ቀጥታ፡

ኢጋድ እና ሩሲያ በትብብር መሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) እና ሩሲያ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ግንኙነት ማጠናከር የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።

የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ አጋርነት ዳይሬክተር ታትያና ዶቭጋሌንኮ ጋር በተቋሙ መቀመጫ ጅቡቲ ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅት ኢጋድ እና ሩሲያ በፖሊሲና ደኅንነት፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን፣ ሳይንስ እና ትምህርት ዘርፎች ትብብር ማጎልበት የሚያስችላቸውን ስምምነት እና የድርጊት መርሐ-ግብር ተፈራርመዋል።

ውይይቱ ሁለቱ ወገኖች የጋራ ፍላጎታቸው በሆኑ ጉዳዮች ተቀራርበው ለመሥራት ያላቸውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም