በከተማዋ በተያዘው በጀት ዓመት ለአንድ መቶ ሺህ ዜጎች የፋይዳ መታወቂያ ለማዳረስ እየተሰራ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በከተማዋ በተያዘው በጀት ዓመት ለአንድ መቶ ሺህ ዜጎች የፋይዳ መታወቂያ ለማዳረስ እየተሰራ ነው
ደገሃቡር፤ የካቲት 20/2018(ኢዜአ)፦በሶማሌ ክልል ደገሃቡር ከተማ በተያዘው በጀት ዓመት ለአንድ መቶ ሺህ ዜጎች የፋይዳ መታወቂያ ለማዳረስ እየተሰራ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ አብዲሀኪም መአሊን ገለጹ።
የደገሃቡር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አብዲሀኪም መአሊን ለኢዜአ እንደገለጹት፣ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ዜጎች ወጥ የሆነ ማንነት እንዲኖራቸው በማድረግ የተቀላጠፈና ዘመናዊ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው።
ፋይዳ መታወቂያን ከተለያዩ አገልግሎቶች ጋር ማስተሳሰር ከተጀመረ ወዲህ የተመዝጋቢዎች ቁጥር እየጨመረ ነው
ፋይዳ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የተቀመጠው ሀገራዊ ግብ እንዲሳካና ለዜጎች ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ብለዋል።
በተያዘው በጀት ዓመት በከተማዋ 100 ሺህ ዜጎችን የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ እስካሁን ከ30 ሺህ በላይ ለሚሆኑት ተደራሽ መደረጉን አመልክተዋል።
በከተማ አስተዳደሩ የወጣቶችን የዲጂታል ክህሎት ለማሳደግ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑንም ተናግረዋል።
ስልጠናው በቴክኖሎጂ የዳበረ ወጣት ለመፍጠር የላቀ ሚና እንዳለው ጠቅሰው፣ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ዜጎች የዲጂታል መታወቂያውን በመያዝ ከሚሰጡ ዘመናዊ አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል።