ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአዘርባጃን የሕዝብ አገልግሎት እና ማኅበራዊ ፈጠራ የመንግሥት ኤጀንሲን ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአዘርባጃን የሕዝብ አገልግሎት እና ማኅበራዊ ፈጠራ የመንግሥት ኤጀንሲን ጎበኙ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2018(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ልዑካቸው የአዘርባጃን የሕዝብ አገልግሎት እና ማኅበራዊ ፈጠራ የመንግሥት ኤጀንሲ (ASAN) የፈጠራ ማዕከልን ጎብኝተዋል።
ጉብኝቱ አዘርባጃን በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የሚመራ አስተዳደርን ለማስፋፋት እና የሕዝብ አገልግሎቶችን በዲጂታል ለማዘመን የምትከተለውን ስትራቴጂያዊ አካሄድ የሚያሳይ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሀገሪቱ የAI ኢንጂነሪንግ እና የአመራር ሥልጠና ዋና ማዕከል የሆነውን የAI አካዳሚን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ልዑኩ ጉብኝቱን በመቀጠል በክልሉ ውስጥ ካሉ ትላልቅ የነዳጅ እና የጋዝ ማቀነባበሪያ ማዕከላት አንዱ ወደሆነው ሳንጋቻል ተርሚናል እና ወደ አላት ነፃ የኢኮኖሚ ቀጣና አምርቷል።
ጉብኝቶቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ፣ የኢነርጂ እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትብብር ይበልጥ የማጠናከር አቅም እንዳላቸው ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።