በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መቻል እና ሃዋሳ ከተማ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መቻል እና ሃዋሳ ከተማ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር መቻል እና ሃዋሳ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሴናፍ ዋቁማ በ34ኛው ደቂቃ ባስቆጠረችው ግብ መቻል መሪ ሆኗል።
ከእረፍት መልስ ብርቱካን ገብረክርስቶስ ጁላ በ74ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ላይ ያሳረፈችው ግብ ለሃዋሳ ከተማ አንድ ነጥብ አስገኝቷል።
ለሃዋሳ ጎሉን ያስቆጠረችው ብርቱካን ገብረክርስቶስ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
ውጤቱን ተከትሎ መቻል በ31 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።
ሃዋሳ ከተማ በ29 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።