ቀጥታ፡

አዲስ አዳጊው ነጌሌ አርሲ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 11/2018 (ኢዜአ)፦  በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ነጌሌ አርሲ ከመመራት ተነስቶ አዳማ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አህመድ ሁሴን በ83ኛው ደቂቃ አዳማ ከተማን መሪ ማድረግ ችሎ ነበር።

ይሁንና ሮሆቦት ሰላሎ በ92ኛው እና ገብረመስቀል ዱባለ በ96ኛው ደቂቃ ያስቆጠሯቸው ግቦች ነጌሌ አርሲን ወሳኝ ሶሶት ነጥብ እንዲያገኝ አስችሎታል።


 

አዲስ አዳጊው ነጌሌ አርሲ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን በማስመዝገብ በስድስት ነጥብ ደረጃውን ወደ 11ኛ ከፍ አድርጓል።

በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዳማ ከተማ በበኩሉ በዘጠኝ ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።

ዛሬ አስቀድሞ በተደረገ የሰባተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ከመቀሌ 70 እንደርታ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም