ኢትዮጵያና አዘርባጃን በመከላከያ ኢንዱስትሪ ዘርፎች በጋራ ለመሥራት በሚያስችላቸው ጉዳይ ላይ መከሩ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያና አዘርባጃን በመከላከያ ኢንዱስትሪ ዘርፎች በጋራ ለመሥራት በሚያስችላቸው ጉዳይ ላይ መከሩ
አዲስ አበባ፤ሕዳር 11/2018(ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያና አዘርባጃን በመከላከያ ኢንዱስትሪ ዘርፎች በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የሁለትዮች የጋራ ውይይት አድርገዋል፡፡
የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ (ኢ/ር) እና በአዘርባጃን የመከላከያ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ቩጋር ሙስታፋይ የተመራ ልዑክ በሁለትዮሽ በትብብር በሚሠሩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
በውይይታቸው ላይም ፥ኢትዮጵያ የመከላከያ-ኢንዱስትሪ መሠረተ ልማቷን ለማጠናከር ትኩረት ሰጥታ እየሠራች መሆኑን ሚኒስትር አይሻ መሐመድ (ኢ/ር) አስረድተዋል።
ሁለቱ ሀገሮች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ኢትዮጵያ ቁርጠኛ ናት ማለታቸውን የመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ለኢዜአ የላከው መረጃ አመላክቷል።
ሚኒስትር ቩጋር ሙስታፋይ በበኩላቸው፣ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር ለማጠናከር በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል።
ሀገራቸው ኢትዮጵያን የመከላከያ ኢንዱስትሪ አጋሯ ለማድረግ ፍላጎት እንዳላትም ጠቁመዋል።