በተመሳሳይ ቀደም ሲል ለደን የነበረው ዝቅተኛ አመለካከት ተቀይሮ፣ ዛሬ ሕብረተሰቡ የተራቆቱ ቦታዎችን መልሶ በማልማትና በመንከባከብ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ለዘንድሮው ተከላም አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል።
የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት በአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው
Apr 22, 2026 126
ሐዋሳ፤ ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት በአፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ጥምረት (AGRA) የቦርድ ሊቀመንበር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ። ሊቀመንበሩ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ከሀገር ባለፈ አህጉራዊ የልማት ትብብርና ትስስርን መሰረት ባደረገ መልኩ በስኬት መቀጠሉን አንስተዋል። ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂዋ ከተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለውጥን ከመከላከል ባለፈ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል። በተለይም ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የልማት ሥራዎች አስደናቂ መሆናቸውን አውስተው፤ እንደ ሀገር ትልቅ ስኬት የተመዘገበበት መሆኑን ተናግረዋል። ባለፉት ዓመታት በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞች መተከላቸው የተፈጥሮ ሃብትን ከመጠበቅና የአየር ንብረት ለውጥን ከመከላከል ባለፈ የምግብ ዋስትና መሰረት መሆናቸው በተግባር ታይቷል ብለዋል። በመሆኑም የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት በአፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ነው ያመላከቱት። ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ላይ ትኩረት ተደርጎ መሠራቱም ለግብርና ልማትና ምርታማነት መሰረት እየሆነ መጥቷል ነው ያሉት። የዘርፉ ልማት ቀጣይነትን የሚጠይቅ በመሆኑ ችግኞችን መትከል እንዳለ ሆኖ፤ የተተከሉትን የመጠበቅና የመንከባከብ ልምድ እየዳበረ መሄድ እንዳለበትም ጠቁመዋል።
በከተማ አስተዳደሩ የተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ ሥራዎች አርሶ አደሩን ተጠቃሚ አድርገዋል
Apr 21, 2026 315
ወላይታ ሶዶ፤ሚያዚያ 13/2018(ኢዜአ)፦በወላይታ ሶዶ ከተማ በአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት እያረጋገጡ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ። በከተማ አስተዳደሩ "አረንጓዴ አሻራ ለተምሳሌት ሀገር ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል የዘንድሮ የበልግ ወቅት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በመርካቶ ክፍለ ከተማ ቦሳ ዝጋ ቀበሌ ተካሂዷል። የከተማው ከንቲባ ወይዘሮ እታገኝ ኃይለማርያም በመርሃ ግብሩ ላይ እንደገለጹት ባላፉት የለውጡ ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት አረጋግጠዋል። በመርሀ ግብሩ የተተከሉ ችግኞች የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ በተጨማሪ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና ሚዛኑን ለመጠበቅ እያገዙ መሆናቸውን ተናግረዋል። በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም የችግኝ ተከላ ሥራውን ለማስቀጠል የቡና፣ የእንሰት የአቮካዶና ሌሎች የፍራፍሬ ችግኞችን ለመትከል ሙሉ ዝግጅት በማድረግ ወደ ሥራ መገባቱንም ተናግረዋል። የወላይታ ሶዶ ከተማ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ንጋቱ ቡሹራ በበኩላቸው ባለፉት ዓመታት በተሰሩ የአረንጓዴ አሻራ ስራዎች የአርሶ አደሩን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ ተችሏል። ለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ለተከላ ከተዘጋጁ ችግኞች ውስጥ 150 ሺህ የሚሆኑት የተሻሻሉ የቡና ዝርያ ችግኞች መሆናቸውንም አመልክተዋል። ከዚህ በተጨማሪ ምርታማነታቸው በምርምር የተረጋገጡ የእንሰት፣ የአቮካዶ እና ሌሎች የፍራፍሬ ችግኞች መዘጋጀታቸውን ነው የገለጹት። የሚተከሉ ችግኞች ውጤታማ እንዲሆኑም የተጠናከረ የባለሙያዎች ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል። በመርሀ ግብሩ ላይ ከተሳተፉ አርሶ አደሮች አቶ ደበላ ዳና እና አቶ ኤልያስ ጁና በውሃ ገብ መሬቶችና እና በእርሻ ማሳቸው ላይ ባህር ዛፎችን እና ያረጁ ቡናዎችን በመተካት ልማቱን ማከናወናቸውን ጠቁመዋል። በችግኝ ተከላው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ፍራፍሬዎችን በመትከል ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ በበኩላቸው በዞኑ ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች መተከላቸውን አንስተዋል። በዘንድሮ የአረንጎዴ አሻራ መርሃግብርም የቡና ችግኝ በስፋት ለመትከል ዝግጅት መደረጉን ነው የገለጹት። አርሶ አደሮችም በመርሀግብሩ ቡናና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የፍራፍሬ ችግኞችን ተክለው በመንከባከብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያሳድጉ አሳስበዋል። በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የዞንና የከተማ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎች እንዲሁም አርሶ አደሮች ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የወሰደቻቸው ተጨባጭ እርምጃዎች ውጤት እያስገኙ ነው
Apr 21, 2026 170
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የወሰደቻቸው ተጨባጭ እርምጃዎች ውጤት እያስገኙ መሆኑን የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለጸ። ኢንስቲትዩቱ ከአፍሪካ የሚቲዎሮሎጂ ሶሳይቲ ጋር በመተባበር ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀውን ሳይንሳዊ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተርና በዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዚዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ለዘርፉ ተስማሚ የሆኑ የኃይል አማራጮችንና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን በተግባር እያከናወነች ትገኛለች፡፡ ለዚህም እንደ አብነት ከሚጠቀሱት መካከልም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የታዳሽ ኃይል ልማት ተምሳሌትና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ግንባታ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተተገበረ ያለው የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና የደን ልማት ስራዎች ተጨባጭ መፍትሄዎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ድንበር ተሻጋሪ በመሆኑ ተጽዕኖውን ለመቋቋም የጋራ ጥረትና ትብብር መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከኮንፈረንሱ ለአፍሪካ ውጤታማ የሆኑ ሳይንሳዊ መፍትሄዎች እንደሚገኙም ገልጸዋል፡፡ የአፍሪካ የሚቲዎሮሎጂ ሶሳይቲ የቦርድ ሰብሳቢ ቡሩሃኒ ናይንዚ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ሶሳይቲው የተቋቋመው ሀገር አቀፍ የሚቲዎሮሎጂ ማህበራትን ለማጠናከርና በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎችን ለማስተሳሰር መሆኑን ገልጸዋል። ሳይንሳዊ ኮንፈረንሱ በአካባቢ ጥበቃ፣ በአየር ትንበያና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የሚሰሩ ተቋማትና ባለድርሻ አካላትን እንደሚያገናኝም ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም የልምድና የዕውቀት ልውውጥ በማድረግ የባለሙያዎችን አቅም እንደሚገነባ ጠቅሰው በአፍሪካ የሚቲዎሮሎጂ ሳይንስ እድገት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ጠቁመዋል፡፡ ይህ ኮንፈረንስ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ያላትን ተሞክሮ ለማካፈል እንደሚረዳም ተጠቁሟል፡፡
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ እሴቶች ተምሳሌት ነበሩ
Apr 7, 2026 480
አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ከፍተኛ እሴት በተግባር ያሳዩ ታላቅ ዲፕሎማት ነበሩ ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። ሊቀመንበሩ በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ ስመጥር በሆኑት አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል። ሊቀመንበሩ አምባሳደሯን የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት አገልግሎት ፈር ቀዳጅ፣ ታላቅ ዲፕሎማት እና ህይወታቸውን ለሀገራቸውና ለአህጉሪቱ እድገት የሰጡ ጽኑ አፍሪካዊት ሲሉ አወድሰዋቸዋል። አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ ለበርካታ አስርተ አመታት የዘለቀ አርአያነት ያለው ሙያዊ ስኬት ማስመዝገባቸውንና ከኢትዮጵያ ቀዳሚ ሴት አምባሳደሮች አንዷ በመሆንም ለአፍሪካውያን ሴት ዲፕሎማቶች የብርሃን ፋና መሆናቸውን አመልክተዋል። የአፍሪካን ጥቅም ለማስከበርና ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጠናከር የነበራቸው የማይናወጥ ቁርጠኝነት ለአህጉራዊ የጋራ ግቦች መሳካት የጎላ ሚና እንደነበረውም አውስተዋል። ሊቀመንበሩ አምባሳደር ቆንጂት በታማኝነት፣ በልዩ ብቃት እና ለጋራ የወደፊት እጣ ፈንታ የነበራቸው ጽኑ ቁርጠኝነት የአፍሪካ ዲፕሎማሲ እሴቶች ያላቸውን ጽኑ አቋም ያሳየ መሆኑንም ነው ያነሱት። የአምባሳደሯ የዲፕሎማሲ አሻራ ለቀጣይ ትውልድ ዲፕሎማቶች፣በተለይም ለሴቶች፣በድፍረትና በዓላማ እንዲያገለግሉ ዘላቂ መነሳሳት ሆኖ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል። ሊቀመንበሩ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ስም ለአምባሳደር ቆንጂት ቤተሰቦች፣ ለኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ፣ እንዲሁም ለሁሉም አፍሪካውያን ልባዊ መጽናናትን ተመኝተዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት ሊቀ መንበርነትን ተረከበች
Apr 3, 2026 386
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 25/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የእ.አ.አ አፕሪል 2026 የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት (AU PSC) ተዘዋዋሪ ሊቀመንበርነትን በይፋ መረከቧን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ኢትዮጵያ ሊቀ መንበርነቱን የተረከበችው ከኮትዲቯር ነው። ኢትዮጵያ መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ.ም የምክር ቤቱን አጀንዳዎች በሊቀመንበርነት መምራት እንደምትጀምር ሚኒስቴሩ አመልክቷል። በዚህም ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2025 በድጋሚ የምክር ቤቱ አባል ሆና ከተመረጠች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊቀ መንበር መሆን ችላለች። በሊቀመንበርነት ቆይታዋ ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ በሚገኙ አገራዊ እና ወቅታዊ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ ውይይቶችን እንደምትመራ ሚኒስቴሩ አስታውቋል። የኢትዮጵያን ሊቀ መንበርነት በይፋ ለማብሰር እና አዲስ የተመረጡ የምክር ቤቱን አባላት ለመቀበል መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሰብሳቢነት የሰንደቅ ዓላማ የማውለብለብ ሥነ-ሥርዓት ይከናወናል። ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2004 ምክር ቤቱ ከተመሰረተ ጀምሮ በአባልነት ስታገለግል የቆየች መሆኑን የጠቀሰው የሚኒስቴሩ መግለጫ፤ እ.አ.አ በ2025 በድጋሚ ለሦስት ዓመታት አባል ሆና መመረጧን አውስቷል። ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም አራት ጊዜ የምክር ቤት አባል ሆና ተመርጣ በንቃት ስትሳተፍ መቆየቷ ተወስቷል።
ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል
Mar 28, 2026 674
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት እንደሚያስፈልግ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ አስገነዘቡ። 11ኛው የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ በማላቡ ኢኳቶሪያል ጊኒ እየተካሄደ ይገኛል። በጉባኤው እየተሳተፋ የሚገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል ብለዋል። ተለዋዋጭ በሆነው የአለም የኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ውስጥ የአባል ሀገራቱን ጥቅም የሚያስከብር ጠንካራ ድርጅት ሆኖ መቀጠል እንዳለበትም በአፅንኦት ተናግረዋል። ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በንግግራቸው ለድርጅቱ ጥንካሬ ይበጃሉ ያላቸውን ሀሳቦችም አካፍለዋል። በዚህም ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል ነው ያሉት። ለዚህም የደቡብ - ደቡብ ግንኙነትን ማጠናከር ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ያሉ ሲሆን መካከለኛ እና ከፍተኛ ኢኮኖሚን ከገነቡ ሀገራትና ድርጅቶች ጋር ያለን ግንኙነት ከቀደመው የእርዳታ ሰጭ እና ተቀባይ ግንኙነት ወደ የጋራ ተጠቃሚነት ለማሸጋገር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። የድርጅቱ አባል ሀገራት ተመሳሳይ የባለቤትነት ስሜትን ማዳበር እንዳለባቸውም ፕሬዚዳንቱ ጠቁመዋል። ቀጣይነት ያለው ልማት ማረጋገጥ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ መገንባትና ሰላምና ፀጥታን ለማስፈን መስራት የአባል ሀገራት የጋራ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆን እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት አባል ሀገራት ዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ ያላቸው ሚና ከተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት(አምራችነት) መሸጋገር እንዳለበትም ተናግረዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ ሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ጉዳይ በልዩ ትኩረት ሊሰራባቸው እንደሚገባም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት ረገድ ባስመዘገበቻቸው ውጤቶች ቀጣዩን የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን (ኮፕ 32) እንድታስተናግድ መመርጧን አስታውሰዋል። ይህም የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ልማት በመገንባት ሂደት ያላቸውን ተሞክሮ የሚያቀርቡበት ትልቅ ዕድል እንደሆነም ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በበኩላቸው ሶስቱም ቀጣናዎች የጎላ አስተዋጽኦ ባላደረጉበት የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ጉዳት እያስተናገዱ መሆናቸውን አንስተዋል። የአየር ንብረት ፍትህ እንዲረጋገጥ የተባበረ እንቅስቃሴ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። በጉባኤው አፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ክልሎችን የወከሉ መሪዎች ንግግር ያደረጉ ሲሆን አፍሪካን በመወከል የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር እና የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ኤቫሪስት ንድዪሺሚዬ መልእከት አስተላልፈዋል። የድርጅቱን የፋይናንስ ምንጭ ቀጣይነት ማረጋገጥ፣ የድርጅቱን መዋቅራዊ አሰራር ማጠናከር እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የጋራ አቋም መያዝ በጉባኤው ጎልተው የተሰሙ ድምፆች መሆናቸውን ኢዜአ ከስፍራው ዘግቧል። በማላቡ ኢኳቶሪያል ጊኒ እየተካሄደ የሚገኘው 11ኛው የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ እስከ ነገ መጋቢት 20/2018 ዓም ድረስ ይቆያል። በጉባኤው ከሶስቱም ክልሎች የሚገኙ የሀገራት መሪዎች እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የዓለም የውሃ ቀን እየተከበረ ነው
Mar 22, 2026 368
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 13/2018 (ኢዜአ)፦ 34ኛው የዓለም የውሃ ቀን ዛሬ በዓለም ደረጃ እየተከበረ ይገኛል። “ውሃ እና ስርዓተ ጾታ” የዘንድሮ መሪ ቃል ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የውሃ ቀን ቁልፍ መልዕክቶችን ይፋ አድርጓል። ተመድ የዓለም የውሃ ቀውስ ለሁሉም ሰው የሚተርፍ ቢሆንም ተፅዕኖው ግን እኩል እንዳልሆነ አመልክቷል። ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ እና የንጽሕና መጠበቂያ አገልግሎቶችን የማግኘት ሰብአዊ መብታቸው በማይከበርባቸው ቦታዎች ላይ ኢ-ፍትሃዊነት ጎልቶ እንደሚታይ ገልጿል። በዚህም ሴቶችና ልጃገረዶች የችግሩ ዋነኛ ሰለባ እንደሚሆኑ ጠቅሶ ሴቶችና ልጃገረዶች የውሃ መፍትሔዎች ማዕከል የምናደርግበት ጊዜ አሁን ነው ብሏል። ሴቶች የውሃን የወደፊት ዕጣ ፈንታ መቅረጽ አለባቸው ያለው ተመድ ለዚህም የሴቶች ድምፅ፣ አመራር እና ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ ነው ያስታወቀው። በዘንድሮው የዓለም ውሃ ቀን ከሚተላለፉ መልዕክቶች አንዱ ውሃ ባለበት እኩልነት ያብባል የሚለው እሳቤ ነው። ሴቶችና ልጃገረዶች በውሃ ውሳኔዎች ላይ እኩል ድምፅ ሲኖራቸው፣ አገልግሎቶቹ ይበልጥ አካታች፣ ቀጣይነት ያላቸው እና ውጤታማ እንደሚሆኑ ተመድ አመልክቷል። ለሁሉም የሚተርፍ ጤናማ፣ የበለጸገ እና እኩልነት የሰፈነበት መጻኢ ጊዜን ለመገንባት፤ የሴቶች የውሃ ዘርፍ አመራር ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችል ስራን ማከናወን እንደሚገባም አስታውቋል። የዓለም የውሃ ቀን ከእ.አ.አ 1993 ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል። እ.አ.አ 1992 በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የከባቢ አየር እና ልማት ኮንፍረንስ (ሪዮ ኮንፍረንስ) የዓለም መሪዎች የውሃ ሀብቶችን መጠበቅ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አንስተዋል። ከኮንፈረንሱ ውጤቶች መካከል አንዱ ውሃን አስመልክቶ ግንዛቤ መፍጠር ላይ ያተኮረ ቀን የመሰየም ምክረ ሀሳብ ነው። በዚሁ መሰረት ተመድ እ.አ.አ 1992 ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ በዓለም አቀፍ ደረጃ በማርች 22 እንዲከበር ውሳኔ አስተላልፏል። ውሳኔውን ተከትሎ የዓለም የውሃ ቀን ከእ.አ.አ 1993 ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል። በዓለም በላይ ከሁለት ቢሊዮን በላይ ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ እንደማያገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ። የአየር ንብረት ለውጥ እና ፈጣን የህዝብ እድገት ለውሃ እጥረት ዋንኛ መንስኤዎች ናቸው።
ሐተታዎች
ከአፍሪካ አቪዬሽን መሪነት እስከ አህጉራዊ የኢኮኖሚ ትስስር
Apr 23, 2026 200
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት በቢሾፍቱ ከተማ በይፋ መጀመሯን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል። ጋዜጠኛ ዳንኤል ኦሊቫሬስ ጋሌጎ በሲኤንኤን የጉዞ ገጽ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ እንደገለጸው፣ ይህ ሜጋ ፕሮጀክት አፍሪካውያን ተጓዦች ከአህጉሩ ውጭ ባሉ እንደ ዱባይ፣ ፓሪስና ለንደን ባሉ ማዕከላት በኩል የሚያደርጉትን አድካሚ ጉዞ በማስቀረት፣ አዲስ አበባን የአህጉሪቱ ቀዳሚ የመገናኛ ማዕከል ለማድረግ ያለመ ነው። ከአዲስ አበባ ከተማ በስተደቡብ ምስራቅ 48 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ ግዙፍ ግንባታ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአቪዬሽን መሰረተ ልማት ተብሎ መጠቀሱን ጋዜጠኛው በዚሁ ጽሁፉ አመልክቷል። ስራው በይፋ የተጀመረው ባለፈው ጥር ወር ሲሆን፣ አውሮፕላን ማረፊያው በ2023 ዓ.ም (2030 እ.ኤ.አ) የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር፣ በዓመት 60 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም እንደሚኖረው በሲኤንኤን የጉዞ ገጽ ላይ ተመልክቷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፣ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በዓመት እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል። ይህም አውሮፕላን ማረፊያውን በዓለም ላይ በርካታ ተጓዦችን ከሚያስተናግደው የአትላንታው ሀርትስፊልድ-ጃክሰን አውሮፕላን ማረፊያ ካለው አቅም በላይ እንደሚያደርገው ዳንኤል ኦሊቫሬስ ጋሌጎ ባሰፈረው ጽሁፍ አብራርቷል። አውሮፕላን ማረፊያው ከመንገደኞች አገልግሎት ባለፈ፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠናን (AfCFTA) በላቀ ሁኔታ ለመደገፍ ታቅዶ የተገነባ መሆኑን ጋዜጠኛው በሲኤንኤን የጉዞ ገጽ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ በዝርዝር አስቀምጧል። በዓመት 3 ነጥብ 73 ሚሊዮን ቶን ጭነት የማስተናገድ አቅም ያለው ይህ መሠረተ ልማት፣ በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣውን የአፍሪካን የጭነት በረራ ፍላጎት በሚገባ ምላሽ መስጠት የሚችል መሆኑን ተጠቁሟል። የአውሮፕላን ማረፊያው የተርሚናል ዲዛይን በዓለም አቀፍ ደረጃ ዝነኛ በሆነው ዛሃ ሃዲድ አርክቴክትስ የቀረበ መሆኑን የጠቀሰው ጋዜጠኛው፣ዲዛይኑ የኢትዮጵያን ታላቁ ስምጥ ሸለቆና የተለያየ መልክዓ ምድራዊ ውበትን የሚያንፀባርቅ መሆኑን በጽሁፉ አካቷል። ተጓዦች በአውሮፕላን ማረፊያው ውስጥ ሲዘዋወሩ የኢትዮጵያን ባህልና ተፈጥሮ እንዲመለከቱ በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ ሲሆን፣ለዘላቂነት ቅድሚያ በመስጠት የፀሐይ ብርሃን ኃይልንና የዝናብ ውሃ አሰባሰብ ስርዓትን እንዲጠቀም ተደርጎ ተቀርጿል። በአጠቃላይ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ መጠናቀቅ፣ኢትዮጵያ በአፍሪካ አቪዬሽን ያላትን መሪነት ከማረጋገጡ ባለፈ የአህጉሪቱን የኢኮኖሚ ትስስር ወደ አዲስ ምዕራፍ እንደሚያሸጋግረው ጋዜጠኛው በሲኤንኤን የጉዞ ገጽ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ ደምድሟል። ይህ ፕሮጀክት ከሌሎች የአፍሪካ አየር መንገዶች ጋር በመተባበር የነጠላ የአፍሪካ አየር ትራንስፖርት ገበያን (SAATM) ወደ ተግባር ለመቀየር የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ እንደሚያግዝም ተመልክቷል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
በኢዜአ ዐይን …!
Apr 19, 2026 324
የምግብ ሉዓላዊነት - ከተረጂነት መላቀቂያው መንገድ በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ ከተረጂነትና ጠባቂነት መፋቻ መንገዶች መካከል የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ አንዱ ብልኀት አድርጋ እየታተረች ነው። ይህን ተከትሎም የዜጎችን የምግብ ፍላጎት በራስ የምርት ዐቅም የመሸፈን ሥራ በመከወን ከጠባቂነት ለመላቀቅ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ስኬታማ ናቸው። ለዚህም ኢትዮጵያ በስንዴ ልማት ከልመና ወጥታ ወደ ውጭ ገበያ መላክ መጀመሯ አሥረጅ ነው። በመሆኑም ከውጭ የኢኮኖሚ ጥገኝነት በመላቀቅ የዜጎችን የምግብ ሉዓላዊነት ለማስከበር በስንዴ ልማት የተመዘገበውን ስኬት በሌሎች የግብርና ዘርፎች ለመድገም ርብርብ እየተደረገ ነው። በዚህም መሠረት በሩዝ፣ አትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ ሻይ ቅጠል እና ሌሎች የተለያዩ ሰብሎች ላይ እየተከናወነ ያለው ሥራ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው። የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የግብርና ድርጅት (ፋኦ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምግብ ዋስትናና በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ላሳዩት ርዕይ፣ የአመራር ቁርጠኝነት የአግሪኮላ ሜዳሊያ በ2016 ዓ.ም ማበርከቱ ለምግብ ሉዓላዊነት ጥረት የተሰጠ ዕውቅና ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ረሃብን ከማስቀረት ባለፈ የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ብሔራዊ ብልጽግናን ዕውን ለማድረግ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በርካታ ያልተነኩ ጥሬ ሃብቶች፣ተስማሚ የዓየር ንብረት፣ ለሥራ ትጉ የሆነ ወጣት እንዳላት እና እነዚህን ሃብቶች ታሳቢ በማድረግ የታሪክ ዐውራ የሆነችውን ሀገር ልማት ወደፊት ለማራመድ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም አስረድተዋል። በአንድ ወቅት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር ዋጋ እንደከፈልን ሁሉ፤ ከምግብ ጥገኝነት ለመላቀቅ በትጋት መሥራት ይገባል ሲሉ ማስገንዘባቸው ይታወሳል። የምግብ ሉዓላዊነት፣የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት፣ የበጀት ሉዓላዊነት ታላቁን የሀገር ሉዓላዊነት በጽናት የሚያቆሙ መሆናቸውንም አብራርተዋል። እነዚህን የሉዓላዊነት ዘርፎች ለማስከበርም ብሔራዊ ዐርበኝነት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል። ሀገራዊ ትልሙ ኢትዮጵያን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ክብር፣ ነጻነት እና ሉዓላዊነት የሚያሸጋግር መልካም ጅማሮ ነው።
የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር
Apr 19, 2026 159
ክልሎች፤ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡-የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በሀገራችን ሁሉም ክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን? የንፋስ ሃይል በቀጥታ የምናመራው በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ ኢተያ አካባቢ ነው። በኢተያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተገኝተው የመረቁትን የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫን እንመለከታለን። የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ 100 ሜጋ ዋት ኃይል የሚያመነጭ ሲሆን ኢትዮጵያ በታዳሽ ሃይል ልማት ወደ ፊት እየተራመደች መሆኑን በተግባር ያረጋገጠ ሥራ ነው። ኢትዮጵያ ዘንድሮ ከጉባ እስከ አሰላ፣ ገናሌ እና አይሻ በሃይል ልማት ዘርፍ ትልቅ ትርጉም ያላቸውን ፕሮጀክቶች አስመርቃለች። የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ደግሞ በዚህ ሳምንት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተመርቆ በይፋ ሥራ ጀምሯል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በምርቃቱ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ከለውጡ በፊት የነበረው 4 ሺህ ሜጋ ዋት የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅም አሁን ላይ ወደ 10 ሺህ ሜጋ ዋት በመድረስ ከእጥፍ በላይ እድገት የተመዘገበበትን ትልቅ ስኬት አንስተዋል። የስንዴና ገብስ ሰብሎችን በከፍተኛ መጠን የሚያመርተው አርሲና አካባቢው አሁን ላይ የኤሌክትሪክ ሃይል የሚመረትበት አካባቢ መሆኑንም ገልጸዋል። በመሆኑም በሁሉም መስክ የኢትዮጵያን የብልፅግና ጉዞ እናስቀጥላለን ሲሉ አረጋግጠዋል። ቢሾፍቱ የኦሮሚያ ክልል መንግስት የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማም በዚህ ሳምንት በቢሾፍቱ ሀርሰዴ አዳራሽ መካሄዱ ይታወቃል። በዚህ መድረክ ላይ የተገኙት የክልሉ ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ፤ በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በርካታ ስኬታማ የልማት ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል። በተለይም የክልሉን ሕዝብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በተሻለ መልኩ ያሳደጉ የከተማ እና የገጠር የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን ነው ያስረዱት። ከዚህ ባለፈ የክልሉን የልማት ሥራዎች ለማቀላጠፍ የሚያግዙ በቴክኖሎጂ የተደገፉ የአገልግሎት አሰጣጥ አሰራሮች መተግበራቸውንም ተናግረዋል። የቢሾፍቱ መድረክ በድምሩ የግብርና፣ የገጠርና የከተሞች ልማት፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ክንውን በዝርዝር የታየበት ውጤታማ መድረክ እንደነበረም ተመላክቷል። የአሎማ ክላስተር ሌላ የሳምንቱ ዓበይት ጉዳይ ወደ አማራ ክልል ደቡብ ወሎ ይወስደናል። የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት በይፋ አገልግሎት መስጠት የጀመረው በዚህ ሳምንት ነው። በመስኖ የለማ የስንዴ ክላስተር የተጎበኘበትና በተሁለደሬ ወረዳ በክላስተር ለሚከናወነው የተቀናጀ የፍራፍሬ ልማት የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በይፋ የተጀመረበት እንዲሁም የክልሉ የ10 ዓመት የግብርና ሽግግር ፍኖተ ካርታ ይፋ የተደረገበትን ሁነት እናገኛለን። በእነዚህ ሁነቶች ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ የመደመር መንግሥት በሁሉም ዘርፎች ለሀገር እድገትና ማንሰራራት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህም በግብርና፣ በመስኖ ልማት፣ በቱሪዝምና ሌሎች መስኮች በተግባር የተመለከትናቸው የልማት ሥራዎች ተጨባጭ ማሳያዎች ናቸው ሲሉ ተናግረዋል። የአሎማ ክላስተር የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት፣ የሓይቅ ዳር አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራስን የማቻል ጥረት በስኬት መንገድ ላይ መሆኑን የሚያሳዩ መሆኑን ጠቅሰው፤ ሀገርን የማሻገር ሥራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የታሪክ መሰነጃ የሳምንቱ በረራችን እንደቀጠለ ሲሆን አሁን ደግሞ የሰው ልጅ መገኛ፣ የኤርታሌ ትኩሳት የሚገነፍልባትና የአዋሽ ወንዝ የተንጣለለባት አፋር ክልል ገብተናል። በአፋር ቆይታችን ትኩረታችንን ሰመራ በማድረግ በስፍራው ሊገነባ የታሰበውን የሉሲ ሙዚየም እንመለከታለን። ሙዚየሙን ለመገንባት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን እና የአፋር ክልል ቱሪዝም ቢሮ የፕሮጀክት ግንባታ ስምምነት አድርገዋል። ለሉሲ አፋር ቤቷ ነው፤ ሀዳር የተባለው ስፍራ ደግሞ መገኛዋ ነው። በመሆኑም በዚህ ከሰው ልጅ መገኛ ጋር የተቆራኘን ስፍራ ሙዚየም ገንብቶ፣ የቱሪስት መስህብ አልምቶና አካባቢውን በስፋት አስተዋውቆ የገቢ ምንጭ ማድረግ ሲቻል ለምን ተዘንግቶ ቆየ? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ይሆናል። የጊዜ ጉዳይ ሆኖ አሁን አፋር ሰመራ ላይ በሉሲ የተሰየመ የሀገር ታሪክና ቅርስ ማጣቀሻ፤ የአፋር ክልል ህዝብ ቱባ ባህሎች ማሳያ የሆነ ሙዚየም ለመገንባት ዝግጅት መደረጉ ትልቅ ትርጉም ይኖረዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው (ረዳት ፕሮፌሰር)፤ የሚገነባው ሙዚየም የሀገር ታሪክና ቅርስ የሚሰነድበት፣ የአፋር ክልል ህዝብ ቱባ ባህሎች ተጠብቀው የሚዘልቁበት፣ የሰው ልጅ አመጣጥና ዝግመተ ለውጥ የሚያሳይ ዐውደ ርዕይ የሚካሄድበት ይሆናል ብለዋል። እሳቸው እንዳሉት የሙዚየሙ ግንባታ በ18 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ለአገለግሎት የሚበቃ ይሆናል። የአፋር ክልል በመስኖ ቢያለሙበት፣ የጥጥ እና የቴምር ልማት ቢካሄድበት ተዝቆ የማያልቅ እምቅ አቅም ያለው መሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም በለውጡ ሰፊ የልማት እንቅስቃሴ እየተደረገ ሲሆን እምቅ የቱሪዝም ሃብቱንም በማልማትና በመጠበቅ የሃገር ሃብት የማድረግ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን የሉሲ ሙዚየም ግንባታ ሁነኛ ማሳያ ነው። የሳምንቱ ቅኝታችን እንደቀጠለ ሲሆን አሁን ደግሞ በቀጥታ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ አሶሳ ተገኝተናል። አሶሳ በሳምንቱ በሃይማኖት አባቶች ጸሎትና ዱአ ተባርካ ስለ ሰላምና አብሮነት የሚመከርባት ከተማ ሆና እንግዶቿን ተቀብላ አስተናግዳለች። የተለያዩ የኃይማኖት አባቶች፣ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ ምሁራንና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት 7ኛው ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ "ሰላምን ይበልጥ ለማስፋት እና ለማስረጽ የሃይማኖቶች ሚና" በሚል መሪ ሃሳብ በአሶሳ ከተማ ተካሂዷል። በመድረኩ አባቶች ስለ ሰላም እና አብሮነት እንትጋ ለትውልድ ግንባታም መስራት ግድ ይለናል በማለት አፅንኦት በመስጠት መክረዋል። የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ኃይማኖቶች ለሰላም እና ለህዝቦች አብሮነት ያላቸውን አስተምህሮ በመጠቀም ለዘላቂ ሰላም ግንባታ እና ሀገራዊ የልማት ስራዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊ መሆን አለባቸው ብለዋል። በኢትዮጵያ ሰላምን ለማጽናት እና የወንድማማችነት ድልድይን ለመገንባት እንስራ በማለትም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። ከአሶሳ ወደ ሀዋሳ ከአሶሳ ወደ ሀዋሳ ስንጓዝ የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ጥምረት (አግራ-AGRA) ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች የኤልቶ ገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን የሥራ እንቅስቃሴን መጎብኘታቸውን እናገኛለን። በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጥምረቱ የቦርድ ሊቀ መንበር ኃይለማርያም ደሳለኝ፤ አርሶ አደሮች ምርታማነትን በማሳደግ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የሚያደርጉት ጥረት ጥሩ ተስፋ የተሰነቀበት መሆኑን ተመልክተናል ብለዋል። የግብርና ልማትን የማዘመን፣ ምርታማነትን የማሳደግና የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ተግባር መሆኑንም አፅንኦት ሰጥተዋል። የጥምረቱ ፕሬዚዳንት አሊስ ሩህዌዛ፤ በአፍሪካ የግብርና ስርዓት ሽግግርን ለማጠናከር በተለይም አነስተኛ ማሳ ያላቸው አርሶ አደሮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማስቻል ስራ ውጤት እያመጣ ይገኛል ብለዋል። በአፍሪካ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ሂደት ውስጥ ደግሞ የኢትዮጵያ ለውጥ አስደናቂ ስለመሆኑ አንስተዋል። ሌሎች በዚህ ሳምንት በሁሉም ክልሎች ባደረግነው ምልክታ በተለይም የምርጫ ጉዳይ ዋነኛ አጀንዳ ሆኖ ዜጎች የምርጫ ካርዳቸውን እየወሰዱ ሲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎችም የምረጡኝ ቅስቃሳ ማድርጋቸውን ቀጥለዋል። የግብርና ልማት ስራዎች፣ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ዝግጅት እና ሌሎችም የልማት ሥራዎች በተጠናከረ መልኩ የቀጠሉበት ሳምንት ነበር ማለት ይቻላል።
የጤና ነገር …
Apr 17, 2026 360
በዮሐንስ ደርበው ማዲያት ታክሞ ይድናል? እነማንንስ ያጠቃል? የሥነ-ውበት ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ሱመያ ኑርሁሴን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ስለማዲያት መንስዔ፣ ምልክቶች እና ሕክምና ሙያዊ ሐሳባቸውን አጋርተዋል። እንደ ባለሙያ ቢደረግ ያሉትንም መክረዋል። • ማዲያት እነማንን ያጠቃል? ማዲያት ማንኛውንም ሰው እንደሚያጠቃ ያነሱት ዶ/ር ሱመያ፤ በብዛት ግን በሴቶች ላይ እንደሚከሰት ያስረዳሉ። በዚህም መሠረት ይላሉ፤ እርግዝና ላይ ያሉ እንዲሁም የወሊድ መከላከያ የሚወስዱ ሴቶች እና ሆርሞናል ቴራፒ ላይ ያሉ ሰዎች በስፋት ለማዲያት ተጋላጭ ናቸው። በተጨማሪም በብዛት ምግብ ማብሰል (ኪችን) ላይ የሚሠሩ ሰዎች ለማዲያት እንደሚጋለጡ ጠቁመዋል። ባብዛኛው ማዲያት የሚያጠቃው በዕድሜ ከ25 ወይም ከ30ዎቹ በላይ የሆኑትን መሆኑንም አንስተዋል። • መንስዔ እንደ ዶክተር ሱመያ ገለጻ፤ ለማዲያት ከሚያጋልጡ መንስዔዎች መካከል ዋነኛው የፀሐይ ጨረር ነው። በተጨማሪም ሆርሞናል ፋክተር (የወሊድ መከላከያ መጠቀም፣ እርግዝና ላይ መሆን፣ ሆርሞናል ቴራፒ መውሰድ) ለማዲያት አጋላጭ መንስዔ ሆነው ይጠቀሳሉ ይላሉ። ጭንቀት እንዲሁም ቆዳን የሚያስቆጡ ነገሮች ለማዲያት አጋላጭ መሆናቸውንም ነው ያብራሩት። • ምልክቶች ማዲያት ቀላ፣ ጠቆር ወይም ደብዘዝ ያለ ቀለም (መልክ) ይዞ ከትንሽ ጀምሮ የሚሰፋ መሆኑን ዶክተር ሱመያ አስገንዝበዋል። ለምሳሌ ይላሉ፤ ጉንጭ ላይ መውጣት ቢጀምር ወደ ሁለቱም ጉንጮች ከዚያም ወደ ግንባር እንዲሁም አገጭ እና አፍንጫ ሊደርስ እንደሚችል ገልጸዋል። በሂደትም የማቃጠል፣ የመቆጥቆጥ እና ማሳከክ ሁኔታ ሊኖረው እንደሚችል ነው ያነሱት። • ሕክምና መንስዔዎቹን ዐውቆ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ የሕክምናው አካል መሆኑን ያስገነዘቡት ዶክተር ሱመያ፤ የፀሐይ ጨረር መከላከያዎችን መጠቀም፣ በሕክምና የሚሰጡ መድኃኒቶችን ሳያቋርጡ በትዕግስት መጨረስ (ቶሎ ለውጥ አላየሁበትም ብሎ አለማቋረጥ) እንደሚገባም መክረዋል። የማዲያት ሕክምና ስኬታማነቱ ለሁሉም ሰው በዕኩል ጊዜ እንደማይታይ በመግለጽ፤ እንደተከሰተበት ጊዜ ከሰው ሰው እንደሚለያይ በአጽኦት ተናግረዋል። ለምሳሌ አሉ፤ ዓመታት ያለፉት ማዲያት እና 2 ወራት የሆኑት ሕክምና እኩል ቢጀመርም በተመሳሳይ ጊዜ ላይድኑ እንደሚችሉ አመላክተዋል። ስለዚህ የሌላኛው ድኖ የኔ አልዳነም በሚል ሕክምናን ማቋረጥ ስህተት መሆኑንም ነው ያስረዱት። በሌላ በኩል ማዲያትን አስቀድሞ መከላከል እንደሚቻል አረጋግጠው፤ ይህም የሚሆነው መንስዔዎቹን በማወቅ የማዲያት ተጋላጭ ባለመሆን ነው ብለዋል። ከተቻለ በየሥድስት ወሩ ወይም በየዓመቱ የቆዳ ጤና ምርመራ ማድረግ እና ያለበትን ደረጃ ማወቅም የሚከሰት ችግር ቢኖር እንኳ ሥር ሳይሰድድ በማከም ቶሎ እንዲድን ማድረግ ይቻላል ነው ያሉት።
ትንታኔዎች
ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና በዲጂታል ጤና ከሀገር በቀል ስኬት ወደ አህጉራዊ መሪነት
Apr 23, 2026 181
(በሙሴ መለሰ) ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዘርፍ እያከናወነች ያለችው ስራ ውጤታማ እንዲሆን ስትራቴጂካዊ የሆኑ ተቋማዊና የፖሊሲ መሰረቶች ተጥለዋል። የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መቋቋም ለሀገራዊ ችግሮች በቴክኖሎጂ የታገዘ መፍትሄ ለማግኘት ትልቅ አቅም የፈጠረ ሲሆን፣ ብሄራዊ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፖሊሲ ተቀርጾ መጽደቁ ደግሞ የዘርፉን ልማትና አጠቃቀም በተደራጀ መንገድ ለመምራት አስችሏል። እነዚህ እርምጃዎች ሀገሪቱ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 እና 2030 ስትራቴጂ ውስጥ ቴክኖሎጂውን እንደ ቁልፍ የለውጥ አቅጣጫ እንድትጠቀም በማድረግ ላይ ይገኛሉ። የቴክኖሎጂ ሽግግሩን ዘላቂ ለማድረግም በሰው ኃይል ልማት ላይ ትኩረት ተሰጥቷል። በአሁኑ ወቅት አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን በኮዲንግ፣ በዳታ ሳይንስ እና በክህሎት ለማሰልጠን የተጀመረው ግዙፍ ፕሮግራም የለውጡ አንቀሳቃሽ ኃይል እየሆነ ነው። ከዚህም ባለፈ፣ በአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነው የኤአይ ዩኒቨርሲቲ እንዲገነባ መታቀዱና በዚህ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባልነት ውስጥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስርዓት እንዲሳተፍ መወሰኑ፣ ሀገሪቱ ቴክኖሎጂውን ለውሳኔ ጥራትና ለምርምር በከፍተኛ ደረጃ እየተጠቀመችበት መሆኑን ያሳያል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ጽህፈት ቤቱ እንደገለጸው፣ ሹመቱ የተሰጠው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዘርፉ ላሳዩት አመራር እና ኢትዮጵያ በአህጉሩ የሰው ሰራሽ አስተውሎትንና የፈጠራ ሥራዎችን ለማስፋፋት እየተገበረች ላለው የላቀ ሚና እውቅና ለመስጠት ነው። በሹመት ደብዳቤው ላይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማስፋፋት ያደረጉት አመራር፣ AI ለአፍሪካ ሉዓላዊነት፣ ለውጤታማነት እና ለአሳታፊ እድገት ቁልፍ መሣሪያ ሆኖ እንዲያገለግል በማስቻል ረገድ ትልቅ እገዛ ማድረጉ ተመልክቷል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አክሎ እንደገለጸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልታዊ በሆነ መልኩ የቴክኖሎጂ ነጻነትን እና ዐቅምን ለመገንባት የሚያደርጉት ተከታታይ ቅስቀሳ፣ አህጉሩ በኃላፊነት እና በፍትሐዊነት በታጀበ የAI አጠቃቀም ረገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት የዲጂታል መሰረተ ልማትን ማስፋፋት፣ የኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት አገልግሎቶችን ሥራ ላይ ማዋል እና በፈጠራ ሥነ-ምህዳር ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ለሀገራዊ ለውጡ ጠንካራ መሰረት የጣሉ ተግባራት መሆናቸውን ጽህፈት ቤቱ በዝርዝር አስፍሯል። በተጨማሪም ራሱን የቻለ የAI ዩኒቨርሲቲ ለማቋቋም የተያዘው ሥራ ምርምርን፣ የክህሎት ልማትን እና አህጉራዊ ትብብርን ይበልጥ እንደሚያጠናክርም ተገልጿል። ይህ አህጉራዊ እውቅና በተለይ በጤናው ዘርፍ የታዩ ውጤቶችን ያካትታል። ኢትዮጵያ በኤአይ የታገዘ ዲጂታል ኤክስሬይን ለሳንባ ነቀርሳ ምርመራ ካዋሉ የአፍሪካ ሀገራት መካከል በቀዳሚነት ትጠቀሳለች። በተጨማሪም የ"HEP Assist" መተግበሪያን በሙከራ ደረጃ በማስጀመር፣ በገጠር የሚገኙ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ውስብስብ ምልክቶችን ሲያዩ ሙያዊ የሕክምና ውሳኔ እንዲሰጡ ድጋፍ እየተደረገ ነው። እነዚህ የዲጂታል ጤና ስራዎች በ7 ክልሎችና በ15 ወረዳዎች ተግባራዊ መደረግ መጀመራቸው፣ ቴክኖሎጂው በገጠርና በከተማ መካከል ያለውን የአገልግሎት ልዩነት ለማጥበብ ያለውን ፋይዳ ያሳያል። በአጠቃላይ፣ የኤአይ ቴክኖሎጂ በጤናው ዘርፍ ከሚሰጠው የጡት ካንሰር፣ የአንጎል እብጠትና የቆዳ በሽታዎች ምርመራ ባለፈ፣ በግብርና፣ በፋይናንስና በመንግስታዊ አገልግሎቶች ውስጥም በስፋት እየገባ ይገኛል። በ2030 በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ሆስፒታሎችን ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል አገልግሎት ለመቀየር የተቀመጠው ግብ፣ ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት የጀመረችውን የቴክኖሎጂ ነጻነትና የመሪነት ጉዞ ይበልጥ የሚያጠናክር ነው። በኢትዮጵያ እየተገነባ ያለው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሥርዓት በጤና፣ በግብርና እና በመንግስታዊ አገልግሎቶች ውስጥ ለውጥ እያመጣ ይገኛል። በጤናው ዘርፍ እንደ ካንሰር እና ሳንባ ነቀርሳ ያሉ በሽታዎችን ቀድሞ በመለየት የህክምና ጥራትን ሲያሻሽል፣ በግብርናው ደግሞ የሰብል ተባዮችንና የቡና በሽታዎችን በመለየት ምርታማነትን እያሳደገ ነው። ከዚህ ባለፈም ቴክኖሎጂው በመንግስት የአገልግሎት አሰጣጥ እና በፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ ሰፊ የመረጃ ትንታኔዎችን በፍጥነት በማከናወን፣ የሥራ ፍጥነትን እና የውሳኔ አሰጣጥ ጥራትን ወደ ላቀ ደረጃ እያሸጋገረ ይገኛል። የዘርፉ ፋይዳ ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም ባለፈ የሀገሪቱን የዲጂታል ሉዓላዊነት እና የሰው ኃይል አቅም በመገንባት ላይ ያተኩራል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶችን በኮዲንግ እና በዳታ ሳይንስ በማሰልጠን እንዲሁም የፈጠራ ማዕከላትን (Startups) በመገንባት፣ ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ በሌሎች ላይ ጥገኛ ከመሆን ወጥታ የራሷን የዲጂታል ኢኮኖሚ መሠረት እየጣለች ትገኛለች። ይህም በአህጉር ደረጃ ለሚደረጉ የቴክኖሎጂ ሽግግሮች እንደ አርአያ በመሆን፣ ቴክኖሎጂውን ለኢኮኖሚ እድገትና ለማህበራዊ ፍትሃዊነት የመጠቀም ጥቅል ፋይዳው የጎላ እንዲሆን አድርጎታል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመት ኢትዮጵያ በአፍሪካ የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ ያላትን የመሪነት ሚና ይበልጥ ያጎላል። በተጨማሪም ሹመቱ የኢትዮጵያ ተሞክሮ በአህጉር አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ማግኘቱንና አፍሪካ በኃላፊነትና በፍትሐዊነት በታጀበ የኤአይ አጠቃቀም ረገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም እንድትሆን የመሪነት ሚናዋን እንድትወጣም ያደርጋታል።
ኢትዮጵያ በአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ መንገድ
Apr 21, 2026 1437
(በዮሐንስ ደርበው) ታሪክ እንደሚነግረን፤ የአዕምሯዊ ንብረት ጥቅም ለመጀመሪያ ጊዜ ዕውቅና ያገኘው የኢንዱስትሪያዊ ንብረት ጥበቃን በሚመለከተው በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1883 በተፈረመው የፓሪስ ስምምነት እንዲሁም፤ በ1886 የተፈረመውን የሥነ-ጽሑፍና ሥነ-ጥበብ ሥራዎች ጥበቃን የተመለከተውን የበርን(ስዊዘርላንድ) ስምምነት ተከትሎ ነው። እነዚህ ስምምነቶችም በዓለም አዕምሯዊ ንብረት ድርጅት የሚተዳደሩ መሆናቸው ይታወቃል። ኢትዮጵያ የአዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣንን፤ በ2022 ዓ.ም ፈጠራንና ኢኖቬሽንን በማበረታታት የፈጠራ ሐሳቦችን ወደ ዕሴት በመለወጥ ሂደት ለሀገራዊ ብልጽግና ቁልፍ ሚና የሚጫወት በአፍሪካ ተምሳሌት የአዕምሯዊ ንብረት ተቋም ለማድረግ እየታተረች ነው። ለዚህ ርዕይ መሳካትም፤ ተቋሙ የአዕምሯዊ ንብረት ሥርዓት ለሀገራዊ ፈጠራ መጎልበት፣ የኢኖቬሽን፣ ቴክኖሊጂ ሽግግር እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ማደግ ጥቅም ላይ የሚውልበትን ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ሀገራዊ የመዋቅር ሽግግርን መደገፍ የሚል ተልዕኮ አንግቦ እየሠራ ይገኛል። የእስካሁኑ የንግድ ምልክት፣ ቅጅና ተዛማጅ መብቶች እና የፈጠራ ባለቤትነት (ፓተንት) ምዝገባ የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ወርቅነህ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ2015 ዓ.ም እስከ ያዝነው በጀት ዓመት ያለፉት ዘጠኝ ወራት ድረስ በንግድ ምልክት፣ በቅጅና ተዛማጅ መብቶች እና በፈጠራ ባለቤትነት (ፓተንት) 20 ሺህ 476 ምዝገባዎች መከናወናቸውን አስረድተዋል። በዚህም መሠረት ይላሉ፤ 14 ሺህ 729 የንግድ ምልክቶች፣ 5 ሺህ 254 የቅጅና ተዛማጅ መብቶች እንዲሁም 1 ሺህ 781 የፈጠራ ሥራ ባለቤትነት ምዝገባ በተቋማችን አማካኝነት ተከናውኗል። የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች ምንድን ናቸው? አዕምሯዊ ንብረት ማለት በሰው ልጅ አዕምሮ የሚፈጠሩ የፈጠራ ሥራዎችን የሚመለከት መሆኑን የገለፁት አቶ ብሩክ፤ እነዚህ የፈጠራ ሥራዎች እንደማንኛውም ቁሳዊ ሀብት በንብረትነት የሚታወቁበትን አግባብ የያዘው ሥርዓት ደግሞ የአዕምሯዊ ንብረት መብት እንደሚሰኝ ያስረዳሉ። በዚህ አግባብ፤ የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች እንደማንኛውም ቁሳዊ ንብረት ሁሉ የፈጠራ ሥራዎችን ለሚያመነጩ ባለመብቶች የሚሰጡ የባለቤትነት መብቶች መሆናቸውን እንረዳለን። ለዚህም እንደ ምክንያት የሚቀርበው እንደ አቶ ዳንኤል ገለጻ፤ ወጥ ሥራዎችን ለማመንጨት የፈጠራ ባለመብቶች ዕውቀታቸውን፣ ገንዘባቸውንና ጊዜያቸውን መስዋዕት በማድረግ ከብዙ ድካም በኋላ ያገኟቸው የፈጠራ ውጤቶች በመሆናቸው ነው። ለአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ማድረግ ለምን አስፈለገ? አንድም፤ የሰው ልጅ ቀጣይ ዕድገትና የኑሮ ደኅንነት ዋስትና መሠረት የሚያርፈው በቴክኖሎጂና ባሕል ዘርፎች በሚያሳርፋቸው ፈጠራዊ ብቃቶቹ በመሆኑ እንዲሁም የምርምርና የፈጠራ ሥራዎችን ለማካሄድ ተጨማሪ ሀብት የሚያስገኝ በመሆኑና ይህም የኢኖቬሽን ሥርዓቱን ስለሚያሳድግ ነው ይላሉ አቶ ብሩክ። እንዲሁም፤ የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃና ዘርፉን ለሕዝብ የማስተዋወቅ ተግባር ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገትን በማረጋገጥ የድርሻውን ስለሚወጣና የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት በአጠቃላይ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ በተሻለ ደረጃ ላይ እንዲቆም ስለሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም፤ ሀገራት ጠንካራ የአዕምሯዊ ንብረት ሥርዓት በፈጠሩ ቁጥር ዘርፉ ለኢኮኖሚ ዕድገት ቁልፍ የልማት መሣሪያ መሆኑን ይገነዘባሉ። ጠንካራና ፍትሐዊ የአዕምሯዊ ንብረት ሥርዓት በፈጠራ ባለቤቶችና በተጠቃሚው ሕዝብ ዘንድ ሚዛናዊ ነው ያሉት አቶ ብሩክ። በአጠቃላይ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ በመሆኑ ለአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ማድረግ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን በአጽነዖት አንስተዋል። ዜጎች በአዕምሯዊ ንብረት ሥርዓት እንዴት ተጠቃሚ ይሆናሉ? ባለብዙ ቢሊየን ዶላር የፊልምና ድምጽ ሪከርድስ አሳታሚዎችና ሶፍትዌር ኢንዱስትሪዎች ለብዙ ሚሊየኖች የመዝናኛ ሥራዎች የሚያበረክቱት የቅጅ መብት ጥበቃ በመኖሩ መሆኑን መገንዘብ እንደሚገባም አቶ ብሩክ ይናገራሉ። በሌላ በኩል ተጠቃሚዎች የሚፈልጓቸውን ምርቶችና አገልግሎቶችን መለየት የሚያስችላቸው ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ የንግድ ምልክቶች ጥበቃና የመብት ማስከበር ሥርዓቶች ባይኖሩ ኖሮ ተመሳስለው በሚቀርቡ ምርቶችና አገልግሎቶች መታለልና ሌሎችም ችግሮች ያጋጥማቸው እንደነበርም ጠቁመዋል። ስለዚህ ምርቶችን በመሸመት ሂደትም በምርቶችና አገልግሎቶች ላይ ያለምንም ግራ መጋባት ግብይቱን ማከናወን እንደሚያስችላቸው መገንዘብ ይቻላል። እንደ አቶ ብሩክ ገለጻ፤ ለፓተንት የፈጠራ ሥራዎች ጥበቃ በመደረጉ መሰጠት የሚገባቸው ማበረታቻዎች የማይሰጡ ከሆነ፤ የፈጠራ ባለሙያዎች ቀጣይ የምርምር ሥራዎችን ማሳደግና ማስፋት እንደማይችሉ ይገመታል። በቀጣይነት የሚገኙ የተሻሻሉ የፈጠራ ሥራዎች አለመኖራቸው ደግሞ፤ በምርቶች ተጠቃሚና አጠቃላይ የኑሮ መሻሻል ሂደት ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ተፅዕኖ ይኖረዋል። የአዕምሯዊ ንብረት ዓይነቶች እንዴት ይመደባሉ? የአዕምሯዊ ንብረት፤ የኢንዱስትሪያዊ ንብረት (Industrial Property) እና የቅጅና ተዛማጅ መብቶች (Copyright and Related Rights) በሚሉ ሁለት ዋና ዋና ክፍሎች እንደሚመደብ ያስረዳሉ። አክለውም፤ ኢንዱስትሪያዊ ንብረት በውስጡ፤ የፓተንት፣ የንግድ ምልክት፣ የኢንዱስትሪያዊ ንድፍ እና የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካቾች የተሰኙ አራት ክፍሎችን እንደሚይዝ ያብራራሉ። ፓተንት ምንድን ነው?፡- ፓተንት ማለት በአንድ ቴክኒካዊ ባሕርይ ባለው የፈጠራ ሥራ ላይ የሚኖር የፈጠራ ባለቤትነት ብቸኛ መብት መሆኑን አቶ ብሩክ አስረድተዋል። የፓተንት መብት በአንድ ምርት (ለምሳሌ ማሽን ወይም የአመራረት ሂደት (Process) ሊሰጥ የሚችል ሲሆን፤ ፈጠራውም ለአንድ ቴክኒካዊ ችግር መፍትሔ የሚያስገኝ መሆን ይኖርበታል ይላሉ። ከፈጠራ ሥራው አመንጪ ይሁንታ ውጭ ሥራውን ገበያ ላይ ማዋል፣ መጠቀም፣ ማሰራጨት፣ መሸጥ ወዘተ… እንደማይቻልም አክለዋል። ፓተንት ለባለ መብቱ የጥበቃ መብት የሚያስገኝ ሲሆን፤ የጥበቃው ዘመንም በአጠቃላይ እስከ 20 ዓመት ሊደርስ ይችላል። ፓተንት የሚያስገኛቸው ሕጋዊ (የጥበቃ) መብቶች፡- የፈጠራ ሥራውን መጠቀም የሚችሉና የማይችሉ ሰዎችን መወሰን፤ ሦስተኛ ወገኖች ሥራውን እንዲጠቀሙ የመፍቀድ ወይም የፈቃድ ውል ስምምነት የመስጠት እንዲሁም የፈጠራ ሥራውን የመሸጥ (ለአዲስ የፓተንት ባለመብት) የሚሉት ይገኙበታል ብለዋል ሥራ አስፈጻሚው። የፓተንት ሥራዎች ለምን ያስፈልጋሉ?፡- ይህን ሲያብራሩም፤ ፓተንት ለፈጠራ ባለመብቶች ዕውቅናንና ሽልማቶችን (ማበረታቻዎችን) የሚሰጥ በመሆኑ፣ ፈጠራዎቹ የኢኖቬሽን ሥራዎችን ስለሚያጠናክሩና በዚህም ቀጣይነት ያለው የሰው ልጅ ሕይወት መሻሻልን የሚያረጋግጥ በመሆኑ እና በሌሎችም በጎ አስተዋጽዖዎች ፓተንት በዕጅጉ አስፈላጊ ነው ብለዋል። የንግድ ምልክት ምንድን ነው?፡- የንግድ ምልክት ማለት አንድን ምርት ወይም አገልግሎት ከሌላው ምርትና አገልግሎት እንዲለይ ለማስቻል በንግድ ምልክት ባለቤቶች ለምርታቸውና አገልግሎታቸው መለያ እንዲሆን ጥቅም ላይ የሚውል ልዩ ምልክት መሆኑን ተናግረዋል። የንግድ ምልክት ሸማቹ ሕብረተሰብ የሚፈልገውን ምርትና አገልግሎት በቀላሉ ለይቶ እንዲገዛ ከማስቻሉም በላይ በሚገዛው ምርትና አገልግሎት ጥራት ላይ በመተማመን ፍላጎቱን እንዲያሟላ ያደርጋል። የንግድ ምልክት ለባለመብቱ ምን ጥቅም ያስገኛል?፡- ምርቶቹ (አገልግሎቶቹ) በተጠቃሚዎች እንዲለዩለት ወይም እንዲታወቁለት ያደርጋል፣ ክፍያን መሠረት አድርጎ ሦስተኛ ወገን እንዲጠቀምበት የመፍቀድ፣ የንግድ ምልክቶች በራሳቸው ዋጋ አላቸው (የአዕምሯዊ ንብረት ዋጋ ትመና (IP Valuation) ለምሳሌ በፈረንጆቹ በ2026 የመጀመሪያ ወራት አፕል (Apple) 600 ቢሊየን ዶላር፣ ማይክሮሶፍት (Microsoft) 565 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር፣ ጉግል (Google) 433 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ግምት እንደነበራቸው ተብራርቷል። በተጨማሪም፤ የንግድ ምልክት በሕግ በሚቀመጥ የጊዜ ገደብ መሠረት እየታደሠ ለዘላለም ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፤ የንግድ ምልክት ባለቤቱን በማስተዋወቅ ዕውቅናና የገንዘብ ትርፍን ያስገኛል፤ የንግድ ምልክት ተገቢ ያልሆኑ የንግድ ውድድሮችን በመግታት ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል (ተመሳስለው የሚሠሩና ለገበያ የሚቀርቡ ሥራዎችን (Counterfieited Products) ለመዋጋት ዓይነተኛ መሣሪያ ሆኖ ያገለግላል፤ የንግድ ምልክት ሰዎች ምርቶቻቸውንና አገልግሎቶቻቸውን ሚዛናዊ በሆነ አግባብ እንዲያቀርቡ በማድረግና በብሔራዊና ዓለም አቀፍ ደረጃ የተሳለጠ የንግድ ሥርዓት እንዲኖር ምቹ ሁኔታ በመፍጠር አስተዋጽዖው የላቀ ነው ብለዋል። ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ ምንድን ነው?፡- ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ በምርቶች ሥነ-ውበት (Esthetics) ላይ ተመስርቶ ቅርጽን፣ መስመሮችን ወይም ቀለምን በመጠቀም ለገበያ የሚቀርቡ ምርቶች የገዥዎችን (ሸማቾችን) ቀልብ ለመሳብ እንዲችሉ በምርቶች ላይ የሚገለጽ የንድፍ ጥበብ ዘርፍ ነው ያሉት አቶ ብሩክ፤ ኢንዱስትሪያዊ ንድፎች በኢንዱስትሪና ዕደ-ጥበብ ምርቶች ላይ ተዘጋጅተው ሊወጡና ለገበያ ሊቀርቡ ይችላሉ ይላሉ። ዘርፉ ከቴክኒካልና ሕክምና መሣሪያዎች አንስቶ እንደ ሠዓት፣ ጌጣጌጦችና ሌሎች የቅንጦት ምርቶች ዕቃዎችን ሊያካትት ይችላልም ብለዋል። የቤት ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሪክ መሣሪያዎችን፣ ተሽከርካሪዎችና የሕንጻ ንድፎችን እንዲሁም የጨርቃጨርቅ ንድፍ ውጤቶች በኢንዱስትሪያዊ ንድፍ ሥር የሚወድቁ ይሆናሉ ይላሉ። ኢንዱስትሪያዊ ንድፎች ጥበቃ የሚደረግላቸው አዲስ ወይም ወጥ ከሆኑ ብቻ መሆኑን ገልጸው፤ በዲዛይኑ ውስጥ ከሚገለጸው ምርት ጋር ተያያዥ የሆኑ የቴክኒክ ጉዳዮች ጥበቃ እንደማይደረግላቸው አስታውቀዋል። ለኢንዱስትሪያዊ ንድፍ ጥበቃ ማድረግ ለምን ያስፈልጋል?፡- በምርቶች ውበት ላይ የሚገለጽ በመሆኑ የተጠቃሚውን ዐይን ይስባል፣ የምርቶችን ዋጋ ይጨምራል፣ ፈጠራንና ውድድርን ያበረታታል፣ ለባለመብቱ ብቸኛ መብትን ያጎናጽፋል፣ በኢንዱስትሪዎች፣ ባሕላዊ ጥበብና በዕደ ጥበብ ዘርፍ ፈጠራ በማሻሻል ኢኮኖሚ እንዲያድግ ያደርጋል፣ የወጭ ንግድን (Export Trade) ያሳድጋል በማለት የኢንዱስትሪ ንድፍ ጥበቃ አስፈላጊነትን ያብራራሉ። የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካች ምንድን ነው?፡- የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካቾች በምርቶች ላይ የሚቀርቡ ምልክቶች ሆነው እነዚህ ምልክቶች አንድ የተወሰነ አካባቢን በምርቱ ምንጭነት የሚያመላክቱና ጥራትንና ዝናን ከቦታው ጋር አስተሳስረው የሚያንጸባርቁ መሆናቸውን አቶ ብሩክ ያስረዳሉ። በአብዛኛው የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካቾች ልዩ ምርቱ የሚገኝበትን የቦታ ስም (Specific Local Geographyical Factors – Climate, Soil) ይይዛሉ። ለምሳሌ፡- Roquefort for Cheese -France፣ የማረቆ በርበሬ፣ የሸኖ ቅቤ፣ የዓድኣ ጤፍ … የመሳሰሉት ምርቶች ተጠቃሾች ናቸው። የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካቾችን መጠበቅ ለምን ያስፈልጋል?፡- ተጠቃሚዎች ምርቶች የሚገኙበትን ሀገር ወይም አካባቢ በቀላሉ ለመለየት፣ ሕጋዊነት በሌላቸው ወገኖች የምርቱ መገኛ አካባቢ እና የምርቱ ዝና በተሳሳተ መልኩ ለሌላ ምርት መጠሪያ እንዳይውል ለመከላከል ይረዳል ይላሉ። የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ምንድን ናቸው?፡- የቅጅ መብት በሥነ-ጽሑፍ እና ሥነ-ጥበብ ዘርፍ ወጥ የፈጠራ ሥራዎችን ለሚያመነጩ ደራስያን፣ አርቲስቶች ወዘተ… የባለቤትነት መብት የሚሰጥ የሕግ ማዕቀፍ መሆኑንም ነው ሥራ አስፈጻሚው የሚያስረዱት። በአንጻሩ ተዛማጅ የቅጅ መብት ማለት ይላሉ አቶ ብሩክ፤ በወጥ የፈጠራ ሥራዎች ላይ ተመስርተው የሚሠሩ ተዛማጅ (Related) የፈጠራ ሥራዎችን ያካትታል። ለምሳሌ፡- ከዋኞቹ (ተዋንያን እና ዘፋኞች)፣ ድምጽ ሪከርዲንግስ፣ አሳታሚዎች (ኮምፓክት ዲስኮች)፣ የብሮድካስት ተቋማት፣ (ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን) የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ ሲሉ ዘርዝረዋል። የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ምን ዓይነት መብቶች ያስገኛሉ?፡- ባለመብቶች ሥራዎቻቸውን ለመጠቀም ወይም ሦስተኛ ወገኖች እንዲጠቀሙባቸው የመፍቀድ፣ ሥራዎች እንዲባዙ፣ ለሕዝብ እንዲዳረሱ፣ እንዲሠራጩ፣ እንዲተረጎሙ ወይም ወደሌላ ሥራ እንዲቀየሩ የመፍቀድ ወይም የመከልከል፣ የደራሲነት (የአመንጭነት) መብት ዕውቅና እንዲያገኙ፣ በብዕር ስም የመጠቀም መብት፣ ክብሩንና መልካም ስሙን የሚያጎድፍ የሥራ መዛባት እንዳይኖር የመጠበቅ ወይም የሥራው ወደሌላ መቀየር የሚያስከትለውን ጉዳት የመቃወም ወዘተ መብቶችን ያስገኛሉ ብለዋል። የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ ምን ጥቅሞች ያስገኛል?፡- የሰውን ልጅ የፈጠራና ኢኖቬሽን ጥረቶችን ያሳድጋል፣ ለፈጠራ አመንጭዎች መበረታታትን ይፈጥራል፣ የሕጋዊ ተፈጻሚነትን በማረጋገጥ አመንጭዎችና በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች መዋዕለ-ነዋይ እንዲያፈሱ የፈጠራ ሥራዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚኖራቸውን የሥርጭት ሽፋን ያሳድጋል ነው ያሉት አቶ ብሩክ። የፓሪስ ስምምነት አባል ኢትዮጵያ ግንቦት 7 ቀን 2017 ዓ.ም የፓሪስ ስምምነት አባል ሀገር ለመሆን ለዓለም አዕምሯዊ ንብረት ድርጅት (WIPO) ያስገባችው ጥያቄ ተቀባይነት በማግኘቱና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስምምነቱን ነሐሴ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በማጽደቁ ከዚሁ ዕለት ጀምሮ ለስምምነቱ ተገዢ ሆናለች። አቶ ብሩክ እንዳብራሩት፤ የፓሪስ ስምምነት በጥቅሉ የኢንዱስትሪያዊ ንብረቶችን ጥበቃ የሚመለከት ነው። የፓተንት፣ የንግድ ምልክት፣ ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ፣ የግልጋሎት ሞዴል (በአንዳንድ ሀገራት ሕግ ኢትዮጵያን ጨምሮ “የአነስተኛ ፈጠራ የባለቤትነት መብት” በመባል የተደነገገ)፣ የአገልግሎት ምልክት፣ የንግድ ስም (የኢንዱስትሪ ወይም የንግድ እንቅስቃሴ የሚካሄድባቸው ስያሜዎች)፣ ጂኦግራፊያዊ አመላካች እና ፍትሐዊ ያልሆነ ውድድርን መከላከል ያካተተ ነው። የስምምነቱ መሠረታዊ ድንጋጌዎች በሦስት ዋና ዋና መርሆዎች እንደሚከፈሉ ጠቁመው፤ እነሱም፡- የፓሪስ ስምምነት አባል ሀገር መሆን በሌሎች አባል ሀገራት ውስጥ እንደ ዜጋ የመስተናገድ መብት፣ የቀዳሚነት መብት የማግኘት፣ በቀላሉ ዓለም አቀፍ ጥበቃ የማግኘት አሠራር እና መሰል ጉልህ ጥቅሞችን የማግኘት ዕድል ይሰጣል ሲሉ ይገልጻሉ። በመሠረቱ የፓሪስ ስምምነት የአዕምሯዊ ንብረት መብት ጥበቃን በማቀላጠፍ አዳዲስ ግኝቶችንና ፈጠራዎችን እንዲሁም የንግድ ሥራዎች ድንበር ሳይገድባቸው የፓተንትና የንግድ ምልክት መብቶች በቀላሉ እንዲጠበቁ በማድረግ ፈጠራን፣ ንግድን እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን እውን ያደርጋል ብለዋል። የዘንድሮው የአዕምሯዊ ንብረት ቀን የፊታችን ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም “አዕምሯዊ ንብረትና ስፖርት፤ እንዘጋጅ፣ እንጀምር፣ እንፍጠር!” በሚል መሪ ሐሳብ ዓለም አቀፉ የአዕምሯዊ ንብረት ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል። በስፖርት ዓለም ውስጥ የሚከሰቱ ተወዳዳሪዎች የግልና የጋራ ፈጠራዎች፣ ንድፎች፣ ብራንዶችና የመልካም ዝና ታሪኮችን ለመጠበቅና ሀገራትን ጭምር ለማስተዋወቅ የአዕምሯዊ ንብረት መብት ጥበቃ ሥርዓት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ይታመናል። ምክንያቱም ስፖርት በባሕርይው በውድድር ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን፤ ከሀገራት ዝና፣ ከፋሽን ዲዛይን፣ ከመዝናኛ፣ ከሚዲያ ሥርጭት፣ ከጤናና ከዕለት ተዕለት መገልገያ ቁሶች ጋር የሚገናኝ በመሆኑ ነው።
ባሳለፍነው ሳምንት …
Apr 18, 2026 947
ከሚያዝያ 5 እስከ ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … • የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ መመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ኢትዮጵያ በንፋስ ኃይል አማካኝነት ጨለማን ለመግፈፍ፣ ዐቅምን በለየ የቅድመ ጥናት እና ልዩ ዕቅድ የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫን ዕውን አድርጋለች ብለዋል። ይህ ፕሮጀክት 100 ሜጋ ዋት ንጹህ የኃይል አቅርቦት በመጨመር ወደ ዘርፈ-ብዙ እና ቀጣይነት ባለው የኃይል መጻዒ ዕጣ ፈንታ ለመገንባት የምናደርገውን ጉዞ ያጠናክረዋል ሲሉም ገልጸዋል። ይህም አስተማማኝ የኃይል አቅርቦትን ለማረጋገጥና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ያለንን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ አብነት ነው ብለዋል በወቅቱ። በሁሉም ዘርፎች የምናስመዘግበው የኢትዮጵያ የዕድገት ጉዞ ተጠናክሮ እየቀጠለ ይበልጥም እየለማ ይሄዳል፤ ከምንጊዜውም በላይ ታላቅ የምንሆንበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ሲሉም አመላክተዋል። • ከኮፕ32 አስተናጋጅነት ጋር በተያያዘ ምክክር መደረጉ የኮፕ32 አስተናጋጇ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ኮሚቴ በማቋቋም ዝግጅቷን ቀደም ብላ መጀመሯን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታውቀዋል። ከብሔራዊ ኮሚቴው ጋር በነበረን ስብሰባ፤ በተለያዩ ዘርፎች የተከናወኑ ሥራዎችን በመገምገም ክፍተቶችን የመለየት እና ሁሉም ጥረቶቻችን ከሀገራዊ ርዕያችን ጋር የተጣጣሙ መሆናቸው ተዳሷል ሲሉ ገልጸዋል። ከግምገማ ባሻገር የቀጣይ አቅጣጫ መቀመጡን ጠቅሰው፤ ትኩረታችን ግልጽ ነው፤ በጠንካራ ትብብር፣ በተዋሃደ ታላቅ ርዕይ እና የጋራ ጽኑ ትጋት ተናበን ይህን ዓለም አቀፍ ሁነት በልኅቀት በማስተናገድ የሀገርን ታላቅነት ዳግም ማሳየት ነው ብለዋል። • የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማድረጋቸው ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ ለመጡት የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከዚያም በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት አቀባበል አድርገውላቸዋል። በነበራቸው የሁለትዮሽ ውይይትም፤ ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በቅኝ ያልተገዙ፣ ለአኅጉሩ ነፃነትና አንድነት ድምፅ በመሆን ከጋራ የጽናት ታሪክ የሚመነጭ ጥልቅና ዘመናትን የተሻገረ ግንኙነት አላቸው ያሉት ጠላይ ሚኒስትሩ፤ ዛሬም እንደ ሁሌው ኢትዮጵያ ከሰፊ ገበታዋ ያላትን ታላቅ ዐቅምና ዘላቂ ወዳጅነት አብረዋት ለሚጓዙ ሁሉ ለማካፈል ዝግጁ ናት ብለዋል። ጉብኝቱም በተለያዩ ዘርፎች ያለንን የቆየ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና ለማስፋት ወሳኝ ምዕራፍን ከፍቷል ሲሉ ገልጸዋል። ከሁለትዮሽ ስብሰባው በመቀጠልም በሁለቱ ሀገራት በኩል ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ለማሳካት ያለንን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጡ የመግባቢያ ስምምነቶች እንዲፈረሙ አድርገናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ስምምነቶቹ ኢትዮጵያ በፈጣን የለውጥ ጉዞ ያካበተችውን ልምድ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለማካፈል እንዲሁም ከአጋሮቻችን የተለያዩ ዕይታዎችን በመቅሰም ለአኅጉሩ ዕድገት ዘላቂና አፍሪካዊ መፍትሔዎችን በጋራ ለማፍለቅ እንደ ወሳኝ መሠረት ያገለግላሉ ነው ያሉት። • የፖርቹጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፖርቹጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓውሎ ራንገል ጋር ባሳለፍነው ሳምንት በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅትም፤ የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን እና ቀጣይ ትብብሮችን በምናጠናክርባቸው ቁልፍ መስኮች ላይ መክረናል ብለዋል። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከኢቢሲ ጋር ቆይታ ማድረጋቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “የሉዓላዊነት ልብ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ቆይታ አድርገዋል። በቆይታቸውም፤ ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ፣ የተሻገረ ኢኮኖሚ ለመፍጠር፣ በበቂ ሁኔታ ዜጎችን ሥራ ለማስያዝ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ሚና አይተኬ መሆኑን በአጽንኦት አንስተዋል። በዚሁ ወቅትም፤ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ሥራ ይፈጥራል፣ ኢኮኖሚ ያሸጋግራል፣ ወደሚቀጥለው ደረጃ ለመሻገር እንደ መስፈንጠሪያ ሆኖ ያገለግላል በማለት አብራርተዋል። በእነዚህ እና በሌሎች ምክንያቶች ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን የሉዓላዊነት አንዱ አንጓ ነው በማለት አስረድተዋል። የብዙ መንግሥታትና የእኛም ትኩረት ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ላይ የሆነበት ዋናው ምክንያት፤ ኢንዱስትሪ ማደግ ለሚያስብ ሀገር በጣም ወሳኝ ነገር ስለሆነ ነው ብለዋል። አክለውም፤ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የኢኮኖሚ ልብ መሆኑን አስገንዝበዋል። አንድ ሰው ልቡ ካልሠራ ሌላው አካላቱ ጤነኛ ቢሆንም ውጤታማ እንደማይሆን ሁሉ፤ ኢኮኖሚን ኢኮኖሚ የሚያደርገው የኢኮኖሚ ልብ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ነው ብለዋል። እንዲሁም የከተማ እና የከተሜነት እሳቤ ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ስኬት ያለውን ወሳኝ ሚና አንስተው፤ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሊከናወንና ሊሳካ የሚችለው በጥግግት የሚኖሩ ሰዎች ሲኖሩ መሆኑን አስገንዝበዋል። የሕዝብ ጥግግት ለልማት እጅግ ወሳኝ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ልማትንና ብልጽግናን የሚያስብ ማንኛውም መንግሥት ከተማን፣ ከተሜነትን፣ ግብር መክፈልንና አገልግሎት መስጠትን ማዕከሉ ካላደረገ ልማት ሊያመጣ እንደማይችል አብራርተዋል። ከተማ አያስፈልግኝም፤ የእኔ ትኩረት አርሶ አደር ብቻ ነው የሚል እሳቤ ካለ ልማትን ማሰብ እንደማይቻልም አመላክተዋል። • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በወሎ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባሳለፍነው ሳምንት በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ አሎማ ክላስተር በበጋ መስኖ የለማውን የደረሰ የስንዴ ማሳ በጎበኙበት ወቅት፤ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ሀገራችን በምግብ ራሷን ለመቻል የጀመረችው ጉዞ በተግባር ሥር እየሰደደ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል። የመደመር መንግሥት ለበጋ መስኖና ለስንዴ ምርታማነት የሰጠው ትኩረት የዜጎችን ሕይወት እየቀየረና የሀገርን የምግብ ሉዓላዊነት እያረጋገጠ ይገኛል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የተመለከትነው የስንዴ ልማትም የራዕያችንን ውጤት፣ የሐሳባችን መሬት መንካትና ፍሬ የማግኘታችን ተጨባጭ ማሳያ ነው በማለት ገልጸዋል። እንዲሁም በ "ገበታ ለትውልድ" መርሐ ግብር የተገነባውን የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ሥራ ማስጀመራቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ጸጋን የመለየት፣ የማልማትና ወደ ሀብት የመቀየር ማሳያ እና የወሎ የብልጽግና ተስፋ ነው ብለዋል። ይህ ፕሮጀክት ከግንባታው ጅማሮ እስከ ፍጻሜው የ"መደመር" ዕሳቤ በተግባር የታየበት፣ የመንግሥት ሐሳብ፣ የባለ ሀብቱ ታታሪነት እና የሕዝቡ ትጋት የተሰባጠረበት ድንቅ ውጤት ነው ሲሉም ገልጸል። ያየነው ልማት የሰላም ውጤት ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሐይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች ሰላማቸውን አጥብቀው እንዲጠብቁ አደራ በማለት፤ በአንድነት እና በትጋት ከሠራን ይህ ቀጣና የዕድገትና ብልጽግና መዳረሻ መሆኑ አይቀሬ ነው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። እንዲሁም የኢትዮጵያ የመሠረተ-ልማት እና ኮንስትራክሽን ሳምንትን የከፈቱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን፤ በዚሁ ወቅት መሠረተ-ልማት ለሀገር ዕድገት ወሳኝ ግብዓቶችን በማመላለስ የኢኮኖሚያችን የደም ሥር፣ የብልጽግናችን መሠረት ነው ብለዋል። በዐውደ ርዕዩ የተመለከትነውም ወሳኝ የልማት ተቋሞቻችን፣ መሠረተ-ልማትን እንደ ሀገር በቅንጅትና በትብብር የመምራት አዲስ የሥራ ባህል እየገነቡ መሆናቸው ነው ሲሉም ገልጸዋል። መንግሥት በመንገድ፣ በኃይል፣ በመስኖ፣ በባቡርና በዲጂታል መሠረተ-ልማት ዘርፍ ፈጣንና ፍትሐዊ ልማት ለማረጋገጥ የሚሠራውን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመላክተዋል። አሁን ያለንበት ወቅት የሥራ፣ የውጤት እና የተስፋ ዘመን ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ትናንት የተገነባው ለዛሬ፣ ዛሬ የምንገነባው ደግሞ ለነገው ትውልድ ኩራት እና የብልጽግና ዋስትና ነው ብለዋል። #ባሳለፍነው_ሳምንት #ኢዜአ #Ethiopian_News_Agency
የንፋስ ኃይል፤ የኢትዮጵያ የብርሃን አድማስ የአረንጓዴ ልማት ሌላኛው ብስራት!!
Apr 18, 2026 155
በቁምልኝ አያሌው የሰው ልጅ የታዳሽ ኃይል ምንጮችን መጠቀም የጀመረው በጥንታዊ ሥልጣኔዎች ዘመን እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። ለአብነትም፤ ግብፃውያን ከአምስት ሺህ ዓመታት በፊት ጀልባዎችን በባሕር ላይ ለመንዳት የንፋስ ኃይልን ይጠቀሙ ነበር። በሰባተኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ደግሞ ፋርስ (የአሁኗ ኢራን) የመጀመሪያውን በንፋስ ኃይል የሚሠራ የጥራጥሬ መፍጫ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ማዋል ጀመረች። ግሪኮችና ሮማውያን የውሃ መንኮራኩሮችን በመጠቀም እህል መፍጨት የሚያስችል ፈጠራን እንዳስጀመሩ የታዳሽ ኃይል የታሪክ ማኅደሮች ይጠቁማሉ። ጥንታዊያን ሕዝቦች የፀሐይ ኃይልን ለብርሃንና ለሙቀት ምንጭነት ከመጠቀም ባለፈ፣ የፀሐይ ጨረርን በማሰባሰብ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚጠቀሙባቸውን ጥበቦች ነበሯቸው። ምንም እንኳን የ19ኛው ክፍለ ዘመን የኢንዱስትሪ አብዮት በድንጋይ ከሰልና በተፈጥሮ ዘይት የበላይነት ቢያዝም፤ በዚሁ ወቅት ለታዳሽ ኃይል ቴክኖሎጂ ልማት መሠረት መጣሉን ታሪክ ያስትውሰናል። ለዚህም ማሳያ የሚሆነው እ.አ.አ በ1839 ፈረንሳዊ የፊዚክስ ሊቅ ኤድመንድ ቤኩረል፤ የፀሐይ ብርሃንን ወደ ኤሌክትሪክ መቀየር የሚቻልበትን የ'ፎቶቮልታይክ' (Photovoltaic effect) ክስተት ማገኘቱ ነው። በተጨማሪም እ.አ.አ በ1882 የመጀመሪያው በውሃ ኃይል የሚሰራ የኤሌክትሪክ ማመንጫ በአሜሪካ ሥራ ጀመረ። እ.አ.አ በ1883 ደግሞ በኦስትሪያ ቪየና በተካሄደው ዓለም አቀፍ የኤሌክትሪክ ኤግዚቢሽን፣ የንፋስ ኃይልን ወደ ኤሌክትሪክ የሚቀይሩ ተርባይኖችን ለመትከል የሚያስችሉ ወሳኝ የቴክኖሎጂ ዕድሎች ታይተዋል። በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ለታዳሽ ኃይል የሚሰጠው ትኩረት መቀዛቀዝ ቢያሳይም፣ በ1970ዎቹ የተከሰተው ዓለም አቀፍ የነዳጅ እጥረት ዓለም አማራጮችን እንድታማትር አስገድዷታል። በዚህም ምክንያት የነዳጅ ዋጋ መናር ሀገራት ከነዳጅ ጥገኝነት ለመውጣት ወደ ውሃ፣ ፀሐይና ንፋስ ኃይል ፊታቸውን እንዲያዞሩና በዘርፉ ለሚካሄድ ጥናትና ምርምር ከፍተኛ መነሳሳት እንዲፈጠር አድርጓል። የንፋስ ኃይል ታሪካዊ ዳራና የቴክኖሎጂ እድገት የንፋስ ኃይልን ወደ ኤሌክትሪክ የመቀየር ታሪክ እ.አ.አ በ1883 በኦስትሪያ ቪየና በተካሄደው ዓለም አቀፍ የኤሌክትሪክ ኤግዚቢሽን ላይ ፍሬድላንድ በተሰኙ ሳይንቲስት አማካኝነት የመጀመሪያው የንፋስ ኤሌክትሪክ ተርባይን ለእይታ መቅረቡ ይነገራል። ይህ የፈጠራ ሥራ በየጊዜው እየተሻሻለ መጥቷል። በ1887 ስኮትላንዳዊው የኮሌጅ ፕሮፌሰር ጄምስ ብሊዝ የቤታቸውን መብራት ለማብራት የተጠቀሙበት የንፋስ ተርባይን በዘርፉ ትልቅ እመርታ ተደርጎ ይወሰዳል። ፕሮፌሰሩ ቀስ በቀስ የፈጠራ ውጤታቸውን አሳድገዋል። የአካባቢው ማኅበረሰብም የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ እንዲሆን ያቸሉትን አድርገዋል። የንፋስ ኃይል ማመንጫ ግንባታ በበርካታ ሀገራት የተለያዩ ሙከራዎች መደረጉን ድርሳናት ሲፈተሹ የሚያሳዩት እውነት ነው። ሆኖም ዘርፉ ትኩረት አግኝቶ እንዲያድግ ያደረገው በ1973 በዓለም ላይ የተከሰተው የነዳጅ ቀውስ ነው። ይህ ክስተት ሀገራት ወደ አማራጭ ኃይል ምንጮች እንዲያተኩሩ ዕድል ፈጥሮላቸዋል። ይህን ተከትሎም አሜሪካ መጠነ ሰፊ የንፋስ ኃይል እርሻዎችን (Wind Farms) በመገንባት ግንባር ቀደም መሆን ችላለች። እ.አ.አ እስከ 2008 ድረስ ከዘርፉ የምታመነጨውን የኃይል መጠን ወደ 24.4 ጊጋ ዋት አሳድጋለች። የንፋስ ኃይል የማመንጨት ሂደት የንፋስን የተፈጥሮ እንቅስቃሴ በተርባይኖች አማካኝነት ወደ ሜካኒካዊ ኃይል፣ በመቀጠልም ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚቀይር ዘመናዊ የታዳሽ ኃይል ቴክኖሎጂ ነው። ሂደቱም የተርባይን ክንፎች በንፋስ ግፊት አማካኝነት በሚፈጥሩት ሽክርክሪት ጀኔሬተሩን በማንቀሳቀስ ኤሌክትሪክ እንዲመነጭ ያደርጋል። የዓለማችን ግዙፍ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎች የት ይገኛሉ? በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ከ350 ሺህ በላይ የንፋስ ተርባይኖች ተተክለው ኃይል እየሰጡ ይገኛል። ቻይና በንፋስ ኃይል ማመንጨት የዓለማችን ቀዳሚ ሀገር ስትሆን፤ አሜሪካ እና ጀርመን በቅደም ተከተል ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል። የቻይናው ጂኳን (Gansu) የንፋስ ኃይል ማመንጫም ከ20,000 ሜጋ ዋት በላይ የማመንጨት አቅም እንዲኖረው ታቅዶ እየተገነባ ያለ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው። የንፋስ ኃይል በኢትዮጵያ ዓለም ለታዳሽ ኃይል ልማት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል። ኢትዮጵያም በአፍሪካ የንፋስ ኃይል ልማት ቀዳሚ ተዋናይ የሚያደርጋትን ስራዎች እያከናወነች ነው። ሀገሪቷ በምስራቅ አፍሪካ ያላት ስትራቴጂካዊ መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ የታደለችውን የተፈጥሮ ፀጋ ወደ አማራጭ ኃይል ለመቀየር ሰፊ ዕድል ፈጥሮላታል። በንፋስ ኃይል ልማት የመጣው ከፍተኛ ለውጥም የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ፍላጎትን በመሙላት የብዝኅ ታዳሽ ኃይል አማራጭ ልማት እንዲጎለብት እያደረገ ይገኛል። የተፈጥሮ ስጦታና ያልተነካው የኢትዮጵያ እምቅ የንፋስ ኃይል ፀጋ ኢትዮጵያ ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አኳያ በንፋስ ኃይል አማራጭ እምቅ የመልማት ፀጋን ተችሯታል። በተለይም የታላቁ ስምጥ ሸለቆ፣ ሰሜናዊ ተራራማ ስፍራዎችና ምስራቃዊ ቆላማ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የንፋስ ፍጥነት ኃይልን ለማመንጨት ተስማሚ መልክዓ ምድሮች ናቸው። በዚህም ኢትዮጵያ እስከ አንድ ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ሜጋ ዋት የንፋስ ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላት ጥናቶች ያመለክታሉ። ይህ አሃዛዊ መረጃም ከአሁኑ ወቅት አጠቃላይ ኃይል የማመንጨት አቅም ጋር ሲነፃጸር ሰፊ የልማት ዕድል መኖሩን ያረጋግጣል። ከጅምር እስከ ዛሬ የስኬት ጉዞ ምዕራፍ የኢትዮጵያ የንፋስ ኃይል ልማት በ2001 ዓ.ም አሸጎዳ ፕሮጀክት ግንባታ ተጀምሯል። በአዳማ 1 እና 2 ስራውን በማስፋት አሁን ላይ እስከ አይሻ 1 እና አሰላ ፕሮጀክቶች ደርሷል። እነዚህ የአዳማ፣ የአሸጎዳ፣ የአይሻ እና የአሰላ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል አድማስ መስፋፋትን የሚያረጋግጡ ናቸው። ለሀገሪቷ አረንጓዴ ልማት ብስራት የሆኑ ታላላቅ ስራዎች ናቸው። አዳማ-1 እና ሁለት፡- በአጠቃላይ 204 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያላቸው የአዳማ የኤሌከትሪክ ማመንጫዎች የኢትዮጵያን የንፋስ ኃይል የማመንጨት አቅም በተግባር ያረጋገጡ ፋና ወጊዎች ናቸው። አሸጎዳ፡- በፈረንሳይ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ የተገነባ ሁለተኛው የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ነው። 120 ሜጋ ዋት የሚያመነጨው ይህ ጣቢያ በሰሜን ኢትዮጵያ ለሚገኙ ዜጎች ከሚሰጠው ብርሃን በተጨማሪ የኢንዱስትሪ አቅም ሆኗል። አይሻ-2፡- በቅርቡ ተመርቆ ወደ ስራ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ 80 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል። በኢትዮ-ጅቡቲ ድንበር አቅራቢያ መገናባቱም ቀጣናዊ የኃይል ትስስርን ለማጠናከር ጉልህ ፋይዳ አለው። አሰላ፡- በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የምትገኝ የኢትዮጵያ ብርቅየ አትሌቶች መፍለቂያ ስፍራ ናት። በስንዴና ገብስ የግብርና ምርታማነትም በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። ነፋሻማ የአየር ሁኔታዋም ለኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አቅም የሚሆን ፀጋን ተችሯታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚያዚያ 08 ቀን 2018 ዓ.ም 100 ሜጋ ዋት ማመንጨት የሚያስችለውን የአሰላ ንፋስ ኃይል መርቀዋል። በዚሁ ወቅትም አርሲ በስንዴና ገብስ ብቻ ሳይሆን በንፋስ ኃይልም የኢትዮጵያ ብልፅግና ማዕከል መሆኗን የአካባቢውን የብዝኅ ፀጋ አረጋግጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የአሰላ ንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትም ኢትዮጵያ ከዕዳና ኪሳራ ወጥታ ፕሮጀክቶችን በታቀደላቸው ጊዜ ማጠናቀቅና ማትረፍ መጀመሯን በተግባር ያሳየ ነው። ከዚህም በላይ በንፋስ እና በጂኦተርማል ኃይል ማመንጫዎች የኢነርጂ ማዕከል እየሆነ መምጣቷን ያረጋግጣል። "አርሲ በኃይል ዘርፍ ልክ እንደ ስንዴ እና ገብስ ተጨማሪ አቅም ያለው አካባቢ መሆኑን ማየት ችለናል" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በንግግራቸው። የአሰላ ንፋስ ኃይል ማመንጫ በ145 ሚሊዮን ዩሮ ወጪ የተገነባ መሆኑን በመጥቀስ፤ ፕሮጀክቱ በአዋጭነት ደረጃ ሲታይ እጅግ ስኬታማ ነው ብለዋል። ከዚህ ቀደም የሚወሰዱ ብድሮች ለትውልድ ዕዳ ትተው የሚያልፉ እንደነበሩ በማስታወስ፣ የአሁኑን ፕሮጀክት የተለየ የሚያደርገውን ነጥብ ሲያነሱ ይህ ፕሮጀክት ቢበዛ በሁለት ዓመት ሙሉ ወጪውን ሸፍኖ ትርፋማ ስለሚሆን ልጆቻችን ትርፍ ሀብት የሚያገኙ እንጂ ዕዳ የሚረከቡ አይሆኑም በማለት ነው የገለጹት። ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን ግማሹን በእርዳታ እንዲሁም ቀሪውን ከወለድ ነጻ በሆነ ብድር ላቀረበችው የዴንማርክ መንግሥት የላቀ ምስጋና አቅርበዋል። የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቱም ቢበዛ በሁለት ዓመት ሙሉ ወጪውን ሸፍኖ ትርፋማ ስለሚሆን ልጆቻችን ምንዳ እንጂ ዕዳ የሚረከቡ እንደማይሆን አስገንዝበዋል። በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ ኢተያ ላይ በደማቅ ሁኔታ የተመረቀው የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ልማት የጀመረችውን ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ሌላኛው ታሪካዊ አሻራ ነው። በመደመር መንግስት መፅሐፍ ገፅ 206 ላይ እንደተጠቀሰው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን ለማስፋፋት ባለፉት ዓመታት ሰፊ ኢንቨስትመንት ተካሂዷል። ለአምራች ኢንዱስትሪው የሚቀርበው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትም ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷል። የታላቁ ሕዳሴ የኃይል ማመንጫን ጨምሮ ሌሎች በጅምር ያሉና በሚገባ አገልግሎት እየሰጡ ያልነበሩ ማመንጫዎችን ወደ መስመር ለማስገባት ተችሏል። በዚህም ሀገራችን ለአምራች ኢንዱስትሪው የሚያስፈልጋትን የኃይል አቅርቦት በሚገባ መሸፈን ችለናል በማለት ተከትቧል። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች 504 ሜጋ ዋት ኃይል ብሔራዊ የኃይል ቋትን በመመገብ የኃይል አቅርቦት የጀርባ አጥንት ሆነዋል። በኢትዮጵያ የንፋስ ኃይል ልማት የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ቀደም ሲል የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች በመንግስት ብቸኛ ይዞታነት ብቻ ሲካናወኑ ቆይተዋል። በአሁኑ ወቅት ግን ይህን አሰራር የሚቀይር የፖሊሲ ማሻሻያ ተደርጓል። ባለሃብቶች በመንግስትና የግል አጋርነት (PPP) ማዕቀፍ የሚሳተፉበት ሰፊ ዕድል ለመፍጠር ተችሏል። ይህም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ከማበረታታቱም በላይ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማፋጠን ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የግሉን ዘርፍ በኃይል ልማት ላይ ለማሳተፍ የተወሰዱት የፖሊሲ እርምጃዎች አሁን ላይ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ ጀምረዋል። ለአብነትም፤ በሶማሌ ክልል በመንግስትና በግል አጋርነት የሚገነባው የአይሻ-1 እና 3 የንፋስ ኃይል ፕሮጀክት ከ300 ሜጋ ዋት በላይ ኃይል የማመንጨት አቅም አለው። የኢትዮጵያ የንፋስ ኃይል ልማት የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ከመሸፈን ባለፈ፣ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን የኃይል ትስስር በማጠናከር ለጋራ ዕድገት መፋጠን ጉልህ ፋይዳ አለው። ኢትዮጵያ አረንጓዴ ኢኮኖሚ በመገንባትና የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን በመቀነስ ረገድ የምትከተለው የልማት መንገድ ለሌሎች ሀገራትም ተምሳሌት የሚሆን ነው። የኢትዮጵያ የንፋስ ኃይል ከብርሃን ባሻገር የንፋስ ኃይል የኢትዮጵያን የኃይል አቅርቦት በማሟላት ለሁለንተናዊ የብልፅግና ጉዞ ስትራቴጂክ መሰረት እየጣለ ይገኛል። ለአብነትም በኢትዮጵያ የዕድገት ጉዞ እያበረከተ ያለውን ፋይዳ መጥቀስ ይቻላል። የኢነርጂ ዋስትና እና የኃይል ምንጭ ስብጥር፡- በኢትዮጵያ ከውሃ ኃይል የማመንጨት ተግባር ቀዳሚውን ድርሻ ይይዛል። ይህም በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በሚከሰት የድርቅ አደጋ የኃይል አቅርቦት ተጋላጭነት በማስፋት ተፅዕኖ ያሳድራል። የንፋስ ኃይልም የአቅርቦት ተጋላጭነትን ለመቀነስ ጉልህ ስትራቴጂክ ፋይዳ አለው። በበጋ ወራት የውሃ መጠን ሲቀንስ የንፋስ ኃይልን በመጠቀም ደግሞ የተፈጥሮ ሚዛንን የጠበቀ አስተማማኝ የኃይል ስብጥር ለመገንባት ጉልህ ፋይዳ ያበረክታል። የኢንዱስትሪ መፋጠንና የሥራ ዕድል፡- የኃይል አቅርቦት ለአስተማማኝ የኢንዱስትሪ ምርታማነት የጀርባ አጥንት ነው። የኢንዱስትሪው ዘርፍ ደግሞ ለሀገር ዕድገት ወሳኝ ሚና አለው። በተለይም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚገነቡ የንፋስ ኃይል ፕሮጀክቶች የዕውቀትና የምርታማነት ሽግግርን በማፋጠን ረገድ ፋይዳቸው የጎላ ነው። እነዚህ ፕሮጀክቶች በንፋስ ኃይል ማመንጫ ተርባይኖች ተከላና ጥገና ወቅት የዜጎችን የምህንድስና ክህሎት በማጎልበት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግሩን በተጨባጭ ያጠናክራሉ። ፋብሪካዎች አስተማማኝ ኃይል እንዲያገኙ በማድረግ የገቢ ምርቶችን የመተካትና የወጪ ንግድ አቅማቸውን በማሳደግ ለሀገር ኢኮኖሚ ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ። ቀጣናዊ ትስስርና የውጭ ምንዛሬ ግኝት፡- የኢትዮጵያን የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ማዕከልነት አቅም የሚያጎለብቱ ከአነስተኛ እስከ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል፤ በመገንባታ ሂደትም ናቸው። የንፋስ ኃይል ልማትም ቀጣናው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን እየደገፈ ይገኛል። ይህም የዕድገት ትስስርን በማፋጠን በየዓመቱ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ ገቢን ለማሳደግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያበረክታል። የአረንጓዴ አሻራና የአካባቢ ጥበቃ፡- የንፋስ ኃይል ከብክለት የፀዳ ንፁህ የኃይል ምንጭ ነው። ይህም ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማት የተቸራትን ዓለም አቀፍ ዕውቅና ለማፅናት በቀላሉ አይታይም። የአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ የፋይናንስ ገቢን በማሳደግም ተጨማሪ የታዳሽ ኃይል ልማትን ለማጠናከር ያስቻላል። የገጠሩን ማህበረሰብ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚነት በማስፋትም የአካባቢና የደን መራቆትን ለመቀነስ ያስቻል። የንፋስ ኃይል ልማት ለኢትዮጵያ ቅንጦት አይደለም፤ ይልቁንስ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ዕድገትን የማፋጠን የህልውና ጉዳይ ነው። ለዚህም የንፋስ ኃይል ፀጋዎችን በማልማት ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የንፁህ ኢኮኖሚ ግንባታ ፋና ወጊነት የሚያረጋግጥ የልማት አቅጣጫ ተተልሞ እየተሰራበት ነው። የኢትዮጵያ የንፋስ ኃይል ልማትም አዲስ ተስፋን የፈነጠቀ የብርሃን አድማስና የአረንጓዴ ልማት ሌላኛው ብስራት እየሆነ ይገኛል።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 3914
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2668
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 8456
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6946
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
ፋሲካ -አብሮነት የሚደምቅበት የደስታ በዓል
Apr 12, 2026 536
በኢትዮጵያ የፋሲካ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበር በዓል ነው። የትንሳኤ በዓል የሚከበረው ከ55 ቀናት የጾም ወቅት በኋላ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች እነዚህን ቀናት ፈጣሪያቸውን በጾምና ጸሎት ከመለመን ባለፈ ከሥጋ፣ ከወተትና መሰል የእንስሳት ተዋጽኦ ምግቦች ታቅበው ነው የሚያሳልፉት። የትንሣኤ በዓል ከመድረሱ በፊት ያለው አንድ ሳምንት "ሰሞነ ሕማማት" በመባል ይታወቃል። የእምነቱ ተከታዮች በሰሞነ ሕማማት ኢየሱስ ክርስቶስ ያሳለፈውን መከራና ስቃይ በማሰብ በቤተ ክርስቲያን በስግደት፣ በጸሎትና በጾም በተለየ ሁኔታ ያሳልፋሉ። ምእመናን በእለተ አርብ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች መዳን ብሎ በቀራኒዮ አደባባይ የከፈለውን መከራ፣ ግርፋትና ስቅላት በማሰብ በስግደት፣ በጸሎትና በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች ያሳልፋሉ። የትንሳኤ (የፋሲካ) በዓልም ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትል ድል አድርጎ መነሳቱን ተከትሎ የሚከበር ነው። ትንሳኤው ይቅርታ፣ ለሰው ለጆች መዳን የተከፈለ ፍቅርና መስዋዕትነት ጎልቶ የሚታይበት ነው። በመሆኑም ፋሲካ ሞትን ድል በመንሳት በትንሳኤ የምስራች የተበሰረበት ታላቅ በዓል ነው ማለት ይቻላል። ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን በትንሳኤ የለወጠበት ለሰው ልጅም ፍቅርን በቤዛነት ተክቶ ያሳየበት ዕለት ነው። ዕለቱ ትንሳኤ ብርሀን የታየበት በመሆኑ በትንሣኤ ዋዜማ ቅዳሜ ምሽት ምዕመናን ነጭ ልብስ ለብሰው ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ሌሊቱን በጸሎትና በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርአቶች ያሳልፋሉ። የሌሊቱ ቅዳሴና ስርአተ ፀሎት ከተጠናቀቀ በኋላ ምዕመናን ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ጾም ይፈታሉ። ከቅባት ምግቦች ለሁለት ወራት በመቆጠብ ያሳለፉበት ወቅት በመሆኑም በትንሳኤ ሌሊት ዶሮ በመብላት ጾማቸውን ይፈስካሉ። በበዓሉ ቀንም በነጭ የሀበሻ ልብስ ደምቀው ይታያሉ። በዓሉ ከሃይማኖታዊ ሥርአቱ ባለፈ የአብሮነት፣ የፍቅርንና የመተሳሰብ እሴት ያለው ነው። ዘመድ አዝማድ በመጠራራትና ከጎረቤት ጋር አብሮ በመብላትና በመጠጣት የሚያሳልፉት ነው። ቤት ያፈራውን በመቋደስ በዓሉን በአብሮነት በደስታ ያሳልፋሉ። የፋሲካ በዓል ማህበራዊ ትስስር የሚገለጥበትና አብሮነት የሚደምቅበት የደስታ በዓል ነው። በተለይ በፋሲካ በዓል ለዶሮ ወጥ ልዩ ትኩረት ይሰጣል። ፋሲካና ዶሮ ወጥ ጥብቅ የሆነ ባህላዊ ቁርኝት ያላቸው በመሆኑ አንዱ የበዓሉ ማድመቂያ ተደርጎ ይወሰዳል። ከዚህ በተጨማሪ የበሬ ቅርጫ፣ በግ፣ ፍየል፣ ዳቦና ጠላ እንደየ አቅም በማዘጋጀት ይከበራል። በአንዳንዶች ዘንድም ከገብስ ብቻ የሚዘጋጅ "ኬኔቶ" የተሰኘ (ከአልኮል ነፃ የሆነ መጠጥ) በማዘጋጀት በአማራጭነት ይቀርባል።
በኅብረትና ጽናት የሚቀረጽ ብርሃን፤ የኢትዮጵያ ትንሣኤ
Apr 12, 2026 1017
በኅብረትና ጽናት የሚቀረጽ ብርሃን፤ የኢትዮጵያ ትንሣኤ በቀበኔሳ ገቢሳ ትንሣኤ ለሰው ልጅ ተስፋን፣ ዘለዓለማዊ ሕይወትን እና ከኃጢአት ነፃ መውጣትን የሚያበስር ኃይማኖታዊ በዓል ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ በመነሳቱ የሰው ልጅ የዘለዓለም የሕይወት አክሊልን ተስፋ ያደረገበት፣ የእግዚአብሔር ፍቅር የተገለጠበት እንዲሁም የሰው ልጅ ከዘለዓለም ሞትና ከኃጢአት ባርነት ነፃ የወጣበት የድኅነት፣ የፍቅር፣ የጽናትና የተስፋ ብርሃን ብስራት ነው፡፡ የትንሣኤ በዓል ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ የመነሳቱ ታላቅ ምሥጢር የሚታሰብበት ብቻ አይደለም፤ ይልቁንስ የሰው ልጅ ከውርደት ወደ ክብር፣ ከኃጢያት ባርነት ወደ ድኅነት እንዲሁም ከጉስቁልና ወደ ብሩህ ተስፋ የተሸጋገረበት የድል አዋጅ ነው። በዕለቱም በሞት ላይ ሕይወት፣ በሐዘን ላይ ደስታ፣ በቂም ላይ ይቅርታ ተበስሮበታል። ከበዓላት ሁሉ የላቀ የነጻነት ተምሳሌት ነው ትንሣኤ። 👉የትንሣኤ ሕያው አስተምሮ በዕለት ተዕለት ሕይወት ትንሣኤ ሲከበር ከሥርዓተ አምልኮ ባለፈ፣ በዓሉ የሚሰጠውን ታላቅ አስተምሮ ማጤን ይገባል። ትንሣኤ በየቀኑ ካለንበት ድካምና ውድቀት በአዲስ መንፈስ የመነሳት አቅም ነው። በዓሉ የሚያስተምረንን የጽናት፣ የተስፋና የአብሮነት ዕሴት በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ መኖር ያስፈልጋል። ለዚህም የተቸገሩን መርዳት፣ የታመሙትን መጠየቅና የተጣሉትን ማስታረቅ የበዓሉን ትርጉም እውነተኛ ያደርገዋል። 👉የኢትዮጵያ ትንሣኤ፤ በፈተና የጸና ብርሃን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዓሉን በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት፤ "የዘንድሮውን የትንሣኤ በዓል የምናከብረው ሀገራችን ኢትዮጵያ በፈታኝ የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ ሆና እያለች ነው። መንገዳችን ረጅም፣ ጉዟችንም እሾህ የበዛበት ሊሆን ይችላል። ብርሃን እንዳናይ የሚጋርዱ፣ በጨለማ ወጥመድ ሊያሥሩን የሚሞክሩ መሰናክሎች ቢበዙም፣ እምነታችን ግን ከሕማማት በኋላ ትንሣኤ እንደሚመጣ ነው" ብለዋል፡፡ "ኢትዮጵያ ዛሬም ትንሳኤዋን እያየች ነው። መቃብሯ ተከፍቷል፤ ማኅተሙም ተሰብሯል። የትንሣኤውን ዜና ሊያደበዝዙ የሚሞክሩ የውሸት ወሬዎችና ተስፋ አስቆራጭ ትረካዎች የሀገራችንን የብርሃን ጉዞ ሊገቱት አይችሉም። ትንሳኤው እውነት ነው፤ ብርሃኑም የማይቀለበስ ሀቅ ሆኗል" ሲሉም አረጋግጠዋል፡፡ 👉ዴሞክራሲ እና ብሔራዊ ምክክር፤ የተስፋ ምዕራፎች የኢትዮጵያ ትንሣኤ አንዱ መገለጫ ዴሞክራሲን የመገንባት ጽናት ነው። ትንሣኤ ያለ ሕማማት እንደማይገኝ ሁሉ ዴሞክራሲ ያለ ፈተና በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ዴሞክራሲ የሚገነባው በጽናት እንጂ በፍርሃት አይደለም። ዴሞክራሲን እየገነባን በትዕግሥትና በቆራጥነት ወደ ተስፋዋ ምድር እንደርሳለን። አሁን ያለው የዓለም ነባራዊ ሁኔታ ጦርነት፣ የኢኮኖሚ ቀውስና ማህበራዊ አለመረጋጋት የትንሳኤን ትምህርት ከመቼውም ጊዜ በላይ አስፈላጊ ያደርገዋል፡፡ ችግሮችን በብቸኝነት የምንወጣበት ጊዜ አብቅቷል። ዛሬ እንደህዝብ የሚያስፈልገን ከ"እኔ" ወደ "እኛ" መሸጋገር፣ የግል ፍላጎትን ለጋራ ስኬት መስዋዕት ማድረግ ግድ የሚልበት ወቅት ላይ ነን። የአንድነት ጉዟችንን በማጠናከር ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ ጫናዎችን ለመቋቋም በጋራ መቆም ይገባናል። የተቸገሩትን በመርዳት፣ የታመሙትን በመጠየቅና የተጣሉትን በማስታረቅ የተግባር አብሮነትን በማሳየት የበዓሉን እውነተኛ ትርጉም መግለጥ ይገባል፡፡ 👉ምርጫ፤ ከኢትዮጵያን ትንሣኤ ማብሰሪያዎች አንዱ ምዕራፍ ትንሣኤ ሞት ድል የተነሳበትና ተስፋ የታደሰበት ዕለት ነው። እኛም በምርጫ ካርዳችን የሃሳብ ልዩነትን በዴሞክራሲያዊ አንድነት ድል በማድረግ የኢትዮጵያን የብልፅግና ትንሳኤ እናረጋግጣለን። በትንሣኤ በዓል የምንማረው ይቅርታና ጽናትም ለምርጫችን ስኬት አቅም ይሆናል። በኅብረት የምንሰጠው ድምፅም የነገዋን ብሩህ ኢትዮጵያ የመቅረጽ ኃይል በእጃችን መሆኑን ያሳያል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው "ምርጫ የኢትዮጵያን ትንሣኤ ማብሰሪያዎች አንዱ ምዕራፍ ነው። ትንሣኤን ያለ ሕማማት እንደማናስበው ሁሉ ዴሞክራሲንም ከውጣ ውረድ ነጥሎ ማየት አይቻልም። በዓለም ላይ በደልዳላ መንገድ ተጉዞ ዴሞክራሲን የገነባ ሀገር የለም። ዴሞክራሲና ብልፅግና ያለ ጽናት አይሳኩም። ከእኛ በፊት ዐመጻውን በትዕግሥት የመከቱ ተሻግረዋል፤ ሑካታውን በጽናት ያለፉ አሳክተዋል። ብንመኝም ፈተናውን አናስቀርም፤ መጽናት ግን እንችላለን። ከድኅነት መውጫው ብርታታችን፣ ወደ ዴሞክራሲ መድረሻችው ትዕግሥታችን እንደሆነ አምነን ለኢትዮጵያ ትንሣኤ በሙሉ ልባችን እንትጋ!!" ብለዋል። 👉የወደፊት እጣ ፈንታችን በእጃችን ከፊታችን የሚጠብቁን ሀገራዊ ምክክርና የ2018 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያን የወደፊት መጻኢ ዕድል የሚወስኑ ታላላቅ ሁነቶች ናቸው። እነዚህ ሂደቶች ስኬታማ የሚሆኑት እያንዳንዱ ዜጋ የድርሻውን ሲወጣ ብቻ ነው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር በልባችን ውስጥ ይቅርታና አብሮነት ሲነግስ ብቻ ግቡን ይመታል። ትንሣኤ ሞት ድል የተነሳበት እንደሆነው ሁሉ፣ በምክክሩም ጥልን፣ ጥርጣሬን፣ ያለመግባባት መንፈስን ድል መንሳት ይገባል፤ ቅንነት፣ ተስፋና መተሳሰብ ለምክክሩ ስኬት የመተማመኛ ቁልፎች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ 2018 ዓ.ም ደግሞ የዜጎች ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ ማሳያ አንጓ ነው፤ የዜጎች ነፃ ተሳትፎ መብታቸውን የሚያስከብሩበት ፍላጎታቸውን የሚያረጋግጡበት ማረጋገጫ ማህተም ጭምር፡፡ ዜጎች የመምረጥና የመመረጥ መብታቸውን የሚያስከብሩበት፤ የሌላውን ሃሳብ አክብረው የራሳቸውን የሚያስከብሩበት ለኢትዮጵያ ትንሣኤ በጋራ የሚቆሙበት መድረክ ነው፡፡ ትንሣኤ የድልና የነጻነት በዓል ነው። ይህንን ታላቅ ዕለት ስናከብር ያለፈውን ቁስል ሽረን፣ ለነገ ተስፋ ሰንቀን መሆን አለበት። እርስ በእርስ በመደጋገፍ፣ ችግሮችን በንግግር በመፍታት ለሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ስኬታማነት የድርሻችንን መወጣት ይገባናል። የተሻለችና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት በጋራ እንቁም! መልካም የትንሳኤ በዓል!!