ቀጥታ፡

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ ሪያል ማድሪድ ከማንችስተር ሲቲ ፒኤስጂ ከቼልሲ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2018 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ዛሬ በስዊዘርላንድ ኒዮን ተካሄዷል።

በዚሁ መሰረት ሪያል ማድሪድ ከማንችስተር ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል

የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ፒኤስጂ ከቼልሲ ጋር የሚያደርገው ጨዋታም ትኩረትን ስቧል።

በሊግ ምዕራፉ ሁሉንም ጨዋታዎች በማሸነፍ አንደኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው አርሰናል ከጀርመኑ ባየር ሌቨርኩሰን ጋር ይጫወታል።


 

ጋላታሳራይ ከሊቨርፑል፣ ኒውካስትል ዩናይትድ ከባርሴሎና፣ አትሌቲኮ ማድሪድ ከቶተንሃም ሆትስፐርስ፣ አትላንታ ከባየር ሙኒክ እና ቦዶ ግሊምት ከስፓርቲንግ ሊዝበን ሌሎች በጥሎ ማለፉ የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።

የጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ጨዋታ መጋቢት 1 እና 2 ፣ የመልስ ጨዋታ መጋቢት 8 እና 9 ቀን 2018 ዓ.ም ይደረጋል።

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ በቀጥታ ያለፉ ስምንት ክለቦች የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከሜዳቸው ውጪ ያደርጋሉ።

በማጣሪያ ጥሎ ማለፉን የተቀላቀሉት ቀሪ ስምንት ክለቦች የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከሜዳው ውጪ እንደሚያከናውኑ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር አስታውቋል።

በተያያዘም የሩብ ፍጻሜ ድልድልም ይፋ ሆኗል።


 

የሪያል ማድሪድ እና ማንችስተር ሲቲ አሸናፊ ከአትላንታ እና ባየር ሙኒክ አሸናፊ፣ የፒኤስጂ እና ቼልሲ አሸናፊ ከጋላታሰራይ እና ሊቨርፑል አሸናፊ፣ የባየር ሌቨርኩሰን እና አርሰናል አሸናፊ ከቦዶ ግሊምት እና ስፖርቲንግ ሊዝበን እንዲሁም የኒውካስትል ዩናይትድ እና ባርሴሎና አሸናፊ ከአትሌቲኮ ማድሪድ እና ቶተንሃም ሆትስፐርስ አሸናፊ በሩብ ፍጻሜው ይገናኛሉ።

የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች በመጋቢት ወር መጨረሻ እና ሚያዚያ ወር መጀመሪያ ላይ ይካሄዳሉ።

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም በሀንጋሪ ቡዳፔስት ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም