ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
የኢትዮ-ጅቡቲ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሮጀክት የሎጂስቲክስ ወጪን በእጅጉ የሚቀንስ ነው
Sep 25, 2026 45
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ)፦ በጅቡቲ ዳመርጆግና በኢትዮጵያ ደወሌ መካከል የሚዘረጋው የ120 ኪሎ ሜትር የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሮጀክት የነዳጅ አቅርቦትን በማቀላጠፍ የሎጂስቲክስ ችግሮችን እንደሚያቃልል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አስታወቀ። ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) እና በዳንጎቴ ግሩፕ መካከል በተደረገ አጋርነት የሚተገበር ሲሆን፤ ከ1 ሚሊዮን ኩቢክ ሜትር በላይ የተጣራ የነዳጅ ምርቶችን የመያዝ እና የማስተላለፍ አቅም ይኖረዋል። ፕሮጀክቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑመር ጌሌ እና የዳንጎቴ ግሩፕ ፕሬዚዳንት አሊኮ ዳንጎቴ በተገኙበት ይፋ ተደርጓል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ለ‘ፐልስ ኦፍ አፍሪካ’ እንደገለጹት፤ አሁን ባለው አሰራር ነዳጅ በጅቡቲ ወደብ ከመርከብ ወርዶ ወደ ማከማቻ ከገባ በኋላ በቦቴዎች አማካኝነት 750 ኪሎ ሜትር ያህል ተጓጉዞ ወደ ኢትዮጵያ ይገባል። በኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር በቀን ከሚጓጓዙ 1000 የጭነት ተሽከርካሪዎች መካከል 35 በመቶ የሚሆኑት ነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች መሆናቸውንና ይህ አሰራርም ውጤታማ አለመሆኑን ገልጸው አዲሱ የቧንቧ መስመር የሎጂስቲክስ ወጪን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ አስረድተዋል። በተጨማሪም በጅቡቲ ወደብ የቦቴዎች ወይም የማከማቻ ተቋማት አለመዘጋጀት ምክንያት መርከቦች ለቀናት በመቆም የሚከፍሉትን ከፍተኛ የዲመሬጅ ወጪ የሚያስቀር መሆኑንም ጠቅሰዋል። በመሆኑም አዲሱ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ መርከቦች እንደደረሱ ነዳጁን በቀጥታ ወደ ማከማቻው እንዲያወርዱና በቧንቧ መስመር ወደ ኢትዮጵያ እንዲጓጓዝ ስለሚያደርግ የትራንስፖርት ቀናትን በከፍተኛ ሁኔታ ያሳጥራል። ፕሮጀክቱ ሁለት ዋና ዋና የገቢና የኢኮኖሚ ጥቅሞችን የሚያስገኝ ሲሆን፤ የመጀመሪያው ከቧንቧው እና ከነዳጅ ማከማቻው አገልግሎት የሚገኝ ቀጥታ ገቢ ነው። ሁለተኛው ደግሞ በኢኮኖሚው ውስጥ የናፍጣ፣ የቤንዚንና የሌሎች ነዳጅ ምርቶች የትራንስፖርት ወጪ በመቀነሱ ምክንያት የሚፈጠረው አጠቃላይ የአገልግሎት እና የንግድ ውድድር አቅም ማደግ መሆኑንም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የሀገሪቱን መንግሥት ፍላጎት በመወከል በፕሮጀክቱ ውስጥ ባለድርሻ ሆኖ እንደሚሳተፍ የተገለጸ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ የሀገሪቱን የሎጂስቲክስ አሰራር ከዘመናዊ የትራንስፖርት ሞዴል ጋር ለማጣጣም የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑም ተመላክቷል።
ሕወሓት - “ድመት መንኩሳ ……”
Sep 25, 2026 169
ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ /ሕወሓት/ በዘወትር መደበቂያው በደደቢት በረሃ ውስጥ ተጸንሶ የካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም ለኢትዮጵያ መከራ ይዞ ተወለደ።የመጀመሪያዎቹ የትግሉ እንቅስቃሴ መስራች ወጣቶች 11 ነበሩ። ሕወሓት በኢትዮጵያውያን ላይ የተጣባውን የጭቆና ቀንበር ለማስወገድ ተፀንሶ ገንጣይ አስገንጣይ ባንዳ ሆኖ ህልው ሆነ፤ ለዚህም ነው እነ አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) በጊዜ የተገለሉት፤ እነ ገሠሠ አሠፋ /ስሁል በሴራ የተገደሉት። በእርግጥ ድርጅቱ ሲመሰረት ተጋድሎ ሓርነት ሕዝቢ ትግራይ /ተሓሕት የሚል መጠሪያ ነበረው፤ በኋላ የስም እንጂ የግብር ለውጥ ሳያደርግ ወደ ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ /ሕወሓት/ ተቀየረ። ሕወሓት የኢትዮጵያውያን ጭቆና “ጥራኝ ጫካው” ያስባላቸው ድርጅቶችን በማታለልና በማጭበርበር ከጎኑ በማሰለፍ በ1983 ዓ.ም ወታደራዊውን የደርግ ስርዓት አስወግዶ መንበረ ስልጣኑን ተቆጣጠረ።ታላቋን ትግራይ ለመመስረት ዓላማ አንግቦት የተነሳው ጸረ ኢትዮጵያው ሕወሓት የሚጠላትን ሀገር የሚመራበት ዕድል ከዕጁ ሰተት ብሎ ገባለት። በ27 ዓመታት የአምባገነንነት የአገዛዝ ዘመኑ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ብቻ በሚያወጧቸው ሪፖርቶች መሰረት በሚመራው ህዝብ ላይ በርካታ ግፎችን የፈጸመ ድርጅት ሆኖ ተመዝግቧል። ሰብዓዊ መብት ጥሰት የዜጎች እስር በገፍ ሆነ። የፖለቲካና የዲሞክራሲ ምህዳሩን ክርችም አድርጎ በመዝጋቱ ህዝብ አንቅሮ ተፍቶት እያለ የ1997ቱን ምርጫ 99 ነጥብ 6 በመቶ አሸነፍኩ ብሎ የዓለም መሳለቂያነቱን፣ የአምባገነን ቁንጮነቱን፣ ጮሌ ማፍያነቱን በገሀድ አሳይቷል። የኢትዮጵያን ህዝብ በዘርና በሀይማኖት እየከፋፈለ እስር በርስ በማጋጨት ለዘመናት ተጋምደው በኖሩ ህዝቦች (በተለይም በአማራና ኦሮሞ ህዝቦች) ዘንድ ጥላቻና ቁርሾን እየዘራ ሀገር ጠልነቱን አስመስክሯል። በሜቴክና ኢፈርት በተባሉ ድርጅቶች የራሱን ወታደራዊ አዛዦችና አንጃዎች በማሰማራት የኢትዮጵያን መርከብ ሳይቀር የሚዘርፉ የማፍያ ቡድኖችና ግለሰቦችን ፈጥሯል። የመከላከያ ሠራዊት እና ሌሎች የጸጥታና ደህንነት ተቋማት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና የህዝቦቿን ደህንነት ከማስጠበቅ ይልቅ የወያኔ ፍላጎት ማስፈፀሚያ አንጃዎች ሆነዋል፤ ለ27 ዓመታት በህዝብ ላይ የፈጸመው ግፍ በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ በ2010 ዓ.ም ተወግዶ በምትኩ በሀገር በቀል የመደመር እሳቤ የሚመራ በህዝብ የተመረጠ መንግሥት መንበሩን ያዘ። ከለውጡ በኋላ “እኔ ያልመራኋት ኢትዮጵያ መኖር የለባትም” የሚለው እብሪተኛው ሕወሓት መቀሌ መሽጎ በስልጣን ላይ በነበረበት ዘመን ያደራጀውን የጥፋት ሴል በማሰማራት በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የእርስ በርስ ግጭት በመፍጠር የተጸነሰበትን የጥፋት ዓላማ አስቀጥሏል። ለዚህም ነው የትግራይ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገብሩ አስራት “ሕወሓት እኔ ብቻ አውቃለሁ፣ የሚል ተቸካይ ሀሳብ ያለው የቁሞ ቀር ግለሰቦች ስብሰብ ነው” የሚሉት። ዛሬም አብዮታዊ ዲሞክራሲ በተሰኘ “የእውር ድንበር” ፅንሰ ሀሳብ ላይ ተጣብቆ “እኔ ያልመራኋት ሀገር ትፍረስ” የሚል ግትር አቋም እንዳለው የገለጹትን በዋቢነት መጥቀስ ይቻላል። ሕወሓት ከምስረታው ጀምሮ አምባገነን መሆኑን በማንሳት፤ “በህዝብ ግፊት ከስልጣን ከተወገደ በኋላ አሸባሪነትን ጨምሮ የለየለት ማፍያ ሆኗል” ብለዋል።በፊት የአምባገነንነቱ ማስፈፀሚያ ህግና አሰራር እንደነበረው አስታውሰው፤በአሁኑ ወቅት ህዝብን በማናለብኝነት የሚያንገላታ የፖለቲካ ድርጅት እንኳን መሆን የተሳነው መርህ አልባ ስብስብ መሆኑን ያነሳሉ። ሕወሓት በትግራይ ሕዝብ ላይ የዘረጋውን ህገ ወጥ ሥርዓት በመጠቀም በዘረፋና ብዝበዛ ላይ ተሰማርቷል፤ ጥቂት ቡድኖች ብቻ ሀብት የሚያከማቹበት፣ ሕዝቡን ለከፋ ረሀብ፣ ስደትና ድህነት የሚዳርግ ሥርዓት ሆኗል ይላሉ። ይህ አልበቃው ብሎ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. የትግራይ እናቶችን ሰብል ሲሰበስቡ፤ የትግራይ ህፃናትን ትምህርት ቤት ሲገነቡ በዋሉ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ አባላት ላይ ጥቃት ፈጽሟል።የሀገር ክህደት አውራ የባንዳነት ቁንጮ መሆኑን ደጋግሞ አሳይቷል፤ ዛሬም ክህደት ቤት ሰርቶበታል። በትግራይ ክልል ህፃናት የብዕር መጨበጫ ጣቶቻቸው የክላሽ ምላጭ እንዲስቡ ተገደዋል፤ ወጣቶች ከትምህርት ገበታ ታፍሰው ራሳቸውን እቶን እሳት ከሚተፋ የጥይት ሀሩር ውስጥ ያገኙታል።ይህ የትግራይ ወጣቶች ዘወትራዊ ልምድ፤ በሕወሓት የተፃፈላቸው እጣ ፋንታ ሆኗል። የወንጀለኞች ቡድን የሆነው የሕወሓት አንጃ የትግራይን እናቶች ያለ ጧሪ አስቀርቷቸዋል። በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ወጣቶችን አስፈጅቶ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ምት ከእርሱ ላይ ሊያርፍበት ሲል ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የድረሱልኝ ጩኸት አሰማ። የወታደራዊ ሀይል መዛባትና የፖለቲካ ህልውነት አደጋ ሲያጋጥመው ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም የፕሪቶሪያን የሰላም ስምምነት ለምኖ ፈርሟል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት የቀድሞዋ አፈ ጉባኤና የስምረት ፓርቲ ምክር ቤት አባል ኬሪያ ኢብራሂም የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የትግራይ እናቶችና ወጣቶችን የመኖር ተስፋ ያለመለመ፤ ለነገ ህልም አለኝ፣ ሰላም ተፈጥሯል ጥያቄዎች በሰላም ይፈታሉ የሚል ተስፋ ያላቸው ወጣቶችን የፈጠረ፤ የጥይት ድምጽ የጠፋበት መልካም ዕድል ያበሰረ መሆኑን ያስታውሳሉ። የትግራይ ህዝብና የሕወሓት ፍላጎት የተለያዩ መሆኑን የሚገልጹት ኬሪያ ኢብራሂም፤ ስምምነቱን ሰላም እንደሚያመጣ በመረዳት የደገፈው ህዝቡ ቢሆንም የሕወሓት ቡድን ግን ለጊዜ መግዣ ካባ አድርጎት እንደነበር በመጥቀስ፤ “ስምምነቱን በግልጽ በመጣስ ጦርነት ህልውናው መሆኑን አሳይቷል” ብለዋል። ጦርነት ልብሱ የህዝብ ሲቃ ጉርሱ የሆነው የሕወሓት አንጃ ለምኖ የፈረመውን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ገና በጠዋቱ በመጣስ የጦርነት ነጋሪት መጎሰም ጀምሯል። የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ፤ የሕወሓት ቡድን አባላት ከስልጣን ውጭ መኖር እችላለሁ ብለው የማያምኑ፤ ከስልጣን የለቀቁ ዕለት ተጠያቂ የሚሆኑበትን ብዙ ወንጀል የሰሩ አሁንም እየሰሩ ያሉ የወንጀል ኢንተርፕራይዞች መሆናቸውን ይናገራሉ። የትግራይ ህዝብ የሰላም ስምምነቱን ደጋፊ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ጌታቸው፤ ”የፕሪቶሪያው የሰላም ሥምምነት የኮንትሮባንድ ጥቅሜን ያስቀርብኛል ብሎ ያሰበው ቡድን ግን ስምምነቱን በገሃድ ጥሶ ወንጀል ይፈጽማል” ብለዋል። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሕወሓት ድርብርብ ወንጀል እየፈጸመ መሆኑን ተረድቷል፤ ሊያወግዘውም እንደሚገባ አሳስበዋል። የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል ሰላም እንዲሰፍን ያሳየው ትዕግስት የሚደገፍ ነው፤ ዋናው የለውጡ ባለቤቶች የትግራይ ወጣቶችና ፖለቲከኞች በመሆናቸው ቡድኑን በጋራ መታገል አለባቸው ብለዋል። “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ” እንዲሉ በመቃብር አፋፍ ላይ ሆኖም ግብዓተ መሬቱ እስኪፈጸም የትግራይን ወጣት ለማስጨረስ ቆርጦ ተነስቷል። የትግራይ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገብሩ አስራት፤ ተስፋ በቆረጠ ሰዓት ያገኘውን የፕሪቶሪያ ሥምምነት እንኳን መተግበር ተስኖት በሥምምነቱ መሰረተ የተቋቋመውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በመፈንቀል ስልጣን የተቆጣጠረ የሥልጣን ጥመኛ ቡድን መሆኑን አንስተዋል። “ሰላም ከመጣ በትግራይ ወጣቶችና እናቶች ተጠያቂነት እንደሚኖር ስለሚያውቅ በጦርነትና በትርምስ ውስጥ ብቻ መኖርን መርሁ አድረጎታል” ብለዋል። የሕወሓት ታጣቂዎች ከባድና ቀላል መሣሪያዎችን ለሀገር መከላከያ ሠራዊት በማስረከብ ወደ ተሀድሶ ገብተው ማህበረሰቡን እንዲቀላቀሉ፤ ተፈናቃዮች እንዲመለሱ የገባውን ውል ለጦርነት አጀንዳው ማስፈጸሚያ ብሎ አንገራገረ፤ ይባስ ብሎ በፌዴራል መንግሥቱና በሕወሓት ሥምምነት የተመሰረተውን ጊዜያዊ አስተዳደር በሀይል በመፈንቀል መንበረ ስልጣኑን ተቆጣጥሮ የራሱን የዘረፋ አንጃ በትግራይ ክልል መንግሥትነት ሰይሟል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት የቀድሞዋ አፈ ጉባኤና የስምረት ፓርቲ ምክር ቤት አባል ኬሪያ ኢብራሂም ወጣቶችን አስገድዶ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማስገባት በዓለም አቀፍ ህግ ጭምር የተከለከለ ቢሆንም፤ ትምህርት ቤቶችን በመዝጋት ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋማትን ከፍተው የትግራይን ወጣትና ሀብት የገንዘብ ምንጫቸው አድርገውታል ብለዋል። በእርግጥም ወጣቶችን በግዳጅ መመልመያ አዋጅ በማውጣት የጭካኔያቸውን ጥግ ለዓለም አሳይተዋል። ለሕወሓት በትግራይ የሚኖር ትግራዋይ “ትግራዋይ” የሚሆነው የእነሱን አስተሳሰብ ከተቀበል ብቻ ነው።ስለሆነም ሁሉም ከትግራይ ህዝብ ጎን በመታገል ጥይት ሳይተኮስ ሰላም ማስፈንና የትግራይ ወጣቶችን ጥያቄ መመለስ እንደሚገባ አሳስበዋል። ትናንት ራሱ በለኮሰው እሳት የትግራይን ህዝብ ሲገድልና ሲዘርፍ ከነበረው ጸረ ኢትዮጵያ ሻዕቢያ ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን ለማፍረስ “ጽምዶ” የተባለ የጥፋት አደረጃጀት ፈጥሯል። የኢትዮጵያ ዕድገትና ሰላም ከወትሮም የማይዋጥላት ግብጽ የምትጋልበው ፈረስ ሆኗል። ሕወሓት የኢትዮጵያን አለመረጋጋት እንደ ቋሚ አጀንዳ አድርገው ከሚሰሩ የውጭ አካላት ጋር እየሰራ ነው።ትግራይን ወደ ኋላ ለመመለስ ትግራይ ውስጥ መሰረተ ልማት በማውደም በመዝረፍና ተቋማትን ሆነ ብሎ ካፈረሰው የኤርትራ መንግስት ጋር መተባበር ትልቅ ወንጀል እንደሆነ አስረድተዋል። “ሕወሓት የሰብዓዊ ጥሰትና የኮንትሮባንድ ህልውናውን የሚያስቀጥልለት ካገኘ የትም ሀገር ይሄዳል” ያሉት አቶ ጌታቸው፤ ከትግራይ ህዝብ ህልውና በላይ ለራሱ ህልውና ቅድሚያ የሚሰጥ ይሉንታ ቢስ ድርጅት መሆኑን ነው የተናገሩት። በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረው የትግራይ ህዝብ ይሄንን እኩይ ዓላማ ያነገበ የጥፋት ቡድን በቃህ ሊለው ይገባል።ለኢትየጵያ ዳር ድንበር መከበር ልጆቹን ሲገብር የኖረው የትግራይ ህዝብ ከአብራኩ በወጡ ባንዳዎች ሀገሩን አሳልፎ በመስጠት ከታሪካዊ ጠላቶቹ ጋር ሲዶልት ቆሞ ማየት የለበትም። አቶ ገብሩ አስራት “ሕወሓት እወክልሀለሁ” የሚለው የትግራይ ህዝብ ላይ ጭፍጨፋና ዘረፋ ከፈጸመው የሻዕቢያ ሀይል ጋር በማበር የትግራይ እናቶችን ለዳግም ሰቆቃ እያዘጋጀ ነው። ከውጭ ሀይሎችና ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በመተባበር የሚፈጽመውን የሀገር ክህደት ወንጀል የትግራይ ህዝብ በጋራ በቃህ ሊለው ይገባል ብለዋል። በትግራይ ክልል የወጣቶች የግዳጅ ምልምላ ህጋዊ ሆኖ በአዋጅ ወጥቷል። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጭምር ውጉዝ የሆኑ ወንጀሎችን በመፈጸም ጭካኔውን በግላጭ አሳይቷል።በትግራይ ክልል ወጣቶችን በግዳጅ ይመለምላሉ፤ ፈቃደኛ ያልሆኑት ይረሽናሉ። በዚህም አብዛኛው ወጣት የግዳጅ አፈሳውን በመፍራት ከክልሉ ወጥቶ እየተሰደደ ተፈናቃይ ሆኗል፤ በትግራይ ህዝብ ላይም የህልውና አደጋ ደቅነዋል። “ይህ ወንጀል ነው” ያሉት አቶ ጌታቸው፤ የትግራይ ህዝብ ልዕልና የሚረጋገጠው በሰላም ብቻ እንደሆነ ይናገራሉ።እነዚህን በህገ አራዊት የሚመሩ የሰው ህይወት እንደከንቱ የሚያዩ የጥፋት ቡድኖችን የትግራይ ወጣቶች በቃችሁ ሊሏቸው ይገባል ብለዋል። ወይዘሮ ኬሪያ እንደሚሉት፤ የሕወሓት ቡድን አጀንዳ አጥፊ መሆኑን በውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ ያለው ትግራዋይ ይገነዘባል። መንግስት ለሰላም ያሳየውን ቁርጠኝነት በማድነቅ፤ ቀጣይነት እንዲኖረው ጠይቀዋል። እኛ ለሰላም ቅድሚያ ስንሰጥ በትግራይ ህዝብ ጥቅም ላይ የምንደራደር ይመስላቸዋል፤ ከጦርነት ኪሳራ እንጂ ትርፍ የለም፤ ሰላም ደግሞ አክስሮ አያውቅም፤ የትግራይ ህዝብም ተገድደው ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ መታገል አለበት በማለት ነው አፅንኦት የሰጡት።
አዲስ መንግሥት፤ የጸናች ኢትዮጵያ
Sep 25, 2026 65
በፖለቲካ ሳይንስ ጽንሰ ሐሳብ፣ የአንድ መንግሥት ጥንካሬ የሚለካው በሕዝብ ዘንድ ባለው የፖለቲካ ቅቡልነት ነው። ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከቅቡልነት ጋር እጅጉን ይቆራኛል። በጠቅላላ ምርጫውም ከ54 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ተሳትፎ አድርጓል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ ባደረገው የምርጫ ውጤት ብልፅግና ፓርቲ አብላጫ ድምፅ በማግኘት ማሸነፉን ገልጿል። በድምፅ አሰጣጥ እለትም፤ በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች በነበረው ከፍተኛ የመራጮች ሰልፍና በአንዳንድ አካባቢዎች በነበረው የዝናብ ሁኔታ ምክንያት የድምፅ አሰጣጡ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ተራዝሞ የተካሄደበት በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክም አድስ ምዕራፍ የተፈጸመበት ነበር። ይህ መጠነ ሰፊ የሕዝብ ተሳትፎ መንግሥት ባለፉት ዓመታት ላከናወናቸው ሀገራዊ የልማት፣ የኢኮኖሚና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሥራዎች የሰጠው ትልቅ ዕውቅና ማሳያ ነው። ዜጎች በምርጫው አሉታዊ ጫናዎችን ሳይበግሯቸው መሳተፋቸው የሀገሪቱን የዴሞክራሲ ባህል ብስለት ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግሮታል። የምርጫ ሂደቱ ለሀገረ መንግሥት ግንባታ መጠናከር የሚጫወተው ሚናም ቁልፍ የሚባል ነው። ምርጫው 42 የፖለቲካ ፓርቲዎችና ከ10 ሺህ በላይ ዕጩዎች የተሳተፉበት በመሆኑ፣ የፖለቲካ ኃይሎች ጥያቄዎቻቸውን ከኃይልና ከግጭት ይልቅ በምርጫ ካርድ መፍታት እንደሚገባ የጋራ ስምምነት የፈጠሩበት ሲሆን ይህም ህጋዊ የሀገረ መንግሥት መዋቅርን ያጠናክራል። የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት ላይ ያበረከተው ቀዳሚው አስተዋጽኦ፣ የፖለቲካ ሥልጣን ይዞታን ሙሉ በሙሉ በሕግና በሕዝብ ፍላጎት ማዕቀፍ ውስጥ በማስገባት የመንግሥትን ህጋዊ ቅቡልነት ማሰደጉ ነው። ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተመዝግበው በነቂስ ወጥተው ድምፅ መስጠታቸው፣በዜጋውና በሀገረ መንግሥቱ መካከል ያለውን ማኅበራዊ ውል በከፍተኛ ደረጃ አጠናክሮታል። ይህ መጠነ ሰፊ ሕዝባዊ ተሳትፎ፣ የሥልጣን ፉክክር ከመሣሪያ ግጭትና ከትጥቅ እንቅስቃሴ ወጥቶ በሰላማዊ የምርጫ ካርድ ውድድር ላይ ብቻ እንዲመሠረት በማድረግ፣ መንግሥት ያለ አስገዳጅ ኃይል በህዝብ ፈቃደኝነት ላይ ብቻ እንዲመሠረት ትልቅ መሰረት የሚጥል ነው። ምርጫው መንግሥት ካገኘው የስራዎቹ እውቅና በተጨማሪ ህዝቡ ትልቅ አደራ የሰጠበትም ጭምር ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የምርጫ ውጤቱን ተከትሎ በሰጡት አስተያየት የተገኘው ድምፅ ፍጹም መዘናጋትን የሚፈጥር ሳይሆን ለመንግሥት የተሰጠ ታላቅ ህዝባዊ አደራ መሆኑን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳመለከቱት፣ ህዝቡ ጥይትና ማስፈራሪያዎችን ሳይበግሩት በነቂስ ወጥቶ ድምፅ የሰጠው፣ በመንግሥት የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን በላቀ ስኬት እንዲያስቀጥል፣ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ እና በተለይም ሥርዓታዊ ሌብነትንና ሙስናን በቁርጠኝነት እንዲያጠፋ ነው። ይህ መጠነ-ሰፊ የህዝብ ተሳትፎ ለአዲሱ መንግሥት የማይናወጥ ህጋዊ መሠረትና ከፍተኛ የፖለቲካ ቅቡልነት የሰጠ ሲሆን፣ ኢትዮጵያውያን ለሰላም፣ ለአካታችነትና ለዴሞክራሲያዊ ውድድር ያላቸውን የጸና አቋም ለዓለም ያስመከሩበት መሆኑንም ተናግረዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባወጣው መረጃ መሠረት፤ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም. ለሚከናወነው አዲስ የመንግሥት ምሥረታና የምክር ቤቶች መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል። የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማ መሆን የኢትዮጵያን ሀገረ መንግሥት ግንባታ ወደ አዲስና አስተማማኝ ምዕራፍ ያሸጋገረ ክስተት ነው። የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደትና መስከረም 25 ቀን የሚከናወነው አዲሱ የመንግሥት ምሥረታ በሀገሪቱ የፖለቲካ ባህል ውስጥ የተቋማዊ አቅምና የህግ የበላይነት መጎልበትን በተግባር ያሳዩ ናቸው። ቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የተጀመሩትን ስራዎች በተጨባጭ ወደ ላቀ ህዝባዊ ተጠቃሚነትና ብልጽግና የሚቀይርበት ዘመን ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
አልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ - የባለ ጥቁር ጋማ አንበሳ መገኛ
Sep 25, 2026 77
ጎብኚዎች ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ከሚነሳሱባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል ያሏት ጥንታዊና ድንቅ የታሪክ፣ የባህልና የተፈጥሮ ሀብት ስብስቦች እንደሆኑ ዋነኛዎቹ ናቸው። በዩኔስኮ የተመዘገቡ በርካታ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት መሆኗ ፣ የሰው ልጅ መገኛነቷን የሚያረጋግጡ ሳይንሳዊ ግኝቶች፣ እንዲሁም የአረቢካ ቡና የመጀመሪያ መገኛ መሆኗ እና ሌሎችንም መጥቀስ ይቻላል። “ታሪኳንና ቅርሶቿን ገልጦ ለተመለከተ መልክአ ምድሯን ለቃኘ በማህጸኗ ያቀፈቻቸውን እንስሳት ፣ አዕዋፍና ዕጽዋት ዓይኑን ገልጦ ላሰሰ ፣ የሕዝቦቿን ባህል ፣ ትውፊት ፍልስፍና በማስተዋል ለመረመረ ኢትዮጵያ የመስህቦች ማንጸሪያ የልዩነት አጽናፍ ማስረጃ ናት” …የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ገጽ 260 ቱሪዝምን ማሳደግ ሃገራችን ከዘርፉ ልታገኘው የሚገባትን ሰፊ ጥቅም ማረጋገጥ የመደመር መንግስት ትኩረት ካደረገባቸው አምስቱ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ነው። የበርካታ ቱሪስቶችን ቀልበ ከሚስቡትና በተፈጥሮ ፀጋዎች ከታደሉ ሥፍራዎች አንዱ የአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ በኢትዮጵያ በስነ-ምህዳር ልዩነቱና ለዱር እንስሳት ምቹ በሆነው የተፈጥሮ ሁኔታው የሚታወቅ ነው። ፓርኩ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ በ1998 ዓ.ም በይፋ በብሔራዊ ፓርክነት ተከልሎ ለጎብኚዎች ክፍት ተደርጓል። የፓርኩ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት 3 ሺህ 276 ካሬ ኪሎ ሜትር የሚያካልል ሲሆን፣ ከሱዳን ድንበር ጋር ይገናኛል። ፓርኩ ስሙን ያገኘው አካባቢውን አቋርጦ ከሚያልፈውና ለዱር እንስሳቱ ዋነኛ የውሃ ምንጭ ከሆነው "አልጣሽ" ከተባለው ወንዝ ነው። ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ 1 ሺህ 025 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ ፓርክ፣ ያልተነካ ተፈጥሮንና የዱር እንስሳት ህይወትን ለመመልከት ትልቅ እድልን የሚሰጥ ስፍራ ነው። የአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ መልክአ-ምድር በዋናነት ሜዳማና ዝቅተኛ ቦታዎችን ያካተተ ሲሆን ከፍታው ከባህር ጠለል በላይ ከ500 እስከ 900 ሜትር ይደርሳል። የአየር ጠባዩ ሞቃታማና ደረቅ ሲሆን፣ በዋናነት በሳቫና ሳር ምድር፣ በጥቅጥቅ የግራርና የቀርከሃ ደኖች የተሸፈነ ነው። በፓርኩ ውስጥ የሚያልፉት የአልጣሽና አዩባ ወንዞች በተለይም በደረቁ ወቅት ለዱር እንስሳቱ አስፈላጊውን ውሃ ያቀርባሉ። በተጨማሪም በዝናብ ወቅት የሚፈጠሩ ጊዜያዊ ረግረጎችና የውሃ አካላት ለተለያዩ አእዋፍና የውሃ ውስጥ ህይወት ፍጥረታት ምቹ የመኖሪያ ከባቢን ይፈጥራሉ። አልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ አልፎ አልፎ የሚታዩና የመጥፋት አደጋ የተደቀነባቸው የዱር እንስሳት መኖሪያም ነው። በፓርኩ ከሚገኙ አጥቢ እንስሳት መካከል አንበሳ፣ ነብር፣ ሳላ፣ አጋዘን፣ ሚዳቋ፣ ጦጣ፣ ዝንጀሮ፣ የዱር አህያና የዱር ውሾች ይጠቀሳሉ። በተለይም በአፍሪካ ብቸኛ የሆነው ባለ ጥቁር ጋማ አንበሳ የሚገኘውም በዚሁ ፓርክ ነው። እ.ኤ.አ. በ2016 የተደረገ ሳይንሳዊ ጥናት እንደጠቆመውም፣ በዛ ያሉ የአንበሳ መንጋዎች በዚህ ፓርክና በአጎራባቹ ይዞታ ውስጥ እንደሚኖሩም ተረጋግጧል። ከ200 በላይ የሚሆኑ የአገር ውስጥና ከሌሎች ዓለማት (ከአውሮፓና ኤስያ) የሚሰደዱ የአእዋፍ ዝርያዎች በፓርኩ ውስጥ ይገኛሉ። ይህም ፓርኩን ለወፍ አድናቂዎችና ተመልካቾች ተመራጭ ያደርገዋል። በፓርኩ ውስጥ የመድኃኒትነትና የኢኮኖሚ እሴት ያላቸው የተለያዩ የግራር ዝርያዎች፣ የቀርከሃ ጫካዎችና የዕጣን ዛፎች በስፋት ይበቅላሉ። የአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ ከሱዳኑ ዲንደር ብሔራዊ ፓርክ ጋር ተጎራባች የሚያደርገው ሰፊ የድንበር ግንኙነትም አለው። ሁለቱ ፓርኮች ተያያዥ በመሆናቸው በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል ድንበር ተሻጋሪ የተፈጥሮ ጥበቃ ቀጣና እንዲፈጠር ምክንያት ሆነዋል። ይህ ግንኙነት የዱር እንስሳቱ ያለ ምንም የወሰን ችግር በነጻነት እንዲንቀሳቀሱና የመራባት ወሰናቸውን እንዲያሰፉ ትልቅ ዕድልን ፈጥሮላቸዋል። በብሔራዊ ፓርኩ የወሰን ማካለል፣ የጥበቃ አቅምን የማጠናከር፣ የህገ-ወጥ አደን እና የሰደድ እሳት ስጋቶችን የመቀነስ ስራዎች ተሰርተዋል። የአካባቢው ማህበረሰብም ፓርኩን በባለቤትነት እንዲንከባከብና ተጠቃሚም እንዲሆን በንብ ማነብ፣ በእንሰሳት መኖ ልማት እና በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ እንዲሰማራ ለማድረግ የማህበረሰብ ተኮር ፕሮጀክቶች ተቀርፀዋል። ወደ ፓርኩ የሚያስገቡ የውስጥ ለውስጥ መንገድ መተላለፊያዎችን የማስተካከል፣ የመቆጣጠሪያ ኬላዎችን የመገንባት እና ወደፊት የስነ-ምህዳር ቱሪዝም መስህብ የሚሆኑ ቦታዎችን የመለየት ቅድመ-ዝግጅቶች እየተከናወኑ እንደሚገኙም መረጃዎች ያሳያሉ።
የሚታይ

የኢትዮ-ጅቡቲ ወዳጅነት፡ ከጉርብትና እስከ ስትራቴጂያዊ የኢኮኖሚ ትስስር
Sep 25, 2026 185
የኢትዮጵያና የጅቡቲ ሕዝቦች በታሪክ፣በቋንቋ፣ በባህልና በማኅበራዊ እሴቶች እጅግ የተሳሰሩና በደም የተቆራኙ ወንድማማቾች ናቸው።የሀገራቱ የትብብር ታሪክም ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ የተሻገረ ሆኖ ይገኛል። ኢትዮጵያ በዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ዘመነ መንግሥት የመጀመሪያውን ቆንስላ ጽሕፈት ቤት በጅቡቲ ከፍታለች።ለኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያው የውጭ አገር ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ ነበር። እ.አ.አ በ1897 የፈረንሳይ አስተዳደር ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በመስማማት ጅቡቲን ከአዲስ አበባ የሚያገናኘውን ታሪካዊ የባቡር መስመር ግንባታ አስጀምሯል።   ይህ መሠረተ ልማት የሁለቱን አገራት የንግድና የሕዝብ ትስስር ከመነሻው ያጠናከረ ዋነኛ ምሰሶ ነው። የኢትዮጵያና የጅቡቲ ሕዝቦች በታሪክ፣ በቋንቋ፣ በባህልና በማኅበራዊ እሴቶች እጅግ የተሳሰሩና በደም የተቆራኙ ወንድማማቾች ናቸው። ይህ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር የፖለቲካና የኢኮኖሚ ግንኙነቱ ጠንካራ መሠረት ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ በሀገራቱ መካከል ግዙፍ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች መገንባታቸው ትስስሩን ስትራቴጂካዊ መልክ እንዲይዝ አስችሏል። ይህንን ትስስር ይበልጥ ዘላቂ ለማድረግ ዘመናዊው የአዲስ አበባ-ጅቡቲ የኤሌክትሪክ ባቡር መስመር፣ የድንበር ማቋረጫ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች፣ የፍጥነት መንገዶች እና የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ተዘርግተዋል። ይህም አገራቱን በፖለቲካዊ ስምምነት ብቻ ሳይሆን በመሠረተ ልማት አስተሳስሯቸዋል። በአሁኑ ወቅት ደግሞ ትስስራቸው ይበልጥ እያደገ መጥቷል።በሁለቱ ሀገራት መሪዎች መካከል የሚደረጉ የጉብኝት ልውውጦችም ትስስሩን የማጠናከር ወሳኝ ሚና እየተወጣ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ ጊዜያት ወደ ጅቡቲ በማቅናት እንዲሁም የጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ዑመር ጊሌ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የሁለትዮሽና ቀጣናዊ ትስስሮችን የሚያጠናክሩ ውይይቶችን አድርገዋል። ኢትዮጵያ ቅድሚያ ለጎረቤት በሚሰጠው የመደመር መንግሥት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ አማካኝነት በቀጣናው በምታደርገው የልማት ትስስር የኢትዮ-ጅቡቲ ወዳጅነት በአብነት የሚነሳ ነው። የኢትዮ-ጅቡቲ ወዳጅነት በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ የተመሠረተ ሲሆን፤ በሀገራቱ መካከል የተመሠረተው የሕዝብ ለሕዝብ መድረክ እንደ ፍልሰት እና የአየር ንብረት ለውጥ ያሉ የጋራ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት ያስችላል። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ተሞክሮን በጅቡቲ ጭምር የማጋራትና የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሮች ተግባራዊ ማሳያ ናቸው። በዛሬው ዕለት ደግሞ ይህንን ጠንካራ ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ስትራቴጂካዊ ትስስር ተበስሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የጅቡቲ ፕሬዚዳንት እስማኤል ዑመር ጊሌ እና አፍሪካዊው ባለሀብት አሊኮ ዳንጎቴ በጋራ ዛሬ አዲሱን የትብብር ምዕራፍ አስጀምረዋል። ይህም በጅቡቲ ዳመርጆግን ከኢትዮጵያ ደወሌ የሚያገናኝ አዲስ የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት ነው። ፕሮጀክቱ በሁለቱም ጫፎች የሚገነቡ የማከማቻ ተርሚናሎችን የሚያካትት ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስና በዳንጎቴ ግሩፕ ጥምረት የሚተገበር ነው። ዋና ዓላማው የነዳጅ ማጓጓዣ ወጪንና መዘግየትን በመቀነስ፣ የኢነርጂ አቅርቦትን ማሻሻል እና የኢትዮ–ጅቡቲ የንግድ ኮሪደርን ይበልጥ ማቀላጠፍ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደገለጹትም፣ ፕሮጀክቱ የሎጂስቲክስ ወጪንና መዘግየትን በመቀነስ የኢነርጂ ዋስትናን ያጠናክራል፤ የኢትዮ–ጅቡቲ የንግድ መስመርንም ፍጥነትና ዘላቂነት ያሳድጋል። ነገር ግን ይህ መሠረተ ልማት ከነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር በላይ የሚታይ ትርጉም አለው።ከንግድና ከሎጂስቲክስ ባሻገር፣ በአፍሪካውያን ኢንቨስትመንትና በጋራ ልማት ላይ የተመሠረተ ቀጣናዊ ትስስርን የሚያጠናክር አዲስ የትብብር ደረጃ ነው። ይህም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚመራው የመደመር መንግሥት የሚከተለው የቅድሚያ ለጎረቤት የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ጅቡቲን ጨምሮ በቀጣናው የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያጎለብቱ አስተሳሳሪ ልማቶችን በመተግበር ቀጣናዊ ትስስርን ለማጠናከር የሚከተለውን አቅጣጫ ያሳያል። የኢትዮጵያ እና የጅቡቲ የመጻኢ ጊዜ የሁለትዮሽ ትብብር በሀገራቱ መካከል የተጀመሩትን ግዙፍ የምጣኔ ሀብት እና የመሠረተ ልማት ትስስሮች ይበልጥ ወደ ላቀ የተሟላ ቀጣናዊ ትስስር የሚሸጋገርበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። የሁለቱ አገራት መሪዎች እና ሕዝቦች ያላቸው ዘመን ተሻጋሪ ወዳጅነት፣ የጋራ ህልውና እና እምነት የወደፊት ወዳጅነታቸውን ይበልጥ አስተማማኝ እንደሚያደርገው ይታመናል።  
ተቋሙ የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎችንና ራሳቸውን የቻሉ ኢንተርፕሩነሮችን በማፍራት ረገድ የበኩሉን ሚና እየተወጣ ይገኛል
Sep 25, 2026 340
‎አዲስ አበባ፣መስከረም 15/2019 (ኢዜአ)፦የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎችንና ራሳቸውን የቻሉ ኢንተርፕሩነሮችን በማፍራት ረገድ የበኩሉን ሚና እየተወጣ መሆኑን ገለጸ። ተቋሙ የሥራ እንቅስቃሴዎቹን ለህብረተሰቡ ለማስተዋወቅ የሚያስችለውንና ለ15 ቀናት የሚቆየውን 'የመረጃ ሳምንት' በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።   ‎‎የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ሙሉጌታ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ በተቋሙ ውስጥ የተደራጁ ዎርክሾፖች፣ ላቦራቶሪዎች እና የመለማመጃ ቦታዎች መኖራቸው ለወጣቶች ትልቅ አቅም እና ዕድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል። ተቋሙ ወጣቶች ስራ ለመፍጠር የሚያስችላቸው ትልቅ ዕድል እንዳስገኘ ጠቅሰዋል። በዚህ መሰረት ተቋሙ ሀገሪቱን ሊለውጡ የሚችሉ ቴክኖሎጂ ፈጣሪዎችንና ራሳቸውን የቻሉ ኢንተርፕሩነሮችን በማፍራት ረገድ የበኩሉን ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በ2019 ዓ.ም የሚቀበላቸውን ተማሪዎች ውጤታማ ትምህርት ለመስጠት በቂ ዝግጅት ማድረጉንም ተናግረዋል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ የዘመኑን ፍላጎት የዋጁ ወደ 11 የሚጠጉ አዳዲስ ፕሮግራሞች መጀመራቸውን አስታውቀዋል። ከእነዚህ መካከል የሰው ሰራሽ አስተውሎት(ኤአይ) ስልጠና ፕሮግራም አንዱ ሲሆን፣ በዚሁ መርሀ ግብር ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያሰለጠነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።   የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ጸዳለ ተክሉ በበኩላቸው፣ ኢንስቲትዩቱ ለትምህርት ጥራት የሰጠው ትኩረት ተጨባጭ ውጤቶችን እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል። ተቋሙ የ ISO 9001:2015 እውቅናን በዋናው ካምፓስ ማረጋገጥ መቻሉን አስረድተዋል። ‎
የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ መስመሩ ፓን-አፍሪካዊ ፕሮጀክት ነው - የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ
Sep 24, 2026 420
አዲስ አበባ፤ መስከረም 14/2019 (ኢዜአ):- የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ የቱቦ መስመር የአፍሪካውያን የትብብር መንፈስ የገለጠ ፓን-አፍሪካዊ ፕሮጀክት መሆኑን የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ ገለጹ። በጅቡቲ ዳመርጆግን ከኢትዮጵያ ደወሌ የሚያገናኝ እና ታላቅ ስትራቴጂካዊ ኢንቨስትመንት የሆነውን አዲስ የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ መስመር ዝርጋታ ዛሬ ይፋ ሆኗል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፕሮጀክቱ መሠረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓት ላይ ታድመዋል። የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መገኘት በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መካከል ያለውን ጥልቅ እምነት እና የጋራ ጽኑ አቋም የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ኢንቨስትመንት የአፍሪካ መንግሥታትና የግሉ ዘርፍ ሲተባበሩ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ መሆን እንደምትችል የሚያሳይ ፓን-አፍሪካዊ ፕሮጀክት መሆኑን አመልክተዋል። ፕሮጀክቱ ከ375 ሺህ ኪዩቢክ ሜትር በላይ የሚሆን የነዳጅ ማከማቻ ተርሚናል እንደሚኖረው እና በዓመት 5 ሚሊዮን ቶን ምርቶችን በማስተናገድ የትራፊክ ማነቆዎችን እንደሚፈታ ተናግረዋል። አፍሪካ ጥሬ ዕቃዎችን እየላከች የተጣራ ነዳጅ በውድ ዋጋ የመግዛት አዙሪት እና ጥገኝነት አሁን ሊጠናቀቅ እንደሚገባና እውነተኛ ነፃነት የሚገኘው በኢነርጂ ራስን በመቻል መሆኑን ነው የገለጹት። እርስ በእርስ ያልተሳሰሩ መሰረተ ልማቶች ድንበር ተሻጋሪ አይደሉም ያሉት ፕሬዝዳንቱ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና የደነገገውን ህጋዊ ማዕቀፍ በተጨባጭ መሠረተ ልማት መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ እምቅ አቅም እና የጅቡቲ ወደቦች ሲቀናጅ የላቀ ስኬት ማስመዝገብ እንደሚቻል አመልክተዋል። ፕሮጀክቱ በአፍሪካዊ የካፒታል ወጪ የተገነባ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ቴክኖሎጂውንና እውቀቱን ይዘው የሚሠሩት አፍሪካዊ መሐንዲሶችና ወጣቶች መሆናቸው ትልቅ እምርታ መሆኑን ነው የተናገሩት። ጅቡቲ መሠረተ ልማቶቿን በማዘመን፣ የኢኮኖሚ አማራጮቿን በማስፋት እና ለቀጣናዊ መረጋጋት አስተማማኝ አጋር ሆና እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል። ፕሬዝዳንቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ለአሊኮ ዳንጎቴ፣ ለጅቡቲ ወደቦች እና ነፃ የንግድ ቀጣናዎች ባለሥልጣን እንዲሁም ለፕሮጀክቱ ድጋፍ ላደረጉ ሌሎች አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
አዲስ የሚመሰረተው መንግሥት ሜጋ ፕሮጀክቶችንና የልማት ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል ይጠበቅበታል
Sep 25, 2026 160
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦ አዲስ የሚመሰረተው መንግሥት የዜጎችን ተጠቃሚነት ይበልጥ የሚያረጋግጡ ሜጋ ፕሮጀክቶች አጠናክሮ መቀጠል እንደሚጠበቅበት የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አሕመድ ሁሴን ገለጹ። የአዲሱ መንግሥት ምሥረታና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ሥነ ሥርዓት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም እንደሚካሄድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ50 ሚሊዮን በላይ መራጮች ድምጻቸውን በመስጠት ለሀገር ይጠቅማል ያሉትን የፖለቲካ ፓርቲ በመምረጥ ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ያላቸውን ጽኑ መሻት በተግባር አሳይተዋል። ምርጫው በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ ያደረገው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በገለጸው ውጤት መሰረት ህዝቡ ይበጀኛል ይጠቅመኛል በማለት አብላጫ ድምጽ የሰጠው ብልፅግና ፓርቲ መንግስት መመስረት የሚያስችለውን ይሁንታ ማግኘቱን ማሳወቁም ይታወቃል፡፡ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትንና የክልሎች ምክር ቤቶችን መቀመጫ እንዲያገኙ ድምጽ ሰጥቷቸዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን የረጅም ዘመን የሀገረ መንግሥት ግንባታ ልምድ ያላቸው፣ ለሰላም፣ ለፍትህና ርትዕ ቀናኢ እይታ ያላቸው ህዝቦች መሆናቸውንም አስመስክረዋል። የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አሕመድ ሁሴን ለኢዜአ እንዳሉት፤ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ ዴሞክራሲያዊ መብቱን በነጻነት በመጠቀም ለሀገር ይጠቅማል ብሎ ያመነበትን ፓርቲ የመረጠበት ነው። መንግሥት መመስረት የሚያስችለውን ድምጽ ያገኘው ፓርቲ በርካታ ሀገራዊ ኃላፊነቶችን የሚቀበልበት፣ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ለህዝቡ ይጠቅማል ብሎ ለገባው ቃል ተግባራዊነት የሚተጋበት ጊዜ መሆኑንም ገልጸዋል። አዲስ የሚመሰረተው መንግሥት የዜጎችን የመልማትና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ጠንካራና ሉዓላዊነቷ የተጠበቀች ሀገር የመገንባት ኃላፊነት እንዳለበት አንስተዋል። መንግሥት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር የጀመራቸውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች አጠናክሮ እንዲቀጥል ይጠበቃል ብለዋል። የማዳበሪያ ፋብሪካ፣ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቤቶች ልማትና ሌሎችንም ሜጋ ፕሮጀክቶች ለማሳካት የተጀመረውን ሪፎርም አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተናግረዋል። አዲስ መንግሥት በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት እንደሚጠበቅበት ገልፀው፤ ሰላም የአንድ ሀገር የልማትና የዕድገት መሠረት መሆኑንም አስረድተዋል። በሀገራዊ ምክክር ጉባዔው የተመከረባቸው ሀገራዊ ጉዳዮችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ውይይትና ንግግር ባህል ሆኖ እንዲቀጥል የመሪነት ሚናውን መወጣት እንዳለበትም ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም በማስፈንና ልማትን በማረጋገጥ ረገድ ከሚመሰረተው መንግሥት ብዙ እንደሚጠበቅ ገልጸው፤ ህዝቡ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ሌሎችም ተቋማት የሰላም አጋርነት ሚናቸውን መወጣት አለባቸው ብለዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ የሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ላልተወሰነ ጊዜ ተከለከለ
Sep 25, 2026 256
አዲስ አበባ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ከዛሬ ከመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ባለ ሁለት እግር ሞተር ብስክሌት በአዲስ አበባ ማሽከርከር መከልከሉን አስታውቋል። አንዳንድ ወንጀል ፈጻሚዎች ሞተር ብስክሌትን በመጠቀም የቅሚያ እና የስርቆት ወንጀል ሲፈጽሙ ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝም የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ገልጿል። ወንጀል ፈጻሚዎች ከቦታ ቦታ ለመዘዋወር እና የተሰረቁ እቃዎችን ለማጓጓዝ ሞተር ብስክሌትን በብዛት እንደሚጠቀሙም አመልክቷል፡፡ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የትራፊክ ደንቡን እንደማያከብሩም ገልጿል። በተለይም ቀይ መብራትን መጣስ፣ ሌሎች ተሽከርካሪዎችን በመግጨት ማምለጥ፣ ሄልሜት ሳያደርጉ ማሽከርከር፣ የተፋፋቀ እና ለእይታ አስቸጋሪ የሆኑ የሠሌዳ ቁጥሮችን መጠቀም በአሽከርካሪዎቹ በስፋት የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶች መሆናቸውን ፖሊስ ገልጿል። ወንጀልን ለመከላከል እና በሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የሚፈጸምን የደንብ ጥሰት ለመቆጣጠር ከዛሬ ከመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ከኮድ 4 እና ከፖሊስ ሞተር ብስክሌት ውጭ ባለ ሁለት እግር ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር መከልከሉ ተገልጿል፡፡ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች እና ባለ ንብረቶች አስፈላጊውን እንዲፈጽሙ ያሳሰበው ፖሊስ ይሄንን በሚተላለፉት ላይ ሕጋዊ ርምጃ እንደሚወስድም አስታውቋል፡
የኢትዮ-ጅቡቲ ወዳጅነት፡የመደመር መንግሥት የጎረቤት ተኮር ዲፕሎማሲ ህያው አብነት
Sep 24, 2026 491
የኢትዮጵያና የጅቡቲ ሕዝቦች በታሪክ፣በቋንቋ፣ በባህልና በማኅበራዊ እሴቶች እጅግ የተሳሰሩና በደም የተቆራኙ ወንድማማቾች ናቸው።የሀገራቱ የትብብር ታሪክም ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ የተሻገረ ሆኖ ይገኛል። ኢትዮጵያ በዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ዘመነ መንግሥት የመጀመሪያውን ቆንስላ ጽሕፈት ቤት በጅቡቲ ከፍታለች።ለኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያው የውጭ አገር ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ ነበር። እ.አ.አ በ1897 የፈረንሳይ አስተዳደር ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በመስማማት ጅቡቲን ከአዲስ አበባ የሚያገናኘውን ታሪካዊ የባቡር መስመር ግንባታ አስጀምሯል። ይህ መሠረተ ልማት የሁለቱን አገራት የንግድና የሕዝብ ትስስር ከመነሻው ያጠናከረ ዋነኛ ምሰሶ ነው። የኢትዮጵያና የጅቡቲ ሕዝቦች በታሪክ፣ በቋንቋ፣ በባህልና በማኅበራዊ እሴቶች እጅግ የተሳሰሩና በደም የተቆራኙ ወንድማማቾች ናቸው። ይህ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር የፖለቲካና የኢኮኖሚ ግንኙነቱ ጠንካራ መሠረት ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ በሀገራቱ መካከል ግዙፍ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች መገንባታቸው ትስስሩን ስትራቴጂካዊ መልክ እንዲይዝ አስችሏል። ይህንን ትስስር ይበልጥ ዘላቂ ለማድረግ ዘመናዊው የአዲስ አበባ-ጅቡቲ የኤሌክትሪክ ባቡር መስመር፣ የድንበር ማቋረጫ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች፣ የፍጥነት መንገዶች እና የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ተዘርግተዋል። ይህም አገራቱን በፖለቲካዊ ስምምነት ብቻ ሳይሆን በመሠረተ ልማት አስተሳስሯቸዋል። በአሁኑ ወቅት ደግሞ ትስስራቸው ይበልጥ እያደገ መጥቷል። በሁለቱ ሀገራት መሪዎች መካከል የሚደረጉ የጉብኝት ልውውጦችም ትስስሩን የማጠናከር ወሳኝ ሚና እየተወጣ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ ጊዜያት ወደ ጅቡቲ በማቅናት እንዲሁም የጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ዑመር ጊሌ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የሁለትዮሽና ቀጣናዊ ትስስሮችን የሚያጠናክሩ ውይይቶችን አድርገዋል። ኢትዮጵያ ቅድሚያ ለጎረቤት በሚሰጠው የመደመር መንግሥት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ አማካኝነት በቀጣናው በምታደርገው የልማት ትስስር የኢትዮ-ጅቡቲ ወዳጅነት በአብነት የሚነሳ ነው። የኢትዮ-ጅቡቲ ወዳጅነት በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ የተመሠረተ ሲሆን፤ በሀገራቱ መካከል የተመሠረተው የሕዝብ ለሕዝብ መድረክ እንደ ፍልሰት እና የአየር ንብረት ለውጥ ያሉ የጋራ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት ያስችላል። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ተሞክሮን በጅቡቲ ጭምር የማጋራትና የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሮች ተግባራዊ ማሳያ ናቸው። በዛሬው ዕለት ደግሞ ይህንን ጠንካራ ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ስትራቴጂካዊ ትስስር ተበስሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የጅቡቲ ፕሬዚዳንት እስማኤል ዑመር ጊሌ እና አፍሪካዊው ባለሀብት አሊኮ ዳንጎቴ በጋራ ዛሬ አዲሱን የትብብር ምዕራፍ አስጀምረዋል። ይህም በጅቡቲ ዳመርጆግን ከኢትዮጵያ ደወሌ የሚያገናኝ አዲስ የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት ነው። ፕሮጀክቱ በሁለቱም ጫፎች የሚገነቡ የማከማቻ ተርሚናሎችን የሚያካትት ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስና በዳንጎቴ ግሩፕ ጥምረት የሚተገበር ነው። ዋና ዓላማው የነዳጅ ማጓጓዣ ወጪንና መዘግየትን በመቀነስ፣ የኢነርጂ አቅርቦትን ማሻሻል እና የኢትዮ–ጅቡቲ የንግድ ኮሪደርን ይበልጥ ማቀላጠፍ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደገለጹትም፣ ፕሮጀክቱ የሎጂስቲክስ ወጪንና መዘግየትን በመቀነስ የኢነርጂ ዋስትናን ያጠናክራል፤ የኢትዮ–ጅቡቲ የንግድ መስመርንም ፍጥነትና ዘላቂነት ያሳድጋል። ነገር ግን ይህ መሠረተ ልማት ከነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር በላይ የሚታይ ትርጉም አለው። ከንግድና ከሎጂስቲክስ ባሻገር፣ በአፍሪካውያን ኢንቨስትመንትና በጋራ ልማት ላይ የተመሠረተ ቀጣናዊ ትስስርን የሚያጠናክር አዲስ የትብብር ደረጃ ነው። ይህም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚመራው የመደመር መንግሥት የሚከተለው የቅድሚያ ለጎረቤት የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ጅቡቲን ጨምሮ በቀጣናው የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያጎለብቱ አስተሳሳሪ ልማቶችን በመተግበር ቀጣናዊ ትስስርን ለማጠናከር የሚከተለውን አቅጣጫ ያሳያል። የኢትዮጵያ እና የጅቡቲ የመጻኢ ጊዜ የሁለትዮሽ ትብብር በሀገራቱ መካከል የተጀመሩትን ግዙፍ የምጣኔ ሀብት እና የመሠረተ ልማት ትስስሮች ይበልጥ ወደ ላቀ የተሟላ ቀጣናዊ ትስስር የሚሸጋገርበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። የሁለቱ አገራት መሪዎች እና ሕዝቦች ያላቸው ዘመን ተሻጋሪ ወዳጅነት፣ የጋራ ህልውና እና እምነት የወደፊት ወዳጅነታቸውን ይበልጥ አስተማማኝ እንደሚያደርገው ይታመናል።
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ያነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች
Sep 24, 2026 531
ኢትዮጵያ 32ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በኃላፊነት ታዘጋጃለች፤ ጉባኤው የግሉን ዘርፍ እና ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላትን ያካተተ እንዲሁም ውጤታማ መፍትሔ የሚያመጣ እንዲሆን ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት ትሠራለች፤ ፕሬዝዳንቱ ሁሉም የዓለም መሪዎች በጉባኤው ላይ በመሳተፍ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ታሪካዊ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ ጥሪ አቅርበዋል፤ ኢትዮጵያ እየገነባችው ላለው ጠንካራ ኢኮኖሚ አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ የባህር በር ያስፈልጋታል፤ የኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ጉዳይ ለሁሉም የቀጣናው ሀገራት ከሚያስገኘው የጋራ ጥቅም፣ ትብብርና ዕድገት አንጻር ሊታይ ይገባል፤ ኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎቷን ለማሳካትና ከዓለም አቀፍ የንግድ ሥርዓት ጋር በጥብቅ ለመተሳሰር ሁሉንም የዲፕሎማሲ አማራጮች ተጠቅማ እየሠራች ትገኛለች፤ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን አፍሪካውያን እኩል ውክልና የማግኘት መብት ለዘመናት መነፈጋቸውን እንዴት የዓለም ህሊና ሊቀበለው ይችላል? የፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ሪፎርም ማድረግ የትውልዱ የእውነትና የሞራል ጥያቄ ነው፤ ድርጅቱ የዓለምን ነባራዊ እውነታ ያገነዘበ፣ በፍትሕና በእኩልነት ላይ የተመሠረተ መሠረታዊ ሪፎርም በማድረግ ወቅታዊ የዓለም ፈተናዎችን በተሻለ አቅም መወጣት አለበት፤ ኢትዮጵያ የሰዎች ሰብአዊ ክብር እንዲጠበቅ፣ ፍትሕ እንዲሰፍንና የነፃ ሕዝቦች አብሮነት እንዲከበር ባላት ታሪካዊ ቁርጠኝነት ጸንታ ትቀጥላለች፤ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በውሃ ሀብት የጋራ ቀጣናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚቻል ያሳየ ታላቅ ፕሮጀክት ነው፤ ኢትዮጵያ እስከ እ.ኤ.አ. 2030 ተጨማሪ 13,000 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት የምሥራቅ አፍሪካን የኢነርጂ ገበያ ፍላጎት ለማሟላት አቅዳ እየሠራች ትገኛለች፤ ኢትዮጵያ በመሠረተ ልማት፣ በንግድ እና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ቀጣናዊ ትስስርን ለማጠናከር እየሠራች ነው፤ በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና አለመረጋጋት ለመፍጠር የሚሠሩ የውጭ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፤ ታዳጊ ሀገራት የቴክኖሎጂ አብዮቱ ተመልካች ሳይሆኑ ባለቤት መሆን አለባቸው፤ የኢትዮጵያ የ"5 ሚሊዮን ኮደሮች" መርሃ ግብር እና የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ግንባታ አፍሪካ ለቴክኖሎጂው ዘመን ዝግጁ መሆኗን ማሳያ ነው ባለፉት 8 ዓመታት በተካሄደው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር 56 ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸውንና ይህም በዓመት 9 ቢሊዮን ቶን ካርቦን የማመቅ አቅም ይኖራቸዋል፤ ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከስንዴ አስመጪነት ወጥታ በአፍሪካ ከሚገኙ ትላልቅ የስንዴ አምራች ሀገራት አንዷ መሆን ችላለች፤ በምግብ ዋስትና ረገድም ከፍተኛ እመርታ ማስመዝገብ ችላለች፤ የአየር ንብረት ለውጥን የሚያቋቁሙ የተሻሻሉ የስንዴ ዝርያዎችን በስፋት በመጠቀም ረገድ አበረታች ስኬት አስመዝግባለች፤ የምግብ አቅርቦት የፖለቲካ አጀንዳ በሆነበት እና የዓለም የምግብ አቅርቦት ሰንሰለት በተፈተነበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ የስንዴ ምርታማነት አፍሪካ ራሷን መመገብ እንደምትችል ማሳያ ሆኗል፤
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ቀጣናዊ ብልጽግናን ማሳካት እንደሚቻል ያረጋገጠ ፓን-አፍሪካዊ ፕሮጀክት ነው-ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ
Sep 24, 2026 520
አዲስ አበባ፤ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ):- የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በውሃ ሀብት የጋራ ቀጣናዊ ብልጽግና ልማት እውን ማድረግ እንደሚቻል ያረጋገጠ ታላቅ ፓን-አፍሪካዊ ፕሮጀክት መሆኑን ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገለጹ። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በኒው ዮርክ እየተካሄደ ይገኛል። ፕሬዝዳንቱ ማምሻውን በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ በመሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ በንግድ እና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት በኩል በምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ትስስርና ትብብርን ለማጠናከር በትጋት እየሠራች መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ጠቁመዋል። አንዳንድ የውጭ አካላት በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና አለመረጋጋት ለመፍጠር እየሰሩ መሆኑን አንስተው፤ እነዚህ አካላት ከድርጊታቸው መቆጠብ አለባቸው ብለዋል። ከኢነርጂ ጋር በተያያዘ፣ ኢትዮጵያ ከ60,000 ሜጋ ዋት በላይ ኃይል ማመንጨት አቅም እንዳላት የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ እ.ኤ.አ. እስከ 2030 ድረስ ተጨማሪ 13,000 ሜጋ ዋት ለማመንጨት ማቀዷን ጠቁመዋል። ይህም የምሥራቅ አፍሪካን የኢነርጂ ገበያና ከዚያም አልፎ ያለውን ፍላጎት ለማሟላት እንደሚያስችል አስታውቀዋል። በዚህ ረገድም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሀብት የጋራ ቀጣናዊ ብልጽግና ዕድገትና ልማት መፍጠር እንደሚቻል ያረጋገጠ ታላቅ ፓን-አፍሪካዊ ፕሮጀክት ነውም ብለዋል። በሌላ በኩል በዲጂታል አብዮትና በሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘመን አፍሪካ የምታነሳው ወሳኝ ጥያቄ የቴክኖሎጂው ዘመን ዓለም አቀፍ አለመመጣጠንን የሚያባብስ ወይስ የጋራ እድገት ማፋጠኛ ነው? የሚለውን ጥያቄ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ አመልክተዋል። ዓለም አቀፉ የደቡብ ክፍለ ዓለም የቴክኖሎጂ አብዮቱን በባለቤትነት መምራት እንጂ ተመልካች መሆን የለበትም ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ የኢትዮጵያ የ"5 ሚሊዮን ኮደሮች" መርሃ ግብር እና የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ግንባታ አህጉሪቱ ለቀጣዩ ጊዜ ዝግጁ መሆኗን ማሳያ ናቸው ብለዋል። ከአካባቢ ጥበቃ እና ከተፈጥሮ ሀብት አንፃርም፤ ከስምንት ዓመታት በፊት በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እስከ አሁን 56 ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ፕሬዝዳንቱ አስታውሰዋል። መርሃ ግብሩ የደን ሽፋን ከማስፋቱም በላይ የአካባቢ ሥነ-ምህዳርን ወደ ነበረበት እየመለሰ መሆኑን ጠቅሰው ፤ ይህም በዓመት 9 ቢሊዮን ቶን ካርቦን የማመቅ አቅም እንደሚኖረው ይጠበቃል ብለዋል።
አፍሪካውያን በተመድ ፍትሃዊ ውክልና መነፈጋቸው በአስቸኳይ መታረም ያለበት ጉዳይ ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
Sep 23, 2026 598
አዲስ አበባ፤ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ):- 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን አፍሪካውያን በተመድ ፍትሃዊ ውክልና መነፈጋቸው በአስቸኳይ መታረም ያለበት ጉዳይ ነው ሲሉ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ። ተመድ የዓለምን ነባራዊ እውነታ ያገነዘበ መሰረታዊ ሪፎርም ሊያደርግ ይገባልም ብለዋል። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በኒው ዮርክ እየተካሄደ ነው። ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ማምሻውን በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ንግግር አድርገዋል። ፕሬዝዳንት ታዬ በንግግራቸው ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአሁኑ ሰዓት ዓለም ላይ ፈታኝ ሁኔታዎችን በተሻለ አቅም መፍታት እንዲችል መሰረታዊ የሆነ ሪፎርም እንዲያደርግ አጥብቃ ታሳስባለች ብለዋል። ተመድ በእኩልነት እና ፍትሃዊነት ላይ የተመሰረተ እንዲሁም የዓለምን ነባራዊ እውነት ባገነዘበ መልኩ ማሻሻያ ሊደረግበት እንደሚገባ ተናግረዋል። አፍሪካ በዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪነት ውስጥ ለረጅም ጊዜ ተግላ መቆየቷን አውስተው የፀጥታ ምክር ቤት አስቸኳይ ሪፎርም ማከናወን እንዳለበት አስገንዝበዋል። "እውነተኛ የፖለቲካ ፍላጎት ካለ፣ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን አፍሪካውያን እኩል ውክልና የማግኘት መብት ለዘመናት መነፈጋቸውን እንዴት የዓለም ህሊና ሊቀበለው ይችላል?" ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ጠይቀዋል። ይህ የትውልዱ የእውነት እና የሞራል ጥያቄ መሆኑንም ገልጸዋል። በሌላ በኩል ፕሬዚዳንቱ የባለብዙ ወገን ትብብርን አስፈላጊነት ሲያስረዱ፤ የጋራ ጸጥታ ምሰሶዎች ሙሉ በሙሉ ከመፍረሳቸው በፊት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ቆራጥ እርምጃ በመውሰድ ግጭቶችን ለመከላከል አበክሮ ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል። ባለብዙ ወገን ትብብር እንደ ቀላል የዲፕሎማሲያዊ መሳሪያ አይደለም፤ ይልቁንም ዓለም አቀፍ የኃይል ፖለቲካን ለመቋቋም የሚያስችል እና በሉዓላዊ እኩልነት ላይ የተመሰረተ ህያው ጋሻችን ነው ሲሉ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ሰዎች ሰብአዊ ክብራቸው እንዲጠበቅ፣ ፍትሕ እንዲሰፍን እና የነፃ ሕዝቦች ጽኑ አብሮነት እንዲከበር ባላት ታሪካዊ ቁርጠኝነት ጸንታ እንደምትቀጥል ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል።

ማህበራዊ
የጤና ተቋማት በራሳቸው የፋይናንስ አቅም የመድሃኒቶች ግዥ የመፈጸም አቅም ጎልብቷል 
Sep 25, 2026 66
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦የሀገሪቱ የጤና ተቋማት በራሳቸው የውስጥ ገቢ አስፈላጊ የሆኑ መድሃኒቶችና የህክምና ግብዓቶች ግዥ የመፈጸም አቅማቸው እየጎለበተ መምጣቱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። የኢትዮጵያ ፋርማሲ ማህበር ለ6ተኛ ጊዜ የዓለም የፋርማሲ ባለሙያዎች ቀንን አክብሯል። በዚሁ ጊዜም የማህበረሰብ ፋርማሲ ላይ ትኩረት ያደረገ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።   በጤና ሚኒስቴር የሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ በቀለ አሻግሬ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ የጤና ተቋማት በራሳቸው የፋይናንስ አቅም መድሃኒቶችና የህክምና ግብዓቶች ግዥ የመፈጸም አቅማቸው እያደገ መጥቷል። ለአብነትም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የጤና ተቋማት በራሳቸው በጀት 17 ቢሊዮን ብር ወጪ በማድረግ የመድሃኒት ግዥ መፈጸማቸውን ጠቅሰዋል። ይህም የአቅርቦት ሂደቱን ወጥ የሚያደርገው መሆኑን ጠቁመው፤ ለዚህ ደግሞ የፋርማሲ ባለሙያዎች ድርሻ ትልቅ መሆኑን አንስተዋል። ከውጭ የሚገባውን ክትባት በሀገር ውስጥ ለመተካት ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም ገልጸዋል። በመስኩ የሚካሄደው ምርምር፣ ፈጠራ እና የእውቀት ሽግግር ለጤናው ሥርዓት መጠናከር ጉልህ ድርሻ አለው ያሉት አማካሪው፣ በዚህ ረገድ የፋርማሲ ባለሙያዎች አበርክቶ ሊጠናከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል። በተለይም የመድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት ሪፖርት ማድረግ ላይ ያሉ ክፍተቶችን በጥናት ለይቶ መፍትሄ በማመላከት ረገድም የፋርማሲ ባለሙያዎች ተሳትፎ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል። በኢትዮጵያ የእናቶችና ህጻናት ሞት እንዲሁም ተላላፊ በሽታዎች እየቀነሱ መሆኑን የገለጹት አማካሪው፣ ለዚህም የፋርማሲ ባለሙያዎች ድርሻ ትልቅ መሆኑን አንስተዋል። የፋርማሲ ባለሙያዎችን ማብቃት እና በቅንጅት መስራት ከተቻለ ትልልቅ ውጤቶችን ማምጣት እንደሚቻል የተገኘው ውጤት ማሳያ ነው ሲሉም ተናግረዋል። የአገር ውስጥ መድኃኒት አምራቾች ጥራታቸውንና አቅማቸውን እንዲያሳድጉ የጤና ሚኒስቴር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል።   የኢትዮጵያ ፋርማሲ ማህበር ፕሬዝዳንት ዶክተር ዳንኤል ዋቅቶሌ በበኩላቸው፤ የፋርማሲ ባለሙያዎች መድሃኒቶች ለተጠቃሚዎች ሙያዊ በሆነ መንገድ ተደራሽ በማድረግ፣ ለታካሚዎች በሚሰጡት ምክር እንዲሁም በመድሃኒት አስተዳደር ላይ የማይተካ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል። ማህበሩ የፋርማሲ ባለሙያዎች ከወቅቱ ጋር የሚራመድ እውቀት እንዲገነቡ የሙያ ላይ ሥልጠናዎችን እየሰጠ ነው ብለዋል። ከዚህ ባለፈም ማህበሩ በአጠቃላይ ለጤናው ዘርፍ ግብዓት የሚሆኑ ፖሊሲዎች፣ አሰራሮችና ደንቦች ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲዘጋጁም በንቃት በመሳተፍ ሀገራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን አብራርተዋል። የዘንድሮ የዓለም የፋርማሲ ባለሙያዎች ቀን "የፋርማሲ ባለሙያዎችን ማብቃት ለተሻለ ነገ" በሚል መሪ ሀሳብ በመከበር ላይ ይገኛል።
በአዳማ ከተማ የመስቀል ደመራ በዓልን በድምቀት ለማክበር የሚያስችል ዝግጅት ተደርጓል
Sep 25, 2026 81
አዳማ ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦ በአዳማ ከተማ የመስቀል ደመራ በዓልን በድምቀት ለማክበር የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ዝግጅቱን በማስመልከት የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ጎርጎሪዮስ እና የሃይማኖት አባቶች ዛሬ ማምሻውን የደመራ ሥፍራውን ጎብኝተዋል።   የጽሕፈት ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መላከ ሣህል ቀሲስ ነጋሽ ሀብተወልድ ለኢዜአ እንዳስታወቁት፤ የመስቀል ደመራ በዓል ሃይማኖታዊና ብሔራዊ በዓል ነው። የመስቀል ደመራ በዓል የፍቅር፣ የሰላም፣ የአንድነትና የነፃነት አርማ በመሆኑ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዓሉን በድምቀትና ባማረ መልኩ ታከብረዋለች ብለዋል። በዚህ ረገድ በአዳማ ከተማ በነገው ዕለት የመስቀል ደመራ በዓል የሚከበርበትን የመስቀል አደባባይ በከተማው አስተዳደር እና በሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስተባባሪነት ዛሬ ጠዋት የማጽዳት እና ሌሎችም የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል። በደመራ ክብረ በዓል ማክበሪያ ሥፍራ የጽዳት ዘመቻ ላይ የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ ከሰንበት ትምህርት ቤት የተውጣጡ ወጣቶችና በጎ ፈቃደኞች እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎች ተሳታፊ መሆናቸውን ገልጸዋል።   አዳማ ከተማን ጨምሮ በምሥራቅ ሸዋ ዞን በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎችና ከተሞች የመስቀል ደመራ በዓልን ሃይማኖታዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ ማክበር የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ አረጋግጠዋል። በዓሉ የአንድነት፣ የፍቅር፣ የይቅርታ፣ የአብሮነት፣ የምሥጋናና የተስፋ እሴቶች የሚገለጹበት ሃይማኖታዊ ክብረ በዓል መሆኑንም አስረድተዋል። በነገው የአከባበር ሥነ ሥርዓት ላይ ከከተማ አስተዳደሩና ከሁሉም ደብራት የተውጣጡ የሃይማኖት አባቶች፣ የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና የእምነቱ ተከታዮች እንደሚገኙ አውስተዋል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ የአደባባይ በዓላት መካከል አንዱ የመስቀል ደመራ በዓልን ምዕመናን ደመራ ደምረው፣ ችቦ እያበሩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በመጠበቅ ያከብሩታል።
መስቀል የፍቅር፣ የሰላም እና የአንድነት መገለጫ ነው - ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ
Sep 25, 2026 241
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦መስቀል የፍቅር፣ የሰላም እና የአንድነት ማሳያ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ እና የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ገለጹ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ የሃይማኖት አባቶች እና የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት በመስቀል ደመራ ማክበሪያ ስፍራ የጽዳት መርሃ ግብር ተከናውኗል።   በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ እና የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ መስቀል የፍቅር፣ የሰላም እና የአንድነት ትልቅ መገለጫ ነው። በዛሬው ዕለት የሃይማኖት ተቋማት በጋራ በመሆን በበዓሉ ማክበሪያ ስፍራ የጽዳት መርሀግብር በጋራ ማከናወናቸው ትልቅ አርአያነት ያለው የአንድነት ተግባር መሆኑን አንስተዋል። በፍቅርና በአንድነት ሆነን በየትኛውም የሃይማኖት በዓል በዚሁ መልኩ ተገናኝተን በጋራ የመስራት ባህላችንን ማጠናከር ይኖርብናልም ብለዋል። አካባቢን ማጽዳትና ማስዋብ ለሚመጡ እንግዶች አቀባበል ምቹ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥር ገልጸው በጽዳት መርሃ-ግብሩ ላይ ለተሳተፉ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ቡዜና አልከድር በበኩላቸው ፣ የመስቀል ደመራ በዓል የሃይማኖት ሥርዓት ብቻ ሳይሆን የጋራ ባህል፣ የትብብር፣ የአንድነትና የሰላም መገለጫ ነው ብለዋል።   የመስቀል ደመራ በዓል የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የማይዳሰስ የሰው ልጅ የዓለም ቅርስ ሆኖ መመዝገቡን አስታውሰው፤ ይህም የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለም ጭምር የጋራ ሀብት መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል። በመስቀል አደባባይ የተከናወነው መርሃ ግብር ከጽዳት በላይ ትርጉም እንዳለው አመልክተው፤ ይህም የዜግነት ተሳትፎን፣ የጋራ ኃላፊነትንና ለከተማዋ ያለንን ፍቅር የምናሳይበት ተግባር ነው ሲሉም ገልጸዋል። አዲስ አበባ ፈጣን እድገት ላይ የምትገኝ የባህል፣ የታሪክና የቱሪዝም ማዕከል መሆኗንም ጠቁመዋል። ወደ ከተማዋ የሚመጡ እንግዶች የሚያዩት የጽዳት፣ የሰላምና የእንግዳ ተቀባይነት እሴት ለሀገር ገጽታ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለውም ተናግረዋል። ሰላማዊ እና ንጹህ ከተማ የጎብኚዎች ቁጥር እንዲጨምር በማድረግ የሆቴል እና መስተንግዶ፣ የትራንስፖርት፣ የንግድና አገልግሎት ዘርፎችን በማንቀሳቀስ ለዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ጠቁመው፤ ይህም የሀገርን ኢኮኖሚ የማነቃቃትና የማሳደግ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል። የከተማዋ ነዋሪዎች እንግዶችን በክብር በመቀበል፣ አካባቢን ንጹህ በማድረግ፣ ቅርሶችን በመጠበቅና የበዓላትን ሰላም በማስጠበቅ በኩል ወሳኝ ሚናቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።   የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ገዛኸኝ ዴሲሳ፤ የመስቀል ደመራ በዓል የአብሮነትና የወንድማማችነት መገለጫ ታላቅ የአደባባይ በዓልና በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ እንግዶች የሚታደሙበት በመሆኑ አካባቢን ማስዋብ አስፈላጊ ነው ብለዋል።   የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ምክትል ዋና ጸሐፊ ሼህ አብዱልሃሚድ አህመድ በበኩላቸው፤ የመስቀል ደመራ በዓል የዓለምን ትኩረት የሳበ ትልቅ ሀብት በመሆኑ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቱን ጠብቆ እንዲከበር ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።   የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት የአዲስ አበባ ክልል ዋና ጸሐፊ ፓስተር ሙላት ኤርሚያስ፤ በጽዳት መርሃ ግብሩ መሳተፋቸው በኢትዮጵያ የብዝሃነት እውነታ ውስጥ እርስ በእርስ በመከባበርና በሰላም አብሮ መኖር እንደሚቻል ለማሳየት መሆኑን ተናግረዋል።
በባሕር ዳር የትምህርት ቤት ምገባ የተማሪዎችን ውጤት በማሻሻል ተጨባጭ ለውጥ አምጥቷል
Sep 25, 2026 103
ባህር ዳር ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ያለው የተማሪዎች ምገባ መጠነ ማቋረጥን ከመቀነስ ባለፈ የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ ረገድ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቱን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት መምሪያ አስታወቀ። የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የምክር ቤት አባላት በከተማዋ የመማር ማስተማር ሥራንና የምገባ እንቅስቃሴን ጎብኝተዋል።   የመምሪያው ኃላፊ ሙሉዓለም አቤ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ተማሪዎች እንዳያረፍዱ፣ እንዳይቀሩና ትምህርት እንዳያቋርጡ በማድረግ በኩል ተጨባጭ ለውጥ አስገኝቷል። ተማሪዎች ትምህርታቸውን በተገቢው መንገድ እንዲከታተሉ እና ውጤታማ እንዲሆኑ በማድረግ በኩልም ውጤት እየተገኘበት መሆኑን ገልጸዋል። የምገባ ፕሮግራሙ የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ በሚደረገው ጥረት እገዛ እያደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል። በከተማ አስተዳደሩ በያዝነው የትምህርት ዘመን 30 ሺህ ሕፃናትን ለመመገብ ታቅዶ እየተተገበረ ሲሆን፣ እስካሁን በአራት ትምህርት ቤቶች ምገባውን ማስጀመር ተችሏል ብለዋል። የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ጌትነት እውነቱ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ለተማሪዎች ምገባ ውጤታማነት የሁሉም አካላት ትብብርና ድጋፍ ወሳኝ ነው ብለዋል።   ከምገባው በተጨማሪ የትምህርት ጥራትንና ተደራሽነትን ለማሳካት ለመማር ማስተማር ሂደቱ የሚያግዙ ግብዓቶችን የማሟላት ሥራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ጠቁመዋል። ምክር ቤቱ የሕዝብ ውክልናውን በመጠቀም መንግሥትንና ኅብረተሰቡን በማገናኘት እየሠራ ሲሆን፣ በቀጣይም በትምህርት ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ክትትልና ድጋፎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። በከተማዋ የሚገኘው የጠይማ 2ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ሙሉጌታ ባለው እንዳሉት፤ በከተማዋ የተጀመረው የተማሪዎች ምገባ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በጉጉት እንዲከታተሉ እያደረጋቸው ነው። አሁንም የተማሪዎች የክፍል ጥምርታ ተመጣጣኝ እንዲሆን በማድረግ በኩል የተጀመሩ የተቀናጁ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልጸዋል። ከተማ አስተዳደሩ ባለፈው ዓመት ለትምህርት ቤት ምገባ 69 ሚሊዮን ብር ወጪ ማድረጉንም ጠቅሰዋል። በከተማዋ በሚገኙ 250 ትምህርት ቤቶች 187 ሺህ ተማሪዎችን መዝግቦ ለማስተማር እየተሠራ ሲሆን፣ እስካሁን በተደረገ ጥረት 94 በመቶ ማሳካት እንደተቻለም አስረድተዋል።
ኢኮኖሚ
የኢትዮ-ጅቡቲ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሮጀክት የሎጂስቲክስ ወጪን በእጅጉ የሚቀንስ ነው
Sep 25, 2026 45
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ)፦ በጅቡቲ ዳመርጆግና በኢትዮጵያ ደወሌ መካከል የሚዘረጋው የ120 ኪሎ ሜትር የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሮጀክት የነዳጅ አቅርቦትን በማቀላጠፍ የሎጂስቲክስ ችግሮችን እንደሚያቃልል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አስታወቀ። ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) እና በዳንጎቴ ግሩፕ መካከል በተደረገ አጋርነት የሚተገበር ሲሆን፤ ከ1 ሚሊዮን ኩቢክ ሜትር በላይ የተጣራ የነዳጅ ምርቶችን የመያዝ እና የማስተላለፍ አቅም ይኖረዋል። ፕሮጀክቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑመር ጌሌ እና የዳንጎቴ ግሩፕ ፕሬዚዳንት አሊኮ ዳንጎቴ በተገኙበት ይፋ ተደርጓል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ለ‘ፐልስ ኦፍ አፍሪካ’ እንደገለጹት፤ አሁን ባለው አሰራር ነዳጅ በጅቡቲ ወደብ ከመርከብ ወርዶ ወደ ማከማቻ ከገባ በኋላ በቦቴዎች አማካኝነት 750 ኪሎ ሜትር ያህል ተጓጉዞ ወደ ኢትዮጵያ ይገባል። በኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር በቀን ከሚጓጓዙ 1000 የጭነት ተሽከርካሪዎች መካከል 35 በመቶ የሚሆኑት ነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች መሆናቸውንና ይህ አሰራርም ውጤታማ አለመሆኑን ገልጸው አዲሱ የቧንቧ መስመር የሎጂስቲክስ ወጪን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ አስረድተዋል። በተጨማሪም በጅቡቲ ወደብ የቦቴዎች ወይም የማከማቻ ተቋማት አለመዘጋጀት ምክንያት መርከቦች ለቀናት በመቆም የሚከፍሉትን ከፍተኛ የዲመሬጅ ወጪ የሚያስቀር መሆኑንም ጠቅሰዋል። በመሆኑም አዲሱ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ መርከቦች እንደደረሱ ነዳጁን በቀጥታ ወደ ማከማቻው እንዲያወርዱና በቧንቧ መስመር ወደ ኢትዮጵያ እንዲጓጓዝ ስለሚያደርግ የትራንስፖርት ቀናትን በከፍተኛ ሁኔታ ያሳጥራል። ፕሮጀክቱ ሁለት ዋና ዋና የገቢና የኢኮኖሚ ጥቅሞችን የሚያስገኝ ሲሆን፤ የመጀመሪያው ከቧንቧው እና ከነዳጅ ማከማቻው አገልግሎት የሚገኝ ቀጥታ ገቢ ነው። ሁለተኛው ደግሞ በኢኮኖሚው ውስጥ የናፍጣ፣ የቤንዚንና የሌሎች ነዳጅ ምርቶች የትራንስፖርት ወጪ በመቀነሱ ምክንያት የሚፈጠረው አጠቃላይ የአገልግሎት እና የንግድ ውድድር አቅም ማደግ መሆኑንም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የሀገሪቱን መንግሥት ፍላጎት በመወከል በፕሮጀክቱ ውስጥ ባለድርሻ ሆኖ እንደሚሳተፍ የተገለጸ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ የሀገሪቱን የሎጂስቲክስ አሰራር ከዘመናዊ የትራንስፖርት ሞዴል ጋር ለማጣጣም የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑም ተመላክቷል።
አልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ - የባለ ጥቁር ጋማ አንበሳ መገኛ
Sep 25, 2026 77
ጎብኚዎች ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ከሚነሳሱባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል ያሏት ጥንታዊና ድንቅ የታሪክ፣ የባህልና የተፈጥሮ ሀብት ስብስቦች እንደሆኑ ዋነኛዎቹ ናቸው። በዩኔስኮ የተመዘገቡ በርካታ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት መሆኗ ፣ የሰው ልጅ መገኛነቷን የሚያረጋግጡ ሳይንሳዊ ግኝቶች፣ እንዲሁም የአረቢካ ቡና የመጀመሪያ መገኛ መሆኗ እና ሌሎችንም መጥቀስ ይቻላል። “ታሪኳንና ቅርሶቿን ገልጦ ለተመለከተ መልክአ ምድሯን ለቃኘ በማህጸኗ ያቀፈቻቸውን እንስሳት ፣ አዕዋፍና ዕጽዋት ዓይኑን ገልጦ ላሰሰ ፣ የሕዝቦቿን ባህል ፣ ትውፊት ፍልስፍና በማስተዋል ለመረመረ ኢትዮጵያ የመስህቦች ማንጸሪያ የልዩነት አጽናፍ ማስረጃ ናት” …የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ገጽ 260 ቱሪዝምን ማሳደግ ሃገራችን ከዘርፉ ልታገኘው የሚገባትን ሰፊ ጥቅም ማረጋገጥ የመደመር መንግስት ትኩረት ካደረገባቸው አምስቱ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ነው። የበርካታ ቱሪስቶችን ቀልበ ከሚስቡትና በተፈጥሮ ፀጋዎች ከታደሉ ሥፍራዎች አንዱ የአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ በኢትዮጵያ በስነ-ምህዳር ልዩነቱና ለዱር እንስሳት ምቹ በሆነው የተፈጥሮ ሁኔታው የሚታወቅ ነው። ፓርኩ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ በ1998 ዓ.ም በይፋ በብሔራዊ ፓርክነት ተከልሎ ለጎብኚዎች ክፍት ተደርጓል። የፓርኩ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት 3 ሺህ 276 ካሬ ኪሎ ሜትር የሚያካልል ሲሆን፣ ከሱዳን ድንበር ጋር ይገናኛል። ፓርኩ ስሙን ያገኘው አካባቢውን አቋርጦ ከሚያልፈውና ለዱር እንስሳቱ ዋነኛ የውሃ ምንጭ ከሆነው "አልጣሽ" ከተባለው ወንዝ ነው። ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ 1 ሺህ 025 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ ፓርክ፣ ያልተነካ ተፈጥሮንና የዱር እንስሳት ህይወትን ለመመልከት ትልቅ እድልን የሚሰጥ ስፍራ ነው። የአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ መልክአ-ምድር በዋናነት ሜዳማና ዝቅተኛ ቦታዎችን ያካተተ ሲሆን ከፍታው ከባህር ጠለል በላይ ከ500 እስከ 900 ሜትር ይደርሳል። የአየር ጠባዩ ሞቃታማና ደረቅ ሲሆን፣ በዋናነት በሳቫና ሳር ምድር፣ በጥቅጥቅ የግራርና የቀርከሃ ደኖች የተሸፈነ ነው። በፓርኩ ውስጥ የሚያልፉት የአልጣሽና አዩባ ወንዞች በተለይም በደረቁ ወቅት ለዱር እንስሳቱ አስፈላጊውን ውሃ ያቀርባሉ። በተጨማሪም በዝናብ ወቅት የሚፈጠሩ ጊዜያዊ ረግረጎችና የውሃ አካላት ለተለያዩ አእዋፍና የውሃ ውስጥ ህይወት ፍጥረታት ምቹ የመኖሪያ ከባቢን ይፈጥራሉ። አልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ አልፎ አልፎ የሚታዩና የመጥፋት አደጋ የተደቀነባቸው የዱር እንስሳት መኖሪያም ነው። በፓርኩ ከሚገኙ አጥቢ እንስሳት መካከል አንበሳ፣ ነብር፣ ሳላ፣ አጋዘን፣ ሚዳቋ፣ ጦጣ፣ ዝንጀሮ፣ የዱር አህያና የዱር ውሾች ይጠቀሳሉ። በተለይም በአፍሪካ ብቸኛ የሆነው ባለ ጥቁር ጋማ አንበሳ የሚገኘውም በዚሁ ፓርክ ነው። እ.ኤ.አ. በ2016 የተደረገ ሳይንሳዊ ጥናት እንደጠቆመውም፣ በዛ ያሉ የአንበሳ መንጋዎች በዚህ ፓርክና በአጎራባቹ ይዞታ ውስጥ እንደሚኖሩም ተረጋግጧል። ከ200 በላይ የሚሆኑ የአገር ውስጥና ከሌሎች ዓለማት (ከአውሮፓና ኤስያ) የሚሰደዱ የአእዋፍ ዝርያዎች በፓርኩ ውስጥ ይገኛሉ። ይህም ፓርኩን ለወፍ አድናቂዎችና ተመልካቾች ተመራጭ ያደርገዋል። በፓርኩ ውስጥ የመድኃኒትነትና የኢኮኖሚ እሴት ያላቸው የተለያዩ የግራር ዝርያዎች፣ የቀርከሃ ጫካዎችና የዕጣን ዛፎች በስፋት ይበቅላሉ። የአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ ከሱዳኑ ዲንደር ብሔራዊ ፓርክ ጋር ተጎራባች የሚያደርገው ሰፊ የድንበር ግንኙነትም አለው። ሁለቱ ፓርኮች ተያያዥ በመሆናቸው በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል ድንበር ተሻጋሪ የተፈጥሮ ጥበቃ ቀጣና እንዲፈጠር ምክንያት ሆነዋል። ይህ ግንኙነት የዱር እንስሳቱ ያለ ምንም የወሰን ችግር በነጻነት እንዲንቀሳቀሱና የመራባት ወሰናቸውን እንዲያሰፉ ትልቅ ዕድልን ፈጥሮላቸዋል። በብሔራዊ ፓርኩ የወሰን ማካለል፣ የጥበቃ አቅምን የማጠናከር፣ የህገ-ወጥ አደን እና የሰደድ እሳት ስጋቶችን የመቀነስ ስራዎች ተሰርተዋል። የአካባቢው ማህበረሰብም ፓርኩን በባለቤትነት እንዲንከባከብና ተጠቃሚም እንዲሆን በንብ ማነብ፣ በእንሰሳት መኖ ልማት እና በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ እንዲሰማራ ለማድረግ የማህበረሰብ ተኮር ፕሮጀክቶች ተቀርፀዋል። ወደ ፓርኩ የሚያስገቡ የውስጥ ለውስጥ መንገድ መተላለፊያዎችን የማስተካከል፣ የመቆጣጠሪያ ኬላዎችን የመገንባት እና ወደፊት የስነ-ምህዳር ቱሪዝም መስህብ የሚሆኑ ቦታዎችን የመለየት ቅድመ-ዝግጅቶች እየተከናወኑ እንደሚገኙም መረጃዎች ያሳያሉ።
ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያየን ነው- ሸማቾችና ነጋዴዎች
Sep 25, 2026 104
ቢሻን ጉራቻ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦በቢሻን ጉራቻ ከተማ ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆናቸውን ሸማቾችና ነጋዴዎች ገለጹ። በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚከበሩ ሀይማኖታዊ በዓላት መካከል አንዱ የሆነው የመስቀል በዓል መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ.ም ይከበራል። የበዓል የእርድ እንስሳት ግብይት ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች መካከል ደግሞ የቢሻን ጉራቻ የቁም እንስሳት ገበያ ተጠቃሽ ነው። የበዓል ገበያውን አስመልክተው ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ ሸማቾችና ነጋዴዎች፤ በከተማው ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆኑን ገልጸዋል።   አስተያየታቸውን ከሰጡ የእርድ ከብት ሲገዙ ያገኘናቸው አቶ ሀይለኢየሱስ ሻንካ እና አቶ በለጠ አሰፋ የመስቀል በዓል ገበያው ካለፉት በዓላት አንጻር በዋጋም ሆነ በአቅርቦት የተሻለ ነው ብለዋል።   አርሶ አደሩም እንስሳትን በአግባቡ አደልቦ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ ለመሆን እንዳስቻለውም ገልጸዋል።   የእርድ ሰንጋ ነጋዴ የሆኑት አቶ ከድር ሁሴን በበኩላቸው፤ በበዓል ገበያው ሸማቹ እንደ አቅሙ ገዝቶ ለመጠቀም የሚያስችል አቅርቦት መኖሩን ጠቅሰው ግብይቱም የተረጋጋ መሆኑን ተናግረዋል።
በክልሉ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን በማልማትና በማስተዋወቅ ዘርፉን ለማነቃቃት እየተቻለ ነው
Sep 25, 2026 111
ደሴ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦በአማራ ክልል የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን በማልማትና በማስተዋወቅ ዘርፉን ለማነቃቃት እየተቻለ መሆኑን የክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ገለጸ። የደሴ ከተማ አስተዳደር "ዲጂታል አጀንዳና ሰው ሰራሽ አስተውሎት ለቱሪዝም አዲስ ቅኝት" በሚል መሪ ቃል የዓለም የቱሪዝም ቀንን በፓናል ውይይት አክብሯል።   በዚሁ ወቅት የቢሮው ምክትል ኃላፊ አየለ አናውጤ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ በክልሉ ያለውን እምቅ የቱሪዝም ሀብት አልምቶ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችሉ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው። ባለፉት ዓመታት የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማልማት፣ በማስተዋወቅና ንቅናቄ በመፍጠር ረገድ አበረታች ውጤቶች ለማስመዝገብ በመቻሉ ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። ለዚህም አገልግሎቱን ከዲጂታል ቴክኖሎጂ ጋር በማስተሳሰር ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊና ሃይማኖታዊ የቱሪስት መዳረሻዎችን በተሻለ መንገድ ለማልማት እንደሚሰራ ጠቅሰዋል። በተጨማሪም የቱሪዝም ሀብቶችን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ለማስመዝገብ በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። በተያዘው በጀት ዓመትም የተለያዩ ቅርሶችንና የቱሪስት መዳረሻዎችን በማልማትና በመጠገን ወደ አገልግሎት ለማስገባት የታቀደ መሆኑን ገልጸዋል። የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው፤ በከተማው የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎች በተሻለ መንገድ ለጎብኝዎች ምቹ እየተደረጉ መሆኑን አስረድተዋል።   ይህም የአካባቢውን የአብሮነት፣ የመቻቻል፣ የፍቅርና የአንድነት ባህል ከማስተዋወቅ ባለፈ፣ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠርና ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ገልጸዋል። በደሴ ከተማ ሁለት ቤተ መንግሥቶች፣ ሙዚየምና ሌሎችም የቱሪስት መዳረሻዎች መኖራቸውን የጠቀሱት ደግሞ የደሴ ከተማ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰይድ አራጋው ናቸው።   አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ በመደገፍ የቱሪስቶችን ቆይታ ከማራዘም ባሻገር ሀብቱን ለትውልድ ለማስተላለፍ የተከናወኑ ተግባራት ውጤት የተገኘባቸው መሆኑንም አብራርተዋል። በወሎ ዩኒቨርሲቲ የቱሪዝምና ሆቴል ማኔጅመንት ትምህርት ክፍል መምህር አስናቀው አትሉግ በበኩላቸው፤ የዓለም የቱሪዝም ቀን ሲከበር ዘርፉን በአዲስ መንገድ ለመቃኘትና ለማልማት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።   በአሁኑ ወቅት የቱሪዝም እንቅስቃሴ በዲጂታል ቴክኖሎጂ እየተመራ መሆኑን ጠቁመው፣ አሰራሩን ዘመናዊ በማድረግ ዘርፉን ለማነቃቃት የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አመላክተዋል። በፓናል ውይይቱ ላይ የክልል፣ የደሴ ከተማና የአጎራባች ዞኖችና ከተሞች አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ተቋሙ የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎችንና ራሳቸውን የቻሉ ኢንተርፕሩነሮችን በማፍራት ረገድ የበኩሉን ሚና እየተወጣ ይገኛል
Sep 25, 2026 340
‎አዲስ አበባ፣መስከረም 15/2019 (ኢዜአ)፦የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎችንና ራሳቸውን የቻሉ ኢንተርፕሩነሮችን በማፍራት ረገድ የበኩሉን ሚና እየተወጣ መሆኑን ገለጸ። ተቋሙ የሥራ እንቅስቃሴዎቹን ለህብረተሰቡ ለማስተዋወቅ የሚያስችለውንና ለ15 ቀናት የሚቆየውን 'የመረጃ ሳምንት' በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።   ‎‎የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ሙሉጌታ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ በተቋሙ ውስጥ የተደራጁ ዎርክሾፖች፣ ላቦራቶሪዎች እና የመለማመጃ ቦታዎች መኖራቸው ለወጣቶች ትልቅ አቅም እና ዕድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል። ተቋሙ ወጣቶች ስራ ለመፍጠር የሚያስችላቸው ትልቅ ዕድል እንዳስገኘ ጠቅሰዋል። በዚህ መሰረት ተቋሙ ሀገሪቱን ሊለውጡ የሚችሉ ቴክኖሎጂ ፈጣሪዎችንና ራሳቸውን የቻሉ ኢንተርፕሩነሮችን በማፍራት ረገድ የበኩሉን ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በ2019 ዓ.ም የሚቀበላቸውን ተማሪዎች ውጤታማ ትምህርት ለመስጠት በቂ ዝግጅት ማድረጉንም ተናግረዋል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ የዘመኑን ፍላጎት የዋጁ ወደ 11 የሚጠጉ አዳዲስ ፕሮግራሞች መጀመራቸውን አስታውቀዋል። ከእነዚህ መካከል የሰው ሰራሽ አስተውሎት(ኤአይ) ስልጠና ፕሮግራም አንዱ ሲሆን፣ በዚሁ መርሀ ግብር ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያሰለጠነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።   የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ጸዳለ ተክሉ በበኩላቸው፣ ኢንስቲትዩቱ ለትምህርት ጥራት የሰጠው ትኩረት ተጨባጭ ውጤቶችን እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል። ተቋሙ የ ISO 9001:2015 እውቅናን በዋናው ካምፓስ ማረጋገጥ መቻሉን አስረድተዋል። ‎
"አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የመጨረሻ ፈጠራ ወይስ የፈጠራ መጨረሻ?" በሚል ርዕስ በሰለሞን ሙሉጌታ የተጻፈ መጽሐፍ ለንባብ በቃ
Sep 23, 2026 253
አዲስ አበባ፤ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ):- "አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የመጨረሻ ፈጠራ ወይስ የፈጠራ መጨረሻ?" በሚል ርዕስ በሰለሞን ሙሉጌታ የተጻፈ መጽሐፍ ለንባብ በቃ። "አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የመጨረሻ ፈጠራ ወይስ የፈጠራ መጨረሻ?" በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መፅሀፍ ሲሆን፤ የመንግሥት የስራ ሃላፊዎች፣ የጸሀፊው ቤተሰቦችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በሳይንስ ሙዚየም ተመርቋል።   የመጽሐፉ ጸሀፊ ሰለሞን "ቴክ ቶክ ዊዝ ሰለሞን" በሚል ርዕስ በሚያዘጋጀው ፕሮግራም የቴክኖሎጂ ዜናዎችን፣ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ስኬታማ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችና ሳይንቲስቶች በማስተዋወቅ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። በአዲስ አበባ ባቋቋመው የቴክኖሎጂ የፈጠራ ማዕከልም ወጣት የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ስታርታፖችን በመደገፍ በስራ ዕድል ፈጠራ እና ዲጂታል ሽግግርን ማፋጠን እንዲሁም ለቴክኖሎጂው ዕድገት የበኩሉን ሚና እየተወጣም ይገኛል። ሰለሞን ሙሉጌታ ያስመረቀው መጽሐፍ በኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ እና ዲጂታል ሽግግር ውስጥ ትልቅ አሻራ የሚያሳርፍ መሆኑ ተጠቁማል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢኒስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት፤ መጽሐፉ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በቀላል ቋንቋ የሚያስረዳ በመሆኑ ግንዛቤን ለማስፋት መሰረት ይጥላል ብለዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ጥቅምና ስጋቶች በአግባቡ እንደሚተነትን ጠቁመው፤ በዘርፉ ውጤታማ ሆኖ ለመዝለቅ አመላካች ሃሳቦች የተካተቱበት በመሆኑ ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ ገልጸዋል። ጂኦ ፖለቲካ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘመን ያለውንም ቦታ በተመለከተ ጥልቅ ጽንሰ ሃሳብ የያዘ በመሆኑ ለዘርፉ ዕድገት ጉልህ አበርክቶ እንደሚኖረው ተናግረዋል።   የስነ አዕምሮ ሀኪሙ ዶክተር ምህረት ደበበ በበኩላቸው፤ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ትምህርት፣ ጤና፣ ፖለቲካ፣ ወታደራዊ መስኮችን ጨምሮ በሁሉም የህይወት መስኮች በሚባል ደረጃ ሚና መጫወት መጀመሩን አንስተዋል። ስለሆነም ከሰው ሰራሽ አስተውሎት መራቅ እንደማይቻል አንስተው፤ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን እንዴት ጠቃሚ በሆነ መንገድ ልንጠቀም ይገባል የሚለው ቁልፍ ጉዳይ ነው ብለዋል። መጽሐፉ ለእነዚህ ጉዳዮች በቂ ምላሽ የሚሰጥ በመሆኑ ጠቀሜታው ከፍ ያለ ነው ሲሉም ተናግረዋል። ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ከሞራል ጋር ባስተሳሰረ መልኩ የመጠቀምን አስፈላጊነትንም መጽሐፉ እንደሚዳስስ ጨምረው አብራርተዋል። የመጽሐፉ ጸሀፊ ሰለሞን በበኩሉ፤ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ለአፍሪካ የህክምና፣ የአየር ንብረት ለውጥን ጨምሮ የህልውና ጥያቄ መፍቻ ቁልፍ እንደሚሆን አብራርቷል። የስራ ዕድል ፈጠራ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘመን በምን መልኩ ሊቃኝ ይገባል? የአፍሪካ ሀገራትም በምን መልኩ ሊያዩት ይገባል? የሚለውንም ጥያቄ በማንሳት መጽሐፉ እንደሚያብራራ ገልጸዋል። በሰው ሰራሽ አስተውሎት ውስጥ የአፍሪካ ዕጣ ፈንታ እንዴት ይሆናል? የሚለው ጉዳይ በመጽሐፉ ውስጥ መካተቱን ጠቁሞ፤ ከዘርፉ የአፍሪካን የተጠቃሚነት ድርሻ ለማሳደግ በቁርጠኝነት መረባረብ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥቷል ነው ያለው። ጸሀፊው ሰለሞን ሙሉጌታ ከዚህ ቀደም "ግርመተ ሳይቴክ" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ማብቃቱ ይታወሳል።
በአስተዳደሩ የተዘረጋው የዲጂታል አሠራር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት አስችሏል
Sep 22, 2026 212
ድሬደዋ፣ መስከረም 12/2018 (ኢዜአ)፡- በድሬዳዋ አስተዳደር የተዘረጋው የዲጂታል አሠራር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በፍጥነትና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ለመፍታት ማስቻሉ ተገለፀ። በድሬደዋ አስተዳደር የተገልጋዮችን ቅሬታና አቤቱታ ለመፍታት በተዘረጋው የዲጂታል ቴክኖሎጂ አሠራር ላይ የግንዛቤ ማሳደጊያ ሥልጠና ተሰጥቷል።   በወቅቱም የአስተዳደሩ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ሰዓዳ አዋሌ እንደገለጹት፤ በአስተዳደሩ የተዘረጋው የዲጂታል አሠራር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በፍጥነትና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ለመፍታት አስችሏል። ዘመናዊ የዲጂታል አሠራሩ በከንቲባው ጽሕፈት ቤት የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ዳይሬክቶሬት ሥር በሚገኙ ተቋማት ተተግብሮ ውጤታማ መሆኑንም አስረድተዋል። በከንቲባው ጽሕፈት ቤት የተገኘውን ውጤት ሕዝብ በብዛት በሚገለገልባቸው የወረዳ ተቋማት ውስጥ ለማስጀመር የዛሬው ሥልጠና መሰጠቱን ገልጸዋል። ሥልጠናው የዲጂታል አሠራሩን በዚህ ሳምንት በሁሉም ወረዳዎች ለማስጀመር ያለመ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀጣይም በገጠር ክላስተሮች እንደሚቀጥልም አስረድተዋል። የዲጂታል አሠራር መተግበሪያውን አስተዳደሩ ከድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመቀናጀት ለተለያዩ ተቋማት እያበለጸገ መሆኑንም ገልጸዋል።   በከንቲባ ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ቅሬታ፣ አቤቱታና ሥልጠና ቡድን መሪ አቶ አሻግሬ ታደሰ በበኩላቸው፤ በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የበለጸገው ዲጂታል መተግበሪያ የሕዝብን ቅሬታ በፍጥነት ለመፍታት ማገዝ እንደሚያስችል ተናግረዋል። የዲጂታል አሠራሩ በየደረጃው የሚገኘው አመራር የሚቀርቡለትን የትኛውንም ቅሬታዎች ባለበት ቦታ ሆኖ በፍጥነት ለመመለስ የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል። በሶፍትዌር አተገባበሩ ላይ የተሳተፉት ሰልጣኞች በበኩላቸው፤ ሥልጠናው የዲጂታል አሠራሩን በፍጥነት ወደ ተግባር በማውረድ የተሻለ አገልግሎትን ለነዋሪው ለመስጠት እንደሚያግዛቸውም ጠቁመዋል።  
ዩኒቨርሲቲው የሚያካሄደው የምርምርና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት የአካባቢውን ህብረተሰብ ተጠቃሚ እያደረገ ነው
Sep 21, 2026 379
ሮቤ፤ መስከረም 11/2019 (ኢዜአ)፦ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሚያካሄዳቸው የምርምርና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶች የአካባቢውን ህብረተሰብ ተጠቃሚ እያደረጉ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ብርሃነመስቀል ጠና (ዶ/ር) ገለጹ። ዩኒቨርሲቲው የጭብጥ ተኮር የምርምርና ማህበረሰብ ልማት ንድፈ ሀሳቦችን የሚገመግም የአቅም ግንባታ ዐውደ ጥናት እያካሄደ ነው። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ብርሃነመስቀል ጠና (ዶ/ር) እንዳሉት፤ ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን ለማህበረሰቡ ችግሮች መፍትሔ የሚያመላክቱ ምርምሮችን እያካሄደ ይገኛል። በተለይም የዩኒቨርሲቲው የልህቀት ማዕከል የሆኑት የግብርና፣ ጤና፣ ቱሪዝም፣ ብዝሃ-ሕይወትና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ዘርፎች ዋና ዋና የምርምር ትኩረት መስኮች መሆናቸውን አክለው ገልጸዋል። የዩኒቨርሲቲው ምሁራንም ባለፉት ዓመታት ባካሄዷቸው የምርምርና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶች የበርካታ ዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እመርታዊ ውጤቶች መገኘታቸውን ገልጸዋል። በተለይም በግብርናው የኩታ-ገጠም አሰራር፣ በካንሰር ህክምናና ህብረተሰቡን ግንዛቤ በማስጨበጥ ረገድ በተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ለውጦች መመዝገባቸውን በማሳያነት ጠቅሰዋል። ዩኒቨርሲቲው የሚያከናውናቸው የምርምርና ማህበረሰብ ልማት አገልግሎቶች የህዝብን ችግሮች በተሻለ ሁኔታ ለመፍታት እንዲችሉ በዘርፉ ለተሰማሩ ተመራማሪዎችና ገምጋሚዎች የሚሰጠው ቀጣይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠናም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ፕሬዝዳንቱ አውስተዋል።   የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ፣ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት በዛብህ ወንድሙ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የአቅም ግንባታ ዐውደ ጥናቱ በምርምር ዘርፍ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን በመለየት የተሻለ ተፅዕኖና ውጤት የሚያመጣ ምርምር ለማከናወን እንደሚረዳ ገልጸዋል። በተለይም ተመራማሪዎቹ በስልጠናው ቆይታቸው በጭብጥ ተኮር የምርምር ንድፎች ምንነትና አዘገጃጀት፣ በማህበረሰብ ተኮር ልማት ስራዎች ንድፈ-ሀሳብ አዘገጃጀትና በዓለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ በቂ ግንዛቤ እንደሚያገኙ ተናግረዋል። የዩኒቨርሲቲው ምሁራን በ2018 የበጀት ዓመት በተለያዩ የትኩረት መስኮች ላይ ያተኮሩ ከ24 በላይ ምርምሮችን ማካሄዳቸውን በማስታወስ፤ በአዲሱ የበጀት ዓመት ደግሞ 96 የምርምር ንድፈ-ሀሳቦች ለግምገማ መቅረባቸውን አመልክተዋል። ዩኒቨርሲቲው የሚያካሄዳቸው የምርምርና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶች የአካባቢውን ህብረተሰብ ችግሮች በመቅረፍ ተጠቃሚነቱን ይበልጥ ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመልክተዋል።
ስፖርት
አዲስ አበባ፣ ኦሮሚያ እና ድሬዳዋ በሀገር አቀፍ የውሃ ዋና ውድድር አሸናፊ ሆኑ
Sep 25, 2026 93
አዲስ አበባ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ውሃ ዋና ስፖርቶች ፌዴሬሽን ያዘጋጀው የ2019 ክልሎች እና ክለቦች የውሃ ዋና ውድድር ፍጻሜውን አግኝቷል። ውድድሩ በጋምቤላ ክልል ከመስከረም 10 እስከ 14 ቀን 2019 ዓ.ም በሁለቱም ጾታዎች ተካሄዷል። ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍራት እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ ውድድሮች ላይ ሀገራቸውን የሚወክሉ ስፖርተኞችን መምረጥ ዓላማ በማድረግ ውድድሩ ተከናውኗል። በውድድሩ አዲስ አበባ፣ ኦሮሚያ፣ ድሬዳዋ፣ጋምቤላ፣ ኦሮሚያ ፖሊስ፣ ሮቤል ክለብ፣ ላፍቶ ክለብ እና ጊዮን ሆቴል ተሳትፈዋል። በአዋቂ ምድብ በተካሄደው ውድድር አዲስ አበባ በሴቶች 17፣ በወንዶች ደግሞ 11 የወርቅ ሜዳሊያዎችን በማስመዝገብ ውድድሩን በበላይነት አጠናቋል። በታዳጊ ሴቶች ምድብ ኦሮሚያ በበላይነት ሲያጠናቅቅ በወንዶች ድሬዳዋ አሸናፊ ሆኗል። ጋምቤላ ክልል ልዩ የዋንጫ ተሸላሚ በመሆን ውድድሩን ማጠናቀቁን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በመረጃ ያመለክታል።
የአፍሪካ ዋንጫ መስራቾቹን ኢትዮጵያ እና ሱዳን ያገናኘው የማጣሪያ ጨዋታ
Sep 25, 2026 133
አዲስ አበባ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ)፦ በ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድብ 10 የመጀመሪያ ጨዋታውን ከሱዳን ጋር ዛሬ ጨዋታዋን ያደርጋል። የሁለቱ ሀገራት ጨዋታ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በጁባ ብሔራዊ ስታዲየም ይካሄዳል። በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ከሱዳንና ሴኔጋል ጋር ለሚደረጉት የማጣሪያ ጨዋታዎች ከአንድ ወር በላይ በሀገር ቤት ዝግጅቱን አድርጓል። አሰልጣኝ ዮሐንስ በመጀመሪያ ዙር ለ39 ተጫዋቾች ጥሪ ካደረጉ በኋላ በዝግጅት ሂደት የመጨረሻ ስብስቡን ወደ 23 ዝቅ አድርገዋል። ቡድኑ በሀገር ቤት ቆይታው ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን፣ ከሀዋሳ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የአቋም መለኪያ ጨዋታዎችን አከናውኗል። ዋልያዎቹ ከሱዳን ጋር ላለባቸው ጨዋታ ማክሰኞ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ጁባ ገብተው ዝግጅታቸውን ሲያደርጉ ቆይተዋል። በ66 ዓመቱ ጋናዊ ጀምስ ክዌሲ አፒያ የሚመራው የሱዳን ብሔራዊ ቡድን 33 ተጫዋቾን በመያዝ ለሁለት ሳምንት ገደማ ለጨዋታው ዝግጅቱን ሲያደርግ ቆይቷል። ብሔራዊ ቡድኑ መጀመሪያ ዝግጅቱን ሳዑዲ አረቢያ ላይ ካካሄደ በኋላ ቀሪውን የዝግጅት ጊዜ ወደ ደቡብ ሱዳን በማምራት አከናውኗል። ኢትዮጵያ እና ሱዳን በአፍሪካ እግር ኳስ ውስጥ ትልቅ የታሪክ አሻራ ያላቸው ሀገራት ናቸው። ሁለቱ ሀገራት እ.አ.አ በ1957 ለመጀመሪያ ጊዜ በሱዳን በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ተሳትፎ አድርገዋል። በዛው ዓመት የተመሰረተው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መስራች አባል ሀገራትም ነበሩ። እ.አ.አ በ1956 ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታ ተገናኝተው ኢትዮጵያ 2 ለ 1 አሸንፋለች። እ.አ.አ በ1959 በግብጽ አስተናጋጅነት በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ያደረጉት ጨዋታ ተገናኝተው ነበር። በወቅቱ ሱዳን 1 ለ 0 አሸንፋለች። ለ70 ዓመታት በዘለቀው የሁለቱ ሀገራት ፉክክር ውስጥ 41 ጊዜ በውድድርና በወዳጅነት ጨዋታዎች ተገናኝተዋል። በነዚህ ጨዋታዎች ሱዳን 16 ጊዜ ድል ሲቀናት ኢትዮጵያ በ14ቱ ጨዋታዎች አሸንፋለች። በቀሪ 11 ጨዋታዎች አቻ ተለያየተዋል። ኢትዮጵያ በነዚህ 41 ጨዋታዎች ላይ 59 ግቦችን ስታስቆጥር ሱዳን 57 ጎሎችን ከመረብ ላይ አሳርፋለች። ሁለቱ ሀገራት ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት እ.አ.አ በ2022 ነበር። በአበበ በቂላ ስታዲየም በተካሄደው የወዳጅነት ጨዋታ ሁለት አቻ ተለያይተዋል። በአፍሪካ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጣቸው ሀገራት የሚያደርጉት ጨዋታ ትኩረትን ስቧል። ኢትዮጵያ ሁለተኛ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዋን ማክሰኞ መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ.ም ከሴኔጋል ጋር ታደርጋለች። 36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ በ2027 በኬንያ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛንያ ጣምራ አዘጋጅነት ይካሄዳል። አህጉራዊው ውድድር ከሰኔ 12 እስከ ሐምሌ 10 ቀን 2019 ዓ.ም በሶስቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በሚገኙ ሰባት ስታዲየሞች ይካሄዳል። በውድድሩ ላይ 24 ሀገራት ይሳተፋሉ። ቀሪ ወደ አፍሪካ ዋንጫው የሚያልፉ 21 ሀገራት በማጣሪያ ጨዋታዎች ይለያሉ። በዚህም 48 ሀገራት በ12 ምድቦች ተከፍለው ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
አካባቢ ጥበቃ
በሐረሪ ክልል ለተፈጥሮ አደጋዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠት የሚያስችል የተሟላ ዝግጅት ተደርጓል
Sep 24, 2026 1128
ሀረር፤ መስከረም 14/2019 (ኢዜአ):- ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ለሚያጋጥሙ አደጋዎች ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል የተሟላ ዝግጅት መደረጉን የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ልማት ቢሮ ሃላፊ ሮዛ ኡመር ገለጹ። በአየር ንብረት መለዋወጥ ሳቢያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኤልኒኖ ክስተት ጋር የተያያዘ ችግር ስለመኖሩ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ሰሞኑን አመላክቷል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በዘንድሮው የበጋ ወቅት በደቡብና ደቡብ ምሥራቅ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተሻለ የዝናብ መጠን እንደሚኖር ይጠበቃል ብሏል፡፡ በአንጻሩ በመካከለኛውና በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍሎች አልፎ አልፎ ያልተጠበቀ ዝናብ ሊኖር ይችላል ሲልም አሳውቋል። በመሆኑም ለሚያጋጥሙ ችግሮች ፈጣን ምላሽ በመስጠት ረገድ በሐረሪ ክልል ያለውን ዝግጁነት በተመለከተ ኢዜአ የክልሉን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አነጋግሯል። የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ልማት ቢሮ ሃላፊ ሮዛ ኡመር፤ በማብራሪያቸው በክልሉ በአየር ንብረት ለውጥ ሊያጋጥም የሚችልን ችግር ለመቋቋም የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ስለመደረጉ ገልጸዋል። በራስ አቅም የተቀናጀ ቅድመ ዝግጅት ስራ ሲከናወን መቆየቱን በማስታወስ ለሚያጋጥሙ አደጋዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠት የሚያስችል የተሟላ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል። በክልሉ ለድርቅ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን ቀደም ብሎ በመለየት የመስኖና የከርሰ ምድር ውሃ በመጠቀም የማልማትና የምርት አማራጮችን የማስፋት ስራ መከናወኑን ገልጸዋል። በዚህም በቤተሰብ ደረጃ ጭምር በምግብ ራስን የመቻል ስኬት መኖሩን አንስተው የሌማት ትሩፋትና ሌሎችም ኢንሸቲቮች መሰረታዊ ለውጥ ያመጡ መሆኑንም ተናግረዋል። የምርትና ምርታማነት አቅምን በማሳደግ ከተረጅነት ለመላቀቅ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት መመዝገቡንም ተናግረዋል። በዚህም በተለይ የዝናብ እጥረት ሲያጋጥም ክስተቱን በራስ አቅም ለመቋቋም የሚያስችል አቅም እየተፈጠረ መሆኑን ጠቁመው ፈጥነው የሚደርሱ ምርጥ ዘሮች በመለየት የውሃ እጥረትን የሚቋቋሙ ሰብሎች በስፋት ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየተደረገ መሆኑን ለአብነት ጠቅሰዋል። በተጨማሪም የምርት ክምችት የማድረግና ድጋፍ የመስጠት እንዲሁም የከብት መኖ የማቅረብ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል። አሁን ላይም እየጣለ የሚገኘውን ዝናብ በማጠራቀም አርሶ አደሩ ባለው መሬት እንዲያለማ እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል። በቀጣይም የአየር ንብረትና ሁኔታ መረጃን ለአርሶ አደሩ የማድረስና የመስኖና የከርሰ ምድር ውሃ ሃብትን በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን የበለጠ የማሳደግ ስራዎች እንደሚጠናከሩ አስታውቀዋል።   የሐረሪ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ቢሮ ሃላፊ አቶ ኤልያስ መሀመድ በበኩላቸው የኤልኒኖ ክስተት በአንዳንድ አካባቢዎች ጉዳት እንዳያስከትልና አፋጣኝ ምላሽ መስጠት እንዲቻል የአደጋ መከላከልና ፈጣን ምላሽ ሰጪ ምክር ቤት መቋቋሙን ተናግረዋል። በዚህም ችግሩ የታየባቸውን አካባቢዎች የመለየትና ምርጥ ዘር በማከፋፈል ወደ ምርት እንዲገቡ መደረጉን ጠቅሰዋል። በተለይም የምግብ እጥረት እንዳይከሰት በራስ አቅም መቋቋም የሚያስችል የምርት ክምችት የማድረግ ስራም መከናወኑን ገልጸዋል።
አረንጓዴ ዓሻራ፡ የመደመር እሳቤ አብነት
Sep 24, 2026 158
በሀገራችን አንዱ የማድረግ ዐቅም ማሳያ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ነው።የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በዓለም በስፋት እየተስተዋለ ካለው የአየር ንብረት ግብዝነት (Greenwashing) ፍጹም ተቃራኒ በሆነ መንገድ ከንግግር ተግባርን ያስቀደመ መርሐ ግብር ዓላማው የደን ሽፋንን ማሳደግና የደን መጨፍጨፍ፣ የመሬት መራቆትና የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮችን መፍታት የሆነው የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር፤ የአካባቢ መራቆትና የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶችን ተጨባጭ በሆኑ ተግባራት ለመፍታት መሰጠ ሰፊና የላቀ ውጤት የተመዘገበበት ተግባራዊ ጥረት ነው። እንዲህ ያለው ትልቅ ፕሮጀክት በፌዴራል፣ በክልልና በአካባቢ ደረጃና ልዩ የሆነ የአመራር ቁርጠኝነትና ቅንጅትን ይፈልጋል። ይህ የአመራር ጥበብና ቅንጅት የተለያዩ ማኅረሰቦችን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ የንግድ ተቋማትና ዓለም አቀፍ አጋሮችን ያሳተፈ አካታች መርሐ ግብር ነው። የአረንጓዴ ዐሻራ ፕሮግራም የጋራ የኃላፊነት ስሜትን በማጎልበት፣ ተነሣሽነቱ ከዛፍ ተከላ በላይ ሆኖ ወደ ሀገራዊ ንቅናቄ አድጓል። የተለያዩ ቡድኖች ለጋራ ዓላማ ተባብረው እንዲሠሩ አስችሏል። የማስፈጸም ሂደቱ ዛፍ በመትከል ላይ ብቻ ያተኮረ አልነበረም። ሁሉንም ማኅበረሰብ ያሳተፈ ነበር። አካሄዱም ሊላካ የሚችል ከባቢያዊ ጥቅም የሚያስገኝ እንቅስቃሴ መፍጠር ነበር። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ስኬት ሀገራዊ ኩራትና ጽናት እንዲጎለብት አስችሏል። አጣዳፊ ሀገራዊና ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በመደመር ስሌት ጠንካራ የአፈጻጸም ጥበብ ያለውን ዐቅምም አሳይቷል። የመደመር መንግሥት ገጽ 127 እና 128
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ትልቅ አቅም እየሆነ ነው 
Sep 24, 2026 165
ሀዋሳ፤ መስከረም 14/2019 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ በመቋቋም ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ትልቅ አቅም እየሆነ መምጣቱን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ምሁራን ገለጹ። በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ የዘርፉ ተመራማሪዎች ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ልማት የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ በመቋቋም ዘላቂ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እያስቻለ ነው። ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን ለመንከባከብ የተሰጠው ሀገራዊ ትኩረት ሁለንተናዊ ዕድገትን ለማፋጠን ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑንም አመልክተዋል። በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ፀጋዬ በቀለ እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የአረንጓዴ አሻራ ልማት ንቅናቄን በመፍጠር መላውን ማህበረሰብ በማሳተፍ የተከናወነው ተግባር በዘርፉ አስደናቂ ውጤት አስመዝግቧል። በሀገር አቀፍ ደረጃ ችግኝን የመትከልና የመንከባከብ ባህል እያደገ በመምጣቱ ዘርፍን የተሻለ ውጤት እንዲታይበት አድርጓል ብለዋል። ይህም ተፈጥሮን በመጠበቅ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ችግር በመቋቋም የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የጎላ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ፕሮፌሰር ፀጋዬ ተናግረዋል። መርሃ ግብሩ የመሬት ለምነትና የውሃ አቅም በማሻሻል የግብርና ምርትና ምርታማነት ለመጨመር ማስቻሉንም ተናግረዋል። ንብ ማነብን ጨምሮ አዳዲስ የስራ ዘርፎች በስፋት እንዲፈጠሩ በማድረግ የዜጎች ተጠቃሚነት እንዲጎለብት ማስቻሉንም ጠቁመዋል። የኮሌጁ ዲን ተሻለ ወልደአማኑኤል (ዶ/ር) በበኩላቸው እንዳሉት፤ ባለፉት ዓመታት የተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ ልማት አመርቂ ውጤቶች እያስገኘ ነው።   ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት የምታከናውነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለአፍሪካም ሆነ ለዓለም ትልቅ አርአያ መሆኑን ተናግረዋል። የስነ-ምህዳር እና ብዝሃ ህይወት በዘላቂነት እንዲጠበቅ በማድረግ ረገድ መርሃ ግብሩ የማይተካ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ኮሌጁ ከሀገሪቱ መልክአ ምድርና ስነምህዳር ጋር የሚስማሙ ችግኞችን በምርምር በማውጣት እንዲሁም በማፍላትና በማሰራጨት መርሃ ግብሩን በመደገፍ የሚጠበቅበትን ሀላፊነት እየተወጣ መሆኑን ጠቅሰዋል። ኮሌጁ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ ልማት ልምድ ወደ ሌሎች ሀገራት እንዲስፋፋ በጥናት የተደገፉ ሰነዶች በማዘጋጀት የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተሻለ (ዶ/ር) አስታውቀዋል።
በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብና እርጥበት ይኖራል
Sep 22, 2026 245
አዲስ አበባ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ)፦በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብና እርጥበት እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፤ በሚቀጥሉት ቀናት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ አብዛኛዎቹ ቦታዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው የአፈር ውስጥ እርጥበት ይኖራል። በተመሳሳይ በሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ቀላል መጠን ያለው እርጥበት እንደሚኖርና በክረምት ዝናብ ተጠቃሚ ተፋሰሶች ላይ ደግሞ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው የገጽ ምድር የውኃ ፍሰት እንደሚኖር መግለጫው ጠቅሷል። ምዕራብ ወለጋ፣ ኢሉባቦር፣ አርሲ፣ አብዛኞቹ የሸዋ ዞኖች፣ የምዕራብ፣ መካከለኛ፣ ደቡብ እና ሰሜን ጎንደር፣ የሰሜን፣ የምዕራብ እና የምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ማኦ ኮሞ፣ ምዕራብ ኦሞ እና አሶሳ ከመካከለኛ እስከ ከባድ እርጥበት የሚያገኙ አካባቢዎች መሆናቸውን አስታውቋል፡፡ በተጨማሪም ምስራቅ እና ምዕራብ ሀረርጌ፣ ደቡብ እና ሰሜን ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ትግራይ፣ የሲዳማ ሁሉም ዞኖች እና የወላይታ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ እርጥበት የሚያገኙ አካባቢዎች መሆናቸውን ጠቅሷል፡፡ ይህ የአየር ሁኔታ የአፈር እርጥበትን ለማሻሻል፣ ለረጅም እና መካከለኛ ጊዜ ሰብሎች እድገት እንዲሁም ዘግይተው ተዘርተው በተለያየ የእድገት ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሰብሎች ፍሬያማነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለውም አስታውቋል፡፡ በተጨማሪም ለቋሚ ተክሎች ልምላሜ፣ ለእንስሳት መኖና ለመጠጥ ውኃ አቅርቦት መጎልበት እንዲሁም የዝናብ ውኃን አሰባስቦ ለማስቀረት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብሏል። የመኸር ሰብል አብቃይ አከባቢዊች አርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች ምርታማነትን ለመጨመር የሰብል በሽታና አረምን አስቀድመው እንዲከላከሉ፤ ፀረ-አረምና ፀረ-ተባይ ኬሚካሎችንም የግብርና ባለሙያዎችን በማማከር ብቻ እንዲጠቀሙ አሳስቧል። የውኃ ትነትን ለመቀነስ የሚያስችሉ የግብርና ስራዎችን ማከናወን፣ የሚገኘውን እርጥበት በአግባቡ ለልማት ማዋል፣ ለእንስሳት ግጦሽ ሳርን በተቆጠበ መንገድ መጠቀም እና የዝናብ ውኃን አጠናክሮ ማከማቸት እንደሚገባ መክሯል።    
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካ ህብረት እና ተመድ ያላቸውን የጋራ ውጥኖች በቁርጠኝነት ለመተግበር እንደሚሰሩ ገለጹ  
Sep 21, 2026 579
አዲስ አበባ፤ መስከረም 10/2019 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ ኢኮኖሚና ፍትሃዊ ዓለምን ለማስፈን በጋራ እያከናወኑ የሚገኘውን ስራ ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከመስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም አንስቶ በኒው ዮርክ እየተካሄደ ይገኛል። “መተማመንን ዳግም መገንባት እና አዳዲስ ለውጦችን በአግባቡ መምራት፣ ለሁሉም የሚሰራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን መፍጠር” የጉባኤው መሪ ሀሳብ ነው። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በጉባኤው ላይ ለመታደም ኒው ዮርክ ይገኛሉ። ከጠቅላላ ጉባኤው ጎን ለጎን ስትራቴጂካዊ ትብብር ማጎልበት፣ የሰላምና ደህንነት ማዕቀፎችን ማጠናከርና አፍሪካን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ሪፎርሞች ላይ ያተኮረ ከፍተኛ የምክክር መድረክ ተካሄዷል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ መድረኩን በጋራ መርተውታል። ስብስባው ሁለቱ ተቋማት አፍሪካ መዋቅራዊ ፈተናዎችን ለመፍታት እያደረገች ያለቻቸውን ጥረቶች ለመደገፍና ፍትሃዊ የዓለም ስርዓትን ለመፍጠር ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ይበልጥ ያረጋገጠ መሆኑን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። የዓለም አቀፍ የፋይናንስ አወቃቀርን ማሻሻል፣ ዘላቂ የእዳ አስተዳደር እና የአፍሪካ ሀገራት ከቁልፍ የማዕድን ሀብቶች ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ ውይይት ከተደረገባቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ሁለቱ ወገኖች በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ህብረት እና የተመድን ትብብር ያለውን ስትራቴጂካዊ ፋይዳ አጽንኦት ሰጥተዋል። የተቋማቱ ሶስት ነባር የትብብር ማዕቀፎች በአዲስ መልክ ለማደስ እና እ.አ.አ በ2026 ትግበራው የሚጠናቀቀውን የጋራ ፍኖተ ካርታ የተፈጻሚነት ገደብ ለማራዘም መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ያሉ የሰላም እና የደህንነት ተግዳሮቶችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የአፍሪካ ህብረት ቁልፍ አጋር ሆኖ እንደሚቀጥል ዳግም አረጋግጧል። የአፍሪካን የሰላምና ደህንነት መዋቅር ማጠናከር፣ ግጭትን አስቀድሞ የመከላከል ዲፕሎማሲና የእርቅ ሂደትን በሚገባ መተግበርና ለአፍሪካ ፈተናዎች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ማረጋገጥ የሚያስችል በቂ አቅም መገንባት እንደሚያስፈልግ በስብሰባው ላይ ተነስቷል። በውይይቱ በሳሄል ቀጠና፣ በሊቢያ፣ በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያሉ ወቅታዊ ጉዳዮችና የሰላም ጥረቶች ተገምግመዋል። በስብስባው ላይ ግጭቶች፣ በዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ የተፈጠሩ መስተጓጎሎች እና የባህር በር መስመሮችን መዝጋትን ጨምሮ ሌሎች ውጫዊ ሁኔታዎች በአፍሪካ ኢኮኖሚ እና ምግብ ዋስትና ላይ ተጨማሪ ጫና እየፈጠሩ መሆኑ ተነስቷል። የአየር ንብረት ለውጥ እያደረሰ ያለው ጉዳትም ምክክር ተደርጎበታል። ሁለቱ ወገኖች በውይይቶች ጠንካራ የጋራ ግብረ መልስ መስጫ ማዕቀፍ ለመፍጠር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። የአፍሪካ ህብረት እና ተመድ ፍኖተ ካርታ ዝግጅን ለማጠናቀቅ፣ በአፍሪካ ሀገራት የሰላም ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር፣ የምግብ ዋስትና ተግዳሮቶችን ለመፍታትና ለድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ የአሰራር ማዕቀፎችን ለመቅረጽ በቅርበት እንደሚሰሩ መግለጻቸውን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ እስከ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።
በቀጣናው ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመፍታት የሀገራት የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው - ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)
Sep 15, 2026 847
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ)፦ በቀጣናው እያጋጠሙ የሚገኙ ፈተናዎች በዘላቂነት እንዲፈቱ የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት 74ኛው አስቸኳይ ስብሰባውን ዛሬ በጅቡቲ አካሂዷል። በስብሰባው ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮች ተሳትፈዋል። በቀጣናው ሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም በሌሎች አበይት ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በቀጣናው እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመቋቋም የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው።   በኢጋድ ሴክሬታሪያት በኩል የተከናወኑ የልማትና የሰላም ሥራዎች አበረታች ውጤቶችን እያስገኙ መሆናቸውን በመግለጽ፣ ተቋሙ ለቀጣናው ህዝቦች ብልጽግና መረጋገጥ የጸና አቋም እንዳለው አመልክተዋል። ምንም እንኳን የተለያዩ ጂኦፖለቲካዊ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ የኢጋድ ሴክሬታሪያት ያለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸም አበረታች የሚባል መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣናዊ መሠረተ ልማት እና የጤና ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን ያነሱት ዋና ፀሐፊው፤ የቀጣናው የከርሰ ምድር ውሃ መረጃ ሥርዓት የአገልግሎት ተደራሽነት የላቀ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቁመዋል። እንዲሁም የቀጣናው ዓለም አቀፍ የጤና ሽፋን መረጃ ጠቋሚ (ኢንዴክስ) ከ60 ወደ 65 በመቶ ከፍ ማለቱንና ይህም እ.አ.አ በ2027 70 በመቶ ለማድረስ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት የሚያስችል መሆኑን ነው ያነሱት። በሌላ በኩል ሱዳን ወደ ኢጋድ ሙሉ አባልነቷ መመለሷ የቀጣናውን ትብብርና አንድነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል። ዋና ፀሐፊው እ.አ.አ ጁላይ 2026 ወደ ሱዳን ባቀኑበት ወቅት የኢጋድ የሱዳን ልዑክ ቢሮ በድጋሚ በይፋ መከፈቱን አስታውሰው ይህ እርምጃ ከቀጣናው ሕዝቦች ጋር ያለውን ቀጥተኛና ዘላቂ ትስስር አጠናክሮ የሚያስቀጥል መሆኑን አመላክተዋል። ኢጋድ ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች እና ከሌሎች ስትራቴጂካዊ አጋሮች ጋር ያለው ግንኙነት ለቀጣናው ዘላቂ ልማት ወሳኝ ነው ብለዋል። አጋርነቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን አቅም በማጠናከር ረገድ የጎላ ድርሻ እንደሚያበረክትም ነው ያነሱት። በቀጣይ ሊከሰቱ የሚችሉ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋዎችን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን በማጠናከር ለመቋቋም የሚያስችሉ አሰራሮች እየተቀረፁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ሀገራት የኤልኒኖ (El Niño) የአየር ንብረት መዛባት የሚያስከትለውን ስጋት ለመቀነስ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል። በሌላ በኩል ቀጣናውን ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር ለማስተሳሰርና በቴክኖሎጂ የታገዘ የልማት መሠረት ለመጣል የተጀመሩ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ገልጸዋል። ስብሰባው የቀጣናውን ሰላም፣ ደህንነት እና ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠን በሚያስችሉ ሀገራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በመምከርና ውሳኔዎችን በማሳለፍ መጠናቀቁን ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የኢጋድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ከተቋሙ ቁልፍ የፖሊሲ አደረጃጀቶች መካከል አንዱ ሲሆን፣ የድርጅቱን ሥራዎች በመምራትና በአባል ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር ረገድ ጉልህ ሚና የሚጫወት ነው።
አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ ይልቁንም የሚገባትን ስፍራ በባለቤትነት እየያዘች ነው
Sep 9, 2026 733
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ):- አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ የሚገባትን ስፍራ እና ክብር በራሷ እያረጋገጠች ነው ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ህብረት ቀን ዛሬ እየተከበረ ይገኛል። የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ቀኑን በማስመልከት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ሊቀ መንበሩ የአፍሪካ ህብረት ቀን እ.አ.አ በ1999 የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ለመተካት ይፋዊ ውሳኔ የተላለፈበት የሰርጥ ድንጋጌ (Sirte Declaration) የሚታወስበት እንደሆነ ገልጸዋል። በዚያን ወቅት የአፍሪካ መሪዎች አህጉራዊ ትስስርን ለማፋጠን እና የአፍሪካን ድምጽ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ለማድረግ የአፍሪካ ህብረትን ለመመስረት ወሳኝ እና ታሪካዊ እርምጃ የወሰዱበት ምዕራፍ ነው ብለዋል። የዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት ቀን ለአህጉሪቱ እጅግ ልዩ ትርጉም ባለው ወቅት ላይ እየተከበረ እንደሚገኝ አውስተዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን እውነተኛ ቁመና እና ትክክለኛ መጠን የሚያሳይ የዓለም ካርታ አጠቃቀምን የሚደግፍ፣ በአፍሪካ መሪነት የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል። በቶጎ ሃሳብ አመንጪነትና በአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እውን የሆነው ይህ እርምጃ ከቀላል የካርታ ማስተካከያ በላይ ትርጉም አለው ብለዋል ሊቀ መንበሩ። አፍሪካ በዓለም ፊት እንዴት እንደምትታይ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን እና አፍሪካ ራሷን የምትገመግምበትንና የምታሳይበትን ትርክት ራሷ መቅረጽ እንዳለባት አበክሮ የሚያስታውስ ነው። ይህ ውሳኔ አፍሪካ በዓለም ፊት በምን መልኩ መታየት እንዳለባት ከማሳየቱም በላይ፤ አፍሪካ ራሷን የምትመዝንበትንና እውነታዋን ለዓለም የምታሳይበትን ትርክት በራሷ መቅረጽ እንዳለባት በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን ነው ያነሱት። የአፍሪካ እጣ ፈንታ የሚወሰነው በአፍሪካውያን የራሳቸው እይታ ነው። አፍሪካን በእውነተኛ ቁመናዋ፣ኃይሏ እና አቅሟ የምንመለከትበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር አያይዘውም ካርታውን የማስተካከል እርምጃ አፍሪካ ወደ ላቀ የጋራ ራዕይ የምታደርገው አህጉራዊ ጉዞ አካል መሆኑን አንስተዋል። ይህም በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) አማካኝነት የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከርን፣ ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥን፣ ዘላቂ ልማትን እውን ማድረግን እና በዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪ አካላት ውስጥ የአፍሪካን ተሳትፎ ማሳደግን እንደሚያካትት በዝርዝር አስረድተዋል። የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የተሳሰረች፣ የበለጸገች እና ሰላማዊት አፍሪካን ለመገንባት የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ ትስስርን በማፋጠን እና የአፍሪካን ዓለም አቀፍ ተሰሚነት መጨመር የአፍሪካ ህብረት ቀዳሚ ትኩረቶች ናቸው ብለዋል። አፍሪካ በዓለም ፊት እውቅና ለማግኘት አትለምንም፤ ይልቁንስ በዓለም አቀፍ መድረክ የሷ የሆነውን ትክክለኛ ስፍራ በራሷ ባለቤትነት እየያዘች ነው። አሁን የሚጠበቅብን ይህንን ጠንካራ እምነት ወደ ህብረት፣ ሀብትና ብልጽግና፣ ሰላም እና ተደማጭነት መለወጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሊቀመንበሩ አፍሪካ የምታስመዘግበው እድገት በዓለም አቀፍ መድረኮች በሚኖራት ውክልና ብቻ ሳይሆን፣ በዜጎቿ ላይ የኑሮ ጥራት መሻሻል ጭምር መለካት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። በዚህም መሰረት የአፍሪካ ህብረት የ2026 ዓመት ትኩረቱን በዘላቂ የንጹህ ውሃ አቅርቦት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አገልግሎት ላይ ማድረጉ፣ ህብረቱ አህጉራዊ ራዕዮችን ከዕለት ተዕለት የዜጎች ህይወት ጋር ለማያያዝ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ አመልክተዋል። በአፍሪካ ህብረት ቀን አከባበር አባል ሀገራት፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ የአፍሪካ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ሴቶች እና ወጣቶች ተባብረው ይበልጥ የተሳሰረች፣ በራሷ አቅም የምትተማመን እና የራሷን እጣ ፈንታ በራሷ መወሰን የምትችል አፍሪካን እንዲገነቡ ሊቀመንበሩ ጥሪ አቅርበዋል። የምንፈልጋት አፍሪካ የሚለውን አህጉራዊ ራዕይ እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ እና የሰርት ድንጋጌ ለቀጣዩ የአፍሪካ ትውልድ ዘላቂ የትምህርት እና የዕድገት መሰረት ሆኖ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የነገዋ አፍሪካ በካርታ ላይ ብቻ የተሻለ ውክልና ያላት ብቻ ሳትሆን፤ በዓለም አቀፍ መድረክ ሉዓላዊነቷ የጸና፣ ጠንካራ ውስጣዊ አንድነት ያላት፣ ለህዝቦቿም ዘላቂ ብልጽግናን የምታጎናጽፍ አህጉር መሆን ይኖርባታል ነው ያሉት። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ለመላው አፍሪካውያን እና በውጭ ሀገር ለሚገኙ የአፍሪካ ዳያስፖራዎች ሰላማዊ እና የትብብር መንፈስ የተሞላበት የአፍሪካ ህብረት ቀን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Sep 4, 2026 924
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን እና ሁሉን አቀፍ ትብብራቸውን የበለጠ ለማላቅ እንደሚሰሩ አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ውይይቱ በአፍሪካ ህብረትና አሜሪካ መካከል ያለውን ለረጅም ጊዜ የቆየ አጋርነት ማጠናከር እና በአህጉሪቱ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የአፍሪካና አሜሪካን ትብብር ታሪካዊ መሆኑን አውስተው በህብረቱ፣ በአባል ሀገራት እና በአሜሪካ መካከል የሁለቱንም ወገኖች ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ጠንካራ አጋርነት መገንባት እንደሚገባ አሳስበዋል። በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሱዳን እየተደረጉ ላሉ አፍሪካ መር የሰላም ጥረቶች አሜሪካ እያደረገች ላለው ገንቢ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ በበኩላቸው አፍሪካ አሜሪካ ቀዳሚ ትኩረት የምትሰጣት አህጉር እንደሆነች ገልጸዋል። የጋራ ፍላጎቶችንና ግቦችን ከህብረቱ ኮሚሽንና ከአባል ሀገራት ጋር በመሆን ለማሳካት ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በዲፕሎማሲ፣ እንዲሁም በሰላምና ጸጥታ ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል። በውይይቱ ላይ በሱዳን ጉዳይ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የሰብአዊ እርዳታ ያለ ገደብ እንዲገባ እና በሲቪሎች የሚመራ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመር አጽንዖት ተሰጥቷል። በአፍሪካ ባለቤትነት የሚመሩ የሰላም ጥረቶች እና አሜሪካ የምትደግፋቸው የሰላም ሂደቶች በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር ከስምምነት ላይ ተደርሷል። በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት እና በሰላም መስኮች የሁለቱን ወገኖች ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ የትብብር መስኮች ተገምግመዋል። ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ህብረትና በአሜሪካ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ውስጥ የተደረጉ ስምምነቶችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። በሊቢያ ጉዳይ ዘላቂ የፖለቲካ መፍትሄ ማግኘት እንደሚያስፈልግም ተነስቷል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር እና ረዳት ሚኒስትሩ የሁለቱን ወገኖች ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና የትብብር አድማሱን ለማስፋት የጋራ ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሐተታዎች
ቡና እና ሰላም አትጡ!
Sep 25, 2026 98
ጅማ፣ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ)፡-ቡና እና ሰላም አትጡ! - "Bunaaf nagaa hindhabinaa" ስለ ጅማ ሲነሳ ቡና እና ሰላም ሁልጊዜም አብረው የሚጠሩ ህያው እሴቶች ናቸው። በምናብ ለሚያስባትም ሆነ ደርሶ የተመለከታት ሁሉ እንደሚያረጋግጠው፣ ጅማ የመዓዛማው ቡናዋ መፍለቂያ ብቻ ሳትሆን፤ የአረንጓዴ ተፈጥሮዋን ውበትና የሰላሟን ሙቀት ለእንግዶቿ የምታድል ልዩ ከተማ ናት። የጅማ ከተማ ታሪካዊ እሴቷን ጠብቃ ወደፊት በሚያራምዳት የልማት ጉዞ ላይ ትገኛለች። ከተማዋ በየዕለቱ አዲስ ገጽታ በመላበስ ላይ ስትሆን፣ ሰፊ የከተማ ገጽታዋ፣ ንጹሕ አየሯና አረንጓዴ ውበቷ የሚያልፉ እንግዶችን ሁሉ በልዩ ሁኔታ በመሳብ ላይ ይገኛሉ። ዛሬ ጅማ ይበልጥ ማራኪና ውብ እየሆነች መጥታለች። ታሪካዊ ቅርሷንና ማንነቷን እንደጠበቀች ወደ አዲስ ምዕራፍ እየተሸጋገረች የምትገኘው ይህች ከተማ፤ እውነትም ጅማ ሆናለች።   የኮሪደር ልማት ለጅማ ከተማ አዲስ ህይወትና ማራኪ ውበት ሰጥቷታል። በአረንጓዴ ስፍራዎቿና በንጹህ አየሯ ጎብኚዎችን በመሳብ ላይ የምትገኘው ይህች ከተማ፣ በልማቱ አማካኝነት ለበርካታ ወጣቶች የኑሮ መሠረት የሚሆን የሥራ ዕድል ፈጥራለች። የተቀየሩት ጎዳናዎቿና በዙሪያቸው የደማመቁት የንግድ እንቅስቃሴዎቿ ደግሞ ጅማን ወደፊት የመራመድ ጉዞ ቁልጭ አድርገው ያሳያሉ። በጅማ እየተከናወነ ያለው የዘመናዊ መንገዶች ግንባታ ለከተማዋ አዲስ ህይወት ከመስጠቱም በላይ፣ የማኅበረሰቡን የቆየ የመሠረተ ልማት ጥያቄ በመመለስ የኑሮ ዘይቤን እያቀለለ ይገኛል። ይህ የተሻሻለ የመንገድ ዝርጋታ ከተማዋን ምቹና ተደራሽ በማድረግ የባለሃብቶችን ትኩረት በመሳብ ላይ ሲሆን፣ ጅማንም የክልሉ የኢንቨስትመንትና የንግድ ማዕከል የማድረግ ራዕይን እውን እያደረገ ነው። አዌቱ ወንዝ ዛሬ የጅማ ከተማ አዲስ የውበትና የሰላም ማዕከል ሆኗል። ከተማዋን የበለጠ ማራኪ ያደረገው ይህ የወንዝ ዳርቻ ልማት፣ ቀደም ሲል ማኅበረሰቡን ስጋት ላይ ይጥል የነበረውን የጎርፍ አደጋ በማስቀረት የነዋሪዎችን ስጋት አስወግዷል። ይህም የከተማ ልማት ውበትን ከማስፈን ባለፈ የሕዝብን ደኅንነትና ምቾት የታደገ ተግባራዊ አርአያነቱን አረጋግጧል።   የታሪክና የባህል ማዕከል የሆነችው ጅማ፤ በቡና መዓዛዋ ብቻ ሳይሆን በድንቅ የእንጨት ቅርጻ ቅርጽ ጥበቧም የብዙዎች ትኩረት ስባለች። የዚህች ውብ ከተማ እንግዳ የሆነ ሁሉ ተፈጥሯዊ ውበቷን ብቻ አይቶ አይመለስም፤ የጅማን መዓዛማ ቡና ቀምሶ፣ የጥበብ ባለሙያዎችን እጅ ሥራ የሆኑ ውብ የእንጨት ቅርጾችን በመታሰቢያነት በመያዝ የከተማዋን ሕያው ታሪክ ይዞ ይጓዛል። የታሪክና የተፈጥሮ ውህደት ማሳያ የሆነችው ጅማ፤ የንጉሥ አባ ጅፋር ቤተመንግሥት እድሳትና የቦዬ ሐይቅ ልማት ተደምረው አዲስ የቱሪዝም ምዕራፍ ከፍተውላታል። በቦዬ ሐይቅ ዙሪያ የተከናወነው አስደናቂ ለውጥ የአካባቢውን የተፈጥሮ ህይወት ያላቀ ሲሆን፣ ለአካባቢው ነዋሪዎችና ለከተማዋ እንግዶች ተመራጭና ጥሩ ትዝታ የሚያስቀር የመዝናኛ መዳረሻ ሆኗል። ጅማ ታሪኳንና ማንነቷን ጠብቃ በከፍተኛ ፍጥነት በመልማት፣ በመገንባትና በማደግ ላይ ትገኛለች። ከተማዋ የቀድሞውን ታሪካዊ ትውስታ ከአዲሱ የከተማ ገጽታ ጋር በማዋሃድ፣ በታሪክና በዘመናዊነት መካከል ጥንካሬ ያለው አዲስ ድልድይ በመገንባት ላይ ናት።   ከዚህ ባሻገር ጅማ ማራኪ የኮንፈረንስ ማዕከል እየሆነችም መጥታለች። ትልልቅ ሆቴሎች ተገንብተዋል፤ የተለያዩ ትልልቅ ሁነቶችንም እያስተናገደች ትገኛለች። ይህም ከተማዋን ለጎብኚዎች፣ ለቢዝነስ ሰዎችና ለተለያዩ ተቋማት ሳቢ መዳረሻ እያደረጋት ነው። ዛሬ ጅማ በዓመት ከ300 ሺህ በላይ ዜጎች የሚጎበኟት ከተማ ሆናለች። የሚመጡትም የከተማዋን ውበት ለማየት ብቻ ሳይሆን፣ ታሪኳን ለመዳሰስ፣ ቡናዋን ለመቅመስ፣ ተፈጥሯዊ ጸጋዋን ለመለማመድና የጅማን ልዩ ማንነት ለመረዳት ነው።   ጅማ ታሪኳን ጠብቃ፣ ውበቷን አስጠብቃ ወደፊት እየተራመደች ነው። አረንጓዴው ውበቷ፣ የአዌቱ ወንዝ ፍሰት፣ የቦዬ ሐይቅ ገጽታ፣ የአባ ጅፋር ቤተ መንግስትና ታሪክ እንዲሁም የቡና ሽታዋ ተደምረው ለከተማዋ የራሷን ልዩ ቀለም ሰጥተዋታል። ቡናዋን ጠጥቶ ሰላሟን ያየ እንግዳም የጅማን ትዝታ ይዞ ይመለሳል። ኑ ቡና ጠጡ የሚለውን የጅማዎች የቆየ ግብዣ ተከትሎ "Bunaaf nagaa hindhabinaa" - ቡና እና ሰላም አትጡም ከጅማዎችና እንግዶቿ አፍ ስምም ፈጥሮ ይኖራል።    
የባሌ ተራሮች እውነታ
Sep 24, 2026 351
በኢትዮጵያ ከሚገኙ ውብ እና አስደናቂ የተፈጥሮ መስህቦች መካከል የባሌ አካባቢ ልዩ ስፍራ የሚሰጠው ነው። የባሌ የተፈጥሮ ሀብት ከማራኪ መልክዓ ምድር ባለፈ የብርቅዬ እንስሳትና አእዋፋት መገኛም መሆኑ ይታወቃል። ከሰማይ ጠቀስ ተራሮቹ እስከ ጥቁር አንበሳ መኖሪያው የሃረና ደን፣ ከገዳ ስርዓት የጥበቃ እሴት እስከ ካርቦን ንግድ ተጠቃሚነቱ ባሌ በተፈጥሮ የታደለ እውነተኛ ድንቅ ምድር ነው፤ በአንድ አባባል፡ 'ባሌ፡ አንድ ፓርክ፣ የብዙ ዓለማት መገኛ! (Bale: One Park Many Worlds) እየተባለ የሚጠራው። የባሌ መልክዓ-ምድር የተፈጥሮ ድንቅ ጥበብ ማሳያ ነው፤ የበርካታ ወንዞች ምንጭ፣ የጥቅጥቅ ደኖችና የአረንጓዴ ምድር ነፃብራቅ። ከባህር ጠለል በላይ ሰማይን በሚነኩ ግዙፍ ተራሮቹ፣ ሰፋፊ አምባዎቹና ውብ ሸለቆቹ የታጀበው ይህ አስደናቂ ስፍራ፣ በተፈጥሮ ለጋስነት ከተጎናፀፋቸው እምቅ የውሃ ሀብቶች ጋር ተደምሮ እውነተኛ የምድር ላይ ገነት ያደርገዋል።   የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ከ2 ሺህ 150 ካሬ ኪሎ ሜትር በላይ ስፋት ያለው ሲሆን በከፍተኛ ቦታዎች ላይ የተለያዩ የዕፅዋት ዝርያዎችን የያዘ እምቅ የደን ሀብትም አለው። መልክዓ ምድራዊ አቀማመጡም ሲታይ ከባህር ጠለል በላይ ዝቅተኛው 1 ሺህ 500 ሜትር እንዲሁም ከፍተኛው ጫፍ የቱሉ ዲምቱ ተራራ በ4 ሺህ 377 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ። በፓርኩ ከ260 በላይ የአእዋፍ ዝርያዎች እና ልዩ ልዩ ብርቅዬ የዱር አንስሳት የሚገኙ መሆኑም ይታወቃል። በዚህም ድንቅ ተፈጥሯዊና ብዝሃ-ሕይወታዊ ሀብቱ ምክንያት፣ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በዩኔስኮ የዓለም የተፈጥሮ ቅርስ ሆኖ በቋሚነት መመዝገቡ ይታወቃል። በባሌ ተጠቃሽ ከሆኑት የቱሪስት መዳረሻዎች መካከል ከ4 ሺህ ሜትር በላይ ከፍታ ላይ የሚገኘው በረዷማው የሳነቴ አምባ ይጠቀሳል። በዚህ አስደናቂ የተፈጥሮ እይታ ባለው አካባቢ ብርቅዬ የሆኑ ቀይ ቀበሮዎችን በቀላሉ ማየት ይቻላል።   የሃረና ጥቅጥቅ ደን ደግሞ ከሳነቴ አምባ በስተደቡብ በኩል የሚወርድ ሰፊና እርጥበታማ አካባቢ ሲሆን በዛፎች የተሞላ፣ በርካታ የዱር እንስሳት የሚገኙበት እንዲሁም ኩልል ያሉ አስደናቂ ፏፏቴዎች የሚገኙበት ነው። የሀገራችን ጋሻና መከታ የሆነው የጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ተምሳሌት የሆነው ብርቅዬው ጥቁር አንበሳ፣ በዚህ አስደናቂ የሃረና ተፈጥሮ ደን ውስጥ ይገኛል። የአካባቢው ማህበረሰብ ከገዳ ስርዓት በወረሰው ድንቅ ባህላዊ እሴትና ተፈጥሮን የመንከባከብ እውቀቱ ደኑን ጠብቆ በማቆየቱ፣ ከስነ-ምህዳሩ ከሚያገኘው በርካታ አገልግሎት ባሻገር፣ ዛሬ ላይ በአሳታፊ የደን አስተዳደር አማካኝነት ከካርቦን ሽያጭ ቀጥተኛ ተጠቃሚ መሆን ችሏል።   ለተራራ ላይ የእግር ጉዞ አፍቃሪ ጎብኚዎች ደግሞ የቱሉ ዲምቱ ተራራ ከነ ግርማ ሞገሱ የሚጠብቃቸው ይሆናል። ብርቅዬው ቀይ ቀበሮ ዋነኛ ምግቡ የሆነውን ፍልፈል የዓይጥ ዝርያ በቀስታ ሲያድንና ዘሎ በሹል አፉ ሲይዝ ማየት ለናፈቀው ጎብኚም ሳነቴ ተመራጩ ቦታ ነው። ባለ ክራቫቱ የደጋ አጋዘን ከእነግርማሞገሱ ቆሞ ፊትለፊት የሚታየው ደግሞ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ አካል በሆነው ዲንሾ ጫካ ውስጥ ነው። የባሌ እና አካባቢው መልክዓ ምድር በአብዛኛው የሁለት ጊዜ የዝናብ ወቅት በመሆኑ ይህም ለምለምና አረንጓዴ እንዲሆን አድርጎታል። ከጎኑ እየታረሰ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የደረሰ ሰብል የሚሰበሰብበት ባሌ ለስንዴና ለቢራ ገብስ ልማት እጅግ ተመራጭና ተስማሚ የአየር ጠባይ እንዲሁም የመልክዓ-ምድር አቀማመጥ ያለው ምድር ነው። የእነዚህ ሁሉ ድምር ውጤቶች ባሌን እና የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክን ተመራጭና ተወዳጅ የቱሪስት መዳረሻ ያደርገዋል። በቅርብ ዓመታት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች ባሌ ያለውን የተፈጥሮና የቱሪዝም አቅም ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ጥቅም ለመለወጥ እያስቻለ ይገኛል። ወደ ቱሪስት መዳረሻዎች የሚወስዱ የመንገድ ግንባታዎች፣ የኤሌክትሪክ እና የቴሌኮም መሰረተ ልማት ዝርጋታዎች በስፋት በመከናወን ላይ ይገኛሉ። ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት የሎጅ ግንባታዎች፣ የዕደ-ጥበብ ስራዎች ማስተዋወቅ እና እንግድነትን መሰረት ያደረጉ የኢኮ-ቱሪዝም ስራዎች ደረጃቸውን ጠብቀው እየተሰሩ መሆኑ ይታወቃል። እንደ አጠቃላይ የባሌ የተፈጥሮ ሀብት፣ አስደናቂ መልክዓ ምድር፣ ብርቅዬ እንስሳትና አእዋፋት እንዲሁም የውሃ ሃብት ተደምሮ ለኢትዮጵያ ትልቅ የቱሪዝም ሃብት መሆን የሚችል ነው። ከባሌ ሰፊ የተፈጥሮ ጸጋ ባለፈ በታሪክ፣ በባህል እሴቶችና በጠንካራ ማህበራዊ ትስስርም የሚጠቀስ ሲሆን የአካባቢው ማህበረሰብ ተፈጥሮን በማስጠበቅና በመንከባከብ ረገድ የዳበረ ልምድ እንዳለው ይታወቃል።  
ከባህር በር ጥያቄ እስከ ፍትሃዊ ውክልና በተመድ ጉባኤ የተንጸባረቁ የኢትዮጵያ አቋሞች
Sep 24, 2026 193
በኒውዮርክ እየተካሄደ የሚገኘው 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የዓለምን ትኩረት የሳበና በርካታ አንገብጋቢ ጉዳዮች እየተነሱበት ይገኛል። “መተማመንን ዳግም መገንባት እና አዳዲስ ለውጦችን በአግባቡ መምራት፣ ለሁሉም የሚሰራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን መፍጠር” የጠቅላላ ጉባኤው መሪ ሀሳብ ነው። በዚህ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን መሪ እና የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ያደረጉት ንግግር የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ አቋም፣ የልማት ጉዞ እና አህጉራዊ ራዕይ በሰፊው ያንጸባረቀ ነበር። የፕሬዝዳንቱ መልዕክት የኢትዮጵያን ፍላጎቶች ከዓለም አቀፉ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ያጣጣመና የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ አቅጣጫ ግልጽ ያደረገም ጭምር ነው። ኢትዮጵያ 32ኛውን የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ-32) በታላቅ ዝግጅት እንደምታስተናግድ አብስረዋል። ይህ ጉባኤ ከንግድ ተቋማት እስከ ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት ድረስ ሁሉን አካታች እና ተጨባጭ መፍትሄዎችን የሚያመጣ እንዲሆን ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ አረጋግጠዋል። የአየር ንብረት ቀውሱን ለመከላከል ዓለም አቀፍ መሪዎች በኮፕ-32 ጉባኤ ላይ እንዲገኙ ጥሪ ያቀረቡት ፕሬዝዳንቱ፣ ሁሉም አካላት ታሪካዊ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ አሳስበዋል። መልዕክታቸውም በኢትዮጵያ በ8 ዓመታት ውስጥ የተተከሉት 56 ቢሊዮን ችግኞች፣ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ጥበቃ ላይ ንግግር ብቻ ሳይሆን በቢሊዮን የሚቆጠሩ ዛፎችን በመትከል ከፍተኛ የካርቦን የመምጠጥ አቅም የፈጠረች ሀገር መሆኗን በሚገባ ያሳየ ነው። የአየር ንብረት ርዕሰ ጉዳይን ተከትሎ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገትና የባህር በር ጥያቄን በማንሳት ጠንካራ ሀሳቦችን አቅርበዋል። ጠንካራና የጸና ኢኮኖሚ ለመገንባት አስተማማኝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የባህር በር ማግኘት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎት ከማንኛውም ሌላ ወገን ጥቅም ጋር የማይጋጭና ለቀጣናው ሀገራት የጋራ ፕሬዝዳንቱ የባህር በር ማግኘት የሌሎችን ጥቅም እንደማይጎዳና ሁሉንም ወገኖች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ማብራራታቸው፣ ጥያቄው በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ህጋዊና ሰላማዊ የልማት ጥያቄ ሆኖ እንዲወሰድ ትልቅ እድል የሚፈጥር ነው። ዕድገትና ትብብር ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑን በግልጽ አስምረውበታል። ይህንን ፍላጎት እውን ለማድረግም ሀገሪቱ ያላትን የዲፕሎማሲ አማራጮች በሙሉ በመጠቀም ከዓለም አቀፍ የንግድ ሥርዓት ጋር ለመተሳሰር እየሰራች መሆኑንም ገልጸዋል። ይህም ኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘት የሌሎችን ጥቅም እንደማይጎዳና ሁሉንም ወገኖች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ማብራራታቸው፣ ጥያቄው በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ህጋዊና ሰላማዊ የልማት ጥያቄ ሆኖ እንዲወሰድ መንገድ ይከፍታል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አወቃቀር ላይ ሀሳባቸውን የሰነዘሩት ፕሬዝዳንት ታዬ፣ አንድ ነጥብ ስድስት ቢሊዮን የሚሆኑ አፍሪካውያን ተገቢውን ፍትሃዊ ውክልና ማጣታቸው በአስቸኳይ ሊታረም የሚገባው የሞራል ጥያቄ መሆኑን ተናግረዋል። ተመድ የዓለምን ነባራዊ እውነታዎች ባገናዘበ መልኩ መሠረታዊ ሪፎርም ሊያደርግ እንደሚገባው አጥብቀው ያሳሰቡ ሲሆን፣ የአፍሪካን አህጉር በዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪነት ውስጥ ማካተት የዘመኑ ግዴታ መሆኑን አብራርተዋል። እውነተኛ የፖለቲካ ፍላጎት ካለ የአፍሪካ ህዝቦች የረጅም ጊዜ የውክልና መነፈግ አግባብነት እንደሌለው ጠቁመው፣ ይህ ጉዳይ የትውልዱ ትልቁ የህሊና እና የሞራል ጥያቄ መሆኑን አመልክተዋል። የፕሬዝዳንቱ መልዕክት የአህጉሪቱን የጋራ አቋም የሚያጠናክር እና ኢትዮጵያ የቀደመች የተመድ መስራች አባልነቷን በመጠቀም የአፍሪካን ድምፅ በዓለም አቀፍ ደረጃ በግንባር ቀደምነት ተሞጋች ሆና እንድትቆም ያደርጋታል። ከምግብ ዋስትና አንፃር ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው ስኬት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መልዕክት አስተላልፈዋል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ከስንዴ አስመጪነት ወጥታ በአፍሪካ ግንባር ቀደም የስንዴ አምራች ሀገር መሆን የቻለችው ኢትዮጵያ፣ አፍሪካ በራሷ አቅም ራሷን መመገብ እንደምትችል በተግባር ማሳየቷን ተናግረዋል። በተጨማሪም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በውሃ ሀብት አጠቃቀም ዙሪያ የጋራ ቀጣናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚቻል ያረጋገጠ ታላቅ ፓን-አፍሪካዊ ፕሮጀክት መሆኑን አንስተዋል። ኢትዮጵያ ከ60 ሺህ ሜጋዋት በላይ የኃይል ማመንጨት አቅም እንዳላት ጠቅሰው፣ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ተጨማሪ ኃይል በማመንጨት የምስራቅ አፍሪካን የኢነርጂ ፍላጎት ለማሟላት እቅድ ይዛ እየተንቀሳቀሰች መሆኑን አብራርተዋል። ግድቡ የምስራቅ አፍሪካ የጋራ ብልጽግና እና የታዳሽ ኃይል ምንጭ ተደርጎ መቅረቡ የሀገሪቱን የልማት አተያይ ላይ መግባባት ለመፍጠርና የኢትዮጵያን ቀጣናዊ ተጽዕኖና ኢኮኖሚያዊ ትስስር የሚያጎላ ነው። በቴክኖሎጂ እና በዲጂታል አብዮት ዘመን አፍሪካውያን ተመልካች ብቻ ሳይሆን የለውጡ ባለቤት መሆን እንደሚገባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ የአምስት ሚሊዮን ኮደሮች መርሃ-ግብር እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ግንባታ አህጉሪቱ ለዲጂታል ዘመን ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳዩ መሆናቸውን አስገንዝበዋል። በአካባቢ ጥበቃ ረገድም ባለፉት ዓመታት የተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም ከሀገር አልፎ ዓለም አቀፍ ትኩረት የሰበሰበ ስኬት መሆኑን አብራርተዋል። በስምንት ዓመታት ውስጥ 56 ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸው የደን ሽፋንን ከማሳደግም በላይ ከፍተኛ መጠን ያለው ካርቦን የመምጠጥ አቅም በመፍጠር የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ቀውስን ለመታገዝ የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ኢትዮጵያ ሰብአዊ ክብርን በሚያስከብር፣ ፍትሕ በሚያሰፍን እና በነጻ ህዝቦች ጽኑ አብሮነት ላይ በተመሰረተ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ ጸንታ እንደምትቀጥል ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል። በአጠቃላይ፣ የፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ንግግር ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ መፍትሔ አመንጪ፣ የቀጣናው የኢኮኖሚ ትስስር መሪ እና የአፍሪካ ፍትሃዊ ውክልና ተሞጋች መሆኗን ያረጋገጠ መልዕክት ነው።
የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግርን እያረጋገጠ የሚገኘው አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ
Sep 24, 2026 144
የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለሀገር የኢኮኖሚ እድገት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እና ለውጭ ምንዛሬ ግኝት ዋና ማዕከል ነው። በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ታሪክ ውስጥ ዘርፉ የፖሊሲ እና መዋቅራዊ ፈተናዎች ሲያጋጥሙት የቆየ ቢሆንም፣ በየጊዜው በተወሰዱ የማሻሻያ እርምጃዎች፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት እና በቅርብ ጊዜ በተጀመረው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አማካኝነት ወደ አዲስ የስኬት እና የእድገት ምዕራፍ እየተሸጋገረ ይገኛል። 👉በኢንዱስትሪ ዘርፉ የነበሩ ፈተናዎች በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ዘርፉ ተገቢው እድገት እንዳይመዘገብ በርካታ መዋቅራዊ ችግሮች ነበሩበት። የአምራች ኢንዱስትሪዎች የጥሬ፣ የካፒታል ዕቃዎች እና የፋብሪካ ማሽኖች እንዲሁም የማሽኖች መለዋወጫዎች ግዢ በውጭ ምንዛሬ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። የውጭ ምንዛሬ እጥረት ደግሞ የማምረቻ ዘርፉ ብቻ ሳይሆን ሀገሪቷ ትልቁ ፈተና እንደነበር ይታወቃል። ይህ የውጭ ምንዛሬ እጥረት በአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ላይ ከፍተኛ ችግር ሆኖ ቆይቷል። ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት የሚሆኑ የግብርና ምርቶች በሚፈለገው ጥራት እና መጠን አለመመረትም እንዲሁ አንዱ ተግዳሮት ሆኖ ይጠቀሳል። የግብርናው ዘርፍ ከኢንዱስትሪዎች ጋር ያለው የአቅርቦት ሰንሰለት በደላላ የተተበተበ፣ አምራቹንና ተቀባይ ኢንዱስትሪዎችን በቀጥታ ለማገናኘት እንቅፋት ሆኖ የቆየ ነበር። ከአቅርቦት ሰንሰለቱ መበታተን በተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ፣ የመንገድ እና የሎጂስቲክስ ቀልጣፋ አለመሆን የምርታማነት ወጪን ከፍ አድርጎት መቆየቱም ይነሳል። አዳዲስ የኢንዱስትሪ ባለሀብቶች እና ነባር ፋብሪካዎች ለማስፋፊያ የሚሆን የረጅም ጊዜ ብድር የማግኘት እድላቸው ጠባብ ሆኖ መቆየቱም እንዲሁ ፋብሪካዎች ሙሉ አቅማቸውን እንዳይጠቀሙ አድርጓል።   👉ከችግር ወደ መፍትሔ መዋቅራዊ ሽግግር እና የፖሊሲ ማሻሻያዎች ባለፉት ዓመታት በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ይታዩ የነበሩ ስር የሰደዱ መዋቅራዊ ችግሮችን ለማቃለል እና የዘርፉን የኢኮኖሚ ዋና አንቀሳቃሽነት ሚና ለማሳደግ የመደመር መንግስት በርካታ የፖሊሲ እና የተግባር እርምጃዎችን ወስዷል። አጠቃላይ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ የማምረት አቅም ከነበረበት 47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ እንዲል ሰፊ ጥናቶችና የድጋፍ ስራዎች መከናወናቸውንና የወጪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት ስትራቴጂ ተግባራዊ መደረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 30ኛው መደበኛ ስብሰባ ላይ መግለጻቸው ዘርፉን ለማሳደግ መንግስት የወሰዳቸውን እርምጃዎች የሚያመላክት ነው። መንግስት ከነባሮቹ የኮምቦልቻ፣ የመቀሌ እና የሐዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች በተጨማሪ አስር አዳዲስ የኢኮኖሚ ዞኖችን በመገንባት ከ80 በመቶ በላይ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን መሳብ መቻሉን መጥቀሳቸውም ይህንኑ ያስረግጣል። የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ምርቶች ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነትን የማሳደግና ለውጭ ገበያ የማቅረብ አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ ማደጉን እንዲሁም የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ በሀገሪቷ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ላይ የላቀ ሚና እያበረከተ መምጣቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል መግለጻቸው እንዲሁ የዘርፉን ውጤታማነት ያረጋግጣል። በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ምክንያት በተነደፈው በ”ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ ዘርፉን ከመቼውም ጊዜ በላይ በማነቃቃቱ ለወጪ ንግድ የሚሆኑ ምርቶችን በመጠንም ሆነ በጥራት በማሳደግ የውጭ መንዛሬ ግኝት ላይ ትርጉም ያለው እድገት ተመዝግቧል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባቸውን የተለያዩ ምርቶች በሀገር ውስጥ በማምረት ወደ ሀገር ይገቡ ለነበሩ ምርቶች ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ማዳን የተቻለበት አቅምም ተፈጥሯል። ኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን መሳብ የሚያስችሉ መሰረተ ልማቶችን ከማሟላት በተጨማሪ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስርዓትን በመዘርጋት የሀገር ውስጥ እና የውጭ ባለሀብቶችን በኢትዮጵያ ኢንቨስት የማድረግ ተነሳሽነት ማሳደግና ውጤት ማስመዝገብ አስችሏታል። በተለይ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በተገነቡ የኢንደስትሪ ፓርኮች በተፈጠሩ የኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎችና በተሟሉ መሰረተ ልማቶች ተጠቅመው ምርቶቻቸውን ለውጭ ገበያ እያቀረቡ የሚገኙ አምራቾች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደጉ መምጣታቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ። እነዚህ የኢንዱስትሪ ፓርኮች የውጭ ኢንቨስትመንትን በመሳብ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር በማምጣትና ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር በኩል ትልቅ ሚና እየተጫወቱም ይገኛሉ። ፓርኮቹ የተቀናጀ መሰረተ ልማት እና ደረጃቸውን የጠበቁ አሰራሮች በማቅረብ ባለሀብቶች በፋብሪካ ግንባታ ላይ የሚያባክኑትን ጊዜ ቀንሰዋል።   👉የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ትሩፋቶች የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ እና የኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ የተደቀኑ ችግሮችን ለመፍታት፣ የሀገር ውስጥ ምርታማነትን ለማሳደግና ኢንዱስትሪውን የኢኮኖሚው ዋና አንቀሳቃሽ ለማድረግ የተጀመረ ሀገራዊ ንቅናቄ ሲሆን አጠቀላይ በዘርፉ ያሉ ተግዳሮችን በመቅረፍ በኩል ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል። በዚህም ኢንደስትሪዎች ሲገጥማቸው የነበሩ የመሬት፣ የኃይል እና የፋይናንስ ችግሮችን በመፍታት የማምረት አቅማቸውን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ማሸጋገር ተችሏል። በጨርቃጨርቅ፣ በቆዳ፣ በሲሚንቶ፣ በኬሚካል፣ በምግብ እና መጠጥ ዘርፎች የሚመረቱ የሀገር ውስጥ ምርቶች ከውጭ የሚገቡትን በመተካት ከፍተኛ ሀገራዊ ወጪን አስቀርተዋል። ሲሚንቶ፣ ብረት፣ ብርጭቆ እና ሴራሚክስን የመሳሰሉ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ብቻ ወደ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ምንዛሬ መቆጠብ መቻሉን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዘርፉ እያስመዘገበ ባለው ፈጣን እድገትም በማዕድን ዘርፍ 24 በመቶ፣ በማኑፋክቸሪንግ 20 ነጥብ 3 በመቶ እና በኢነርጂ ዘርፍ ደግሞ 23 በመቶ ጭማሪ መታየቱን ማንሳታቸው ዘርፉ በተደረገለት ድጋፍ ወደ ውጤታማነት መሸጋገሩን ያሳያል። በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና በባለሃብቶች መካከል የተደረጉ ተከታታይ ውይይቶች በዘርፉ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን የሚፈቱ ትልልቅ ውሳኔዎች እንዲወሰኑ አስችለዋል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የሀገር ውስጥ ምርቶች ዕድገት እንዲጨምር አስችለዋል፤ የአምራቾችና የሸማቾችን ትስስር አጠናክረዋል እንዲሁም የህብረተሰቡን የሀገር ውስጥ ምርት የመጠቀም ባህል አሳድገዋል። በአጠቃላይ ንቅናቄው አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ከነበረበት ፈተና ተላቆ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል። 👉የሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ እና የፋይናንስ ዘርፍ ሪፎርም በኢትዮጵያ የተደረጉ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያዎችና የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ስርዓት ለወጥ የኢንዱስትሪው ዘርፍ የነበረበትን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለማቃለል፣ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብና የሀገር ውስጥ አምራቾች ጥሬ ዕቃዎችን በነፃነት እንዲያስገቡ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።   👉የግብርና እና ኢንዱስትሪ ትስስር በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ትስስር ለዘላቂ እድገት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እና ለውጭ ምንዛሬ ግኝት ዕድገት መሠረታዊ ምሰሶ ናቸው። ግብርናው ለኢንዱስትሪው ጥሬ ዕቃ የሚያቀርብ ሲሆን፣ ኢንዱስትሪው ደግሞ የግብርና ምርቶችን እሴት በመጨመርና መልሶ ለግብርናው ዘርፍ ግብዓቶችን በማቅረብ ባለሁለት ወገን ትስስር ይፈጥራሉ። 👉በተወሰዱ እርምጃዎች የተመዘገቡ ውጤቶች የመደመር መንግስት እና ባለድርሻ አካላት የኢንደስትሪ ዘርፉን ውጤታማነት ለማሳደግ ባደረጉት የተቀናጀ ጥረት እና በተወሰዱ መዋቅራዊ ማሻሻያዎች የፋብሪካዎች የማምረት አቅምን 67 በመቶ ማድረስ ተችሏል። ይህ ቀደም ሲል 30 እና 40 በመቶ ከነበረው የፋብሪካዎች የማምረት አቅም አንጻር ሲታይ ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱን የሚያመላክት ነው። ኢትዮጵያ በመደመር እሳቤ በመመራት ባለፉት ዓመታት የኢንደስትሪ ዘርፏን ለማሳደግ በርካታ ተግባራትን በማከናወን እና የማሻሻያ እርምጃዎችን በመውሰድ በዘርፉ እምርታዊ ውጤት አስመዝግባለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2018 “ኢትዮጵያ ታምርት” ኤክስፖን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልእክት በውጤት ተኮር አመራር ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የኢንዱስትሪ መስፋፋት መንጸባረቁን መናገራቸው ይህንኑ የሚገልጽ ነው፡፡ እመርታውን በተጨባጭ ማሳያ ሲያቀርቡም የአምራች ኢንዱስትሪዎችን አማካይ የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ማድረግ መቻሉን፣ ከ2 ሺህ 800 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ መቻሉን እንዲሁም አዳዲስ ኢንዱስትሪ ፓርኮች መገንባታቸውንና በሀገር ውስጥ ምርትን በማስፋፋት እስከ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ምንዛሬ መቆጠቡን መግለጻቸውም እንዲሁ። የመደመር መንግስት በአምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ ይስተዋል የነበረውን የፋይናንስ ማነቆ ለመፍታት በወሰደው እርምጃ፣ ቀደም ሲል 40 ቢሊዮን ብር የነበረውን የብድር መጠን ወደ 115 ቢሊዮን ብር ከፍ ማድረግ መቻሉንና የኢንዱስትሪዎችን ተወዳዳሪነት፣ ምርታማነት፣ ትርፋማነት እና የመስፋፋት ዕድል ከፍ እያለ መምጣቱን የኢንደስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል መግለጻቸው የመንግስት ውሳኔዎች ውጤታማነትን የሚያረጋግጡ ናቸው። የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ የንግድ ሚዛንን በማጣጣም በኩል ያለውን አስተዋጽኦ ሲገልጹም የኢትዮጵያን ዘላቂ ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ድርሻ አበርክቷል። በዚህ መነሻነትም መንግስት በ2019 በጀት ዓመት ከወጭ ንግድ የሚገኘውን ገቢ ወደ 1 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ዕቅድ ነድፎ ለስኬታማነቱ እየታተረ ይገኛል። እነዚህ የፖሊሲም ሆነ ሌሎች የመንግስት እርምጃዎች በሙሉ የዘርፉን ውጤታማነት ለማሳደግ ያለውን ቁርጠኝነት ያረጋግጣሉ። 👉ማጠቃለያ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ጉዞ ከብዙ መሰናክሎች በኋላ በተለይ የመደመር መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት እና በወሰዳቸው የፖሊሲና የመዋቅራዊ ማሻሻያ እርምጃዎች፣ የሀገር ውስጥ ምርታማነትን በማስቀደም በሂደት ወደ ጠንካራ መዋቅር እየተሸጋገረ ይገኛል። አሁን የተጣጣሙት የፖሊሲ እርምጃዎች እና የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ተጠናክረው ሲቀጥሉ፣ ዘርፉ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ በመገንባት በአፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል የሚያደርግ ትልቅ አቅም አለው።
ትንታኔዎች
ሕወሓት - “ድመት መንኩሳ ……”
Sep 25, 2026 169
ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ /ሕወሓት/ በዘወትር መደበቂያው በደደቢት በረሃ ውስጥ ተጸንሶ የካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም ለኢትዮጵያ መከራ ይዞ ተወለደ።የመጀመሪያዎቹ የትግሉ እንቅስቃሴ መስራች ወጣቶች 11 ነበሩ። ሕወሓት በኢትዮጵያውያን ላይ የተጣባውን የጭቆና ቀንበር ለማስወገድ ተፀንሶ ገንጣይ አስገንጣይ ባንዳ ሆኖ ህልው ሆነ፤ ለዚህም ነው እነ አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) በጊዜ የተገለሉት፤ እነ ገሠሠ አሠፋ /ስሁል በሴራ የተገደሉት። በእርግጥ ድርጅቱ ሲመሰረት ተጋድሎ ሓርነት ሕዝቢ ትግራይ /ተሓሕት የሚል መጠሪያ ነበረው፤ በኋላ የስም እንጂ የግብር ለውጥ ሳያደርግ ወደ ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ /ሕወሓት/ ተቀየረ። ሕወሓት የኢትዮጵያውያን ጭቆና “ጥራኝ ጫካው” ያስባላቸው ድርጅቶችን በማታለልና በማጭበርበር ከጎኑ በማሰለፍ በ1983 ዓ.ም ወታደራዊውን የደርግ ስርዓት አስወግዶ መንበረ ስልጣኑን ተቆጣጠረ።ታላቋን ትግራይ ለመመስረት ዓላማ አንግቦት የተነሳው ጸረ ኢትዮጵያው ሕወሓት የሚጠላትን ሀገር የሚመራበት ዕድል ከዕጁ ሰተት ብሎ ገባለት። በ27 ዓመታት የአምባገነንነት የአገዛዝ ዘመኑ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ብቻ በሚያወጧቸው ሪፖርቶች መሰረት በሚመራው ህዝብ ላይ በርካታ ግፎችን የፈጸመ ድርጅት ሆኖ ተመዝግቧል። ሰብዓዊ መብት ጥሰት የዜጎች እስር በገፍ ሆነ። የፖለቲካና የዲሞክራሲ ምህዳሩን ክርችም አድርጎ በመዝጋቱ ህዝብ አንቅሮ ተፍቶት እያለ የ1997ቱን ምርጫ 99 ነጥብ 6 በመቶ አሸነፍኩ ብሎ የዓለም መሳለቂያነቱን፣ የአምባገነን ቁንጮነቱን፣ ጮሌ ማፍያነቱን በገሀድ አሳይቷል። የኢትዮጵያን ህዝብ በዘርና በሀይማኖት እየከፋፈለ እስር በርስ በማጋጨት ለዘመናት ተጋምደው በኖሩ ህዝቦች (በተለይም በአማራና ኦሮሞ ህዝቦች) ዘንድ ጥላቻና ቁርሾን እየዘራ ሀገር ጠልነቱን አስመስክሯል። በሜቴክና ኢፈርት በተባሉ ድርጅቶች የራሱን ወታደራዊ አዛዦችና አንጃዎች በማሰማራት የኢትዮጵያን መርከብ ሳይቀር የሚዘርፉ የማፍያ ቡድኖችና ግለሰቦችን ፈጥሯል። የመከላከያ ሠራዊት እና ሌሎች የጸጥታና ደህንነት ተቋማት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና የህዝቦቿን ደህንነት ከማስጠበቅ ይልቅ የወያኔ ፍላጎት ማስፈፀሚያ አንጃዎች ሆነዋል፤ ለ27 ዓመታት በህዝብ ላይ የፈጸመው ግፍ በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ በ2010 ዓ.ም ተወግዶ በምትኩ በሀገር በቀል የመደመር እሳቤ የሚመራ በህዝብ የተመረጠ መንግሥት መንበሩን ያዘ። ከለውጡ በኋላ “እኔ ያልመራኋት ኢትዮጵያ መኖር የለባትም” የሚለው እብሪተኛው ሕወሓት መቀሌ መሽጎ በስልጣን ላይ በነበረበት ዘመን ያደራጀውን የጥፋት ሴል በማሰማራት በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የእርስ በርስ ግጭት በመፍጠር የተጸነሰበትን የጥፋት ዓላማ አስቀጥሏል። ለዚህም ነው የትግራይ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገብሩ አስራት “ሕወሓት እኔ ብቻ አውቃለሁ፣ የሚል ተቸካይ ሀሳብ ያለው የቁሞ ቀር ግለሰቦች ስብሰብ ነው” የሚሉት። ዛሬም አብዮታዊ ዲሞክራሲ በተሰኘ “የእውር ድንበር” ፅንሰ ሀሳብ ላይ ተጣብቆ “እኔ ያልመራኋት ሀገር ትፍረስ” የሚል ግትር አቋም እንዳለው የገለጹትን በዋቢነት መጥቀስ ይቻላል። ሕወሓት ከምስረታው ጀምሮ አምባገነን መሆኑን በማንሳት፤ “በህዝብ ግፊት ከስልጣን ከተወገደ በኋላ አሸባሪነትን ጨምሮ የለየለት ማፍያ ሆኗል” ብለዋል።በፊት የአምባገነንነቱ ማስፈፀሚያ ህግና አሰራር እንደነበረው አስታውሰው፤በአሁኑ ወቅት ህዝብን በማናለብኝነት የሚያንገላታ የፖለቲካ ድርጅት እንኳን መሆን የተሳነው መርህ አልባ ስብስብ መሆኑን ያነሳሉ። ሕወሓት በትግራይ ሕዝብ ላይ የዘረጋውን ህገ ወጥ ሥርዓት በመጠቀም በዘረፋና ብዝበዛ ላይ ተሰማርቷል፤ ጥቂት ቡድኖች ብቻ ሀብት የሚያከማቹበት፣ ሕዝቡን ለከፋ ረሀብ፣ ስደትና ድህነት የሚዳርግ ሥርዓት ሆኗል ይላሉ። ይህ አልበቃው ብሎ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. የትግራይ እናቶችን ሰብል ሲሰበስቡ፤ የትግራይ ህፃናትን ትምህርት ቤት ሲገነቡ በዋሉ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ አባላት ላይ ጥቃት ፈጽሟል።የሀገር ክህደት አውራ የባንዳነት ቁንጮ መሆኑን ደጋግሞ አሳይቷል፤ ዛሬም ክህደት ቤት ሰርቶበታል። በትግራይ ክልል ህፃናት የብዕር መጨበጫ ጣቶቻቸው የክላሽ ምላጭ እንዲስቡ ተገደዋል፤ ወጣቶች ከትምህርት ገበታ ታፍሰው ራሳቸውን እቶን እሳት ከሚተፋ የጥይት ሀሩር ውስጥ ያገኙታል።ይህ የትግራይ ወጣቶች ዘወትራዊ ልምድ፤ በሕወሓት የተፃፈላቸው እጣ ፋንታ ሆኗል። የወንጀለኞች ቡድን የሆነው የሕወሓት አንጃ የትግራይን እናቶች ያለ ጧሪ አስቀርቷቸዋል። በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ወጣቶችን አስፈጅቶ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ምት ከእርሱ ላይ ሊያርፍበት ሲል ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የድረሱልኝ ጩኸት አሰማ። የወታደራዊ ሀይል መዛባትና የፖለቲካ ህልውነት አደጋ ሲያጋጥመው ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም የፕሪቶሪያን የሰላም ስምምነት ለምኖ ፈርሟል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት የቀድሞዋ አፈ ጉባኤና የስምረት ፓርቲ ምክር ቤት አባል ኬሪያ ኢብራሂም የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የትግራይ እናቶችና ወጣቶችን የመኖር ተስፋ ያለመለመ፤ ለነገ ህልም አለኝ፣ ሰላም ተፈጥሯል ጥያቄዎች በሰላም ይፈታሉ የሚል ተስፋ ያላቸው ወጣቶችን የፈጠረ፤ የጥይት ድምጽ የጠፋበት መልካም ዕድል ያበሰረ መሆኑን ያስታውሳሉ። የትግራይ ህዝብና የሕወሓት ፍላጎት የተለያዩ መሆኑን የሚገልጹት ኬሪያ ኢብራሂም፤ ስምምነቱን ሰላም እንደሚያመጣ በመረዳት የደገፈው ህዝቡ ቢሆንም የሕወሓት ቡድን ግን ለጊዜ መግዣ ካባ አድርጎት እንደነበር በመጥቀስ፤ “ስምምነቱን በግልጽ በመጣስ ጦርነት ህልውናው መሆኑን አሳይቷል” ብለዋል። ጦርነት ልብሱ የህዝብ ሲቃ ጉርሱ የሆነው የሕወሓት አንጃ ለምኖ የፈረመውን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ገና በጠዋቱ በመጣስ የጦርነት ነጋሪት መጎሰም ጀምሯል። የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ፤ የሕወሓት ቡድን አባላት ከስልጣን ውጭ መኖር እችላለሁ ብለው የማያምኑ፤ ከስልጣን የለቀቁ ዕለት ተጠያቂ የሚሆኑበትን ብዙ ወንጀል የሰሩ አሁንም እየሰሩ ያሉ የወንጀል ኢንተርፕራይዞች መሆናቸውን ይናገራሉ። የትግራይ ህዝብ የሰላም ስምምነቱን ደጋፊ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ጌታቸው፤ ”የፕሪቶሪያው የሰላም ሥምምነት የኮንትሮባንድ ጥቅሜን ያስቀርብኛል ብሎ ያሰበው ቡድን ግን ስምምነቱን በገሃድ ጥሶ ወንጀል ይፈጽማል” ብለዋል። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሕወሓት ድርብርብ ወንጀል እየፈጸመ መሆኑን ተረድቷል፤ ሊያወግዘውም እንደሚገባ አሳስበዋል። የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል ሰላም እንዲሰፍን ያሳየው ትዕግስት የሚደገፍ ነው፤ ዋናው የለውጡ ባለቤቶች የትግራይ ወጣቶችና ፖለቲከኞች በመሆናቸው ቡድኑን በጋራ መታገል አለባቸው ብለዋል። “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ” እንዲሉ በመቃብር አፋፍ ላይ ሆኖም ግብዓተ መሬቱ እስኪፈጸም የትግራይን ወጣት ለማስጨረስ ቆርጦ ተነስቷል። የትግራይ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገብሩ አስራት፤ ተስፋ በቆረጠ ሰዓት ያገኘውን የፕሪቶሪያ ሥምምነት እንኳን መተግበር ተስኖት በሥምምነቱ መሰረተ የተቋቋመውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በመፈንቀል ስልጣን የተቆጣጠረ የሥልጣን ጥመኛ ቡድን መሆኑን አንስተዋል። “ሰላም ከመጣ በትግራይ ወጣቶችና እናቶች ተጠያቂነት እንደሚኖር ስለሚያውቅ በጦርነትና በትርምስ ውስጥ ብቻ መኖርን መርሁ አድረጎታል” ብለዋል። የሕወሓት ታጣቂዎች ከባድና ቀላል መሣሪያዎችን ለሀገር መከላከያ ሠራዊት በማስረከብ ወደ ተሀድሶ ገብተው ማህበረሰቡን እንዲቀላቀሉ፤ ተፈናቃዮች እንዲመለሱ የገባውን ውል ለጦርነት አጀንዳው ማስፈጸሚያ ብሎ አንገራገረ፤ ይባስ ብሎ በፌዴራል መንግሥቱና በሕወሓት ሥምምነት የተመሰረተውን ጊዜያዊ አስተዳደር በሀይል በመፈንቀል መንበረ ስልጣኑን ተቆጣጥሮ የራሱን የዘረፋ አንጃ በትግራይ ክልል መንግሥትነት ሰይሟል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት የቀድሞዋ አፈ ጉባኤና የስምረት ፓርቲ ምክር ቤት አባል ኬሪያ ኢብራሂም ወጣቶችን አስገድዶ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማስገባት በዓለም አቀፍ ህግ ጭምር የተከለከለ ቢሆንም፤ ትምህርት ቤቶችን በመዝጋት ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋማትን ከፍተው የትግራይን ወጣትና ሀብት የገንዘብ ምንጫቸው አድርገውታል ብለዋል። በእርግጥም ወጣቶችን በግዳጅ መመልመያ አዋጅ በማውጣት የጭካኔያቸውን ጥግ ለዓለም አሳይተዋል። ለሕወሓት በትግራይ የሚኖር ትግራዋይ “ትግራዋይ” የሚሆነው የእነሱን አስተሳሰብ ከተቀበል ብቻ ነው።ስለሆነም ሁሉም ከትግራይ ህዝብ ጎን በመታገል ጥይት ሳይተኮስ ሰላም ማስፈንና የትግራይ ወጣቶችን ጥያቄ መመለስ እንደሚገባ አሳስበዋል። ትናንት ራሱ በለኮሰው እሳት የትግራይን ህዝብ ሲገድልና ሲዘርፍ ከነበረው ጸረ ኢትዮጵያ ሻዕቢያ ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን ለማፍረስ “ጽምዶ” የተባለ የጥፋት አደረጃጀት ፈጥሯል። የኢትዮጵያ ዕድገትና ሰላም ከወትሮም የማይዋጥላት ግብጽ የምትጋልበው ፈረስ ሆኗል። ሕወሓት የኢትዮጵያን አለመረጋጋት እንደ ቋሚ አጀንዳ አድርገው ከሚሰሩ የውጭ አካላት ጋር እየሰራ ነው።ትግራይን ወደ ኋላ ለመመለስ ትግራይ ውስጥ መሰረተ ልማት በማውደም በመዝረፍና ተቋማትን ሆነ ብሎ ካፈረሰው የኤርትራ መንግስት ጋር መተባበር ትልቅ ወንጀል እንደሆነ አስረድተዋል። “ሕወሓት የሰብዓዊ ጥሰትና የኮንትሮባንድ ህልውናውን የሚያስቀጥልለት ካገኘ የትም ሀገር ይሄዳል” ያሉት አቶ ጌታቸው፤ ከትግራይ ህዝብ ህልውና በላይ ለራሱ ህልውና ቅድሚያ የሚሰጥ ይሉንታ ቢስ ድርጅት መሆኑን ነው የተናገሩት። በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረው የትግራይ ህዝብ ይሄንን እኩይ ዓላማ ያነገበ የጥፋት ቡድን በቃህ ሊለው ይገባል።ለኢትየጵያ ዳር ድንበር መከበር ልጆቹን ሲገብር የኖረው የትግራይ ህዝብ ከአብራኩ በወጡ ባንዳዎች ሀገሩን አሳልፎ በመስጠት ከታሪካዊ ጠላቶቹ ጋር ሲዶልት ቆሞ ማየት የለበትም። አቶ ገብሩ አስራት “ሕወሓት እወክልሀለሁ” የሚለው የትግራይ ህዝብ ላይ ጭፍጨፋና ዘረፋ ከፈጸመው የሻዕቢያ ሀይል ጋር በማበር የትግራይ እናቶችን ለዳግም ሰቆቃ እያዘጋጀ ነው። ከውጭ ሀይሎችና ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በመተባበር የሚፈጽመውን የሀገር ክህደት ወንጀል የትግራይ ህዝብ በጋራ በቃህ ሊለው ይገባል ብለዋል። በትግራይ ክልል የወጣቶች የግዳጅ ምልምላ ህጋዊ ሆኖ በአዋጅ ወጥቷል። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጭምር ውጉዝ የሆኑ ወንጀሎችን በመፈጸም ጭካኔውን በግላጭ አሳይቷል።በትግራይ ክልል ወጣቶችን በግዳጅ ይመለምላሉ፤ ፈቃደኛ ያልሆኑት ይረሽናሉ። በዚህም አብዛኛው ወጣት የግዳጅ አፈሳውን በመፍራት ከክልሉ ወጥቶ እየተሰደደ ተፈናቃይ ሆኗል፤ በትግራይ ህዝብ ላይም የህልውና አደጋ ደቅነዋል። “ይህ ወንጀል ነው” ያሉት አቶ ጌታቸው፤ የትግራይ ህዝብ ልዕልና የሚረጋገጠው በሰላም ብቻ እንደሆነ ይናገራሉ።እነዚህን በህገ አራዊት የሚመሩ የሰው ህይወት እንደከንቱ የሚያዩ የጥፋት ቡድኖችን የትግራይ ወጣቶች በቃችሁ ሊሏቸው ይገባል ብለዋል። ወይዘሮ ኬሪያ እንደሚሉት፤ የሕወሓት ቡድን አጀንዳ አጥፊ መሆኑን በውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ ያለው ትግራዋይ ይገነዘባል። መንግስት ለሰላም ያሳየውን ቁርጠኝነት በማድነቅ፤ ቀጣይነት እንዲኖረው ጠይቀዋል። እኛ ለሰላም ቅድሚያ ስንሰጥ በትግራይ ህዝብ ጥቅም ላይ የምንደራደር ይመስላቸዋል፤ ከጦርነት ኪሳራ እንጂ ትርፍ የለም፤ ሰላም ደግሞ አክስሮ አያውቅም፤ የትግራይ ህዝብም ተገድደው ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ መታገል አለበት በማለት ነው አፅንኦት የሰጡት።
አዲስ መንግሥት፤ የጸናች ኢትዮጵያ
Sep 25, 2026 65
በፖለቲካ ሳይንስ ጽንሰ ሐሳብ፣ የአንድ መንግሥት ጥንካሬ የሚለካው በሕዝብ ዘንድ ባለው የፖለቲካ ቅቡልነት ነው። ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከቅቡልነት ጋር እጅጉን ይቆራኛል። በጠቅላላ ምርጫውም ከ54 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ተሳትፎ አድርጓል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ ባደረገው የምርጫ ውጤት ብልፅግና ፓርቲ አብላጫ ድምፅ በማግኘት ማሸነፉን ገልጿል። በድምፅ አሰጣጥ እለትም፤ በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች በነበረው ከፍተኛ የመራጮች ሰልፍና በአንዳንድ አካባቢዎች በነበረው የዝናብ ሁኔታ ምክንያት የድምፅ አሰጣጡ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ተራዝሞ የተካሄደበት በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክም አድስ ምዕራፍ የተፈጸመበት ነበር። ይህ መጠነ ሰፊ የሕዝብ ተሳትፎ መንግሥት ባለፉት ዓመታት ላከናወናቸው ሀገራዊ የልማት፣ የኢኮኖሚና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሥራዎች የሰጠው ትልቅ ዕውቅና ማሳያ ነው። ዜጎች በምርጫው አሉታዊ ጫናዎችን ሳይበግሯቸው መሳተፋቸው የሀገሪቱን የዴሞክራሲ ባህል ብስለት ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግሮታል። የምርጫ ሂደቱ ለሀገረ መንግሥት ግንባታ መጠናከር የሚጫወተው ሚናም ቁልፍ የሚባል ነው። ምርጫው 42 የፖለቲካ ፓርቲዎችና ከ10 ሺህ በላይ ዕጩዎች የተሳተፉበት በመሆኑ፣ የፖለቲካ ኃይሎች ጥያቄዎቻቸውን ከኃይልና ከግጭት ይልቅ በምርጫ ካርድ መፍታት እንደሚገባ የጋራ ስምምነት የፈጠሩበት ሲሆን ይህም ህጋዊ የሀገረ መንግሥት መዋቅርን ያጠናክራል። የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት ላይ ያበረከተው ቀዳሚው አስተዋጽኦ፣ የፖለቲካ ሥልጣን ይዞታን ሙሉ በሙሉ በሕግና በሕዝብ ፍላጎት ማዕቀፍ ውስጥ በማስገባት የመንግሥትን ህጋዊ ቅቡልነት ማሰደጉ ነው። ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተመዝግበው በነቂስ ወጥተው ድምፅ መስጠታቸው፣በዜጋውና በሀገረ መንግሥቱ መካከል ያለውን ማኅበራዊ ውል በከፍተኛ ደረጃ አጠናክሮታል። ይህ መጠነ ሰፊ ሕዝባዊ ተሳትፎ፣ የሥልጣን ፉክክር ከመሣሪያ ግጭትና ከትጥቅ እንቅስቃሴ ወጥቶ በሰላማዊ የምርጫ ካርድ ውድድር ላይ ብቻ እንዲመሠረት በማድረግ፣ መንግሥት ያለ አስገዳጅ ኃይል በህዝብ ፈቃደኝነት ላይ ብቻ እንዲመሠረት ትልቅ መሰረት የሚጥል ነው። ምርጫው መንግሥት ካገኘው የስራዎቹ እውቅና በተጨማሪ ህዝቡ ትልቅ አደራ የሰጠበትም ጭምር ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የምርጫ ውጤቱን ተከትሎ በሰጡት አስተያየት የተገኘው ድምፅ ፍጹም መዘናጋትን የሚፈጥር ሳይሆን ለመንግሥት የተሰጠ ታላቅ ህዝባዊ አደራ መሆኑን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳመለከቱት፣ ህዝቡ ጥይትና ማስፈራሪያዎችን ሳይበግሩት በነቂስ ወጥቶ ድምፅ የሰጠው፣ በመንግሥት የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን በላቀ ስኬት እንዲያስቀጥል፣ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ እና በተለይም ሥርዓታዊ ሌብነትንና ሙስናን በቁርጠኝነት እንዲያጠፋ ነው። ይህ መጠነ-ሰፊ የህዝብ ተሳትፎ ለአዲሱ መንግሥት የማይናወጥ ህጋዊ መሠረትና ከፍተኛ የፖለቲካ ቅቡልነት የሰጠ ሲሆን፣ ኢትዮጵያውያን ለሰላም፣ ለአካታችነትና ለዴሞክራሲያዊ ውድድር ያላቸውን የጸና አቋም ለዓለም ያስመከሩበት መሆኑንም ተናግረዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባወጣው መረጃ መሠረት፤ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም. ለሚከናወነው አዲስ የመንግሥት ምሥረታና የምክር ቤቶች መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል። የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማ መሆን የኢትዮጵያን ሀገረ መንግሥት ግንባታ ወደ አዲስና አስተማማኝ ምዕራፍ ያሸጋገረ ክስተት ነው። የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደትና መስከረም 25 ቀን የሚከናወነው አዲሱ የመንግሥት ምሥረታ በሀገሪቱ የፖለቲካ ባህል ውስጥ የተቋማዊ አቅምና የህግ የበላይነት መጎልበትን በተግባር ያሳዩ ናቸው። ቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የተጀመሩትን ስራዎች በተጨባጭ ወደ ላቀ ህዝባዊ ተጠቃሚነትና ብልጽግና የሚቀይርበት ዘመን ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
አልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ - የባለ ጥቁር ጋማ አንበሳ መገኛ
Sep 25, 2026 77
ጎብኚዎች ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ከሚነሳሱባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል ያሏት ጥንታዊና ድንቅ የታሪክ፣ የባህልና የተፈጥሮ ሀብት ስብስቦች እንደሆኑ ዋነኛዎቹ ናቸው። በዩኔስኮ የተመዘገቡ በርካታ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት መሆኗ ፣ የሰው ልጅ መገኛነቷን የሚያረጋግጡ ሳይንሳዊ ግኝቶች፣ እንዲሁም የአረቢካ ቡና የመጀመሪያ መገኛ መሆኗ እና ሌሎችንም መጥቀስ ይቻላል። “ታሪኳንና ቅርሶቿን ገልጦ ለተመለከተ መልክአ ምድሯን ለቃኘ በማህጸኗ ያቀፈቻቸውን እንስሳት ፣ አዕዋፍና ዕጽዋት ዓይኑን ገልጦ ላሰሰ ፣ የሕዝቦቿን ባህል ፣ ትውፊት ፍልስፍና በማስተዋል ለመረመረ ኢትዮጵያ የመስህቦች ማንጸሪያ የልዩነት አጽናፍ ማስረጃ ናት” …የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ገጽ 260 ቱሪዝምን ማሳደግ ሃገራችን ከዘርፉ ልታገኘው የሚገባትን ሰፊ ጥቅም ማረጋገጥ የመደመር መንግስት ትኩረት ካደረገባቸው አምስቱ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ነው። የበርካታ ቱሪስቶችን ቀልበ ከሚስቡትና በተፈጥሮ ፀጋዎች ከታደሉ ሥፍራዎች አንዱ የአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ በኢትዮጵያ በስነ-ምህዳር ልዩነቱና ለዱር እንስሳት ምቹ በሆነው የተፈጥሮ ሁኔታው የሚታወቅ ነው። ፓርኩ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ በ1998 ዓ.ም በይፋ በብሔራዊ ፓርክነት ተከልሎ ለጎብኚዎች ክፍት ተደርጓል። የፓርኩ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት 3 ሺህ 276 ካሬ ኪሎ ሜትር የሚያካልል ሲሆን፣ ከሱዳን ድንበር ጋር ይገናኛል። ፓርኩ ስሙን ያገኘው አካባቢውን አቋርጦ ከሚያልፈውና ለዱር እንስሳቱ ዋነኛ የውሃ ምንጭ ከሆነው "አልጣሽ" ከተባለው ወንዝ ነው። ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ 1 ሺህ 025 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ ፓርክ፣ ያልተነካ ተፈጥሮንና የዱር እንስሳት ህይወትን ለመመልከት ትልቅ እድልን የሚሰጥ ስፍራ ነው። የአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ መልክአ-ምድር በዋናነት ሜዳማና ዝቅተኛ ቦታዎችን ያካተተ ሲሆን ከፍታው ከባህር ጠለል በላይ ከ500 እስከ 900 ሜትር ይደርሳል። የአየር ጠባዩ ሞቃታማና ደረቅ ሲሆን፣ በዋናነት በሳቫና ሳር ምድር፣ በጥቅጥቅ የግራርና የቀርከሃ ደኖች የተሸፈነ ነው። በፓርኩ ውስጥ የሚያልፉት የአልጣሽና አዩባ ወንዞች በተለይም በደረቁ ወቅት ለዱር እንስሳቱ አስፈላጊውን ውሃ ያቀርባሉ። በተጨማሪም በዝናብ ወቅት የሚፈጠሩ ጊዜያዊ ረግረጎችና የውሃ አካላት ለተለያዩ አእዋፍና የውሃ ውስጥ ህይወት ፍጥረታት ምቹ የመኖሪያ ከባቢን ይፈጥራሉ። አልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ አልፎ አልፎ የሚታዩና የመጥፋት አደጋ የተደቀነባቸው የዱር እንስሳት መኖሪያም ነው። በፓርኩ ከሚገኙ አጥቢ እንስሳት መካከል አንበሳ፣ ነብር፣ ሳላ፣ አጋዘን፣ ሚዳቋ፣ ጦጣ፣ ዝንጀሮ፣ የዱር አህያና የዱር ውሾች ይጠቀሳሉ። በተለይም በአፍሪካ ብቸኛ የሆነው ባለ ጥቁር ጋማ አንበሳ የሚገኘውም በዚሁ ፓርክ ነው። እ.ኤ.አ. በ2016 የተደረገ ሳይንሳዊ ጥናት እንደጠቆመውም፣ በዛ ያሉ የአንበሳ መንጋዎች በዚህ ፓርክና በአጎራባቹ ይዞታ ውስጥ እንደሚኖሩም ተረጋግጧል። ከ200 በላይ የሚሆኑ የአገር ውስጥና ከሌሎች ዓለማት (ከአውሮፓና ኤስያ) የሚሰደዱ የአእዋፍ ዝርያዎች በፓርኩ ውስጥ ይገኛሉ። ይህም ፓርኩን ለወፍ አድናቂዎችና ተመልካቾች ተመራጭ ያደርገዋል። በፓርኩ ውስጥ የመድኃኒትነትና የኢኮኖሚ እሴት ያላቸው የተለያዩ የግራር ዝርያዎች፣ የቀርከሃ ጫካዎችና የዕጣን ዛፎች በስፋት ይበቅላሉ። የአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ ከሱዳኑ ዲንደር ብሔራዊ ፓርክ ጋር ተጎራባች የሚያደርገው ሰፊ የድንበር ግንኙነትም አለው። ሁለቱ ፓርኮች ተያያዥ በመሆናቸው በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል ድንበር ተሻጋሪ የተፈጥሮ ጥበቃ ቀጣና እንዲፈጠር ምክንያት ሆነዋል። ይህ ግንኙነት የዱር እንስሳቱ ያለ ምንም የወሰን ችግር በነጻነት እንዲንቀሳቀሱና የመራባት ወሰናቸውን እንዲያሰፉ ትልቅ ዕድልን ፈጥሮላቸዋል። በብሔራዊ ፓርኩ የወሰን ማካለል፣ የጥበቃ አቅምን የማጠናከር፣ የህገ-ወጥ አደን እና የሰደድ እሳት ስጋቶችን የመቀነስ ስራዎች ተሰርተዋል። የአካባቢው ማህበረሰብም ፓርኩን በባለቤትነት እንዲንከባከብና ተጠቃሚም እንዲሆን በንብ ማነብ፣ በእንሰሳት መኖ ልማት እና በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ እንዲሰማራ ለማድረግ የማህበረሰብ ተኮር ፕሮጀክቶች ተቀርፀዋል። ወደ ፓርኩ የሚያስገቡ የውስጥ ለውስጥ መንገድ መተላለፊያዎችን የማስተካከል፣ የመቆጣጠሪያ ኬላዎችን የመገንባት እና ወደፊት የስነ-ምህዳር ቱሪዝም መስህብ የሚሆኑ ቦታዎችን የመለየት ቅድመ-ዝግጅቶች እየተከናወኑ እንደሚገኙም መረጃዎች ያሳያሉ።
ለትውልዱ የብልጽግና መሠረት እየጣለች ያለች ሀገር፡ ኢትዮጵያ
Sep 25, 2026 72
ኢትዮጵያ ታላላቅ ሀሳቦችን ወደ መሬት በማውረድ የነገዋን የበለጸገች ሀገር ለመገንባት የምታደርገው ጥረት ከዕለት ወደ ዕለት ይበልጥ እየተጠናከረ መጥቷል። የሀገሪቱ የልማት ምዕራፎች የዕለት ተዕለት ችግሮችን ከመቅረፍ ባለፈ ዘላቂና አስተማማኝ የኢኮኖሚ መሠረት የሚጥሉ ስትራቴጂካዊ ውጥኖችን ተፈጻሚ ማድረግ ላይ ያተኮሩ ናቸው። ትናንት የነበሩ የሎጂስቲክስ ማነቆዎችን በመስበር የኢነርጂ ደህንነትን የሚያረጋግጡ እና ቀጣናዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ዘመናዊ መሠረተ ልማቶችን በቁርጠኝነት በመገንባት የሀገርን መፃኢ ጊዜ የተቃና ከሚያደርጉ ተግባራት መካከል የሚጠቀስ ነው። የዛሬ ኢንቨስትመንቶች ነገ ለሚፈጠረው የኢንዱስትሪ፣ የግብርና እና የንግድ አውታር አስተማማኝ ዋስትና የሚሆኑ ናቸው። በዚህ አውድ ውስጥ በጅቡቲ ዳመርጆግ እና በኢትዮጵያ ደወሌ መካከል የሚዘረጋው አዲስ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ፕሮጀክት ትልቅ የሚባል ታሪካዊ ውሳኔ ነው። የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ፕሮጀክት የመሠረት ድንጋይ ማስቀመጥ ሥነ ሥርዓቱ ትናንት በጅቡቲ ተካሄዷል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ታድመዋል። ፕሮጀክቱ በሁለቱም ጫፎች ላይ በሚገነቡ የማከማቻ ተርሚናሎች የተደገፈ ሲሆን፤ ይህ ታሪካዊ መሠረተ ልማት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በዳንጎቴ ግሩፕ ጥምረት የሚተገበር መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ይህ የኢነርጂ መሠረተ ልማት ፕሮጀክት ሀገሪቱ ለዓመታት ስትጋፈጠው የነበረውን የትራንስፖርት መዘግየት እና ውስን የማጠራቀሚያ አቅም በዘላቂነት የሚፈታ እጅግ ወሳኝ እርምጃ ነው ብለዋል። መልክአ ምድሩ ለሁለቱ ሀገራት የሰጠው የጋራ ኮሪደር ጅቡቲን ከሰፊ ገበያ፣ ኢትዮጵያን ደግሞ ወደ ዓለም አቀፍ ንግድ የሚያገናኝ ቋሚ ድልድይ እንደሆነ ተናግረዋል። ዛሬ አዲስ አበባ የሚገባ እያንዳንዱ ሊትር ነዳጅ በቦቴ መኪናዎች አምስት ቀናትን አሳልፎ የሚመጣበትን አስቸጋሪ ሂደት አዲሱ የቧንቧ መስመር ወደ አንድ ቀን ገደማ ዝቅ እንደሚያደርገው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በጅቡቲ፣ በኢትዮጵያ እና በዳንጎቴ ግሩፕ የጋራ ትብብር የሚዘረጋው ይህ 120 ኪሎ ሜትር የሚረዝም የነዳጅ ቧንቧ መስመር የሎጂስቲክስ ማነቆዎችን ሙሉ በሙሉ የሚቀርፍ ነው። በሁለቱም ወገኖች ከአንድ ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በላይ የሚሆን የጋራ ማከማቻ ቦታ የሚዘጋጅ ሲሆን፣ ይህም ዓለም አቀፍ ቀውሶች ሲያጋጥሙ የኢነርጂ አቅርቦቱ እንዳይስተጓጎል ትልቅ ዋስትና የሚሰጥ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ላይ አንስተዋል። የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመሩ የአፍሪካውያን የትብብር መንፈስ የገለጠ ፓን-አፍሪካዊ ፕሮጀክት መሆኑን ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ገልጸዋል። ይህ ኢንቨስትመንት የአፍሪካ መንግሥታትና የግሉ ዘርፍ ሲተባበሩ አህጉሪቱ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ መሆን እንደምትችል የሚያሳይ ግልጽ ማሳያ ነው ብለዋል። ከአፍሪካ ግዙፍ ኢኮኖሚ ያላት ኢትዮጵያ የኢነርጂ፣ ሎጂስቲክስ እና የኢንዱስትሪ አቅሟን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጠናከረች ትገኛለች። የዳንጎቴ ግሩፕ መሥራችና ናይጄሪያዊው ባለሀብት አሊኮ ዳንጎቴ እንደገለጹት ኢትዮጵያ ከነበረው በቦቴ ትራንስፖርት የማጓጓዝ በመላቀቅ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ፈጣን እና ቀልጣፋ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መዘርጋቷ ታላቅ የኢኮኖሚ ድል ነው። ይህ የተቀናጀ ሥርዓት የምርት ጥራት ቁጥጥርን በማሻሻል እንደ ኢንዱስትሪ፣ አቪዬሽን፣ ትራንስፖርት፣ ግብርና እና ኮንስትራክሽን ያሉት ቁልፍ ዘርፎች በዘላቂነት እንዲደገፉ ያደርጋል። በጣም ታላቁና ሊሰመርበት የሚገባው ነጥብ ይህ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ በአፍሪካዊ ካፒታል እና በወጣት አፍሪካውያን መሐንዲሶች የሚገነባ መሆኑ ነው። ይህ ሁኔታ አፍሪካ የራሷን የልማት ችግሮች በራሷ ዕውቀትና አቅም መፍታት እንደምትችል ትልቅ ማሳያ በመሆን ለአህጉሪቱ ምዕራፍ ይከፍታል። በዚህ መሠረተ ልማት ግንባታ ላይ የተሳተፉ አካላት ቅንጅት የጋራ እምነትን እና ጽኑ አቋምን ያሳያል። ጅቡቲ መሠረተ ልማቶቿን በማዘመን፣ የኢኮኖሚ አማራጮቿን በማስፋት እና ለቀጣናዊ መረጋጋት አስተማማኝ አጋር ሆና መቀጠሏን አረጋግጣለች። ይህ ሁሉ ጥረት የሚያሳየው ኢትዮጵያ ለዛሬው ትውልድ ብቻ ሳይሆን ለነገዋ የበለጸገች ሀገር ቋሚ መሠረት እየጣለች መሆኑን ነው። የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ፕሮጀክት ትውልዱ በራሱ አቅም ተማምኖ ነገን በእርግጠኝነት መገንባት እንደሚችል የሚያበስር ታላቅ የድል ምዕራፍ ነው።
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና 
Jun 17, 2026 13774
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል።   የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።   የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ? 
Oct 13, 2025 22723
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 15743
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል።   በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 21489
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 107880
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 81267
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 59580
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 57184
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 40622
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 40551
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 39981
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 38469
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 107880
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 81267
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 59580
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 57184
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
ጣና- የውበት ፈርጥ፣ የሀገር ጌጥ 
Sep 25, 2026 177
ባህር ዳር ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦ጣና- የውበት ፈርጥ፣ የሀገር ጌጥ የተፈጥሮ፣ የታሪክ፣ የባህልና የስልጣኔ መገለጫዎች ያሏት ኢትዮጵያ የሁሉ መገኛ፣ ምቹ መኖሪያና ተመራጭ የቱሪስቶች መዳረሻ ሀገር መሆኗ ይታወቃል። የተራሮች ውበት የፏፏቴዎች ድምቀት የአራት ወቅቶች ፍርርቅ የሚመላለስባት በተፈጥሮ የታደለች ሀገርም ናት። ከጥንታዊ ቤተ መንግሥቶቿ እስከ ገዳማቷ፣ ከተፈጥሯዊ ውበቶቿ እስከ ዘመናዊ የከተማ ልማቶቿ በስፋት እየተሰራባት ተጨባጭ ውጤትም እየተመዘገበባት ይገኛል። በኢትዮጵያ ትልቁ ሐይቅ ጣና፤ የአባይ ውሃ የህልውና መሰረት፤ የጣና ሐይቅ ውበት የሚገለጥበት ባህር ዳር እና አካባቢው ከሃብትም ባለፈ የታሪክ፣ የባህል፣ የብዝሃ ሕይወት፣ የኢኮኖሚና የቱሪዝም መሰረትም ነው። ከዚሁ በመነሳትም የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የጣና ሐይቅን እና አካባቢውን የባዮስፌር ሪዘርቭ በማለት መዝግቦታል። በጣና ሃይቅ ላይ የሚገኙት ደሴቶችና ልዩ ልዩ ገዳማትም የሃይማኖት፣ የታሪክና የባህል መሰረቶች ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ።   የጣና ገዳማት የኢትዮጵያን መንፈሳዊና ሥነ-ጥበባዊ ታሪክ የሚያስተላልፉ ሕያው ማህደሮች ሲሆኑ በገዳማቱ የቆዩ መጻሕፍት፣ የሃይማኖት ጥበብ ሥራዎችና ታሪካዊ ቁሳቁሶች ይገኛሉ። በመሆኑም የውበት ፈርጥ፣ የሀገር ጌጥ የሆነው ጣና እና ገዳማቱ ከቱሪዝም መስህብነት ያለፈ ትርጉም ያለቸው የሀገር ሃብቶች ናቸው። የጣና የቱሪዝም እድገት ከውሃ መጓጓዣ ጋር በቀጥታ የተያያዘ በመሆኑ የውሃ ላይ የትራንስፖርት አማራጮችን ግዙፏን ጣና ነሽ 2 እና ሌሎችም ዘመናዊ ጀልባዎችን ወደ ስራ በማስገባት ለቱሪስቶች ምቹ ሁኔታ መፍጠር አስችሏል። ለጉብኝት ወደ ባህር ዳር የሚያቀኑ ሁሉ ከጣና ሃይቅ ጋር ተሰናስሎ የተገነባውን የኮሪደር ልማት በማድነቅ በዘመናዊ ጀልባዎች ተሳፍረው ጎርጎራን፣ ገዳማቱንና ሌሎችንም የቱሪዝም መስህቦች በቀላሉ መጎብኘት እየቻሉ ነው።   በመሆኑም በጣና ውበት የተቀረጸች፣ በተፈጥሮና በታሪክ ሃብቶች የታደለችው ባህር ዳር ከተማ በእድገትና ማንሰራራት ላይ ትገኛለች። የባህር ዳር የኮሪደር ልማትም ከጣና ሐይቅና ማራኪ ውበቱ፣ ከገዳማቱና ዓለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ የተገነባው የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ጋር ተሰናስሎ አስደናቂ የመስህብ ስፍራ ሆኗል። ከአካባቢው ከመልክአ ምድር እና ከጣና ሃይቅ ጋር በተናበበ መልኩ ደረጃውን ጠብቆ የተገነባው የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት የቱሪስቶች ምቹና ተመራጭ መዳረሻ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። የባህር ዳር ከተማ የኮሪደር ልማት ከአካባቢው የተፈጥሮ ሃብት ጋር ተሰናስሎ ምቹ መዝናኛዎች፣ ዘመናዊ ጀልባዎች፣ የእግርና የሳይክል መጓጓዣዎች ተጨምረውበት ባህር ዳርን ይበልጥ ውብና ማራኪ አድርጓታል። ለጉብኝት ወደ ባህር ዳር የሚያቀኑ ቱሪስቶችም ጣናን አይተው፣ ገዳማቱን ጎብኝተው፣ ጎርጎራ ላይ ተዝናንተው ቆይታቸውን አራዝመው ይመለሳሉ።
መስቀል በጉራጌ - 'ከወሬት የኸና' እስከ 'አዳብና'
Sep 24, 2026 266
(በእንዳልካቸው ደሳለኝ ከኢዜአ ወልቂጤ ቅርንጫፍ) በኢትዮጵያ ከሚከበሩ ታላላቅና ደማቅ ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል መስቀል ይጠቀሳል። የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊ ቢሆንም በተለያዩ ባህላዊ እሴቶች ጎልቶ የሚታይበት ነው፡፡ በቤተ ጉራጌ መስቀል ከሃይማኖታዊ ሥርዓት ባሻገር ሰፊ ማህበራዊ ክዋኔ ያለው ሲሆን፣ የተቀያየመ የሚታረቅበት፣ የተራራቀ ወዳጅና ዘመድ የሚገናኝበት፣ ጋብቻ የሚፈፀምበት እንዲሁም የፍቅርና የአንድነት ማንፀባረቂያ ነው። በዓሉ በዋናነት በቤተ ጉራጌዎች መስከረም 15 ቀን የሚከበር ቢሆንም፣ የዝግጅት ሂደቱና አከባበሩ ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ እስከ ጥቅምት ወር መጀመሪያ ድረስ የተዘረጋ ረጅም የደስታና የምስጋና ወቅት ነው።   የመስቀል ዝግጅት በይፋ የሚጀምረው ነሐሴ 12 ቀን እንደሆነ የሚናገሩት የሀገር ሽማግሌ አቶ በለጠ ወልዴ፣ በዚህ ዕለት የዓመቱ የመስቀል ደመራ የሚቆምበት እንደሆነ ያብራራሉ። ከዚህ ዕለት ጀምሮ በቤተሰቡ ውስጥ የሥራ ክፍፍል ተደርጎ አጠቃላይ የዝግጅት እንቅስቃሴው ይፋ ይሆናል። በዚህም መሰረት የስራ ኃላፊነቶችን ሲጠቅሱ፤ ልጃገረዶች የቤቱን የውስጥ ክፍል ማፅዳት፣ በባህላዊ ቀለማትና ጌጣጌጦች ቤት ማስዋብ እንዲሁም ለበዓሉ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ያዘጋጃሉ። የወጣት ወንዶች ዋነኛ ኃላፊነት ደግሞ ጀፎረን በማስዋብ አጥር ማጠር፣ ለበዓሉ የሚሆን የማገዶ እንጨት ማዘጋጀትና ለደመራ የሚሆኑ እንጨቶችን አስቀድሞ ማደራጀት ነው። አባወራዎች ለበዓሉ የእርድ ሰንጋዎችን የመግዛትና የማዘጋጀት ኃላፊነት ሲኖርባቸው፤ የእናቶች ድርሻ ደግሞ ለባህላዊ ምግቦች የሚያስፈልጉ እንደ ቆጮ፣ ቡላ፣ አይብ፣ ቅቤ እና የመገልገያ ባህላዊ ቁሳቁሶችን የማደራጀትና የማዘጋጀት ኃላፊነት ነው። በቤተ ጉራጌ ከመስከረም 12 እስከ ጥቅምት 5 ባለው ጊዜ ውስጥ በዓሉ በየቀኑ ልዩ ልዩ ባህላዊ ስያሜዎችና ሥርዓቶች ተሰጥተውት በደመቀ ሁኔታ ይከበራል። በጋራ ሆነው ክትፎና መሰል ባህላዊ ምግቦችን እየተመገቡ በጭፈራና በፈንጠዝያ የመስቀልን በዓል ያከብራሉ። የቀናቶቹን ስያሜና ባህላዊ ክዋኔ በተመለከተ ያነጋገርናቸው የሀገር ሽማግሌ ጐታ ኩየ እንደገለጹት፤ መስከረም 13 ቀን ‘ወሬት የኸና’ (እንቅልፍ ከልካዩ ቀን) ሲሆን በዚህ ቀን ሴቶች ለበዓሉ ዝግጅት ለማድረግ የሚጓጉበት ቀን ከመሆኑ ጋር በተያያዘ እንደሆነ ይነገራል። በዚህ ቀን ለበዓሉ ለመመገቢያነት የሚያገለግሉ ባህላዊ ቁሳቁሶች ለዓመት ከተሰቀሉበት ቦታ ወርደው በጥንቃቄ ተጣጥበው ዝግጁ ይሆናሉ። ቀኑ ከአፈር በተዘጋጁ ቀለማት ግድግዳዎች የሚያሸበርቁበትና አዳዲስ ጅባዎች ተነጥፈው ለበዓሉ ዝግጁ የሚሆኑበት ቀን ነው።   መስከረም 14 ቀን ደግሞ ‘ደንጔሳት’ የሚል ስያሜ ያለው ሲሆን ዕለቱ ልጆች ደመራ ደምረው ባህላዊ ጭፈራዎቻቸውን የሚያቀልጡበት ነው። ከደመራው በኋላም ሴቶች የጎመን ክትፎ በማዘጋጀት በእያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ውክልና በተዘጋጀ ጣባ አድርገው ለምግብነት ያቀርባሉ። ባለትዳር የሆኑ አባላት በአንድ ጣባ የጎመን ክትፎው ተዘጋጅቶ ይሰጣቸዋል። ተምሳሌትነቱም የትዳር አጋሮች "አንድ አካል፣ አንድ አምሳል ናቸው" ተብሎ ስለሚታመን የሚፈፀም ነው። ጉራጌዎች ‘ወኸምያ’ ብለው የሚጠሩት መስከረም 15 ዋናው የመስቀል በዓል የሚውልበት ቀን ነው። በዚህ ዕለት ከሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች በተለየ በሁሉም የቤተ ጉራጌ አካባቢዎች የእርድ ቀን ነው። በሌሎች አካባቢዎች ዕለቱ መስከረም 17 ቀን ላይ እንደሚከበር ልብ ይሏል። በ 'ወኸምያ' ቀን የሚታረደው በሬም ሆነ ወይፈን በሽማግሌዎች ፊት ቀርቦ ስለ ሀገር ሰላም እንዲሁም በዓሉ መልካም ነገር እንዲያመጣ ምርቃት ይወርዳል። የቤተሰቡ አባላትም በእያንዳንዱ ምርቃት መጨረሻ ላይ “ኬር ኬር ኬር ይሁን” (ሰላም ይሁን) በማለት ምርቃቱን ይቀበላሉ። በዚህ ባህላዊ የምርቃት ሥነ ሥርዓት አብዛኛውን ጊዜ እንዲመርቁ የሚጋበዙት በዕድሜያቸው ገፋ ያሉ አረጋውያን ሲሆኑ፣ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች እኩል ተሳትፎ ይኖራቸዋል። መስከረም 16 ቀን (‘ያባንዳ እሳት’ ወይም 'የጉርዝ ኧሳት') የሚል ስያሜ ያለው ሲሆን ዕለቱ አባቶች ደመራ ይዘው የሚወጡበት ነው። በዚህ ዕለት ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል ተሳትፎ የሚያደርግበት የደመራ በዓል ይከወናል። በዕለቱ አባቶች የተለየ ክብር ተሰጥቷቸው የደመራ በዓሉን በምርቃት ያስጀምሩታል። ቀኑ ከባህላዊ ይልቅ መንፈሳዊ ይዘትን ተላብሶ ይከበራል። ጎረምሶችና ልጃገረዶች ደመራውን በመክበብ በተለያዩ ጭፈራዎች አካባቢውን ያደምቁታል። ከጭፈራው በኋላም ሁሉም ወደ ቤቱ በመመለስ በራሱ ጣባ የተዘጋጀለትን ክትፎ ይመገባል። ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በአንድ አካባቢ የሚገኙ የቤተ ጉራጌ ነዋሪዎች ደመራው ወደተቃጠለበት ቦታ በመሄድ የአካባቢያቸውን የዕድር ዳኛ በመቀየር አዲስ የሚመርጡበትና ቃለ መሐላ የማስፈፀም ተግባር የሚያከናውኑበት ቀን የሚከበረው መስከረም 17 ቀን ሲሆን ይህም ‘ንቅባር’ ወይም 'የከሰል ማይ' በሚል ስያሜ ይጠራል። በዕለቱም ሁሉም የአካባቢው የቤተሰብ አባላት የተቃጠለውን የደመራ ከሰል እየዘለሉ በመጪው ዘመን መልካም ነገር እንዲገጥማቸው ይመኛሉ፤ ይማፀናሉም። ወጣቶች ንጋት ላይ ተቀጣጥለው የቀሩ ጉማጅ እንጨቶችን ተሽቀዳድመው በመውሰድ እርሻ ላይ ያቆማሉ፤ ይህም እርኩስ መናፍስትን ይከላከላል ተብሎ ይታመናል።   መስከረም 18 ቀን ‘የፊቃቆ ማይ’ ይባላል። በዚህ ቀን የአካባቢው ልጃገረዶች ሰፌድ ለመስራት የሚያገለግል ስንደዶዎችን ይሰበስባሉ። የስንደዶ ለቀማው በባህላዊ ዜማዎች ታጅቦ ይከናወናል። ከመስከረም 17 እስከ መስከረም 23 ያለው ጊዜ ደግሞ የዘመድ መጠየቂያ ወቅት ሲሆን ‘የጀወጀ’ ወይም ‘የጀመቸ’ ተብሎ ይጠራል። ለዓመት ተነፋፍቀው የቆዩ ቤተሰቦች ተገናኝተው ናፍቆታቸውን የሚገልፁበት፣ የባልና ሚስት እናትና አባት የሚጠየቁበት እንዲሁም ስጦታ የሚቀበሉበት ዕለት ነው። ሴት ልጆች ለእናቶቻቸው የፀጉር ቅቤ፣ ባርኔጣ፣ ጭራ እና ሌሎች ስጦታዎችን ሲያቀርቡ፣ ባሎቻቸው ደግሞ የበግ ሙክት በመያዝ ይጠይቋቸዋል። ስጦታው የቀረበላቸው እናትና አባቶችም የልጆቻቸውን ባሎችና ሚስቶች በየተራ ይመርቋቸዋል።   የጉራጌ ጋብቻ በብዛት የሚከወነው በዚሁ በመስቀል ሰሞን በመሆኑ፣ ከመስከረም 16 እስከ ጥቅምት 5 ያለው ጊዜ በቤተ ጉራጌ ወጣቶች ዘንድ እጅግ ተወዳጅ ነው። በዚህ ጊዜ በተለያዩ የገበያ ቦታዎችና አብያተ ክርስቲያናት ወጣቶች ባህላዊ ጭፈራዎቻቸውን ያሳያሉ፤ እግረ መንገዳቸውንም ለትዳር የምትሆናቸውን ጉብል መልከት መልከት ያደርጋሉ። የወጣቶቹ ባህላዊ ጨዋታ “አዳብና” በሚል ስያሜ የሚታወቅ ሲሆን፣ በንግድና በተለያዩ ምክንያቶች ቆይተው ስለመጡባቸው ቦታዎች ተገናኝተው የሚያወጉበትም ነው::
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም