በብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የተመራ የልዑካን ቡድን ከጅቡቲ አቻው ጋር ውጤታማ ውይይት አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
በብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የተመራ የልዑካን ቡድን ከጅቡቲ አቻው ጋር ውጤታማ ውይይት አደረገ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 10/2018(ኢዜአ)፦ ዛሬ ረፋድ ላይ ጅቡቲ የገባው በብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የተቋሙ ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ሲሳይ ቶላን ያካተተው የልዑካን ቡድን ከጅቡቲ አቻው ጋር የደኅንነት ትብብሮችን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውጤታማ ውይይት አደረገ።
ውይይቱ የሁለትዮሽ ግንኙነትን፣ ቀጣናዊ የደህንነት ትብብሮችን እና ተያያዥ ጉዳዮችን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።