ቀጥታ፡

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከአሜሪካ ባንክ ጋር የአምስት ዓመት የአጋርነት ስምምነት ተፈራረመ 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 11/2018(ኢዜአ)፦ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከአሜሪካ ባንክ ጋር የአምስት ዓመት የአጋርነት ስምምነት ተፈራረመ።

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 25ኛ ዓመት  የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ አትሌቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በኃይሌ ግራንድ ሆቴል ተከብሯል።

ከዚህም ባሻገር የአሜሪካ ባንክ  (Bank of America) ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር እ.ኤ.አ ከ2026 ጀምሮ ለአምስት ዓመት የሚያቆየውን የአጋርነት ስምምነት ተፈራርሟል።


 

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መስራች አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በዚህ ወቅት፤ ስምምነቱ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር ሳይሆን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የተደረገ መሆኑን ገልጿል።

የአሜሪካ ባንክ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ ተደራሽነት ለማስፋት ወደ ኢትዮጵያ ስለመጣ ምስጋና አቅርቧል።

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 25ኛ ዓመት ከአሜሪካ ባንክ ጋር አጋርነት የተፈራረምንበት ትልቁ የደስታዬ ቀን ነው ብሏል።

ስምምነቱ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን አቅም ለማሳደግ ትልቅ የመሰረት ድንጋይ መሆኑንም ገልጿል።


 

የአሜሪካ ባንክ ዓለም አቀፍ የገበያ ትብብር ኃላፊ ብራድ ሮዝ በበኩላቸው፤ የዓለም አሻራ  ከሆነው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር ለአምስት ዓመታት ስለምንሰራ ኩራት ይሰማናል ብለዋል።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አንድነትን የሚፈጥር፣ የኢኮኖሚ መነቃቃትን የሚያሳልጥ መሆኑንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም