ቀጥታ፡

የኢጋድ እና ተመድ ትብብር ለቀጣናዊ ሰላም

አዲስ አበባ፤ የካቲት 19/2018 (ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና መረጋጋት ያላቸውን የጋራ ትብብር የበለጠ ለማጎልበት ቁርጠኛ መሆናቸውን አስታወቁ።

የኢጋድ የደቡብ ሱዳን ልዩ ልዑክ አምባሳደር ሙሳ ጃማ አሊ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ጉዋንግ ኮንግ ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይተዋል።

ልዩ ልዑኮቹ በቀጣናዊ ሰላም እና ደህንነት በተለይም በደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ሀሳቦችን ተለዋውጠዋል።

በቅርቡ የአፍሪካ ህብረት የአምስት አባል ሀገራት ኮሚቴ (AU C5) እና ኢጋድ ያደረጉት የጋራ ጉባኤ የተገኙ ውጤቶች ላይም መክረዋል።

ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ቀንድ ሰላም፣ መረጋጋት እና ቀጣናዊ ትብብር እውን እንዲሆን ያላቸውን ቅንጅት ለማጠናከር ቁርጠኛ እንደሆኑ መግለጻቸውን ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም