ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል ቀንቶታል 

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲዳማ ቡናን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ ሪያል ማድሪድ ከማንችስተር ሲቲ ፒኤስጂ ከቼልሲ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ እሙሽ ዳንኤል ሁለት ግቦችን ስታስቆጥር ሰናይት ቦጋለ እና እፀገነት ግርማ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ እፀገነት ግርማ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።

በሊጉ 12ኛ ድሉን ያስመዘገበው የወቅቱ የሊጉ የዋንጫ ባለቤት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ38 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

ከሊጉ መሪ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ዝቅ አድርጓል።

በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሲዳማ ቡና በ18 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም