ቀጥታ፡

አኅጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና የፈጠረውን የንግድ ትስስር ለማሳደግ የተቀናጀ ጥረት ወሳኝ ነው

አዲስ አበባ፤ የካቲት 14/2018 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት የፈጠረውን የንግድ ትስስር ዕድል በአግባቡ ለመጠቀም በመንግሥታትና በግሉ ዘርፍ መካከል ያለ አጋርነትን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ።


 

የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ዋና ጸሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የስምምነቱ ትግበራ የንግድ መሰናክሎችን በማስቀረት የሀገራትን የንግድ ልውውጥ ለማሳለጥ አዲስ ምዕራፍ እየከፈተ ነው።

እስካሁን 50 ሀገራት ፈርመው ያጸደቁት ይህ የንግድ ቀጣና፤ በዲጂታል የኢኮኖሚ ዕድገት የፋይናንስ ቴክኖሎጂን በማስፋት የአኅጉሪቱን የንግድ እንቅስቃሴ በማዘመንና የገንዘብ ዝውውርን በማቀላጠፍ ፋይዳው የላቀ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት የአሰራር ስርዓቱን ቀልጣፋ እና ተዳራሽ ለማድረግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ዘርግቷል

የኢትዮጵያ ቱሪዝም አዲሱ ገጽታ፤ ከአማራጭ ማጣት ወደ መዳረሻዎች ብዛት

በኢትዮጵያ ለግል ዘርፉ ምቹ ሁኔታ በመፈጠሩ ኢኮኖሚው እየተነቃቃ ነው

የአፍሪካን የተፈጥሮ ሃብትም በተሻለ የኢንቨስትመንት ተወዳዳሪነት በማልማት የመሰረተ ልማት፣ የዋጋ ግሽበትና የንግድ መሰናክሎችን ለመቀነስ አይነተኛ ፋይዳ እንደሚኖረውም አስረድተዋል።


 

በዚህም አባል ሀገራት የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራን በማፋጠን የእርስበርስ የንግድ ልውውጥን ማሳለጥ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት የፈጠረውን ዕድል ለመጠቀም የግሉ ዘርፍና የአባል ሀገራት መንግሥታት የእርስ በርስ የንግድ ልውውጥን ማጠናከር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት መሰረትም የአባል ሀገራት ኢንቨስትመንትን የሚያነቃቃ የኢንቨስትመንት ጥበቃ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋቱን አስረድተዋል።

የስምምነቱ የኢንቨስትመንት ጥበቃም የአፍሪካን በመተማመን ላይ የተመሰረተ የእርስበርስ ንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ለማጎልበት የሚያስችል መሆኑን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም